ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
69 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ነጥብ ሁለት
አላህ የሰማያትና የምድር፣ በሁለቱም መካካል ላለዉ ሁሉ ጌታ ነዉ፦
45:36 ምስጋናም ለአላህ፣ ለሰማያት ጌታ፣ ለምድርም ጌታ፣ ለአለማት ጌታ የተገባው ነው።
13:16 የሰማያትና የምድር ጌታ ማን ነው? በላቸው፤ አላህ ነው በል፤
19:65 እርሱ የሰማያትና የምድር፣ በሁለቱም መካካል ላለዉ ሁሉ ጌታ ነዉና ተገዛዉ፤
37:5 የሰማያትና የምድር በመካከላቸዉ ያለዉም ፍጡር ሁሉ ጌታ ነዉ። የምሥራቆችም ጌታ ነዉ።
38:66 «የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ሁሉ ጌታ አሸናፊው መሓሪው ነው፡፡»
21:56 አይደለም፣ ጌታችሁ የሰማያትና የምድር ጌታ ያ የፈጠራቸው ነው፤

ነጥብ ሶስት
አላህ የታላቁ ዐርሽ ጌታ ነው፦
9:129 ቢያፈገፍጉም አላህ በቂዬ ነው፤ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ በርሱ ላይ ተጠጋሁ፤ እርሱም የታላቁ ዐርሽ ጌታ ነው በላቸው።
43:82 የሰማያትና ምድር ጌታ የዙፋኑ ጌታ ከሚሉት ነገር ሁሉ ጠራ።
27:26 አላህ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ የታላቁ ዐርሽ ጌታ ነው።
23:86 «የሰባቱ ሰማያት ጌታና የታላቁ ዐርሽ ጌታ ማን ነው» በላቸው፡፡
23:116 የእውነቱም ንጉስ አላህ ከፍተኛነት ተገባው፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ የሚያምረው ዐርሽ ጌታ ነው፡፡

ነጥብ አራት
አላህ የካዕባ ጌታ ነው፦
27:91 የታዘዝኩት የዚህችን አገር ጌታ ያንን ክልል ያደረጋትን እንድግገዛ ብቻ ነው፤

ነጥብ አምስት
አላህ የቤቱ ጌታ ነው፦
106:3 ስለዚህ የዚህን ቤት ጌታ ይግገዙ።

ነጥብ ስድስት
አላህ የሺዕራ ጌታ ነው፦
53:49 እነሆ እርሱም የሺዕራ ጌታ ነው።

ነጥብ ሰባት
አላህ የምስራቅና የምዕራብ ጌታ ነው፦
73:9 እርሱም የምስራቅና የምዕራብ ጌታ ነው፤ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ መጠጊያ አድርገህም ያዘው።
መደምደሚያ
ጌታችን ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው፦
47:54 ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው፤
50:38 ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ በእርግጥ ፈጠርን፡፡

አላህ ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ፤ ፍሩኝ ይላል፦
21:92 ይህች አንዲት መንገድ ስትኾን በእርግጥ ሃይማኖታችሁ ናት፤ እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ።
23:52 ይህችም አንድ መንገድ ስትኾን ሃይማኖታችሁ ናት፡፡ እኔም ጌታችሁ ነኝና ፍሩኝ፡፡

የሙሴ አምላክ የሲና አምላክ ነው፦
መዝሙር 68:8 ከሲና አምላክ ፊት፥ ከእስራኤል አምላክ ፊት ሰማያትም አንጠበጠቡ።
ሲና ደግሞ አረብ ሃገር ናት፦
ገላ 4:25 ይህችም አጋር በዓረብ ምድር ያለችው ደብረ ሲና ናት፤

ያቺ የሲና መሬት ደግሞ የተቀደሰች ናት፦
ዘጸአት 3:5 እርሱም፦ እነሆኝ አለ። ወደዚህ አትቅረብ አንተ የቆምህባት ስፍራ የተቀደሰች መሬት ናትና ጫማህን ከእግርህ አውጣ አለው።

አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ኢየሱስ ጌታ ነውን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

6፥164 በላቸው «እርሱ አላህ “”የሁሉ ጌታ”” ሲሆን ከአላህ በቀር “”ሌላን ጌታ”” እፈልጋለሁን? ነፍስም ሁሉ በራሷ ላይ እንጅ ክፉን አትሠራም፡፡ قُلْ أَغَيْرَ ٱللَّهِ أَبْغِى رَبًّۭا وَهُوَ رَبُّ كُلِّ شَىْءٍۢ ۚ وَلَا تَكْسِبُ كُلُّ نَفْسٍ إِلَّا عَلَيْهَا

መግቢያ
ብዙ ጊዜ ክርስቲያን ሚሽነሪዎች ኢየሱስ ጌታ ነው ብለው ሲሰብኩ ይታያል፤ ሙስሊሙ በተቃራኒው ኢየሱስ የዓለማት ጌታ አይደለም ብሎ ክፉኛ ይሟገታል፤ በእርግጥም አላህ የዓለማቱ ጌታ ነው፦
40:65 ምስጋና ለዓለማት ጌታ ለአላህ ይሁን፣ የምትሉ ሆናችሁ አምልኩት።
40:66 ለዓለማት ጌታም እንዳመልከው ታዝዣለሁ በላቸው።

አምላካችን አላህ ጌታችን ነው፤ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ ነገርን ሁሉ ፈጣሪ ነው፦
10፥3 ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው፡፡ ከዚያም ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብር ሲኾን በዐርሹ ላይ ተደላደለ፡፡
6፥102 ይህ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ ነገርን ሁሉ ፈጣሪ ነው፡፡ ስለዚህ አምልኩት፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነው፡፡

አምላካችን አላህ የሁሉ ጌታ ነው፤ ከእርሱ በቀር ሌላ ጌታ የለም፦
6፥164 በላቸው «እርሱ አላህ “”የሁሉ ጌታ”” ሲሆን ከአላህ በቀር “”ሌላን ጌታ”” እፈልጋለሁን? ነፍስም ሁሉ በራሷ ላይ እንጅ ክፉን አትሠራም፡፡ قُلْ أَغَيْرَ ٱللَّهِ أَبْغِى رَبًّۭا وَهُوَ رَبُّ كُلِّ شَىْءٍۢ ۚ وَلَا تَكْسِبُ كُلُّ نَفْسٍ إِلَّا عَلَيْهَا

ይህ እውነታ በመለኮታዊ ቅሪት ባይብል ላይ እንዲህ ተቀምጧል፦
ማርቆስ 12:29 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው። ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ። እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ *ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው* اسْمَعْ يَا إِسْرَائِيلُ. الرَّبُّ إِلَهُنَا رَبٌّ وَاحِدٌ. ።

ልብ አድርጉ ዐረብ ክርስቲያኖች ባስቀመጡበት እዚህ ጥቅስ ላይ “ጌታ” ተብሎ የተቀጠው ቃል “ረብ” رَبّ ነው፤ ነገር ግን ሃዋርያት ኢየሱስን “ጌታ” ያሉትና ያረጋገጠላቸው ቃል ግን “ረብ” አይደለም፦
ዮሐንስ 13:13 እናንተ *መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ*፤ እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ أَنْتُمْ تَدْعُونَنِي مُعَلِّماً وَسَيِّداً وَحَسَناً تَقُولُونَ لأَنِّي أَنَا كَذَلِكَ ።

ልብ አድርጉ “ጌታ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሰይድ” سَيِّد ነው፤ “ሰይድ” ማለት በአማርኛችን “ጌታ” ይባል እንጂ ይህ ቃል ማእረግና ሹመትን ለማመልከት ለየህያህ ሆነ ለሰዎች ቁርአን ተጠቅሞበታል፦
3፥39 እርሱም በጸሎት ማድረሻው ክፍል ቆሞ ሲጸልይ መላእክት ጠራችው፡፡ «አላህ በየሕያ ከአላህ በኾነ ቃል የሚያረጋግጥ *ጌታም* ድንግልም ከደጋጎቹ ነቢይም ሲኾን ያበስርሃል» በማለት ጠራው فَنَادَتْهُ ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ وَهُوَ قَآئِمٌۭ يُصَلِّى فِى ٱلْمِحْرَابِ أَنَّ ٱللَّهَ يُبَشِّرُكَ بِيَحْيَىٰ مُصَدِّقًۢا بِكَلِمَةٍۢ مِّنَ ٱللَّهِ وَسَيِّدًۭا وَحَصُورًۭا وَنَبِيًّۭا مِّنَ ٱلصَّٰلِحِينَ ፡፡
33፥67 ይላሉም *ጌታችን* ሆይ! እኛ *ጌቶቻችንን* እና ታላላቆቻችንን ታዘዝን፡፡ መንገዱንም አሳሳቱን وَقَالُوا۟ رَبَّنَآ إِنَّآ أَطَعْنَا سَادَتَنَا وَكُبَرَآءَنَا فَأَضَلُّونَا ٱلسَّبِيلَا۠ ፡፡

ልብ አድርጉ ሰዎቹ የትንሳኤ ቀን ሰዎችን “ሳደተና” سَادَتَنَا ሲሉ አላህን ግን “ረበና” رَبَّنَا ብለው ተጠቅመዋል፤ ስለዚህ ኢየሱስ የዓለማት ጌታ ነኝ አላለም፤ ባይሆን አንድ ጌታ ብሎ ያለው የላከውን ነው፤ ይህንን ለቅምሻ ያክል ካየን ወደ ባይብሉ መሰረት እንሂድ፦
ነጥብ አንድ
“አዶኒ”
“አዶኒ” אֲדֹנִ֖י የሚለው ቃል “አዶን” אָדוֹן ለሚለው ቃል አገናዛቢ ሲሆን “ጌታዬ” ማለት ነው፤ ይህ ቃል ለፍጡራን ክብርና ማእረግ አሊያም ስልጣንና ሹመትን ያሳያል፤ በዚህ ቃል ጌታ የተባሉት ፍጡራን ለናሙና ያክል፦
@አብርሐም፦
ዘፍጥረት18:12 ሣራም በልብዋ እንዲህ ስትል ሳቀች። ካረጀሁ በኋላ በውኑ ፍትወት ይሆንልኛልን? ጌታዬም אדֹנִ֗י ፈጽሞ ሸምግሎአል።
@ዔሳው፦
ዘፍጥረት 32:4 እንዲህም ብሎ አዘዛቸው። ለጌታዬ אדֹנִ֗י ለዔሳው። ባሪያህ ያዕቆብ እንዲህ አለ ብላችሁ ንገሩት። በላባ ዘንድ በስደት ተቀመጥሁ፤ እስከ አሁን ድረስ ቆየሁ፤
@ሙሴ፦
ዘኊልቅ 11:28 ከልጅነቱ ጀምሮ የሙሴ አገልጋይ የነበረው የነዌ ልጅ ኢያሱ። ጌታዬ אדֹנִ֗י ሙሴ ሆይ፥ ከልክላቸው አለው።
@ሚካኤል፦
ኢያሱ 5:14 እርሱም። አይደለሁም፤ እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቼአለሁ አለ። ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደና። ጌታዬ אדֹנִ֗י ለባሪያው የሚነግረው ምንድር ነው? አለው።
@ሳኦል፦
1ሳሙኤል 24:8፤ ከእርሱም በኋላ ዳዊት ደግሞ ተነሣ፥ ከዋሻውም ወጣ፥ ከሳኦልም በኋላ። ጌታዬ אדֹנִ֗י ንጉሥ ሆይ፥ ብሎ ጮኸ፤ ሳኦልም ወደ ኋላው ተመለከተ፥ ዳዊትም ወደ ምድር ተጐንብሶ እጅ ነሣ።
@ናቡከነደጾር፦
ዳንኤል 4:24፤ በጌታዬ אדֹנִ֗י በንጉሥ ላይ የወረደው የልዑሉ ትእዛዝ ነው፤
@መሢሑ፦
መዝሙር 110:1 ያህዌህ ጌታዬን אדֹנִ֗י ። ጠላቶችህን ለእግርህ መቀመጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው።

በተለይ ዳዊት መሢሁን “አዶኒ” אדֹנִ֗י ያለበት ሣራ አብርሐም ፣ ኢያሱ ሙሴን፣ ኢያሱ ሚካኤልን፣ ዳንኤል ናቡከነደጾርን “ጌታዬ” ባሉበት ሂሳብ እንደሆነ እሙንና ቅቡል ነው፤ ይህንን የገባቸው የአዲስ ኪዳን ተርጓሚዎች ጴጥሮስ ከመዝሙር 110:1 ላይ የጠቀሰውን እንግን አስቀምጠውታል፦
ሐዋርያት ስራ 2:34 ዳዊት ወደ ሰማያት አልወጣምና፥ ነገር ግን እርሱ። ጌታ ጌታዬን። ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው። *””The LORD said unto my Lord”” *
New Living Translation, King James Bible, Webster’s Bible Translation.

ምሁራን አንዱ አምላክ አብ “ጌታ” የተባለበት ለማመልከት በካፒታል ፊደል *The LORD* ብለው ሲያስቀምጡ ነገር ግን ኢየሱስ “ጌታ” የተባለበት ለማመልከት በስሞል ፊደል *Lord * አስቀምጠዋል፣ ትልቁ ጌታ *The LORD* አብ ትንሹን ጌታ *Lord * ኢየሱስን በቀኜ ተቀመጥ አለው፤ የሚገርም ነው የኢየሱስ ጌትነት ማእረግ በሚለው ቀመር ካላየነው በስተቀር ሁለት ጌቶች ሊሆኑ ነው፤ ይህ ደግሞ አምላክ አንድ ጌታ ነው ከሚል አስተምህሮት ጋር ሊላተም ነው፤ ስለዚህ የኢየሱስ ጌትነት የፍጡር ማእረግ ብቻ ነው፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ኢየሱስን ጌታ አደረገው ስለሚል፦
ሐዋርያት ስራ 2:36 አለ። እንግዲህ ይህን እናንተ የሰቀላችሁትን *ኢየሱስን እግዚአብሔር ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው* የእስራኤል ወገን ሁሉ በእርግጥ ይወቅ።

መቼም አንድ ጤነኛ የሆነ ሰው ፈጣሪን ፈጣሪ ጌታ አደረገው ብሎ እንደማይቀበል እሙን ነው፤ ይስሐቅ ያዕቆብን ጌታ አደረግሁት ይላል፦
ዘፍጥረት 27፥37 ይስሐቅም መለሰ ዔሳውንም አለው። እነሆ፥ *ጌታህ አደረግሁት*፥ ወንድሞቹንም ሁሉ ለእርሱ ተገዦች ይሆኑ ዘንድ ሰጠሁት፥

ይህም ስልጣንና ሹመትን አሊያም እልቅናና ክብርን ያመለክታል፤ ዮሴፍ፦ እግዚአብሔር ጌታ አደረገኝ” ይላል፦
ዘፍጥረት 45፥9 እ*ግዚአብሔር በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ጌታ አደረገኝ*፤ ወደ እኔ ና፥ አትዘግይ፤

ኢየሱስ ጌታ ተደረገ ሲባል ያዕቆብ ጌታ ተደረገ ዮሴፍ ጌታ ተደረገ በተባለበት ሒሳብ እንጂ የዓለማቱ ጌታ የሚለውን አያመለክትም፤ ይህም በራሡ የተብቃቃ አሊያም የባህርይ ገንዘቡ ሣይሆን በስጦታ ያገኘው ነው። ለምን ይሆን ግን ተርጓሚዎች ለአብ በትልቁ *The LORD* ብለው ለኢየሱስ በትንሹ *Lord * ብለው ያስቀመጡት? የሚቀጥለው ነጥብ ይህንን ሙግት ያብራራል፦
ነጥብ ሁለት
“አዶናይ”
“አዶናይ” אֲדֹנָ֥י ደግሞ “የአዶኒ” ብዙ ቁጥር ሲሆን ለአንድ አምላክ ብቻ የሚጠቀምበት ነው፤ ያህዌህ ብቻውን “አዶናይ” ተብሏል፤ አንድም ፍጡር “አዶናይ” ተብሎ የተጠራ የለም፤ እስቲ አንዱ አምላክ አዶናይ የተባለበትን አናቅፅ ለናሙና ያክል እንየው፦
መዝሙር 16:2 ያህዌህን አንተ “ጌታዬ” אֲדֹנָ֥י ነህ አልሁ፤ ከአንተ በቀር በጎነት የለኝም።
መዝሙር 35:23 አምላኬ “ጌታዬም” אֲדֹנָ֥י ፥ ወደ ፍርዴ ተነሥ፥ አቤቱ፥ ፍርዴን አድምጥ።
መዝሙር 110:5 “ጌታዬ” אֲדֹנָ֥י በቀኝህ ነገሥታትን በቍጣው ቀን ይቀጠቅጣቸዋል።

ስለዚህ ዳዊት አንዱን አምላክ “አዶናይ” ሲል መሲሁን ግን “አዶኒ” ብሎታል፤ ተርጓሚዎች ይህንን ስለተረዱ ለአብ በትልቁ *The LORD* ብለው ለኢየሱስ በትንሹ *Lord * አስቀምጠውታል፤ አንድ ሰው ተነስቶ፦ “የእኔ ጌታ አምላክ አለው” ቢል ጌታው ማእረግ እንጂ እውን ለጌታ የፈጠረው አምላክ አለውን? አስተግፊሩላህ! ጳውሎስ ጌታችን አምላክ አለው ይለናል፤ “””የጌታችን አምላክ”””፦
Ephesians 1:17 That *the God of our Lord* Jesus Christ,

“”ጌታችን” የተባለው ኢየሱስ ሲሆን ጌትነቱ አምላክ አለው፤ ለእነ ጳውሎስ ጌታቸው አምላክ አለው፤ የጌታቸው አምላክ አብ ነው። ስለዚህ “”ጌታችን”” መባል ማዕረግን ብቻ ያሳያል። ሰዎች “”ጌታችን”” ተብለዋል፦
@ዮሴፍ
ዘፍጥረት 44፥9 ከባሪያዎችህ ጽዋው የተገኘበት እርሱ ይሙት፤ እኛም ደግሞ “ለጌታችን ባሪያዎች እንሁን”።
@ሙሴ
ዘኁልቅ 36፥2 አሉም፦ ምድሪቱን ለእስራኤል ልጆች ርስት አድርገህ በዕጣ ከፍለህ ትሰጣቸው ዘንድ እግዚአብሔር አንተን “”ጌታችንን”” አዘዘህ፤ እግዚአብሔርም የወንድማችንን የሰለጰዓድን ርስት ለሴቶች ልጆቹ ትሰጥ ዘንድ አንተን ጌታችንን አዘዘ።
@ዳዊት፦
1ኛ ነገሥት 1፥43 ዮናታንም ለአዶንያስ እንዲህ ብሎ መለሰ፦ በእውነት “”ጌታችን”” ንጉሥ ዳዊት ሰሎሞንን አነገሠው።
መደምደሚያ
ኢየሱስ የዓለማቱ ጌታ አይደለም። ኢየሱስ ከአላህ ሰምቶ የሚያስተላልፍ ሰው እና የአላህ ባሪያ ነው፦
ዮሐንስ 8:40 ነገር ግን አሁን *ከአላህ የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን ሰው* ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ፤ አብርሃም እንዲህ አላደረገም و لكنكم الان تطلبون ان تقتلوني و انا انسان قد كلمكم بالحق الذي سمعه من الله هذا لم يعمله ابراهيم ።
የሐዋርያት ሥራ 3:26 ለእናንተ አስቀድሞ *አላህ ባሪያውን አስነሥቶ፥ እያንዳንዳችሁን ከክፋታችሁ እየመለሰ ይባርካችሁ ዘንድ፥ ላከው* إِلَيْكُمْ أَوَّلاً إِذْ أَقَامَ اللهُ فَتَاهُ يَسُوعَ أَرْسَلَهُ يُبَارِكُكُمْ بِرَدِّ كُلِّ وَاحِدٍ مِنْكُمْ عَنْ شُرُورِهِ». ።

የዐረቢኛው ባይብል ከላይ ኢየሱስን የላከው አላህ እንደሆነ ያስቀምጠዋል፦
John 8 :: Arabic/English Online Bible

http://www.copticchurch.net/cgibin/bible/index.php

አምላካችን አላህ ኢየሱስ ተናገር ብሎ ያዘዘው ቃል “ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ” ማለትን ነው፦
5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል “ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ” ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ፀሐይና ጨረቃ በኢስላም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

መግቢያ
ብዙ ጊዜ ኢስላምን ለማጠልሸት የሚዳክሩ ዳካሪዎች በእነርሱ ያለውን አምልኮ ሆነ የሚያመልኩት ጉዳይ ጥያቄ ሲጭርባቸው ከጥያቄው መልስ ይልቅ ያንን ድክመት ለመሸፈን በእጅ አዙር ፦እናንተ እኮ የምታመልኩት የጨረቃ አምላክ ነው፣ መሆኑ የሚታወቀው ፀሐይና ጨረቃ በመስኪድ ማማ ላይ መሆኑ ነው ይላሉ፣ ፀሐይና ጨረቃ ማማ ላይ መሆኑ መስኪዱን ከሌላ ነገር ለመለየት ካልሆነ በቀር ምንም ከአምልኮአችን ጋር አይያያዝም። ኢስላም ስለ ፀሐይና ጨረቃ ምን ይላል?

ነጥብ አንድ
ፀሐይና ጨረቃን የፈጠረው አላህ ነው፦
29:61 ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ፀሐይንና ጨረቃንም የገራ ማን እንደሆነ ብትጠይቃቸው በእርግጥ አላህ ነው ይሉሃል፤ ታዲያ እንዴት ይመለሳሉ።
41:37 ሌሊትና ቀንም፣ ጸሐይና ጨረቃም፣ ከምልክቶቹ ናቸው፤ ለፀሐይና ለጨረቃ አትስገዱ፤ ለዚያም ለፈጠራቸው አላህ ሰገዱ፤ እርሱን ብቻ የምትግገዙ እንደሆናችሁ፣ ለሌላ አትስገዱ፣

ነጥብ ሁለት
አላህ ፀሐይና ጨረቃ ለጊዜ መቁጠሪያ አድራጊ ነው፦
10:5 እርሱ ያ ፀሐይን አንጻባራቂ ጨረቃንም አብሪ ያደረገ ነው፡፡ የዓመታትን ቁጥርና ሒሳብን ታውቁ ዘንድም ለእርሱ መስፈሪያዎችን የለካ ነው፡፡ አላህ ይህንን በእውነት እንጂ በከንቱ አልፈጠረውም፡፡ ለሚያውቁ ሕዝቦች አንቀጾችን ያብራራል፡፡
6:96 እርሱም ጎህን ከሌሊት ጨለማ ፈልቃቂ ሌሊትንም ማረፊያ ፀሐይንና ጨረቃንም ለጊዜ መቁጠሪያ አድራጊ ነው፡፡
2:189 ከለጋ ጨረቃዎች ይጠየቁሃል፡፡ እነርሱ ለሰዎች ጥቅም ለሐጅም ማወቂያ ጊዜያቶች ምልክቶች ናቸው በላቸው፡፡
መዝሙረ ዳዊት 104.19 ጨረቃን ለጊዜዎች አደረገ ፀሐይም መግቢያውን ያውቃል።
የወር መባቻ የሚለው የዕብራይስጥ ቃል ቆደሽ ሲሆን ትርጉሙ ለጋ ጨረቃ ማለት ነው ፣ ይህም ቃል በባይብል 28 ጊዜ ተወስቷል፦
ዘኍልቍ 10፥10 ደግሞ በደስታችሁ ቀን፥ በበዓላታችሁም ዘመን፥ በወርም መባቻ፥ በሚቃጠል መሥዋዕታችሁና በደኅንነት መሥዋዕታችሁ ላይ መለከቶቹን ንፉ እነርሱም በአምላካችሁ ፊት ለመታሰቢያ ይሆኑላችኋል እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ። ዘኍልቍ 28፥11 በወሩም መባቻ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ታቀርባላችሁ ሁለት ወይፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ ነውርም የሌለባቸውን ሰባት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች፥
ዘኍልቍ 28፥14 የመጠጥ ቍርባናቸውም ለአንድ ወይፈን የኢን ግማሽ፥ ለአውራው በግም የኢን ሢሶ፥ ለአንዱም ጠቦት የኢን አራተኛ እጅ የወይን ጠጅ ይሆናል ይህ ለዓመቱ የወር መባቻ ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕት ነው።
ዘኍልቍ 29፥6 በወሩ መባቻ ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቍርባን፥ በዘወትርም ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቍርባን፥ ከመጠጡም ቍርባን ሌላ፥ እንደ ሕጋቸው ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርቡ ናቸው።

ነጥብ ሶስት
አላህና የጨረቃ አምላክ፦
የጨረቃ አምላክ ማለት በጥንት ጊዜ ሰዎች የተለያየ አምላክ ያመልኩ ነበር ወንዙን የሚገዛ የወንዝ አምላክ፣ ዝናብን የሚገዛ የዝናብ አምላክ፣ ጸሃይን የሚገዛ የጸሃይ አምላክ፣ መሬትን የሚገዛ የመሬት፣ ጨረቃን የሚገዛ የጨረቃ አምላክ ወዘተ እያሉ በግብጽ፣ በአሶር፣ በባቢሎን፣ በፋርስ ወንዝን፣ ዝናብን፣ ጸሃይን፣ መሬትን፣ ጨረቃን ያመልኩ ነበር፣ ይህንን ነው የጨረቃ አምላክ የሚሉት።
ሙስተሽሪቆች ማለትም የመካከለኛው ምስራቅ ጥንተነገር የሚያጠኑ orientalists ሆነ የስነ-ቅርስ ጥናት ተመራማሪዎች አንድም ጊዜ በዘብተኛ ጽሁፋቸው ላይ አላህ የጨረቃ አምላክ ነው ብለው አያቁም። ከዚህ ይልቅ የጨረቃ አምላክ ተብሎ የሚታመነው በአረቢያን ስነ-ተረት ጥናት mythology ታላብ*Ta’lab* ሲሆን በሞሶፖታሚያን ስነ-ተረት ጥናት ደግሞ ሲን*sin* ነው። አላህ የጨረቃ አምላክ ብለው የሚያብጠለጥሉት ወሊድ ሹባትና ሮበርት ሙሬ ናቸው፣ ወሊድ ሹባት ሆነ ሮበርት ሙሬ የክርስትና ሚሲኦናዊ*ሙበሲር* እንጂ የስነ-ቅርስ ጥናት ተመራማሪዎች አይደሉም።
የስነ-ቅርስ ጥናት ዋቢ መጻሕፍት፦
1.Dexter, Miriam Robbins. Proto-Indo-European Sun Maidens and Gods of the Moon. pp. 137–144.
2.Walker, Barbara G., The Woman’s Encyclopedia of Myths and Secrets, San Francisco: Harper, 1983, p. 669
ነጥብ አራት
አረቦች ቁርአን ከመውረዱ በፊት አላህን ማን ነበር የሚሉት፦
31:25 ሰማያትንና ምድርንም የፈጠረ ማን እንደኾነ ብትጠይቃቸው በእርግጥ አላህ ነው ይላሉ፤ ምስጋና ለአላህ ይገባው፣ በላቸው፤ ይልቁንም አብዛኞቹ አያውቁም።
29:61 ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ፀሐይንና ጨረቃንም የገራ ማን እንደሆነ ብትጠይቃቸው በእርግጥ አላህ ነው ይሉሃል፤ ታዲያ እንዴት ይመለሳሉ።
10:31 «ከሰማይና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማን ነው መስሚያዎችንና ማያዎችንስ የፈጠረ ማን ነው ከሙትም ሕያውን የሚያወጣ ከሕያውም ሙትን የሚያወጣስ ማን ነው ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብርስ ማን ነው» በላቸው፡፡ «በእርግጥም አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ ለምን ታጋራላችሁ አትፈሩትምን» በላቸው፡፡
ለሙሴ ተውራት ከመውረዱ በፊት ኤል ሆነ ያህዌህ ከነ አናውያን ጣኦታውያን ታላቁ አምላክ ብለው ያመልኩት ነበር ያ ማለት *ኤል* የጣኦታውያን ጣኦት ነውን?

መደምደሚያ
አላህ የነቢያት አምላክ ነው፦
21:25 ከአንተ በፊትም፣ እነሆ ከኔ ሌላ አምላክ የለምና ተገዙኝ፣ በማለት ወደርሱ የምናወርድለት ቢሆን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም።
16:36 በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ አላህን ተገዙ፤ ጣዖትንም ራቁ፤ በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል፤
1.የኑሕ አምላክ ነው፦
11:25-26 ኑሕንም ወደ ሕዝቦቹ በእርግጥ ላክን፤ አላቸውም ፦ እኔ ለናንተ ግልጽ አስፈራሪ ነኝ። አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ፤ እኔ በናንተ ላይ የአሳማሚን ቀን ቅጣት እፈራላችኋለሁና።
2.የሁድ አምላክ ነው፦
11:50 ወደ ዓድም ወንድማቸውን ሁድን ላክን አላቸው ፦ ወገኖቼ ሆይ አላህን ተገዙ ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም፤ እናንተም ቀጣፊዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም።
3.የሷሊህ አምላክ ነው፦
11:61 ወደ ሠሙዶችም ወንድማቸውን ሷሊህን ላክን፤ ፦ሕዝቦቼ ሆይ አላህን ተገዙ፤ ከርሱ ሌላ ለናንተ አምላክ፣ የላችሁም፤ .. አላቸው።
4.የኢብራሒም አምላክ ነው፦
19:48 እናንተንም ከአላህ ሌላ የምትግዙትንም እርቃለሁ፤ ጌታየንም እግዛለሁ፤ ጌታየን በመገዛት የማፍር አለመኾኔን እከጅላለሁ።
5.የሹዐይብ አምላክ ነው፦
11:84 ወደ መድየንም ወንድማችውን ሹዐይብን፣ (ላክን)፤ አላቸው ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፤ ከርሱ ሌላ ለናንተ አምላክ የላችሁም፤ ስፍርንና ሚዛንንም አታጉድሉ፤ እኔ በጸጋ ላይ ሆናችሁ አያችኋለሁ፤ እኔም በናንተ ላይ የከባቢን ቀን ቅጣት እፈራለሁ።
6.የሙሳ አምላክ ነው፦
7:104-105 ሙሳም አለ፦ፈርኦን ሆይ! እኔ ከዓለማት ጌታ የተላክሁ መልክተኛ ነኝ፤ በአላህ ላይ ከእውነት በቀር አለመናገር ተገቢዬ ነው፤ ከጌታችሁ በታምር በእርግጥ መጣኋችሁ፤ የእስራኤልንም ልጆች ከኔ ጋር ልቀቅ።
7.የኢሳ አምላክ ነው፦
3:51 አላህ ጌታየና ጌታችሁ ነዉ፤ ስለዚህ ተገዙት፤ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነዉ አላቸዉ።

አላህ ሂዳያ ይስጣቸው ለእኛም ጽናቱን አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
እውን ኢየሱስ አምላክ ነውን?

ክፍል አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

5:17 እነዚያ አላህ اللَّهَ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ الْمَسِيحُ ነው ያሉ፣ በእርግጥ ካዱ፤
5.72 እነዚያ አላህ اللَّهَ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ الْمَسِيحُ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ፤

መግቢያ
“አላህ” الله የሚለው መለኮታዊ ስም አራት የዐረብኛ ሃርፎችን በውስጡ አቅፏል الله ፣ ከአራቱ ሃርፎች ሁለቱ ሁለት ላም ሲሆኑ ከሁለቱ የላም ሃርፎች አንዱን ስንቀንሰው ውጤቱ “ኢላህ” إِلَهَ የሚል ይሆናል፣ ትርጉሙም “አምላክ” ማለት ነው፡፡
“መሢሕ” الْمَسِيحُ በእብራይስጥ፣ በአረማይክና በአረቢኛ ሲሆን በግሪክ ደግሞ “ክርስቶስ” ነው ትርጉሙ “የተቀባ” ማለት ነው፣ ይህም ኢየሱስ በአምላክ የተሾመ ባሪያ መሆኑን የሚያሳይና ለኢሳም የተሰጠ ማዕረግ ነው፦
3:45 መላእክት ያሉትን አስታዉስ፡- መርየም ሆይ አላህ ከርሱ በሆነዉ ቃል፣ ስሙ አልመሲሕ ዒሳ የመርየም ልጅ፣ በዚህ ዓለምና በመጨረሻዉም ዓለም የተከበረ፣ ከባለማሎችም በሆነ ያበስረሻል፤
4:172 አልመሲሕ፣ ለአላህ ባሪያ ከመሆን ፈጽሞ አይጠየፍም፤

ይህም ባርያ በአምላክ የተሾመ ቅቡዕ እንደሆነ የራሳቸውም መጽሐፍ ይመሰክራል፦
ሐዋ.10:38 እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥
ሐዋ.4:26-28 የምድር ነገሥታት ተነሡ አለቆችም በጌታና በተቀባው ላይ አብረው ተከማቹ ብለህ የተናገርህ አምላክ ነህ። በቀባኸው በቅዱሱ ባሪያህ በኢየሱስ ላይ ሄሮድስና ጴንጤናዊው ጲላጦስ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር፥ እጅህና አሳብህ እንዲሆን አስቀድመው የወሰኑትን ሁሉ ሊፈጽሙ፥ በዚች ከተማ በእውነት ተሰበሰቡ።
ኢሳ.61:1፤ የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤
ሉቃ4:17-ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና ።
ዕብ 1:9 ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ
መዝ 45:7 ስለዚህ ከባልንጀሮችህ ይልቅ እግዚአብሔር አምላክ የደስታ ዘይትን ቀባህ።

የኢየሱስ አምላክ እግዚአብሔር ኢየሱስን እንደቀባው ከተገለጸ ኢየሱስ መሲሕ መሆኑ እሙንና ቅቡል ነው፣ ነገር ግን አላህ ማለትም አምላክ ግን አይደለም፣ ኢየሱስ አምላክ ነው ብሎ ማለት እምነት ሳይሆን ክህደት ነው፣ የኢየሱስ ማንነት በኢስላም ክቡርና ክቡድ ቢሆንም በክርስትና ግን ቅጥ አምባሩ የጠፋና ውጥ ቅጡ የወጣ አስተምህሮት ነው ያለው ብዬ ብናገር ግነትና ዕብለት አይሆንብኝ፣ ኢየሱስ ሰው ነው ከተባለ ወዲያ ደግሞም አምላክ ነው ማለት ቂልነት ነው፣ ምክንያቱም ሰውና አምላክ ሁለት ተቃራኒ ባህርያት ስለሆኑ፦
ኢሳይያስ 31፥3 ግብጻውያን *ሰዎች* እንጂ *አምላክ* አይደሉም፥
ሆሴዕ 11፥9 እኔ አምላክ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁምና፥
ሕዝቅኤል 28:9 በውኑ በገዳይህ ፊት። *እኔ አምላክ ነኝ* ትላለህን? ነገር ግን በገዳይህ እጅ *ሰው ነህ እንጂ አምላክ* አይደለህም።

ኢየሱስ ሰው ነው ስንል አምላክ አይደለም ማለት ነው፣ አሏህ አምላክ ነው ስንል ሰው አይደለም ማለት ነው፣ አምላክ ፈጣሪና ፍጡር አይደለም፣ አምላክ አለ የለም አይባልም፣ ኢየሱስ አምላክ አለመሆኑን የሚያሳዩ የተለያዩ የሰዋስው ሙግት ከራሳቸው መጽሐፍ በእማኝነትና በአስረጂነት እናቀርባለን፦
ሙግት አንድ
ኢየሱስ ከአምላክ ሰምቶ የሚያስተላልፍ ሰው መሆኑ መናገሩ በራሱ ኢየሱስ አምላክ አለመሆኑን እንረዳለን ምክንያቱም አምላክ አሰሚ ባለቤት*subject* ሰው ደግሞ ሰሚ ተሳቢ*object* ሆኖ በአሰሚ አምላክና በሰሚ ሰው መካከል አጫፋሪ ግስ*transitive verb* መኖሩ በራሱ አምላክና ሰው የተባለው ኢየሱስ ሁለት የተለያዩ ህላዌዎች መሆናቸውን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፦
ዮሐንስ 8፥40 ነገር ግን አሁን ከአምላክ Θεοῦ የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን ሰው ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ፤

ሙግት ሁለት
አምልኮ የሚለው ቃል በእብራይስጥ አቫድ עָבַד ሲሆን በግሪክ ደግሞ ላትሬኦ λατρεύω ይባላል። ይህም ለአንዱ አምላክ ብቻ በሙሉ ሁለንተና የሚቀርብ ልመና፣ ስእለት፣ማጎብደድ፣ መተናነስ፣ ስግደት፣ መገዛት ፣ አገልግሎት Adoration ነው። ላትሬኦ λατρεύω ከአንዱ አምላክ ከአብ ውጪ ለኢየሱስ አገልግሎት ላይ የዋለበት አንድ ጥቅስ ከማቴዎስ እስከ ራዕይ የለም ። ከዚህ ይልቅ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ የሚመለክ አንድ ተመላኪ አለ፣ ይህም ለኢየሱስ ስልጣን የሰጠ ጌታ አምላክ አብ ነው፣ የሚመልክ አንድ ማንነት መሆኑን *እርሱንም* በሚል ተሳቢ ተውላጥ ስም ተገልጿል፣ ከአብ ውጪ የሚመለክ አለመኖሩን ደግሞ *ብቻ* በሚል ግድባዊ-ገላጭ*bounded-adjective* ተጠፍንጓል፦
ማቴዎስ 4፥10 ያን ጊዜ ኢየሱስ፦ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ *እርሱንም* *ብቻ* አምልክ λατρεύσεις ተብሎ ተጽፎአልና አለው።
ሉቃስ፥32 እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ *ጌታ አምላክም* የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤

ሙግት ሶስት
ኢየሱስ እራሱን ከአንድ አምላክ ውጪ ማድረጉ ኢየሱስ አምላክ አለመሆኑ ማስረጃ ነው፣ ምክንያቱም *እኔን* የሚለው ተሳቢ ተውላጠ-ስም*objective pronoun* እና አንዱ አምላክ በተለያየ ሁኔታው ተቀምጣል፣ ከዚያም ባሻገር ኢየሱስ የማንነቱ አምላክ መኖሩን ተናግሯል፣ የእኔ አምላክ የሚለው አገናዛቢ ተውላጠ-ስም*posessive pronoun* የእኔነቱ አምላክ እንዳለውና የኢየሱስና የሃዋርያት አምላክ አንድ አምላክ መሆኑ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፦
ማርቆስ 10፥18 ኢየሱስም፦ ስለ ምን ቸር *እኔን* με ትለኛለህ? *ከአንዱ ከአምላክ* εἷς ὁ Θεός በቀር ቸር ማንም የለም።
ዮሐንስ 20፥17 እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ ብለሽ ንገሪአቸው አላት።

ኢንሻላህ የሙግቱ ነጥብ በክፍል ሁለት ይቀጥላል…………

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https፡//t.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
እውን ኢየሱስ አምላክ ነውን?

ክፍል ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

ሙግት አራት
ኢየሱስ አምላክ እንዳልሆነ ከምንረዳበት ነገር አንዱ ኢየሱስ የላከውን ህልውና በሁለተኛ መደብ*second person* አንተ በማለት ወደ አምላኩ መጸለዩ፣ *እና* በሚል መስተጻምር*conjuction* እውነተኛ አምላክና እራሱን መለየቱ፣ የላከው ብቻውን እውነተኛ አምላክ መሆኑን መግለጹ፣ በእርሱና በአምላኩ መካከል አምላኩን *አንተ* በማለት የባለቤት ተውላጠ ስም*subjective pronoun* መጠቀሙ እራሱን *እኔ* በማለት የተሳቢ ተውላጠ ስም*objective pronoun* መጠቀሙ ፣ *ተውከኝ* የሚል አጫፋሪ ግስ*transitive verb* መጠቀሙ፣ ኢየሱስ አምላክ እንዳልሆነ ያስረዳል፦
ዮሐንስ 17፥3 *እውነተኛ አምላክ ብቻህ የሆንህ አንተን* *እና* የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።NIV TRANSLATION
ማቴዎስ 27፥46 በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ፦ ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህም፦ አምላኬ አምላኬ፥ *አንተ እኔን* ስለ ምን ተውኸኝ? ማለት ነው።NIV TRANSLATION

ሙግት አምስት
ኢየሱስ አምላክ አለመሆኑን ከምናቅናቸው የሰዋስው ጥናት አንዱ ኢየሱስ ወደ አምላክ መጸለዩ፣ መሄዱ ነው፣ *ወደ* የሚለው መስተዋድድ*preposition* መጠቀሙ በሁለት ማንነት መካከል ለመለየት የሚመጣ ነው፣ ኢየሱስ ማርያምን *ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ* ማለቱ ወንድሞቹና ማርያም የተለያየ ማንነት እንዳላቸው እንደሚያሳይ ሁሉ *ወደ አምላኬ አርጋለው* ማለቱ አምላኩና ኢየሱስ ሁለት የተለያዩ ህላዌዎች መሆናቸውን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፦
ሉቃስ 6፥12 በነዚህም ወራት ይጸልይ ዘንድ ወደ ተራራ ወጣ፥ ሌሊቱንም ሁሉ *ወደ* አምላክ Θεοῦ ሲጸልይ አደረ።
ዮሐንስ 20፥17 ኢየሱስም፦ ገና *ወደ* አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ፤ ነገር ግን *ወደ* ወንድሞቼ ሄደሽ፦ እኔ *ወደ* አባቴና *ወደ* አባታችሁ *ወደ* አምላኬና *ወደ* አምላካችሁ ዓርጋለሁ ብለሽ ንገሪአቸው አላት።
ዮሐንስ 20፥11 ከዚህም በኋላ በዓለም አይደለሁም፥ እነርሱም በዓለም ናቸው፥ ”እኔም” *ወደ* ”አንተ” እመጣለሁ።

ሙግት ስድስት
ኢየሱስ ስለ ራሱ በሚናገርበት አንቀጽ ላይ *ከራሴ*my self* የሚል ድርብ ተውላጠ ስም*reflexive pronoun* መጠቀሙና አምላክን ደግሞ *ከራሱ*him self* በሚል ድርብ ተውላጠ ስም መጠቀሙ አምላኩና ኢየሱስ ሁለት የተለያየ ሃልዎት እንደሆኑ ያሳያል፣ ከዚያም ባሻገር አምላክ የሚባለው ከራሱ *ሌላ* እንደሆነና ከዚያ ሌላ ከሆነ ህላዌ ምስክርነት ሰምቶ ማስተላለፉን ተናግሯል፦
ዮሐንስ 7፥16-17 ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው፦ ትምህርቴስ *ከላከኝ* ነው እንጂ *ከእኔ* አይደለም፤ ፈቃዱን ሊያደርግ የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ ይህ ትምህርት ከአምላክ Θεοῦ ቢሆን ወይም እኔ *ከራሴ* የምናገር ብሆን ያውቃል።
ዮሐንስ 5፥30-32 እኔ *ከራሴ* አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ *እንደ ሰማሁ* እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፥ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና። እኔ ስለ እኔ *ስለ ራሴ* ብመሰክር ምስክሬ እውነት አይደለም፤ ስለ እኔ የሚመሰክር *ሌላ* ነው፥ *እርሱም* ስለ እኔ የሚመሰክረው ምስክር እውነት እንደ ሆነ አውቃለሁ።

ሙግት ሰባት
ኢየሱስ የማያውቀው ነገር ስላለ አምላክ አይደለም፣ *ልጅ* የሚለው የግሪኩ ቃል ሁዎስ Υἱός ሲሆን ወልድ ማለት ነው፣ ወልድ የተባለው ኢየሱስ ከሆነ ኢየሱስ ቀንና ሰዓቱን አያውቅም ማለት ነው፣ አይ በሰውነቱ እንዳይባል እውቀት የስጋ ሳይሆን የዓይምሮ ባህርይ ነው፣ ጥቅሱ *ከአብ በቀር* በማለት ይዘጋዋል፣ *በቀር* ደግሞ ተውሳ-ከግስ*ad-verb* ስለሆነ ያ እውቀት የአብ ብቻ መሆኑን ፍንትው አድርጎ ያሳያል፣ *አባት* የሚለው የግሪኩ ቃል ፓተር Πατήρ ሲሆን አብ ማለት ነው፣ በተጨማሪም ኢየሱስ *ከእኔ አብ ይበልጣልና* ብሏል፣*ከእኔ አብ ይበልጣልና* የሚለው ቃላት ላይ *እኔ* የሚል ባለቤት ተውላጠ-ስም የኢየሱስን ማንነት የሚያሳይ ሲሆን ከኢየሱስ ማንነት አብ ከበለጠ አብ ኢየሱስ በማንነት ይበልጠዋል ማለት ነው፣ በስጋ ነው የበለጠው እንዳንል ስጋ *እኔ* ማለት አይችልም፣ ንጽጽሩ ወልድ ከአብ ጋር እንጂ አብ ከሰውነት ጋር አይደለም፣ አብ እግዚአብሔር ነው ወልድ ደግሞ ኢየሱስ ነው፣ ይህን ጉዳይ ራሳቸውን የሚያስጠጉበት ጳውሎስ እንኳን እግዚአብሔር ከኢየሱስ እንደሚበልጥ በአጽንኦትና በአንክሮት ይናገራል፦
ማርቆስ 13:32 ስለዚያች ቀን ወይም ስለዚያች ሰዓት ግን የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ *ልጅም* ቢሆን *ከአባት በቀር* የሚያውቅ የለም።
ዮሐንስ 14፤28 የምትወዱኝስ ብትሆኑ *ከእኔ አብ ይበልጣልና* ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር።
1ኛ ቆሮንቶስ 11፣3 የክርስቶስም ራስ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ልታውቁ እወዳለሁ።

ኢንሻላህ የሙግቱ ነጥብ ይቀጥላል…………

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https፡//t.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
እውን ኢየሱስ አምላክ ነውን?

ክፍል ሶስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

ሙግት ስምንት
አብ የወልድ ህይወት ሰጪ ሲሆን ወልድ ደግሞ ህይወት አላባ ሆኖ በባዶነት ተቀድሞ ህይወትን ከአብ ያገኘ ነው፣ ኢየሱስን አምላክ በእናቱ ማህጸን ሰርቶ ወደ ህልውና ሰው ነው፦
ዮሐ 5:26 አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው እንዲሁ ደግሞ ለወልድ በራሱ ሕይወት ያመጣውእንዲኖረው ሰጥቶታልና።
ኢሳይያስ 49:5 አሁንም በእግዚአብሔር ዓይን ከብሬአለሁና፥ *አምላኬም* ጕልበት ሆኖኛልና ያዕቆብን ወደ እርሱ እንድመልስ እስራኤልንም ወደ እርሱ እንድሰበስብ *ባሪያ* እሆነው ዘንድ *ከማኅፀን ጀምሮ የሠራኝ* እግዚአብሔር እንዲህ ይላል።
ሐዋርያት ሥራ 13:23 *ከዚህም ሰው ዘር* አምላክ Θεοῦ እንደ ተስፋው ቃል ለእስራኤል መድኃኒትን እርሱም ኢየሱስን *አመጣ*።

ሙግት ዘጠኝ
ኢየሱስ በእኔ እመኑ ሲል እርሱ የተላከ መልዕክተኛ መሆኑን እመኑ ማለት ሲሆን በአምላክ እመኑ ሲል ደግሞ አምላክ ላኪው እንደሆነ እመኑ ማለት ነው፣ በአምላክና በኢየሱስ መካከል የሚለይ መስተጻምር *ደግሞ* የሚል አለ፣ ይህ መስተጻምር በሁለቱ ሃልዎት ማለትም በላኪው አምላክና በተላኪው ሰው መካከል ልዩነት አለ፣ ከዚያም ባሻገር አምላክና ኢየሱስ ከሚለው ቃል በፊት *በ* የሚለው መተዋድድ መነሻ ቅጥያ ሆኖ መመጣቱ ከስነ-ሰዋስው አንጻንጻ ኢየሱስና አምላክ ሁለት ማንነቶች እንደሆኑ ያሳያል፣ በእርግጥም በመልክተኛው ማመን በላከውም ማመን ነው፣ የላከውን አምላክ የሚያምን ደግሞ የዘላለም ሕይወት አለው፦
ዮሐንስ 14:1 ልባችሁ አይታወክ፤ *በ*አምላክ Θεοῦ እመኑ፥ *በ*እኔም *ደግሞ* እመኑ።
ዮሐንስ 12:44 ኢየሱስም ጮኸ፥ እንዲህም አለ፦ *በእኔ* የሚያምን *በላከኝ* ማመኑ ነው እንጂ በእኔ አይደለም፤
ዮሐንስ 5:24 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ *የላከኝንም የሚያምን* የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።

ሙግት አስር
በአንድ አምላክና በሰዎች መካከል ያለ ሰው መሆኑ፣ በአምላክና በሰው ፊት በጥበብና በቁመት በሞገስም ማደጉ፣ በአምላክና እና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በሥራና በቃል ብርቱ ነቢይ መሆኑ፣ ኢየሱስ አምላክ አለመሆኑን ያስረዳል፣ ምክንያቱም አምላክ በአምላክ ፊት አያድግም፣ አምላክ በአምላክና በሰዎች መካከል ሰው አይሆንም፣ አምላክ በአምላክና በህዝቡ መካከል ብርቱ ነቢይ አይሆንም፣ አምላክ ነው ለአምላክ ነብይ የሚሆነው? ሱብሃንአላህ፦
1ኛ ጢሞቴዎስ 2:5 አንድ አምላክ Θεοῦ አለና፥ በአምላክ Θεοῦ እና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም *ሰው* የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤
ሉቃስ 2:52 ኢየሱስም ደግሞ በጥበብና በቁመት በሞገስም በአምላክ Θεοῦ እና በሰው ፊት *ያድግ* ነበር።
ሉቃስ 24:19 እነርሱም እንዲህ አሉት፦ በአምላክ Θεοῦ እና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በሥራና በቃል ብርቱ ነቢይ ስለ ነበረው ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ፤

መደምደሚያ
3:79 ለማንም ሰዉ አላህ መጽሐፍንና ጥበብን ነቢይነትንም ሊሰጠዉና ከዚያም ለሰዎች ከአላህ ሌላ ለእኔ ባሮች ሆኑ ሊል አይገባዉም፤

አንድ ሰው ነብይ ሆኖ መጽሐፍ ተሰጦት ከተላከ ወዲህ ተመልሶ አምላክ ነኝ አሊያም አምልኩኝ ሊል አይገባውም፣ ኢየሱስ አምላክ ነኝ አሊያም አምልኩኝ አላለም፣ ኢየሱስ አምላክ ነው ማለት ክህደት ነው፦
5:17 እነዚያ አላህ اللَّهَ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ الْمَسِيحُ ነው ያሉ፣ በእርግጥ ካዱ፤

የካሃድያን መጨረሻ ደግሞ የገሀነም ቅጣት ነውና ክርስቲኣኖች ሆይ ወደ አላህ በተውበት ማለት በንስሃ ተመለሱ፦
67:6 ለነዚያም በጌታቸው ለካዱት፣ የገሀነም ቅጣት አልላቸው፤ መመላሻይቱም ከፋች!
39:54 ቅጣቱም ወደ እናንተ ከመምጣቱና ከዚያም የማትረዱ ከመሆናችሁ በፊት፣ ወደ ጌታችሁ በመጸጸት ተመለሱ፤ ለርሱም ታዘዙ።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https፡//t.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ነቅልና አቅል በቁርአን እሳቤ

ክፍል አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

መግቢያ
ሁለት እሳቤዎች እውቀት ሆነው ለሰው ልጆች ይጠቅማሉ፣ አንዱ ነቅል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ አቅል ነው፡፡
ነቅልنفل አላህ በነቢያቱ ለሰው ልጆች የሚያስተላልፈው ግልጠተ-መለኮት*Revelation* ሲሆን፣ አቅል عقل ደግሞ አላህ ለሰው ልጆች እንዲያመዛዝኑ፣ እንዲያስተነትኑ፣ እንዲያስተውሉ፣ እንዲመራመሩ የሰጠው አመክንዮ*Reason* ነው፣ እነዚህን ሁለት እሳቤዎች ጥልልና ጥንፍፍ ባለ መልኩ እንዳስሳቸው፦

እሳቤ አንድ
ነቅል
አላህ በነቢያቱ ለሰው ልጆች የሚያስተላልፈው ግልጠተ-መለኮት ወህይና ተንዚል ይባላል፦
ነጥብ አንድ
ወህይ
ወህይ وَحْيٌ የሚለው ቃል አውሃ أَوْحَىٰ ማለትም ገለጠ ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን ትርጉሙ ግልጠት አሊያም ግህደት የሚል ፍቺ አለው፣ ወህይ የሚለው ቃል በቁርአን 6 ጊዜ ተወስቷል፦11:37 20:114 21:45 23:27 42:51 53:4 አላህ የወይህ ባለቤት ሲሆን ከነቢያች በፊት ላሉት ነቢያትና ለነቢያች መጽሐፍን የሚገልጠው እርሱ ነው፦
4:163 እኛ ወደ ኑሕና ከርሱ በኋላ ወደ ነበሩት ነቢያት *እንዳወረድንأَوْحَيْنَا፣ ወደ አንተም *አወረድን أَوْحَيْنَا፤ ወደ ኢብራሂምም፣ ወደ ኢስማዒልም፣ ወደ ኢስሐቅም፣ ወደ ያዕቆብም፣ ወደ ነገዶቹም ወደ ዒሳም፣ ወደ አዮብም፣ ወደ ዩኑስም፣ ወደ ሀሩንና ወደ ሱለይማንም *አወረድንوَأَوْحَيْنَا፤ ለዳዉድም ዘቡርን ሰጠነው።

አውሃይና أَوْحَيْنَا ገለጥን አሊያም አወረድን የሚለው ቃል የመጀመሪያ መደብ ያለቀ አላፊ ግስ ሆኖ የመጣ ሲሆን አላህ በቁርአን 24 ጊዜ አውሃይና ብሏል፣ እንዲሁ ኑሂ نُوحِي የምንገልጥ አሊያም የምናወርድ የሚለው ቃል የመጀመሪያ መደብ ያላለቀ አላፊ ግስ ሆኖ የመጣ ሲሆን አላህ በቁርአን 5 ጊዜ ኑሂ ብሏል፦
21:25 ከአንተ በፊትም፣ እነሆ ከኔ ሌላ አምላክ የለምና ተገዙኝ፣ በማለት ወደርሱ *የምናወርድለትنُوحِي ቢሆን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም።
12:109 ካንተ በፊትም ከከተሞች ሰዎች ወደነርሱ ራዕይ *የምናወርድላቸው نُوحِي የሆኑን ወንዶችን እንጂ አልላክንም፤
21:7 ከአንተም በፊት ወደነሱ *የምናወርድላቸው نُوحِي የኾኑ እንጂ ሌላን አልላክንም፤
16:43 ከአንተም በፊት ወደነሱ ወሕይን *የምናወርድላቸውን نُوحِي ሰዎችን እንጂ፣ ሌላን አልላክንም፤
3:44 ይኽ ወደ አንተ *የምናወርደዉ نُوحِيهِ የሆነ ከሩቅ ወሬዎች ነዉ፤

ምንኛ ያማረ ቃል ነው? አላህ እውነት ተናገረ፣ ጥንት ለነቢያት ተውሂድን ሲገልጥ የነበረው አንዱ አምላክ ዘመኑ ሲደርስ ቁርአንን በነቢያች ላይ ገልጦታል፦
42:3 እንደዚሁ አሸናፊው፣ ጥበበኛው አላህ ወዳንተ *ያወርዳል يُوحِي ፤ ወደነዚያም ከአንተ በፊት ወደነበሩት ሕዝቦች፣ አውርዷል።

ነጥብ ሁለት
ተንዚል
ተንዚል تَنزِيل የሚለው ቃል ነዝዘለ نَزَّلَ ማለትም አወረደ አሊያም ገለጠ ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን *የተወረደ* አሊያም *የተገለጠ* ማለት ነው፣ ተንዚል የሚለው ቃል በቁርአን 15 ጊዜ ሰፍሮ ይገኛል፣ ለናሙና ያክል ይህ በቂ ነው፦ 41:2 41:42 46:2 32:2 5:2 39:1 40:2 20:4
ይህም ቃል ወህይ ከሚለው ቃል ጋር ተለዋዋጭ ሆኖ የሚመጣ ቃል ነው፣ ቁርአን አሊያም ሌሎች ኪታቦች ወረዱ ሲባል በወረቀት የተጻፈ ጥቅል ወረደ ማለት ሳይሆን የአላህ ንግግር ተገጠለ ማለት ነው፣ ምክንያቱም ወረቀት ልብ ላይ ሊወርድ አይችልም ባይሆን ወህይ እንጂ፦
6:7 ባንተም ላይ በወረቀት የተጻፈን መጽሐፍ ባወረድንና በእጆቻቸው በነኩት ኖሮ እነዚያ የካዱት ሰዎች «ይህ ግልጽ ድግምት እንጅ ሌላ አይደለም» ባሉ ነበር፡፡
2:97 ለጂብሪል ጠላት የኾነ ሰው በቁጭት ይሙት በላቸው፡፡ እርሱ ቁርኣኑን ከበፊቱ ለነበሩት መጻሕፍት አረጋጋጭ ለምእመናን መሪና ብስራት ሲኾን በአላህ ፈቃድ በልብህ ላይ አውርዶታልና፡፡
26:192-194 እርሱም ቁርኣን በእርግጥ ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው፡፡ እርሱን ታማኙ መንፈስ አወረደው፤ ከአስጠንቃቂዎቹ ትኾን ዘንድ *በልብህ* ላይ አወረደው፡፡

አንዘልናሁ أَنْزَلْنَاهُ አወረድነው የሚለው ቃል አንድ ጊዜ መውረድን ለቁርአን ከተጠበቀው ሰሌዳ ወደ ቅይቢቱ ሰማይ መውረድና ለሌሎቹ መጽሐፍት መውረድ አገልግሎት ላይ የዋለ ሲሆን 16 ጊዜ ተጠቅሷል፣ ነዝዘልናሁ وَنَزَّلْنَاهُ አወረድነው የሚለው ቃል ደግሞ ቀስ በቀስ መውረድን የሚያሳይ ሲሆን በነቢያን ቀልብ ላይ የወረደውን ቁርአን ለማመልከት አገልግሎት ላይ የዋለ ሲሆን 12 ጊዜ ተጠቅሷል፣ ይህ የስነ-ቋንቋ ሙግት ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው፦
57:25 መልክተኞቻችንን በግልጽ ማስረጃዎች በእርግጥ ላክን፤ ሰዎችም በትክክል ቀጥ እንዲሉ መጽሐፎችንና ሚዛንን ወደነርሱ አወረድን وَأَنْزَلْنَا ።
2:213 አላህም ነቢያትን አብሳሪዎችና አስፈራሪዎች አድርጎ ላከ፡፡ ከእነርሱም ጋር መጻሕፍትን በሰዎቹ መካከል በዚያ በርሱ በተለያዩበት ነገር ይፈርድ ዘንድ በእውነት አወረደ وَأَنْزَلَ፡፡

ቁርአንን ሆነ የቀድሞ መጽሐፍት ያወረደው የዓለማቱ ጌታ አላህ ነው፦
2:4 ለእነዚያም ወደ አንተ በተወረደው أُنْزِلَ እና ከአንተ በፊትም በተወረደው أُنْزِلَ የሚያምኑ በመጨረሻይቱም ዓለም እነርሱ የሚያረጋግጡ ለኾኑት መሪ ነው፡፡
4:60 ወደ እነዚያ፣ እርሱ ባንተ ላይ በተዋረደው أُنْزِلَ እና ከአንተ በፊትም በተወረደው أُنْزِلَ አምነናል ወደሚሉት አላየህምን?
4:162 ግን ከነርሱ ውስጥ በዕውቀት የጠለቁትና ምእምናኖቹ በአንተ ላይ በተወረደው أُنْزِلَ እና ከአንተም በፊት በተወረደው أُنْزِلَ መጽሐፍ የሚያምኑ ሲኾኑ፤
3:3 ከርሱ በፊት ያሉትን መጻሕፍት የሚያረጋግጥ ሲሆን መጽሐፉን ባንተ ላይ ከፋፍሎ በዉነት አወረደ نَزَّلَ። ተዉራትንና ኢንጅልንም አውርዷል وَأَنْزَلَ።

ኢንሻላህ በሚቀጥለው ክፍል ስለ አቅል እሳቤ እንዳስሳለን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ነቅልና አቅል በቁርአን እሳቤ

ክፍል ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

እሳቤ ሁለት
አቅል
አላህ ለሰው ልጆች እንዲያመዛዝኑ፣ እንዲያስተነትኑ፣ እንዲያስተውሉ፣ እንዲመራመሩ የሰጠው አመክንዮ*Reason* ነው፣ ይህ አመክኖ አቅል عقل ይባላል፣ አቅል የቀጥታ ትርጉሙ *ግንዛቤ* ማለት ነው፣ አላህ ስለ አቅል በተለያየ ጉዳይ ላይ ይነግረናል፦
ነጥብ አንድ
ቁርአንና አቅል
አላህ ቁርአን ያወረደው የግንዛቤ ባለቤቶች በአቅላቸው አስተንትነው እንዲገነዘቡ ነው፦
12:2 በእርግጥ እኛ ትገነዘቡ تَعْقِلُونَ ዘንድ ዐረብኛ ቁርአን ሲሆን አወረድነው።
43:3 በእርግጥ እኛ ትገነዘቡ تَعْقِلُونَ ዘንድ ዐረብኛ ቁርአን አደረግነው።
2:242 እንደዚሁ አላህ አንቀጾቹን ትገነዘቡ تَعْقِلُونَ ዘንድ ለናንተ ያብራራላችኋል፡፡
21:10 ክብራችሁ በውሥጡ ያለበትን መጽሐፍ ወደናንተ በእርግጥ አወረድን፤ አትገነዘቡምን? أَفَلَا تَعْقِلُونَ.

ነጥብ ሁለት
እንስሳና አቅል
ሰው ከእንስሳ የሚለውየው በአቅሉና በቀውሉ ነው፣ ያ የተገነዘብውን ስሜትና ሃሳብ በአንደበቱ መግለጹ ነው፣ ሰው አላህ ያወረደውን ቁርአንና በፍጥረት ውስጥ ያሉትን ነገሮች በአቅሉ ካልተመራመረና ካላስተነተነ እንደ እንስሳ ነው፦
25:44 ይልቁንም አብዛኛዎቻቸው የሚሰሙ፣ ወይም የሚገነዘቡ يَعْقِلُونَ ፣ መሆናቸውን፣ ታስባለህን? እነርሱ እንደ እንሰሳዎች እንጂ ሌላ አይደሉም፣
2:171 የነዚያም የካዱት ምሳሌ እንደዚያ ድምጽንና ጥሪን በስተቀር ሌላን በማይሰማ እንስሳ ላይ እንደሚጮህ ብጤ ነው፡፡ እነርሱ ደንቆሮዎች፣ ዲዳዎች፣ ዕውሮች ናቸው፤ ስለዚህ እነርሱ አይገነዘቡም لَا يَعْقِلُونَ፡፡
8:22 ከተንቀሳቃሾች ሁሉ አላህ ዘንድ መጥፎ ተንኮለኞች እነዚያ የማይገነዘቡት لَا يَعْقِلُونَ ደንቆሮዎቹ ዲዳዎቹ ናቸው።
10:42 አንተ ደንቆሮዎችን የማይገነዘቡ لَا يَعْقِلُونَ ቢኾኑም ታሰማለህን?
23:80 የሌሊትና የቀን መተካካትም የእርሱ ነው፡፡ አትገነዘቡምን? أَفَلَا تَعْقِلُونَ.

ነጥብ ሶስት
ህዋስና አቅል
ህዋሳት የሚባሉት መስሚያ፣ ማያም፣ ልብም ናቸው፣ መስሚያ፣ ማያም፣ ልብም እንሰሳዎች አላቸው ነገር ግን የሚያገናዝቡበት አቅል የላቸውም፣ ሰውም የሚያገናዝብበትን አይን፣ ጆሮ፣ ልብ ካልተጠቀመበት አላህ ይጠይቀዋል፣ አላህ የሰጠውን የማገናዘቢያ አቅል ካልተጠቀመ ይቀጣዋል፦
67:10 የምንሰማ ወይንም የምናገናዝብ نَعْقِلُ በነበርን ኖሮ በነዳጅ እሳት ጓዶች ውስጥ ባልሆን ነበር ይላሉ።
17:36ለአንተም በርሱ *ዕውቀት* የሌለህን ነገር አትከተል፤ መስሚያ፣ ማያም፣ ልብም፣ እነዚህ ሁሉ ባለቤታቸው ከነሱ ተጠያቂ ነውና።አታውቁምን?

ለዚህ ነው አላህ አቅላችንን መጠቀም እንዳለብል ሲነግረን አታውቁምን? አያስተውሉምን? አትገነዘቡምን? አታስተነትኑምን? አታስተነትኑምን? አትሰሙምን? አታዩምን? አትመለከቱምን? የሚለን፦
21:10 ክብራችሁ በውሥጡ ያለበትን መጽሐፍ ወደናንተ በእርግጥ አወረድን፤ አታውቁምን?
30:8 በነፍሶቻቸው ሁኔታ አያስተውሉምን أَوَلَمْ يَتَفَكَّرُوا ?
56:62 የፊተኛይቱንም አፈጣጠር በእርግጥ አውቃችኋል፤ አትገነዘቡምን?
6:50 «ዕውርና የሚያይ ይስተካከላሉን አታስተነትኑምን?» በላቸው፡፡
28:71 «አላህ በእናንተ ላይ ሌሊትን እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ ዘውታሪ ቢያደርገው ከአላህ ሌላ ብርሃንን የሚያመጣላችሁ አምላክ ማነው አትሰሙምን?» በላቸው፡፡
31:20 አላህ በሰማያት ያለውንና በምድርም ያለውን ሁሉ ለናንተ ያገራላችሁ ጸጋዎቹንም ግልጽም ድብቅም ሲሆኑ የሞላላችሁ፣ መሆኑን አታዩምን?
51:21 በነፍሶቻችሁም ውስጥ ምልክቶች አሉ ፤ ታዲያ አትመለከቱምን?

ነጥብ አራት
የግንዛቤ ባለቤትና አቅል
አላህ የሚያገናዝቡ ሰዎችን ልሊቀውሚን የዕቂሉን لِقَوْمٍ يَعْقِلُونَ የሚያገናዝቡ ሕዝቦች ይላቸዋል፦
13:4 ለሚያገናዝቡ ሕዝቦች لِقَوْمٍ يَعْقِلُونَ ታምራት አለበት።
16:12 ለሚያገናዝቡ ሕዝቦች لِقَوْمٍ يَعْقِلُونَ በእርግጥ ታምራቶች አሉ።
29:35 በእርግጥ ለሚያገናዝቡ لِقَوْمٍ يَعْقِلُونَ ሰዎች ከርሷ ግልጽ ምልክትን አስቀረን።
30:24 ለሚያገናዝቡ ሕዝቦች لِقَوْمٍ يَعْقِلُونَ ታምራቶች አሉበት።
30:28 ለሚያገናዝቡ ሕዝቦች لِقَوْمٍ يَعْقِلُونَ አንቀጾችን እንገልጻለን።
45:5 ለሚያገናዝቡ ሕዝቦች لِقَوْمٍ يَعْقِلُونَ ማስረጃ አልሉ።
16:67 ለሚያገናዝቡ ሕዝቦች لِقَوْمٍ يَعْقِلُونَ እርግጠኛ ምልክቶች አሉ፡፡

አላህ ቁርአንን ያወረደው የአእምሮ ባለ-ቤቶችም አንቀጾቹን እንድናስተነትን ነው፦
38:29 ይህ ወዳንተ ያወረድነው ብሩክ መጽሐፍ ነው፡፡ አንቀጾቹን እንዲያስተነትኑና لِيَدَّبَّرُوا የአእምሮ ባለ ቤቶችም እንዲገሰጹ አወረድነው፡
47:24 ቁራንንም አያስተነትኑምን?أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ በውነቱ በልቦቻቸው ላይ ቁልፎቿ አልሉባትን?
4:82 ቁርአንን አያስተነትኑምን? أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ፣ በርሱ ውስጥ ብዙ መለያየት ባገኙ ነበር።
23:68 የቁርኣንን ንግግሩንም አያስተነትኑምን أَفَلَمْ يَدَّبَّرُوا ወይስ ለመጀመሪያዎቹ አባቶቻቸው ያልመጣ ነገር መጣባቸውን?
መደምደሚያ
96:1-5 አንብብ በዚያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም። ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው ጌታህ ስም። አንብብ፤ ጌታህ በጣም ቸር ሲሆን፤ ያ በብዕር ያስተማረ፤ ሰውን ያልወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲሆን።

ኢቅራ اقْرَأْ ማለትም *አንብብ* የሚለው ትዕዛዛዊ ግስ*imperative verb?* ሁለት ጊዜ መምጣቱ ሁለት ይዘት እንዳለው ምሁራን ይናገራሉ፦
አንደኛ ይዘት *አንብብ በዚያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም* ማለት መለኮታዊ መገለጥ የሆነው ቁርአንን እያንዳንዱን ሱራ በአላህ ስም መነበቡም ሲያመለክት ይህ ነቅል የሚባለውን የእውቀት ምንጭ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፦
7:52 *ከእውቀት* ጋርም የዘረዘርነው የሆነን መጽሐፍ ለሚያምኑ ሕዝቦች መመሪያና እዝነት ሲሆን፣ በእርግጥ አመጣንላቸው።
13:37 እንደዚሁ በዐረብኛ የተነገረ ፍትሕ ሲሆን አወረድነው፤ *ዕውቀቱ* ከመጣልህም በኋላ፥ ዝንባሌዎቻቸውን ብትከተል፥ ከአላህ ቅጣት ምንም ረዳትም ጠባቂም የለህም።
17:36ለአንተም በርሱ *ዕውቀት* የሌለህን ነገር አትከተል፤ መስሚያ፣ ማያም፣ ልብም፣ እነዚህ ሁሉ ባለቤታቸው ከነሱ ተጠያቂ ነውና።

ሁለተኛው ይዘት ደግሞ *አንብብ፤ ጌታህ በጣም ቸር ሲሆን፤ ያ በብዕር ያስተማረ፤ ሰውን ያልወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲሆን* ስለሚል በብዕር ማለትም በትምህርት የሚገበይ እውቀትን ማንበብ ያሳያል፣ አላህ ሰውን ያላወቀውን ሁሉ አሳውቆታል፣ ሳይንስ*science* የሚለው ቃል ሳይንሲያ ከሚል ከላቲን ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙ እውቀት ማለት ነው፣ ይህ ቋንቋዊ ፍቺው ሲሆን ሙያዊ ፍቺው ደግሞ ህይወት ስላላቸውና ስለሌላቸው ነገሮች የሚያጠና የምርምር ዘርፍ ነው፣ ይህ የምርምር ጥናት እንደሚመጣ አላህ በቁርአን ነግሮናል፦
41.53 እርሱም ቁርአን እውነት መሆኑ ለነርሱ እስከሚገለጽላቸው ድረስ፣ በአጽናፎቹ ውስጥና በራሶቻቸውም ውስጥ ያሉትን ታምራቶቻችንን በእርግጥ እናሳያቸዋለን፤ ጌታህም እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ዐዋቂ መሆኑ አይበቃቸውምን?
27:92-93 ታምራቶቹን ወደፊት ያሳያችኋል፤ ታውቁታላችሁ በላቸው፤

ዛሬ የስነ-ምርምር ጥናት ተመራማሪዎች በአጽናፎች ያሉትን ፈለኮች፣ ፕላኔቶች፣ ምህዳሮች፣ ፍኖተ-ሃሊብ፣ ክላስተሮች፣ አድማሳትን መርምረው አይተዋል፣ ይህን ቁርአን በወረደበት ጊዜ የማይታሰብ ነው፣ ነገር ግን አላህ በአጽናፎች ያሉትን ታምራቶቻችንን በእርግጥ እናሳያቸዋለን ብሎ ቃል በገባው መሰረት ተፈጽሟል፣ ቁርአን እውነት መሆኑ በዚህ ይገለጻል። በራሶቻቸውም ያሉትን ስነ-አካል Physiology፣ ስነ-ልቦና Psychology፣ ስነ-መንፈስ Pneumatology፣ ስለ-ህይወት Biology፣ የወንድ ጾታ ጥናት Andrology፣ የሴት ጾታ ጥናት gynaecology መርምረው አይተዋል፣ ይህን ቁርአን በወረደበት ጊዜ የማይታሰብ ነው፣ ነገር ግን አላህ በራሶቻቸውም ያሉትን ታምራቶቻችንን በእርግጥ እናሳያቸዋለን፤ ታምራቶቹን ወደፊት ያሳያችኋል፤ ታውቁታላችሁ ብሎ በገባው ቃል መሰረት ዛሬ በዘመናችን አይተናል፣ ኣውቀናል። ቁርአን እውነት መሆኑ በዚህ ይገለጻል፤

ዋቢ መጽሐፍት፦
1. Revelation and Reason in Islam
AvA.J. Arberry Volume 3.
2. Ibn Taymiyyah Fatawa 3:338-9 – Taken from “Ibn Taymiyyah Expounds on Islam.

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ሰለዋት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

33፥56 *አላህ እና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ*፡፡ إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا

“ሰለዋት” صَلَوَاتٌ የሚለው ቃል “ሰላ” صَلَّىٰ “አዘነ” “ባረከ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “እዝነት” ወይም “በረከት”salutation” ማለት ነው፤ “ሰለዋት” ማለት ነብያችን”ﷺ” ስማቸው ሲጠራ “ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሠለም” صلى الله عليه وسلم ብለን የምንመልሰው ነው፤ ይህንን ያዘዘን አምላካችን አላህ በተከበረ ንግግሩ ነው፦
33፥56 *አላህ እና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ*፡፡ إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا

እዚህ አንቀጽ ላይ “ሰሉ” صَلُّوا እና “ሠለሙ” سَلِّمُوا የሚለው ትእዛዝ የአምላካችን የአላህ ትእዛዝ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል፤ “ሰለሏህ” صلى الله ማለት “የአላህ እዝነት” ማለት ሲሆን ሰለዋት ነው፤ “ወሠለም” وسلم ደግሞ “ተሥሊማህ” تَسْلِيمًا ማለትም “ሰላምታ” ነው።
አላህ እና መላእክቱ በነቢዩ ላይ ሰለዋት ያወርዳሉ የሚለውን ሚሽነሪዎች አላህ እና መላእክቱ ወደ ነቢዩ ይጸልያሉ በማለት ሊያንሻፍፉ ይሞክራሉ። እዚህ አንቀጽ ላይ በትክክልም “ዩሰሉነ” يُصَلُّونَ ማለት “እዝነትን ያወርዳሉ” ማለት እንጂ “ይጸልያሉ” ማለት በፍጹም አይደለም።

ዐረቢኛ ላይ ተመሳሳይ ቃል ቢኖረው እንኳን ተመሳሳይ ሀሳብና ትርጉም አለው ማለት አይደለም፤ የአንድን ቃል አማራጭ ትርጒም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ ቅቡል ነው፤ ቃሉ ሳይሆን ቃሉ የወከለው ሐሳብ መታየት ያለበት። ለናሙና ያክል አንዳንድ የቋንቋ ሙግት እንመልከት፦
“ፊ” فِي ማለት “ውስጥ” ማለት ቢሆንም “ቢ” بـِ ማለትም “በ” በሚል እና “ፈውቅ” فَوْق ማለትም “በላይ” በሚል ይመጣል።
“ወ” وَ ማለት “እና” ማለት ቢሆንም “ቢ” بـِ ማለትም “በ” በሚል ይመጣል።
“ላ” َلَا ማለት “አይደለም” ማለት ቢሆንም “ለቀድ” َلَقَدْ ማለትም “እርግጥ” በሚል ይመጣል።
“ማ” مَا ማለት “አይደለም” ማለት ቢሆንም “አለዚ” الَّذِي ማለትም “ያ” በሚል ይመጣል።
“በአሠ” بَعَثَ ማለት “አስነሳ” ማለት ቢሆንም “አርሰለ” أَرْسَلَ ማለትም “ላከ” በሚል ይመጣል።
“ጀንብ” جَنب ማለት “ጎን” ማለት ቢሆንም “ሚን” مِن ማለትም “በኩል” በሚል ይመጣል።
“ተእዊል” تَأْوِيل ማለት “ትርጉም” ማለት ቢሆንም “አኺር” آخِر ማለትም “መጨረሻ” በሚል ይመጣል።
ይህንን በወፍ በረር ለቅምሻ ያክል ካየን ዘንዳ “ሰለዋት” የሚለው ቃል “በረካት” بَرَكَٰت በሚል የመጣው ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 60, ሐዲስ 48
አቡ ሑመይድ አሥ-ሣዒዲይ”ረ.ዐ” እንደተረከው፦ *”ሰዎች፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሆይ! በእርሶ ላይ እንዴት ሰለዋት እናውርድ? አሉ፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ “አላህ ሆይ! ሰለዋትን በሙሐመድ፣ በባልተቤቶቹ እና በዝርዮቹ ላይ አውርድ፥ ሰለዋትን በኢብራሂም ቤተሰብ ላይ እንዳወረድክ በረካትን በሙሐመድ፣ በባልተቤቶቹ እና በዝርዮቹ ላይ አውርድ ልክ በኢብራሂም ቤተሰብ ላይ እንዳወረድክ፤ አንተ የተመሰገንክ እና የተከበርክ ነህ*። أَخْبَرَنِي أَبُو حُمَيْدٍ السَّاعِدِيُّ ـ رضى الله عنه ـ أَنَّهُمْ قَالُوا يَا رَسُولَ اللَّهِ كَيْفَ نُصَلِّي عَلَيْكَ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ قُولُوا اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَأَزْوَاجِهِ وَذُرِّيَّتِهِ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، وَبَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَأَزْوَاجِهِ وَذُرِّيَّتِهِ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ ‏”‌‏.‏
ይህ ግልጽ ነው። ምን ትፈልጋለህ? “ሰለዋትን በኢብራሂም ቤተሰብ ላይ እንዳወረድክ በረካትን በሙሐመድ፣ በባልተቤቶቹ እና በዝርዮቹ ላይ አውርድ” የሚለው ይሰመርበት፤ “ሰለይተ” صَلَّيْتَ የሚለው ቃል “ባረክተ” بَارَكْتَ ለሚለው ቃል ተለዋዋጭ ሆኖ ነው የመጣው፤ አላህ ሰለዋት የሚያወርደው በነቢያችን”ﷺ” ብቻ ነውን? ሐዲሱ ላይ በባልተቤቶቻቸው ላይ፣ በዝርያወቻቸው ላይ እና በኢብራሂም ቤተሰብ ላይም ጭምር ነው። ሰለዋት የሚለውን ቃል ጸሎት ብለን ከወሰድነው እዚህ ጋር ችግር ይፈጠራል፤ አላህ ወደ ባልተቤቶቻቸው፣ ወደ ዝርያወቻቸው እና ወደ ኢብራሂም ቤተሰብ ይጸልያል ትርጉም አይሰጥም። “ወደ” የሚለው መስተዋድ “ኢላ” إِلَى ሲሆን ለሰለዋት ጥቅም ላይ አልዋለም፤ ለሰለዋት የዋለው መስተዋድድ “ዐላ” عَلَى ማለትም “ላይ” ነው፤ “ላይ” ደግሞ ለሰላም፣ ለእዝነት እና ለበረከት የሚውል መስተዋድድ ነው፦
11፥73 «ከአላህ ትዕዛዝ ትደነቂያለሽን *የአላህ ራህመት እና በረካት በእናንተ እና በኢብራሂም ቤተሰቦች “ላይ” ይሁን* እርሱ ምስጉን ለጋስ ነውና» አሉ፡፡ قَالُوا أَتَعْجَبِينَ مِنْ أَمْرِ اللَّهِ ۖ رَحْمَتُ اللَّهِ وَبَرَكَاتُهُ عَلَيْكُمْ أَهْلَ الْبَيْتِ ۚ إِنَّهُ حَمِيدٌ مَّجِيدٌ
11፥48 «ኑሕ ሆይ! *ከእኛ በሆነ ሰላም እና በረካት በአንተ ላይ እና አንተም ጋር ባሉት ሕዝቦች ላይ በሆኑ የተጎናጸፍክ ሆነህ ውረድ*፡፡ قِيلَ يَا نُوحُ اهْبِطْ بِسَلَامٍ مِّنَّا وَبَرَكَاتٍ عَلَيْكَ وَعَلَىٰ أُمَمٍ مِّمَّن مَّعَك

ጸሎት ለሚቀበለት ለፈጣሪ የሚያገለግለው መስተዋድድ ደግሞ “ሊ” لِ ማለትም “ለ” ነው፤ ለምሳሌ ሶላት “ለ”አላህ የሚቀርብ አምልኮ ነው፦
6፥162 *«ሶላቴ፣ መስዋዕቴም፣ ሕይወቴም፣ ሞቴም ለዓለማት ጌታ “ለ”አላህ ነው»* በል፡፡ قُلْ إِنَّ صَلَاتِي وَنُسُكِي وَمَحْيَايَ وَمَمَاتِي لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ
20፥14 እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና አምልከኝ፡፡ *ሶላትንም እኔን ለማውሳት ስገድ*፡፡ إِنَّنِي أَنَا اللَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدْنِي وَأَقِمِ الصَّلَاةَ لِذِكْرِي

ደግሞ አላህ እና መላእክቱ ሰለዋት የሚያወርዱት በአማንያንም ጭምር መሆኑ ሰለዋት “እዝነት” መኑነን ያስረዳል፦
33፥43 *እርሱ ያ በእናንተ ላይ “እዝነትን” የሚያወርድ ነው፡፡ መላእክቶቹም እንደዚሁ፡፡ ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ያወጣችሁ ዘንድ ያዝንላችኋል፡፡ ለአማኞችም በጣም አዛኝ ነው*፡፡ هُوَ الَّذِي يُصَلِّي عَلَيْكُمْ وَمَلَائِكَتُهُ لِيُخْرِجَكُم مِّنَ الظُّلُمَاتِ إِلَى النُّورِ ۚ وَكَانَ بِالْمُؤْمِنِينَ رَحِيمًا

“ዩሰሊ” يُصَلِّي የሚለው ቃል እዚህ ዐውድ ላይ “እዝነት” የሚለውን ፍቺ ይሰጠናል፤ ሲዘጋም አላህ “ረሒማህ” رَحِيمًا ማለትም “በጣም አዛኝ” በሚለው አንቀጹ ስለሚዘጋ። ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ያወጣቸው ተመሪዎቹ ላይ ከጌታቸው የሚወርዱት ሰለዋት እና ምህረት ናቸው፦
2፥157 *እነዚያ በእነርሱ "ላይ" ከጌታቸው የኾኑ ምሕረቶች እና ችሮታም አሉ፡፡ እነርሱም ወደ እውነት ተመሪዎቹ እነርሱ ናቸው*፡፡ أُولَـٰئِكَ عَلَيْهِمْ صَلَوَاتٌ مِّن رَّبِّهِمْ وَرَحْمَةٌ ۖ وَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْمُهْتَدُونَ

“ሰለዋት” صَلَوَاتٌ እና “ረሕማህ” َرَحْمَةٌ የሚሉት ቃላት “ወ” و በሚል አያያዥ መስተጻምር መምጣታቸው በአማንያን ላይ ከአላህ የሚወርዱ በረከትና እዝነት መሆናቸውን እንጂ ጸሎት አለመሆናቸውን ፍንትው አድርጎ ያሳያል፤ አላህ እና መላእክቱ ብቻ ሳይሆኑ የሰማይና የምድር ሕዝቦች፣ ጉንዳንና አሳ ሳይቀሩ ለሰዎች መልካምን በሚያስተምር ዐዋቂ ላይ በረከትን ያወርዳሉ፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 41, ሐዲስ 41
አቢ ኡማማህ አል-ባሂሊይ እንደተረከው፦ *”በአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ፊት ሁለት ተዘከሩ፤ ከእነርሱም አንዱ አላህን አምላኪ ሲሆን ሁለተኛው ዐዋቂ ነው፤ ከዚያም የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ “እኔ ከእናንተ እንደምበጥ ዐዋቂም ከአምላኪ ይበልጣል። በመቀጠልም የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ “አላህ፣ መላእክቱ፣ የሰማያትና የምድር ሕዝቦች፣ በተራራ ውስጥ ያሉት ጉንዳኖች ሳይቀሩ፣ አሳም ሳይቀሩ ለሰዎች መልካምን በሚያስተምረው ላይ ሰለዋትን ያወርዳሉ*። عَنْ أَبِي أُمَامَةَ الْبَاهِلِيِّ، قَالَ ذُكِرَ لِرَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم رَجُلاَنِ أَحَدُهُمَا عَابِدٌ وَالآخَرُ عَالِمٌ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ فَضْلُ الْعَالِمِ عَلَى الْعَابِدِ كَفَضْلِي عَلَى أَدْنَاكُمْ ‏”‏ ‏.‏ ثُمَّ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّ اللَّهَ وَمَلاَئِكَتَهُ وَأَهْلَ السَّمَوَاتِ وَالأَرْضِ حَتَّى النَّمْلَةَ فِي جُحْرِهَا وَحَتَّى الْحُوتَ لَيُصَلُّونَ عَلَى مُعَلِّمِ النَّاسِ الْخَيْرَ ‏
አላህ እና ፍጡራኑ ወደ ፍጡራን ይጸልያሉ የሚል ስሁት ተሟጋች ካለ ጊዜውን በጉንጭ አልፋ ንትርክ እና በእሰጣ ገባ ማቃጠል የሚፈልግ ሰው ብቻ ነው፤ ከዚያም ባሻገር በመሃይምነት አራንቋ ውስጥ የተዘፈቀ ነው። ሚሽነሪዎች፦ “አላህ ይጸለያል” የሚለው ለማምጣት የፈለጉት አምላክና ፈጣሪ ነው ብለው የሚያምኑበት ኢየሱስ መጸለዩ የፍጡር ባህርይ አያሲዘውም ብለው ውኃ ለማያነሳ ስሁት ሙግት ይረዳናል ብለው ነው፤ ግን ውኃ አይቋጥርም።
ይህንን ካየን ዘንዳ ከላይ ያለውን መጣጥፍ በተመሳሳይ የንጽጽር ሙግት እንቋጨዋለን፤ በባይብል እግዚአብሔርን መባረክ የአምልኮ ክፍል ነው፦
መዝሙር 34፥1 *እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እባርከዋለሁ*፥
1ኛ ዜና መዋዕል 29፥20 ዳዊትም ጉባኤውን ሁሉ፦ *አምላካችሁን እግዚአብሔርን ባርኩ አላቸው። ጉባኤውም ሁሉ የአባታቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ባረኩ*፥
መዝሙር 103፥21 *ፈቃዱን የምታደርጉ አገልጋዮቹ እግዚአብሔርን ባርኩ*።

እግዚአብሔር እና መልአኩ እስራኤልን ይባርካሉ፦
ዘፍጥረት 28፥3 ሁሉን የሚችል አምላክም ለብዙ ሕዝብ ጉባኤ እንድትሆን *ይባርክህ*፥ ያፍራህ፥ ያብዛህ፤
ዘፍጥረት 48፥16 ከክፉ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ፥ እርሱ እነዚህን ብላቴኖች *ይባርክ*፤

ሁሉን የሚችል አምላክም እና መልአኩ ይባርካሉ ማለት እና ሰዎች ሁሉን የሚችል አምላክን ይባርካሉ ማለት አንድ ነው ወይ? አይ አይደለም፤ እግዚአብሔር እና መልአኩ ይባርካሉ ማለት ረድኤትን ይሰጣሉ ማለት ነው፥ ሰዎች እግዚአብሔር ይባርካሉ ማለት አምልኮ ነው ከተባለ እንግዲያውስ ከላይ ያለው የቃላት ዐውዱ ይወስነዋል ብላችሁ በዚህ ስሌት እና ቀመር ተረዱት። የሚሽነሪዎች ጥያቄ ከሙስተሽሪቆች ማለትም የመካከለኛው ምስራቅ ጥንተ-ነገር አጥኝዎች”Orientalists” ከሆኑት የሚያነቡት ነው። አላህ ሂዳያ ይስጣቸው፥ ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አምስት ወቅት ሶላት በቁርአን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4:103 “ሶላት” በምእመናን ላይ “በጊዜያት” የተወሰነች ግዴታ ናትና፤

መግቢያ
ብዙ ጊዜ ሚሽነሪዎሽ ፦”አምስት ወቅት ሶላት ቁርአን ላይ የለም” ብለው በማያውቁት ነገርና ባላነበቡት ጉዳይ እንደ በቀቀን በመደጋገም ሲዘላብዱ ሰንበትበት አለ፤ ይህን መጣጥፍ ልፅፍ የቻልኩበት ምክንያት ለሙስሊሞች አምስት ወቅት ሶላት የቱ ጋር እንዳለ ለማሳየት ሳይሆን የሚሽነሪዎችን ቅጥፈት ለማጋለጥ ነው፤ በእርግጥም አምስት ወቅት ሶላት በቁርአን አላህ ነግሮናል፤ ሶላት በምእመናን ላይ “በጊዜያት” የተወሰነ ፈርድ ነው፤ ይህን አንድ በአንድ እንይ፦

1. “ሶላተል ፈጅር”
“ፈጅር” فَجْر ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ጎህ” ሲሆን አምላካችን አላህ ይህን የጎህ ወቅት በሶላት እንድንቆም ያዘናል፦
17:78 ሶላትን ከፀሐይ መዘንበል እስከ ሌሊት ጨለማ ድረስ ስገድ፤ “የጎህ” الْفَجْرِ ሰላት ስገድ፣ “የጎህ” الْفَجْرِ ሶላት መላእክት የሚጣዱት ነውና።
24:58 እላንተ ያመናችሁ ሆይ! እነዚያ እጆቻችሁ የጨበጧቸው፣ እነዚያም ከናንተ ለአካለ መጠን ያልደረሱት፣ “ከጎህ” الْفَجْرِ ሶላት በፊት፣ በቀትርም ልብሶቻችሁን በምታወልቁ ጊዜ፣ ከምሽት ሶላትም በኃላ ሦስት ጊዜያት ያስፈቅዷችሁ።

አላህ ፈጅርን ለማመልከት “በምታነጉም ጊዜ”፣ “ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት”፣ “በማለዳም”፣ “በቀን ጫፍ”፣ “በምትንነሳ ጊዜ” በማለት በአፅንኦትና በአንክሮት ይናገራል፦
30:17-18 አላህንም፣ በምታመሹ ጊዜ፣ “በምታነጉም ጊዜ”፣ አጥሩት ።
20:130 በሚሉትም ላይ ታገስ፤ ጌታህንም “ፀሃይ ከመውጣትዋ በፊት” ከመግባትዋም በፊት የምታመሰግን ሆነህ አጥራው፤
50:39 በሚሉትም ላይ ታገሥ፤ ጌታህንም ከማመስገን ጋር “ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት” ከመግባቷም በፊት አወድሰው፡፡
40:55 በቀትር “በማለዳም” ጌታህን ከማመስገን ጋር አጥራው።
11:114 ሶላትንም “በቀን ጫፎች”፤ ከሌሊትም ክፍሎች ፈጽም፤
52:48-49 ለጌታህ ፍርድም ታገሥ፤ አንተ በጥበቃችን ውስጥ ነህና፤ ጌታህንም “በምትንነሳ ጊዜ” ከማመስገን ጋር አወድሰው።

2 . “ሰላት አዝሁር”
“ዝሁር” ظهر በቁርአን “ዘሂረት” ظَّهِيرَة በሚል ስም የመጣ ሲሆን “ቀትር” ማለት ነው፤ አምላካችን አላህ ይህን የቀትር ወቅት በሶላት እንድንቆም ያዘናል፦
24:58 እላንተ ያመናችሁ ሆይ! እነዚያ እጆቻችሁ የጨበጧቸው፣ እነዚያም ከናንተ ለአካለ መጠን ያልደረሱት፣ ከጎህ ሶላት በፊት፣ “በቀትርም” الظَّهِيرَةِ ልብሶቻችሁን በምታወልቁ ጊዜ፣ ከምሽት ሶላትም በኃላ ሦስት ጊዜያት ያስፈቅዷችሁ።
30:18 ምስጋናም በስማያትና በምድር ውስጥ ለርሱ ብቻ የተገባው ነው። በሠርክም “በቀትር” تُظْهِرُونَ ውስጥ በምትገቡም ጊዜ፤ አጥሩት።

3. “ሶላተል አስር”
“አስር” عَصْ ማለት “ጊዜ” ወይም “ሰርክ” ማለት ሲሆን የዓለማቱ ጌታ የማለበት ወቅት ነው፤ ይህቺ የሰርክ ሰላት በቁርአን የመካከለኛይቱ ሶላት ትባላለች፦
103:1″በጊዜያቱ እምላለሁوَالْعَصْرِ ፤
2:238 “በሶላቶች” الصَّلَوَاتِ “እና” በተለይ “በመካከለኛይቱም ሶላት” وَالصَّلَاةِ الْوُسْطَىٰ ላይ ተጠባበቁ፡፡ ታዛዦች ኾናችሁም ለአላህ ቁሙ፡፡

“መካከለኛይቱም ሶላት” የተባለችው ከሌሎች ሶላቶች ለመለየትና ለማያያዝ “ወ” وَ የሚል መስተፃምር ይጠቀማል፤ ታዲያ መካከለኛነቷ ለማን ነው? ስንል ለሁለት ሶላቶች ቢሆን ኖሮ ሙተና”dual” ያለው “ሷላተዪን” صلاتين በመንሱብና በመጅሩር”በተሳቢና በአገናዛቢ” አሊያም “ሷላታን” صلاتان በመርፉ”በባለቤት” ይጠቀም ነበር ነገር ግን መካከለኝነቷ ለሁለት ሳይሆን ጀመዕ”plural” ያለው “ሰለዋት” الصَّلَوَات የሚል ነው፣ ይህ የሚያሳየው ከፊቷ ሁለት ከኃላዋ ሁለት ያላት መካከለኛይቱ ሰላተል አስር ናት፤ ይህቺ ሶላት “ሰርክ”፣ “ፀሐይ ከመግባቷም በፊት”፣ “ከፀሐይ መዘንበል” ትባላለች፦
30:17 ምስጋናም በስማያትና በምድር ውስጥ ለርሱ ብቻ የተገባው ነው። “በሠርክም” በቀትር ውስጥ በምትገቡም ጊዜ፤ አጥሩት።
50:39 በሚሉትም ላይ ታገሥ፤ ጌታህንም ከማመስገን ጋር ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት “ከመግባቷም በፊት” አወድሰው፡፡
20:130 በሚሉትም ላይ ታገስ፤ ጌታህንም ፀሃይ ከመውጣትዋ በፊት “ከመግባትዋም በፊት” የምታመሰግን ሆነህ አጥራው፤ ስገድ፤
17:78-79 ሶላትን “ከፀሐይ መዘንበል” እስከ ሌሊት ጨለማ ድረስ ስገድ፤

4. “ሶላተል መግሪብ”
“መግሪብ” مَغْرِب “ምዕራብ” ማለትም “የጸሃይ መጥለቂያ” ማለት ነው፣ ይህ ሌላኛው የቀን ጫፍ ይባላል፦
11:114 ሶላትንም በቀን “ጫፎች” طَرَفَيِ ፤ ከሌሊትም ክፍሎች ፈጽም፤ መልካም ሥራዎች ኅጢአቶችን ያስወግዳሉና፤ ይህ ለተገሣጮች ግሣጤ ነው።
20:130 በሚሉትም ላይ ታገስ፤ ጌታህንም ፀሃይ ከመውጣትዋ በፊት ከመግባትዋም በፊት የምታመሰግን ሆነህ አጥራው፤ ስገድ፤ ከሌሊት ሰዓቶችም “በቀን “ጫፎች” طَرَفَيِ አጥራው በሚሰጥህ ምንዳ ልትወድ ይከጀላልና።

“ተረፍ” طَرَف ማለት “ጫፍ” ማለት ሲሆን እዚህ ጋር የተጠቀመው ቃል ሙተና”dual” ሆኖ “ተረፈዪ” طَرَفَيِ ነው፤ የቀን ጫፍ አንዱ ጎህ ሲሆን ሌላው ምሽት ነው፤ ይህ “ምሽት” በቁርአን “በምታመሹ ጊዜ”፣ “በከዋክብት መደበቂያ ጊዜም” ይባላል፦
30:17-18 አላህንም፣ “በምታመሹ ጊዜ”፣ በምታነጉም ጊዜ፣ አጥሩት ።
52:48-49 ጌታህንም በምትንነሳ ጊዜ ከማመስገን ጋር አወድሰው። ከሌሊቱም አወድሰው፤ “በከዋክብት መደበቂያ ጊዜም አወድሰው” ።

5. “ሶላተል ኢሻአ”
“ኢሻአ” عِشَآء ማለት “ማታ” ማለት ሲሆን አምላካችን አላህ ይህን የማታ ወቅት በሶላት እንድንቆም ያዘናል፦
24:58 እላንተ ያመናችሁ ሆይ! እነዚያ እጆቻችሁ የጨበጧቸው፣ እነዚያም ከናንተ ለአካለ መጠን ያልደረሱት፣ ከጎህ ሶላት በፊት፣ በቀትርም ልብሶቻችሁን በምታወልቁ ጊዜ፣ “ከማታ” الْعِشَاءِ ሶላትም በኃላ ሦስት ጊዜያት ያስፈቅዷችሁ።
40:55 ታገስም፤ የአላህ ተስፋ እውነት ነውና፤ ለስሕተትህም ምሕረትን ለምን፤ “በማታ” بِالْعَشِيِّ
በማለዳም ጌታህን ከማመስገን ጋር አጥራው።
18:28 ነፍስህንም፤ ከነዚያ ጌታቸውን ፊቱን የሚሹ ሆነው በጧትና “በማታ” وَالْعَشِيِّ ከሚግገዙት ጋር አስታግሥ፤

“ዙልፈ” زُلْفَة ” ፊተኛው የሌሊት ክፍል” ሲሆን የሌሊቱ ክፍል ኢሻአ ነው፦
11:114 ሶላትንም በቀን ጫፎች፤ ከሌሊትም “ክፍል وَزُلَفًا مِنَ اللَّيْلِ ፈጽም፤ መልካም ሥራዎች ኅጢአቶችን ያስወግዳሉና፤ ይህ ለተገሣጮች ግሣጤ ነው።
ማጠቃለያ
አሏህ ስለ ሶላት የነገረን በጊዜ የተወሰነና በአምስት ወቅት መሰገድ እንዳለበት ብቻ ሳይሆን “የተስተካከለ ደንብ” እንዳለውም ጭምር ነው፦
29:45 ከመጽሐፉ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ፤ ሶላትንም “ደንቡን” ጠብቀህ ስገድ፤
4:77 ሶላትንም “ደንቡን” ጠብቃችሁ ስገዱ፣
2:43 ሶላትንም “ደንቡን” ጠብቃችሁ ስገዱ፤
30:31 ሶላትም “አስተካክላችሁ” ስገዱ፤
22:78 ሶላትንም “አስተካክላችሁ” ስገዱ፤
24:56 ሶላትንም “አስተካክላችሁ” ስገዱ፤

የሰላት ደምብ ደግሞ በውስጡ ተክቢራ፣ ተህሊል፣ ተስቢህ፣ ተሸሁድ፣ ተስሊም ወዘተ የመሳሰሉትን ያቅፋል፤ ይህን የተስተካከለ ደንብ የምናገኘው ደግሞ በነብያችን ሱና ነው፤ ስለዚህ ሱና አላህ ይናገራል፦
2:231 የአላህንም ጸጋ በናንተ ላይ ያደረገውን “ከመጽሐፍ” እና “ከጥበብም” በእርሱ የሚገስጻችሁ ሲኾን በእናንተ ላይ “ያወረደውን” አስታውሱ፡፡

“መጽሐፍ” የተባለው የአሏህ ንግግር ቁርአን ሲሆን “ጥበብ” የተባለው ደግሞ የረሱል “ንግግር” ነው፤ ሁለቱም የተወረዱ መሆናቸው ይሰመርበት፤ ስለዚህ የሶላት ዝርዝርና አፈፃፀም የነብያችን ሱና ላይ ተገልፃል።

አሏህ ሶላት ላይ ቆመው ከሚሞቱ ባሮቹ ያድርገን አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም