ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ባሪያ በኢሥላም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

90፥12 ዓቀበቲቱም መውጣቷ ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ? وَمَا أَدْرَاكَ مَا الْعَقَبَةُ

ዐውቀን በድፍረት ሆነ ሳናውቅ በስህተት ለማልነው መሓላ ከማካካሻ መካከል አንዱ ባሪያዎችን ከባርነት ነጻ ማውጣት ነው፦
58፥3 እነዚያም ከሚስቶቻቸው "እንደናቶቻችን ጀርባዎች ኹኑብን" በማለት የሚምሉ ከዚያም ወደ ተናገሩት የሚመለሱ ሳይነካኩ በፊት ባሪያን ነጻ ማውጣት በእነርሱ ላይ አለባቸው፡፡ وَالَّذِينَ يُظَاهِرُونَ مِن نِّسَائِهِمْ ثُمَّ يَعُودُونَ لِمَا قَالُوا فَتَحْرِيرُ رَقَبَةٍ مِّن قَبْلِ أَن يَتَمَاسَّا
5፥89 "አላህ በመሐላዎቻችሁ በውድቁ አይዛችሁም፥ ግን መሐላዎችን ባሰባችሁት ይይዛችኋል፡፡ ማስተሰሪያውም ቤተሰቦቻችሁን ከምትመግቡት ከመካከለኛው ምግብ አሥርን ምስኪኖች ማብላት ወይም እነርሱን ማልበስ ወይም ባሪያን ነጻ ማውጣት ነው"፡፡ لَا يُؤَاخِذُكُمُ اللَّهُ بِاللَّغْوِ فِي أَيْمَانِكُمْ وَلَـٰكِن يُؤَاخِذُكُم بِمَا عَقَّدتُّمُ الْأَيْمَانَ ۖ فَكَفَّارَتُهُ إِطْعَامُ عَشَرَةِ مَسَاكِينَ مِنْ أَوْسَطِ مَا تُطْعِمُونَ أَهْلِيكُمْ أَوْ كِسْوَتُهُمْ أَوْ تَحْرِيرُ رَقَبَةٍ ۖ

"ማስተሰሪያ" ለሚለው ቃል የገባው “ከፋራህ” كَفّارَة መሆኑን ልብ በል! “ከፋራህ” كَفّارَة ማለት "ማስተሰረያ" "ማካካሺያ" ማለት ነው። “ኒካሕ” نِكَاح የሚለው ቃል "ነከሐ" نَكَحَ ማለትም "አገባ" ወይም "ተዳራ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ጋብቻ" ወይም "ትዳር" ማለት ነው፥ ባርነት ከማስቀሪያ አንዱ ባሮችን ማግባት ነው፦
24፥32 "ከእናንተም ትዳር የሌላቸውን አጋቡ! ከወንዶች ባሮቻችሁ እና ከሴቶች ባሮቻችሁም ለጋብቻ ብቁ የኾኑትን አጋቡ! ድኾች ቢኾኑ አላህ ከችሮታው ያከብራቸዋል፡፡ አላህም ስጦታው ሰፊ ዐዋቂ ነው፡፡ وَأَنكِحُوا الْأَيَامَىٰ مِنكُمْ وَالصَّالِحِينَ مِنْ عِبَادِكُمْ وَإِمَائِكُمْ ۚ إِن يَكُونُوا فُقَرَاءَ يُغْنِهِمُ اللَّهُ مِن فَضْلِهِ ۗ وَاللَّهُ وَاسِعٌ عَلِيمٌ

እዚህ አንቀጽ ላይ “አጋቡ” የሚለው የግስ መደብ የገባው ቃል “አንኪሑ” َأَنكِحُوا መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል። ማንም ባሪያ ያለችው አስተምሮ፣ መልካም ሆኖላት፣ ከዚያ ነጻ አውጥቶ ያገባ ሁለት አጅር አለው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 49, ሐዲስ 27
አቡ ሙሣ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ማንም ባሪያ ያለችው ያስተምራት፣ መልካም ይሁንላት፣ ከዚያም ነጻ ያውጣት እና ያግባት! ለእርሱም ሁለት ትሩፋት አለው"። عَنْ أَبِي مُوسَى ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ مَنْ كَانَتْ لَهُ جَارِيَةٌ فَعَالَهَا، فَأَحْسَنَ إِلَيْهَا ثُمَّ أَعْتَقَهَا وَتَزَوَّجَهَا، كَانَ لَهُ أَجْرَانِ ‏"‌‏.‏

"አጅር" أَجْر ማለት አምላካችን አሏህ በአኺራ የሚመነዳን "ምንዳ" "ትርሲት" "ስርጉት" "ትሩፋት" ነው። የዘካቱል ማል ገንዘብ ከሚውልበት ግልጋሎት አንዱ በባርነት ተገዢዎችን ነጻ ለማውጣት ነው፦
9፥60 ግዴታ ምጽዋቶች የሚከፈሉት ለድኾች፣ ለምስኪኖችም፣ በርሷም ላይ ለሚሠሩ ሠራተኞች፣ ልቦቻቸውም በኢሥላም ለሚለማመዱት፣ "በባርነት ተገዢዎችን ነጻ በማውጣት"፣ በባለ ዕዳዎችም፣ በአላህ መንገድም በሚሠሩ፣ በመንገደኛም ብቻ ነው፡፡ ከአላህ የተደነገገች ግዴታ ናት፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡ إِنَّمَا الصَّدَقَاتُ لِلْفُقَرَاءِ وَالْمَسَاكِينِ وَالْعَامِلِينَ عَلَيْهَا وَالْمُؤَلَّفَةِ قُلُوبُهُمْ وَفِي الرِّقَابِ وَالْغَارِمِينَ وَفِي سَبِيلِ اللَّهِ وَابْنِ السَّبِيلِ ۖ فَرِيضَةً مِّنَ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ

ነቢያችን"ﷺ" በነቢይነት ከመላካቸው በፊት በዐረቡ ምድር ባሪያ ይሸጥ እና ይገዛ ነበር፥ ከዚያም ባሻገር እነርሱን መማታት፣ አካል ማጉደል እና መግደል መደበኛ ነገር ነበር። ነገር ግን ቁርኣን ሲወርድ ባሪያን ከባርነት ነጻ ማውጣት፣ የባሪያን አካል ያጎደለ ማጉደል፣ ባሪያን የገደለ መግደል ተደነገገ፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 21, ሐዲስ 49
ሠሙራህ ኢብኑ ጁንዱብ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ማንም ባሪያውን የገደለ እንገድለዋለን፥ ማንም አካሉን ያጎደለ አካሉን እናጎድለዋለን"። عَنْ سَمُرَةَ بْنِ جُنْدُبٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ مَنْ قَتَلَ عَبْدَهُ قَتَلْنَاهُ وَمَنْ جَدَعَهُ جَدَعْنَاهُ ‏"‏ ‏.‏

ነቢያችን"ﷺ" የራሳቸውን አገልጋዮች እና የሌሎችንም ጭምር ሚስት እና ባልደረባ በማድረግ ነጻ አውጥተዋል፥ ሶፊያህ፣ ማሪያህ፣ ዘይድ፣ አነሥ፣ ቢላል፣ ዐማር፣ ሱሀይብ ተጠቃሽ ናቸው፦
90፥11 ዓቀበቲቱንም አልወጣም። فَلَا اقْتَحَمَ الْعَقَبَةَ
90፥12 ዓቀበቲቱም መውጣቷ ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ? وَمَا أَدْرَاكَ مَا الْعَقَبَةُ
90፥13 እርሱም ባሪያን መልቀቅ ነው፡፡ فَكُّ رَقَبَةٍ

"ረቀባህ" رَقَبَة ማለት "ባሪያ" ወይም "አገልጋይ" ማለት ሲሆን ባለቤቱ ባሪያ ነጻ እስኪወጣ ድረስ የሚበላውን ማብላት፣ የሚለብሰውን ማልበስ ግዴታ አለበት። ከዐቅማቸው በላይ የሆነን ጫናን መጫን ሆነ መማታት ግን ሐራም ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 33, ሐዲስ 34
አቢ ዘር እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "አሏህ በእጃችሁ ሥር ያረጋቸው ባሮችን ወንድሞቻችሁ ናቸው፥ የምትበሉትን አብሏቸው፣ የምትለብሱትን አልብሷቸው፣ ከዐቅማቸው በላይ የሆነን ጫናን አትጫኗቸው። ከተጫናችዋቸው አግዟቸው"። عَنْ أَبِي ذَرٍّ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ "‏ إِخْوَانُكُمْ جَعَلَهُمُ اللَّهُ تَحْتَ أَيْدِيكُمْ فَأَطْعِمُوهُمْ مِمَّا تَأْكُلُونَ وَأَلْبِسُوهُمْ مِمَّا تَلْبَسُونَ وَلاَ تُكَلِّفُوهُمْ مَا يَغْلِبُهُمْ فَإِنْ كَلَّفْتُمُوهُمْ فَأَعِينُوهُمْ ‏"‏ ‏.‏

ባሪያ ነጻ በማውጣት አጅር ከሚያገኙት አሏህ ያርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ባሪያ በባይብል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

90፥13 እርሱም ባሪያን መልቀቅ ነው፡፡ فَكُّ رَقَبَةٍ

በባይብል ዕብራዊ ባሪያ በገንዘብ ከተገዛ ስድስት ዓመት አገልግሎ በሰባተኛው ዓመት ነጻ ይወጣል፥ ዕብራዊ ባሪያ ብቻውን በገንዘብ ተሽጦ ከሆነ ብቻውን ነጻ ይወጣል፥ ከእነ ሚስቱ ተሽጦ ከሆነ ሚስቱም በሰባተኛው ዓመት ከእርሱ ጋር ነጻ ትወጣለች፦
ዘጸአት 21፥2 ዕብራዊ ባሪያ የገዛህ እንደሆነ ስድስት ዓመት ያገልግልህ፥ በሰባተኛውም በከንቱ አርነት ይውጣ።
ዘጸአት 21፥3 ብቻውን መጥቶ እንደሆነ ብቻውን ይውጣ፤ ከሚስቱ ጋር መጥቶ እንደሆነ ሚስቱ ከእርሱ ጋር ትውጣ።

ቅሉ ግን ባሪያው ብቻውን ከተሸጠ በኃላ ገዢው ጌታ ሚስት ከዳረው እና ልጆች ከወለደ እርሱ በሰባተኛው ዓመት ነጻ ሲወጣ ሚስቱ እና ልጆቹ ግን ለገዛው ጌታ ባሪያ ይሆናሉ፥ በሰባተኛው ዓመት ይህ በገንዘብ የተገዛው ባሪያ ሚስቱ እና ልጆቹን ጥሎ ላለመሄድ ከፈለገ በገንዘቡ የገዛው ጌታ ወደ ፈራጆቹ ወስዶ ጆሮውን በወስፌ በስቶ ለዘላለም ባሪያ ያረገዋል፦
ዘጸአት 21፥4 ጌታው ሚስት አጋብቶት እንደ ሆነ ወንዶች ወይም ሴቶች ልጆች ብትወልድለት፥ ሚስቱና ልጆችዋ ለጌታው ይሁኑ፥ እርሱም ብቻውን ይውጣ።
ዘጸአት 21፥5 ባሪያውም፦ "ጌታዬን ሚስቴን ልጅቼንም እወድዳለሁ፥ አርነት አልወጣም" ብሎ ቢናገር፥ ጌታው ወደ "አማልክቱ" הָ֣אֱלֹהִ֔ים ይውሰደው፥ ወደ ደጁም ወደ መቃኑ አቅርቦ ጆሮውን በወስፌ ይብሳው፤ ለዘላለምም ባሪያው ይሁን።

እዚህ አንቀጽ ላይ "ሃ- ኤሎሂም" הָ֣אֱלֹהִ֔ים የተባሉት ፈራጆች ሲሆኑ ሰውን በዚህ ደረጃ ማሰቃየት ተገቢ ነውን? ከዕብራዊ ውጪ ያለ ባሪያ ደግሞ ባርነቱ የጊዜ ገደብ የለውም፥ ምክንያቱም እንደ ቦታ ርስት ናቸውና፦
ዘሌዋውያን 25፥44 ወንድ ባሪያና ሴት ባሪያ መግዛት ብትፈልግ ግን በዙሪያችሁ ካሉት ከእነርሱ ከአሕዛብ ወንድና ሴት ባሪያዎችን ግዙ።
ዘሌዋውያን 25፥45 ደግሞም በእናንተ መካከል ከሚቀመጡት መጻተኞች፥ በምድራችሁም ውስጥ ከወለዱአቸው በእናንተ መካከል ከሚቀመጡት ከዘራቸው ውስጥ ባሪያዎችን ግዙ፤ ርስትም ይሁኑላችሁ።

ሰውን ባሪያ አርጎ እንደ ሸቀጥ መግዛት እና መሸጥ በባይብል መደበኛ ሕግ ነው፥ እንግዲህ ከበርቴ መሸጥ የሚቻለው የሌላ ሰው ልጅ ብቻ ሳይሆን የገዛ ሴት ልጅን ጭምር ነው፦
ዘጸአት 21፥7 ሰውም ሴት ልጁን ለባርነት ቢሸጥ ባሪያዎች እንደሚወጡ እርስዋ አትውጣ።

በባይብል ባሪያ እንደ ሰው አይታይም፥ ሰው ሰውን ቢገድል ይገደላል፥ ነገር ግን ሰው ባሪያውን ቢገድል ይቀጣል እንጂ አይገደልም፦
ዘጸአት 21፥12 ሰው ሰውን ቢመታ ቢሞትም፥ እርሱ ፈጽሞ ይገደል።
ዘጸአት 21፥20 ሰውም ወንድ ባሪያውን ወይም ሴት ባሪያውን በበትር ቢመታ፥ ቢሞትበትም፥ ፈጽሞ ይቀጣ። የተመታው ግን አንድ ወይም ሁለት ቀን ቢቈይ ገንዘቡ ነውና አይቀጣ።

ሰው ባሪያውን ደብድቦት ባይሞት ምንም አይቀጣም። ባሪያ መግረፍ መደበኛ ሕግ መሆኑን የምናየው በኢየሱስ ትምህርት ውስጥ በተሰጠው ምሳሌ ነው፦
ሉቃስ 12፥47 የጌታውንም ፈቃድ አውቆ ያልተዘጋጀ እንደ ፈቃዱም ያላደረገ ያ ባሪያ እጅግ ይገረፋል።

"ሎሌ" ማለት "ወንድ ባሪያ" ማለት ሲሆን "ገረድ" ደግሞ "ሴት ባሪያ" ማለት ነው፥ በአዲስ ኪዳን እንኳን ባርነት ሊቀር ይቅርና ባሮች ለጠማማ ጌቶቻቸው በፍርሃት እንዲገዙ ወፍራም ትእዛዝ አለ፦
1 ጴጥሮስ 2፥18 ሎሌዎች ሆይ! ለበጎዎችና ለገሮች ጌቶቻችሁ ብቻ ሳይሆን ለጠማሞች ደግሞ በፍርሃት ሁሉ ተገዙ።
ኤፌሶን 6፥5 ባሪያዎች ሆይ! ለክርስቶስ እንደምትታዘዙ በፍርሃት እና በመንቀጥቀጥ በልባችሁ ቅንነት በሥጋ ጌቶቻችሁ ለሆኑ ታዘዙ።

ባሮች ለጌቶቻቸው መታዘዝ ያለባቸው ልክ ለክርስቶስ በፍርሃት እና በመንቀጥቀጥ እንደሚታዘዙት መሆን እንዳለበት ጳውሎስ አስረግጦና ረግጦ ይናገራል። መገዛት ያለባቸው ለታይታ ሳይሆን ከልባቸው መሆን አለበት፥ ከቀንበር በታች ያሉቱ ባሪያዎች ሁሉ ለገዙአቸው ጌቶች መገዛታቸው እና መታዘዛቸው እንደ ክብር መቁጠር አለባቸው፦
ቆላስይስ 3፥22 ባሪያዎች ሆይ፥ በቅን ልብ ጌታን እየፈራችሁ እንጂ፥ ለሰው ደስ እንደምታሰኙ ለታይታ የምትገዙ ሳትሆኑ በሥጋ ጌቶቻችሁ ለሆኑ በሁሉ ታዘዙ።
ቲቶ 2፥9-10 ባሪያዎች ስለ መድኃኒታችን ስለ እግዚአብሔር የሚሆነውን ትምህርት በሁሉ ነገር ያስመሰግኑ ዘንድ ለገዛ ጌቶቻቸው እንዲገዙ፣ በሁሉም ደስ እንዲያሰኙ፣ ሳይቃወሙና ሳይሰርቁም በጎ ታማኝነትን ሁሉ እንዲያሳዩ ምከራቸው።
1 ጢሞቴዎስ 6፥1 የእግዚአብሔር ስምና ትምህርቱ አንዳይሰደብ ከቀንበር በታች ያሉቱ ባሪያዎች ሁሉ ለገዙአቸው ጌቶች ክብር ሁሉ እንደ ተገባቸው ይቍጠሩአቸው።

ጥቁር ሰው በተለምዶ "ባሪያ" "ባሪዬ" "ባርች" የሚል ስያሜ የመጣው ምዕራባውያን አፍሪካውያንን በባርነት ከገዙበት ወዲህ ነው፥ ምዕራባውያ ክርስቲያኖች የባሪያ ንግድ ያጧጧፉት ብሉይ እና አዲስ ኪዳን ላይ ያሉትን አናቅጽ መሠረት አድርገው ነው። ስሌቭ"slave" የሚለው የእንግሊዙ ቃል እራሱ የመጣው ጀርመን ክርስቲያኖች ስላቭ"slavonic" ሕዝቦችን ወደ አሜሪካ አህጉር በባርነት መግዛት ከጀመሩበት ወዲህ ነው፥ ደቡብ አሜሪካን ያሉትን 642 ሚልዮን ሕዝቦች የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በባርነት እና በጉልበት በመግዛት ላቲን አሜሪካ ያደረገችበት እና ዛሬ ከላቲን አሜሪካ ሕዝብ 69% ካቶሊክ የሆነው በባርነት ነው። በኢሥላም ባሪያን ከባርነት ማላቀቅ የከፍታ ማማ ነው፦
90፥11 ዓቀበቲቱንም አልወጣም። فَلَا اقْتَحَمَ الْعَقَبَةَ
90፥12 ዓቀበቲቱም መውጣቷ ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ? وَمَا أَدْرَاكَ مَا الْعَقَبَةُ
90፥13 እርሱም ባሪያን መልቀቅ ነው፡፡ فَكُّ رَقَبَةٍ

ክርስቲያኖች ሆይ! የቱን ትመርጣላችሁ? በሕጉ ውስጥ ባሪያን ነጻ ለማውጣት የሚያስተምረውን እሥልምናን ወይስ ባርነትን የሚያጠናክር እና የሚያበረታታ ክርስትና? አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አምልኮተ ማርያም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥116 አላህም፡- «የመርየም ልጅ ዒሣ ሆይ! አንተ ለሰዎቹ፡- "እኔን እና እናቴን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጋችሁ ያዙ ብለሃልን?» በሚለው ጊዜ አስታውስ ፡፡ وَإِذْ قَالَ اللَّهُ يَا عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ أَأَنتَ قُلْتَ لِلنَّاسِ اتَّخِذُونِي وَأُمِّيَ إِلَـٰهَيْنِ مِن دُونِ اللَّهِ

እኛ ሙሥሊሞች፦ "ዐበይት ክርስቲያኖች ማለትም ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክ እና አንግሊካን ማርያምን ያመልካሉ" ስንል በተቃራኒው እነርሱ፦ "እናከብራታለን እንጂ አናምልካትም" ብለው ዓይናቸውን በጨው አጥበው ይዋሻሉ፥ ምክንያቱም "እናመልካታለን" ካሉ አምልኮ የሚገባው አንድ አምላክ እንደሆነ ባይብል ላይ በቅጡ ሰፍሯል፦
1ኛ ሳሙኤል 7፥3 ልባችሁንም ወደ ያህዌህ አቅኑ፥ እርሱንም ብቻ አምልኩ።
ማቴዎስ 4፥10 ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ።

"እርሱንም ብቻ አምልኩ" "እርሱንም ብቻ አምልክ" የሚል ጥብቅ ትእዛዝ አስምርበት! "እርሱ" ተብሎ የተቀመጠ ነጠላ ተሳቢ ተውላጠ ስም አንድ ቀዋሜ ማንነትን ቁልጭ እና ፍንትው አርጎ ያሳያል፥ አምልኮ የሚገባው ይህ አንዱ ማንነት ብቻ ነው። ይህንን ጥቅስ ሲያዩ ጭራሽ ወደ ማርያም፦ "ከልጅሽ ጋር አስታርቂን ብለን እጠይቃታለን እንጂ ወደ እርሷ አንጸልይም" የሚል ቅጥፈት ይቀጥፋሉ።

፨ሲጀመር ሁሉን ዐዋቂ፣ ሁሉን ሰሚ እና ሁሉን ተመልካች አንዱ አምላክ ሆኖ ሳለ የማወቅ፣ የመስማት እና የመመልከት ውስንነት ያለበትን ፍጡር በሌለበት መለማመን ሆነ መጠየቅ ሺርክ ነው።

፨ሲቀጥል ወደ ማርያም ድብን አርጋችሁ ትጸልያላችሁ፥ የአዋልድ መጻሕፍቶቻችሁ ይህንን ያሳብቃሉ፦
መጽሐፈ አርጋኖን ዘሰኞ ምዕራፍ 2 ቁጥር 1
"እኔ በዚህ ጸሎት በጸለይሁ ጊዜ ወደ አንደበቴ ነገር ጆሮሽን ዘንበል አድርገሽ ስሚ፥ ሰምተሽም ቸል አትበይ። በብሩኅ ልቦና በንጹሕ አሳብ የአንደበቴን ነገር ተቀበይው እንጂ"።
ክብረ ድንግል ማርያም 1
"እርሷን "ደስ ይበልሽ" እያልን ይቅርታ እንድትሰጠው ወደ እርሷ እንጸልያለን"።

፨ሢሰልስ በግልጽ እና በማያሻማ መልኩ ለማርያም አምልኮ እንደሚገባት ኢትዮጵያዊ ቄርሎስ ተብሎ የሚሽሞነሞነው አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ተናግሯል፦
እንዚራ ስብሐት ምዕራፍ 12 ቁጥር 98, "ለአንቺም የምስጋና እጅ መንሻን አቀርባለሁ፣ በመፍራት እገዛልሻለሁ፣ በመስገድም እጅ እነሣሻለሁ። የአምልኮ መሥዋዕትንም ለአንቺ እሠዋለሁ"።

የአምልኮ መሥዋዕት ሊሰዋለት የሚገባው አንድ አምላክ ሆኖ ሳለ ለማርያም መሠዋቱ በራሱ ዓይን ያስፈጠጠ እና ጥርስ ያስገጠጠ ሺርክ ነው።
፨ሲያረብብ በ 376 ድኅረ-ልደት የተነሱት ኮልይሪዲያን"collyridian" ክርስቲያኖች ኢየሱስ "ቴዎስ" θεός ብለው ባሉበት አፋቸው ማርያምን በግልጽ "ቴአ" θεά ማለትም "ሴት አምላክ" ይሏታል፥ ካቶሊክ፣ ኦርቶዶስ፣ አንግሊካን ኢየሱስን "ኩሪዮስ" κύριος ብለው ባሉበት አፋቸው ማርያምን በግልጽ "ኩሪያ" κυρία ማለትም "ሴት ጌታ" ይሏታል። በአገራችን ኦርቶዶክሶች ደግሞ ኢየሱስን "እግዚእ" ብለው ባሉበት አፋቸው ማርያምን በግልጽ "እግዚኢት" ማለትም "ሴት ጌታ" ይሏታል፥ ኢየሱስን "እግዚኢነ" ማለትም "ጌታችን" እንደሚሉት ሁሉ ማርያምን "እግዚኢትነ" ማለትም "ጌታችን" ይሉአታል። "አምላክ" ለሚለው ነጠላ ቃል ብዜት "አማልክት" ሲሆን ጸያፍ ርቢው "አምላኮች" ነው፥ እናማ ከዚህ የበለጠ ማርያምን አምላክ አድርጎ መያዝ አለን? ይህ አምልኮ ካልሆነ ምን ይባላል? ይህ አምልኮተ ማርያም ከልጇ የተገኘ ትምህርት ስላልሆነ አምላካችን አሏህ ኢየሱስን፦ "አንተ ለሰዎቹ፡- "እኔን እና እናቴን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጋችሁ ያዙ ብለሃልን? ብሎ ይጠይቀዋል፦
5፥116 አላህም፡- «የመርየም ልጅ ዒሣ ሆይ! አንተ ለሰዎቹ፡- "እኔን እና እናቴን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጋችሁ ያዙ ብለሃልን?» በሚለው ጊዜ አስታውስ ፡፡ وَإِذْ قَالَ اللَّهُ يَا عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ أَأَنتَ قُلْتَ لِلنَّاسِ اتَّخِذُونِي وَأُمِّيَ إِلَـٰهَيْنِ مِن دُونِ اللَّهِ

እርሱም፦ "በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል ጌታዬን እና ጌታችሁን አላህን ማለት ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም" በማለት መልስ ይሰጣል፦
5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል ጌታዬን እና ጌታችሁን አላህን ማለት ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَا أَمَرْتَنِي بِهِ أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ رَبِّي وَرَبَّكُمْ

"አምላክ" የሚለውም ቃል "መለከ" ማለትም "አመለከ" ከሚል የግዕዝ ቃል የመጣ ሲሆን "የሚመለክ" ማለት ነው። ከሣቴ ብርሃን ተሰማ የዐማርኛ መዝገበ ቃላት (2005) ገጽ 708)

ከዚህ አንጻር ዐበይት ክርስትና ማርያምን አያመልኳትምን? እንዴታ! ድብን አርገው ያመልካሉ። አንድ ሰው ፍላጎቱን አምላኩ አድርጎ ያዘ ማለት ፍላጎቱን አምላኬ ብሎ ጠራ ማለት ሳይሆን ለአምላክ የሚሰጠውን የአምልኮ ክፍል ለፍላጎቱ ቅድሚያ ሰጠ ማለት ነው፦
25፥43 ፍላጎቱን አምላኩ አድርጎ የያዘውን ሰው አየህን? አንተ በእርሱ ላይ ጠባቂ ትሆናለህን? أَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَـٰهَهُ هَوَاهُ أَفَأَنتَ تَكُونُ عَلَيْهِ وَكِيلًا

የማርያምን አምላክ አርጎ መያዝ በዚህ ሒሳብ መረዳት ይቻላል። በተመሳሳይ ጳውሎስ፦ "ሆዳቸው አምላካቸው ነው" ብሏል፦
ፊልጵስዩስ 3፥19 መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው።

ያ ማለት ማለት ሆዳቸውን "አምላኬ" ብለው ጠሩ ማለት ሳይሆን ለአምላክ የሚሰጠውን የአምልኮ ክፍል ለሆዳቸው ቅድሚያ ሰጡ ማለት ነው፥ የማርያምን አምላክ አርጎ መያዝ በዚህ ስሌት መረዳት ይቻላል። በዐበይት ክርስትና አምልኮተ ማርያም የተዘፈቃችሁ ካላችሁ ሞት ሳይመጣባችሁ አሊያም የፍርዱ ቀን ከመምጣቱ በፊት ወደ አሏህ በንስሓ ተመለሱ!
አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ያክብሩት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥80 መልእክተኛውን የሚታዘዝ ሰው በእርግጥ አላህን ታዘዘ፡፡ مَّن يُطِعِ الرَّسُولَ فَقَدْ أَطَاعَ اللَّهَ

አምላካችን አሏህ የላከውን መልእክተኛ የሚታዘዝ አሏህ ታዘዘ ማለት ነው፥ ለምሳሌ፦ ነቢያችንን”ﷺ” መታዘዝ አሏህን መታዘዝ ነው፥ በነቢያችን”ﷺ” ላይ ማመጽ በአሏህ ላይ ማመጽ ነው፦
4፥80 መልእክተኛውን የሚታዘዝ ሰው በእርግጥ አላህን ታዘዘ፡፡ مَّن يُطِعِ الرَّسُولَ فَقَدْ أَطَاعَ اللَّهَ
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 33, ሐዲስ 46
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "እኔን የሚታዘዝ በእርግጥ አሏህን ታዘዘ፥ እኔን የሚያምጽ በእርግጥ አሏህን አመጸ"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏”‏ مَنْ أَطَاعَنِي فَقَدْ أَطَاعَ اللَّهَ وَمَنْ يَعْصِنِي فَقَدْ عَصَى اللَّهَ

በተመሳሳይ መልእክተኛውን ኢየሱስን የሚያከብር የላከውን አምላክ ያከብራል፥ መልእክተኛውን ኢየሱስን የማያከብር የላከውን አምላክ አያከብርም፦
ዮሐንስ 5፥23 ሰዎች ሁሉ አብን "እንደ" ሚያከብሩት ወልድን ያክብሩት! ወልድን የማያከብር የላከውን አብን አያከብርም።

New International Version፦ "That all may honor the Son just as they honor the Father. Whoever does not honor the Son does not honor the Father, who sent him".

ግሪክ ኮይኔ፦ ἵνα πάντες τιμῶσι τὸν υἱὸν καθὼς τιμῶσι τὸν πατέρα. ὁ μὴ τιμῶν τὸν υἱὸν οὐ τιμᾷ τὸν πατέρα τὸν πέμψαντα αὐτόν.

እዚህ አንቀጽ ላይ "እንደ" ለሚለው ተውሳከ-ግስ አብ የአምልኮ ክብር እንደሚገባው ወልድም የአምልኮ ክብር ይገባዋል ማለት ሳይሆን ወልድ መልእክተኛ ስለሆነ ይዞት የመጣውን መልእክት ታሳቢ በማድረግ መልእክተኛው ማክበር የላከውን ማክበር ነው፥ "ወልድን የማያከብር የላከውን አብን አያከብርም" የሚለው ኃይለ-ቃል ሊሰመርበት ይገባል። ተመሳሳይ ሰዋስው እስቲ እንይ፦
ኤፌሶን 5፥22 ሚስቶች ሆይ! ለጌታ "እንደ" ምትገዙ ለባሎቻችሁ ተገዙ።

እዚህ አንቀጽ ላይ "እንደ" ለሚለው ተውሳከ-ግስ መግባቱ ሚስት ጌታን እንደምትገዛ ባሏን መገዛት ይገባታል እያለ ነውን? ለጌታ በመስገድ እና በማምለክ እንደምትገዛ ለባሏ በመስገድ እና በማምለክ ትገዛ እያለ ነውን? "አይ አይደለም፥ ጌታን የምትገዛ ሴት ባሏን ትገዛ ማለት እንጂ ባሏን ጌታዋን በምትገዛው መጠን እና ይዘት ትገዛው ማለት አይደለም" ካላችሁ እንግዲያውስ ላኪውን የሚያከብር የተላከውን ማክበር አለበት በሚል ስሌት እና ቀመር ተረዱት! እንቀጥል፦
ኤፌሶን 6፥7 ለሰው ሳይሆን ለጌታ "እንደ" ምትገዙ በትጋት እና በበጎ ፈቃድ ተገዙ።

እዚህ አንቀጽ ላይ "እንደ" ለሚለው ተውሳከ-ግስ መግባቱ ባሮች ጌታን እንደሚገዙት ጌቶቻቸውን መገዛት ይገባቸዋል እያለ ነውን? ለጌታ በመስገድ እና በማምለክ እንደሚገዙት ለጌቶቻቸው በመስገድ እና በማምለክ ይገዙ እያለ ነውን? "አይ አይደለም፥ ጌታን የሚገዙ ባሮች ጌቶቻቸውን ይገዙ ማለት እንጂ ባሮች ጌቶቻቸውን በሚገዙበት መጠን እና ይዘት ይገዙት ማለት አይደለም" ካላችሁ እንግዲያውስ ላኪውን የሚያከብር የተላከውን ማክበር አለበት በሚል መልክ እና ልክ ተረዱት! ኢየሱስ፦ "እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል" ብሏል፥ እና ሐዋርያት ኢየሱስ ናቸውን? ተመሳሳይ ሰዋስው ነው፦
ማቴዎስ 10፥40 እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።

"እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል" ማለት "ሐዋርያትን መቀበል ኢየሱስን እንደ መቀበል ነው" ማለት ከሆነ እንግዲያውስ "ወልድን የማያከብር የላከውን አብን አያከብርም" ማለት "ወልድን አለማክበር አብን እንደ አለማክበር ነው" ማለት ነው፥ "እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል" ማለት "ወልድን መቀበል አብን እንደ መቀበል ነው" ማለት ከሆነ "ወልድን ማክበር አብን እንደ ማክበር ነው" ማለት ነው። በእርግጥም ፈጣሪ እና ፍጡር በአንድ ነጠላ ግሥ ውስጥ ስለመጡ ያ ፍጡር ፈጣሪ ነው ወይም ያ ፍጡር ከፈጣሪ ጋር ይመለካል ማለት በፍጹም አይደለም፥ ምክንያቱም በብሉይ ኪዳን ይህንን የሚያሳይ ናሙና አለ፦
ዜና 35፥3 አሁንም አምላካችሁን ያህዌህን እና ሕዝቡን እስራኤልን አገልግሉ። עִבְדוּ֙ אֶת־יְהוָ֣ה אֱלֹֽהֵיכֶ֔ם וְאֵ֖ת עַמֹּ֥ו יִשְׂרָאֵֽל׃

"ዒብዱ" עִבְדוּ֙ ማለት "አገልግሉ" "ተገዙ" "አምልኩ" ማለት ነው፥ እና የእስራኤል ሕዝብ ከያህዌህ ጋር ይመለካል ማለት ነውን? "አይ የእስራኤል ሕዝብ ይገለገላል የተባለው ያህዌህ በሚገለገልበት ሒሣብ አይደለም" ካላችሁ እንግዲያውስ ወልድ የሚከበረው አብ በሚከበርበት ሒሣብ በፍጹም አይደለም። በተጨማሪም ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" "ሰውን ያላመሰገነ አሏህን አያመሰግንም" ብለዋል፥ ያ ማለት ሰው የሚመሰገነው አሏህ በሚመሰገንበት መጠን እና ይዘት አይደለም፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 39
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ሰውን ያላመሰገነ አሏህን አያመሰግንም"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ لاَ يَشْكُرُ اللَّهَ مَنْ لاَ يَشْكُرُ النَّاسَ ‏"‏ ‏.‏

አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ፀሐይ እና ጨረቃ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

10፥5 እርሱ ያ ፀሐይን "አንጻባራቂ" ጨረቃንም "አብሪ" ያደረገ ነው፡፡ هُوَ الَّذِي جَعَلَ الشَّمْسَ

"ሢራጅ" سِرَاج ማለት በዓይን ለማየት አስቸጋሪ ከመሆኑ የተነሳ "አንጸባራቂ" ማለት ሲሆን "ሙኒር" مُّنِير ማለት ደግሞ "አብሪ" ማለት ነው፥ አምላካችን አሏህ በቅርቢቱ ሰማይ ላይ "ሢራጅ" سِرَاج የተባለችው ፀሐይ እና "ሙኒር" مُّنِير የተባለው ጨረቃ አድርጓል፦
10፥5 እርሱ ያ ፀሐይን ሲራጅ ጨረቃንም ሙኒር ያደረገ ነው፡፡ هُوَ الَّذِي جَعَلَ الشَّمْسَ ضِيَاءً وَالْقَمَرَ نُورًا

አምላካችን አሏህ በቅርቢቱ ሰማይ ላይ ከዋክብትን ያረጋቸው በረጨት ነው፥ “ረጨት” ማለት የከዋክብት ስብስብ”galaxy” ማለት ሲሆን የእኛ ረጨት “ፍኖተ-ሃሊብ”Milky Way” ይባላል። ይህ ረጨት ውፍረቱ 1000 የብርሃን ዓመት እንደሆነ ይገመታል፥ ከአንዱ ጫፍ እስከሌላኛው ጫፍ ያለው ርቀት በዲያሜትር ሲለካ እንኳን እራሱ 100,000 የብርሃን ዓመት ይሆናል። የሚያጅበው በውስጡ ከ100 እስከ 400 ቢልዮን ከዋክብቶች እንደያዘ ይገመታል፥ ይህ አንዱ ኅብረ-ከዋክብት ወይም ማዛሮት”constellation” ደግሞ “ቡርጅ” بُرْج ይባላል። በቅርቢቱ ሰማይ ብዙ ረጨቶች ስላሉ አምላካችን አሏህ “ቡሩጅ” بُرُوج በማለት ነግሮናል፦
37፥6 እኛ ቅርቢቱን ሰማይ በከዋክብት ጌጥ አጌጥናት፡፡ إِنَّا زَيَّنَّا السَّمَاءَ الدُّنْيَا بِزِينَةٍ الْكَوَاكِبِ
25፥61 “ያ በሰማይ ቡሩጆችን ያደረገ እና በእርሷም ፀሐይን ሲራጅ እና ጨረቃን ሙኒር ያደረገ ጌታ ክብሩ በጣም ላቀ”፡፡ تَبَارَكَ الَّذِي جَعَلَ فِي السَّمَاءِ بُرُوجًا وَجَعَلَ فِيهَا سِرَاجًا وَقَمَرًا مُّنِيرًا

"ፊ-ሃ" فِيهَا ማለት "በ-ውስጧ" ማለት ሲሆን "ሃ" هَا የሚለው ተሳቢ ተውላጠ ስም "ሠማኡ አድ-ዱንያ" سَّمَاء الدُّنْيَا ማለትም "ቅርቢቱን ሰማይ" የሚለውን ቃል ተክቶ የመጣ ነው። አሏህ በሌላ አንቀጽ ፀሐይን "ዲያእ" ضِيَاء ጨረቃን ደግሞ "ኑር" نُور ይለዋል፦
71፥16 በውስጣቸውም ጨረቃን ኑር አደረገ፥ ፀሐይንም ሲራጅ አደረገ፡፡ وَجَعَلَ الْقَمَرَ فِيهِنَّ نُورًا وَجَعَلَ الشَّمْسَ سِرَاجًا

"ፊ-ሂነ" فِيهِنَّ ማለት "በ-ውስጣቸውም" ማለት ሲሆን "ሂነ" هِنَّ የሚለው ተሳቢ ተውላጠ ስም "ሰማዋት" سَمَاوَات የሚለውን አንስታይ ብዜት ተክቶ የመጣ ነው፥ ታዲያ ፀሐይ እና ጨረቃ በቅርቢቱ ሰማይ ውስጥ ሆነው ሳሉ ለምን "በሰማያት ውስጥ" ተባሉ? ሲባል ቅርቢቱ ሰማይ ከሰባቱ ሰማያት ውስጥ የመጀመሪያይቱ ሰማይ ናት፦
ሪያዱ አስ-ሷሊሒን መጽሐፍ 1, ሐዲስ 184
ስለ ኢሥራእ በዝነኛ ሐዲስ አነሥ”ረ. ዐ.” እንደተረከው፦ “የአላህ መልክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ጂብሪል ከእኔ ጋር ወደ ቅርቢቱ ሰማይ ወጣ፥ እንዲከፈት ተጠየቀ። ዘበኛው፦ “ይህ ማን ነው? ብሎ ጠየቀ፥ ጂብሪልም፦ “ጂብሪል” አለ። “ከአንተ ጋር ያለውስ? እርሱም፦ “ሙሐመድ ነው” አለ። ከዚያም በተመሳሳይ ወደ ሁለተኛ፣ ወደ ሦስተኛ፣ ወደ አራተኛ እና ወደተቀሩት ሰማያት ሁሉ ወጣ። የሁሉም ሰማይ በር ላይ “ይህ ማን ነው? ተብሎ ተጠየቀ፥ “ጂብሪል ነው” ተባለ”። عن أنس رضي الله عنه في حديثه المشهور في الإسراء قال‏:‏ قال رسول الله صلى الله عليه وسلم ‏:‏ ‏ “‏ثم صعد بي جبريل إلي السماء الدنيا فاستفتح، فقيل‏:‏ من هذا‏؟‏ قال‏:‏ جبريل، قيل‏:‏ومن معك‏؟‏ قال‏:‏ محمد‏.‏ ثم صعد إلي السماء الثانية والثالثة والرابعة وسائرهن، ويقال في باب كل سماء‏:‏ من هذا‏؟‏ فيقول‏:‏ جبريل‏”‏

ለምሳሌ፦ "እኔ የምኖረው አፍሪካ ውስጥ ነው" ብል "ኢትዮጵያ ውስጥ ነው" ለማለት ፈልጌ እንጂ "ታንዛኒያ፣ አልጄሪያ፣ ናይጄሪያ ወዘተ ውስጥ ነው" ማለት አይደለም፥ በተመሳሳይ "ፀሐይ እና ጨረቃ በሰማያት ውስጥ ናቸው" ሲባል "ከሰባቱ ሰማያት የመጀመሪያይቱ ሰማይ ቅርቢቱ ሰማይ ውስጥ ናቸው" ማለት ነው። በተጨማሪ መላእክት የሚኖሩት በሰባተኛው ሰማይ ላይ እንደሆነ እሙን እና ቅቡል ነው፦
40፥7 እነዚያ ዐርሹን የሚሸከሙት እና እነዚያም በዙሪያው ያሉት በጌታቸው ምስጋና ያወድሳሉ፡፡ በእርሱም ያምናሉ፡፡ الَّذِينَ يَحْمِلُونَ الْعَرْشَ وَمَنْ حَوْلَهُ يُسَبِّحُونَ بِحَمْدِ رَبِّهِمْ وَيُؤْمِنُونَ بِهِ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 10, ሐዲስ 176
አቢ ሁረይራህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም አሉ፦ "ከእናንተ ውስጥ አንዱ "አሚን" በሚልበት ጊዜ በሰማይ ውስጥ ያሉት መላእክት "አሚን" ይላሉ"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ إِذَا قَالَ أَحَدُكُمْ آمِينَ‏.‏ وَقَالَتِ الْمَلاَئِكَةُ فِي السَّمَاءِ آمِينَ‏.‏

ነገር ግን መላእክት በሰባተኛ ሰማይ ቢኖሩም ሰባተኛ ሰማይ የሰማያት ክፍል ስለሆነ መልአክ በሰማያት ውስጥ እንደሚኖር ተገልጿል፦
53፥26 "በሰማያት ውስጥ ካለ መልአክም" ብዙዎች ሊማለዱለት ለሚሻው እና ለሚወደው ሰው ከፈቀደ በኋላ ቢኾን እንጂ ምልጃቸው ምንም አትጠቅምም፡፡ وَكَم مِّن مَّلَكٍ فِي السَّمَاوَاتِ لَا تُغْنِي شَفَاعَتُهُمْ شَيْئًا إِلَّا مِن بَعْدِ أَن يَأْذَنَ اللَّهُ لِمَن يَشَاءُ وَيَرْضَىٰ

ፀሐይ እና ጨረቃ በሰማያት ውስጥ መደረግን በዚህ ልክ እና መልክ መረዳት ነው እንጂ "ቁርኣን ስለ ሥነ-አጽናፈ ዓለም ጥናት"cosmology" ያለው ምልከታ የተሳሳተ ነው" ብሎ ያለ ዕውቅት የውሸት ድሪቶ በቅሰጣ ስልቻ ውስጥ መደረት ተገቢ አይደለም፥ እኛም "ከባዶ አንድ ሰርዶ" ብለን ከሚነሱ ቅሰጣዎች አንዱ ለሆነውን ቅሰጣ መልስ ሰተናል። ፀሐይ እና ጨረቃ የአሏህ ተአምራት ናቸው፦
41፥37 ሌሊትና ቀንም፥ ፀሐይ እና ጨረቃ ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 16, ሐዲስ 9
አቢ በክራህ" እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም አሉ፦ "ፀሐይ እና ጨረቃ ከአሏህ ተአምራት መካከል ሁለት ተአምራት ናቸው"። عَنْ أَبِي بَكْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ إِنَّ الشَّمْسَ وَالْقَمَرَ آيَتَانِ مِنْ آيَاتِ اللَّهِ،

"አያህ" آيَة ማለት "ምልክት" "ታምር" ማለት ሲሆን "አያት" آيَتَان ማለት ደግሞ "ምልክቶች" "ታምራት" ማለት ነው፥ በእርግጥም ፀሐይ እና ጨረቃ ከአሏህ ተአምራት መካከል ሁለት ተአምራት ናቸው። አሏህ ቀሳጢዎችን ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛን ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
እዚህ ቴሌ ግራም ውስጥ ከ 500 በላይ በሆኑ አርዕስት ተከሽኖ ተከትቧል። በየርዕሱ ቅድመ ተከተል የተሰደረ ስለሆነ ሰርች እያረጋችሁ ማንብበብ ትችላላችሁ። ፦ https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid06tVAncTpGi2htM688c4NBpdZihUmR56sCWdSQBuYs4ER1BCWkWDs9PfjvQNei7Sil&id=100001488132377
ንጽጽር ላይ የምንጦምረው ጦማር እንደ ኮሶ ቢመራችሁ እና እንደ እንቆቆ ቢቆመጥጣችሁ ኮሶ መጠጣቱ እና እንቆቆ መብላቱ ፍቱን መድኃኒት ነው።
የሼይኽ ሑሤን ጅብሪል ትንቢት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

33፥40 ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንድንም ሰው አባት አይደለም፤ ነገር ግን የአላህ መልክተኛ እና *”የነቢያት መደምደሚያ”* ነው፤ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው። مَا كَانَ مُحَمَّدٌ أَبَا أَحَدٍ مِنْ رِجَالِكُمْ وَلَٰكِنْ رَسُولَ اللَّهِ وَخَاتَمَ النَّبِيِّينَ وَكَانَ اللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمًا

ቁርኣን አንድ ሦስተኛው “ገይብ” غَيْب ማለትም “የሩቅ ወሬ” ነው፤ “ገይብ” በጥቅሉ በሶስት ይከፈላል፦
፦አንደኛው “አል-ገይቡል ማዲ” الغيبه الماضي ሲሆን ያለፈ ክስተት ነው፤ ይህም ድርጊቱ ከዚህ በፊት አላፊ የሆነ ነገር ነው።
፦ሁለተኛው “አል-ገይቡል ሙዷሪዕ” الغيب المضارع ሲሆን እየተፈጸመ ያለ ክስተት ነው፤ ይህም ድርጊቱ በአሁኑ ሰዓት ቀጣይነት ያለው ከህዋስ ባሻገር ያለ ነገር ነው።
፦ሦስተኛው እና የመጨረሻው “አል-ገይቡል ሙሥተቅበል” الغيب المستقبل ሲሆን መጪው ክስተት ነው፤ ይህም ድርጊቱ ገና ያልተፈጸመ ወደፊት የሚሆን ነው። አላህ ከፍጡራን በኃላ ወደ ፊት ምን እንሚከሰት ያውቃል፥ ይህ ለምሳሌ ከአሁን እስከ ትንሳኤ ቀን ክስተቶችን ምን እንሚመከሰቱ ከአላህ በቀር ማንም አያውቅም፦
28፥65 *«በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ ”ሩቅን ምስጢር” አያውቅም፤ ግን አላህ ያውቀዋል*፡፡ መቼ እንደሚቀሰቀሱም አያውቁም» በላቸው፡፡ قُل لَّا يَعْلَمُ مَن فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ ٱلْغَيْبَ إِلَّا ٱللَّهُ ۚ وَمَا يَشْعُرُونَ أَيَّانَ يُبْعَثُونَ
6፥59 *”የሩቅ ነገርም” መክፈቻዎች እርሱ ዘንድ ናቸው፡፡ ከእርሱ በቀር ማንም አያውቃቸውም*፡፡ وَعِندَهُۥ مَفَاتِحُ ٱلْغَيْبِ لَا يَعْلَمُهَآ إِلَّا هُوَ ۚ

“ገይብ” በተናጥል ሁለት ደረጃ አለው አንዱ አላህ ብቻ የሚያውቀው ሲሆን “አል-ገይቡል ሙጥለቅ” الغيب المطلق ሲባል፣ ሁለተኛው ደግሞ አላህ ለሚልከው ነቢይ ሲያሳውቅ ያ የሚያሳውቀው የሩቅ ነገር ምስጢር “አል-ገይቡ አን-ኒስቢይ” الغيب النسبي ይባላል፤ አላህ ወደፊት የሚከሰተውን ክስተት አስቀድሞ ለሚወደው ነቢይ ይገልጥለታል፦
72፥26 *«እርሱ ”ሩቁን ምስጢር” ዐዋቂ ነው፡፡ በምስጢሩም ላይ አንድንም አያሳውቅም፡፡»* عَٰلِمُ ٱلْغَيْبِ فَلَا يُظْهِرُ عَلَىٰ غَيْبِهِۦٓ أَحَدًا
72፥27 *ከመልክተኛ ለወደደው ቢኾን እንጅ ለሌላ አይገልጽም*፡፡ إِلَّا مَنِ ٱرْتَضَىٰ مِن رَّسُولٍۢ

አላህ ስለ ራሱ በሦስተኛ መደብ “ኢዝ ቃለ” إِذْ قَالَ ማለትም “ባለ ጊዜ አስታውስ” ወይም በመጀመሪያ መደብ “ኢዝ ቁልና” إِذْ قُلْنَا ማለትም “ባልን ጊዜ አስታውስ” በማለት ከነቢያችን”ﷺ” በኃላ ወደፊቱ የሚከሰተውን ምን እንደሚል ይናገራል፤ ፍጡራንም ምን እንደሚሉ ሲናገር “ኢዝ ቃሉ” إِذْ قَالُوا ማለትም “ባሉ ጊዜ አስታውስ” በማለት ይናገራል። ይህንን የሩቅ ወሬ አምላካችን አላህ ለነቢያችን”ﷺ” “ኑሒሂ ኢለይከ” نُوحِيهِ إِلَيْكَ ማለትም “ወደ አንተ እናወርዳለን” ወይም “ነቁስሱ ዐለይከ” نَقُصُّ عَلَيْكَ ማለትም “እንተርክልሃለን” በማለት ይናገራል። ይህንን የሩቅ ወሬ “ፈዘከር” فَذَكِّرْ ማለትም “አስታውስ” ይላቸዋል። ነቢያችን”ﷺ” ደግሞ “ሙዘከር” مُذَكِّرٌ ማለትም “አስታዋሽ” ናቸው፦
88፥21 *አስታውስም፤ አንተ አስታዋሽ ብቻ ነህና*፡፡ فَذَكِّرْ إِنَّمَا أَنتَ مُذَكِّرٌ

ነቢያችን”ﷺ” የሚያሳታውሱት ከራሳቸው አመንጭተው ሳይሆን በተወረዳቸው “ዚክር” ذِكْر ማለትም “ማስታወሻ” ብቻ ነው፤ ይህም ዚክር ቁርኣን ነው፦
21፥50 *ይህም ያወረድነው የኾነ ብሩክ “ዚክር” ነው*፡፡ ታዲያ እናንተ ለእርሱ ከሓዲዎች ናችሁን? وَهَـٰذَا ذِكْرٌ مُّبَارَكٌ أَنزَلْنَاهُ ۚ أَفَأَنتُمْ لَهُ مُنكِرُونَ
21፥45 *”የማስጠነቅቃችሁ በተወረደልኝ ብቻ ነው”*፡፡ ግን ደንቆሮዎች በሚስጠነቀቁ ጊዜ ጥሪን አይሰሙም» *በላቸው*፡፡ قُلْ إِنَّمَا أُنذِرُكُم بِالْوَحْيِ ۚ وَلَا يَسْمَعُ الصُّمُّ الدُّعَاءَ إِذَا مَا يُنذَرُونَ
50፥45 እኛ የሚሉትን ሁሉ ዐዋቂ ነን፤ አንተም በእነርሱ ላይ አስገዳጅ አይደለህም፡፡ ስለዚህ ዛቻዬን የሚፈራን ሰው *በቁርኣን አስታውስ*፡፡ نَّحْنُ أَعْلَمُ بِمَا يَقُولُونَ ۖ وَمَا أَنتَ عَلَيْهِم بِجَبَّارٍ ۖ فَذَكِّرْ بِالْقُرْآنِ مَن يَخَافُ وَعِيدِ

“አል-ገይቡል ሙሥተቅበል” የመጪው ጊዜ "ትንቢት" ነው፤ "ትንቢት" ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ነበእ” نَبَإِ ነው። “ነቢይ” نبي የሚለው ቃል “ነበአ” نَبَّأَ ከሚለው የግስ መደብ እና “ነበእ” نَبَإِ ከሚለው የስም መደብ የመጣ ሲሆን “የሩቅ ወሬ አውሪ” ማለት ነው፤ ነቢያችን"ﷺ" "ነቢይ" ሲሆኑ አላህ ያወረደላቸው ቁርኣን ደግሞ "ነበእ" ነው፦
78፥1-4 ከምን ነገር ይጠያየቃሉ? *ከታላቁ ትንቢት*፤ ከዚያ እነርሱ በእርሱ የተለያዩበት ከኾነው፡፡ ይከልከሉ፤ *ወደፊት በእርግጥ ያውቃሉ*፡፡ عَمَّ يَتَسَآءَلُونَ عَنِ ٱلنَّبَإِ ٱلْعَظِيمِ ٱلَّذِى هُمْ فِيهِ مُخْتَلِفُونَ كَلَّا سَيَعْلَمُونَ
38፥67 በላቸው *«እርሱ ቁርኣን ታላቅ ትንቢት ነው*፡፡ قُلْ هُوَ نَبَأٌ عَظِيمٌ

ቁርኣን ታላቁ ትንቢት ነው፤ ይህንን ትንቢት አምላካችን አላህ፦ "ትንቢቱን በእርግጥ ከጊዜ በኋላ ወደፊትም ታውቁታላችሁ" ይለናል፦
38፥88 *«ትንቢቱንም ከጊዜ በኋላ በእርግጥ ታውቁታላችሁ፡፡* وَلَتَعْلَمُنَّ نَبَأَهُ بَعْدَ حِينٍ
6፥67 *ለትንቢት ሁሉ የሚደርስበት መርጊያ አለው፡፡ ወደፊትም ታውቁታላችሁ*፡፡ لِّكُلِّ نَبَإٍ مُّسْتَقَرٌّ ۚ وَسَوْفَ تَعْلَمُونَ

አምላካችን አላህ ይህንን ትንቢት ነቢያችን"ﷺ" እንዲያስጠነቅቁ "አንተ ነቢዩ ሆይ" በማለት እያናገራቸው ልኳቸዋል፦
33፥45 *አንተ ነቢዩ ሆይ! እኛ መስካሪ፣ አብሳሪና አስጠንቃቂም አድርገን ላክንህ*፡፡ يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ إِنَّا أَرْسَلْنَاكَ شَاهِدًا وَمُبَشِّرًا وَنَذِيرًا
ነቢያችን”ﷺ” የነቢያት መደምደሚያ ናቸው፤ ወሕይ መውረድ እሳቸው ጋር ቆሟል፤ ከእርሳቸው በኃላ ሪሳላ መውረድ አሊያም ነበእ መውረድ ቆሟል፦
33፥40 ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንድንም ሰው አባት አይደለም፤ ነገር ግን የአላህ መልክተኛ እና *”የነቢያት መደምደሚያ”* ነው፤ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው። مَا كَانَ مُحَمَّدٌ أَبَا أَحَدٍ مِنْ رِجَالِكُمْ وَلَٰكِنْ رَسُولَ اللَّهِ وَخَاتَمَ النَّبِيِّينَ وَكَانَ اللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمًا
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 2272
አነስ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”በእርግጥም መልእክተኛነት እና ነብይነት ተዘግቷል። ከእኔ በኃላ መልእክተኛም ነብይም የለም*። حَدَّثَنَا أَنَسُ بْنُ مَالِكٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ” إِنَّ الرِّسَالَةَ وَالنُّبُوَّةَ قَدِ انْقَطَعَتْ فَلاَ رَسُولَ بَعْدِي وَلاَ نَبِيَّ

ምን ትፈልጋለህ? ነቢያችን"ﷺ" ከእርሳቸው በኃላ የፈጣሪ ነቢይ ፈጽሞና ጨልጦ እንደማይመጣ ፍርጥ አርገው እንቅጩን ነግረውናል። እዚሁ ሐዲስ ላይ "ነቢይነት"Prophethood" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ኑቡወት" نُّبُوَّة ሲሆን “ነበእ” نَبَإِ ለሚለው ቃል ተለዋዋጭ ቃል ነው፤ ነቢይነት ከተዘጋ ትንቢትም ተዘግቷል። ከእርሳቸው በኃላ የሚመጣ ነቢይ እና መልክተኛ ከሌለ ከቁርኣን በኃላ የምሰማው ከፈጣሪ የመጣ መልእክት እና ትንቢት የለም። አለ የተባለው ሁሉ የሐሳዌ መልእክት እና ትንቢት ነው። “አድ-ደጃል” الدجّال‌‎ የሚለው ቃል “ደጀለ” دَجَلَ ማለትም “ቀላቀለ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “ቀላቃይ” ማለት ነው፤ እውነትን ከሐሰት ጋር የሚቀላቅል ማለት ነው፤ ይህ ቋንቋዊ ፍቺው ሲሆን ሃይማኖታዊ ፍቺው ደግሞ “ኀሳዌ” ማለትም “አሳሳች” “ውሸተኛ” “ቀጣፊ” ማለት ነው። ዋናው ደጃል “መሢሑል ደጃል” ማለትም “ኀሳዌ መሢሕ” ሲሆን እርሱ ከመምጣቱ በፊት የሚመጡ ሠላሳ ደጃሎች አሉ፤ “ደጅጃሉን” دَجَّالُونَ የሚለው ቃል “ደጃል” دجّال‌‎ ለሚለው ነጠላ ቃል ብዜት ነው፤ እነዚህ ወደ ሠላሳ የሚቃረቡ ደጃሎች “እኔ የአላህ መልእክተኛ ነኝ” ወይም “እኔ የአላህ ነብይ ነኝ” ብለው ይነሳሉ፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 54, ሐዲስ 108
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው ነብዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“የመጨረሻይቱ ሰአት አትቆምም ሠላሳ የሚቃረቡ ደጃሎች ቀጣፊዎች ተነስተውስ፦ “እኔ የአላህ መልእክተኛ ነኝ” ብለው ቢናገሩ ቢሆን እንጂ”*። عَنْ أَبِي، هُرَيْرَةَ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ” لاَ تَقُومُ السَّاعَةُ حَتَّى يُبْعَثَ دَجَّالُونَ كَذَّابُونَ قَرِيبٌ مِنْ ثَلاَثِينَ كُلُّهُمْ يَزْعُمُ أَنَّهُ رَسُولُ اللَّهِ
ሱነን አቢ ዳውድ :መጽሐፍ 37, ሐዲስ 13
የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *ከእኔ ኡማህ ውስጥ ሠላሳ የሚያህሉ ቀጣፊዎች፦ “ነብይ ነኝ” ብለው ይነሳሉ፤ ነገር ግን እኔ የነብያት መደምደሚያ ነኝ፤ ከእኔ በኃላ ነብይ የለም”*። وَحَتَّى تَعْبُدَ قَبَائِلُ مِنْ أُمَّتِي الأَوْثَانَ وَإِنَّهُ سَيَكُونُ فِي أُمَّتِي كَذَّابُونَ ثَلاَثُونَ كُلُّهُمْ يَزْعُمُ أَنَّهُ نَبِيٌّ وَأَنَا خَاتَمُ النَّبِيِّينَ لاَ نَبِيَّ بَعْدِي

በነቢያችን"ﷺ" ኡማህ ውስጥ የሚነሱት እነዚህ ሐሰተኛ ነቢያት ሲሆኑ በክርስትናው ደግሞ የተነሱት እልፍ አእላፍ ናቸው። "ነቢይ ነኝ" ብለው የተነሱት ባሃኦላህ፣ ረሺድ ኸሊፋህ፣ ጉላም አሕመድ ወዘተ መነሻቸው "ለወልይ የሚሰጥ ከራመት አለኝ" በሚል ሽፋን ነው፤ "ዶሮን ሲያታልሏት፥ ሙቁ ውኃው ለገላሽ ነው አሏት" ይባል የለ? የወደፊቱን ክስተት፣ ክንውን፣ እና ድርጊት ዕናውቃለን የሚሉት ጋር ሄዶ ማመን ትልቁ ሺርክ ነው፥ ከኢሥላም አጥር ያስወጣል፤ ድርጊቱ ኩፍር ነው፦
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 682
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንዳለው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው፦ ማንም በሓይድ ላይ ካለች ሴት ወይም በመቀመጫዋ በኩል ተራክቦ ቢያደርግ *"አሊያም ወደ ተንባይ ቢሄድና የተነገረውን ቢያምን በሙሐመድ”ﷺ” ላይ በተወረደው ክዷል"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ "‏ مَنْ أَتَى حَائِضًا أَوِ امْرَأَةً فِي دُبُرِهَا أَوْ كَاهِنًا فَصَدَّقَهُ بِمَا يَقُولُ فَقَدْ كَفَرَ بِمَا أُنْزِلَ عَلَى مُحَمَّد

"ካሂን" كَاهِن የሚለው ቃል "ከሀነ" كَهَنَ‎ ማለትም "ተነበየ" ከሚል ሥርወ-ቃል የተገኘ ሲሆን "የሩቅ ነገር ተንባይ" ማለት ነው፤ እነዚህ የሩቅ ነገርን ዕናውቃለን የሚሉ ጠንቋዮችንም ያመለክታል። ስለዚህ ትንቢት ተነበዩ የተባሉት በዓለማችን ውስጥ ኖስትራዳመስ"Nostradamus" እንዲሁ በአገራችን እዩ ጩፋ፣ እኅተ ማርያም ሆነ ሼህ ሑሤን ጅብሪል ከአላህ ያልሆነ የሐሳዌ ጽርፈት መሆኑን ከወዲሁ መጠንቀቅ ነው። በተለይ ክርስቲያኖች የሼይኽ ሑሤን ጅብሪል ትንቢት እያሉ የሚያናፍሱት፣ የሚደርሱትና የሚጽፉት እሥልምና ትክክል መሆኑን ለማሳወቅ ሳይሆን ቅቤ አንጓችና አስብቶ አራጅ ስለሆኑ ነው። "አሞኛችሁ ዘንድ ዐይናችሁን ጨፍኑ፥ ጆሮአችሁን ድፈኑ" ብንባል ፍንክች የአባ ቢላዋ ልጅ ብለናል። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የሣሚሪይ ጥጃ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

7፥148 የሙሣም ሕዝቦች ከእርሱ መኼድ በኋላ ከጌጦቻቸው ወይፈንን አካልን ለእርሱ "ማግሳት" ያለውን አምላክ አድርገው ያዙ፡፡ وَاتَّخَذَ قَوْمُ مُوسَىٰ مِن بَعْدِهِ مِنْ حُلِيِّهِمْ عِجْلًا جَسَدًا لَّهُ خُوَارٌ

ሙሣ ለአርባ ቀን ወደ ተራራ ከሄደ በኃላ የሙሣ ሕዝቦች ከጌጦቻቸው ወይፈንን አካልን ለእርሱ ማግሳት ያለውን አምላክ አድርገው ያዙ፦
7፥148 የሙሣም ሕዝቦች ከእርሱ መኼድ በኋላ ከጌጦቻቸው ወይፈንን አካልን ለእርሱ "ማግሳት" ያለውን አምላክ አድርገው ያዙ፡፡ وَاتَّخَذَ قَوْمُ مُوسَىٰ مِن بَعْدِهِ مِنْ حُلِيِّهِمْ عِجْلًا جَسَدًا لَّهُ خُوَارٌ

"ዒጅል" عِجْل ማለት "ጥጃ" ማለት ሲሆን ይህም ጥጃ "ወይፈን" ነው፥ "ወይፈን" ማለት "ወጣት ጥጃ" ማለት ነው፥ "ጀሠዳ" جَسَدًا ማለት "አካል" ማለት ሲሆን እዚህ ዐውድ ላይ "ምስል" ወይም "ቅርጽ" የሚል ፍቺን ለማመልከት የገባ ነው። የሙሣም ሕዝቦች በምድረበዳ አምላክ አርገው የያዙት ይህ የጥጃ ቅርጽ ማናገር እና መምራት የማይችል ጣዖት ነበረ፦
7፥148 እርሱ የማያናግራቸው እና መንገድንም የማይመራቸው መኾኑን አይመለከቱምን? አምላክ አድርገው ያዙት፡፡ በዳዮችም ኾኑ፡፡ أَلَمْ يَرَوْا أَنَّهُ لَا يُكَلِّمُهُمْ وَلَا يَهْدِيهِمْ سَبِيلًا ۘ اتَّخَذُوهُ وَكَانُوا ظَالِمِينَ

ሣሚሪይ የሙሣም ሕዝቦች ካመጡለት ጌጣጌጥ ቅርጽ በመቅረጽ እና የጂብሪል ፈረስ ከረገጠው ዱካ ማለትም ኮቴ ላይ አፈር ዘግኖ በቅርጹ ላይ በማድረግ ማግሳት ያለው ጣዖት ሠርቷል፦
20፥96 «ያላዩትን ነገር አየሁ፥ ከመልእክተኛው ዱካም ጭብጥ አፈርን ዘገንኩ፡፡ በቅርጹ ላይ ጣልኳትም፡፡ እንደዚሁም ነፍሴ ሸለመችልኝ» አለ፡፡ قَالَ بَصُرْتُ بِمَا لَمْ يَبْصُرُوا بِهِ فَقَبَضْتُ قَبْضَةً مِّنْ أَثَرِ الرَّسُولِ فَنَبَذْتُهَا وَكَذَٰلِكَ سَوَّلَتْ لِي نَفْسِي

እዚህ አንቀጽ ላይ "መልእክተኛ" የተባለው ጂብሪል ሲሆን ሣሚሪይ የጂብሪል ፈረስ ዱካ የረገጠበትን አፈር ጥጃው ውስጥ ሲበትነው ጥጃው መጓጎር ያለው ሆነ፥ የሙሣ ሕዝቦችም፦ "ይህ አምላካችሁ የሙሣም አምላክ ነው ግን ረሳው" አሉ፦
20፥88 ለእነርሱም አካል የኾነ ጥጃን ለእርሱ መጓጎር ያለውን አወጣላቸው፡፡ ተከታዮቹ «ይህ አምላካችሁ የሙሣም አምላክ ነው ግን ረሳው» አሉም፡፡ فَأَخْرَجَ لَهُمْ عِجْلًا جَسَدًا لَّهُ خُوَارٌ فَقَالُوا هَـٰذَا إِلَـٰهُكُمْ وَإِلَـٰهُ مُوسَىٰ فَنَسِيَ

"ኹዋር" خُوَار የሚለው ቃል "ኻረ" خَارَ‎ ማለትም "አገሳ" "ጓገረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ማግሳት" "መጓጎር" ማለት ነው፥ ያ የጥጃ ቅርጽ ልክ እንደ ጥጃ ድምፅ ነበረው። ሚሽነሪዎች፦ "ድምፅ ካለው ሕይወት አለው፥ ሕይወት ካለው ደግሞ ሣሚሪይ ለቅርጹ ሕይወት እንዴት ሰጠው? ሕይወት መስጠት የፈጣሪ ችሎት ብቻ ነው" ብለው ይጠይቃሉ።
፨ሲጀመር አንድ ግዑዝ ነገር ድምፅ ስላለው ሕይወት አለው ብሎ መደምደም ቂልነት ነው፥ ምክንያቱም ዕሩቅ ሳንሄድ ሠው ሠራሽ"artificial" የሆኑት ሮቦት ልክ እንደ ሰው ድምፅ ከማውጣት አልፈው የማሰብ ክህሎት"intelligence" ኖሯቸው ሒሣብ ያሥባሉ፣ ስም እና ቁጥር ይመዘግባሉ፣ መረጃ እና ማስረጃ ያቀብላሉ። ቅሉ ግን ሕይወት የላቸው፥ በተመሳሳይ የሳምራዊው ጥጃ ልክ እንደ ጥጃ ድምፅ ስለነበረው ሕይወት አለው ማለት አይደለም።

፨ሲቀጥል "ሕይወት የነበረው ጥጃ ማስመሰል ነበረ" ቢባል እንኳን ፈጣሪ ሕይወት ከሚሰጥበት ችሎት ጋር የሚመዛዘን፣ የሚነጻር እና የሚለካ አይደለም፥ ምክንያቱም የሙሣ በትር እባብ ሲሆን በተመሳሳይ የፊርዐውን ደጋሚዎች ገመዶቻቸው እና ዘንጎቻቸው የማስለሰል እባቦች አድርገዋል። የሙሣም እባብ የደጋሚዎችን የማስመሰል እባቦች ውጣቸዋለች፦
20፥66 «አይደለም ጣሉ» አላቸው፡፡ ወዲያውም ገመዶቻቸው እና ዘንጎቻቸው ከድግምታቸው የተነሳ እነርሱ የሚሮጡ እባቦች ኾነው ወደ እርሱ ተመለሱ፡፡ قَالَ بَلْ أَلْقُوا ۖ فَإِذَا حِبَالُهُمْ وَعِصِيُّهُمْ يُخَيَّلُ إِلَيْهِ مِن سِحْرِهِمْ أَنَّهَا تَسْعَىٰ
20፥69 «በቀኝ እጅህ ያለቸውንም በትር ጣል! ያንን የሠሩትን ትውጣለችና፥ ያ የሠሩት ሁሉ የድግምተኛ ተንኮል ነውና፡፡ ድግምተኛም በመጣበት ስፍራ ሁሉ አይቀናውም» አልን፡፡ وَأَلْقِ مَا فِي يَمِينِكَ تَلْقَفْ مَا صَنَعُوا ۖ إِنَّمَا صَنَعُوا كَيْدُ سَاحِرٍ ۖ وَلَا يُفْلِحُ السَّاحِرُ حَيْثُ أَتَىٰ

እኛም በተራችን ጥያቄ እንጠይቃለን። ሕይወት መስጠት የፈጣሪ ብቻ ችሎት ከሆነ ደጋሚዎቹ እንዴት የማስመሰል እባቦች ሠሩ? ይህ ጉዳይ እኮ በባብይልም አለ፦
ዘጸአት 7፥10-12 ሙሴ እና አሮንም ወደ ፈርዖን ገቡ፥ ያህዌህም እንዳዘዛቸው እንዲሁ አደረጉ፤ አሮንም በትሩን በፈርዖን እና በባሮቹ ፊት ጣለ፥ እባብም ሆነች። ፈርዖንም ጠቢባንንና መተተኞችን ጠራ፤ የግብፅም ጠንቋዮች በአስማታቸው እንዲሁ ደግሞ አደረጉ። እያንዳንዳቸውም በትራቸውን ጣሉ፥ እባቦችም ሆኑ፤ የአሮን በትር ግን በትራቸውን ዋጠች።

በሰፈሩት ቁና መሰፈር ይሉካል እንደዚህ ነው፥ ሕይወት መስጠት የፈጣሪ ብቻ ችሎት ከሆነ የግብፅም ጠንቋዮች እንዴት በትራቸውን እባቦች አደረጉ? በመተትስ ቢሆን ሕይወት ያለው እንስሳ ማስመሰል ይቻላልን? ይህንን መልስ ስትሰጡ የሣሚሪይ ጥጃ ድምፅ ያለው ቅርጽ መሆኑ አይደንቃችሁም። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የመሢሑ አወጣጥ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥36 «እኔም እርስዋን እና ዝርያዋን ከተረገመው ሰይጣን በአንተ እጠብቃቸዋለሁ» وَإِنِّي أُعِيذُهَا بِكَ وَذُرِّيَّتَهَا مِنَ الشَّيْطَانِ الرَّجِيمِ

አምላካችን አሏህ በአደም፣ በኑሕ፣ በኢብራሂም፣ በዒምራን ቤተሰብ ውስጥ መሢሑ እንዲመጣ አድርጓል፥ መርየም የዒምራን ልጅ ስትሆን መሢሑ ደግሞ ዘሯ ነው፦
3፥33 አላህ አደምን፣ ኑሕንም፣ የኢብራሂምንም ቤተሰብ፣ የዒምራንንም ቤተሰብ በዓለማት ላይ መረጠ፡፡ إِنَّ اللَّهَ اصْطَفَىٰ آدَمَ وَنُوحًا وَآلَ إِبْرَاهِيمَ وَآلَ عِمْرَانَ عَلَى الْعَالَمِينَ
3፥36 «እኔም እርስዋን እና ዝርያዋን ከተረገመው ሰይጣን በአንተ እጠብቃቸዋለሁ» وَإِنِّي أُعِيذُهَا بِكَ وَذُرِّيَّتَهَا مِنَ الشَّيْطَانِ الرَّجِيمِ

"ዙሪያህ" ذُرِّيَّة ማለት "ዘር"offspring" ማለት ሲሆን "ዙሪያህ" ذُرِّيَّة በሚለው መድረሻ ቅጥያ ላይ "ሃ" هَا የሚለው አንስታይ አገናዛቢ ተውላጠ ስም መርየምን አመላካች ስለሆነ ዒሣ የመርየም ዘር መሆኑን ቁልጭ እና ፍንትው አርጎ ያሳያል። በተመሳሳይ ባይብል ላይ መሢሑ ከአብርሃም፣ ከይስሐቅ፣ ከያዕቆብ፣ ከይሁዳ፣ ከእሴይ ወዘተ ... እንደሚወጣ ተተንብይዋል፦
ሚክያስ 5፥2 አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፤ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል። וְאַתָּ֞ה בֵּֽית־לֶ֣חֶם אֶפְרָ֗תָה צָעִיר֙ לִֽהְיֹות֙ בְּאַלְפֵ֣י יְהוּדָ֔ה מִמְּךָ֙ לִ֣י יֵצֵ֔א לִֽהְיֹ֥ות מֹושֵׁ֖ל בְּיִשְׂרָאֵ֑ל וּמֹוצָאֹתָ֥יו מִקֶּ֖דֶם מִימֵ֥י עֹולָֽם

እዚህ አንቀጽ ላይ "ቀድሞ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ቄዴም" קֶדֶם ሲሆን ይህ "ቀድሞ" የተባለው ጊዜ አብርሃም፣ ይስሐቅ፣ ያዕቆብ የነበሩበትን ጊዜ ነው፦
ሚክያስ 7፥20 ከ-"ቀድሞ" ዘመን ጀምረህ ለአባቶቻችን የማልህላቸውን እውነት ለያዕቆብ፥ ምሕረትንም ለአብርሃም ታደርጋለህ። תִּתֵּ֤ן אֱמֶת֙ לְיַֽעֲקֹ֔ב חֶ֖סֶד לְאַבְרָהָ֑ם אֲשֶׁר־נִשְׁבַּ֥עְתָּ לַאֲבֹתֵ֖ינוּ מִ֥ימֵי קֶֽדֶם

"ለአባቶቻችን የማልህላቸውን" የሚለው ይሰመርበት! ይህም መሃላ ከእነርሱ ዘር በሚወጣው መሢሕ እንደሚባረኩ ነው፥ ዘፍጥረት 22፥18 ዘፍጥረት 26፥4 ዘፍጥረት 28፥14 ተመልከት! "ቄዴም" קֶדֶם ሌላ ትርጉሙ "ምሥራቅ" ማለት ነው፦
ዘፍጥረት 10፥30 ስፍራቸውም ከማሴ አንሥቶ ወደ ስፋር ሲል እስከ "ምሥራቅ" ተራራ ድረስ ነው። וַֽיְהִ֥י מֹושָׁבָ֖ם מִמֵּשָׁ֑א בֹּאֲכָ֥ה סְפָ֖רָה הַ֥ר הַקֶּֽדֶם

እዚህ አንቀጽ ላይ "ምሥራቅ" ለሚለው የገባው ቃል "ቄዴም" קֶדֶם እንደሆነ ልብ አድርግ! ከ 306 እስከ 373 ድኅረ ልደት ይኖር የነበረ ሶሪያዊ ኤፍሬም ድንግል ማርያምን "ምሥራቅ" ኢየሱስን "ኮከብ" በማለት "አወጣጡ ከምሥራቅ ነው" የሚለውን ፈሥሯታል፦
ውዳሴ ማርያም ዘዐርብ ቁጥር 6 "አንቲ ውእቱ ምሥራቅ ዘወጽአ እምኔኪ ኮከብ"

ትርጉም፦ "ኮከብ ከአንቺ የወጣብሽ ምሥራቅ አንቺ ነሽ"

"ከዘላለም የሆነ" የሚለውን ደግሞ በቀጣይ የመጣ ነው፥ “ዘላለም” የሚለው የዕብራይስጡ ቃል “ዖላም” עוֹלָ֗ם ሲሆን አላፊ ወይም መጻኢ ውስን ጊዜን ለማመልከት ይውላል፥ ለምሳሌ አላፊ ውስን ጊዜን ለማመልከት ይህንን ጥቅስ እንመልከት፦
ዘዳግም 33፥15 በቀደሙትም ተራሮች ከፍተኛነት፥ በዘላለሙም ኮረብቶች ገናንነት። וּמֵרֹ֖אשׁ הַרְרֵי־קֶ֑דֶם וּמִמֶּ֖גֶד גִּבְעֹ֥ות עֹולָֽם׃

እዚህ አንቀጽ ላይ ለተራራ ቀዳማይነት የገባው ቃል "ቄዴም" קֶדֶם ሲሆን ለኮረብታ የገባው ቃል ደግሞ “ዖላም” עוֹלָ֗ם ነው፥ ለጌታው ባሪያ ለዘላለምም ባሪያው ይሁን ሲባል የተጠቀመበት ቃል “ዖላም” עוֹלָ֗ם ሲሆን መጻኢ ውስን ጊዜን ለማመልከት መጥቷል፦
ዘጸአት 21፥6 ወደ ደጁም ወደ መቃኑ አቅርቦ ጆሮውን በወስፌ ይብሳው፤ “ለዘላለምም” ባሪያው ይሁን። וְהִגִּישֹׁ֤ו אֲדֹנָיו֙ אֶל־הָ֣אֱלֹהִ֔ים וְהִגִּישֹׁו֙ אֶל־הַדֶּ֔לֶת אֹ֖ו אֶל־הַמְּזוּזָ֑ה וְרָצַ֨ע אֲדֹנָ֤יו אֶת־אָזְנֹו֙ בַּמַּרְצֵ֔עַ וַעֲבָדֹ֖ו לְעֹלָֽם׃ ס

መሢሑ ከ-"ቀድሞ" ዘመን ጀምሮ አወጣጡ ከአብርሃም፣ ከይስሐቅ፣ ከያዕቆብ፣ ከይሁዳ፣ ከእሴይ ወዘተ ... ነው፦
ዘኍልቍ 24፥17 ከያዕቆብ ኮከብ “ይወጣል”።
ዘኍልቍ 24፥19 ከያዕቆብም “የሚወጣ” ገዥ ይሆናል።
ዕብራውያን 7፥14 ጌታችን ከይሁዳ ነገድ “እንደወጣ” የተገለጠ ነውና።
ኢሳይያስ 11፥1 ከእሴይ ግንድ በትር “ይወጣል”።

ስለዚህ ሚክያስ 5፥2 ኢየሱስ ዓለም ሳይፈጠር እና ዘመን ሳይቆጠ አብን አህሎ እና መስሎ እንዲሁ ከባሕርይው ባሕርይው እና ከአካሉ አካሉ ወስዶ ወጣ፣ ተገኘ፣ ተወለደ ለሚለው "ልደት ዘይኃልቅ" ማለትም የዘላለማዊ ውልደት”eternal generation” ደርዛዊ ሥነ-መለኮት ማስረጃ መሆን አይችልም። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
https://www.youtube.com/c/Tiriyachen

በዓይነታቸው ለየት ያሉ፣ አጫጭር የኢስላማዊ ጥሪ መልእክቶች የተዳሰሱባቸው፣ አዳዲስ የኡስታዝ አቡሐይደር ፕሮግራሞች ይዘን ብቅ ብለናል።

በቅርብ ቀን በጥሪያችን የዩትዩብ ቻናል ይጠብቁን።

ይህንን መልእክት ለሌሎች በማጋራት ይህ ጠቃሚ ፕሮግራም ለሁሉም እንዲዳረስ እናድርግ።

ፕሮግራሙ በዋናነት ታሳቢ ያደረገው በተለይ #ከእስልምና_ውጪ_ላሉ_ወገኖቻችን ስለሆነ ይህ መልእክት እንዲደርሳቸው ሼር በማድረግ ይተባበሩን።
------
Tiriyachen | ጥሪያችን

#የኢስላም_መልእክት
#የኢስላም_ጥሪ
#ኡስታዝ_አቡሐይደር
#ጥሪያችን
#TiriyachenVideos

Follow us on:
-----
https://fb.me/tiriyachen
https://tttttt.me/tiriyachen
https://www.youtube.com/c/Tiriyachen
https://tiriyachen.org
እኚህ ሰው ማን ናቸው?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

15፥95 *"ተሳላቂዎችን ሁሉ እኛ በቅተንልሃል"*፡፡ إِنَّا كَفَيْنَاكَ الْمُسْتَهْزِئِينَ

ከሊቅ እስከ ደቂቅ፣ ከሕፃን እስከ አዋቂ፣ ወጣትም ሆነ አዛውንት ስለ እሳቸው ሲወራ "ጆሮ ዳባ ልበስ" የሚል የለም። ሁሉ ስለ እሳቸው ሲወራ አዳሜ ሆነ ሔዋኔ ጆሮውን አስግጎ ይሰማል፥ ከሁሉም ከሁሉም የሚገርመው ደግሞ የሚጠሏቸው ሳይቀር እንኳን ቢሆን ስለ እሳቸው ለመስማት እና ስለ እሳቸው ለማወቅ ይፈልጋሉ። ዝም ብለህ ሰው የተሰበሰበበት መሀል ገብተህ እና ድምጽክን ከፍ አድርገህ፦ "እከሌ" ብለህ ወይም "እከሊት" ብለህ ብትጣራ ፊቱን እና ትኩረቱን ወደ አንተ የሚያዞረው የጠራከውን ስም ባለቤት ብቻ ነው፥ ከሌለም ደግሞ ማንም ፊት እና ትኩረት የሚሰጥክ አይኖርም። ነገር ግን ሰው የተሰበሰበበት ስፍራ ሄደህ የእሳቸውን ስም ጠርተህ ንግግር ብትጀምር ሁሉም ፊቱን እና ትኩረቱን ወደ አንተ ያደርጋል፥ ትኩረት የማይሰጥህ የለም ቢባል ማጋነን እና ማበል አይሆንም። ስለ እሳቸው ለማወቅ የማይሰለፍ አይኖርም፥ እኚህ ሰው፦

1ኛ. የእልፍ አእላፋት መጻሕፍት ርእስ በመሆን ብዙ ጸሐፊያን የከተቡላቸው ናቸው፣
2ኛ. በሁሉም ልብ ውስጥ በአሉታዊ ሆነ በአንታዊ በሁለት ወገን እንደተሳለ ሰይፍ ሰርስረው የገቡ ናቸው፣
3ኛ. አስተምህሮታቸው የተሟላ መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ የሕይወት ዘይቤ በመሆኑ የዓለማችን ተግዳሮት ነው የተባለላቸው ናቸው፣
4ኛ. "የዓለማችን ቁጥር አንድ አውንታዊ እና አሉታዊ ተጽዕኖ አሳዳሪ" ተብለዋል፥ ለሕሩያን አውንታ ተጽዕኖ እንዲሁ ለእኵያን አሉታዊ ተጽዕኖ አሳዳሪ ናቸው፣
5ኛ. ስለ እርሳቸው ማንነት የገባው ሰው፦ "ሕይወትህን መስዋዕት አርግ" ቢባል ያለ አንዳች ማቅማማት ሕይወቱን እስከ ሞት የሚያደርግላቸው ናቸው።
6ኛ. በታሪክ ውስጥ እሳቸውን ለማነወር፣ ለማበሻቀጥ፣ ለማብጠልጠል ብዙ ጦማሪያን ጦምረዋል፣ ብዙ ኃያሲያን ኃይሰዋል፤ ብዙ ተቺዎች ተችተዋል፣ ብዙ ተሳላቂዎች ተሳልቀዋል። ቅሉ ግን የጦማሪያን ጦማር፣ የኃያሲያን ኂስ፣ የተቺዎች ትችት፣ የተሳላቂዎች ስላቅ ከሟቾች ጋር ሲያልፍ የእሳቸው ስም እና የሰዎችን ሕይወት የቀየሩበት መጽሐፍ እስካሁን አለ የተባለላቸው ናቸው።

እኚህ ሰው ማን ናቸው? አዎ! የዓለማቱ ጌታ የአሏህ መልእክተኛ እና የነቢያት መደምደሚያ ነቢዩ ሙሐመድ"ﷺ" ናቸው። በእርሳቸው ላይ የወረደው ሐቅ ለሰዎች የሚጠቅም ስለሆነ በምድር 1400 ዓመት ቆይቷል፥ ባጢል ቢሆን ኖሮ በእንጭጩ ኮረፋት ሆኖ ተግበስብሶ ይጠፋ ነበር፦
13፥17 *"እንደዚሁ አላህ ለእውነት እና ለውሸት ምሳሌን ያደርጋል። ኮረፋቱማ ግብስብስ ኾኖ ይጠፋል፥ ለሰዎች የሚጠቅመውማ በምድር ላይ ይቆያል፡፡ እንደዚሁ አላህ ምሳሌዎችን ይገልፃል"*፡፡ كَذَٰلِكَ يَضْرِبُ اللَّهُ الْحَقَّ وَالْبَاطِلَ ۚ فَأَمَّا الزَّبَدُ فَيَذْهَبُ جُفَاءً ۖ وَأَمَّا مَا يَنفَعُ النَّاسَ فَيَمْكُثُ فِي الْأَرْضِ ۚ كَذَٰلِكَ يَضْرِبُ اللَّهُ الْأَمْثَالَ
ሐዋ. ሥራ 5፥38-39 አሁንም እላችኋለሁ፦ ከእነዚህ ሰዎች ተለዩ ተዉአቸውም! *ይህ አሳብ ወይም ይህ ሥራ ከሰው እንደ ሆነ ይጠፋልና፥ ከእግዚአብሔር እንደ ሆነ ግን ታጠፉአቸው ዘንድ አይቻላችሁም። በእርግጥ ከእግዚአብሔር ጋር ስትጣሉ ምናልባት እንዳትገኙ"*።

ገማሊያ እንደተናገረው ይህ የነቢያችን"ﷺ" እሳቦት ከሰው ከሆነ ይጠፋ ነበር፥ ግን የነቢያችን"ﷺ" ግልጠተ-መለኮት ከፈጣሪ ስለሆነ ገና በእንጭጭነቱ የመካህ ቁሬይሾች፣ የመዲና በኑ ቁሬይዛህ፣ የሮሙ ባዛንታይን በዕውቀት መሞገት ሲያቅታቸው በጉልበት ሊጠፉት ሞክረው አልተሳካላቸው። ከርሞም ሆነ ዘንድሮም እሳቸው ላይ ለሚሳለቁን ተሳላቂዎች አሏህ በቅቶላቸዋል፥ በእርሳቸው ላይ የወረደውን የአሏህን ብርሃን በአፎቻቸው ለማጥፋት ቢፈልጉ እና ቢጠሉም አሏህ ብርሃኑን ገላጭ ነው፦
15፥95 *"ተሳላቂዎችን ሁሉ እኛ በቅተንልሃል"*፡፡ إِنَّا كَفَيْنَاكَ الْمُسْتَهْزِئِينَ
61፥8 *"የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ሊያጠፉ ይሻሉ፥ ከሓዲዎቹ ቢጠሉም እንኳ አላህ ብርሃኑን ገላጭ ነው"*፡፡ يُرِيدُونَ لِيُطْفِئُوا نُورَ اللَّهِ بِأَفْوَاهِهِمْ وَاللَّهُ مُتِمُّ نُورِهِ وَلَوْ كَرِهَ الْكَافِرُونَ

ይህንን ብርሃን ለማጥፋት እፍ ባሉ ቁጥር እያነደዱት መሆኑን ይዘነጋሉ፥ ኢሥላም በፍጥነት መጠነ-ሰፊ የእድገት መርሓ-ግብር እየታየበት ያለው በምዕራባውያን መሆኑ እፍ ባሉ ቁጥር የሚያነዱበት ውጤት ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

“ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያ ረሡሉሏህ” فِدَاكَ أَبِي وَأُمِّي يَا رَسُول اللَّه

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሥርጸት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

3፥49 ወደ እስራኤልም ልጆች መልእክተኛ ያደርገዋል፡፡ ይላልም፡- "እኔ ከጌታችሁ በተአምር ወደ እናንተ መጣሁላችሁ"፡፡ وَرَسُولًا إِلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ أَنِّي قَدْ جِئْتُكُم بِآيَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ

"ሥርጸት" የሚለው የግዕዙ ቃል "ሠረጸ" ማለትም "ወጣ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መውጣት"procession" ማለት ነው፥ "ወጣ" የሚለው ቃል በግዕዝ "ወጽአ" "ሠረቀ" "ሠረጸ" ነው። በቁርኣን ውስጥ አሏህ አፍ እንዳለው ያልተገለጸ ሲሆን በባይብል ውስጥ ግን አምላክ አፍ ኖሮት ከአፉ ጥበብ፣ ማስተዋል፣ ዕውቀት፣ ቃል፣ እስትንፋስ ይወጣሉ፦
ሲራክ 24፥3 እኔ(ጥበብ) ከልዑል "አፍ ወጣሁ" ምድርንም እንደ ጉም ሽፈንኋት።
ምሳሌ 2፥6 "ከ-"አፉም" ዕውቀት እና ማስተዋል "ይወጣሉ"።
ኢሳይያስ 55፥11 "ከ-"አፌ" የሚወጣ "ቃሌ" እንዲሁ ይሆናል።
ኢዮብ 15፥30 "በ-"አፉ እስትንፋስ" አበባዎቹም ይረግፋሉ። וְ֝יָס֗וּר בְּר֣וּחַ פִּֽיו׃

ከአፉ የሚወጡት ጥበብ፣ ማስተዋል፣ ዕውቀት፣ ቃል፣ እስትንፋስ ሸንሽነን ማንነት ካበጀንላቸው ሥላሴ ሦስት መሆኑ ቀርቶ ስድስት ይሆናሉ፥ ቅሉ ግን በባይብል ጥበብ፣ ማስተዋል፣ ዕውቀት፣ ቃል፣ እስትንፋስ ባሕዮት እንጂ አካላት አይደሉም። ኢየሱስ፦ "ከአብ ወጥቼ" ሲል "ከአፉ ወጥቼ" ማለቱ ሳይሆን "ከአብ መጥቼ" "ከአብ ተልኬ" ማለቱ ነው፦
ዮሐንስ 16፥28 ከአብ ወጥቼ ወደ ዓለም መጥቻለሁ።

ምክንያቱም ሰይጣን እራሱ "ወጥቼ" የሚለውን ቃል ሲጠቀም ጌታም የእርሱን ንግግር ተቀብሎ "ውጣ" አለው፦
1ኛ ነገሥት 22፥22 ጌታም፦ በምን? አለው እርሱም፦ "ወጥቼ" በነቢያቶቹ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ እሆናለሁ አለ። ጌታም፦ ማሳሳትስ ታሳስተዋለህ፥ ይሆንልሃልም "ውጣ"፥ እንዲሁም አድርግ አለ።” καὶ εἶπε πρὸς αὐτὸν Κύριος· ἐν τίνι; καὶ εἶπεν· ἐξελεύσομαι καὶ ἔσομαι πνεῦμα ψευδὲς εἰς τὸ στόμα πάντων τῶν προφητῶν αὐτοῦ. καὶ εἶπεν· ἀπατήσεις καί γε δυνήσῃ, ἔξελθε καὶ ποίησον οὕτως.

ሰይጣን ከአብ ወጥቶ ሲያሳስት ከአብ መላኩን እና መምጣቱን እንጂ ከአብ አፍ ወይም ከአብ አካል ተወልዶ መምጣቱን አያሳይም። በተጨማሪም ሐሰተኛ ነቢያት ወጥተው ወደ ዓለም ገብተዋል፦
1ኛ ዮሐንስ 4፥1 ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም "ወጥተዋልና"።
2ኛ ዮሐንስ 1፥7 ብዙ አሳቾች ወደ ዓለም "ገብተዋል"።

ወደ ዓለም የገቡት ከየት ነው? የወጡትስ? የወጡት ከሰዎች መካከል እንጂ ከሰዎች አፍ ወይም አብራክ ተከፍለው አይደለም፦
1ኛ ዮሐንስ 2፥19 "ከ-"እኛ ዘንድ "ወጡ"።

"ወጡ" ማለት "መጡ" ማለት ከሆነ ኢየሱስ "ወጥቼ" ሲል "ተልኬ" "መጥቼ" ማለቱ ነው። "መውጣት" ተብሎ የተቀመጠው የግሪኩ ቃል "አክ ኤርኮማይ" ἐξέρχομαι ሲሆን "ኤክ" ἐκ እና "ኤርኮማይ" ἔρχομαι ከሚሉ ሁለት ቃላት የተዋቀረ ነው፥ "ኤክ" ἐκ የሚለው መስተዋድድ "ከ" ማለት ሲሆን "ኤርኮማይ" ἔρχομαι ማለት "መምጣት" ማለት ነው፦
ዮሐንስ 5፥43 እኔ በአባቴ ስም መጥቻለሁ አልተቀበላችሁኝምም፥ ሌላው በራሱ ስም ቢመጣ እርሱን ትቀበሉታላችሁ። ἐγὼ ἐλήλυθα ἐν τῷ ὀνόματι τοῦ Πατρός μου, καὶ οὐ λαμβάνετέ με· ἐὰν ἄλλος ἔλθῃ ἐν τῷ ὀνόματι τῷ ἰδίῳ, ἐκεῖνον λήμψεσθε.

እዚህ አንቀጽ ላይ "መምጣት" ለሚል የግሥ መደብ የገባው ቃል "ኤርኮማይ" ἔρχομαι እንደሆነ 2064 ጠንካራ ቁጥር ተመልከት! "በራሱ ስም መምጣት" ማለት "ሳይላክ ተልኬአለው" ማለትን ከገለጸ "በአብ ስም መምጣት" ማለት "አብ ልኮት መምጣት" ማለት ነው፦
ዮሐንስ 8፥42 እርሱ ላከኝ እንጂ "ከራሴ አልመጣሁምና"።
ዮሐንስ 7፥28 እኔም "በራሴ አልመጣሁም"፥ ነገር ግን እናንተ የማታውቁት "የላከኝ" እውነተኛ ነው።

ስለዚህ "ወጥቼ" የሚለው ቃል "እምቅድመ ዓለም ያለ እናት አብን አህሎ እና መስሎ እንዲሁ ከአካል አካልን ወስዶ ከባሕርይ ባሕርይ ወስዶ ተወለደ" ለሚል ትምህርት መሠረት በፍጹም አይሆንም፥ "መወለድ" ማለት "መውጣት" ማለት ከሆነ መንፈስ ቅዱስ "ከአብ የሚወጣ" ስተለባለ ለምንስ "ተወለደ" "ልጅ" ነው አይባልም?

በ 381 ድኅረ ልደት የተሰበሰበው የቁስጥንጥንያ ጉባኤ መንፈስ ቅዱስ "ከአብ የሠረጸ" የሚል ትውፊት ከጽባሓውያን ኦርቶዶክስ እና ከመለካውያን ኦርቶዶክስ የመጣ ሲሆን "ከአብ እና ከወልድ የሠረጸ" የሚል ትውፊት ከካቶሊክ እና ከፕሮቴስታንት ትውፊት መጥቷል፥ የቁስጥንጥንያ ጉባኤ የቱን በትክክል እንዳሉ አሻሚ ስለነበር በሁለት ባሕርይ የሚያምኑት ካቶሊክ እና መለካውያን ኦርቶዶክስ በ 1053 ድኅረ ልደት በጉባኤ ተሰብስበው ባለመግባባት ተወጋግዘው ተለያይተዋል። ይህም ክፍፍል ቤተክርስቲያንን የምሥራቅ እና የምዕራብ ቤተክርስቲያን አርጎ ስለከፈለ ታላቁ ክፍፍል"great Schism" ይባላል፥ በ 1517 ከካቶሊክ የተገነለጠለው የፕሮቴስታንት አንጃም በሥርጸት ጉዳይ የካቶሊክን ትውፊት የያዘ ነው።

ወደ ቁርኣን ስንመጣ ዒሣ ኢብኑ መርየም ከአሏህ በተአምር የመጣ መልእክተኛ ነው፦
3፥49 ወደ እስራኤልም ልጆች መልእክተኛ ያደርገዋል፡፡ ይላልም፡- "እኔ ከጌታችሁ በተአምር ወደ እናንተ መጣሁላችሁ"፡፡ وَرَسُولًا إِلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ أَنِّي قَدْ جِئْتُكُم بِآيَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ

ይህም ተአምር ዕውር ማብራት፣ ለምጻም ማንጻት፣ ሙት ማስነሳት ወዘተ ነው። በተመሳሳይ ነቢዩሏህ ሙሣ ከአሏህ በተአምር የመጣ መልእክተኛ ነው፦
7፥105 «በአላህ ላይ ከእውነት በቀር አለመናገር ተገቢዬ ነው፡፡ "ከጌታችሁ በተአምር በእርግጥ መጣሁላችሁ"፡፡ حَقِيقٌ عَلَىٰ أَن لَّا أَقُولَ عَلَى اللَّهِ إِلَّا الْحَقَّ ۚ قَدْ جِئْتُكُم بِبَيِّنَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ

ዒሣ እና ሙሣ፦ "ከጌታችሁ በተአምር በእርግጥ መጣሁላችሁ" ብለው ያሉት ጣምራ ንግግር "ኢየሱስ ከአምላክ ዘንድ መጥቷል" ስንል "ሙሴ ከአምላክ ዘንድ መጥቷል" በተባለበት ሒሣብ እንደሆነ ያስረዳል፥ ኒቆዲሞስም የተረዳው በዚህ ስሌት ነው፦
ዮሐንስ 3፥2 "መምህር ሆነህ ከአምላክ ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን" አለው። καὶ εἶπεν αὐτῷ Ῥαββεί, οἴδαμεν ὅτι ἀπὸ Θεοῦ ἐλήλυθας διδάσκαλος·

ኢየሱስን ከዳዊት ዘር ወደ ዓለም ያመጣው አምላክ ነው፥ የተወለደውም ወደ ዓለም ከመጣ በኃላ ሳይሆን ከተወለደ በኃላ ነው ወደ ዓለም የመጣው፥ ከተወለደ በኃላ የተላከ ነው፦
የሐዋርያት ሥራ 13፥23 "ከዚህም ሰው ዘር" አምላክ እንደ ተስፋው ቃል ለእስራኤል መድኃኒትን እርሱም ኢየሱስን "አመጣ"።
ዮሐንስ 18፥37 እኔ ለእውነት ልመሰክር ስለዚህ ተወልጃለሁ፥ ስለዚህም ወደ ዓለም መጥቻለሁ።
ገላትያ 4፥4 አምላክ "ከሴት የተወለደውን" ከሕግም በታች የተወለደውን "ልጁን ላከ"።

ስለዚህ ታሪክን ከነገረ-መለኮት ጋር ግጣም አርጎ ማጎላበት እና ማጎልበት ክብረት እንጂ ክስረት የለውም። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሚካኤል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

2፥98 ለአላህ እና ለመላእክቱ፣ ለመልእክተኞቹ፣ ለጂብሪል፣ ለሚካኤል ጠላት የኾነ ሰው አላህ ለከሓዲዎች ጠላት ነው፡፡ مَن كَانَ عَدُوًّا لِّلَّهِ وَمَلَائِكَتِهِ وَرُسُلِهِ وَجِبْرِيلَ وَمِيكَالَ فَإِنَّ اللَّهَ عَدُوٌّ لِّلْكَافِرِينَ

"ሚካኢል" مِيكَائِيل የሚለው የዐረቢኛው ቃል ከሦስት ቃላት የተዋቀረ ነው፥ "ሚ" مِي ወይም "መን" مَن ማለት "ማን" ማለት ሲሆን መጠይቅ ተውላጠ ስም ነው፣ "ካ" كَا ወይም "ከ" كَ ማለት "እንደ" ማለት ሲሆን መስተዋድድ ነው፣ "ኢል"  ئِيل ወይም "ኢላህ" إِلَـٰه  ማለት "አምላክ" ማለት ሲሆን ስም ነው። በጥቅሉ "ሚካኢል" مِيكَائِيل ማለት "ማን እንደ አምላክ" "መኑ ከመ አምላክ" ማለት ነው፦
2፥98 ለአላህ እና ለመላእክቱ፣ ለመልእክተኞቹ፣ ለጂብሪል፣ ለሚካኤል ጠላት የኾነ ሰው አላህ ለከሓዲዎች ጠላት ነው፡፡ مَن كَانَ عَدُوًّا لِّلَّهِ وَمَلَائِكَتِهِ وَرُسُلِهِ وَجِبْرِيلَ وَمِيكَالَ فَإِنَّ اللَّهَ عَدُوٌّ لِّلْكَافِرِينَ
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 59 , ሐዲስ 47
ሠሙራህ እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “በሌሊት ላይ ሁለት ሰዎች ወደ እኔ ሲመጡ አየሁኝ፥ ከእነርሱ አንዱ እንዲህ አለ፦ “ያ እሳት የሚያይዝ “ማሊክ” ሲሆን የእሳት ዘበኛ ነው፥ “እኔ ጂብሪል ነኝ”። ይህ ሚካኢል ነው”። عَنْ سَمُرَةَ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ رَأَيْتُ اللَّيْلَةَ رَجُلَيْنِ أَتَيَانِي قَالاَ الَّذِي يُوقِدُ النَّارَ مَالِكٌ خَازِنُ النَّارِ، وَأَنَا جِبْرِيلُ، وَهَذَا مِيكَائِيلُ ‏”‌‏.‏

በኢሥላም አስተምህሮት ሚካኢል ከመላእክት ሊቃውንት(አለቆች) አንዱ ሊቀ መላእክት እና እራሱ በምንነቱ መልአክ ነው። በባይብል "ሚካኤል" מִיכָאֵל የሚለው የዕብራይስጥ ቃል ከሦስት ቃላት የተዋቀረ ነው፥ "ሚ" מִי ማለት "ማን" ማለት ሲሆን መጠይቅ ተውላጠ ስም ነው፣ "ካ" כָ ማለት "እንደ" ማለት ሲሆን መስተዋድድ ነው፣ "ኤል" אֵל ማለት "አምላክ" ማለት ሲሆን ስም ነው። በጥቅሉ "ሚካኤል" מִיכָאֵל ማለት "ማን እንደ አምላክ" ማለት ነው፦
ዘዳግም 33፥26 እንደ አምላክ ማንም የለም። אֵ֥ין כָּאֵ֖ל

እዚህ አንቀጽ ላይ "እንደ አምላክ" ለሚለው ቃላት የገባው ቃላት "ካኤል" כָּאֵ֖ל እንደሆነ ልብ አድርግ! "ሚካኤል" מִיכָאֵל የሚለው ስም ለሰዎች የተጸውዖ ስም ሆኖ መጥቷል፦
ዘኍልቍ 13፥13 ከአሴር ነገድ የ-"ሚካኤል" ልጅ ሰቱር።
ዕዝራ 8፥8 የሰፋጥያስ ልጆች የ-"ሚካኤል" ልጅ ዝባድያ፥ ከእርሱም ጋር ሰማንያ ወንዶች።

ነገር ግን ይህ ስም ለመላእክት አለቃ ለመልአኩ የተጸውዖ ስም ነው፥ ሚካኤል ከመላእክት አለቆች አንዱ ነው፦
ይሁዳ 1፥9 የመላእክት አለቃ ሚካኤል..።
ዳንኤል 10፥13 ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ፤
ዳንኤል 12፥1 በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል።
ኢያሱ 5፥14 እኔ የያህዌህ ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቼአለሁ።

በኢያሱ ፊት የተመዘዘ ሰይፉን የያዘው የያዘው የመላእክት አለቃ ሚካኤል እንደሆነ ድርሳነ ሚካኤል ይናገራል፦
ድርሳነ ሚካኤል ዘወርኃ ኅዳር 3፥148
"የነዌ ልጅ ኢያሱ በንጉሡ የጦር ቢትወደድ አምሳል ክቡር ገናና ሀኖ ያየው ይህ ሚካኤል ነው"

ይህ ከመሆኑ ጋር ከ 1695 እስከ 1758 ይኖር የነበረው የአይሪሽ ፕሮቴስታንት መሪ ሮበርት ክላይቶን"Robert Clayton፣ የአድቬንቲስት ቤተክርስቲያን እና የይሆዋ ምስክሮች፦ "ኢየሱስ ብሉይ ኪዳን ላይ ሲላክ የነበረ መልአክ ወይም የመላእክት አለቃ ሚካኤል ነው" ብለው ያምናሉ፥ ምክንያታቸው ደግሞ የጥንት የቤተክርስቲያን አባቶች፦ "ኢየሱስ ብሉይ ኪዳን ላይ ሲላላክ የነበረ የመላእክት አለቃ እና መልአክ ነው" ብለው ስለተናገሩ ነው።

ሰማዕቱ ዮስጦስ፦
"ክርስቶስ ንጉሥ፣ ካህን፣ አምላክ፣ ጌታ፣ መልአክ፣ ሰው እና አለቃ ነው፥ ኢያሱ 5፥13-15"
Justin Martyr’s Dialogue w/ Trypho Ch. 34

የልዮኑ ኢራኒዮስ፦
፨"እርሱ(ክርስቶስ) ሁሉ በሁሉ ነው፥ ከአባቶች መካከል አባት ነው፣ በሕግጋት መካከል ሕግ ነው፣ በካህናት መካከል ሊቀ ካህናት ነው፣ በነገሥታት መካከል ገዥ ነው፣ በነቢያት መካከል ነቢይ ነው፣ በመላእክት መካከል መልአክ ነው፣ በሰዎች መካከል ሰው ነው"
Fragments of Irenaeus Ch. 53

፨"እርሱ በካህናት መካከል ካህን ነው፣ በነገሥታት መካከል ጠቅላይ ገዥ ነው፣ በነቢያት መካከል ነቢይ ነው፣ በመላእክት መካከል መልአክ ነው፣ በሰዎች መካከል ሰው ነው፣ በአብ ደግሞ ልጅ ነው"
Fragments of Irenaeus Ch. 54

የሰርዴሱ ሚልጦን፦
"እርሱ በሕግ ሕግ ነው፣ በካህናት መካከል ሊቀ ካህናት ነው፣ በነገሥታት መካከል ገዥ ነው፣ በነቢያት መካከል ነቢይ ነው፣ በመላእክት መካከል የመላእክት አለቃ ነው"
Melito of Sardis’ Fragments Ch. 4

የቂሳርያው አውሳቢዮስ፦
፨"እርሱ አምላክ እና የቅዱሳን ጌታ ተብሎ ቢጠራም ነገር ግን የልዑል አባቱ መልአክ ነው"
Eusebius’ The Proof of the Gospel Book 1 Ch. 5

፨"እርሱ(ክርስቶስ) የሰማይ ሰራዊት አለቃ ነው፥ የጌታ ሠራዊት አለቃ ኢያሱ 5፥13-15።"
Eusebius’ The Proof of the Gospel Book 4 Ch. 10
የሚያጅበት በኢሳይያስ 9፥6 ላይ ከማሶሬት በተቃራኒው ከ 330–360 ድኅረ ልደት በክርስቲያኖች እጅ በተዘጋጀው በኮዴክስ ሲናቲከስ ኮድ በፊደል S በቁጥር 01ውስጥ የግሪክ ሰፕቱአጀንት ቅጂ፦ "የታላቁ ጉባኤ መልአክ" ይለዋል፦
ኢሳይያስ 9፥6 ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል። ስሙም፦ "የታላቁ ጉባኤ መልአክ" ይባላል፥ በአለቆች ላይ ሰላምን እና በእርሱ ላይ ጤናን አመጣለው። ὅτι παιδίον ἐγεννήθη ἡμῖν, υἱὸς ἐδόθη ἡμῖν, οὗ ἡ ἀρχὴ ἐγενήθη ἐπὶ τοῦ ὤμου αὐτοῦ, καὶ καλεῖται τὸ ὄνομα αὐτοῦ Μεγάλης βουλῆς ἄγγελος· ἄξω γὰρ εἰρήνην ἐπὶ τοὺς ἄρχοντας καὶ ὑγείαν αὐτῷ.
For a child is born to us, and a son is given to us, whose government is upon his shoulder, and his name is called the angel of great counsel, for I will bring peace upon the princes, and health to him.

"ሜጋሌስ ቡሌስ አንጌሎስ" Μεγάλης βουλῆς ἄγγελος ማለት "የታላቁ ጉባኤ መልአክ"the angel of great counsel" ማለት ነው፥ በማሶሬት ላይ፦ "ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ" የሚለውን አሽቀንጥረው ጥለው "የታላቁ ጉባኤ መልአክ" ብለውታል። ይህም ጉባኤ የቅዱሳን መላእክት ጉባኤ ነው፦
መዝሙር 88(89)፥6 ጌታ ሆይ! ሰማያት ተኣምራትህን እውነትህንም ደግሞ በቅዱሳን ጉባኤ ያመሰግናሉ፥ ἐξομολογήσονται οἱ οὐρανοὶ τὰ θαυμάσιά σου, Κύριε, καὶ τὴν ἀλήθειάν σου ἐν ἐκκλησίᾳ ἁγίων.
መዝሙር 88(89)፥7 ጌታን በሰማይ የሚተካከለው ማን ነው? ከአምላክ ልጆች ጌታን ማን ይመስለዋል? ὅτι τίς ἐν νεφέλαις ἰσωθήσεται τῷ Κυρίῳ; καὶ τίς ὁμοιωθήσεται τῷ Κυρίῳ ἐν υἱοῖς Θεοῦ;
መዝሙር 88(89)፥8 በቅዱሳን ጉባኤ አምላክ ክቡር ነው፥ በዙሪያው ባሉት ሁሉ ላይ ታላቅና ግሩም ነው። ὁ Θεὸς ἐνδοξαζόμενος ἐν βουλῇ ἁγίων, μέγας καὶ φοβερὸς ἐπὶ πάντας τοὺς περικύκλῳ αὐτοῦ.

ኢየሱስን የዚህ ጉባኤ መልእክተኛ ማድረግ የመላእክት አለቃ ከሚለው ማዕረግ ዝቅ ማድረግ ነው። በእርግጥ "መልአከ ምክር(የጉባኤ መልአክ) ሚካኤል ነው፦
ድርሳነ ሚካኤል ዘወርኃ መጋቢት 7፥184
"ተአምሪሁ ለመልአክ ክቡር ሚካኤል ሊቀ መላእክት "መልአክ ምክሩ" ለአብ"
ቅዳሴ ዮሐንስ አፈ ወርቅ 15፥17
"ፈነወ ለነ ወልዶ መድኅነ ወመቤዝወ "መልአከ ምክሩ" የማኑ እደ መዝራዕቱ ኃይሉ ወጥበቡ ለአቡሁ"

ለአብ የጉባኤ መልአክ ማን ነው ሚካኤል ወይስ ኢየሱስ? በእርግጥ ዐበይት ክርስትና ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክ፣ አንግሊካን እና ፕሮቴስታንት በሥነ-መለኮት ትምህርታቸው "ኢየሱስ ሚካኤል ነው" ባይሉም "ኢየሱስ ብሉይ ኪዳን ላይ ሲላክ የነበረ መልአክ ነው" ብለው ያምናሉ፦
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 83 ቁጥር 12
"-"የእግዚአብሔር ልጅ፣ መልአክ፣ ክንድ፣ ነቢይ" ተባለ።"
ሰይፈ ሥላሴ ምዕራፍ 4 ቁጥር 48
"መልአክ የተባለውም የእግዚአብሔር ልጅ ነው"

እውን መልአክ ይመለካልን? "መልአክ" የሚለው የግዕዝ ቃል "ለአከ" ማለትም "ላከ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ተላላኪ" "መልእክተኛ" ማለት ነው፥ እንግዲህ ኢየሱስ መልእክተኛ ከሆነ እርሱ ጋር የሌለ ግን ሌላ ማንነት ጋር ያለው ዕውቀት ለማስተላለፍ የተላከ ተላላኪ ነው ማለት ነው። አንድ ሁሉን ዐዋቂ አምላክ ሙሉ ዕውቀት ካለው ለሌላ ምንነት እና ማንነት እንዴት መልእክተኛ ይሆናል? ከሌላ ምንነት እና ማንነት ምን እንደሚናገር መልእክት እየተቀበለ እንዴት ይናገራል? መልእክተኛ የሌላ መልእክት እንጁ የራሱን አይናገርም፥ ከራሱ ምንም መናገር ካልቻለ እራሱ ጋር በቂ ትምህርት፣ ዕውቀት እና መልእክት የለውም ማለት ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
መሢሑ ሰሎሞን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

38፥30 ለዳውድም ሡለይማንን ሰጠነው፡፡ ምን ያምር ባሪያ! እርሱ ተመላሽ ነው፡፡ وَوَهَبْنَا لِدَاوُودَ سُلَيْمَانَ ۚ نِعْمَ الْعَبْدُ ۖ إِنَّهُ أَوَّابٌ

አምላካችን አሏህ ለዳውድ ሡለይማንን ልጅ አርጎ ሰቶታል፥ እርሱም ወደ አሏህ በንስሓ ተመላሽ ነው፦
38፥30 ለዳውድም ሡለይማንን ሰጠነው፡፡ ምን ያምር ባሪያ! እርሱ ተመላሽ ነው፡፡ وَوَهَبْنَا لِدَاوُودَ سُلَيْمَانَ ۚ نِعْمَ الْعَبْدُ ۖ إِنَّهُ أَوَّابٌ

"ተውባህ" تَوْبَة የሚለው ቃል "ታበ" تَابَ ማለትም "ተመለሰ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ከነበሩበት ስህተት በንስሐ ወደ አሏህ መመለስ” ማለት ነው፥ አሏህ ወደ እርሱ የሚመለሱት ንስሐን የሚቀበል ስለሆነ “አት-ተዋብ” التَّوَّاب ሲሆን ወደ እርሱ "ተመላሽ" ባሪያ ደግሞ "አዋብ" أَوَّاب ይባላል።
ስለ ሡለይማን በቁርኣን ጥቂት ካልን ዘንዳ በባይብል ደግሞ ይህ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን መሢሕ ተብሏል፦
1ኛ ሳሙኤል 2፥35 የታመነም ካህን ለእኔ አስነሣለሁ፥ በልቤም በነፍሴም እንዳለ እንዲሁ ያደርጋል፤ እኔም የታመነ ቤት እሠራለታለሁ፥ ዘመኑን ሁሉ "በ"-መሢሔ" ሰው ፊት ይሄዳል። וַהֲקִימֹתִ֥י לִי֙ כֹּהֵ֣ן נֶאֱמָ֔ן כַּאֲשֶׁ֛ר בִּלְבָבִ֥י וּבְנַפְשִׁ֖י יַעֲשֶׂ֑ה וּבָנִ֤יתִי לֹו֙ בַּ֣יִת נֶאֱמָ֔ן וְהתְהַלֵּ֥ךְ לִפְנֵֽי־מְשִׁיחִ֖י כָּל־הַיָּמִֽים׃

በዕብራይስጥ ማሶሬት ላይ "ማሺያኽ" מָשִׁיחַ‎ የሚለው የማዕረግ ስም ትርጉሙ "የተቀባ" "ቅቡዕ" "መሢሕ" "ክርስቶስ" ማለት ነው፥ ይህ የማዕረግ ስም ለነገሥታት፣ ለነቢያት እና ለካህናት የሚውል ስም ነው። ይህ ጥቅስ ትንቢት ሲሆን ትንቢቱም ስለ ካህን እና ካህኑ ስለሚሄድበት መሢሑ ነው፥ ካህኑ ሳዶቅ ሲሆን መሢሑ ደግሞ ቤት የሠራው ሰለሞን ነው። ካህኑም ሳዶቅ ከድንኳኑ የቅብዓቱን ቀንድ ወስዶ ሰሎሞንን ቀባ፦
1ኛ ነገሥት 1፥39 ካህኑም ሳዶቅ ከድንኳኑ የቅብዓቱን ቀንድ ወስዶ ሰሎሞንን "ቀባ"።

ንጉሥ ዳዊት ስለ ልጁ ስለ ሰሎሞን በተናገረበት አንቀጽ ላይ ንጉሡ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን መሢሕ እንደሆነ የዐረማይክ ታርገም በዚህ መልኩ አስቀምጦቷል፦
መዝሙር 72፥1 አምላክ ሆይ! ፍርድህን ለንጉሡ መሢሕ ስጥ፥ ጽድቅህንም ለንጉሥ ዳዊት ልጅ። אֱלָהָא הִילְכוֹת דִינָךְ לְמַלְכָּא מְשִׁיחָא הַב וְצִדְקָתָךְ לִבְרֵיהּ דְדָוִד מַלְכָּא

"ታርገም" תרגום‎ ማለት "ትርጉም"translation ማለት ነው፥ ከ 35 እስከ 120 ድኅረ ልደት ይኖር የነበረው አኪላስ(አቂላስ) ያዘጋጀው ቶራህን መሠረት ያደረገ ማብራሪያ ታርገም አኪላስ"Targum Onkelos" ሲባል ከ 110 ቅድመ ልደት እስከ 10 ድኅረ ልደት ይኖር ነበር ተብሎ በሚገመተው ዮናታን ቤን ዑዚኤል ያዘጋጀው ነቢምን መሠረት ያደረገ ማብራሪያ ደግሞ ታርገም ዮናታን"Targum Jonathan" ይባላል። ዳዊት ለልጁ የምድረ በዳ ዘላኖች እንደሚንበረከኩለት ተናግሯል፦
መዝሙር 72፥9 የምድረ በዳ ዘላኖች በፊቱ ይንበረከካሉ። לְ֭פָנָיו יִכְרְע֣וּ צִיִּ֑ים

"ጺዪ" צִיִּי ማለት "የምድረ በዳ ዘላን" ማለት ሲሆን የጺዪ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ጺዪም" צִיִּ֑ים ነው፥ ይህም ቃል የበረሃ ሰውን ወይም የዱር አውሬን ለማመልከት ይመጣል። እዚህ አንቀጽ ላይ "ይንበረከካሉ" ለሚለው የገባው ቃል "ይክራዩ" יִכְרְע֣וּ ሲሆን "ካራ" כָּרַע ማለትም "ተንበረከከ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ነው፥ በተመሳሳይም አምሳ አለቃው በኤልያስ ፊት በጒልበቱ ተንበርክኮለታል፦
2ኛ ነገሥት 1፥13 በኤልያስ ፊት በጒልበቱ "ተንበረከከ"። וַיִּכְרַ֥ע עַל־ בִּרְכָּ֣יו לְנֶ֣גֶד אֵלִיָּ֗הוּ

"ዪክራ" כְרַ֥ע የሚለው የግሥ መደብ "ካራ" כָּרַע ለሚለው አሁናዊ ግሥ ነው። ታዲያ አምሳ አለቃው ለኤልያስ በጒልበቱ ስለተንበረከከ ኤልያስን እያመለከው ነበርን? እረ በፍጹም። በመቀጠል ንጉሥ ዳዊት ለልጁ ለሰሎሞን ነገሥታት እንደሚሰግዱ እና ሕዝቦች እንደሚገዙ ተናግሯል፦
መዝሙር 72፥11 ነገሥታት ሁሉ ይሰግዱለታል፥ አሕዛብም ሁሉ ይገዙለታል። וְיִשְׁתַּחֲווּ־לֹ֥ו כָל־מְלָכִ֑ים כָּל־גֹּויִ֥ם יַֽעַבְדֽוּהוּ׃
እዚህ አንቀጽ ላይ "ይሰግዳሉ" ለሚለው የገባው ቃል "ዪስታሀዉ" יִשְׁתַּחֲווּ ሲሆን "ሻኻህ" שָׁחָה ማለትም "ሰገደ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ነው፥ "ይገዙለታል" ለሚለው የገባው ቃል ደግሞ "የዐብዱ-ሁ" יַֽעַבְדֽוּהוּ ሲሆን "ዐበድ" עָבַד ማለትም "ተገዛ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ነው። ይስሐቅ ልጁን ያዕቆብን ሲባርከው የተጠቀመው ቃል ተመሳሳይ ነው፦
ዘፍጥረት 27፥29 አሕዛብ ይገዙልህ ሕዝብም ይስገዱልህ። יַֽעַבְד֣וּךָ עַמִּ֗ים [וְיִשְׁתַּחוּ כ] (וְיִֽשְׁתַּחֲו֤וּ ק) לְךָ֙ לְאֻמִּ֔ים 

እዚህ አንቀጽ ላይ "ይገዙልህ" ለሚለው የገባው ቃል "የዐብዱ-ከ" יַֽעַבְד֣וּךָ ሲሆን "ይስገዱ" ለሚለው የገባው ቃል ደግሞ "ዪስታሀዉ" יִֽשְׁתַּחֲו֤וּ ነው፥ ታዲያ ያዕቆብ አሕዛብ ስለተገዙለት እና ስለሰገዱለት እንደሚመለክ ያሳያልን? እረ በፍጹም። ስለዚህ "አይነኬ" ብለው ያሉት የሚሽነሪዎች ሙግት እንዲህ ዶግ አመድ እና አፈር ደቼ ይገባል፥ ዳዊት ከልጁ ባሻገር በድርብ መልእክት ለሚመጣው መሢሕ ትንቢት ከተናገረ ያ የሚመጣው መሢሕ ኢየሱስ ነው። ሚሽነሪዎች፦ "መሢሑ ይሰገድለታል፥ ይመለካል" ብለው መዝሙር 72፥11 ላይ ያለውን "ነገሥታት ሁሉ ይሰግዱለታል፥ አሕዛብም ሁሉ ይገዙለታል" የሚለውን ኃይለ-ቃል ይጠቀማሉ፥ ቅሉ ግን "መስገድ" እና "መገዛት" ለያዕቆብ እና ለንጉሡ ሰሎሞን ስለገባ እነዚህ ሰዎች ይመለካሉን? "እረ በፍጹም" ከተባለ እንግዲያውስ "የሚመጣው መሢሕ ይመለካል" ማለት በምንም አግባብ አንዳች ቊብ እና ረብ የለውም። ሚሽነሪዎች ኢየሱስ እንደሚመለክ ለማስመሰል የማይቆፍሩት ጉድጓድ፣ የማይፈነቅሉት ድንጋይ እና የማይደረምሱት መሬት የለም፥ ዐረብ ክርስቲያኖች በ 867 ድኅረ ልደት ከዕብራይስጥ ወደ ዐረቢኛ ባዘጋጁት በኮዴክስ ዐረቢከስ ላይ "ይገዙለታል" ለሚለው "ሊ-ተኽዲም-ሁ" لِتَخْدِمْهُ አሉት እንጂ "ሊ-ተዕቡዱ-ሁ" لِيَعْبُدُوهُ በፍጹም አላሉትም፦
لِيَنْحَنِ خُضُوعًا لَهُ كُلُّ المُلُوكِ، وَلِتَخْدِمْهُ كُلُّ الشُّعُوبِ.

"ኺድማህ" خِدْمَة የሚለው ቃል "ኸደመ" خَدَمَ ማለትም "አስተናገደ" "አገለገለ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መስተንግዶ" "አገልግሎት" ማለት ነው፥ "ኻዲም" خَادِمْ ማለት "አስተናጋጅ" "አገልጋይ" ማለት ሲሆን ለምሳሌ፦ አነሥ "ረ.ዐ." ነቢዩን"ﷺ" በአላፊ ግሥ "አገለገልኩኝ" ለማለት የተጠቀመበት ቃል በተመሳሳይ "ኸደምቱ" خَدَمْتُ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 78, ሐዲስ 68
አነሥ "ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "እንዲህ አለ፦ "ነቢዩን"ﷺ" አሥር ዓመት አስተናገድኩኝ(አገለገልኩኝ)"። يَقُولُ حَدَّثَنَا أَنَسٌ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ خَدَمْتُ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم عَشْرَ سِنِينَ،

ስለዚህ "ኢየሱስ ይመለካል" ብሎ ኲታ ገጠም ርእስ አርጎ በደምሳሳው መሞገት ወትሮም ቢሆን ዘንድሮም የሚያዋጣ ሙግት አይደለም። አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም