ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
"መኪን" مَكِين ማለት ሳይጨምር ሳይቀንስ የሚያስተላልፍ "ባለሟል" ማለት ሲሆን "አሚን" أَمِين ማለት ደግሞ አደራውን የሚወጣ "ታማኝ" ማለት ነው። ጂብሪል በእነዚህ ባሕርያት ከተገለጸ ቁርኣንን ከአላህ ወደ ነቢዩ"ﷺ" በታማኝነት ያስተላለፈ የአላህ መልእክተኛ ነው፥ እርሱ ስለሚያስተላልፍ የእርሱ ቀውል ነው እንጂ የእርሱ ከላም አይደለም።
ነቢያችንም"ﷺ" ከእርሱ ሰምተው ወደ ሰዎች ስለሚያስተላልፉ ቁርኣን የእርሳቸው ቀውል ነው ተብሏል፦
69፥40 *"እርሱ ቁርአን የተከበረ መልክተኛ ቃል ነው"*። إِنَّهُ لَقَوْلُ رَسُولٍ كَرِيمٍ

እዚህ አንቀጽ ላይ "መልእክተኛ" የተባሉት ነቢያችን"ﷺ" ሲሆኑ በቁርኣን ላይ ያላቸው ድርሻ መልእክቱን ማስተላለፍ ብቻ እንጂ በቁርኣኑ ላይ የራሳቸውን ቃል ቢጨምሩ ኖሮ አላህ ባልተሟገተላቸው ነበር፦
69፥44 *"በእኛ ላይም ከፊልን ቃላት ያላልነውን በቀጠፈ ኖሮ*፤ وَلَوْ تَقَوَّلَ عَلَيْنَا بَعْضَ الْأَقَاوِيلِ
69፥45 *በኀይል በያዝነው ነበር*፡፡ لَأَخَذْنَا مِنْهُ بِالْيَمِينِ
69፥46 *ከዚያም ከእርሱ የልቡን ሥር የተንጠለጠለበትን ጅማት በቆረጥን ነበር"*፡፡ ثُمَّ لَقَطَعْنَا مِنْهُ الْوَتِينَ

እዚሁ ዐውድ ላይ "የመልእክተኛ ቃል ነው" ብሎ ግን ያ ቃል በማስተላለፍ ደረጃ መሆኑን እንጂ ከራስ አላህ ያላለውን መናገር እንዳልሆነ ለማሳየት፦ "በእኛ ላይም ከፊልን ቃላት ያላልነውን በቀጠፈ ኖሮ በኀይል በያዝነው ነበር ፡፡ከዚያም ከእርሱ የልቡን ሥር የተንጠለጠለበትን ጅማት በቆረጥን ነበር" በማለት ሳይጨምሩ ሳይቀንሱ እንዳስተላለፉ ይናገራል፦
5:67 *"አንተ መልክተኛ ሆይ! ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደውን አድርስ፤ ባታደርግ መልክቱን አላደረስክም"*። يَا أَيُّهَا الرَّسُولُ بَلِّغْ مَا أُنزِلَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ ۖ وَإِن لَّمْ تَفْعَلْ فَمَا بَلَّغْتَ رِسَالَتَهُ ۚ

መልእክቱ ከጌታ አላህ ወደ እርሳቸው የተወረደው ቁርኣን ከሆነ ቁርኣን የአላህ ንግግር ብቻ ነው። "መልክተኛ ሆይ" የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት። ጂብሪል ሆነ ነቢያችን"ﷺ" መልእክተኛ ከተባሉ ቁርኣን በእነርሱ የእነርሱ ተላላፊ ቃል እንጂ የእነርሱ ንግግር አይደለም። እነርሱ ቃል አቀባይና አፈ-ቀላጤ ናቸው።
ለምሳሌ ገብርኤል ተልኮ የተናገረው የምስራች የአምላክ ንግግር ሆኖ ሳለ ነገር ግን ያንን የምስራች ወደ ራሱ በማስጠጋት “ቃሌ” ማለቱ አስተላላፊነትን እንጂ አመንጪነትን አያሳይም ከተባለ ከላይ ያለውንም ሙግት በዚህ ቀመርና ስሌት መረዳት ይቻላል፦
ሉቃስ 1፥19-20 መልአኩም መልሶ፦ እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፥ *እንድናገርህም ይህችንም የምሥራች እንድሰብክልህ ተልኬ ነበር*፤ እነሆም፥ በጊዜው የሚፈጸመውን *ቃሌን* ስላላመንህ፥ ይህ ነገር እስከሚሆን ቀን ድረስ ዲዳ ትሆናለህ መናገርም አትችልም፡ አለው።

ሌላው “ቶራህ” תּוֹרָה ማለት “ሕግ” ማለት ነው፤ ይህ ሕግ ምንጩ ፈጣሪ ነው፤ የፈጣሪ ሕግ ነው፦
ዘጸአት 16፥4 እግዚአብሔርም ሙሴን፦ *”በሕጌ”* ይሄዱ ወይም አይሄዱ እንደሆነ እኔ እንድፈትናቸው፥ እነሆ ከሰማይ እንጀራን አዘንብላችኋለሁ፤

ነገር ግን ይህ የአምላክ ሕግ የሙሴ ሕግ ተብሏል፦
ሚልክያስ 4፥4 ለእስራኤል ሁሉ *”ሥርዓትንና ፍርድን አድርጌ በኮሬብ ያዘዝሁትን የባሪያዬን “የሙሴን ሕግ” አስቡ”*።

ፈጣሪ በሙሴ በኩል ለእስራኤል ሁሉ ያዘዘው ሥርዓትንና ፍርድን ወደ ሙሴ በማስጠጋት የሙሴን ሕግ ስላለው እውን ቃሉ የሙሴ ነው ማለት ነውን? አይ ቃል አቀባይና አፈ-ቀላጤ ስለሆነ የሙሴ ሕግ ተባለ ከሆነ መልሱ እንግዲውስ ከላይ ያለውን የነብያችንን"ﷺ" እና የጂብሪልን አስተላላፊነት በዚህ ሒሳብና ስሌት ተረዱት።

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር አርባ ሦስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 43
ያለ ወሲባዊ ግንኙነት ልጅ መውለድ ይቻላል ወይስ አይቻልም?

ይቻላል፡- 
19፡19-21 “እኔ ንጹሕን ልጅ ለአንቺ ልሰጥሽ፣ የጌታሽ መልክተኛ ነኝ አላት። (በጋብቻ) ሰዉ ያልነካኝ ኾኜ፣ አመንዝራም ሳልኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል! አለች። አላት (ነገሩ) እንደዚህሽ ነው ፤ ጌታሽ ፦ እርሱ በእኔ ላይ ገር ነው።”

አይቻልም፡- 6:101 “እርሱ ሰማያትንና ምድርን ያለ ብጤ ፈጣሪ ነው። ለእርሱ ሚስት የሌለችው ሲኾንእንዴት ለእርሱ ልጅ ይኖረዋል? ነገርንም ሁሉ ፈጠረ፡፡ እርሱም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡”

መልስ
የምናመልከው አምላክ በፈጣሪነቱ ፍጡርነት የሌለበት ነው። በእርሱ ባህርይ ውስጥ ማስሆን እንጂ መሆን የሚባል ባህርይ የለውም። ይህንን እሳቤ ለመረዳት ስለ ተቅዲድ እሳቤ እስቲ እንይ፦ 
“ተቅዲር” تَقْدِير ማለት “ሁሉን ቻይነት” ማለት ነው፤ “አል-ቀዲር”  القَدِير ማለት “ሁሉን ቻይ” “ከሃሊ ኩሉ” ማለት ሲሆን ከአላህ ስሞች ውስጥ አንዱ ነው፤ “ቀዲር” قَدِير የሚለው ቃል “ቀደረ” قَدَرَ ማለትም “ቻለ” ወይም “ወሰነ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “ቃዲር” قَادِر ማለትም “ኃያል” ማለትም ነው፤ “ቀደር” قَدَر ማለት “ችሎታ” ማለት ሲሆን “ቀድር” قَدْر ደግሞ “ውሳኔ” ማለት ነው፤ ይህ የአላህ ባህርይ ነው፤ አላህ “ሁሉን ቻይ” ነው ማለት “ሁሉንም ነገር ማድረግ ይችላል” ማለት ነው፦
24፥45 *አላህ የሚሻውን ሁሉ ይፈጥራል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና*፡፡ يَخْلُقُ اللَّهُ مَا يَشَاءُ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

አላህ ቻይነቱ በነገር ሁሉ ነው፤ የሚሻውን ሁሉ ይፈጥራል፤ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና፤ መፍጠር የፈጣሪ ባህርይ ሲሆን መፈጠር የፍጡር ባህርይ ነው፤ “ነገር ሁሉ” በሚለው ዓረፍተ-ነገር ውስጥ “ነገር” የሚለው ቃል ፍጥረትን እንጂ ፈጣሪን አያካትትም ምክንያቱም ነገር ፍጡር ነው፤ የተፈጠረ ነገር እራሱን አይፈጥርም፤ “ሸይዕ” شَىْء ማለት “ነገር’thing” ማለት ሲሆን አምላካችን አላህ ደግሞ የሁሉ ነገር ፈጣሪ ነው፦
39፥62 *አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው*፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው፡፡ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ

ሁሉንም ነገር ሁሉ ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው፡- «ኹን ነው» ወዲያውም ይኾናል፦
2፥117 ሰማያትንና ምድርን ያለብጤ ፈጣሪ ነው፤ *ነገርንም ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው፡- «ኹን ነው» ወዲያውም ይኾናል*፡፡ بَدِيعُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ وَإِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ
16፥40 *ለማንኛውም ነገር መኾኑን በሻነው ጊዜ ቃላችን ለእርሱ «ኹን» ማለት ብቻ ነው፤ ወዲውም ይኾናል*፡፡ إِنَّمَا قَوْلُنَا لِشَيْءٍ إِذَا أَرَدْنَاهُ أَن نَّقُولَ لَهُ كُن فَيَكُونُ
መርየም፦ “ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል” ስትል መለኮታዊ መልስ፦ “አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፤ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል” የሚል መልስ ነው፦
3፥47 ፡-ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል አለች፡፡ ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ አንዳችን በሻ ጊዜ ለርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል አላት፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

መርየም ልጅ የሚኖራት አላህ ኹን በሚለው ንግግሩ ነው። እርሷ ፍጡር ናት፥ በእርሷ ተፈጥሮ ውስጥ መከፋፈልና መዋለድ አለ። ነገር ግን አላህ አስገኝ ስለሆነ እና በእርሱ ባሕርይ መከፋፈልና መዋለድ የለውም፥ ፈጣሪ ጾታ የለውምና። አላህ የሚጋራው ባልደረባ ስለሌለው ልጅም አይኖረውም፤ ምክንያቱም ልጅ የአባት ምትክ፣ ተጋሪ፣ ሞክሼ ስለሚሆን ነው፦
6፥101 እርሱ ሰማያትንና ምድርን ያለ ብጤ ፈጣሪ ነው፡፡ *ለእርሱ ሚስት የሌለችው ሲኾን እንዴት ለእርሱ ልጅ ይኖረዋል? ነገርንም ሁሉ ፈጠረ*፡፡ እርሱም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ بَدِيعُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ أَنَّىٰ يَكُونُ لَهُ وَلَدٌ وَلَمْ تَكُن لَّهُ صَاحِبَةٌ ۖ وَخَلَقَ كُلَّ شَيْءٍ ۖ وَهُوَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

“የኩኑ” يَكُونُ ማለት “ይኖረዋል” ማለት ሲሆን ባሕርይን ያሳያል፤ አላህ ነገርንም ሁሉ ፈጠረ፤ ልጅ የሚመጣው በሴት ነው። ያለ ሴት እንዴት ልጅ ይኖራል? የሚለው የሥነ-አመክንዮ ጥያቄ ነው። ይህ ባሕርይ ታሳቢ ያደረገ እንጂ ችሎታን ታሳቢ ያደረገ አይደለም። እንዴት ይችላል? ተብሎ አልተጠየቀም። ሲቀጥል ከመነሻው “ሚስት” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሷሒበት” صَٰحِبَة ሲሆን “ባልደረባ” ማለት ነው፤ “አስሐብ” أَصْحَٰب ወይም “ሷሒብ صَاحِب ደግሞ “ባልደረባ” “አጋር” “ሞክሼ” “ባለንጀራ” ከሆነ ፈጣሪ ከመነሻው “ባልደረባ” “ተጋሪ” “አጋር” “ሞክሼ” “ባለንጀራ” የለውም፦
6፥163 *ለእርሱ ተጋሪ የለውም፡፡ በዚህም በማጥራት ታዘዝኩ*፡፡ እኔም የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ» በል፡፡ لَا شَرِيكَ لَهُ ۖ وَبِذَٰلِكَ أُمِرْتُ وَأَنَا أَوَّلُ الْمُسْلِمِينَ

በባይብል አብርሃምንና ሳራን፣ ዘካሪያስንና ኤልሳቤጥን በስተ-እርጅናቸው ልጅ ለመስጠት የሚሳነው ምንም ነገር እንደሌለ ሁሉ ኢየሱስን ያለ አባት ለማስገኘት የሚሳነው ነገር የለም፦
ዘፍጥረት 18፥14 በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው *ነገር* አለን?
ሉቃስ 1፥37 ለእግዚአብሔር የሚሳነው *ነገር* የለምና።

“ነገር” በሚለው ውስጥ ኢየሱስም እንደሚካተት አንባቢ ልብ ይለዋል፤ ፈጣሪ ነገር ለማስገኘት የሚያቅተው ነገር የለም፤ ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው፦
ኤርምያስ 32፥27 እነሆ፥ እኔ የሥጋ ሁሉ አምላክ ያህዌህ ነኝ፤ በውኑ እኔን የሚያቅተኝ *ነገር* አለን?
መክብብ 3፥11 *ነገርን ሁሉ* በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው፤

“ኤልሻዳይ” אֵל שַׁדַּי ማለት ደግሞ “ሁሉን ቻይ አምላክ” ማለት ነው፤ ፈጣሪ ሁሉን ቻይ ያሰኘው ሁሉን ነገር በማድረግ፣ ልጅ በመስጠት እና ዘር በማብዛት እንጂ ነገር በመሆን ወይም እራሱን በመፍጠሩ አሊያም ሁሉን ነገር በመደረግ አይደለም፦
ኢዮብ 42፥2 *ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ እንደ ሆንህ*፥ አሳብህም ይከለከል ዘንድ ከቶ እንደማይቻል አወቅሁ።
ዘፍጥረት 17፥1 አብራምም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለትና፦ *እኔ ኤልሻዳይ ነኝ* በፊቴ ተመላለስ፥ ፍጹምም ሁን፤
ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል *አደርጋለሁ፥ እጅግም አበዛሃለሁ* አለው።
ዘፍጥረት 28፥3 *ሁሉን የሚችል አምላክም ለብዙ ሕዝብ ጉባኤ እንድትሆን ይባርክህ፥ ያፍራህ፥ ያብዛህ*፤ 

ፈጣሪ “ነው” እንጂ “ሆነ” አይባልም፤ ከሆነ ማን አደረገው? እራሱን እራሱ አስገኘ? ፈጣሪ ሁሉን ቻይነቱ በማስሆን እንጂ በመሆን አይደለም፤ በማድረግ እንጂ በመደረግ አይደለም፤ “ሆነ” ከተባለ የሚያስሆን አለ፤ “ተደረገ” ከተባለ አድራጊ አለ፤ የሚያስሆንና የሚያደርግ አድራጊ ፈጣሪ ነው፤ የሚሆንና የሚደረግ ተደራጊ ደግሞ ፍጡር ነው፤ “ሆነ” “ተደረገ” ማለት መለወጥና መለዋወጥን ያሳያል፤ ፈጣሪ አይለወልጥም አይለዋወጥም፦
ሚልክያስ 3፥6 *እኔ ያህዌህ አልለወጥም*፤

በተረፈ ፈጣሪ ነገር መሆን ይችላል ወይም አይችልም ተብሎ በባይብል ላይ ሆነ በቁርኣን ላይ ስላልተቀመጠ ይህ ጥያቄ በራሱ አውራ የሆነ ፍልስፍናዊ ተፋልሶ”philosophical fallacy” ነው።  ለምሳሌ ፈጣሪ ሊሸከመው የማይችለውን ድንጋይ መፍጠር ይችላል ወይስ አይችልም? ብዬ ብጠይቅ፤ ሊሸከመው የማይችለውን ድንጋይ መፍጠር ይችላል ቢባል ሁሉን ቻይ አይደለም፤ ምክንያቱም ሊሸከመው የማይችል ድንጋይ ስላለ። ሊሸከመው የማይችለውን ድንጋይ መፍጠር አይችልም ቢባል ሁሉን ቻይ አይደለም፤ ምክንያቱም ሊሸከመው የማይችል ድንጋይ መፍጠር ስላልቻለ። በሁለቱም መልስ ሁሉን ቻይነትነቱን ያበላሸዋል፤ ይህ ጥያቄ ፋላስይ ነው፤ ፈጣሪ ሁሉን ቻይ አለመሆን ይችላል ወይስ አይችልም? ሁሉን ቻይ አለመሆን ካልቻለ ሁሉን ቻይ አይደለም። ሁሉን ቻይ አለመሆን ከቻለ ሁሉን ቻይ አይሆንም። ፈጣሪ መከራን ማስወገድ አይችልም ወይስ መከራን ማስወገድ አይፈልግም? ፈጣሪ መከራን ማስወገድ ካልቻለ ፈጣሪ ደካማ ነው፤ ወይም ፈጣሪ መከራን ማስወገድ ካልፈለገ ፈጣሪ መልካም አይደለም።
ስለዚህ ፈጣሪ ደካማ ነው ወይም መልካም አይደለም፡፡ ይህ አለሌ ጥያቄ መጽሐፍትን ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ስላልሆነ ስሁት ሙግት ነው። ፍልስፍና የተቆላ ገብስ ነው፤ ሲበሉት ይጣፍጣል፤ ግን ሲዘሩት አይበቅልም። 

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር አርባ አራት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 44
የመጀመሪያ ሙስሊም ማን ነው?

A. ኢብራሒም
3:67 ኢብራሒም ይሁዳዊም ክርስቲያንም አልነበረም ግን ወደ ቀጥተኛዉ ሃይማኖት የተዘነበለ ሙስሊም ነበረ፤ ከአጋሪዋችም አልነበረም።

B. ነቢያችን
6:163 «ለእርሱ ተጋሪ የለውም፡፡ በዚህም በማጥራት ታዘዝኩ፡፡ እኔም የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ» በል፡፡

መልስ
“ሙሥሊም” مُسْلِم የሚለው ቃል “አሥለመ” أَسْلَمَ “ታዘዘ”፣ “ተገዛ”፣ ” አመለከ” “ሁሉ ነገሩን ሰጠ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን ትርጉሙ “አቢድ” عَابِدُ ማለትም “አምላኪ” አሊያም “ቃኒት” قَانِتِ ማለትም “ታዛዥ” ማለት ነው፥ የኢብራሂምን ሃይማኖት ኢስላም ነው፤ አላህ ከነብያችን”ﷺ” በፊት “ታዛዦች” ብሎ ሰይሟቸዋል፦
22:78 በአላህም ሃይማኖት ተገቢውን ትግል ታገሉ፤ እርሱ መርጧችኃል፤ በእናንተም ላይ በሃይማኖቱ ውስጥ ምንም ችግር አላደረገባችሁም፤ የአባታችሁን የኢብራሂምን ሃይማኖት ተከተሉ፤ እርሱ *”ከዚህ በፊት ሙስሊሞች”* ብሎ ሰይሟችኋል፤ وَجَٰهِدُوا۟ فِى ٱللَّهِ حَقَّ جِهَادِهِۦ ۚ هُوَ ٱجْتَبَىٰكُمْ وَمَا جَعَلَ عَلَيْكُمْ فِى ٱلدِّينِ مِنْ حَرَجٍۢ ۚ مِّلَّةَ أَبِيكُمْ إِبْرَٰهِيمَ ۚ هُوَ سَمَّىٰكُمُ ٱلْمُسْلِمِينَ مِن قَبْلُ

“ከዚህ በፊት” የሚለው አገናዛቢ መስተዋድድ “ሚን ቀብሉ” مِنْ قَبْلُ ሲሆን የአደም ጊዜ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፤ አላህ ወደ አደም ወሕይ ሲያወርድ “ሙስሊም” ብሎ ተጣራ፦
20፥115 ወደ አደምም *”ከዚህ በፊት”* ኪዳንን በእርግጥ አወረድን፡፡ وَلَقَدْ عَهِدْنَآ إِلَىٰٓ ءَادَمَ مِن قَبْلُ

አላህ ለኢብራሂም “አሥሊም” أَسْلِمْ ማለትም “ታዘዝ” ብሎ ሲለው እርሱም ለዓለማት ጌታ “አስሥለምቱ” أَسْلَمْتُ ማለትም “ታዘዝኩ” አለ፦
2፥131 ጌታው ለእርሱ *”ታዘዝ”* ባለው ጊዜ መረጠው፡፡ ለዓለማት ጌታ *”ታዘዝኩ”* አለ፡፡ إِذْ قَالَ لَهُۥ رَبُّهُۥٓ أَسْلِمْ ۖ قَالَ أَسْلَمْتُ لِرَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ

ስለዚህ ኢብራሒም ይሁዳዊም ክርስቲያንም አልነበረም ግን ወደ ቀጥተኛዉ ሃይማኖት የተዘነበለ ሙስሊም ነበረ፤ ይሁዲነት ከተውራት መውረድ በኃላ እንዲሁ ክርስትና ከኢንጅል መውረድ በኃላ የመጡ ስያሜዎች ናቸው፤ ተውራትና ኢንጂልም ደግሞ ከእርሱ በኋላ እንጅ በፊት አልተወረዱም፦
3:67 ኢብራሒም ይሁዳዊም ክርስቲያንም አልነበረም ግን ወደ ቀጥተኛዉ ሃይማኖት የተዘነበለ *”ሙስሊም ነበረ”*፤ ከአጋሪዋችም አልነበረም። مَا كَانَ إِبْرَٰهِيمُ يَهُودِيًّۭا وَلَا نَصْرَانِيًّۭا وَلَٰكِن كَانَ حَنِيفًۭا مُّسْلِمًۭا وَمَا كَانَ مِنَ ٱلْمُشْرِكِينَ

ታዲያ ነብያት አስተምህሮቻቸው ኢስላም እነርሱ ሙስሊም ከተባሉ ለምንድን ነው አላህ ነቢያችንን”ﷺ” “እኔም የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ በል” ያላቸው? ይህንን ጥልልና ጥንፍፍ ባለ መልኩ እስቲ እንየው፦
6፥163 «ለእርሱ ተጋሪ የለውም፡፡ በዚህም በማጥራት ታዘዝኩ፡፡ እኔም *የሙስሊሞች መጀመሪያ* ነኝ» በል፡፡ لَا شَرِيكَ لَهُۥ ۖ وَبِذَٰلِكَ أُمِرْتُ وَأَنَا۠ أَوَّلُ ٱلْمُسْلِمِينَ
39፥11-12 በል «እኔ አላህን ሃይማኖትን ለርሱ ያጠራሁ ኾኜ እንድግገዛው ታዘዝኩ፡፡ *የሙስሊሞችም መጀመሪያ* እንድኾን ታዘዝኩ፡፡» وَأُمِرْتُ لِأَنْ أَكُونَ أَوَّلَ ٱلْمُسْلِمِينَ

“መጀመሪያ” የሚለው የዐረቢኛ ቃል “አወል” أَوَّل ሲሆን በሁለት ይከፈላል፦ አንደኛው “አወሉል ሙብተዳ” ሲሆን አወሉል ሙብተዳ ማለት መጀመሪያነት “መርፉዕ” مرفوع ማለትም “ባለቤት ሙያ”nominative case” ሆኖ ሲመጣ “ሙጥለቅ” مطلق ማለትም “ፍጹማዊ መጀመሪያ”Absolute first” ይባላል። ሁለተኛው “አወሉል ዘርፉል ዘመን” ሲሆን መጀመሪያነት “መንሱብ” منصوب ማለትም “ተሳቢ ሙያ”accusative case” ሆኖ ሲመጣ “ቀሪብ” قريب ማለትም “አንጻራዊ መጀመሪያ”Relative first” ይባላል። ይህ የሥነ-ሰዋስውና የቋንቋ ሙግት ታሳቢና ዋቢ አድርገን የነቢያችን”ﷺ” የሙስሊሞች መጀመሪያ መሆን በአንጻራዊ መጀመሪያ ደረጃ የተቀመጠ እንጂ በፍጹማዊ መጀመሪያ ደረጃ የተቀመጠ አይደለም። ይህን ሙግት ከተረዳን ነብያችን”ﷺ” የመጀመሪያው ሙስሊም ሳይሆኑ የሙስሊሞች መጀመሪያ ናቸው፣ አላህ በሁለተኛ መደብ “እናንተ” ሙስሊሞች እያለ የሚያነጋግረው የነቢያችንን”ﷺ” ኡማ ነው፦
3:102 እላንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገቢዉን መጠንቀቅ ተጠንቀቁት፤ *እናንተም ሙስሊሞች* ሆናችሁ እንጅ አትሙቱ። يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ حَقَّ تُقَاتِهِۦ وَلَا تَمُوتُنَّ إِلَّا وَأَنتُم مُّسْلِمُونَ
ታዲያ አንጻራዊነት ከምን አኳያ? ካልን የቁርአን ትእዛዝ ተቀብሎ የታዘዘ ከኡማው መጀመሪያው እሳቸው ናቸው፦
6:14 «እኔ *መጀመሪያ ትእዛዝን* ከተቀበለ ሰው ልኾን *ታዘዝኩ*፡፡ ከአጋሪዎችም ፈጽሞ አትኹን ተብያለሁ» በላቸው፡፡ قُلْ إِنِّىٓ أُمِرْتُ أَنْ أَكُونَ أَوَّلَ مَنْ أَسْلَمَ ۖ وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ ٱلْمُشْرِكِينَ

“ትእዛዝን ከተቀበለ” የሚለው ይሰመርበት፣ ይህም ትእዛዝ በእሳቸው ላይ የተወረደው ቁርአን ነው፦
65:5 ይህ *”የአላህ ትእዛዝ ነው”*። ወደ *እናንተም* አወረደው፤ ذَٰلِكَ أَمْرُ ٱللَّهِ أَنزَلَهُۥٓ إِلَيْكُمْ
42:15 በላቸውም፦ ከመጽሐፍ አላህ ባወረደው ሁሉ አመንኩ፤ በመካከላችሁም ላስተካክል *”ታዘዝኩ”*፤ وَقُلْ ءَامَنتُ بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ مِن كِتَٰبٍۢ ۖ وَأُمِرْتُ لِأَعْدِلَ بَيْنَكُمُ

ከሐዲ የሙስሊም ተቃራኒ ሆኖ አገልግሏል፣ የሙስሊም መጀመሪያ በኣንጻራዊነት ደረጃ እንደተጠቀመ ሁሉ የከሐዲ መጀመሪያ በኣንጻራዊነት ደረጃ ተቀምጧል፦
68:35 *ሙስሊሞቹን እንደ ከሐዲዎች* እናደርጋለን?
2:41 ከእናንተ ጋር ያለውን መጽሐፍ የሚያረጋግጥ ሆኖ ባወረድኩትም ቁርኣን እመኑ፡፡ በእርሱም *”የመጀመሪያ ከሓዲ”* አትሁኑ፡፡ وَءَامِنُوا۟ بِمَآ أَنزَلْتُ مُصَدِّقًۭا لِّمَا مَعَكُمْ وَلَا تَكُونُوٓا۟ أَوَّلَ كَافِرٍۭ بِهِۦ

በእርሱ የመጀመሪያ ከሓዲ አትሁኑ የሚለው ይሰመርበት፣ በቁርአን ማመን የመጀመሪያው ታዛዥ ነቢያችን”ﷺ” እንደሆኑ ሁሉ በቁርአን የመጀመሪያው ከሓዲ እነርሱ ናቸው፤ እኔ የሞባይል የመጀመሪያው ተጠቃሚ ነኝ ብል፤ መጀመሪያነት ከምን አንጻር? ከቤተሰብ? ከከተማ? ከአገር ወይስ ከዓለም? ይህ ቅድሚያ መጠየቅ አለበት፤ ስለ መጀመሪያነት ብዙ ናሙናዎችን መጥቀስ ይቻላል፤ ሙሳ፦ የምእምናን መጀመሪያ ነኝ ብሏል፤ ያ ማለት የሙሳ መጀመሪያነት በአንጻራዊነት ደረጃ እንጂ ከእርሱ በፊት አማኝ አልነበረም ማለት አይደለም፤ የፈርኦን ደጋሚዎች፦ የምእምናን መጀመሪያ ነን ብለዋል፤ ያ ማለት የፈርኦን ደጋሚዎች መጀመሪያነት በአንጻራዊነት ደረጃ እንጂ ከእነርሱ በፊት አማኝ አልነበረም ማለት አይደለም፦
7፥143 «ጥራት ይገባህ፡፡ ወዳንተ ተመለስኩ፡፡ እኔም *የምእምናን መጀመሪያ* ነኝ» አለ፡፡ قَالَ سُبْحَٰنَكَ تُبْتُ إِلَيْكَ وَأَنَا۠ أَوَّلُ ٱلْمُؤْمِنِينَ
26፥51 «እኛ *የምእምናን መጀመሪያ* በመኾናችን ጌታችን ኀጢአቶቻችንን ለእኛ ሊምር እንከጅላለን፡፡» إِنَّا نَطْمَعُ أَن يَغْفِرَ لَنَا رَبُّنَا خَطَٰيَٰنَآ أَن كُنَّآ أَوَّلَ ٱلْمُؤْمِنِينَ

ይህንን በቀላሉ ለመረዳት ከባይብል አንድ ናሙና ላቅርብላችሁ። መላእክእት፣ አዳም እና እስራኤል የእግዚአብሔር ልጆች ተብለዋል፦
ኢዮብ 38፥7 አጥቢያ ኮከቦች በአንድነት ሲዘምሩ፥ *የእግዚአብሔርም ልጆች* ሁሉ እልል ሲሉ፥
ሉቃስ 3፥38 የሴት ልጅ፥ የአዳም ልጅ፥ *የእግዚአብሔር ልጅ*።
ዘጸአት 4፥22 ፈርዖንንም፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ *”እስራኤል የበኵር ልጄ ነው”*፤

እስራኤል የመጀመሪያ ልጄ ከሆነ ከእስኤል በፊት አዳም እና መላእክት እንዴት ልጆች ተባሉ? “በኵር” ተብሎ የተቀመጠው የግሪኩ ቃል “ፕሮቶ-ቶኮስ” πρωτότοκος ሲሆን ከላይ ለእስራኤል ከዚያ ለኤፍሬም፣ ቀጥሎ ለዳዊት፣ ለጥቆ ለኢየሱስ አገልግሎት ላይ ውሏል፦
ኤርምያስ 31፥9 እኔ ለእስራኤል አባት ነኝና፥ *”ኤፍሬምም በኵሬ ነውና”*።
መዝሙር 89፥27 *እኔም ደግሞ በኵሬ አደርሀዋለው* ከምድር ነገሥታትም ከፍ ይላል።
ዕብራውያን 1፥6 *”እግዚአብሔር የበኵር ልጁን ልኮ ወደ ዓለም”* ሲያገባ፦ የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉ ይስገዱለት፥ ይላል። (1980 አዲስ ትርጉም)

የበኵር ማለትም የመጀመሪያ ልጅ ማን ነው? እስራኤል ወይስ ኤፍሬም ወይስ ዳዊት ወይስ ኢየሱስ? መልሱ "በኵር" የሚለው ቃል አንጻራዊ ነው ከተባለ እንግዲያውስ "አወል" የሚለየውም ቃል አንጻራዊ እንጂ ፍጹማዊ አይደለም።

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
"ወሰነ" ለሚለው ቃል የተቀመጠው "ቀደረ" قَدَّرَ ሲሆን በምድር ውስጥ ያለውን መወሰኑን እንጂ መፍጠሩን አያሳም። "ቀደረ" እና "ኸለቀ" በይዘትም ሆነ በአይነት፥ በመንስኤውም ሆነ በውጤት ሁለት የተለያዩ ለየቅል የሆኑ ቃላትና ትርጉም ናቸው። በየትኛው ቀምርና ስሌት ቀምራችሁን አስልታችሁ፥ በየትኛው መስፈትና ሚዛን ለክታችሁና መዝናችሁ ነው "ወሰነ" የሚለውን "ፈጠረ" ብላችሁ 2+4= 6 ብላችሁ ድምር ውስጥ የገባችሁት? ዐውዱን ንባቡን"contextual setting" ቀጥለን እንየው፦
42፥11 *"ከዚያም ወደ ሰማይ እርሷ ጭስ ኾና ሳለች አሰበ፡፡ ለእርሷም ለምድርም «ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ» አላቸው፡፡ «ታዛዦች ኾነን መጣን» አሉ*፡፡ ثُمَّ ٱسْتَوَىٰٓ إِلَى ٱلسَّمَآءِ وَهِىَ دُخَانٌۭ فَقَالَ لَهَا وَلِلْأَرْضِ ٱئْتِيَا طَوْعًا أَوْ كَرْهًۭا قَالَتَآ أَتَيْنَا طَآئِعِينَ

“ጭስ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ዱኻን” دُخَانٌۭ ሲሆን “ጋዝ” ማለት ነው፤ ሰማይ በጋዝ ደረጃ እያለች አላህ ለእርሷም ለምድርም «ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ» አላቸው፡፡ እነርሱም፦ «ታዛዦች ኾነን መጣን» አሉ። “ሱመ” ثُمَّ ማለትም ከዚያም” የሚለው አያያዥ መስተጻምር ተርቲብ ነው፤ “ተርቲብ” ترتيب ማለት “ቅድመ-ተከተል” ማለት ነው፤ ይህ ቅድመ-ተከተል በሁለት ይከፈላል፤ አንዱ የጊዜ ቅድመ-ተከተል ሲሆን ሁለተኛው የንግግር ቅድመ-ተከተል ነው። እዚህ አንቀጽ ላይ ግን ዓውዱ የንግግር ቅድመ-ተከተል ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው፤ አላህ ከዚያም ወደ ሰማይ እርሷ ጭስ ኾና ሳለች አሰበ፤ ጭስ የነበረችውን ሰማይ በሁለት ቀኖችም ውስጥ ሰባት ሰማያት አደረጋቸው፦
41፥12 *በሁለት ቀኖችም ውስጥ ሰባት ሰማያት አደረጋቸው*፡፡ فَقَضَىٰهُنَّ سَبْعَ سَمَٰوَاتٍۢ فِى يَوْمَيْنِ
2፥29 እርሱ ያ በምድር ያለውን ሁሉ ለእናንተ የፈጠረ ነው፡፡ *ከዚያም ወደ ሰማይ አሰበ፤ ሰባት ሰማያትም አደረጋቸው*፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ هُوَ ٱلَّذِى خَلَقَ لَكُم مَّا فِى ٱلْأَرْضِ جَمِيعًۭا ثُمَّ ٱسْتَوَىٰٓ إِلَى ٱلسَّمَآءِ فَسَوَّىٰهُنَّ سَبْعَ سَمَٰوَٰتٍۢ ۚ وَهُوَ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمٌۭ

ቁጥር ሲገኝ 2+4+2= 8 ማለት ዝም ብሎ ቀላል አይደለም። ማን መደመር ውስጥ ግባ አለህ? ምድር በሁለት ቀን ውስጥ መፈጠሩን፣ የነበረው ሰማይ ሰባት ሰማያት በሁለት ቀን ውስጥ መደረጋቸው እና በምድር ውስጥ ምግቦችዋን በአራት ቀናት ውሰጥ መወሰኑን ነው የሚናገረው። ሲቀጥል “ፊ” فِي የሚለው መስተዋድድ “ውስጥ” ማለት ሲሆን 1 ቀን በሁለት ውስጥ 2 ቀን በአራት ውስጥ አሉ። ምግቦችዋን በአራት ቀናት ውሰጥ ወሰነ ማለት እና ምግቦችዋን በአራተኛው ቀናት ወሰነ ማለት የተለያየ ትርጉም ይሰጣል። ስለዚህ 2 ቀናት 4 ቀናት ውስጥ ይካተታሉ። እሩቅ ሳንሄድ ምድር በሁለት ቀኖች ውስጥ ቢፈጠርም ምድር በስድስት ቀናት ውስጥ እንደተፈጠረች ይናገራል፦
7፥54 *ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው*፡፡ إِنَّ رَبَّكُمُ اللَّهُ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ فِي سِتَّةِ أَيَّام

ይህ የሚያሳየው 2 ቀናት በስድስት ቀናት ውስጥ መኖራቸውን እንጂ እዚህ ጋር 6 ስለሚል 6+2+4+2=14 ብለን የቂል አስተሳሰብ ማሰብ አለሌነት ነው። እኔ በነካ እጄ በሰማይና ምድር አፈጣጠር ዙሪያ እንዲገባቸው አንድ ጥያቄ ከባይብል ልጠይቃቸው፦ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን የፈጠረው በመጀመሪያ ቀን ወይስ በስድስት ቀን?

A.በመጀመሪያ ቀን፦
ዘፍጥረት 1፥1-5 *"በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።
ዘፍጥረት 2፥4 እግዚአብሔር አምላክ *"ሰማይንና ምድርን ባደረገ ቀን*፥ በተፈጠሩ ጊዜ የሰማይና የምድር ልደት ይህ ነው።

B. በስድስት ቀን፦
ዘጸአት 31፥17 *"እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን በስድስት ቀን ስለ ፈጠረ"*፥
ዘጸአት 20፥11 *እግዚአብሔር በስድስት ቀን ሰማይንና ምድርን፥ ባሕርንም፥ ያለባቸውንም ሁሉ ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን ዐርፎአልና"*።

እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን የፈጠረው በመጀመርያ ቀን ነው ወይስ በስድስት ቀን? በስድስት ቀናት "ውስጥ" ቢል ኖሮ ምናልባት 1 ቁጥር በስድስት "ውስጥ" ስላለች ችግር አይኖረውም ነበር። ይህ ወፍራም የቤት ሥራ ነው።

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር አርባ ስድስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 46
ፈጣን ወይንስ ዘገምተኛ የመፍጠር ሒደት?

ዘገምተኛ፡- 
7፡54 “ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው፤

ፈጣን፡- 
2፡117 “ሰማያትንና ምድርን ያለብጤ ፈጣሪ ነው፤ ነገርንም (ማስገኘት) በሻ ጊዜ ለርሱ የሚለው፡- «ኹን ነው፤» ወዲያውም ይኾናል፡፡”

መልስ
አምላካችን አላህ ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ እንደፈጠረ ይናገራል፦
7፥54 *ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው*፡፡ إِنَّ رَبَّكُمُ اللَّهُ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ فِي سِتَّةِ أَيَّام
50፥38 *ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ በእርግጥ ፈጠርን*፡፡ ድካምም ምንም አልነካንም፡፡ وَلَقَدْ خَلَقْنَا السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ وَمَا مَسَّنَا مِن لُّغُوبٍ

አምላካችን አላህ ደግሞ የሁሉ ነገር ፈጣሪ ነው፤ ነገር ማስገኘት በሻ ጊዜ “ኹን” ይለዋል፤ ወዲያው ይኾናልም፦
36፥82 *ነገሩም አንዳችን በሻ ጊዜ “ኹን” ማለት ነው፡፡ ወዲያው ይኾናልም*፡፡ إِنَّمَا أَمْرُهُ إِذَا أَرَادَ شَيْئًا أَن يَقُولَ لَهُ كُن فَيَكُونُ
40፥68 እርሱ ያ ሕያው የሚያደርግ የሚገድልም ነው፡፡ *አንዳችን ነገር በሻም ጊዜ ለእርሱ የሚለውን «ኹን» ነው፤ ወዲያውም ይኾናል*፡፡ هُوَ الَّذِي يُحْيِي وَيُمِيتُ ۖ فَإِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ
16፥40 *ለማንኛውም ነገር መኾኑን በሻነው ጊዜ ቃላችን ለእርሱ “ኹን” ማለት ብቻ ነው፤ ወዲውም ይኾናል*፡፡ إِنَّمَا قَوْلُنَا لِشَيْءٍ إِذَا أَرَدْنَاهُ أَن نَّقُولَ لَهُ كُن فَيَكُونُ

“ሸይእ” شَىْء ማለት “ነገር’thing” ማለት ሲሆን “ነገር” አንድ ነጠላ ሃልዎትን የሚያመለክትበት ጊዜ አለ። ለምሳሌ አላህ አደምን ኹን ሲለው ሆኗል፦
3፥59 አላህ ዘንድ *የዒሳ ምሳሌ እንደ አዳም ብጤ ነው፡፡ ከዐፈር ፈጠረው፡፡ ከዚያም ለእርሱ «ኹን» አለው፤ ኾነም*፡፡ إِنَّ مَثَلَ عِيسَىٰ عِندَ اللَّهِ كَمَثَلِ آدَمَ ۖ خَلَقَهُ مِن تُرَابٍ ثُمَّ قَالَ لَهُ كُن فَيَكُونُ

በተመሳሳይ ክርስቲያኖች ፈጣሪ ልጅ አለው ሲሉ አምላካችን አላህ፦ “ነገርንም ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው “ኹን” ነው፤ ወዲያውም ይኾናል” የሚል ምላሽ ሰጠ፦
2፥116 *አላህም ልጅ አለው አሉ፡፡ ከሚሉት ጥራት ተገባው፡፡ አይደለም በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ ሁሉም ለእርሱ ታዛዦች ናቸው*፡፡ وَقَالُوا۟ ٱتَّخَذَ ٱللَّهُ وَلَدًۭا ۗ سُبْحَٰنَهُۥ ۖ بَل لَّهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ ۖ كُلٌّۭ لَّهُۥ قَٰنِتُونَ
2፥117 ሰማያትንና ምድርን ያለብጤ ፈጣሪ ነው፤ *ነገርንም ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው፡- «ኹን» ነው፤ ወዲያውም ይኾናል*፡፡ بَدِيعُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ وَإِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ
19፥35 *ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል*፡፡ مَا كَانَ لِلَّهِ أَن يَتَّخِذَ مِن وَلَدٍ ۖ سُبْحَانَهُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

ነገርን ማስገኘት ሲፈልግ በንግግሩ “ኹን” ይላል ይሆናል፤ ዒሣንም ኹን ሲለው ሆነ። መርየምም፦ “ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል?” ስትል፤ መለኮታዊ ምላሽ፦ “አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፤ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል” የሚል ምላሽ ነው፦
3፥47 *፡-ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለች፡፡ ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፤ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል አላት*፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

ስለዚህ በፍጥረት ውስጥ ያሉት እያንዳንዱ ነገር ኹን ይለዋል ይሆናል። ምናልባት ይህንን ጥያቄ ያቀረበው ሰው "ወዲያው" የሚል ተውሳከ-ግስ "ከመቅጽበት" በሚል ስለተረዳው ነው እንጂ ሲጀመር ቁርኣኑ የሚለው፦ "የቁሉ ለሁ ኩን ፈየኩን" يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُون ነው። እዚህ ሃይለ-ቃል ውስጥ "ወዲያው" የሚል ቃል የለም። በዐማርኛ፣ በኢንግሊሽ፣ በፍሬንች ወዘተ የተጻፉ የቁርኣን ትርጉማት ቁርኣን አይደሉም። ሲቀጥል "ወዲያው" የሚል ቃል ቢኖር እንኳን በፍጥረት ውስጥ ያሉት እያንዳንዱ ነገር ኹን ይለዋል ወዲውኑም ይኾናል እንጂ በጥቅሉ ከአጠቃላይ ፍጥረት በስድስት ቀናት ውስጥ መፈጠር ጋር በፍጹም አይጋጭም።
እስቲ እንዲገባችሁ በነካ እጃችን እኛም ከባይብል ጥያቄ እናቅርብ። ፍጥረት የተፈጠረው በስድስት ቀናት ወይስ ሁን በሚል ንግግር?

በስድስት ቀን፦
ዘጸአት 31፥17 *"እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን በስድስት ቀን ስለ ፈጠረ"*፥
ዘጸአት 20፥11 *እግዚአብሔር በስድስት ቀን ሰማይንና ምድርን፥ ባሕርንም፥ ያለባቸውንም ሁሉ ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን ዐርፎአልና"*።

ሁን በሚል ቃል፦
ዘፍጥረት 1፥3 እግዚአብሔርም፦ ብርሃን *"ይሁን አለ ብርሃንም ሆነ"*።
መዝሙር 33፥9 *"እርሱ ተናግሮአልና፥ ሆኑም"*።
መዝሙር 148፥5 *"እርሱ ብሎአልና ሆኑም፤ እርሱም አዝዞአልና ተፈጠሩም"*።
ዮሐንስ 1፥3 *"ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም"*።
ኢሳይያስ 55፥11 *"ከአፌ የሚወጣ ቃሌ እንዲሁ ይሆናል፤ የምሻውን ያደርጋል"*።

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር አርባ ሰባት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 47
ከሰማይና ከምድር ቀድሞ የተፈጠረው የቱ ነው?

ምድርን፦
2፥29 *”እርሱ ያ በምድር ያለውን ሁሉ ለእናንተ የፈጠረ ነው፡፡ ከዚያም ወደ ሰማይ አሰበ፤ ሰባት ሰማያትም አደረጋቸው”*፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ هُوَ الَّذِي خَلَقَ لَكُم مَّا فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا ثُمَّ اسْتَوَىٰ إِلَى السَّمَاءِ فَسَوَّاهُنَّ سَبْعَ سَمَاوَاتٍ ۚ وَهُوَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

ሰማይን፦
79፥27 *”ባፈጣጠር እናንተ ይበልጥ የበረታችሁ ናችሁን? ወይንስ ሰማይ? አላህ ገነባት”*፡፡ أَأَنتُمْ أَشَدُّ خَلْقًا أَمِ السَّمَاءُ ۚ بَنَاهَا
79፥30 *”ምድርንም ከዚህ በኋላ ዘረጋት”*፡፡ وَالْأَرْضَ بَعْدَ ذَٰلِكَ دَحَاهَا

መልስ
አምላካችን አላህ ምድርን ፈጥሮ በምድር ያለውን ፈጠረ ከዚያም ወደ ሰማይ አሰበ፤ ሰባት ሰማያትም አደረጋቸው፦
2፥29 *”እርሱ ያ በምድር ያለውን ሁሉ ለእናንተ የፈጠረ ነው፡፡ ከዚያም ወደ ሰማይ አሰበ፤ ሰባት ሰማያትም አደረጋቸው”*፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ هُوَ الَّذِي خَلَقَ لَكُم مَّا فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا ثُمَّ اسْتَوَىٰ إِلَى السَّمَاءِ فَسَوَّاهُنَّ سَبْعَ سَمَاوَاتٍ ۚ وَهُوَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

እዚህ አንቀጽ ላይ፦ “በምድር ያለውን ከፈጠረ በኃላ ሰማይ ፈጠረ” የሚል ሽታው የለውም። ከዚህ ይልቅ “ወደ ሰማይ አሰበ” የሚል ሃይለ-ቃል አለ፤ “ኢላ”إِلَى ማለትም “ወደ” የሚለው መስተዋድድ መግባቱ በራሱ ሰማይ እንደነበረች ያሳያል። “ወደ” ፒያሳ አስቤአለው ማለት ፒያሳን ፈጠርኳት ማለት አይደለም፤ ፒያሳ ሳትኖር ወደ ፒያሳ ማቅናት አይቻልም። ሰማይ በህልውና ጭስ ኾና ሳለች አሰበ፦
41፥11 *”ከዚያም ወደ ሰማይ እርሷ ጭስ ኾና ሳለች አሰበ፡፡ ለእርሷም ለምድርም «ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ» አላቸው”*፡፡ «ታዛዦች ኾነን መጣን» አሉ፡፡ ثُمَّ اسْتَوَىٰ إِلَى السَّمَاءِ وَهِيَ دُخَانٌ فَقَالَ لَهَا وَلِلْأَرْضِ ائْتِيَا طَوْعًا أَوْ كَرْهًا قَالَتَا أَتَيْنَا طَائِعِينَ

“ሳለች” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ ለሰማይም ለምድርም፦ ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ” ማለቱ በራሱ ሰማይ እንደነበረች መረዳት ይቻላል። ከዚያም በጭስ ደረጃ የነበረችውን ሰማይ ሰባት ሰማያት አደረጋቸው፦
41፥12 በሁለት ቀኖችም ውስጥ *”ሰባት ሰማያት አደረጋቸው”*፡፡ فَقَضَاهُنَّ سَبْعَ سَمَاوَاتٍ فِي يَوْمَيْنِ
2፥29 እርሱ ያ በምድር ያለውን ሁሉ ለእናንተ የፈጠረ ነው፡፡ ከዚያም ወደ ሰማይ አሰበ፤ *”ሰባት ሰማያትም አደረጋቸው”*፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ هُوَ الَّذِي خَلَقَ لَكُم مَّا فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا ثُمَّ اسْتَوَىٰ إِلَى السَّمَاءِ فَسَوَّاهُنَّ سَبْعَ سَمَاوَاتٍ ۚ وَهُوَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

“ሱመ” ثُمَّ ማለትም ከዚያም” የሚለው አያያዥ መስተጻምር ተርቲብ ነው፤ “ተርቲብ” ترتيب ማለት “ቅድመ-ተከተል” ማለት ነው፤ ይህ ቅድመ-ተከተል በሁለት ይከፈላል፤ አንዱ የጊዜ ቅድመ-ተከተል ሲሆን ሁለተኛው የንግግር ቅድመ-ተከተል ነው፤ የንግግር ቅድመ-ተከተል ናሙናዎችን ማየት ይቻላል፦
7፥11 *በእርግጥም ፈጠርናችሁ፥ ከዚያም ቀረጽናችሁ፡፡ ከዚያም ለመላእክት «ለአዳም ስገዱ» አልን*፡፡ ወዲያውም ሰገዱ፡፡ ኢብሊስ ዲያብሎስ ሲቀር ከሰጋጆቹ አልኾነም፡፡ وَلَقَدْ خَلَقْنَاكُمْ ثُمَّ صَوَّرْنَاكُمْ ثُمَّ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ لَمْ يَكُن مِّنَ السَّاجِدِينَ

ይህ አንቀጽ ለአደም እና ለሐዋ ቢሆን ኖሮ በሙተና “ኸለቅናኩማ” خَلَقْنَاكُما “ሰወርናኩማ” صَوَّرْنَاكُما ይሆን ነበር፤ ነገር ግን ከሁለት በላይ እኛን ለማሳየት በጀመዕ “ኸለቅናኩም” خَلَقْنَاكُمْ “ሰወርናኩም” صَوَّرْنَاكُمْ ነው የሚለው፤ ከዚያም ለመላእክት ለአደም ስገዱ አለ፤ በጊዜ ቅድመ-ተከተል ካየነው እኛ ከመፈጠራችን በፊት ነው አላህ ለመላእክት፦ “ለአዳም ስገዱ” ያለው፤ ነገር ግን መስተጻምሩ የገባው የንግግር ቅድመ-ተከተል ለማሳየት ስለሆነ “ፈጠርናችሁ” “ቀረጽናችሁ” በንግግር ይቀድማል፦
6፥153 *«ይህም ቀጥተኛ ሲኾን መንገዴ ነው፤ ተከተሉትም፡፡ የጥመት መንገዶችንም አትከተሉ”*፡፡ ከቀጥተኛው መንገዱ እናንተን ይለያዩዋችኋልና፡፡እነሆ ትጠነቀቁ ዘንድ በርሱ አዘዛችሁ፡፡» وَأَنَّ هَـٰذَا صِرَاطِي مُسْتَقِيمًا فَاتَّبِعُوهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعُوا السُّبُلَ فَتَفَرَّقَ بِكُمْ عَن سَبِيلِهِ ۚ ذَٰلِكُمْ وَصَّاكُم بِهِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُون
6፥154 *”ከዚያም ለሙሳ በዚያ መልካም በሠራው ላይ ለማሟላት ነገርንም ሁሉ ለመዘርዘር መጽሐፉን ለእስራኤል ልጆች መሪና እዝነት ይኾን ዘንድ ሰጠነው*”፡፡ ثُمَّ آتَيْنَا مُوسَى الْكِتَابَ تَمَامًا عَلَى الَّذِي أَحْسَنَ وَتَفْصِيلًا لِّكُلِّ شَيْءٍ وَهُدًى وَرَحْمَةً لَّعَلَّهُم بِلِقَاءِ رَبِّهِمْ يُؤْمِنُون

“ይህም ቀጥተኛ ሲኾን መንገዴ ነው፤ ተከተሉትም” የተባለው ቁርኣን ሲሆን በንግግር ከቁርኣን በኃላ ስለ ተውራት ሲናገር፦ “ከዚያም” የሚል የንግግር ቅድመ-ተከተል ይጠቀማል፤ ያ ማለት ተውራት ከቁርኣን በኃላ መውረዱ ሳይሆን አላህ ስለ ቁርኣን ከተናገረ በኃላ ስለ ተውራት መናገሩ የሚያሳይ ነው፤ በተመሳሳይም አላህ ስለ ምድር ከተናገረ በኃላ ስለ ሰማይ መናገሩ የሚያሳይ ነው። እንደውም “ሱመ” የሚለውን ተርቲብ “እንዲሁ”simultaneously” በሚል ቃል ይመጣል። “እርሱ ያ በምድር ያለውን ሁሉ ለእናንተ የፈጠረ ነው፡፡ “እንዲሁ” ወደ ሰማይ አሰበ፤ ሰባት ሰማያትም አደረጋቸው” ብለን መረዳት እንችላለን።
አምላካችም አላህ ሰማይን በኀይል ፈጥሯታል፦
79፥27 *”ባፈጣጠር እናንተ ይበልጥ የበረታችሁ ናችሁን? ወይንስ ሰማይ? አላህ ገነባት”*፡፡ أَأَنتُمْ أَشَدُّ خَلْقًا أَمِ السَّمَاءُ ۚ بَنَاهَا
51፥47 *”ሰማይንም በኀይል ገነባናት”*፡፡ እኛም በእርግጥ ቻዮች ነን፡፡ وَالسَّمَاءَ بَنَيْنَاهَا بِأَيْدٍ وَإِنَّا لَمُوسِعُونَ
91፥5 *”በሰማይቱም በገነባትም ጌታ*፤ وَالسَّمَاءِ وَمَا بَنَاهَا
“በና” بَنَا የሚለው ቃል “ኸለቀ” خَلَقَ ለሚለው ቃል ተለዋዋጭ ቃል ሆኖ እንደመጣ እሙንና ቅቡል ነው። አላህ ሰማይን ጭስ እንድትሆን አድርጎ ከፈጠረ በኃላ ምድርንም ዘረጋት፦
79፥30 *”ምድርንም ከዚህ በኋላ ዘረጋት”*፡፡ وَالْأَرْضَ بَعْدَ ذَٰلِكَ دَحَاهَا

“ፈጠራት” ሳይሆን “ዘረጋት” ነው የሚለው፤ “ዘረጋት” ተብሎ የገባው ቃል “ደሓሃ” دَحَاهَا ሲሆን “ደሓ” دَحَىٰ ደግሞ በቁርኣን ላይ የመጣው በግስ መደብ እዚህ አንቀፅ ላይ ብቻ ነው፤ “ደሓ” በስም መደብ ሲመጣ “አድ-ደሕያ” الدِّحْية ነው፤ ትርጉሙም “የሰጎን እንቁላል” ማለት ነው፤ አላህ ምድርን “የእንቁላል ቅርጽ አደረጋት”He made the earth egg-shaped” የሚል ትርጉም አለው፤ ይህንን አንዳንድ የእንግሊዝኛ ትርጉም ላይ ይገኛል፦
1.Dr. Kamal Omar Translation
“And the earth, after this stage, He gave it *an oval form”*
2. Ali Unal Translation
“And after that He has spread out the earth in *the egg-shape”*
3. Shabbir Ahmed Translation
“And after that He made the earth *egg-shaped”*.

አላህ ምድርን ለእኛ የዘረጋት በርሷም ውስጥ እንመራ ዘንድ መንገዶችን አደረገልን፦
43፥10 *”እርሱ ያ ምድርን “ለእናንተ” ምንጣፍ ያደረገላችሁ በርሷም ውስጥ ትመሩ ዘንድ ለእናንተ መንገዶችን ያደረገላችሁ ነው”*፡፡ الَّذِي جَعَلَ لَكُمُ الْأَرْضَ مَهْدًا وَجَعَلَ لَكُمْ فِيهَا سُبُلًا لَّعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ
71፥19 *”አላህም ምድርን “ለእናንተ” ምንጣፍ አደረጋት”*፡፡ وَاللَّهُ جَعَلَ لَكُمُ الْأَرْضَ بِسَاطًا

“ለእናንተ” የሚለው ይሰመርበት፤ ለእኛ መንገድ መኪና ስንነዳ ዝርግ ሆኖ የሚታየን ልክ እንደ ምንጣፍ ነው፤ አላህ ሰማይን ከፈጠረ በኃላ ለእኛ የነበረችውን ምድር እንደ ምንጣፍ ዘረጋት። “በዕደ” بَعْدَ ማለትም “ከዚያም” የሚለው ተሳቢ የጊዜ ተውሳከ-ግስ ልክ እንደ “ሱመ” ቅድመ-ተከተል ሲሆን የንግግር ቅድመ-ተከተል ሆኖ ሊመጣ ይችላል፦
68.13 *”ልበ ደረቅን ከዚህ በኋላ ዲቃላን ሁሉ አትታዘዝ*”። عُتُلٍّ بَعْدَ ذَٰلِكَ زَنِيم

እዚህ አንቀጽ ላይ “ልበ ደረቅን እንዲሁ ዲቃላን ሁሉ አትታዘዝ” ተብሎ እንደተቀመጠ ሁሉ “ሰማይንም በኀይል ገነባናት እንዲሁ ምድርንም ዘረጋት” ተብሎ ሊቀመጥ ይችላል።
ስለዚህ ቁርኣን ላይ ግጭት የለም። ይጋጫል የሚል ተሟጋች ካለ ግን ያቀረብነውን ሙግት የሚያስተባብልበት የዐውድ፣ የተዛማች፣ የቋንቋና የሰዋስው ሙግት ማቅረብ ይጠበቅበታል።

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር አርባ ስምንት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 48
አላህ መላእክትን የሚያወርደው በቅጣት ብቻ ወይስ በራዕይ?

በቅጣት እንጂ በሌላ አያወርድም፡- 
ሱራ 15:7-8 “«ከእውነተኞቹ እንደ ኾንክ በመላእክት (መስካሪ) ለምን አትመጣንም» (አሉ)፡፡መላእክትን በእውነት (በቅጣት) እንጂ አናወርድም፡፡ ያን ጊዜም የሚቆዩ አይደሉም፡፡”

በራዕይ ያወርዳቸዋል፡- 
ሱራ 16:2 ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ መላእክትን ከራእይ ጋር በፈቃዱ ያወርዳል ከሓዲዎችን በቅጣት አስጠንቅቁ፤ እነሆ ከኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ ፍሩኝም ማለትን አስታውቁ በማለት ያወርዳል፡፡

መልስ
አምላካችን አላህ መላእክትን በራእይ ጉዳይ ወይም በቅጣት ጉዳይ ያወርዳል፦
16፥2 *"ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ መላእክትን ከራእይ ጋር በፈቃዱ ያወርዳል"*። ከሓዲዎችን በቅጣት አስጠንቅቁ፤ እነሆ ከኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ ፍሩኝም ማለትን አስታውቁ በማለት ያወርዳል፡፡ يُنَزِّلُ الْمَلَائِكَةَ بِالرُّوحِ مِنْ أَمْرِهِ عَلَىٰ مَن يَشَاءُ مِنْ عِبَادِهِ أَنْ أَنذِرُوا أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا فَاتَّقُونِ
8፥9 ከጌታችሁ እርዳታን በፈለጋችሁ ጊዜ *«እኔ በሺህ መላእክት ተከታታዮች ሲኾኑ እረዳችኋለሁ»* ሲል ለእናንተ የተቀበላችሁን አስታውሱ፡፡ إِذْ تَسْتَغِيثُونَ رَبَّكُمْ فَاسْتَجَابَ لَكُمْ أَنِّي مُمِدُّكُم بِأَلْفٍ مِّنَ الْمَلَائِكَةِ مُرْدِفِينَ

አምላካችን አላህ መላእክትን በራእይ ጉዳይ ወይም በቅጣት ጉዳይ እንደሚያወድ ከላይ ከተመለከትን ዘንዳ እነዚህ መላእክት በእውነት እንጂ በሌላ አያወርድም፦
15፥8 *"መላእክትን በእውነት (በቅጣት) እንጂ አናወርድም"*፡፡ ያን ጊዜም የሚቆዩ አይደሉም፡፡ مَا نُنَزِّلُ الْمَلَائِكَةَ إِلَّا بِالْحَقِّ وَمَا كَانُوا إِذًا مُّنظَرِينَ

መላእክትን በሁለት ነገር ያወርዳል፥ አንደኛው "በእውነት" ሁለተኛው "በቅጣት" ነው። ግን "በቅጣት" የሚለው በቅንፍ ነው ብሎ አንድ ሰው ቢሞግት ችግር የለውም። አላህ መላእክትን የሚልከው "ቢል-ሐቅ" بِالْحَقّ ማለትም "በእውነት" እንጂ ለአሽሟጣቾች ቀልድ አይደለም። ዐረቦች በለበጣ ንግግር፦ "አንተ ያ በእርሱ ላይ ቁርኣን የተወረደለት ሆይ" በማለት እያላገጡ፦ "ከእውነተኞቹ እንደ ኾንክ በመላእክት ለምን አትመጣንም" አሉ፦
15፥6 *«አንተ ያ በእርሱ ላይ ቁርኣን የተወረደለት ሆይ! አንተ በእርግጥ ዕብድ ነህ» አሉም*"፡፡ وَقَالُوا يَا أَيُّهَا الَّذِي نُزِّلَ عَلَيْهِ الذِّكْرُ إِنَّكَ لَمَجْنُونٌ
15፥7 *«ከእውነተኞቹ እንደ ኾንክ በመላእክት ለምን አትመጣንም» አሉ*፡፡ لَّوْ مَا تَأْتِينَا بِالْمَلَائِكَةِ إِن كُنتَ مِنَ الصَّادِقِين

አላህም ለዚህ ሽሙጥ ንግግር ምላሽ፦ "መላእክትን "በእውነት" እንጂ አናወርድም" ብሎ ተናገረ። መላእክት "በጌታ ትእዛዝ" እንጂ አይወርዱም፥ ነቢያችን”ﷺ” ጂብሪልን “አሁን ከምትጎበኘን በብዛት እኛን ለመጎብኘት ምን ያግድሃል? ሲሉት፤ እርሱም፦ “በጌታህም ትእዛዝ እንጅ አንወርድም፡፡ በፊታችን ያለው፣ በኋላችንም ያለው በዚህም መካከል ያለው ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ ጌታህም ረሺ አይደለም” ብሎ መለሰ፤ አላህ ይህንን የመለሰውን መልስ በተከበረው ቃሉ ለእኛ እንዲህ ነገረን፦
19፥64 *ጂብሪል አለ፦ «በጌታህም ትእዛዝ እንጅ አንወርድም፡፡ በፊታችን ያለው፣ በኋላችንም ያለው በዚህም መካከል ያለው ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ ጌታህም ረሺ አይደለም»* وَمَا نَتَنَزَّلُ إِلَّا بِأَمْرِ رَبِّكَ ۖ لَهُۥ مَا بَيْنَ أَيْدِينَا وَمَا خَلْفَنَا وَمَا بَيْنَ ذَٰلِكَ ۚ وَمَا كَانَ رَبُّكَ نَسِيًّۭا
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 97 , ሐዲስ 81:
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"ጂብሪል ሆይ! አሁን ከምትጎበኘን በብዛት እኛን ለመጎብኘት ምን ያግድሃል? አሉት፤ እርሱም፦ "በጌታህም ትእዛዝ እንጅ አንወርድም፡፡ በፊታችን ያለው፣ በኋላችንም ያለው በዚህም መካከል ያለው ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ ጌታህም ረሺ አይደለም፤ ከዚያም፦ ጂብሪል አለ፦ “በጌታህም ትእዛዝ እንጅ አንወርድም፡፡ በፊታችን ያለው፣ በኋላችንም ያለው በዚህም መካከል ያለው ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ ጌታህም ረሺ አይደለም” የሚለው አንቀፅ ከዚያም ወረደ፤ ይህም ለሙሐመድ”ﷺ” መልስ ነው*። حَدَّثَنَا خَلاَّدُ بْنُ يَحْيَى، حَدَّثَنَا عُمَرُ بْنُ ذَرٍّ، سَمِعْتُ أَبِي يُحَدِّثُ، عَنْ سَعِيدِ بْنِ جُبَيْرٍ، عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما ـ أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏”‏ يَا جِبْرِيلُ مَا يَمْنَعُكَ أَنْ تَزُورَنَا أَكْثَرَ مِمَّا تَزُورُنَا ‏”‌‏.‏ فَنَزَلَتْ ‏{‏وَمَا نَتَنَزَّلُ إِلاَّ بِأَمْرِ رَبِّكَ لَهُ مَا بَيْنَ أَيْدِينَا وَمَا خَلْفَنَا‏}‏ إِلَى آخِرِ الآيَةِ‏.‏ قَالَ هَذَا كَانَ الْجَوَابَ لِمُحَمَّدٍ صلى الله عليه وسلم‏.‏

"በጌታህ ትእዛዝ" የምትለዋን ቆርጠን "አንወርድም" የምትለዋን ይዘን መላእክት አይወርዱም እንደማንል ሁላ "በእውነት" የምትለዋን ቆርጠን "አናወርድም" የምትለዋን ይዘን መላእክት አይወርዱም ማለት የለብንም። "በእውነት" የሚለው ቃል "በጌታ ትእዛዝ" በሚል ተለዋዋጭ ቃል"interchange word" መጥቷል ማለት ነው። አላህ መላእክትን በራሱ ትእዛዝ እንጂ አያወርድም፥ በራሱ ትእዛዝ ግን መላእክትን ከራእይ ጋር ያወርዳል።

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር አርባ ዘጠኝ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 49
አላህ ሰማይና ምድርን ወደ አንድ ጠራቸው ወይስ ለያያቸው?

ወደ አንድ ጠራቸው፡- 
41:11 “ከዚያም ወደ ሰማይ እርሷ ጭስ ሆና ሳለች አሰበ፤ ለርሷም ለምድርም ወዳችሁም ሆነ ወይም ጠልታችሁ፣ ኑ፤ አላቸው። ታዛዦች ሆነን መጣን አሉ።”

ለያያቸው፡- 
21:30 “እነዚያም የካዱት ሰማያትና ምድር የተጣበቁ የነበሩና የለያየናቸው መሆናችንን አያውቁምን? ሕያው የኾነንም ነገር ሁሉ ከውሃ ፈጠርን አያምኑምን?”

መልስ
41፥11 *”ከዚያም ወደ ሰማይ እርሷ ጭስ ኾና ሳለች አሰበ፡፡ ለእርሷም ለምድርም «ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ» አላቸው”*፡፡ «ታዛዦች ኾነን መጣን» አሉ፡፡ ثُمَّ اسْتَوَىٰ إِلَى السَّمَاءِ وَهِيَ دُخَانٌ فَقَالَ لَهَا وَلِلْأَرْضِ ائْتِيَا طَوْعًا أَوْ كَرْهًا قَالَتَا أَتَيْنَا طَائِعِينَ

“ሳለች” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ ለሰማይም ለምድርም፦ ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ” ማለቱ በራሱ ሰማይ እንደነበረች መረዳት ይቻላል። በጭስ ደረጃ የነበረችውን ሰማይ እና ምድርን፦ "ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ" ሲላቸው፥ እነርሱም፦ "ታዛዦች ኾነን መጣን" አሉ። ከዚያም ምድርን ዘረጋት፦
79፥30 *”ምድርንም ከዚህ በኋላ ዘረጋት”*፡፡ وَالْأَرْضَ بَعْدَ ذَٰلِكَ دَحَاهَا

በጭስ ደረጃ የነበረችውን ሰማይ ሰባት ሰማያት አደረጋቸው፦
41፥12 በሁለት ቀኖችም ውስጥ *”ሰባት ሰማያት አደረጋቸው”*፡፡ فَقَضَاهُنَّ سَبْعَ سَمَاوَاتٍ فِي يَوْمَيْنِ
2፥29 እርሱ ያ በምድር ያለውን ሁሉ ለእናንተ የፈጠረ ነው፡፡ ከዚያም ወደ ሰማይ አሰበ፤ *”ሰባት ሰማያትም አደረጋቸው”*፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ هُوَ الَّذِي خَلَقَ لَكُم مَّا فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا ثُمَّ اسْتَوَىٰ إِلَى السَّمَاءِ فَسَوَّاهُنَّ سَبْعَ سَمَاوَاتٍ ۚ وَهُوَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

ሲጠራቸው ሰማይና ምድር ተገጣጥመው ሳለ ምድርን በመዘርጋት እንዲሁ ሰማይን ሰባት ሰማያት በማድረግ ለያያቸው፦
21፥30 እነዚያም የካዱት *"ሰማያት እና ምድር የተጣበቁ የነበሩና የለያየናቸው መኾናችንን ዐያውቁምን?* ሕያው የኾነንም ነገር ሁሉ ከውሃ ፈጠርን፡፡ አያምኑምን? أَوَلَمْ يَرَ الَّذِينَ كَفَرُوا أَنَّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ كَانَتَا رَتْقًا فَفَتَقْنَاهُمَا ۖ وَجَعَلْنَا مِنَ الْمَاءِ كُلَّ شَيْءٍ حَيٍّ ۖ أَفَلَا يُؤْمِنُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ረትቅ" رَتْق ማለት "መገጣጠም"connect" ማለት ነው። ሰማይ ጭስ ሆና ሳለች ከምድር ጋር አብረው ነበሩ፥ ከዚያ ምድርን ዘረጋት ሰማይን ደግሞ ሰባት ሰማያት አደረጋቸው። ቁርኣን ላይ፦ "አይመለከቱምን" "አይሰሙምን" "አይገሰጹምን" "አያስተውሉምን" "አያስተነትኑምን" "አይገነዘቡምን" የሚል ሃይለ-ቃል በተደጋጋሚ ጊዜ አለ። ያ ማለት "ይመልከቱ" "ይስሙ" ይገሰጹ" "ያስተውሉ" "ያስተንትኑ" "ይገንዘቡ" ማለት እንደሆነ ሁሉ "አያውቁምን" ማለት "ይወቁ" ማለት ነው። አዎ ሰማይ እና ምድር የተጣበቁ የነበሩና አላህ ምድርን በመዘርጋት ሰማይን ሰባት ሰማያት በማድረግ የለያያቸው መኾኑን ይወቁ።
በባይብልም ከሄድን እግዚአብሔር በሕዝቡ ለመፍረድ ሰማይና ምድር ጊዜ በአንድነት ይቆማሉ፦
ኢሳይያስ 48፥13 እጄም ምድርን መሥርታለች ቀኜም ሰማያትን ዘርግታለች፤ *"በጠራኋቸው ጊዜ በአንድነት ይቆማሉ"*።
መዝሙር 50፥4 በላይ ያለውን *"ሰማይን ምድርንም በሕዝቡ ለመፍረድ ይጠራል"*።

እረ ይህ ብቻ ሳይሆን ያመሰግናሉ፣ እልል ይላሉ፣ ይመላለሱ፦
መዝሙር 69፥34  *"ሰማይና ምድር ባሕርም በእርስዋም የሚንቀሳቀስ ሁሉ ያመሰግኑታል"*።
ኤርሚያስ 51፥48  አጥፊዎች ከሰሜን ይመጡባታልና *"ሰማይና ምድር በእነርሱም ያለው ሁሉ ስለ ባቢሎን እልል ይላሉ"*፥ ይላል እግዚአብሔር።
ሆሴዕ 2፥23  በዚያንም ቀን እመልሳለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ *"ለሰማይ እመልሳለሁ፥ ሰማይም ለምድር ይመልሳል"*።

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር አምሳ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 50
ጂኒዎች ከምንድነው የተፈጠሩት?

ከእሳት፡- 
15:27 “ጃንንም ከሰው በፊት ከእሳት ነበልባል ፈጠርነው፡፡”
ከውኃ፡- 
21፡30 “…ሕያው የኾነንም ነገር ሁሉ ከውሃ ፈጠርን አያምኑምን?”

መልስ
ጂኒዎች የተፈጠሩት ከሰው በፊት ነው፤ ሰው የተፈጠረበት ንጥረ-ነገር ዐፈር እንደሆነ፤ መልአክ የተፈጠረበት ንጥረ-ነገር ብርሃን እንደሆነ ሁሉ ጂን የተፈጠረበት ንጥረ-ነገር ደግሞ እሳት ነው፦
15፥27 *ጃንንም ከሰው በፊት ከእሳት ነበልባል ፈጠርነው*፡፡ وَالْجَانَّ خَلَقْنَاهُ مِن قَبْلُ مِن نَّارِ السَّمُومِ
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 55, ሐዲስ 78
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”መላእክት ከብርሃን ተፈጥረዋል፤ ጂንዎች ከእሳት ነበልባል ተፈጥረዋል፤ አደም ለእናንተ እንደተገለጸላችሁ ከሚጭለቀለቅ ሸክላ ተፈጥሯል”*፡፡ عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم‏ خُلِقَتِ الْمَلاَئِكَةُ مِنْ نُورٍ وَخُلِقَ الْجَانُّ مِنْ مَارِجٍ مِنْ نَارٍ وَخُلِقَ آدَمُ مِمَّا وُصِفَ لَكُمْ ‏.‏

እንስሳት፣ ሰው፣ ጂን እና መላእክት ግዑዛን ፍጥረታት ሳይሆኑ ሕያዋን ፍጥረታት ናቸው። ሕያው የኾነንም ነገር ሁሉ ከውኃ እንደተፈጠረ አላህ ይናገራል፦
21፥30 እነዚያም የካዱት ሰማያት እና ምድር የተጣበቁ የነበሩና የለያየናቸው መኾናችንን ዐያውቁምን? *ሕያው የኾነንም ነገር ሁሉ ከውኃ ፈጠርን"*፡፡ አያምኑምን? أَوَلَمْ يَرَ الَّذِينَ كَفَرُوا أَنَّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ كَانَتَا رَتْقًا فَفَتَقْنَاهُمَا ۖ وَجَعَلْنَا مِنَ الْمَاءِ كُلَّ شَيْءٍ حَيٍّ ۖ أَفَلَا يُؤْمِنُونَ

እና ጂን እና መላእክት ከውኃ ነው የተፈጠሩትን? እዚህ አንቀጽ ላይ "ኩል” كُلّ የሚለው ገላጭ ቅጽል “ኢስቲስናዕ” اِسْتِثْنَاء‏ ሆኖ የመጣ ነው፥ በአንጻራዊ ሁሉነት“Relative all” ሲመጣ "ቀሪብ” قريب ይባላል። ይህንን ለመረዳት የተለያዩ ናሙና ማየት ይቻላል፦
46፥25 በጌታዋ ትእዛዝ *"ነገሩን ሁሉ ታጠፋለች አላቸው"* تُدَمِّرُ كُلَّ شَيْءٍ بِأَمْرِ رَبِّهَا
51፥49 ትገነዘቡም ዘንድ *"ከነገሩ ሁሉ ሁለት ተቃራኒ ዓይነትን ፈጠርን"*። وَمِن كُلِّ شَيْءٍ خَلَقْنَا زَوْجَيْنِ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ
27፥16 ሱለይማንም ዳውድን ወረሰ፤ አለም፦ ሰዎች ሆይ! የበራሪን ንግግር ተስተማርን፤ *"ከነገሩም ሁሉ ተሰጠን"*፤ ይህ እርሱ በእርግጥ ግልጽ የሆነ ችሮታ ነው። وَوَرِثَ سُلَيْمَانُ دَاوُودَ ۖ وَقَالَ يَا أَيُّهَا النَّاسُ عُلِّمْنَا مَنطِقَ الطَّيْرِ وَأُوتِينَا مِن كُلِّ شَيْءٍ ۖ إِنَّ هَـٰذَا لَهُوَ الْفَضْلُ الْمُبِينُ

እነዚህ ሦስት አናቅጽ ላይ፦ "ኩለ ሸይእ" كُلِّ شَيْء ማለትም "ነገር ሁሉ" የሚል ቃል በአጻራዊነት መጥቷል እንጂ ነፋስ የተፈጠረ ነገር ሁሉ ያጠፋል፣ የተፈጠረ ነገር ሁሉ ተቃራኒ አለው፣ ሱለይማን ነገርን ሁሉ ያውቃል ማለት አይደለም። ይህንን ከተረዳን ዘንዳ ከውኃ የተፈጠረ ሕያው የሆነ ነገር የሚለው ሰው እና እንስሳት ነው፦
25፥54 እርሱም ያ *"ከውኃ ሰውን የፈጠረ"*፣ የዝምድናና የአማችም ባለቤት ያደረገው ነው፡፡ ጌታህም ቻይ ነው፡፡ وَهُوَ الَّذِي خَلَقَ مِنَ الْمَاءِ بَشَرًا فَجَعَلَهُ نَسَبًا وَصِهْرًا ۗ وَكَانَ رَبُّكَ قَدِيرًا
24፥45 *አላህም ተንቀሳቃሽን ሁሉ ከውኃ ፈጠረ"*፡፡ ከእነርሱም በሆዱ ላይ የሚኼድ አለ፡፡ ከእነሱም በሁለት እግሮች ላይ የሚኼድ አለ፡፡ አላህ የሚሻውን ሁሉ ይፈጥራል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና፡፡ وَاللَّهُ خَلَقَ كُلَّ دَابَّةٍ مِّن مَّاءٍ ۖ فَمِنْهُم مَّن يَمْشِي عَلَىٰ بَطْنِهِ وَمِنْهُم مَّن يَمْشِي عَلَىٰ رِجْلَيْنِ وَمِنْهُم مَّن يَمْشِي عَلَىٰ أَرْبَعٍ ۚ يَخْلُقُ اللَّهُ مَا يَشَاءُ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
ምን ትፈልጋለህ? 21፥30 ላይ "ኩለ ሸይእ" كُلِّ شَيْء ማለትም "ነገር ሁሉ" የሚለው 24፥45 ላይ "ኩለ ዳባህ" كُلَّ دَابَّة ማለትም "ተንቀሳቃሽ ሁሉ" በሚል ተፈስሯል። ስለዚህ "ነገር" የተባለው "ተንቀሳቃሽ" ከሆነ ይህ ተንቀሳቃሽ በምድር ላይ ያሉት ሰው እና እንስሳት ናቸው፦
11፥6 *"በምድርም ላይ ምንም ተንቀሳቃሽ የለችም ምግቧ በአላህ ላይ ያለ ቢኾን እንጂ"*፡፡ ማረፊያዋንም መርጊያዋንም ያውቃል፡፡ ሁሉም ግልጽ በሆነው መጽሐፍ ውስጥ ነው፡፡ وَمَا مِن دَابَّةٍ فِي الْأَرْضِ إِلَّا عَلَى اللَّهِ رِزْقُهَا وَيَعْلَمُ مُسْتَقَرَّهَا وَمُسْتَوْدَعَهَا ۚ كُلٌّ فِي كِتَابٍ مُّبِينٍ

ይህ አንደኛው ማብራሪያ ሲሆን ሁለተኛው ማብራሪያ "ዳባህ" دَابَّة ማለት "ቁስ"matter” ማለት ሲሆን "ቁስ" አራት ፍሰት”Fluid” አሉት እነርሱም፦ “ፈሳሽ"liquid"፣ “ጠጣር”solid"፣ “ጋዝ”gas" እና “ፕላዝማ”plasma" ናቸው። እነዚህ አራት ፍሉድ መሠረታቸው "ውኃ" መሆኑን የደረሰበት ሬኔ ደስካተርስ በ 1650 ድኅረ-ልደት"AD" ነው። እንግዲህ ውኃ የሁሉ ነገር ሥረ-መሰረት ከሆነ እሳትና ብርሃን ቁስ መሆናቸውን እና ከጋዝ ወይም ከፕላዝማ እንደሚመደቡ ዕወቅ። ታዲያ ከእሳት የተፈጠሩት ጂን እና ከብርሃን የተፈጠሩት መላእክት ሕያው ነገር ከሆኑ እሳትና ብርሃንም ቁስ ከሆነ የቁስ መገኛው ውኃ ከሆነ ሕያው የሆኑ ፍጥረታት ከውኃ ተፈጠሩ ቢባል ምን ያስደንቃል? "ሸይእ" شَيْء የሚለው "ዳባህ" دَابَّة የሚለውን ተክቶ ከመጣ አላህ ተንቀሳቃችን በምድር ውስጥ እንዳደረገ ሁሉ በሰማያትም ውስጥ ማድረጉን አንባቢ ልብ ይለዋል፦
42፥29 *"ሰማያትንና ምድርንም መፍጠሩ፣ ከተንቀሳቃሽም "በሁለቱ ውስጥ" የበተነውን መፍጠሩ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው*፡፡ እርሱም በሚሻ ጊዜ እነርሱን በመሰብሰብ ላይ ቻይ ነው፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ خَلْقُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا بَثَّ فِيهِمَا مِن دَابَّةٍ ۚ وَهُوَ عَلَىٰ جَمْعِهِمْ إِذَا يَشَاءُ قَدِيرٌ

ስለዚህ "ኩል” كُلّ የሚለው ቃል “ሙጥለቅ” مطلق ማለትም "በፍጹማዊ ሁሉነት“Absolute all” ሆኖ ነው የመጣው ብንል እንኳን ሕያው የሆነ ነገር እንስሳት፣ እጽዋት፣ ጅን፣ መላእክት የተፈጠሩበት ሥረ-መሰረት ውኃ ነው። እዚህ ጋር እኛም እንዲገባችሁ ጥያቄ እናቀርባለን። እንስሳት የተፈጠሩት ከምንድን ነው? ከውኃ ወይስ ከአፈር?

ከውኃ፦
ዘፍጥረት 1፥20 እግዚአብሔርም አለ፦ *"ውኃ ሕያው ነፍስ ያላቸውን ተንቀሳቃሾች ታስገኝ"*።
ዘፍጥረት 1፥21 *"ውኃይቱ እንደ ወገኑ ያስገኘቻቸውንም ተንቀሳቃሾቹን ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ፥ እንደ ወገኑ የሚበሩትንም ወፎች ሁሉ ፈጠረ"*።

ከአፈር፦
መክብብ 3፥19 *"የሰው ልጆችና የእንስሳ እድል ፈንታ አንድ ነው"*።
መክብብ 3፥20 ሁሉ ወደ አንድ ቦታ ይሄዳል፤ *"ሁሉ ከአፈር ነው ሁሉም ወደ አፈር ይመለሳል"*።

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር አምሳ አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 51
መናፍቃን ዕውሮች ናቸው ወይስ አይደሉም?

ዕውሮች ናቸው፡- 
2፡17-18 በንፍቅና ምሳሌያቸው እንደዚያ እሳትን እንዳነደደ ሰው በዙሪያው ያለውን ሁሉ ባበራች ጊዜም አላህ ብርሃናቸውን እንደወሰደባቸው በጨለማዎችም ውስጥ የማያዩ ኾነው እንደተዋቸው ብጤ ነው፡፡ እነርሱ ደንቆሮዎች፣ ዲዳዎች፣ ዕውሮች ናቸው፤ ስለዚህ እነርሱ አይመለሱም፡፡”

በመጠኑ ያያሉ፡- 
2፡20 “በእነሱም ላይ ባጨለመ ጊዜ ይቆማሉ፡፡ አላህም በሻ ኖሮ "መስሚያቸውንና ማያዎቻቸውን በወሰደ ነበር፤ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና፡፡”

መልስ
አምላካችን አላህ ለሁሉም ሰው ማለትም ለሙሥሉሙ ሆነ ለሙሽሪኩ፣ ለሙዕሚኑ ሆነ ለካፊሩ፣ ለሙናፊቁ ሆነ ለሙኽሊሱ መስሚያ፣ ማያዎችን እና ልቦችን ፈጥሯል፦
67፥23 «እርሱ ያ የፈጠራችሁ ለእናንተም *"መስሚያ፣ ማያዎችን እና ልቦችንም ያደረገላችሁ ነው"*። ጥቂትንም አታመስግኑም?» በላቸው፡፡ قُلْ هُوَ الَّذِي أَنشَأَكُمْ وَجَعَلَ لَكُمُ السَّمْعَ وَالْأَبْصَارَ وَالْأَفْئِدَةَ ۖ قَلِيلًا مَّا تَشْكُرُونَ
23፥78 እርሱም ያ *"መስሚያዎችን፣ ማያዎችን እና ልቦችን ለእናንተ የፈጠረላችሁ ነው"*፡፡ ጥቂትን እንጅ አታመሰግኑም፡፡ وَهُوَ الَّذِي أَنشَأَ لَكُمُ السَّمْعَ وَالْأَبْصَارَ وَالْأَفْئِدَةَ ۚ قَلِيلًا مَّا تَشْكُرُونَ

አላህ ቢፈልግ ኖሮ ይህንን መስሚያና ማያዎችን ከሙናፊቃን በወሰደ ነበር፦
2፥20 *"አላህም በሻ ኖሮ መስሚያቸውንና ማያዎቻቸውን በወሰደ ነበር፤ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና፡፡ وَلَوْ شَاءَ اللَّهُ لَذَهَبَ بِسَمْعِهِمْ وَأَبْصَارِهِمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

"ወለው" وَلَوْ የሚለው ሁኔታዊ መስተዋድድ አላህ ቢፈልግ ኖሮ የማያዩና የማይሰሙ ማረግ ይችል ነበር፥ ግን እንደዛ አላደረጋቸው። ሙናፊቃን ውጫው መስሚያና ማያዎች ቢኖራቸውም ውሳጣዊ ማያቸው እና መስሚያቸው የታወረና የደኖቆረ ነው፦
2፥18 *"እነርሱ ደንቆሮዎች፣ ዲዳዎች፣ ዕውሮች ናቸው"*፤ ስለዚህ እነርሱ አይመለሱም፡፡ صُمٌّ بُكْمٌ عُمْيٌ فَهُمْ لَا يَرْجِعُونَ
2፥171 *"የእነዚያም የካዱት ምሳሌ እንደዚያ ድምጽንና ጥሪን በስተቀር ሌላን በማይሰማ እንስሳ ላይ እንደሚጮህ ብጤ ነው፡፡ እነርሱ ደንቆሮዎች፣ ዲዳዎች፣ ዕውሮች ናቸው"*። ስለዚህ እነርሱ አያውቁም፡፡ وَمَثَلُ الَّذِينَ كَفَرُوا كَمَثَلِ الَّذِي يَنْعِقُ بِمَا لَا يَسْمَعُ إِلَّا دُعَاءً وَنِدَاءً ۚ صُمٌّ بُكْمٌ عُمْيٌ فَهُمْ لَا يَعْقِلُونَ

እንስሳ ድምጽ ይሰማሉ፥ ብርሃንም ያያሉ ግን ውሳጣዊ ጆሮና ዓይን የላቸውም። ልክ እንደነርሱ እነዚያ የካዱት ውሳጣዊ ዓይናቸው ታውሯል፤ ውሳጣዊ ጆራቸው ደንቁሯል፦
7፥179 ከጂኒም ከሰዎችም ብዙዎችን ለገሀነም በእርግጥ ፈጠርን፡፡ *"ለ"እነርሱ ልቦች አሏቸው፥ ግን አይገነዘቡበትም፡፡ "ለ"እነርሱም ዓይኖች አሉዋቸው፥ ግን ዐያዩበትም፡፡ "ለ"እነርሱም ጆሮዎች አሉዋቸው ግን አይሰሙበትም"*፡፡ ይልቁንም እነርሱ በጣም የተሳሳቱ ናቸው፡፡ እነዚያ ዘንጊዎቹ እነርሱ ናቸው። وَلَقَدْ ذَرَأْنَا لِجَهَنَّمَ كَثِيرًا مِّنَ الْجِنِّ وَالْإِنسِ ۖ لَهُمْ قُلُوبٌ لَّا يَفْقَهُونَ بِهَا وَلَهُمْ أَعْيُنٌ لَّا يُبْصِرُونَ بِهَا وَلَهُمْ آذَانٌ لَّا يَسْمَعُونَ بِهَا ۚ أُولَـٰئِكَ كَالْأَنْعَامِ بَلْ هُمْ أَضَلُّ ۚ أُولَـٰئِكَ هُمُ الْغَافِلُون

ስለዚህ ይህንን ጥያቄ ያቀረበው ባይብልን በቅጡ ያላነበበ ሰው ነው። ባይብልም ላይ እኮ ውሳጣዊ ዓይንና ጆሮ የታወረና የደኖቆረን ሰው ዕውርና ደንቆሮ ይላል፦
ማቴዎስ 23፥17  *"እናንተ ደንቆሮዎችና ዕውሮች"*፥ ማናቸው ይበልጣል? ወርቁ ነውን? ወይስ ወርቁን የቀደሰው ቤተ መቅደስ?
ማቴዎስ 23፥19  *"እናንተ ደንቆሮዎችና ዕውሮች"*፥ ማናቸው ይበልጣል? መባው ነውን? ወይስ መባውን የሚቀድሰው መሠዊያው?

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር አምሳ ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 52
ከሃዲያን በፍርድ ቀን ከአላህ የሚደብቁት ነገር አለ ወይስ የለም?

አለ፡- 
6:22-23 “ሁላቸውንም የምንሰበስብበትንና ከዚያም ለእነዚያ ጣዖታትን ለአጋሩት እነዚያ ለአላህ ተጋሪዎች ናቸው ብላችሁ ታስቧቸው የነበራችሁት ተጋሪዎቻችሁ የት ናቸው የምንልበትን ቀን አስታውስ፡፡ ከዚያም መልሳቸው «በጌታችን በአላህ ይኹንብን አጋሪዎች አልነበርንም» ማለት እንጅ ሌላ አትኾንም፡፡”

የለም፡- 
4:42 “በዚያ ቀን እነዚያ የካዱትና መልዕክተኛውን ያልታዘዙት በነሱ ምድር ብትደፋባቸው ይመኛሉ፤ ከአላህም ወሬን አይደብቁም።”

መልስ
በትንሳኤ ቀን አላህ ለእነዚያ ለአጋሩት፦ "እነዚያ ለአላህ ተጋሪዎች ናቸው ብላችሁ ታስቧቸው የነበራችሁት ተጋሪዎቻችሁ የት ናቸው? ብሎ ይጠይቃቸዋል። እነርሱም፦ "በአላህ ላይ አጋሪዎች አልነበርንም" ብለው ይቀጥፋሉ፦
6፥22 ሁላቸውንም የምንሰበስብበትንና ከዚያም *"ለእነዚያ ለአጋሩት፦ "እነዚያ ለአላህ ተጋሪዎች ናቸው ብላችሁ ታስቧቸው የነበራችሁት ተጋሪዎቻችሁ የት ናቸው? የምንልበትን ቀን አስታውስ*፡፡ وَيَوْمَ نَحْشُرُهُمْ جَمِيعًا ثُمَّ نَقُولُ لِلَّذِينَ أَشْرَكُوا أَيْنَ شُرَكَاؤُكُمُ الَّذِينَ كُنتُمْ تَزْعُمُونَ
6፥23 ከዚያም መልሳቸው *«በጌታችን በአላህ ይኹንብን አጋሪዎች አልነበርንም»* ማለት እንጅ ሌላ አትኾንም፡፡ ثُمَّ لَمْ تَكُن فِتْنَتُهُمْ إِلَّا أَن قَالُوا وَاللَّهِ رَبِّنَا مَا كُنَّا مُشْرِكِينَ

አላህ፦ "እነዚያ ለአላህ ተጋሪዎች ናቸው ብላችሁ ታስቧቸው የነበራችሁት ተጋሪዎቻችሁ የት ናቸው? ብሎ ለሚጠይቃቸው ጥያቄ መልሳቸው፦ "አጋሪዎች አልነበርንም" ማለት እንጅ ሌላ አትኾንም። ነገር ግን ስለ ቁርኣን ሲጠየቁ እንቅጯን ፍርጥ አድርገው ይናገራሉ እንጂ አይደብቁም፦
4፥42 *"በዚያ ቀን እነዚያ የካዱትና መልክተኛውን ያልታዘዙት በእነርሱ ምድር ብትደፋባቸው ይመኛሉ፡፡ ከአላህም ወሬን አይደብቁም"*፡፡ يَوْمَئِذٍ يَوَدُّ الَّذِينَ كَفَرُوا وَعَصَوُا الرَّسُولَ لَوْ تُسَوَّىٰ بِهِمُ الْأَرْضُ وَلَا يَكْتُمُونَ اللَّهَ حَدِيثًا

"ወሬ" ተብሎ የተቀመው ቃል "ሐዲስ" حَدِيث ሲሆን "ንግግር" ማለት ነው። ይህም ንግግር ቁርኣን ነው፦
18፥6 *"በዚህም ንግግር በቁርኣን ባያምኑ በፈለጎቻቸው ላይ በቁጭት ነፍስህን አጥፊ ልትሆን ይፈራልሃል"*፡፡ فَلَعَلَّكَ بَاخِعٌ نَّفْسَكَ عَلَىٰ آثَارِهِمْ إِن لَّمْ يُؤْمِنُوا بِهَـٰذَا الْحَدِيثِ أَسَفًا

አላህ ቁርኣንን እውነት አድርጎ አውርዶ ሳለ እነዚያ የካዱት፦ "ይህ ግልጽ ድግምት ነው" አሉ። ነገር ግን አላህ በትንሳኤ ቀን ስለ ቁርኣኑ፦ "ይህ እውነት አይደለምን? ብሎ ይጠይቃቸዋል፥ እነርሱም፦ "እውነት ነው፤ በጌታችን ይኹንብን" ይላሉ፥ ከአላህ ንግግር ምንም አይደብቁም፦
46፥7 *"በእነርሱም ላይ አንቀጾቻችን ግልጾች ኾነው በተነበቡ ጊዜ እነዚያ እውነቱን በመጣላቸው ጊዜ የካዱት «ይህ ግልጽ ድግምት ነው» አሉ"*፡፡ وَإِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ آيَاتُنَا بَيِّنَاتٍ قَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا لِلْحَقِّ لَمَّا جَاءَهُمْ هَـٰذَا سِحْرٌ مُّبِينٌ
46፥34 *"እነዚያም የካዱት ሰዎች በእሳት ላይ በሚቀረቡ ቀን «ይህ እውነት አይደለምን?» ይባላሉ፡፡ «እውነት ነው፤ በጌታችን ይኹንብን» ይላሉ፡፡ አላህም «ትክዱ በነበራችሁት ምክንያት ቅጣቱን ቅመሱ» ይላቸዋል"*፡፡ وَيَوْمَ يُعْرَضُ الَّذِينَ كَفَرُوا عَلَى النَّارِ أَلَيْسَ هَـٰذَا بِالْحَقِّ ۖ قَالُوا بَلَىٰ وَرَبِّنَا ۚ قَالَ فَذُوقُوا الْعَذَابَ بِمَا كُنتُمْ تَكْفُرُونَ

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር አምሳ ሦስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 53
በሉጥ ዘመን የነበሩት ህዝቦች ለሉጥ የመለሱለት መልስ የትኛውን ነው?

ከከተማችሁ አውጡ፡፡እነርሱ የሚጥራሩ ሰዎች ናቸውና» ማለት እንጅ ሌላ አልነበረም፦
27:55-56 “«እናንተ ከሴቶች አልፋችሁ ወንዶችን ለመከጀል ትመጣላችሁን በእውነቱ እናንተ የምትሳሳቱ ሕዝቦች ናቸሁ፡፡» የሕዝቦቹም መልስ የሉጥን ቤተሰቦች «ከከተማችሁ አውጡ፡፡እነርሱ የሚጥራሩ ሰዎች ናቸውና» ማለት እንጅ ሌላ አልነበረም፡፡”

ከእውነተኞቹ እንደ ኾንክ የአላህን ቅጣት አምጣብን ማለት እንጂ ሌላ አልነበረም፦
29፥29 “እናንተ በእርግጥ ወንዶችን ትመጣላችሁን? መንገድን ትቆርጣላችሁን? በሸንጓችሁም የሚነወርን ነገር ትሠራላችሁን?(አላቸው)፤ የሕዝቦቹም መልስ ከውነተኞቹ እንደ ኾንክ የአላህን ቅጣት አምጣብን ማለት እንጂ ሌላ አልነበረም።”

መልስ
ቁርኣን አንድ እሳቤ በአንድ ሱራህ ላይ ያንጠለጥል እና በሌላ ሱራህ የተቀሩትን እሳቤ ይጨርሰዋል፤ ይህ የቁርኣን አንዱ ውበት ነው፦
39፥23 *አላህ ከዜና ሁሉ መልካምን፣ ተመሳሳይ፣ ተደጋጋሚ የኾነን መጽሐፍ አወረደ*፡፡ اللَّهُ نَزَّلَ أَحْسَنَ الْحَدِيثِ كِتَابًا مُّتَشَابِهًا مَّثَانِيَ تَقْشَعِرُّ

“ሙተሻቢህ” مُتَشَٰبِه ማለትም “ተመሳሳይ” ማለት ሲሆን አንቀጾችን አንዱ ሱራህ ላይ ተናግሮ ሌላ ሱራህ ላይ ተመሳሳዩን የተቀረውን ይናገራል፤ ይህ አላህ ከነቢያችን”ﷺ” በፊት የነበረውን ክስተትና መስተጋብር አንዱ ሱራህ ላይ ተናግሮ ያንጠለጥለው እና እንደገና በሌላ ሱራህ የተቀሩትን መሳ ለመሳ ይደግመዋል። “መሳኒይ” مَّثَانِى ማለት “ተደጋጋሚ” ማለት ነው። ይህንን በተለያዩ ሱራዎች የተለያዩ ናሙናዎችን ማየት እንችላለን፦

ናሙና አንድ
ኢብራሂም ለመላእክቶቹ ያላቸው ሙሉ ንግግሩ፦ “ሰላም ያልታወቃችሁ ሕዝቦች ናችሁ፤ እኛ ከእናንተ ፈሪዎች ነን” ሲሆን አላህ ግን ይህንን የኢብራሂም ንግግር በአንድ ሱራህ ላይ አንጠልጥሎ የተቀረውን በሌላ ሱራህ ላይ ደግሞ ይጨርሰዋል፦
51፥24 *የተከበሩት የኢብራሂም እንግዶች ወሬ መጥቶሃልን?* هَلْ أَتَاكَ حَدِيثُ ضَيْفِ إِبْرَاهِيمَ الْمُكْرَمِينَ
51፥25 በእርሱ ላይ በገቡ እና ሰላም ባሉት ጊዜ አስታውስ፤ እርሱም፦ *«ሰላም ያልታወቃችሁ ሕዝቦች ናችሁ»* አላቸው፡፡ إِذْ دَخَلُوا عَلَيْهِ فَقَالُوا سَلَامًا ۖ قَالَ سَلَامٌ قَوْمٌ مُّنكَرُونَ
15፥51 *ከኢብራሂም እንግዶችም ወሬ ንገራቸው*፡፡ وَنَبِّئْهُمْ عَن ضَيْفِ إِبْرَاهِيمَ
15፥25 በእርሱ ላይ በገቡ እና ሰላም ባሉት ጊዜ የኾነውን አስታውስ፤ እርሱም፦ *«እኛ ከእናንተ ፈሪዎች ነን»* አላቸው፡፡ إِذْ دَخَلُوا عَلَيْهِ فَقَالُوا سَلَامًا قَالَ إِنَّا مِنكُمْ وَجِلُونَ

ናሙና ሁለት
ሙሳ ለጌታው ያለው ሙሉ ንግግሩ፦ “ጌታዬ ሆይ! እኔ ከእነርሱ ነፍስን ገድያለሁ፣ ለእነርሱም በእኔ ላይ የደም ወንጀል አለ” ሲሆን አላህ ግን ይህንን የሙሳን ንግግር በአንድ ሱራህ ላይ አንጠልጥሎ የተቀረውን በሌላ ሱራህ ላይ ደግሞ ይጨርሰዋል፦
28፥33 ሙሳም አለ፦ *«ጌታዬ ሆይ! እኔ ከእነርሱ ነፍስን ገድያለሁ*፤ ስለዚህ እንዳይገድሉኝ እፈራለሁ፡፡ قَالَ رَبِّ إِنِّي قَتَلْتُ مِنْهُمْ نَفْسًا فَأَخَافُ أَن يَقْتُلُون
26፥14 ሙሳም አለ፦ *«ለእነርሱም በእኔ ላይ የደም ወንጀል አለ*፤ ስለዚህ እንዳይገድሉኝ እፈራለሁ። وَلَهُمْ عَلَيَّ ذَنبٌ فَأَخَافُ أَن يَقْتُلُونِ
ናሙና ሦስት
ኑሕ ለጌታው የጸለየው ሙሉ ጸሎት፦ “ጌታዬ ሆይ! ባስተባበሉኝ ምክንያት እርዳኝ፤ ከከሓዲዎቹ በምድር ላይ አንድንም አትተው” ሲሆን አላህ ግን ይህንን የኑሕን ጸሎት በአንድ ሱራህ ላይ አንጠልጥሎ የተቀረውን በሌላ ሱራህ ላይ ደግሞ ይጨርሰዋል፦
23፥26 ኑሕም፦ *«ጌታዬ ሆይ! ባስተባበሉኝ ምክንያት እርዳኝ»* አለ፡፡قَالَ رَبِّ انصُرْنِي بِمَا كَذَّبُونِ
71፥26 ኑሕም፦ *«ጌታዬ ሆይ! ከከሓዲዎቹ በምድር ላይ አንድንም አትተው»* አለ፡፡ وَقَالَ نُوحٌ رَّبِّ لَا تَذَرْ عَلَى الْأَرْضِ مِنَ الْكَافِرِينَ دَيَّارًا

ይህንን ከተረዳን ዘንዳ የሉጥ ሙሉ ንግግር፦ "እናንተ ጠያፍን ስራ ትሠራላችሁን? በእርሷ ከዓለማት አንድም አልቀደማችሁም፡፡ እናንተ በእርግጥ ወንዶችን ትመጣላችሁን መንገድንም ትቆርጣላችሁን በሸንጓችሁም የሚነወርን ነገር ትሠራላችሁን? እናንተ ከሴቶች አልፋችሁ ወንዶችን ለመከጀል ትመጣላችሁን? በእውነቱ እናንተ የምትሳሳቱ ሕዝቦች ናቸሁ" የሚል ነው። አላህ ግን ይህንን የሉጥ ስብከት በአንድ ሱራህ ላይ አንጠልጥሎ የተቀረውን በሌላ ሱራህ ላይ ደግሞ ይጨርሰዋል፦
28፥28 ሉጥንም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ *«እናንተ ጠያፍን ስራ ትሠራላችሁን በእርሷ ከዓለማት አንድም አልቀደማችሁም፡፡ وَلُوطًا إِذْ قَالَ لِقَوْمِهِ إِنَّكُمْ لَتَأْتُونَ الْفَاحِشَةَ مَا سَبَقَكُم بِهَا مِنْ أَحَدٍ مِّنَ الْعَالَمِينَ
29፥28 *«እናንተ በእርግጥ ወንዶችን ትመጣላችሁን መንገድንም ትቆርጣላችሁን በሸንጓችሁም የሚነወርን ነገር ትሠራላችሁን»* አላቸው፡፡ أَئِنَّكُمْ لَتَأْتُونَ الرِّجَالَ وَتَقْطَعُونَ السَّبِيلَ وَتَأْتُونَ فِي نَادِيكُمُ الْمُنكَر
27፥55 *«እናንተ ከሴቶች አልፋችሁ ወንዶችን ለመከጀል ትመጣላችሁን በእውነቱ እናንተ የምትሳሳቱ ሕዝቦች ናቸሁ፡፡»* أَئِنَّكُمْ لَتَأْتُونَ الرِّجَالَ شَهْوَةً مِّن دُونِ النِّسَاءِ ۚ بَلْ أَنتُمْ قَوْمٌ تَجْهَلُونَ

የሕዝቦቹም መልስ፦ "ከእውነተኞቹ እንደ ሆንክ የአላህን ቅጣት አምጣብን። ከከተማችሁ አውጡ፥ እነርሱ የሚጥራሩ ሰዎች ናቸውና" ማለት እንጂ ሌላ አልነበረም፡፡ አላህ ግን ይህንን የሕዝቦቹም መልስ በአንድ ሱራህ ላይ አንጠልጥሎ የተቀረውን በሌላ ሱራህ ላይ ደግሞ ይጨርሰዋል፦
29፥29 የሕዝቦቹም መልስ *«ከእውነተኞቹ እንደ ሆንክ የአላህን ቅጣት አምጣብን»* ማለት እንጂ ሌላ አልነበረም፡፡ فَمَا كَانَ جَوَابَ قَوْمِهِ إِلَّا أَن قَالُوا ائْتِنَا بِعَذَابِ اللَّهِ إِن كُنتَ مِنَ الصَّادِقِينَ
27፥56 የሕዝቦቹም መልስ *«ከከተማችሁ አውጡ፡፡ እነርሱ የሚጥራሩ ሰዎች ናቸውና»* ማለት እንጅ ሌላ አልነበረም፡፡ فَمَا كَانَ جَوَابَ قَوْمِهِ إِلَّا أَن قَالُوا أَخْرِجُوا آلَ لُوطٍ مِّن قَرْيَتِكُمْ ۖ إِنَّهُمْ أُنَاسٌ يَتَطَهَّرُونَ

እንዲህ አይነት የአላህ አተራረክ ብዙ ቦታ አለ። ደርዝና ፈርጅ ባለው መልኩ ብዙ ናሙናዎችን ማቅረብ ይቻል ነበር። ግን ለአንባቢ ጊዜን እንዲሁ ለንባብ ደግሞ ቦታ ማጣበብ ይሆናል፥ ቅሉ ግን በወፍ በረር ለቅምሻ ያክል ይህ በቂ ነው። ከላይ ባሉት ናሙናዎች ሌሎችንም ትረካ ስታገኙ በዚህ ስሌት መረዳት ነው። ይህ አይነት አፈሳሰር "የተዛማች ሙግት”textual approach” ይባላል። ይህ የአተራረክ ስልት እንዲገባችሁ ከባይብል አንድ ናሙና ላቅርብ፦
ማቴዎስ 20፥20-21  በዚያን ጊዜ *"የዘብዴዎስ ልጆች እናት ከልጆችዋ ጋር እየሰገደችና አንድ ነገር እየለመነች ወደ እርሱ ቀረበች። እርሱም፦ ምን ትፈልጊያለሽ? አላት። እርስዋም፦ እነዚህ ሁለቱ ልጆቼ አንዱ በቀኝህ አንዱም በግራህ በመንግሥትህ እንዲቀመጡ እዘዝ አለችው"*።

እዚህ ትረካ ላይ የያዕቆብና የዮሐንስ እናትን ኢየሱስ፦ "ምን ትፈልጊያለሽ" ሲላት እና እርሷም፦ "ሁለቱ ልጆቼ አንዱ በቀኝህ አንዱም በግራህ በመንግሥትህ እንዲቀመጡ እዘዝ" እንዳለችው ይናገራል። ነገር ግን በሌላ ትረካ ላይ ይህ እራሱ ታሪክ ላይ እናትየው ሳትሆን ልጆቿን ኢየሱስ፦ "ምን ላደርግላችሁ ትወዳላችሁ" እንዳላቸው እና እነርሱም፦ "በክብርህ ጊዜ አንዳችን በቀኝ አንዳችንም በግራህ መቀመጥን ስጠን" እንዳሉት ይናገራል፦
ማርቆስ 10፥35-37  *"የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብና ዮሐንስም ወደ እርሱ ቀርበው፦ መምህር ሆይ፥ የምንለምንህን ሁሉ እንድታደርግልን እንወዳለን አሉት። እርሱም፦ ምን ላደርግላችሁ ትወዳላችሁ? አላቸው። እነርሱም፦ በክብርህ ጊዜ አንዳችን በቀኝ አንዳችንም በግራህ መቀመጥን ስጠን አሉት"*።

በአንድ ጊዜና ክስተት ውስጥ ያለ አንድ ታሪክ ግን የተለያየ አተራረክ ነው። ኢየሱስ በትክክል ያለው የትኛውን ነው? "ምን ትፈልጊያለሽ" ወይስ "ምን ላደርግላችሁ ትወዳላችሁ"? ለማኙስ ማን ነው? የዘብዴዎስ ሚስት ወይስ ልጆች? የተጠየቀውስ "እነዚህ ሁለቱ ልጆቼ አንዱ በቀኝህ አንዱም በግራህ በመንግሥትህ እንዲቀመጡ እዘዝ" ወይስ "በክብርህ ጊዜ አንዳችን በቀኝ አንዳችንም በግራህ መቀመጥን ስጠን"?

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር አምሳ አራት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 54
የሙሴን እጅ መንጣት በተመለከተ አላህ ምን አለው?

ዘገባ አንድ፡- 
20፡22 “እጅህንም ወደ ብብትህ አግባ፣ ሌላ ታምር ስትሆን ያለ ነውር ነጭ ሆና ትወጣለችና።”

ዘገባ ሁለት፡- 
27፡12 “እጅህንም በአንገትጌህ ውስጥ አግባ፤ ያለነውር ነጭ ሆና ትወጣለችና…”

መልስ
አምላካችን አላህ ከነቢያችን"ﷺ" በፊት የነበረውን ክስተት ፦“ነቁሱ ዐለይከ” نَقُصُّ عَلَيْكَ ማለትም “እንተርክልሃለን” በማለት ለነቢያችን”ﷺ” ይተርካል። ይህ ክስተት ሲከሰት ነቢያችን”ﷺ” አልነበሩም፤ ነገር ግን አምላካችን አላህ ተፈላጊውን የሩቅ ወሬ የአእምሮ ባለቤቶችም እንዲገሰጹ ተርኮልናል። “ወሬ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ነበእ” نَبَإِ ሲሆን “ነቢይ” نبي የሚለው ቃል የመጣበት ሥርወ-ቃል ነው፥ ለነቢያችን”ﷺ” መተረኩ ለምእምናን ግሳጼ እና ማስታወሻ ነው፦
11፥120 *ከመልክተኞቹም ወሬዎች* ተፈላጊውን ሁሉንም ልብህን በእርሱ የምናረካበትን “*እንተርክልሃለን*፤ በዚህችም እውነቱ ነገር *ለምእምናን ግሳጼ እና ማስታወሻ* መጥቶልሃል፡፡ وَكُلًّۭا نَّقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنۢبَآءِ ٱلرُّسُلِ مَا نُثَبِّتُ بِهِۦ فُؤَادَكَ ۚ وَجَآءَكَ فِى هَٰذِهِ ٱلْحَقُّ وَمَوْعِظَةٌۭ وَذِكْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ

አምላካችን አላህ ለሙሳ፦ "እጅህንም ወደ ብብትህ አግባ" ብሎት እንደነበር ይናገራል፦
20፥22 *«እጅህንም ወደ ብብትህ አግባ*፡፡ ሌላ ተዓምር ስትኾን ያለነውር ነጭ ኾና ትወጣለችና፡፡ وَاضْمُمْ يَدَكَ إِلَىٰ جَنَاحِكَ تَخْرُجْ بَيْضَاءَ مِنْ غَيْرِ سُوءٍ آيَةً أُخْرَىٰ

"ጀናሕ" جَنَاح ማለት "ብብት" ማለት ነው፥ "ጀናሒከ" جَنَاحِكَ ማለትም "ብብትክ" ማለት ነው። "ጀናሒከ" جَنَاحِكَ የሚለው ቃል በሌላው ትረካው ላይ "ጀይቢከ" جَيْبِكَ ማለትም "ጉያህ" በሚል መጥቷል፤ "ጀይብ" جَيْب ማለት "ጉያ" "እቅፍ" ማለት ነው፦
27፥12 *«እጅህንም በጉያህ"bosom" ውስጥ አግባ፡፡ ያለነውር ያለ ለምጽ ነጭ ኾና ትወጣለችና"*፡፡ وَأَدْخِلْ يَدَكَ فِي جَيْبِكَ تَخْرُجْ بَيْضَاءَ مِنْ غَيْرِ سُوءٍ ۖ فِي تِسْعِ آيَاتٍ إِلَىٰ فِرْعَوْنَ وَقَوْمِهِ ۚ إِنَّهُمْ كَانُوا قَوْمًا فَاسِقِينَ
28፥32 *«እጅህን በጉያህ"bosom" ውስጥ አግባ፡፡ ያለ ነውር ነጭ ሆና ትወጣለችና*፡፡ اسْلُكْ يَدَكَ فِي جَيْبِكَ تَخْرُجْ بَيْضَاءَ مِنْ غَيْرِ سُوءٍ وَاضْمُمْ إِلَيْكَ جَنَاحَكَ مِنَ الرَّهْبِ ۖ فَذَانِكَ بُرْهَانَانِ مِن رَّبِّكَ إِلَىٰ فِرْعَوْنَ وَمَلَئِهِ ۚ إِنَّهُمْ كَانُوا قَوْمًا فَاسِقِينَ

"አንገትጌ" የድሮ ዐማርኛ ላይ "ጉያ" ለማለት ተፈልጎ እንጂ "አንገት" ለማለት ተፈልጎ አይደለም። "አንገት" በዐረቢኛ "ዑኑቅ" عُنُق ነው፦
17፥29 *"እጅህንም ወደ አንገትህ የታሰረች አታድርግ"*፡፡ መዘርጋትንም ሁሉ አትዘርጋት፤ የተወቀስክ የተቆጨኽ ትኾናለህና፡፡ وَلَا تَجْعَلْ يَدَكَ مَغْلُولَةً إِلَىٰ عُنُقِكَ وَلَا تَبْسُطْهَا كُلَّ الْبَسْطِ فَتَقْعُدَ مَلُومًا مَّحْسُورًا

መቼም "እቅፍ" ወይም "ጉያ" ብብት ውስጥ እንጂ አንገት ውስጥ እንዳልሆነ እሙንና ቅቡል ነው።
መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር አምሳ አምስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 55
ከሚከተሉት ውስጥ መሐመድ"ﷺ" የትኛውን ነው?

አስፈራሪ ብቻ፡-
11፡12 “አንተ አስፈራሪ ብቻ ነህ”

አብሳሪና አስፈራሪ ብቻ፡- 
34፡28 “አንተንም ለሰዎች ሁሉ በመላ፣ አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን ቢሆን እንጂ አልላክንህም፤ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም።”

መስካሪ አብሳሪና አስፈራሪ፡- 
33፡45 “አንተ ነቢዩ ሆይ! እኛ መስካሪ አብሳሪና አስፈራሪም አድርገን ላክንህ።”

መልስ
11፥12 *በእርሱ ላይ የገንዘብ ድልብ ለምን አልተወረደም ወይም ከእርሱ ጋር መልአክ ለምን አልመጣም? ማለታቸውንም በመፍራት ወደ አንተ ከሚወርደው ከፊሉን ልትተው በእርሱም ልብህ ጠባብ ሊኾን ይፈራልሃል፡፡ አንተ አስጠንቃቂ ብቻ ነህ"*፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ተጠባባቂ ነው፡፡ فَلَعَلَّكَ تَارِكٌ بَعْضَ مَا يُوحَىٰ إِلَيْكَ وَضَائِقٌ بِهِ صَدْرُكَ أَن يَقُولُوا لَوْلَا أُنزِلَ عَلَيْهِ كَنزٌ أَوْ جَاءَ مَعَهُ مَلَكٌ ۚ إِنَّمَا أَنتَ نَذِيرٌ ۚ وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ

እዚህ ዐውደ-ንባብ ላይ ዐረቦች፦ "በእርሱ ላይ የገንዘብ ድልብ ለምን አልተወረደም ወይም ከእርሱ ጋር መልአክ ለምን አልመጣም" ብለው አሉ፥ የገንዘብ ድልብ ማውረድም ወይም መልአክን መላክ የሚችለው አላህ ብቻ ነው። ነቢያችን"ﷺ" ይህንን አድራጊ ሳይሆኑ "አስጠንቃቂ" ብቻ ናቸው፦
17፥93 *«ወይም ከወርቅ የኾነ ቤት አንተ እስከሚኖርህ፤ ወይም በሰማይ እስከምትወጣ፤ ለመውጣትህም በእኛ ላይ የምናነበው የኾነን መጽሐፍ እስከምታወርድልን ድረስ ፈጽሞ አናምንልህም» አሉ፡፡ «ጌታዬ ጥራት ይገባው፤ እኔ ሰው የሆነ መልክተኛ እንጂ ሌላ አይደለሁም» በላቸው*"፡፡ أَوْ يَكُونَ لَكَ بَيْتٌ مِّن زُخْرُفٍ أَوْ تَرْقَىٰ فِي السَّمَاءِ وَلَن نُّؤْمِنَ لِرُقِيِّكَ حَتَّىٰ تُنَزِّلَ عَلَيْنَا كِتَابًا نَّقْرَؤُهُ ۗ قُلْ سُبْحَانَ رَبِّي هَلْ كُنتُ إِلَّا بَشَرًا رَّسُولًا
18፥110 «እኔ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ማለት ወደ እኔ የሚወረድልኝ *”ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ”*፡፡ የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፤ መልካም ሥራን ይሥራ፡፡ በጌታውም መገዛት አንድንም አያጋራ» *”በላቸው”* قُلْ إِنَّمَآ أَنَا۠ بَشَرٌۭ مِّثْلُكُمْ يُوحَىٰٓ إِلَىَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَمَن كَانَ يَرْجُوا۟ لِقَآءَ رَبِّهِۦ فَلْيَعْمَلْ عَمَلًۭا صَٰلِحًۭا وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِۦٓ أَحَدًۢا

"በእኛ ላይ የምናነበው የኾነን መጽሐፍ እስከምታወርድልን ድረስ ፈጽሞ አናምንልህም" ማለታቸው ትክክል አይደለም። ይህንን ማድረግ የሚችለው አላህ ብቻ ነው። እርሳቸው "ሰው ብቻ ናቸው"። "ብቻ" ብሎ የገባው ገላጭ ቅጽል "ኢነማ" إِنَّمَا ሲሆን ብዙ ቦታ በአንጻራዊት ደረጃ የሚገባበት ጊዜ አለ፥ ለምሳሌ፦
64፥15 *"ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁ ለእናንተ መፈተኛ ብቻ ናቸው"*፤ አላህም እርሱ ዘንድ ታላቅ ምንዳ አልለ፡፡ إِنَّمَآ أَمْوَٰلُكُمْ وَأَوْلَٰدُكُمْ فِتْنَةٌۭ ۚ وَٱللَّهُ عِندَهُۥٓ أَجْرٌ عَظِيمٌۭ

"ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁ ለእናንተ መፈተኛ ብቻ ናቸው" ናቸው ማለት ከፈተና ሌላ መደሰቻ አይደሉም ማለት እንዳልሆነ ሁሉ "ሰው ብቻ ነኝ" "አስጠንቃቂ ብቻ ነኝ" ማለት አምላክ አይደለሁም ለማለት ተፈልጎ እንጂ አብሳሪና መስካሪ አይደሉም ለማለት ተፈልጎ አይደለም። ዐረቦቹ በወቅቱ፦ "አላህ ሰውን መልክተኛ አድርጎ ላከን? በእኛ ላይ ለምን መላእክት አልወረደም? ብለው ጠይቀው ነበር፦
17፥94 *ሰዎችንም መሪ በመጣላቸው ጊዜ ከማመን «አላህ ሰውን መልክተኛ አድርጎ ላከን?» ማለታቸው እንጂ ሌላ አልከለከላቸውም"*፡፡ وَمَا مَنَعَ النَّاسَ أَن يُؤْمِنُوا إِذْ جَاءَهُمُ الْهُدَىٰ إِلَّا أَن قَالُوا أَبَعَثَ اللَّهُ بَشَرًا رَّسُولًا
25፥21 እነዚያም መገናኘታችንን የማይፈሩት፦ *"በእኛ ላይ ለምን መላእክት አልወረደም፡፡ ወይም ጌታችንን ለምን አናይም አሉ”*፤ በነፍሶቻቸው ውስጥ በእርግጥ ኮሩ፡፡ ታላቅንም አመጽ አመፁ፡፡ وَقَالَ ٱلَّذِينَ لَا يَرْجُونَ لِقَآءَنَا لَوْلَآ أُنزِلَ عَلَيْنَا ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ أَوْ نَرَىٰ رَبَّنَا ۗ لَقَدِ ٱسْتَكْبَرُوا۟ فِىٓ أَنفُسِهِمْ وَعَتَوْ عُتُوًّۭا كَبِيرًۭا

ለዚያ ነው አላህ፦ "ለእናንተም እኔ መልአክ ነኝ አልልም" በላቸው" ብሎ መልስ የሰጠው፦
6፥50 «ለእናንተ የአላህ ግምጃ ቤቶች እኔ ዘንድ ናቸው አልልም፡፡ ሩቅንም አላውቅም፡፡ *”ለእናንተም እኔ መልአክ ነኝ አልልም”*፡፡ ወደ እኔ *”የሚወርድልኝን”* እንጅ ሌላን አልከተልም» በላቸው قُل لَّآ أَقُولُ لَكُمْ عِندِى خَزَآئِنُ ٱللَّهِ وَلَآ أَعْلَمُ ٱلْغَيْبَ وَلَآ أَقُولُ لَكُمْ إِنِّى مَلَكٌ ۖ إِنْ أَتَّبِعُ إِلَّا مَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ

ስለዚህ የመልአክ መልእክተኛ ካልመጣ ብለው ሲሟገቱ እኔ አምጪ ሳልሆን አስጠንቃቂ ብቻ ነኝ፥ ይህ የአላህ ድርሻ ነው፥ እኔ ሰው ብቻ ነኝ ብለው መልስ ሰጡ እንጂ አብሳሪ እና መስካሪ አለመሆናቸውን በፍጹም አያሳይም። "ብቻ" የሚለው ገላጭ ቅጽል በአንጻራዊነት የመጣ ነው። ነቢያችን"ﷺ" በእርግጥም አስጠንቃቂ፣ አብሳሪ እና መስካሪም ናቸው፦
33፥45 *"አንተ ነቢዩ ሆይ! እኛ መስካሪ፣ አብሳሪ እና አስጠንቃቂም አድርገን ላክንህ"*፡፡ يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ إِنَّا أَرْسَلْنَاكَ شَاهِدًا وَمُبَشِّرًا وَنَذِيرًا

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር አምሳ ስድስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 56
የጀነት ስፋት እንደማን ነው?

እንደ ሰማይ እና ምድር፦
57:21 ከጌታችሁ ወደ ሆነች ምሕረት ወርዷ እንደ ሰማይ እና ምድር ወርድ ወደ ሆነችም ገነት ተሽቀዳደሙ፤

እንደ ሰማያት እና ምድር፦
3:133 ከጌታችሁ ወደ ኾነችም ምሕረትና ስፋትዋ እንደ ሰማያት እና ምድር ወደ ሆነች ገነት፥ አላህን ለሚፈሩ የተዘጋጀች ስትሆን ተቻኮሉ።

መልስ
አምላካችን አላህ ምድርን ፈጥሮ በምድር ያለውን ፈጠረ ከዚያም ወደ ሰማይ አሰበ፤ ሰባት ሰማያትም አደረጋቸው፦
2፥29 *”እርሱ ያ በምድር ያለውን ሁሉ ለእናንተ የፈጠረ ነው፡፡ ከዚያም ወደ ሰማይ አሰበ፤ ሰባት ሰማያትም አደረጋቸው”*፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ هُوَ الَّذِي خَلَقَ لَكُم مَّا فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا ثُمَّ اسْتَوَىٰ إِلَى السَّمَاءِ فَسَوَّاهُنَّ سَبْعَ سَمَاوَاتٍ ۚ وَهُوَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

እዚህ አንቀጽ ላይ፦“ወደ ሰማይ አሰበ” የሚል ሃይለ-ቃል አለ፤ “ኢላ”إِلَى ማለትም “ወደ” የሚለው መስተዋድድ መግባቱ በራሱ ሰማይ እንደነበረች ያሳያል። “ወደ” ፒያሳ አስቤአለው ማለት ፒያሳን ፈጠርኳት ማለት አይደለም፤ ፒያሳ ሳትኖር ወደ ፒያሳ ማቅናት አይቻልም። ሰማይ በህልውና ጭስ ኾና ሳለች አሰበ፦
41፥11 *”ከዚያም ወደ ሰማይ እርሷ ጭስ ኾና ሳለች አሰበ፡፡ ለእርሷም ለምድርም «ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ» አላቸው”*፡፡ «ታዛዦች ኾነን መጣን» አሉ፡፡ ثُمَّ اسْتَوَىٰ إِلَى السَّمَاءِ وَهِيَ دُخَانٌ فَقَالَ لَهَا وَلِلْأَرْضِ ائْتِيَا طَوْعًا أَوْ كَرْهًا قَالَتَا أَتَيْنَا طَائِعِينَ

“ሳለች” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ ለሰማይም ለምድርም፦ ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ” ማለቱ በራሱ ሰማይ እንደነበረች መረዳት ይቻላል። ከዚያም በጭስ ደረጃ የነበረችውን ሰማይ ሰባት ሰማያት አደረጋቸው፦
41፥12 በሁለት ቀኖችም ውስጥ *”ሰባት ሰማያት አደረጋቸው”*፡፡ فَقَضَاهُنَّ سَبْعَ سَمَاوَاتٍ فِي يَوْمَيْنِ
2፥29 እርሱ ያ በምድር ያለውን ሁሉ ለእናንተ የፈጠረ ነው፡፡ ከዚያም ወደ ሰማይ አሰበ፤ *”ሰባት ሰማያትም አደረጋቸው”*፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ هُوَ الَّذِي خَلَقَ لَكُم مَّا فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا ثُمَّ اسْتَوَىٰ إِلَى السَّمَاءِ فَسَوَّاهُنَّ سَبْعَ سَمَاوَاتٍ ۚ وَهُوَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

ከዚያ በኃላ "ሠማእ" سَمَآء ማለትም "ሰማይ" ጥቅላዊ አነጋገር ሲሆን "ሠማዋት" سَّمَاوَات ማለትም "ሰማያት" ደግሞ ተናጥሎአዊ አነጋገር ነው። "አደረጋቸው" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ሠዋሁነ" سَوَّاهُنَّ ሲሆን በመድረሻው ቅጥያ ላይ "ሁነ" هُنَّ ማለትም "እነርሱ" የሚል የብዜት አንስታይ ተውላጠ ስም አለ፥ ይህ አንስታይ ተውላጠ ስም በነጠላ "ሂየ" هِيَ የተባለችው በጭስ"gas" ደረጃ የነበረችው ሰማይ ሰባት ሰማያት ሆና ነው። አላህ ሰማይን ሰባት ብርቱዎች ሰማያት አድርጎ ገነባት፦
51፥47 *"ሰማይንም በኀይል ገነባናት"*፡፡ እኛም በእርግጥ ቻዮች ነን፡፡ وَالسَّمَاءَ بَنَيْنَاهَا بِأَيْدٍ وَإِنَّا لَمُوسِعُونَ
78፥12 *"ከበላያችሁም ሰባትን ብርቱዎች ገነባን"*፡፡ وَبَنَيْنَا فَوْقَكُمْ سَبْعًا شِدَادًا

እዚህ ድረስ ከተግባባን በቁርኣን ሰማይ የሚለው ቃል ሰማያት ለሚለው ቃል ተለዋዋጭ ሆኖ መጥቷል ማለት ነው፦
3፥133 ከጌታችሁ ወደ ኾነችም ምሕረት፥ *"ስፋትዋ እንደ ሰማያት እና ምድር ወደ ኾነች ገነት"* አላህን ለሚፈሩ የተዘጋጀች ስትኾን ተቻኮሉ፡፡ وَسَارِعُوا إِلَىٰ مَغْفِرَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ وَجَنَّةٍ عَرْضُهَا السَّمَاوَاتُ وَالْأَرْضُ أُعِدَّتْ لِلْمُتَّقِين
57፥21 ከጌታችሁ ወደ ኾነች ምሕረት፥ *"ስፋቷ እደ ሰማይና ምድር ወርድ ወደ ሆነችም ገነት"* ተሽቀዳደሙ፡፡ ለእነዚያ በአላህና በመልክተኞቹ ላመኑት ተዘጋጅታለች፡፡ سَابِقُوا إِلَىٰ مَغْفِرَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ وَجَنَّةٍ عَرْضُهَا كَعَرْضِ السَّمَاءِ وَالْأَرْضِ أُعِدَّتْ لِلَّذِينَ آمَنُوا بِاللَّهِ وَرُسُلِهِ

ሰማይ የሚለው ቃል ለሰባቱ ሰማይ ጥቅላዊ መጠሪያ ሆና መምጣት የተለመደ አገላለጽ ነው፦
44፥38 *"ሰማያትን እና ምድርንም በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ ቀላጆች ኾነን አልፈጠርንም"*፡፡ وَمَا خَلَقْنَا السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا لَاعِبِينَ
21፥16 *"ሰማይን እና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ ቀላጆች ኾነን አልፈጠርንም"*፡፡ وَمَا خَلَقْنَا السَّمَاءَ وَالْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا لَاعِبِينَ

ሰማይ ለሰማያት ጥቅላዊ ንግግር ሆኖ እንደመጣ ልብ በል። የትንሳኤ ቀን ሰማያት የሚጠቀለሉ ቢሆንም ሰማይ እንደምትጠቀለል በጥቅሉ ተነግሯል፦
39፥67 *"አላህንም በትንሣኤ ቀን ምድር በመላ ጭብጡ ስትኾን፤ ሰማያትም በኀይሉ የሚጠቀለሉ ሲኾኑ ተገቢ ክብሩን አላከበሩትም"*፡፡ ከሚያጋሩት ጠራ፤ ላቀም፡፡ وَمَا قَدَرُوا اللَّهَ حَقَّ قَدْرِهِ وَالْأَرْضُ جَمِيعًا قَبْضَتُهُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ وَالسَّمَاوَاتُ مَطْوِيَّاتٌ بِيَمِينِهِ ۚ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَىٰ عَمَّا يُشْرِكُونَ
21፥104 *"ለመጽሐፎች የኾኑ ገጾች እንደሚጠቀለሉ "ሰማይን" የምንጠቀልልበትን ቀን አስታውስ"*፡፡ يَوْمَ نَطْوِي السَّمَاءَ كَطَيِّ السِّجِلِّ لِلْكُتُبِ

ነጠላ ቃል ለብዜት ቃል አገልግሎት ላይ እንደሚውል ከራሳችሁ ባይብል በአንድ ናሙና ልሞግት፥ ለምሳሌ "ቀን" የሚለው ነጠላ ቃላት ለብዙ ቀናት ቃሉ አገልግሎት ላይ ውሏል፦
ዘጸአት 31፥17 እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን *"በስድስት "ቀን" ስለ ፈጠረ"*፥
ዘፍጥረት 2፥4 እግዚአብሔር አምላክ፥ ሰማይንና ምድርን ባደረገ *"ቀን"* ፥ በተፈጠሩ ጊዜ፥ የሰማይና የምድር ልደት ይህ ነው።

ስድስት ተብሎ "ቀን" አይባልም፣ ባይሆን "ቀናት" እንጂ፣ ነገር ግን ባይብል የተጠቀመበት ቃል ነጠላ ሲሆን "ዮውም" י֔וֹם ማለትም "ቀን" እንጂ "ያሚም" לְיָמִ֖ים ማለትም "ቀናት" አይደለም፣ አይ "ዮውም" የሚለው "ያሚም" የሚለውን ጠቅልሎ ይይዛል ከተባለ እንግዲያውስ የቁርኣኑን አናቅጽ በዚህ ሒሳብ ተረዱት።

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም