ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር አምሳ ሰባት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 57
መላእክት በአላህ ትእዛዝ ላይ ያምፃሉ ወይንስ አያምፁም?

አያምፁም፡- 
16፥49-50 “ለአላህም በሰማያት ያለው ከተንቀሳቃሻም በምድር ያለው ሁሉ መላክትም ይሰግዳሉ፤ እነርሱም አይኮሩም። ጌታቸውን ከበላያቸው ሲሆን ይፈሩታል፤ የታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ።”

ያምፃሉ፡- 
2፥102 “ሰይጣናትም በሱለይማን ዘመነ መንግስት የሚያነቡትን ድግምት ተከተሉ፡፡ ሱለይማንም አልካደም፤ ግን ሰይጣናት ሰዎችን ድግምትን የሚያስተምሩ ሲኾኑ ካዱ፡፡ ያንንም በባቢል በሁለቱ መላእክት በሃሩትና ማሩት ላይ የተወረደውን ነገር ያስተምሩዋቸዋል፡፡ «እኛ መፈተኛ ነንና አትካድ» እስከሚሉም ድረስ አንድንም አያስተምሩም፡፡ ከእነሱም በሰውየውና በሚስቱ መካከል በእርሱ የሚለዩበትን ነገር ይማራሉ፡፡ 

መልስ
ከመነሻው መላእክት በባሕያቸው ውስጥ ኩራትና አመጽ የለም፦
16፥49 ለአላህም በሰማያት ያለው ከተንቀሳቃሽም በምድር ያለው ሁሉ፣ *"መላእክትም ይሰግዳሉ፡፡ እነርሱም አይኮሩም"*፡፡ وَلِلَّهِ يَسْجُدُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ مِن دَابَّةٍ وَالْمَلَائِكَةُ وَهُمْ لَا يَسْتَكْبِرُونَ
21፥19 በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉም የእርሱ ነው፡፡ *"እርሱ ዘንድ ያሉትም መላእክት እርሱን ከመገዛት አይኮሩም"*፡፡ አይሰለቹምም፡፡ وَلَهُ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ وَمَنْ عِندَهُ لَا يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِهِ وَلَا يَسْتَحْسِرُونَ
66፥6 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጋዮች ከኾነች እሳት ጠብቁ፡፡ በእርሷ ላይ ጨካኞች፣ ኀይለኞች የኾኑ መላእክት አሉ፡፡ *"አላህ ያዘዛቸውን ነገር በመጣስ አያምጹም፤ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ"*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا قُوا أَنفُسَكُمْ وَأَهْلِيكُمْ نَارًا وَقُودُهَا النَّاسُ وَالْحِجَارَةُ عَلَيْهَا مَلَائِكَةٌ غِلَاظٌ شِدَادٌ لَّا يَعْصُونَ اللَّهَ مَا أَمَرَهُمْ وَيَفْعَلُونَ مَا يُؤْمَرُونَ

መላእክት አላህ ያዘዛቸውን ነገር በመጣስ አያምጹም፤ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ። እዚህ ድረስ ከተግባባን የሚቀጥለውን አንቀጽ ጥልልና ጥንፍፍ ባለ መልኩ እንይ። በባቢሎት በሚገኙት በሀሩትና በማሩት ላይ የተወረደው የሲሕር ትምህርት ሰዎችን እንዴት እንደሚጎዳ ማስጠንቀቂያ ሆኖ ነው። ነገር ግን ሰይጣናትም በሱለይማን ዘመነ መንግስት ሰዎችን የሚያስተምሩት ለአሉታዊ ነገር ነበር፦
2፥102 *"ሰይጣናትም በሱለይማን ዘመነ መንግስት የሚያነቡትን ተከተሉ፡፡ ሱለይማንም አልካደም፤ ግን ሰይጣናት ሰዎችን ድግምትን የሚያስተምሩ ሲኾኑ ካዱ፡፡ ያንንም በባቢል በሁለቱ መላእክት በሃሩትና ማሩት ላይ የተወረደውን ነገር ያስተምሩዋቸዋል፡፡ «እኛ መፈተኛ ነንና አትካድ» እስከሚሉም ድረስ አንድንም አያስተምሩም፡፡ ከእነሱም በሰውየውና በሚስቱ መካከል በእርሱ የሚለዩበትን ነገር ይማራሉ"*፡፡ وَٱتَّبَعُوا۟ مَا تَتْلُوا۟ ٱلشَّيَٰطِينُ عَلَىٰ مُلْكِ سُلَيْمَٰنَ ۖ وَمَا كَفَرَ سُلَيْمَٰنُ وَلَٰكِنَّ ٱلشَّيَٰطِينَ كَفَرُوا۟ يُعَلِّمُونَ ٱلنَّاسَ ٱلسِّحْرَ وَمَآ أُنزِلَ عَلَى ٱلْمَلَكَيْنِ بِبَابِلَ هَٰرُوتَ وَمَٰرُوتَ ۚ وَمَا يُعَلِّمَانِ مِنْ أَحَدٍ حَتَّىٰ يَقُولَآ إِنَّمَا نَحْنُ فِتْنَةٌۭ فَلَا تَكْفُرْ ۖ فَيَتَعَلَّمُونَ مِنْهُمَا مَا يُفَرِّقُونَ بِهِۦ بَيْنَ ٱلْمَرْءِ وَزَوْجِهِۦ
እዚህ አንቀጽ ላይ "ሃሩትና ማሩት" እንዳመጹ የሚያሳይ ኃይለ-ቃል ወይም ፍንጭ ሽታው የለም። ምናልባት፦ "እነርሱም በአላህ ፈቃድ ካልኾነ በእርሱ አንድንም ጎጂዎች አይደሉም" የተባለው ስለ ሃሩትና ማሩት መስሏችሁ ከሆነ ተሳስታችኃል፦
2፥102 *"እነርሱም በአላህ ፈቃድ ካልኾነ በእርሱ አንድንም ጎጂዎች አይደሉም፥ የሚጎዳቸውንና የማይጠቅማቸውንም ይማራሉ"*፡፡ وَمَاوَمَا هُم بِضَارِّينَ بِهِ مِنْ أَحَدٍ إِلَّا بِإِذْنِ اللَّهِ ۚ وَيَتَعَلَّمُونَ مَا يَضُرُّهُمْ وَلَا يَنفَعُهُم

ምክንያቱም ሃሩትና ማሩት ሁለት ስለሆኑ ለእነርሱ የምንጠቀምበት ተውላጠ-ስም በሙተና "ሁማ" هُمَا ነው፥ ነገር ግን "በአላህ ፈቃድ ካልኾነ በእርሱ አንድንም ጎጂዎች አይደሉም" የተባሉትን ላይ "እነርሱም" ለሚለው የገባው "ሁም" هُم ሲሆን ከሁለት በላይ ጀመዕ መሆኑ "ሸያጢን" شَّيَٰطِين የሚለውን ተክቶ የመጣ ነው። ሸያጢን ሰዎችን ድግምትን የሚያስተምሩ ሲኾኑ ካዱ፥ ሰዎች ከሸያጢን የሚጎዳቸውንና የማይጠቅማቸውንም ይማራሉ።
ሲጀመር እዚህ አንቀጽ ላይ “ወ” وَ የሚለው መስተጻምር ሕዝብን ሲሕር የሚያስተምሩት ሸያጢን እና ሀሩትና ማሩትን የሚያስጠነቅቁበትን ትምህርት ለመለየት የገባ መስተፃምር ነው። ከመነሻው ሸያጢን የሚያስተምሩት ድግምት እና ለሀሩትና ማሩት ተወረደ የተባለው ነገር ሁለት ለየቅል የሆኑ ሀረግ መሆናቸው ፍንትውና ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ሃሩትና ማሩት፦ "እኛ መፈተኛ ነንና አትካድ" እስከሚሉም ድረስ አንድንም አያስተምሩም፥ እነርሱ ላይ የተወረደው ስለ ሲሕር አውንታዊነት ሳይሆን አሉታዊነት የሚያስረዳ ትምህርት ነው።

ሲቀጥል “ማ” مَا የሚለው ቃል ሁለት ፍቺ ይኖረዋል፤ አንዱ “ማ” مَا “መውሱላ" ሲሆን ሁለተኛው “ማ” مَا "መስደሪያ" ነው። “ማ” مَا የሚለውን “መውሱላ” ማለትም “አንፃራዊ ተውላጠ-ስም" ሆኖ ከተቀራ በባቢሎት በሚገኙት በሀሩትና በማሩት ላይ የተወረደ ነገር እንዳለ ያመለክታል፥ ያ ነገር ግን ከላይ ባየነው የሰዋስም ሙግት ከሸያጢን ሲሕር ተለይቶ በመስተፃምር ተቀምጧል።
“ማ” مَا የሚለው መስደሪያ ማለት “አፍራሽ-ቃል” በሚለው ከተቀራ ደግሞ በባቢሎት በሚገኙት በሀሩትና በማሩት ላይ የሸያጢን ሲሕር አልተወረደም የሚል ፍቺ ይኖረዋል። ምክንያቱም አይሁዳውያን ሚድራሽ በሚባለው መፅሐፋቸው ላይ፦ “ሲሕር በሁለቱ መላእክት በኩል ባቢሎን ላይ ከፈጣሪ የተወረደ ነው” የሚሉትን ቅጥፈት አላህ እያጋለጣቸው ነው። ምክንያቱም አይሁዳውያን አስማት የሰለሞን ጥበብ ነው የሚል እምነት አላቸው፤ ይህንን እሳቤ አንዳንድ ዐበይት ክርስትና በትውፊት ይጋሩታል። ይህንን ነጥብ ኢብኑ ዐባሥ፣ ኢብኑ ጀሪር፣ ቁርጡቢ ያነሱታል።

ሢሰልስ “ሀሩትና ማሩት” ማንና ምን ናቸው? የሚለውን ነጥብ ሁለት አመለካከቶች አሉት፤ ይህንም ጤናማ የተለያየ አመለካከት ያመጣው ጤናማው የቂርኣት ውበት ነው።
“መለከይኒ” مَلَكَيْنِ የሚለው ቃል ”መለክ” مَلَك ማለትም ”መልአክ” ለሚለው ቃል ሙተና”dual” ሲሆን “ሁለት መላእክት” የሚል ፍቺ የሚኖረው “ላምን”ل ላም ፈትሓ “ለ” لَ ተብሎ ሲቀራ ነው። ሌላው “መሊከይኒ” مَلِكَيْنِ የሚለው ቃል "መሊክ” مَلِك ማለትም "ንጉሥ” ቃል ሙተና ሲሆን “ሁለት ነገሥታት” የሚል ፍቺ “ላምን” ل ላም ከስራ “ሊ” لِ ተብሎ ሲቀራ ነው። ሁለቱም ቂርኣት ከመለኮት የተወረደ እስከሆነ ድረስ በሁለቱም መቅራት ይቻላል። ይህ ነጥብ በጀላለይን፣ በአጥ-ጠበሪ፣ በዛማኽሻሪ፣ በባጋዊ እና በራዚ ተወስቷል። የውይይታችን ዋናውና ተቀዳሚው ሙግት ሀሩትና ማሩት ማንና ምን ናቸው? ሳይሆን መላእክት በፍጹም አምጸው አያውቅም የሚል ነው።

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር አምሳ ስምንት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 58
ቁርኣንን ማን አወረደ? አላህ ወይስ ጂብሪል?

አላህ፦
25፥1 ያ ፉርቃንን በባሪያው ላይ ለዓለማት አስጠንቃቂ ይኾን ዘንድ ያወረደው ክብርና ጥራት ተገባው፡፡

ጂብሪል፦
2፥97 ለጂብሪል ጠላት የኾነ ሰው በቁጭት ይሙት በላቸው፡፡ እርሱ ቁርኣኑን ከበፊቱ ለነበሩት አረጋጋጭ ለምእመናን መሪና ብስራት ሲኾን በአላህ ፈቃድ በልብህ ላይ አውርዶታልና፡፡

መልስ
ቁርኣንን ወደ ነቢያችን”ﷺ” ያወረደው አምላካችን አላህ ነው፥ እራሱ አላህ፦ “በባሪያችንም ላይ ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ብትኾኑ ከብጤው አንዲትን ምዕራፍ አምጡ” በማለት ይናገራል፦
2፥23 *በባሪያችንም ላይ ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ብትኾኑ ከብጤው አንዲትን ምዕራፍ አምጡ*፡፡ እውነተኞችም እንደኾናችሁ ከአላህ ሌላ መስካሪዎቻችሁን ጥሩ፡፡ وَإِن كُنتُمْ فِي رَيْبٍ مِّمَّا نَزَّلْنَا عَلَىٰ عَبْدِنَا فَأْتُوا بِسُورَةٍ مِّن مِّثْلِهِ وَادْعُوا شُهَدَاءَكُم مِّن دُونِ اللَّهِ إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ
25፥1 *ያ ፉርቃንን በባሪያው ላይ ለዓለማት አስጠንቃቂ ይኾን ዘንድ ያወረደው ክብርና ጥራት ተገባው*፡፡ تَبَارَكَ الَّذِي نَزَّلَ الْفُرْقَانَ عَلَىٰ عَبْدِهِ لِيَكُونَ لِلْعَالَمِينَ نَذِيرًا

አላህ ወደ ነቢያት ወሕይ የሚያወርድበት መንገድ ሦስት ናቸው፤ እነርሱም፦ በራዕይ፣ ወይም “ከግርዶ ወዲያ”፣ ወይም “መልክተኛን መልአክን” የሚልክ እና በፈቃዱ የሚሻውን ያወርዳል፦
42:51 *ለሰው አላህ "በራእይ" ወይም “ከግርዶ ወዲያ”፣ ወይም “መልክተኛን መልአክን” የሚልክ እና በፈቃዱ የሚሻውን “የሚያወርድለት” ቢሆን እንጅ በገሃድ “ሊያናግረው” ተገቢው አይደለም*፤ እርሱ የበላይ ጥበበኛ ነውና። وَمَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُكَلِّمَهُ ٱللَّهُ إِلَّا وَحْيًا أَوْ مِن وَرَآئِ حِجَابٍ أَوْ يُرْسِلَ رَسُولًۭا فَيُوحِىَ بِإِذْنِهِۦ مَا يَشَآءُ ۚ إِنَّهُۥ عَلِىٌّ حَكِيمٌۭ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ረሱል” رَسُول የሚለው ቃል “ተላላኪ” ማለት ሲሆን “መለክ” مَلَك ማለትም “መልአክ” ለሚለው ቃል ተለዋዋጭ”inter-change” ሆኖ የመጣ ነው፤ ይህም የወሕይ መልአክ ጂብሪል ነው። ከእነዚህ ሦስቱ መንገድ አላህ ቁርኣን ለነብያችን”ﷺ” ያወረደው በሦስተኛው መንገድ ነው፥ ይህም መልእክተኛ መልአክ በመላክ ማናገር ነው። “መልአክን የሚልክ እና በፈቃዱ የሚሻውን የሚያወርድለት ቢሆን እንጅ” የሚለው ይሰመርበት፤ ጂብሪልም መልአክ እንደመሆኑ መጠን ከአላህ ወደ ነብያችን”ﷺ” ቀልብ ቁርኣንን በአላህ ፈቃድ አውርዶታል፦
2፥97 ለጂብሪል ጠላት የኾነ ሰው በቁጭት ይሙት በላቸው፡፡ *እርሱ ቁርኣኑን ከበፊቱ ለነበሩት አረጋጋጭ ለምእመናን መሪና ብስራት ሲኾን በአላህ ፈቃድ በልብህ ላይ አውርዶታልና*፡፡ قُلْ مَن كَانَ عَدُوًّا لِّجِبْرِيلَ فَإِنَّهُ نَزَّلَهُ عَلَىٰ قَلْبِكَ بِإِذْنِ اللَّهِ مُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ وَهُدًى وَبُشْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ

“በአላህ ፈቃድ በልብህ ላይ አውርዶታልና” የሚለው ሃይለ-ቃል እና “መልክተኛን መልአክን የሚልክ እና በፈቃዱ የሚሻውን የሚያወርድለት ቢሆን እንጅ” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ ጅብሪል ተልኮ የመጣ መልአክ ነውና ከራሱ አመንጭቶ አይደለም ያወረደው፤ ከዛ ይልቅ ባይሆን ጅብሪል እራሱ የዙፋኑ ባለቤት በሆነው በአላህ ዘንድ የአላህ ባለሟል ነው፤ የአላህ ታማኝ መልእክተኛ ነው፦
81፥20 የኀይል ባለቤት በዙፋኑ ባለቤት ዘንድ *ባለሟል* የኾነ፡፡ ذِى قُوَّةٍ عِندَ ذِى ٱلْعَرْشِ مَكِينٍۢ
81፥21 በዚያ ስፍራ ትእዛዙ ተሰሚ፤ *ታማኝ የኾነ ነው*፡፡ مُّطَاعٍ ثَمَّ أَمِينٍ

ጂብሪል “ባለሟል” እና “ታማኝ” መባሉ በራሱ ላኪ እንዳለው ያሳያል፤ ላኪው አላህ፣ ተላኪው ጂብሪል፣ መልእክቱ ቁርኣን ነው፤ ጂብሪል ታማኙ መንፈስ ሆኖ ከአላህ ዘንድ ቁርኣንን አውርዶታል፦
26፥193 እርሱን *ታማኙ መንፈስ* አወረደው፤ نَزَلَ بِهِ الرُّوحُ الْأَمِينُ
16፥102 እነዚያን ያመኑትን ለማረጋጋት ሙስሊሞቹንም ለመምራትና ለማብሰር *ቁርኣንን ቅዱሱ መንፈስ እውነተኛ ሲኾን ከጌታህ አወረደው* በላቸው፡፡ قُلْ نَزَّلَهُ رُوحُ الْقُدُسِ مِن رَّبِّكَ بِالْحَقِّ لِيُثَبِّتَ الَّذِينَ آمَنُوا وَهُدًى وَبُشْرَىٰ لِلْمُسْلِمِينَ

“ረቢከ” رَّبِّكَ ማለትም “ጌታህ” ከሚለው ቃል መነሻ ቅጥያ ላይ “ሚን” مِن ማለትም “ከ” የሚል መስተዋድድ አለ፤ ይህ የሚያሳየው ታማኙ መንፈስ ጂብሪል ከነብያችን”ﷺ” ጌታ ከአላህ በታማኝነት ቁርኣንን እንዳወረደው ነው፤ ስለዚህ ነው አላህ ስለ ጂብሪል ሲናገር፦ “ወደ ባሪያውም አላህ ያወረደውን አወረደ” ብሎ ያለው፦
53፥10 *ወደ ባሪያውም አላህ ያወረደውን አወረደ*፡፡ فَأَوْحَىٰ إِلَىٰ عَبْدِهِ مَا أَوْحَىٰ

ምን ትፈልጋለህ? አላህ ወደ ነቢዩ ያወረደውን ቁርኣንን ጂብሪል አወረደው። 
መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር አምሳ ዘጠኝ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 59
59 የስግደት አቅጣጫ ውስን ነውን?

አዎ፦
2፥149 ከየትም ለጉዞ ከወጣህበት ስፍራ ፊትህን ወደ ተከበረው መስጊድ አግጣጫ አዙር፡፡

አይደለም፦
ሱራ 2፥115 ምሥራቁም ምዕራቡም የአላህ ነው ፊቶቻችሁን ወደ የትም ብታዞሩ የአላህ ፊት እዚያ ነው፡፡ አላህ ችሮታው ሰፊ ዐዋቂ ነውና፡፡

መልስ
“ቂብላህ” قِبْلَة የሚለው ቃል “አቅበለ” أَقْبَلَ ማለትም “ተቀጣጨ” ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን “አቅጣጫ”direction” ማለት ነው፥ ይህ መቀጣጨት “የውዳሴ ነጥብ”point of adoration” ነው፦
2፥149 *"ከየትም ለጉዞ ከወጣህበት ስፍራ ፊትህን ወደ ተከበረው መስጊድ አግጣጫ አዙር"*፡፡ وَمِنْ حَيْثُ خَرَجْتَ فَوَلِّ وَجْهَكَ شَطْرَ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ ۖ

ይህ የስግደት ቂብላህ ትእዛዝ ስለሆነ "አዙር" የሚል ኃይለ-ቃል አለ። ነገር ግን ይህ መቀጣጨት ግዴታ የሚሆነው የቂብላህ ነጥብ የሆነው በይቱል ሐረም ማለትም መሥጂዱል ሐረም የት እንዳለ እስከታወቀ ጊዜ ብቻ ነው። እኛ ሙሥሊማን ቂብላውን ካላወቀን ፊቶቻችን ወደ የትም ብናዞር የአላህ እይታ አለ፥ አላህ ችሮታው ሰፊ ዐዋቂ ነውና በችሎታውና በዕውቀቱ ሁላችንንም ያካበበ ነው፦
ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 5 ሐዲስ 1073
ከአባቱ ሰምቶ ዐብደላህ ኢብኑ ዐምር ኢብኑ ረቢዓህ እንደተረከው፦ *"በጉዞ ከአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ጋር ነበርን፥ ሰማዩ ስለጠቆረ ለእኛ ቂብላው መቀጣጨት አስቸጋሪ ሆነብን። እኛም ሶላታችንን አደረግን፥ ምልክትም አደረግን። በኃላ ጸሐይ ስትወጣ ጊዜ የተቃጣጨንበት ከቂብላው ሌላ መሆኑን ተገነዘብን። እኛም ይህንን ለነቢዩ"ﷺ" አነሳን፥ አላህም፦ "ምሥራቁም ምዕራቡም የአላህ ነው፥ ፊቶቻችሁን ወደ የትም ብታዞሩ የአላህ ፊት እዚያ ነው" የሚለውን አንቀጽ አወረደ"*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَامِرِ بْنِ رَبِيعَةَ، عَنْ أَبِيهِ، قَالَ كُنَّا مَعَ رَسُولِ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ فِي سَفَرٍ فَتَغَيَّمَتِ السَّمَاءُ وَأَشْكَلَتْ عَلَيْنَا الْقِبْلَةُ فَصَلَّيْنَا وَأَعْلَمْنَا فَلَمَّا طَلَعَتِ الشَّمْسُ إِذَا نَحْنُ قَدْ صَلَّيْنَا لِغَيْرِ الْقِبْلَةِ فَذَكَرْنَا ذَلِكَ لِلنَّبِيِّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ فَأَنْزَلَ اللَّهُ ‏{فَأَيْنَمَا تُوَلُّوا فَثَمَّ وَجْهُ اللَّهِ}‏ ‏.‏
2፥115 *"ምሥራቁም ምዕራቡም የአላህ ነው፥ ፊቶቻችሁን ወደ የትም ብታዞሩ የአላህ ፊት እዚያ ነው፡፡ አላህ ችሮታው ሰፊ ዐዋቂ ነውና"*፡፡ وَلِلَّهِ الْمَشْرِقُ وَالْمَغْرِبُ ۚ فَأَيْنَمَا تُوَلُّوا فَثَمَّ وَجْهُ اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ وَاسِعٌ عَلِيمٌ

 መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር ስድሳ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 60
የሚመለሱት በስንት ዓመት ነው?

በአንድ ሺሕ ዓመት፦
32፥5 ነገሩን ሁሉ ከሰማይ ወደ ምድር ያዘጋጃል፤ ከዚያም ከምትቆጥሩት ልኩ ሺሕ ዓመት በሆነ ቀን ውስጥ ወደርሱ *ይወጣል* يَعْرُجُ።

በአምሳ ሺህ ዓመት፦
70፥4 መላእክቱና መንፈሱም፣ ልኩ አምሳ ሺህ ዓመት በሆነ ቀን ውስጥ ወደርሱ ያርጋሉ።

መልስ
አምላካችን አላህ የትንሳኤ ቀን ነገርን ሁሉ ከሰማይ ወደ ምድር ያዘጋጃል፦
32፥5 *"ነገሩን ሁሉ ከሰማይ ወደ ምድር ያዘጋጃል፡፡ ከዚያም ከምትቆጥሩት ልኩ ሺህ ዓመት በሆነ ቀን ውስጥ ወደ እርሱ ይመለሳል"*፡፡ يُدَبِّرُ الْأَمْرَ مِنَ السَّمَاءِ إِلَى الْأَرْضِ ثُمَّ يَعْرُجُ إِلَيْهِ فِي يَوْمٍ كَانَ مِقْدَارُهُ أَلْفَ سَنَةٍ مِّمَّا تَعُدُّونَ

ከዚያም በእኛ አቆጣጠር አንድ ቀን፣ ሁለት ቀን፣ ሦስት ቀን እያልን በምንቆጥርበት ሺህ ዓመት በሆነ ቀን ውስጥ ወደ እርሱ ይመለሳል። ማነው የሚመለሰው? "አል-አምር" الْأَمْرَ "ነገሩ" ነው፥ በነጠላም "የዕሩጁ" يَعْرُجُ ማለትም "ይመለሳል" ይላል። እስቲ የሚቀጥለውን አንቀጽ ደግሞ እንመልከት፦
70፥4 *"መላእክቱና መንፈሱም ልኩ አምሳ ሺሕ ዓመት በኾነ ቀን ውስጥ ወደእርሱ ይመለሳሉ*"፡፡ تَعْرُجُ الْمَلَائِكَةُ وَالرُّوحُ إِلَيْهِ فِي يَوْمٍ كَانَ مِقْدَارُهُ خَمْسِينَ أَلْفَ سَنَةٍ

እዚህ አንቀጽ ላይ ይመለሳሉ የሚለው "ነገሩን" ሳይሆን "መላእክቱና መንፈሱ" ናቸው፥ የሚመለሱትም በሺህ ዓመት በሆነ ቀን ውስጥ ሳይሆን በአምሳ ሺሕ ዓመት በኾነ ቀን ውስጥ ነው። በነጠላም "የዕሩጁ" ሳይሆን በብዛት ተዕሩጁ" تَعْرُجُ ማለትም "ይመለሳሉ" ነው።
ስለዚህ ሁለት የተለያዩ ጉዳዮችን አንስቶ ይጋጫሉ ማለት እጅግ የከፋ ስህተት ነው። ለመሆኑ በባይብል አንድ ቀን ስንት ነው?

አንድ ዓመት፦
ሕዝቅኤል 4፥6 *አንድን ዓመት አንድ ቀን* አድርጌ አርባ ቀን ሰጥቼሃለሁ።

አንድ ሺህ ዓመት፦
2ኛ ጴጥ 3፥8 እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፥ በጌታ ዘንድ *አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን* እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ።

መደምደሚያ
ቁርኣን የአምላካችን የአላህ ንግግር ነው። አላህ ሁሉን ነገር የፈጠረ የዓለማቱ ጌታ ነው፥ የእርሱ ንግግር በፍጹም አይጣረስም፦
4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

አንድ ቂል "ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር" ማለት "ጥቂትን መለያየት ይገኛል" ብሎ ተረድቶታል። "ብዙ" ማለት "ጥቂት" አለ ማለትን አያሳይም፦
4፥1 እናንተ ሰዎች ሆይ! ያንን ከአንዲት ነፍስ የፈጠራችሁን ከእርስዋም መቀናጆዋን የፈጠረውን ከእነርሱም *"ብዙ ወንዶችንና ሴቶች የበተነውን ጌታችሁን ፍሩ"*፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ اتَّقُوا رَبَّكُمُ الَّذِي خَلَقَكُم مِّن نَّفْسٍ وَاحِدَةٍ وَخَلَقَ مِنْهَا زَوْجَهَا وَبَثَّ مِنْهُمَا رِجَالًا كَثِيرًا وَنِسَاءً

"ከእነርሱም ብዙ ወንዶችንና ሴቶች የበተነውን" ማለት "ከአደምና ሐዋ ጥቂት ያልተበተኑ አሉ የሚለውን ያስይዛልን? በአይሁድና ክርስትና ሰው ሁሉ ይነሳል ተብሎ ይታመናል፦
ዳንኤል 12፥2፤ *"በምድርም ትቢያ ውስጥ ካንቀላፉቱ ብዙዎች ይነቃሉ"*፤ እኵሌቶቹ ወደ ዘላለም ሕይወት፥ እኵሌቶቹም ወደ እፍረትና ወደ ዘላለም ጕስቍልና።

"በምድርም ትቢያ ውስጥ ካንቀላፉቱ ብዙዎች ይነቃሉ" ማለት "በምድርም ትቢያ ውስጥ ካንቀላፉቱ ጥቂቶች አይነሱም" ማለትን ያስይዛልን? የቋንቋ ምሁራን፦ "የቋንቋ ክህሎት በአራት ይከፈላል" ይላሉ፥ እነርሱም፦ "መስማት፣ መናገር፣ ማንበብ እና መጻፍ ናቸው። እንዚህ ድጋሚ ውሳጣዊት"input" እና ውጺዓት"output" ለሁለት ይከፈላሉ፤ ማዳመጥና ማንበብ አሳብና ስሜት ወደ ውስጥ የምናስገባበት ሲሆን መናገርና መጻፍ አሳብና ስሜት ወደ ውጪ የምናስወጣበት ነው። ጥሩ ተናጋሪ ለመሆን ጥሩ አንባቢ፥ ጥሩ ጸሐፊ ለመሆን ጥሩ አንባቢ መሆን ግድ ይላል። እነዚህ የአገራችም ሚሽነሪዎች ሲናገሩ ፈራ ተባ እያሉ መሆኑ በራሱ አዳማጮች እንዳልሆኑ፥ አጻጻፋቸው አንባቢ እንዳልሆኑ ያሳብቅባቸዋል። ኢቭን በዐማርኛ እንኳን "ሀ" እና "ሐ"፣ "ሠ" እና "ሰ"፣ "አ" እና "ዐ"፣ "ኀ" እና ኸ" የትርጉም ልዩነት እንዳለው ዐያውቁም። ለውይይትም ደንባሮች ሆነው ይበረግጋሉ፥ ንግግራቸውም ቶራህ ቦራህ አርቲ ቡርቲ ነው። ይህ መደዴ አካሄድ ነውጥን እንጂ ለውጥን አላመጣላቸው። ይህ የቁርኣን ግጭት ብለው ያቀረቡትን ጥያቄ እኔ እና ታላቁ ዐሊም ሼህ ሙሐመድ ሐመዲን የዛሬ ሦስት ዓመት ከአንሰሪንግ ኢሥላም ላይ እያየን የመለስነው መልስ ነው። አህያ፦ "እኛ ያልፈሳንበት ዳገት የለም" አለች አሉ፥ እኛ ሳናነበው የተጠየቀ ጥያቄ የለም። እኛም ብዕራችንን እዚህ ጋር እናጠናቅ፥ አላህ ሂዳያ ይስጣችሁ ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ቁርኣን አይጋጭም!

ጥያቄ ቁጥር አንድ
አጋሪ ሴቶችን ማግባት ተፈቅዷል ወይስ አልተፈቀደም?
http://bit.ly/2IduZqi

ጥያቄ ቁጥር ሁለት
ጂን እና ሰው የተፈጠሩት ለምንድ ነው?
http://bit.ly/2Iim0Ej

ጥያቄ ቁጥር ሦስት
ሰዎችን የሚያጠመው ማን ነው? አላህ ወይንስ ሰይጣን?
http://bit.ly/2IasdC1

ጥያቄ ቁጥር አራት
አማላጆች አሉ ወይስ የሉም?
http://bit.ly/2IbGaQb

ጥያቄ ቁጥር አምስት
አላህ ያለሚስት ልጅ ሊኖረው ይችላል ወይስ አይችልም?
http://bit.ly/2I8HNxW

ጥያቄ ቁጥር ስድስት
አላህ ብቸኛ ረዳት ወይስ ሌሎች ረዳቶችም አሉ?
http://bit.ly/2Iafyiw

ጥያቄ ቁጥር ሰባት
የመላእክት ስግደት ለማን ነው?
http://bit.ly/2IdhpmK

ጥያቄ ቁጥር ስምንት
የአላህ ቃል ይለወጣል ወይስ አይለወጥም?
http://bit.ly/2IagrYo

ጥያቄ ቁጥር ዘጠኝ
በገሃነም ውስጥ የተጣሉ ሰዎች ምግባቸው አንድ ብቻ ነው ወይስ ብዙ?
http://bit.ly/2I8IPdi

ጥያቄ ቁጥር አስር
ነቢዩ ቢሳሳት የሚጐዳው ማነው?
http://bit.ly/2TUlMFj

ጥያቄ ቁጥር አስራ አንድ
ማርያም የተገለጡላት ስንት መላእክት ነበሩ?
http://bit.ly/2YOT1O0

ጥያቄ ቁጥር አስራ ሁለት
ዓድ የጠፋው በስንት ቀን ነው?
http://bit.ly/2YU39F9

ጥያቄ ቁጥር አስራ ሦስት
አንዲት ነፍስ የሌላይቱን ኃጢአት አትሸከምም ወይስ ትሸከማለች?
http://bit.ly/2uQjnl9

ጥያቄ ቁጥር አስራ አራት
ነቢዩ አስጠንቃቂነታቸው ለአማንያን? ለካሃዲያን ወይስ ለሁሉም?
http://bit.ly/2uPZ336

ጥያቄ ቁጥር አስራ አምስት
መልዕክተኞች የተላኩባቸው ከተሞች በሙሉ ክደዋል ወይንስ ያልካዱ አሉ?
http://bit.ly/2uOAHXB

ጥያቄ ቁጥር አስራ ስድስት
አላህ ሁሉን አዋቂ ነው ወይንስ አይደለም?
http://bit.ly/2IpWE86

ጥያቄ ቁጥር አስራ ሰባት
ካፊሮች በፍርድ ቀን ይናገራሉ ወይስ አይናገሩም?
http://bit.ly/2InguRm

ጥያቄ ቁጥር አስራ ስምንት
አላህ ፍጥረቱን በቀጥታ ያናግራል ወይስ አያናግርም?
http://bit.ly/2IpD4sB

ጥያቄ ቁጥር አስራ ዘጠኝ
አላህ የሺርክ ኃጢአትን ይቅር ይላል ወይስ አይልም?
http://bit.ly/2IpDeQJ

ጥያቄ ቁጥር ሃያ
ሰው ነፃ ፈቃድ አለው ወይስ የለውም?
http://bit.ly/2InsimV

ጥያቄ ቁጥር ሃያ አንድ
ክፋት እና ደግነት ከማነው?
http://bit.ly/2IoTiSP

ጥያቄ ቁጥር ሃያ ሁለት
ሙስሊሞች የማያምኑ ሰዎችን እንዲዋጉ ወይስ ይቅር እንዲሉ ነው የታዘዙት?
http://bit.ly/2IpGA6f

ጥያቄ ቁጥር ሃያ ሦስት
የሙሐመድ"ﷺ" ኃላፊነት መልእክቱን ማድረስ ብቻ ወይስ ያልተቀበሉትን በኃይል ማስለም?
http://bit.ly/2IqMMLp

ጥያቄ ቁጥር ሃያ አራት
የሰውን ነፍስ የሚያወጣው ማን ነው?
http://bit.ly/2IreNSS

ጥያቄ ቁጥር ሃያ አምስት
ሙስሊሞች ስንት እናቶች ናቸው ያሏቸው?
http://bit.ly/2IskCjk

ጥያቄ ቁጥር ሃያ ስድስት
መዳን የሚችሉት እነማን ናቸው?
http://bit.ly/2IpXxxs

ጥያቄ ቁጥር ሃያ ሰባት
ያላመኑ ቤተሰቦችን መወዳጀት ተፈቅዷል ወይስ አልተፈቀደም?
http://bit.ly/2IshcwF

ጥያቄ ቁጥር ሃያ ስምንት
ሙስሊሞች ከክርስቲያኖች ጋር እንዲወዳጁ ተፈቅዷል ወይስ አልተፈቀደም?
http://bit.ly/2IrMkN0

ጥያቄ ቁጥር ሃያ ዘጠኝ
መልእክተኞች ሆነው የተላኩት ሰዎች ብቻ ወይስ ሌሎች ፍጥረታትም ጭምር?
http://bit.ly/2IpIGmD

ጥያቄ ቁጥር ሠላሳ
የሙሐመድ"ﷺ" ገነት መግባት እርግጥ ነው ወይስ አይታወቅም?
http://bit.ly/2IreE25
ጥያቄ ቁጥር ሠላሳ አንድ
ዮናስ በምድረ በዳ ተጥሏል ወይስ አልተጣለም?
http://bit.ly/2IslXXo

ጥያቄ ቁጥር ሠላሳ ሁለት
ሕፃናት ጡት እንዲጥሉ አላህ ያዘዘው ከምን ያህል ጊዜ በኋላ ነው?
http://bit.ly/2IpIXGb

ጥያቄ ቁጥር ሠላሳ ሦስት
ለጦርነት ላለመዝመት መሐመድን"ﷺ" ፈቃዱ የጠየቁት ሁሉ ተወቃሾች ናቸው ወይስ አይደሉም?
http://bit.ly/2IscSNV

ጥያቄ ቁጥር ሠላሳ አራት
ሙሴ ሕዝቡን ነፃ ለማውጣት በተላከ ጊዜ ያመኑለት ጥቂት ወገኖቹ ብቻ ወይንስ የግብፅ ደጋሚዎችም ጭምር?
http://bit.ly/2IpJ7NN

ጥያቄ ቁጥር ሠላሳ አምስት
ዒሳ እንደ ማንኛውም ሰው የሆነ ሰው ወይንስ የአላህ ቃልና መንፈስ ብቻ?
http://bit.ly/2InvXRH

ጥያቄ ቁጥር ሠላሳ ስድስት
የዒሳ “አፈጣጠር” እንደ አደም ከአፈር ወይንስ በልደት?
http://bit.ly/2IqFrLW

ጥያቄ ቁጥር ሠላሳ ሰባት
ዒሳ ፈጣሪ ነው ወይስ አይደለም?
http://bit.ly/2IqGxY4

ጥያቄ ቁጥር ሠላሳ ስምንት
ኢብሊስ መልአክ ወይንስ ጂን?
http://bit.ly/2IrgjEy

ጥያቄ ቁጥር ሠላሳ ዘጠኝ
አላህ ብቸኛ ፈራጅ ወይስ በፍርዱ ተጋሪ አለው?
http://bit.ly/2IsiE25

ጥያቄ ቁጥር አርባ
ዒሳ ሞቷል ወይንስ አልሞተም?
http://bit.ly/2IoVA4p

ጥያቄ ቁጥር አርባ አንድ
ዒሳ በገሃነም ይቃጠላል ወይስ አይቃጠልም?
http://bit.ly/2IqPRLt

ጥያቄ ቁጥር አርባ ሁለት
ቁርአን የማን ቃል ነው?
http://bit.ly/2Iu4Moa

ጥያቄ ቁጥር አርባ ሦስት
ያለ ወሲባዊ ግንኙነት ልጅ መውለድ ይቻላል ወይስ አይቻልም?
http://bit.ly/2IoWCxj

ጥያቄ ቁጥር አርባ አራት
የመጀመሪያ ሙስሊም ማን ነው?
http://bit.ly/2IrPtfM

ጥያቄ ቁጥር አርባ አምስት
አላህ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረው በስድስት ቀን ወይስ በስምንት ቀን?
http://bit.ly/2Is4UEw

ጥያቄ ቁጥር አርባ ስድስት
ፈጣን ወይንስ ዘገምተኛ የመፍጠር ሒደት?
http://bit.ly/2IoXrGn

ጥያቄ ቁጥር አርባ ሰባት
ከሰማይና ከምድር ቀድሞ የተፈጠረው የቱ ነው?
http://bit.ly/2XrrxwB

ጥያቄ ቁጥር አርባ ስምንት
አላህ መላእክትን የሚያወርደው በቅጣት ብቻ ወይስ በራዕይ?
http://bit.ly/2Iqa3x2

ጥያቄ ቁጥር አርባ ዘጠኝ
አላህ ሰማይና ምድርን ወደ አንድ ጠራቸው ወይስ ለያያቸው?
http://bit.ly/2IpIfc1

ጥያቄ ቁጥር አምሳ
ጂኒዎች ከምንድነው የተፈጠሩት?
http://bit.ly/2Iq4Wgg

ጥያቄ ቁጥር አምሳ አንድ
መናፍቃን ዕውሮች ናቸው ወይስ አይደሉም?
http://bit.ly/2IpvDSr

ጥያቄ ቁጥር አምሳ ሁለት
ከሃዲያን በፍርድ ቀን ከአላህ የሚደብቁት ነገር አለ ወይስ የለም?
http://bit.ly/2Iu6A0q

ጥያቄ ቁጥር አምሳ ሦስት
በሉጥ ዘመን የነበሩት ህዝቦች ለሉጥ የመለሱለት መልስ የትኛውን ነው?
http://bit.ly/2IqWSvW

ጥያቄ ቁጥር አምሳ አራት
የሙሴን እጅ መንጣት በተመለከተ አላህ ምን አለው?
http://bit.ly/2XruXPX

ጥያቄ ቁጥር አምሳ አምስት
ከሚከተሉት ውስጥ መሐመድ"ﷺ" የትኛውን ነው?
http://bit.ly/2Xj1Hup

ጥያቄ ቁጥር አምሳ ስድስት
የጀነት ስፋት እንደማን ነው?
http://bit.ly/2KMUvFG

ጥያቄ ቁጥር አምሳ ሰባት
መላእክት በአላህ ትእዛዝ ላይ ያምፃሉ ወይንስ አያምፁም?
http://bit.ly/2UqoZNg

ጥያቄ ቁጥር አምሳ ስምንት
ቁርኣንን ማን አወረደ? አላህ ወይስ ጂብሪል?
http://bit.ly/2Gkm9V0

ጥያቄ ቁጥር አምሳ ዘጠኝ
የስግደት አቅጣጫ ውስን ነውን?
http://bit.ly/2Gn6pAF

ጥያቄ ቁጥር ስድሳ
የሚመለሱት በስንት ዓመት ነው?
http://bit.ly/2GjUTG8

ለወዳጅ፣ ለባለንጀራዎ፣ ለቤተሰብዎ እና ለዘመድዎ ሼር በማድረግ የዳዋ ተደራሽነትዎን ይወጡ።
የኒውዝላንዱ ሙሥሊም ይቅርባይነት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

3፥134 ለእነዚያ በድሎትም ኾነ በችግር ለሚለግሱት፣ ቁጭትንም ገቺዎች *ከሰዎችም ይቅርታ አድራጊዎች ለኾኑት ተደግሳለች*፡፡ አላህም በጎ ሠሪዎችን ይወዳል፡፡ ٱلَّذِينَ يُنفِقُونَ فِى ٱلسَّرَّآءِ وَٱلضَّرَّآءِ وَٱلْكَٰظِمِينَ ٱلْغَيْظَ وَٱلْعَافِينَ عَنِ ٱلنَّاسِ ۗ وَٱللَّهُ يُحِبُّ ٱلْمُحْسِنِينَ

በኒውዝላንዱ በአሸባሪው ነፍሰ-ገዳይ ሚስቱን ሑሥና አሕመድን ያጣው ባንግላዴሻዊ ፈሪድ አሕመድ አስገራሚ ኢንተርቪው ነው የሰጠው። እርሱ ሲናገር፦ "እኔ መንቀሳቀስ ስለማልችል የሚሆነውን ነገር እመለከት ነበር፥ አንድን ሰው በአንድ ጥይት ሳይሆን ደጋግሞ ይመታቸው ነበር፤ የወደቁትንም ደግሞ ይመታል።
ባለቤቴ ደግሞ እራሷን ረስታ ብዙ ሕፃናትና ሴቶችን በመስኮትና በኃላ በር አስመልጣለች። እዚያ እንደጨረሰች ዊልቸሬን ልትገፋልኝ እኔ ጋር ስትመጣ ተኮሰ እና ገደላት፥ ሀዘኔ ከባድ ነው። እና አሁን ገዳዩን ባገኘውና አጠገቡ ብሆን ቁጭ አድርጌው፦ "ውስጡ ትልቅ ኃይል እንዳለ፥ ያንን ኃይሉን ያለ ዕውቀት ለጥላቻ እንደተጠቀመበት እና ለመልካም ቢያውለው ደግሞ እጅግ ብዙ ነፍሶችን ከሞት እንደሚያድን እመክረው ነበር፥ ለእርሱ ላደርግለት የምችለው እንግዲህ ይቅርታ በላጭ ነው። ሕይወቱንና አስተሳሰቡን እንዲቀይር ከይቅርታ ውጭ ምንም ላደርግለት አልችልም። ሀዘኔ ከባድና መራት ነው፤ ባለቤቴን እና ተንከባካቢዬን ሑሥናን አጥቻለሁኝ" ብሎ ለቅሶው አለቀሰ!

ይህ ሰው ይቅር እንዲል መንስኤው ምን ነበር? አዎ የአምላካችን የአላህ ንግግር ቁርኣን ነው። በቁርኣን ከተገለጹ የአላህ ስሞች መካከል “አል-ዐፉው” العَفُوّ ሲሆን “ዐፋ” عَفَا ማለት “ይቅር አለ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ይቅር ባዩ” ማለት ነው፤ አላህ እጅግ በጣም “ይቅርባይ” ነው፦
42፥25 *እርሱም ያ ከባሮቹ ንስሓን የሚቀበል፣ ከኃጢአቶችም ይቅር የሚል፣ የምትሠሩትንም ሁሉ የሚያውቅ ነው*፡፡ وَهُوَ الَّذِي يَقْبَلُ التَّوْبَةَ عَنْ عِبَادِهِ وَيَعْفُو عَنِ السَّيِّئَاتِ وَيَعْلَمُ مَا تَفْعَلُونَ
4፥99 እነዚያም አላህ ከእነርሱ ይቅርታ ሊያደርግ ይሻል፡፡ *አላህም ይቅር ባይ መሓሪ ነው*፡፡ فَأُولَـٰئِكَ عَسَى اللَّهُ أَن يَعْفُوَ عَنْهُمْ ۚ وَكَانَ اللَّهُ عَفُوًّا غَفُورًا
4፥43 *አላህ ይቅር ባይ መሓሪ ነውና*፡፡ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَفُوًّا غَفُورًا

የአል-ዐፉው” ተለዋዋጭ ቃል “አል-ገፋር” الغَفَّار ወይም “አል-ገፉር” الغَفُور ሲሆን “ገፈረ” غَفَرَ ማለትም “ማረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መሐሪው” ማለት ነው።
“ዐፍዉ” عَفْو ወይም “መግፊራህ” مَّغْفِرَة ማለት “ይቅርባይነት” “ምህረት” ማለት ነው። ተበድለው ለአላህ ብለው ይቅር የሚሉ ይቅርታ አድራጊዎች “ዐፊን” عَافِين ወይም “ሙሥተግፊር” مُسْتَغْفِر ይባላሉ፦
3፥134 ለእነዚያ በድሎትም ኾነ በችግር ለሚለግሱት፣ ቁጭትንም ገቺዎች *ከሰዎችም ይቅርታ አድራጊዎች ለኾኑት ተደግሳለች*፡፡ አላህም በጎ ሠሪዎችን ይወዳል፡፡ ٱلَّذِينَ يُنفِقُونَ فِى ٱلسَّرَّآءِ وَٱلضَّرَّآءِ وَٱلْكَٰظِمِينَ ٱلْغَيْظَ وَٱلْعَافِينَ عَنِ ٱلنَّاسِ ۗ وَٱللَّهُ يُحِبُّ ٱلْمُحْسِنِينَ

አንድ ሰው ተበድሎ የተበደለበትን ሃቅ ማስመለስ ወቀሳ የለበትም፤ ፍትሕ ነውና። የመጥፎም ነገረ ዋጋ ብጤዋ መጥፎ ነው። ነገር ግን ለአላህ ብሎ ይቅርባይ የሆነ አላህ ዘንድ የሚያገኘው ወሮታ፣ አጸፌታ፣ ምንዳና ትሩፋት ያለ ግምት ነው፦
42፥41 ከተበደሉም በኋላ *በመሰሉ የተበቀሉ እነዚያ በነርሱ ላይ ምንም የወቀሳ መንገድ የለባቸውም*፡፡ وَلَمَنِ ٱنتَصَرَ بَعْدَ ظُلْمِهِۦ فَأُو۟لَٰٓئِكَ مَا عَلَيْهِم مِّن سَبِيلٍ
42፥40 የመጥፎም ነገረ ዋጋ ብጤዋ መጥፎ ናት፡፡ *ይቅርም ያለና ያሳመረ ሰው ምንዳው በአላህ ላይ ነው*፡፡ እርሱ በደለኞችን አይወድም፡፡ وَجَزَٰٓؤُا۟ سَيِّئَةٍۢ سَيِّئَةٌۭ مِّثْلُهَا ۖ فَمَنْ عَفَا وَأَصْلَحَ فَأَجْرُهُۥ عَلَى ٱللَّهِ ۚ إِنَّهُۥ لَا يُحِبُّ ٱلظَّٰلِمِينَ

አላህ ይቅርባዮችም ኀጢኣታቸውን ይቅር ይላቸዋል፦
42፥37 ለእነዚያም የኀጢኣትን ታላላቆችና ጠያፎችን የሚርቁ *”በተቆጡም ጊዜ እነርሱ የሚምሩት ለኾኑት”*፡፡ وَٱلَّذِينَ يَجْتَنِبُونَ كَبَٰٓئِرَ ٱلْإِثْمِ وَٱلْفَوَٰحِشَ وَإِذَا مَا غَضِبُوا۟ هُمْ يَغْفِرُونَ
4፥149 ደግ ነገርን ብትገልጹ ወይም ብትደብቁት ወይም ከመጥፎ ነገር *ከበደል ይቅርታ ብታደርጉ አላህ ይቅር ባይ ኃያል ነው*፡፡ إِن تُبْدُوا۟ خَيْرًا أَوْ تُخْفُوهُ أَوْ تَعْفُوا۟ عَن سُوٓءٍۢ فَإِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَفُوًّۭا قَدِيرًا
የይቅርባይነት ተቃራኒ ቁርሾ ነው፤ ቁርሾ ከጥላቻ የሚመጣ ሲሆን ቁርሾ ወደ ይቅርባይነት የሚቀየረው በፍቅር ብቻ ነው፤ ፍቅር የሻከረን ግንኙነት ያለሰልሳል፤ ጥላቻ ኪሳራም ጉዳትም ያመጣል፤ ፍቅር ግን ትርፍም ጥቅምም ያመጣል። ይቅርታ ማድረግ እና የሰዎችን ጥፋት በይቅታ ማለፍ ከአላህ ዘንድ ይቅርባይነት ያሰጣል፤ በተቃራኒው ቂምን መዶለት ቅጣት አለው፦
24፥22 ከእናንተም የችሮታና የክብረት ባለቤቶች የኾኑት ለቅርብ ዘመዶችና ለድኾች በአላህም መንገድ ለተሰደዱ ሰዎች ላይሰጡ አይማሉ፡፡ *ይቅርታም ያድርጉ፡፡ ጥፋተኞቹን ይለፉም፡፡ አላህ ለእናንተ ሊምር አትወዱምን? አላህም መሓሪ አዛኝ ነው*፡፡ وَلَا يَأْتَلِ أُولُو الْفَضْلِ مِنكُمْ وَالسَّعَةِ أَن يُؤْتُوا أُولِي الْقُرْبَىٰ وَالْمَسَاكِينَ وَالْمُهَاجِرِينَ فِي سَبِيلِ اللَّهِ ۖ وَلْيَعْفُوا وَلْيَصْفَحُوا ۗ أَلَا تُحِبُّونَ أَن يَغْفِرَ اللَّهُ لَكُمْ ۗ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
35፥10 ማሸነፍን የሚፈልግ የኾነ ሰው አሸናፊነት ለአላህ ብቻ ነው፤ እርሱን በመገዛት ማሸነፍን ይፈልግ፡፡ መልካም ንግግር ወደ እርሱ ይወጣል፡፡ በጎ ሥራም ከፍ ያደርገዋል፡፡ *እነዚያም መጥፎ ሥራዎችን የሚዶልቱ ለእነርሱ ብርቱ ቅጣት አላቸው፡፡ የእነዚያም ተንኮል እርሱ ይጠፋል*፡፡ مَن كَانَ يُرِيدُ ٱلْعِزَّةَ فَلِلَّهِ ٱلْعِزَّةُ جَمِيعًا ۚ إِلَيْهِ يَصْعَدُ ٱلْكَلِمُ ٱلطَّيِّبُ وَٱلْعَمَلُ ٱلصَّٰلِحُ يَرْفَعُهُۥ ۚ وَٱلَّذِينَ يَمْكُرُونَ ٱلسَّيِّـَٔاتِ لَهُمْ عَذَابٌۭ شَدِيدٌۭ ۖ وَمَكْرُ أُو۟لَٰٓئِكَ هُوَ يَبُورُ

ክፉውን በመልካም ማሸነፍ ሁለት ምንዳ አለው፦
28፥54 እነዚያ በመታገሳቸው ዋጋቸውን ሁለት ጊዜ ይሰጣሉ፡፡ *ክፉውንም ነገር በበጎ ምግባር ይገፈትራሉ*፡፡ ከሰጠናቸውም ሲሳይ ይለግሳሉ፡፡ أُولَـٰئِكَ يُؤْتَوْنَ أَجْرَهُم مَّرَّتَيْنِ بِمَا صَبَرُوا وَيَدْرَءُونَ بِالْحَسَنَةِ السَّيِّئَةَ وَمِمَّا رَزَقْنَاهُمْ يُنفِقُونَ

አላህ የተብቃቃ ነው፤ ሰደቃ ስንሰጥ ለእርሱ ታዛዥነትና ፍቅር መገለጫ ብቻ ነው፤ ይቅርባይነት ግን ማስከፋት ከሚከተላት ምጽዋት በላጭ ነው። አምላካችን አላህ ይቅርባዮች ከሚላቸው ባሮቹ ያድርገን! አሚን፦
2፥263 *መልካም ንግግር እና ምሕረት ማድረግ ማስከፋት ከሚከተላት ምጽዋት በላጭ ነው፡፡ አላህም ተብቃቂ ታጋሽ ነው*፡፡ قَوْلٌۭ مَّعْرُوفٌۭ وَمَغْفِرَةٌ خَيْرٌۭ مِّن صَدَقَةٍۢ يَتْبَعُهَآ أَذًۭى ۗ وَٱللَّهُ غَنِىٌّ حَلِيمٌۭ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ጅኒ እና ሸያጢን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

2፥208 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሁላችሁም በመታዘዝ ውስጥ ግቡ፡፡ የሰይጣንንም እርምጃዎች አትከተሉ፤ እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا ادْخُلُوا فِي السِّلْمِ كَافَّةً وَلَا تَتَّبِعُوا خُطُوَاتِ الشَّيْطَانِ ۚ إِنَّهُ لَكُمْ عَدُوٌّ مُّبِينٌ

“ጂን” جِنّ የሚለው ቃል “ጀንነ” جَنَّ ማለትም “ተሰወረ” ወይም “ተደበቀ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “ስውር” ወይም “ድብቅ” ማለት ነው፤ “ጅኒ” جني ደግሞ የጂን ብዙ ቁጥር ነው፤ ጂኒዎች የተፈጠሩት ከሰው በፊት ነው፤ ሰው የተፈጠረበት ንጥረ-ነገር ዐፈር እንደሆነ፤ መልአክ የተፈጠረበት ንጥረ-ነገር ብርሃን እንደሆነ ሁሉ ጂን የተፈጠረበት ንጥረ-ነገር ደግሞ እሳት ነው፦
15፥27 *ጃንንም ከሰው በፊት ከእሳት ነበልባል ፈጠርነው*፡፡ وَالْجَانَّ خَلَقْنَاهُ مِن قَبْلُ مِن نَّارِ السَّمُومِ
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 55, ሐዲስ 78
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”መላእክት ከብርሃን ተፈጥረዋል፤ ጂንዎች ከእሳት ነበልባል ተፈጥረዋል፤ አደም ለእናንተ እንደተገለጸላችሁ ከሚጭለቀለቅ ሸክላ ተፈጥሯል”*፡፡ عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم‏ خُلِقَتِ الْمَلاَئِكَةُ مِنْ نُورٍ وَخُلِقَ الْجَانُّ مِنْ مَارِجٍ مِنْ نَارٍ وَخُلِقَ آدَمُ مِمَّا وُصِفَ لَكُمْ ‏.‏

ጂኒዎች የተፈጠሩበት አላማ የፈጠራቸው አላህ እንዲያመልኩ ነው፦
51፥56 *ጂኒን እና ሰውንም ሊያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም*፡፡ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

ጂኒዎች እንደ ሰው ወንድና ሴት ሆነው የሚወለዱና የሚወልዱ፣ የሚኖሩና የሚሞቱ፤ የሚበሉና የሚጠጡ ፍጡሮች ናቸው፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 87, ሐዲስ 13
ኢብኑ ዐባስ”ረ.ዐ.” እንደተረከው ነብዩም”ﷺ” እንዲህ ይሉ ነበር፦ *”በሃያልነትህ እጠበቃለው፤ በእውነት የሚመለክ ከአንተ ከማትሞተው ሌላ የለም፤ ጂን እና ሰው ግን ይሞታል”*። أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم كَانَ يَقُولُ ‏ أَعُوذُ بِعِزَّتِكَ الَّذِي لاَ إِلَهَ إِلاَّ أَنْتَ، الَّذِي لاَ يَمُوتُ وَالْجِنُّ وَالإِنْسُ يَمُوتُونَ
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 312
ዘይድ ኢብኑ አርቀም እንደተረከው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ “ቆሻሻ ቦታዎች በሰይጣናት ይጎበኛሉ፤ ከእናንተም ወደዚያ ሲገባ፦ *”አላህ ሆይ! ከወንድ እና ከሴት ሰይጣናት በአንተ እጠበቃለው”* ይበል። عَنْ زَيْدِ بْنِ أَرْقَمَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ “‏ إِنَّ هَذِهِ الْحُشُوشَ مُحْتَضَرَةٌ فَإِذَا دَخَلَ أَحَدُكُمْ فَلْيَقُلِ اللَّهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنَ الْخُبُثِ وَالْخَبَائِثِ ‏”‏ ‏.‏

ጂኒዎች እንደ ሰው ነጻ ምርጫ ያላቸው ፍጡሮች ናቸው፤ በምርጫቸው ጀነት ወይም ጀሃነም መግባት ይችላሉ፦
11፥119 የጌታህም ቃል፣ *ገሀነምን ከጂኒዎ እና ከሰዎች ከሁሉም በእርግጥ እሞላታለሁ* በማለት ተፈጸመች። وَتَمَّتْ كَلِمَةُ رَبِّكَ لَأَمْلَأَنَّ جَهَنَّمَ مِنَ الْجِنَّةِ وَالنَّاسِ أَجْمَعِينَ
55፥45 *ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?* فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَان
55፥46 *በጌታውም ፊት መቆምን ለፈራ ሁለት ገነቶች አሉት*፡፡ وَلِمَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ جَنَّتَانِ

በተለይ “ጌታችሁ” የሚለው ቃል “ረቢኩማ” رَبِّكُمَا ሲሆን ሁለተኛ መደብ ሙተና”dual” ነው፤ ይህም ሁለቱንም ማለትም ሰውንና ጃንን ያመለክታል፤ “ታስተባብላላችሁ” የሚለው ቃል “ቱከዚባኒ” تُكَذِّبَانِ ሲሆን ሁለተኛ መደብ ሙተና”dual” ነው፤ ይህም ሁለቱንም ማለትም ሰውንና ጃንን ያመለክታል፤ የትንሳኤ ቀን ለሁለቱም የተቀጠረ ቀጠሮ ነው፦
55፥39 *በዚያም ቀን ሰውም ጃንም ከኃጢኣቱ ገና አይጠየቅም*፡፡ فَيَوْمَئِذٍ لَّا يُسْأَلُ عَن ذَنبِهِ إِنسٌ وَلَا جَانٌّ
44፥40 *የመለያው ቀን ለሁሉም ቀጠሯቸው ነው*፡፡ إِنَّ يَوْمَ الْفَصْلِ مِيقَاتُهُمْ أَجْمَعِينَ
6፥130 *የጂኒዎች እና የሰዎች ጭፍሮች ሆይ! አንቀጾቼን በእናንተ ላይ የሚተርኩ የዚህንም ቀናችሁን ቅጣት ማግኘትን የሚያስጠነቅቋችሁ ከእናንተው የኾኑ መልክተኞች አልመጧችሁምን? ይባላሉ*፡፡ يَا مَعْشَرَ الْجِنِّ وَالْإِنسِ أَلَمْ يَأْتِكُمْ رُسُلٌ مِّنكُمْ يَقُصُّونَ عَلَيْكُمْ آيَاتِي وَيُنذِرُونَكُمْ لِقَاءَ يَوْمِكُمْ هَـٰذَا
6፥128 *ሁሉንም የሚሰበስብባቸውንም ቀን አስታውስ፡፡ የጂኒዎች ጭፍሮች ሆይ! ከሰዎች ጭፍራን በማጥመም በእርግጥ አበዛችሁ* ይባላሉ፡፡ وَيَوْمَ يَحْشُرُهُمْ جَمِيعًا يَا مَعْشَرَ الْجِنِّ قَدِ اسْتَكْثَرْتُم مِّنَ الْإِن

ለጂኒዎች ጀነት እና ጀሃነም እንዲሁ የትንሳኤ ቀን ቀጠሮ እንዳላቸው እና የተፈጠሩበት አላማ ካየን ዘንዳ በነጻ ምርጫቸው ሙሥሊም አልያም ካፊር የመሆን ምርጫ አላቸው፦
72፥14 *«እኛም ከእኛ ውስጥ ሙስሊሞች አሉ፡፡ ከእኛም ውስጥ በዳዮች አሉ፡፡ የሰለሙም ሰዎች እነዚያ ቅንን መንገድ መረጡ፡፡»* وَأَنَّا مِنَّا الْمُسْلِمُونَ وَمِنَّا الْقَاسِطُونَ ۖ فَمَنْ أَسْلَمَ فَأُولَـٰئِكَ تَحَرَّوْا رَشَدًا
ከጂኒዎች መካከል አማንያን እንዳሉ ሁሉ ከሃድያንም አሉ፤ ከሃድያኑ ሰይጣናት ይባላሉ። “ኢብሊስ” إِبْلِيس በተፈጥሮው ከሰው ወይም ከመልአክ ሳይሆን ከጂን ሲሆን በመጥፎ ባህርይው ደግሞ “ሸይጧን” ነው፤ ለአደም አልሰግድም ብሎ ያመጸ እና አደም እና ሐዋን ያሳሳተ እርሱ ነው፦
18፥50 ለመላእክትም ለአደም ስገዱ፥ ባልናቸው ጊዜ የሆነውን አስታውስ ። ወዲያውም ሰገዱ፤ *ኢብሊስ ብቻ ሲቀር ከጂን ነበር*፤ ከጌታውም ትእዛዝ ወጣ፡፡ وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ كَانَ مِنَ الْجِنِّ فَفَسَقَ عَنْ أَمْرِ رَبِّهِ
2፥36 *ከእርሷም ሰይጣን አዳለጣቸው በውስጡም ከነበሩበት ድሎት አወጣቸው*፡፡فَأَزَلَّهُمَا الشَّيْطَانُ عَنْهَا فَأَخْرَجَهُمَا مِمَّا كَانَا فِيه

“ሸይጧን” شَّيْطَان የሚለው ቃል “ሸጠነ” شطن ማለትም “ራቀ” ወይም “ተገለለ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “የተገለለ” ወይም “የራቀ” ማለት ነው፤ “ሸያጢን” شَيَاطِين ደግሞ የሽይጧን ብዙ ቁጥር ሲሆን “ሰይጣናት” ማለት ነው፤ “ሸይጧን” ልክ እንደ “ሌባ” “ውሸታም” “ባለጌ” የባህርይ ስም እንጂ የተፀውኦ ስም አይደለም፤ ሸይጧን የሰውም የጂኒም አለ፦
6፥112 እንደዚሁም ለነቢያት ሁሉ *ከሰው እና ከጂን የኾኑን ሰይጣናት ጠላት* አደረግን፡፡ وَكَذَٰلِكَ جَعَلْنَا لِكُلِّ نَبِيٍّ عَدُوًّا شَيَاطِينَ الْإِنسِ وَالْجِن
114፥6 *«ከጂኒዎችም ከሰዎችም ሰይጣናት እጠበቃለሁ»* በል። مِنَ الْجِنَّةِ وَالنَّاسِ
23፥97 በልም *«ጌታዬ ሆ! ከሰይጣናት ጉትተጎታዎች በአንተ እጠበቃለሁ»* ፡፡ وَقُل رَّبِّ أَعُوذُ بِكَ مِنْ هَمَزَاتِ الشَّيَاطِينِ
7፥200 *ከሰይጣንም በኩል ጉትጎታ ቢያገኝህ በአላህ ተጠበቅ፡፡ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነውና*፡፡ وَإِمَّا يَنزَغَنَّكَ مِنَ الشَّيْطَانِ نَزْغٌ فَاسْتَعِذْ بِاللَّهِ ۚ إِنَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ

“ወሥዋሥ” وَسْوَاس ማለት “ጉትጎታ” ማለት ሲሆን ይህ ጉትጎታ የሚመጣው ከጂኒ ሰይጣናት ብቻ ሳይሆን ከሰውም ሰይጣናት ነው፤ ከዚህ ውስዋስ የምንጠበቀው በተዐዉዝ ነው፤ አላህ የሙናፊቂን መሪዎቻቸውን ፦ “ሰይጣኖቻቸው” ብሏል፤ ይህ የሚያሳየው የሰው ሸይጧን እንዳለ ነው፤ ሸይጧን ከአላህ ራህመት የተገለለ የራቀ ማለት መሆኑ ልብ በል፦
2፥14 እነዚያንም ያመኑትን በተገናኙ ጊዜ «አምነናል» ይላሉ፡፡ *ወደ ሰይጣኖቻቸውም* ባገለሉ ጊዜ «እኛ ከእናንተ ጋር ነን፤ እኛ በእነርሱ ተሳላቂዎች ብቻ ነን» ይላሉ፡፡ وَإِذَا لَقُوا الَّذِينَ آمَنُوا قَالُوا آمَنَّا وَإِذَا خَلَوْا إِلَىٰ شَيَاطِينِهِمْ قَالُوا إِنَّا مَعَكُمْ إِنَّمَا نَحْنُ مُسْتَهْزِئُونَ

እዚህ ድረስ ስለ ሸይጧን እሳቤ ከተረዳን ዘንዳ ረመዷን ላይ የሚታሰሩት ሸያጢን ከኩፋሩል ጂን ሲሆኑ ከእነርሱም የሚታሰሩት መሪዎቻቸው ናቸው፦
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 30, ሐዲስ 9
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው የአላህም መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”የረመዷን ወር ሲጀመር የሰማይ ደጆች ይከፈታሉ፤ የጀሃነም ደጆች ይዘጋሉ፤ ሰይጣናትም ይታሰራሉ”* سَمِعَ أَبَا هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ يَقُولُ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ إِذَا دَخَلَ شَهْرُ رَمَضَانَ فُتِّحَتْ أَبْوَابُ السَّمَاءِ، وَغُلِّقَتْ أَبْوَابُ جَهَنَّمَ، وَسُلْسِلَتِ الشَّيَاطِينُ ‏”‌‏
ኢማም አብኑ ኹዘይማህ: መጽሐፍ 3, ቁጥር 188
ነብዩም”ﷺ”፦ *”ሰይጣናት ይታሰራሉ” ያሉት ከእነርሱ አመጸኞቹ እንጂ ሁሉም ሰይጣናት አይደለም*። باب ذكر البيان أن النبي – صلى الله عليه وسلم – إنما أراد بقوله : ” وصفدت الشياطين ” مردة الجن منهم ، لا جميع الشياطين ”

ሚሽነሪዎች፦ “ሰይጣናት ከታሰሩ ሰው እንዴት በረመዷን ወር ይሳሳታል?” ብለው ይጠይቃሉ፤ ጥሩ ጥያቄ ነው። ሲጀመር በረመዷን ወር ሁሉም ሰይጣናት አይታሰሩም። ሲቀጥል የታሰሩት በሁለተኛ ደረጃ ያሉትን “ማሪድ” مَّارِد የተባሉትን መሪዎች ናቸው፤ የመጀመሪያ ደረጃ ያለው ዋናው ሸይጧን ኢብሊስ ነውና። ሲሰልስ ሰውን የሚወሰውሱ የሰው ሰይጣናት እራሳቸው አልታሰሩም፤ እነርሱን በረመዳን ወር ሊወሰውሱ ይችላሉ። ሲያረብብም ሰይጣን ቢታሰርም እርምጃዎቹ አልታሰሩም፤ አላህ አትከተሉ ያለው ሰይጣንን ብቻ ሳይሆን የሰይጣንን እርምጃዎች ጭምር ነው፦
2፥208 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሁላችሁም በመታዘዝ ውስጥ ግቡ፡፡ የሰይጣንንም እርምጃዎች አትከተሉ፤ እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا ادْخُلُوا فِي السِّلْمِ كَافَّةً وَلَا تَتَّبِعُوا خُطُوَاتِ الشَّيْطَانِ ۚ إِنَّهُ لَكُمْ عَدُوٌّ مُّبِينٌ

የሰይጣን እርምጃዎች “አህዋዕ” أَهْوَآء ማለት “ዝንባሌ”inclination” እና “ነፍሢያህ” نفسيه ናቸው፤ አህዋዕ ሊመለክ የሚችል ክፉ አዛዥ ነው፤ በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፦
25፥43 *ዝንባሌውን አምላኩ አድርጎ የያዘውን ሰው አየህን አንተ በእርሱ ላይ ጠባቂ ትኾናለህን?* أَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَـٰهَهُ هَوَاهُ أَفَأَنتَ تَكُونُ عَلَيْهِ وَكِيلًا
79፥40 *በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ* وَأَمَّا مَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ وَنَهَى النَّفْسَ عَنِ الْهَوَى
79፥41 *ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት*፡፡ فَإِنَّ الْجَنَّةَ هِيَ الْمَأْوَىٰ

ነፍሢያ አላህ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና፤ ነፍሲያ በራሷ ላይ እንጅ ክፉን አትሠራም፦
12፥53 «ነፍሴንም ከስሕተት አላጠራም፡፡ *ነፍስ ሁሉ ጌታዬ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር *”በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና*፡፡ ጌታዬ በጣም መሓሪ አዛኝ ነው» አለ፡፡ وَمَا أُبَرِّئُ نَفْسِي ۚ إِنَّ النَّفْسَ لَأَمَّارَةٌ بِالسُّوءِ إِلَّا مَا رَحِمَ رَبِّي ۚ إِنَّ رَبِّي غَفُورٌ رَّحِيمٌ
6፥164 በላቸው «እርሱ የሁሉ ጌታ ሲኾን ከአላህ በቀር ሌላን ጌታ እፈልጋለሁን *ነፍስም ሁሉ በራሷ ላይ እንጅ ክፉን አትሠራም*፡፡ قُلْ أَغَيْرَ ٱللَّهِ أَبْغِى رَبًّۭا وَهُوَ رَبُّ كُلِّ شَىْءٍۢ ۚ وَلَا تَكْسِبُ كُلُّ نَفْسٍ إِلَّا عَلَيْهَا
ሰይጣን የትንሳኤ ቀን፦ “ለእኔም በእናንተ ላይ ምንም ስልጣን አልበረኝም፤ ግን ጠራኋችሁ፡፡ ለእኔም ታዘዛችሁ፤ ስለዚህ አትውቀሱኝ፤ ነፍሶቻችሁንም ውቀሱ” ይላል፦
14፥22 ነገሩም በተፈጸመ ጊዜ ሰይጣን ይላቸዋል፦ *«አላህ እውነተኛውን ቃል ኪዳን ገባላችሁ፡፡ ቃል ኪዳንም ገባሁላችሁ፤ አፈረስኩባችሁም፡፡ ለእኔም በእናንተ ላይ ምንም ስልጣን አልበረኝም፡፡ ግን ጠራኋችሁ፡፡ ለእኔም ታዘዛችሁ፡፡ ስለዚህ አትውቀሱኝ፤ ነፍሶቻችሁንም ውቀሱ፡፡ እኔ የምረዳችሁ አይደለሁም፡፡ እናንተም የምትረዱኝ አይደላችሁም፡፡ እኔ ከአሁን በፊት ለአላህ ተጋሪ በአደረጋችሁት ነገር ካድኩ፡፡ በዳዮቹ ለእነርሱ በእርግጥ አሳማሚ ቅጣት አላቸው»*። وَقَالَ الشَّيْطَانُ لَمَّا قُضِيَ الْأَمْرُ إِنَّ اللَّهَ وَعَدَكُمْ وَعْدَ الْحَقِّ وَوَعَدتُّكُمْ فَأَخْلَفْتُكُمْ ۖ وَمَا كَانَ لِيَ عَلَيْكُم مِّن سُلْطَانٍ إِلَّا أَن دَعَوْتُكُمْ فَاسْتَجَبْتُمْ لِي ۖ فَلَا تَلُومُونِي وَلُومُوا أَنفُسَكُم ۖ مَّا أَنَا بِمُصْرِخِكُمْ وَمَا أَنتُم بِمُصْرِخِيَّ ۖ إِنِّي كَفَرْتُ بِمَا أَشْرَكْتُمُونِ مِن قَبْلُ ۗ إِنَّ الظَّالِمِينَ لَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ

ስለዚህ ለምንሰራው መጥፎ ሥራ ሰይጣንን ተጠያቂ ማድረግ አንችልም፤ ሰይጧን ለእኛ ግልጽ ጠላት ነው፤ እርሱ የሚያጠቃን በእርምጃዎቹ ነው። አላህ ከሸይጧን እና ከእርምጃዎቹ ይጠብቀን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ያህዌህ ነውን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥72 እነዚያ *«አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው»* ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ

የሥላሴ አማንያን ኢየሱስን አምላክ ለማድረግ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የማይደረምሱት መሬት የለም። መዝሙር ላይ "ያህዌህ ዐረገ" ስለሚል ያ ያረገው ያህዌህ ኢየሱስ ነው ብለው ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል፦
መዝሙር 47፥5 አምላክ በእልልታ፥ *"ያህዌህ በመለከት ድምፅ ዐረገ*"። (KJV) God is *"gone up"* with a shout, the LORD with the sound of a trumpet.

"ዐረገ" የሚለው የዕብራይስጥ ቃል "ዓላህ" עָלָ֣ה ሲሆን "ወጣ" ወይም "ከፍ አለ"gone up" ማለት ነው። ወደ ሰማየ ሰማያት አብ ወጥቷል፦
መዝሙር 68፥33 በምሥራቅ በኩል *"ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለያህዌህ ዘምሩ"*፤ የኃይል ቃል የሆነ ቃሉን፥ እነሆ፥ ይሰጣል።
መዝሙር 68፥4 *"ወደ ሰማያት ለወጣም መንገድ አድርጉ፤ ስሙ “ያህ” בְּיָ֥הּ ነው"*፥
(KJV) Sing unto God, sing praises to his name: extol him that rideth upon the heavens by his name JAH, and rejoice before him.

ያህ የያህዌህ ምጻረ-ቃል ነው። በእነዚህ ጥቅስ መሰረት ወደ ሰማይ የወጣው ማን ነው? ያህዌህ! ይህን ታውቅ እንደ ሆንህ ስሙ ማን ነው? ያህዌህ! የልጁ ስምስ ማን ነው? ኢየሱስ፦
ምሳሌ 30፥4 ወደ ሰማይ የወጣ የወረደስ ማን ነው? ነፋስንስ በእጁ የጨበጠ ማን ነው? ውኃንስ በልብሱ የቋጠረ ማን ነው? የምድርን ዳርቻ ሁሉ ያጸና ማን ነው? ይህን ታውቅ እንደ ሆንህ፥ ስሙ ማን ነው? የልጁስ ስም ማን ነው?

በዚህ ጥቅስ መሰረት የልጁ ባለቤት ወደ ሰማይ ወጣ የተባለው አብ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር ወጣ የተባለው አብ ነው። አይ አይደለም! ወደ ሰማይ የወጣ የወረደስ ማን ነው? ኢየሱስ! ይህን ታውቅ እንደ ሆንህ ስሙ ማን ነው? ኢየሱስ! የልጁ ስምስ ማን ነው? ኢየሱስ! ያስኬዳልን? አየሱስ የአብና የወልድ ስም ነውን? ኢየሱስ ልጅ አለውን? የኢየሱስ ልጅ የሚባል ኢየሱስ አለን? ቅሉ ግን የወጣው ያህዌህ አብ ሲሆን የልጁ ስም ኢየሱስ ነው ካላችሁ እንግዲያውስ ወጣ የተባለው በመዝሙር ላይ አብ ነው። ያህዌህ አብ ይወርዳል፦
ዘፍጥረት 46፥4 እኔ ወደ ግብፅ አብሬህ *"እወርዳለሁ"*፥ ከዚያም ደግሞ እኔ አወጣሃለሁ፤ ዮሴፍም እጁን በዓይንህ ላይ ያኖራል።
ዘጸአት 19፥18 *ያህዌህም በእሳት ስለ ወረደበት"* የሲና ተራራ ሁሉ ይጤስ ነበር፤
ዘኍልቍ 11፥17 *እኔም እወርዳለሁ*፥ በዚያም እነጋገርሃለሁ፥

የወረደው እንደሚወጣ ከላይ አይተናል። ያህዌህ መውረድ መውጣት ብቻ ሳይሆን ክንፉና ላባ አለው ይበራል፦
መዝሙር 91፥4 *በላባዎቹ ይጋርድሃል፥ በክንፎቹም* በታች ትተማመናለህ።
2ኛ ሳሙኤል 22፥11 በኪሩብም ላይ ተቀምጦ *"በረረ"*፤
መዝሙር 18፥10 በኪሩቤልም ላይ ተቀምጦ *"በረረ"*፥

ስለዚህ "ዐረገ" "ወጣ" "ወረደ" "በረረ" ስለአብ ነው የሚናገረው። ለመሆኑ ያህዌህ አንድ ነው። ያ አንዱ ያህዌህ ዐረገ ሲባል ኢየሱስን ካመለከተ ይህ አንዱ ያህዌው አምላኩ ማን ነው? ምክንያቱም ዐራጊው ማንነት የሚያርገው ወደ እግዚአብሔር አምላኩ ነው፤ ዐርጎም የሚቀመጠው በእግዚአብሔርም ቀኝ ነው፦
ማርቆስ 16፥19 ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ *ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ*።
ዮሐንስ 17፥11 *”እኔም ወደ አንተ እመጣለሁ”*።
ዮሐንስ 20፥17 *እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ”* ብለሽ ንገሪአቸው፥ አላት።

ልብ አድርጉ ኢየሱስ እራሱን በመጀመሪያ መደብ “እኔ” እያለ እግዚአብሔር ደግሞ በሁለተኛ መደብ “አንተ” እያለ በጸሎት ሲናነጋግረው ተመልከቱ፤ ዓራጊው ኢየሱስ ሲሆን ከሚያርግበት ከእግዚአብሔር ማንነት ለመለየት “ወደ” የሚል መስተዋድድ ተጠቅሟል፤ “ወደ አምላኬ ዓርጋለሁ” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ “አምላኬ” ማለቱ የሚያርገው ማንነት አምላክ አለው። እግዚአብሔር ከሆነ ወደ እግዚአብሔር የሚያርገው እግዚአብሔር አምላክ አለውን? አዎ! ብሎ ማመን ምን አይነት ድራማና ቁማር ነው? ኢየሱስ ያያረገው በአካል እንጂ በመለከት አይደለም። ሲቀጥል "ያህዌህ ወጣ" ትንቢት ሳይሆን አላፊ ግስ ነው፥ ትንቢት ነው ከተባለ ወደ ሰማይ የወጣ ኤልያስ ያህዌህ ነውን? ምክንያቱም ኤልያስም ወደ ሰማይ ወጣ ስለሚል፦
2 ነገሥት 2፥11 *"ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ወጣ"*።

ስለዚህ ያህዌህ ወጣ የሚለውን ትንቢት ነው ብሎ መሞገት ውኃ የማይቋጥርና የማያነሳ ስሁት ሙግት ነው።
"አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው" ያሉ በእርግጥ ካዱ፦
5፥72 እነዚያ *«አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው»* ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ያህዌህ አይደለም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥72 እነዚያ *«አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው»* ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ

ሥላሴአውያን መዝሙር ላይ "ያህዌህ ይመጣል" ስለሚል ያ የሚመጣው ያህዌህ ኢየሱስ ነው ብለው ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል፦
መዝሙር 50፥2-3 ከክብሩ ውበት ከጽዮን *"ያህዌህ ግልጥ ሆኖ ይመጣል"*። *"አምላካችን ይመጣል"* ዝምም አይልም፤

ያህዌህ ለፍርድ እንደሚመጣ ብዙ የብሉያት አናቅጽ ይናገራሉ፦
መዝሙር 96፥13 ይመጣልና፤ *በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣልና፤ እርሱም ዓለምን በጽድቅ አሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል"*።
1ኛ ዜና መዋዕል 16፥33 *"በምድር ሊፈርድ ይመጣልና"*፥
መዝሙር 98፥8 ወንዞችም በአንድነት በእጅ ያጨብጭቡ፤ ተራሮች ደስ ይበላቸው፥ *"በምድር ሊፈርድ ይመጣልና"*።
ኢሳይያስ 66፥15 እነሆ *"ያህዌህ መዓቱን በቍጣ፥ ዘለፋውንም በእሳት ነበልባል ይመልስ ዘንድ ከእሳት ጋር ይመጣል"*፥

ያህዌህ ለፍርድ እንደሚመጣ በእነዚህ ጥቅሶች ካየን ዘንዳ ይህ ያህዌህ አብ እንደሆነ በሰከነ እና በሰላ አእምሮ ማየት ይቻላል፦
ዳንኤል 7፥22 *በዘመናት የሸመገለው እስኪመጣ ድረስ፥ ፍርድም ለልዑሉ ቅዱሳን እስኪሰጥ ድረስ"*፥

"በዘመናት የሸመገለው" መጥቶ ፍርድን ለልዑል ቅዱሳን እንደሚሰጥ ይናገራል። "በዘመናት የሸመገለው" እዛው ዐውድ ላይ ለሰው ልጅ ግዛትና ክብር መንግሥትም እንደሰጠው ይናገራል፦
ዳንኤል 7፥13-14 በሌሊት ራእይ አየሁ፤ እነሆም፥ *"የሰው ልጅ የሚመስል ከሰማይ ደመናት ጋር መጣ በዘመናት ወደ ሸመገለውም ደረሰ"*፤ ወደ ፊቱም አቀረቡት። ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የሚናገሩ ሁሉ ይገዙለት ዘንድ *"ግዛትና ክብር መንግሥትም ተሰጠው"*።

በዘመናት የሸመገለው አባት አብ ከሆነ የሰው ልጅ የተባለው ወልድ ነው ካላችሁ፥ ወልድ ወደ አብ ደርሶ ግዛትና ክብር መንግሥትም ከተሰጠው እንግዲያውስ "በዘመናት የሸመገለው እስኪመጣ ድረስ፥ ፍርድም ለልዑሉ ቅዱሳን እስኪሰጥ ድረስ" የተባለው አብ ነው። አብ ለፍርድ ይመጣል ማለት ነው። "በዘመናት የሸመገለው" ለመፍረድ በዙፋኑ ይቀመጣል፦
ዳንኤል 7፥9 ዙፋኖችም እስኪዘረጉ ድረስ አየሁ፥ *"በዘመናት የሸመገለውም ተቀመጠ"*፤

ልጁን የላከው የወይን አትክልት ጌታ አብ ሲመጣ ክፉዎችን በክፉ ያጠፋል፦
ማቴዎስ 21፥33 ሌላ ምሳሌ ስሙ። *"የወይን አትክልት የተከለ ባለቤት ሰው ነበረ"*፤
ማቴዎስ 21፥37 በኋላ ግን፦ *"ልጄንስ ያፍሩታል፡ ብሎ ልጁን ላከባቸው"*።
ማቴዎስ 21፥40 እንግዲህ *የወይኑ አትክልት ጌታ በሚመጣ ጊዜ"* በእነዚህ ገበሬዎች ምን ያደርግባቸዋል? እነርሱም፦ *"ክፉዎችን በክፉ ያጠፋቸዋል"*፥ አሉት።

ልብ አድርግ "የወይን አትክልት ጌታ" በሚመጣ ጊዜ እንደተባለ። ራእይ ላይም ያለውና የነበረው የሚመጣው ጌታ አምላክ ከኢየሱስ "እና" በሚል መስተጻምር ተለይቷል፦
ራእይ 1፥4 *"ካለውና ከነበረው ከሚመጣውም "እና" በዙፋኑም ፊት ካሉት ከሰባቱ መናፍስት "እና" ከታመነውም ምስክር ከሙታንም በኵር የምድርም ነገሥታት ገዥ ከሆነ ከኢየሱስ ክርስቶስ"* ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። KJV
Ο Ιωάννης προς τις επτά εκκλησίες στην επαρχία της Ασίας: Χάρη και ειρήνη σε σας από αυτόν που είναι, και ποιος ήταν και ποιος θα έρθει, και από τα επτά πνεύματα πριν από το θρόνο του, και από τον Ιησού Χριστό, ο οποίος είναι ο πιστός μάρτυρας, ο πρωτότοκος εκ των νεκρών, και ο άρχων των βασιλέων της γης.

ጸጋና ሰላም፦
1. ካለውና ከነበረው ከሚመጣውም
2. ከሰባቱ መናፍስት
3. ከኢየሱስ ክርስቶስ
ለእናንተ ይሁን! ይላል። ልክ ጸጋና ሰላም "ከእግዚአብሔር ከአባታችን እና ከጌታም ከኢየሱስ" ለእናንተ ይሁን! እንደሚል እንደ ጳውሎስ ሰላምታ። በግራንቪል ሻርፕ የግሪክ ሰዋስው አምስተኛው ሕግ "ካይ" και ማለትም "እና" የሚል መስተጻምር እና "አፓ" από ማለትም "ከ" የሚለው መስተዋድድ ተያይዘው የሚመጣውን አብን እና ኢየሱስን ሁለት የተለያዩ ማንነቶች"persons" አድርጎ አስቀምጧቸዋል።
አብ ይመጣል ማለት ቃል በቃል ሳይሆን የእርሱ አላማ መፈጸምንና የእርሱ ክብር መገለጥ ያመለክታል፣ ምክንያቱም አብ ብዙ ጊዜ በብሉይ ኪዳን እንደመጣ ስለሚናገር፦
ዘኍልቍ 23፥3 በለዓምም ባላቅን፦ በመሥዋዕትህ ዘንድ ቆይ፥ እኔም እሄዳለሁ፤ ምናልባት *"ያህዌህ ሊገናኘኝ ይመጣል"*፤ እርሱም የሚገልጥልኝን እነግርሃለሁ አለው።
ዘፍጥረት 18፥14 በውኑ ለያህዌህ የሚሳነው ነገር አለን? *"የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ አንተ እመለሳለሁ"*፤ ሣራም ልጅን ታገኛለች።

ያህዌህ በዓመቱ ከይስሐቅ ልደት በኃላ መጥቶ ሲመለስ ቃል በቃል ጽንፈ-ዓለሙን ለቆና ትቶ መጣ ማለት እንዳልሆነ እሙንና ቅቡል ነው። ከላይ የብሉያት እና የአዲሳት አናቅጽ የአብን ለፍርድ መምጣት በዚህ ልክና መልክ ተረዱት። ስለዚህ ያህዌህ ለፍርድ ይመጣል ማለት አብ ሊፈርድ ይመጣል ማለት እንጂ ኢየሱስ ይመጣል ስለተባለ ያህዌህ ነው ማለት በፍጹም አይደለም። በላይ ባለው በመዝሙር 50፥2-3 ጥቅስ መሠረት ኢየሱስ ያህዌህ አይደለም። ኢየሱስ ያህዌህ ነው ብሎ መሞገት ውኃ የማይቋጥርና የማያነሳ ስሁት ሙግት ነው።
"አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው" ያሉ በእርግጥ ካዱ፦
5፥72 እነዚያ *«አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው»* ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሺርክ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥48 *"አላህ በእርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም፡፡ ከዚህ ሌላ ያለውንም ኀጢአት ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው ታላቅን ኀጢአት በእርግጥ ቀጠፈ"*፡፡ إِنَّ اللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَن يَشَاءُ ۚ وَمَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدِ افْتَرَىٰ إِثْمًا عَظِيمًا

“ሺርክ” شِرْك የሚለው ቃል “አሽረከ” أَشْرَكَ ማለትም “አጋራ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን በአላህ ላይ “ማጋራት” ማለት ነው። ሺርክ ሁለት ነገርን ያቅፋል፥ አንደኛ “ሙሽሪክ” ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ “ሸሪክ” ነው። በአላህ ላይ የሚጋራው ማንነት “ሙሽሪክ” مُشْرِك ማለትም “አጋሪ” ሲባል በአላህ ላይ የሚያጋሩት ማንነትና ምንነት ደግሞ “ሸሪክ” شَرِيك ማለትም “ተጋሪ” ይባላሉ።
እዚህ ድረስ በቋንቋው ማብራሪያ ከተረዳን ዘንዳ አንድ ሰው በዱኒያ እያለ ማንኛውንም ኀጢያት ሰርቶ ነገር ግን በተውበት ወደ አላህ ቢመለስ ይቅር ይባላል፦
39፥53 በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ *"አላህ ኃጢኣቶችን በሙሉ ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና"*፡፡ قُلْ يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ أَسْرَفُوا عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ لَا تَقْنَطُوا مِن رَّحْمَةِ اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ جَمِيعًا ۚ إِنَّهُ هُوَ الْغَفُورُ الرَّحِيمُ
39፥54 *«ቅጣቱም ወደ እናንተ ከመምጣቱ እና ከዚያም የማትረዱ ከመኾናችሁ በፊት ወደ ጌታችሁ በመጸጸት ተመለሱ"*፡፡ ለእርሱም ታዘዙ፡፡ وَأَنِيبُوا إِلَىٰ رَبِّكُمْ وَأَسْلِمُوا لَهُ مِن قَبْلِ أَن يَأْتِيَكُمُ الْعَذَابُ ثُمَّ لَا تُنصَرُونَ

"ጀሚዓ" جَمِيعًا ማለት "በሙሉ" ማለት ነው። በሞት አሊያም በትንሳኤ ቀን ቅጣቱ ከመምጣቱ በፊት ወደ ጌታችን በንስሃ ከተመለስን አላህ ማንኛውም ኃጢኣት ይምራል። ለዚህ ናሙና የሚሆነው የእስራኤል ልጆች በምድረ በዳ በአላህ ላይ ወይፈንን አጋርተው ከዚያም ወደ አላህ በተውበት ሲመለሱ ይቅር መባላቸው ነው፦
7፥152 *"እነዚያ ወይፈኑን አምላክ አድርገው የያዙ ከጌታቸው ዘንድ ቁጣ በቅርቢቱም ሕይወት ውርደት በእርግጥ ያገኛቸዋል"*፡፡ እንዲሁም ቀጣፊዎችን እንቀጣለን፡፡ إِنَّ الَّذِينَ اتَّخَذُوا الْعِجْلَ سَيَنَالُهُمْ غَضَبٌ مِّن رَّبِّهِمْ وَذِلَّةٌ فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا ۚ وَكَذَٰلِكَ نَجْزِي الْمُفْتَرِينَ
7፥153 *"እነዚያም ኃጢአቶችን የሠሩ ከዚያም ከእርሷ በኋላ የተጸጸቱ ያመኑም ጌታህ ከእርሷ በኋላ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነው"*፡፡ وَالَّذِينَ عَمِلُوا السَّيِّئَاتِ ثُمَّ تَابُوا مِن بَعْدِهَا وَآمَنُوا إِنَّ رَبَّكَ مِن بَعْدِهَا لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ

ዐውዱ ላይ "አለዚነ" الَّذِينَ ማለትም "እነዚያ" በሚለው አንጻራዊ ተውላጠ-ስም በፊት መነሻ ላይ "ወ" وَ የሚል አያያዥ መስተጻምር ይጠቀማል። ይህ የሚያሳየው "እነዚያም" የተባሉት ወይፈኑን አምላክ አድርገው የያዙት ሰዎች መሆናቸውን እንረዳለን ማለት ነው። በተለይ "ከእርሷ" ተብላ የተጠቀሰችው ተውላጠ-ስም ከላይ የተጠቀሰውን የኃጢያት ድርጊት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። ከዚያም ድርጊታቸው የተጸጸቱትን አላህ ይቅር ብሏቸዋል፦
4፥153 *"ከዚያም ተዓምራቶች ከመጡላቸው በኋላ ወይፈኑን አምላክ አድርገው ያዙ፡፡ ከዚያም ይቅር አልን"*፡፡ ሙሳንም ግልጽ ስልጣንን ሰጠነው፡፡ ثُمَّ اتَّخَذُوا الْعِجْلَ مِن بَعْدِ مَا جَاءَتْهُمُ الْبَيِّنَاتُ فَعَفَوْنَا عَن ذَٰلِكَ ۚ وَآتَيْنَا مُوسَىٰ سُلْطَانًا مُّبِينًا

ነገር ግን አንድ ሰው ካጋራ በኋላ ምህረት የሚያገኘው በህይወት ዘመን ቆይታው እንጂ ሞት በመጣበት ጊዜ አሊያም ከኃዲዎች ሆነው ለሚሞቱ አይደለም፦
4፥17 *ጸጸትን መቀበል በአላህ ላይ የሚገባው ለእነዚያ ኀጢአትን በስህተት ለሚሠሩና ከዚያም ከቅርብ ጊዜ ለሚጸጸቱት ብቻ ነው፡፡ እነዚያንም አላህ በእነርሱ ላይ ጸጸትን ይቀበላል"*፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡ إِنَّمَا التَّوْبَةُ عَلَى اللَّهِ لِلَّذِينَ يَعْمَلُونَ السُّوءَ بِجَهَالَةٍ ثُمَّ يَتُوبُونَ مِن قَرِيبٍ فَأُولَـٰئِكَ يَتُوبُ اللَّهُ عَلَيْهِمْ ۗ وَكَانَ اللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمًا
4፥18 *"ጸጸትንም መቀበል ለእነዚያ ኀጢአቶችን ለሚሠሩ አንዳቸውንም ሞት በመጣበት ጊዜ «እኔ አሁን ተጸጸትኩ» ለሚልና ለነዚያም እነርሱ ከሓዲዎች ኾነው ለሚሞቱ አይደለችም፡፡ እነዚያ ለእነርሱ አሳማሚን ቅጣት አዘጋጅተናል"*፡፡ وَلَيْسَتِ التَّوْبَةُ لِلَّذِينَ يَعْمَلُونَ السَّيِّئَاتِ حَتَّىٰ إِذَا حَضَرَ أَحَدَهُمُ الْمَوْتُ قَالَ إِنِّي تُبْتُ الْآنَ وَلَا الَّذِينَ يَمُوتُونَ وَهُمْ كُفَّارٌ ۚ أُولَـٰئِكَ أَعْتَدْنَا لَهُمْ عَذَابًا أَلِيمًا

"ከዚያም ከቅርብ ጊዜ" የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት። ከኃዲዎች ሆነው የሚሞቱ በትንሳኤ ቀን በሰሩት ነገር ይጸጸታሉ፣ ነገር ግን ምንም አይጠቅማቸውም፦
39፥56 *የካደች ነፍስ፦ «እኔ ከሚሳለቁት የነበርኩ ስኾን በአላህ በኩል ባጓደልኩት ዋ ጸጸቴ» ማለቷን ለመፍራት፤ أَن تَقُولَ نَفْسٌ يَا حَسْرَتَىٰ عَلَىٰ مَا فَرَّطتُ فِي جَنبِ اللَّهِ وَإِن كُنتُ لَمِنَ السَّاخِرِينَ
39፥57 *ወይም ቅጣቱን በምታይ ጊዜ፣ ለኔ ወደ ምድረ ዓለም አንድ ጊዜ መመለስ በኖረኝና ከበጎ አድራጊዎቹ በሆንኩ ማለቷን ለመፍራት أَوْ تَقُولَ لَوْ أَنَّ اللَّهَ هَدَانِي لَكُنتُ مِنَ الْمُتَّقِينَ
39፥58 *"ወይም ቅጣቱን በምታይ ጊዜ «ለእኔ ወደ ምድረ ዓለም አንድ ጊዜ መመለስ በኖረኝና ከበጎ አድራጊዎቹ በኾንኩ» ማለቷን ለመፍራት መልካሙን ተከተሉ"*፡፡ أَوْ تَقُولَ حِينَ تَرَى الْعَذَابَ لَوْ أَنَّ لِي كَرَّةً فَأَكُونَ مِنَ الْمُحْسِنِينَ
ስለዚህ አንድ ሰው በሞት ጣዕር ላይ አሊያም በሚቀሰቀስበት ቀን በተውበት ቢጸጸት ጸጸቱ ተቀባይነት የለውም። “ላ ኢላሃ ኢለ ሏህ” لَا إِلَٰهَ إِلَّا اللَّهُ ብሎ ጣዖታትን ውድቅ አድርጎ እና አንዱን አምላክ አላህ በብቸኝነት ያመለከ ሰው ለሠራው መጥፎ ሥራ ተውበት ከገባ አላህ መጥፎ ሥራዎቻቸውን በመልካም ሥራዎች ይለውጥለታል፦
25፥70 *ተጸጽቶ የተመለሰና ያመነ መልካምንም ሥራ የሠራ ሰው ብቻ ሲቀር፡፡ እነዚያም አላህ መጥፎ ሥራዎቻቸውን በመልካም ሥራዎች ይለውጣል፡፡ አላህም እጅግ መሓሪ አዛኝ ነው*፡፡ إِلَّا مَن تَابَ وَآمَنَ وَعَمِلَ عَمَلًا صَالِحًا فَأُولَـٰئِكَ يُبَدِّلُ اللَّهُ سَيِّئَاتِهِمْ حَسَنَاتٍ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا
16፥119 ከዚያም ጌታህ *ለእነዚያ በስሕተት መጥፎን ለሠሩና ከዚያም ከዚህ በኋላ ለተጸጸቱ ሥራቸውንም ላበጁ ጌታህ ከእርሷ በኋላ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነው*፡፡ ثُمَّ إِنَّ رَبَّكَ لِلَّذِينَ عَمِلُوا السُّوءَ بِجَهَالَةٍ ثُمَّ تَابُوا مِن بَعْدِ ذَٰلِكَ وَأَصْلَحُوا إِنَّ رَبَّكَ مِن بَعْدِهَا لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ

ነገር ግን “ላ ኢላሃ ኢለ ሏህ” ይዘው በሚሠሩት መጥፎ ሥራ ተውበት ካላደረጉ ብጤዋን እንጅ አይመነዱም፤ በመጥፎም የመጡ ሰዎች ፊቶቻቸው በእሳት ውስጥ ይደፋሉ፤ በክፉም ሥራ የመጡ ሰዎች እነዚህ መጥፎዎችን የሠሩ ይሠሩት የነበሩትን እንጅ አይመነዱም፦
27፥90 *በመጥፎም የመጡ ሰዎች ፊቶቻቸው በእሳት ውስጥ ይደፋሉ፡፡ «ትሠሩት የነበራችሁትን እንጅ አትመነዱም»* ይባላሉ፡፡ وَمَن جَاءَ بِالسَّيِّئَةِ فَكُبَّتْ وُجُوهُهُمْ فِي النَّارِ هَلْ تُجْزَوْنَ إِلَّا مَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ
29፥4 *ይልቁንም እነዚያ መጥፎዎችን ሥራዎች የሚሠሩት ሊያመልጡን ይጠረጥራሉን?* ያ የሚፈርዱት ፍርድ ከፋ፡፡ أَمْ حَسِبَ الَّذِينَ يَعْمَلُونَ السَّيِّئَاتِ أَن يَسْبِقُونَا ۚ سَاءَ مَا يَحْكُمُونَ

አማንያን “ላ ኢላሃ ኢለ ሏህ” በመያዛቸው በሠሩት መጥፎ ሥራ ልክ ተቀጥተው አሊያም በነቢያችን”ﷺ” ምልጃ የጀነት ናቸው። የነቢያችን”ﷺ” ምልጃ በትንሳኤ ቀን የሚያገኘው ከልቡ ወይም ከነፍሱ፦ “ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም” ላለ ሰው ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 3, ሐዲስ 41
አቢ ሁረይራ እንደተረከው፦ *”እኔም፦ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሆይ! በትንሳኤ ቀን ማነው እድለኛ ሰው የእርስዎን ምልጃ የሚያገኘው? አልኩኝ፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ “አቢ ሁረይራ ሆይ! ንግግር ለመማር የአንተን ቆይታ ዐውቃለው፤ እንደማስበው ስለዚህ ጉዳይ ከአንተ በፊት ማንም አልጠየቀኝም። በትንሳኤ ቀን የእኔን ምልጃ የሚያገኝ እድለኛ ሰው ከልቡ ወይም ከነፍሱ፦ “ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም” ያለ ነው*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّهُ قَالَ قِيلَ يَا رَسُولَ اللَّهِ، مَنْ أَسْعَدُ النَّاسِ بِشَفَاعَتِكَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ لَقَدْ ظَنَنْتُ يَا أَبَا هُرَيْرَةَ أَنْ لاَ يَسْأَلَنِي عَنْ هَذَا الْحَدِيثِ أَحَدٌ أَوَّلُ مِنْكَ، لِمَا رَأَيْتُ مِنْ حِرْصِكَ عَلَى الْحَدِيثِ، أَسْعَدُ النَّاسِ بِشَفَاعَتِي يَوْمَ الْقِيَامَةِ مَنْ قَالَ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ، خَالِصًا مِنْ قَلْبِهِ أَوْ نَفْسِهِ ‏”‌‏.‏

በአላህ አምልኮ ላይ ሌላ ማንነትን እና ምንነት ያላሻረከ ነገር ግን ዐበይት ወንጀሎችን የሠራ በነቢያችን”ﷺ” ምልጃ ከጀሃነም ቅጣት ነጻ ወጥቶ ወደ ጀነት ይገባል፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 2622
አነሥ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ *”የእኔ ምልጃ ከእኔ ኡማህ ዐበይት ወንጀሎችን ለሰሩ ሰዎች ነው*። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ شَفَاعَتِي لأَهْلِ الْكَبَائِرِ مِنْ أُمَّتِي
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 81, ሐዲስ 155
ዒምራን ኢብኑ ሑሴይን”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *”ጥቂት ሕዝብ ከእሳት ወጥተው ወደ ጀነት በሙሐመድ”ﷺ” ምልጃ ይገባሉ፤ ጀሀነሚዪን ተብለው ይጠራሉ*። حَدَّثَنَا عِمْرَانُ بْنُ حُصَيْن ٍ ـ رضى الله عنهما ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ يَخْرُجُ قَوْمٌ مِنَ النَّارِ بِشَفَاعَةِ مُحَمَّدٍ صلى الله عليه وسلم فَيَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ، يُسَمَّوْنَ الْجَهَنَّمِيِّينَ ‏
በአላህ ላይ ያላሻረከ ለሠራው ማንኛውም ወንጀል ተውበት እስካላደረገ ድረስ ቅጣቱን በጀሃነም ይቀጣል። ቅጣቱ ሲያልቅ ወደ ጀነት ይመለሳል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 113
አቡ ዘር እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ጂብሪል ወደ እኔ መጣና፦ "ማንም በአላህ ላይ ሳያጋራ የሞተ ጀነት ይገባል" ብሎ የምስራች ሰጠኝ። እኔም፦ "ቢሰርቅም ዝሙትም ቢሰራ? ብዬ ጠየኩት፥ እርሱም፦ "አዎ ቢሰርቅም ዝሙትም ቢሰራ" አለኝ*። قَالَ سَمِعْتُ أَبَا ذَرٍّ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ أَتَانِي جِبْرِيلُ فَبَشَّرَنِي أَنَّهُ مَنْ مَاتَ لاَ يُشْرِكُ بِاللَّهِ شَيْئًا دَخَلَ الْجَنَّةَ ‏"‌‏.‏ قُلْتُ وَإِنْ سَرَقَ وَإِنْ زَنَى قَالَ ‏"‏ وَإِنْ سَرَقَ وَإِنْ زَنَى
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 10, ሐዲስ 201
አቢ ሁረይራ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦.... *"ከሰዎች መካከል በሥራቸው ለዘላለም በጀሃነም ሲዘወትሩ ሌሎች ደግሞ ቅጣት ተቀብለው ከጀሃነም ይወጣሉ፣ አላህ የሻው ከጀሃነም ሰዎች መካከል ምህረት ያደርግለታል። ለመላእክትም፦ "እርሱን ብቻ ያመለከውን አውጡ" ብሎ ያዛቸዋል"*። تَخْطَفُ النَّاسَ بِأَعْمَالِهِمْ، فَمِنْهُمْ مَنْ يُوبَقُ بِعَمَلِهِ، وَمِنْهُمْ مَنْ يُخَرْدَلُ ثُمَّ يَنْجُو، حَتَّى إِذَا أَرَادَ اللَّهُ رَحْمَةَ مَنْ أَرَادَ مِنْ أَهْلِ النَّارِ، أَمَرَ اللَّهُ الْمَلاَئِكَةَ أَنْ يُخْرِجُوا مَنْ كَانَ يَعْبُدُ اللَّهَ

"ከሰዎች መካከል ለዘላለም በጀሃነም የሚዘወተሩ" በአላህ ላይ ያጋሩ ናቸው። አላህ በእርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም። ከዚህ ሌላ ያለውንም ኀጢአት ለሚሻው ሰው ቀጥቶ አሊያም በነቢያችን"ﷺ" ሸፋዓ ይምራል። የሚያጋራን ሰው አላህ ገነትን በእርሱ ላይ በእርግጥ እርም አደረገ፤ የአጋሪው መኖሪያውም እሳት ናት፦
4፥48 *"አላህ በእርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም፡፡ ከዚህ ሌላ ያለውንም ኀጢአት ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው ታላቅን ኀጢአት በእርግጥ ቀጠፈ"*፡፡ إِنَّ اللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَن يَشَاءُ ۚ وَمَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدِ افْتَرَىٰ إِثْمًا عَظِيمًا
5:72 *"እነሆ በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በእርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፤ መኖሪያውም እሳት ናት"*። ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም። إِنَّهُ مَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدْ حَرَّمَ اللَّهُ عَلَيْهِ الْجَنَّةَ وَمَأْوَاهُ النَّارُ ۖ وَمَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ أَنصَارٍ

አላህ ከሺርክ ይጠብቀን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
"ወሰነ" ለሚለው ቃል የተቀመጠው "ቀደረ" قَدَّرَ ሲሆን በምድር ውስጥ ያለውን መወሰኑን እንጂ መፍጠሩን አያሳም። "ቀደረ" እና "ኸለቀ" በይዘትም ሆነ በአይነት፥ በመንስኤውም ሆነ በውጤት ሁለት የተለያዩ ለየቅል የሆኑ ቃላትና ትርጉም ናቸው። በየትኛው ቀምርና ስሌት ቀምራችሁን አስልታችሁ፥ በየትኛው መስፈትና ሚዛን ለክታችሁና መዝናችሁ ነው "ወሰነ" የሚለውን "ፈጠረ" ብላችሁ 2+4= 6 ብላችሁ ድምር…
ጥያቄ ቁጥር 45
በስህተት ጥያቄው ሳይገባ ተቆርጧል። እዚህ ሙሉውን እዩት፦

ጥያቄ 45
አላህ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረው በስድስት ቀን ወይስ በስምንት ቀን?

በስድስት ቀን፦
57:4 እርሱ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረ፣ ከዚያም በዙፋኑ ላይ የተደላደለ ነው፤

በስምንት ቀን፦
41:9-12 በላቸው፦ እናንተ በዚያ ምድርን በሁለት ቀኖች ውስጥ በፈጠረው አምላክ በእርግጥ ትክዳላችሁን? ለርሱም ባላንጣዎችን ታደርጋላችሁን? ያ ይህንን የሠራው የዓለማት ጌታ ነው። በርሷም ከበላይዋ የረጉ ጋራዎችን አደረገ፤ በርሷም በረከትን አደረገ፤ በውስጧም ምግቦችዋን በአራት ቀናት ውስጥ፣ ለጠያቂዎች ትክክል ሲሆኑ ወሰነ።…..በሁለት ቀኖችም ውስጥ ሰባት ሰማያት አደርጋቸው፤

መልስ
አምላካችን አላህ ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ እንደፈጠረ ይናገራል፦
7፥54 *ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው*፡፡ إِنَّ رَبَّكُمُ اللَّهُ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ فِي سِتَّةِ أَيَّام
50፥38 *ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ በእርግጥ ፈጠርን*፡፡ ድካምም ምንም አልነካንም፡፡ وَلَقَدْ خَلَقْنَا السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ وَمَا مَسَّنَا مِن لُّغُوبٍ

ይህ ጥቅላዊ ገለጻ ሲሆን በተናጥል አስፈላጊ የሆነው አፈጠጠሩ እንዲህ ይገልጻል፦
41፥9 በላቸው «እናንተ በዚያ *"ምድርን በሁለት ቀኖች ውስጥ በፈጠረው አምላክ በእርግጥ ትክዳላችሁን?"* ለእርሱም ባለንጣዎችን ታደርጋላችሁን? ያ ይህንን የሠራው የዓለማት ጌታ ነው፡፡ قُلْ أَئِنَّكُمْ لَتَكْفُرُونَ بِٱلَّذِى خَلَقَ ٱلْأَرْضَ فِى يَوْمَيْنِ وَتَجْعَلُونَ لَهُۥٓ أَندَادًۭا ۚ ذَٰلِكَ رَبُّ ٱلْعَٰلَمِينَ

"ኸለቀ" ማለት "ፈጠረ" ማለት ሲሆን ከመጀመሪያው ቀን እስከ አራተኛው ቀናት ባሉት በአራት ቀናት ውስጥ በምድር ላይ የረጉ ጋራዎችን፣ በውስጧም ምግቦችዋን ለጠያቂዎች ትክክል ሲኾኑ ወሰነ፦
42፥10 በእርሷም ከበላይዋ የረጉ ጋራዎችን አደረገ፡፡ በእርሷም በረከትን አደረገ፡፡ *"በውስጧም ምግቦችዋን በአራት ቀናት ውሰጥ ለጠያቂዎች ትክክል ሲኾኑ ወሰነ"*፡፡ وَجَعَلَ فِيهَا رَوَٰسِىَ مِن فَوْقِهَا وَبَٰرَكَ فِيهَا وَقَدَّرَ فِيهَآ أَقْوَٰتَهَا فِىٓ أَرْبَعَةِ أَيَّامٍۢ سَوَآءًۭ لِّلسَّآئِلِينَ
"ወሰነ" ለሚለው ቃል የተቀመጠው "ቀደረ" قَدَّرَ ሲሆን በምድር ውስጥ ያለውን መወሰኑን እንጂ መፍጠሩን አያሳም። "ቀደረ" እና "ኸለቀ" በይዘትም ሆነ በአይነት፥ በመንስኤውም ሆነ በውጤት ሁለት የተለያዩ ለየቅል የሆኑ ቃላትና ትርጉም ናቸው። በየትኛው ቀምርና ስሌት ቀምራችሁን አስልታችሁ፥ በየትኛው መስፈትና ሚዛን ለክታችሁና መዝናችሁ ነው "ወሰነ" የሚለውን "ፈጠረ" ብላችሁ 2+4= 6 ብላችሁ ድምር ውስጥ የገባችሁት? ዐውዱን ንባቡን"contextual setting" ቀጥለን እንየው፦
42፥11 *"ከዚያም ወደ ሰማይ እርሷ ጭስ ኾና ሳለች አሰበ፡፡ ለእርሷም ለምድርም «ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ» አላቸው፡፡ «ታዛዦች ኾነን መጣን» አሉ*፡፡ ثُمَّ ٱسْتَوَىٰٓ إِلَى ٱلسَّمَآءِ وَهِىَ دُخَانٌۭ فَقَالَ لَهَا وَلِلْأَرْضِ ٱئْتِيَا طَوْعًا أَوْ كَرْهًۭا قَالَتَآ أَتَيْنَا طَآئِعِينَ

“ጭስ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ዱኻን” دُخَانٌۭ ሲሆን “ጋዝ” ማለት ነው፤ ሰማይ በጋዝ ደረጃ እያለች አላህ ለእርሷም ለምድርም «ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ» አላቸው፡፡ እነርሱም፦ «ታዛዦች ኾነን መጣን» አሉ። “ሱመ” ثُمَّ ማለትም ከዚያም” የሚለው አያያዥ መስተጻምር ተርቲብ ነው፤ “ተርቲብ” ترتيب ማለት “ቅድመ-ተከተል” ማለት ነው፤ ይህ ቅድመ-ተከተል በሁለት ይከፈላል፤ አንዱ የጊዜ ቅድመ-ተከተል ሲሆን ሁለተኛው የንግግር ቅድመ-ተከተል ነው። እዚህ አንቀጽ ላይ ግን ዓውዱ የንግግር ቅድመ-ተከተል ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው፤ አላህ ከዚያም ወደ ሰማይ እርሷ ጭስ ኾና ሳለች አሰበ፤ ጭስ የነበረችውን ሰማይ በሁለት ቀኖችም ውስጥ ሰባት ሰማያት አደረጋቸው፦
41፥12 *በሁለት ቀኖችም ውስጥ ሰባት ሰማያት አደረጋቸው*፡፡ فَقَضَىٰهُنَّ سَبْعَ سَمَٰوَاتٍۢ فِى يَوْمَيْنِ
2፥29 እርሱ ያ በምድር ያለውን ሁሉ ለእናንተ የፈጠረ ነው፡፡ *ከዚያም ወደ ሰማይ አሰበ፤ ሰባት ሰማያትም አደረጋቸው*፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ هُوَ ٱلَّذِى خَلَقَ لَكُم مَّا فِى ٱلْأَرْضِ جَمِيعًۭا ثُمَّ ٱسْتَوَىٰٓ إِلَى ٱلسَّمَآءِ فَسَوَّىٰهُنَّ سَبْعَ سَمَٰوَٰتٍۢ ۚ وَهُوَ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمٌۭ

ቁጥር ሲገኝ 2+4+2= 8 ማለት ዝም ብሎ ቀላል አይደለም። ማን መደመር ውስጥ ግባ አለህ? ምድር በሁለት ቀን ውስጥ መፈጠሩን፣ የነበረው ሰማይ ሰባት ሰማያት በሁለት ቀን ውስጥ መደረጋቸው እና በምድር ውስጥ ምግቦችዋን በአራት ቀናት ውሰጥ መወሰኑን ነው የሚናገረው። ሲቀጥል “ፊ” فِي የሚለው መስተዋድድ “ውስጥ” ማለት ሲሆን 1 ቀን በሁለት ውስጥ 2 ቀን በአራት ውስጥ አሉ። ምግቦችዋን በአራት ቀናት ውሰጥ ወሰነ ማለት እና ምግቦችዋን በአራተኛው ቀናት ወሰነ ማለት የተለያየ ትርጉም ይሰጣል። ስለዚህ 2 ቀናት 4 ቀናት ውስጥ ይካተታሉ። እሩቅ ሳንሄድ ምድር በሁለት ቀኖች ውስጥ ቢፈጠርም ምድር በስድስት ቀናት ውስጥ እንደተፈጠረች ይናገራል፦
7፥54 *ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው*፡፡ إِنَّ رَبَّكُمُ اللَّهُ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ فِي سِتَّةِ أَيَّام

ይህ የሚያሳየው 2 ቀናት በስድስት ቀናት ውስጥ መኖራቸውን እንጂ እዚህ ጋር 6 ስለሚል 6+2+4+2=14 ብለን የቂል አስተሳሰብ ማሰብ አለሌነት ነው። እኔ በነካ እጄ በሰማይና ምድር አፈጣጠር ዙሪያ እንዲገባቸው አንድ ጥያቄ ከባይብል ልጠይቃቸው፦ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን የፈጠረው በመጀመሪያ ቀን ወይስ በስድስት ቀን?

A.በመጀመሪያ ቀን፦
ዘፍጥረት 1፥1-5 *"በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።
ዘፍጥረት 2፥4 እግዚአብሔር አምላክ *"ሰማይንና ምድርን ባደረገ ቀን*፥ በተፈጠሩ ጊዜ የሰማይና የምድር ልደት ይህ ነው።

B. በስድስት ቀን፦
ዘጸአት 31፥17 *"እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን በስድስት ቀን ስለ ፈጠረ"*፥
ዘጸአት 20፥11 *እግዚአብሔር በስድስት ቀን ሰማይንና ምድርን፥ ባሕርንም፥ ያለባቸውንም ሁሉ ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን ዐርፎአልና"*።

እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን የፈጠረው በመጀመርያ ቀን ነው ወይስ በስድስት ቀን? በስድስት ቀናት "ውስጥ" ቢል ኖሮ ምናልባት 1 ቁጥር በስድስት "ውስጥ" ስላለች ችግር አይኖረውም ነበር። ይህ ወፍራም የቤት ሥራ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም