ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
69 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ጥያቄዎቻችን!

የአብያ እናት ማን ናት? የማንስ ልጅ ናት? የነገሥት ጸሐፊ፦ "እናቱ መዓካ ናት፣ የአቤሴሎም ልጅ ናት" ይለናል።
የዜና መዋዕል ጸሐፊ ደግሞ፦ "ሚካያ ናት፣ የገብዓ ሰው የኡርኤል ልጅ ናት" ይለናል።
የቱ ነው ትክክል?

A. እናቱ መዓካ ናት፣ የአቤሴሎም ልጅ ናት፦
1 ነገሥት 15፥2 በኢየሩሳሌምም ሦስት ዓመት ነገሠ፤ *እናቱም መዓካ የተባለች የአቤሴሎም ልጅ ነበረች*።

B. እናቱ ሚካያ ናት፣ የገብዓ ሰው የኡርኤል ልጅ ናት፦
2 ዜና 13፥2 ሦስት ዓመት በኢየሩሳሌም ነገሠ፤ *የእናቱም ስም ሚካያ ነበረ፥ የገብዓ ሰው የኡርኤል ልጅ ነበረች*።

የአብያ እናት ማን ናት? መዓካ ወይስ ሚካያ? የማንስ ልጅ ናት? የአቤሴሎም ልጅ ወይስ የገብዓ ሰው የኡርኤል ልጅ?

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ጂሃድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥35 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ ወደ እርሱም መቃረቢያን መልካም ሥራን ፈልጉ፡፡ ትድኑ ዘንድም *በእርሱ መንገድ ታገሉ*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَابْتَغُوا إِلَيْهِ الْوَسِيلَةَ وَجَاهِدُوا فِي سَبِيلِهِ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ

“ጂሃድ” جِهَاد የሚለው ቃል “ጃሀደ” جَٰهَدَ ማለትም “ታገለ” ወይም “ጣረ” አሊያም “ተጋደለ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ትግል” ወይም “ጥረት” አሊያም “ገድል” ማለት ነው፤ “ጁሁድ” جُهْد ማለት ደግሞ “መጣጣር” “መታገል” “መጋደል” ነው፤ እውነትን ለማንገስ ሃሰትን ለማርከስ፥ ከሙገሳ እና ከወቀሳ ነጻ ሆኖ በአላህ መንገድ የሚታገል፣ የሚጥርና የሚጋደል በነጠላ “ሙጃሂድ” مُجَٰهِد ይባላል፤ በብዜት ደግሞ “ሙጃሂዲን” مُجَٰهِدِين ይባላሉ። ፊቅህ” فقه ማለት “ጥልቅ መረዳት” ማለት ሲሆን የሥነ-ሕግ ጥናት”the study of law” ነው፤ ሕግ ዐዋቂ ደግሞ “ፈቂህ” فقيه ይባላል፤ በፊቂህ ጥናት ውስጥ “ኢጅቲሀድ” ትልቁን ቦታ ይይዛል፤ “ኢጅቲሀድ” اجتهاد‌‎ ማለት ቁርኣንና ሱናህን ባማከለ ሁኔታ የሚደረግ ፍለጋ ወይም ግኝት “ኢጅቲሀድ” ይባላል፤ ዐዋቂ ሆኖ የሚያደርገው ሰው ደግሞ “ሙጅተሂድ” مجتهد‎ ይባላል።

እዚህ ድረስ ቋንቋዊ ፍቺውን ካየን ዘንድ አሁን ደግሞ ሃይማኖታዊ ትንታኔውን እናያለን፤ ሠቢል” سَبِيل ማለት “መንገድ” ማለት ሲሆን ጂሃድ በምን መንገድ? የሚለውን ጥያቄ ማስተናገድ ግድ ነው፤ ምክንያቱም በነፍሲያህ መንገድ ወይም በዝንባሌ መንገድ ሰው ሲጥር፣ ሲታገልና ሲጋደል ስለሚታይ ማለት ነው። ነገር ግን እውነተኛ ጂሃድ “ፊ ሰብሊልላህ” فِي سَبِيلِ ٱللَّه ማለትም “በአላህ መንገድ” ነው፤ በአላህ መንገድ ለአላህ ተብሎ ወይም አላህ ባስቀመጠልን መስፈርት ብቻ ማለት ነው፤ ለምሳሌ፦
2፥195 *በአላህም መንገድ ለግሱ፡፡ በእጆቻችሁም ነፍሶቻችሁን ወደ ጥፋት አትጣሉ፡፡ በጎ ሥራንም ሥሩ፤ አላህ በጎ ሠሪዎችን ይወዳልና*፡፡ وَأَنفِقُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَلَا تُلْقُوا بِأَيْدِيكُمْ إِلَى التَّهْلُكَةِ ۛ وَأَحْسِنُوا ۛ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُحْسِنِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ ልግስና “በአላህ መንገድ” መባሉ በራሱ “እዩልኝና ስሙልኝ” ያልተቀላቀለበት እንደሆነ ሁሉ ጅሃድም በእርሱ መንገድ ብቻ መሆን አለበት፦
5፥35 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ ወደ እርሱም መቃረቢያን መልካም ሥራን ፈልጉ፡፡ ትድኑ ዘንድም *በእርሱ መንገድ ታገሉ*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَابْتَغُوا إِلَيْهِ الْوَسِيلَةَ وَجَاهِدُوا فِي سَبِيلِهِ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ

“ታገሉ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ጃሂዱ” َجَاهِدُوا ሲሆን “በእርሱ መንገድ” ብቻ ነው፤ ነብያችንም”ﷺ” በአላህ መንገድ ስለሚደረገው ጂሃድ እንዲህ ይሉናል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 25 , ሐዲስ 7:
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው፦ *“ነብዩን”ﷺ” የትኛው ነው የተሻለ ሥራ? ብለው ጠይቀው ነበር፤ እርሱም፦ “በአላህ እና በመልእክተኛው ማመን” አለ፤ በመቀጠልስ? ብሎ ጠየቀ፤ “በአላህ መንገድ ጂሃድ ላይ መሳተፍ” አለ፤ በመቀጠልስ? ብሎ ጠየቀ፤ “ሐጅ መብሩር” አለ*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ سُئِلَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم أَىُّ الأَعْمَالِ أَفْضَلُ قَالَ ‏”‏ إِيمَانٌ بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ ‏”‌‏.‏ قِيلَ ثُمَّ مَاذَا قَالَ ‏”‏ جِهَادٌ فِي سَبِيلِ اللَّهِ ‏”‌‏.‏ قِيلَ ثُمَّ مَاذَا قَالَ ‏”‏ حَجٌّ مَبْرُورٌ ‏”‌‏.‏
ይህም ጂሃድ ወሰን አልፈው ለሚመጡ ሁሉ በእርሱ መንገድ መጋደልን ይጨምራል፦
2፥190 *እነዚያንም የሚጋደሉዋችሁን በአላህ መንገድ ተጋደሉ፡፡ ወሰንንም አትለፉ፤ አላህ ወሰን አላፊዎን አይወድምና*፡፡ وَقَاتِلُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ الَّذِينَ يُقَاتِلُونَكُمْ وَلَا تَعْتَدُوا ۚ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْمُعْتَدِينَ
2፥218 *እነዚያ ያመኑትና እነዚያም ከአገራቸው የተሰደዱት በአላህም መንገድ ላይ የተጋደሉት እነዚያ የአላህን እዝነት ይከጅላሉ*፡፡ አላህም እጅግ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَالَّذِينَ هَاجَرُوا وَجَاهَدُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ أُولَـٰئِكَ يَرْجُونَ رَحْمَتَ اللَّهِ ۚ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
2፥193 *ሁከት እስከማይገኝ እና ሃይማኖት ለአላህ ብቻ እስከሚኾን ድረስ ተጋደሉዋቸው፡፡ ቢከለክሉም ወሰንን ማለፍ በበዳዮች ላይ እንጂ የለም ወሰን አትለፉባቸው*፡፡ وَقَاتِلُوهُمْ حَتَّىٰ لَا تَكُونَ فِتْنَةٌ وَيَكُونَ الدِّينُ لِلَّهِ ۖ فَإِنِ انتَهَوْا فَلَا عُدْوَانَ إِلَّا عَلَى الظَّالِمِينَ

ይህ የሚሆነው ሰላም ሆኖ ሁከት እስከሚጠፋ ድረስ እና ሃይማኖት ለአላህ እስከሚሆን ድረስ ነው፤ “ዲን” دِين ማለት ደግሞ “ሃይማኖት” “ፍትህ” “ፍርድ” “ሕግ” “መርህ” ማለት ነው፤ ይህ ዲን ለአላህ የሚሆነው የዲኑ ቀን ነው፤ አላህ የዲኑ ቀን ባለቤት ነው፦
1፥4 *የፍርዱ ቀን ባለቤት ለኾነው*፡፡ مَالِكِ يَوْمِ الدِّينِ
26፥82 ያም *በፍርዱ ቀን* ኀጢአቴን ለእኔ ሊምር የምከጅለው ነው፡፡ وَالَّذِي أَطْمَعُ أَن يَغْفِرَ لِي خَطِيئَتِي يَوْمَ الدِّينِ
37፥20 «ዋ ጥፋታችን! *ይህ የፍርዱ ቀን ነው*» ይላሉም፡፡ وَقَالُوا يَا وَيْلَنَا هَـٰذَا يَوْمُ الدِّينِ

“እነዚያንም የሚጋደሉዋችሁን በአላህ መንገድ ተጋደሉ” እስከ መቼ? “ሃይማኖት ለአላህ ብቻ እስከሚኾን ድረስ” መቼ ነው ዲን ለአላህ የሚሆነው? የዲኑ ቀን በተባለው በትንሣኤ ቀን፤ እስከዛ እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ወሰን አልፎ በሚመጣው ላይ ለእነዚያ ለሚገደሉት ምእመናን እነርሱ የተበደሉ በመኾናቸው መጋደል ተፈቀደላቸው፦
22፥39 *ለእነዚያ ለሚገደሉት ምእመናን እነርሱ የተበደሉ በመኾናቸው መጋደል ተፈቀደላቸው*፡፡ أُذِنَ لِلَّذِينَ يُقَاتَلُونَ بِأَنَّهُمْ ظُلِمُوا ۚ وَإِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ نَصْرِهِمْ لَقَدِيرٌ

ምዕራባውያን ጂሃድ ማለት የሰውን ነጻነት እና መብት የሚጋፋ አሉታዊ ነገር አድርገው ነው በማህበራዊ መገናኛ ብዙኃን ላይ የቀረጹት፤ ነገር ግን ጅሃድ ማለት ወሰን አልፈው የሚነኩንን በአላህ መንገድ መጋደል እንጂ ወሰን ማለፍ እና ሕግ ጥሰት በፍጹም አይደለም፤ በተቃራኒው በኢስላም በሃይማኖት ማስገደድ የለም፤ ቅኑ መንገድ ከጠማማው ከተገለጠ በኃላ በጣዖትም የሚክድና በአላህ የሚያምን ሰው ለእርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ፦
2፥256 *በሃይማኖት ማስገደድ የለም፡፡ ቅኑ መንገድ ከጠማማው በእርግጥ ተገለጠ፡፡ በጣዖትም የሚክድና በአላህ የሚያምን ሰው ለእርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ*፡፡ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡ لَا إِكْرَاهَ فِي الدِّينِ ۖ قَد تَّبَيَّنَ الرُّشْدُ مِنَ الْغَيِّ ۚ فَمَن يَكْفُرْ بِالطَّاغُوتِ وَيُؤْمِن بِاللَّهِ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَىٰ لَا انفِصَامَ لَهَا ۗ وَاللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ

እንግዲያውስ ትልቁ ጂሃድ በማስተማር የሚደረግ ጂሃድ ነው፤ ይህም በአላህም ሃይማኖት ተገቢውን መታገል፤ በቁርኣን ታላቅን ትግል መታገል ነው፦
22፥78 *በአላህም ሃይማኖት ተገቢውን ትግል ታገሉ*፡፡ وَجَاهِدُوا فِي اللَّهِ حَقَّ جِهَادِهِ
25፥52 ከሓዲዎችንም አትታዘዛቸው፡፡ *በእርሱ በቁርኣን ታላቅን ትግል ታገላቸው*፡፡ فَلَا تُطِعِ الْكَافِرِينَ وَجَاهِدْهُم بِهِ جِهَادًا كَبِيرًا

እዚህ አንቀጽ ላይ “ታገላቸው” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ጃሂድሁም” جَاهِدْهُم ሲሆን በቁርኣን ማስተማር የሚደረገውን ጥረት ለማመልከት አገልግሎት ላይ ውሏል፤ “በቁርኣን ታላቅን ትግል ታገላቸው” የሚለው ይሰመርበት። ነብያችንም”ﷺ” የተሻለ ጂሃድ ምንድን ነው? ለሚለው፦ “በጨቃኝ ገዢ ፊት እውነትን መናገር ነው” ብለዋል፦
ሪያዱ አስ-ሳሊሂን መጽሐፍ 1, ሐዲስ 195
አንድ ሰው ነብዩን’ﷺ’ እንዲህ ብሎ ጠየቃቸው፦ *“የተሻለ ጂሃድ ምንድን ነው? እርሳቸውም፦ “በጨቃኝ ገዢ ፊት እውነትን መናገር ነው” አሉት*። أن رجلاً سأل النبي صلى الله عليه وسلم، وقد وضع رجله في الغرز‏:‏ أي الجهاد أفضل‏؟‏ قال‏:‏ “كلمة حق عند سلطان جائر‏”
ጂሃድ መልካም ሥራን መስራትም ያካትታል፤ ለምሳሌ፦ ሐጅና ዑምራህ የአረጋዊያ፣ የደቂቃን፣ የአቅመ-ደካማ እና የሴቶች ጅሃድ ነው፦
ሱነን ነሣኢ መጽሐፍ 24 , ሐዲስ 0:
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ *“የአረጋዊያ፣ የደቂቃን፣ የአቅመ-ደካማ እና የሴቶች ጂሃድ ሐጅና ዑምራህ ነው*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ جِهَادُ الْكَبِيرِ وَالصَّغِيرِ وَالضَّعِيفِ وَالْمَرْأَةِ الْحَجُّ وَالْعُمْرَةُ ‏”‏ ‏.‏
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 56 , ሐዲስ 91:
የአማኞች እናት ዓኢሻህ”ረ.ዓ.” እንደተረከችው፦ *ነብዩን”ﷺ” ጂሃድ ውስጥ እንድሳተፍ እንዲፈቅዱልኝ ጠየኳቸው፤ ነገር ግን “የአንቺ ጂሃድ ሐጅን መፈጸም ነው” አሉ*። عَنْ عَائِشَةَ أُمِّ الْمُؤْمِنِينَ ـ رضى الله عنها ـ قَالَتِ اسْتَأْذَنْتُ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم فِي الْجِهَادِ‏.‏ فَقَالَ ‏ “‏ جِهَادُكُنَّ الْحَجُّ ‏”‌‏
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 25 , ሐዲስ 2901:
ዓኢሻህ”ረ.ዓ.” እንደተረከችው፦ *“የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሆይ! ለሴት ጂሃድ ግዴታ ነውን? አልኩኝ፤ እርሳቸውም፦ “አዎ ለእነርሱ ፍልሚያ የለም ሐጅና ዑምራህ ቢሆን እንጂ*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قُلْتُ يَا رَسُولَ اللَّهِ عَلَى النِّسَاءِ جِهَادٌ قَالَ ‏ “‏ نَعَمْ عَلَيْهِنَّ جِهَادٌ لاَ قِتَالَ فِيهِ الْحَجُّ وَالْعُمْرَةُ ‏”‏ ‏.‏

ለወንድም ቢሆን ወላጆቹ በህይወት ካሉ እነርሱን መንከባከብ ጂሃድ ነው፦
ሱነን ነሣኢ መጽሐፍ 25 , ሐዲስ 19:
ዐብደላህ ኢብኑ ዐምር እንደተረከው፤ አንድ ሰው ወደ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” መጥቶ፦ *“ወደ ጂሃድ እንዲሄድ ፈቃድ ጠየቃቸው፤ እርሳቸውም፦ “ወላጆችህ በህይወት አሉን? አሉት፤ እርሱም፦ “አዎ” አላቸው፤ እርሳቸውም፦ “ለእነርሱ ታገል” አሉት*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، قَالَ جَاءَ رَجُلٌ إِلَى رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَسْتَأْذِنُهُ فِي الْجِهَادِ فَقَالَ ‏”‏ أَحَىٌّ وَالِدَاكَ ‏”‏ ‏.‏ قَالَ نَعَمْ ‏.‏ قَالَ ‏”‏ فَفِيهِمَا فَجَاهِدْ “‌‌‏.‏

ስናጠቃልለው ጂሃድ ማለት በአላህ መንገድ የሚደረግ ፍትሐዊ ትግል፣ ጥረት፣ ገድል እንጂ የሰው ሃቅን በመንካት ወሰን ማለፍ፣ የሰው ሃቅን በመንካት ንብረት ማባከን፣ የሰው ሃቅን በመንካት ህይወትና ንብረትን ማጥፋት አይደለም፤ አላህ፦ “ወሰንንም አትለፉ” “አታባክኑም” “በምድርም ውስጥ ማጥፋትን አትፈልግ” ይለናል፤ አይ አሻፈን ካልን አላህ ወሰን አላፊዎችን፣ አባካኞችን፣ አጥፊዎችን አይወድም፦
5፥87 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህ ለናንተ የፈቀደላችሁን ጣፋጮች እርም አታድርጉ፡፡ *ወሰንንም አትለፉ፡፡ አላህ ወሰን አላፊዎችን አይወድምና*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تُحَرِّمُوا طَيِّبَاتِ مَا أَحَلَّ اللَّهُ لَكُمْ وَلَا تَعْتَدُوا ۚ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْمُعْتَدِينَ
7፥31 የአዳም ልጆች ሆይ! ኀፍረተ ገላችሁን የሚሸፍኑትን ጌጦቻችሁን በመስገጃው ሁሉ ዘንድ ያዙ፡፡ ብሉም፤ ጠጡም፤ *አታባክኑም፡፡ እርሱ አባካኞችን አይወድምና*፡፡ يَا بَنِي آدَمَ خُذُوا زِينَتَكُمْ عِندَ كُلِّ مَسْجِدٍ وَكُلُوا وَاشْرَبُواአ وَلَا تُسْرِفُوا ۚ إِنَّهُ لَا يُحِبُّ الْمُسْرِفِينَ
28፥77 «አላህም በሰጠህ ሀብት የመጨረሻይቱን አገር ፈልግ፡፡ ከቅርቢቱም ዓለም ፋንታህን አትርሳ፡፡ አላህም ወደ አንተ መልካምን እንዳደረገልህ ለሰዎች መልካምን አድርግ፡፡ *በምድርም ውስጥ ማጥፋትን አትፈልግ፡፡ አላህ አጥፊዎችን አይወድምና*» አሉት፡፡ وَابْتَغِ فِيمَا آتَاكَ اللَّهُ الدَّارَ الْآخِرَةَ ۖ وَلَا تَنسَ نَصِيبَكَ مِنَ الدُّنْيَا ۖ وَأَحْسِن كَمَا أَحْسَنَ اللَّهُ إِلَيْكَ ۖ وَلَا تَبْغِ الْفَسَادَ فِي الْأَرْضِ ۖ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْمُفْسِدِينَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ሽብርተኝነት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

6፥82 *እነዚያ ያመኑ እና እምነታቸውን በበደል ያልቀላቀሉ እነዚያ ለእነርሱ “ጸጥታ" አላቸው፤ እነርሱም የተመሩ ናቸው*። ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَلَمْ يَلْبِسُوٓا۟ إِيمَٰنَهُم بِظُلْمٍ أُو۟لَٰٓئِكَ لَهُمُ ٱلْأَمْنُ وَهُم مُّهْتَدُونَ

“ሠላም” سَلَٰم የሚለው ቃል “ሠለመ” سَلَّمَ ማለትም “ሰላምታ ሰጠ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ሰላም” ማለት ነው፤ የአላህን ሰላም አንዱ አማኝ በሌላው አማኝ ላይ እንዲሆን መመኘት የሙስሊም ሰላምታ ነው፤ “ተሥሊም” تَسْلِيم ማለት “ሰላምታ” ማለት ነው፤ ይህም ሰላምታ “አሠላሙ አለይኩም” السَّلَامُ عَلَيْكُم ነው፤ ትርጉሙ “የአላህ ሰላም በእናንተ ላይ ይሁን” ማለት ነው። አንድ ሙስሊም መጥቶ “አሠላሙ አለይኩም” ቢለን፥ እርሱ ካለን ይበልጥ ባማረ መልኩ “ወአለይኩም አሥ-ሠላም፣ ወራሕመቱላሂ ወበረካቱህ” السَّلاَمُ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَةُ اللهِ وَبَرَكَاتُهُ  ማለትም “የአላህ ሰላም፣ ምህረት፣ በረከት በእናንተ ላይ ይሁን” ብለን እንመልሳለን፤ ወይንም እራሷኑ “ወአለይኩም አሥ-ሠላም” وَعَلَيْكُم السَّلَام ብለን እንመልሳለን፤ በቁርአን ከተገለጹት የአላህ ስሞች አንዱ “አሥ-ሠላም” السَّلَام ሲሆን ትርጉሙ የሰላም ባለቤት”the source of peace” ማለት ነው። የአላህ ሰላም የሚገኘው አላህን በኢኽላስ በመታዘዝ ብቻ ነው፤ “ኢሥላም” إِسْلَٰم የሚለው ቃል “አሥለመ” أَسْلَمَ ማለትም “ታዘዘ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መታዘዝ” ማለት ነው። “ሠለም” سَلَم ማለት ደግሞ “ታዛዥነት” ማለት ነው።
“ሙሥሊም” مُسْلِم ማለት “ታዛዥ” ማለት ነው፤ አንድ ሙስሊም አላህን በፍጹም ሲታዘዝ የአላህ ሰላም ከእርሱ ጋር ይሆናል፤ ያኔ ውስጡ “ሠሊም” سَلِيم ማለትም “ንፁህ” ይሆናል፤ እርሱም “ሠሊሙን” سَٰلِمُون ማለትም “ሰላማዊ” ይሆናል፤ ፍርሃት እና ሃዘን ይወገዳል፦
2፥112 አይደለም እርሱ በጎ ሠሪ ኾኖ *ፊቱን ለአላህ የሰጠ ሰው ለእርሱ በጌታው ዘንድ ምንዳ አለው፡፡ *በእነሱም ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነሱም አያዝኑም*፡፡ بَلَىٰ مَنْ أَسْلَمَ وَجْهَهُ لِلَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ فَلَهُ أَجْرُهُ عِندَ رَبِّهِ وَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ

እዚህ ድረስ ከተግባባን ዘንድ ስለ ሽብርተኝነት ደግሞ እያለን። "ሽብርተኝነት" በጥንታዊ ዘመን”clasical age” ቃሉ አገልግሎት ላይ የሚውለው ከጀግነነት ጋር በተያያዘ መልኩ አሸባሪ በራስ መተማመንን ተሸባሪው በራስ አለመተማመንን የሚያሳይ በአውንታዊ መልኩ ነበር፤ ነገር ግን ዘመናዊ ዘመን”modern age” ሲመጣ ቃሉ በአሉታዊ መልኩ ሰላም ለሚነሱ ሰዎች አገልግሎት ላይ ዋለ፤ ለምሳሌ እንግሊዝ በአንድ ወቅት በቅኝ ግዛት አንገዛትም ያሉትን አሸባሪ የሚል ስም ትለጥፍ ነበር፤ ከጥቅም 11 2001 እንደ ጎርጎርዮሳውያን አቆጣጠር የፔንታጎኑ ህንፃ ከተመታ ጀምሮ ይህ ታፔላ ለሙስሊሙ ስም ከሆነ ዛሬ 17 ዓመት ሆነው። “ኢርሀብ” إرهاب ማለት “ሽብር” ማለት ሲሆን የሰው ሃቅ ላይ በመድረስ የሚሰራ በደል ነው፤ ሽብርተኝነት አላህ ዘንድ የተጠላ እንደሆነ በቁና ጥቅስ ማቅረብ ይቻላል። ሚሽነሪዎች ግን ቃላትን በመጠምዘዝ ፍርሃት የሚለውን ወደ ሽብር ሲያሸብሩ ይታያል። ይህንን ነጥብ በነጥብ እስቲ እንመልከት፦
ነጥብ አብድ
"ሩዕብ"
“ሩዕብ” رُعْب ማለት “ፍርሃት” ማለት ሲሆን ይህ ፍርሃት በሙሽሪክ እና በካፊር ቀልብ ላይ አላህ የሚጥለው የመረጋጋት፣ የሰላምና የፀጥታ ተቃራኒ ነው፦
3፥151 *በእነዚያ “በካዱት ሰዎች” ልቦች ዉስጥ አላህ በእርሱ አስረጅ ያላወረደበትን ነገር በአላህ “በማጋራታቸዉ” ምክንያት “ፍርሃትን” እንጥላለን*፤ መኖሪያቸዉም እሳት ናት፤ “የበዳዮችም” መኖርያ ምን ትከፋ! سَنُلْقِي فِي قُلُوبِ الَّذِينَ كَفَرُوا الرُّعْبَ بِمَا أَشْرَكُوا بِاللَّهِ مَا لَمْ يُنَزِّلْ بِهِ سُلْطَانًا وَمَأْوَاهُمُ النَّارُ وَبِئْسَ مَثْوَى الظَّالِمِينَ

አላህ ለመላእክቱ በእነዚያ በካዱት ልቦች ውስጥ ፍርሃትን በእርግጥ እጥላለሁ ብሏል፦
8፥12 ጌታህ ወደ መላእክቱ፦ እኔ ከናንተ ጋር ነኝና፣ እነዚያን ያመኑትን አጽናኑ፤ *በእነዚያ በካዱት ልቦች ውስጥ ፍርሃትን በእርግጥ እጥላለሁ"*፤ ከአንገቶችም በላይ ምቱ፤ ከእነሱም የቅርንጫፎችን መለያልይ ሁሉ ምቱ፤ ሲል ያወረደውን አስታውስ። إِذْ يُوحِى رَبُّكَ إِلَى ٱلْمَلَٰٓئِكَةِ أَنِّى مَعَكُمْ فَثَبِّتُوا۟ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ۚ سَأُلْقِى فِى قُلُوبِ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ ٱلرُّعْبَ فَٱضْرِبُوا۟ فَوْقَ ٱلْأَعْنَاقِ وَٱضْرِبُوا۟ مِنْهُمْ كُلَّ بَنَانٍۢ ።

ታዲያ አሸብሩ የሚል ቃል ቁርአን ላይ የት አለ? አላህ በማሻረክ እና በመክፈር ላይ ላሉ ሙሽሪኪንና ካፊሪን ልብ ላይ ፍርሃት መጣል ማለት እናንተ አሸብሩ ማለት ነው ብሎ መረዳት ከጥራዝ ጠለቅ ዕውቀት ሳይሆን ከጥራዝ ነጠቅ ዕውቀት የሚመጣ የተንሸዋረረ መረዳት ነው፤ እስቲ ወደ ነብያችን”ﷺ” ሐዲስ ደግሞ ጎራ ብለን ይህንን ገለባ ሂስ ድባቅ እናስገባው፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 56 , ሐዲስ 186
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደነገረን የአላህ መልክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፡- *“ጠቅላይ ንግግርን በመስጠት ተላክሁኝ፤ በጠላት ልብ ውስጥም “ፍርሀት” እንዲጣል በመደረግ ተረዳኹኝ*፤ ተኝቼ ሳለ የምድር ካዝናዎችም በእጄ ላይ ተደረጉልኝ። عَنِ ابْنِ شِهَابٍ، عَنْ سَعِيدِ بْنِ الْمُسَيَّبِ، عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ بُعِثْتُ بِجَوَامِعِ الْكَلِمِ، وَنُصِرْتُ بِالرُّعْبِ، فَبَيْنَا أَنَا نَائِمٌ أُتِيتُ بِمَفَاتِيحِ خَزَائِنِ الأَرْضِ، فَوُضِعَتْ فِي يَدِي ‏”‌‏ ።
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 7 , ሐዲስ 2
ጃቢር ኢብኑ ዐብዲላህ”ረ.ዐ.” እንዳስተላለፈው ነብዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፡- “ከኔ በፊት ለነበሩት ነቢያት ያልተሰጠ አምስት ነገር ተሰጠኝ፦ *የወር መንገድ ያህል ሲቀረው በጠላት ልብ ውስጥ “ፍርሀት” እንዲገባ በማድረግ ተረዳሁ*፣ ምድር በጠቅላላ ጡሀራና የመስገጃ ክልል ተደረገልኝ፣ ከኡመቶቼ ማንኛውም ሙስሊም ሶላት ወቅቱ በገባበት ማንኛውም ቦታ ላይ ሁኖ ይስገድ፣ የምርኮ ገንዘብ ከዚህ በፊት ለነበሩት ነቢያት ያልተፈቀደ ሲሆን ለኔ ሐላል ተደረገልኝ፣ የአማላጅነት ፈቃድ ተሰጠኝ፣ ከኔ በፊት የነበሩት ነቢያት ለህዝቦቻቸው ሲላኩ፡ እኔ ግን ለሰዎች በመላ ተላክሁኝ”። قَالَ أَخْبَرَنَا جَابِرُ بْنُ عَبْدِ اللَّهِ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ أُعْطِيتُ خَمْسًا لَمْ يُعْطَهُنَّ أَحَدٌ قَبْلِي نُصِرْتُ بِالرُّعْبِ مَسِيرَةَ شَهْرٍ، وَجُعِلَتْ لِيَ الأَرْضُ مَسْجِدًا وَطَهُورًا، فَأَيُّمَا رَجُلٍ مِنْ أُمَّتِي أَدْرَكَتْهُ الصَّلاَةُ فَلْيُصَلِّ، وَأُحِلَّتْ لِيَ الْمَغَانِمُ وَلَمْ تَحِلَّ لأَحَدٍ قَبْلِي، وَأُعْطِيتُ الشَّفَاعَةَ، وَكَانَ النَّبِيُّ يُبْعَثُ إِلَى قَوْمِهِ خَاصَّةً، وَبُعِثْتُ إِلَى النَّاسِ عَامَّةً

ሲጀመር ከመነሻው ቢሆን ሐዲሱ ላይ “ሩዕብ” رُعْب ማለትም “ፍርሃት” የሚል ቃል እንጂ “ሽብር” የሚል ቃል ሽታው የለም። ሲቀጥል “በጠላት ልብ ውስጥም ፍርሀት እንዲጣል ተደረኩኝ” ማለትና አስፈራራ ተባልኩኝ ማለት በይዘትም ሆነ በአይነት፤ በመንስኤም ሆነ በውጤት ሁሉት ለየቅል የሆኑ ቃላት ናቸው፤ ከቁርአኑ ሆነ ከሐዲሱ የምንረዳው በካሃድያንና በጣኦታውያን ቀልብ ላይ ፍርሃት የሚጥለው አላህ እንጂ ነብያችን”ﷺ” ወይም አማኞች አይደሉም፤ እንግዲያውስ አላህ በካሃድያንና በጣኦታውያን ቀልብ ላይ ፍርሃት ከጣለ በምዕመናን ልብ ውስጥ ምንን ይጥላል? የሚለውን በሚቀጥለው ነጥብ እንመልከት፦
ነጥብ ሁለት
“አምን”
“አምን” أَمْن ማለት “ጸጥታ” ማለት ሲሆን አላህን በማንነት ሆነ በምንነት አንድ ነው ብሎ በማመንና በብቸኝነት በማምለክ በቀልብ ላይ የሚመጣ “ጸጥታ” “መረጋጋት” እና “ሰላም” ነው፦
6፥82 *እነዚያ ያመኑ እና እምነታቸውን በበደል ያልቀላቀሉ እነዚያ ለእነርሱ “ጸጥታ" አላቸው፤ እነርሱም የተመሩ ናቸው*። ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَلَمْ يَلْبِسُوٓا۟ إِيمَٰنَهُم بِظُلْمٍ أُو۟لَٰٓئِكَ لَهُمُ ٱلْأَمْنُ وَهُم مُّهْتَدُونَ

የአላህ ሃቅ የሆነውን አምልኮ ለሌላ ማንነት ሆነ ምንነት መስጠት በእርሱ ላይ የሚፈፀም ዙልም ነው፤ “ዙልም” ظُلْم ማለት “በደል” ማለት ሲሆን በአላህ ላይ ማጋራት ታላቁ በደል ነው፤ ሱረቱል አንዓም 6፥82 አንቀጽ በወረደ እና በተነበበ ጊዜ “ዙልም” የተባለው ሺርክን መሆኑን በዚህ ሐዲስ ላይ ተገልጿል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 65 , ሐዲስ 4776
*“እነዚያ ያመኑ እና እምነታቸውን “በበደል” ያልቀላቀሉ እነዚያ ለእነርሱ “ጸጥታ” አላቸው፤ እነርሱም የተመሩ ናቸው” የሚለው አንቀፅ በወረደ ጊዜ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ባልደረቦች የሆኑት ቃሉ ከባድ ስለነበር እነርሱም፦ “ከኛ ውስጥ በደለኛ ያልሆነ ማን አለ?” ብለው ሲጠይቁ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሉቅማን ለልጁ፡- በአላህ አታጋራ፤ ማጋራት “ታላቅ በደል” ያለውን አልሰማችሁምን? ብለው ተናገሩ*። حَدَّثَنَا قُتَيْبَةُ بْنُ سَعِيدٍ، حَدَّثَنَا جَرِيرٌ، عَنِ الأَعْمَشِ، عَنْ إِبْرَاهِيمَ، عَنْ عَلْقَمَةَ، عَنْ عَبْدِ اللَّهِ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ لَمَّا نَزَلَتْ هَذِهِ الآيَةُ ‏{‏الَّذِينَ آمَنُوا وَلَمْ يَلْبِسُوا إِيمَانَهُمْ بِظُلْمٍ‏}‏ شَقَّ ذَلِكَ عَلَى أَصْحَابِ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم وَقَالُوا أَيُّنَا لَمْ يَلْبِسْ إِيمَانَهُ بِظُلْمٍ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّهُ لَيْسَ بِذَاكَ، أَلاَ تَسْمَعُ إِلَى قَوْلِ لُقْمَانَ لاِبْنِهِ ‏{‏إِنَّ الشِّرْكَ لَظُلْمٌ عَظِيمٌ‏}‌‏”‏
31፥13 ሉቅማንም ለልጁ እርሱ የሚገስጸው ሲሆን፦ ልጄ ሆይ! *በአላህ አታጋራ፤ ማጋራት “ታላቅ በደል” ነውና* ያለውን አስታውስ። وَإِذْ قَالَ لُقْمَٰنُ لِٱبْنِهِۦ وَهُوَ يَعِظُهُۥ يَٰبُنَىَّ لَا تُشْرِكْ بِٱللَّهِ ۖ إِنَّ ٱلشِّرْكَ لَظُلْمٌ عَظِيمٌۭ ።

በእርግጥም ሺርክ በአላህ ሃቅ ላይ ታላቅ በደል ነው፦ “ዛሊም” ظَالِم ተብሎ በዚህ ነጥብ ላይ የተጠቀሰው በአላህ ላይ የሚያጋራ ሰው ሲሆን የዚህ ሰው ቅጣቱ በቅርቢቱ ዓለም በልቡ ላይ ፍርሃት መኖር ሲሆን በመጨረሻይቱ ዓለም ደግሞ የጀሃነም ቅጣት ነው፦
3፥151 *በእነዚያ “በካዱት ሰዎች” ልቦች ዉስጥ አላህ በእርሱ አስረጅ ያላወረደበትን ነገር በአላህ “በማጋራታቸዉ” ምክንያት “ፍርሃትን” እንጥላለን*፤ መኖሪያቸዉም እሳት ናት፤ “የበዳዮችም” መኖርያ ምን ትከፋ! سَنُلْقِي فِي قُلُوبِ ነገርَذِينَ كَفَرُوا الرُّعْبَ بِمَا أَشْرَكُوا بِاللَّهِ مَا لَمْ يُنَزِّلْ بِهِ سُلْطَانًا وَمَأْوَاهُمُ النَّارُ وَبِئْسَ مَثْوَى الظَّالِمِينَ

ሙዕሚን ግን በልቡ ሰኪናህ አለ፤ “ሠኪናህ” سَكِينَة ማለት “እርጋታ”tranquillity” ማለት ሲሆን አላህ በሙዕሚን ልብ ላይ የሚያወርደው መረጋጋት ነው፦
48፥26 *አላህም በመልክተኛው ላይና በምእምናኖቹ ላይ እርጋታውን አወረደ*፡፡ فَأَنزَلَ اللَّهُ سَكِينَتَهُ عَلَىٰ رَسُولِهِ وَعَلَى الْمُؤْمِنِين
መደምደሚያ
“በሃላል” בֶּהָלָה ማለት በዕብራይስጥ “ሽብር” ማለት ነው፤ ይህንን ቃል በአማርኛ “ፍርሃት” ተብሎ ተቀምጧል፤ በባይብል እግዚአብሔር ትእዛዙን፣ ሥርዓቱን፣ ፍርዱንና ቃል ኪዳኑን ቢንቁ፣ ቢያፈርሱና ቢያቃልሉ “ፍርሃት” በልባቸው እንደሚያወርድባቸው ተናግሯል፤ ዳዊትም በእነዚህ አይነት ሰዎች ፍርሃትን በላያቸው እንዲጭን አምላክን ተማፅኗል፦
ዘሌዋውያን 26፥15-16 ሥርዓቴንም ብትንቁ፥ ትእዛዛቴንም ሁሉ እንዳታደርጉ፥ ቃል ኪዳኔንም እንድታፈርሱ ነፍሳችሁ ፍርዴን ብትጸየፍ፥ *እኔም እንዲህ አደርግባችኋለሁ፤ "ፍርሃትን" בֶּֽהָלָה֙ ፥ ክሳትንም፥ ዓይናችሁንም የሚያፈዝዝ፥ ሰውነታችሁንም የሚያማስን ትኩሳት አወርድባችኋለሁ*፤ ዘራችሁንም በከንቱ ትዘራላችሁ፥ ጠላቶቻችሁ ይበሉታልና።
ዘሌዋውያን 26፥36 በጠላቶቻቸውም ምድሮች ሳሉ ከእናንተ ተለይተው በቀሩት ላይ *በልባቸው ድንጋጤን እሰድድባቸዋለሁ*፤
ኤርሚያስ 49፥5 እነሆ፥ በዙሪያሽ ካሉት ሁሉ ዘንድ *ፍርሃትን አመጣብሻለሁ*፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤
መዝሙር 9፥20 አቤቱ፥ *ፍርሃትን በላያቸው ጫንባቸው*፤

ትንሽ ቆይታችሁ እግዚአብሔር ሽብርተኛ ነው እንዳትሉ ብቻ፤ ለማንኛውም ነብያችን”ﷺ” እናንተ እንደምታጣምሙት ሳይሆኑ ለዓለማት እዝነት ሆነው የተላኩ የአላህ መልእክተኛ ናቸው፦
21፥107 *ለዓለማትም እዝነት አድርገን እንጅ አልላክንህም*። وَمَا أَرْسَلْنَاكَ إِلَّا رَحْمَةً لِلْعَالَمِينَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ጥያቄዎቻችን!

ኢያኢሮስ የተባለ መኰንን ምንድን ነው ያለው? የማቴዎስ ጸሐፊ፦ "ልጄ አሁን ሞተች" ይለናል።
የማርቆስ ጸሐፊ ደግሞ፦ "ታናሽቱ ልጄ ልትሞት ቀርባለች" ይለናል።
የቱ ነው ትክክል?

A. ልጄ አሁን ሞተች፦
ማቴዎስ 9፥18-19 ይህንም ሲነግራቸው፥ አንድ መኰንን መጥቶ፦ *ልጄ አሁን ሞተች*፤ ነገር ግን መጥተህ እጅህን ጫንባት፥ በሕይወትም ትኖራለች፡ እያለ ሰገደለት። ኢየሱስም ተነሥቶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተከተለው።

B. ታናሽቱ ልጄ ልትሞት ቀርባለች፦
ማርቆስ 5፥22-24 ኢያኢሮስ የተባለ ከምኵራብ አለቆች አንዱ መጣ፤ ባየውም ጊዜ በእግሩ ላይ ወደቀና፦ *ታናሽቱ ልጄ ልትሞት ቀርባለችና እንድትድንና በሕይወት እንድትኖር መጥተህ እጅህን ጫንባት*፡ ብሎ አጥብቆ ለመነው። ከእርሱም ጋር ሄደ። ብዙ ሕዝብም ተከተሉት አጋፉትም።

ኢያኢሮስ የተባለ መኰንን የተናገረው "ልጄ አሁን ሞተች" ወይስ "ታናሽቱ ልጄ ልትሞት ቀርባለች"?
የቱ ነው ትክክል?

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
አዲስ ዓመት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

79፥40-41 በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ *ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት*፡፡ وَأَمَّا مَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ وَنَهَى النَّفْسَ عَنِ الْهَوَىٰ فَإِنَّ الْجَنَّةَ هِيَ الْمَأْوَىٰ

“ዒድ” عِيد የሚለው ቃል “ዓደ” عَادَ ማለትም “ተመላለሰ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ምልሰት” ማለት ነው፤ ይህ “መደሰቻ” ወይም “በዓል” በየዓመቱ ስለሚመላለስ ይህንን ስያሜ አግኝቷል፤ ነብያችን”ﷺ” የነገሩን ዓመታዊ በዓል ሁለት ብቻና ብቻ ናቸው፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ናቸው፦
ሡነን አቢ ዳዉድ : መጽሐፍ 2, ሐዲስ 745
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” መዲና ሲገቡ የመዲና ሠዎች የሚደሰቱባቸው ሁለት በዓላት እንዳሏቸው አወቁ። እርሳቸውም እነዚህ ሁለቱ ቀናት ምንድን ናቸው? በማለት ጠየቁ፤ ሰዎችም በጃሂሊያ ጊዜ እንጫወትባቸው የነበሩ በዓላት ናቸው አሏቸው። የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ “አላህ ከእነርሱ የተሻሉ ሁለት ዒዶችን ሠጥቷችኋል፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓን። አሏቸው። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ قَدِمَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْمَدِينَةَ وَلَهُمْ يَوْمَانِ يَلْعَبُونَ فِيهِمَا فَقَالَ ‏”‏ مَا هَذَانِ الْيَوْمَانِ ‏”‏ ‏.‏ قَالُوا كُنَّا نَلْعَبُ فِيهِمَا فِي الْجَاهِلِيَّةِ ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّ اللَّهَ قَدْ أَبْدَلَكُمْ بِهِمَا خَيْرًا مِنْهُمَا يَوْمَ الأَضْحَى وَيَوْمَ الْفِطْرِ ‏”‏ ‏.‏
ጃሚዒ አት-ተርሚዲህ : መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፤ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ‏”‏
ጃሚዒ አት-ተርሚዲህ : መጽሐፍ 8, ሐዲስ 91
አቡ ሰዒደል ኹድሪይ እንደተረከው፥ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” በሁለቱ በአል በኢደል አደሐ እና ኢደል ፈጥር መጾም ከልክለዋል። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ، قَالَ نَهَى رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم عَنْ صِيَامَيْنِ يَوْمِ الأَضْحَى وَيَوْمِ الْفِطْرِ ‏.

ታዲያ በየዓመቱ ዘመን ሲለወጥ በዐረቦች በሙሐረም፤ በኢትዮጵያ መስከረም፣ በምዕራባውያን ጃኑአሪይ ላይ የሚከበሩ በዓላት እና እንኳን አደረሳችሁ መባባል ቢድዓ እንጂ ከቀደምት ሰለፎች ማለትም ሶሐባህ ወይም ታቢኢይ አሊያም አትባኡ ታቢኢይ የተገኘ አይደለም። ኢብኑ ባዝ"ረሒመሁላህ"፦ "በየአዲስ ዓመቱ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት መለዋወጥ ከሰለፉ-ሷሊሕ የተገኘ መሰረት ያለው መኾኑን የምናውቀው አንዳች ነገር የለም፤ ከቁርኣንም ሆነ ከሐዲስ አሊያም ሸሪዓዊ መሠረት እንዳለውም የሚያሳይ ነገር አይታወቅም" ብለዋል።
ስለዚህ አዲስ ዓመትን ጠብቆ ማክበር በቁርኣንና በሐዲስ አሕካሙ ካልተቀመጠ እና አይ የፈለግነውን በዲኑ ላይ እንጨምራለን ከሆነ ቢድዓ ነው፤ ሑክም የአላህ እና የመልክተኛ ብቻና ብቻ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ : መጽሐፍ 53, ሐዲስ 7
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ማንኛውም ሰው ከትእዛዛችን ያልሆነ አንድ ነገር ቢፈጥር ተቀባይነት የለውም عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَنْ أَحْدَثَ فِي أَمْرِنَا هَذَا مَا لَيْسَ فِيهِ فَهُوَ رَدٌّ ‏”‌‏.‏
ከትእዛዛችን” የሚለው ይሰመርበት። አንድ ነገር ፈርድ ነው፣ ሙስተሐብ ነው፣ ሙባሕ ነው፣ መክሩህ ነው፣ ሐራም ነው ማለት የሚቻለው ከአላህ እና ከመልእክተኛ ትእዛዝ ሲመጣ ብቻና ብቻ ነው፦
3፥32 *አላህን እና መልክተኛውን ታዘዙ*፡፡ ብትሸሹም አላህ ከሓዲዎችን አይወድም» በላቸው፡፡ قُلْ أَطِيعُوا اللَّهَ وَالرَّسُولَ ۖ فَإِن تَوَلَّوْا فَإِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْكَافِرِينَ
4፥80 *መልክተኛውን የሚታዘዝ ሰው በእርግጥ አላህን ታዘዘ፡፡ ከትእዛዝም የሸሸ ሰው አያሳስብህ*፡፡ በእነርሱ ላይ ጠባቂ አድርገን አልላክንህምና፡፡ مَّن يُطِعِ الرَّسُولَ فَقَدْ أَطَاعَ اللَّهَ ۖ وَمَن تَوَلَّىٰ فَمَا أَرْسَلْنَاكَ عَلَيْهِمْ حَفِيظًا

“ከትእዛዛችን ያልሆነ አንድ ነገር ቢፈጥር ተቀባይነት የለውም” የሚለው የነብያችን”ﷺ” ንግግር ይሰመርበት፤ ማንኛውም መመሪያ ቁርአን እና የነብያችን”ﷺ” ሐዲስ ላይ ይገኛል፤ አላህን የሚወድ መልእክተኛውን ይከተላል፤ አላህም፦ “መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፤ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ” ብሎናል፦
3፥31 *በላቸው፡- አላህን የምትወዱ እንደኾናችሁ “ተከተሉኝ*፤ አላህ ይወዳችኋልና፤ ኀጢኣቶቻችሁንም ለእናንተ ይምራልና፤ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው” قُلْ إِن كُنتُمْ تُحِبُّونَ ٱللَّهَ فَٱتَّبِعُونِى يُحْبِبْكُمُ ٱللَّهُ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ ۗ وَٱللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ ፡፡
59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና وَمَآ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمْ عَنْهُ فَٱنتَهُوا۟ ۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ ፡፡

ሙሐረምን ጠብቆ ማክበር ጥሩ ቢድዓ ከሆነ ለምንስ የሌሎችን አዲስ ዓመት አይከበርም? ይህ ደግሞ ዲኑን ያባሻል። አይ ዝንባሌአችን ደስ ያለውን መልካም ነገር በዒባዳህ ላይ እናካትት ማለት ዲኑ ሙሉ ነው የሚለንን አምላካችን አላህን እየተቃረንን ነው፦
5፥3 *ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ*፡፡ ጸጋዬንም በእናንተ ላይ ፈጸምኩ፡፡ ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ፡፡ الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ الْإِسْلَامَ دِينًا

“ነፍስያ” نفسيه ማለትም “የራስ ዝንባሌ” ጌታችን የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ነው፤ ነፍስም ሁሉ በራሷ ላይ እንጅ ክፉን አትሠራም፦
12፥53 ነፍሴንም ከስሕተት አላጠራም፡፡ *ነፍስ ሁሉ ጌታዬ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና*፡፡ ጌታዬ በጣም መሓሪ አዛኝ ነው» አለ፡፡ وَمَا أُبَرِّئُ نَفْسِي ۚ إِنَّ النَّفْسَ لَأَمَّارَةٌ بِالسُّوءِ إِلَّا مَا رَحِمَ رَبِّي ۚ إِنَّ رَبِّي غَفُورٌ رَّحِيمٌ
6፥164 በላቸው እርሱ የሁሉ ጌታ ሲኾን ከአላህ በቀር ሌላን ጌታ እፈልጋለሁን *ነፍስም ሁሉ በራሷ ላይ እንጅ ክፉን አትሠራም*፡፡ قُلْ أَغَيْرَ ٱللَّهِ أَبْغِى رَبًّۭا وَهُوَ رَبُّ كُلِّ شَىْءٍۢ ۚ وَلَا تَكْسِبُ كُلُّ نَفْسٍ إِلَّا عَلَيْهَا

ቢድዓ፣ ኩርፍ፣ ሽርክ እና ኒፋቅ ምንጫቸው ዝንባሌ ነው፤ ብዙ ጊዜ ሰርጎ-ገብ የሆኑት ቡድንተኝነት፣ ጎጠኝነት፣ ጠርዘኝነት መነሻቸው ዝንባሌ ነው፤ አንድ ሙስሊም ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፦
79፥40-41 በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ *ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት*፡፡ وَأَمَّا مَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ وَنَهَى النَّفْسَ عَنِ الْهَوَىٰ فَإِنَّ الْجَنَّةَ هِيَ الْمَأْوَىٰ

አላህ ከነፍሲያ ከሚመጣ ዝንባሌ ጠብቆን፤ እርሱንና መልእክተኛው ባስቀመጡልን ሑክም የምንመራ ያድርገን አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ኃጢአት ምንድን ነው?

ክፍል አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

ኃጢአት በመፅሐፍ ቅዱስ

መግቢያ
“ኃጢአት” የሚለው ቃል በዕብራይስጥ “ሃታት” חַטָּאָה ሲሆን በግሪክ ኮይኔ ደግሞ “ሃማርቲአ” ἁμαρτία ነው፤ ትርገሙም “አለመታዘዝ” “አመፅ” “ኢላማን መሳት” የሚል ነው፤ ስለ ኃጢአት የሚያጠናው ጥናት “ነገረ-ኃጢአት”Hamartiology” ነው፤ ፈጣሪ ህግ ሰጥቶና አሳውቆ ያንን ህግ አለመታዘዝ ” ኃጢአት” ይባላል፤ ኃጢአት ያለ ሕግ ምውት ነው አይሰራም፤ ኃጢአት የሚታወቀው በህግ ነው፤ ያለ ሕግ ኃጢአት አይቆጠርም፦
ሮሜ 3፥20 “ኃጢአት በሕግ ይታወቃልና”።
ሮሜ 5፥13 ነገር ግን “ሕግ በሌለበት ጊዜ ኃጢአት” አይቈጠርም፤
ሮሜ 7፥7 እንግዲህ ምን እንላለን? “ሕግ ኃጢአት” ነውን? አይደለም፤ ነገር ግን “በሕግ ባይሆን ኃጢአትን ባላወቅሁም” ነበር፤ ሕጉ፦ አትመኝ ባላለ ምኞትን ባላወቅሁም ነበርና። ኃጢአት ግን ምክንያት አግኝቶ ምኞትን ሁሉ “በትእዛዝ ሠራብኝ”፤ “ኃጢአት ያለ ሕግ ምውት” ነውና።
1 ቆሮ 15፥56 የሞት መውጊያ ኃጢአት ነው “”የኃጢአትም ኃይል ሕግ” ነው፤

ነጥብ አንድ
“ኃጢአት በብሉይ ኪዳን”
የጥንቶቹ ሆነ የአሁኖቼ አይሁዳውያን ኃጢአት ማለት አንድ ሰው አድርግ አታድርግ የሚለውን ትዕዛዝን ከሰማበት ጊዜ ጀምሮ አታድግ የተባለውን ማድረጉ፥ አድርግ የተባለው አለማድረጉ ነው ብለው ያምናሉ፤ አንድ ሰው ይህንን ትዕዛዝ ከተላለፈ ኃጢአተኛ ይባላል፤ በዚህ ኃጢአቱ የሚጠየቀው እራሱ እንጂ እንደ ስኳርና ሳይነስ ለትውልድ በዘር የሚተላለፍ በሽታ”metabolic diseases” አይደለም፤ ይህንን ብሉይ ኪዳን በአፅንኦት ያሰምርበታል፦
ዘሌ 5፥17 ማናቸውም ሰው “ኃጢአት ቢሠራ”፥ እግዚአብሔርም፦ “አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት” አንዲቱን ቢተላለፍ፥ ባያውቅም፥ ያ ሰው በደለኛ ነው፥ “ኃጢአቱንም” ይሸከማል።
ዘኍልቍ 5፥6 ለእስራኤል ልጆች ንገራቸው፦ ወንድ ወይም ሴት “የእግዚአብሔርን ትእዛዝ” ይተላለፍ ዘንድ ሰው የሚሠራውን ኃጢአት ቢሠራ፥ በዚያም ሰው ላይ በደል ቢሆን፥ “በሠራው ኃጢአት ይናዘዝ”፤

አባት ለሰራው ኃጢአት ልጅ አይጠየቅም፤ ልጅ ለሰራው ኃጢአት አባት አይጠየቅም፤ በሁሉም በራሱ
ኃጢአት ይጠየቃል ይቀጣል፤ በአይሁዳውያን እሳቤ አዳም ለሰራው ኃጢአት ተጠያቂው እርሱ እራሱ እንጂ ልጆቹ ላይ የተላለፈ በሽታ አይደለም፦
ዘዳግም 24፥16 አባቶች ስለ ልጆች አይገደሉ፥ ልጆችም ስለ አባቶች አይገደሉ፤ “ነገር ግን ሁሉ እያንዳንዱ በኃጢአቱ ይገደል”።
2ኛ ነገሥት 14፥6 በሙሴ ሕግ መጽሐፍም እንደ ተጻፈ፥ እግዚአብሔርም፦ ሁሉ “በኃጢአቱ ይሙት” እንጂ አባቶች በልጆች አይሙቱ፥ ልጆችም በአባቶች አይሙቱ ብሎ እንዳዘዘ የነፍሰ ገዳዮቹን ልጆች አልገደለም።
ሕዝቅኤል 18 20 “ልጅ የአባቱን ኃጢአት አይሸከምም፥ አባትም የልጁን ኃጢአት አይሸከምም”፤

ነጥብ ሁለት
“ኃጢአት በአዲስ ኪዳን”
በብሉይ ኪዳን ኃጢአት በዘር ሃረግ ይመጣል ብሎ ያስተማረ አንድም ነብይ የለም። በአዲስ ኪዳንም ቢሆን ያለው ነብይ ኢየሱስ ነው ይህም ነብይ ኃጢአት በውርስ ከአባት ወደ ልጅ ይተላለፋል ብሎ አላስተማረም፤ ከዚህ ይልቅ ለኢየሱስ ኃጢአት ማለት እርሱ መጥቶ የተናገረውን ትምህርት ማስተባበል እንጂ ሌላ አይደለም፦
ዮሐንስ 15፥22 እኔ መጥቼ “ባልነገርኋቸውስ” “ኃጢአት” ባልሆነባቸውም ነበር፤ አሁን ግን “ለኃጢአታቸው” ምክንያት የላቸውም።

ኃጢአት ማለት ዓመፅ ሲሆን በጎ ለማድረግ አውቆ ለማይሠራው ኃጢአት ይባላል፤ ኃጢአት በዘር ሃረግ የሚመጣ ሳይሆን እያንዳንዱ “በራሱ” ምኞት ሲሳብና ሲታለል ምኞት ፀንሳ የምትወልደው ነገር ነው፦
1 ዮሐ 3፥4 “ኃጢአትን የሚያደርግ ሁሉ ዓመፅን ደግሞ ያደርጋል፥ “ኃጢአትም ዓመፅ ነው”።
ያዕቆብ 4፥17 እንግዲህ “በጎ ለማድረግ አውቆ ለማይሠራው ኃጢአት” ነው።
ያዕቆብ 1፥14-15 ነገር ግን እያንዳንዱ “በራሱ” ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል፤ ከዚህ በኋላ ምኞት ፀንሳ “ኃጢአትን” ትወልዳለች፤

“ኃጢአትን” በውርስ ይተላለፋል የሚለው ትምህርት “ጥንተ-ተአብሶ”Original sin” ይባላል፤ ይህን ትምህርት ያስተማረው ነብይ አሊያም ከአስራ ሁለቱ ሃዋርያት መካከል ያለ ሃዋርያ ሳይሆን ጳውሎስ ነው፦
ሮሜ 5:12 ስለዚህ ምክንያት “ኃጢአት በአንድ ሰው” ወደ ዓለም፤

እንደ አውዱ አንድ ሰው የተባለው አዳም ከሆነ ኃጢአት በአዳም ወደ ዓለም የገባው የሚለው ሃረግ ለውርስ ኃጢአት ትምህርት መሰረት ነው፤ ከመነሻው ይህ ንግግር መቼ የአምላክ ቃል ሆነና? ይህ የጳውሎስ ደብዳቤ ነው፤ “መልዕክት” ተብሎ የተቀመጠው የግሪኩ ቃል “ኢፕስትል” ἐπιστολή ሲሆን “ደብዳቤ”letter” ማለት ነው፣ የኣዲስ ኪዳን ትልቁን ጽሁፍ የያዘው የጳውሎስ ደብዳቤዎች ሲሆኑ እነዚህም በቁጥር 14 ናቸው፣ እነዚህ ደብዳበዎች ጳውሎስ ለባለንጀሮቹ፣ ለተማሪዎቹና ለአጥቢያዎች የላከው የግል ሃሳብ እንጂ የፈጣሪ ቃል አይደሉም፣ እነዚህን ደብዳቤዎች እንደ የፈጣሪ ቃል አድርጎ የተቀበለው በ 397 AD የካርቴጅ ጉባኤ ነው፤ ኃጢአት በአዳም ከመጣ ሰይጣን እና መላእክት ኃጢአትን የወረሱት ከአዳም ነውን? ምክንያቱም ሰይጣን እና መላእክት ኃጢአትን እንደሰሩ ስለሚናገር፦
1ዮሐንስ 3፥8 ኃጢአትን የሚያደርግ ከዲያብሎስ ነው፥ “ዲያብሎስ” ከመጀመሪያ “ኃጢአትን” ያደርጋልና”።
2ኛ ጴጥሮስ 2፥4 እግዚአብሔር “ኃጢአትን ላደረጉ” መላእክት” ሳይራራላቸው ወደ ገሃነም ጥሎ በጨለማ ጉድጓድ ለፍርድ ሊጠበቁ አሳልፎ ከሰጣቸው፤
ኢንሻላህ ይቀጥላል….


ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom


ወሰላሙ አለይኩም
ኃጢአት ምንድን ነው?

ክፍል ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

ኃጢአት በቁርአን

መግቢያ
“ኃጢአት” ማለት በቁርአን አበሳ፣ አመፅ፣ አለመታዘዝ፤ ወንጀል፣ ጥፋት ተብሎ የተቀመጠው ቃል ለማመልከት እንደየ አውዱ በተለያየ ስም መጥቷል፦
“ዘንብ” ذَنب
3፥16 እነርሱም እነዚያ፡- «ጌታችን ሆይ! እኛ አመንን “ኀጢአቶቻችንንም” ذُنُوبَنَا ለእኛ ማር፤ የእሳትንም ቅጣት ጠብቀን» የሚሉ ናቸው፡፡
“ኢሥም” إِثْم
2:219 አእምሮን ከሚቃወም መጠጥና ከቁማር ይጠይቁሃል፡፡ «በሁለቱም ውስጥ ታላቅ ኃጢኣት إِثْمٌ እና ለሰዎች ጥቅሞች አሉባቸው፡፡ ግን ኃጢኣታቸው وَإِثْمُهُمَا ከጥቅማቸው በጣም ትልቅ ነው» በላቸው፡፡
“ኸጢዓ” خَطِيٓـَٔة
112 ኀጢአትን ወይም አበሳን የሚሠራም ሰው፣ ከዚያም በርሱ ንጹሕን ሰው የሚሰድብ፣ ቅጥፈትንና ግልፅ አበሳን በቁርጥ ተሸከመ።
“ጁናህ” جُنَاح
4:24 ከመወሰንም በኋላ በተዋደዳችሁበት ነገር በእናንተ ላይ “ኃጢያት” جُنَاحَ የለም። አላህ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና።
“አጅረሙ” أَجْرَمُ
83፥29 እነዚያ “ያምመጹት” أَجْرَمُوا۟ በእነዚያ ባመኑት በእርግጥ ይስቁ ነበሩ፡፡

ኃጢአት ከቅጣት፣ ከፍትህ፣ ከሰው አቅም እና ከምህረት ጋር ያለውን መስተጋብር ነጥብ በነጥብ እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
“ኃጢአት እና ቅጣት”
ኃጢአት የሚባለው አላህ አድርግ ወይም አታድርግ የሚለውን ትእዛዝ መተላለፍ ሲሆን ይህን ትእዛን በመልእክተኛው በኩል አንድ ሰው መልእክቱ ካልደረሰው አይቀጣም፦
17:15 መልክተኛንም እስከምንልክ ድረስ “የምንቀጣ አይደለንም”።

አንድ ሰው የአላህን መልእክት ሰምቶ እራሱ በሰራው አበሳ ይቀጣል፦
6:120 የኃጢአትንም الْإِثْمِ ግልጹንም ድብቁንም ተውዉ፡፡ እነዚያ ኃጢአትን የሚሠሩ፤ ይሠሩት በነበሩት ነገር በእርግጥ “ይቀጣሉ”፡፡

ነጥብ ሁለት
“ኃጢአት እና ተሸካሚ ነፍስ”
በቁርአን እስተምህሮት ውስጥ እንደ ክርስትናው “ጥንተ-ተአብሶ”Original sin” ማለትም እንደ ስኳርና ሳይነስ ለትውልድ በዘር የሚተላለፍ ኃጢአት የለም፤ ኃጢአት ተሸካሚ ነፍስ የሌላይቱን ነፍስ ኃጢአት አትሸከምም፤ ይህን ነጥብ አምላካችን አላህ እንዲህ ይነግረናል፦
17:15 የተመራ ሰው የሚመራው ለራሱ ብቻ ነው፤ የተሳሳተም ሰው፣ የሚሳሳተው ጉዳቱ በርሷ ላይ ነው፤ “ተሸካሚም ነፍስ የሌላይቱን ኃጢአት አትሸከምም”፤
53:38 እርሱም “ኃጢአት ተሸካሚ ነፍስ የሌላይቱን ነፍስ ኃጢአት አትሸከምም”።
35:18 “ኀጢአትን ተሸካሚም ነፍስ የሌላዋን ሸክም አትሸከምም”፤
39:7 “ማንኛይቱም ኀጢአትን ተሸካሚ ነፍስ፣ የሌላይቱን ኃጢያት አትሸከምም”፤ ከዚያም መመለሻችሁ ወደ ጌታችሁ ነው፤ ትሠሩት የነበራችሁትንም ይነግራችኋል፤ እርሱ በልቦች ውስጥ ያሉትን ዐዋቂ ነውና።
6:164 “ተሸካሚም ነፍስ የሌላይቱን ሸክም ኃጢአት አትሸከምም”፡፡ ከዚያም መመለሻችሁ ወደ ጌታችሁ ነው፡፡ ወዲያውም በእርሱ ትለያዩበት የነበራችሁትን ሁሉ ይነገራችኋል፡፡»

ነጥብ ሶስት
“ነፍስ እና ችሎታዋ”
የዓለማቱ ጌታ አላህ ሰውን ይህን አድርግ ይህን አታድርግ ብሎ ቢያዘውም ጥቅሙና ጉዳቱ ለታዛዡ ሰው እንጂ ለአዛዡ ለአላህ ምንም ተፅእኖ የለውም፤ ምክንያቱም አላህ ተብቃቂ ሲሆን ፍጡራን ደግሞ የአላህ ጥገኛ ሆነው ከጃዮች ናቸው፤ አላህ የሚያዘን አድርጉ በማለት እራሳችን እንድንጠቀምና አታድርጉ በማለት እንዳንጎዳ ነው፤ አድርጉና አታድርጉ ያለን ከነፍሳችን አቅም በላይ ሳይሆን ለነፍስ ችሎታ ተመጣጣኝ ብቻ ነው፦
7:42 እነዚያም ያመኑና መልካሞችን የሰሩ “ነፍስን ችሎታዋን እንጂ አናስገድድምና”፤
2:286 አላህ “ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም”፡፤ ለርስዋ የሠራችው አላት፤ በእርስዋም ላይ ያፈራችው ኀጢአት አለባት፡፡
6:152 ስፍርንና ሚዛንንም በትክክሉ ሙሉ፡፤ “ነፍስን ችሎታዋን እንጂ አናስገድድም”፡፡
23:62 “ማንኛይቱንም ነፍስ ችሎታዋን እንጂ አናስገድዳትም”፡፤ እኛም ዘንድ በእውነት የሚናገር መጽሐፍ አልለ፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡

ነጥብ አራት
“ኀጢአት እና መጠኑ”
ኀጢአት በቁርአን ታላላቅ ኃጢያቶች እና ታናናሽ ኃጢያቶች ተብለው ይከፈላሉ፤ ታላላቅ ኃጢያቶች የሚባሉት፦ ሽርክ፣ ዚና፣ አራጣ፣ ሌብነት፣ መግደል፣ ቁማር ወዘተ ወደ 70 የሚደርሱ የመሳሰሉት ሲሆኑ ታናናሽ ኃጢያቶች ደግሞ ከዚያ ወዲህ ያሉት ናቸው፦
53፥32 እነዚያ የኃጢያትን الْإِثْمِ “ታላላቆችና” አስጠያፊዎቹን የሚርቁ ናቸው፤ ግን ትናንሾቹ የሚማሩ ናቸው። ጌታህ ምሕረተ ሰፊ ነውና፤
4፥31 ከእርሱ ከተከለከላችሁት “ታላላቆቹን” ብትርቁ “ትናንሾቹን” “ኃጢአቶቻችሁን” ከናንተ እናብሳለን፤
42፥37 ለነዚያም “የኀጢያትን” الْإِثْمِ “ታላላቆችና” ጠያፎችን የሚርቁ በተቆጡም ጊዜ እነርሱ የሚምሩ ለሆኑት።
ነጥብ አምስት
“ኀጢአት እና ምህረት”
አንድ ሰው በዱኒያ እያለ ማንኛውንም አጢያት ሰርቶ ነገር ግን በተውበት ወደ አላህ ቢመለስ ይቅር ይባላል፦
39:53 በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ አላህ “ኃጢኣቶችን በሙሉ” جَمِيعًا ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና፡፡ «ቅጣቱም ወደ እናንተ ከመምጣቱና ከዚያም የማትርረዱ ከመኾናችሁ በፊት ወደ ጌታችሁ በመጸጸት ተመለሱ፡፡ ለእርሱም ታዘዙ፡፡

“ጀሚኣ” جَمِيعًا “በሙሉ” የሚለው ቃል ይሰመርበት፣ ይህ ቃል ያገለገለው ሰው በዚህ ዓለም ቆይታው መሆኑን የምንረዳው ጥቅሱ ላይ “ቅጣቱም ወደ እናንተ ከመምጣቱና ከዚያም የማትርረዱ ከመኾናችሁ በፊት” የሚል ሃይለ-ቃል አለ፣ ይህም ሃይለ-ቃል ሰው በሞት ላይ ከመሆኑ በፊት በተውበት ከልቡ ከተመለሰ አላህ ኃጢኣቶችን በሙሉ ይምራል፣ ለዛ ነው አውዱ ላይ “ወደ ጌታችሁ በመጸጸት ተመለሱ”የሚል ሃይለ-ቃል ያለው፣ አላህ ብዙ ቦታ ላይ ከአጢያት በኋላ የሚኖረውን ምህረት ለመግለጽ “ከዚያም” ተጸጽቶ ብሎ ይናገራል፦
4:110 መጥፎም የሚሠራ ሰው ወይንም ነፍሱን የሚበድል “ከዚያም” ተጸጽቶ አላህን ምሕረት የሚለምን አላህን መሐሪ አዛኝ ሆኖ ያገኘዋል።

አንድ ሰው በአላህ ላይ ጣኦትን አጋርቶ ነገር ግን በተውበት ከተመለሰ ከአላህ ምህረትን ያገኛል፣ ይህን የእስራኤል ልጆች ማየት ይቻላል፣ የእስራኤል ልጆች በምድረ በዳ በአላህ ላይ ወይፈንን አጋርተው ከዚያም ወደ አላህ በተውበት ሲመለሱ ይቅር ብሏቸዋል፦
7:152-153 እነዚያ ወይፈኑን አምላክ አድርገው የያዙ፣ ከጌታቸው ዘንድ ቁጣ፤ ከቅርቢቱም ሕይወት ውርደት በእርግጥ ያገኛቸዋል፤ እንዲሁም ቀጣፊዎችን እንቀጣለን። “እነዚያም” وَالَّذِينَ ኃጢአቶችን የሠሩ ከዚያም “ከእርሷ” بَعْدِهَا በኋላ የተጸጸቱ፣ ያመኑም ጌታህ ከርሷ በኋላ በእርግጥ መሐሪ አዛኝ ነው።

“አልለዚነ” الَّذِينَ “እነዚያም” ከሚለው አንጻራዊ ተውላጠ-ስም በፊት መነሻ ላይ “ወ” وَ የሚል ሃርፉል ዓጥፍ ማለትም አያያዥ መስተጻምር ይጠቀማል፣ ያ ማለት “እነዚያም” የተባሉት ወይፈኑን አምላክ አድርገው የያዙት ሰዎች መሆናቸውን እንረዳለን ማለት ነው፣ በተለይ “በዲሃ” بَعْدِهَا “እርሷ” ተብላ የተጠቀሰችው አገናዛቢ ተውላጠ-ስም ከላይ የተጠቀሰውን የአጢያት ድርጊት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፣ ከዚያም ድርጊታቸው የተጸጸቱትን አላህ ይቅር ብሏቸዋል፦
4:153 ከመጡዋቸው በኋላ ወይፈኑን አምላክ አድርገው ያዙ፤ ከዚያም “ይቅር አልን”።

ነገር ግን አንድ ሰው ካጋራ በኋላ ምህረት የሚያገኘው በህይወት ዘመን ቆይታው እንጂ ሞት በመጣበት ጊዜ አሊያም ከኃዲዎች ሆነው ለሚሞቱ አይደለም፦
4:17 ፀፀትን መቀበል በአላህ ላይ የሚገባው ለነዚያ ኀጢአትን በስሕተት ለሚሠሩና ከዚያም “ከቅርብ ጊዜ” ለሚጸጸቱት ብቻ ነው። እነዚያንም አላህ በነርሱ ላይ ጸጸትን ይቀበላል።
4:18 ጸጸትንም መቀበል ለነዚያ ኃጢያቶችን ለሚሠሩ፣ አንዳቸውንም “ሞት በመጣበት ጊዜ” እኔ አሁን ተጸጸትኩ ለሚልና ለነዚያም እነርሱ ከኃዲዎች ሆነው ለሚሞቱ አይደለችም። እነዚያ ለነሱ አሳማሚ ቅጣት አዘጋጅተናል።

የተውበት በሩ ከመዘጋቱ በፊት ሁላችንም በንስሃ ወደ አላህ እንመለስ።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ሞት

ክፍል አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

67፥2 ያ የትኛችሁ ሥራው ይበልጥ ያማረ መኾኑን *”ሊፈትናችሁ ሞትንና ሕይወትን የፈጠረ ነው”*፡፡ እርሱም አሸናፊው መሓሪው ነው፡፡ ٱلَّذِى خَلَقَ ٱلْمَوْتَ وَٱلْحَيَوٰةَ لِيَبْلُوَكُمْ أَيُّكُمْ أَحْسَنُ عَمَلًۭا ۚ وَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْغَفُورُ

1. ሞት በባይብል
በባይብል “ሞት” ተፈጥሮአዊ፣ መንፈሳዊ እና ምሳሌአዊ ሆነው ቀርበዋል፦

ነጥብ አንድ
“ተፈጥሮአዊ ሞት”
“ተፈጥሮአዊ ሞት” አምላክ ባስቀመጠው የጊዜ ሂደት ውስጥ ውልደትና ሞት ውብ የሆኑ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው፦
መክብብ 3፥1 ለሁሉ ዘመን አለው፥ *”ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው”*።
መክብብ 3፥2 *”ለመወለድ ጊዜ አለው፥ ለመሞትም ጊዜ”* አለው፤ ለመትከል ጊዜ አለው፥ የተተከለውንም ለመንቀል ጊዜ አለው፥
መክብብ 3፥11 *”ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው”*፤

ለሁሉም ጊዜ አለው፣ ለሞትም ጊዜ አለው፤ ጊዜው ሲደርስ ሁሉም ሰው በተጻፈው የቀደመው የመለኮት ዕውቀቱ ይሞታል፦
መክብብ 7፥17 እጅግ ክፉ አትሁን፥ እልከኛም አትሁን፥ *”ጊዜህ ሳይደርስ እንዳትሞት”*።
መዝሙር 139፥16 ያልተሠራ አካሌን ዓይኖችህ አዩኝ፤ *”የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ አንድ ስንኳ ሳይኖር በመጽሐፍህ ተጻፉ”* ።

ትውልድ በመወለድ ይመጣል በሞት ይሄዳል፤ ብዙ ተባዙ የሚለው መዋለድ ተፈጥሮአዊ እንደሆነ ሁሉ ሞትም ተፈጥሮአዊ ሂደት ነው፤ ምድርም ቋሚ ሆና ለሁሉም ነዋሪዋቿ የሞትና የህይወት ስፍራ ናት፦
መክብብ 1፥4 *”ትውልድ ይሄዳል፥ ትውልድም ይመጣል”*፤ ምድር ግን ለዘላለም ነው።
ዘፍጥረት 1፥28 እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ *”ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት”*፥
መዝሙር 115፥16 የሰማያት ሰማይ ለእግዚአብሔር ነው፤ *”ምድርን ግን ለሰው ልጆች ሰጣት”*።

ሴል እራሱ አንዱ ሲሞት ሌላው በሚተካ ኡደት ህይወት ይቀጥላል ከዚያ ይሞታል፤ ይህ በእፅዋት፣ እንስሳት እና በሰው ላይ የተቀመጠ የተፈጥሮ ሕግ ነው፦
መክብብ 3፥19-20 *”የሰው ልጆችና የእንስሳ እድል ፈንታ አንድ ነው፤ ድርሻቸውም ትክክል ነው፤ አንዱ እንደሚሞት ሌላውም እንዲሁ ይሞታል፤ የሁሉም እስትንፋስ አንድ ነው”*፤ ሁሉም ከንቱ ነውና ሰው ከእንስሳ ብልጫ የለውም፤ *”ሁሉ ወደ አንድ ቦታ ይሄዳል፤ ሁሉ ከአፈር ነው ሁሉም ወደ አፈር ይመለሳል”*።

ሰው፣ እንስሳ እና እፅዋት ህይወት እንዳላቸው ሁሉ ሞት አላቸው። ሞት እንደ ጳውሎስ አስተምህሮት በአዳም ነው የገባው ካለን እንስሳት እና እፅዋት በምን ወንጀላቸው ነው የሌላ ወንጅል ገፈት ቀማሽ የሚሆኑት?
ሮሜ 5:12 ስለዚህ ምክንያት *”ኃጢአት በአንድ ሰው ወደ ዓለም ገባ በኃጢአትም ሞት”*፥ እንደዚሁም ሁሉ ኃጢአትን ስላደረጉ *”ሞት ለሰው ሁሉ ደረሰ”*፤”
1ኛ ቆሮ 15፥22 “ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ” እንዲሁ *”ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና”*።

ሁሉም በአዳም ከሞተ እንስሳትና እፅዋትስ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉናን? ሞት በአዳም ያለምርጫቸው ከተቀበሉ ለምን ሁሉም ያለምርጫው ህይወት አያገኙም? ህይወት የሚሰጠው፣ ሩህን በማውጣት የሚያሞት እና ከመቃብር የሚያወጣው ፈጣሪ ነው፦
1ኛ ሳሙኤል 2:6 እግዚአብሔር *”ይገድላል ያድናልም፤ ወደ ሲኦል ያወርዳል፥ ያወጣል”*።
ዘዳግም 32፥39፤ አሁንም እኔ ብቻዬን እኔ እንደ ሆንሁ፥ ከእኔም በቀር አምላክ እንደሌለ እዩ፤ *እኔ እገድላለሁ፥ አድንማለሁ*፤
መዝሙር 89:48 *”ሕያው ሆኖ የሚኖር፥ ሞትንስ የማያይ ማን ነው?”* ነፍሱንስ ከሲኦል እጅ የሚያድን ማን ነው?
መዝሙር 104፥29 ፊትህን ስትሰውር ይደነግጣሉ፤ *”ነፍሳቸውን ታወጣለህ ይሞታሉም፥ ወደ አፈራቸውም ይመለሳሉ”*።
ነጥብ ሁለት
“መንፈሳዊ ሞት”
አንድ ሰው በቁሙ በህይወት እያለ ከፈጣሪው ጋር ጤናማ ህይወት ከሌለው በቁሙ ሞቷል፤ ይህ ሞት መንፈሳዊ ሞት ይባላል፤ ይህ ሞት እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ከዚህ በኋላ ምኞት ፀንሳ ኃጢአትን ትወልዳለች፤ ኃጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች እንጂ በአዳም የመጣ ሞት አይደለም፦
ያዕቆብ 1፥14-15 ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል፤ ከዚህ በኋላ ምኞት ፀንሳ ኃጢአትን ትወልዳለች፤ *”ኃጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች”*።

ኢየሱስ የማይከተሉት ሰዎች ሙታን የሚከተሉትን ደግሞ ህያዋን ናቸው ብሏቸዋል፦
ሉቃስ 9፥60 ኢየሱስም፦ *”ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው”*፤
ዮሐንስ 5:25 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ *”ሙታን”* የእግዚአብሔርን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል እርሱም አሁን ነው፤ የሚሰሙትም *”በሕይወት ይኖራሉ”*።
ራእይ 3:1 ሥራህን አውቃለሁ ሕያው እንደ መሆንህ ስም አለህ *”ሞተህማል”*።

ይህንን እሳቤ ጳውሎስም ይጋራል፦
ኤፌሶን 5፥14 ስለዚህ፦ አንተ የምትተኛ ንቃ *”ከሙታንም ተነሣ”* ክርስቶስም ያበራልሃል ይላል።
1ኛ ጢሞቴዎስ 5፥6 ቅምጥሊቱ ግን *”በሕይወትዋ ሳለች “የሞተች ናት”*።

ስለዚህ አዳም በበላ ቀን ሲሞት የሞተው መንፈሳዊ ሞት በራሱ እራሱ ላይ እንጂ እንደ ስኳር በዘር ያስተላለፈው በሽታ አይደለም። በበላበት ቀን ቃል በቃል ስላልሞተ፦
ዘፍጥረት 2፥17 ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ *”በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና”*።

ነጥብ ሶስት
“ምሳሌአዊ ሞት”
ጀሃነም በምሳሌ ሁለተኛ ሞት ተብሏል፦
ራእይ 2፥11 ድል የነሣው *”በሁለተኛው ሞት”* አይጐዳም።
ራዕይ 21፥8 ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና *”በእሳት በሚቃጠል ባሕር”* ነው፤ ይኸውም *”ሁለተኛው ሞት”* ነው።
“ይሁዳ 1:12 በነፋስ የተወሰዱ ውኃ የሌለባቸው ደመናዎች፥ ፍሬ የማያፈሩ *”ሁለት ጊዜ የሞቱ”* ከነሥራቸው የተነቀሉ በበጋ የደረቁ ዛፎች፥”

ሁለተኛ ሞት ማለት መንፈስንና አካልን በጀሃነም መቅጣት ነው፦
ማቴዎስ 10:28 ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ *”ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ”*።
ያዕቆብ 4:12 ሕግን የሚሰጥና የሚፈርድ አንድ ነው፤ እርሱም *”ሊያድን ሊያጠፋም የሚችል ነው”*፤ በሌላው ግን የምትፈርድ አንተ ማን ነህ?”.

በገሃነም መጥፋት ማለት የይሆዋ ምስክሮች እንደሚሉት ህልውና አልባ”Total Annihilation” ማለት ሳይሆን ከጌታ እና ከሃይሉ ፊት መራቅ ነው። ልክ በግ ከእረኛው፣ ድሪም ከሴት፣ ልጅ ከአባቱ ሲጠፋ ማለት ነው፦
2ኛ ተሰሎንቄ 1:10 *”ከጌታ ፊት ከኃይሉም ክብር ርቀው በዘላለም ጥፋት ይቀጣሉ”*።
ሉቃስ 15:4 መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ *”ቢጠፋ”*፥ ዘጠና ዘጠኙን በበረሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሄድ ከእናንተ ማን ነው?”
ሉቃስ 15:8 ወይም አሥር ድሪም ያላት አንድ ድሪም ቢጠፋባት፥ መብራት አብርታ ቤትዋንም ጠርጋ እስክታገኘው ድረስ አጥብቃ የማትፈልግ ሴት ማን ናት?”
ሉቃስ 15:32 ዳሩ ግን ይህ ወንድምህ *”ሞቶ ነበረ ሕያው ስለ ሆነ ጠፍቶም”* ነበር ስለ ተገኘ ደስ እንዲለን ፍሥሐም እንድናደርግ ይገባናል አለው።

ኢንሻላህ ሞት በቁርአን በክፍል ሁለት እናያለን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ሞት

ክፍል ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

67፥3 ያ የትኛችሁ ሥራው ይበልጥ ያማረ መኾኑን *”ሊፈትናችሁ ሞትንና ሕይወትን የፈጠረ ነው”*፡፡ እርሱም አሸናፊው መሓሪው ነው፡፡ ٱلَّذِى خَلَقَ ٱلْمَوْتَ وَٱلْحَيَوٰةَ لِيَبْلُوَكُمْ أَيُّكُمْ أَحْسَنُ عَمَلًۭا ۚ وَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْغَفُورُ

2. ሞት በቁርአን
አምላካችን አላህ ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት ብሎ ነው የነገረን፤ ህይወት የስራችን ሽልማለት እንዳልሆነ ሁሉ ሞትም የስራችን ቅጣት አይደለም። ለፈተና ሞትንና ሕይወትን የፈጠረ እርሱ ነው፤ “ሊፈትናችሁ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሊየብሉወኩም” لِيَبْلُوَكُمْ ሲሆን ሞትንና ሕይወት በሰጠን ፀጋ ፈተና ነው፤ ይህም አላማው አንዱ ሲወለድ ሌላ ሲሞት በምድር ላይ ለመተካካት ነው፦
67፥3 ያ የትኛችሁ ሥራው ይበልጥ ያማረ መኾኑን *”ሊፈትናችሁ ሞትንና ሕይወትን የፈጠረ ነው”*፡፡ እርሱም አሸናፊው መሓሪው ነው፡፡ ٱلَّذِى خَلَقَ ٱلْمَوْتَ وَٱلْحَيَوٰةَ لِيَبْلُوَكُمْ أَيُّكُمْ أَحْسَنُ عَمَلًۭا ۚ وَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْغَفُورُ
21፥35 ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፡፡ *”ለመፈተንም በክፉም በበጎም እንፈትናችኋለን”*፤ ወደኛም ትመለሳላችሁ፡፡ كُلُّ نَفْسٍۢ ذَآئِقَةُ ٱلْمَوْتِ ۗ وَنَبْلُوكُم بِٱلشَّرِّ وَٱلْخَيْرِ فِتْنَةًۭ ۖ وَإِلَيْنَا تُرْجَعُونَ
11፥7 እርሱም ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ ነው፡፡ ዐርሹም በውሃ ላይ ነበር፡፡ *”የትኛችሁ ሥራው ያማረ መሆኑን ይፈትናችሁ”* ዘንድ ፈጠራቸው፡፡
6፥165 እርሱም ያ *”በምድር ምትኮች”* ያደረጋችሁ *”በሰጣችሁም ጸጋ ሊፈትናችሁ”* ከፊላችሁን ከከፊሉ በላይ በደረጃዎች ከፍ ያደረገ ነው፡፡
2:30 ጌታህ ለመላእክት፡- «እኔ *”በምድር ላይ ምትክን”* አድራጊ ነኝ፤» ባለ ጊዜ የኾነውን አስታውስ፤

ነጥብ አንድ
“ነፍስ”
“ነፍስ” نَفْس የሚለው የአረቢኛው ቃል “ደሚሩል-ነፍሲያ” ማለትም ድርብ ተውላጠ-ስም”Rreflexive pronoun” ሲሆን ራስነት”self-hood”፣ ሁለንተናዊ ግላዊነት”own individuality” ያሳያል፦
4:79 *ከደግም*حَسَنَةٍ የሚያገኝህ ከአላህ ነው፤ *ከፉዉም* سَيِّئَةٍ የሚደርስብህ *ከራስህ* نَفْسِكَ ነው፤

*ከራስህ* የሚለው ቃል “ነፍሲከ” نَفْسِكَ ሲሆን “ነፍስ” نَفْس ከሚለው የአረቢኛው ቃል ደሚሩል-ነፍሲያ ሲሆን የሰው ማንነትን ያሳያል፤ ለምሳሌ የአደምን አንድ ማንነት ለማሳየት “አንዲት ነፍስ” ይላል፦
4:1 እናንተ ሰዎች ሆይ! ያንን *ከአንዲት ነፍስ* مِنْ نَفْسٍ وَاحِدَةٍ የፈጠራችሁን፣ ከእርስዋም መቀናጆዋን የፈጠረውን፣ ከነርሱም ብዙ ወንዶችንና ሴቶችን የበተነውን፣ ጌታችሁን ፍሩ።

ሰው ወደ ጀነት የሚገባው በመንፈሱና በአካሉ ነው። ነፍስ እዚህ ጋር የሰውን ሁለንተና ያመለክታል፦
89:27 ለአመነች ነፍስም *”«አንቺ የረካሺው “ነፍስ” النَّفْسُ ሆይ”*!
89:30 *”ገነቴንም ግቢ”*፤» ትባላለች፡፡

ነፍስ አንዳንዴ አካልን ሲያመለክት አንዳንዴ መንፈስን ያመለክታል እንጂ ሁሌም ነፍስ ሩህ ነው ብሎ አራት ነጥብ አይዘጋም፣ ነፍስ አካል ሲያመለክት “ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት” ይላል፦
3:185 *”ነፍስ” نَفْس ٍ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት”*፤ ምንዳዎቻችሁንም የምትሞሉት በትንሣኤ ቀን ብቻ ነዉ።
29:57 *”ነፍስ” نَفْسٍ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት*”፤ ከዚያም ወደኛ ትመለሳለችሁ።
21:35 *”ነፍስ” نَفْسٍ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት”*፤ ለመፈተንም በክፉም በበጎም እንሞክራችኋለን፤ ወደኛም ትመለሳላችሁ።

ነፍስ ሩሕ በሚል ይመጣል፤ አላህ የሰውን መንፈስ በሞት ጊዜ ይወስዳል፣ ያልሞተውን ሰው በእንቅልፉ ጊዜ ይወስዳታል፤ እንቅልፍ መንፈስና አካል ለመለያየት የሚያደርጉበት ልምምድ ነው፣ ሰው በእንቅልፍ ጊዜ ያለ አይን ያያል፣ ያለ ጆሮ ይሰማል፣ ያለ እግር ይሄዳል፣ ያለ አፍ ይናገራል፣ ይህ የሚያሳየው ሰው በሞት ጊዜ አካሉ ላይ ያሉት አይን፣ ጆሮ፣ እግር፣ አፍ ሲፈርሱ መንፈስ ግን ይወስዳል፣ መንፈስ ከጌታ ነገር ነው ወደ ጌታ ይወሰዳል፤ መንፈስ ነፍስ እንደተባለ አስተውል፦
39:42 አላህ *”ነፍሶችን” الْأَنْفُسَ “በሞታቸው ጊዜ” ይወስዳል፤ ያችንም ያልሞተችውን “በእንቅልፏ ጊዜ” ይወስዳታል*፤
17:85 ከሩሕም ይጠይቁሃል፤ *”ሩሕ ከጌታዬ ነገር ነው”* ከዕውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም፤ በላቸው።

ነፍስ የሚለው ቃል “ነፍስያ” نفسيه ማለትም “የራስ ዝንባሌ” ለማመልከት ይመጣል፤ ይህ ዝንባሌ በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ነው፦
12፥53 «ነፍሴንም ከስሕተት አላጠራም፡፡ *ነፍስ ሁሉ ጌታዬ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር *”በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና*፡፡ ጌታዬ በጣም መሓሪ አዛኝ ነው» አለ፡፡
ነጥብ ሁለት
“በርዘኽ”
“በርዘኽ” برزخ ማለት የቃሉ ትርጉም “ጋራጅ” ማለት ሲሆን “መለያ” እና “መቆያ” ነው፤ አላህ ሩህን በሞት ጊዜ ይወስዳል፣ በእንቅልፍ ጊዜ የምንወሰደው ነገር ማለትም ያለ አይን ማየቱ፣ ያለ ጆሮ መስማቱ፣ ያለ እግር መሄዱ፣ ያለ አፍ መናገሩ ሩህ ከሞት በኋላ ያለውን ሁኔታ በጥቂቱ የምናይበት ነው፣ ምነው እንቅልፍ የሞት ታናሽ ወንድም ይባል የለ አይደል? ሩህ እስከ ቂያማ ቀን ድረስ በበርዘክ ይቆያሉ፣ “በርዘኽ” በሞትና በትንሳኤ መካከል ያለ ሁኔታ”Intermediate zone” ነው፦
23:99-100 አንዳቸውንም ሞት በመጣበት ጊዜ እንዲህ ይላል «ጌታዬ ሆይ! ወደ ምድረ ዓለም መልሱኝ፡፡ በተውኩት ነገር በጎን ሥራ ልሠራ እከጅላለሁና፡፡» ይህን ከማለት ይከልከል፡፡ እርስዋ እርሱ ተናጋሪዋ የኾነች ከንቱ ቃል ናት፡፡ *”ከስተፊታቸውም እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ “ግርዶ” بَرْزَخٌ አለ”*፡፡

የሁሉም ሩህ ወደ አላህ ቢመለስም ነገር ግን የሙስሉምና የካፊር ሩህ እንዳይገናኙ በመካከላቸው “በርዘኽ” አለ፤ የበርዘኽ ምሳሌ ምንድን ነው? የበርዘኽ ምሳሌ በባህር ውስጥ በጣፋጩና በጨው ባሕር መካከል ግርዶ መኖሩን ምሳሌ ይጠቀማል፦
55:19-20 ሁለቱን ባሕሮች የሚገናኙ ሲሆኑ ለቀቃቸው። *”እንዳይዋሐዱ በመካከላቸው “ጋራጅ” بَرْزَخًا አለ፤ አንዱ ባንዱ ላይ ወሰን አያልፍም”*፤
25:53 እርሱም ያ ሁለቱን ባሕሮች፣ አጐራብቶ የለቀቀ ነው፤ ይህ ጥምን የሚቆርጥ ጣፋጭ ነው፤ ይህም የሚመረግግ ጨው ነው፤ *”በመካከላቸውም ከመቀላቀል መለያንና የተከለለን “ክልል” بَرْزَخًا ያደረገ ነው”*።
27:61 *”በሁለቱ ባሕሮችም በጣፋጩና በጨው ባሕር መካከል ግርዶን ያደረገ”* ይበልጣልን? ወስ የሚያጋሩት? ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም።

ነጥብ ሶስት
“ሞት”
ሞት በአላህ ሁን በሚል ትእዛዝ የሚሆን ነው፤ የሚያሞትም እና ሕያው የሚያደርግ እርሱ ነው፤ ከእኛ አንፃር ሞት እኩይ ህይወት ሰናይ ቢሆንም ሁለቱም ግን ከአላህ ዘንድ ናቸው፤ ሁለቱንም የፈጠረው እርሱ ነው፦
40:68 እርሱ ያ *”ሕያው የሚያደርግ፣ የሚያሞትም ነው፤ አንዳችን ነገር ባሻም ጊዜ የሚለው ሁን ነው፤ ወዲያውም ይሆናል”*።
4:78 የትም ስፍራ ብትኾኑ፣ በጠነከሩ ሕንጻዎች ውስጥ ብትኾኑም እንኳን *”ሞት ያገኛችኋል”*፤ ደግም ነገር ብታገኛቸው ይህች ከአላህ ዘንድ ናት፣ ይላሉ፤ መከራም ብታገኛቸው ይህቺ ከአንተ ዘንድ ናት ይላሉ፤ *”ሁሉም ከአላህ ዘንድ ነው”* በላቸው፤
67፥3 ያ የትኛችሁ ሥራው ይበልጥ ያማረ መኾኑን *”ሊፈትናችሁ ሞትንና ሕይወትን የፈጠረ ነው”*፡፡
56:60 እኛ *”ሞትን በመካከላችሁ ወሰንን*፤ እኛም ተሸናፊዎች አይደለንም።

ቁርአን ሞት የሚለውን ቃል ለተለያየ ነገር ይጠቀምበታል፤ ለምሳሌ ከመፈጠራችን በፊት የነበረውን ህልውና አልባ ሁኔታ ሙታን ህልውናችንን ደግሞ ሕያው ይለዋል፦
2:28 *”ሙታን የነበራችሁ ስትኾኑ ሕያው ያደረጋችሁ”* وَكُنْتُمْ أَمْوَاتًا فَأَحْيَاكُمْ ከዚያም የሚገድላችሁ يُمِيتُكُمْ ከዚያም ሕያው የሚያደርጋችሁ يُحْيِيكُمْ ሲኾን ከዚያም ወደርሱ የምትመለሱ ስትኾኑ በአላህ እንዴት ትክዳለችሁ!

ከመፈጠራችን በፊት ያለውን ህልውና አልባ እና ከተፈጠርን በኃላ ያለው ህልውና አልባ ሁኔታ ሁለት ሞት ሲለው ከተፈጠርን በኃላ ያለውን ህይወት እና ከትንሳኤ በኃላ ያለውን ህይወት ሁለት ህይወት ይለዋል፦
40:11 ጌታችን ሆይ! *”ሁለትን ሞት አሞትከን”፣ ሁለትንም ሕይወት”* ሕያው አደረግከን أَمَتَّنَا اثْنَتَيْنِ وَأَحْيَيْتَنَا اثْنَتَيْنِ፤ በኃጢአቶቻችንም መሰከርን፤ ታዲያ ከእሳት ወደ መውጣት መንገድ አለን? ይላሉ።

አንድ ቁስ”matter” ቁስ ከመሆኑ በፊት ኢነርጂ”energy” ነው፤ ይህ ቁስ ከኢነርጂ ይገኛል፤ በተቃራኒው ከቁስ ኢነርጂ ይገኛል፤ አላህ ይህንን ኢነርጂ ህያው ሲለው ቁስን ደግሞ ሙት ይለዋል፣ አላህ ከኢነርጂ ቁስን ከቁስ ደግሞ ኢነርጂን ያወጣል፦
3:27 ሌሊቱን በቀን ዉስጥ ታስገባለህ፤ ቀኑንም በሌሊቱ ዉስጥ ታስገባለህ፤ *”ሕያዉንም ከሙት ዉስጥ ታወጣለህ፤ ሙትንም ከሕያዉ ዉስጥ ታወጣለህ”*፣ ለምትሻዉም ሰዉ ያለግምት ትሰጣለህ።
6:95 አላህ ቅንጣትንና የፍሬን አጥንት ፈልቃቂ ነው፡፡ *ሕያውን ከሙት ያወጣል፤ ሙትንም ከሕያው አውጪ ነው*፡፡
30:19 *”ሕያውን ከሙት ያወጣል፤ ሙትንም ከሕያው ያወጣል”*፤ ምድርንም ከሞተች በኋላ ሕያው ያደርጋታል፤ እንደዚሁም ከመቃብር ትወጣላችሁ።
10:31 «ከሰማይና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማን ነው መስሚያዎችንና ማያዎችንስ የፈጠረ ማን ነው? *ከሙትም ሕያውን የሚያወጣ ከሕያውም ሙትን የሚያወጣስ ማን ነው?* ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብርስ ማን ነው» በላቸው፡፡ «በእርግጥም አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ ለምን ታጋራላችሁ አትፈሩትምን?» በላቸው፡፡

አንድ ካፊር በኩፍር ውስጥ ካላ ሙታን ነው፤ ይህ ሙታንነት ከውስጣዊ እውርነትና ድንቁርናነት ስለመጣ ውስጣዊ ሞት ነው፦
30:52 አንተም *”ሙታንን”* አታሰማም፤ ደንቆሮዎችንም ዟሪዎች ሆነው በሸሹ ጊዜ ጥርሪን አታሰማም።
27:80 አንተ *”ሙታንን”* አታሰማም፤ *ደንቆሮችንም* የሚተው ሆነው በዞሩ ጊዜ ጥሪን አታሰማም።
43:40 አንተ *ደንቆሮዎቹን ታሰማለህን? ወይንስ እውሮችን* እና በግልጽ ጥመት ውስጥ የሆኑን ሰዎች ትመራለህን?

አንድ ሙሽሪክ በጀሃነም ስቃዩና ቅጣቱ እንደ ሞት ሆኖ ይመጣበታል፤ ግን አይሞትም፤ ይህንን ሞት በጀነት ያሉት አይቀምሱትም፤ የፊተኛይቱን ሞት ሁሉም ሰው የሚሞተው ተፍጥሮአዊ ሲሆን የኃለኛው ግን የጀሃነም ቅጣት ነው፦
14:17 ይጎነጨዋል፤ ሊውጠውም አይቀርብም፤ *”ሞትም ከየስፍራው ሁሉ ይመጣበታል፤ እርሱም የሚሞት አይደለም”*፤ ከስተፊቱም ከባድ ቅጣት አለ።
44:56 *”የፊተኛይቱን ሞት እንጂ ዳግመኛ በርሷ ውስጥ ሞትን አይቀምሱም”*፤ የገሀነምንም ቅጣት አላህ ጠበቃቸው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ሂጅራህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥100 *በአላህም መንገድ የሚሰደድ ሰው በምድር ውስጥ ብዙ መሰደጃንና ምቾትን ያገኛል፡፡ ወደ አላህና ወደ መልክተኛውም ስደተኛ ኾኖ ከቤቱ የሚወጣ ከዚያም በመንገድ ሞት የሚያገኘው ሰው ምንዳው በእርግጥ አላህ ዘንድ ተረጋገጠ*፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ وَمَن يُهَاجِرْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ يَجِدْ فِي الْأَرْضِ مُرَاغَمًا كَثِيرًا وَسَعَةً ۚ وَمَن يَخْرُجْ مِن بَيْتِهِ مُهَاجِرًا إِلَى اللَّهِ وَرَسُولِهِ ثُمَّ يُدْرِكْهُ الْمَوْتُ فَقَدْ وَقَعَ أَجْرُهُ عَلَى اللَّهِ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا

ነቢያችን”ﷺ” ለመጀመሪያ ጊዜ ወሕይ ማለትም “ግልጠተ-መለኮት”Revelation” የመጣላቸው በ 610 ድህረ-ልደት”AD” ነው፤ ከዚያም በ 613 ድህረ-ልደት የወሕይ ጭብጥ የሆነው ተህሊል ለመካ ሰዎች አወጁ፤ ይህንን አዋጅ ያልተቀበሉት መካውያን የነቢያችንን”ﷺ” ባልደረቦች በማሳደዳቸው የመጀመሪያው ስደት በ 615 ድህረ-ልደት ወደ ሃበሻ ምድር ወደ ኢትዮጵያ ሆኗል። አምላካችን አላህ በእርሱ መንገድ ስለሚሰደዱት ስደተኞች እንዲህ ይለናል፦
4፥100 *በአላህም መንገድ የሚሰደድ ሰው በምድር ውስጥ ብዙ መሰደጃንና ምቾትን ያገኛል፡፡ ወደ አላህና ወደ መልክተኛውም ስደተኛ ኾኖ ከቤቱ የሚወጣ ከዚያም በመንገድ ሞት የሚያገኘው ሰው ምንዳው በእርግጥ አላህ ዘንድ ተረጋገጠ*፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ وَمَن يُهَاجِرْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ يَجِدْ فِي الْأَرْضِ مُرَاغَمًا كَثِيرًا وَسَعَةً ۚ وَمَن يَخْرُجْ مِن بَيْتِهِ مُهَاجِرًا إِلَى اللَّهِ وَرَسُولِهِ ثُمَّ يُدْرِكْهُ الْمَوْتُ فَقَدْ وَقَعَ أَجْرُهُ عَلَى اللَّهِ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا
2፥218 *እነዚያ ያመኑትና እነዚያም ከአገራቸው የተሰደዱት በአላህም መንገድ ላይ የተጋደሉት እነዚያ የአላህን እዝነት ይከጅላሉ*፡፡ አላህም እጅግ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَالَّذِينَ هَاجَرُوا وَجَاهَدُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ أُولَـٰئِكَ يَرْجُونَ رَحْمَتَ اللَّهِ ۚ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

“ሂጅራህ” هِجْرَة የሚለው ቃል “ሃጀረ” هَاجَرَ ማለትም “ተሰደደ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ስደት”migration” ማለት ነው። ነቢያችን”ﷺ” እና ባልደረቦቻቸው ከሚኖሩበት ቀዬ ከመካ ወደ መዲና በ 622 ድህረ-ልደት ተሰደዋል፦
16፥41 *እነዚያም ከተበደሉ በኋላ በአላህ መንገድ ላይ የተሰደዱት በቅርቢቱ ዓለም መልካሚቱን አገር (መዲናን) በእርግጥ እናሰፍራቸዋለን፡፡ የመጨረሻይቱም ዓለም ምንዳ ታላቅ ነው*፡፡ ከሓዲዎች ቢያውቁ ኖሮ በተከተሏቸው ነበር፡፡ وَالَّذِينَ هَاجَرُوا فِي اللَّهِ مِن بَعْدِ مَا ظُلِمُوا لَنُبَوِّئَنَّهُمْ فِي الدُّنْيَا حَسَنَةً ۖ وَلَأَجْرُ الْآخِرَةِ أَكْبَرُ ۚ لَوْ كَانُوا يَعْلَمُونَ
9፥20 *እነዚያ ያመኑት፣ ከአገራቸውም የተሰደዱት፣ በገንዘቦቻቸው እና በነፍሶቻቸውም በአላህ መንገድ ላይ የታገሉት አላህ ዘንድ በደረጃ በጣም የላቁ ናቸው*፡፡ እነዚያም እነሱ ፍላጎታቸውን ያገኙ ናቸው፡፡ الَّذِينَ آمَنُوا وَهَاجَرُوا وَجَاهَدُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ بِأَمْوَالِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ أَعْظَمُ دَرَجَةً عِندَ اللَّهِ ۚ وَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْفَائِزُونَ

“የተሰደዱ” ለሚለው ቃል የገባው “ሃጀሩ” هَاجَرُوا ሲሆን “ሃጀረ” هَاجَرَ ከሚለው ሥርወ-ቃል መምጣቱ አንባቢ ልብ ይለዋል፤ “ሙሃጂር” مُهَاجِر ማለት ደግሞ “ስደተኛ” ማለት ሲሆን ከመካ ወደ መዲና የተሰደዱትን መካውያን ሰሃባዎችን ያመለክታል፤ መዲና ላይ ከመካ የተሰደዱትን እረድተው የተቀበሉ “ነሲር” نَصِير ማለትም “ረዳት” ይባላሉ፦
8፥74 *እነዚያም ያመኑና የተሰደዱ በአላህም መንገድ ላይ የታገሉ፣ እነዚያም ያስጠጉ እና የረዱ እነዚያ እነርሱ በእውነት አማኞች ናቸው፡፡ ለእነሱም ምሕረትና የከበረ ሲሳይ አላቸው*፡፡ وَالَّذِينَ آمَنُوا وَهَاجَرُوا وَجَاهَدُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَالَّذِينَ آوَوا وَّنَصَرُوا أُولَـٰئِكَ هُمُ الْمُؤْمِنُونَ حَقًّا ۚ لَّهُم مَّغْفِرَةٌ وَرِزْقٌ كَرِيمٌ
9፥100 *ከስደተኞቹ እና ከረዳቶቹም ሲኾኑ የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች እነዚያም በበጎ ሥራ የተከተሏቸው አላህ ከእነሱ ወዷል ከእርሱም ወደዋል፡፡ በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ነዋሪዎች ሲኾኑ ለእነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡ ይህ ታላቅ ዕድል ነው*፡፡ وَالسَّابِقُونَ الْأَوَّلُونَ مِنَ الْمُهَاجِرِينَ وَالْأَنصَارِ وَالَّذِينَ اتَّبَعُوهُم بِإِحْسَانٍ رَّضِيَ اللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا عَنْهُ وَأَعَدَّ لَهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي تَحْتَهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا ۚ ذَٰلِكَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ

“ረዳቶች” ለሚለው ቃል የገባው “አንሷር” أَنْصَار ሲሆን “ነሲር” نَصِير ለሚለው ቃል ብዜት ነው፤ ይህም ስም መዲናውያን ሰሃባዎችን ያመልክታል፦
8፥72 *እነዚያ ያመኑና የተሰደዱ፡፡ በአላህም መንገድ ላይ በገንዘቦቻቸው እና በነፍሶቻቸው የታገሉ፡፡ እነዚያም ስደተኞቹን ያስጠጉና የረዱ፡፡ እነዚያ ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው*፡፡ إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَهَاجَرُوا وَجَاهَدُوا بِأَمْوَالِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَالَّذِينَ آوَوا وَّنَصَرُوا أُولَـٰئِكَ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَاءُ بَعْضٍ

622 ድህረ-ልደት በነቢያችን”ﷺ” ላይ የወረደው ወሕይ በነጻነት የተላለፈበት እና የአምልኮ ነጻነት የሆነበት ቀን ነው፤ በዚህ ዓመት በመዲና ውስጥ የቁባ መስጊድ የተገነባበት ነው፦
9፥108 በእርሱ ውስጥ በፍጹም አትስገድ፡፡ *ከመጀመሪያ ቀን ይዞ በአላህ ፍራቻ ላይ የተመሠረተው የቁባ መስጊድ በውስጡ ልትሰግድበት ይልቅ የተገባው ነው*፡፡ በእሱ ውስጥ መጥራራትን የሚወዱ ወንዶች አሉ፡፡ አላህም ተጥራሪዎችን ይወዳል፡፡ لَا تَقُمْ فِيهِ أَبَدًا ۚ لَّمَسْجِدٌ أُسِّسَ عَلَى التَّقْوَىٰ مِنْ أَوَّلِ يَوْمٍ أَحَقُّ أَن تَقُومَ فِيهِ ۚ فِيهِ رِجَالٌ يُحِبُّونَ أَن يَتَطَهَّرُوا ۚ وَاللَّهُ يُحِبُّ الْمُطَّهِّرِينَ