ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ነፍስ መግደል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

17፥33 ያቺንም አላህ እርም ያረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግደሉ፡፡ وَلَا تَقْتُلُوا النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ

ኢሥላም ሰም እና ወርቅ የያዘ ቅኔ ነው፥ ሰሙ ሐቅ ሲሆን ወርቁ ፍትሕ ነው። “ቂሷስ” قِصَاص የሚለው ቃል “ቋሶ” قَاصَّ ማለትም “አመሳሰለ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማመሳሰል” ማለት ነው፥ በቂሷስ ነፍስ ያጠፋ ነፍሱ ይጠፋል፣ ዓይን ያጠፋ ዓይኑ ይጠፋል፣ አፍንጫም ያጠፋ አፍንጫው ይጠፋል፣ ጆሮም ያጠፋ ጆሮው ይጠፋል፣ ጥርስ የሰበረ ጥርሱ ይሰበራል። እነዚህ ቁስሎችን በቂሷስ ይፈታሉ፦
5፥45 *”በእነርሱም ላይ በውስጧ፦ «ነፍስ በነፍስ ዓይንም በዓይን አፍንጫም በአፍንጫ ጆሮም በጆሮ ጥርስም በጥርስ ይያዛል፥ ቁስሎችንም “ማመሳሰል” አለባቸው» ማለትን ጻፍን*፡፡ وَكَتَبْنَا عَلَيْهِمْ فِيهَا أَنَّ النَّفْسَ بِالنَّفْسِ وَالْعَيْنَ بِالْعَيْنِ وَالْأَنفَ بِالْأَنفِ وَالْأُذُنَ بِالْأُذُنِ وَالسِّنَّ بِالسِّنِّ وَالْجُرُوحَ قِصَاصٌ

አሁንም እዚህ አንቀጽ ላይ “ማመሳሰል” ለሚለው ቃል የገባው “ቂሷስ” قِصَاص መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። መጥፎ ለሠሩ ሠዎች መጥፎ ቅጣት መቅጣት ቂሷስ ነው፥ የአሏህ መጽሐፍ ጭብጡ ቂሷስ ነው፦
42፥40 *የመጥፎም ነገረ ዋጋ ብጤዋ መጥፎ ናት፡፡ ይቅርም ያለና ያሳመረ ሰው ምንዳው በአላህ ላይ ነው፡፡ እርሱ በደለኞችን አይወድም*፡፡ وَجَزَاءُ سَيِّئَةٍ سَيِّئَةٌ مِّثْلُهَا ۖ فَمَنْ عَفَا وَأَصْلَحَ فَأَجْرُهُ عَلَى اللَّهِ ۚ إِنَّهُ لَا يُحِبُّ الظَّالِمِينَ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 26
አነሥ እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”የአሏህ መጽሐፍ ቂሷስ ነው”*። أَنَّ أَنَسًا، حَدَّثَهُمْ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ كِتَابُ اللَّهِ الْقِصَاصُ ‏”‌‏.‏

ከዚህ ሕግ ውጪ ነፍስን መግደል አሏህ እርም አድርጓል፥ ያለ ቂሷስ ነፍስን መግደል ሐራም እና ከዐበይት ኃጢአቶች አንዱ ነው፦
17፥33 *”ያቺንም አላህ እርም ያረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግደሉ”*፡፡ وَلَا تَقْتُلُوا النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 83, ሐዲስ 53
ዐብደሏህ ኢብኑ ዐምሪው እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *”ዐበይት ኃጢአቶች በአሏህ ላይ ማሻረክ፣ ወላጆችን አለማክበር፣ ነፍስን መግደል እና የውሸት መሓላ ናቸው”*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ الْكَبَائِرُ الإِشْرَاكُ بِاللَّهِ، وَعُقُوقُ الْوَالِدَيْنِ، وَقَتْلُ النَّفْسِ، وَالْيَمِينُ الْغَمُوسُ ‏”‌‏.‏
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 86, ሐዲስ 80
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ሰባት አጥፊ ወንጀሎችን አስወግዱ! ሶሓባዎችም፦ "የአሏህ መልእክተኛ ሆይ! እነርሱ ምንድን ናቸው? አሉ። እርሳቸውም፦ "በአሏህ ላይ ማጋራት፣ መተት፣ አሏህ እርም ያረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ መግደል፣ ወለድ መብላት፣ የየቲሞችን ገንዘብ መብላት፣ በፍልሚያ ወቅት ማፈግፈግ እና ጥብቅ የሆኑ ምእመናትን በዝሙት መወንጀል ነው" አሉ*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ اجْتَنِبُوا السَّبْعَ الْمُوبِقَاتِ ‏"‌‏.‏ قَالُوا يَا رَسُولَ اللَّهِ وَمَا هُنَّ قَالَ ‏"‏ الشِّرْكُ بِاللَّهِ، وَالسِّحْرُ، وَقَتْلُ النَّفْسِ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلاَّ بِالْحَقِّ، وَأَكْلُ الرِّبَا، وَأَكْلُ مَالِ الْيَتِيمِ، وَالتَّوَلِّي يَوْمَ الزَّحْفِ، وَقَذْفُ الْمُحْصَنَاتِ الْمُؤْمِنَاتِ الْغَافِلاَتِ ‏"‌‏.‏

“እርም ያረጋት” ለሚለው የገባው ቃል “ሐረመ” حَرَّمَ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። “ሐራም” حَرَام የሚለው ቃል እራሱ “ሐረመ” حَرَّمَ ማለትም “ከለከለ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “የተከለከለ” ማለት ነው፥ እንደውም ያለጥፋት አንድን ሰው መግደል ሰዎችን ሁሉ እንደገደለ ነው፦
5፥32 *”በዚህ ምክንያት በእስራኤል ልጆች ላይ እነሆ ያለ ነፍስ መግደል ወይም በምድር ላይ ያለማጥፋት ካልሆነ በስተቀር ነፍስን የገደለ ሰው ሰዎቹን ሁሉ እንደገደለ ነው፥ ሕያው ያደረጋትም ሰው ሰዎቹን ሁሉ ሕያው እንዳደረገ ነው”* ማለትን ጻፍን፡፡ مِنْ أَجْلِ ذَٰلِكَ كَتَبْنَا عَلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ أَنَّهُ مَن قَتَلَ نَفْسًا بِغَيْرِ نَفْسٍ أَوْ فَسَادٍ فِي الْأَرْضِ فَكَأَنَّمَا قَتَلَ النَّاسَ جَمِيعًا وَمَنْ أَحْيَاهَا فَكَأَنَّمَا أَحْيَا النَّاسَ جَمِيعًا

ከዚህ ውጪ ወሰን ታልፎባቸው ለእነዚያ ለሚገደሉት ምእመናን እነርሱ የተበደሉ በመኾናቸው መጋደል ተፈቀደላቸው፦
22፥39 *”ለእነዚያ ለሚገደሉት ምእመናን እነርሱ የተበደሉ በመኾናቸው መጋደል ተፈቀደላቸው፡፡ አላህም እነርሱን በመርዳት ላይ በእርግጥ ቻይ ነው”*፡፡ أُذِنَ لِلَّذِينَ يُقَاتَلُونَ بِأَنَّهُمْ ظُلِمُوا ۚ وَإِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ نَصْرِهِمْ لَقَدِيرٌ

አንቀጹ ይቀጥልና ሲበደሉ በቂሷስ ፍትሕ የሚያስተካክሉ አካላት ከሌሉ ገዳማት፣ ቤተክርስቲያኖችም፣ ምኩራቦችም እና በውስጣቸው የአላህ ስም በብዛት የሚወሳባቸው መስጊዶችም ይፈርሳሉ፦
22፥40 ለእነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ከማለታቸው በስተቀር ያለ አግባብ ከአገራቸው የተባረሩ ለሆኑት ተፈቀደ፡፡ *”አላህ ሰዎችን ከፊላቸውን በከፊሉ መገፍተሩ ባልነበረ ኖሮ ገዳማት፣ ቤተክርስቲያኖችም፣ ምኩራቦችም እና በውስጣቸው የአላህ ስም በብዛት የሚወሳባቸው መስጊዶችም በተፈረሱ ነበር*”፡፡ አላህም ሃይማኖቱን የሚረዳውን ሰው በእርግጥ ይረዳዋል፡፡ አላህ ብርቱ አሸናፊ ነውና፡፡ الَّذِينَ أُخْرِجُوا مِن دِيَارِهِم بِغَيْرِ حَقٍّ إِلَّا أَن يَقُولُوا رَبُّنَا اللَّهُ ۗ وَلَوْلَا دَفْعُ اللَّهِ النَّاسَ بَعْضَهُم بِبَعْضٍ لَّهُدِّمَتْ صَوَامِعُ وَبِيَعٌ وَصَلَوَاتٌ وَمَسَاجِدُ يُذْكَرُ فِيهَا اسْمُ اللَّهِ كَثِيرًا ۗ وَلَيَنصُرَنَّ اللَّهُ مَن يَنصُرُهُ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَقَوِيٌّ عَزِيزٌ
ስለዚህ ገዳማት፣ ቤተክርስቲያኖችም፣ ምኩራቦችም እና መስጊዶች ማፍረስ ወሰን ማለፍ ነው። “አላህ ሰዎችን ከፊላቸውን በከፊሉ መገፍተሩ” የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! አንደኛው በሌላኛ ፍትሕ ለማስከበር መገፍተሩ ማለትም መጋደል ከሌለ ወሰን አላፊዎች ምድሩቱን ያበላሻሉ። በቂሷስ እነዚያንም ወሰን አላፊዎች በአላህ መንገድ ተጋደሉ! ወሰንንም አትለፉ! አላህ ወሰን አላፊዎን አይወድምና፦
2፥190 *እነዚያንም የሚጋደሉዋችሁን በአላህ መንገድ ተጋደሉ፡፡ ወሰንንም አትለፉ፤ አላህ ወሰን አላፊዎን አይወድምና*፡፡ وَقَاتِلُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ الَّذِينَ يُقَاتِلُونَكُمْ وَلَا تَعْتَدُوا ۚ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْمُعْتَدِينَ

የአልረሕማንም ባሮች ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ቂሷስ ሕግ የማይገድሉ ናቸው፥ ነገር ግን ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ቂሷስ ሕግ በመግደል ይህንንም የሚሠራ ሰው ከዱንያ ፍርድ ቢያመልጥ በአኺራ ከአሏህ ቅጣትን ያገኛል፦
25፥68 *”እነዚያም ምእመናን ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ የማይገዙት፣ ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ የማይገድሉት፣ የማያመነዝሩትም ናቸው፡፡ ይህንንም የሚሠራ ሰው ግን ቅጣትን ያገኛል”*፡፡ وَالَّذِينَ لَا يَدْعُونَ مَعَ اللَّهِ إِلَـٰهًا آخَرَ وَلَا يَقْتُلُونَ النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ وَلَا يَزْنُونَ ۚ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ يَلْقَ أَثَامًا

የእሥልምና አስተምህሮት ይህ ነው። ሰሞኑን በሁለቱም ጽንፈኞች በፋኖ እና በሾኔ እየተገደለ ያለው ሙሥሊሙ መሆኑ በጣም ቢያምም ቅሉ ግን ማንም ሰው ያለ ሕግ መገደል ይቅርና ጉንፋን እንዲያመው እሥልምናችን አያስተምርም።
አሏህ ለሁላችንም ሂዳያህ ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ብርዘት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥75 ከእነርሱ የኾኑ ጭፍሮች የአላህን ንግግር የሚሰሙ እና ከዚያም ከተረዱት በኋላ እነርሱ እያወቁ “የሚለውጡት” ሲኾኑ ለእናንተ ማመናቸውን ትከጅላላችሁን?” أَفَتَطْمَعُونَ أَن يُؤْمِنُوا لَكُمْ وَقَدْ كَانَ فَرِيقٌ مِّنْهُمْ يَسْمَعُونَ كَلَامَ اللَّهِ ثُمَّ يُحَرِّفُونَهُ مِن بَعْدِ مَا عَقَلُوهُ وَهُمْ يَعْلَمُون

"ተሕሪፍ" تَحْرِيف የሚለው ቃል "ሐረፈ" حَرَّفَ ማለትም "በረዘ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ብርዘት"corruption" ማለት ነው፥ የመጽሐፉ ሰዎች አይሁዳውያን እና ክርስቲያኖች ከአሏህ ዘንድ የወረደውን እውነት በውሸት መቀላቀላቸው ብርዘት ይባላል፦
3፥71 የመጸሐፉ ሰዎች ሆይ! እዉነቱን በዉሸት ለምን ትቀላቅላላችሁ? እዉነቱንም እናንተ የምታወቁ ስትሆኑ ለምን ትደብቃላችሁ? يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لِمَ تَلْبِسُونَ ٱلْحَقَّ بِٱلْبَٰطِلِ وَتَكْتُمُونَ ٱلْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ

ከአሏህ ዘንድ የወረደው እውነት ሆኖ ሳለ ውሸቱ ደግሞ መጽሐፉን በእጆቻቸው ጽፈው «ይህ ከአሏህ ዘንድ ነው» ማለታቸው ነው፦
2፥79 ለነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉ እና ከዚያም በርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው፡፡ ለእነርሱም ከዚያ እጆቻቸው ከጻፉት ወዮላቸው፡፡ ለእነርሱም ከዚያ ከሚያፈሩት ኃጢኣት ወዮላቸው፡፡ فَوَيْلٌۭ لِّلَّذِينَ يَكْتُبُونَ ٱلْكِتَٰبَ بِأَيْدِيهِمْ ثُمَّ يَقُولُونَ هَٰذَا مِنْ عِندِ ٱللَّهِ لِيَشْتَرُوا۟ بِهِۦ ثَمَنًۭا قَلِيلًۭا ۖ فَوَيْلٌۭ لَّهُم مِّمَّا كَتَبَتْ أَيْدِيهِمْ وَوَيْلٌۭ لَّهُم مِّمَّا يَكْسِبُونَ

"ለሚጽፉ" የሚለው ቃል "የክቱቡነ" يَكْتُبُونَ ሲሆን ከላይ ያለውን ሲያቅ ስንከተል የአሏህን ንግግር እያወቁ መበረዛቸውን ያሳያል፥ "ሢያቅ" سِيَاق ማለት "ዐውድ"context" ማለት ሲሆን የሡረቱል በቀራህ 2፥79 ዐውደ ንባቡን"contextual passege" እና ክፍለ ንባቡን"paragraphical passage" ስንከተል የበረዙት የአሏህን ንግግር መሆኑን በቀላሉ እንረዳለን፦
2፥75 ከእነርሱ የኾኑ ጭፍሮች የአላህን ንግግር የሚሰሙ እና ከዚያም ከተረዱት በኋላ እነርሱ እያወቁ “የሚለውጡት” ሲኾኑ ለእናንተ ማመናቸውን ትከጅላላችሁን?” أَفَتَطْمَعُونَ أَن يُؤْمِنُوا لَكُمْ وَقَدْ كَانَ فَرِيقٌ مِّنْهُمْ يَسْمَعُونَ كَلَامَ اللَّهِ ثُمَّ يُحَرِّفُونَهُ مِن بَعْدِ مَا عَقَلُوهُ وَهُمْ يَعْلَمُون

እዚህ አንቀጽ ላይ "የሚለውጡ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ዩሐረፉነ" يُحَرِّفُونَ ሲሆን "የሚበርዙት" ማለት ነው፥ "ዩሐረፉ" يُحَرِّفُ የሚለው በሙሥተቅበል የመጣ አላፊ ግሥ "ሐረፈ" حَرَّفَ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል። "ዩሐረፉነ" يُحَرِّفُونَ በሚል መዳረሻ ላይ "ሁ" هُ የሚለው ተሳቢ ተውላጠ ስም "ከላመል ሏህን" ያመለክታል፥ "ከላመል ሏህን" كَلَامَ اللَّه ማለት "የአሏህ ንግግር" ማለት ነው። በተዛማች ሙግት"textual approach" ስንመለከት ደግሞ የአሏህን ንግግር ከሥፍራው በሌላ የሰው ቃል ይበርዛሉ፦
5፥13 ቃል ኪዳናቸውንም በማፍረሳቸው ረገምናቸው፡፡ ልቦቻቸውንም ደረቆች አደረግን፡፡ ቃላትን ከቦታዎቻቸው ይለውጣሉ፡፡ فَبِمَا نَقْضِهِم مِّيثَاقَهُمْ لَعَنَّاهُمْ وَجَعَلْنَا قُلُوبَهُمْ قَاسِيَةً ۖ يُحَرِّفُونَ الْكَلِمَ عَن مَّوَاضِعِهِ

"ከሊም" كَلِم የሚለው ቃል "ከሊማህ" كَلِمَة ለሚለው ጀምዕ እና "ከላም" كَلَام ለሚለው ቃል ሙአነስ ነው። ይህ የብርዘት ሂደት "አት-ተሕሪፉል ለፍዝ" ٱلْتَحْرِيف ٱلْلَفْظ ይባላል፥ "ለፍዝ" لَفْظ ማለት "ቃል"Verbatim” ማለት ነው።

የመጽሐፉ ሰዎች ብርዘታቸው በዚህ አላበቃም፥ በመጽሐፉ ያለውን ንግግር ለማለት ያልፈለገውን "እንዲህ ለማለት ፈልጎ ነው" በማለት እየተረጎሙ ቋንቋውን ያጣምማሉ፦
3፥78 ከእነሱም እርሱ ከመጽሐፉ ያይደለ ሲኾን ከመጽሐፉ መኾኑን እንድታስቡ በመጽሐፉ ምላሶቻቸውን የሚያጣምሙ ክፍሎች አሉ፡፡ እርሱ ከአላህ ዘንድ ያልኾነ ሲኾን «እርሱ ከአላህ ዘንድ ነውም» ይላሉ፡፡ እነርሱ የሚያውቁ ሲኾኑም በአላህ ላይ ውሸትን ይናገራሉ፡፡ وَإِنَّ مِنْهُمْ لَفَرِيقًا يَلْوُونَ أَلْسِنَتَهُم بِالْكِتَابِ لِتَحْسَبُوهُ مِنَ الْكِتَابِ وَمَا هُوَ مِنَ الْكِتَابِ وَيَقُولُونَ هُوَ مِنْ عِندِ اللَّهِ وَمَا هُوَ مِنْ عِندِ اللَّهِ وَيَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ الْكَذِبَ وَهُمْ يَعْلَمُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ምላስ" ለሚለው የገባው ቃል "ሊሣን" لِسَان ሲሆን "ቋንቋ" ማለት ነው፥ ቃሉ የወረደበትን ቋንቋ ወደ ሌላ ቋንቋ በመተርጎም እና ሙዳየ ቃላት"dictionary" በማበጀት መልእክቱን በትርጉም"interpretation" ያጣምማሉ። ሁለተኛ "ሊሣን" لِسَان ማለት "ምላስ" ማለት ሲሆን ዐውደ-ንባቡ ለማለት ያልፈለገውን እጁን ጠምዝዞ "እንዲህ ለማለት ነው" ብሎ በምላስ ማጣመም “ስሑት ትርጓሜ” ወይም “ሰጊጎት”Eisegesis” ይባላል። በምላስ ሆነ በቋንቋ የሚተረጎመውን አተረጓጎም ከአሏህ ዘንድ ያልኾነ ሲኾን «እርሱ ከአሏህ ዘንድ ነው» ይላሉ፡፡ ይህ የብርዘት ሂደት "አት-ተሕሪፉል መዕና" ٱلْتَحْرِيف ٱلْمَعْنًى ይባላል፥ "መዕና" مَعْنًى ማለት "መልእክት" "እሳቤ" "አሳብ"notion" ማለት ነው። የመጽሐፉ ሰዎች ክርስቲያን እና አይሁድ አሳላጭ በመሆን በመጻሕፍት ውስጥ ስርዋጽ በማሳለጥ አስገብተዋል፥ ስርዋጽ ማለት በመቀነስ እና በመጨመር እንዲሁ የሌለን እንዳለ በማስመሰል መበረዝ ነው። አሏህ ከመጽሐፉ ሰዎች ፈሣድ ይጠብቀን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ማዛጋት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

24፥21 እርሱ በመጥፎ እና በሚጠላ ነገር ያዛልና፡፡ فَإِنَّهُ يَأْمُرُ بِالْفَحْشَاءِ وَالْمُنكَرِ

አምላካችን አሏህ መጥፎ ነገር እንድናደርግ አያዝም፥ ከዚያ ይልቅ በመልካም ነገር ያዛል። በተቃራኒው ከፈሕሻእ እና ከሙንከር ይከለክላል፦
7፥28 «አላህ በመጥፎ ነገር አያዝም፡፡ በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁን» በላቸው፡፡ قُلْ إِنَّ اللَّهَ لَا يَأْمُرُ بِالْفَحْشَاءِ ۖ أَتَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ
16፥90 አላህ በማስተካከል፣ በማሳመርም እና ለዝምድና ባለቤት በመስጠትም ያዛል፡፡ ከመጥፎ እና ከሚጠላም ነገር ሁሉ፣ ከመበደልም ይከለክላል፡፡ إِنَّ اللَّهَ يَأْمُرُ بِالْعَدْلِ وَالْإِحْسَانِ وَإِيتَاءِ ذِي الْقُرْبَىٰ وَيَنْهَىٰ عَنِ الْفَحْشَاءِ وَالْمُنكَرِ وَالْبَغْيِ

"ፈሕሻእ" فَحْشَاء ማለት "መጥፎ" ማለት ሲሆን "ሙንከር" مُنكَر ደግሞ "የሚጠላ" ማለት ነው፥ ፈሕሻእ እና ሙንከር የሸይጧን እርምጃዎች ናቸው። ሸይጧን በፈሕሻእ እና በሙንከር ያዛልና፦
24፥21 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የሰይጣንን እርምጃዎች አትከተሉ፡፡ የሰይጣንንም እርምጃዎች የሚከተል ሰው ኀጢአትን ተሸከመ፡፡ እርሱ(ሰይጣን) በመጥፎ እና በሚጠላ ነገር ያዛልና፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّبِعُوا خُطُوَاتِ الشَّيْطَانِ ۚ وَمَن يَتَّبِعْ خُطُوَاتِ الشَّيْطَانِ فَإِنَّهُ يَأْمُرُ بِالْفَحْشَاءِ وَالْمُنكَرِ ۚ

ስለዚህ አንድ ድርጊት "ከአሏህ ነው" ማለት "ሐላል ነው" ማለት ሲሆን "ከሸይጧን ነው" ማለት ደግሞ "ሐራም ነው" ማለት ነው። እዚህ ድረስ ከተግባባን ማስነጠስ ከአሏህ ነው፥ ማዛጋት ደግሞ ግን ከሸይጧን ነው፦
ጃሚዒ አት-ተርሚዚይ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 16
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ ሲሉ አሉ፦ "ማስነጠስ ከአሏህ ነው፥ ማዛጋት ግን ከሸይጧን ነው"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ الْعُطَاسُ مِنَ اللَّهِ وَالتَّثَاؤُبُ مِنَ الشَّيْطَانِ

"ማዛጋት ግን ከሸይጧን ነው" ማለት "ማዛጋት ሐራም ነው" ማለት ሲሆን ማዛጋት ክልክልነቱ ኢሥቲስናእ ሆኖ የመጣ ነው፥ ኢሥቲስናእ" اِسْتِثْنَاء‏ ማለት "ፍትቅታ"exceptional" ማለት ሲሆን ማዛጋት ክልክልነቱ በሶላት ውስጥ ነው፦
ጃሚዒ አት-ተርሚዚይ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 222
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ ሲሉ አሉ፦ "ማዛጋት በሶላት ውስጥ ከሸይጧን ነው፥ ከእናንተ አንደኛችሁ የሚያዛጋ በተቻለ መጠን ያፍነው"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ التَّثَاؤُبُ فِي الصَّلاَةِ مِنَ الشَّيْطَانِ فَإِذَا تَثَاءَبَ أَحَدُكُمْ فَلْيَكْظِمْ مَا اسْتَطَاعَ ‏"‏ ‏

ሶላት ክቡር እና ክቡድ ሲሆን በሶላት ውስጥ የሚረብሽ ነገር መቆጣጠር አለብን፥ ማዛጋት በማፈን የምንጎዳን የጤና እክል ስለሌለው እና በሶላት ውስጥ ማፈን ለሶላታችን ጥቅም አለው። በሶላት ውስጥ ማዛጋትን ማፈን ሲቻል ማስነጠስን ማፈን ግን ፈጽሞ ከባድ ነው፥ ማስነጠስን ማፈን ከጤና አንጻር ወደ ታምቡር ስብራት ሊያመራ ይችላል። ምክንያቱም ማስነጠስን ማፈን ኃይለኛ የአየር ፍሰት በአፍንጫው በኩል አይወጣም፣ ወደ ውጭ ያልወጡ በሽታ አምጪ ተህዋሲያን ማይክሮቦች ወደ ጆሮው ክፍል ውስጥ ይገባሉ፣ የደም ሥሮች መሰባበር እና አልፎ አልፎም ዓይነ ስውርነትን ያስከትላል። ይህ ጉዳት ስላለው በሶላት ውስጥ ማስነጠስ እና "አል-ሓምዱ ሊሏህ" ማለት ሐላል ነው፥ ዋቢ ማስረጃዎች ይመልከቱ፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 5, ሐዲስ 192
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 15, ሐዲስ 126

እንግዲህ ኢሥልምና ዱር ሙሥሊሙ ሐሩር እንዲሆን ቀን ከሌሊት ደፋ ቀና እና ጠብ እርግፍ የሚሉት አግድም አደግ ዕውቀት ያላቸው ሚሽነሪዎች በኢሥላም ላይ ለሚቀጥፉት ቅጥፈት እኛ ዐቃቢያነ እሥልምና የኢሥላምን መሠረትና ውቅር፣ ዋልታና ማገር፣ ጥልቀትና ስፋት፣ ድርና ማግ በቅጡ ተረድተን ለሚቀጥፉት ቀጣፊዎች በምንተ አፍረት ሳይሆን በምንተ እዳ እንዲህ መልስ መስጠት እና የታሪክ ምፀት ከዐሊሞቻችን ለሚቀጥለው ትውልድ የሚሆን ሰፊ ምዕላድ ትተን መሄድ ግድ ይለናል።
አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ታላቁ ስም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥2 አላህ ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ እርሱ "ሕያው" ሁሉን ነገር አስተናባሪ ነው፡፡ اللَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ

በአንድ ወቅት ሙሴ አምላክን፦ "እነሆ እኔ ወደ እስራኤል ልጆች በመጣሁ ጊዜ፦ "የአባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናንተ ላከኝ" ባልሁም ጊዜ፦ "ስሙስ ማን ነው? ባሉኝ ጊዜ፥ ምን እላቸዋለሁ? አለው፦
ዘጸአት 3፥13 ሙሴም ኤሎሂምን፦ "እነሆ እኔ ወደ እስራኤል ልጆች በመጣሁ ጊዜ፦ "የአባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናንተ ላከኝ" ባልሁም ጊዜ፦ "ስሙስ ማን ነው? ባሉኝ ጊዜ፥ ምን እላቸዋለሁ? አለው። ויאמר משה אל־האלהים הנה אנכי בא אל־בני ישראל ואמרתי להם אלהי אבותיכם שלחני אליכם ואמרו־לי מה־שמו מה אמר אלהם׃

አምላክም ሙሴን፦ «ኤህዬህ አሼር ኤህዬህ» አለው፥ እንዲህ ለእስራኤል ልጆች፦ «ኤህዬህ» ወደ እናንተ ላከኝ" ትላለህ" አለው፦
ዘጸአት 3፥14 ኤሎሂምም ሙሴን፦ «ኤህዬህ አሼር ኤህዬህ» አለው፤ እንዲህ ለእስራኤል ልጆች፦ «ኤህዬህ» ወደ እናንተ ላከኝ ትላለህ" አለው። וַיֹּ֤אמֶר אֱלֹהִים֙ אֶל־מֹשֶׁ֔ה אֶֽהְיֶ֖ה אֲשֶׁ֣ר אֶֽהְיֶ֑ה וַיֹּ֗אמֶר כֹּ֤ה תֹאמַר֙ לִבְנֵ֣י יִשְׂרָאֵ֔ל אֶֽהְיֶ֖ה שְׁלָחַ֥נִי אֲלֵיכֶֽם׃

በዚህ ዐውድ መሠረት "ኤህዬህ" אֶֽהְיֶ֖ה የአምላክ ስም ነው፥ "ኤህዬህ" אֶֽהְיֶ֖ה ማለት "እሆናለው" "እኖራለው" "እኔ ነኝ" ማለት ነው፦
ዘጸአት 3፥12 በእውነት እኔ ከአንተ ጋር "እሆናለሁ"። וַיֹּ֙אמֶר֙ כִּֽי־אֶֽהְיֶ֣ה עִמָּ֔ךְ

እዚህ አንቀጽ ላይ "እሆናለሁ" ለሚለው የገባው የግሥ መደብ "ኤህዬህ" אֶֽהְיֶ֖ה ነው፥ "ኤህዬህ አሼር ኤህዬህ" אֶֽהְיֶ֖ה אֲשֶׁ֣ר אֶֽהְיֶ֑ה ማለት "እኔ ነኝ ማን እኔ ነኝ"I am who i am" ማለት ነው። በግዕዝ ንባባት ውስጥ "አህያ ሸራህያ" "ዘሀሎ ወይሄሉ" "እሄሉ ዘይሄሉ" "እከውን ዘእከውን" ይሉታል። በብሉይ ከተገለጹ ሌላው ስሙ "የህ" ወይም "ያህ" ነው፦
መዝሙረ ዳዊት 68፥4 ወደ ደመናዎች ለወጣም መንገድ አድርጉ! ስሙ "ያህ" ነው። סֹ֡לּוּ לָרֹכֵ֣ב בָּ֭עֲרָבֹות בְּיָ֥הּ שְׁמֹ֗ו וְעִלְז֥וּ לְפָנָֽיו׃

"ያህ" יָהּ የሚለው ስም "ያህዌህ" יְהוָ֔ה ለሚለው ስም ምጻረ-ቃል ነው፥ "ያህ" יָהּ በተለይ በሰዎች የተጸውዖ ስም ላይ በመነሻ ቅጥያ አሊያም በመድረሻ ቅጥያ ይመጣል። ለምሳሌ፦ "ኤል-ያህ" אֵלִיָּה በግዕዝ "ኤል-ያስ" በዐረቢኛ "ኢል-ያሥ" إِلْيَاس ሲሆን በመድረሻ ቅጥያ ላይ አለ፥ "ያህ-ሁ" יֵהוּא በግዕዝ "ኢዩ" በዐረቢኛ "ያ-ሁወ" يَاهُو ሲሆን በመነሻ ቅጥያ ላይ አለ። ቁርኣን ውስጥ "ያሥ" يَاس ወይም "ያ" يَّا ይህንኑ ምጻረ ቃል የሚያሳይ ነው፦
37፥123 ኢልያስም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው፡፡ وَإِنَّ إِلْيَاسَ لَمِنَ الْمُرْسَلِينَ
19፥2 ይህ ጌታህ ባሪያውን ዘከሪያን በችሮታው ያወሳበት ነው፡፡ ذِكْرُ رَحْمَتِ رَبِّكَ عَبْدَهُ زَكَرِيَّا

"ኢል-ያሥ" إِلْيَاس ማለት "ያህ አምላክ ነው" ማለት ሲሆን "ዘከሪ-ያ" زَكَرِيَّا ማለት ደግሞ "ያህ ያወሳው" ማለት ነው። ያህ ምጻረ-ቃል የሆነበት ስም "ቴትራግራማተን" ወይም "ቴትራግራማቶን" τετραγράμματος ይባላል፥ "ቴትራስ" τέτταρες ማለት "አራት" ማለት ሲሆን "ግራማ" γράμμα ደግሞ "ፊደል" ማለት ነው። ከቀኝ ወደ ግራ የሚነበቡ አራቱ ተነባቢ ፊደላት "ዮድ" י‎ "ሔ" ה‎ "ዋው" ו‎ "ሔ" ה ወይም "የሐዋሐ" ሲሆኑ የፈጣሪ ታላቅ ስም ነው፦
ኢሳይያስ 42፥8 እኔ ያህዌህ ነኝ፥ ስሜ ይህ ነው። אֲנִ֥י יְהוָ֖ה ה֣וּא שְׁמִ֑י
ኤርምያስ 44፥26 "እነሆ በታላቅ ስሜ ምያለሁ" ይላል ያህዌህ፡፡הִנְנִ֨י נִשְׁבַּ֜עְתִּי בִּשְׁמִ֤י הַגָּדֹול֙ אָמַ֣ר יְהוָ֔ה

"ሃሼም" השם‌‎ ማለት "ስሙ" ማለት ሲሆን ይህ ታላቅ ስም በማሶሬት ጽሑፍ ውስጥ 6,518 ቦታ ተጠቅሷል፥ ቅሉ ግን አይሁዳውያን ይህንን ታላቅ ስም በከንቱ ላለመጥራት "አዶናይ" אֲדֹנָ֥י የሚለውን ስም ይጠቀሙ ነበር። "አዶናይ" אֲדֹנָ֥י ከሚለው ቃል "አታፍ ባታህን" א "ኦላም" o "ቃሜጽ" o‌ የሚባቡትን አናባቢ ፊደላት በ "ዮድ-ሄ-ዋው-ሄ" י‎ה‎ו‎ה ላይ ሲደቅሉት "ያህዌህ" יְהוָ֔ה የሚባል ስም ተፈጠረ፥ ይህንን የተለያዩ መድብለ ዕውቀቶች ያትታሉ፦
፨"ያህዌህ፦ ባዕድ ከሆነ ድምጽ ሰጪ ፊደላት ተዋቅሮ ያህዌህ በመባል በስህተት የተነበበ ነው"። Encyclopedia international volume 9, 1974 Edition.
፨"ያህዌህ፦ የቴትራግራማቶን የተሳሳተ አነባነብ ነው"። The universal jewish encyclopedia volume 6, 1948 Edition.
፨"ያህዌህ፦ ለእስራኤል አምላክ የተሳሳተ ስም ነው"። Encyclopedia Americana volume 16, 1976 Edition.

ላቲኖቹ ደግሞ "የ" የሚለውን "ጀ" እንዲሁ "ወ" የሚለውን "ቨ" በመጠቀም "ጆሆቫህ" በማለት ይጠቀማሉ። ከመነሻው ነቢያት ሲጠቀሙበት የነበረው ዕብራይስጥ ፓሌዎ ዕብራይስጥ እንጂ ማሶሬት ዕብራይስጥ አይደለም፥ ስለዚህ በፓሌዎ ዕብራይስጥ የተቀመጠው "ዮድ-ሄ-ዋው-ሄ" 𐤉𐤄𐤅𐤄 አጠራሩ በትክክል አይታወቅም። ሆነም ቀረ "ዮድ-ሄ-ዋው-ሄ" י‎ה‎ו‎ה የሚለው ቃል "ሀ-ወ-ሀ" הוה ማለትም "ኖረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ሐዋሕ" חַוָּה ማለትም "ሕያው"the living one" ማለት ነው።
እዚህ ድረስ ካየን ዘንዳ አምላካችን አሏህ እራሱን በቁርኣን የወሰፈበትን ወስፍ የነገረን ሲሆን የእርሱ ሲፋህ የተሰየመበት ስሞች በቁርኣን ውስጥ የተገለጹት ዘጠና ዘጠኝ ናቸው፥ ከእነዚህ ስሞች ውስጥ ታላቁ ስም ተገልጿል፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 34, ሐዲስ 30
አል-ቃሲም እንደተረከው፦ "የአሏህ ታላቁ ስም በእርሱ በተማጸኑት ጊዜ የሚቀበልበት ነው፥ ይህም በሦስት ሡራዎች በበቀራህ፣ በአለ-ዒምራን እና በጧሀ ውስጥ ይገኛል"። عَنِ الْقَاسِمِ، قَالَ اسْمُ اللَّهِ الأَعْظَمُ الَّذِي إِذَا دُعِيَ بِهِ أَجَابَ فِي سُوَرٍ ثَلاَثٍ الْبَقَرَةِ وَآلِ عِمْرَانَ وَطَهَ ‏.‏

"አልሐይ" الْحَيّ ማለት "ሕያው"the living one" ማለት ነው፥ "አልሐይ" الْحَيّ ማለት "እንዲሆን የሚያደርግ"He Causes to Become" የሚል ትርጉምም አለው፦
18፥16 ከነገራችሁም ለእናንተ መጠቃቀሚያን ያደርግላችኋል፡፡ وَيُهَيِّئْ لَكُم مِّنْ أَمْرِكُم مِّرْفَقًا

እዚህ አንቀጽ "ያደርጋል" ለሚለው የግሥ መደብ የገባው ቃል "ዩሐዪ" يُهَيِّئْ ሲሆን "እንዲሆን ያደረጋል" ማለት እንደሆነ ልብ አድርግ! ይህ ታላቅ ስም በሡረቱል በቀራህ፣ በሡረቱል አለ-ዒምራን እና በሡረቱ አጥ-ጧሀ ውስጥ በግልጽ ተቀምጧል፦
2፥255 አላህ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ "ሕያው" ራሱን ቻይ ነው፡፡ اللَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ
3፥2 አላህ ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ እርሱ "ሕያው" ሁሉን ነገር አስተናባሪ ነው፡፡ اللَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ
20፥111 ፊቶችም ሁሉ "ሕያው" አስተናባሪ ለኾነው አላህ ተዋረዱ፡፡ በደልንም የተሸከመ ሰው በእርግጥ ከሰረ፡፡ وَعَنَتِ الْوُجُوهُ لِلْحَيِّ الْقَيُّومِ ۖ وَقَدْ خَابَ مَنْ حَمَلَ ظُلْمًا
ተፍሢር ኢብኑ ከሲር 2፥255
"አቡ ኡማማህ እንደተረከው ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "የአሏህ ታላቁ ስም በእርሱ በተማጸኑት ጊዜ የሚቀበልበት ነው፥ ይህም በሦስት ቦታ በሱረቱል በቀራህ፣ አለ-ዒምራን እና ጣሃ ውስጥ ይገኛል"። «اسْمُ اللهِ الْأَعْظَمُ، الَّذِي إِذَا دُعِيَ بِهِ أَجَابَ، فِي ثَلَاثٍ: سُورَةِ الْبَقَرَةِ وَآلِ عِمْرَانَ وَطه»

ዛሬ በመላው ዓለም የምንገኘው ሙሥሊሞች ጠዋት እና ማታ አያቱል ኩርሢይን ስንቀራ ይህንን ታላቅ ስም በመጥራት ጥንት ነቢያት ሲያመልኩት የነበረውን አንዱን አምላክ አሏህን ለማምለካችን በቂ ማሳያ ነው። ኢሥላም ዐቂደቱ አር-ረባንያህ ስንል አርቲ ቡርቲና ቶራ ቦራ የሆነ ስሑትና መሪር የቡና ወሬ ይዘን ሳይሆን ስሙርና ጥዑም ማስረጃ ይዘን ነው። አምላካችን አሏህ ታላቁ ስሙን በመጥራት ዱዓቸው መቅቡል ከሆኑት ያርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የአሏህ ባሪያ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

19፥30 ሕፃኑም አለ «እኔ የአላህ ባሪያ ነኝ፡፡ መጽሐፍን ሰጥቶኛል ነቢይም አድርጎኛል፡፡» قَالَ إِنِّي عَبْدُ اللَّهِ آتَانِيَ الْكِتَابَ وَجَعَلَنِي نَبِيًّا

"መዕቡድ" مَعْبُود‎ ማለት "ተመላኪ" ማለት ሲሆን "ዓቢድ" عَابِد‎ ማለት ደግሞ "አምላኪ" ማለት ነው፥ በተመላኪ እና በአምላኪ መካከል ያለው ሥርዓት "ዒባዳህ" عِبَادَة‎ ነው። ለአሏህ አምልኮን የሚያቀርብ "ባሪያ" በቁርኣን "ዐብድ" عَبْد ይባላል፥ ዒሣ አሏህን በብቸኝነት ስለሚያመልክ "ዐብዱሏህ" عَبْدُ اللَّه ማለትም "የአሏህ አምላኪ" "የአሏህ ባሪያ" ተብሏል፦
4፥172 አልመሲሕ ለአላህ ባሪያ ከመኾን ፈጽሞ አይጠየፍም፡፡ لَّن يَسْتَنكِفَ الْمَسِيحُ أَن يَكُونَ عَبْدًا لِّلَّهِ
19፥30 ሕፃኑም አለ «እኔ የአላህ ባሪያ ነኝ፡፡ መጽሐፍን ሰጥቶኛል ነቢይም አድርጎኛል፡፡» قَالَ إِنِّي عَبْدُ اللَّهِ آتَانِيَ الْكِتَابَ وَجَعَلَنِي نَبِيًّا
43፥59 እርሱ በርሱ ላይ የለገስንለት ለእስራኤለም ልጆች ተዓምር ያደረግነው የኾነ ባሪያ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ إِنْ هُوَ إِلَّا عَبْدٌ أَنْعَمْنَا عَلَيْهِ وَجَعَلْنَاهُ مَثَلًا لِّبَنِي إِسْرَائِيلَ

በዕብራይስጥ "ዔቤድ" עֶבֶד ማለት "ባሪያ" ወይም "አምላኪ" ማለት ሲሆን "ዐባድ" עָבַד ማለትም "አምልኮ" ከሚል የመጣ ቃል ነው፥ ኢየሱስ የአንዱ አምላክ ባሪያ መሆኑን በግልጽ እና በማያሻማ መልኩ ተቀምጧል፦
ኢሳይያስ 42፥1 እነሆ ደግፌ የያዝሁት ባሪያዬ፤ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ምርጤ፤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ፥ እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያወጣል። הֵ֤ן עַבְדִּי֙ אֶתְמָךְ־בֹּ֔ו בְּחִירִ֖י רָצְתָ֣ה נַפְשִׁ֑י נָתַ֤תִּי רוּחִי֙ עָלָ֔יו מִשְׁפָּ֖ט לַגֹּויִ֥ם יֹוצִֽיא׃
ማቴዎስ 12፥18 እነሆ የመረጥሁት "ባሪያዬ" ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ወዳጄ፤ መንፈሴን በእርሱ ላይ አኖራለሁ፥ ፍርድንም ያወራል። Ἰδοὺ ὁ παῖς μου ὃν ᾑρέτισα, ὁ ἀγαπητός μου ὃν εὐδόκησεν ἡ ψυχή μου· θήσω τὸ πνεῦμά μου ἐπ' αὐτόν, καὶ κρίσιν τοῖς ἔθνεσιν ἀπαγγελεῖ.

ልብ ብላችሁ ከሆነ የብሉይ ግሪክ ሰፕቱአጀንት በኢሳይያስ 42፥1 "ባሪያ" ለሚለው የተጠቀመው ቃል "ፓይስ" παῖς ሲሆን የማቴዎስ ጸሐፊም ከኢሳይያስ 42፥1 ላይ ጠቅሶ በግሪክ ኮይኔ ያስቀመጠውም ቃል "ፓይስ" παῖς ነው፥ ፈጣሪ ኢየሱስን በአገናዛቢ ተውላጠ ስም "ባሪያዬ"my servant" ማለቱ ብቻ ሳይሆን ሐዋርያትም ኢየሱስ ባርነቱ ለአንድ አምላክ ስለሆነ በአገናዛቢ ተውላጠ ስም "ባርያው"his servant" ብለው አስቀምጠዋል፦
የሐዋርያት ሥራ 3፥13 የአብርሀም፣ የይስሐቅ፣ የያዕቆብ አምላክ እና የአባቶቻችን አምላክ እናንተ አሳልፋችሁ የሰጣችሁትንና ሊፈታው ቈርጦ ሳለ በጲላጦስ ፊት የካዳችሁትን "ባሪያዬውን" ኢየሱስን አከበረው። ὁ θεὸς Ἀβραὰμ καὶ Ἰσαὰκ καὶ Ἰακώβ, ὁ θεὸς τῶν πατέρων ἡμῶν, ἐδόξασεν τὸν παῖδα αὐτοῦ Ἰησοῦν, ὃν ὑμεῖς μὲν παρεδώκατε καὶ ἠρνήσασθε κατὰ πρόσωπον Πειλάτου, κρίναντος ἐκείνου ἀπολύειν·

እዚህ አንቀጽ ላይ "ባሪያ" ለሚለው የገባው ቃል "ፓይዳ" Παῖδα ሥረ-መሠረቱ "ፓይስ" παῖς ሲሆን በግልጽ "ባሪያ" ማለት ስለሆነ New International Version ላይ ሳያቅማሙ "ባሪያ"servant" ብለውታል፥ ዐውዱ ላይም አምላክ ለእስራኤል ያስነሳው ነቢዩ ኢየሱስ "ፓይዳ" Παῖδα ተብሏል፦
የሐዋርያት ሥራ 3፥26 ለእናንተ አስቀድሞ አምላክ "ባሪያዬውን" አስነሥቶ እያንዳንዳችሁን ከክፋታችሁ እየመለሰ ይባርካችሁ ዘንድ ላከው። ὑμῖν πρῶτον ἀναστήσας ὁ θεὸς τὸν παῖδα αὐτοῦ ἀπέστειλεν αὐτὸν εὐλογοῦντα ὑμᾶς ἐν τῷ ἀποστρέφειν ἕκαστον ἀπὸ τῶν πονηριῶν ὑμῶν.

እዚህ አንቀጽ ላይ ደግሞ ኢየሱስን በነቢይነት ያስነሳው አምላክ ተመላኪ ሲሆን ኢየሱስ ግን የተላከ ባሪያ ነው። ሚሽነሪዎች ሆይ! እናንተ "ባሪያ" መባል ያፈራችሁበትን ነቢያት እና ሐዋርያት ኢየሱስን "ባሪያ" ብለውታና ለአንዱ አምላክ ባሪያ ትሆኑ ዘንድ ጥሪአችን ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ላት፣ ዑዛ፣ መናት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

7፥180 ለአላህም መልካም ስሞች አሉት፡፡ ስትጸልዩ በእርሷም ጥሩት! እነዚያንም ስሞቹን የሚያጣምሙትን ተዋቸው፡፡ ይሠሩት የነበሩትን ነገር በእርግጥ ይመነዳሉ፡፡ وَلِلَّهِ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ فَادْعُوهُ بِهَا ۖ وَذَرُوا الَّذِينَ يُلْحِدُونَ فِي أَسْمَائِهِ ۚ سَيُجْزَوْنَ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ

አምላካችን አሏህ ከፍጡራን ጋር የማይመሳሰሉ "አል-አሥ ማኡል ሑሥና" الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ ማለትም "የተዋቡ ስሞች" አሉት፦
20፥8 አላህ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ለእርሱ መልካሞች የኾኑ ስሞች አሉት፡፡ اللَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ
7፥180 ለአላህም መልካም ስሞች አሉት፡፡ ስትጸልዩ በ-"እርሷም" ጥሩት! እነዚያንም ስሞቹን የሚያጣምሙትን ተዋቸው፡፡ ይሠሩት የነበሩትን ነገር በእርግጥ ይመነዳሉ፡፡ وَلِلَّهِ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ فَادْعُوهُ بِهَا ۖ وَذَرُوا الَّذِينَ يُلْحِدُونَ فِي أَسْمَائِهِ ۚ سَيُجْزَوْنَ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ

"እርሷ" ለሚለው ተሳቢ ተውላጠ ስም የገባው "ሃ" هَا ሲሆን "አሥማእ" أَسْمَاء የሚለውን ስም ተክቶ የመጣ ነው፥ ሙአነስ አንዳንዴ ጀምዕን ለማመልከት እንደሚመጣ በነሕው ደርሥ ግልጽ ነው። ነገር ግን ቁሬይሾች የአሏህ ስሞችን በማጣመም ነፍሶች የሚዘነበሉበትን ጥርጣሬ ተከትለዋል፥ "አሏህ" اللَّه ከሚለው ስም "ላት" لَّات በማለት፣ "ዐዚዝ" عَزِيزِ ከሚለው ስም "ዑዛ" عُزَّىٰ በማለት፣ "መናን" مَنَّان ከሚለው ስም "መናት" مَنَاة በማለት አጣመዋል፦
53፥19 ላትን እና ዑዛን አያችሁን? أَفَرَأَيْتُمُ اللَّاتَ وَالْعُزَّىٰ
53፥20 ሦስተኛይቱንም አነስተኛዋን መናትን አያችሁን? وَمَنَاةَ الثَّالِثَةَ الْأُخْرَىٰ

፨የመጀመሪያይቱ ጣዖት በግሪክ "አቴና" በሮም "ሚነርቫ" በከነዓ "አናት" በግብጽ "ኔዝ" ትባል ነበር፥ ይህቺ የጥበብ፣ የእጅ ሥራ፣ የፍትሕ፣ የሕግ፣ የድል አምላክ ተብላ የምትጠራውን ጣዖት ወደ ጧዒፍ ከተማ በወጅ ሸለቆ አምጥተው ስሟን "አሏህ" اللَّه ከሚለው ስም በማጣመም "ላት" لَّات አሏት። ላት በላይዋ ላይ የተቀረጹ ጽሑፎች ያሏ ነጭ ድንጋይ ነበረች፥ ላት ብለው በአንስታይ የሰየሟት ጣዖት ጥንት በአሏህ ቤት ሐጅ ለሚያደርጉ ሑጃጅ የገብስ ሾርባ የሚያቀርብ ሷሊሕ ሰው ሲሆን እርሱ ሲሞት እሳቤውን ከፓጋን በመውሰድ በእርሱን መቃብር ማምለክ ጀመሩ፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 380
ኢብኑ ዐባሥ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "ላት እና ዑዛ" ስለሚለውን ንግግር፦ "ላት ለሐጅ ሰዎች የገብስ ሾርባ የሚያቀርብ ሰው ነበር" አለ። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، رضى الله عنهما فِي قَوْلِهِ ‏{‏اللاَّتَ وَالْعُزَّى‏}‏ كَانَ الَّلاَتُ رَجُلاً يَلُتُّ سَوِيقَ الْحَاجِّ‏.‏

ይህቺን ጣዖት በ 9 የሒጅራህ አቆጣጠር ወይም በ 630 የጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በጥቅም ወር ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" አቡ ሡፍያን ኢብኑ ሐርብን እና አል-ሙጊራህ ኢብኑ ሹዕባህን ልከዋቸው አፈራርሰዋታል።

፨ሁለተኛይቱን በከነዓን "አስታሮት" በባቢሎን "ኤሽታር" በሮም "ቬኑስ" በግሪክ "አፍሮዳይት" በግብጽ "አዞር" ትባል ነበር፥ ይህቺ የጦርነት፣ የፍቅር፣ የአደን አምላክ ተብላ የምትታመን ጣዖትን በመካህ እና በጧዒፍ መካከል ባለው በነኽላህ አምጥተው ስሟን "ዐዚዝ" عَزِيزِ ከሚለው ስም በማጣመም "ዑዛ" عُزَّىٰ አሏት። ዑዛ በመጋረጃ የተኖረች እና በመታሰቢያ ሐውልት የተለወሰች ዛፍ ነበረች፥ በ 8 የሒጅራህ አቆጣጠር ወይም በ 630 የጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በጥር ወር ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ኻሊድ ኢብኑል ወሊድን ልከውት ዑዛ የተባለችውን ጣዖት አፈራርሷል፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 11, ሐዲስ 8
ሠዕድ እንደተረከው፦ ስለ ላት እና ዑዛ የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ከአሏህ በቀር በሐቅ የሚመለክ አምላክ የለም፥ ለእርሱ አንድም ተጋሪ የለውም"። عَنْ سَعْدٍ، قَالَ حَلَفْتُ بِاللاَّتِ وَالْعُزَّى فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ "‏ قُلْ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَحْدَهُ لاَ شَرِيكَ لَهُ

፨ሦስተኛይቱ በመካህ እና በመዲናህ መካከል በሚገኘው በሙሸለል አካባቢ የምትመለከው የእጣ፣ የዕድል፣ የጊዜ እና የመዳረሻ አምላክ ተብላ የምትታመነበው የነበረችው መናት ከላት እና ዑዛ በፊት የነበረች ስትሆን ስሟን "መናን" مَنَّان ከሚለው ስም በማጣመም "መናት" مَنَاة አሏት። "ሐናን" حَنَان ማለት "ርኅራኄ" ማለት ሲሆን ከአሏህ የሚሰጥ ነው፦
19፥13 ከእኛም የሆነን ርኅራኄ ንጽሕናንም ሰጠነው፡፡ ጥንቁቅም ነበር፡፡ وَحَنَانًا مِّن لَّدُنَّا وَزَكَاةً ۖ وَكَانَ تَقِيًّا

እዚህ አንቀጽ ላይ "ርኅራኄ" ለሚለው የገባው ቃል "ሐናን" حَنَان ነው። "አል-መናን" الْمَنَّان ደግሞ "ርኅራኄ ሰጪ" ማለት ሲሆን በሐዲስ የተገለጸ የአሏህ ስም ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 34, ሐዲስ 32
Iአነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "አንድ ሰው(ጂብሪል)፦ "አሏህ ሆይ! በእውነት በጎነት ምስጋና ሁሉ ለአንተ እንዲሆን እለምንሃለው፥ ከአንተ በቀር በሐቅ የሚመለክ አምላክ የለም፥ ለአንተ አንድም ተጋሪ የለህም። አንተ አል-መናን፣ የሰማያት እና የምድር አስገኚ፣ የግርማ እና የክብር ባለቤት ነህ" ሲል ሰምቻለው"። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، قَالَ سَمِعَ النَّبِيُّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ رَجُلاً يَقُولُ اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ بِأَنَّ لَكَ الْحَمْدَ لاَ إِلَهَ إِلاَّ أَنْتَ وَحْدَكَ لاَ شَرِيكَ لَكَ الْمَنَّانُ بَدِيعُ السَّمَوَاتِ وَالأَرْضِ ذُو الْجَلاَلِ وَالإِكْرَامِ"‏ ‏

በ 8 የሒጅራህ አቆጣጠር ወይም በ 630 የጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ሠዒድ ኢብኑ ዘይድ አል-አሽሀሊይን ልከውት መናህ የተባለችውን ይህቺን ጣዖት አፈራርሷል።
እነዚህ ዐረብ ጣዖታውያን "መላእክት የአሏህ ሴቶች ልጀች ናቸው" በማለት መላእክትን ሴቶች በማድረግ ለአሏህ የማይገባውን ነገር ተናገሩ፦
53፥27 እነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት መላእክትን በሴት አጠራር ይጠራሉ፡፡ إِنَّ الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِالْآخِرَةِ لَيُسَمُّونَ الْمَلَائِكَةَ تَسْمِيَةَ الْأُنثَىٰ
37፥150 ወይስ እኛ እነርሱ የተጣዱ ሆነው መላእክትን ሴቶች አድርገን ፈጠርን? أَمْ خَلَقْنَا الْمَلَائِكَةَ إِنَاثًا وَهُمْ شَاهِدُونَ
43፥19 መላእክትንም እነርሱ የአልረሕማን ባሮች የኾኑትን ሴቶች አደረጉ፡፡ ሲፈጠሩ ነበሩን? መመስከራቸው በእርግጥ ትጻፋለች፡፡ ይጠየቃሉም፡፡ وَجَعَلُوا الْمَلَائِكَةَ الَّذِينَ هُمْ عِبَادُ الرَّحْمَـٰنِ إِنَاثًا ۚ أَشَهِدُوا خَلْقَهُمْ ۚ سَتُكْتَبُ شَهَادَتُهُمْ وَيُسْأَلُونَ
17፥40 ጌታችሁ በወንዶች ልጆች መረጣችሁ እና ከመላእክት ሴቶችን ልጆች ያዝን? እናንተ ከባድን ቃል በእርግጥ ትናገራላችሁ፡፡ أَفَأَصْفَاكُمْ رَبُّكُم بِالْبَنِينَ وَاتَّخَذَ مِنَ الْمَلَائِكَةِ إِنَاثًا ۚ إِنَّكُمْ لَتَقُولُونَ قَوْلًا عَظِيمًا
16፥57 ለአላህም ከመላእክት ሴቶች ልጆችን ያደርጋሉ። ጥራት ተገባው፡፡ ለእነርሱም የሚፈልጉትን ወንዶች ልጆችን ያደርጋሉ፡፡ وَيَجْعَلُونَ لِلَّهِ الْبَنَاتِ سُبْحَانَهُ ۙ وَلَهُم مَّا يَشْتَهُونَ

ከእነርሱ አንዳቸው ግን ለአልረሕማን ምሳሌ ባደረጉለት ነገር በሴት ልጅ በተበሰረ ጊዜ የተቆጨ ኾኖ ፊቱ ጠቁሮ ይውላል፥ ነገር ግን ለአሏህ መላእክትን ሴቶች ልጆች በማድረግ በአሏህ ላይ ቀጠፉ፦
43፥16 ከሚፈጥረው ውስጥ ሴቶች ልጆችን ያዘን? በወንዶች ልጆችም እናንተን መረጣችሁን? أَمِ اتَّخَذَ مِمَّا يَخْلُقُ بَنَاتٍ وَأَصْفَاكُم بِالْبَنِينَ
52፥39 ወይስ ለእርሱ ሴቶች ልጆች አሉትን? ለእናንተም ወንዶች ልጆች አሏችሁን? أَمْ لَهُ الْبَنَاتُ وَلَكُمُ الْبَنُونَ
16፥58 አንዳቸውም በሴት ልጅ በተበሰረ ጊዜ እርሱ የተቆጨ ኾኖ ፊቱ ጠቁሮ ይውላል፡፡ وَإِذَا بُشِّرَ أَحَدُهُم بِالْأُنثَىٰ ظَلَّ وَجْهُهُ مُسْوَدًّا وَهُوَ كَظِيمٌ
43፥17 አንዳቸውም ለአልረሕማን ምሳሌ ባደረጉለት ነገር በሴት ልጅ በተበሰረ ጊዜ እርሱ በቁጭት የተመላ ኾኖ ፊቱ የጠቆረ ይኾናል፡፡ وَإِذَا بُشِّرَ أَحَدُهُم بِمَا ضَرَبَ لِلرَّحْمَـٰنِ مَثَلًا ظَلَّ وَجْهُهُ مُسْوَدًّا وَهُوَ كَظِيمٌ

እነርሱ ወንድ ልጅ ሲወለድ ለራሳቸው ደስ ሲላቸው በተቃራኒው ሴት ስትወለድ የሚከፋቸው ሲሆን ለአሏህ መላእክትን ሴቶች ልጆች ማድረጋቸው አድሏዊ ንግግር ነው፥ አሏህም፦ "ለእናንተ ወንድ ልጅ ለእርሱም ሴት ልጅ ይኖራልን? ይህቺ ያን ጊዜ አድላዊ ክፍያ ናት" በማለት መልስ ሰጣቸው፦
53፥21 ለእናንተ ወንድ ልጅ ለእርሱም ሴት ልጅ ይኖራልን? أَلَكُمُ الذَّكَرُ وَلَهُ الْأُنثَىٰ
53፥22 ይህቺ ያን ጊዜ አድላዊ ክፍያ ናት፡፡ تِلْكَ إِذًا قِسْمَةٌ ضِيزَىٰ

እነዚህን ጣዖታት ሙሽሪኮች እና አባቶቻቸው "ላት፣ ዑዛ እና መናህ" ብለው የሰየሟቸው ስሞች እንጂ መጥቀም ሆነ መጉዳት የሚችሉ አይደሉም፥ አሏህን ሰዎች እነዚህን ጣዖታት እንዲያመልኩ ማስረጃ አላወረደም፦
53፥23 እነርሱንም እናንተ እና አባቶቻችሁ የሰየማኋቸው ስሞች ብቻ እንጅ ምንም አይደሉም፥ አላህ በእርሷ ምንም ማስረጃ አላወረደም። إِنْ هِيَ إِلَّا أَسْمَاءٌ سَمَّيْتُمُوهَا أَنتُمْ وَآبَاؤُكُم مَّا أَنزَلَ اللَّهُ بِهَا مِن سُلْطَانٍ

"አህዋእ" أَهْوَآء ማለት "ዝንባሌ"inclination" ማለት ነው፥ ይህ ዝንባሌ ከነፍሢያህ ሲሆን አሏህን ሰዎች እነዚህን ጣዖታት እንዲያመልኩ ማስረጃ ያላወረደበትን ነገር በዝንባሌአቸው ጥርጣሬን እንዲከተሉ ሆነዋል፥ በእርግጥም ከአሏህ ዘንድ የመጣው መመሪያ ቁርኣን አሏህ አንድ አምላክ ብቻ መኾኑን ሊያውቁበት የመጣ ነው፦
53፥23 ነፍሶች የሚዘነበሉበትን ጥርጣሬን እንጅ ሌላ አይከተሉም፥ በእርግጥ ከጌታቸውም መምሪያ መጥቶላቸዋል። إِن يَتَّبِعُونَ إِلَّا الظَّنَّ وَمَا تَهْوَى الْأَنفُسُ ۖ وَلَقَدْ جَاءَهُم مِّن رَّبِّهِمُ الْهُدَىٰ
45፥11 ይህ ቁርኣን መመሪያ ነው፡፡ እነዚያም በጌታቸው አንቀጾች የካዱት ለእነርሱ ከብርቱ ቅጣት የኾነ አሳማሚ ስቃይ አላቸው፡፡ هَـٰذَا هُدًى ۖ وَالَّذِينَ كَفَرُوا بِآيَاتِ رَبِّهِمْ لَهُمْ عَذَابٌ مِّن رِّجْزٍ أَلِيمٌ
14፥52 ይህ ቁርኣን ለሰዎች ገላጭ ነው፡፡ በእርሱም ሊያስጠነቅቁበት፣ እርሱም አንድ አምላክ ብቻ መኾኑን ሊያውቁበት፣ የአእምሮ ባለቤቶችም ሊገሰጹበት የተወረደ ነው፡፡ هَـٰذَا بَلَاغٌ لِّلنَّاسِ وَلِيُنذَرُوا بِهِ وَلِيَعْلَمُوا أَنَّمَا هُوَ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ وَلِيَذَّكَّرَ أُولُو الْأَلْبَابِ

አምላካችን አሏህ በተውሒድ የምንጸና ሙዋሒድ ያርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መምህር ምሕረተ አብ፦ "ሰካራሞች የኦርቶዶክስ ተከታዮች ናቸው" የሚል ምጸታዊ ቃላት ተጠቅሟል። ይህ ነውር አይደለምን እንዴ? መምህር ተው! እንዲህ አይባል።

በነገራችን ላይ በኦርቶዶክስ ዶግማ አስካሪ መጠጥ መጠጣት ሐላል ነው፥ እነርሱ ግን አስካሪ መጠጥ ይጨልጣሉ እንጂ አይጠጡም እኮ።

ይህንን ድርጊት እንዲያወግዙ ሼር አርጉላቸው!
የጀነት ዛፍ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

76፥14 ዛፎችዋም በእነርሱ ላይ የቀረበች እና ፍሬዎችዋም ለለቃሚዎች መግገራትን የተገራች ስትኾን ገነትን መነዳቸው፡፡ وَدَانِيَةً عَلَيْهِمْ ظِلَالُهَا وَذُلِّلَتْ قُطُوفُهَا تَذْلِيلًا

“ጀናህ” جَنَّة የሚለው ቃል “ጀነ” جَنَّ ማለትም “ተሰወረ” ወይም “ተደበቀ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “ድብቅ” ወይም “ስውር” ማለት ነው፥ በጀነት ውስጥ ያለው ለሙሥሊሞች የተደበቀላቸውን ፀጋ ደግሞ ማንኛይቱም ነፍስ ስለማያውቅ ድብቅ እና ስውር ነው። በሐዲሰል ቁድሢይ ላይ የተዘጋጀው የጀነት ጸጋ ዓይን ዓይቶት፣ ጆሮ ሰምቶት፣ ልብ አስቦት የማያውቅ መሆኑ ተገልጿል፦
32፥17 ይሠሩትም በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለእነርሱ የተደበቀላቸውን ጸጋ ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም፡፡ فَلَا تَعْلَمُ نَفْسٌ مَّا أُخْفِيَ لَهُم مِّن قُرَّةِ أَعْيُنٍ جَزَاءً بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 123:
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ ነብዩ”ﷺ” እንዲህ ብለው አሉ፦ “አላህም እንዲህ አለ፦ እኔ ለደጋግ ባሮቼ ዓይን ዓይቶት የማያውቅ፣ ጆሮ ሰምቶት የማያውቅ እና በሰው ልቦና ውል ብሎ የማያውቅ ጸጋን አዘጋጅቻለው”። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ قَالَ اللَّهُ أَعْدَدْتُ لِعِبَادِي الصَّالِحِينَ مَا لاَ عَيْنٌ رَأَتْ، وَلاَ أُذُنٌ سَمِعَتْ، وَلاَ خَطَرَ عَلَى قَلْبِ بَشَرٍ ‏”

ስለዚህ በጀነት ውስጥ ያሉትን አሏህ ለባሮቹ ያዘጋጃቸው ፀጋዎች ዓይን ዓይቶት፣ ጆሮ ሰምቶት፣ ልብ አስቦት የማያውቅ ከሆነ ጀነት ውስጥ ያለው ሙዝ፣ ዘንባባ፣ ወይን፣ ተምር እንዲሁ ዛፍ ከዱንያው ውስጥ ካለው ነገር ጋር የስም መመሳሰል እንጂ ቅርጽና ይዘቱ አሊያም ጥፍጥናውና ጣዕሙ አንድ አይደለም፦
76፥14 ዛፎችዋም በእነርሱ ላይ የቀረበች እና ፍሬዎችዋም ለለቃሚዎች መግገራትን የተገራች ስትኾን ገነትን መነዳቸው፡፡ وَدَانِيَةً عَلَيْهِمْ ظِلَالُهَا وَذُلِّلَتْ قُطُوفُهَا تَذْلِيلًا
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 53 ሐዲስ 7
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "በጀናህ ውስጥ በጥላ ሥር ፈረሰኛ መቶ ዓመት የሚምታስጓዝ ዛፍ አለች"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم أَنَّهُ قَالَ ‏ "‏ إِنَّ فِي الْجَنَّةِ لَشَجَرَةً يَسِيرُ الرَّاكِبُ فِي ظِلِّهَا مِائَةَ سَنَةٍ ‏"‏ ‏.‏

ጊዜ የሚለካው በሰከንድ፣ በደቂቃ፣ በሰዓት፣ በቀን፣ በወር፣ በዓመት ሲሆን በተመሳሳይ ከሜትር ቁጥጥር ውጪ ያለ ርዝመት የሚለካው በዓመት ነው፥ በፈረሰኛ መቶ ዓመት መገለጹ በራሱ ጀናህ ምን ያክል ሰፊ እንደሆነች በቀላሉ መረዳት ይቻላል። ቀለብ እንጂ ቀልብ የሌላቸው ሚሽነሪዎች በጀናህ ውስጥ ዛፍ መኖሩ ለመሳቅ እና ለመሳለቅ ሲቃታቸው ዓይተን ነበር፥ እንዚህ ዘንጋታዎች እየተጎማለሉ እና ዘንፈል እያሉ ቁርኣን እና ሐዲስ ውስጥ እንደገቡ እኛም እንዲማሩበት በጨዋ ደንብ እና ሥርዓት ከባይብል በጀነት ውስጥ ዛፍ እንዳለ ጠቅሰንና አጣቅሰን እናቀርባለን፦
ሕዝቅኤል 31፥ 9 በእግዚአብሔርም ገነት በዔድን የነበሩ "ዛፎች" ሁሉ ቀኑበት።
ራእይ 2፥7 ድል ለነሣው በእግዚአብሔር ገነት ካለው ከሕይወት "ዛፍ" እንዲበላ እሰጠዋለሁ።
ራእይ 22፥2 በወንዙም ወዲያና ወዲህ በየወሩ እያፈራ አሥራ ሁለት ፍሬ የሚሰጥ የሕይወት "ዛፍ" ነበረ፥ የዛፉም ቅጠሎች ለሕዝብ መፈወሻ ነበሩ።

እነዚህ ሦስት አናቅጽ ላይ በገነት ውስጥ ዛፎች እንዳሉ አስረግጠውና ረግጠው ያስረዳሉ፥ "የሕይወት ዛፍ" ማለት አዳም እና ሔዋን በገነት እያሉ እንዲበሉት የበቀለ ዛፍ ነው፦
ዘፍጥረት 2፥9 በገነትም መካከል "የሕይወትን ዛፍ"፥ መልካምንና ክፉን የሚያስታውቀውንም ዛፍ አበቀለ።
ዘፍጥረት 2፥16 እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤

እሥልምና እንዲጠፋ ሙሥሊም እንዲገፋ ቀን ከሌሊት የሚዋትሩ እነዚህ እብሪተኞች እና ዳተኞች የሚሰበሰቡበት አዳራሽ ክበብ ይሁን ክለብ ለይተው ሳያውቁ እነዚህ አናቅጽ ያነቡአቸዋል ብለን አናስብም፥ ሚሽነሪዎች ሆይ! መቅኖ አጥታችሁ መቀመቅ ከመውረዳችሁ በፊት ጨርቄን እና ማቄን ሳትሉ ወደ ዱኑል ኢሥላም እንድትመጡ ጥሪአችን ነው። አምላካችን አሏህ ለኢሥላም ጸር እና አጽራር ከመሆን አርነት አውጥቶ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የኢብራሂም ሣራህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

51፥29 ሚስቱም እየጮኸች መጣች፥ ፊቷንም መታች፡፡ «መካን አሮጊት ነኝ» አለችም። فَأَقْبَلَتِ امْرَأَتُهُ فِي صَرَّةٍ فَصَكَّتْ وَجْهَهَا وَقَالَتْ عَجُوزٌ عَقِيمٌ

ኢብራሂም የአሏህ ነቢይ ሲሆን ሚስቱ ደግሞ ሣራህ ትባላለች፥ የኢብራሂም ሚስት ሣራህ ማንነቷ እንጂ ስሟ በቁርኣን አልተጠቀሰም። ቅሉ ግን በሐዲስ ላይ ኢብራሂም ከከለዳውያን ወደ ከነዓን በነበረው ስደት ትረካ ላይ ስሟን ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ነግረውናል፦
ቡኻርይ መጽሐፍ 51, ሐዲስ 67
አቢ ሁረይራህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ኢብራሂም ከሣራህ ጋር ተሰደደ"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ هَاجَرَ إِبْرَاهِيمُ بِسَارَةَ،

አሏህ ለተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" የኢብራሂም እንግዶች ወሬ በቁርኣን ተርኮላቸዋል፥ አምላካችን አሏህ መላእክትን ወደ ኢብራሂም በመላክ በኢሥሐቅ አበሰረው፦
51፥24 የተከበሩት የኢብራሂም እንግዶች ወሬ መጥቶሃልን? هَلْ أَتَاكَ حَدِيثُ ضَيْفِ إِبْرَاهِيمَ الْمُكْرَمِينَ
37፥112 በኢሥሐቅም አበሰርነው፡፡ ከመልካሞቹ የሆነ ነቢይ ሲሆን፡፡ وَبَشَّرْنَاهُ بِإِسْحَاقَ نَبِيًّا مِّنَ الصَّالِحِينَ
11፥69 መልክተኞቻችንም ኢብራሂምን በልጅ ብስራት በእርግጥ መጡለት፡፡ ሰላም አሉት፡፡ ሰላም አላቸው፡፡ ጥቂትም ሳይቆይ ወዲያውኑ የተጠበሰን የወይፈን ስጋ አመጣ፡፡ وَلَقَدْ جَاءَتْ رُسُلُنَا إِبْرَاهِيمَ بِالْبُشْرَىٰ قَالُوا سَلَامًا ۖ قَالَ سَلَامٌ ۖ فَمَا لَبِثَ أَن جَاءَ بِعِجْلٍ حَنِيذٍ
51፥28 ከእነርሱ መፍራትንም በልቡ አሳደረ፡፡ «አትፍራ» አሉት፡፡ በዐዋቂ ወጣት ልጅም አበሰሩት፡፡ فَأَوْجَسَ مِنْهُمْ خِيفَةً ۖ قَالُوا لَا تَخَفْ ۖ وَبَشَّرُوهُ بِغُلَامٍ عَلِيمٍ

መላእክት ስለ ኢሥሐቅ ለኢብራሂም ያበሰሩትን ብስራት ሣራህ ቆማ ታዳምጥ ስለነበር፦ "መካን አሮጊት ነኝ" በማለት የማይሆን መስሏት በስላቅ ሳቀች፥ አሏህም እርሱ ጥበበኛ ዐዋቂ መሆኑን በመናገር አበሰራት፦
51፥29 ሚስቱም እየጮኸች መጣች፥ ፊቷንም መታች፡፡ «መካን አሮጊት ነኝ» አለችም። فَأَقْبَلَتِ امْرَأَتُهُ فِي صَرَّةٍ فَصَكَّتْ وَجْهَهَا وَقَالَتْ عَجُوزٌ عَقِيمٌ
11፥71 ሚስቱም የቆመች ስትኾን ሳቀችም፡፡ በኢስሐቅ አበሰርናት፡፡ ከኢስሐቅም በኋላ በያዕቁብ አበሰርናት፡፡ وَامْرَأَتُهُ قَائِمَةٌ فَضَحِكَتْ فَبَشَّرْنَاهَا بِإِسْحَاقَ وَمِن وَرَاءِ إِسْحَاقَ يَعْقُوبَ
51፥30 ጌታሽ እንደዚህ ብሏል፦ «እነሆ እርሱ ጥበበኛ ዐዋቂ ነውና» አሏት፡፡ قَالُوا كَذَٰلِكِ قَالَ رَبُّكِ ۖ إِنَّهُ هُوَ الْحَكِيمُ الْعَلِيمُ

ከሳቀች በኃላ በኢሥሐቅ ስለተበሰረች ሚሽነሪዎች፦ "ከምን አንጻር እንደ ሳቀች ቅድመ ተከተሉን አልጠበቀም" በማለት ይተቻሉ፥ ቆማ የሳቀችውማ ለእርሷ ከመበሰሩ በፊት ለኢብራሂም በተበሰረው ብስራት ነው። ይህንን በተመሳሳይ ባይብል ላይ አለ፦
ዘፍጥረት 18፥9-11 እነርሱም፦ ሚስትህ ሣራ ወዴት ናት? አሉት። እርሱም፦ በድንኳኑ ውስጥ ናት፡ አላቸው። እርሱም፦ የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ በእውነት እመለሳለሁ፤ ሚስትህ ሣራም ልጅን ታገኛለች" አለ። ሣራም በድንኳን ደጃፍ በስተ ኋላው ሳለች ይህንን ሰማች።

ፈጣሪ በመላእክቱ ለአብርሃም ስለ ልጅ ሲነግረው ሣራ በድንኳን ደጃፍ በስተ ኋላው ሆኖ ትሰማ ነበር፥ ሣራ የሳቀችበት ልክ እንደ ቁርኣኑ፦ "ካረጀሁ በኋላ በውኑ ፍትወት ይሆንልኛልን? ጌታዬም ፈጽሞ ሸምግሎአል" በማለት ነበር፦
ዘፍጥረት 18፥12 ሣራም በራሷ፦ "ካረጀሁ በኋላ በውኑ ፍትወት ይሆንልኛልን? ጌታዬም ፈጽሞ ሸምግሎአል" ስትል ሳቀች"። וַתִּצְחַ֥ק שָׂרָ֖ה בְּקִרְבָּ֣הּ לֵאמֹ֑ר אַחֲרֵ֤י בְלֹתִי֙ הָֽיְתָה־לִּ֣י עֶדְנָ֔ה וַֽאדֹנִ֖י זָקֵֽן׃

ባይብሉ ታሪኩን ያቀረበው ሣራ የሳቀችው መላእክት ለአብርሃም ስለ ልጅ በነገሩት መሠረት እንደሆነ ሁሉ ቁርኣኑም ያስቀመጠው መላእክት ለኢብራሂም ስለ ልጅ በነገሩት መሠረት እንደሆነ በተዛማች ሙግት"textual approach" የሥነ-አፈታት ጥናት"hermeneutics" መረዳት ይቻላል፥ የተዛማች ሙግት ማለት አንዱ ሡራህ ላይ የተንጠለጠለ አሳብ በሌላ ሡራህ ላይ የሚጨርሰው ሲሆን ከቁርኣን የአነጋገር ውበት አንዱ ነው። አምላካችን አሏህ ስለዚህ እሳቦት እንዲህ ይነግረናል፦
39፥23 አላህ ከዜና ሁሉ መልካምን፣ ተመሳሳይ፣ ተደጋጋሚ የኾነን መጽሐፍ አወረደ፡፡ اللَّهُ نَزَّلَ أَحْسَنَ الْحَدِيثِ كِتَابًا مُّتَشَابِهًا مَّثَانِيَ تَقْشَعِرُّ

አሏህ ጥንት የተከናወኑትን ድርጊቶች በዜና የሚተርክልን ሙተሻቢህ በማድረግ አንዱ ሡራህ ላይ ተናግሮ ያንጠለጠለውን በሌላ ሡራህ ላይ የቀረውን ተመሳሳይ በማምጣት እና መሳኒይ በማድረግ አንዱ ሡራህ ላይ ተናግሮ ያንጠለጠለውን በሌላ ሡራህ ላይ የቀረውን በመድገም ነው፥ "ሙተሻቢህ" مُتَشَٰبِه ማለት "ተመሳሳይ" ማለት ሲሆን "መሳኒይ" مَّثَانِى ማለት "ተደጋጋሚ" ማለት ነው። አምላካችን አሏህ ቀደም ብለው የተከሰቱትን ክስተቶች የሚተርክልን መልካም፣ ተመሳሳይ እና ተደጋጋሚ ዜና ለእኛ እንድንማርበት ግሳጼ እና ማስታወሻ ነው፦
11፥120 ከመልክተኞቹም ዜናዎች ሁሉንም ልብህን በእርሱ የምናረካበትን እንተርክልሃለን፡፡ በዚህችም እውነቱ ነገር ለምእምናን ግሳጼ እና ማስታወሻ መጥቶልሃል፡፡ وَكُلًّا نَّقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنبَاءِ الرُّسُلِ مَا نُثَبِّتُ بِهِ فُؤَادَكَ ۚ وَجَاءَكَ فِي هَـٰذِهِ الْحَقُّ وَمَوْعِظَةٌ وَذِكْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ

"ለምእምናን ግሳጼ እና ማስታወሻ መጥቶልሃል" የሚለው ይሰመርበት! ሲጀመር ቁርኣን ላይ የሚመጣ ትረካ "እከሌ እከሌን ወለደ" የሚል የቀበሌ እና የእድር መጽሐፍ አይደለም። ሲቀጥል ለነቢያችን"ﷺ" የወረደላቸው የኢብራሂም ወሬ ኩረጃ ሳይሆን የሁሉን ዓዋቂው፣ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለን ምስጢር የሚያውቀው የአሏህ ንግግር ነው፦
33፥54 አላህ ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው። فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمًا
25፥6 «ያ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለን ምስጢር የሚያውቀው አወረደው፡፡ እርሱ መሓሪ አዛኝ ነውና» በላቸው፡፡ قُلْ أَنزَلَهُ الَّذِي يَعْلَمُ السِّرَّ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ إِنَّهُ كَانَ غَفُورًا رَّحِيمًا

ስለዚህ ከላይ ያለው የእናንተ የሚሽነሪዎች ኂስ ያልተጠና ኂስ ነው፥ ያልተጠና ኂስ የሚኃይስ ኃያሲ ለማሳለጥ ከሆነ መጥኔ ያጣ መኳተት ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
"ምላጭ ከምሣር እጅጉን የበለጠ ስለት አለው። ነገር ግን እንጨትን ለመቁረጥ አልታደለም አይሳካለትም። ምሣርም ቢሆን የራሱ ስለትና ብርቱ ጉልበት መኖሩ ፀጉርን ለመቁረጥ አይሳካለትም"
ወንድም ዑሥማን(አቡ ማሂራህ)
https://tttttt.me/AbuMahira55
ነቢዩ ኢሥማዒል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

19፥54 በመጽሐፉ ኢሥማዒልን አውሳ፡፡ እርሱ ቀጠሮን አክባሪ ነበረና፡፡ መልክተኛ ነቢይም ነበር፡፡ وَاذْكُرْ فِي الْكِتَابِ إِسْمَاعِيلَ ۚ إِنَّهُ كَانَ صَادِقَ الْوَعْدِ وَكَانَ رَسُولًا نَّبِيًّا

አምላካችን አሏህ ወደ ኢሥማዒል ወሕይ አውርዷል፥ አሏህ ስለ ኢሥማዒል ሲናገር "በኢሥማዒል... ላይ በተወረደው አመንን በሉ" በማለት ግህደተ-መለኮት ወርዶለት እንደነበር በሡረቱል አለ ዒምራን 3፥84 በሡረቱል በቀራህ 2፥136 እና በሡረቱ አን-ኒስሳእ 4፥163 ላይ ይናገራል። ኢሥማዒል መልክተኛ እና ነቢይ ነበር፥ ቤተሰቦቹንም በሶላት እና በዘካህ ያዝ ነበር፦
19፥54 በመጽሐፉ ኢሥማዒልንም አውሳ፡፡ እርሱ ቀጠሮን አክባሪ ነበረና፡፡ መልእክተኛ ነቢይም ነበር፡፡ وَاذْكُرْ فِي الْكِتَابِ إِسْمَاعِيلَ ۚ إِنَّهُ كَانَ صَادِقَ الْوَعْدِ وَكَانَ رَسُولًا نَّبِيًّا
19፥55 ቤተሰቦቹንም በሶላት እና በዘካህ ያዝ ነበር፡፡ እጌታውም ዘንድ ተወዳጅ ነበር፡፡ وَكَانَ يَأْمُرُ أَهْلَهُ بِالصَّلَاةِ وَالزَّكَاةِ وَكَانَ عِندَ رَبِّهِ مَرْضِيًّا

"እርሱ ቀጠሮን አክባሪ ነበረ" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! ይህም ቀጠሮ ኢብራሂም ለሥራ በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፤ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?» አለው፤ እርሱም «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አሏህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ» አለ፦
37፥102 ከእርሱ ጋርም ለሥራ በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፡፡ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?» አለው፡፡ «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ» አለ፡፡ فَلَمَّا بَلَغَ مَعَهُ ٱلسَّعْىَ قَالَ يَٰبُنَىَّ إِنِّىٓ أَرَىٰ فِى ٱلْمَنَامِ أَنِّىٓ أَذْبَحُكَ فَٱنظُرْ مَاذَا تَرَىٰ ۚ قَالَ يَٰٓأَبَتِ ٱفْعَلْ مَا تُؤْمَرُ ۖ سَتَجِدُنِىٓ إِن شَآءَ ٱللَّهُ مِنَ ٱلصَّٰبِرِينَ

ይህ በእውነት ግልጽ ፈተና ነው፥ አሏህ ኢብራሂምን ልጁን እንዲሠዋ በጠየቀው ቃላት ፈተነው፦
37፥106 ይህ እርሱ በእውነት ግልጽ ፈተና ነው፡፡ إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ ٱلْبَلَٰٓؤُا۟ ٱلْمُبِينُ
2፥124 ኢብራሂምንም ጌታው በቃላት በፈተነው እና በፈጸማቸው ጊዜ አስታውስ! «እኔ ለሰዎች መሪ አድራጊህ ነኝ» አለው፡፡ «ከዘሮቼም አድርግ» አለ፡፡ ቃል ኪዳኔ በዳዮቹን አያገኝም አለው፡፡ وَإِذِ ٱبْتَلَىٰٓ إِبْرَٰهِـۧمَ رَبُّهُۥ بِكَلِمَٰتٍۢ فَأَتَمَّهُنَّ ۖ قَالَ إِنِّى جَاعِلُكَ لِلنَّاسِ إِمَامًۭا ۖ قَالَ وَمِن ذُرِّيَّتِى ۖ قَالَ لَا يَنَالُ عَهْدِى ٱلظَّٰلِمِينَ

ኢብራሂም የተፈተነበት ልጅ ኢሥማዒልን ስለመሆኑ 2፥124 እና 37፥106 ከላይ እና ከታች ዐውደ ንባቡ ያስረዳል፥ "ኢሥማዒል" إِسْمَٰعِيْل የሚለው ስም የሁለት ቃላት ውቅር ነው፥ "ኢሥም" إِسْم የሚለው ቃል "አሥመዐ" أَسْمَعَ‎ ማለት "ሰማ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ይሰማል" ማለት ነው። "ዒል" عِيْل ደግሞ "ኢላህ" إِلَـٰهً ለሚል ምጻረ-ቃል ሲሆን "አምላክ" ማለት ነው፥ በጥቅሉ "ኢሥማዒል" إِسْمَٰعِيْل ማለት "አምላክ ይሰማል" ማለት ነው። ኢብራሂም፦ "ጌታዬ ሆይ! ከመልካሞቹ የሆነን ልጅ ስጠኝ" ብሎ አሏህ ጠይቆ አሏህም ዱዓውን በመስማት ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅ አበሰረው፦
37፥100 ጌታዬ ሆይ! ከመልካሞቹ የሆነን ልጅ ስጠኝ፡፡ رَبِّ هَبْ لِى مِنَ ٱلصَّٰلِحِينَ
37፥101 *ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰርነው*፡፡ فَبَشَّرْنَٰهُ بِغُلَٰمٍ حَلِيمٍۢ
14፥39 ጌታዬ ልመናን በእርግጥ ሰሚ ነውና፡፡ إِنَّ رَبِّي لَسَمِيعُ الدُّعَاءِ

ኢብራሂም፦ "ጌታዬ ልመናን በእርግጥ ሰሚ ነው" ማለቱ በራሱ ኢብራሂም አሏህን ለምኖ ያገኘው እና ለዕርድ ሲጠየቅ የታገሰ ትእግስተኛ ልጁ ኢሥማዒል መሆኑን ቁልጭ እና ፍንትው አርጎ ያሳያል። አሏህ በልጅ ጉዳይ ኢብራሂም ያበሰረው ሁለት ጊዜ ነው፥ የመጀመሪያው ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም ሲሆን ሁለተኛው በኢሥሐቅ ነው፦
37፥101 ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰርነው፡፡ فَبَشَّرْنَٰهُ بِغُلَٰمٍ حَلِيمٍۢ
37፥112 በኢሥሐቅም አበሰርነው፡፡ ከመልካሞቹ የሆነ ነቢይ ሲሆን፡፡ وَبَشَّرْنَٰهُ بِإِسْحَٰقَ نَبِيًّۭا مِّنَ ٱلصَّٰلِحِينَ

"በኢሥሐቅ-"ም" የሚለው ይሰመርበት! "ም" የሚለው ጥገኛ ምዕላድ በዐማርኛ ተጨማሪ ነገርን ያሳያል፥ "አበሰርነው" የሚለው ቃል አንድ ዐውድ ላይ ሁለቴ መምጣቱ ኢሥሐቅ እና ከላይ የተጠቀሰው በዱዓ የመጣው ልጅ ይለያያሉ። በተጨማሪም "ወ" وَ የሚለው አርፉል አጥፍ ብስራቱ ሁለት ጊዜ መሆኑን ያሳያል፥ አንደኛው ረድፍ “ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅ” ሲሆን ሁለተኛው ረድፍ “በኢሥሐቅም አበሰርነው” የሚለው ነው። ኢሥሐቅ ደግሞ ኢብራሂም አሏህን ለምኖ የተሰጠ ልጅ ሳይሆን እርሱ እና ሣራህ አንወልድም ብለው ተስፋ በቆረጡበት የተበሰሩት ልጅ ነው፦
15፥53 «አትፍራ፤ እኛ ዐዋቂ በኾነ ወንድ ልጅ እናበስርሃለን» አሉት፡፡ قَالُوا۟ لَا تَوْجَلْ إِنَّا نُبَشِّرُكَ بِغُلَٰمٍ عَلِيمٍۢ
15፥54 «እርጅና የደረሰብኝ ከመኾኔ ጋር አበሰራችሁኝን በምን ታበስሩኛላችሁ» አለ፡፡ قَالَ أَبَشَّرْتُمُونِى عَلَىٰٓ أَن مَّسَّنِىَ ٱلْكِبَرُ فَبِمَ تُبَشِّرُونَ
15፥55 «በእውነት አበሰርንህ፡፡ ከተሰፋ ቆራጮችም አትኹን» አሉ፡፡ قَالُوا۟ بَشَّرْنَٰكَ بِٱلْحَقِّ فَلَا تَكُن مِّنَ ٱلْقَٰنِطِينَ
51፥29 ሚስቱም እየጮኸች መጣች፥ ፊቷንም መታች፡፡ «መካን አሮጊት ነኝ» አለችም። فَأَقْبَلَتِ امْرَأَتُهُ فِي صَرَّةٍ فَصَكَّتْ وَجْهَهَا وَقَالَتْ عَجُوزٌ عَقِيمٌ
11፥71 ሚስቱም የቆመች ስትኾን አትፍራ አሉት፤ ሳቀችም፡፡ በኢሥሐቅም አበሰርናት፡፡ ከኢስሐቅም በኋላ በልጁ በያዕቁብ አበሰርናት፡፡ وَٱمْرَأَتُهُۥ قَآئِمَةٌۭ فَضَحِكَتْ فَبَشَّرْنَٰهَا بِإِسْحَٰقَ وَمِن وَرَآءِ إِسْحَٰقَ يَعْقُوبَ
ኢብራሂም በኢሥሐቅ ሲበሰር፦ "እርጅና የደረሰብኝ ከመኾኔ ጋር አበሰራችሁኝን በምን ታበስሩኛላችሁ?" ማለቱ ለምኖ ያገኘው ልጅ ሳይሆን ያላሰበው ልጅ መሆኑ አስረግጦና ረግጦ ያሳያል፥ ኢብራሂም እና ሣራህ የተበሰሩት በኢሥሐቅ ብቻ ሳይሆን በልጅ ልጃቸውም በያዕቁብም ነው። ኢብራሂም ኢሥሐቅ ሳይታረድ ተርፎ የልጅ ልጁ ያዕቆብ እንደሚወለድ ካወቀማ እና ይሥሐቅም ያዕቁብ የሚባል ልጅ እንደሚኖረዉ አስቀድሞ ከተበሰረ ልጅህን ዕረድልኝ ብሎ ማዘዙ ፈተናው ትርጉም አልባ ይሆን ነበር፥ ምክንያቱም ልጅህን ዕረድልኝ በእውነት ግልጽ ፈተና ነው። ፈተና ትርጉም የሚኖረው ተፈታኙ የሚፈተነውን የማያውቅ ሲሆን ብቻ እና ብቻ ነው፦
37፥106 ይህ እርሱ በእውነት ግልጽ ፈተና ነው፡፡ إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ ٱلْبَلَٰٓؤُا۟ ٱلْمُبِينُ
2፥124 ኢብራሂምንም ጌታው በቃላት በፈተነው እና በፈጸማቸው ጊዜ አስታውስ! «እኔ ለሰዎች መሪ አድራጊህ ነኝ» አለው፡፡ «ከዘሮቼም አድርግ» አለ፡፡ ቃል ኪዳኔ በዳዮቹን አያገኝም አለው፡፡ وَإِذِ ٱبْتَلَىٰٓ إِبْرَٰهِـۧمَ رَبُّهُۥ بِكَلِمَٰتٍۢ فَأَتَمَّهُنَّ ۖ قَالَ إِنِّى جَاعِلُكَ لِلنَّاسِ إِمَامًۭا ۖ قَالَ وَمِن ذُرِّيَّتِى ۖ

ሲጀመር ኢብራሂም የበኲር ልጁን ሊሰዋ ሲል በልጁ ፋንታ ዕርድ በግ መቅረቡ እና ይህም ሥርዓት መሠረት በማድረግ ዕርድ የሚካሄደው መካህ እንጂ ሻም አይደለም። ሲቀጥል አሏህ፦ "ቤቴን ለዘዋሪዎቹ፣ ለተቀማጮቹ፣ ለአጎንባሾቹ እና ለሰጋጆቹ አጥሩ" በማለት ቃል ኪዳን የያዘው ከኢብራሂም እና ከኢሥማዒል ጋር ነው፦
2፥125 ቤቱንም ለሰዎች መመለሻ እና ጸጥተኛ ባደረግን ጊዜ አስታውስ፡፡ ከኢብራሂምም መቆሚያ መስገጃን አድርጉ፡፡ ወደ ኢብራሂምና ወደ ኢስማዒልም፦ "ቤቴን ለዘዋሪዎቹ፣ ለተቀማጮቹ፣ ለአጎንባሾቹ እና ለሰጋጆቹ አጥሩ" ስንል ቃል ኪዳን ያዝን፡፡ وَإِذْ جَعَلْنَا الْبَيْتَ مَثَابَةً لِّلنَّاسِ وَأَمْنًا وَاتَّخِذُوا مِن مَّقَامِ إِبْرَاهِيمَ مُصَلًّى ۖ وَعَهِدْنَا إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ أَن طَهِّرَا بَيْتِيَ لِلطَّائِفِينَ وَالْعَاكِفِينَ وَالرُّكَّعِ السُّجُودِ

ይህ ጊዜው እዛው ዐውድ ላይ፦ "ኢብራሂምንም ጌታው በቃላት በፈተነው እና በፈጸማቸው ጊዜ" በማለት ይናገራል፥ በዚያን ጊዜ ኢብራሂም እና ኢሥማዒል፦ "ጌታችን ሆይ! ከእኛ ተቀበል፡፡ አንተ ሰሚውና ዐዋቂው አንተ ነህና" በማለት የቤቱን መሠረት ከፍ አርገዋል፦
2፥127 ኢብራሂም እና ኢሥማዒል «ጌታችን ሆይ! ከእኛ ተቀበል፡፡ አንተ ሰሚውና ዐዋቂው አንተ ነህና» የሚሉ ሲኾኑ ከቤቱ መሠረቶቹን ከፍ ባደረጉ ጊዜ አስታውስ፡፡ وَإِذْ يَرْفَعُ إِبْرَاهِيمُ الْقَوَاعِدَ مِنَ الْبَيْتِ وَإِسْمَاعِيلُ رَبَّنَا تَقَبَّلْ مِنَّا ۖ إِنَّكَ أَنتَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ

"ኑሡክ" نُسُك ማለት "ሥርዓተ መሥዋዕት" ማለት ሲሆን እዚሁ ቦታ ሥርዓተ መሥዋዕት እንዲፈጸም ወደ አሏህ ዱዓህ ያረጉት ኢብራሂም እና ኢሥማዒል ናቸው፦
2፥128 «ጌታችን ሆይ! ለአንተ ታዛዦችም አድርገን፡፡ ከዘሮቻችንም ለአንተ ታዛዦች ሕዝቦችን አድርግ፡፡ ሥርዓተ መሥዋዕቶቻችንንም አሳየን። رَبَّنَا وَاجْعَلْنَا مُسْلِمَيْنِ لَكَ وَمِن ذُرِّيَّتِنَا أُمَّةً مُّسْلِمَةً لَّكَ وَأَرِنَا مَنَاسِكَنَا

"ሀድይ" هَدْي ማለት "የዕርድ እንስሳ" ማለት ሲሆን ይህም እንስሳ ጊደር፣ በግ፣ ፍየል፣ ጥጃ፣ ግመል ነው፥ ይህም ዕርድ የሚካሄደው መካህ ውስጥ ነው፦
2፥196 ሐጅን እና ዑምራንም ለአላህ ሙሉ፤ ብትታገዱም ከሀድይ የተገራውን መሠዋት አለባችሁ፡፡ وَأَتِمُّوا الْحَجَّ وَالْعُمْرَةَ لِلَّهِ ۚ فَإِنْ أُحْصِرْتُمْ فَمَا اسْتَيْسَرَ مِنَ الْهَدْيِ
5፥97 አላህ ከዕባን የተከበረውን ቤት ለሰዎች መቋቋሚያ አደረገ፣ የተከበረውን ወር ሀድዩን እና ባለ ምልክቶቹንም መንጋዎች አደረገ፡፡ جَعَلَ اللَّهُ الْكَعْبَةَ الْبَيْتَ الْحَرَامَ قِيَامًا لِّلنَّاسِ وَالشَّهْرَ الْحَرَامَ وَالْهَدْيَ وَالْقَلَائِدَ
2፥200 የሐጅ ሥራዎቻችሁንም በፈጸማችሁ ጊዜ አባቶቻችሁን እንደምታወሱ ወይም ይበልጥ የበረታን ማውሳት አላህን አውሱ፡፡ فَإِذَا قَضَيْتُم مَّنَاسِكَكُمْ فَاذْكُرُوا اللَّهَ كَذِكْرِكُمْ آبَاءَكُمْ أَوْ أَشَدَّ ذِكْرًا

"ሥራዎቻችሁ" ለሚለው ቃል የተቀመጠው “መናሢከኩም" مَنَاسِكَكُمْ ሲሆን "ሥርዓተ መሥዋዕቶቻችሁ” ማለት ነው። ኢሥላም ዐቂደቱ አር-ረባንያህ ስንል አርቲ ቡርቲና ቶራ ቦራ የቡና ወሬ ይዘን ሳይሆን የአሏህን ንግግር ደሊል አድርገን ነው። አምላካችን አሏህ ቤቱን ከሚጎበኙት ሑጇጅ ያርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የዕርዱ ልጅ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

37፥102 ከእርሱ ጋርም ለሥራ በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፡፡ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?» አለው፡፡ «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ» አለ፡፡ فَلَمَّا بَلَغَ مَعَهُ ٱلسَّعْىَ قَالَ يَٰبُنَىَّ إِنِّىٓ أَرَىٰ فِى ٱلْمَنَامِ أَنِّىٓ أَذْبَحُكَ فَٱنظُرْ مَاذَا تَرَىٰ ۚ قَالَ يَٰٓأَبَتِ ٱفْعَلْ مَا تُؤْمَرُ ۖ سَتَجِدُنِىٓ إِن شَآءَ ٱللَّهُ مِنَ ٱلصَّٰبِرِينَ

"ኢሽማኤል" יִשְׁמָעֵאל‎ የሚለው ቃል የሁለት ዕብራይስጥ ቃላት ውቅር ነው፥ "ኢሽማ" שָׁמַע ማለት "ይሰማል" ማለት ሲሆን "ኤል" אֵל ማለት "አምላክ" ማለት ነው። በጥቅሉ "ኢሽማኤል" יִשְׁמָעֵאל‎ ማለት "አምላክ ጸሎቴን ሰማኝ" ማለት ነው፥ ይህ ስም የወጣበት ምክንያት አብርሃም፦ "አቤቱ ያህዌህ ሆይ! ምንን ትሰጠኛለህ? ያለ ልጅ እሄዳለሁ” ብሎ ለለመነው ልመና መልስ ፈጣሪም፦ "ከጉልበትህ የሚወጣው ይወርስሃል" በማለት ይመልስለታል፦
ዘፍጥረት 15፥2 አብራምም፦ አቤቱ አቤቱ ያህዌህ ሆይ! ምንን ትሰጠኛለህ? ያለ ልጅ እሄዳለሁ።
ዘፍጥረት 15፥4 እነሆም የያህዌህ ቃል እንዲህ ሲል መጣለት፦ ይህ አይወርስህም፤ ነገር ግን ከጉልበትህ የሚወጣው ይወርስሃል።

ፈጣሪም ከአብርሃም ጉልበት ስለወጣው የአብራኩ ክፋይ ሲናገር፦ "ስለ እስማኤልም ሰምቼሃለሁ፤ እነሆ ባርኬዋለሁ" በማለት ጸሎቱን ሰምቶታል፥ አብርሃምም አምላክ ጸሎቱን ስለሰማው የልጁን ስም "እስማኤል" ብሎ ጠራው፦
ዘፍጥረት 17፥20 ስለ እስማኤልም ሰምቼሃለሁ፤ እነሆ "ባርኬዋለሁ"።
ዘፍጥረት16፥15 አብራምም አጋር የወለደችለትን የልጁን ስም እስማኤል ብሎ ጠራው።

"ልጁን" የሚለው ይሰመርበት! አንዳንድ ዐላዋቂ የክርስትና መምህራን እስማኤል የአብርሃም ልጅ እንዳልሆነ እና እንዳልተባረከ ሲናገሩ ስንስማ ምን ያክል ባይብልን እንዳማያነቡ ያሳብቅብባቸዋል። አጋር የሳራ ባሪያ ብትሆንም ለአብርሃም ሚስቱ እንደነበረች እሙን እና ቅቡል ነው፥ ስለዚህ ልጇ ለኢብራሂም ሕጋዊ ልጅ ነው፦
ዘፍጥረት 16፥3 የአብራም ሚስት ሦራ ግብፃዊት ባሪያዋን አጋርን ወስዳ ለባልዋ ለአብራም ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠችው።

አጋር የሳራ ባሪያ የነበረች መሆኗ በእስማኤል ልጅነት ላይ የሚፈይደው አሉታዊ ቁብ የለውም። ለምሳሌ ባላን የራሔል ባሪያ ስትሆን ለያዕቆብ ግን ሚስት ነበረች፥ ከእርሷም የተወለዱት ዳን እና ንፍታሌም ሕጋዊ ልጆች ናቸው፦
ዘፍጥረት 30፥4 ባሪያዋን ባላንም ሚስት ትሆነው ዘንድ ለእርሱ ሰጠችው፤ ያዕቆብም ደረሰባት።

በተጨማሪም ዘለፋ የልያ ባሪያ ስትሆን ለያዕቆብ ግን ሚስት ነበረች፥ ከእርሷም የተወለዱት ጋድ እና አሴር ሕጋዊ ልጆች ናቸው፦
ዘፍጥረት 30፥9 ልያም መውለድን እንዳቆመች ባየች ጊዜ ባሪያዋን ዘለፋን ወሰደች፥ ሚስት ትሆነውም ዘንድ ለያዕቆብ ሰጠችው።

ያዕቆብ አሥራ ሁለት ሕጋዊ ልጆች ያሉት ከባላን እና ከዘለፋ የወለዳቸውን ልጆች ጨምሮ እንደሆነ ሁሉ አብርሃምም ከሳራ ባሪያ ከሚስቱ ከአጋር የወለደው የበኲር ልጁም ሕጋዊ ልጁ ነው፦
ዘፍጥረት 17፥26 በዚያው ቀን አብርሃም ተገረዘ፥ እንዲሁ ልጁ እስማኤልም።
ዘፍጥረት 25፥9 ልጆቹ ይስሐቅ እና እስማኤል.....ቀበሩት።
ዘፍጥረት 16፥15 አብራምም አጋር የወለደችለትን የልጁን ስም እስማኤል ብሎ ጠራው።

ይህ የበኲር ልጅ እስማኤል ሁለተኛው ልጅ ይስሐቅ እስኪወለድ ድረስ የአብርሃም ብቸኛ ልጅ ነው፦
ዘፍጥረት 22፥16 እንዲህም አለው፦ ያህዌህ፦ በራሴ ማልሁ ይላል፤ ይህን ነገር አድርገሃልና፥ ብቸኛ ልጅህንም አልከለከልህምና። וַיֹּ֕אמֶר בִּ֥י נִשְׁבַּ֖עְתִּי נְאֻם־יְהוָ֑ה כִּ֗י יַ֚עַן אֲשֶׁ֤ר עָשִׂ֙יתָ֙ אֶת־הַדָּבָ֣ר הַזֶּ֔ה וְלֹ֥א חָשַׂ֖כְתָּ אֶת־בִּנְךָ֥ אֶת־יְחִידֶֽךָ׃

"ያኺድ" יָחִיד ማለት "ብቸኛ" ማለት ነው፥ እዚህ አንቀጽ ላይ የተቀመጠው ወሳኝ ቃል "ያኺድከ" יְחִידֶֽךָ ማለት "ብቸኛክ" ማለት ሲሆን የበኲር ልጅ ሌላ ልጅ እስኪወለድ ድረስ ለወላጅ ብቸኛ ልጅ ነው፦
ዘካርያስ 12፥10 ሰውም ለብቸኛ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኵር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኀዘን ያዝኑለታል። אֲשֶׁר־דָּקָ֑רוּ וְסָפְד֣וּ עָלָ֗יו כְּמִסְפֵּד֙ עַל־הַיָּחִ֔יד וְהָמֵ֥ר עָלָ֖יו כְּהָמֵ֥ר עַֽל־הַבְּכֹֽור׃

እዚህ አንቀጽ ላይ የመጀመሪያ ልጅ ብቸኛ ልጅ መባሉን ልብ በል! ስለዚህ አብርሃም ሊሰዋ የነበረው የዕርዱ ልጅ የመጀመሪያ ልጁን ነው። ሲጀመር የዕርዱ ልጅ ይስሐቅ ቢሆን ኖሮ "ብቸኛ ልጅህን" የሚለው ትርጉም ይሰጣልን? ሲቀጥል ይስሐቅ ከመወለዱ በፊት አድጎ ዘር እንደሚኖረው ለአብርሃም ተነግሮታልም ያውቃልም፦
ዘፍጥረት 17፥19 ስሙንም ይስሐቅ ብለህ ትጠራዋለህ፤ ከእርሱ በኋላ ለዘሩ የዘላለም ቃል ኪዳን እንዲሆን ቃል ኪዳኔን ከእርሱ ጋር አቆማለሁ።

ታዲያ አብርሐም ልጁ ይስሐቅ ሳይወለድ ዘሩ እንደሚቀጥል እያወቀ ፈተና ነው ማለት ትርጉም ይኖረዋልን? ምክንያቱም ልጅህን ዕረድልኝ ፈተና ነው፥ ፈተና ትርጉም የሚኖረው ተፈታኙ የሚፈተነውን የማያውቅ ሲሆን ብቻ እና ብቻ ነው፦
ዘፍጥረት 22፥1 ከእነዚህም ነገሮች በኋላ ያህዌህ አብርሃምን "ፈተነው"።
በሙሴ ሕግ አስቀድሞ የተወለደው የበኲር ልጅ ለያህዌህ ይሆናል፥ የበኵር ልጅ በእርሱ ፋንታ እንስሳ ይታረዳል። ይህንን ሕግ አብርሃም ፈጽሞታል፦
ዘጸአት 13፥2 በእስራኤል ልጆች ዘንድ ከሰውም ከእንስሳም ማሕፀንን የሚከፈት በኵር ሁሉ ለእኔ ቀድስልኝ የእኔ ነው።
ዘፍጥረት 26፥5 አብርሃም ቃሌን ሰምቶአልና፥ ፍርዴን ትእዛዜን ሥርዓቴን "ሕጌንም ጠብቆአልና"።

አብርሃም ሕጉ ከጠበቀ የበኵር ልጁ ሊሰዋ ነበር ማለት ነው። አምላካችን አሏህ ሁሉንም ነገር ዐዋቂ ነው፥ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለን ምስጢር የሚያውቀው ይህ አንዱ አምላክ ቁርኣንን ወደ ነቢያችን"ﷺ" አውርዷል፦
33፥54 አላህ ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው። فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمًا
25፥6 «ያ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለን ምስጢር የሚያውቀው አወረደው፡፡ እርሱ መሓሪ አዛኝ ነውና» በላቸው፡፡ قُلْ أَنزَلَهُ الَّذِي يَعْلَمُ السِّرَّ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ إِنَّهُ كَانَ غَفُورًا رَّحِيمًا

"ነበእ" نَبَأ የሚለው ቃል "ነበአ" نَبَّأَ ማለትም "አወራ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ነቢብ" "የሩቅ ወሬ" ማለት ነው፥ ከአሏህ ዘንድ የሩቅ ወሬ የሚወርድለት ሰው "ነቢይ" نَبِيّ ሲባል "ነባቢ" "የሩቅ ወሬ አውሪ" ማለት ነው። ከአሏህ ዘንድ ወደ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ከወረደው የሩቅ ወሬ አንዱ ስለ ኢብራሂም እና ስለ ቤተሰቡ ነው፦
26፥69 በእነርሱም ላይ የኢብራሂምን "ወሬ" አንብብላቸው፡፡ وَاتْلُ عَلَيْهِمْ نَبَأَ إِبْرَاهِيمَ
37፥102 ከእርሱ ጋርም ለሥራ በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፡፡ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?» አለው፡፡ «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ» አለ፡፡ فَلَمَّا بَلَغَ مَعَهُ ٱلسَّعْىَ قَالَ يَٰبُنَىَّ إِنِّىٓ أَرَىٰ فِى ٱلْمَنَامِ أَنِّىٓ أَذْبَحُكَ فَٱنظُرْ مَاذَا تَرَىٰ ۚ قَالَ يَٰٓأَبَتِ ٱفْعَلْ مَا تُؤْمَرُ ۖ سَتَجِدُنِىٓ إِن شَآءَ ٱللَّهُ مِنَ ٱلصَّٰبِرِينَ

ኢብራሂም ሊሰዋው የነበረው ልጅ ኢስማኤል እንደሆነ ከቁርኣን ብቻ ሳይሆን ከባይብልም መለኮታዊ ቅሪት ከላይ እንዳብራራነው እናገኛለን። አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የአምላክነት አዋጅ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል ጌታዬን እና ጌታችሁን አላህን አምልኩ ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَا أَمَرْتَنِي بِهِ أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ رَبِّي وَرَبَّكُمْ

"የአምላክነት አዋጅ" ማለት ፈጣሪ "እኔ አምላክ ነኝ፥ አምልኩኝ" ያለበት አዋጅ"claim" ነው፥ ለምሳሌ አምላካችን አሏህ፦ "እኔ አምላክ ነኝ፥ አምልኩኝ" ብሏል፦
20፥14 እኔ አላህ እኔ ነኝ፥ ያለ እኔ አምላክ የለምና አምልከኝ፡፡ ሶላትንም በእርሷ እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡ إِنَّنِىٓ أَنَا ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدْنِى وَأَقِمِ ٱلصَّلَوٰةَ لِذِكْرِىٓ
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ እኔንም ብቻ አምልኩኝ፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ
21፥92 ይህች አንዲት መንገድ ስትሆን በእርግጥ ሃይማኖታችሁ ናት፤ እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ፡፡ إِنَّ هَٰذِهِۦٓ أُمَّتُكُمْ أُمَّةًۭ وَٰحِدَةًۭ وَأَنَا۠ رَبُّكُمْ فَٱعْبُدُونِ
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ

በግነት የምናወርድለት የሚለው አሏህ፦ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" ማለቱን እንረዳለን፥ ይህንን በመለኮታዊ ቅሪት ፈጣሪ "እኔ አምላክ ነኝ፥ ከእኔ በቀር አምላክ የለም" ይላል፦
ዘዳግም 32፥39 አሁንም እኔ ብቻዬን እኔ እንደ ሆንሁ፥ ከእኔም በቀር አምላክ እንደሌለ እዩ።
ኢሳይያስ 45፥5 እኔ ያህዌህ ነኝ፥ ከእኔም ሌላ ማንም የለም፤ ከእኔም በቀር አምላክ የለም።

እኛም ሙሥሊሞች፦ "ኢየሱስ አምላክ እና የሚመለክ ከሆነ "እኔ አምላክ ነኝ፥ አምልኩኝ" ያለበት ጥቅስ ስጡን" ብለን በቅንነት ስንጠይቅ፥ ክርስቲያኖች ያለበት ካለ ጠቅሶ እና አጣቅሶ ከማቅረብ ወይም ከሌለ "የለም" ብሎ መልስ ከመስጠት ይልቅ፦ "እኔ አምላክ አይደለሁም፥ አታምልኩኝ" ያለበትስ ጥቅስ የት አለ? ብለው ሱሪ በአንገት ልከክልህ እከክልኝ መልስ ይሰጣሉ፥ ይህ ስሑት ሙግት "Appeal to ignorance" ነው። ፕሮቴስታንት፦ "ማርያም ታማልዳለች" የሚል ባይብል ላይ የት አለ? ብለው ሲጠይቁ ኦርቶዶክሶች፦ "ማርያም አታማልድም" የሚል የት አለ? ብለው እንደሚመልሱት የቂል መልስ ነው፥ እኔም ተነስቼ፦ "አብርሃም አምላክ ነው፥ ይመለካል" ብል ማስረጃ አምጣ ስባል "አብርሃም "እኔ አምላክ አይደለሁም፥ አታምልኩኝ" ያለበትን ጥቅስ የት አለ ብዬ ልሞግት? "አብርሃም "እኔ አምላክ አይደለሁም፥ አታምልኩኝ" ያለበት ጥቅስ አለመኖሩ አብርሃን አምላክ እንደሆነ እና እንደሚመለክ ማስረጃ እንደማይሆን ሁሉ ኢየሱስም፦ "እኔ አምላክ አይደለሁም፥ አታምልኩኝ" ያለበት ጥቅስ አለመኖሩ ኢየሱስ አምላክ እንደሆነ እና እንደሚመለክ ማስረጃ እረ በፍጹም አይሆንም። ኢየሱስ እራሱን በመልእክተኛ ደረጃ ማስቀመጡ በራሱ የአምላክነት አዋጅ እንዳላወጀ በቂ ማስረጃ ነው፦
ዮሐንስ 12፥49 እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና፤ ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ።

አንድ ሁሉን ዐዋቂ አምላክ ሙሉ ዕውቀት ካለው ለሌላ ማንነት እና ምንነት እንዴት መልእክተኛ ይሆናል? ከሌላ ማንነት እና ምንነት ምን እንደሚናገር ትእዛዝ እየተቀበለ እንዴት ይናገራል? ከራሱ ምንም መናገር ካልቻለ እራሱ ጋር በቂ ትምህርት፣ ዕውቀት እና መልእክት የለውም ማለት ነው፦
ዮሐንስ 14፥10 እኔ የምነግራችሁን ቃል ከራሴ አልናገረውም።
ዮሐንስ 14፥24 የምትሰሙትም ቃል የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም።

ከራሱ የማይናገር እና የሚናገረው የላከው እንጂ የራሱ ካልሆነ እንዴት ሙሉ አምላክ ይሆናል? እውነት "እግዚአብሔር ወልድ" የሚባል ሙሉ አምላክነት ያለው ከሆነ ከሌላ ማንነት እና ምንነት መልእክት እየሰማ ለሕዝብ እንዴት ይናገራል? ይህ መልእክተኛ ግን ከላከው እየሰማ እና እየተማረ የሚናገር ነቢይ ነበር፦
ዮሐንስ 8፥26 ዳሩ ግን የላከኝ እውነተኛ ነው፥ እኔም ከእርሱ የሰማሁትን ይህን ለዓለም እናገራለሁ።
ዮሐንስ 7፥16 ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከእኔ አይደለም።

እውነት አንድ እውነተኛ አምላክ ሙሉ ዕውቀት እያለው ከሌላ ማንነት እና ምንነት ይማራልን? ከሌላ ኑባሬ ተምሮ ማስተላለፍ በምን ስሌት እና ቀመር ነው ሙሉ አምላክ የሚያስብለው? በእርግጥ እነርሱ እንደሚሉት "እግዚአብሔር ወልድ" የሚባል አምላክ "እግዚአብሔር አብ" ከሚባል አምላክ እየሰማ እና እያዳመጠ የሚናገር ሳይሆን ከአንዱ አምላክ እየሰማ ሲያስተላልፍ የነበረው ሰው ነው፦
ዮሐንስ 8፥40 ነገር ግን አሁን ከእግዚእብሔር የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን ሰው ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ።

አምላካችን አሏህ ለኢየሱስ አዞት የነበረው ቃል፦ "ጌታዬን እና ጌታችሁን አላህን አምልኩ" የሚል ነው፦
5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል ጌታዬን እና ጌታችሁን አላህን አምልኩ ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَا أَمَرْتَنِي بِهِ أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ رَبِّي وَرَبَّكُمْ

ኢየሱስን ዕውቀት እና መልእክት አስጨብጦ የላከውን አንዱን አምላክ አሏህን እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኤጎ ኤይሚ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥75 የመርየም ልጅ አልመሢሕ ከበፊቱ መልእክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልእክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ

በአንድ ወቅት ሙሴ አምላክን፦ “እነሆ እኔ ወደ እስራኤል ልጆች በመጣሁ ጊዜ፦ “የአባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናንተ ላከኝ” ባልሁም ጊዜ፦ “ስሙስ ማን ነው? ባሉኝ ጊዜ፥ ምን እላቸዋለሁ? አለው፦
ዘጸአት 3፥13 ሙሴም ኤሎሂምን፦ “እነሆ እኔ ወደ እስራኤል ልጆች በመጣሁ ጊዜ፦ “የአባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናንተ ላከኝ” ባልሁም ጊዜ፦ “ስሙስ ማን ነው? ባሉኝ ጊዜ፥ ምን እላቸዋለሁ? አለው። ויאמר משה אל־האלהים הנה אנכי בא אל־בני ישראל ואמרתי להם אלהי אבותיכם שלחני אליכם ואמרו־לי מה־שמו מה אמר אלהם׃

አምላክም ሙሴን፦ «ኤህዬህ አሼር ኤህዬህ» አለው፥ እንዲህ ለእስራኤል ልጆች፦ «ኤህዬህ» ወደ እናንተ ላከኝ” ትላለህ” አለው፦
ዘጸአት 3፥14 ኤሎሂምም ሙሴን፦ «ኤህዬህ አሼር ኤህዬህ» አለው፤ እንዲህ ለእስራኤል ልጆች፦ «ኤህዬህ» ወደ እናንተ ላከኝ ትላለህ” አለው። וַיֹּ֤אמֶר אֱלֹהִים֙ אֶל־מֹשֶׁ֔ה אֶֽהְיֶ֖ה אֲשֶׁ֣ר אֶֽהְיֶ֑ה וַיֹּ֗אמֶר כֹּ֤ה תֹאמַר֙ לִבְנֵ֣י יִשְׂרָאֵ֔ל אֶֽהְיֶ֖ה שְׁלָחַ֥נִי אֲלֵיכֶֽם׃

“ኤህዬህ አሼር ኤህዬህ” אֶֽהְיֶ֖ה אֲשֶׁ֣ר אֶֽהְיֶ֑ה ማለት “እኔ ነኝ ማን እኔ ነኝ”I am who i am” ማለት ነው። በግዕዝ ንባባት ውስጥ “አህያ ሸራህያ” “ዘሀሎ ወይሄሉ” “እሄሉ ዘይሄሉ” “እከውን ዘእከውን” ይሉታል። በግሪክ ሰፕቱአጀንት"(LXX)" ደግሞ "ኤጎ ኤይሚ ሆ ኦን" ἐγώ εἰμι ὁ ὤν ነው፥ በባይብል ከፈጣሪ ውጪ በማሶሬት “ኤህዬህ አሼር ኤህዬህ” אֶֽהְיֶ֖ה אֲשֶׁ֣ר אֶֽהְיֶ֑ה ወይም በሰፕቱአጀንት አሊያም በአዲስ ኪዳን ግሪክ ኮይኔ "ኤጎ ኤይሚ ሆ ኦን" ἐγώ εἰμι ὁ ὤν ብሎ የተጠቀመ ፍጡር የለም። ይህ ሆኖ ሳለ ክርስቲያን ሚሽነሪዎች፦ "ኢየሱስ "ኤጎ ኤይሚ" ብሏልና እርሱ በብሉይ ኪዳን ያለው ያህዌህ ነው" የሚል የተንሸዋረረ ሙግት ያቀርባሉ፦
ዮሐንስ 18፥4-6 ኢየሱስም የሚመጣበትን ሁሉ አውቆ ወጣና፦ ማንን ትፈልጋላችሁ? አላቸው። የናዝሬቱን ኢየሱስን፡ ብለው መለሱለት። ኢየሱስ፦ "እኔ ነኝ" አላቸው። አሳልፎ የሰጠውም ይሁዳ ደግሞ ከእነርሱ ጋር ቆሞ ነበር። እንግዲህ፦ "እኔ ነኝ" ባላቸው ጊዜ ወደ ኋላ አፈግፍገው በምድር ወደቁ።

እዚህ አንቀጽ ላይ "እኔ ነኝ" ለሚለው የገባው ቃል በግሪክ ኮይኔ "ኤጎ ኤይሚ" ἐγὼ εἰμί ሲሆን በቀላል ሰዋስው "እኔ ነኝ" ማለት እንጂ ዘጸአት 3፥14 ላይ ያለውን “ኤህዬህ አሼር ኤህዬህ” אֶֽהְיֶ֖ה אֲשֶׁ֣ר אֶֽהְיֶ֑ה ወይም "ኤጎ ኤይሚ ሆ ኦን" ἐγώ εἰμι ὁ ὤν አያመለክትም፥ ምክንያቱም የዘጸአት 3፥14 "እኔ ነኝ" ለሚለው የገባው ቃል "ኤህዬህ" אֶֽהְיֶ֑ה እንጂ "አኒ" אֲנִ֣י አይደለም። "አኒ" אֲנִ֣י በቀላል ሰዋስው "እኔ ነኝ" ማለት ነው፥ ኢየሱስ "እኔ ነኝ" ያለበትን ቃል ለማመልከት በዕብራይስጥ አዲስ ኪዳን የተቀመጠው "አኒ" אֲנִ֣י እንጂ "ኤህዬህ" אֶֽהְיֶ֑ה በፍጹም አይደለም፦
ዮሐንስ 18፥5 וַיַעֲנוּ אֹתוֹ אֶת־יֵשׁוּעַ הַנָּצְרִי וַיֹּאמֶר אֲלֵיהֶם יֵשׁוּעַ אֲנִי הוּא וִיהוּדָה הַמַּסְגִּיר עֹמֵד אֶצְלָם

በዕብራይስጥ "አኒ" אֲנִ֣י ወይም በግሪክ "ኤጎ ኤይሚ" ἐγὼ εἰμί ማለት አምላክነትን ካሳየማ አምላክ ሊሆን የሚችለው ቁጥር አንድ ኢዮአብ የተባለ ሰው ነው፦
2ሳሙኤል 20፥17 ወደ እርስዋም ቀረበ፤ ሴቲቱም። ኢዮአብ አንተ ነህን? አለች። እርሱም። "እኔ ነኝ" ብሎ መለሰላት።

ማሶሬት፦ וַיִּקְרַ֣ב אֵלֶ֔יהָ וַתֹּ֧אמֶר הָאִשָּׁ֛ה הַאַתָּ֥ה יֹואָ֖ב וַיֹּ֣אמֶר אָ֑נִי וַתֹּ֣אמֶר לֹ֗ו שְׁמַע֙ דִּבְרֵ֣י אֲמָתֶ֔ךָ וַיֹּ֖אמֶר שֹׁמֵ֥עַ אָנֹֽכִי׃

ሰፕቱአጀንት፦ καὶ προσήγγισε πρὸς αὐτήν, καὶ εἶπεν ἡ γυνή· εἰ σὺ εἶ ᾿Ιωάβ; ὁ δὲ εἶπεν· ἐγώ. εἶπε δὲ αὐτῷ· ἄκουσον τοὺς λόγους τῆς δούλης σου. καὶ εἶπεν ᾿Ιωάβ· ἀκούω ἐγώ εἰμι.

ኢዮአብ "አኒ" אֲנִ֣י ወይም "ኤጎ ኤይሚ" ἐγὼ εἰμί ማለቱን ልብ አርግ! ኢዮአብ "አኒ" אֲנִ֣י ወይም "ኤጎ ኤይሚ" ἐγὼ εἰμί ማለቱ አምላክ ያደርገዋልን? እንቀጥል! ኢየሱስ የፈወሰው ዓይነ ስውርም፦ "እኔ ነኝ" ብሏል፦
ዮሐንስ 9፥9 ሌሎች፦ እርሱ ነው፡ አሉ፤ ሌሎች፦ አይደለም፡ እርሱን ይመስላል እንጂ፡ አሉ፤ እርሱ፦ "እኔ ነኝ" አለ።

ግሪክ ኮይኔ፦ Ἄλλοι ἔλεγον ὅτι Οὗτός ἐστιν· ἄλλοι δὲ ὅτι Ὅμοιος αὐτῷ ἐστιν. Ἐκεῖνος ἔλεγεν ὅτι Ἐγώ εἰμι.

የዕብራይስጥ አዲስ ኪዳን፦ אֵלֶּה אָמְרוּ כִּי־זֶה הוּא וְאֵלֶּה לֹא־כֵן רַק דּוֹמֶה־לּוֹ וְהוּא אָמַר אֲנִי הוּא
ኢየሱስ የፈወሰው ዓይነ ስውር "አኒ" אֲנִ֣י ወይም "ኤጎ ኤይሚ" ἐγὼ εἰμί ማለቱ አምላክ ያደርገዋልን? "እረ በፍጹም" ከተባለ እንግዲያውስ ኢየሱስ "እኔ ነኝ" ማለቱ አምላክነቱን በፍጹም አያመላክትም። ጴጥሮስ፦ "እኔ ነኝ" ብሏል፦
የሐዋርያት ሥራ 10፥21 ጴጥሮስም ወደ ሰዎቹ ወርዶ፦ እነሆ፥ የምትፈልጉኝ "እኔ ነኝ" የመጣችሁበትስ ምክንያት ምንድር ነው? አላቸው።

ግሪክ ኮይኔ፦ καταβὰς δὲ Πέτρος πρὸς τοὺς ἄνδρας εἶπεν Ἰδοὺ ἐγώ εἰμι ὃν ζητεῖτε· τίς ἡ αἰτία δι' ἣν πάρεστε;

የዕብራይስጥ አዲስ ኪዳን፦ וַתִּפָּעֶם רוּחַ כֵּיפָא לָדַעַת מָה הוּא הַמַּחֲזֶה אֲשֶׁר חָזָה וְהִנֵּה הָאֲנָשִׁים שְׁלוּחֵי קָרְנֵילִיּוֹס מְבַקְשִׁים בֵּית שִׁמְעוֹן וְעֹמְדִים עַל־הַפָּתַח

ጴጥሮስ "አኒ" אֲנִ֣י ወይም "ኤጎ ኤይሚ" ἐγὼ εἰμί ማለቱ አምላክ ያደርገዋልን? ጴጥሮስ ሆነ ዓይነ ስውሩ ሰው "እኔ ነኝ" ሲሉ የተጠቀሙት ባለቤት ያለበት አያያዥ ግሥ እንጂ ሌላ እንዳልሆነ ሁሉ ኢየሱስም "እኔ ነኝ" ሲል የተጠቀመው ባለቤት ያለበት አያያዥ ግሥ እንጂ ሌላ በፍጹም አይደለም። ታዲያ "እኔ ነኝ" ባላቸው ጊዜ ወደ ኋላ አፈግፍገው በምድር መውደቃቸው ምንን ያሳያል? ከተባለ እንግዲያውስ አፍግፍገው መውደቃቸው ፍርሃታቸውን እንጂ ሌላ ምንንም አያሳይም፥ ምክንያቱም ዳንኤል ገብርኤልን ሲያይ በምድር ላይ በግምባሩ ተደፍቷል፦
ዳንኤል 8፥18 ሲናገረኝም ደንግጬ በምድር ላይ በግምባሬ ተደፋሁ፤ እርሱም ዳሰሰኝ ቀጥ አድርጎም አቆመኝ።
ዳንኤል 9፥21 ገናም በጸሎት ስናገር "አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል" እነሆ እየበረረ መጣ።

ተግባባን መሰለኝ? የመርየም ልጅ አልመሢሕ ከበፊቱ መልእክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልእክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፦
5፥75 የመርየም ልጅ አልመሢሕ ከበፊቱ መልእክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልእክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ

አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ዋቢ ማጣቀሻዎች
1. የዕብራይስጥ ብሉይ ኪዳን፦
https://mechon-mamre.org/p/pt/pt0.htm
2. ግሪክ ሰፕቱአጀንት ብሉይ ኪዳን፦
http://www.ellopos.net/elpenor/greek-texts/septuagint
3. አዲስ ኪዳን ግሪክ ኮይኔ፦
http://www.greekbible.com/index.php
4. የዕብራይስጥ አዲስ ኪዳን፦
https://www.ancient-hebrew.org/hebrewnt/index.html

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም