ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.1K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
አሥ-ሠላሙ ዐለይኩም ሙሥሊም ወንድሞቼ እና እኅቶቼ!

ክርስቲያን ወገኖች ሁላችሁም ሰላም ብያለው። ክርስቲያኖች ሆይ "የኢየሱስ ምንነት እና ማንነት" የሚለው መጽሐፍ በውስጡ የሰውን እምነት የሚነካ ምንም ዓይነት ስድብ፣ ነቀፌታ፣ ማሳነስ የለበትም። ከምታምኑበት እና ከምትሉት ውጪ በተሳሳተ መንገድ የማታምኑትን እና የማትሉትን ነገር መጽሐፉ ውስጥ ካለ ለመታረም ዝግጁ ነኝ።

ያላነበባችሁት በታላቁ አንዋር መሥጂድ ዙሪያ እና በዋናው መግቢያ በር ላይ ባሉት መጽሐፍት መሸጫዎች ያገኛሉ።

ለበለጠ መረጃ በ 0912501818 አወል ሠይድ ብላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ!
የዓኢሻህ"ረ.ዐ." ትዳር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

61፥8 *"የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ሊያጠፉ ይሻሉ፡፡ አላህም ከሓዲዎቹ ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን ገላጭ ነው"*፡፡  يُرِيدُونَ لِيُطْفِئُوا نُورَ اللَّهِ بِأَفْوَاهِهِمْ وَاللَّهُ مُتِمُّ نُورِهِ وَلَوْ كَرِهَ الْكَافِرُونَ

አንዲት እንስት ወጣት ናት፥ በሙሥሊሞች ዘንድ በአውንታዊ መልኩ በኢሥላም ታሪክ ላይ አሻራዋን ካስተቀመጡ እና ጉልህ ሚና ከተጫወቱት ሰዎች አንዷ ናት። ይህቺ ወጣት ከነቢያችን"ﷺ" ሰምታ ስለ ነቢያችን"ﷺ" ሕይወትና አኗኗር፣ ስለ ውርስ፣ ስለ ጋብቻ፣ ስለ መጨረሻው ዘመን ትምህርት ወዘተ 2,210 የሚደርሱ ሐዲሳትን ተርካለች፥ ቁርኣን የምእመናት እናቶች ከሚላቸው አንዷ ናት፦
33፥6 *"ነቢዩ በምእምናን ከራሳቸው ይበልጥ ተገቢ ነው፥ ሚስቶቹም እናቶቻቸው ናቸው"*፡፡ النَّبِيُّ أَوْلَىٰ بِالْمُؤْمِنِينَ مِنْ أَنفُسِهِمْ ۖ وَأَزْوَاجُهُ أُمَّهَاتُهُمْ

ይህችም ወጣት ሴት "ኡመል ሙእሚኒን" أُمِّ الْمُؤْمِنِين ማለትም "የምእመናን እናት" በሚል ማዕረግ የምትጠራ ዓኢሻህ"ረ.ዐ." ናት፥ በአንድ ወቅት ዝሙት ሠርታለች ተብላ የሐሰት ክስ ቀርቦባት አምላካችን አሏህ ሡረቱ አን-ኑር 24፥11-20 ያለውን አንቀጽ ስለ ንጽህናዋ አውርዷል፦
24፥15 *"በምላሶቻችሁ በምትቅበባሉት ጊዜ ለእናንተም በእርሱ ዕውቀት በሌላችሁ ነገር በአፎቻችሁ በተናገራችሁና እርሱ አላህ ዘንድ ከባድ ኀጢአት ኾኖ ሳለ ቀላል አድርጋችሁ ባሰባችሁት ጊዜ ከባድ ቅጣት በነካችሁ ነበር*፡፡ إِذْ تَلَقَّوْنَهُ بِأَلْسِنَتِكُمْ وَتَقُولُونَ بِأَفْوَاهِكُم مَّا لَيْسَ لَكُم بِهِ عِلْمٌ وَتَحْسَبُونَهُ هَيِّنًا وَهُوَ عِندَ اللَّهِ عَظِيمٌ
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 447
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ "ነቢዩም"ﷺ"፦ *"ዓኢሻህ ሆይ አብሽሪ!  አሏህ ስለ ንጽህናሽ ወሕይ አውርዷል፥ ከዚያም ለእርሷ የቁርኣኑን አንቀጽ ቀሩላት። ወላጆቿም፦ "የአሏህ መልእክተኛን"ﷺ" ግንባር ሳሚ!" አሏት፥ እርሷም፦ "ለእናንተ ሳይሆን ለአሏህ ምስጋና ይሁን!" አለች"*። أَنَّ عَائِشَةَ، رضى الله عنها قَالَتْ ثُمَّ قَالَ تَعْنِي النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ أَبْشِرِي يَا عَائِشَةُ فَإِنَّ اللَّهَ قَدْ أَنْزَلَ عُذْرَكِ ‏"‏ ‏.‏ وَقَرَأَ عَلَيْهَا الْقُرْآنَ فَقَالَ أَبَوَاىَ قُومِي فَقَبِّلِي رَأْسَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏.‏ فَقَالَتْ أَحْمَدُ اللَّهَ لاَ إِيَّاكُمَا ‏.‏
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 64, ሐዲስ 188
አቢ ኢብኑ መለይካህ እንደተረከው፦ *"ዓኢሻህ፦ "በምላሶቻችሁ በምትቅበባሉት ጊዜ" የሚለውን አንቀጽ ትቀራ ነበር፥ "አል-ወልቅ" ቅጥፈት ነው" ትል ነበር። አቢ ኢብኑ መለይካህም፦ "ይህን አንቀጽ ስለ እርሷ እንደሚናገር ከማንም ይልቅ ታውቅ ነበር" አለ"*። حَدَّثَنِي يَحْيَى، حَدَّثَنَا وَكِيعٌ، عَنْ نَافِعِ بْنِ عُمَرَ، عَنِ ابْنِ أَبِي مُلَيْكَةَ، عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ كَانَتْ تَقْرَأُ ‏{‏إِذْ تَلِقُونَهُ بِأَلْسِنَتِكُمْ‏}‏ وَتَقُولُ الْوَلْقُ الْكَذِبُ‏.‏ قَالَ ابْنُ أَبِي مُلَيْكَةَ وَكَانَتْ أَعْلَمَ مِنْ غَيْرِهَا بِذَلِكَ لأَنَّهُ نَزَلَ فِيهَا‏.‏

ዓኢሻህ"ረ.ዐ." አባቷ አቡበከር አስ-ሲዲቅ እናቷ ኡሙ ሩማን ሲሆኑ የነቢያችን"ﷺ" ባልደረቦች ናቸው፥ ዓኢሻህ ለነቢያችን"ﷺ" ሚስት እንድትሆን ለቤተሰቦቿ አሳቡን ያመጣችው የነቢያችን"ﷺ" ሴት ባልደረባ የነበረችው ኸውላህ ቢንት ሐኪም"ረ.ዐ." ናት። ቅሉ ግን ዓኢሻህ ለነቢያችን"ﷺ" ሚስት እንደምትሆን ነቢያችን"ﷺ" በሕልማቸው ሁለት ጊዜ አይተዋታል፦ 
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 67, ሐዲስ 16
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"በሕልሜ ሁለት ጊዜ አይቼሻለው፥ አንድ ሰው(ጂብሪል) በሐር ጨርቅ ተሸክሞሽ፦ "ይህቺ የአንተ ሚስት ናት" አለኝ። ስገልጥ እነሆ አንቺ ነበርሽ። እኔም ዓኢሻህ ለራሴ፦ "ይህ ሕልም ከአሏህ ከሆነ ይፈጸማል" አልኩኝ"*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ أُرِيتُكِ فِي الْمَنَامِ مَرَّتَيْنِ، إِذَا رَجُلٌ يَحْمِلُكِ فِي سَرَقَةِ حَرِيرٍ فَيَقُولُ هَذِهِ امْرَأَتُكَ، فَأَكْشِفُهَا فَإِذَا هِيَ أَنْتِ، فَأَقُولُ إِنْ يَكُنْ هَذَا مِنْ عِنْدِ اللَّهِ يُمْضِهِ

ዓኢሻህ ለነቢያችን"ﷺ" የተዳረችው በስድስት ዓመቷ ሲሆን ለዐቅመ-ሐዋህ እስክትደርስ ድረስ ለሦስት ዓመት ከተጠበቀ በኃላ በዘጠኝ ዓመቷ ወደ ነቢያችን"ﷺ" ቤት ገብታለች፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 16, ሐዲስ 82
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"ነቢዩ"ﷺ" ሲያገቡኝ የስድስት ዓመት እንስት ነበርኩኝ፥ የዘጠኝ ዓመት እንስት ስሆን ወደ ቤቱ ገባሁኝ"*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ تَزَوَّجَنِي النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم وَأَنَا بِنْتُ سِتِّ سِنِينَ وَبَنَى بِي وَأَنَا بِنْتُ تِسْعِ سِنِينَ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 67, ሐዲስ 69
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ *"ነቢዩ"ﷺ" ሲያገቧ የስድስት ዓመት ነበረች፥ የዘጠኝ ዓመት እንስት ሲሆናት ደረሱባት"*። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم تَزَوَّجَهَا وَهْىَ بِنْتُ سِتِّ سِنِينَ

ሥነ-ጋብቻ ጥናትMatrimony" እንደሚያትተው አንዲት እንስት ለዐቅመ-ሐዋህ ለመድረስ ከሚታዩ ምልክቶች አንዱ ሐይድ ማየት ነው። "ሐይድ" حَيْض ማለት "የወር አበባ" ማለት ነው፥ የወር አበባ ላይ ያለች ሴት ደግሞ "ሓኢድ" حَائِض ትባላለች። አንዲት እንስት የወር አበባ ልታይበት የምትችለው አማካኝ ዕድሜ ከ 12-13 ሲሆን እንደየ እንስቷ ሁኔታ ከ 12 በታች እስከ 9 ቶሎ ሊመጣ አሊያም ከ 13 በላይ እስከ 16 ሊዘገይ ይችላል። በኢሥላማዊ መዛግብትም አጥ-ጦበሪን ጨምሮ እንደተዘገበው የአንዲት እንስት የወር አበባ የምታየበት ትንሹ እድሜ ዘጠኝ መሆኑ እንዲህ ተዘግቧል፦
አልካፊ ፊ ፊቅህ ኢብነ ሀንበል፣ ጥራዝ 1፣ ገጽ 74፣ ሸርህ አል– ዑምዳ፣ ጥራዝ 1፣ ገጽ 480
*"ትንሹ የሴት ልጅ የወር አበባ የምታይበት እድሜ ዘጠኝ ዓመት ነው"*።
የጋብቻ ጊዜ በጥንታዊ ጊዜ፣ በዘመናዊ ጊዜ፣ በድኅረ-ዘመናዊ ጊዜ ከትውልድ ወደ ትውልድ፥ ከባህል ወደ ባህል ይለያያል። ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ እንዲህ ይላል፦
*“ለጋብቻ ትንሹ የዕድሜ ገደብ በፊት 12 ዓመት አልያም ከዚያም ያነሰ የነበረው ሲሻሻል እና ከፍ ሲል ቆይቶ በአብዛኛው አገሮች አሁን በ15 እና በ21 ዕድሜ መካከል ሆኗል"*፡፡ Encyclopedia Britannica 2006 page 171.
የጋብቻ ጥናት ምሁር ብራውን ዮናታን፦ *"አብዛኛው የጋብቻ ምሁራን ዓኢሻህ በዘጠኝ ዓመቷ ለዐቅመ-ሔዋን ደርሳለች ብለዋል"*።
Brown, Jonathan (2014). Misquoting Muhammad: The Challenge and Choices of Interpreting the Prophet's Legacy. Oneworld Publications. pp. 143–4.

ጋብቻ ማለት በሁለት ተቃራኒ መካከል ያለ ስምምነት ነው፥ አንድ ተባእት አንዲትን እንስት አስገድዶ ማግባት ሐላል አይደለም። ነቢያችንም”ﷺ” ዓኢሻን ሊደርሱባት ሲሉ ፈቃደኝነቷት ጠይቀዋታል፦
4፥19 እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ! *”ሴቶችን ያስገደዳችሁ ኾናችሁ ልትወርሱ ለእናንተ አይፈቀድም”*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا يَحِلُّ لَكُمْ أَن تَرِثُوا النِّسَاءَ كَرْهًا
አል-ሙሥተድረክ አል-ሐኪም ጥራዝ 4 ገጽ 11
ሰዒድ ኢብን ከሲር ከአባቱ አባቱ ከዓኢሻህ "ረ. ዐ." እንዳስተላለፈው፦ *የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" ለአዒሻ እንዲህ አሏት፦ *“በዱንያህ ሆነ በአኺራ የእኔ ባለቤት መሆንን አትፈልጊምን? እርሷም፦ “ወሏሂ እፈልጋለሁ እንጂ” አለች፡፡ እርሳቸውም፦ "አንቺ በዱንያህ ሆነ በአኺራም የእኔ ባለቤቴ ነሽ" አሏት"*፡፡  عن سَعِيدُ بْنُ كَثِيرٍ  عَنْ أَبِيهِ ، قَالَ حَدَّثَتْنَا عَائِشَةُ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهَا أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قال لعائشة -رضي الله عنها-: «أَمَا تَرْضَيْنَ أَنْ تَكُونِي زَوْجَتِي فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ؟» قُلْتُ: بَلَى وَاللَّهِ، قَالَ: «فَأَنْتِ زَوْجَتِي فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ».

ሚሽነሪዎች ዓኢሻህ ለነቢያችን"ﷺ" መዳሯ የሚያንገበግባቸው፣ ልወቅልሽ እና ልቆርቆርልሽ የሚሏት አስብቶ አራጅ እና ቅቤ አንጓች ሆነው እንጂ ለእርሷ አስበው አይደለም። እርሷ ጋብቻውን ወዳ እና ፈቅዳ የገባችበት ጉዳይ ነው፥ ለነቢያችን"ﷺ" ልዩ ፍቅር የነበራት ሴት ነበረች፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 63, ሐዲስ 43
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ *"በማንም ሴት እንደ ኸዲጃህ ቅናት ተሰምቶኝ ዐያውቅም፥ የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" ብዙ ጊዜ ያነሷት ነበር። እኔን ያገቡኝ እርሷ በሞተች በሦስት ዓመቷ ነው፥ ከጌታቸው ዐዘ ወጀል ወይንም ከጂብሪል"ዐ.ሠ." እርሷ በጀነት ጨፌ ሥርፋ እንዳላት ይበሰሩ ነበር"*።   عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ قَالَتْ مَا غِرْتُ عَلَى امْرَأَةٍ مَا غِرْتُ عَلَى خَدِيجَةَ، مِنْ كَثْرَةِ ذِكْرِ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم إِيَّاهَا‏.‏ قَالَتْ وَتَزَوَّجَنِي بَعْدَهَا بِثَلاَثِ سِنِينَ، وَأَمَرَهُ رَبُّهُ عَزَّ وَجَلَّ أَوْ جِبْرِيلُ ـ عَلَيْهِ السَّلاَمُ ـ أَنْ يُبَشِّرَهَا بِبَيْتٍ فِي الْجَنَّةِ مِنْ قَصَبٍ‏.‏

በሞተችው ሚስታቸው በኸዲጃህ የምትቀናው ፍቅር ካልሆነ ምንድን ነው? ዓኢሻህ ከነቢያችን"ﷺ" ጋር የነበራትን መስተጋብር ለምእመናን ጋብቻ አርአያ እንዲሆነ ብዙ ጊዜ ታነሳለች። ለምሳሌ አንዲት እንስት ከባሏ ጋር ከተራክቦ በኃላ በአንድ ገንዳ ውስጥ መታጠብ እንደሚችሉ ለማስተማር እርሷ ከባለቤቷ ከነቢያችን"ﷺ" ጋር ከተራክቦ በኃላ በአንድ ገንዳ ትታጠብ እንደነበር ትናገራለች፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 5, ሐዲስ 3
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"እኔ እና ነቢዩ"ﷺ" አል-ፈረቅ በሚባል አንድ ገንዳ እየቀዳን እንታጠብ ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ كُنْتُ أَغْتَسِلُ أَنَا وَالنَّبِيُّ، صلى الله عليه وسلم مِنْ إِنَاءٍ وَاحِدٍ مِنْ قَدَحٍ يُقَالُ لَهُ الْفَرَقُ‏.‏
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 5, ሐዲስ 16
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"እኔ እና ነቢዩ"ﷺ" ከጀናባህ በኃላ በአንድ ገንዳ እንታጠብ ነበር"*።  عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ كُنْتُ أَغْتَسِلُ أَنَا وَالنَّبِيُّ، صلى الله عليه وسلم مِنْ إِنَاءٍ وَاحِدٍ مِنْ جَنَابَةٍ‏.‏
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 5, ሐዲስ 14
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"እኔ እና ነቢዩ"ﷺ" በአንድ ገንዳ እየቀዳን እንታጠብ ነበር፥ እጆቻችንን በገንዳ ውስጥ ይተካኩ ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ كُنْتُ أَغْتَسِلُ أَنَا وَالنَّبِيُّ، صلى الله عليه وسلم مِنْ إِنَاءٍ وَاحِدٍ تَخْتَلِفُ أَيْدِينَا فِيهِ‏.‏

አንዲት እንስት ከባሏ ጋር በወር አበባዋ ጊዜ መነካካት፣ መብላት እና መጠጣት ወዘተ እንደምትችል ለማስተማር እርሷ ከነቢያችን"ﷺ" ጋር በወር አበባዋ ጊዜ ትነካካ፣ ትበላ እና ትጠጣ ወዘተ እንደነበር ትናገራለች፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 6, ሐዲስ 4
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"ነቢዩ”ﷺ” እኔ የወር አበባ ላይ እያለሁኝ ጭኔ ላይ ተደግፈው ቁርኣን ይቀሩ ነበር"*።  أَنَّ عَائِشَةَ حَدَّثَتْهَا أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم كَانَ يَتَّكِئُ فِي حَجْرِي وَأَنَا حَائِضٌ، ثُمَّ يَقْرَأُ الْقُرْآنَ‏.‏
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 3, ሐዲስ 10
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"የወር አበባ ላይ ሆኜ የአሏህን መልእክተኛ"ﷺ" ጠጉር አጥብ ነበር"*።  عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ كُنْتُ أَغْسِلُ رَأْسَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم وَأَنَا حَائِضٌ
ሡነን ነሣኢ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 279
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"የወር አበባ ላይ ሆኜ የአሏህን መልእክተኛ"ﷺ" ጠጉር አበጥር ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، - رضى الله عنها - قَالَتْ كُنْتُ أُرَجِّلُ رَأْسَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم وَأَنَا حَائِضٌ
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 686
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"እኔ በወር አበባ ጊዜ አጥንት እግጥ ነበር፥ የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ስጋውን ከእኔ ይወስዱና አፌ ያረፈበት ቦታ ላይ አፋቸው በማሳረፍ ይግጡ ነበር። እንደዚሁም የወር አበባ ላይ እያለሁ በእቃ ስጠጣ የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እቃውን ይወስዱና አፌ ያረፈበት ቦታ ላይ አፋቸውን በማሳረፍ ይጠጡ ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ كُنْتُ أَتَعَرَّقُ الْعَظْمَ وَأَنَا حَائِضٌ، فَيَأْخُذُهُ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ فَيَضَعُ فَمَهُ حَيْثُ كَانَ فَمِي وَأَشْرَبُ مِنَ الإِنَاءِ فَيَأْخُذُهُ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ فَيَضَعُ فَمَهُ حَيْثُ كَانَ فَمِي وَأَنَا حَائِضٌ ‏.‏
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 675
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ለእኔ፦ *"ከመሥጂድ ሰሌኑን አምጪልኝ" አሉኝ፥ እርሷም፦ "በወር አበባ ላይ ነኝ" አልኩኝ" አለች። እርሳቸውም፦ "የወር አበባሽ እኮ በእጅሽ ውስጥ አይደለም" አሉ"*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ لِي رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏"‏ نَاوِلِينِي الْخُمْرَةَ مِنَ الْمَسْجِدِ ‏"‏ ‏.‏ فَقُلْتُ إِنِّي حَائِضٌ ‏.‏ فَقَالَ ‏"‏ لَيْسَتْ حَيْضَتُكِ فِي يَدِكِ ‏

አንዲት እንስት ከባሏ ጋር በፆም ጊዜ ከተራክቦ በስተቀር መነካካት፣ መሳሳም እና አብሮ መተኛት ወዘተ እንደምትችል ለማስተማር እርሷ ከነቢያችን"ﷺ" ጋር በፆም ጊዜ ትነካካ፣ ትሳሳም ወዘተ እንደነበር ትናገራለች፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 13, ሐዲስ 89
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ *"በፆም ወር ውስጥ የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ይስሟት ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، - رضى الله عنها - قَالَتْ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يُقَبِّلُ فِي شَهْرِ الصَّوْمِ
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 16, ሐዲስ 79
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ *"የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ፆመኛ እያሉ ከሚስታቸውን አንዷን(ዓኢሻህን) ይስሙ ነበር፥ ከዚያም ደስ ይላት ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، - رضى الله عنها - قَالَتْ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يُقَبِّلُ إِحْدَى نِسَائِهِ وَهُوَ صَائِمٌ ‏.‏ ثُمَّ تَضْحَكُ ‏
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 13, ሐዲስ 83
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ *"የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ፆመኛ እያሉ ሚስታቸውን ይስሙ ነበር፥ ከእናንተ ይልቅ እሳቸው ስሜታቸውን ይቆጣጠሩ ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، - رضى الله عنها أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم كَانَ يُقَبِّلُ وَهُوَ صَائِمٌ وَكَانَ أَمْلَكَكُمْ لإِرْبِهِ

"ስሜታቸውን ይቆጣጠሩ ነበር" የሚለው ኃይለ-ቃል በፆም ጊዜ ተራክቦ ማድረግ ክልክል መሆኑን ለማሳየት ነው። አንዲት እንስት ከባሏ ጋር የጨዋታ ጊዜ ሊኖራት እንደምትችል ለማስተማር እርሷ ከነቢያችን"ﷺ" ጋር የጨዋታ ጊዜ እንደነበራት ትናገራለች፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 15, ሐዲስ 102
አቢ ሠለማህ ከዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደዘገበው፦ "ዓኢሻህ ከነቢዩ"ﷺ" ጋር በጉዞ ላይ ሳለች እንዲህም አለች፦ *"ከነቢዩ"ﷺ" ጋር ሩጫ ተወዳደሩኝ እኔም አሸነፍኳቸው፥ ያሸነፍኳቸው ሳልወፍር በፊት ነበር፡፡ ከወፈርኩ በኃላ ግን ተወዳደርኳቸው አሸነፉኝ። እንዲህም አሉኝ፦ "ብድር መለስኩኝ"*። وَعَنْ أَبِي سَلَمَةَ، عَنْ عَائِشَةَ، رَضِيَ اللَّهُ عَنْهَا أَنَّهَا كَانَتْ مَعَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم فِي سَفَرٍ قَالَتْ فَسَابَقْتُهُ فَسَبَقْتُهُ عَلَى رِجْلَىَّ فَلَمَّا حَمَلْتُ اللَّحْمَ سَابَقْتُهُ فَسَبَقَنِي فَقَالَ ‏ "‏ هَذِهِ بِتِلْكَ السَّبْقَةِ ‏"‏ ‏.‏

እውነት ሚሽነሪዎች እንደሚሉት ዓኢሻህ በነቢያችን"ﷺ" የሥነ-ልቦና እና የተክለ-ሰውነት ጥቃት ደርሶባት ቢሆን ከላይ ያለውን የፍቅር፣ የመተሳሰብ፣ የመግባባት ጊዜ ለአማንያን ይጠቅማል ብላ ትተርክ ነበርን? ነቢያችን"ﷺ" ነቢይ ሆነው በተነሱበት ጊዜ የነበሩ የኢሥላም ጠላት ነቢያችንን"ﷺ"፦ "ጠንቋይ፣ ደጋሚ፣ መተተኛ፣ ዕብድ" ወዘተ ሲሉ በዓኢሻህ እና በእሳቸው መካከል የነበረውን ጋብቻ ለምን አልተቹም? እርሷ ስለ ጋብቻዋ በአሉታዊ መልኩ አንድም ቀን አምርራና አማራ የማታውቀውን ሚሽነሪዎች ዙሪያ ገቡን ሳያዩ ኢሥላምን ለማጠልሸት እና ሙሥሊሙን ለማብሸቅ "አስገድዶ መድፈር" የሚሉት የአእምሮ ስንኩላን ስለሆኑ ነው። ብዙ ጊዜ በጥላቻ የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ሊያጠፉ ይሻሉ፥ ነገር ግን አላህም ብርሃኑን ገላጭ ነው፦
61፥8 *"የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ሊያጠፉ ይሻሉ፡፡ አላህም ከሓዲዎቹ ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን ገላጭ ነው"*፡፡  يُرِيدُونَ لِيُطْفِئُوا نُورَ اللَّهِ بِأَفْوَاهِهِمْ وَاللَّهُ مُتِمُّ نُورِهِ وَلَوْ كَرِهَ الْكَافِرُونَ

አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዐቅመ-ጋብቻ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

65፥4 *"እነዚያም ከሴቶቻቸው ከዐደፍ ያቋረጡት በዒዳቸው ሕግ ብትጠራጠሩ ዒዳቸው ሦስት ወር ነው፡፡ እነዚያም ገና ዐደፍ ያላዩት ዒዳቸው እንደዚሁ ነው፡፡ የእርግዝና ባለቤቶችም ጊዜያቸው እርጉዛቸውን መውለድ ነው"*፡፡ وَاللَّائِي يَئِسْنَ مِنَ الْمَحِيضِ مِن نِّسَائِكُمْ إِنِ ارْتَبْتُمْ فَعِدَّتُهُنَّ ثَلَاثَةُ أَشْهُرٍ وَاللَّائِي لَمْ يَحِضْنَ ۚ وَأُولَاتُ الْأَحْمَالِ أَجَلُهُنَّ أَن يَضَعْنَ حَمْلَهُنَّ

"ዐቅመ-ጋብቻ" ማለት አንድ ተባእት ለዐቅመ-አደም ሲደርስ እና አንዲት እንስት ለዐቅመ-ሐዋህ ስትደርስ ማለት ነው። ለምሳሌ “የቲም” يَتِيم ስንል አጠቃላይ “ወላጅ-አልባ” ማለትም “እናትና አባቱ” ወይም “አባቱን በልጅነቱ በሞት የተነጠቀ ሕፃን” ማለት ነው። የቲሞች እራሳቸው ይችሉ ወይም አይችሉ እንደሆነ ይፈተናሉ፥ ይህም ፈተና ለጋብቻ እስከሚደርሱበት ድረስ ነው፦
4፥6 *"የቲሞችንም ጋብቻን እስከደረሱ ጊዜ ድረስ ፈትኑዋቸው"*፡፡ وَابْتَلُوا الْيَتَامَىٰ حَتَّىٰ إِذَا بَلَغُوا النِّكَاحَ

"ኢዛ" إِذَا ማለት "ጊዜ" ማለት ሲሆን የጊዜ ተውሳከ-ግስ ነው። ጋብቻ የራሱ የሆነ ጊዜ እንዳለው አመላካች ነው፥ ይህም ጊዜ ለማመልከት "ጋብቻን እስከደረሱ" ድረስ በማለት ይናገራል። "በለጉ" بَلَغُوا ማለት "ለጋብቻ በሰሉ" ማለት ነው፥ "በለገ" بَلَغَ ማለት "ለጋብቻ በሰለ" ማለት ሲሆን "በለገት" بَلَغَت ማለት ደግሞ "ለጋብቻ በሰለች" ማለት ነው። "ባሊግ" بَٰلِغ ማለት እራሱ "ዐቅመ-ጋብቻ"Puberty" ማለት ነው፦
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 4፥6
*"ጋብቻን እስከደረሱ ጊዜ" የሚለውን ሙጃሂድ፦ "ለዐቅመ-ጋብቻ ነው" ብሏል፥ ዐበይት ምሁራን፦ "ለዐቅመ-ጋብቻ" ለጋዎች ኢሕቲላም ሲኖራቸው ነው" ብለዋል። አቢ ዳውድ በሡናው እንደዘገበው፥ ዐሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "የአላህ መልዕክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "ከዐቅመ-ጋብቻ በኃላ የቲምነት የለም"*።
( حتى إذا بلغوا النكاح ) قال مجاهد : يعني : الحلم . قال الجمهور من العلماء : البلوغ في الغلام تارة يكون بالحلم ، وهو أن يرى في منامه ما ينزل به الماء الدافق الذي يكون منه الولد . وقد روى أبو داود في سننه عن أمير المؤمنين علي بن أبي طالب ، رضي الله عنه ، قال : حفظت من رسول الله صلى الله عليه وسلم : " لا يتم بعد احتلام
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 18, ሐዲስ 12
ዐሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ እንደተረከው፦ "የአላህ መልዕክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"ከዐቅመ-ጋብቻ በኃላ የቲምነት የለም"*። قَالَ عَلِيُّ بْنُ أَبِي طَالِبٍ حَفِظْتُ عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ لاَ يُتْمَ بَعْدَ احْتِلاَمٍ

"ዐቅመ-ጋብቻ" አካል ተራክቦ ለማድረግ ሲበስል ነው፥ ከዐቅመ-ጋብቻ በኃላ የቲምነት ስለሌለ የቲሞች እራሳቸው እንዲችሉ ይፈተናሉ። "ኢሕቲላም" احْتِلاَم ማለት አንድ ልጅ ወይም አንዲት ልጂት ተራክቦ ለማድረግ የሚኖራቸው ፈሳሽ ነው። ይህ ፈሳሽ እስኪመጣ ድረስ ለዐቅመ-ጋብቻ ስላልደረሱ የሚሠሩት ሥራ አይመዘገብም፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 40, ሐዲስ 48
ዓኢሻህ "ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "የአላህ መልዕክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"ብዕር ከሦስት ሰዎች ተነስቷል። እነርሱም፦ የተኛ ሰው እስኪነሳ ድረስ፣ ዕብደ ወደ ዐቅሉ እስኪመለስ ድረስ፣ ልጅ እስኪጎሎብት ድረስ"*። عَنْ عَائِشَةَ، رضى الله عنها أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ رُفِعَ الْقَلَمُ عَنْ ثَلاَثَةٍ عَنِ النَّائِمِ حَتَّى يَسْتَيْقِظَ وَعَنِ الْمُبْتَلَى حَتَّى يَبْرَأَ وَعَنِ الصَّبِيِّ حَتَّى يَكْبَرَ ‏

በእንቅልፍ ልብ፣ በዕብደት እና በእንጭጭነት የሚደረግ ሥራ መላእክት አይመዘግቡትም። አንድ ሕጻን ለዐቅመ-አደም ከደረሰ የሰው ቤት ዘው ብሎ አይገባም፥ ከዚያ ይልቅ አንኳክቶ ያስፈቅዳል፦
24፥59 *"ከእናንተም ሕፃናቶቹ አቅመ አዳምን በደረሱ ጊዜ እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት እንዳስፈቀዱ ያስፈቅዱ"*፡፡ وَإِذَا بَلَغَ الْأَطْفَالُ مِنكُمُ الْحُلُمَ فَلْيَسْتَأْذِنُوا كَمَا اسْتَأْذَنَ الَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ

አሁን እዚህ አንቀጽ ላይ "ኢዛ" إِذَا የሚለው የጊዜ ተውሳከ-ግስ የዐቅመ-ጋብቻ ጊዜ አመላካች ነው፥ ይህንን ዐቅመ-ጋብቻ ለማመልከት "በለገ" بَلَغَ የሚል የግስ መደብ ይጠቀማል።
አንዲት እንስት ለዐቅመ-ሐዋህ የመድረሷ የመጀመሪያው እና ዐቢይ ምልክት አድሬን-አርክ"adrenarche" አካሏ ለተራክቦ ዝግጁ ሲሆን እንዲሁ ጡቷ ሲያጎጠጉጥ ቴል-አርክ"thelarche" እና ብብቷና ብልቷ አካባቢ ጸጉር መብቀል ፑብ-አርክ"Pubarche" ሲጀምር የምታመነጨው ፈሳሽ"Vaginal lubrication" እንጂ የወር አበባ አይደለም፥ የወር አበባ ማየት አንዲት ሴት ለዐቅመ-ሐዋህ መድረሷን ከሚያሳዩ ሁለተኛ እና ንዑስ ምልክት ዕንቁላል ማምረት ጎናድ-አርክ"gonadarche" እንዲሁ የወር አበባ ደም ሜን-አርክ"menarche" ነው። አንዲት ሴት ስታርጥ የወር አበባ ይቋረጣል፥ ያኔ የምታመነጨው ፈሳሽ ያለ የወር አበባ ተራክቦ ማድረግ ትችላለች። ምክንያቱም ተራክቦ ለማድረግ የወር አበባ ብቻውን መስፈት አይደለም፥ የወር አበባ ለፅንስ እንጂ ለተራክቦ መስፈት አይደለም፦
65፥4 *"እነዚያም ከሴቶቻቸው ከዐደፍ ያቋረጡት በዒዳቸው ሕግ ብትጠራጠሩ ዒዳቸው ሦስት ወር ነው፡፡ እነዚያም ገና ዐደፍ ያላዩት ዒዳቸው እንደዚሁ ነው፡፡ የእርግዝና ባለቤቶችም ጊዜያቸው እርጉዛቸውን መውለድ ነው"*፡፡  وَاللَّائِي يَئِسْنَ مِنَ الْمَحِيضِ مِن نِّسَائِكُمْ إِنِ ارْتَبْتُمْ فَعِدَّتُهُنَّ ثَلَاثَةُ أَشْهُرٍ وَاللَّائِي لَمْ يَحِضْنَ ۚ وَأُولَاتُ الْأَحْمَالِ أَجَلُهُنَّ أَن يَضَعْنَ حَمْلَهُنَّ

“ዒዳህ” عِدَّة ማለት ሁለት ጥንዶች ከተጋቡ በኃላ ተራክቦ አድርገው ከዚያም አለመግባባት ቢፈጠር ፍቺ ለማድረግ ቢያስቡ ቅድሚያ ነፍሰ-ጡር መሆኗን ለማረጋገጥ የሚቆይበት የሦስት ወር ጊዜ ቆይታ ነው። "ዐደፍ" ለሚለው የገባው ቃል "መሒድ" مَحِيض ሲሆን "የወር አበባ" ማለት ነው። አንድ ወንድ ከዐደፍ ያቋረጠች ማለትም ያረጠች ሴት ለመፍታት ምናልባት አርጣለች ተብሎ እግዝና ስለሚከሰት የሦስት ወር ጊዜ ይኖራታል። አንዲት ሴት ልጅ ለዐቅመ-ሐዋህ ስደርስ ግንኙነትን ሲታሰብ ወይም ሲፈለግ የሚወጣ ያዝ የሚያደርግና የሚያጣብቅ ቀለም አልባ እና ሽታ አልባ ቀጭን ፈሳሽ"nocturnal emission" አላት፥ ነገር ግን ይህ ፈሳሽ ኖሮ የወር አበባዋ ሳይመጣ ብዙ ጊዜ ሊቆይ ይችላል። ይህንን የወር አበባ ያላዩ ሴቶች መሃል ላይ እንቁላል ማምረት ችለው እርግዝና ሊከሰት ስለሚችል ሦስት ወር ባል የማይፈታበት ጊዜ አለ፦
2፥235 *የተጻፈውም ዒዳህ ጊዜውን እስከሚደርስ ድረስ ጋብቻን ለመዋዋል ቁርጥ አሳብ አታድርጉ፡፡ አላህም በነፍሶቻችሁ ያለውን ነገር የሚያውቅ መኾኑን ዕወቁ፤ ተጠንቀቁትም፡፡ አላህም መሓሪ ታጋሽ መኾኑን ዕወቁ"*፡፡ وَلَا تَعْزِمُوا۟ عُقْدَةَ ٱلنِّكَاحِ حَتَّىٰ يَبْلُغَ ٱلْكِتَٰبُ أَجَلَهُۥ ۚ وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ يَعْلَمُ مَا فِىٓ أَنفُسِكُمْ فَٱحْذَرُوهُ ۚ وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ حَلِيمٌۭ

እንግዲህ ዐቅመ-ሐዋህ ጅማሬው አካላዊ ሽግግር"physical transition" የሆኑት ጡቷ ማጎጥጎጥ፣ ብብትና ብልት አካባቢ ጸጉር ማብቀል፣ የተራክቦ ፈሳሽ ማመንጨት ሲሆን ቀጣዩ የእንቁላል እድገት"ovarian development" ልጅ ለመፅነስ መደላድል ነው፥ እንቁላሉ የወንድ የዘር ሕዋስ ካላገኘ የወር አበባ ሆኖ ይወጣል። ይህንን በቅጡ ያልተረዱ ሚሽነሪዎች ዐይናቸውን በማንሸዋረር "የወር አበባ ያላየች ሴት" የሚለውን "ለዐቅመ-ሐዋህ ያልደረሰች" ብለው በማውረግረግ ኢሥላምን ሊዘልፉ ይፈልጋሉ፥ ይህ የደፈረሰ መረዳት ከላይ ያለውን ተስተምህሮት ጥልልና ጥንፍፍ አድርጎ ካለማየት የመጣ የተሳከረ መረዳት ነው። በኢሥላም ምንም ነገር መጉዳት አይፈቀድም፥ ጉዳትም ካለ በቂሷስ ይፈረዳል እንጂ ጉዳት አይመለስም፦ 
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 13, ሐዲስ 34
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ የአላህ መልዕክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ *"መጉዳት የለም፥ ጉዳትንም መመለስ የለም"*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ لاَ ضَرَرَ وَلاَ ضِرَارَ ‏”‏ ‏.‏

አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የሰይጣን አሳብ ምን ነበር?

A. ኢየሱስ እንዳይሰቀል ነበር፦
ማቴዎስ 16፥22 ጴጥሮስም ወደ እርሱ ወስዶ፦ አይሁንብህ ጌታ ሆይ፤ ይህ ከቶ አይደርስብህም፡ ብሎ ሊገሥጸው ጀመረ። እርሱ ግን ዘወር ብሎ ጴጥሮስን፦ ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል" አለው።

B. ኢየሱስ እንዲሰቀል ነበር፦
ሉቃስ 22፥3 ሰይጣንም ከአሥራ ሁለቱ ቍጥር አንዱ በነበረው የአስቆሮቱ በሚባለው በይሁዳ ገባ፤ ሄዶም እንዴት አሳልፎ እንዲሰጣቸው ከካህናት አለቆችና ከመቅደስ አዛዦች ጋር ተነጋገረ።

የቱ ነው ትክክል?

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom
ሶለዋት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

33፥56 አላህ እና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ

አንድ ቃል ቋንቋዊ ፍቺው "መዕና ሉገዊይ" مَعْنًى لُغَوِيّ ሲባል ሸሪዓዊ ፍቺው ደግሞ "መዕና ሸርዒይ" مَعْنًى شَرْعِيّ ይባላል፥ አንድ ቃል ቋንቋዊ ፍቺው ሆነ ሸሪዓዊ ፍቺው ብዙ ትርጉም ይይዛል። ለምሳሌ፦ "በዐሰ" بَعَثَ ማለት "ላከ" ማለት ነው፦
25፥41 ባዩህም ጊዜ ያ አላህ መልእክተኛ አድርጎ የላከው ይህ ነውን እያሉ መሳለቂያ እንጂ ሌላ አያደርጉህም፡፡ وَإِذَا رَأَوْكَ إِن يَتَّخِذُونَكَ إِلَّا هُزُوًا أَهَـٰذَا الَّذِي بَعَثَ اللَّهُ رَسُولًا

እዚህ አንቀጽ ላይ "ላከ" ለሚለው የገባው ቃል "በዐሰ" بَعَثَ ሲሆን "አርሠለ" أَرْسَلَ ማለት ነው፥ ነገር ግን "በዐሰ" بَعَثَ ማለት "ቀሰቀሰ" ወይም "አስነሳ" ማለት ነው፦
36፥52 «ወይ ጥፋታችን! ከመኝታችን ማን ቀሰቀሰን? ይህ ያ አዛኙ ጌታ በእርሱ የቀጠረን መልክተኞቹም እውነትን የነገሩን ነው» ይላሉ፡፡ قَالُوا يَا وَيْلَنَا مَن بَعَثَنَا مِن مَّرْقَدِنَا ۜ ۗ هَـٰذَا مَا وَعَدَ الرَّحْمَـٰنُ وَصَدَقَ الْمُرْسَلُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ቀሰቀሰ" ለሚለው የገባው ቃል "በዐሰ" بَعَثَ ሲሆን "አስነሳ" ማለት ነው፥ ስለዚህ "አላህ መልእክተኛ አድርጎ የቀሰቀሰው ይህ ነው" ወይም "ወይ ጥፋታችን! ከመኝታችን ማን ላከን" ብለን ብናስቀምጠው ትርጉም አልባ ነው። ሌላ ምሳሌ፦ "ሠበሐ" سَبَّحَ ማለት "አሞገሰ" "አመሰገነ" "አጠራ" ማለት ነው፦
21፥20 በሌሊት እና በቀንም "ያጠሩታል"፤ አያርፉም፡፡ يُسَبِّحُونَ اللَّيْلَ وَالنَّهَارَ لَا يَفْتُرُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ያጠሩታል" ለሚለው የገባው ቃል "ዩሠቢሑነ" يُسَبِّحُونَ ሲሆን ሥርወ-ቃሉ "ሠበሐ" سَبَّحَ ነው፥ ነገር ግን "ሠበሐ" سَبَّحَ ማለት "ዋኘ" ወይም "ተንቀሳቀሰ" ማለት ነው፦
21፥33 እርሱም ሌሊትንና ቀንን፣ ፀሐይንና ጨረቃንም የፈጠረ ነው፡፡ ሁሉም በፈለካቸው ውስጥ "ይዋኛሉ"፡፡ وَهُوَ الَّذِي خَلَقَ اللَّيْلَ وَالنَّهَارَ وَالشَّمْسَ وَالْقَمَرَ ۖ كُلٌّ فِي فَلَكٍ يَسْبَحُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ይዋኛሉ" ለሚለው የገባው ቃል "የሥበሑነ" يَسْبَحُونَ ሲሆን ሥርወ-ቃሉ "ሠበሐ" سَبَّحَ ነው፥ ስለዚህ "በሌሊት እና በቀንም "ይዋኙታል" ወይም "ሁሉም በፈለካቸው ውስጥ "ያጠራሉ" ብለን ብናስቀምጠው ትርጉም አልባል ነው። አንድ ቃል ብዙ ትርጉም እንዳለው እዚህ ድረስ ከተግባባን ዘንዳ ይህ በነሕው ደርሥ "ኢሥሙል ሙሽተሪክ" ይባላል፥ "ኢሥሙል ሙሽተሪክ" اِسْم المُشْتَرِك ማለት "ተመሳሳይ ቃል ግን የተለያየ ትርጉም ያለው አሳብ"Homonym" ነው። "ሶላ" صَلَّىٰ ማለት "ሰገደ" "ጸለየ" ማለት ነው፦
87፥15 የጌታውንም ስም ያወሳ እና "የሰገደ"፡፡ وَذَكَرَ اسْمَ رَبِّهِ فَصَلَّىٰ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ሰገደ" ለሚለው የገባው ቃል "ሶላ" صَلَّىٰ ሲሆን የአምልኮ ክፍል የሆነውን ሶላት ያመላክታል፥ ነገር ግን "ሶላ" صَلَّىٰ  ማለት "ባረከ" ማለት ነው፦
33፥56 አላህ እና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ

"የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ" ለሚለው የገባው ቃል "ዩሶሉነ" يُصَلُّونَ ሲሆን "ይባርካሉ" ማለት ነው፥ ዐረቢኛ ላይ ተመሳሳይ ቃል ቢኖረው እንኳን ተመሳሳይ አሳብ እና ትርጉም አለው ማለት አይደለም። የአንድን ቃል አማራጭ ትርጉም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት አረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ ቅቡል ነው፥ መታየት ያለበት ቃሉ ብቻ ሳይሆን ቃሉ የወከለው አሳብም ጭምር ነው፥ አሏህ እና መላእክቱ ሶለዋትን የሚያወርዱት በነቢያችን"ﷺ" ብቻ ሳይሆን በአማኞችም ላይ ጭምር ነው፦
33፥43 እርሱ ያ “በእናንተ “ላይ” እዝነትን” የሚያወርድ ነው፡፡ መላእክቶቹም እንደዚሁ፡፡ هُوَ الَّذِي يُصَلِّي عَلَيْكُمْ وَمَلَائِكَتُهُ

"እዝነትን የሚያወርድ" ለሚለው የገባው ቃል በተመሳሳይ "ዩሶሊ" يُصَلِّي ነው፥ አንድ አማኝ በነቢያችን"ﷺ" ላይ ሶለዋት ሲያወርድ አሏህ በእርሱ ላይ አሥር ሶለዋት ያወርድለታል፦
33፥56 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 3, ሐዲስ 33
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ”በእኔ ላይ ሶለዋት ያወረደ አሏህ በእርሱ ላይ አሥር ሶለዋት ያወርድለታል”። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَنْ صَلَّى عَلَىَّ صَلاَةً صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ بِهَا عَشْرًا ‏
እንደ ሚሽነሪዎች መጃጃል "አሏህ እና መላእክቱ ወደ ነቢዩ ይጸልያሉ ወይም ለነቢዩ ይሰግዳሉ" ካሉ አሏህ እና መላእክቱ ወደ አማኞች ሶለዋት ማውረዳቸውን ሲያውቁ "ወደ አማኞች ይጸልያሉ ወይም ለአማኞች ይሰግዳሉ" ብለው ሊረዱት ነው? "አንድ ቃልን ለሁለት የተለያዩ ነገሮችን የሚውለውን"two different things by the same word" አንድ ነገር አርጎ መውሰድ "አሻሚ ሕፀፅ"fallacy of equivocation" ነው። ለምሳሌ፦
premise 1
Since only man is rational.
premise 2
And no woman is a man.
conclusion
Therefore, no woman is rational.

ብሎ መተርጎም አሻሚ ሕፀፅ ነው፥ በ 1ኛው ነጥብ "Man" የተባለው "ሰው"human" ሲሆን በ 2ኛው "Man" የተባለው "ወንድ"male" ነው፥ ስለዚህ አንድ ቃልን ለሁለት የተለያዩ ነገሮችን ወክሎ የሚውለውን በተቃራኒው "Man" የሚለውን "ወንድ" ብቻ ብለን ተርጉመን፦ "ወንድ ብቻውን ዐቅለኛ ነው፣ ሴት ወንድ አይደለችም፣ ስለዚህ ሴት ዐቅለኛ አይደለችም" ብሎ መረዳት በሥ-አመክንዮ ሙግት አሻሚ ሕፀፅ ነው። በተመሳሳይም "ሶላ" صَلَّىٰ ማለት "ባረከ" ማለትም ሆኖ ሳለ "ሰገደ "ጸለየ" ማለት ብቻ አርጎ መረዳት ክፉኛ ተፋልሶ"fallacy" ነው፦  
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 118
ጃቢር ኢብኑ ዐብደሏህ እንደተረከው፦ "አንዲት ሴት ለነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አለች፦ "በእኔ ላይ እና በባለቤቴ ላይ ሶላዋት አውርዱ" ነቢዩም"ﷺ"፦ "አሏህ በአንቺ ላይ እና በባለቤትሽ ላይ ሶላዋት ያውርድ" አሉ። عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ، أَنَّ امْرَأَةً، قَالَتْ لِلنَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم صَلِّ عَلَىَّ وَعَلَى زَوْجِي ‏.‏ فَقَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْكِ وَعَلَى زَوْجِكِ ‏"‏ ‏.‏

"ሶላ" صَلَّىٰ ማለት "ባረከ" ማለት ባይሆን ኖሮ ባርኩኝ ሲባሉ አሏህ ይባርክሽ ይሉ ነበር? ይህ መደበኛ ሕፀፅ"formal fallacy" ያለበት ኢ-ምንጨታዊ ሙግት"inductive argument" ነው፥ ምክንያቱም ሙግቱ ድምዳሜ ለማጽናት እክል ያጋጠመው ስለሆነ ነው። ቅሉ እና ጥቅሉ ግን በዚህ ዐውድ ላይ "ሶለዋት" صَلَوَات የሚለው ቃል "በረካት" بَرَكَات የሚለውን ቃል ተክቶ የመጣ ነው፥ አባሪ ናሙና እስቲ እንመልከት፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 60, ሐዲስ 48
አቡ ሑመይድ አሥ-ሣዒዲይ”ረ.ዐ” እንደተረከው፦ "ሰዎች፦ “የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” ሆይ! በእርሶ ላይ እንዴት ሶለዋት እናውርድ? አሉ፥ የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “አሏህ ሆይ! ሶለዋትን በኢብራሂም ቤተሰብ ላይ እንዳወረድክ ሶለዋትን በሙሐመድ፣ በባልተቤቶቹ እና በዝርዮቹ ላይ አውርድ! በረካትን በኢብራሂም ቤተሰብ ላይ እንዳወረድክ በሙሐመድ፣ በባልተቤቶቹ እና በዝርዮቹ ላይ አውርድ! አንተ የተመሰገንክ እና የተከበርክ ነህ" በሉ። أَخْبَرَنِي أَبُو حُمَيْدٍ السَّاعِدِيُّ ـ رضى الله عنه ـ أَنَّهُمْ قَالُوا يَا رَسُولَ اللَّهِ كَيْفَ نُصَلِّي عَلَيْكَ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ قُولُوا اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَأَزْوَاجِهِ وَذُرِّيَّتِهِ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، وَبَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَأَزْوَاجِهِ وَذُرِّيَّتِهِ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ ‏”‌‏.‏

ምን ትፈልጋለህ? እዚህ ዐውድ ላይ “ሶለይተ” صَلَّيْتَ የሚለው ቃል “ባረክተ” بَارَكْتَ በሚል ተለዋዋጭ ቃል መምጣቱ በራሱ ሶለዋት በረካት መሆኑን ያሳያል፥ አሏህ ሶለዋት የሚያወርደው በነቢያችን”ﷺ” ብቻ ሳይሆን በባልተቤቶቻቸው ላይ እና በዝርያወቻቸው ላይ ጭምር መሆኑ በራሱ ሶለዋት ቡራኬን ያሳያል።
በተጨማሪም “ወደ” የሚለው መስተዋድድ “ኢላ” إِلَى ሲሆን ለቡራኬ ጥቅም ላይ አልዋለም፥ ለቡራኬ የዋለው መስተዋድድ “ዐላ” عَلَى ማለትም “ላይ” ነው። “ላይ” ደግሞ ለሰላም፣ ለእዝነት እና ለበረከት የሚውል መስተዋድድ ነው፦
11፥73 «ከአላህ ትዕዛዝ ትደነቂያለሽን የአላህ ራህመት እና በረካት በእናንተ እና በኢብራሂም ቤተሰቦች “ላይ” ይሁን! እርሱ ምስጉን ለጋስ ነውና» አሉ፡፡ قَالُوا أَتَعْجَبِينَ مِنْ أَمْرِ اللَّهِ ۖ رَحْمَتُ اللَّهِ وَبَرَكَاتُهُ عَلَيْكُمْ أَهْلَ الْبَيْتِ ۚ إِنَّهُ حَمِيدٌ مَّجِيدٌ
11፥48 «ኑሕ ሆይ! ከእኛ በሆነ ሰላም እና በረካት በአንተ “ላይ” እና አንተም ጋር ባሉት ሕዝቦች “ላይ” በሆኑ የተጎናጸፍክ ሆነህ ውረድ፡ قِيلَ يَا نُوحُ اهْبِطْ بِسَلَامٍ مِّنَّا وَبَرَكَاتٍ عَلَيْكَ وَعَلَىٰ أُمَمٍ مِّمَّن مَّعَك

ስለዚህ "በነቢዩ ላይ" የሚለውን "ወደ ነቢዩ" ወይም "ለነቢዩ" ብሎ መረዳት ጥራዝ ጠለቅ መረዳት ሳይሆን ጥራዝ ነጠቅ መረዳት ነው፦
108፥2 ስለዚህ "ለ-ጌታህ ስገድ" ሰዋም፡፡ فَصَلِّ لِرَبِّكَ وَانْحَرْ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ስገድ" ለሚለው የገባው የግሥ መደብ "ሶል" صَلِّ ሲሆን ለአሏህ የሚቀርብ የአምልኮ ክፍል የሆነውን ሶላት የሚያመለክት ነው፥ የገባውም መስተዋድድ "ሊ" لِ እንጂ "ዐላ عَلَى አይደለም። ሆን ብሎ ማጣመም ዋጋ ያስከፍላል፥ የቁያማህ ቀንም ያስጠይቃል። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

"አሏሁመ ሶሊ ዐላ ሙሐመድ ወአሊ ሙሐመድ" ٱللّٰهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَآلِ مُحَمَّدٍ

"ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሠለም"  صَلَّى ٱللَّٰهُ عَلَيْهِ وَسَلَّم

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አድመኝነት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

3፥54 “እነርሱም አደሙ አላህም አድማቸውን መለሰባቸው። አላህም ከአድመኞች ሁሉ በላጭ ነው”፡፡ وَمَكَرُوا وَمَكَرَ اللَّهُ ۖ وَاللَّهُ خَيْرُ الْمَاكِرِينَ

አምላካችን አሏህ ከእስራኤል ልጆች እነዚያ የካዱት ዒሣን ሊገሉት ሲማከሩ፣ ሲያቅዱ፣ ሲያሴሩ እና ሲያድሙ በአሸናፊነቱ እና በጥበቡ አከሸፈባቸው፥ አሏህ ምክራቸውን፣ ዕቅዳቸውን፣ ሴራቸውን፣ ተንኮላቸውን እና አድማቸው ዒሣን ወደ ራሱ በመውሰድ መለሰባቸው፦
3፥54 “እነርሱም አደሙ አላህም አድማቸውን መለሰባቸው፡፡ አላህም ከአድመኞች ሁሉ በላጭ ነው”፡፡ وَمَكَرُوا۟ وَمَكَرَ ٱللَّهُ ۖ وَٱللَّهُ خَيْرُ ٱلْمَٰكِرِينَ

“መከሩ” مَكَرُوا۟ ማለት “አሳሳቱ” ማለት ሳይሆን “መከሩ” “ዐቀዱ” “አሴሩ” “አደሙ” ማለት ነው፥ አሏህም ዒሣን ለመግደል የተማከሩትን ምክር፣ ያቀዱትን ዕቅድ፣ ያሴሩትን ሴራ፣ ያደሙትን አድማ ወደ ራሱ በመውሰድ አከሸፈባቸው፥ አሏህም ከአድመኞች ሁሉ በላጭ ነው። “አድመኞች” ለሚለው የገባው ቃል “ማኪሪን” مَٰكِرِين ሲሆን “መካሪዎች” “አቃጂዎች” “ተንኮለኞ” “ሴረኞች” እና “አድመኞች” ማለት ነው፥ እዚህ አንቀጽ ላይ “ማኪሪን” مَٰكِرِين የተባሉት ከእስራኤል ልጆች እነዚያ የካዱት ዒሣን ሊገሉት ሲያሴሩ የነበሩት ናቸው። አሏህ ከእነዚህ ሴረኞች ሁሉ በላጭ ነው፥ ለምሳሌ እነዚያን የመካ ከሃድያን ነቢያችንን”ﷺ” ሊያስሩ ወይም ሊገሉ ወይም ከመካ ሊያወጡ በእሳቸው ላይ በመከሩ ጊዜ አሏህ ምክራቸውን መልሶባቸዋል፦
8፥30 እነዚያም የካዱት ሊያስሩህ ወይም ሊገድሉህ ወይም ከመካ ሊያወጡህ በአንተ ላይ ”በመከሩብህ” ጊዜ አስታውስ፡፡ ”ይመክራሉም” አላህም ”ተንኮላቸውን ይመልስባቸዋል”፡፡ አላህም ”ከመካሪዎቹ ሁሉ በላይ ነው”፡፡ وَإِذْ يَمْكُرُ بِكَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لِيُثْبِتُوكَ أَوْ يَقْتُلُوكَ أَوْ يُخْرِجُوكَ ۚ وَيَمْكُرُونَ وَيَمْكُرُ ٱللَّهُ ۖ وَٱللَّهُ خَيْرُ ٱلْمَٰكِرِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ “መከሩ” ለሚለው የገባው ቃል “የምኩሩ” يَمْكُرُ መሆኑን እና “ይመክራሉ” ለሚለው የገባው ቃል “የምኩሩነ” يَمْكُرُونَ እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል። “መክር” مَكْر ማለት “ምክር” “ዕቅድ” “ሴራ” “ደባ” “ተንኮል” ማለት ነው፥ መላእክት ሰዎች በሚስጥር የሚመሳጠሩትን ምክር ሰምተም ይጽፋሉ፦
10፥21 “አላህ ቅጣተ ፈጣን ነው፥ «መልክተኞቻችን የምትመክሩትን “ምክር” በእርግጥ ይጽፋሉ» በላቸው”፡፡ قُلِ اللَّهُ أَسْرَعُ مَكْرًا ۚ إِنَّ رُسُلَنَا يَكْتُبُونَ مَا تَمْكُرُونَ

ወደ ባይብል ስንመጣ ክርስቲያኖች ወደ ራሳቸው የሚያስጠጉበት ጳውሎስ አድመኝነት "የሥጋ ሥራ" እንደሆነ ተናግሯል፦
ገላትያ 5፥20 መዳራት፥ ጣዖትን ማምለክ፥ ምዋርት፥ ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት።

እዚህ አንቀጽ ላይ "አድመኝነት" ብቻ ሳይሆን "ቁጣ" እራሱ የሥጋ ሥራ እንደሆነ ከተገለጸ እግዚአብሔር ቁጠኛ ሆኖ ይቆጣል፥ በማይታዘዙት ላይ የእርሱ ቁጣ ይመጣል፦
መዝሙር 95፥11 ወደ ዕረፍቴም እንዳይገቡ፡ "በቁጣዬ" ማልሁ።
ዘዳግም 1፥34 እግዚአብሔርም የቃላችሁን ድምፅ ሰምቶ "ተቆጣ"።
ሮሜ 9፥22 ነገር ግን እግዚአብሔር "ቍጣውን" ሊያሳይ ኃይሉንም ሊገልጥ ወዶ።
ኤፌሶን 5፥6 ከዚህ የተነሣ በማይታዘዙት ልጆች ላይ "የእግዚአብሔር ቁጣ" ይመጣልና።

"ቁጣ" የሥጋ ሥራ ከሆነ እግዚአብሔር የሥጋ ሥራ እየሠራ ነውን? የሥጋ ሥራ የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት የማይወርሱ ከሆነ እግዚአብሔር መቆጣቱ እና ቁጠኛ መሆኑን ግምት ውስጥ አስገቡት፦
ገላትያ 5፥21 እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።

በሰፈሩት ቁናህ መሰፈር ይልኩካል እንደዚህ ነው። አሏህ ማደሙ የሥጋ ሥራ ነው ካላችሁ እግዚአብሔር መቆጣቱስ የሥጋ ሥራ አይደለምን? አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ምዕራባውያን ከአንድ በላይ ጋብቻን ይከለክሉና ከአንድ በላይ ዝሙትን ይፈቅዳሉ፥ ምዕራባውያን የመናገር ነጻነት በሚል ብሒል የፈለከውን አሳብ ማንቋሸሽ እና መተቸት ትችላለክ ይሉክና የሶዶማውያንን እሳቤ ካንቋሸሽክ እና ከተቸክ ዘብጥያ ያወርዱካል።
ድንቄም ነጻነት!

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom
የማንን ክብር?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

5፥17 እነዚያ አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَّقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ

ከፈሪሳውያንም ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ ኢየሱስ ምልክቶች የሚያደርገው አምላክ ከእርሱ ጋር ስላለ እንደሆነ እና መምህር ሆኖ የመጣው ከአምላክ ዘንድ እንደሆነ ተናግሯል፦
ዮሐንስ 3፥2 እርሱም በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ፦ መምህር ሆይ! አምላክ ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ የሚችል የለምና፥ መምህር ሆነህ ከአምላክ ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን" አለው። οὗτος ἦλθεν πρὸς αὐτὸν νυκτὸς καὶ εἶπεν αὐτῷ Ῥαββεί, οἴδαμεν ὅτι ἀπὸ Θεοῦ ἐλήλυθας διδάσκαλος· οὐδεὶς γὰρ δύναται ταῦτα τὰ σημεῖα ποιεῖν ἃ σὺ ποιεῖς, ἐὰν μὴ ᾖ ὁ Θεὸς μετ’ αὐτοῦ.

ይህ ከአምላክ የተላከ መምህር ይህን ያህል ምልክት በአይሁዳውያን ፊት ምንም ቢያደርግ በእርሱ አላመኑም፦
ዮሐንስ 12፥37 ነገር ግን ይህን ያህል ምልክት በፊታቸው ምንም ቢያደርግ በእርሱ አላመኑም። Τοσαῦτα δὲ αὐτοῦ σημεῖα πεποιηκότος ἔμπροσθεν αὐτῶν οὐκ ἐπίστευον εἰς αὐτόν,

የዮሐንስ ጸሐፊ ይህን ያህል ምልክት በፊታቸው ምንም ቢያደርግ በእርሱ ያላመኑበትን ምክንያት በኢሳይያስ ላይ እንደተነገረ ይናገራል፦
ዮሐንስ 12፥38 ነቢዩ ኢሳይያስ፦ "ጌታ ሆይ! ማን ምስክርነታችንን አመነ? የጌታ ክንድ ለማን ተገለጠ? ብሎ የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው። ἵνα ὁ λόγος Ἡσαΐου τοῦ προφήτου πληρωθῇ ὃν εἶπεν Κύριε, τίς ἐπίστευσεν τῇ ἀκοῇ ἡμῶν; καὶ ὁ βραχίων Κυρίου τίνι ἀπεκαλύφθη;

እዚህ ዐውድ ላይ "ጌታ ሆይ" እና "ጌታ" የተባለው አብ ሲሆን እንደ ጸሐፊው "የጌታ ክንድ" ደግሞ ወልድ ነው፥ የግሪክ ሰፕቱአጀንት ላይ፦ "ጌታ ሆይ! ማን ምስክርነታችንን አመነ? የጌታ ክንድ ለማን ተገለጠ?" ሲል የዕብራይስጥ ማሶሬት ደግሞ፦ "የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል? የያህዌስ ክንድ ለማን ተገልጦአል?" የሚል ነው፦
ኢሳይያስ 53፥1 ጌታ ሆይ! ማን ምስክርነታችንን አመነ? የጌታ ክንድ ለማን ተገለጠ? ΚΥΡΙΕ, τίς ἐπίστευσε τῇ ἀκοῇ ἡμῶν; καὶ ὁ βραχίων Κυρίου τίνι ἀπεκαλύφθη;
ኢሳይያስ 53፥1 የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል? የያህዌስ ክንድ ለማን ተገልጦአል? מִ֥י הֶאֱמִ֖ין לִשְׁמֻעָתֵ֑נוּ וּזְרֹ֥ועַ יְהוָ֖ה עַל־מִ֥י נִגְלָֽתָה

የዮሐንስ ጸሐፊ የጠቀሰው ከዕብራይስጥ ማሶሬት ሳይሆን ከግሪክ ሰፕቱአጀንት እንደሆነ ማመሳከር ይቻላል፥ ኢሳይያስ በትክክሉ ያለው የትኛውን ነው? የሚል ጥያቄ የቤት ሥራ ይሁንልኝ! በመቀጠል የዮሐንስ ጸሐፊው ኢሳይያስ አይሁዳውያን ያላመኑበትን ምክንያት እንደተናገረ ይናገራል፦
ዮሐንስ 12፥39 ስለዚህ ማመን አቃታቸው፥ ምክንያቱም ኢሳይያስ ድጋሚ እንዲህ አለ፦ διὰ τοῦτο οὐκ ἠδύναντο πιστεύειν, ὅτι πάλιν εἶπεν Ἡσαΐας
ዮሐንስ 12፥40 "በዓይኖቻቸው እንዳያዩ፣ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፣ እንዳይመለሱም፣ እኔም እንዳልፈውሳቸው፣ ዓይኖቻቸውን አሳወረ ልባቸውንም አደነደነ"። Τετύφλωκεν αὐτῶν τοὺς ὀφθαλμοὺς καὶ ἐπώρωσεν αὐτῶν τὴν καρδίαν, ἵνα μὴ ἴδωσιν τοῖς ὀφθαλμοῖς καὶ νοήσωσιν τῇ καρδίᾳ καὶ στραφῶσιν, καὶ ἰάσομαι αὐτούς.

ኢሳይያስ "ጌታ ሆይ" የሚለውን ያህዌህን ሲሆን "የጌታ ክንድ" ያለው እንደ ዮሐንስ ጸሐፊ ኢየሱስን ነው፥ "ክንድ" አገናዛቢ የሆነለት "ጌታ" ያህዌህ ሲሆን በግሪኩ ሰፕቱጀንት ጌታም፦ "ማንን እልካለሁ? ማንስ ለዚህ ሕዝብ ይሄድለታል?" ሲል ኢሳይያስም፦ "እነሆኝ እኔን ላከኝ" አለ፦
ኢሳይያስ 6፥8 የጌታንም ድምፅ፦ ማንን እልካለሁ? ማንስ ለዚህ ሕዝብ ይሄድለታል? ሲል ሰማሁ። እኔም፦ "እነሆኝ እኔን ላከኝ" አልሁ። καὶ ἤκουσα τῆς φωνῆς Κυρίου λέγοντος· τίνα ἀποστείλω, καὶ τίς πορεύσεται πρὸς τὸν λαὸν τοῦτον; καὶ εἶπα· ἰδοὺ ἐγώ εἰμι· ἀπόστειλόν με.

"የጌታ ድምፅ" የሚለው ይሰመርበት! ላኪው ያህዌህ ተላኪው ኢሳይያስ ነው፥ ያህዌህም ለኢሳይያስ ሂድ ይህንን ሕዝብ፦ "በዓይኖቻቸው እንዳያዩ፣ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፣ እንዳይመለሱም፣ እኔም እንዳልፈውሳቸው፣ ዓይኖቻቸውን አሳወረ ልባቸውንም አደነደነ" አለው፦
ኢሳይያስ 6፥10 "በዓይኖቻቸው እንዳያዩ፣ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፣ እንዳይመለሱም፣ እኔም እንዳልፈውሳቸው፣ ዓይኖቻቸውን አሳወረ ልባቸውንም አደነደነ"። ἐπαχύνθη γὰρ ἡ καρδία τοῦ λαοῦ τούτου, καὶ τοῖς ὠσὶν αὐτῶν βαρέως ἤκουσαν καὶ τοὺς ὀφθαλμοὺς αὐτῶν ἐκάμμυσαν μήποτε ἴδωσι τοῖς ὀφθαλμοῖς καὶ τοῖς ὠσὶν ἀκούσωσι καὶ τῇ καρδίᾳ συνῶσι, καὶ ἐπιστρέψωσι, καὶ ἰάσομαι αὐτούς.
ኢሳይያስ ላይ "ጌታ" የተባለው ያህዌህ ሲሆን ኢሳይያስ በራእይ ጌታን በክብሩ አይቶታል፦
ኢሳይያስ 1፥1 በይሁዳ ነገሥታት "በ-"ዖዝያን" እና በኢዮአታም በአካዝና በሕዝቅያስ "ዘመን" ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው የአሞጽ ልጅ የኢሳይያስ "ራእይ"።
ኢሳይያስ 6፥1 ንጉሡ "ዖዝያን" በሞተበት "ዓመት" "ጌታን" በረጅም እና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ "አየሁት"፥ "ክብሩም" ቤቱን ሞልቶት ነበር። ΚΑΙ ἐγένετο τοῦ ἐνιαυτοῦ, οὗ ἀπέθανεν ᾿Οζίας ὁ βασιλεύς, εἶδον τὸν Κύριον καθήμενον ἐπὶ θρόνου ὑψηλοῦ καὶ ἐπῃρμένου, καὶ πλήρης ὁ οἶκος τῆς δόξης αὐτοῦ.

"ዶክሲስ አውቶዩ" δόξης αὐτοῦ ማለት "የእርሱ ክብር" ማለት ነው፥ "እርሱ" የሚለው ተውላጠ ስም "ጌታ" የሚለውን ስም ተክቶ የመጣ ነው፥ ኢሳይያስ ክብሩን ባየ ጊዜ "ይህ" ማለትም "በዓይኖቻቸው እንዳያዩ፣ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፣ እንዳይመለሱም፣ እኔም እንዳልፈውሳቸው፣ ዓይኖቻቸውን አሳወረ ልባቸውንም አደነደነ" የሚለውን አለ፦
ዮሐንስ 12፥41 ክብሩን ባየ ጊዜ ኢሳይያስ ይህን አለ። Tαῦτα εἴπεν Ἠσαΐας, ὅτε εἴδεν τὴν δόξαν αὐτοῦ,

"ዶክሳን አውቶዩ" δόξαν αὐτοῦ ማለት "የእርሱን ክብር" ማለት እንደሆነ ልብ አድርግ! "ኦቴ ኤይዴን" ὅτε εἶδεν ማለት "ባየ ጊዜ"when he saw" ማለት ሲሆን "ኦቴ ኤይዴን" የሚለው የኮዴክስ ቤዛይ እደ-ክታብ ነው፥ ኪንግ ጀምስ ቨርዥን ያንን ተከትሎ በዚህ መልክ እና ልክ "ባየ ጊዜ"when he saw" ብሎ አስቀምጦታል። ስለዚህ ኢሳይያስ ያየው የያህዌህን ክብር እንጂ የኢየሱስን ክብር በፍጹም አይደለም፥ ምክንያቱም "ይህን አለ" ስለሚል "ይህን" የተባለው አመልካች ቃል "በዓይኖቻቸው እንዳያዩ፣ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፣ እንዳይመለሱም፣ እኔም እንዳልፈውሳቸው፣ ዓይኖቻቸውን አሳወረ ልባቸውንም አደነደነ" ብሎ የተናገረውን ነው። ኢሳይያስ ክብሩን ባየ ጊዜ ይህን ከላይ ያለውን ሐረግ ተናገረ፥ ጊዜው ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት ነው። በተጨማሪም ስለ ክንዱ ኢሳይያስ 53፥1 አንድ ላይ ተናገረ፦
ዮሐንስ 12፥41 ስለ እርሱም ተናገረ። καὶ ἐλάλησεν περὶ αὐτοῦ.

"ካይ" καὶ ማለት "እና" ማለት ሲሆን ተጨማሪ ዓረፍተ ነገር ለማሳየት የመጣ ስለሆነ ስለ ክንዱ "ማን ምስክርነታችንን አመነ" ብሎ ተናግሮ ቅሉ ግን ያላመኑበት ምክንያት የክንዱ ባለቤት ጌታ(አብ)፦ "በዓይኖቻቸው እንዳያዩ፣ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፣ እንዳይመለሱም፣ እኔም እንዳልፈውሳቸው፣ ዓይኖቻቸውን አሳወረ ልባቸውንም አደነደነ" ብሏል። "የእርሱ" የተባለው አብን "ስለ እርሱ" የተባለው ወልድን በአንድ ዐውድ ተጠቅሶ ሳለ "የእርሱ" እና "ስለ እርሱ" የተባለው ስለ ኢየሱስ ነው ካላችሁ እንግዲያውስ ክርስቶስ ወላዲ አብ እና ተወላዲ ወልድ ነው በሉ፦
ዕብራውያን 5፥5 እንዲሁ "ክርስቶስ" ደግሞ ሊቀ ካህናት ሊሆን ራሱን አላከበረም፥ ነገር ግን፦ "አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ" ያለው "እርሱ" ነው። Οὕτως καὶ ὁ Χριστὸς οὐχ ἑαυτὸν ἐδόξασεν γενηθῆναι ἀρχιερέα, ἀλλ’ ὁ λαλήσας πρὸς αὐτόν Υἱός μου εἶ σύ, ἐγὼ σήμερον γεγέννηκά σε·

"አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ" ያለው "እርሱ" ነው፥ እንደ እናንተ ሙግት "እርሱ" የተባለው "ክርስቶስ" የሚለውን ተክተን ከተረዳን ልክ የሐዋርያት ቤተክርስቲያን እንደሚያምኑት "አብ እና ወልድ ኢየሱስ ነው" ወደሚል ድምዳሜ ያደርሳል። ቅሉ እና ጥቅሉ ግን "እርሱ" የሚለውን ከላይ ቁጥር 4 ላይ "አምላክ" የሚለውን አብን ተክቶ የመጣ ነው ካላችሁን እንግዲያውስ "የ" አገናዛቢ ዘርፍ ተዛርፎ "እርሱ" የተባለው ከላይ "ጌታ ሆይ" "ጌታ" የሚለውን አብን ተክቶ የመጣ ነው ብላችሁ በዚህ ሒሣብ ተረዱት፦
ዕብራውያን 5፥4 እንደ አሮንም በአምላክ ከተጠራ በቀር ማንም ክብሩን ለራሱ የሚወስድ የለም። καὶ οὐχ ἑαυτῷ τις λαμβάνει τὴν τιμήν, ἀλλὰ καλούμενος ὑπὸ τοῦ Θεοῦ, καθώσπερ καὶ Ἀαρών.

ስለዚህ መሢሑ ከሰው የተገኘ ፍጡር እና ሰው ሆኖ ሳለ “ፈጣሪ ነው” ብሎ ማለት ክህደት ነው፦
5፥17 እነዚያ አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَّقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ

አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
እመኑ!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

57፥7 በአላህ እና በመልክተኛው እመኑ፡፡ آمِنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ

አምላካችን አሏህ በእርሱ አምላክነት እና በመልእክተኛው መልእክተኝነት "እመኑ" በማለት ይናገራል፦
57፥7 በአላህ እና በመልክተኛው እመኑ፡፡ آمِنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ

እዚህ አንቀጽ ላይ አሏህን እና ነቢያችንን"ﷺ" "ወ" وَ በሚል አርፉል አጥፍ እና "አሚኑ" آمِنُوا በሚል በአንድ ግሥ ተጫፍሮ እና ተዛርፎ ስለመጣ ሚሽነሪዎች ነቢያችን"ﷺ" እንደሚመለኩ ለማስመሰል ሲቃጣቸው እና ሲዳዳቸው እያየን ነው፥ ጭራሽ "እመኑ" ማለት "አምልኩ" ማለት አርገው መረዳታቸው ስናይ ደግሞ ምን ያህል ለቅዱሳን መጻሕፍት ባዕድ እና ባይተዋር እንደሆኑ እንረዳለን። አምላካችን አሏህ፦ "በአሏህ እና በመልእክተኞቹ እመኑ" እያለ ብዙ ቦታ ይናገራል፦
3፥179 በአላህ እና በመልክተኞቹም እመኑ፡፡ فَآمِنُوا بِاللَّهِ وَرُسُلِهِ
4፥171 በአላህ እና በመልክተኞቹም እመኑ፡፡ فَآمِنُوا بِاللَّهِ وَرُسُلِهِ

አሏህ ጥንት በላካቸው ነቢያት "እመኑ" ሲል "አምልኩ" ማለቱ ነው ብሎ መረዳት ምን ያህል ቂልነት እንደሆነ በቀላሉ መረዳት ይቻላል፥ አሏህ "በመልክተኛው እመኑ" ሲል "በመልክተኞቹም እመኑ" በተባለበት ስሌት እና ቀመር ነው። እዚህ ድረስ ከተግባባን ከባይብል ይህንን ስሑት ሙግት በስሙር ሙግት እንሞግት፦
ዘጸአት 14፥31 በያህዌህ እና በባሪያው በሙሴ አመኑ። וַיַּֽאֲמִ֙ינוּ֙ בַּֽיהוָ֔ה וּבְמֹשֶׁ֖ה עַבְדֹּֽו׃ פ

እዚህ አንቀጽ ላይ ያህዌህ እና ሙሴ "እና" በሚል መስተጻምር እና "አመኑ" በሚል በአንድ ግሥ ተጫፍሮ እና ተዛርፎ ስለመጣ በእናንተ ስሑት ሙግት ሙሴ ይመለካልን? "በሙሴ አመኑ" ማለትስ "ሙሴን አመለኩ" ማለት ነውን? እንቀጥል፦
2 ዜና መዋዕል 20፥20 "በአምላካችሁ በያህዌህ እመኑ! ትጸኑማላችሁ፥ በነቢያቱም እመኑ ነገሩም ይሰላላችኋል"። הַאֲמִ֜ינוּ בַּיהוָ֤ה אֱלֹהֵיכֶם֙ וְתֵ֣אָמֵ֔נוּ הַאֲמִ֥ינוּ בִנְבִיאָ֖יו וְהַצְלִֽיחוּ׃

ማመን ማምለክ ከሆነ ነቢያቱን አምልኩ እያለን ነውን? "እረ በጭራሽ" ካላችሁ እንግዲያውስ ከላይ ያለውን የቁርኣን አንቀጽ በዚህ መልክ እና ልክ ተረዱት! እዚህ አንቀጽ ላይ "እመኑ" የሚለው ለአምላክ እና ለነቢያቱ ሁለት ጊዜ እንደተጠቀሙበት ኢየሱስም በተመሳሳይ የሰዋስው አወቃቀር "በአምላክ እመኑ" "በእኔም እመኑ" በማለት እርሱ እና አምላኩ ሁለት የተለያዩ ምንነት እና ማንነት እንደሆኑ አበክሮ እና አዘክሮ ተናግሯል፦
ዮሐንስ 14፥1 በአምላክ እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ። πιστεύετε εἰς τὸν Θεόν, καὶ εἰς ἐμὲ πιστεύετε.

"በእኔ" በሚለው ቃል ላይ “ም” የሚለው ጥገኛ ምዕላድ በዐማርኛ ተጨማሪ ነገርን ለማሳየት የገባው በግሪኩ "ካይ" καὶ ማለትም "እና" የሚለውን መስተጻምር ለማሳየት የገባ ነው፥ ይህም አምላክ እና መልእክተኛው ሁለት የተለያዩ ሃልዎት እና ኑባሬ እንደሆኑ ቁልጭ አርጎ ያሳያል። ኢየሱስ መልእክተኛ እንደሆነ ማመን እና አንዱ አምላክ ላኪ እንደሆነ ማመን የእምነት መሠረት ነው፥ በእርግጥም በመልእክተኛው ማመን በላከው ማመን የሚሆንበት ምክንያት መልእክቱ የላኪው እንጂ የተላኪው ስላልሆነ ነው፦
ዮሐንስ 12፥44 ኢየሱስም ጮኸ፥ እንዲህም አለ፦ በእኔ የሚያምን በላከኝ ማመኑ ነው እንጂ በእኔ አይደለም።
ዮሐንስ 14፥24 የምትሰሙትም ቃል የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም።

እንደተግባባን ተስፋ አደርጋለው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የኢየሱስ ምንነት እና ማንነት መጽሐፍ ደሴ ስለሚገኝ ደብረ ብርሃን፣ ደብረ ሲና፣ ሸዋ ሮቢት፣ ከሚሴ እና ኮንቦልቻ ያላችሁ ደውላችሁ ማዘዝ እና ማግኘት ትቻላችሁ፦
አሕመድ +251914711742
ዐረብ ገንዳ ኪታብ ቤት +251911381139
የመስቀል አምልኮ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

11፥2 እንዲህ በላቸው፡- «አላህን እንጂ ሌላን አታምልኩ! እኔ ለእናንተ ከእርሱ የተላክሁ አስጠንቃቂ እና አብሳሪ ነኝ» أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا اللَّهَ ۚ إِنَّنِي لَكُم مِّنْهُ نَذِيرٌ وَبَشِيرٌ

ዘርዓ ያዕቆብ ከደረሳቸው መጻሕፍት አንዱ መስተብቁዕ ዘመስቀል ነው፥ መስተብቁዕ ዘመስቀል ላይ መስቀል እና ማርያም ከፈጣሪ ጋር ተካክለው ምስጋና እንደሚቀርብላቸው ይናገራል፦
መስተብቁዕ ዘመስቀል ቁጥር 8
"ለእሉ ክልኤቱ ፍጡራን ስብሐተ ፈጣሪ ይደልዎሙ እስመ ተዐረዩ በክብሮሙ"

"ለእነዚህ ሁለት ፍጥረታት የፈጣሪ ምስጋና ይገባቸዋል፥ በክብር ተካክለዋልና"

"ሁለቱ" የተባሉት "መስቀል እና ማርያም" ሲሆኑ እነዚህ ሁለት ፍጡራን ከፈጣሪ ጋር "በክብር ተካክለዋል" ይለናል፥ ኢየሱስን፦ "ዘዕሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ(በባሕይርው ከአብ ጋር የሚተካከል)" ሲሉት ሲገርመን ማርያም እና መስቀልን "እስመ ተዐረዩ በክብሮሙ(በክብር ተካክለዋል)" ሲሏቸው አስደመመን። ስለተስተካከሉ ለፈጣሪ የሚገባው የፈጣሪ ምስጋና "ይገባቸዋል" ብለው አረፉት፥ ይህ እልም ያለ ሺርክ ነው። ስብሐት ለሦስቱ ማለትም ለእግዚአብሔር፣ ለድንግል እና ለመስቀል እንደሚገባ የዘወትር ጸሎት ላይ ተገልጿል፦
የዘወትር ጸሎት ቁጥር 9
"ስብሐት ለእግዚአብሔር ወወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር"

ትርጉም፦ "ለእግዚአብሔር፣ ለወለደችው ለድንግል እና ለክቡር መስቀሉ ምስጋና ይገባል"

መስቀል ከመመስገንም አልፎ ይሰገድለታል፦
የዘወትር ጸሎት ቁጥር 8
“እሰግድ “ለ”መስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘተቀደሰ በደሙ ክቡር”

ትርጉም፦ “በደሙ ክቡር “ለ”ተሰቀለበት ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እሰግዳለው”

እንደ ትምህርታቸው ኢየሱስ የተሰቀለበት እና ደሙን ያፈሰሰበት እንጨት እኮ አንድ ነው፥ ዛሬ በእጃቸው የሚያሳልሙበት እና በጉልላት ላይ የሚሰቅሏቸው መስቀሎች የተሰቀለባቸው፣ ደም የፈሰሰባቸው እና ወዝ የተንጠፈጠፈባቸው ስላልሆኑ በምንም ሒሣብ ክቡር አይደሉም።
የሚገርመው መስከረም 17 ቀን "ዮም መስቀል ተሰብሐ" ማለትም "ዛሬ መስቀል ተመሰገነ" በማለት ካመሰገኑት በኃላ መልሰው በደመራ ያቃጥሉታል። "የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፣ አትስገድላቸው፣ አታምልካቸውምም" እየተባለ ለማይሰማ እና ለማይለማ፥ ለማይናገር እና ለማይጋገር ለግዑዝ እንጨት የጸጋ ስግደት መስገድ አግባብ አይደለም፥ ይህ ድርጊት አሳፋሪ እንደሆነም ተገልጿል፦
ዘጸአት 20፥4 የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ! አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም።
መዝሙር 97፥7 ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ፥ በጣዖቶቻቸውም የሚመኩ ይፈሩ።

"ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ ይፈሩ" የሚለው ይሰመርበት! እኛም ሙሥሊሞች የምንለው ደግሞ "የፈጠራችሁን አሏህን ብቻ አምልኩ" ነው፦
11፥2 እንዲህ በላቸው፡- «አላህን እንጂ ሌላን አታምልኩ! እኔ ለእናንተ ከእርሱ የተላክሁ አስጠንቃቂ እና አብሳሪ ነኝ» أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا اللَّهَ ۚ إِنَّنِي لَكُم مِّنْهُ نَذِيرٌ وَبَشِيرٌ

የፈጠረንን አንዱን አምላክ ብቻ ማምለክ ምንኛ መታደል ነው? አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
እውነተኛ ብርሃን ማን ነው?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡

ነጥብ አንድ
"እውነተኛው ብርሃን በቁርአን"
አሏህ ከፍጡራን ጋር በምንም አይመሳሰልም፤ ማንምና ምንም እርሱን የሚመስል የለም፦
42፥11 "የሚመስለው ምንም ነገር የለም"፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡
112፥4 ለእርሱም "አንድም ብጤ የለውም"፡፡
16፥74 ለአላህም "አምሳያዎችን አታድርጉ"፡፡ አላህ መሳይ እንደሌለው ያውቃል፡፡ እናንተ ግን አታውቁም፡፡
19፥65 እርሱ የሰማያትና የምድር በሁለቱም መካከል ላለው ሁሉ ጌታ ነውና ተገዛው፡፡ እርሱን በመገዛትም ላይ ታገስ፡፡ "ለእርሱ ሞክሼን" ታውቃለህን?

አላህ በዛቱ ማለትም በህላዌው"essence" ከማንም ከምንም ነገር ጋር የማይመሳሰል መሆኑን ካየን ዘንዳ የህላዌው መገለጫ ማን መሆኑን የምናውቀው በሲፋቱ ማለትም በባህርያቱ"attribute" ነው፤ አላህ ከፍጡራን ጋር የማይመሳሰል የራሱ ታላቅ ባህርይ አለው፦
16:60 ለአላህም "ታላቅ ባሕርይ" مَثَلُ አለው፤ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው።

"መሰል" مَثَل ማለት "መገለጫ ባህርይ" "description" ሲሆን በሰማይና በምድር ከፍተኛ ማለትም ታላቅ ባህርይ አለው፦
30:27  ለርሱም በሰማያትም በምድርም "ከፍተኛ ባሕርይ" الْمَثَلُ አልለው፤ እርሱም አሸናፊ ጥበበኛ ነው።

አላህ የህላዌው መገለጫ በሰማይና በምድር ታላቅ ባህርይ እንዳለው ከተመለከትን "ኑር" نُور ማለት ብርሃን ማለት ሲሆን አላህ የሰማይና የምድር እውነተኛ ብርሃን ነው፦
24:35 አላህ የሰማያትና የምድር "ብርሃንنُورُ ነው፤ "የብርሃኑ" نُورِهِ  "ምሳሌ" مَثَلُ ፥ በውስጧ መብራት እንዳለባት ዝግ መስኮት፥ መብራቱ በብርጭቆ ውስጥ የሆነ፣ ብርጭቆይቱ ፍጹም ሉላዊ ኮከብ የምትመስል፣ ምሥራቃዊም ምእራባዊም ካልሆነች፣ ከተባረከች የወይራ ዛፍ፣ ዘይቷ እሳት ባይነካውም እንኳ ሊያበራ የሚቀርብ ከሆነች ዘይት የሚቃጠል እንደኾነ መብራት ነው፤ ይህ  በብርሃን ላይ የሆነ ብርሃን ነው፤ አላህ ወደ ብርሃኑ የሚሻውን ሰው ይመራል፤ አላህም ለሰዎች ምሳሌዎችን ያቀርባል። አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው።

አላህ ብርሃን ነው የተባለበት ፍጡራን በተባሉበት ሂሳብ አይደለም፤ አላህ እውነተኛ ብርሃን ነው።

ነጥብ ሁለት
"እውነተኛው ብርሃን በባይብል"
1ኛ ዮሐንስ 1:5 ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት፦ "እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም" የምትል ይህች ናት።

ፀሃፊፍ ከኢየሱስ የሰማው መልእክት "እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም" የሚል ነው፤ ነገር ግን ኢየሱስ በአራቱ ወንጌላት "እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም" ብሎ ያስተማረበት አንድም ቦታ የለም፤ ይህ የሚያሳየው ኢየሱስ ተናግሮ ነገር ግን በአራቱ ወንጌላት ላይ ያልተካተቱ የኢየሱስ መልእክት እንደነበሩ ነው፤ ከቁርአኑ ጋር በተመሳሳይ ፈጣሪ እውነተኛ ብርሃን መሆኑን ካየን ዘንዳ ሚሽነሪዎች ኢየሱስ ብርሃን ተብሏል ስለዚህ በቁርአንና በኢየሱስ ንግግር ፈጣሪ የተባለው ኢየሱስ ነው ብለው አረፉት፦
ዮሐንስ 8፥12 ደግሞም ኢየሱስ፦ "እኔ የዓለም ብርሃን" ነኝ፤

እኛም ምግታችንን ሰፋ አድርገን ታዲያ ኢየሱስ የዓለም ብርሃን መባሉ አምላክ ያሰኘዋልን? ብለን ጥያቄ እናቀርባለን፤ መልሱ አዎ ከሆነ እንግዲያውስ ብዙ አምላኮች ሊኖሩ ነው፤ ምክንያቱም የዓለም ብርሃን የተባለው ኢየሱስ ብቻ ሳይሆን ሃዋርያትም ጭምር ናቸው፦
ማቴዎስ 5፥14 "እናንተ የዓለም ብርሃን" ናችሁ።

አይ ሃዋርያትን ብርሃን ያደረጋቸው እግዚአብሔር ስለሆነ የእነርሱ ብርሃንነት በመደረግ የተመሰረተ የፀጋ እንጂ የባህርይ አይደለም ከተባለ ኢየሱስንስ ብርሃን ያደረገው እግዚአብሔር አይደለምን? ስለዚህ የኢየሱስ ብርሃን መሆን እንደ ሃዋርያት በፀጋ እንጂ የባህርይ አይደለም፦
ኢሳይያስ 49፥6 እርሱም፦ የያዕቆብን ነገዶች እንድታስነሣ ከእስራኤልም የዳኑትን እንድትመስል ባሪያዬ ትሆን ዘንድ እጅግ ቀላል ነገር ነውና እስከ ምድር ዳር ድረስ መድኃኒት ትሆን ዘንድ ለአሕዛብ ""ብርሃን አድርጌ"" ሰጥቼሃለሁ ይላል።
ኢሳይያስ 42፥7 እኔ እግዚአብሔር በጽድቅ ጠርቼሃለሁ፥ እጅህንም እይዛለሁ እጠብቅህማለሁ፥ የዕውሩንም ዓይን ትከፍት ዘንድ የተጋዘውንም ከግዞት ቤት በጨለማም የተቀመጡትን ከወህኒ ቤት ታወጣ ዘንድ ለሕዝብ ቃል ኪዳን ለአሕዛብም ""ብርሃን አድርጌ"" እሰጥሃለሁ።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሥነ-ሰብእ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

51፥21 በራሳችሁም ውስጥ ምልክቶች አሉ፥ ታዲያ አትመለከቱምን? وَفِي أَنفُسِكُمْ ۚ أَفَلَا تُبْصِرُونَ سورت الذاريات

በግዕዝ "ሰብእ" ማለት "ሰው" ማለት ሲሆን ስለ ሰው በመስኩ ምሁራን ዘንድ የሚጠናው ጥናት "ሥነ-ሰብእ ጥናት"anthropology" ይሉታል፥ ይህም ቃል "አንትሮፖስ" ἄνθρωπος ማለትም "ሰው" እና ‎"ሎጊአ" λογία ማለትም "ጥናት" ከሚል ሁለት የግሪክ ቃላት የተዋቀረ ነው። በቁርኣን "ኢንሣን" إِنسَٰن ማለት "ሰው" ማለት ሲሆን ይህም ቃል በነጠላ የተጠቀሰው 65 ጊዜ ብቻ ነው፥ ሰው የተፈጠረው ደግሞ ከአፈር፣ ከፍትወት ጠብታ፣ ከረጋ ደም፣ ከቁራጭ ሥጋ፣ ከአጥንት እና ከጡንጫ ሥጋ ነው፦
23፥12 በእርግጥም ሰውን ከነጠረ ጭቃ ፈጠርነው፡፡ وَلَقَدْ خَلَقْنَا الْإِنسَانَ مِن سُلَالَةٍ مِّن طِينٍ
23፥13 ከዚያም በተጠበቀ መርጊያ ውስጥ የፍትወት ጠብታ አደረግነው፡፡ ثُمَّ جَعَلْنَاهُ نُطْفَةً فِي قَرَارٍ مَّكِينٍ
23፥14 ከዚያም ጠብታዋን የረጋ ደም አድርገን ፈጠርን፡፡ የረጋውንም ደም ቁራጭ ሥጋ አድርገን ፈጠርን፡፡ ቁራጯንም ሥጋ አጥንቶች አድርገን ፈጠርን፡፡ አጥንቶቹንም ሥጋን አለበስናቸው፡፡ ከዚያም ሌላ ፍጥረትን አድርገን አስገኘነው፡፡ ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ፡፡ مَّ خَلَقْنَا النُّطْفَةَ عَلَقَةً فَخَلَقْنَا الْعَلَقَةَ مُضْغَةً فَخَلَقْنَا الْمُضْغَةَ عِظَامًا فَكَسَوْنَا الْعِظَامَ لَحْمًا ثُمَّ أَنشَأْنَاهُ خَلْقًا آخَرَ ۚ فَتَبَارَكَ اللَّهُ أَحْسَنُ الْخَالِقِينَ

ሰው የአፈር፣ የፍትወት ጠብታ፣ የረጋ ደም፣ የቁራጭ ሥጋ፣ የአጥንት እና የጡንጫ ሥጋ ሁሉ ድምር ነው፥ ይህንን በዝርዝር ማየት እንችላለን፦
1. "ቱራብ" تُرَاب ማለት "አፈር" ማለት ሲሆን በቁርኣን የተጠቀሰው 17 ጊዜ ብቻ ነው።
2. "ኑጥፋህ" نُّطْفَة ማለት "የፍትወት ጠብታ" ማለት ሲሆን በቁርኣን የተጠቀሰው 12 ጊዜ ብቻ ነው።
3. "ዐለቃህ" عَلَقَة ማለት "የረጋ ደም" ማለት ሲሆን በቁርኣን የተጠቀሰው 6 ጊዜ ብቻ ነው።
4. "ሙድጋህ" مُضْغَة ማለት "ቁራጭ ሥጋ" ማለት ሲሆን በቁርኣን የተጠቀሰው 3 ጊዜ ብቻ ነው።
5. "ዐዝም" عَظْم ማለት "አጥንት" ማለት ሲሆን በቁርኣን የተጠቀሰው 15 ጊዜ ብቻ ነው።
6. "ለሕም" لَحْم ማለት "የጡንጫ ሥጋ " ማለት ሲሆን በቁርኣን የተጠቀሰው 12 ጊዜ ብቻ ነው።
---------------
በድምሩ = 65 ቁጥር ይሆናል።

ይህም "ኢንሣን" إِنسَٰن የሚለው ቃል 65 ጊዜ መጠቀሱ ያለምክንያት አልነበረም፥ አሏህ ነገር ሁሉ በቁጥር ያጠቃለለ ስለሆነ ነው፦
72፥28 እነርሱ ዘንድ ባለው ነገር ዕውቀቱ የከበበ እና "ነገሩንም ሁሉ በቁጥር ያጠቃለለ ሲኾን" የጌታቸውን መልክቶች ያደረሱ መኾናቸውን ያውቅ ዘንድ ጠባቂ ያደርጋል፡፡ لِّيَعْلَمَ أَن قَدْ أَبْلَغُوا رِسَالَاتِ رَبِّهِمْ وَأَحَاطَ بِمَا لَدَيْهِمْ وَأَحْصَىٰ كُلَّ شَيْءٍ عَدَدًا

"ነገሩንም ሁሉ በቁጥር ያጠቃለለ ሲኾን" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! በራሳችን ውስጥ ብዙ ተአምራት አሉ፥ ከእኛ የሚጠበቀው መመልከት ብቻ ነው፦
51፥21 በራሳችሁም ውስጥ ምልክቶች አሉ፥ ታዲያ አትመለከቱምን? وَفِي أَنفُسِكُمْ ۚ أَفَلَا تُبْصِرُونَ سورت الذاريات

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም