ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.2K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
አንድ ጌታ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

6፥164 በላቸው «እርሱ አላህ የሁሉ ነገር ጌታ ሲሆን ከአላህ በቀር ሌላን ጌታ እፈልጋለሁን? ነፍስም ሁሉ በራሷ ላይ እንጅ ክፉን አትሠራም፡፡ قُلْ أَغَيْرَ ٱللَّهِ أَبْغِى رَبًّۭا وَهُوَ رَبُّ كُلِّ شَىْءٍۢ ۚ وَلَا تَكْسِبُ كُلُّ نَفْسٍ إِلَّا عَلَيْهَا

"የባሕርይ ጌታ" ማለት በራሱ የተብቃቃ እና ጌትነቱ ከማንም ያላገኘው የባሕርይ ገንዘቡ የሆነ ጌታ ማለት ነው፥ አሏህ የሁሉ ነገር ጌታ ሲሆን ጌትነቱ የባሕርይ ነው፦
6፥164 በላቸው «እርሱ አላህ የሁሉ ነገር ጌታ ሲሆን ከአላህ በቀር ሌላን ጌታ እፈልጋለሁን? ነፍስም ሁሉ በራሷ ላይ እንጅ ክፉን አትሠራም፡፡ قُلْ أَغَيْرَ ٱللَّهِ أَبْغِى رَبًّۭا وَهُوَ رَبُّ كُلِّ شَىْءٍۢ ۚ وَلَا تَكْسِبُ كُلُّ نَفْسٍ إِلَّا عَلَيْهَا

ሀለተኛው ጌትነት የጸጋ ጌትነት ሲሆን የጸጋ ጌትነት ሲባል ፍጡራንን ሌላ ማንነት ጌታ የሚያደርጋቸው ነው፥ ለምሳሌ፦ ይስሐቅ ያዕቆብን በዔሳው ላይ ጌታ አደረገው ማለት የያዕቆብ ጌትነት በመደረግ ላይ የተመሠረተ ስለሆነ የባሕርይ ጌትነት አይደለም፦
ዘፍጥረት 27፥37 ይስሐቅም መለሰ ዔሳውንም፦ "እነሆ ጌታህ አደረግሁት" አለው። וַיַּ֨עַן יִצְחָ֜ק וַיֹּ֣אמֶר לְעֵשָׂ֗ו הֵ֣ן גְּבִ֞יר שַׂמְתִּ֥יו לָךְ֙

በመደረግ ላይ የተመሠረተ ጌትነት ሥልጣን እና ሹመት ወይም እልቅና እና ማዕረግን ያሳያል፥ ፈጣሪ አምላክ ዮሴፍን ጌታ ስላረገው ዮሴፍ፦ "አምላክ" በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ "ጌታ" አደረገኝ" ብሎአል፦
ዘፍጥረት 45፥9 "አምላክ" በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ "ጌታ" አደረገኝ። שָׂמַ֧נִי אֱלֹהִ֛ים לְאָדֹ֖ון לְכָל־מִצְרָ֑יִם

"ጌታ አደረገኝ" ሲል የዓለማቱ ጌታ ሆነ ማለት ሳይሆን በጸጋ እና በስጦታ ያገኘው እንጂ የባሕይር ጌትነት በፍጹም አይደለም። በተመሳሳይም የኢየሱስ ጌትነት በመደረግ ላይ የተመሠረተ መነሾ ያለው ስለሆነ የባሕርይ ጌትነት በፍጹም አይደለም፦
የሐዋርያት ሥራ 2፥36 ኢየሱስን አምላክ ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው የእስራኤል ወገን ሁሉ በእርግጥ ይወቅ። ἀσφαλῶς οὖν γινωσκέτω πᾶς οἶκος Ἰσραὴλ ὅτι καὶ Κύριον αὐτὸν καὶ Χριστὸν ἐποίησεν ὁ Θεός, τοῦτον τὸν Ἰησοῦν.

እዚህ አንቀጽ ላይ "አምላክ" ባለቤት ሲሆን "ኢየሱስ" ተሳቢ ነው፥ በባለቤት እና በተሳቢ መካከል "እንዳደረገው" የሚል ተሻጋሪ ግሥ አለ። ጌታ አድራጊ አንዱ አምላክ ሲሆን ጌታ ተደራጊ ኢየሱስ ነው፥ አምላክ ኢየሱስን ጌታ ካረደገው የኢየሱስ ጌትነት መነሾ ያለው ስለሆነ ጌታ ከመደረጉ በፊት በባዶነት ስለሚቀደም ጌትነቱ ሥልጣን እና ሹመት ወይም እልቅና እና ማዕረግን ያሳያል። ኢየሱስ ጌትነቱ መነሻ ካለው፣ እራሱ "ጌታዬ" ብሎ የሚጠራው ጌታ ካለው፣ ለጌታው ባሪያ ከሆነ እና ጌታውን ካመለከ የባሕርይ ጌታ በፍጹም አይደለም፦
ኢሳይያስ 42፥1 እነሆ ደግፌ የያዝሁት ባሪያዬ ያዕቆብ፤ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት "ምርጤ" እስራኤል፤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ፥ እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያወጣል።
ኢሳይያስ 48፥16 ጌታዬ ያህዌህ በመንፈሱ ልኮኛል። אֲדֹנָי יְהוִה שְׁלָחַנִי--וְרוּחו

ሲጀመር የኢየሱስ ጌታ ኢየሱስን "ባሪያዬ" ካለው ኢየሱስ የያህዌህ ባሪያ ከሆነ ያህዌህ የኢየሱስ ጌታ ነው፥ ኢየሱስ ባርነቱ ለአንዱ ጌታ ለአብ ከሆነ ኢየሱስ የጌታ ቅቡዕ እንጂ የባሕርይ አንዱ ጌታ በፍጹም አይደለም። ሲቀጥል "አዶናይ" אֲדֹנָ֥י ማለት "ጌታዬ" ማለት ከሆነ ኢየሱስ "ጌታዬ" የሚለው ጌታ ስላለው ጌትነቱ የጸጋ ነው። በነገራችን ላይ የሥላሴ አማንያን ኢሳይያስ 48፥16 ስለ ኢየሱስ ነው ስለሚሉ "ባመጣሽው ዳኛ ትሆኝ እስረኛ" የሚባል አገርኛ ብሒል ይዘን ለመሞገት እንጂ "ጌታዬ ያህዌህ በመንፈሱ ልኮኛል" የሚለው ኢሳይያስ ነው፦
ታርገም ዮናታን ኢሳይያስ 48፥16 ነቢዩም አለ፦ "አሁን ግን ጌታ አምላክ በቃሉ ልኮኛል። אֲמַר נְבִיָא וּכְעַן יְיָ אֱלֹהִים שַׁלְחַנִי וּמֵימְרֵהּ:
ስለዚህ ኢየሱስ ጌታውን "ጌታዬ" ካለ ጌታው ኢየሱስን "ባሪያዬ" ካለ የሁሉም አንድ ጌታ የኢየሱስ ጌታ ነው። ታዲያ ኢየሱስን ለምን "አንድ ጌታ" ተባለ?
"ረብ" רַב የሚለው የዕብራይጥ ቃል "መምህር" "መሪ" "አለቃ" "ታላቅ" "ብዙ" የሚል ፍቺ አለው፥ 1ኛ ነገሥት 18፥25 ተመልከት! "ረቢ" רַבִּי ደግሞ "መምህር ሆይ" ወይም "መምህሬ" ማለት ነው፦
ዮሐንስ 1፥38 እነርሱም፦ "ረቢ" ወዴት ትኖራለህ? አሉት፥ ትርጓሜው "መምህር ሆይ" ማለት ነው። οἱ δὲ εἶπαν αὐτῷ Ῥαββεί, ὃ λέγεται μεθερμηνευόμενον Διδάσκαλε, ποῦ μένεις;

እዚህ አንቀጽ ላይ በግሪኩ ኮይኔ "ረቢ" Ῥαββεί ብለው ያስቀመጡት "ረቢ" רַבִּי የሚለውን የዕብራይስጥ ቃል ነው፥ "ረቡኒ" Ραββουνι ደግሞ "መምህራችን" ማለት ነው፦
ዮሐንስ 20፥16 ኢየሱስም፦ ማርያም አላት። እርስዋ ዘወር ብላ በዕብራይስጥ፦ "ረቡኒ" አለችው፥ ትርጓሜውም፦ “መምህር ሆይ” ማለት ነው። λέγει αὐτῇ Ἰησοῦς Μαριάμ. στραφεῖσα ἐκείνη λέγει αὐτῷ Ἐβραϊστί Ῥαββουνεί ὃ λέγεται Διδάσκαλε.

ወደ ግሪክ ትምህርት ቤት ገብተን ወንድ መምህር "ኩሪዮስ" κύριος ሲባል ሴት መምህር ደግሞ "ኩሪያ" κυρία ትባላለች፥ ስለዚህ "ኩሪዮስ" κύριος ትርጉሙ "ጌታ" ብቻ ሳይሆን "መምህር" ማለትም ጭምር ነው። ማርቆስ ጴጥሮስ ኢየሱስን በአንድ ጥቅስ ላይ፦ "ረቢ" Ῥαββεί እንዳለው ይናገራል፦
ማርቆስ 9፥5 ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን "ረቢ" በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነውና አንድ ለአንተ አንድም ለሙሴ አንድም ለኤልያስ ሦስት ዳሶች እንሥራ አለው። καὶ ἀποκριθεὶς ὁ Πέτρος λέγει τῷ Ἰησοῦ Ῥαββεί, καλόν ἐστιν ἡμᾶς ὧδε εἶναι, καὶ ποιήσωμεν τρεῖς σκηνάς, σοὶ μίαν καὶ Μωϋσεῖ μίαν καὶ Ἡλείᾳ μίαν.

ነገር ግን የማርቆስን ጽሑፍ መሠረት አድርጎ የጻፈው የማቴዎስ ጸሐፊ ጴጥሮስ ኢየሱስን ከላይ ባለው አንድ ጥቅስ ላይ "ኩሪዮስ" κύριος እንዳለው ይናገራል፦
ማቴዎስ 17፥4 ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን፡- ኩሪዮስ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ አለ። ἀποκριθεὶς δὲ ὁ Πέτρος εἶπεν τῷ Ἰησοῦ Κύριε, καλόν ἐστιν ἡμᾶς ὧδε εἶναι· εἰ θέλεις, ποιήσω ὧδε τρεῖς σκηνάς, σοὶ μίαν καὶ Μωϋσεῖ μίαν καὶ Ἡλείᾳ μίαν.

"ረቢ" Ῥαββεί ማለት "ኩሪዮስ" κύριος ማለት እንደሆነ ከተረዳን ዘንዳ ኢየሱስ፦ "መምህራችሁ አንድ ነው" ሲል "ረቢአችሁ አንድ ነው" ማለቱ ነው፦
ማቴዎስ 23፥8 እናንተ ግን፡- "ረቢ" ተብላችሁ አትጠሩ፤ "መምህራችሁ አንድ ነው" እናንተም ሁላችሁ ወንድማማች ናችሁ። ὑμεῖς δὲ μὴ κληθῆτε Ῥαββεί· εἷς γάρ ἐστιν ὑμῶν ὁ διδάσκαλος, πάντες δὲ ὑμεῖς ἀδελφοί ἐστε.
ዮሐንስ 7፥16  "ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከእኔ አይደለም"።
ዮሐንስ 8፥28 እነዚህን እናገር ዘንድ "አባቴ እንዳስተማረኝ" እንጂ ከራሴ አንዳች እንዳላደርግ በዚያን ጊዜ ታውቃላችሁ።

ኢየሱስ በአንድ አምላክ እና በሰው መካከል ያለ ትምህርት ተሰቶት የሚያስተላልፍ አንድ ረቢ ስለሆነ "ረቢ ተብላችሁ አትጠሩ" ብሎአል። ስለዚህ ጳውሎስ "አንድ ኩሪዮስ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን" ሲል "አንድ መምህር አለን" እያለ ነው፦
1ኛ ቆሮንቶስ 8፥6 ነገር ሁሉም በእርሱ በኩል የሆነ እኛም በእርሱ በኩል የሆንን አንድ ኩሪዮስ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን። καὶ εἷς Κύριος Ἰησοῦς Χριστός, δι’ οὗ τὰ πάντα καὶ ἡμεῖς δι’ αὐτοῦ.

ይህ አንድ መምህር ኢየሱስ ሲሆን መምህሩ ኢየሱስ "አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና" ሲል ጳውሎስ ደግሞ ይህንን አንዱን አባት(አስገኚ) "አንድ አምላክ አብ አለን" በማለት ተናግሯል፦
ማቴዎስ 23፥9 አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም፦ አባት፡ ብላችሁ አትጥሩ።
1ኛ ቆሮንቶስ 8፥6 ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ አለን።
ሚልክያስ 2፥10 ለሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን? አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን?

"አንድ አባት" እና "አንድ አምላክ" አብ ሲሆን በአንዱ አምላክ እና በሰዎች መካከል ያለ መካከለኛ አንድ መምህር አለ፥ እርሱም ሰው ነው፦
1 ጢሞቴዎስ 2፥5 አንድ አምላክ አለና፥ በአምላክ እና በሰዎች መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። εἷς γὰρ Θεός, εἷς καὶ μεσίτης Θεοῦ καὶ ἀνθρώπων, ἄνθρωπος Χριστὸς Ἰησοῦς,

"አባታችን አንዱ እርሱም የሰማዩ ነው" "አንድ አምላክ አብ አለን" "አንድ አምላክ አለ" የሚለው ተመሳሳይ አቀማመጥ አብን ያሳያል፥ "መምህራችሁ አንድ ነው" "አንድ ኩሪዮስ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን" "መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ" የሚለው ተመሳሳይ አቀማመጥ ኢየሱስን ያሳያል።
ኢየሱስ ሁሉንም ጠቅሎ የያዘ አንድ ጌታ(አዶናይ) በፍጹም አይደለም፥ ምክንያቱም አንደኛ ጌትነቱ መነሻ አለው፣ ሁለተኛ ከእርሱ በላይ ያለውን ጌታውን "ጌታዬ" እያለ ተናግሯል፣ ሦስተኛ የእርሱ ጌታ አብ እርሱን "ባሪያዬ" ብሎታል። እርግጥ ነው ኢየሱስ በዘመኑ ከአምላክ የተላከ አንድ መምህር ነው፦
ዮሐንስ 3፥2 "መምህር" ሆነህ ከአምላክ ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን” አለው። οἴδαμεν ὅτι ἀπὸ Θεοῦ ἐλήλυθας διδάσκαλος·

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የሰሞኑ ትኩሳት!

ኦርቶዶክስ ከኦርቶዶክስ ጋር እርስ በእርስ፣ ፕሮቴስታንት ከፕሮቴስታንት ጋር እርስ በእርስ፣ እንዲሁ ኦርቶዶክስ እና ፕሮቴስታንት ሲበባሉ፣ ሲነካከሱ፣ ሲነቋቆሩ እያየን ነው።
ይህ አጋጣሚ የኢሥላምን መልእክት ለዚህ ግራ ለገባው ሕዝብ የማድረስ የሁላችንም አላፍትና አለብን።
አሏህ ይርዳን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom
ሑሉል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

87፥1 ከሁሉ በላይ የኾነውን ጌታህን ስም አሞግሥ፡፡ سَبِّحِ اسْمَ رَبِّكَ الْأَعْلَى

"ሑሉል" حُلُول ማለት "አምላክ ሁሉ ነገር ነው፥ በሁሉ ነገር ውስጥ ነው" የሚል እሳቤ ነው፥ ይህ እሳቤ በኢሥላም ሺርክ ውስጥ ይመደባል። "ፓንቴይዝም"pantheism" የሚለው ቃል የሁለት ቃላት ውቅር ነው፥ "ፓን" እና "ቴዎስ" ከሚሉ ሁለት ቃላት የተዋቀረ ሲሆን "አምላክ ሁሉ ነገር ነው"God is all thing" ማለት ነው።
"ፓን" πᾶν ወይም "ፓስ" πᾶς ማለት "ሁሉ ነገር" ማለት ነው፥ "ፓን" πᾶν ተሳቢ ቅጽል ገላጭ ሲሆን "ፓስ" πᾶς ደግሞ ባለቤት ቅጽል ገላጭ ነው።
"ቴዎን" θεὸν ወይም "ቴዎስ" θεός ማለት "አምላክ" ማለት ነው፥ "ቴዎን" θεὸν ተሳቢ ስም ሲሆን ቴዎስ" θεός ደግሞ ባለቤት ስም ነው።

"አምላክ ሁሉ ነገር ነው፥ በሁሉ ነገር ውስጥ ነው" የሚለው እሳቤ በጥንት ጊዜ በሕንድ፣ በግብፅ፣ በባቢሎን፣ በግሪክ እና በሮም የነበረ አሳብ ነው፥ የሚያሳዝነው ጳውሎስ ከእነዚህ ዐረማዊ እሳቤ ወስዶ አምላክ ሁሉ ነገር እንደሚሆን እና በሁሉ ነገር እንደሚሆን ተናግሯል፦
1 ቆሮንቶስ 15፥28 ሁሉ ከተገዛለት በኋላ ግን አምላክ "ሁሉ" "በሁሉ" ይሆን ዘንድ" በዚያን ጊዜ ልጁ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ይገዛል። ὅταν δὲ ὑποταγῇ αὐτῷ τὰ πάντα, τότε καὶ αὐτὸς ὁ Υἱὸς ὑποταγήσεται τῷ ὑποτάξαντι αὐτῷ τὰ πάντα, ἵνα ᾖ ὁ Θεὸς πάντα ἐν πᾶσιν.

እዚህ አንቀጽ ላይ "ሁሉ" ለሚለው የገባው ቃል "ፓንታ" πάντα ሲሆን "ሁሉ ነገር"all thing" ማለት ነው፥ "አምላክ ሁሉ ነገር ይሆን ዘንድ" "አምላክ በሁሉ ነገር ይሆን ዘንድ" የሚለው አሳብ ከጥንቱ ፓጋን የተቀዳ ነው። "ፈጣሪ በሁሉ ነገር ውስጥ ይገኛል" የሚለው እሳቤ "ምሉዕ በኲለሄ" ይሉታል፥ እንደ ክርስትናው "ፈጣሪ መንፈስ ነው፥ በመንፈሱ ሁሉን የሞላ ነው" ይላሉ። በመንፈሱ ሁሉም ነገር ውስጥ ካለ "የጌታ መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ" ስለሚል ጠንቋይ ቤት፣ ድግምት ቤት፣ ሰይጣን ውስጥ እና የሰይጧን ቤት ካለ በእነዚያ ቦታ አርነት አለን?
2 ቆሮንቶስ 3፥17 ጌታ ግን መንፈስ ነው፥ የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ።

አምላክ ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም፥ አምላክ ሁሉም ቦታ ውስጥ ካለ የመንፈሳዊ ጨለማ ሆነ የሌሊት ጨለማ እና ሰይጣን እንዴት ሊኖሩ ቻሉ?
1 ዮሐንስ 1፥5 አምላክ ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም።
መዝሙር 139፥12 ጨለማ በአንተ ዘንድ አይጨልምምና፥ ሌሊትም እንደ ቀን ታበራለችና፥ እንደ ጨለማዋ እንዲሁ ብርሃንዋ ነው።

"አምላክ ሁሉ ነገር ውስጥ አለ" ሲባል የሴት ብልት ውስጥ፣ የሴት ማኅፀን ውስጥ፣ የሰው ሆድ ውስጥ፣ ሽንት ቤት እና ሰይጣን ውስጥ አለን? "አምላክ ሁሉ ነገር ውስጥ አለ" ከተባለ ሰው በጥፊ ሲመታ መለኮት በሥጋ ተመታ እንላለልን? አምላክ ሥጋ ሆነ እና በሥጋ ተደበደበ፣ ተራበ፣ ተጠማ፣ ሞተ የሚባለው ትምህርት "ኢቲሓድ" اِتِّحَاد ሲባል በክርስትናው ተሠግዎት"incarnation" ይባላል፥ ይህ ትምህርት ከሑሉል የተቀዳ ሲሆን ሺርክ ነው።

አምላካችን አሏህ ፈጣሪ ነው፥ ከፍጥረቱ ጋር በባሕርያቱ ግኑኝነት ቢኖረውም ከፍጥረቱ ውጪ የሚኖር ነው። በፍጥረቱ ውስጥ የለም፥ ፍጥረቱን ያካበበ እንጂ በፍጥረቱ ውስጥ የተካበበ አይደለም። እርሱ ከፍጥረቱ መካከል ማንንም አይመስልም፥ እርሱ ሁሉ ነገር ወይም በሁሉ ነገር ውስጥ ሳይሆን ከሁሉ ነገር በላይ ያለ አምላክ ነው፦
87፥1 ከሁሉ በላይ የኾነውን ጌታህን ስም አሞግሥ፡፡ سَبِّحِ اسْمَ رَبِّكَ الْأَعْلَى

"አምላክ ሁሉ ነገር ነው፥ በሁሉ ነገር ውስጥ ነው" የሚሉትን አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሐጅ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

22፥26 ለኢብራሂምም የቤቱን ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ «በእኔ ምንንም አታጋራ፣ ቤቴንም ለሚዞሩት፣ ለሚቆሙበት፣ ለሚያጎነብሱት እና በግንባራቸውም ለሚደፉት ንጹሕ አድርግላቸው» ባልነው ጊዜ አስታውስ፡፡ وَإِذْ بَوَّأْنَا لِإِبْرَاهِيمَ مَكَانَ الْبَيْتِ أَن لَّا تُشْرِكْ بِي شَيْئًا وَطَهِّرْ بَيْتِيَ لِلطَّائِفِينَ وَالْقَائِمِينَ وَالرُّكَّعِ السُّجُودِ

“ሐጅ” حَجّ የሚለው ቃል “ሐጀ” حَجَّ ማለትም “ጎበኘ” ከሚል ሥርወ-ቃል የተገኘ ሲሆን “ጉብኝት”pilgrimage” ማለት ነው፥ “ሐጅ” መደበኛ ዐብይ ጉብኝት ሲሆን “ዑምራህ” عُمْرَة ደግሞ መደበኛ ያልሆነ ንዑስ ጉብኝት ነው፦
2፥196 *ሐጅን እና ዑምራንም ለአላህ ሙሉ*፡፡ وَأَتِمُّوا الْحَجَّ وَالْعُمْرَةَ لِلَّه
3፥97 ለአላህም በሰዎች ላይ ወደ እርሱ መኼድን በቻለ ሁሉ ላይ ቤቱን መጎብኘት ግዴታ አለባቸው፡፡ وَلِلَّهِ عَلَى النَّاسِ حِجُّ الْبَيْتِ مَنِ اسْتَطَاعَ إِلَيْهِ سَبِيلًا
2፥158 ሶፋ እና መርዋ ከአላህ ምልክቶች ናቸው፥ “ቤቱን በሐጅ ወይም በዑምራህ ሥራ የጎበኘ” ሰው በሁለቱ መካከል በመመላለሱ በእርሱ ላይ ኃጢአት የለበትም፡፡ إِنَّ الصَّفَا وَالْمَرْوَةَ مِن شَعَائِرِ اللَّهِ ۖ فَمَنْ حَجَّ الْبَيْتَ أَوِ اعْتَمَرَ فَلَا جُنَاحَ عَلَيْهِ أَن يَطَّوَّفَ بِهِمَا

“የጎበኘ” ለሚለው ቃል የገባው “ሐጀ” حَجَّ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። ሐጅ የራሱ ጊዜ አለው፦
2፥89 ከለጋ ጨረቃዎች መለዋወጥ ይጠየቁሃል፡፡ እነርሱ ለሰዎች ጥቅም ለሐጅም ማወቂያ ጊዜያቶች ምልክቶች ናቸው በላቸው፡፡ يَسْأَلُونَكَ عَنِ الْأَهِلَّةِ ۖ قُلْ هِيَ مَوَاقِيتُ لِلنَّاسِ وَالْحَج
2፥197 ሐጅ ጊዜያቱ የታወቁ ወሮች ናቸው፡፡ በእነርሱም ውስጥ ሐጅን እንዲሠራ ነፍሱን ያስገደደ ሰው በሐጅ ውስጥ ሴትን መገናኘት ማመጽም ክርክርም የለም፡፡ الْحَجُّ أَشْهُرٌ مَّعْلُومَاتٌ ۚ فَمَن فَرَضَ فِيهِنَّ الْحَجَّ فَلَا رَفَثَ وَلَا فُسُوقَ وَلَا جِدَالَ فِي الْحَج

12ኛ ወር- ዙል-ሒጃህ ላይ የመጀመሪያዎቹ ዐሥሩ ሌሊቶች ናቸው። አምላካችን አሏህ በዚህ ወቅት ቤቱን እንዲጎበኙ ያዘዘው ለኢብራሂም ነው፦
22፥27 አልነውም፡- በሰዎችም ውስጥ በሐጅ ትእዛዝ ጥራ፡፡ እግረኞች ከየሩቅ መንገድ በሚመጡ ከሲታ ግመሎችም ሁሉ ላይ ሆነው ይመጡሃልና፡፡ وَأَذِّن فِي النَّاسِ بِالْحَجِّ يَأْتُوكَ رِجَالًا وَعَلَىٰ كُلِّ ضَامِرٍ يَأْتِينَ مِن كُلِّ فَجٍّ عَمِيقٍ
22፥26 *ለኢብራሂምም የቤቱን ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ «በእኔ ምንንም አታጋራ፣ ቤቴንም ለሚዞሩት፣ ለሚቆሙበት፣ ለሚያጎነብሱት እና በግንባራቸውም ለሚደፉት ንጹሕ አድርግላቸው» ባልነው ጊዜ አስታውስ*፡፡ وَإِذْ بَوَّأْنَا لِإِبْرَاهِيمَ مَكَانَ الْبَيْتِ أَن لَّا تُشْرِكْ بِي شَيْئًا وَطَهِّرْ بَيْتِيَ لِلطَّائِفِينَ وَالْقَائِمِينَ وَالرُّكَّعِ السُّجُودِ

“የሚዞሩት” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ጧዒፊን” طَّائِفِين መሆኑ ልብ አድርግ! "ጦዋፍ" طَواف የሚለው ቃል “ጧፈ” طَافَ ማለትም “ዞረ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ዙረት” ማለት ነው፥ ቤቱን በመጎብኘት ሰባት ጊዜ መዞር አምላካችን አሏህ ለኢብራሂም የሰጠው ትእዛዝ ነው፦
22፥29 ከዚያም እንደ ጠጉርና ጥፍር ያሉትን ትርፍ አካላቸውንና ዕድፋቸውን ያስወግዱ፡፡ ስለቶቻቸውንም ይሙሉ፤ በጥንታዊውም ቤት ይዙሩ፡፡ ثُمَّ لْيَقْضُوا تَفَثَهُمْ وَلْيُوفُوا نُذُورَهُمْ وَلْيَطَّوَّفُوا بِالْبَيْتِ الْعَتِيقِ

“ይዙሩ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “የጧወፉ” يَطَّوَّفُوا መሆኑ ሲሆን ቤቱን የሚዞሩት ዘዋሪዎች ደግሞ “ጧዒፍ” طَآئِف ይባላሉ፦
2፥125 ቤቱንም ለሰዎች መመለሻ እና ጸጥተኛ ባደረግን ጊዜ አስታውስ፡፡ ከኢብራሂምም መቆሚያ መስገጃን አድርጉ፡፡ ወደ ኢብራሂም እና ወደ ኢስማዒልም ቤቴን “ለዘዋሪዎቹ”፣ ለተቀማጮቹም ለአጎንባሾች ሰጋጆቹም አጥሩ ስንል ቃል ኪዳን ያዝን፡፡ وَإِذْ جَعَلْنَا الْبَيْتَ مَثَابَةً لِّلنَّاسِ وَأَمْنًا وَاتَّخِذُوا مِن مَّقَامِ إِبْرَاهِيمَ مُصَلًّى ۖ وَعَهِدْنَا إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ أَن طَهِّرَا بَيْتِيَ لِلطَّائِفِينَ وَالْعَاكِفِينَ وَالرُّكَّعِ السُّجُودِ

ለኢብራሂም በመጀመሪያ አገናዛቢ መደብ “ቤቴን” የሚለው የሚለው የዓለማቱ ጌታ አሏህ እንደሆነ ልብ አድርግ! ስለዚህ መካህ ያለው የአሏህን ቤት መጎብኘት መለኮታዊ ትእዛዝ ያለው ነው።
ዶክተር ዐቢይ ሆይ! በምን ሞራል እና ድፍረት ነው ባሌ ውስጥ እንደ ካዕባህ ሙሥሊሞች እንዲጎበኙት ለማድረግ በንግግር ሊቃጣህ የቻለው? "አወቅሽ አወቅሽ ሲሏት" የባሏን መጽሐፍ አጠበችው አሉ፥ ስለዚህ ከዚህ ንግግርህ ታረም። በማይመለከትህ ቦታ ወጧ እንዳማረላት ሴት በመንጦልጦል ጥልቅ አትበል!

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
መነኮሳት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

9፥31 ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለውን አንድን አምላክ ሊያመልኩ እንጂ ያልታዘዙ ሲኾኑ ሊቃውንቶቻቸውን እና መነኮሳታቸውን ከአላህ ሌላ አርባብ አድርገው ያዙ፥ እንዲሁ የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም ያዙ። ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው፡፡ اتَّخَذُوا أَحْبَارَهُمْ وَرُهْبَانَهُمْ أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ وَالْمَسِيحَ ابْنَ مَرْيَمَ وَمَا أُمِرُوا إِلَّا لِيَعْبُدُوا إِلَـٰهًا وَاحِدًا ۖ لَّا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ سُبْحَانَهُ عَمَّا يُشْرِكُونَ

አሏህን በጌትነቱ ከፍጡራን ነጥሎ ስልጣኑን መቀበል "ተውሒደ አር-ሩቡቢያህ" تَوْحِيد الرُبُوبِيّة ይባላል፥ "ሩቡቢያህ" رُبُوبِيّة ማለት "ጌትነት" ማለት ሲሆን አሏህ ብቻውን ነገርን ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣ ጌታ መሆኑን እና ሕግ በማውጣት ጽንፈ ዓለማትን የሚያስተናብር ጌታ መሆኑን የሚያስረዳ ነው፦
39፥62 አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው፡፡ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ
42፥21 ከሃይማኖት አላህ በእርሱ ያልፈቀደውን ለእነርሱ የደነገጉ ተጋሪዎች ለእነርሱ አሏቸውን? أَمْ لَهُمْ شُرَكَاءُ شَرَعُوا لَهُم مِّنَ الدِّينِ مَا لَمْ يَأْذَن بِهِ اللَّهُ

“ሸሪክ” شَرِيك ማለት “ተጋሪ” ማለት ነው፥ የሸሪክ ብዙ ቁጥር ደግሞ “ሹረካእ” شُرَكَاء ሲሆን “ተጋሪዎች” ማለት ነው። አሏህ በእርሱ ያልፈቀደውን ነገር ሐላል ማድረግ ለእነርሱ የደነገጉ በአላህ ሐቅ ላይ ተጋሪዎች አሏቸው፥ "የደነገጉ" ለሚለው የገባው ቃል “ሸረዑ” شَرَعُوا ሲሆን ሸሪዓህ መደንገጋቸው የሚያሳይ ቃል ነው። ለዚህ ነው “ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው” ነው ያለው፥ አይሁዳውያን ሊቃውንቶቻቸውን እንዲሁ ክርስቲያኖች መነኮሳታቸውን በአሏህ ላይ በማጋራት ጌቶች አድርገው ያዙ፦
9፥31 ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለውን አንድን አምላክ ሊያመልኩ እንጂ ያልታዘዙ ሲኾኑ ሊቃውንቶቻቸውን እና መነኮሳታቸውን ከአላህ ሌላ አርባብ አድርገው ያዙ፥ እንዲሁ የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም ያዙ። ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው፡፡ اتَّخَذُوا أَحْبَارَهُمْ وَرُهْبَانَهُمْ أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ وَالْمَسِيحَ ابْنَ مَرْيَمَ وَمَا أُمِرُوا إِلَّا لِيَعْبُدُوا إِلَـٰهًا وَاحِدًا ۖ لَّا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ سُبْحَانَهُ عَمَّا يُشْرِكُونَ
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3378
ዐዲይ ኢብኑ ሓቲም እንደተረከው፦ ”ወደ ነቢዩም”ﷺ” ስመጣ በአንገቴ ዙሪያ የወርቅ መስቀል ነበረኝ፥ እርሳቸውም፦ “ዐዲይ ሆይ! ይህንን ጣዖት ከአንተ አስወግድ” አሉ። ሱረቱል በራኣህ "ሊቃውንቶቻቸውን እና መነኮሳታቸውን ከአሏህ ሌላ አርባብ አድርገው ያዙ" የሚለው ሲነበብ ሰማዋቸው። እርሳቸውም፦ ለእነርሱ አያመልኳቸውም፥ ነገር ግን ሐላል ባደረጉላቸው ጊዜ ሐላል አርገው ይቀበሉታል። ሐራም ባደረጉላቸው ጊዜ ሐራም አርገው ይቀበሉታል” አሉ። عَنْ عَدِيِّ بْنِ حَاتِمٍ، قَالَ أَتَيْتُ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم وَفِي عُنُقِي صَلِيبٌ مِنْ ذَهَبٍ ‏.‏ فَقَالَ ‏”‏ يَا عَدِيُّ اطْرَحْ عَنْكَ هَذَا الْوَثَنَ ‏”‏ ‏.‏ وَسَمِعْتُهُ يَقْرَأُ فِي سُورَةِ بَرَاءَةََ ‏:‏ ‏(‏ اتَّخَذُوا أَحْبَارَهُمْ وَرُهْبَانَهُمْ أَرْبَابًا مِنْ دُونِ اللَّهِ ‏)‏ قَالَ ‏”‏ أَمَا إِنَّهُمْ لَمْ يَكُونُوا يَعْبُدُونَهُمْ وَلَكِنَّهُمْ كَانُوا إِذَا أَحَلُّوا لَهُمْ شَيْئًا اسْتَحَلُّوهُ وَإِذَا حَرَّمُوا عَلَيْهِمْ شَيْئًا حَرَّمُوهُ

“አርባብ” أَرْبَاب የሚለው ቃል "ረብ" رَبّ ለሚለው ብዙ ቁጥር ሲሆን "ጌቶች" ማለት ነው፥ አንድን ነገር ፈድር፣ ሙስተሐብ፣ ሙባሕ፣ መክሩህ፣ እና ሐራም ማለት የሚችለው ብቸኛው ባለ ሥልጣን አሏህ ብቻ ነው። አሏህም፦ "የሚያሰክር መጠጥ ከሰይጣን ሥራ የኾነ እርኩስ ብቻ ነው" ብሎአል፦
5፥90 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! "የሚያሰክር መጠጥ" ቁማርም ጣዖታትም አዝላምም ከሰይጣን ሥራ የኾኑ "እርኩስ ብቻ ናቸው፡፡ እርኩስንም ራቁት! ልትድኑ ይከጀላልና፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّمَا الْخَمْرُ وَالْمَيْسِرُ وَالْأَنصَابُ وَالْأَزْلَامُ رِجْسٌ مِّنْ عَمَلِ الشَّيْطَانِ فَاجْتَنِبُوهُ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ

ይህ ሆኖ ሳለ እኚህ መነኩሴ በተቃራኒው፦ "መጠጥ የሚፈቀደው ሁለት ይፈቀዳል፥ "መጠጥ እርኩስ ነው" ማለት ኃጢአት ነው። እግዚአብሔር "ቀምሳችሁ አመስግኑ" ብሏል፥ አእምሮን ይሰጣል። እግዚአብሔር በዚህ አልከለከለም" በማለት ከኪሳቸው ሐራሙን ሐላል እያሉ ነው።

በአሏህን ጌትነት ምንም ሳያሻርኩ የአሏህን ሥልጣን መቀበል ምንኛ መታደል ነው? ተውሒደ አር-ሩቡቢያህ ከፊላችንም ከፊሉን ከአሏህ ሌላ አርባብ አድርጎ ላይዝ ነው፦
3፥64 የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛ እና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፡፡ እርሷም አላህን እንጅ ሌላን ላናመልክ፣ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አርባብ አድርጎ ላይዝ ነው” በላቸው፡፡ قُلْ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ تَعَالَوْا إِلَىٰ كَلِمَةٍ سَوَاءٍ بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمْ أَلَّا نَعْبُدَ إِلَّا اللَّهَ وَلَا نُشْرِكَ بِهِ شَيْئًا وَلَا يَتَّخِذَ بَعْضُنَا بَعْضًا أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ ۚ

አሏህ በተውሒድ ጸንተው ከሚሞቱት ሙዋሒዱን ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አሥ-ሠላሙ ዐለይኩም ያ ጀመዓህ!

እንደሚታወቀው ሚሽነሪዎች ለማክፈር ተፍ ተፍ የሚሉት ከተማ ላይ ሳይሆን ገጠሩ ክፍል ነው፥ ያ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በኢትዮጵያ የሃይማኖት ንጽጽር ፈር ቀዳጅ እና ፋና ወጊ የሆነው ኡሥታዙና ሳዲቅ ሙሐመድ(አቡ ሃይደር) በገጠር መሣጂድ ማስገንባት፣ መድረሣዎች ማሠራት፣ ታዳጊ ሕፃናት በዱኑል ኢሥላም ዒልም መኮትኮት መርሐ ግብር ጉልኅ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። አሏህ ሥራውን በኢኽላስ ይቀበለው!

በምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት ይህንን መርሐ ግብር ገጠር ውስጥ የሚያደርገው በክራይ ሞተር ሳይክል ነው፥ ከወንድሞች እና ከእኅቶች በመጣው የተቀደሰ አሳብ ከፍ ያለ መኪና ለመግዛት ታስቧል። ይህም ከፍ ያለ መኪና ለቅንጦት ሳይሆን ገጠር ውስጥ ለደዕዋህ ነው።
በዚህ ኸይር ሥራ መሳተፍ የምትፈልጉ ከታች ባለው የራሱ የአካውንት ቁጥር የቻላችሁትን ማስገባት ትችላላችሁ!

Commercial Bank of Ethiopia
1000329226712
0911 10 32 31

ሼር በማድረግ አላፍትናችንን እንወጣ።
ወጀዛኩሙሏህ ኸይራ!

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
ከአፈር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

40፥67 እርሱ ያ ከአፈር ከዚያም ከፍትወት ጠብታ ከዚያም ከረጋ ደም የፈጠራችሁ ነው፡፡ هُوَ الَّذِي خَلَقَكُم مِّن تُرَابٍ ثُمَّ مِن نُّطْفَةٍ ثُمَّ مِنْ عَلَقَةٍ

አምላካችን አሏህ የሰውን ፍጥረት ከጭቃ የጀመረው ነው፦
32፥7 ያ የፈጠረውን ነገር ሁሉ ያሳመረው የሰውንም ፍጥረት ከጭቃ የጀመረው ነው፡፡ الَّذِي أَحْسَنَ كُلَّ شَيْءٍ خَلَقَهُ ۖ وَبَدَأَ خَلْقَ الْإِنسَانِ مِن طِينٍ

"የጀመረው" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! የመጀመሪያው ሰው አደም ከጭቃ መፈጠሩን የሚያሳይ ነው፥ ለመላእክት፦ "እኔ ሰውን ከጭቃ ፈጣሪ ነኝ" ብሎ አደምን ፈጠረው፦
38፥71 ጌታህ ለመላእክት፦ "እኔ ሰውን ከጭቃ ፈጣሪ ነኝ" ባለ ጊዜ አስታውስ፡፡ إِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي خَالِقٌ بَشَرًا مِّن طِينٍ

ጭቃ ደግሞ የሁለት ነገር ውቅር ነው፥ እርሱም የውኃ እና የአፈር ቅልቅል ነው። ለዚህ ነው አሏህ ሰውን ከአፈር እና ከውኃ እንደፈጠረ የሚናገረው፦
25፥54 እርሱም ያ ከውኃ ሰውን የፈጠረ፤ የዝምድናና የአማችም ባለቤት ያደረገው ነው፡፡ ጌታህም ቻይ ነው፡፡ وَهُوَ الَّذِي خَلَقَ مِنَ الْمَاءِ بَشَرًا فَجَعَلَهُ نَسَبًا وَصِهْرًا ۗ وَكَانَ رَبُّكَ قَدِيرًا
3፥59 አላህ ዘንድ የዒሣ ምሳሌ እንደ ኣደም ብጤ ነው፡፡ ከአፈር ፈጠረው፡፡ ከዚያም ለ"እርሱ" «ኹን» አለው፤ ኾነም፡፡ إِنَّ مَثَلَ عِيسَىٰ عِندَ ٱللَّهِ كَمَثَلِ ءَادَمَ ۖ خَلَقَهُۥ مِن تُرَابٍۢ ثُمَّ قَالَ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ

“ኸለቀ” خَلَقَ ማለትም “ፈጠረ” በሚለው ግሥ መዳረሻ ቅጥያ ላይ “ሁ” هُۥ ማለት “እርሱ” የሚል ተሳቢ ተውላጠ-ስም አለ፥ ይህም የስም ምትክ “ኣደም” ءَادَم የሚለውን የተጸውዖ ስም ተክቶ የመጣ ነው። “ከአፈር” ፈጠረው የሚለው ኣደምን እንጂ በፍጹም ዒሣን አለመሆኑን ለመረዳት አንድ የሰዋስው ሙግት እናቅርብ፦
2፥45 ”በመታገስ እና በሶላትም ተረዱ፡፡ እርሷም በፈሪዎች ላይ እንጅ በሌላው ላይ በእርግጥ ከባድ ናት፡፡ وَاسْتَعِينُوا بِالصَّبْرِ وَالصَّلَاةِ ۚ وَإِنَّهَا لَكَبِيرَةٌ إِلَّا عَلَى الْخَاشِعِينَ

“ሃ” َّهَا ማለትም “እርሷ” የሚለው ተውላጠ-ስም ተክቶ የመጣው ምንን ነው? “መታገስ” የሚለው ቃል ወይስ “ሶላት” የሚለው ቃል? ስልን መልሱ የቅርብ ቃል “ሶላት” ስለሆነ “እርሷ” የሚለው ተክቶ የመጣው “ሶላት” የሚለውን ቃል ነው፥ በተመሳሳይ የቅርብ ቃል “ኣደም” ስለሆነ “እርሱ” የሚለው ተክቶ የመጣው “ኣደም” የሚለውን ቃል ነው። አደም እና ዒሣ የተመሳሰሉበት ነጥብ የተፈጠሩበት ንጥረ-ነገር ሳይሆን የተፈጠሩበት ሁኔታ ነው፥ ሁለቱም በታምር ኹን በሚለው ቃል መፈጠራቸው ነው። አሏህ ኣደምን ከአፈር ፈጥሮ ኹን እንዳለው እንደሆነ ሁሉ ዒሣን ከመርየም ኹን በማለት ፈጥሮታል፦
3፥47 ፡-ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለች፡፡ ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፤ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል አላት*፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

እኛ ሁላችንም የአደም ልጆች ስለሆንን እና ከእርሱ ሥርወ-ግንድ የመጣን ስለሆንን ሥረ-መሠረታችን ታሳቢ በማድረግ ከአፈር እንደፈጠረን ይናገራል፦
40፥67 እርሱ ያ ከአፈር ከዚያም ከፍትወት ጠብታ ከዚያም ከረጋ ደም የፈጠራችሁ ነው፡፡ هُوَ الَّذِي خَلَقَكُم مِّن تُرَابٍ ثُمَّ مِن نُّطْفَةٍ ثُمَّ مِنْ عَلَقَةٍ

በተመሳሳይ ኤሊሁ አዳም ከተፈጠረ ከብዙ ዓመታት በኃላ፦ "ከጭቃ የተፈጠርሁ ነኝ" ብሏል፦
ኢዮብ 33፥6 እኔ ደግሞ "ከጭቃ የተፈጠርሁ ነኝ"።

ያ ማለት ቀጥታ ኤሊሁ ከጭቃ ተፈጥሯልን? "አይ ሥረ-መሠረቱ ጭቃ ነው ማለት ነው" ከተባለ እንግዲያውስ አሏህ "ከአፈር ወይም ከጭቃ ፈጠርኳችሁ" ቢል እውነት አይደለምን? እንኳን የተፈጠርንበት "ጭቃ" መባል ይቅርና ሰው በቁሙ ሥጋ ስለያዘ ኢሳይያስ፦ "እኛ ጭቃ ነን" ብሏል፦
ኢሳይያስ 64፥8 "እኛ ጭቃ ነን"፥ አንተም ሠሪያችን ነህ። እኛም ሁላችን የእጅህ ሥራ ነን።

እኛ ግን ሥጋ እንጂ ጭቃ አይደለለም፥ ቅሉ ግን የሰው ሥረ-መሠረቱ ጭቃ ስለሆን "እኛ ጭቃ ነን" መባል ያንን ዋቢ ያደረገ መሆኑን እንረዳለን። ቁርኣን ላይ "ዒሣ ከአፈር ተፈጠረ" የሚል ስለሌለ "ዒሣ ከአፈር አተፈጠረም" ወይም "የአደም ዘር አይደለም" በፍጹም አያሰኝም፥ ለምሳሌ ሐዋ ከአፈር እንደተፈጠረች ቁርኣን ላይ አይናገርም። ያ ማለት "ሐዋ ከአፈር አተፈጠረችም" ወይም "የአደም ዘር አይደለችም" በፍጹም አያሰኝም፥ አይ "ሐዋ ከአደም የተገኘች ስለሆነች የሰው ዘር ናት" ከተባለ እንግዲያውስ ዒሣም ከመርየም የተገኘ የመርየም ዘር ስለሆነ የሰው ዘር ነው። የመርየም እናት፦ "እርስዋን እና ዝርያዋን" በማለቷ ዒሣ የመርየም ዘር እንደሆነ አስረግጦ እና ረግጦ ያሳያል፦
3፥36 «እኔም እርስዋን እና ዝርያዋን ከተረገመው ሰይጣን በአንተ እጠብቃቸዋለሁ» وَإِنِّي أُعِيذُهَا بِكَ وَذُرِّيَّتَهَا مِنَ الشَّيْطَانِ الرَّجِيمِ

"ዙሪያህ" ذُرِّيَّة ማለት "ዘር"offspring" ማለት ሲሆን "ዙሪያህ" ذُرِّيَّة በሚለው መድረሻ ቅጥያ ላይ "ሃ" هَا የሚለው አንስታይ አገናዛቢ ተውላጠ ስም መርየምን አመላካች ስለሆነ ዒሣ የመርየም ዘር መሆኑን ቁልጭ እና ፍንትው አርጎ ያሳያል። አንድ ሰው አፈጣጠሩ ባይሎጂካል አይደለም ማለት ከወንድ እና ከሴት ተራክቦ የተገኘ አይደለም ማለት ነው፥ ባይሎጂካል ያልሆኑት አደም፣ ሐዋ እና ዒሣ ናቸው። ስለዚህ መንቦጫቦጩን እና መንቦራጨቁን ትታችሁ አበጥራችሁ እና አንጠርጥራችሁ አንብቡ! ሳታውቁ ወረንጦ እና ሜንጦ በመሆን ቁርኣን ላይ ቁጢጥ እና ፊጢጥ አትበሉ። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ከማንኛውም ሰው ጋር በበጎ ነገር እና አሏህን በመፍራትም መረዳዳት እንዳለብን አምላካችን አሏህ ይነግረናል፦
5፥2 *በበጎ ነገር እና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ፡፡ ግን በኃጢአት እና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና*፡፡ وَتَعَاوَنُوا عَلَى الْبِرِّ وَالتَّقْوَىٰ ۖ وَلَا تَعَاوَنُوا عَلَى الْإِثْمِ وَالْعُدْوَانِ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

አሏህን የማያስቆጣ ነገር ሁሉ ማድረግ "ተቅዋ" تَّقْوَىٰ ሲሆን ከዲን ውጪ ባለ የጋራ እሴት መረዳዳት ደግሞ በጎ ነገር ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን በኃጢአት እና ወሰንን በማለፍ መረዳዳት ደግሞ ሐራም ነው፦
5፥51 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አይሁዶችንና ክርስቲያኖችን ረዳቶች አድርጋችሁ አትያዙ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا الْيَهُودَ وَالنَّصَارَىٰ أَوْلِيَاءَ
4፥144 *”እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከምእምናን ሌላ ከሓዲዎችን ረዳቶች አድርጋችሁ አትያዙ*፤ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا الْكَافِرِينَ أَوْلِيَاءَ مِن دُونِ الْمُؤْمِنِينَ
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 24, ሐዲስ 2939
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”የሙሽሪክ እርዳታ አያስፈልገንም”* عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ إِنَّا لاَ نَسْتَعِينُ بِمُشْرِكٍ ‏

"አይሁድ እና ክርስቲያን" ሐይማኖትን ታሳቢ እና ዋቢ ያደረገ ኃይለ-ቃል ነው፥ ከኢሥላም ውጪ ያሉትን ከሓዲያን በሃይማኖት ረዳት አርጎ መያዝ ኃጢአት እና ወሰን ማለፍ ነው። ከሃይማኖት ውጪ በሆነው ማኅበራዊ እሴት በቅርብ ጎረቤት እና በሩቅ ጎረቤት መልካምን ሥራ እንድንሠራ ታዘናል።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ 
https://tttttt.me/Wahidcom
ዒሣ ቃል አይደለም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

4፥71 "የመርየም ልጅ አል-መሲሕ ዒሣ የአላህ መልእክተኛ ብቻ ነው፣ ወደ መርየም የጣላት «የኹን» ቃል ነው፣ ከእርሱ የኾነ መንፈስ ነው”*፡፡ إِنَّمَا الْمَسِيحُ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ اللَّهِ وَكَلِمَتُهُ أَلْقَاهَا إِلَىٰ مَرْيَمَ وَرُوحٌ مِّنْهُ

ከላም” كَلَام የሚለው ተባታይ መደብ "ከለመ" كَلَّمَ ማለትም "ተናገረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ንግግር"speech" ማለት ነው፥ "ከሊማህ" كَلِمَة ደግሞ የከላም አንስታይ መደብ ነው። አምላካችን አሏህ "ሙተከለም” مُتَكَلِّم ማለትም "ተናጋሪ"speaker ሲሆን አንድ ነገርን ማስገኘት ሲፈልግ በቃሉ "ኩን" كُن ይለዋል ወዲያውኑ ይሆናል፦
16፥40 ለማንኛውም ነገር መኾኑን በሻነው ጊዜ "ቃላችን" ለእርሱ “ኹን” ማለት ብቻ ነው፥ ወዲውም ይኾናል፡፡ إِنَّمَا قَوْلُنَا لِشَيْءٍ إِذَا أَرَدْنَاهُ أَن نَّقُولَ لَهُ كُن فَيَكُونُ

"ቃላችን" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! ክርስቲያኖች፦ "ፈጣሪ ልጅ አለው" ሲሉ አምላካችን አሏህ፦ “ነገርንም ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው “ኹን” ነው፥ ወዲያውም ይኾናል” የሚል ምላሽ ሰጠ፦
19፥35 ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል፡፡ مَا كَانَ لِلَّهِ أَن يَتَّخِذَ مِن وَلَدٍ ۖ سُبْحَانَهُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

መርየምም፦ "ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል?” ስትል፥ መለኮታዊ መልስ፦ "አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፥ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል" የሚል ነው፦
3፥47 ፡-ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለች፡፡ ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፥ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል አላት*፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

አንድ ጊዜ የየመን ክርስቲያኖች፦ "ዒሣ የአላህ ልጅ ካልሆነ እንግዲያውስ አባቱ ማን ነው? ብለው ጠየቁ፥ አምላካችን አሏህም ይህንን አንቀጽ አወረደ፦
3፥59 አላህ ዘንድ የዒሣ ምሳሌ እንደ ኣደም ብጤ ነው፡፡ ከአፈር ፈጠረው፡፡ ከዚያም ለ"እርሱ" «ኹን» አለው፤ ኾነም፡፡ إِنَّ مَثَلَ عِيسَىٰ عِندَ ٱللَّهِ كَمَثَلِ ءَادَمَ ۖ خَلَقَهُۥ مِن تُرَابٍۢ ثُمَّ قَالَ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ

“ኸለቀ” خَلَقَ ማለትም “ፈጠረ” በሚለው ግሥ መዳረሻ ቅጥያ ላይ “ሁ” هُۥ ማለት “እርሱ” የሚል ተሳቢ ተውላጠ-ስም አለ፥ ይህም የስም ምትክ “ኣደም” ءَادَم የሚለውን የተጸውዖ ስም ተክቶ የመጣ ነው። አደም እና ዒሣ የተመሳሰሉበት ነጥብ የተፈጠሩበት ንጥረ-ነገር ሳይሆን የተፈጠሩበት ሁኔታ ነው፥ ሁለቱም በታምር ኹን በሚለው ቃል መፈጠራቸው ነው። አሏህ ዒሣን ከመርየም ለመፍጠር ወደ እርሷ የጣላት ቃል "ኩን" كُن የምትል ናት፦
4፥71 "የመርየም ልጅ አል-መሲሕ ዒሣ የአላህ መልእክተኛ ብቻ ነው፣ ወደ መርየም የጣላት «የኹን» ቃል ነው፣ ከእርሱ የኾነ መንፈስ ነው”*፡፡ إِنَّمَا الْمَسِيحُ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ اللَّهِ وَكَلِمَتُهُ أَلْقَاهَا إِلَىٰ مَرْيَمَ وَرُوحٌ مِّنْهُ

የመጀመሪያው ዓረፍተ-ነገርን ላይ “ኢነማ” إِنَّمَا ማለት “ብቻ” ማለት ሲሆን ይህ ገላጭ ቅጽል ዒሣ የአሏህ መልእክተኛ እንጂ ሌላ እንዳልሆነ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
፨ሁለተኛው ዓረፍተ-ነገርን ላይ "ወ" وَ የሚል አርፉል አጥፍ ከመጀመሪያ ዓረፍተ-ነገርን ለመለየት የመጣ ነው፥ "ወ-ከሊመቱ-ሁ አልቃሃ ኢላ መርየም" وَكَلِمَتُهُ أَلْقَاهَا إِلَىٰ مَرْيَم ማለትም "ወደ መርየም የጣላት የይኹን ቃላት ናት" ማለት ነው። "ከሊማህ" كَلِمَة አንስታይ መደብ ናት። ይቺ ቃሊት አንስታይ መደብ ስለሆነች “አልቃ-ሃ” أَلْقَاهَا ማለትም “የጣላት” ተብላለች፥ ዒሣ ቃል ቢሆን ኖሮ በተባታይ መደብ “አልቃ-ሁ” أَلْقَاهُ ማለትም “የጣለው” ይባል ነበር። ቅሉ ግን ይህቺ የይኹን ቃላት መንስኤ ስትሆን ዒሣ ደግሞ ውጤት ነው። ቀደምት ሠለፎች የተረዱት በዚህ መልክ እና ልክ ነው፦
ተፍሢፉ ኢብኑ ከሲር 4፥171
ኢብኑ አቢ ሐቲም እንደዘገበው፦ “አሕመድ ኢብኑ ሢናነል ዋሢጢይ እንደተናገረው፦ “ሻዝ ኢብኑ የሕያ”ረ.ዐ.” እንዲህ አለ፦ ”ወደ መርየም የጣላት የሁን ቃሉም ነው” የሚለው “ቃሊቷ እራሷ ዒሣ አልሆነችም፥ ነገር ግን በቃሊቱ ዒሣ ተገኘ እንጂ”። وقال ابن أبي حاتم : حدثنا أحمد بن سنان الواسطي قال : سمعت شاذ بن يحيى يقول : في قول الله : ( وكلمته ألقاها إلى مريم وروح منه ) قال : ليس الكلمة صارت عيسى ، ولكن بالكلمة صار عيسى
፨ሦስተኛው ዓረፍተ-ነገርን ላይ "ወ" وَ የሚል አርፉል አጥፍ ከሁለተኛው ዓረፍተ-ነገርን ለመለየት የመጣ ነው፥ "ወ-ሩሑን ሚን-ሁ" وَرُوحٌ مِّنْهُ ማለትም "ከእርሱ የኾነ መንፈስ ነው" ይላል፥ “ሁ” هُ ማለትም “እርሱ” የተባለው አሏህ ሲሆን “ሁ” هُ በሚለው ተውላጠ-ስም መነሻ ላይ “ሚን” مِنْ የሚል መስተዋድድ የዒሣ ሩሕ ከአሏህ ዘንድ መሆኑን የሚያሳይ ነው። ይህንን የሚያስረዳ አንድ ተመሳሳይ የሰዋስው ሙግት እንይ፦
45፥13 ለእናንተም በሰማያት ያለውንና በምድርም ያለውን ሁሉ በመላ “ከ-እርሱ” ሲኾን የገራላችሁ ነው፡፡ وَسَخَّرَ لَكُم مَّا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا مِّنْهُ

“በሰማያት ያለውንና በምድርም ያለውን ሁሉ በመላ ከእርሱ ነው” የሚለው ይሰመርበት! “ሚን-ሁ” مِنْهُ ማለትም “ከ-እርሱ” የሚለው ፍጥረት ከአሏህ መሆኑን እንደሚያሳይ ሁሉ የዒሣም ሩሕ ከአሏህ መሆኑን ያሳያል፦
21፥91 ያችንም ብልቷን የጠበቀቺውን ”በእርሷም ውስጥ ከመንፈሳችን የነፋንባትን” እርሷንም ልጅዋንም ለዓለማት ተዓምር ያደረግናትን መርየምን አስታውስ፡፡ وَالَّتِي أَحْصَنَتْ فَرْجَهَا فَنَفَخْنَا فِيهَا مِن رُّوحِنَا وَجَعَلْنَاهَا وَابْنَهَا آيَةً لِّلْعَالَمِينَ

“ፊ-ሃ” فِيهَا ማለት “በ-እርሷ ውስጥ” ማለት ነው፥ “እርሷ” የተባለችው የዒሣ እናት መርየም ናት። በመርየም ማኅፀን ውስጥ ሩሕ ሲነፋ ይህ የተነፋው ሩሕ ከአሏህ ነው፥ አምላካችን አሏህ ወደ መርየም የነፋውን ሩሕ ወደራሱ በማስጠጋት “ሩሒ-ና” رُّوحِنَا ማለትም “መንፈሳችን” እንደሚል ሁሉ ወደ አደም አካል የነፋውንም ሩሕ ወደራሱ በማስጠጋት “ሩሒ-ሂ” رُّوحِهِ ይላል፦
32፥9 “ከዚያም ቅርጹን አስተካከለው፥ “በ-እርሱ ውስጥም” ከመንፈሱ ነፋበት”። ثُمَّ سَوَّاهُ وَنَفَخَ فِيهِ مِن رُّوحِهِ

ለአደም ሩሕ ስለተሰጠው “አደም የአሏህ መንፈስ ነው” እንደማንል ሁሉም ለዒሣም ሩሕ ስለተሰጠው “ዒሣ የአሏህ መንፈስ ነው” አይባልም። የዒሣም ሆነ የአደም አሊያም የሁላችንም ሩሕ ከአሏህ ነው፦
17፥85 ስለ ሩሕ ይጠይቁሃል፥ «ሩሕ ከጌታዬ ነገር ነው፥ ከዕውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም» በላቸው፡፡ وَيَسْأَلُونَكَ عَنِ الرُّوحِ ۖ قُلِ الرُّوحُ مِنْ أَمْرِ رَبِّي وَمَا أُوتِيتُم مِّنَ الْعِلْمِ إِلَّا قَلِيلًا

“ሩሕ ከጌታዬ ነገር ነው” የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! በዚህ አንቀጽ መሠረት የሁላችንም ሩሕ ከአፈር ሳይሆን ከጌታችን ከአላህ ነገር ነው፥ ያ ማለት “እኛ የአሏህ መንፈስ ነን” ማለት አይደለም። የሰው ሩሕ ደግሞ “ነገር” ነው፥ አሏህ የሁሉ “ነገር” ፈጣሪ ስለሆነ የማንም ሰው ሩሕ ፍጡር ነው፦
39፥62 አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው፡፡ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ

ቁርኣን ላይ፦"ዒሣ የአሏህ ቃል ነው ወይም ዒሣ የአሏህ መንፈስ ነው" የሚል ፍንጭ ይቅርና ሽታው የለም። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ነቢይነት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

33፥45 አንተ ነቢዩ ሆይ! እኛ መስካሪ፣ አብሳሪ እና አስጠንቃቂም አድርገን ላክንህ፡፡ يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ إِنَّا أَرْسَلْنَاكَ شَاهِدًا وَمُبَشِّرًا وَنَذِيرًا

"ነቢይ" نَبِيّ የሚለው ቃል "ነበአ" نَبَّأَ ማለትም "የሩቅ ወሬን አወራ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "የሩቅ ወሬ አውሪ" "ባለ ራእይ" "ነባይ" "ነባቢ" ማለት ነው፥ የሚወርድለት "የሩቅ ወሬ" ደግሞ "ነበእ" نَبَأ ይባላል። ይህንን የሩቅ ወሬ ለአንድ ነቢይ ከሦስት መንገድ በአንዱ ይወርድለታል፦
42፥51 ለሰው አላህ “በራእይ”፣ ወይም “ከግርዶ ወዲያ”፣ ወይም “መልክተኛን መልአክን” የሚልክ እና በፈቃዱ የሚሻውን “የሚያወርድለት” ቢሆን እንጅ በገሃድ “ሊያናግረው” ተገቢው አይደለም"፥ እርሱ የበላይ ጥበበኛ ነውና። وَمَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُكَلِّمَهُ ٱللَّهُ إِلَّا وَحْيًا أَوْ مِن وَرَآئِ حِجَابٍ أَوْ يُرْسِلَ رَسُولًۭا فَيُوحِىَ بِإِذْنِهِۦ مَا يَشَآءُ ۚ إِنَّهُۥ عَلِىٌّ حَكِيمٌۭ

እዚህ አንቀጽ ላይ እንደተጠቀሰው አምላካችን አሏህ አንድን ነቢይ የሚያናግረው አንደኛው መንገድ በራእይ የሚያናግረው ነው፥ "ራዕይ" ያ ነቢይ በሰመመን ወይም በተመስጦ ውስጥ ሆኖ አሏህ የሚያናግርበት መንገድ ነው። ሁለተኛው መንገድ አሏህ በቀጥታ የሚያናግረው ነው፥ ይህም ያለ ራዕይ ወይም ያለ መልአክ ሳይታይ ከግርዶ ወዲያ ሆኖ የሚያናግርበት መንገድ ነው።
ሦስተኛው መንገድ አላህ በመልአክ የሚያናግረው ነው። ይህንን ከተረዳን ዘንዳ አሏህ ይህንን የሩቅ ወሬ ለአንድ ሰው ሲያሳውቀው ያ ሰው ነቢይ ይባላል፥ አምላካችን አሏህ ነቢያችንን"ﷺ" በሦስተኛ መንገድ በመልአኩ ጂብሪል አናግሯቸዋል። አሏህ ወደ እርሳቸው ያወረደላቸው ቁርኣን ደግሞ "ነበእ" ነው፦
38፥67 በላቸው «እርሱ ቁርኣን ታላቅ ነበእ ነው፡፡ قُلْ هُوَ نَبَأٌ عَظِيمٌ

አምላካችን አሏህ በሦስተኛው መንገድ ለነቢያችንን"ﷺ"፦ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" ብሏል፦
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ "እኔንም ብቻ አምልኩኝ"፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ
21፥92 ይህች አንዲት መንገድ ስትሆን በእርግጥ ሃይማኖታችሁ ናት፤ "እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ"፡፡ إِنَّ هَٰذِهِۦٓ أُمَّتُكُمْ أُمَّةًۭ وَٰحِدَةًۭ وَأَنَا۠ رَبُّكُمْ فَٱعْبُدُونِ
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ

አምላካችን አሏህ ነቢያችንን"ﷺ" በሁለተኛ መደብ፦ "አንተ ነቢዩ ሆይ" በማለት እራሱ እንደላከ ለማመልከት "ላክንህ" በማለት "ለሰዎች ሁሉ" እንደተላኩ ይናገራል፦
33፥45 አንተ ነቢዩ ሆይ! እኛ መስካሪ፣ አብሳሪ እና አስጠንቃቂም አድርገን ላክንህ፡፡ يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ إِنَّا أَرْسَلْنَاكَ شَاهِدًا وَمُبَشِّرًا وَنَذِيرًا

ወደ ባይብል ስንመጣ ፈጣሪ በተለያየ መንገድ ለአንድ ነቢይ ይናገራል፥ በሕልም፣ በሌሊት ራእይ ወዘተ ማለት ነው፦
ኢዮብ 33፥14-15 አምላክ በአንድ መንገድ በሌላም ይናገራል፤ ሰው ግን አያስተውለውም። በሕልም፣ በሌሊት ራእይ፣ አፍላ እንቅልፍ በሰዎች ላይ ሲወድቅ፥ በአልጋ ላይ ተኝተው ሳሉ።

ፈጣሪ በራእይ የሚያናግረው ሰው ባለ ራእይ ይባል ነበር፥ ሰው አምላክን ለመጠየቅ ወደ ነቢይ ሲሄድ፦ "ኑ! ወደ ባለ ራእይ እንሂድ" ይል ነበር፦
1 ሳሙኤል 8፥9 ዛሬ ነቢይ የሚባለው ቀድሞ ባለ ራእይ ይባል ነበርና አስቀድሞ በእስራኤል ዘንድ ሰው አምላክን ለመጠየቅ ሲሄድ፦ "ኑ! ወደ ባለ ራእይ እንሂድ" ይል ነበር።

አምላክ ነቢያትን ማለትም አብርሃምን፣ ያዕቆብን፣ ኢሳይያስን፣ ዳንኤልን፣ ሙሴን በራእይ አራግሯል፦
ዘፍጥረት 15፥1 ከዚህ ነገር በኋላም የያህዌህ ቃል በራእይ ወደ አብራም መጣ።
ዘፍጥረት 46፥2 አምላክም በሌሊት ራእይ፦ "ያዕቆብ ያዕቆብ" ብሎ ለእስራኤል ተናገረው።
ኢሳይያስ 1፥1 የአሞጽ ልጅ የኢሳይያስ ራእይ።
ዳንኤል 2፥19 የዚያን ጊዜም ምሥጢሩ በሌሊት ራእይ ለዳንኤል ተገለጠለት።
ዘጸአት 3፥3 ሙሴም፦ ልሂድና ቍጥቋጦው ስለ ምን አልተቃጠለም ይህን ታላቅ "ራእይ" ልይ አለ።

ሙሴ "ታላቅ ራእይ ልይ" ያለው መልአክ ተልኮ በመልአኩ ፈጣሪ፦ "እኔ የአባትህ አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅም አምላክ፣ የያዕቆብም አምላክ ነኝ" በማለት የተነገረውን ነው፦
ዘጸአት 3፥2 የያህዌህም መልአክ በእሳት ነበልባል በእሾህ ቍጥቋጦ መካከል ታየው።
ዘጸአት 3፥6 ደግሞም፦ እኔ የአባትህ አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅም አምላክ፣ የያዕቆብም አምላክ ነኝ" አለው።
የሐዋርያት ሥራ 7፥35 ሙሴን በቍጥቋጦው በታየው በመልአኩ እጅ አምላክ ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው።

ስለዚህ "ፈጣሪ ከራእይ ወይም ከመልአክ ውጪ በቀጥታ ያለ ራእይ እና ያለ መልአክ አንድን ነቢይ ካላናገረ" ብሎ ያዙኝ ልቀቁኝ፣ አሸሼ ገዳዬ፣ እንቧ ከረዮ፣ እሪ ከረዮ ማለት አያዋጣም፥ ፈጣሪ አብዛኛው ነቢያት በራእይ ዕውቀት ይገልጥላቸዋል ወይም በሕልም ያናግራቸዋል እንጂ ቀጥታ አያናግራቸውም፦
ዘኍልቍ 12፥6 እርሱም፦ ቃሌን ስሙ፤ በመካከላችሁ ነቢይ ቢኖር፥ እኔ ያህዌህ በራእይ እገለጥለታለሁ፥ ወይም በሕልም እናገረዋለሁ።

ሙሴን ቢሆን በነቢይነቱ መጀመሪያ ላይ ሳይሆን መሃል ላይ ቀጥታ ያለ ራእይ እና ያለ መልአክ ቢያናግረውም ግልጠተ መለኮት የመጣለት ግን በመልአክ ነው፦
ዘኍልቍ 12፥7-8 ባሪያዬ ሙሴ ግን እንዲህ አይደለም፤ እርሱ በቤቴ ሁሉ የታመነ ነው። እኔ አፍ ለአፍ በግልጥ እናገረዋለሁ።

ስለዚህ ቁርኣን የአሏህ ንግግር ነው፥ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" እያለ የሚናገረው አሏህ ነው፥ የአምልኮ ሐቅ የሚገባውም ብቻውን የፈጠረ ብቻ እንደሆነ እራሱ አሏህ በመጀመሪያ መደብ "ጂንን እና ሰውን ሊያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም" በማለት ተናግሯል፦
51፥56 ጂንን እና ሰውን ሊያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አማልክት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

21፥22 በሁለቱ (በሰማያትና በምድር) ውስጥ ከአላህ ሌላ አማልክት በነበሩ ኖሮ በተበላሹ ነበር፡፡ የዐርሹ ጌታ አላህም ከሚሉት ሁሉ ጠራ፡፡ لَوْ كَانَ فِيهِمَا آلِهَةٌ إِلَّا اللَّهُ لَفَسَدَتَا ۚ فَسُبْحَانَ اللَّهِ رَبِّ الْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ

በሄለናዊ ግሪክ ሥነ-ተረት"hellenistic Greek mythology" ስለ አማልክት ያላቸው እሳቦት በሦስት ይከፈላል፥ አንደኛ አባት የሆነ አምላክ፣ ሁለተኛ ልጅ የሆነ አምላክ እና ሦስተኛ መንፈስ የሆነ አምላክ ነው።
"ቴዎስ" θεός ማለት በግሪክ ኮይኔ "አምላክ" ማለት ነው፥ የቴዎስ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ቴዎኢ" Θεοί ሲሆን "አማልክት" ማለት ነው። "ዘዩስ" Ζεύς የአማልክት ንጉሥ፣ የሰማዩ አባት ሲሆን ማዕረጉ "ፓተር" πατήρ ማለትም "አባት" ነው፥ "ቴዎ ፓተር" Θεῷ πατήρ ማለት "አምላክ አባት"God the father" ማለት ነው።

"ሄሚሱስ" ἥμισυς ማለት "ከፊል"demi" ማለት ሲሆን "ሄሚቴዎስ" ἡμιθεός" ማለት "ከፊል አምላክ" ማለት ነው፥ ለምሳሌ "ሄራክለስ" Ἡρακλῆς የተባለው አምላክ ከዘይዩስ የተገኘ የዘዩስ ልጅ ሲሆን ማዕረጉ "ሁዮስ" υἱός ማለትም "ልጅ" ነው። "ቴዎ ሁዮስ" Θεῷ υἱός ማለት "አምላክ ልጅ"God the son" ማለት ነው። ሄራክለስ አምላክ ከሆነው ከአባቱ ከዘዩስ ስለተወለደ አምላክ ቢሆንም ሰው ከሆነችው ከእናቱ "አልክሜኔ" Ἀλκμήνη ከተባለች ሴት ሰው ስለተገኘ ሰው ነው፥ አምላክ እና ሰው በአንድ ማንነት"hypostatic union" ያለ ነው።

"ዳይሞን" δαίμων ማለት በግሪክ ኮይኔ "አምላክ" ማለት ነው፥ የዳይሞን ብዙ ቁጥር ደግሞ "ዳይሞንዮን" δαιμονίων ሲሆን "አማልክት" ማለት ነው፦
የሐዋርያት ሥራ 17፥18 "አዲሶችን አማልክት የሚያወራ ይመስላል" Ξένων δαιμονίων δοκεῖ καταγγελεὺς εἶναι·

ኢስጦኢኮች ከተባሉት ፈላስፎች "አማልክት" ለሚለው የተጠቀሙበት ቃል "ዳይሞንዮን" δαιμονίων እንደሆነ ልብ አድርግ!
"አጋቶስ" ἀγαθός ማለት "ቅዱስ" "ሰናይ" "መልካም" "ጥሩ" "ደግ" ማለት ነው፥ "አጋቶዳይሞን" ἀγαθοδαίμων ማለት "ቅዱስ አምላክ" ማለት ነው።
"ካኮስ" κακός ማለት "ርኩስ" "እኩይ" "መጥፎ" "ክፉ" "ከይሲ" ማለት ነው፥ "ካኮዳይሞን" κακοδαίμων ማለት "ርኩስ አምላክ" ማለት ነው።
"ፕኒውማ" πνεῦμα ማለት "መንፈስ" ማለት ነው፥ የፕኒውማ ብዙ ቁጥር "ፕኒውማታ" πνεύματα ሲሆን "መናፍስት(መንፈሶች) ማለት ነው። ለምሳሌ፦ ከዘንዶውም አፍ፣ ከአውሬው አፍ እና ከሐሰተኛውም ነቢይ አፍ የሚወጡ "የአማልክት መናፍስት" ተብለዋል፦
ራእይ 16፥14 ምልክት እያደረጉ የአማልክት መናፍስት ናቸውና። εἰσὶν γὰρ πνεύματα δαιμονίων ποιοῦντα σημεῖα,

"አማልክት" ለሚለው የገባው የግሪኩ ቃል "ዳይሞንዮን" δαιμονίων እንደሆነ ልብ አድርግ! እነዚህ ምድባቸው "ካኮዳይሞን" κακοδαίμων ማለትም "ርኩስ አምላክ" ነው፥ "ርኩስ መንፈስ" ወይም "ርኵሳን መናፍስት" በመባል ይታወቃሉ፦
ማቴዎስ 12፥43 "ርኩስ መንፈስ" ግን ከሰው በወጣ ጊዜ ዕረፍት እየፈለገ ውኃ በሌለበት ቦታ ያልፋል፥ አያገኝምም።
ራእይ 16፥13 ከዘንዶውም አፍ፣ ከአውሬው አፍ እና ከሐሰተኛውም ነቢይ አፍ ጓጕንቸሮች የሚመስሉ ሦስት "ርኵሳን መናፍስት" ሲወጡ አየሁ።

"ቅዱሳን መናፍስት" "ቅዱሳን አማልክት" አለቃቸው "አጋቶዳይሞን" ἀγαθοδαίμων ማለትም "ቅዱስ አምላክ" ሲሆን "ፕኒውማ ሐጊዎን" πνεῦμα ἁγίων ማለትም "ቅዱስ መንፈስ" ይሉታል፥ ይህን "ቴዎ ፕኒውማ ሐጊዎን" Θεῷ πνεῦμα ἁγίων ማለትም "አምላክ መንፈስ ቅዱስ"God the holy Spirit" ይሉታል።

ክርስትና ሦስተኛ ክፍለ ዘመን ላይ በበግሪክ እና በሮም የተጀመረው የአሞኒየስ"Ammonius" እና የተማሪው ፕሎቲኒየስ"Plotinus" ፍልስፍና ተጽዕኖ ላይ ወድቋል፥ የአሞኒየስ እና የተማሪው ፕሎቲኒየስ ፍልስፍና "አዲሱ አፍላጦናዊነት"Neoplatonism" ነው።
በ325 ድኅረ ልደት በንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ሊቀ መንበርነት የተካሄደው የኒቂያ ጉባኤ ኢየሱስን "ሆ ቴዎስ ሆ ሁዎስ" Ο Θεός ο γιος ማለትም "እግዚአብሔር ወልድ"God the Son" የሚል የአቋም መግለጫ መስጠቱ እና "ቴዎን ኤክ ቴዉ" Θεὸν ἐκ Θεοῦ ማለትም "ከአምላክ የተገኘ አምላክ ነው" ማለቱ የጤና ይሆን?
በ381 ድኅረ ልደት በንጉሥ ቀዳማይ ቴዎዶስዮስ ሊቀ መንበርነት የተካሄደው የቆስጠንጢኒያ ጉባኤ መንፈስ ቅዱስን "ሆ ቴዎስ ሆ ኑማ ቶ ሐጊዎን" Ο Θεός ο Πνεῦμα τὸ Ἅγιον ማለትም "እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ"God the Holy Spirit" ማለቱ የጤና ይሆን?

አምላካችን አሏህ ምንም ልጅን አልወለደም፥ ከእርሱም ጋር አንድም አምላክ የለም፡፡ ያን ጊዜ ሌላ አምላክ በነበረ ኖሮ አምላክ ሁሉ በፈጠረው ነገር በተለየ ነበር፥ ከፊላቸውም በከፊሉ ለይ በላቀ ነበር፡፡ አሏህ ከሚሉት ነገር ሁሉ ጠራ፦
23፥91 አላህ ምንም ልጅን አልወለደም፥ ከእርሱም ጋር አንድም አምላክ የለም፡፡ ያን ጊዜ ሌላ አምላክ በነበረ ኖሮ አምላክ ሁሉ በፈጠረው ነገር በተለየ ነበር፡፡ ከፊላቸውም በከፊሉ ለይ በላቀ ነበር፡፡ አላህ ከሚሉት ነገር ሁሉ ጠራ፡፡ مَا اتَّخَذَ اللَّهُ مِن وَلَدٍ وَمَا كَانَ مَعَهُ مِنْ إِلَـٰهٍ ۚ إِذًا لَّذَهَبَ كُلُّ إِلَـٰهٍ بِمَا خَلَقَ وَلَعَلَا بَعْضُهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ ۚ سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يَصِفُونَ

በሰማያት እና በምድር ውስጥ ከአሏህ ሌላ አማልክት በነበሩ ኖሮ በተበላሹ ነበር፥ የዐርሹ ጌታ አላህም ከሚሉት ሁሉ ጠራ፦
21፥22 በሁለቱ (በሰማያትና በምድር) ውስጥ ከአላህ ሌላ አማልክት በነበሩ ኖሮ በተበላሹ ነበር፡፡ የዐርሹ ጌታ አላህም ከሚሉት ሁሉ ጠራ፡፡ لَوْ كَانَ فِيهِمَا آلِهَةٌ إِلَّا اللَّهُ لَفَسَدَتَا ۚ فَسُبْحَانَ اللَّهِ رَبِّ الْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ነቢዩ ዙልኪፍል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

21፥85 ኢስማዒልን፣ ኢድሪስን፣ ዙልኪፍልን አስታውስ! ሁሉም ከታጋሾቹ ናቸው፡፡ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِدْرِيسَ وَذَا الْكِفْلِ ۖ كُلٌّ مِّنَ الصَّابِرِينَ

"ዙ" ذَا ማለት በአገዛዛቢ መደብ የመጣ ሲሆን "ባለቤት" ማለት ነው፥ "ኪፍል" كِفْل ማለት "ክፍል" ማለት ሲሆን "ዙልኪፍል" ذَا الْكِفْل ማለት "የክፍል ባለቤት" ማለት ነው። ይህ ነቢይ በባቢሎን ምርኮ ጊዜ ዒራቅ ውስጥ ነበረ፥ እዛ የተወሰነ ክፍል ተሰቶት ይኖር ነበር። ያ የኖረበት ቦታ "ኪፍል" كِفْل ሲባል ነቢዩ ደግሞ "የክፍል ባለቤት" ተብሏል፥ ይህ ነቢይ በቁርኣን ውስጥ ልክ እንደ ኢድሪሥ በማዕረግ ስም ተጠርቷል። የተጸውዖ ስሙ "ሒዝቂያል" حِزْقِيَال ይባላል፥ አይሁዳውያን ኪፍል በሚባል ቦታ የሕዝቅኤልን መቃብር ይጎበኙ ነበር። አምላካችን አሏህ ዙልኪፍልን ከኢስማዒል እና ከኢድሪስ ጋር ያወሳዋል፦
21፥85 ኢስማዒልን፣ ኢድሪስን፣ ዙልኪፍልን አስታውስ! ሁሉም ከታጋሾቹ ናቸው፡፡ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِدْرِيسَ وَذَا الْكِفْلِ ۖ كُلٌّ مِّنَ الصَّابِرِينَ
21፥86 ከችሮታችንም ውስጥ አገባናቸው፡፡ እነርሱ ከመልካሞቹ ናቸውና፡፡ وَأَدْخَلْنَاهُمْ فِي رَحْمَتِنَا ۖ إِنَّهُم مِّنَ الصَّالِحِينَ

አሏህ ኢስማዒልን፣ ኢድሪስን፣ ዙልኪፍልን ከችሮታው ውስጥ አገባቸው፥ ይህም ችሮታ ወሕይ በማውረድ የሚሰጥ ነቢይነት ነው፦
3፥74 በችሮታው (በነቢይነት) የሚሻውን ይመርጣል፡፡ አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው፡፡ يَخْتَصُّ بِرَحْمَتِهِ مَن يَشَاءُ ۗ وَاللَّهُ ذُو الْفَضْلِ الْعَظِيمِ
2፥90 አላህ ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ ከችሮታው (ራእይን) ማውረዱን በመመቅኘት አላህ ባወረደው ነገር መካዳቸው ነው፡፡ أَن يَكْفُرُوا بِمَا أَنزَلَ اللَّهُ بَغْيًا أَن يُنَزِّلَ اللَّهُ مِن فَضْلِهِ عَلَىٰ مَن يَشَاءُ مِنْ عِبَادِهِ

አሏህ "ባሪያችንን አዩብን፣ ባሮቻችንን ኢብራሂምን፣ ኢሥሐቅን፣ የዕቁብን አውሳ" ካለ በኃላ በማለት "ኢስማዒልን፣ አልየሰዕን፣ ዙልኪፍልን አውሳ! በማለት ከነቢያት ምድብ ውስጥ ይከታቸዋል፥ ኢስማዒል፣ አልየሰዕ፣ ዙልኪፍል ከበላጮቹ ናቸው። አሏህ መጽሐፍን፣ ጥበብን እና ነቢይነትን ሰቷቸዋል፦
38፥48 ኢስማዒልን፣ አልየሰዕን፣ ዙልኪፍልን አውሳ! ሁሉም ከበላጮቹ ናቸው፡፡ وَاذْكُرْ إِسْمَاعِيلَ وَالْيَسَعَ وَذَا الْكِفْلِ ۖ وَكُلٌّ مِّنَ الْأَخْيَارِ
6፥89 እነዚህ እነዚያ መጽሐፍን፣ ጥበብን እና ነቢይነትን የሰጠናቸው ናቸው፡፡ أُولَـٰئِكَ الَّذِينَ آتَيْنَاهُمُ الْكِتَابَ وَالْحُكْمَ وَالنُّبُوَّةَ

አምላካችን አሏህ በትንሳኤ ቀን በእነርሱ ላይ ከለገሳቸው ከነቢያት ጋር ያማረ ጓደኛ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የኤፍራጥስ ወንዝ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

53፥4 እርሱ ንግግሩ የሚወረድ ራእይ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ إِنْ هُوَ إِلَّا وَحْيٌ يُوحَىٰ

"ሷሒብ" صَاحِب ማለት "ጓደኛ" "ሞክሼ" "ባልደረባ" ማለት ሲሆን ነቢያችን"ﷺ" ለመጡበት ሕዝብ ባልደረባ ነበሩ፥ የመጡበት ሕዝብ ነቢያችንን"ﷺ" እንደተሳሳቱ እና እንደጠመሙ ሰው አሊያም ዕብድ አርጎ ስላያቸው አምላካችን አሏህ፦ "ባልደረባችሁ አልተሳሳተም፤ አልጠመመም። በፍጹም ዕብድ አይደለም" በማለት ለተሳላቂዎች መልስ ይሰጥ ነበር፦
53፥2 ባልደረባችሁ አልተሳሳተም፤ አልጠመመም፡፡ مَا ضَلَّ صَاحِبُكُمْ وَمَا غَوَىٰ
81፥22 ባልደረባችሁ በፍጹም ዕብድ አይደለም፡፡ وَمَا صَاحِبُكُم بِمَجْنُونٍ

የመጡበት ሕዝብ ነቢያችንን"ﷺ" እንደተሳሳቱ እና እንደጠመሙ ሰው አሊያም ዕብድ አርጎ ያየበት ምክንያት ነቢያችን"ﷺ" ያዩት እና የሚናገሩት የሩቅ ነገር ወሬ ነው። ይህ የሩቅ ነገር ወሬ ምን ነበር? "ውኃን ከጥሩ ነገርን ከሥሩ" የሚለውን አገርኛ ብሒል ይዘን እንጀምር! ጂብሪል ወደ ነቢያችን”ﷺ” የሚመጣው በሚወዱት ባልደረባ በዲሕያህ ኢብኑ ኸሊፋህ በሚባል ሰው ተመስሎ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 66, ሐዲስ 2
አቡ ዑስማን እንደተረከው፦ “ጂብሪል ወደ ነቢዩ”ﷺ” ሲመጣ ኡሙ ሠላማህ ከእርሳቸው ጋር ነበረች፥ ጂብሪል መናገር ጀመረ። ነቢዩም”ﷺ”፦ “ኡሙ ሠላማህ ይህ ማን ነው? አሉ፥ እርሷም፦ “ይህ ዲሕያህ ነው” አለች። ጂብሪል በሄደ ጊዜ እርሷም፦ “ወሏሂ! በነቢዩ”ﷺ” ሑጥባህ ላይ ስለ ጂብሪል ዜና እስኪነግሩን ድረስ ከዲሕያህ በስተቀር ሌላ ማንንም አላሰብኩም ነበር”። عَنْ أَبِي عُثْمَانَ، قَالَ أُنْبِئْتُ أَنَّ جِبْرِيلَ، أَتَى النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم وَعِنْدَهُ أُمُّ سَلَمَةَ فَجَعَلَ يَتَحَدَّثُ فَقَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم لأُمِّ سَلَمَةَ ‏ “‏ مَنْ هَذَا ‏”‌‏.‏ أَوْ كَمَا قَالَ قَالَتْ هَذَا دِحْيَةُ‏.‏ فَلَمَّا قَامَ قَالَتْ وَاللَّهِ مَا حَسِبْتُهُ إِلاَّ إِيَّاهُ حَتَّى سَمِعْتُ خُطْبَةَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم يُخْبِرُ خَبَرَ جِبْرِيلَ أَوْ كَمَا قَالَ،

ነቢያችን"ﷺ" በመንገድ ጉዞ እያሉ ጂብሪል በተፈጥሮ ቅርጹ ግን ለመጀመሪያ ጊዜ ወርዶ በሰማይ እና በምድር መካከል ተቀምጦ አይተውታል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 78, ሐዲስ 238
ጃቢ ኢብኑ ዐብደሏህ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰማው ብሎ እንደተረከው፦ “እርሳቸውም እንዲህ አሉ፦ “ከዚያም ወሕይ ወደ እኔ ተቋረጦ ነበር፥ ድንገት እየተጓዝኩኝ እያለ ከሰማይ ድምፅ ሰማሁኝ። እራሴን ቀና አድርጌ ወደ ሰማይ ስመለከት በሒራእ ዋሻ የጎበኘኝ መልአክ በሰማይ እና በምድር መካከል በመንበር ላይ ተቀምጦ አየሁት”። عَنِ جَابِرُ بْنُ عَبْدِ اللَّهِ، أَنَّهُ سَمِعَ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ “‏ ثُمَّ فَتَرَ عَنِّي الْوَحْىُ، فَبَيْنَا أَنَا أَمْشِي سَمِعْتُ صَوْتًا مِنَ السَّمَاءِ، فَرَفَعْتُ بَصَرِي إِلَى السَّمَاءِ فَإِذَا الْمَلَكُ الَّذِي جَاءَنِي بِحِرَاءٍ قَاعِدٌ عَلَى كُرْسِيٍّ بَيْنَ السَّمَاءِ وَالأَرْضِ ‏”‌‏.‏

ነቢያችን"ﷺ" ጂብሪልን በተፈጥሮ ቅርጹ ለሁለተኛ ጊዜ ያዩት ደግሞ ሲድረቱል ሙንተሃ ላይ ነው፥ “ሲድረቱል ሙንተሃ” سِدْرَة الْمُنْتَهَى የሰባተኛው ሰማይ መጨረሻ ሊታለፍ የማይችል ድንበራዊ ዛፍ ነው፦
53፥14 “በሲድረቱል ሙንተሃ አጠገብ አይቶታል”። عِندَ سِدْرَةِ الْمُنتَهَىٰ
53፥15 “እርሷ ዘንድ መኖሪያይቱ ጀናህ ያለች ስትኾን”፡፡ عِندَهَا جَنَّةُ الْمَأْوَىٰ
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 53፥13-15 “በሌላይቱም መውረድ ጊዜ በእርግጥ አይቶታል፣ በሲድረቱል ሙንተሃ አጠገብ አይቶታል፣ እርሷ ዘንድ መኖሪያይቱ ጀናህ ያለች ስትኾን” የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ “ጂብሪልን አይቼዋለው፥ ስድስት መቶ ክንፍ አለው”። وَلَقَدْ رَءَاهُ نَزْلَةً أُخْرَى – عِندَ سِدْرَةِ الْمُنتَهَى – عِندَهَا جَنَّةُ الْمَأْوَى قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله «رَأَيْتُ جِبْرِيلَ وَلَهُ سِتُّمِائَةِ جَنَاحٍ »

“ሙንተሃ” مُنتَهَىٰ የሚለው ቃል “ነሃ” نَهَىٰ ማለትም “ከለከለ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ክልክል” ማለት ነው፥ የሰባተኛው ሰማይ ድንበሩ የሢድራህ ዛፍ ናት። የብርታት ባለቤት የኾነውን ጂብሪል በላይኛውና በግልጹ አድማስ በሲድረቱል ሙንተሃ ላይ ኾኖ ተደላድሎ ሲወርድ አዩት፦
53፥6 “የዕውቀት ባለቤት የኾነው ተደላደለም”፡፡ ذُو مِرَّةٍ فَاسْتَوَىٰ
53፥7 “እርሱ በላይኛው አድማስ ኾኖ”፡፡ وَهُوَ بِالْأُفُقِ الْأَعْلَىٰ
81፥23 “በግልጹ አድማስም በእርግጥ አይቶታል”፡፡ وَلَقَدْ رَآهُ بِالْأُفُقِ الْمُبِينِ

ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ወደ ሲድረቱል ሙንተሃ ሲወጡ አራት ወንዞችን አይተዋል፥ እነዚህም አራት ወንዞች ሠይሓን፣ ጀይሓን፣ ፉራት እና ኒል ናቸው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 74, ሐዲስ 36
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “አራቱን ወንዞች ባየሁ ጊዜ ወደ ሢድራን ወጣሁኝ”። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ رُفِعْتُ إِلَى السِّدْرَةِ فَإِذَا أَرْبَعَةُ أَنْهَارٍ،
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 53, ሐዲስ 30
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ሠይሓን፣ ጀይሓን፣ፉራት እና ኒል ሁሉም ከጀናህ ወንዞች ናቸው"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ سَيْحَانُ وَجَيْحَانُ وَالْفُرَاتُ وَالنِّيلُ كُلٌّ مِنْ أَنْهَارِ الْجَنَّةِ ‏"‏ ‏.‏

"ሠይሓን" سَيْحَان ማለት "ፊሶን" ማለት ሲሆን፣ "ጀይሓን" جَيْحَان ማለት "ጤግሮስ" ማለት ሲሆን፣ "ፉራት" فُرَات ማለት "ኤፍራስጥ" ማለት ሲሆን፣ "ኒል" نِّيل ማለት ደግሞ "ግዮን" ማለት ነው። አሏህ ሰማይ ላይ ያሉ ሥርዓት በምድር ላይም አርጓል፥ ለምሳሌ፦ በሰባተኛ ሰማይ ከዕባህ ንድፍ የሆነበት ሰባ ሺህ መላእክት አምልኮ የሚፈጽሙበት የደመቀው ቤት "በይቱል መዕሙር" بَيْت الْمَعْمُور ሲባል በተመሳሳይ ምድር ላይ መካህ የሚገኘው የአሏህ ቤት "በይቱል መዕሙር" بَيْت الْمَعْمُور ተብላል፦
52፥4 በደመቀው ቤት እምላለው፡፡ وَالْبَيْتِ الْمَعْمُورِ
በተመሳሳይ አሏህ በሰማይ ላይ እንዳሉት ወንዞች በምድር ላይ ወንዞች አድርጓል፥ ከዚያው ውስጥ በሐዲስ በስም የተጠቀሰ ወንዝ የኤፍራጥስ ወንዝ ነው። ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" መስጴጦምያ ስለሚገኘው ስለ ኤፍራጥስ ወንዝ እንዲህ በማለት ትንቢት ተናግረዋል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 54, ሐዲስ 38
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ሰዓቲቱ የኤፍራጥስ ወንዝ የወርቅ ተራራ እስኪገልጥ ድረስ ቢደርቅና በእርሱ ጉዳይ ሰዎች ቢዋጉ እንጂ አትቆምም"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ لاَ تَقُومُ السَّاعَةُ حَتَّى يَحْسِرَ الْفُرَاتُ عَنْ جَبَلٍ مِنْ ذَهَبٍ يَقْتَتِلُ النَّاسُ عَلَيْهِ
ሪያዱ አስ-ሷሊሒን መጽሐፍ 18, ሐዲስ 15
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ሰዓቲቱ የኤፍራጥስ ወንዝ የወርቅ ተራራ እስኪገልጥ ድረስ ቢደርቅና ሰዎች በእርሱ ጉዳይ ቢዋጉ እንጂ አትቆምም"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ "‏ لاَ تَقُومُ السَّاعَةُ حَتَّى يَحْسِرَ الْفُرَاتُ عَنْ جَبَلٍ مِنْ ذَهَبٍ فَيَقْتَتِلُ النَّاسُ عَلَيْهِ ‏"‏ ‏.‏

ከሰዓቲቱ ምልክት አንዱ የኤፍራጥስ ወንዝ መድረቅ ከሆነ ይህ ትንቢት በዘመናችን እየተፈጸመ ነው። የኤፍራጥስ ወንዝ እየደረቀ ነው፥ የወርቁ ተራራ ኢንሻሏህ ሲገለጥ ታላቁ ጦርነት ይመጣል። አምላካችን አሏህ ይህንን ገይብ ለነቢዩ"ﷺ" አሳውቋል፥ "ገይብ" غَيْب የሚለው ቃል "ጋበ" غَابَ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "የሩቅ ወሬ" "የሩቅ ሚስጥር" ማለት ነው፦
81፥24 እርሱም በሩቁ ወሬ ላይ ንፉግ አይደለም፡፡ وَمَا هُوَ عَلَى الْغَيْبِ بِضَنِينٍ

"ዘኒን" ظَنِين ማለት "ሰሳች" "ንፉግ" ማለት ሲሆን ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ከአሏህ የተቀበሉትን ገይብ ሳይሰስቱ ነግረውናል። ይህንን ገይብ ከልብ ወለድም አልተናገሩም፥ ንግግራቸው የሚወርድ ግልጠተ መለኮት እንጂ ሌላ አይደለም፦
53፥3 ከልብ ወለድም አይናገርም፡፡ وَمَا يَنطِقُ عَنِ الْهَوَىٰ
53፥4 እርሱ ንግግሩ የሚወረድ ራእይ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ إِنْ هُوَ إِلَّا وَحْيٌ يُوحَىٰ

አምላካችን አሏህ በነቢያችን"ﷺ" ሡናህ ከሚጠቀሙ ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የእግር ኳስ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

49፥10 ምእመናን ወንድማማች ናቸው፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ إِخْوَةٌ

"ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" لَا إِلٰهَ إِلَّا اللّٰه ጠንካራ ዘለበት ነው፥ በጣዖት ክደን በአሏህ ስናምን እራሳችንን ለአሏህ እንሰጣለን፦
2፥256 "በጣዖትም የሚክድ እና በአላህ የሚያምን ሰው ለእርሷ መበጠስ የሌላትን "ጠንካራ ዘለበት" በእርግጥ ጨበጠ"፡፡ فَمَن يَكْفُرْ بِالطَّاغُوتِ وَيُؤْمِن بِاللَّهِ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَىٰ لَا انفِصَامَ لَهَا
31፥22 "እርሱ መልካም ሠሪ ሆኖ ፊቱን ወደ አላህ የሚሰጥም ሰው "ጠንካራን ዘለበት" በእርግጥ ጨበጠ"፡፡ وَمَن يُسْلِمْ وَجْهَهُ إِلَى اللَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَىٰ

እዚህ አንቀጽ "የሚሰጥ" ለሚለው የገባው ቃል እራሱ "ዩሥሊም" يُسْلِمْ መሆኑ በራሱ "ሙሥሊም" مُسْلِم ማለት የላ ኢላሀ ኢለል ሏህ ዘለበት በትክክል ዐውቆ እራሱ ለአሏህ የሰጠ ማለት ነው፥ "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" የሚለውን የአሏህን ገመድ የያዘ ሰው በዘር፣ በብሔር፣ በዘውግ፣ በቋንቋ፣ በባህል አይለያይም፦
3፥103 የአላህን ገመድ ሁላችሁም ያዙ! አትለያዩም። وَاعْتَصِمُوا بِحَبْلِ اللَّهِ جَمِيعًا وَلَا تَفَرَّقُوا ۚ

"ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" በዘር፣ በብሔር፣ በዘውግ፣ በቋንቋ፣ በባህል ጠበኞች የነበሩትን ሊያስተሳስር የሚችል የአሏህ ፀጋ ነው፦
3፥103 ጠበኞችም በነበራችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ የዋለውን የአላህን ጸጋ አስታውሱ! በልቦቻችሁም መካከል አስማማ፥ በጸጋውም ወንድማማቾች ኾናችሁ፡፡ በእሳት ጉድጓድ አፋፍም ላይ ነበራችሁ፥ ከእርስዋም አዳናችሁ፡፡ እንደዚሁ ትመሩ ዘንድ አላህ ለእናንተ አንቀጾቹን ያብራራል፡፡ وَاذْكُرُوا نِعْمَتَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ إِذْ كُنتُمْ أَعْدَاءً فَأَلَّفَ بَيْنَ قُلُوبِكُمْ فَأَصْبَحْتُم بِنِعْمَتِهِ إِخْوَانًا وَكُنتُمْ عَلَىٰ شَفَا حُفْرَةٍ مِّنَ النَّارِ فَأَنقَذَكُم مِّنْهَا ۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمْ آيَاتِهِ لَعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ

ከእሳት ጉድጓድ ተንጠልጥሎ ለመውጣት የሚያስችል ብቸኛው ገመድ "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" የሚለው የአሏህ ገመድ ነው፥ በዘር፣ በብሔር፣ በዘውግ፣ በቋንቋ፣ በባህል ጥላቻ እና ቂም አጥፍቶ የሚያስማማ፣ የሚያስተሳስር፣ ወንድማማች የሚያረግ ይህ ገመድ ነው።

እግር ኳስ ደግሞ እራሱ የቻለ ጥበብ የያዘ የእስፓርት ክፍል ነው፥ እግር ኳስ ማየት ወይም አለማየት ሐራም እና መክሩሕ አሊያም ፈርድ እና ሙሥተሐብ ሳይሆን ሙባሕ ነው። ሰዎች ቡድን ሠርተው እየተቧደኑ ሙሥሊም ለሙሥሊም መሰዳደብ፣ መጠዛጠዝ፣ መናቆር ከዚያ አልፎ መመታታት የአሏህ ገመድ ከሁሉም በላይ ያለማስበለጥ ምልክት ነው፥ አንድን ኳስ ከሃይማኖት፣ ከብሔር፣ ከዘር ጋር አያይዞ መደገፍ ሆነ መቃወም ዲናዊ አይደለም።
አንድ አገር ሙሥሊም ስለሚበዛባት ልክ እንደ ክርስቲያን ቱዩብ ያለ ቻናል ጭፍን ጥላቻ በመያዝ መንዛት ጭፍንነት ነው፥ በኳስ ሙሥሊም የሚበዛበት አሊያም ክርስቲያን የሚበዛበት አገር ስላሸነፈ ሆነ ስለተሸነፈ ከእምነት ጋር አንዳች ትስስር የለውም። ኳስን ከእምነት ጋር የምታያይዙም ሰዎች የላ ኢላሀ ኢለል ሏህ ጠንካራ ዘለበት በቅጡ የተደረዳችሁ አይመስለኝም።
አምላካችን አሏህ በላ ኢላሀ ኢለል ሏህ ጠንካራ ዘለበት ወንድማማችነታችንን የምንጠብቅ ያርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ብቻውን ያለ ጌታ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

39፥45 አላህም ብቻውን በተወሳ ጊዜ የእነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ሰዎች ልቦች ይደነብራሉ፡፡ وَإِذَا ذُكِرَ اللَّهُ وَحْدَهُ اشْمَأَزَّتْ قُلُوبُ الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِالْآخِرَةِ

"ሞኖስ" μόνος በባለቤት የሚገባ ቅጽል ነው፣ "ሞኖ" μόνῳ በርቱዕ ተሳቢ የሚገባ ቅጽል ነው፣ "ሞኖን" μόνον ደግሞ በኢርቱዕ ተሳቢ የሚገባ ቅጽል ሲሆን "ብቻ" ማለት ነው፥ ይህ ገላጭ ቅጽል ለአብ ብዙ ቦታ ገብቷል፦
ዮሐንስ 17፥3 እውነተኛ አምላክ ብቻህን የሆንህ አንተን እና የላክኸውን ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት። αὕτη δέ ἐστιν ἡ αἰώνιος ζωή, ἵνα γινώσκωσιν σὲ τὸν μόνον ἀληθινὸν θεὸν καὶ ὃν ἀπέστειλας Ἰησοῦν Χριστόν.
ሮሜ 16፥27 "ብቻውን" ጥበብ ላለው "ለ-"አምላክ" "በ-"ኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን! አሜን። μόνῳ σοφῷ Θεῷ, διὰ Ἰησοῦ Χριστοῦ, ᾧ ἡ δόξα εἰς τοὺς αἰῶνας τῶν αἰώνων· ἀμήν.

ኢየሱስ የላከው ብቻውን እውነተኛ አምላክ የሆነው እስከ ዘላለም ድረስ ክብር በኢየሱስ በኩል የሚቀርብለት ከሆነ የተላከውን ኢየሱስ እና ብቻውን ጥበብ ያለው አምላክ በማንነት ሆነ በምንነት ይለያያሉ፥ ብቻውን ለሆነ አምላክ ክብር፣ ግርማ፣ ኃይል እና ሥልጣን በኢየሱስ አማካኝነት ይቀርብለታል፦
ይሁዳ 1፥25 "ብቻውን "ለ-ሆነ አምላክ እና መድኃኒታችን  ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ ዘላለምም ድረስ በጌታችን "በ-"ኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ ኃይልም ሥልጣንም ይሁን፤ አሜን። μόνῳ Θεῷ Σωτῆρι ἡμῶν διὰ Ἰησοῦ Χριστοῦ τοῦ Κυρίου ἡμῶν δόξα μεγαλωσύνη κράτος καὶ ἐξουσία πρὸ παντὸς τοῦ αἰῶνος καὶ νῦν καὶ εἰς πάντας τοὺς αἰῶνας· ἀμήν.

ይህ ብቻውን እውነተኛ አምላክ የሆነው፣ ብቻውን ጥበብ ያለው የማይሞት እና አንድ ሰው እንኳ ያላየው ነው፦
1 ጢሞቴዎስ 1፥17 "ብቻውን" አምላክ ለሚሆን ለማይሞተው፣ ለማይታየው፣ ለዘመናት ንጉሥ ምስጋናና ክብር እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን። Τῷ δὲ Βασιλεῖ τῶν αἰώνων, ἀφθάρτῳ ἀοράτῳ μόνῳ Θεῷ, τιμὴ καὶ δόξα εἰς τοὺς αἰῶνας τῶν αἰώνων· ἀμήν.
1 ጢሞቴዎስ 6፥16 እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኃይል ይሁን፤ አሜን። ὁ μόνος ἔχων ἀθανασίαν, φῶς οἰκῶν ἀπρόσιτον, ὃν εἶδεν οὐδεὶς ἀνθρώπων οὐδὲ ἰδεῖν δύναται· ᾧ τιμὴ καὶ κράτος αἰώνιον· ἀμήν.
1 ጢሞቴዎስ 6፥15 ያንም መገለጡን በራሱ ጊዜ ብፁዕና "ብቻውን የሆነ ገዥ" የነገሥታት ንጉሥ እና የጌቶች ጌታ ያሳያል። ἣν καιροῖς ἰδίοις δείξει ὁ μακάριος καὶ μόνος Δυνάστης, ὁ Βασιλεὺς τῶν βασιλευόντων καὶ Κύριος τῶν κυριευόντων,

1 ጢሞቴዎስ 6፥16 ላይ "እርሱ" የሚለው ተውላጠ ስም 1 ጢሞቴዎስ 6፥15 ላይ "ብቻውን የሆነ ገዥ" የተባለውን ማንነት ተክቶ የመጣ ነው፥ ስለዚህ "እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም" የተባለው አብ ሲሆን ይህም "ብቻውን የሆነ ገዥ" ነው። "ብቻውን የሆነ ገዥ" የተባለው አብ ይሁዳ ላይ "ብቻውን ያለውን ጌታ" ተብሏል፦
ይሁዳ 1፥4 ብቻውን ያለውን ጌታ እና ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ። καὶ τὸν μόνον Δεσπότην καὶ Κύριον ἡμῶν Ἰησοῦν Χριστὸν ἀρνούμενοι.

"ዴስፖቴስ" δεσπότης ማለት "ጌታ" ማለት ሲሆን በግሪክ ሰፕቱአጀንት "ያህዌህ" יְהוָ֣ה የሚለው ቴትራግራማቶን ተክቶ የመጣ ነው፦
ኢሳይያስ 1፥24 ስለዚህ የእስራኤል ኃያል የሠራዊት ያህዌህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ לָכֵ֗ן נְאֻ֤ם הָֽאָדֹון֙ יְהוָ֣ה צְבָאֹ֔ות אֲבִ֖יר יִשְׂרָאֵ֑ל
ኢሳይያስ 1፥24 ስለዚህ የእስራኤል ኃያል የሠራዊት ጌታ ጌታ እንዲህ ይላል፦ διὰ τοῦτο τάδε λέγει Κύριος ὁ δεσπότης σαβαώθ, ὁ δυνάστης τοῦ ᾿Ισραήλ·