ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
69 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ነፍስ

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

75፥2 *ራሷን ወቃሽ በኾነች ነፍስም እምላለሁ*፡፡ በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ፡፡ وَلَا أُقْسِمُ بِالنَّفْسِ اللَّوَّامَةِ

"ነፍስ" ማለት እንደ አማርኛ የቋንቋ ምሁራን "ልባዊት" ማለትም "ዕውቀት"፣ "ነባቢት" ማለትም "ንግግር"፣ "ህያዊት" ማለትም "ሕይወት" ነው ይሉታል።
የግሪክ ኮይኔ ምሁራን "ፕስሂ" ψυχή ማለት "ናኡስ" ˈnaʊs ማለትም "ዕውቀት"፣ "ቱሞስ" θυμός ማለትም "ስሜት" ለምሳሌ፦ መውደድ፣ መጥላት፣ ማዘን፣ መደሰት፣ መቆጣት እና መታገስ ወዘተ... እና "ኤሮስ" ἔρως "ፍላጎት" ወይም "ፈቃድ" ነው።
የዕብራይስጥ ምሁራን "ነፈሽ" נפש ማለት "ግላዊነት" ወይም "ራስነት" መሆንን ያመለክታል፤ ይህ ቃል በብሉይ ኪዳን 754 ጊዜ የተጠቀሰ ሲሆን "መንፈስን" "እስትንፋስን" ህይወትን" "ተክለ-ሰውነትን"body" "ማንነትን"person" "ልብን" "አዕምሮን" ወዘተ ለማመልከት አገልግሎት ላይ ውሏል።

እዚህ ድረስ ከተግባባን ፈጣሪ የራሱን ማንነትን እና ስሜቱን ለመግለፅ "ነፍሴ" የሚል አገናዛቢ ተውላጠ ስም ይጠቀማል፤ ይደሰታል ይጠላል፦
ኤርምያስ 12፥7 ቤቴን ትቼአለሁ ርስቴንም ጥያለሁ፥ *"ነፍሴም" የምትወድዳትን* በጠላቶችዋ እጅ አሳልፌ ሰጥቻለሁ።
ዘሌዋውያን 26፥11 ማደሪያዬንም በእናንተ መካከል አደርጋለሁ፤ *"ነፍሴም" አትጸየፋችሁም*።
ዘሌዋውያን 26፥30 *"ነፍሴም" ትጸየፋችኋለች*።
ኢሳይያስ 1፥14 መባቻችሁንና በዓላቶቻችሁን *"ነፍሴ" ጠልታለች*
ኢሳይያስ 42፥1 እነሆ ደግፌ የያዝሁት ባሪያዬ፤ *"ነፍሴ" ደስ የተሰኘችበት ምርጤ*፤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ፥
ኤርምያስ 5፥9 በውኑ ስለ እነዚህ ነገሮች አልቀሥፍምን? ይላል እግዚአብሔር፤ *"ነፍሴስ" እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን*?
ኤርምያስ 5፥29 በውኑ ስለ እነዚህ ነገሮች አልቀሥፍምን? ይላል እግዚአብሔር *"ነፍሴስ" እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን*?
ኤርምያስ 9፥9 በውኑ ስለዚህ ነገር አልቀሥፍምን? ይላል እግዚአብሔር፤ *ነፍሴስ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን*?
ኤርምያስ 6፥8 ኢየሩሳሌም ሆይ፥ *"ነፍሴ" ከአንቺ እንዳትለይ*፥ አንቺንም ባድማና ወና እንዳላደርግሽ፥ ተግሣጽን ተቀበዪ።
ሕዝቅኤል 23፥18 ግልሙትናዋንም ገለጠች ኅፍረተ ሥጋዋንም አሳየች፤ *"ነፍሴም" ከእኅትዋ እንደ ተለየች እንዲሁ "ነፍሴ" ከእርስዋ ተለየች*።

ለሰው "ነፍስ" የሚለው ቃል "መንፈስ" ለሚለው ቃል ተለዋዋጭ ሆኖ መጥቷል፦
ማቴዎስ 10፥28 *"አካልንም" σῶμα የሚገድሉትን "ነፍስን" ψυχή ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም አካልንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ*።

በብሉይ ግሪክ ሰፕቱጀንት እና በአዲስ ግሪክ ኮይኔ ውስጥ “ሶማ” σῶμα ማለት “አካል” ማለት ሲሆን እዚህ ዐውድ ላይ "ነፍስ" የአካል ተቃራኒ እና የመንፈስ ተለዋዋጭ ቃል ሆኖ መጥቷል ማለት ነው፦
ያዕቆብ 2፥26 *"ከመንፈስ" πνεῦμα የተለየ "አካል" σῶμα የሞተ እንደ ሆነ* እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው።

መንፈስ ከአካል ሲለይ አካል ይሞታል፤ "ከመንፈስ የተለየ አካል የሞተ ነው" የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ "አካል" ደግሞ "ስጋን" ለማመልከት ነው የገባው፦
1 ቆሮንቶስ 7፥34 ያልተጋባች ሴትና ድንግል *"በአካል" σώματι እና "በመንፈስ" πνεύματι እንዲቀደሱ የጌታን ነገር ያስባሉ*፤
2 ቆሮንቶስ 7፥1 እንግዲህ፥ ወዳጆች ሆይ፥ የዚህ ተስፋ ቃል ካለን፥ በእግዚአብሔር ፍርሃት ቅድስናን ፍጹም እያደረግን *"ሥጋን" σαρκὸς እና "መንፈስን" πνεύματος ከሚያረክስ ሁሉ ራሳችንን እናንጻ*።

በብሉይ ግሪክ ሰፕቱጀንት እና በአዲስ ግሪክ ኮይኔ ውስጥ “ኑማ” πνεῦμα የሚለው ቃል "መንፈስ" ማለት ነው፤ ይህ የሰው መንፈስ ከፈጣሪ እፍ በማለት የተሰጠ እና የተፈጠረ ነው፦
ዘፍጥረት 2፥7 በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን* እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ሆነ።
ዘካርያስ 12፥1 *የሰውንም መንፈስ በውስጡ የሠራ* እግዚአብሔር እንዲህ ይላል።

"የሰራ" የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ የሰው መንፈስ የተሰራ ነገር ሆኖ በሰው ውስጥ የሚኖር ረቂቅ እና ምጡቅ ነገር ነው። ሰው ውጫዊ ተፈጥሮ ማለትም አካል እንዳለው ሁሉ ውሳጣዊ ተፈጥሮ "መንፈስ" አለው፤ በሰው ውስጥ ሰው የራሱ መንፈስ አለው፦
ኢዮብ 32፥8 *ነገር ግን በሰው ውስጥ መንፈስ አለ*።
1 ቆሮንቶስ 2፥11 *በእርሱ ውስጥ ካለው ከሰው መንፈስ* በቀር ለሰው ያለውን የሚያውቅ ሰው ማን ነው?

"ሰው" የሚለው ቃል ለሁለቱም ማለትም ለአካልም ለመንፈስም ይውላል፤ ሁለቱም ሰው ተብለዋል፦
2 ቆሮንቶስ 4፥16 ስለዚህም አንታክትም፥ ነገር ግን *የውጭው ሰውነታችን ἄνθρωπος ቢጠፋ እንኳ የውስጡ ሰውነታችን* ἄνθρωπος ዕለት ዕለት ይታደሳል።

"የውጪ ሰውነት" አካል ሲሆን "የውስጥ ሰውነት" መንፈስ ነው፤ "ሰውነት" ተብሎ የተተረጎመው ቃል "አንትሮፖስ" ἄνθρωπος ሲሆን "ሰው" ማለት ነው፤ ስለ ሰው የሚያጠናው ምርምር "አትንሮፓሎጅይ"Anthropology" ቃሉ የተወሰደው "አንትሮፖስ" ἄνθρωπος ከሚለው ግሪክ ኮይኔ ነው። የሚታየው አካል ለጊዜው ነው ይፈራርሳል፤ የማይታየው መንፈስ ግን ለዘላለም ነው፦
2 ቆሮንቶስ 4፥18 *የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው*።
“ሩዋሕ” רוּחַ‎ የሚለው የዕብራይስጥ ቃል "መንፈስ" ማለት ሲሆን ይህ መንፈስ አካል ሕያው የሚሆንበት ነገር ነው፤ ይህ ሩዋሕ ወደ ፈጣሪ ሲመለስ ስጋ ወደ አፈር ይመለሳል፦
መክብብ 12፥7 *አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ፥ “መንፈስም” ר֫וּחַ ወደ "ሰጠው" ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ*። NIV
መዝሙር 104፥29 *"መንፈሳቸውን" רוּחַ‎ ታወጣለህ ይሞታሉም፥ ወደ አፈራቸውም ይመለሳሉ*። NIV
ኢዮብ 34፥14 እርሱ ልቡን ወደ ራሱ ቢመልስ፥ *"መንፈሱን" רוּחַ‎ እና እስትንፋሱን ወደ ራሱ ቢሰበስብ፥ ሥጋ ለባሽ ሁሉ በአንድነት ይጠፋል፥ ሰውም ወደ አፈር ይመለሳል*።

ለሰው የሰጠውን መንፈስ ወደራሱ በማስጠጋት "መንፈሱ" ይላል፤ ይህ የሰው መንፈስ የእግዚአብሔር መብራት ነው፤ መንፈሶች ሁሉ የእርሱ ናቸው፦
ምሳሌ 20፥27 *የሰው መንፈስ የእግዚአብሔር መብራት ነው* የሆዱን ጕርጆች ሁሉ የሚመረምር።
ሕዝቅኤል 18፥4 *እነሆ፥ ነፍሳት ሁሉ የእኔ ናቸው፤ የአባት ነፍስ የእኔ እንደ ሆነች ደግሞ የልጅ ነፍስ የእኔ ናት*፤

ይህንን ሩዋሕ የሚወስዱት መላእክት ናቸው፦
ሉቃስ 16፥22 *ድሀውም ሞተ፥ መላእክትም ወደ አብርሃም እቅፍ ወሰዱት*፤ ባለ ጠጋው ደግሞ ሞተና ተቀበረ።
ሉቃስ 12፥20 እግዚአብሔር ግን፦ አንተ ሰነፍ፥ በዚች ሌሊት *ነፍስህን ከአንተ ሊወስዱአት ይፈልጓታል*፤ ይህስ የሰበሰብኸው ለማን ይሆናል? አለው።

"ነፍስ" የሚለው ቃል ማንነትን ያሳያል፤ ለምሳሌ አንድ ሰው ሌላን ማንነት ሲገድል "ነፍሰ ገዳይ" ይባላል፤ ነፍስም ትገደላለች፣ ትሞታለች፣ ትጠፋለች፦
ዘኁልቊ 35፥11 *በስሕተት "ነፍስ" נֶ֖פֶשׁ የገደለ ወደዚያ ይሸሽ ዘንድ* የመማፀኛ ከተሞች እንዲሆኑላችሁ ከተሞችን ለእናንት ለዩ።
ራእይ 16፥3 ሁለተኛውም ጽዋውን በባሕር ውስጥ አፈሰሰ፤ እንደ ሞተም ሰው ደም ሆነ፥ በባሕርም ከሚኖሩት ሕይወት ያለበት *"ነፍስ"ψυχὴ ሁሉ ሞተ*።
ዘፍጥረት 17፥14 የቍልፈቱን ሥጋ ያልተገረዘ ቈላፍ ሰው ሁሉ፥ *ያች "ነፍስ" הַנֶּ֥פֶשׁ ከወገንዋ ተለይታ ትጥፋ*፤ ቃል ኪዳኔን አፍርሳለችና።

እነዚህ አናቅጽ ላይ ነፍስ የሚገደል፣ የሚሞት እና የሚጠፋ እንደሆነ ያሳይል። ያ ማለት ነፍስ የአንድን ሰው ስብዕና ስለሚያመለክት ነው እንጂ መንፈስ በሚለው ስሌት ነፍስን መግደል ማንም አይችልም፦
ማቴዎስ 10፥28 *"አካልንም" σῶμα የሚገድሉትን "ነፍስን" ψυχή ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም አካልንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ*።

ስለ ነፍስ የባይብል አስተምህሮት ከቁርኣን ጋር ልዩነት የለውም።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
አል-ወላእ ወል በራእ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥8 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለአላህ ቀጥተኞች በትክክል መስካሪዎች ኹኑ፡፡ ሕዝቦችንም መጥላት ባለማስተካከል ላይ አይገፋፋችሁ፡፡ አስተካክሉ፡፡ እርሱ ማስተካከል ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ لِلَّهِ شُهَدَاءَ بِالْقِسْطِ ۖ وَلَا يَجْرِمَنَّكُمْ شَنَآنُ قَوْمٍ عَلَىٰ أَلَّا تَعْدِلُوا ۚ اعْدِلُوا هُوَ أَقْرَبُ لِلتَّقْوَىٰ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ

"አል-ወላእ ወል በራእ" الْوَلَاء وَالبَراء‎ ማለት እውነትን ለማንገሥ ሐሰትን ለማርከሥ እና የአላህን ሉዓላዊነት ለማስፈን ከወቀሳና ከሙገሳ ነጻ የሆነ ትግል ነው።
"አል-ወላእ ወል በራእ" እራሱን የቻለ"አስል" أصل‎ ማለትም "ቋንቋዊ ፍቺ"etymological meaning" እና "ኢስጢላሕ" اِصْطِلَاح‎ ማለትም "ሸሪዓዊ ትርጉም"Terminological definition" አለው።

ነጥብ አንድ
"ወላእ"
"ወላእ" وَلَاء ማለት ቋንቋዊ ፍቺ "መውደድ" "መቅረብ" "መርዳት" ማለት ሲሆን ሸሪዓዊ ትርጉሙ ደግሞ "አላህን፣ መልእክተኛው፣ እንዲሁም ዲነል ኢሥላምን እና ሙሥሊሞችን መወደድ፣ መቅረብ እና መርዳት ማለት ነው"።

ነጥብ ሁለት
"በራእ"
"በራእ" بَراء‎ ማለት ቋንቋዊ ፍቺ "መጥላት" "መራቅ" "መተው" ማለት ሲሆን ሸሪዓዊ ትርጉሙ ደግሞ "ከአላህ ውጭ የሚመለኩ ጣዖታትን እና የአላህ ጠላቶችን ለአላህ ብሎ መጥላት፣ መራቅ እና መተው ነው"።

አንድ ሙዕሚን ለአላህ ብሎ ቀጥተኛ በፍትሕ መስካሪ መሆን አለበት፤ ጥላቻ ካለማስተካከል ከመጣ ከአላህ ፍራቻ የራቀ ነው፦
5፥8 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለአላህ ቀጥተኞች በትክክል መስካሪዎች ኹኑ፡፡ ሕዝቦችንም መጥላት ባለማስተካከል ላይ አይገፋፋችሁ፡፡ አስተካክሉ፡፡ እርሱ ማስተካከል ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ لِلَّهِ شُهَدَاءَ بِالْقِسْطِ ۖ وَلَا يَجْرِمَنَّكُمْ شَنَآنُ قَوْمٍ عَلَىٰ أَلَّا تَعْدِلُوا ۚ اعْدِلُوا هُوَ أَقْرَبُ لِلتَّقْوَىٰ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ

"ቂሥጥ" قِسْط ማለት "ፍትሕ" ማለት ነው፤ ለአላህ ተብሎ ቀጥተኛ ለመሆን ፍትሕ ወሳኝ ነጥብ ነው፤ ይህ በነሲብ ከመመስከር ይታደገናል፤ "ተዕዲሉ" تَعْدِلُوا ተብሎ የተቀመጠው የግስ መደብ የስም መደቡ "ዐድል" عَدْل ሲሆን አሁን "ፍትሕ" ማለት ነው፤ ፍትሕ ለአላህ ፍራቻ ተብሎ እና አላህ በምንሠራው ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው ተብሎ የሚደረግ ነው። አላህ በፍትሕ ያዛል፤ ከአስከፊ፤ ከሚጠላ ነገር ሁሉ እና ከመበደልም ይከለክላል፦
16፥90 *አላህ በማስተካከል፣ በማሳመርም፣ ለዝምድና ባለቤት በመስጠትም ያዛል፡፡ ከአስከፊም፣ ከሚጠላም ነገር ሁሉ እና ከመበደልም ይከለክላል፡፡ ትገነዘቡ ዘንድ ይገስጻችኋል*፡፡ إِنَّ اللَّهَ يَأْمُرُ بِالْعَدْلِ وَالْإِحْسَانِ وَإِيتَاءِ ذِي الْقُرْبَىٰ وَيَنْهَىٰ عَنِ الْفَحْشَاءِ وَالْمُنكَرِ وَالْبَغْيِ ۚ يَعِظُكُمْ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ማስተካከል" ለሚለው ቃል የገባው "ዐድል" عَدْل መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል፤ በፍትሕ የሚጠላ ነገር ሁሉ ለአላህ ብሎ ጠልቶ መከልከል ከመበደል ይታደጋል፤ ፍትሕ ከራስ፣ ከወላጅ እና ከቅርብ ዘመድ በላይ ለአላህ ተብሎ የሚደረግ፣ ከዝንባሌ የጸዳ፣ ሀብታም ወይም ድኻ ሳይል አላህ ውስጠ ዐዋቂ ነው ብሎ በትክክል መቆም ነው፦
4፥135 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *በትክክል ፍትሕ ቀዋሚዎች በራሳችሁ ወይም በወላጆች እና በቅርብ ዘመዶች ላይ ቢኾንም እንኳ ለአላህ መስካሪዎች ኹኑ፡፡ ሀብታም ወይም ድኻ ቢኾን አላህ በእነርሱ ከእናንተ ይበልጥ ተገቢ ነው፡፡ እንዳታደሉም ዝንባሌን አትከተሉ፡፡ ብታጠምሙም ወይም መመስከርን ብትተው አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ بِالْقِسْطِ شُهَدَاءَ لِلَّهِ وَلَوْ عَلَىٰ أَنفُسِكُمْ أَوِ الْوَالِدَيْنِ وَالْأَقْرَبِينَ ۚ إِن يَكُنْ غَنِيًّا أَوْ فَقِيرًا فَاللَّهُ أَوْلَىٰ بِهِمَا ۖ فَلَا تَتَّبِعُوا الْهَوَىٰ أَن تَعْدِلُوا ۚ وَإِن تَلْوُوا أَوْ تُعْرِضُوا فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرًا

እዚህ አንቀጽ ላይ "ተዕዲሉ" تَعْدِلُوا የሚለው ቃል አሁንም ይሰመርበት፤ ይህ ለአላህ ተብሎ የሚደረግ ፍትሕ ለአማንያን ብቻ ሳይሆን ለከሃድያንም ጭምር ነው፦
60፥8 *ከእነዚያ በሃይማኖት ካልተጋደሏችሁ፣ ከአገሮቻችሁም ካላወጡዋችሁ ከሓዲዎች መልካም ብትውሉላቸው እና ወደ እነርሱ ብታስተካክሉ አላህ አይከለክላችሁም፡፡ አላህ ትክክለኞችን ይወዳልና*፡፡ لَّا يَنْهَاكُمُ اللَّهُ عَنِ الَّذِينَ لَمْ يُقَاتِلُوكُمْ فِي الدِّينِ وَلَمْ يُخْرِجُوكُم مِّن دِيَارِكُمْ أَن تَبَرُّوهُمْ وَتُقْسِطُوا إِلَيْهِمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُقْسِطِينَ

ዲናችንን አክብረው ካልተጋደሉንና ካላሳደዱን ከሃድያን ጋር በዝምድና፣ በባልደረባ፣ በጉርብትና መልካም መዋዋል እና ማስተካከል ይቻላል፤ "ብታስተካክሉ" ለሚለው ቃል አሁንም የገባው "ቱቅሢጡ" َتُقْسِطُوا ሲሆን የስም መደቡ "ቂሥጥ" قِسْط ማለትም "ፍትሕ" ነው፤ ለአላህ ብለን ስናስተካክል "ሙቅሢጢን" مُقْسِطِين ማለትም "ፍትኸኞችን" "ትክክለኞች" "አስተካካዮች" እንባላለን፤ አላህ ሙቅሢጢንን ይወዳልና፤ አላህ የወደደውን እንወዳለን፦
49፥9 *በነገሩ ሁሉ አስተካክሉም፡፡ አላህ አስተካካዮችን ይወዳልና*፡፡ وَأَقْسِطُوا ۖ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُقْسِطِينَ

አላህ እንዳንዋዋል እና እንዳናስተካክል የከለከለን ዲናችንን አዋርደው ከተጋደሉንና ካላሳደዱን ከሃድያን ጋር ነው፦
60፥9 *አላህ የሚከለክላችሁ ከእነዚያ በሃይማኖት ከተጋደሉዋችሁ፣ ከቤቶቻችሁም ካወጡዋችሁ፣ እናንተም በማውጣት ላይ ከረዱት ከሓዲዎች እንዳትወዳጁዋቸው ብቻ ነው፡፡ ወዳጅ የሚያደርጓቸውም ሰዎች እነዚያ እነርሱ በዳዮቹ ናቸው*፡፡ إِنَّمَا يَنْهَىٰكُمُ ٱللَّهُ عَنِ ٱلَّذِينَ قَٰتَلُوكُمْ فِى ٱلدِّينِ وَأَخْرَجُوكُم مِّن دِيَٰرِكُمْ وَظَٰهَرُوا۟ عَلَىٰٓ إِخْرَاجِكُمْ أَن تَوَلَّوْهُمْ ۚ وَمَن يَتَوَلَّهُمْ فَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلظَّٰلِمُونَ
አላህ ወሰን አላፊዎችን፣ በዳዮችን፣ አበላሺዎችን ወዘተ አይወድም፦
5፥87 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህ ለናንተ የፈቀደላችሁን ጣፋጮች እርም አታድርጉ፡፡ *ወሰንንም አትለፉ፡፡ አላህ ወሰን አላፊዎችን አይወድምና*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تُحَرِّمُوا طَيِّبَاتِ مَا أَحَلَّ اللَّهُ لَكُمْ وَلَا تَعْتَدُوا ۚ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْمُعْتَدِينَ
3፥57 *አላህም በዳዮችን አይወድም*፡፡ وَاللَّهُ لَا يُحِبُّ الظَّالِمِينَ
5፥64 *አላህም አበላሺዎችን አይወድም*፡፡ وَاللَّهُ لَا يُحِبُّ الْمُفْسِدِينَ

አላህ የጠላውን እኛም እንጠላለን፤ ይህ ነው አል-ወላእ ወል በራእ፤ አል-ወላእ ወል በራእ በጭፍን መውደድና መጥላት ሳይሆን ለአላህ ተብሎ የሚጠላ ነገር ሁሉ መጥላት፥ ለአላህ ተብሎ የሚወደድ ነገር ሁሉ መውደድ፣ በበጎ ነገር እና አላህን በመፍራትም መረዳዳት ነው፦
5፥2 *በበጎ ነገር እና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ፡፡ ግን በኃጢአት እና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና*፡፡ وَتَعَاوَنُوا عَلَى الْبِرِّ وَالتَّقْوَىٰ ۖ وَلَا تَعَاوَنُوا عَلَى الْإِثْمِ وَالْعُدْوَانِ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 45, ሐዲስ 46
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንዳስተላለፈው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"የትንሳኤ ቀን አላህ እንዲህ ይላል፦ "በእኔ ምክንያት እርስ በእርሳቸው የተዋደዱ የት አሉ? ዛሬ በጥላዬ እጠልላቸዋለው፤ በዚህን ጊዜ ምንም ጥላ የለም፤ ከእኔ ጥላ በቀር"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ إِنَّ اللَّهَ يَقُولُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ أَيْنَ الْمُتَحَابُّونَ بِجَلاَلِي الْيَوْمَ أُظِلُّهُمْ فِي ظِلِّي يَوْمَ لاَ ظِلَّ إِلاَّ ظِلِّي

ለዘሩ፣ ለብሔሩ፣ ለፓለቲካው፣ ለዝንባሌው፣ ለስሜቱ ብሎ መውደድ እና መጥላት ኪሳራ አለው፥ በዱንያም በአኺራም ይጎዳል፤ ነገር ግን ለአላህ ብሎ መውደድ እና መጥላት ትርፍ አለው፥ በዱንያም በአኺራም ይጠቅማል፦
አቢ ዳውድ መጽሐፍ 42, ሐዲስ 86
አቢ ኡማማህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ማንኛውም ሰው ለአላህ ብሎ የወደደ እና የጠላ፣ ለአላህ ብሎ የሰጠ እና የነፈገ የተሟላ ኢማን አለው"*። عَنْ أَبِي أُمَامَةَ، عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم أَنَّهُ قَالَ ‏ "‏ مَنْ أَحَبَّ لِلَّهِ وَأَبْغَضَ لِلَّهِ وَأَعْطَى لِلَّهِ وَمَنَعَ لِلَّهِ فَقَدِ اسْتَكْمَلَ الإِيمَان

አል-ወላእ ወል በራእ በወሰን በማለፍ አይረዳዳም፤ በግድ እመኑ ብሎም አያስገድድም፤ ምክንያቱም በሃይማኖት ማስገደድ የለም፤ የፈለገ ያምናል፤ ያልፈለገ ይክዳል፦
2፥256 በሃይማኖት ማስገደድ የለም፡፡ *ቅኑ መንገድ ከጠማማው በእርግጥ ተገለጠ*፡፡ لَا إِكْرَاهَ فِي الدِّينِ ۖ قَد تَّبَيَّنَ الرُّشْدُ مِنَ الْغَيِّ ۚ
18፥29 *«እውነቱም ከጌታችሁ ነው፡፡ የሻም ሰው ይመን፤ የሻም ሰው ይካድ»* በላቸው፡፡ وَقُلِ الْحَقُّ مِن رَّبِّكُمْ ۖ فَمَن شَاءَ فَلْيُؤْمِن وَمَن شَاءَ فَلْيَكْفُر
አል-ወላእ ወል በራእ ከተውሒድ ቀጥሎ ያለ መርሕ ሲሆን ሰዎችን እንዲያምኑ አያስገድድም፦
10፥99 ጌታህም በሻ ኖሮ በምድር ያሉት ሰዎች ሁሉም የተሰበሰቡ ሆነው ባመኑ ነበር፡፡ *ታዲያ አንተ ሰዎችን አማኞች እንዲኾኑ ታስገድዳለህን?* وَلَوْ شَآءَ رَبُّكَ لَـَٔامَنَ مَن فِى ٱلْأَرْضِ كُلُّهُمْ جَمِيعًا ۚ أَفَأَنتَ تُكْرِهُ ٱلنَّاسَ حَتَّىٰ يَكُونُوا۟ مُؤْمِنِينَ
11፥28 «ሕዝቦቼ ሆይ! ንገሩኝ ከጌታዬ በግልጽ ማስረጃ ላይ ብሆን ከእርሱም ዘንድ የሆነን ችሮታ ነብይነት ቢሰጠኝ እና በእናንተ ላይ ብትደበቅባችሁ *እናንተ ለርሷ ጠይዎች ስትሆኑ እርሷን በመቀበል እናስገድዳችኋለን?*» አላቸው፡፡ قَالَ يَٰقَوْمِ أَرَءَيْتُمْ إِن كُنتُ عَلَىٰ بَيِّنَةٍۢ مِّن رَّبِّى وَءَاتَىٰنِى رَحْمَةًۭ مِّنْ عِندِهِۦ فَعُمِّيَتْ عَلَيْكُمْ أَنُلْزِمُكُمُوهَا وَأَنتُمْ لَهَا كَٰرِهُونَ

አል-ወላእ ወል በራእ ሕገ-መንግሥቱ ቁርኣን ነው፤ በካሃድያን መካከል የምንዳኘው በተወረደው ቁርኣን ነው፦
5፥48 ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭና በእርሱ ላይ ተጠባባቂ ሲኾን በእውነት አወረድን፡፡ *በመካከላቸውም አላህ ባወረደው ሕግ ፍረድ፡፡ እውነቱም ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌዎቻቸውን አትከተል*፡፡ وَأَنزَلْنَا إِلَيْكَ الْكِتَابَ بِالْحَقِّ مُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ الْكِتَابِ وَمُهَيْمِنًا عَلَيْهِ ۖ فَاحْكُم بَيْنَهُم بِمَا أَنزَلَ اللَّهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَاءَهُمْ عَمَّا جَاءَكَ مِنَ الْحَقِّ

"በመካከላቸውም" የሚለው ይሰመርበት፤ የከሃድያን ዝንባሌዎቻቸው ለምሳሌ ወንድ ለወንድ ሴት ለሴት ማጋባት፣ ውርጃ ማስወረድ መፍቀድ፣ ኸምር መጠጣት መፍቀድ፣ የእሪያ ስጋ መብላት መፍቀድ፣ ወለድ መፍቀድ ወዘተ ሊሆን ይችላል። ይህ በቁርኣን ስለማይፈቀድ ፍላጎቶቻቸውን መከተል የለብንም፤ በሰዎች ዝንባሌ በተመሰረተ ሕገ-መንግሥት መፍረድ እንዳያሳስቱን መጠንቀቅ አለብን፤ አል-ወላእ ወል በራእ ጋር በድምፅ ብልጫ ሳይሆን አላህ ባወረደው ሕግ ነው የሚፈረደው፤ የብዙሃን ድምፅ አመጽ ነው፤ ከሰዎቹም ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው፦
5፥49 *በመካከላቸውም አላህ ባወረደው ሕግ ፍረድ፡፡ ፍላጎቶቻቸውንም አትከተል፡፡ አላህም ወደ አንተ ካወረደው ከከፊሉ እንዳያሳስቱህ ተጠንቀቃቸው ማለትን አወረድን፡፡ ቢዞሩም አላህ የሚሻው በከፊሉ ኃጢአታቸው ሊቀጣቸው መኾኑን ዕወቅ፡፡ ከሰዎቹም ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው*፡፡ وَأَنِ احْكُم بَيْنَهُم بِمَا أَنزَلَ اللَّهُ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَاءَهُمْ وَاحْذَرْهُمْ أَن يَفْتِنُوكَ عَن بَعْضِ مَا أَنزَلَ اللَّهُ إِلَيْكَ ۖ فَإِن تَوَلَّوْا فَاعْلَمْ أَنَّمَا يُرِيدُ اللَّهُ أَن يُصِيبَهُم بِبَعْضِ ذُنُوبِهِمْ ۗ وَإِنَّ كَثِيرًا مِّنَ النَّاسِ لَفَاسِقُون

አል-ወላእ ወል በራእ በቁርኣን ጅሃድ ማድረግን ይይዛል፤ እውነተኛ ምእምናን በገንዘቦቻቸው እና በነፍሶቻቸውም በአላህ መንገድ የታገሉት ብቻ ናቸው፦
49፥15 *ምእምናን እነዚያ በአላህ እና በመልእከተኛው ያመኑት ከዚያም ያልተጠራጠሩት "በገንዘቦቻቸው እና በነፍሶቻቸውም በአላህ መንገድ የታገሉት ብቻ ናቸው"፡፡ እነዚያ እነርሱ እውነተኞቹ ናቸው*፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ الَّذِينَ آمَنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ ثُمَّ لَمْ يَرْتَابُوا وَجَاهَدُوا بِأَمْوَالِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ ۚ أُولَـٰئِكَ هُمُ الصَّادِقُونَ
25፥52 *ከሓዲዎችንም አትታዘዛቸው፡፡ በእርሱም በቁርኣን ታላቅን ትግል ታገላቸው*፡፡ فَلَا تُطِعِ الْكَافِرِينَ وَجَاهِدْهُم بِهِ جِهَادًا كَبِيرًا

"የታገሉ" ለሚለው የግስ መደብ የገባው ቃል "ጃሀዱ" َجَاهَدُوا ሲሆን "ታገላቸው" ለሚለው ደግሞ "ጃሂድሁም" جَاهِدْهُم ነው።
አል-ወላእ ወል በራእ በባይብልም አለ፤ እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች፤ አምስቱ ባሕርያት ሲሆኑ ስድስት እና ሰባት ግን በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር የሆነ ሰው እና በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ ሰው ነው፦
ምሳሌ 6፥16-19 *እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች*፤ እነርሱም፦
ትዕቢተኛ ዓይን፥
ሐሰተኛ ምላስ፥
ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ፥
ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ፥
ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር፥
በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር፥ በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ።

እግዚአብሔር ይጠላል፥ የማይወዳቸው ሰዎች አሉ፦
ሆሴእ 9፥15 ክፋታቸው ሁሉ በጌልገላ አለ፤ በዚያ *"ጠልቻቸዋለሁ"፤ ስለ ሠሩት ክፋት ከቤቴ አሳድዳቸዋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ "አልወድዳቸውም"*፤
ሚልክያስ 1፥2 *ያዕቆብንም "ወደድሁ"፥ ዔሳውንም "ጠላሁ"*።
ሮሜ 9፥13 ያዕቆብን *"ወደድሁ" ኤሳውን ግን "ጠላሁ"* ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።
ዘዳግም 18፥11-12 አስማተኛም፥ መተተኛም፥ በድግምት የሚጠነቍልም፥ መናፍስትንም የሚጠራ፥ ጠንቋይም፥ ሙታን ሳቢም በአንተ ዘንድ አይገኝ። *"ይህንም የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ"* ነው ስለዚህም ርኵሰት አምላክህ እግዚአብሔር ከፊትህ ያሳድዳቸዋል።
መዝሙር 11፥5 እግዚአብሔር ጻድቅንና ኅጥእን ይመረምራል *"ዓመፃን የወደዳት ግን ነፍሱን ጠልቶአል"*።

"ጠላቶቻችሁን ውደዱ" ማለት በግል ደረጃ የሚጠሏችሁን ውደዱ ማለት እንጂ እግዚአብሔር የሚጠላውን ውደዱ ማለት አይደለም። ለምሳሌ ዲያብሎስ እና ሰይጣናትን ትወዳላችሁን? አትወዷቸውም። "ዓለም" የሚለው እኮ እራሱ ኢየሱስን እና ተከታዮችን የጠላው ማህበረሰብን ነው፦
ዮሐንስ 15፥18 *ዓለም ቢጠላችሁ ከእናንተ በፊት እኔን እንደ ጠላኝ* እወቁ።
1 ዮሐንስ 3፥13 ወንድሞች ሆይ፥ *ዓለም ቢጠላችሁ* አትደነቁ።
1 ዮሐንስ 4፥4 *በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና*።

እግዚአብሔር የሚጠላውን መውደድ ለእግዚአብሔር ጥል ነው፤ የእግዚአብሔር ጠላት መሆን ነው። ዓለምን እና በዓለም ላይ ያሉትን ዲያብሎስን እና ሰይጣናትን አትውደዱ ተብሏል፦
ያዕቆብ 4፥4 አመንዝሮች ሆይ፥ *ዓለምን መውደድ ለእግዚአብሔር ጥል እንዲሆን አታውቁምን? እንግዲህ የዓለም ወዳጅ ሊሆን የሚፈቅድ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ሆኖአል*።
1ኛ የዮሐንስ 2፥15-16 ዓለምን ወይም *በዓለም ያሉትን አትውደዱ*፤

አል-ወላእ ወል በራእን ከመተቸት ይልቅ ቅድሚያ ባይብላችሁን አንብቡት! ትራስ አታድርጉት።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
አራቱ የሰው አፈጣጠር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡

ነጥብ አንድ
“አደም”
አላህ አደምን ያለ ወንድ ያለ ሴት ከምድር አፈር ፈጠረው፦
3:59 አላህ ዘንድ የዒሳ ምሳሌ፥ እንደ አዳም ብጤ ነዉ፤ *ከዐፈር* ፈጠረዉ፤ ከዚያም ለርሱ ሁን አለዉ፥ ሆነም።
15:28 ጌታህም ለመላእክት ባለጊዜ አስታውስ፡፡ እኔ ሰውን ከሚቅጨለጨል ሸክላ ከሚገማ ጭቃ እፈጥራለሁ፡፡
38:71 ጌታህ «ለመላእክት እኔ ሰውን ከጭቃ ፈጣሪ ነኝ ባለ ጊዜ» አስታውስ፡፡
71:17-18 አላህም *ከምድር* ማብቀልን አበቀላችሁ። ከዚያም በውስጧ ይመልሳችኋል። ማውጣትንም ያወጣችኋል።
20:53-56 እርሱ ያ ምድርን ለናንተ ምንጣፍ ያደረገላችሁ፣ *ከርሷ*مِنْهَا ፈጠርናቸሁ፤ በርሷም ውስጥ እንመልሳችኋለን፤ ከርሷም በሌላ ጊዜ እናወጣችኋለን።

ነጥብ ሁለት
“እኛ”
አላህ ለምን እኛን ከአፈር እንደ አደም አልፈጠረንም? መልሱ የአላህ ምርጫ ነው፣ አደምን ያወንድና ያለ ሴት እንደፈጠረው ሁሉ እኛን ከአደም በተቃራኒው ከሴትና ከወንድ ፈጠረን፦
49:13 እላንተ ሰዎች ሆይ እኛ *ከወንድና ከሴት* ፈጠርናችሁ፤
4:1እላንተ ሰዎች ሆይ! ያንን ከአንዲት ነፍስ የፈጠራችሁን፣ ከእርስዋም መቀናጆዋን የፈጠረውን፣ *ከነርሱም* ብዙ ወንዶችንና ሴቶችን የበተነውን፣ ጌታችሁን ፍሩ።

ነጥብ ሶስት
“ሃዋ”
ሃዋን የሰው ዘር ሁሉ እናት ስትሆን ያለ ሴት ከወንድ የተፈጠረች ናት፣ የአደም መቀናጃ ተብላ የተጠራችው ሴት ሃዋ ናት፦
39:6 ከአንዲት ነፍስ ፈጠራችሁ፤ ከዚያም ከርሷ መቀናጆዋን አደረገ።
7:189 እርሱ ያ ከአንዲት ነፍስ የፈጠራችሁ ከርሷም መቀናጆዋን ወደርሷ ይረካ ዘንድ ያደረገ ነው።
4:1 እላንተ ሰዎች ሆይ! ያንን ከአንዲት ነፍስ የፈጠራችሁን፣ ከእርስዋም መቀናጆዋን የፈጠረውን፣ ከነርሱም ብዙ ወንዶችንና ሴቶችን የበተነውን፣ ጌታችሁን ፍሩ።

አላህ ሃዋን የፈጠረው ከአደም ጎን አጥንት ነው፦
ሰሂኧል ሙስሊም ኪታበል ኒካህ መጽሐፍ 8, ቁጥር 3468″
አቡ ሁረይራ እንደተረከው የአላህ መልእተኛ እንደተናገሩት፦ مَنْ كَانَ يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الآخِرِ فَإِذَا شَهِدَ أَمْرًا فَلْيَتَكَلَّمْ بِخَيْرٍ أَوْ لِيَسْكُتْ وَاسْتَوْصُوا بِالنِّسَاءِ فَإِنَّ الْمَرْأَةَ خُلِقَتْ مِنْ ضِلَعٍ
ማንም በአላህና በመጨረሻ ቀን የሚያምን በምንም ነገር ሲመሰክር መልካም ይናገር አሊያም ዝም ይበል፣ ሴትን በደግነት ተንከባከቡ፣ ሴት የተፈጠረችው ከጎን አጥንት ነውና።

ነጥብ አራት
“ኢሳ”
አላህ አደምን ካለ ወንድና ሴት ሲፈጥር እኛን በተቃራኒው ከወንድና ከሴት ፈጥሯል፣ ሃዋን ከወንድ ያለ ሴት እንደፈጠረ ሁሉ በተቃራኒው ከሴት ያለ ወንድ ይጠበቅ ነበር፣ አላህ ኢሳን የሃዋ ተቃራኒ አድርጎ ያለ ወንድ ከሴት ከመርየም ፈጥሮታል፣ ይህ የአላህ ምርጫና ፍላጎት ነው፦
19:21፦ አላት ነገሩ እንደዚህሽ ነው ፤ ጌታሽ ፦ እርሱ በእኔ ላይ ገር ነው፤ ለሰዎችም “ታምር”፣ ከኛም “ችሮታ” ልናደርገው ይህንን ሠራን የተፈረደም ነገር ነዉ አለ፤
43:59 እርሱ በርሱ ላይ የለገስንለት ለእስራኤል ልጆች “ታምር” ያደረግነው የሆነ ባሪያ እንጂ ሌላ አይደለም።
3:47ጌታዬ ሆይ! ሰዉ ያልነካኝ ስሆን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለች፤ ነገሩ እንደዚህሽ ነዉ፤ አላህ “የሚሻዉን የፈጥራል”፤ አንዳችን በሻ ጊዜ ለርሱ ሁን ይለዋል ወድያዉኑም ይሆናል፥ አላት።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
በቅርብ ቀን ኢንሻላህ ይጠብቁ።
የእግዚአብሔር ልጅ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

18፥4 *እነዚያንም፦ “አላህ ልጅን ይዟል” ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት አወረደው*፡፡ وَيُنذِرَ الَّذِينَ قَالُوا اتَّخَذَ اللَّهُ وَلَدًا

ክርስቲያኖች ኢየሱስ “የእግዚአብሔር ልጅ” ነው ይላሉ፤ “ልጅ” ማለት ምን ማለት ነው? ስንላቸው፦ “አብን አህሎና መስሎ ከአብ “ባህርይ ዘእም-ባህርይ አካል ዘእም-አካል” ማለትም ከባህርይው ባህርይ ወስዶ ከአካሉ አካሉን ወስዶ ተወለደ” ይሉናል። እረ ከሰማናቸው፦ “አምላክ ዘእም-አምላክ ማለትም ከአምላክ የተገኘ አምላክ” ይሉናል። ከእዚህ እሳቤ ቁርኣን በተቃራኒው፦ “አላህ ወለደ” ያሉ በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው፤ አላህ አልወለደም፤ አልተወለደምም፤ እንደውም አላህ ቁርኣን ካወረደበት ምክንያት አንዱ እነዚያንም፦ “አላህ ልጅን ይዟል” ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት ነው፦
37፥152 ፦ *“አላህ ወለደ” አሉ፤ እነርሱም በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው*፡፡ وَلَدَ اللَّهُ وَإِنَّهُمْ لَكَاذِبُونَ
112፥3 *አልወለደም፤ አልተወለደምም*፡፡ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ
18፥4 *እነዚያንም፦ “አላህ ልጅን ይዟል” ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት አወረደው*፡፡ وَيُنذِرَ الَّذِينَ قَالُوا اتَّخَذَ اللَّهُ وَلَدًا

ይህንን የቁርኣን እሳቤ ካየን ዘንዳ ባይብል ላይ እግዚአብሔር አባት መባሉ “አስገኚ” ወይም “ፈጣሪ” በሚል ፍካሬአዊ ቃል መጥቷል፦
ሚልክያስ 2፥10 ለሁላችን *”አንድ አባት”* ያለን አይደለምን? *አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን*?
ዮሐንስ 8፥41 *አንድ አባት* አለን *እርሱም እግዚአብሔር ነው*፡ አሉት።
ኤፌሶን 4፥6 ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር *አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ*።

ለምሳሌ መላእክት መናፍስት ተብለዋል፤ እግዚአብሔር የመናፍስት አባት ነው። መናፍስቱ መላእክት የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው፦
ዕብራውያን 12፥9 እንዴትስ ይልቅ *ለመናፍስት አባት* አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር በተገባን?
ዕብራውያን 1፥14 *ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?*
ኢዮብ 38፥7 አጥቢያ ኮከቦች በአንድነት ሲዘምሩ፥ *የእግዚአብሔርም ልጆች* ሁሉ እልል ሲሉ፥

መላእክት የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉት ያለ እናት እና ያለ አባት ስለፈጠራቸው እንደሆነ ቅቡል ነው፤ አዳምም የእግዚአብሔር ልጅ ተብሏል፦
ሉቃስ 3፥38 የሴት ልጅ፥ የአዳም ልጅ፥ *የእግዚአብሔር ልጅ*።

አዳም የእግዚአብሔር ልጅ የተባለው ያለ እናት እና ያለ አባት ስለፈጠረው እንደሆነ እሙን ነው፤ ታዲያ ያለ አባት በእናት ብቻ የተፈጠረው ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ቢባል ምን ይደንቃል? ከማርያም ተጸንሶ የተወለደው ሰው መሆኑን አንርሳ፦
ሉቃስ 1፥35 ስለዚህ ደግሞ *ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል*።
ገላትያ 4 ፥4 ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ *እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ*፤

ማርያም የወለደችው መለኮትን ሳይሆን ሰው ብቻ ነው፤ ያም ሰው የእግዚአብሔር ልጅ መባሉ ፈጣሪ ያለ አባት ከእርሷ መፍጠሩን ያሳያል። አይ እግዚአብሔር ኢየሱስን ወለደው ይሉናል፦
መዝሙር 2፥7 ትእዛዙን እናገራለሁ፤ *እግዚአብሔር አለኝ። አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ “ወለድሁህ”*።
ዕብራውያን 1:5 ከመላእክትስ። *እግዚአብሔር አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ “ወልጄሃለሁ”*፥ (አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ጭራሽ ይህ ጥቅስ “ዛሬ” የምትለዋ ቃል መነሻ ጊዜን ታመለክታለች፣ ይህም የኢየሱስ መፈጠር በጊዜ ውስጥ መሆኑን ያሳያል፤ ሲቀጥል እዚህ ጥቅስ ላይ እግዚአብሔር ኢየሱስን፦ “አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ” ብሏል ተብሏል፤ ይህ የሚያሳየው ኢየሱስ “አንተ” ብሎ ካናገረው እግዚአብሔር የተለየ መሆኑን ያሳያል፣ እግዚአብሔር ለኢየሱስ “አባት እሆነዋለው” ኢየሱስ ለእግዚአብሔር “ልጅ ይሆነኛል” ብሏል ተብሏል” ሲሰልስ “ወልጄሃለሁ” የሚለው ቃል “ጌኔካ” γεγέννηκά ሲሆን “ጌኑስ” γένος ማለትም “ወለደ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን በፍካሬአዊ ትርጉም “ፈጠረ” ሲሆን አይሁዳውያን አምላክ ፆታ ስለሌለውን “መወለድ” ማለት “መፈጠር” ነው ብለው ያምናሉ፤ ምክንያቱን ተራራ እንደተወለደ ስለሚናገር፤ ያ ማለት ተራራ ተሰራ ማለት ነው፦
አሞፅ 4:13 እነሆ፥ *”ተራሮችን የሠራ”*፥
መዝሙር 90:2 *”ተራሮች ሳይወለዱ”*፥ בְּטֶרֶם, הָרִים יֻלָּדו
ግሪክ ሰፕቱአጀንት፦
πρὸ τοῦ ὄρη γενηθῆναι καὶ πλασθῆναι τὴν γῆν καὶ τὴν οἰκουμένην,
በዕብራይስጡ “ዩላዱ” יֻלָּדו ማለት “ሳይወለዱ” ማለት ነው። “ሳይወለዱ” የሚለው ፍካሬአዊ ቃል በእማሬያዊ ቃል “ሳይፈጠሩ” ማለት ነው። ግሪክ ሰፕቱአጀንት ላይ ደግሞ በተመሳሳይ “ጌኒቲና” γενηθηναι ማለትም “ሳይወለዱ” የሚለው በተመሳሳይ “ጌኑስ” γένος ማለትም “ወለደ” ከሚል ግስ የመጣ ነው፤ “ወለደ” ማለት “ፈጠረ” ማለት መሆኑን “የወለደህን አምላክ” የሚለው ቃል “የፈጠረውን አምላክ” በሚል ተለዋዋጭ ቃል መምጣቱ ነው፦
ዘዳግም 32፥18 *የወለደህን አምላክ ተውህ*፥ NIV
ዘዳግም 32፥15 ይሹሩን ወፈረ፥ ረገጠ፤ ወፈረ፥ ደነደነ፥ ሰባ፤ *የፈጠረውንም አምላክ ተወ*፤ NIV

“ይሽሩ” የእስራኤላውያን የቁልምጫ ስም ነው፤ አምላክ እስራኤላውን “ወለደ” ወይስ “ፈጠረ” ? አይ ፈጣሪ ጾታ ስለሌለው በእማሬአዊ ቃል ወለደ ማለት ሳይሆን በፍካሬአዊ ቃል ፈጠረ ለማለት ነው ከተባለ እንግዲያውስ ከላይ ያለውንም በዚህ ስሌትና ቀመር ተረዱት። አንዳንድ ቂሎች “መወለድ” ከአብ “መውጣት” ነው ይላሉ፤ ምነው መንፈስ ቅዱስ ከአብ የሚወጣ ነው ትሉ የለ እንዴ? ለምን መንፈስ ቅዱስን የአብ ልጅ አትሉትም? አይ “መውጣት” ማለት “መስረጽ” ነው ካላችሁ ለምንስ ወልድን ከአብ የሰረጸ ነው አትሉትም? ምክንያቱም ወልድም ከአብ የወጣ ነው ስለሚል፤ አይ መውጣት መላክ ማለት ነው ካላችሁ ጥሩ። ካልሆነ ልጅ ማለት፦ “አብን አህሎና መስሎ ከአብ ባህርይ ዘእም-ባህርይ አካል ዘእም-አካል ማለትም ከባህርይው ባህርይ ወስዶ ከአካሉ አካሉን ወስዶ ተወለደ፤ አምላክ ዘእም-አምላክ ማለትም ከአምላክ የተገኘ አምላክ” ካላችሁ ይህንን እሳቤ አይደለም ቁርኣን ባይብላችሁም አይደግፋችሁ። በዚህ ስሌት ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል፦
19፥35 *ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል*፡፡ مَا كَانَ لِلَّهِ أَن يَتَّخِذَ مِن وَلَدٍ ۖ سُبْحَانَهُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ
2፥116 *አላህም ልጅ አለው አሉ፡፡ ከሚሉት ጥራት ተገባው፡፡ አይደለም በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ ሁሉም ለእርሱ ታዛዦች ናቸው*፡፡ وَقَالُوا۟ ٱتَّخَذَ ٱللَّهُ وَلَدًۭا ۗ سُبْحَٰنَهُۥ ۖ بَل لَّهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ ۖ كُلٌّۭ لَّهُۥ قَٰنِتُونَ
2፥117 ሰማያትንና ምድርን ያለብጤ ፈጣሪ ነው፤ *ነገርንም ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው፡- «ኹን» ነው፤ ወዲያውም ይኾናል*፡፡ بَدِيعُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ وَإِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
አባት እና ልጅ

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

112፥3 *አልወለደም አልተወለደም*። لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ

“ዋሊዳእ” وَٰلِدَي ማለት “ወላጅ” ማለት ነው፤ አባት የሆነ ወላጅ “ዋሊድ” وَالِد ወይም “መውሉድ” مَوْلُود ሲባል እናት የሆነች ወላጅ ደግሞ “ዋሊዳ” وَٰلِدَٰت ወይም “ዋሊደ” وَٰلِدَة ትባላለች፤ ከወላጅ የሚገኝ ልጅ ደግሞ “ወለድ” وَلَد ወይም “ወሊድ” وَلِيد ይባላል፤ ሁሉም የስም መደብ የመጡት “ወለደ” وَلَدَ ማለትም “ወለደ” ከሚል ግስ የመጡ ናቸው። አላህ ፃታ የለውም፤ ወንድም ሴትም አይደለም፤ አባት ሆኖ አልወለደም ልጅ ሆኖ አልተወለደም፦
112፥3 *አልወለደም አልተወለደም*። لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ

የሥላሴ አማንያን ኢየሱስ ልጅ ሲሆን አባቱ እግዚአብሔር ነው ይላሉ፤ ዓለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቆጠር አብን መስሎና አህሎ ከአብ ማንነትና ምንነት የተገኘ ነው የሚል እሳቤ አላቸው፤ “ተወለደ” ሲባል “ተገኘ” ማለት ነው ይሉናል፤ አብ ማለት “አስገኚ” ሲሆን ወልድ ደግሞ “ግኝት” ማለት ነው፤ በ 325 AD የተሰበሰበው የኒቅያ ጉባኤም፦
በግሪክ፦
Φῶς ἐκ Φωτός, Θεὸν ἀληθινὸν ἐκ Θεοῦ ἀληθινοῦ,
በግዕዝ፦
“ብርሃን ዘእም-ብርሃን፤ አምላክ ዘእም-አምላክ”
በአማርኛ፦
*“ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፤ ከአምላክ የተገኘ አምላክ”* ብሎታል።

አምላክ አምላክን ካስገኘ ሁለት አምላክ አይሆንም ወይ? አምላክ ተገኘ የሚለው ሲያስገርም አምላክ ተፈጠረ ደግሞ ያስደምማል፦
አማርኛ፦
ምሳሌ 8፥22 *እግዚአብሔር ከሁሉ በፊት ፈጠረኝ*፥ (1980 አዲስ ትርጉም)
ግዕዝ፦
ምሳሌ 8፥22 “ፈጠረኒ እግዚእ መቅድመ ተግባሩ”
ኢንግሊሽ፦
Proverbs 8፥22 “The LORD made me as he began his planning, (International Standard Version)
ዕብራይስጥ፦
ምሳሌ 8፥22 יְהוָה–קָנָנִי, רֵאשִׁית דַּרְכּוֹ: קֶדֶם מִפְעָלָיו מֵאָז.
ግሪክ ሰፕቱአጀንት፦
Proverbs 8፥22 κύριος ἔκτισέν με ἀρχὴν ὁδῶν αὐτοῦ εἰς ἔργα αὐτοῦ

በተለይ በግሪኩ ሰፕቱአጀንት”LXX” ላይ “ኪትዞ” ἔκτισέν ማለት “ፈጠረኝ” ማለት ነው፤ በተመሳሳይ ዕብራይስጡ “ቃናኒ” קָ֭נָנִי ማለት “አስገኘኝ” ማለት ነው፤ ይህ ቃል ሔዋን “አገኘሁ” ብላ ለተጠቀመችበት የዋለው ቃል “ቃኒቲ” קָנִ֥יתִי ሲሆን ዳዊት ደግሞ ኲላሊቴን “ፈጥረሃል” ለሚለው የተጠቀመው “ቃኒታ” קָנִ֣יתָ ብሎ ነው፦
ዘፍጥረት 4፥1 ወንድ ልጅ ከእግዚአብሔር *አገኘሁ* קָנִ֥יתִי አለች።
መዝሙር 139፥13 አቤቱ፥ አንተ ኵላሊቴን *ፈጥረሃልና* קָנִ֣יתָ ፥
ዘዳግም 32፥6፤ ለእግዚአብሔር ይህንን ትመልሳለህ? የገዛህ አባትህ አይደለምን? *የፈጠረህ* קָּנֶ֔ךָ እና ያጸናህ እርሱ ነው።
የመጨረሻው ጥቅስ ላይ “የፈጠረክ” ለሚለው የገባው “ቃነካ” קָּנֶ֔ךָ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። እግዚአብሔር “የገዛህ አባትህ” መባሉ “አባት” ማለት ለእግዚአብሔር ፈጣሪ ማለት እንደሆነ ይህ ጥቅስ ያስረዳል።
እንግዲህ “መገኘት” እና “መፈጠር” ተለዋዋጭ ቃል ከሆነ ኢየሱስ ፍጡር እና ግኝት እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል። ይህንን ጥቅስ ተሃድሶና እና ፕሮቴስታት ስለ ኢየሱስ አይደለም ብለው ሽምጥጥ አርገው ቢክዱም፤ ቀደምት ኦርቶዶክስ፣ካቶሊክ፣ አንግሊካን እና የኒቂያ ጉባኤ ስለ ኢየሱስ ፍጥረት ሳይፈጠር መወለዱን ያሳያል ይላሉ፤ በ 325 AD በኒቂያ ጉባኤ አርዮስንና አትናቲዎስ ኢየሱስ ፍጡር ነው ወይስ አይደለም ለሚለው ክርክራቸው ይህ ጥቅስ ነበር፤ አንዳንድ ኦርቶዶክሳውያንም ይህ ስለ ኢየሱስ አይደለም ብለው ሊያቅማሙ ሲሞክሩ አንድምታው ሆነ ሃይማኖተ-አበው አጋልጧቸዋል፤ ቄርሎስ በሃይማኖተ-አበው ላይ ለኢየሱስ ነው ይለናል፦
ሃይማኖተ-አበው ዘቄርሎስ 76:12
ቄርሎስም አለ፦
“ተፈጥረ ጥበብ ዘውእቱ ቃል”
ትርጉም፦
*“ጥበብ ተፈጠረ ይኸውም ቃል ነው”*
ቄርሎስም አለ፦
“ወይእዜኒ ጥበብ ትቤ ፈጠረኒ እግዚእ መቅድመ ተግባሩ”
ትርጉም፦
*“ከፍጥረት አስቀድሞ የነበርኩኝ በቀድሞ ተግባሩ ጌታ ፈጠረኝ አለች”*

የመቃብያን ጸሐፊም ሰሎሞን በምሳሌ መጽሐፍ ላይ ስለ ኢየሱስ፦ “ዛሬም የሚታየው ሁሉ ሳይታይ ዛሬም የሚጠራው ስም ሁሉ ሳይጠራ ፈጠረኝ” ማለቱን ተናግሯል፦
3ኛ መቃብያን 4፥18 ሰሎሞን ፦ *“ዛሬም የሚታየው ሁሉ ሳይታይ ዛሬም የሚጠራው ስም ሁሉ ሳይጠራ ፈጠረኝ”* ብሎ ተናገረ፤

እንግዲህ አባት ማለት “አስገኚ” ወይም “ፈጣሪ” መሆኑን እንዲሁ ልጅ ማለት “ተገኚ” ወይም “ፍጡር” መሆኑን ካየን ዘንዳ ኢንሻላህ በገቢር ሁለት አብ ማን ነው? ወልድ ማን ነው? የሚለውን እናብራራለን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የፕሮቴስታንት ቅጥፈት ማጋለጥ ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ ወደዚህ ቻናል ይቀላቀሉ፦
http://tttttt.me/protestant_lie
የኦርቶዶክስን ኮተት እና ተረት ማጋለጥ ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ ወደዚህ ቻናል ይቀላቀሉ፦
@orthox
አባት እና ልጅ

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

112፥3 *አልወለደም አልተወለደም*። لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ

“ኣብ” אַבָּא ማለት በዕብራይስጥ “አስገኚ”orginator” ማለት ሲሆን በግዕዝ “አብ” ማለት “አባት” ማለት ነው፤ የአብ ተመሳሳይ ትርጉም “አባ” ሲሆን “አባት” ማለት ነው፤ “አበው” የአብ ብዙ ቁጥር ሲሆን “አባቶች” ማለት ነው።
በመጀመሪያ መደብ፦
“አቡየ” ማለት ነጠላ ሲሆን “አባቴ” ማለት ነው፤ “አቡነ” ማለት “አባታችን” ማለት ነው።
ሁለተኛ መደብ፦
“አቡከ” ለወንድ ሲሆን “አባትህ” ማለት ነው፤ “አቡኪ” ለሴት “አባትሽ” ማለት ነው። በብዜት ለወንድ “አቡክሙ” ማለት “አባታችሁ” ሲሆን ለሴት “አቡክን” ማለት “አባታችሁ” ነው።
ሦስተኛ መደብ፦
“አቡሁ” ለወንድ ሲሆን “አባቱ” ማለት ነው፤ “አቡሃ” ለሴት “አባቷ” ማለት ነው። በብዜት ለወንድ “አቡሆሙ” ማለት “አባታቸው” ሲሆን ለሴት “አቡሆን” ማለት “አባታቸው” ነው። ይህንን ካየን ዘንዳ የሚገርመው አበይት ክርስቲያኖች ማለትም ኦርቶዶስ፣ ካቶሊክ፣ ፕሮቴስታንት እና አንግሊካን፦ “ኢየሱስ አብ ሳይሆን ወልድ ብቻ ነው” ይላሉ፤ ትክክል! ምክንያቱም ኢየሱስ የእራሱን ማንነት ከአብ ነጥሎ አስቀምጧል፦
ዮሐንስ 5፥31-32 *እኔ ስለ እኔ ስለ ራሴ ብመሰክር ምስክሬ እውነት አይደለም*፤ ስለ እኔ የሚመሰክር *ሌላ ነው፥ እርሱም ስለ እኔ የሚመሰክረው ምስክር እውነት እንደ ሆነ አውቃለሁ።
ዮሐንስ 8፥18 *ስለ ራሴ የምመሰክር እኔ ነኝ፥ የላከኝም አብ ስለ እኔ ይመሰክራል*።
ዮሐንስ 12፥49 *እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና፤ ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ*።

ወልድ ማን ነው? ስንል ኢየሱስ ይሉናል፤ አብ ማን ነው? አብ ደግሞ እግዚአብሔር ነው፦
ቆላስይስ 1፥3 *የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አባት እግዚአብሔርን* ሁልጊዜ እናመሰግናለን፤
ሮሜ 15፥5 *እግዚአብሔርን፥ እርሱም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት*፥ ታከብሩ ዘንድ፥
1ቆሮንቶስ 15፥24 በኋላም፥ መንግሥቱን *ለእግዚአብሔር ለአባቱ* አሳልፎ በሰጠ ጊዜ፤
ዮሐንስ 5፥18 *እግዚአብሔር አባቴ ነው* ስላለ፥ ስለዚህ አይሁድ ሊገድሉት አብዝተው ይፈልጉት ነበር።

የኢየሱስ አባት እግዚአብሔር ከሆነ ኢየሱስ እግዚአብሔር አይደለም ማለት ነው፤ ምክንያቱም አብ እግዚአብሔር ነውና፤ እግዚአብሔር ደግሞ አንድ ነው፤ እስራኤላውያን አምላካችን የሚሉት አንዱን እግዚአብሔር ነው፣ ኢየሱስም፦ “እናንተ አምላካችን የምትሉት አባቴ ነው” ብሏል፦
ዘዳ.6:4፤ እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ *አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው*፤
ዮሐ.8:54 *እናንተ አምላካችን የምትሉት አባቴ ነው*፤

ይህ አንድ አምላክ የሁሉም አንድ አባት ነው፦
ሚልክያስ 2፥10 ለሁላችን *”አንድ አባት”* ያለን አይደለምን? *አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን*?
ማቴዎስ 23፥9 *አባታችሁ አንዱ* እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ *ማንንም፦ አባት ብላችሁ አትጥሩ*።
ዮሐንስ 8፥41 *አንድ አባት* አለን *እርሱም እግዚአብሔር ነው*፡ አሉት።
ኤፌሶን 4፥6 ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር *አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ*።
ዮሐንስ 20፥17 *እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ* ዓርጋለሁ ብለሽ ንገሪአቸው አላት።
አባትና ልጅ ለኢየሱስ እና ለእግዚአብሔር ብቻ ሳይሆን ለመላእክት ልጅነት እና ለእግዚአብሔር አባትነት አገልግሎት ላይ ውሏል። መላእክት መናፍስት ተብለዋል፤ እግዚአብሔር የመናፍስት አባት ነው። መናፍስትም የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው፦
ዕብራውያን 12፥9 እንዴትስ ይልቅ *ለመናፍስት አባት* አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር በተገባን?
ዕብራውያን 1፥14 *የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?*
ኢዮብ 38፥7 አጥቢያ ኮከቦች በአንድነት ሲዘምሩ፥ *የእግዚአብሔርም ልጆች* ሁሉ እልል ሲሉ፥

የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር በሚል ስሌት ኢየሱስን እግዚአብሔር ካረግን መላእክት የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና እግዚአብሔሮች መሆን ነበረባቸው። ኢየሱስ እግዚአብሔር ቢሆን ኖሮ “የእግዚአብሔር አባት”የሚል ቃል ታገኙ ነበር፤ ግን ኢየሱስ እግዚአብሔር ስላልሆነ 42 ቦታ ላይ “የእግዚአብሔር ልጅ” ብቻ ተብሏል፦
ሉቃስ 1፥35 ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ *የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል*።

ኢየሱስ እግዚአብሔር ቢሆን ኖሮ “እግዚአብሔር ወልድ”የሚል ቃል ታገኙ ነበር፤ ግን ኢየሱስ እግዚአብሔር ስላልሆነ እግዚአብሔር የሚባለው አብ ብቻ ስለሆነ “እግዚአብሔር አብ” የሚል ቃላት 13 ቦታ እናገኛለን፦
ያዕቆብ 1፥27 ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ *በእግዚአብሔር አብ* ዘንድ ይህ ነው፤

ባይብሉ እግዚአብሔር እና ኢየሱስን አባት እና ልጅ አርጎ ነው የሚያስቀምጠው፤ አባት ልጅ አይደለም ልጅም አባት አይደለም ካላችሁ እግዚአብሔር ኢየሱስ አይደለም፤ ኢየሱስም እግዚአብሔር አይደለም። እግዚአብሔር ለኢየሱስ ግህደተ-መለኮት”revelation” ማለትም “ወሕይ” ሰቶቷል፦
ራእይ 1፥1 *እግዚአብሔር ለኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠው ግልጠት በእርሱም የተገለጠው ይህ ነው*፥ The Revelation of Jesus Christ, which God gave unto him,
ዮሐንስ 7፥16-17 ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው፦ *ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከእኔ አይደለም*፤ ፈቃዱን ሊያደርግ የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ *ይህ ትምህርት ከእግዚአብሔር ቢሆን ወይም እኔ ከራሴ* የምናገር ብሆን ያውቃል።

“ከእግዚአብሔር ወይም እኔ ከራሴ” የሚለው ይሰመርበት፤ የሚገርመው እራሱን ከእግዚአብሔር በመለየት “እራሴ” በሚል ድርብ ተውላጠ-ስም”reflexive pronoun ” ተጠቅሟል፤ ትምህርቱ ከላከው ከእግዚአብሔር እንጂ ከራሱ አይደለም። እግዚአብሔር ለኢየሱስ የሰጠው ግልጠት በግሪክ “አፓልካሊፕስ” Ἀποκάλυψις ይባላል፤ ኢየሱስ በአንድ እግዚአብሔር እና በሰዎች መካከል እየሰማ የሚናገር ሰው ነው፦
1 ጢሞቴዎስ 2፥5፤ *አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው*፤
ዮሐንስ 8፥40 ነገር ግን አሁን *ከእግዚእብሔር የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን ሰው* ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ?
ሐዋ ሥራ 2፥22 *የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበረ*፤

እግዚአብሔር አንድ ከሆነ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን ቃል እንዲናገር ከአንድ እግዚአብሔር የተላከ መልእክተኛና አገልጋይ ነው፦
ዮሐንስ 3፥34 *እግዚአብሔር የላከው የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራልና*፤
ሐዋ ሥራ 3፥26፤ ለእናንተ አስቀድሞ *እግዚአብሔር አገልጋዩን አስነሥቶ፥ እያንዳንዳችሁን ከክፋታችሁ እየመለሰ ይባርካችሁ ዘንድ፥ ላከው*። NIV

እግዚአብሔር አንድ ከሆነ ኢየሱስ ሌሊቱንም ሁሉ ሲጸልይ ያደረው ወደዚህ ወደ አንድ እግዚአብሔር ነው፤ ይህ አንድ እግዚአብሔር ኢየሱስን ቀብቶታል፤ ለዲያብሎስም የተገዙትን እንዲፈውስ እግዚአብሔር ከኢየሱስ ጋር ነበረ፦
ሉቃስ 6፥12 በነዚህም ወራት ይጸልይ ዘንድ ወደ ተራራ ወጣ፥ *ሌሊቱንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ አደረ*።
ሐዋ ሥራ 10፥38 *እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው*፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ *እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና*፤

ክርስቶስ የእግዚአብሔር ነው፤ እግዚአብሔር የክርስቶስ ራስ ማለትም የበላይ ነው፦
1 ቆሮንቶስ 3፥23 *ክርስቶስም የእግዚአብሔር ነው*።
1 ቆሮንቶስ 11፥3 *የክርስቶስም ራስ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ልታውቁ እወዳለሁ*።

ኢየሱስ እግዚአብሔር ነው ለምትሉ አልቆላችኃል። ምክንያቱም እግዚአብሔር የኢየሱስ አባት ነው ተብላችኃል፤ ኢየሱስ ደግሞ አብ አይደለም ብላችኃል።
ስለዚህ ኢየሱስ አብ ማለትም እግዚአብሔር ሳይሆን የእግዚአብሔር ልጅ ነው፤ እግዚአብሔርም ወልድ ማለትም ኢየሱስ ሳይሆን አብ”አባት” ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ሙት ማስነሳት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

46፥33 ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ፥ እነርሱንም በመፍጠሩ ያልደከመው አላህ ሙታንን ሕያው በማድረግ ላይ ቻይ መኾኑን አላስተዋሉምን? በማስነሳት ቻይ ነው፡፡ እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና፡፡ أَوَلَمْ يَرَوْا أَنَّ اللَّهَ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَلَمْ يَعْيَ بِخَلْقِهِنَّ بِقَادِرٍ عَلَىٰ أَن يُحْيِيَ الْمَوْتَىٰ ۚ بَلَىٰ إِنَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

ሚሽነሪዎች ሁልጊዜ ቋ ያለ ጉፋያ ሃሳብ እንደ በቀቀን መደጋገም ይወዳሉ፤ የማይመክን ሃሳብ ይዞ ከመሞገት ይልቅ መንፈቅፈቁንና መነፋረቁን፥ መንሰክሰኩንና መንከንከኑን ተያይዘውታል፤ ጭራሽ ኢየሱስ ሙት ማስነሳቱ ለአምላክነቱ ማስረጃ አድርገው አርፈውታል።
አምላካችን እና ጌታችን አላህ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ፤ እነርሱንም በመፍጠሩ ያልደከመው፤ ሙታንን ሕያው በማድረግ ላይ ቻይ ነው፤ እርሱም በመጀመሪያ መደብ፦ "እኛ ሙታንን በእርግጥ ሕያው እናደርጋለን" ይለናል፦
46፥33 ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ፤ እነርሱንም በመፍጠሩ ያልደከመው አላህ ሙታንን ሕያው በማድረግ ላይ ቻይ መኾኑን አላስተዋሉምን? በማስነሳት ቻይ ነው፡፡ እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና፡፡ أَوَلَمْ يَرَوْا أَنَّ اللَّهَ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَلَمْ يَعْيَ بِخَلْقِهِنَّ بِقَادِرٍ عَلَىٰ أَن يُحْيِيَ الْمَوْتَىٰ ۚ بَلَىٰ إِنَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
36፥12 *"እኛ ሙታንን በእርግጥ ሕያው እናደርጋለን"*፡፡ ያስቀደሙትንም ሥራ ፈለጎቻቸውንም እንጽፋለን፡፡ ነገሩንም ሁሉ ገላጭ መሪ በኾነ መጽሐፍ ውስጥ አጠቃለልነው፡፡ إِنَّا نَحْنُ نُحْيِي الْمَوْتَىٰ وَنَكْتُبُ مَا قَدَّمُوا وَآثَارَهُمْ ۚ وَكُلَّ شَيْءٍ أَحْصَيْنَاهُ فِي إِمَامٍ مُّبِينٍ

"ትንሳኤ" ለሚለው የግስ መደብ የገባው ቃል "አቃመ" أَقَامَ "አሕያ" أَحْيَا "በዐሰ" بَعَثَ ነው። ይህንን ቃል ይዘን ወደ ባይብል ከገባን በባይብል ሙት አስነሺ የተባለው ኢየሱስ ብቻ ሳይሆን ሐዋርያት እና ነቢያትም ጭምር ናቸው፦
ማቴዎስ 10፥8 ድውዮችን ፈውሱ፤ *"ሙታንን አስነሡ"*፤ ለምጻሞችን አንጹ፤ አጋንንትን አውጡ፤ በከንቱ ተቀበላችሁ፥ በከንቱ ስጡ። اشفُوا المَرضَى، أقِيمُوا المَوتَى، اشفُوا البُرصَ، أخرِجُوا الأرواحَ الشِّرِّيرَةَ. أخَذْتُمُ السُّلطانَ لِعَمَلِ ذَلِكَ مَجّاناً، فَأعطُوا الآخَرِينَ مَجّاناً أيضاً.

"አስነሱ" ለሚለው ቃል "አቂሙ" أقِيمُوا በሚል መጥቷል፤ ታዲያ ሐዋርያቱ አምላክ ነበሩን? ኢየሱስ የሠራውን ሥራ በእርሱ መልእክተኝነት ያመኑ ሰዎችም እርሱ ከሠራው ሥራ ይበልጥ ሊሠሩ እንደሚችሉ እራሱ ተናግሯል፦
ዮሐንስ 14፥13 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን *”እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል”*፥

በዚህ መሰረት በኢየሱስ ነብይነት ያመኑት ሃዋርያትም ኢየሱስ የሠራውን ሥራ ማለትም ሰው ከሞት ማስነሳት ሠርተውቷል፦
የሐዋርያት ሥራ 9:40 ጴጥሮስም ሁሉን ወደ ውጭ አስወጥቶ ተንበርክኮም ጸለየ፥ *"ወደ ”ሬሳውም ዘወር ብሎ። ጣቢታ ሆይ፥ ”ተነሺ” አላት። እርስዋም ዓይኖችዋን ከፈተች ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ተቀመጠች"*።

ብሉይ ኪዳን ላይ የነበሩት ሁለት ነቢያት ኤልያስ እና ኤልሳዕ የሁለት ሴቶችን ልጆች አስነስተዋል፦
1. ኤልያስ፦
1ኛ ነገሥት 17፥21-23 *በብላቴናውም ላይ ሦስት ጊዜ ተዘረጋበት፥ ወደ እግዚአብሔርም። አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ የዚህ ብላቴና ነፍስ ወደ እርሱ ትመለስ ዘንድ እለምንሃለሁ ብሎ ጮኸ፤ እግዚአብሔርም “የኤልያስን ቃል ሰማ፤ የብላቴናው ነፍስ ወደ እርሱ ተመለሰች”፥ እርሱም ዳነ፤ ኤልያስም ብላቴናውን ይዞ ከሰገነቱ ወደ ቤት አወረደው፥ ኤልያስም። እነሆ፥ “ልጅሽ በሕይወት ይኖራል” ብሎ ለእናቱ ሰጣት*።

2. ኤልሳዕ፦
1ኛ ነገሥት 4፥32-34 *ኤልሳዕም ወደ ቤት በገባ ጊዜ እነሆ፥ “ሕፃኑ ሞቶ” በአልጋው ላይ ተጋድሞ ነበር። ገብቶም በሩን ከሁለቱ በኋላ ዘጋ፥ ወደ እግዚአብሔርም ጸለየ፤ መጥቶም በሕፃኑ ላይ ተኛ፤ “አፉንም በአፉ፥ ዓይኑንም በዓይኑ፥ እጁንም በእጁ ላይ አድርጎ ተጋደመበት፤ የሕፃኑም ገላ ሞቀ”፤ ተመልሶም በቤቱ ውስጥ አንድ ጊዜ ወዲህና ወዲያ ተመላለሰ፤ ደግሞም ወጥቶ ሰባት ጊዜ በሕፃኑ ላይ ተጋደመ፤ ሕፃኑም ዓይኖቹን ከፈተ*።

የዕብራውያን ጸሐፊ ይህንን ጉዳይ በማስታወስ በኤልያስ እና በኤልሳዕ ዘመን የነበሩት ሁለት ሴቶሽ ሙታን ልጆቻቸውን በትንሳኤ ተቀበሉ ይለናል፦
11፥35 *ሴቶች ሙታናቸውን “በትንሣኤ” ተቀበሉ*፤

ልብ በል “ትንሳኤ” የተባለው በብሉይ ኪዳን ሁለት ነብያት የሞቱ ሰዎችን ያስነሱትን የሴቶችን ህፃናት እንደሆነ እሙንና ቅቡል ነው፤ ታዲያ ሁለት ነቢያት ኤልያስ እና ኤልሳዕ የሁለት ሴቶችን ልጆች ስላስነሱ አምላክ ናቸውን? አይ፦ "ሐዋርያቱ እና ነቢያቱ ሙት ያስነሱት በጸሎት ነው" ይሉናል፤ ኢየሱስስ ጸልዮ እኮ ነው ሙት ያስነሳው፤ ኢየሱስ እግዚአብሔርን ለምኖ ሰዎች እግዚአብሔር እንዳላከው እንዲያምኑበት የተሰጠው ስራ እንደሆነ ተናግሯል፦
ዮሐንስ 11፥41-44 ድንጋዩንም አነሡት። *ኢየሱስም ዓይኖቹን ወደ ላይ አንሥቶ። “አባት ሆይ፥ ስለ ሰማኸኝ አመሰግንሃለሁ፤ ሁልጊዜም እንድትሰማኝ” አወቅሁ፤ ነገር ግን “አንተ እንደ ላክኸኝ ያምኑ ዘንድ” በዚህ ዙሪያ ስለ ቆሙት ሕዝብ ተናገርሁ አለ። ይህንም ብሎ በታላቅ ድምፅ። አልዓዛር ሆይ፥ ወደ ውጭ ና ብሎ ጮኸ። የሞተውም እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደ ተገነዙ ወጣ፤ ፈቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበር። ኢየሱስም። ፍቱትና ይሂድ ተዉት አላቸው*።

ኢየሱስ የሚያደርጋቸው ታምራት ሁሉ በፈጣሪ ስም እንጂ ከራሱ ምንም ማድረግ አይችልም፦
ዮሐንስ 10፥25 ኢየሱስም መለሰላቸው፥ እንዲህ ሲል። ነገርኋችሁ አታምኑምም *”እኔ በአባቴ ስም የማደርገው ሥራ ስለ እኔ ይመሰክራል"*።
ዮሐንስ 5:30 *”እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም”*፤

እንዴት አምላክ የሆነ ህላዌ "ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም" ይላል? እንዴትስ አምላክ የሆነ ህላዌ በሌላ ማንነትና ምንነት ስም ታምር ያደርጋል? ጭራሽኑ የሚያደርጋቸው ሥራዎች ከፈጣሪ በጸጋ ያገኛቸው እንደሆኑ እና ለእርሱ መእክተኛነት ማስረጃ እንደሆኑ አበክሮ እና አዘክሮ ይናገራል፦
ዮሐንስ 17፥4 እኔ ላደርገው *የሰጠኸኝን* ሥራ ፈጽሜ በምድር አከበርሁህ፤
ዮሐንስ 5፥36 አብ ልፈጽመው *የሰጠኝ* ሥራ” ይህ የማደርገው ሥራ፥ አብ እንደ ”ላከኝ” ስለ እኔ ይመሰክራልና።
ዮሐንስ 11፥42 ሁልጊዜም እንድትሰማኝ አወቅሁ፤ ነገር ግን *”አንተ እንደ ላክኸኝ ያምኑ ዘንድ"* በዚህ ዙሪያ ስለ ቆሙት ሕዝብ ተናገርሁ አለ።
የየናዝሬቱ ኢየሱስ ያደረጋቸው ተአምራት፣ ድንቆች እና ምልክቶችም እግዚአብሔር በኢየሱስ በኩል ያደረገው ነው፤ በተጨማሪም ከእግዚአብሔር ለእስራኤል ሰዎች የተላከ ሰው መሆኑን በአጽንዖትና በአንክሮት የሚያሳይ ነው፦
የሐዋርያት ሥራ 2፥22 የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁ፥ *የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ “በእርሱ”” በኩል ባደረገው “”ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም” ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእስራኤል ሰዎች የተላከ ሰው ነበረ፤ ይህ ሰው በራሱ ፈቃድ ሳይሆን በላከውን ፈቃድ ሙት ሲያስነሳ የነበረ ሰው ነው፦
ዮሐንስ 5፥30 *እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም"*፤ እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፥ *"የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና"*።

አምላካችን እና ጌታችን አላህም ዒሣ ምን አስተምሮ እንደነበር በተናገረበት አንቀጽ ላይ ዒሣ ሙት ማስነሳቱ ለመልእክተኛነቱ ማስረጃ እንደሆነ ነግሮናል፦
3፥49 ወደ እስራኤልም ልጆች መልክተኛ ያደርገዋል፡፡ ይላልም፡- «እኔ ከጌታዬ ዘንድ በተዓምር ወደ እናንተ መጣሁ፡፡ እኔ ለናንተ ከጭቃ እንደ ወፍ ቅርፅ እፈጥራለሁ፡፡ በርሱም እተነፍስበታለሁ፡፡ በአላህም ፈቃድ ወፍ ይኾናል፡፡ በአላህም ፈቃድ ዕውር ኾኖ የተወለደን፣ ለምጸኛንም አድናለሁ፡፡ ሙታንንም *"አስነሳለሁ"*፡፡ የምትበሉትንና በቤታችሁ የምታደልቡትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ፡፡ የምታምኑ እንደኾናችሁ ለእናንተ በዚህ ውስጥ በእርግጥ ተዓምር አለበት፡፡» وَرَسُولًا إِلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ أَنِّي قَدْ جِئْتُكُم بِآيَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ ۖ أَنِّي أَخْلُقُ لَكُم مِّنَ الطِّينِ كَهَيْئَةِ الطَّيْرِ فَأَنفُخُ فِيهِ فَيَكُونُ طَيْرًا بِإِذْنِ اللَّهِ ۖ وَأُبْرِئُ الْأَكْمَهَ وَالْأَبْرَصَ وَأُحْيِي الْمَوْتَىٰ بِإِذْنِ اللَّهِ ۖ وَأُنَبِّئُكُم بِمَا تَأْكُلُونَ وَمَا تَدَّخِرُونَ فِي بُيُوتِكُمْ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لَّكُمْ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ

ስለዚህ ኢየሱስ በአላህ ፈቃድ ሙት ማስነሳቱ ለእርሱ መልእክተኛነት ማስረጃ መሆኑን እንረዳለን እንጂ ጭራሽ ለአምላክነት ሸርጥ ነው ብሎ እንደ ደሊል መረጃ ማቅረብ እጅግ በጣም ሲበዛ ቂልነት ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ገለባ ክስ

ክፍል አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

15፡95 ተሳላቂዎችን ሁሉ እኛ በቅተንሃል إِنَّا كَفَيْنَٰكَ ٱلْمُسْتَهْزِءِينَ ፡፡

መግቢያ
ለእስልምና መልስ በሚል ድህረ-ገፅ ላይ የነቢያችንን”ﷺ” ነብይነትን ከንቱ ለማድረግ ሳም ሻሙስ የተባለ ተሳላቂ ነብያችን”ﷺ” ትንቢት ተናግረው ያ ትንቢት እንዳልተፈፀመና አንድ ነብይ ትንቢት ተናግሮ ያ ትንቢት ካልተፈፀመ ሐሳዌ ነብይ እንደሚያስብለው ሁሉ ነብያችንን”ﷺ” ሐሳዌ ነብይ ለማድረግ ወሊአዑዙቢላህ ሲቃጣው ይታያል፤ አንድ ሐሳዌ ነብይ ነብይነቱ ውድቅ የሚሆንበት በሁለት ምክንያት ነው፤ አንደኛ የሚናገረው ከገዛ ልቡ ከሆነ እና ሁለተኛ ከሸይጣን ከሆነ ነው፤ ነገር ግን ነብያችን”ﷺ” ከገዛ ልባችው ወይም ከሌላ አካል አላህ ካላቸው ውጪ ምንም እንደማይናገሩ ለተሳላቂዎች ትችት በቅቶላቸዋል፦
53፥3-4 ከልብ ወለድም አይናገርም وَمَا يَنطِقُ عَنِ ٱلْهَوَىٰٓ ፡፡
እርሱ ንግግሩ የሚወርረድ ራእይ እንጅ ሌላ አይደለም إِنْ هُوَ إِلَّا وَحْىٌۭ يُوحَىٰ ፡፡
69፥44-46 በእኛ ላይም ከፊልን ቃላት ያላልነውን በቀጠፈ ኖሮ وَلَوْ تَقَوَّلَ عَلَيْنَا بَعْضَ ٱلْأَقَاوِيلِ ፤ በኀይል በያዝነው ነበር لَأَخَذْنَا مِنْهُ بِٱلْيَمِينِ ፡፡ ከዚያም ከእርሱ የልቡን ሥር በቆረጥን ነበር ثُمَّ لَقَطَعْنَا مِنْهُ ٱلْوَتِينَ ፡፡

ይህንን እሳቤ ይዘን በነቢያችንን”ﷺ” ላይ የተሰጡት ገለባ ክሶች አንድ በአንድ በአላህ ፈቃድ ጥርስ እና ምላሱን እየነቀስን ጥልልና ጥንፍፍ ባለ መልኩ እናየዋለን፦

ገለባ አንድ
ሱነን አቢ ዳውድ :መጽሐፍ 39, ሐዲስ 6
የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ በታላቁ ጦርነት እና በከተማይቱ ውድቀት መካከል ያለው ጊዜ ስድስት ዓመት ነው፤ በሰባተኛው ዓመት ደጃል ይወጣል፤ ዘገባው ደኢፍ ነው أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ بَيْنَ الْمَلْحَمَةِ وَفَتْحِ الْمَدِينَةِ سِتُّ سِنِينَ وَيَخْرُجُ الْمَسِيحُ الدَّجَّالُ فِي السَّابِعَةِ ‏”‏ ‏.‏ قَالَ أَبُو دَاوُدَ هَذَا أَصَحُّ مِنْ حَدِيثِ عِيسَى ‏.‏ ضعيف ።

ትችቱ ሲጀምር፦ “ቆንስጣንጥኒያ የወደቀችው እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር ግንቦት 29 በ 1453 AD ነው፤ ከ 1453-1461 ደጃል መምጣት ነበረበት፤ ይህ ትንቢት ሳይፈፀም ይኸው 556 ዓመት አስቆጠረ፤ ስለዚህ ትንቢቱ ከሽፏል” ወሊአዑዙቢላህ፤ ሲጀመር ሐዲሱ ላይ “አል-መዲናህ” الْمَدِينَةِ ማለትም “ከተማይቱ” አለ እንጂ በስም መቼ ተጠቀሰ? ሲቀጥል ከተማይቱ የሚለው ቆንስጣንጥኒያ ብንል እንኳን በሰለፎች አረዳድ ቆንስጣንጥኒያ መላውን አውሮፓ እንጂ ኦቶማን ግንቦት 29 1453 AD የተቆጣጠራትን ከተማ ነው ማን ነው ያለው?፦
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 36, ሐዲስ 167
ጃቢር አለ፦ ደጃል አይመጣም እናንተ ከሮማዎች ሳትታገሉ قَالَ جَابِرٌ فَمَا يَخْرُجُ الدَّجَّالُ حَتَّى تُفْتَحَ الرُّومُ ‏ ።
በተመሳሳይ ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 54, ሐዲስ 50 ላይም ተዘግቧል፦
ጃቢር አለ፦ ደጃል አይመጣም እናንተ ከሮማዎች ሳትታገሉ قَالَ فَقَالَ نَافِعٌ يَا جَابِرُ لاَ نَرَى الدَّجَّالَ يَخْرُجُ حَتَّى تُفْتَحَ الرُّومُ ‏ ።

እንግዲህ ከተማይቱ የሚለው በዚህ ሪዋያ ሮማዎች ማለትም አውሮፓውያን እንደሆኑ ስለተገለፀ ኦቶማን የያዛት ከተማ ናት የሚለው ገለባ ክስ ድባቅ ይገባል። ምክንያቱን ታላቁ ቆስጠንጥኒዎስ በ 330 AD ባዛንታይንን መሰረት ያደረገ የቆስጠንጥንያ ግዛት መላውን አውሮፓ ያካልል ነበር። ሲሰልስ ሐዲሱ ደረጃው በሸኽ አልባኒ ከመነሻው “ደኢፍ” ضعيف ነው ተብሎ መዝጊያው ላይ ተቀምጧል፤ የሚሽነሪዎች ትልቁ ችግራቸው አንደኛ ታማኝ የሆኑ ምንጮች አለመጠቀማቸው ሲሆን ሁለተኛ የኢስላም መጽሐፍት ሥረ-መሰረቱ”orgin” አረቢኛው እያለ ከጎግል በሚገኘው ትርጉም ላይ መንጠልጠላቸው ነው፤ ሚሽነሪዎች ሥነ-ሐዲስ ጥናት መሰረታዊ ጭብጦች ለማወቅ ፍላጎቱም የላቸውም፤ ምክንያቱም ኃሳውያን ሚሽነሪዎች ኃሳዊ ትምህርታቸው ጽርፈት ማለትም ክህደት ነውና፤ ለዛ ነው ዓሊሞቻችን ያስቀመጡትን የደርስ መዋቅርና መርሃ ግብር ዕቡይ ተግዳሮት የሚሆንባቸው፤ እኔ ለአንባቢያን ስለ ሐዲስ በግርድፉና በሌጣው ከሙስጠለሑል ሐዲስ ልጀምር፤ “ሙስጠለሑል ሐዲስ” مُصْطَلَحُ الحَدِيْث‌‎ ማለት የሐዲስ ስያሜ”Hadith terminology” ናቸው፤ እነርሱም፦ ሰሒሕ፣ ሐሠን፣ ደኢፍ እና መውዱዕ ናቸው፤ ከላይ የተተቸበት ሐዲስ ደኢፍ ይባላል። “ደኢፍ” ضَعِيْف ማለት “ደካማ”weak” ማለት ሲሆን አንድን ዘገባ ደካማ የሚያሰኘው ወደ ሙሐዲስ የሚመጣበት አካሔድ ደካማ መሆኑ ነው። “ሙሐዲስ”محديث‎ ማለት “ዘጋቢ”collector” ማለት ሲሆን እነዚህም ሙሐዲሲን ኢማም ቡኻሪይ፣ ኢማም ሙስሊም፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጃህ፣ አቢ ዳውድ፣ ነሳኢ ወዘተ ናቸው፤ አንድ ዘገባ ደካማ ነው የሚያሰኘው አምስት ሸርጦች አሉት፤ እነርሱም፦
1ኛ. “ሙአለቅ”
“ሙአለቅ” مُعَلَّق ማለት በሙሐዲስ እና በነብያችን”ﷺ” መካከል ምንም አይነት ተራኪና ትረካ ሳይኖር ሲቀር “ሙአለቅ” ይባላል።
2ኛ. “ሙርሰል”
“ሙርሠል”مُرْسَل ማለት በነብያችን”ﷺ” እና በዘጋቢው መካከል ተራኪ ከሌለው ግን ትረካ ካለው “ሙርሰል” ይባላል።
3ኛ. “ሙንቀጢዕ”
“ሙንቀጢዕ” مُنْقَطِع ማለት በነብያችን”ﷺ” እና በተራኪው መካከል ትረካ ከሌለው “ሙንቀጢዕ” ይባላል።
4ኛ. “ሙንከር”
“ሙንከር” مُنْكَر በደካማ ተራኪ ተተርኮ ትረካው ከሰሒሕ ዘገባ ጋር ከተጋጨ “ሙንከር” ይባላል።
5ኛ. “ሙጠሪብ”
“ሙጠሪብ” مُضْطَرِب ማለት አንድ ሐዲስ የተቃረኑ የዘገባ ሰነዶች ሲኖሩት ወይንም ዘገባው የተቃረኑ መትኖች ሲኖሩት “ሙጠሪብ” ይባላል።

ይህ ትውልድ የኢስላም ታሪክ ምፀት ለሚቀጥለው ትውልድ የሚሆን ሰፊ ምዕላድ ትተን መሄድ ግድ ይላል፤ ሚሽነሪዎች እየቀጠፉ አይኖሯትም፤ ኢንሻላህ ገለባው ክስ ድባቅ የሚገባበት ሙግት ይቀጥላል…

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ገለባ ክስ

ክፍል ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

15፡95 ተሳላቂዎችን ሁሉ እኛ በቅተንሃል إِنَّا كَفَيْنَٰكَ ٱلْمُسْتَهْزِءِينَ ፡፡

ገለባ ሁለት
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 3 , ሐዲስ 58:
ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፤ ነብዩም"ﷺ" በመጨረሻቸው ህይወት በኢሻህ ሶላት ላይ መሩንና እንዲህ አሉ፦ "ይህን ሌሊት አጢናችሁታል? ከዚህ ሌሊት እስከ መቶ ሙሉ ዓመት በኃላ በምድር ወለል ማንም አይኖርም" حَدَّثَنَا سَعِيدُ بْنُ عُفَيْرٍ، قَالَ حَدَّثَنِي اللَّيْثُ، قَالَ حَدَّثَنِي عَبْدُ الرَّحْمَنِ بْنُ خَالِدٍ، عَنِ ابْنِ شِهَابٍ، عَنْ سَالِمٍ، وَأَبِي، بَكْرِ بْنِ سُلَيْمَانَ بْنِ أَبِي حَثْمَةَ أَنَّ عَبْدَ اللَّهِ بْنَ عُمَرَ، قَالَ صَلَّى بِنَا النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم الْعِشَاءَ فِي آخِرِ حَيَاتِهِ، فَلَمَّا سَلَّمَ قَامَ فَقَالَ ‏ "‏ أَرَأَيْتَكُمْ لَيْلَتَكُمْ هَذِهِ، فَإِنَّ رَأْسَ مِائَةِ سَنَةٍ مِنْهَا لاَ يَبْقَى مِمَّنْ هُوَ عَلَى ظَهْرِ الأَرْضِ أَحَدٌ ‏"‌‏.‏ ።

በዚህ ሐዲስ መሰረት ሳም ሻሙስ፦ "ይህንን ነብያችን"ﷺ" ሲናገሩ በ 632 AD ነው፤ ከዚህ ቀን ጀምሮ መቶ ዓመት ሲቆጠር 732 AD ትንሳኤ ቆሞ ሁሉም ሰው አይኖርም፤ ግን ይኸው 1285 ዓመት አለፈው፤ ስለዚህ የተነገረው ትንቢት ከሽፋል" የሚል ስሁት ሙግት ያቀርባል፤ አለማወቅ በራሱ ኀጢአት አይደለም፤ ከመተቸት በፊት ይህ ምንድን ነው? ብሎ መጠየቅ ብልህነት ነው፤ አምላካችን አላህ፦ 16፥43 "የማታውቁ ብትሆኑ የዕውቀት ባለቤቶችን ጠይቁ" ይላል፤ እኛም ደረሳ እንደመሆናችን መጠን ኡስታዞቻችን ጠይቀን ያገኘነው መልስ፦ "በነብያችን"ﷺ" ጊዜ ከቆሙት ሰዎች ከመቶ ዓመት በኃላ ማንም አይኖርም ይሞታል" የሚል ነው፤ ይህንን ደሊል የሆነ ሐዲስ እራሱ ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር በተረከው ሐዲስ ላይ እንዲህ ተቀምጧል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 9 , ሐዲስ 77:
ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፤ ነብዩም"ﷺ" በመጨረሻቸው ህይወት በኢሻህ ሶላት ላይ አሰላምተው ሲጨርሱ ቆሙና እንዲህ አሉ፦ "ይህን ሌሊት አጢናችሁታል? ከዚህ ሌሊት እስከ መቶ ሙሉ ዓመት በኃላ በምድር ወለል ማንም አይኖርም"፤ ይህንን የአላህን መልክተኛ"ﷺ" አነጋገር ሰዎች በተሳሳተ ነው የተረዱት፤ አንዳንድ ተራኪዎች( የመጨረሻው ቀን ከመቶ አመት በኃላ ይሆናል) ብለው ተረዱት፤ ነገር ግን ነብዩ"ﷺ" ለማለት የፈለጉት፦ " ያ ክፍለ ዘመን ትውልድ ያልፋል" ነው أَنَّ عَبْدَ اللَّهِ بْنَ عُمَرَ، قَالَ صَلَّى النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم صَلاَةَ الْعِشَاءِ فِي آخِرِ حَيَاتِهِ، فَلَمَّا سَلَّمَ قَامَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم فَقَالَ ‏"‏ أَرَأَيْتَكُمْ لَيْلَتَكُمْ هَذِهِ فَإِنَّ رَأْسَ مِائَةٍ لاَ يَبْقَى مِمَّنْ هُوَ الْيَوْمَ عَلَى ظَهْرِ الأَرْضِ أَحَدٌ ‏"‌‏.‏ فَوَهِلَ النَّاسُ فِي مَقَالَةِ رَسُولِ اللَّهِ ـ عَلَيْهِ السَّلاَمُ ـ إِلَى مَا يَتَحَدَّثُونَ مِنْ هَذِهِ الأَحَادِيثِ عَنْ مِائَةِ سَنَةٍ، وَإِنَّمَا قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ لاَ يَبْقَى مِمَّنْ هُوَ الْيَوْمَ عَلَى ظَهْرِ الأَرْضِ ‏"‏ يُرِيدُ بِذَلِكَ أَنَّهَا تَخْرِمُ ذَلِكَ الْقَرْنَ‏.‏ ።

ገለባ ሶስት
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 54 , ሐዲስ 172:
ዓኢሻ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ የዐረብ ቆለኞች የሆኑትም ወደ አላህ መልእክተኛ"ﷺ" በመምጣት ስለ ሰዓቲቱ ጠየቋቸው፤ እርሳቸውም በዕድሜ ትንሽ የሆነውን ተመልክተው፦ "ይህ ልጅ እርጅና ሳያገኘው ማደግ ከቻለ የእናንተ ሰዓታችሁ በእናንተ ላይ ትመጣለች" ብለው አሉ عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ كَانَ الأَعْرَابُ إِذَا قَدِمُوا عَلَى رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم سَأَلُوهُ عَنِ السَّاعَةِ مَتَى السَّاعَةُ فَنَظَرَ إِلَى أَحْدَثِ إِنْسَانٍ مِنْهُمْ فَقَالَ ‏ "‏ إِنْ يَعِشْ هَذَا لَمْ يُدْرِكْهُ الْهَرَمُ قَامَتْ عَلَيْكُمْ سَاعَتُكُمْ ‏"‏ ።

"ሣዐቱኩም" سَاعَتُكُمْ ማለት "የእናንተ ሰአት" ማለት እንጂ የቂያማ ቀን ሰአት በፍፁም አያመለክትም፤ ምክንያቱም "ኩም" ُكُمْ የሚለው ተሳቢ ተውላጠ ስም በሁለተኛ መደብ ያሉትን የዐረብ ቆለኞች ስለሚያመለክት ነው። ህፃኑ አድርጎ ከማርጀቱ በፊት የዐረብ ቆለኞች የመሞቻ ቀናቸው ወደ እነርሱ ይመጣል፤ ለዛ ነው "ዐለይኩም" عَلَيْكُمْ የሚል ሁለተኛ መደብ ያለበት ተውላጠ ስም ላይ መስተዋድድ መነሻ ቅጥያ ሆኖ የገባው፤ መጨረሻ የሚለው ቃል ለትንሳኤ ቀን ብቻ ሳይሆን ለሞት ቀንም ያገለግላል፤ "ሞት" የሰዎችን ህይወት ሰአት መጨረሻ የሚያደርግ የቂን ነው፦
15:99 "እውነቱም (ሞት) እስኪመጣህ ድረስ" ጌታህን አምልከው وَٱعْبُدْ رَبَّكَ حَتَّىٰ يَأْتِيَكَ ٱلْيَقِينُ ፡፡
62፥8 "ያ ከእርሱ የምትሸሹት ሞት እርሱ በእርግጥ የሚመጣባችሁ ነው፡፡ ከዚያም ሩቁንና ቅርቡን ዐዋቂ ወደ ኾነው ጌታ ትመለሳላችሁ፡፡ ትሠሩትም የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል" በላቸው قُلْ إِنَّ ٱلْمَوْتَ ٱلَّذِى تَفِرُّونَ مِنْهُ فَإِنَّهُۥ مُلَٰقِيكُمْ ۖ ثُمَّ تُرَدُّونَ إِلَىٰ عَٰلِمِ ٱلْغَيْبِ وَٱلشَّهَٰدَةِ فَيُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ ፡፡
63፥10 "አንዳችሁንም ሞት ሳይመጣው" እና ጌታዬ ሆይ! እንድመጸውትና ከደጋጐቹም ሰዎች እንድኾን ወደ ጥቂት ጊዜ ብታቆየኝ ኖሮ እመኛለሁ ከማለቱ በፊት ከሰጠናችሁ ሲሳይ ለግሱ وَأَنفِقُوا۟ مِن مَّا رَزَقْنَٰكُم مِّن قَبْلِ أَن يَأْتِىَ أَحَدَكُمُ ٱلْمَوْتُ فَيَقُولَ رَبِّ لَوْلَآ أَخَّرْتَنِىٓ إِلَىٰٓ أَجَلٍۢ قَرِيبٍۢ فَأَصَّدَّقَ وَأَكُن مِّنَ ٱلصَّٰلِحِينَ ፡፡

ኢንሻላህ ይቀጥላል.....ድምዳሜውን በባይብል ትንቢት እንደመድማለን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም