ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ኢሥቲቃማህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

11፥112 እንደ ታዘዝከውም ቀጥ በል፡፡ ከአንተ ጋር ያመኑትም ቀጥ ይበሉ፡፡ فَاسْتَقِمْ كَمَا أُمِرْتَ وَمَن تَابَ مَعَكَ

በኢሥላም ነገረ-ድኅነት"soteriology" እራሱን የቻለ ትልቅ ነጥብ ሲሆን "ፈላሕ” فَلَّاح ወይም "ነጃህ" نَّجَاة ይባላል፦
40፥41 ወገኖቼም ሆይ! ወደ መዳን የምጠራችሁ ስኾን ወደ እሳት የምትጠሩኝ ስትኾኑ ለእኔ ምን አለኝ? وَيَا قَوْمِ مَا لِي أَدْعُوكُمْ إِلَى النَّجَاةِ وَتَدْعُونَنِي إِلَى النَّارِ

እዚህ አንቀጽ ላይ "መዳን" ለሚለው የገባው ቃል "ነጃህ" نَّجَاة እንደሆነ ልብ በል! ሰዎችን ወደ ኢሥላም ስንጠራ ከእሳት እንዲድኑ ነው። አምላካችን አሏህ ምሕረት አድርጎ ከአሳማሚ ቅጣት የሚያድነን ንስሓ ስንገባ፣ ስናምን፣ መልካም ሥራ ሥንሠራ እና ስንጸና ነው፦
20፥82 እኔም ለተጸጸተ፣ ላመነም፣ መልካምንም ለሠራ፣ ከዚያም ለተመራ ሰው በእርግጥ መሐሪ ነኝ። وَإِنِّي لَغَفَّارٌ لِّمَن تَابَ وَآمَنَ وَعَمِلَ صَالِحًا ثُمَّ اهْتَدَىٰ

"ለተጸጸተ" ሲል ንስሓን፣ "ላመነ" ሲል ኢማንን፣ "መልካምን ለሠራ" ሲል ዐሚሉ ሷሊሓትን፣ "ለተመራ" ሲል ኢሥቲቃማህን ያመለክታል፥ ኢሥቲቃማህ በተጸጸተበት ንስሓ፣ ባመነበት ኢማን እና በምንሠራው መልካም ሥራ መጽናት ነው። "ኢሥቲቃማህ" اِسْتِقَامَة የሚለው ቃል "ኢሥቲቃመ اِسْتَقَامَ ማለትም "ቆመ" ወይም "ጸና" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ጽናት" ማለት ነው፦
42፥15 ለዚህም ድንጋጌ ሰዎችን ጥራ፡፡ እንደታዘዝከውም ቀጥ በል፡፡ فَلِذَٰلِكَ فَادْعُ ۖ وَاسْتَقِمْ كَمَا أُمِرْتَ
11፥112 እንደ ታዘዝከውም ቀጥ በል፡፡ ከአንተ ጋር ያመኑትም ቀጥ ይበሉ፡፡ فَاسْتَقِمْ كَمَا أُمِرْتَ وَمَن تَابَ مَعَكَ

እነዚህ አንቀጽ ላይ "ቀጥ በል" ለሚለው የገባው ቃል "ኢሥተቂም" اسْتَقِمْ ሲሆን "ጽና" ማለት ነው፥ በቀጥተኛው መንገድ ላይ መጽናት ፍርሃት እና ሐዘን ሳይኖር የጀነት ለመሆን መበሰር ነው፦
46፥13 እነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ያሉ፣ ከዚያም ቀጥ ያሉ በእነርሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም። እነርሱም አያዝኑም፡፡ إِنَّ الَّذِينَ قَالُوا رَبُّنَا اللَّهُ ثُمَّ اسْتَقَامُوا فَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ
41፥30 እነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ያሉ ከዚያም ቀጥ ያሉ «አትፍሩ፤ አትዘኑም፤ በዚያችም ተስፋ ቃል ትደረግላችሁ በነበራችሁት ገነት ተበሰሩ» በማለት በእነርሱ ላይ መላእክት ይወርዳሉ፡፡ إِنَّ الَّذِينَ قَالُوا رَبُّنَا اللَّهُ ثُمَّ اسْتَقَامُوا تَتَنَزَّلُ عَلَيْهِمُ الْمَلَائِكَةُ أَلَّا تَخَافُوا وَلَا تَحْزَنُوا وَأَبْشِرُوا بِالْجَنَّةِ الَّتِي كُنتُمْ تُوعَدُون

እነዚህ አናቅጽ ላይ "ቀጥ ያሉ" ለሚለው ቃል የገባው "ኢሥተቃሙ" اسْتَقَامُوا ሲሆን አምላካችን አሏህ በዲኑል ኢሥላም ለሚጸኑ አማንያን ጀነትን ተስፋ ሰቷቸዋል፦
17፥108 ይላሉም «ጌታችን ጥራት ይገባው! እነሆ የጌታችን ተስፋ ተፈጻሚ ነው፡፡» وَيَقُولُونَ سُبْحَانَ رَبِّنَا إِن كَانَ وَعْدُ رَبِّنَا لَمَفْعُولًا
19፥61 የመኖሪያን ገነቶች ያችን አልረሕማን ለባሮቹ በሩቅ ኾነው ሳሉ ተስፋ ቃል የገባላቸውን ይገባሉ፡፡ እርሱ ተስፋው ተፈጻሚ ነውና። جَنَّاتِ عَدْنٍ الَّتِي وَعَدَ الرَّحْمَـٰنُ عِبَادَهُ بِالْغَيْبِ ۚ إِنَّهُ كَانَ وَعْدُهُ مَأْتِيًّا

ለጽናት ጉልኅ ሚናህ ያለው አሏህን ለመገናኘት ተስፋ ማድረግ ነው፥ ከእዝነቱ ተስፋ መቁረጥ ግን ለጽናት እንቅፋት ነው፦
29፥5 የአላህን መገናኘት ተስፋ የሚያደርግ ሰው ይዘጋጅ፡፡ የአላህ ቀጠሮ በእርግጥ መጪ ነውና፡፡ እርሱም ሰሚው ዐዋቂው ነው፡፡ مَن كَانَ يَرْجُو لِقَاءَ اللَّهِ فَإِنَّ أَجَلَ اللَّهِ لَآتٍ ۚ وَهُوَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ
29፥23 እነዚያም በአላህ አንቀጾችና በመገናኘቱ የካዱ እነዚያ ከእዝነቴ ተስፋን ቆረጡ፡፡ እነዚያም ለእነሱ አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡ وَالَّذِينَ كَفَرُوا بِآيَاتِ اللَّهِ وَلِقَائِهِ أُولَـٰئِكَ يَئِسُوا مِن رَّحْمَتِي وَأُولَـٰئِكَ لَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ

አምላካችን አሏህ አንድ አምላክ ብቻ ነውና በሰጠን ተስፋ ወደ እርሱ ቀጥ ማለት ለጀነት ይዳርጋል፦
31፥6 እንዲህ በላቸው «እኔ መሰላችሁ ሰው ብቻ ነኝ፡፡ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ወደ እርሱም "ቀጥ በሉ" ምሕረትንም ለምኑት» ማለት ወደ እኔ ይወረድልኛል፡፡ ለአጋሪዎቹም ወዮላቸው፡፡ قُلْ إِنَّمَا أَنَا بَشَرٌ مِّثْلُكُمْ يُوحَىٰ إِلَيَّ أَنَّمَا إِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ فَاسْتَقِيمُوا إِلَيْهِ وَاسْتَغْفِرُوهُ ۗ وَوَيْلٌ لِّلْمُشْرِكِينَ

አሏህ በዲኑል ኢሥላም ያጽናን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኢሥቲሥላም

ክፍል አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥83 በሰማያት እና በምድር ያሉ በውድ እና በግድ ለእርሱ የታዘዙ እና ወደ እርሱ የሚመለሱ ሲኾኑ ከሓዲዎች ከአላህ ሃይማኖት ሌላን ይፈልጋሉን? أَفَغَيْرَ دِينِ اللَّهِ يَبْغُونَ وَلَهُ أَسْلَمَ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ طَوْعًا وَكَرْهًا وَإِلَيْهِ يُرْجَعُونَ

"ኢሥቲሥላም" اِسْتِسْلَام የሚለው ቃል "ኢሥተሥለመ" اِسْتَسْلَمَ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መታዘዝ" ወይም "መገዛት" ማለት ነው፥ በሰማያት እና በምድር ያሉ ሁሉ በውድም ወይም በግድም ለአሏህ የታዘዙ ናቸው፦
3፥83 በሰማያት እና በምድር ያሉ በውድ እና በግድ ለእርሱ የታዘዙ እና ወደ እርሱ የሚመለሱ ሲኾኑ ከሓዲዎች ከአላህ ሃይማኖት ሌላን ይፈልጋሉን? أَفَغَيْرَ دِينِ اللَّهِ يَبْغُونَ وَلَهُ أَسْلَمَ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ طَوْعًا وَكَرْهًا وَإِلَيْهِ يُرْجَعُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "የታዘዙ" ለሚለው ቃል የገባው የግሥ መደብ "አሥለመ" أَسْلَمَ እንደሆነ ልብ ልብ አድርግ! "ከርህ" كَرْه ማለት "ግዳጅ" ማለት ሲሆን "ጦውዕ" طَوْع ማለት ደግሞ "ፈቃደኝነት" ማለት ነው። ፍጥረት በሁለት መልኩ ለአላህ ይታዘዛል፥ አንዱ በግድ ሲሆን ይህ የግዴታ መታዘዝ "አል ኢሥላም ከውኒይ" الإِسْلَٰم كَوْنِيّ ሲባል ሁለተኛው ደግሞ የውዴታ መታዘዝ "አል ኢሥላም ሸርዒይ" الإِسْلَٰم شَرْعِيّ ነው። እነዚህን ነጥብ በነጥብ እንመልከት፦
ነጥብ አንድ
"አል ኢሥላም ከውኒይ"
"ከውኒይ" كَوْنِيّ የሚለው ቃል "ከወነ" كَوَّنَ‎ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ኹነት" ማለት ነው፥ በሰማያት ያሉ መላእክት ለአሏህ ይታዘዛሉ ይገዛሉ፦
66፥6 አላህን ያዘዛቸውን ነገር በመጣስ አያምጹም፡፡ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ፡፡ لَّا يَعْصُونَ اللَّهَ مَا أَمَرَهُمْ وَيَفْعَلُونَ مَا يُؤْمَرُونَ
7፥206 እነዚያ እጌታህ ዘንድ ያሉት መላእክት እርሱን ከመገዛት አይኮሩም፡፡ إِنَّ الَّذِينَ عِندَ رَبِّكَ لَا يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِهِ
21፥19 በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉም የእርሱ ነው፡፡ እርሱ ዘንድ ያሉትም መላእክት እርሱን ከመገዛት አይኮሩም፡፡ አይሰለቹምም፡፡ وَمَنْ عِندَهُ لَا يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِهِ وَلَا يَسْتَحْسِرُونَ

አምላካችን አሏህ ሰውን በዱኑል ኢሥላም የፈጠረባት ፊጥረተ-ሏህ "አል ኢሥላም ከውኒይ" الإِسْلَٰم كَوْنِيّ ነው፥ ማንም ሰው የሚወለደው በአል-ፊጥራ ላይ ሆኖ ነው፦
30፥30 ወደ እውነት ተዘንባይ ኾነህም ፊትህን ለሃይማኖት ቀጥ አድርግ፡፡ የአላህን ፍጥረት ያችን አላህ ሰዎችን በእርስዋ ላይ የፈጠረባትን ሃይማኖት ያዟት፡፡ فَأَقِمْ وَجْهَكَ لِلدِّينِ حَنِيفًۭا ۚ فِطْرَتَ ٱللَّهِ ٱلَّتِى فَطَرَ ٱلنَّاسَ عَلَيْهَا ۚ لَا تَبْدِيلَ لِخَلْقِ ٱللَّهِ ۚ ذَٰلِكَ ٱلدِّينُ ٱلْقَيِّمُ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ
ኢማም ቡኻርይ መፅሐፍ 23, ሐዲስ 138
ከአቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተላለፈው ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፡- "ማንም ተወላጅ የሚወለደው በአል-ፊጥራ ላይ ሆኖ ነው፥ ወላጆቹ ግን አይሁዳዊ ያደርጉታል ወይም ክርስቲያን ያደርጉታል አሊያም ዞሮስተርያን ያደርጉታል። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ كُلُّ مَوْلُودٍ يُولَدُ عَلَى الْفِطْرَةِ، فَأَبَوَاهُ يُهَوِّدَانِهِ أَوْ يُنَصِّرَانِهِ أَوْ يُمَجِّسَانِهِ

ሡረቱ አር ሩም 30፥30 ላይ አሏህ ሰዎችን የፈጠረበት ሃይማኖት "ሐኒፍ" حَنِيف ማለትም "ቀጥተኛ" ተብሏል፥ "አል-ፊጥራህ" الْفِطْرَةِ ማለት "ተፈጥሮ" ማለት ሲሆን ይህም የአሏህ የተፈጥሮ መንክር ነው። ያችን አሏህ ሰዎችን በእርስዋ ላይ የፈጠረባትን ሃይማኖት ያዟት የተባለችው የአሏህ የተፈጥሮ መንክር ናት፦
2፥138 የአላህን የተፈጥሮ መንክር ያዙ፡፡ በመንከርም ከአላህ ይበልጥ ያማረ ማነው? "እኛም ለርሱ ብቻ ተገዢዎች ነን" በሉ፡፡ صِبْغَةَ اللَّهِ ۖ وَمَنْ أَحْسَنُ مِنَ اللَّهِ صِبْغَةً ۖ وَنَحْنُ لَهُ عَابِدُونَ

አንድ ሰው በ 40 ወይም በ 80 ቀኑ ምንም ስለማያውቅ ወላጆቹ ቢያስጠምቁትም እላዩ ላይ ውኃ ከመፍሰስ በዘለለ መልኩ ምንም አያረጉትም፥ ቅሉ ግን በእነርሱ ዐቂዳህ አጥምመም ከልቡ ተርፎ በአንደበቱ፦ "እኔ የዚህ እምነት ተከታይ ነኝ" እስከሚል ድረስ በ"አል ኢሥላም ከውኒይ ሥር ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 46, ሐዲስ 38
አቢ ሙዓዊያህ እንደተረከው፦ ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ "ማንም የሚወለድ ሰው በአንደበቱ እስከሚል ድረስ በአል-ፊጥራ ላይ ሆኖ እንጂ አይወለድም። لَيْسَ مِنْ مَوْلُودٍ يُولَدُ إِلاَّ عَلَى هَذِهِ الْفِطْرَةِ حَتَّى يُعَبِّرَ عَنْهُ لِسَانُهُ
አሏህ ሰዎችን በቀጥተኛው መንገድ በኢሥላም ላይ ፈጥሮ ሳለ ሸያጢን ግን ከዚህ ዲን በሺርክ ምክንያት ሰዎችን ያርቃሉ፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐግ 53, ሐዲስ 76
ዒያድ ኢብኑ ሒማር እንደተረከው፦ የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” ኹጥባህ በሚደረግበት ቀን እንዲህ አሉ፦ ”ለእናንተ ያስተማርኩት ጌታዬ ያዘዘኝ፥ እናንተ የማታውቁትን እርሱ ዛሬ ያሳወቀኝን። አሏህም አለ፦ “እኔ የሰጠኃቸውንና ሕጋዊ የሆነላቸው ያ ሁሉ ንብረት ነው። እኔ ሁሉንም ባሮቼን በቀጥተኛው መንገድ ላይ ፈጠርኳቸው፥ ሸያጢን መጥተው ከዲናቸው አራቋቸው። عَنْ عِيَاضِ بْنِ حِمَارٍ الْمُجَاشِعِيِّ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ذَاتَ يَوْمٍ فِي خُطْبَتِهِ ‏”‏ أَلاَ إِنَّ رَبِّي أَمَرَنِي أَنْ أُعَلِّمَكُمْ مَا جَهِلْتُمْ مِمَّا عَلَّمَنِي يَوْمِي هَذَا كُلُّ مَالٍ نَحَلْتُهُ عَبْدًا حَلاَلٌ وَإِنِّي خَلَقْتُ عِبَادِي حُنَفَاءَ كُلَّهُمْ وَإِنَّهُمْ أَتَتْهُمُ الشَّيَاطِينُ فَاجْتَالَتْهُمْ عَنْ دِينِهِم

እዚህ ሐዲስ ላይ "ሁነፋእ" حُنَفَاءَ የሚለው ቃል "ሐኒፍ" حَنِيف ለሚለው ብዙ ቁጥር ነው፥ አሏህ ሰዎችን በእርስዋ ላይ የፈጠረባትን ሃይማኖት "ሐኒፍ" حَنِيف ነው። ነቢያችን"ﷺ" ወደ እርሳቸው ወሕይ ከመውረዱ በፊት በፊጥራህ ሐኒፍ የተባለውን አል ኢሥላም ከውኒይ ይተገብሩ ነበር፥ ከዚህ አንጻር እርሳቸው "ሙሥተሥሊም" مُستَسْلِم ነበሩ፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 1 ሐዲስ 3
የምዕመናን እናት ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ ”ከወሕይ ጅማሬ ለአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ልክ እንደ ጎህ ንጋት ደማቅ ሆኖ በሰናይ ህልም ሁኔታ ነበር። ከዚያም የተማልሎ ውዴታ በእርሷቸው ላይ ነበር። በሒራእ ዋሻ ውስጥ ይገለሉ እና “ቀጥ ይሉ ነበር”። እርሳቸውም ቤተሰባቸውን ለማየት ከመፈለጋቸው በፊት ለብዙ ቀናት በተከታታይ አላህ ያመልኩ ነበር"። عَنْ عَائِشَةَ أُمِّ الْمُؤْمِنِينَ، أَنَّهَا قَالَتْ أَوَّلُ مَا بُدِئَ بِهِ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم مِنَ الْوَحْىِ الرُّؤْيَا الصَّالِحَةُ فِي النَّوْمِ، فَكَانَ لاَ يَرَى رُؤْيَا إِلاَّ جَاءَتْ مِثْلَ فَلَقِ الصُّبْحِ، ثُمَّ حُبِّبَ إِلَيْهِ الْخَلاَءُ، وَكَانَ يَخْلُو بِغَارِ حِرَاءٍ فَيَتَحَنَّثُ فِيهِ ـ وَهُوَ التَّعَبُّدُ ـ اللَّيَالِيَ ذَوَاتِ الْعَدَدِ قَبْلَ أَنْ يَنْزِعَ إِلَى أَهْلِهِ

"ቀጥ ይሉ ነበር" ለሚለው የግሥ መደብ የገባው "የተሐነሱ" يَتَحَنَّثُ ሲሆን ኢብኑ ሐጀሩል አሥቀላኒ በፈተሑል ባሪ ፊ ሸርህ ሰሒሑል ቡኻርይ ሐዲስ 3 ላይ፦ "የተሐነሱ" يَتَحَنَّثُ ማለት "የተሐነፉ" يَتَحَنَّفُ ማለት እንደሆነ በቋንቋ ሙግት አስቀምጠዋል፦
قوله : ( فيتحنث ) ‏
‏هي بمعنى يتحنف ، أي : يتبع الحنفية وهي دين إبراهيم ، والفاء تبدل ثاء في كثير من كلامهم . وقد وقع في رواية ابن هشام في السيرة ” يتحنف ” بالفاء أو التحنث إلقاء الحنث وهو الإثم ، كما قيل يتأثم ويتحرج ونحوهما .

በተጨማሪም "ሐኒፋ" حَنِيفًا የኢብራሂም መንገድ ሲሆን ነቢያችን"ﷺ" ወሕይ ወደ እርሳቸው ከመውረዱ በፊት የኢብራሂምን መንገድ ይከተሉ ነበር፦
3፥95 «አላህ እውነትን ተናገረ፡፡ የኢብራሂምንም መንገድ ቀጥተኛ ሲኾን ተከተሉ፡፡ ከአጋሪዎቹም አልነበረም» በላቸው፡፡ قُلْ صَدَقَ اللَّهُ ۗ فَاتَّبِعُوا مِلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِين

እዚህ አንቀጽ ላይ "ቀጥተኛ" ለሚለው የገባው ቃል "ሐኒፍ" حَنِيف ሲሆን አምላካችን አሏህ በኢብራሂም ዘሮች ውስጥ የተህሊል ቀሪ ቃልን ስላደረገ ነቢያችን"ﷺ" የኢብራሂምን መንገድ የሚከተሉ ነበር፦
43፥28 በዝርዮቹም ውስጥ ይመለሱ ዘንድ ቀሪ ቃል አደረጋት፡፡ وَجَعَلَهَا كَلِمَةً بَاقِيَةً فِي عَقِبِهِ لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ

ኢንሻሏህ በክፍል ሁለት ስለ "አል ኢሥላም ሸርዒይ" እንመለከታለን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ለወትሮውም በማይስማሙ ባል እና ሚስት ውስጥ ልጅ እንዲህ ሲል ይጠይቃል፦ "እኛ ከምንድነው የተፈጠርነው?

አባት፦ "የፈጣሪ የእጆቹ ሥራ ነን፥ መጀመሪያ አዳምን ከአፈር አበጀው"

ልጅ እናቱ ጋር ይሄድና፦ እማ እኛ ከምንድነው የተፈጠርነው?

እናት ሆዬ፦ "እኛ የመጣነው ከዝንጀሮ ነው፥ ቀስ በቀስ በዝግመተ ለውጥ ነው"

ልጅ አባቱ ጋር ይሄድና እናቴ እኮ "ሰው የመጣው ከዝንጀሮ በዝግመተ ለውጥ ነው" አለችኝ።

አባት፦ "እርሷ የነገረችህ የእነሱን ቤተሰብ ነው"

ምንጭ ፓፕይ ዘተዋሕዶ
ኢሥቲሥላም

ክፍል ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

6፥163 «ለእርሱ ተጋሪ የለውም፡፡ በዚህም በማጥራት ታዘዝኩ፡፡ እኔም የሙሥሊሞች መጀመሪያ ነኝ» በል፡፡ لَا شَرِيكَ لَهُۥ ۖ وَبِذَٰلِكَ أُمِرْتُ وَأَنَا۠ أَوَّلُ ٱلْمُسْلِمِينَ

በክፍል አንድ "አል ኢሥላም ከውኒይ" الإِسْلَٰم كَوْنِيّ እራሱ "ሙጅመል" مُجّمَل ማለትም "ጥቅላዊ መታዘዝን"general submission" እንደሚያመለክት አይተን ነበር፥ "አል ኢሥላም ሸርዒይ" الإِسْلَٰم شَرْعِيّ ደግሞ "ሙፈሰል" مُفَصَّل ማለትም "የተናጥል መታዘዝን"particular submission" እንደሆነ ኢንሻሏህ ዛሬ እናያለን።

ነጥብ ሁለት
"አል ኢሥላም ሸርዒይ"
"ሸርዒይ" شَرْعِيّ የሚለው ቃል "ሸረዐ" شَرَعَ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ድንጋጌ" "ሕግ" "መርሕ" ማለት ነው፦
45፥18 ከዚያም ከትእዛዝ "በትክክለኛይቱ ሕግ" ላይ አደረግንህ፡፡ ثُمَّ جَعَلْنَاكَ عَلَىٰ شَرِيعَةٍ مِّنَ الْأَمْرِ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ትክክለኛይቱ ሕግ” ለሚለው የገባው ቃል "ሸሪዓህ" شَرِيعَة እንደሆነ ልብ አድርግ! አምላካችን አሏህ በእያንዳንዱ ዘመን ለሁሉም መልእክተኞች ሸሪዓህ እና ሚንሀጅ አድርጓል፦
፥48 ከእናንተ ለሁሉም ሕግን እና መንገድን አደረግን”። ۚ لِكُلٍّۢ جَعَلْنَا مِنكُمْ شِرْعَةًۭ وَمِنْهَاجًۭا

"ሚንሀጅ” مِنْهَج ማለት "ፍኖት" "ፋና" "መንገድ" ማለት ሲሆን እዚህ አንቀጽ ላይ "መንገድ" በሚል ተገልጿል፥ አሏህ በእያንዳንዱ ዘመን ሸሪዓህ እና ሚንሀጅ በማድረግ ሰዎችን በውዴታ እንዲታዘዙ የሚያደርግበት "አል ኢሥላም ሸርዒይ" الإِسْلَٰم شَرْعِيّ ይባላል፦
22፥34 አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱም ብቻ ታዘዙ፡፡ ለአላህ ተዋራጆችንም አብስራቸው፡፡ فَإِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ فَلَهُ أَسْلِمُوا ۗ وَبَشِّرِ الْمُخْبِتِينَ

"ታዘዙ" ለሚለው ቃል የተቀመጠው "አሥሊሙ" أَسْلِمُوا ሲሆን በነጻ ፈቃድ ላይ የተመሠረተውን አል ኢሥላም ሸርዒይ ያመለክታል፥ "አምላክ አንድ አምላክ ብቻ ነው" ብሎ ያንን አንድ አምላክ የሚታዘዝ "ሙሥሊም" مُسْلِم ይሰኛል፦
21፥108 «ያ ወደ እኔ የሚወረደው፦ “አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው” ማለት ነው፥ ታዲያ እናንተ ፍጹም ታዛዦች ናችሁን» በላቸው፡፡ قُلْ إِنَّمَا يُوحَىٰ إِلَيَّ أَنَّمَا إِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّسْلِمُون

እዚህ አንቀጽ ላይ "አምላክ አንድ አምላክ ብቻ ነው" ብለው የሚያመልኩትን ለማመልከት "ታዛዦች" በሚል ቃል ተገልጸዋል፥ "ታዛዦች" ለሚለው የገባው ቃል "ሙሥሊሙን" مُّسْلِمُون ሲሆን "ሙሥሊም" مُسْلِم ለሚለው ብዙ ቁጥር ነው። አምላካችን አሏህ ቁርኣንን ሸሪዓህ አርጎ ወደ ነቢያችን"ﷺ" አውርዷል፥ ይህንን ትእዛዝ ተቀብለው የታዘዙ የመጀመሪያው ታዛዥ እርሳቸው ናቸው፦
65፥5 ይህ “የአላህ ትእዛዝ ነው”። ወደ እናንተም አወረደው። ذَٰلِكَ أَمْرُ ٱللَّهِ أَنزَلَهُۥٓ إِلَيْكُمْ
6፥14 «እኔ መጀመሪያ ትእዛዝን ከተቀበለ ሰው ልኾን ታዘዝኩ፡፡ ከአጋሪዎችም ፈጽሞ አትኹን ተብያለሁ» በላቸው፡፡ قُلْ إِنِّىٓ أُمِرْتُ أَنْ أَكُونَ أَوَّلَ مَنْ أَسْلَمَ ۖ وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ ٱلْمُشْرِكِينَ

"ትእዛዝን የተቀበለ" ለሚለው ቃል የገባው "አሥለመ" أَسْلَمَ ሲሆን በቁርኣን የመጣውን አል ኢሥላም ሸርዒይ ተቀብለው የሠለሙ የሙሥሊሞች መጀመሪያ እርሳቸው ናቸው፥ እዚህ አንቀጽ ላይ "አወል" أَوَّل ማለትም "መጀመሪያ" የሚለው ገላጭ ቅጽል በአንጻራዊነት ደረጃ የመጣ ነው፦
6፥163 «ለእርሱ ተጋሪ የለውም፡፡ በዚህም በማጥራት ታዘዝኩ፡፡ እኔም የሙሥሊሞች መጀመሪያ ነኝ» በል፡፡ لَا شَرِيكَ لَهُۥ ۖ وَبِذَٰلِكَ أُمِرْتُ وَأَنَا۠ أَوَّلُ ٱلْمُسْلِمِينَ

እንግዲህ ቁርኣንን ተቀብሎ የሙሥሊሞች መጀመሪያ ነቢያችን”ﷺ” ናቸው ማለት ነው፥ እዚህ አንቀጽ ላይ "ሙሥሊሚን" مُسْلِمِين የተባሉት የነቢያችን"ﷺ" ተከታዮች ናቸው፦
3፥20 ቢከራከሩህም፡- «ፊቴን ለአላህ ሰጠሁ፤ የተከተሉኝም ሰዎች እንደዚሁ ለአላህ ሰጡ» በላቸው፡፡ فَإِنْ حَاجُّوكَ فَقُلْ أَسْلَمْتُ وَجْهِيَ لِلَّهِ وَمَنِ اتَّبَعَنِ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ሰጠሁ" ለሚለው ቃል የገባው ቃል "አሥለምቱ" أَسْلَمْتُ ሲሆን ከእርሳቸው ቀጥሎ ተከታዮቻቸው እንደ እርሳቸው እራሳቸውን ለአሏህ የሰጡ ናቸው። ነቢያችን"ﷺ" ከአሏህ ወደ እርሳቸው በተወረደው ቁርኣን መጀመሪያ ሲያምኑ ለጥቆ ተከታዮቻቸውም ምእመናን እንደዚሁ አመኑ፦
2፥285 መልክተኛው ከጌታው ወደ እርሱ በተወረደው አመነ፡፡ ምእምኖቹም እንደዚሁ አመኑ”*፡፡ آمَنَ الرَّسُولُ بِمَا أُنزِلَ إِلَيْهِ مِن رَّبِّهِ وَالْمُؤْمِنُون

ሙእሚኑን እና ሙሥሊሙን ተለዋዋጭ ቃል ሆኖ ከመጣ ነቢያችን"ﷺ" የተከታዮቻቸው መጀመሪያ ናቸው፥ በተጨማሪም "አመነ" آمَنَ የሚለው ቃል በራሱ ቁርኣን ከመውረዱ በፊት እርሳቸው ስለ ቁርኣን መጽሐፍ እና እምነት ምን እንደሆነ ዐያውቁም ነው፦
42፥52 እንደዚሁም ወደ አንተ ከትእዛዛችን ሲኾን መንፈስን(ቁርኣንን) አወረድን፡፡ መጽሐፉም እምነቱም ምን እንደኾነ የምታውቅ አልነበርክም፡፡ وَكَذَٰلِكَ أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ رُوحًا مِّنْ أَمْرِنَا ۚ مَا كُنتَ تَدْرِي مَا الْكِتَابُ وَلَا الْإِيمَانُ

እዚህ አንቀጽ ላይ "እምነቱ" የሚለው ቃል "አል-ኢማን" الْإِيمَان በሚል አመልካች መስተአምር መምጣቱ በራሱ ከጌታው ወደ እርሱ በተወረደው ቁርኣን ማመንን ያሳያል፥ "ኢማን" إِيمَان የሚለው ቃል እራሱ “አመነ” آمَنَ ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "እምነት" ማለት ነው።
ኢሥላም ከአሏህ ዘንድ የተወፈቅነው ተውፊቅ ሲሆን ሙሥሊም ከአሏህ ዘንድ የተቸረን ሀዲያህ ነው። ክብር እና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአሏህ ይሁን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሙሥሊም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

15፥2 እነዚያ የካዱት በትንሣኤ ቀን ሙሥሊሞች በኾኑ ኖሩ በብዛት ይመኛሉ፡፡ رُّبَمَا يَوَدُّ الَّذِينَ كَفَرُوا لَوْ كَانُوا مُسْلِمِينَ

"ሙሥሊም" مُسْلِم የሚለው ቃል "አሥለመ" أَسْلَمَ ማለትም "ታዘዘ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ታዛዥ" ማለት ነው፥ የሙሥሊም ብዙ ቁጥር ደግሞ "ሙሥሊሙን" مُّسْلِمُون ወይም "ሙሥሊሚን" مُسْلِمِين ሲሆን "ታዛዦች" ማለት ነው፦
21፥108 «ያ ወደ እኔ የሚወረደው፦ “አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው” ማለት ነው፥ ታዲያ እናንተ ፍጹም ታዛዦች ናችሁን» በላቸው፡፡ قُلْ إِنَّمَا يُوحَىٰ إِلَيَّ أَنَّمَا إِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّسْلِمُون

እዚህ አንቀጽ ላይ "ታዛዦች" ለሚለው የገባው ቃል "ሙሥሊሙን" مُّسْلِمُون ሲሆን "ሙሥሊም" مُسْلِم ማለት "አንዱን አምላክ በብቸኝነት የሚያመልክ ወይም የሚታዘዝ" ማለት ነው፥ የፈጠረንን አሏህን በሙፍረዳት እና በሙሐረማት ወይንም በአምስቱ ሙሐከማት ስንታዘዝ ሙሥሊም እንሰኛለን። አምላካችን አሏህ ወደ አደም ኪዳን ሲያወርድ "ሙሥሊሞች" ብሎ ጠራን፦
20፥115 ወደ አደምም ከዚህ በፊት ኪዳንን በእርግጥ አወረድን፡፡ وَلَقَدْ عَهِدْنَا إِلَىٰ آدَمَ مِن قَبْلُ
22፥78 በአላህም ሃይማኖት ተገቢውን ትግል ታገሉ፡፡ እርሱ መርጧችኋል፡፡ በእናንተም ላይ በሃይማኖቱ ውስጥ ምንም ችግር አላደረገባችሁም፡፡ የአባታችሁን የኢብራሂምን ሃይማኖት ተከተሉ፡፡ እርሱ ከዚህ በፊት ሙሥሊሞች ብሎ ሰይሟችኋል፡፡ وَجَاهِدُوا فِي اللَّهِ حَقَّ جِهَادِهِ ۚ هُوَ اجْتَبَاكُمْ وَمَا جَعَلَ عَلَيْكُمْ فِي الدِّينِ مِنْ حَرَجٍ ۚ مِّلَّةَ أَبِيكُمْ إِبْرَاهِيمَ ۚ هُوَ سَمَّاكُمُ الْمُسْلِمِينَ مِن قَبْلُ

ቁርኣን በወረደበት ጊዜ አሏህ፦ "ሚን ቀብሉ" مِن قَبْلُ ማለትም "ከዚህ በፊት" የሚለውን ኢሥሙል መጅሩር የሚጠቁመን ወደ አደም ወሕይን ያወረደበትን ጊዜ ነው፥ በዚያን ጊዜ "ሙስሊሞች" ብሎ ሰይሟል። "እርሱ" የሚለው ተውላጠ ስም "አሏህ" የሚለውን ስም ተክቶ የመጣ ስለሆነ "ሙስሊሞች" ብሎ የሰየመው ኢብራሂም ሳይሆን አሏህ ነው፥ ምክንያቱም ከኢብራሂም በፊት ኑሕ፦ "ከሙሥሊሞች" እንደሆነ ተናግሯል፦
10፥72 «ብትሸሹም አትጎዱኝም፡፡ ከምንዳ ምንንም አልለምናችሁምና፥ ምንዳዬ በአላህ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም፡፡ ከሙሥሊሞች እንድሆንም ታዝዣለሁ፡፡» فَإِن تَوَلَّيْتُمْ فَمَا سَأَلْتُكُم مِّنْ أَجْرٍ ۖ إِنْ أَجْرِيَ إِلَّا عَلَى اللَّهِ ۖ وَأُمِرْتُ أَنْ أَكُونَ مِنَ الْمُسْلِمِينَ

ከኑሕ በኃላ ኢብራሂም ከልጁ ከኢሥማዒል ጋር፦ "ሙሥሊሞች አርገን" ብሎ ዱዓእ አርጓል፦
2፥128 ጌታችን ሆይ! ለአንተ ታዛዦችም አድርገን፡፡ ከዘሮቻችንም ለአንተ ታዛዦች ሕዝቦችን አድርግ፡፡ رَبَّنَا وَاجْعَلْنَا مُسْلِمَيْنِ لَكَ وَمِن ذُرِّيَّتِنَا أُمَّةً مُّسْلِمَةً لَّكَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ታዛዦች" ለሚለው የገባው ቃል "ሙሥሊማህ" مُّسْلِمَة መሆኑ በራሱ ሙሥሊም ማለት ለአሏህ ታዛዥ መሆኑን ቁልጭ አርጎ አያሳይምን? አሏህ ኢብራሂምን፦ "አሥሊም" أَسْلِمْ ባለው ጊዜ "አሥለምቱ" أَسْلَمْتُ አለው፦
2፥131 ጌታው ለእርሱ ታዘዝ ባለው ጊዜ ለዓለማት ጌታ ታዘዝኩ አለ፡፡ إِذْ قَالَ لَهُ رَبُّهُ أَسْلِمْ ۖ قَالَ أَسْلَمْتُ لِرَبِّ الْعَالَمِينَ

ኢብራሂም ልጆቹን ኢሥማዒልን እና ይስሓቅን እንዲሁ የልጅ ልጁን የዕቁብን በኢሥላም አዘዘ፦
2፥132 በእርሷም ኢብራሂም ልጆቹን አዘዘ፡፡ وَوَصَّىٰ بِهَا إِبْرَاهِيمُ بَنِيهِ
ከዚያም የዕቁብም ልጆቹን፦ "እናንተ ሙሥሊሞች ኾናችሁ እንጂ አትሙቱ" አላቸው፦
2፥132 የዕቁብም፦ «ልጆቼ ሆይ! አላህ ለእናንተ ሃይማኖትን መረጠ፤ ስለዚህ እናንተ ሙሥሊሞች ኾናችሁ እንጂ አትሙቱ» አላቸው፡፡ وَيَعْقُوبُ يَا بَنِيَّ إِنَّ اللَّهَ اصْطَفَىٰ لَكُمُ الدِّينَ فَلَا تَمُوتُنَّ إِلَّا وَأَنتُم مُّسْلِمُونَ

ሙሣም ለሕዝቦቹ፦ "ሙሥሊሞች እንደ ሆናችሁ በአሏህ ላይ ትመካላችሁ" አላቸው፦
10፥84 ሙሣም አለ፡- «ሕዝቦቼ ሆይ! በአላህ አምናችሁ እንደ ሆነ በርሱ ላይ ተጠጉ፡፡ ታዛዦች እንደ ሆናችሁ በአላህ ላይ ትመካላችሁ»። وَقَالَ مُوسَىٰ يَا قَوْمِ إِن كُنتُمْ آمَنتُم بِاللَّهِ فَعَلَيْهِ تَوَكَّلُوا إِن كُنتُم مُّسْلِمِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ታዛዦች" ለሚለው የገባው ቃል "ሙሥሊሚን" مُّسْلِمِين እንደሆነ ልብ አድርግ! የዒሣ ሐዋርያትም ለዒሣ፦ "ሙሥሊሞች መኾናችንን መስክር" ማለታቸው በራሱ ከጥንትም የነበሩት ነቢያት እና ሐዋርያት ሙሥሊሞች ነበሩ፦
3፥52 ሐዋርያት፡- «እኛ የአላህ ረዳቶች ነን፤ በአላህ አምነናል፤ እኛም ትክክለኛ "ታዛዦች" መኾናችንን መስክር» አሉ፡፡ قَالَ الْحَوَارِيُّونَ نَحْنُ أَنصَارُ اللَّهِ آمَنَّا بِاللَّهِ وَاشْهَدْ بِأَنَّا مُسْلِمُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ታዛዦች" ለሚለው የገባው ቃል "ሙሥሊሙን" مُسْلِمُون መሆኑን ልብ አልክን? እንግዲህ ስለ ሉጥ፣ ዩሡፍ፣ ሡለይማን ወዘተ ነቢያት ሁሉ ሙሥሊሞች መሆናቸውን የጊዜ እና የቦታ ጉዳይ እንጂ በቁና ጥቅስ ማቅረብ ይቻላል።
በጥቅሉ ከቁርኣን መውረድ በፊት አንዱን አምላክ የሚያመልኩ የነበሩት ሙዋሒዱን በእነርሱ ላይ ቁርኣን በሚነበብላቸውም ጊዜ፦ "እኛ ከቁርኣን በፊት ሙሥሊሞች ነበርን" ሲሉ ጥንት ነቢያት እና ሐዋርያት ሲያመልኩት የነበረውን አንዱን አምላክ አምላኪ መሆናቸውን ማሳያ ነው፦
27፥53 በእነርሱ ላይ በሚነበብላቸውም ጊዜ «በእርሱ አምነናል፡፡ እርሱ ከጌታችን የኾነ እውነት ነው፡፡ እኛ ከእርሱ በፊት ሙሥሊሞች ነበርን» ይላሉ፡፡ وَإِذَا يُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ قَالُوا آمَنَّا بِهِ إِنَّهُ الْحَقُّ مِن رَّبِّنَا إِنَّا كُنَّا مِن قَبْلِهِ مُسْلِمِينَ
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 15, ሐዲስ 457
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" በረውሓእ ጋላቢዎችን በማግኘት፦ "እናንተ ማን ናችሁ? ብለው ጠይቋቸው፥ እነርሱም "እኛ ሙሥሊሞች ነን" ብለው መለሱላቸው። እነርሱም አንተስ ማን ነህ አሏቸው "እሳቸውም፦ "እኔ የአሏህ መልዕክተኛ ነኝ" አሏቸው"። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم لَقِيَ رَكْبًا بِالرَّوْحَاءِ فَقَالَ ‏"‏ مَنِ الْقَوْمُ ‏"‏ ‏.‏ قَالُوا الْمُسْلِمُونَ ‏.‏ فَقَالُوا مَنْ أَنْتَ قَالَ ‏"‏ رَسُولُ اللَّهِ ‏"‏

አምላካችን አሏህ በፍርድ ቀን እነዚያ በአንቀጾቹ ያመኑ እና ሙሥሊሞች የነበሩትን፦ "ገነትን ግቡ! እናንተም ጥንዶቻችሁም ትደሰታላችሁ ትከበሩማላችሁ" ይላቸዋል፦
43፥69 እነዚያ በአንቀጾቻችን ያመኑና ፍጹም ታዛዦች የነበሩትን «ገነትን ግቡ! እናንተም ጥንዶቻችሁም ትደሰታላችሁ ትከበሩማላችሁ» ይባላሉ፡፡ الَّذِينَ آمَنُوا بِآيَاتِنَا وَكَانُوا مُسْلِمِينَ ادْخُلُوا الْجَنَّةَ أَنتُمْ وَأَزْوَاجُكُمْ تُحْبَرُونَ
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 212
አቢ ሁረይራህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "እነሆ ሙሥሊም የሆነች ነፍስ እንጂ ሌላው ጀነትን አይገባትም"። ﻋَﻦْ ﺃَﺑِﻲ ﻫُﺮَﻳْﺮَﺓَ، ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻪ ﻗَﺎﻝ ﻋﻦ ﺍﻟﻨَّﺒِﻲّ ﺻَﻠَّﻰ ﺍﻟﻠﻪُ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﻭَﺳَﻠَّﻢَ ﺃﻧﻪ ﻗَﺎﻝَ ﺃَﻧَّﻪُ ﻟَﺎ ﻳَﺪْﺧُﻞُ ﺍﻟْﺠَﻨَّﺔَ ﺇِﻟَّﺎ ﻧَﻔْﺲٌ ﻣُﺴْﻠِﻤَﺔٌ

በተቃራኒው ከሃድያን በፍርዱ ቀን ሙሥሊሞች በኾኑ ኖሩ በብዛት ይመኛሉ፦
15፥2 እነዚያ የካዱት በትንሣኤ ቀን ሙሥሊሞች በኾኑ ኖሩ በብዛት ይመኛሉ፡፡ رُّبَمَا يَوَدُّ الَّذِينَ كَفَرُوا لَوْ كَانُوا مُسْلِمِينَ

አሏህ እሥልምናን እንደወፈቀን ሙሥሊም አርጎ ያሙተን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሴት እርሻ ናት!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥223 ሴቶቻችሁ ለእናንተ እርሻ ናቸው፥ እርሻችሁንም በፈለጋችሁት ኹኔታ ድረሱ፡፡ نِسَاؤُكُمْ حَرْثٌ لَّكُمْ فَأْتُوا حَرْثَكُمْ أَنَّىٰ شِئْتُمْ

በቁርኣን አምላካችን አሏህ ወንድ ለሴት "ልብስ" እንደሆነ እንዲሁ ሴት ለወንድ "ልብስ" እንደሆነች ይነግረናል፦
2፥187 በጾም ሌሊት ወደ ሴቶቻችሁ መድረስ ለእናንተ ተፈቀደላችሁ፡፡ እነርሱ ለእናንተ ልብሶች ናቸው፥ እናንተም ለእነርሱ ልብሶች ናችሁ፡፡ أُحِلَّ لَكُمْ لَيْلَةَ الصِّيَامِ الرَّفَثُ إِلَىٰ نِسَائِكُمْ ۚ هُنَّ لِبَاسٌ لَّكُمْ وَأَنتُمْ لِبَاسٌ لَّهُن

እዚህ አንቀጽ ላይ ወንድ ለሴት ሴት ለወንድ "ልብስ" ናቸው ሲል በፍካሬአዊ ሃፍረትን፣ ነውርን እና ገበናን "መሸፈኛ" ማለት እንጂ በእማሬአዊ ወስዶ "ጃኬት" ወይም "ቀሚስ" አሊያም "ሱሪ" ማለት አይደለም። በተመሳሳይ ሴት ለወንድ እርሻ ናት፦
2፥223 ሴቶቻችሁ ለእናንተ እርሻ ናቸው፥ እርሻችሁንም በፈለጋችሁት ኹኔታ ድረሱ፡፡ نِسَاؤُكُمْ حَرْثٌ لَّكُمْ فَأْتُوا حَرْثَكُمْ أَنَّىٰ شِئْتُمْ

መቼም ቂል የሆነ ሰው ካልሆነ ሴት ለወንድ "እርሻ" ናት ሲባል ሞፈርና ቀንበር አዋዶ የሆነው የጓሮ አትክልት አሊያም ሰብል ናት ማለት እንዳልሆነ እሙንና ቅቡል ነው፥ ቃሉ የወከለው እሳቤ እማሬአዊ ሳይሆን ፍካሬአዊ ነው። የሴት ልጅ ማኅፀን ዘር የሚዘራበት "እርሻ" ሲመሰል የእንሥት ማህፀን ላይ ላይ የሚገናኘው የተባእት ዘር ሕዋስ ደግሞ ገበሬ እርሻ ላይ በሚዘራው "ዘር" ተመስሏል፥ ወንድ ዘሩን ዘሪ ሲሆን ሴት ያንን ዘር የምታፈራበት እርሻ ናት። ምክንያቱም አንድ ገበሬ እርሻው ላይ ከዘራ በኃላ ዘሩ ዳብሮ ለፍሬ የሚበቃው በእርሻ ውስጥ እንደሆነ ሁሉ አንድ ተባእትም አንድ እንስት ማኅፀን ውስጥ ዘሩን ተገናኝ ሆኖ ከዘራ በኃላ ሂደቱ ሁሉ ተከናውኖ ለፍሬ የሚበቃው ማኅፀን ውስጥ ስለሆነ ነው። በማኅፀን ውስጥ በመፍሰስ የሚዘራው ዘር የተንጣለለ ደካማ ውኃ የሆነው የፍትወት ሕዋስ ነው፥ ይህም ሕዋስ በተጠበቀ መርጊያ በእርሻው ውስጥ ለፍሬ እስኪበቃ ይቆያል፦
56፥58 በማኅፀኖች የምታፈሱትን አያችሁን? أَفَرَأَيْتُم مَّا تُمْنُونَ
56፥63 የምትዘሩትንም አያችሁን? أَفَرَأَيْتُم مَّا تَحْرُثُون
32፥8 ከዚያም ዘሮቹን ከተንጣለለ ከደካማ ውኃ ያደረገ ነው፡፡ ثُمَّ جَعَلَ نَسْلَهُ مِن سُلَالَةٍ مِّن مَّاءٍ مَّهِينٍ
23፥13 ከዚያም በተጠበቀ መርጊያ ውስጥ የፍትወት ጠብታ አደረግነው፡፡ ثُمَّ جَعَلْنَاهُ نُطْفَةً فِي قَرَارٍ مَّكِينٍ

ታላቁ የቁርኣን ሙፈሢር ኢብኑ ከሲር የኢብኑ ዐባሥን ንግግር ዋቢ በማድረግ የፈሠሩት በዚህ መልክ እና ልክ ነው፦
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 2፥223
ንግግሩ፦ "ሴቶቻችሁ ለእናንተ እርሻ ናቸው" የሚለውን ኢብኑ ዐባሥ፦ "እርሻ የሚለው የእርግዝናን ቦታ ነው”" ብሏል"። وقوله : ( نساؤكم حرث لكم ) قال ابن عباس : الحرث موضع الولد

"ሴት" እና "ወንድ" የሚለው የፆታ መደብ የፍትወት ሕዋሳችንን ታሳቢ እና ዋቢ ያደረገ ቢሆንም ነገር ግን አጠቃላይ ስብዕናችንን እንደሚያሳይ ሁሉ በተመሳሳይ "እርሻዎቻችሁ" ማለት "ሴቶቻችሁ" ማለትን ይይዛል፥ እርሻ ዘር የሚዘራበት እንደሆነ ሁሉ ሴትም ዘር ስለሚዘራባት እርሻ ተብላለች። "እርሻችሁንም በፈለጋችሁት ኹኔታ ድረሱ" የሚለው አንቀጽ የወረደበት ሠበቡ አን-ኑዙል መዲና ላይ የነበሩ አይሁዳውያን፦ "ማንም የሚስቱን ሃፍረት በጀርባ በኩል ተራክቦ ያደረገ ልጁ ጠንጋራ ይሆናል" የሚል የተንጋደደ መረዳት ስለያዙ ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3245
ከጃቢር ኢብኑ ሙንከዲር ሰምቶ እንደተረከው፦ "አይሁዳውያን፦ "ማንም የሚስቱን ሃፍረት በጀርባ በኩል ተራክቦ ያደረገ ልጁ ጠንጋራ ይሆናል" አሉ፥ ከዚያም አላህ፦ "ሴቶቻችሁ ለእናንተ እርሻ ናቸው፥ እርሻችሁንም በፈለጋችሁት ኹኔታ ድረሱ" የሚለውን አንቀጽ አወረደ"። عَنِ ابْنِ الْمُنْكَدِرِ، سَمِعَ جَابِرًا، يَقُولُ كَانَتِ الْيَهُودُ تَقُولُ مَنْ أَتَى امْرَأَتَهُ فِي قُبُلِهَا مِنْ دُبُرِهَا كَانَ الْوَلَدُ أَحْوَلَ فَنَزَلَتْ ‏:‏ ‏(‏نِسَاؤُكُمْ حَرْثٌ لَكُمْ فَأْتُوا حَرْثَكُمْ أَنَّى شِئْتُمْ ‏)‏

"በፈለጋችሁ ሁኔታ" ማለት በጀርባ በኩል ተራክቦ"doggy sex" ማድረግም ክልክል አይደለም ማለትን ይጨምራል፥ ያ ማለት በመቀመጫ በኩል ተራክቦ”anal sex” ማድረግ ይቻላል ማለት እንዳልሆነ ለማሳየት እዛው ዐውድ ላይ፦ "አላህ ካዘዛችሁ ስፍራ ተገናኙዋቸው" በማለት ይናገራል። በመቀመጫ ተራክቦ ማድረግ ሐራም ነው፥ ሐራም ብቻ ሳይሆን ኩፍሩል አስገርም ነው፦
2፥222 ንጹሕ በኾኑም ጊዜ አላህ ካዘዛችሁ ስፍራ ተገናኙዋቸው"፡፡ فَإِذَا تَطَهَّرْنَ فَأْتُوهُنَّ مِنْ حَيْثُ أَمَرَكُمُ اللَّهُ
ጃሚዒ አት-ተርሚዚ : መጽሐፍ 1, ሐዲስ 135
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንዳለው፦ “ነቢዩ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው፦ ማንም በሓይድ ላይ ካለች ሴት ወይም በመቀመጫዋ በኩል ተራክቦ ቢያደርግ በሙሐመድ”ﷺ” ላይ በተወረደው ክዷል"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏”‏ مَنْ أَتَى حَائِضًا أَوِ امْرَأَةً فِي دُبُرِهَا أَوْ كَاهِنًا فَقَدْ كَفَرَ بِمَا أُنْزِلَ عَلَى مُحَمَّدٍ صلى الله عليه وسلم ‏”‏
እዚህ ድረስ ከተግባባን የጴጥሮስ ተማሪ የሮሙ ክሌመንት ሴት እርሻ እንደሆነች አበክሮ እና አዘክሮ ይናገራል፦
ቀለሜንጦስ 10፥50 "አንቲ ገራህት ዕቀቢ ርእሰኪ! ወኢትደምሪ ዘርአ ነኪር፥ እንዘ ሁሉ ዘይናዝዘኪ ሐዘነኪ ሶበ ከመዝ ዘርእኪ ቡሩክ ውእቱ"።

ትርጉም፦ "አንቺ እርሻ ራስሽን ጠብቂ! ሌላ ዘርን አትጨምሪ፥ የሚያጽናናሽ እና ከሐዘንሽ የሚያረጋጋሽ ባልሽ ብቻ ነው"።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የአዲስ ኪዳን መጽሐፍት ቀኖና 35 ናቸው፥ የአዲስ ኪዳን መደበኛ የቀኖና መጽሐፍት 27 ሲሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መጽሐፍት ተጨማሪ ቀኖና 8 ናቸው። ከስምንቱ አንዱ "መጽሐፈ ቀለሜንጦስ" ነው፥ እና ቀለሜንጦስ ሴትን እርሻ ሲል ሞፈርና ቀንበር አዋዶ የሆነው የጓሮ አትክልት አሊያም ሰብል ናት ማለቱ ነውን? በጣም ስመ ጥርና ገናና የአዲስ ኪዳን አራት እደክታባት መካከል ኮዴክስ ኤፍራኤሚ(ኤፍሬም) ሲሆን በ 450 ድኅረ ልደት ያዘጋጀው ሶርያዊው ኤፍሬም ነው፥ ይህ የሶርያ ኤጲጵ ቆጶስ ድንግል ማርያምን እርሻ እንደሆነች አስረግጦ እና ረግጦ በውዳሴም ማርያም ላይ ይናገራል፦
ውዳሴ ማርያም ዘማክሰኞ ቁጥር 4
"አንቲ ውእቱ ገራህት ዘኢተዘርአ ውስቴታ ዘርእ፥ ወጽአ እምኔኪ ፍሬ ሕይወት"።

ትርጉም፦ "ዘር ያልተዘራባት እርሻ አንቺ ነሽ፥ የሕይወት ፍሬ ከአንቺ ወጣ"።

እዚህ ዐውድ ላይ "ዘር" የተባለው የወንድ የዘር ሕዋስ ነው፥ ድንግል ማርያም ኢየሱስን ስትፀንስ የወንድ የዘር ሕዋስ የሌለው ቢሆንም በተፈጥሮዋ የወንድ የዘር ሕዋስ የሚዘራበት ማኅፀን ስላላት "እርሻ" ተብላለች። እና ድንግል ማርያም ሞፈርና ቀንበር አዋዶ የሆነው የጓሮ አትክልት አሊያም ሰብል ናትን? እሩቅ ሳንሄድ አማንያን እርሻ ተብለዋል፦
1 ቆሮንቶስ 3፥9 እናንተ የእግዚአብሔር እርሻ ናችሁ”*፤ you are God’s field. NIV

መልሳችሁ፦ "ውይ ወሒድ ደግሞ ይህ ቀላል ነገር እኮ ነው፦ "እርሻ ናችሁ" ሲለን "የጓሮ አትክልት ናችሁ" ማለት ሳይሆን ልባችን በእርሻ ተመስሏል፥ ቃሉ ደግሞ በዘር ይመሰላል። ይህ እንዴት አይገባህም?" ትላላችሁ፥ ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ ነገር ነው። ከላይ ያለውንም በዚህ ቀመር ተረዱት! "አመድ በዱቄት ይስቃል" እንዲሉ የአሏህ ንግግር ላይ ስትስቁ እና ስትሳለቁ ትውፊት ላይ ሴት እርሻ እንደሆነች ኩልል እና ጥርት ብሎ ተቀምጧል። ለነገሩ ባይብል እና አዋልድ ሴት "ደካማ ፍጥረት ናት፥ በተፈጥሮዋ ደካማ ናት፥ የሰማችውን ሁሉ ሳታመዛዝን አሜን ብላ ትቀበላለችና" ይለናል፦
1 ጴጥሮስ 3፥7 እንዲሁም፥ እናንተ ባሎች ሆይ፥ ደካማ ፍጥረት ስለ ሆኑ ከሚስቶቻችሁ ጋር በማስተዋል አብራችሁ ኑሩ፤
ቀለሜንጦስ 2÷14 ሴት በተፈጥሮዋ ደካማ ናት፤ የሰማችውን ሁሉ ሳታመዛዝን አሜን ብላ ትቀበላለችና።

አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን!

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አዳዲስ የገባችሁ ክርስቲያኖች ወደ ቻናሉ እንኳን ደህና መጣችሁ!

በጥሞና፣ በቅጡ እና በቅንነት ከላይ ጀምራችሁ አንብቡ አስነብቡ። አሏህ ሂዳያህ እንዲሰጣችሁ ዱዓዬ ነው።
ሒጃብ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

33፥59 አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ *ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው*፡፡ ይህ እንዲታወቁ እና በባለጌዎች እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ قُل لِّأَزْوَاجِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَاءِ الْمُؤْمِنِينَ يُدْنِينَ عَلَيْهِنَّ مِن جَلَابِيبِهِنَّ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَن يُعْرَفْنَ فَلَا يُؤْذَيْنَ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا

"ሒጃብ" حِجَاب ማለት "መሸፈኛ" "መሸፋፈኛ" "መጋረጃ" "ግርዶ" ማለት ነው፦
19፥17 *ከእነርሱም መጋረጃን አደረገች*፡፡ መንፈሳችንምም ጂብሪልን ወደ እርሷ ላክን፡፡ ለእርሷም ትክክለኛ ሰው ሆኖ ተመሰለላት፡፡ فَاتَّخَذَتْ مِن دُونِهِمْ حِجَابًا فَأَرْسَلْنَا إِلَيْهَا رُوحَنَا فَتَمَثَّلَ لَهَا بَشَرًا سَوِيًّا

እዚህ አንቀጽ ላይ መርየም እንዳያዩአት ያደረገችው መጋረጃ "ሒጃብ" حِجَاب ተብሎ ተቀምጧል። ሒጃብ ሙሥሊም ሴት የምትሰተርበት ኺማር እና ጂልባብ ነው፦
24፥31 *ለምእምናትም ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ፡፡ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፡፡ ጌጣቸውንም ከእርሷ ግልጽ ከኾነው በስተቀር አይግለጡ፡፡ ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ ያጣፉ*፡፡ የውስጥ ጌጣቸውንም ለባሎቻቸው ወይም ለአባቶቻቸው ወይም ለባሎቻቸው አባቶች ወይም ለወንዶች ልጆቻቸው ወይም ለባሎቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለወንድሞቻቸው ወይም ለወንድሞቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለእህቶቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለሴቶቻቸው ወይም እጆቻቸው ለያዙት ወይም ከወንዶች ለሴት ጉዳይ የሌላቸው ለኾኑ ተከታዮች ወይም ለእነዚያ በሴቶች ሐፍረተ ገላ ላይ ላላወቁ ሕፃኖች ካልኾነ በስተቀር አይግለጹ፡፡ ከጌጣቸውም የሚሸፍኑት ይታወቅ ዘንድ በእግሮቻቸው አይምቱ፡፡ ምእመናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ በመመለስ ተጸጸቱ፡፡ وَقُل لِّلْمُؤْمِنَاتِ يَغْضُضْنَ مِنْ أَبْصَارِهِنَّ وَيَحْفَظْنَ فُرُوجَهُنَّ وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلَّا مَا ظَهَرَ مِنْهَا ۖ وَلْيَضْرِبْنَ بِخُمُرِهِنَّ عَلَىٰ جُيُوبِهِنَّ ۖ وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلَّا لِبُعُولَتِهِنَّ أَوْ آبَائِهِنَّ أَوْ آبَاءِ بُعُولَتِهِنَّ أَوْ أَبْنَائِهِنَّ أَوْ أَبْنَاءِ بُعُولَتِهِنَّ أَوْ إِخْوَانِهِنَّ أَوْ بَنِي إِخْوَانِهِنَّ أَوْ بَنِي أَخَوَاتِهِنَّ أَوْ نِسَائِهِنَّ أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُهُنَّ أَوِ التَّابِعِينَ غَيْرِ أُولِي الْإِرْبَةِ مِنَ الرِّجَالِ أَوِ الطِّفْلِ الَّذِينَ لَمْ يَظْهَرُوا عَلَىٰ عَوْرَاتِ النِّسَاءِ ۖ وَلَا يَضْرِبْنَ بِأَرْجُلِهِنَّ لِيُعْلَمَ مَا يُخْفِينَ مِن زِينَتِهِنَّ ۚ وَتُوبُوا إِلَى اللَّهِ جَمِيعًا أَيُّهَ الْمُؤْمِنُونَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ

"ጉፍታዎች" ለሚለው በብዜት የገባው ቃል "ኹሙር" خُمُر ሲሆን በነጠላ ደግሞ "ኺማር" خِمَار ነው። እዚህ አንቀጽ ላይ አጅነቢይ ያልሆኑት ወንዶች ተዘርዝረዋል። “አጅነቢይ” أَجْنَبِيّ ማለት “ባዕድ” ማለት ሲሆን አንዲት ሙሥሊም በተቃራኒ ፆታ ያሉትን ለመጨበጥ ወይም ጸጉሯን ለማየት ሐላል ያልሆነ ሰው ማለት ነው። ይህ አንቀጽ ሲወርድ ሴቶች በኒቃብ ተሰትረዋል፥ "ኒቃብ" نِقَاب ማለት "መሸፈኛ" ማለት ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 4759
ሶፊያህ ቢንት ሸይባህ እንደተረከችው፦ "ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንዲህ ትል ነበር፦ *"ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ ያጣፉ" የሚለው አንቀጽ በወረደች ጊዜ ሴቶቹ ከወገቦቻቸውን ጨርቆች በኩል ይቆርጡና ጭንቅላታቸውን እና ፊታቸውን በተቆረጡት የጨርቅ ቁርጥራጮች ይሸፍኑ ነበር"*። عَنْ صَفِيَّةَ بِنْتِ شَيْبَةَ، أَنَّ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ كَانَتْ تَقُولُ لَمَّا نَزَلَتْ هَذِهِ الآيَةُ ‏{‏وَلْيَضْرِبْنَ بِخُمُرِهِنَّ عَلَى جُيُوبِهِنَّ‏}‏ أَخَذْنَ أُزْرَهُنَّ فَشَقَّقْنَهَا مِنْ قِبَلِ الْحَوَاشِي فَاخْتَمَرْنَ بِهَا‏.‏

"ጉፍታዎች" በሌላ አንቀጽ "መከናነቢያዎች" በሚል ተለዋዋጭ ቃል መጥቷል፦
33፥59 አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ *ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው*፡፡ ይህ እንዲታወቁ እና በባለጌዎች እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ قُل لِّأَزْوَاجِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَاءِ الْمُؤْمِنِينَ يُدْنِينَ عَلَيْهِنَّ مِن جَلَابِيبِهِنَّ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَن يُعْرَفْنَ فَلَا يُؤْذَيْنَ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا
እዚህ አንቀጽ ላይ "መከናነቢያዎች" ለሚለው በብዜት የገባው ቃል "ጀላቢብ" جَلَٰبِيب ሲሆን በነጠላ ደግሞ "ጂልባብ" جِلْبَاب‎ ነው። ለባለጌዎች በጂልባብ ከተሰተረች ይልቅ የተራቆተች ሴት ለመተንኮስ፣ ለመለከፍ፣ ለመደፈር ቅርብ ናት። የዚህ አንቀጽ ሠበቡ አን-ኑዙሉ በዚህ ሐዲስ እንዲህ ተገልጿል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 4, ሐዲስ 12
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ *"የነቢዩ"ﷺ" ባልተቤቶች በሌሊት ወደ መናሲዕ በጣም ሰፊ ቦታ ይሔዱ ነበር። ዑመርም ለነቢዩ"ﷺ"፦ "ባለቤቶችዎ መሸፈን አለባቸው" አለ፥ የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" ምንም አላደረጉም። በዒሻእ ጊዜ የነቢዩ"ﷺ" ባለቤት ሠውዳህ ቢንት ዘምዓህ ወጣች፥ እርሷም ረጅም እመቤት ነበረች። ዑመርም፦ "ሠውዳህ ሆይ! ዐውቄሻለው" አላት፥ ስለ ሒጃብ ወሕይ እንዲወርድ በጉጉት ተመኘ። አላህም የሒጃብ አንቀጽ አወረደ"*። عَنْ عَائِشَةَ، أَنَّ أَزْوَاجَ النَّبِيِّ، صلى الله عليه وسلم كُنَّ يَخْرُجْنَ بِاللَّيْلِ إِذَا تَبَرَّزْنَ إِلَى الْمَنَاصِعِ ـ وَهُوَ صَعِيدٌ أَفْيَحُ ـ فَكَانَ عُمَرُ يَقُولُ لِلنَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم احْجُبْ نِسَاءَكَ‏.‏ فَلَمْ يَكُنْ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَفْعَلُ، فَخَرَجَتْ سَوْدَةُ بِنْتُ زَمْعَةَ زَوْجُ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم لَيْلَةً مِنَ اللَّيَالِي عِشَاءً، وَكَانَتِ امْرَأَةً طَوِيلَةً، فَنَادَاهَا عُمَرُ أَلاَ قَدْ عَرَفْنَاكِ يَا سَوْدَةُ‏.‏ حِرْصًا عَلَى أَنْ يَنْزِلَ الْحِجَابُ، فَأَنْزَلَ اللَّهُ آيَةَ الْحِجَابِ‏.‏

ሚሽነሪዎች፦ "የሒጃብ አንቀጽ መውረድ ምክንያት ዑመር ነው" ይላሉ። ታዲያ ምን ችግር አለው? ሳራ ለአብርሃም፦ "ይህችን ባሪያ ከነልጅዋ አሳድድ! የዚህች ባሪያ ልጅ ከልጄ ከይስሐቅ ጋር አይወርስም" ብላ አሳቡን አምጥታ እግዚአብሔር ለአብርሃም አሳቧን እንዲቀበል፦ "ሣራም የምትነግርህን ቃል ሁሉ ስማ" ሲለው ለአጋር ብላቴናውንም ሰጥቶ አስወጣት፦
ዘፍጥረት 21፥10 *አብርሃምንም ይህችን ባሪያ ከነልጅዋ አሳድድ! የዚህች ባሪያ ልጅ ከልጄ ከይስሐቅ ጋር አይወርስምና" አለችው*።
ዘፍጥረት 21፥12 *እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፦ ስለ ባሪያህና ስለ ብላቴናው አትዘን፤ ሣራም የምትነግርህን ቃል ሁሉ ስማ"*።
ዘፍጥረት 21፥14 *አብርሃምም ማልዶ ተነሣ፥ እንጀራንም ወሰደ፥ የውኃ አቁማዳንም ለአጋር በትከሻዋ አሸከማት፥ ብላቴናውንም ሰጥቶ አስወጣት"*።

እግዚአብሔር አብርሃምን ያዘዘው ሳራ ባመጣቸው አሳብ ነው። የሒጃብ እሳቤ ዑመር ከመምጣቱ በፊት እኮ ባይብል ላይም አለ። ይስሐቅም ርብቃን ከማግባቱ በፊት አጅነቢይ ስለነበረ እንዳያያት ኺማር ወስዳ ተከናነበች፦
ዘፍጥረት 24፥65 *"እርስዋም መሸፈኛ ወስዳ ተከናነበች"*። فَأخَذَتْ رِفقَةُ الخِمارَ وَغَطَّتْ وَجهَها

"መሸፈኛ" ለሚለው ቃል የገባው "ኺማር" خِمارَ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። "ወጀሀሃ" وَجهَها ማለት "ፊቷን" ማለት ነው፥ በሒጃብ የተሰተረችው ፊቷን ነው። በእስራኤል ሴቶቹ ዓይናቸውን በኒቃብ ይሸፈኑ ነበር። ንጉሥ ሰለሞን የሱላማጢስ ልጃገረጅን በዓይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ዓይኖች እና ጕንጭና ጕንጯ እንዳሉ መናገሩ በኒቃብ ፊታቸው እና አይናቸው ይሰተሩ እንደነበር አመላካች ነው፦
መኃልይ 4፥1 *በዓይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ዓይኖችሽ እንደ ርግቦች ናቸው*። عَيْنَاكِ حَمَامَتَانِ مِنْ تَحْتِ نَقَابِكِ
መኃልይ 4፥3 *በዓይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ጕንጭና ጕንጭሽ እንደ ተከፈለ ሮማን ናቸው*። كَفَلَقَةِ رُمّانَةٍ هُوَ خَدُّكِ تَحتَ خِمارِكِ

ሁለቱም አናቅጽ ላይ "መሸፈኛሽ" ለሚለው ቃል የገባው "ነቃቢኪ" نَقَابِكِ እና "ሒማሪኪ" خِمارِكِ ነው። "ኒቃብ" نِقَاب እና "ኺማር" خِمَار ባይብል ውስጥ እንዲህ በግልጽ ተቀምጧል። በአንድ ወቅት የሱላማጢስ ልጃገረጅን ሒጃብ ቅጥር ጠባቂዎች እንደወሰዱባት መናገሯ በራሱ ሒጃብ ታደርግ እንደነበር ማሳያ ነው፦
መኃልይ 5፥7 *ቅጥር ጠባቂዎችም የዓይነ ርግብ መሸፈኛዬን ወሰዱት*። وَنَزَعَ حُرّاسُ الأسوارِ خِمارِي عَنِّي

“ኺማሪ” خِمارِي የኺማር ቀዳማይ መደብ ነጠላ አገናዛብ ቃል ነው። አንድ ለዐቅመ-ሐዋ የሆነች ሴት ሶላት ላይ በኺማር የተሰተረች መሆን አለባት፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 251
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *”አላህ ለዐቅመ-ሐዋ የሆነች ሴት ሶላት አይቀበል በኺማር የተሰተረች ቢሆን እንጂ”*። عَنْ عَائِشَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم أَنَّهُ قَالَ ‏ “‏ لاَ يَقْبَلُ اللَّهُ صَلاَةَ حَائِضٍ إِلاَّ بِخِمَارٍ ‏”‏ ‏

በባይብል ሴት ራስዋን በኺማር ሳትሸፍን ወደ ፈጣሪ ልትጸልይ አይገባትም፥ ጭራሽ ዲድስቅልያ ላይ ሴት አማኝ ሁሉም ቦታ እንድትከናነብ ወፍራም ትእዛዝ አለ፦
1 ቆሮንቶስ 11፥13 *በእናንተ በራሳችሁ መካከል ፍረዱ፤ ሴት ራስዋን ሳትሸፍን ወደ እግዚአብሔር ልትጸልይ ይገባታልን?*
ዲድስቅልያ 3፥32 ነገር ግን ላመኑ ሴቶች ራሳቸውን በንጽህና “ሊከናነቡ” ይገባል። እነርሱ “ተከናንበው” በጎዳና ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ይሂዱ!።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የአዲስ ኪዳን መጽሐፍት ቀኖና 35 ናቸው፥ የአዲስ ኪዳን መደበኛ የቀኖና መጽሐፍት 27 ሲሆኑ ተጨማሪ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መጽሐፍት ቀኖና 8 ሲሆኑ ከስምንቱ አንዱ "ዲድስቅልያ"didache" ነው።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የኢየሱስ ስም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥75 የመርየም ልጅ አልመሢሕ ከበፊቱ መልእክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልእክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ

"ኢየሱስ" የሚለው የፍጡር ስም የናዝሬቱ ኢየሱስ ከመፀነሱ በፊት ብሉይ ኪዳን ላይ ለብዙ ሰዎች ስም ሆኖ ያገለግል ነበር፥ ይህ ስም አዲስ ኪዳን ላይም ለብዙ ሰዎች ስም ሆኖ ያገለግል ነበር። ታዲያ የፍጡር ስም ከሆነ "በኢየሱስ ስም" ለምንድን ነው ነገራት የሚከናወኑት? ለምሳሌ አብን ለመለመን በኢየሱስ ስም መጠቀምን ይገልጻል፦
ዮሐንስ 15፥16 አብም በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ እንዲሰጣችሁ፥ ልትሄዱና ፍሬ ልታፈሩ ፍሬአችሁም ሊኖር ሾምኋችሁ።

"በስሜ" ማለት "በኢየሱስ ስም" ማለት ነው፥ "በኢየሱስ ስም" ማለት "ኢየሱስ ባስተማረው እና ባዘዘው" ማለት እንደሆነ ዐውደ ንባቡ"contextual passage" ያስቀምጣል፦
ዮሐንስ 15፥14 እኔ ያዘዝኋችሁን ሁሉ ብታደርጉ እናንተ ወዳጆቼ ናችሁ።

ኢየሱስ እንዴት መጸለይ እንዳለባቸው ባዘዛቸው መሠረት ወደ አብ መጸለይ በኢየሱስ ስም መጸለይ ማለት ነው፥ "በ" የሚል መስተዋድድ ባለበት ቃል ላይ "ስም" የሚል ቃላት አንዳንድ ናሙና እንመልከት፦
1ኛ ስሙኤል 25፥9 የዳዊትም ጕልማሶች መጡ፥ ይህንም ቃል ሁሉ "በዳዊት ስም" ለናባል ነግረው ዝም አሉ።

"በዳዊት ስም" የሚለው ይሰመርበት! የዳዊትም ጕልማሶች ለናባል "በዳዊት ስም" ነገሩት ማለት "በዳዊት ትእዛዝ" ነገሩት ከሆነ እንግዲያውስ "በኢየሱስ ስም" አብን መለመን ማለት "በኢየሱስ ትእዛዝ" አብን መለመን ማለት ነው። ሌላ ናሙና እንመልከት፦
ማቴዎስ 10፥42 ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ "በደቀ መዝሙር ስም" የሚያጠጣ እውነት እላችኋለሁ ዋጋው አይጠፋበትም።

"በደቀ መዝሙር ስም" የሚለው ይሰመርበት! "በደቀ መዝሙር ስም" ጽዋ ውኃ ለታናናሾች ማጠጣት ዋጋ እንደሚያሰጥ ሁሉ "በኢየሱስ ስም" ጽዋ ውኃ ማጠጣት ዋጋ ያሰጣል፦
ማርቆስ 9፥41 የክርስቶስ ስለ ሆናችሁ "በስሜ" ጽዋ ውኃ የሚያጠጣችሁ ሁሉ ዋጋው እንዳይጠፋበት እውነት እላችኋለሁ።

እንደ እናንተ ስሑት ሙግት "በኢየሱስ ስም" ማለት ልክ "በአሏህ ስም" እንደ ማለት ከሆነ "በዳዊት ስም" "በደቀ መዝሙር ስም" ማለት "በአምላክ ስም" ማለት ነው ብላችሁ ለምን አልተረዳችሁትም? ዳዊት እና ኢየሱስ ነቢያት ሲሆኑ ሐዋርያቱ ደግሞ ጻድቃን ናቸው፥ ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል፦
ማቴዎስ 10፥41 ነቢይን "በነቢይ ስም" የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም "በጻድቅ ስም" የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል።

"በነቢይ ስም" እና "በጻድቅ ስም" የሚለው ይሰመርበት! ያ ማለት ነቢይን እንደ ነቢይ የሚቀበል ጻድቅን እንደ ጻድቅ የሚቀበል ዋጋ አለው፥ ዐውደ ንባቡ ላይ "እናንተን የሚቀበል" በማለት ሐዋርያትን እንደ ጻድቅ መቀበል እንዲሁ "እኔን የሚቀበል" በማለት መልእክተኛውን ኢየሱስን እንደ ነቢይ መቀበል ምንዳ እና ትሩፋት አለው፦
ማቴዎስ 10፥40 እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።

ስለዚህ "በኢየሱስ ስም" የተባለው "በዳዊት ስም" "በደቀ መዝሙር ስም" "በነቢይ ስም" "በጻድቅ ስም" በተባለበት ስሌት እና ቀመር ነው። የመርየም ልጅ ኢየሱስ ከእርሱ በፊት እንዳሉት መልእክተኞች የሆነ መልእክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፦
5፥75 የመርየም ልጅ አልመሢሕ ከበፊቱ መልእክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልእክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ

አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አስካሪ መጠጥ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥219 አእምሮን ከሚቃወም መጠጥ እና ከቁማር ይጠይቁሃል፡፡ «በሁለቱም ውስጥ ታላቅ ኃጢኣት እና ለሰዎች ጥቅሞች አሉባቸው፡፡ ግን ኃጢኣታቸው ከጥቅማቸው በጣም ትልቅ ነው» በላቸው፡፡ يَسْأَلُونَكَ عَنِ الْخَمْرِ وَالْمَيْسِرِ ۖ قُلْ فِيهِمَا إِثْمٌ كَبِيرٌ وَمَنَافِعُ لِلنَّاسِ وَإِثْمُهُمَا أَكْبَرُ مِن نَّفْعِهِمَا ۗ

"ኸምር" خَمْرየሚለው ቃል "ኸመረ" خَمَرَ ማለትም "ሸፈነ" "ደበቀ" "ሰወረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ "የሚሸፍን" "የሚደብቅ" "የሚሰውር" ማለት ነው፥ እኅቶቻችን ከሚሰተሩበት ሒጃብ መካከል "ጉፍታ" እራሱ በቁርኣን "ኺማር" خِمَار ይባላል፦
24፥31 ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ ያጣፉ። وَلْيَضْرِبْنَ بِخُمُرِهِنَّ عَلَىٰ جُيُوبِهِنَّ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ጉፍታዎች" ለሚለው በብዜት የገባው ቃል "ኹሙር" خُمُر ሲሆን በነጠላ ደግሞ "ኺማር" خِمَار ነው፥ “ኺማር” خِمَار የሚለው ቃል ልክ እንደ “ኸምር” خَمْر ሥርወ-ቃሉ “ኸመረ” خَمَرَ ነው። ጉፍታ ራስን ስለሚሸፍን “ኺማር” خِمَار እንሚባል ሁሉ አእምሮን የሚቃወም ማንኛውም አስካሪ መጠጥ”alcohol" ሁሉ “ኸምር” خَمْر ይባላል፦
2፥219 አእምሮን ከሚቃወም መጠጥ እና ከቁማር ይጠይቁሃል፡፡ «በሁለቱም ውስጥ ታላቅ ኃጢኣትና ለሰዎች ጥቅሞች አሉባቸው፡፡ ግን ኃጢኣታቸው ከጥቅማቸው በጣም ትልቅ ነው» በላቸው፡፡ يَسْأَلُونَكَ عَنِ الْخَمْرِ وَالْمَيْسِرِ ۖ قُلْ فِيهِمَا إِثْمٌ كَبِيرٌ وَمَنَافِعُ لِلنَّاسِ وَإِثْمُهُمَا أَكْبَرُ مِن نَّفْعِهِمَا ۗ

ቁማር መሠረቱ ገንዘብ ስለሆነ ለሰዎች ጥቅም አለው፥ አስካሪ መጠጥ በህክምና አገልግሎት ለሰዎች ጥቅም አለው። ነገር ግን ኸምር ሆነ ቁማር ኃጢኣታቸው ከጥቅማቸው በጣም ትልቅ ስለሆነ ታላቅ ኃጢኣት አለባቸው፥ አስካሪ መጠጥ ውስጥ የሚካተቱት ጠላ፣ ጠጅ፣ አረቄ፣ ውስኪ፣ ቮድካ ወዘተ ናቸው፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 74, ሐዲስ 14
ኢብኑ ዑመር”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “ዑመር በአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” አትሮንስ ላይ ኹጥባህ ሲያደርግ እንዲህ አለ፦ ”ኸምር ሐራም መሆኑ የሚናገረው የወረደው ከአምስት ነገር ማለትም ከወይን፣ ከተምር፣ ከስንዴ፣ ከገብስ እና ከማር ስለሚዘጋጁት ኸምር ናቸው። ዐቅልን የሚሰውር ሁሉ ኸምር ነው”። عَنِ ابْنِ عُمَرَ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ خَطَبَ عُمَرُ عَلَى مِنْبَرِ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَقَالَ إِنَّهُ قَدْ نَزَلَ تَحْرِيمُ الْخَمْرِ، وَهْىَ مِنْ خَمْسَةِ أَشْيَاءَ الْعِنَبِ وَالتَّمْرِ وَالْحِنْطَةِ وَالشَّعِيرِ وَالْعَسَلِ، وَالْخَمْرُ مَا خَامَرَ الْعَقْلَ

እዚህ ሐዲስ ላይ “የሚሰውር” ለሚለው የገባው ቃል “ኻመረ” خَامَرَ መሆኑ ልብ አድርግ! አስካሪ መጠጥ አእምሮን የሚያስት እስከሆነ ድረስ ሙሥኪር ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 36, ሐዲስ 95
ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ “ነቢዩ”ﷺ”፦ ”ሙሥኪር ሁሉ ኸምር ነው፥ ኸምር ሁሉ ሐራም ነው” ሲሉ እንጂ ሌላ ዐላውቅም”። عَنِ ابْنِ عُمَرَ، قَالَ وَلاَ أَعْلَمُهُ إِلاَّ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ كُلُّ مُسْكِرٍ خَمْرٌ وَكُلُّ خَمْرٍ حَرَامٌ ‏”‏
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 30, ሐዲስ 3514
ሙዓዊያህ የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቼ ነበር፦ ”ሙሥኪር ሁሉ ለሁሉም ምእመናን ሐራም ነው”። سَمِعْتُ مُعَاوِيَةَ، يَقُولُ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ يَقُولُ ‏ “‏ كُلُّ مُسْكِرٍ حَرَامٌ عَلَى كُلِّ مُؤْمِنٍ ‏”‏

“ሙሥኪር” مُسْكِر የሚለው ቃል “ሠኪረ” سَكِرَ
ማለትም "ሰከረ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "የሚያሰክር" "የሚያነፍዝ" ማለት ነው፥ “ሠከር” سَكَر እራሱ “አስካሪ”intoxicant” ማለት ሲሆን “ሡክር” سُكْر ደግሞ “አስካሪነት”intoxication” ማለት ነው። ኸምር ከዘምባባ እና ከወይን ፍሬ የሚሠራ ጠጅ ነው፦
16፥67 ከዘምባባዎች እና ከወይኖችም ፍሬዎች እንመግባችኋለን፡፡ ከእርሱ ጠጅን እና መልካም ምግብንም ትሠራላችሁ፡፡ በዚህም ውስጥ ለሚያስቡ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምር አለ፡፡ وَمِن ثَمَرَاتِ النَّخِيلِ وَالْأَعْنَابِ تَتَّخِذُونَ مِنْهُ سَكَرًا وَرِزْقًا حَسَنًا ۗ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لِّقَوْمٍ يَعْقِلُونَ

አሏህ ከዘንባባ እና ከወይን ፍሬ ማብቀሉ በእርግጥ ታምር አለበት፥ ከዚህም ሰው በሠናይ መልካም ምግብ ማለትም ጭማቂ ሲሠራ በተቃራኒው እኩይ የሆነውን አስካሪ ጠጅን ይሠራል። "ዛሊከ" ذَٰلِكَ ማለትም "በዚህም" የተባለው ኢሥሙል ኢሻራህ ከበፊቱ ያለው "ሁ" هُ ማለትም "እርሱ" የተባለው ዶሚሩል ሙንተሲል የሚያመለክት ነው፥ ይህም "እርሱ" የተባለው ፍራፍሬው ነው፦
16፥11 "በ"-"እርሱ" ለእናንተ አዝመራን፣ ወይራንም፣ ዘምባባዎችንም፣ ወይኖችንም፣ ከፍሬዎችም ሁሉ ያበቅልላችኋል፤ በዚህ ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች በእርግጥ ታምር አለ። يُنبِتُ لَكُم بِهِ الزَّرْعَ وَالزَّيْتُونَ وَالنَّخِيلَ وَالْأَعْنَابَ وَمِن كُلِّ الثَّمَرَاتِ ۗ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ
እዚህ አንቀጽ ላይ “ዛሊከ” ذَٰلِكَ የተባለው የአዝመራን፣ የወይራንም፣ የዘምባባዎችንም፣ የወይኖችንም ፍራፍሬ ነው። ተጨማሪ አናቅጽ፦ 6፥99 13፥3 ይመልከቱ!
ፍራፍሬ ሲቆይ ስኳርነቱ ወደ አሲድ ይቀየርና ቆምጣጣነት"Fermentation" ሢሠራ ወይም ጌሾና ብቅል ሲቀላቀልበት ፓስቸራዜሽን”Pasteurization” እና ኒዩትራላይዜሽን”Neutralization” በመሆን ያሰክራል፥ ቢራ ፣ ቮድካ፣ ውስኪ የመሳሰሉት የዛ ውጤት ናቸው። አስካሪ መጠጥ አዕምሮን የሚያደንዝ እና ለጥል፣ ለጥላቻ፣ ለዝሙት፣ ለጣዖት አምልኮ የሚዳርግ፣ ከሶላት እና አሏህ ከማውሳት የሚያዘናጋ እኩይ ነገር ስለሆነ ከሸይጧን ነው፦
5፥90 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የሚያሰክር መጠጥ ቁማርም ጣዖታትም አዝላምም ከሰይጣን ሥራ የኾኑ እርኩስ ብቻ ናቸው፡፡ እርኩስን ራቁትም ልትድኑ ይከጀላልና፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّمَا الْخَمْرُ وَالْمَيْسِرُ وَالْأَنصَابُ وَالْأَزْلَامُ رِجْسٌ مِّنْ عَمَلِ الشَّيْطَانِ فَاجْتَنِبُوهُ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ
5፥91 ሰይጣን የሚፈልገው በሚያሰክር መጠጥና በቁማር በመካከላችሁ ጠብንና ጥላቻን ሊጥል፤ አላህን ከማውሳት እና ከስግደትም ሊያግዳችሁ ብቻ ነው፡፡ ታዲያ እናንተ ከእነዚህ ተከልካዮች ናችሁን ተከልከሉ፡፡ إِنَّمَا يُرِيدُ الشَّيْطَانُ أَن يُوقِعَ بَيْنَكُمُ الْعَدَاوَةَ وَالْبَغْضَاءَ فِي الْخَمْرِ وَالْمَيْسِرِ وَيَصُدَّكُمْ عَن ذِكْرِ اللَّهِ وَعَنِ الصَّلَاةِ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّنتَهُونَ

"ነቢዝ" نَّبِيذ ማለት ከዘምባባ እና ከወይን ፍሬ የሚጠጣ ጭማቂ"juice" ነው፥ እርሱን መጠጣት ሐላል ነው፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 36, ሐዲስ 81
ዐብደላህ ኢብኑ ቡረይዳህ አባቱ እንዳለው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ "በኮዳ በስተቀር ከነቢዝ የሚዘጋጅ ነገር እንዳትጠጡ ከልክያችሁ ነበር፥ ግን አሁን በሁሉም ሰፍነግ መጠጣት ትችላላችሁ። ነገር ግን አስካሪ መጠጥ እንዳትጠጡ። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ بُرَيْدَةَ، عَنْ أَبِيهِ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ نَهَيْتُكُمْ عَنِ النَّبِيذِ إِلاَّ فِي سِقَاءٍ فَاشْرَبُوا فِي الأَسْقِيَةِ كُلِّهَا وَلاَ تَشْرَبُوا مُسْكِرًا ‏”‏

ይህ ጭማቂ ከሁለት ቀናት አሊያም ከሦስት ቀናት በኃላ ስለሚቆመጥጥ ሙሥኪር ይሆናል፥ ሙሥኪር መጠጣት ሐራም ነው። አይደለም ኸምር ጠጪው ይቅርና ቀጂውን፣ ሻጩንም፣ ገዢውንም፣ ጨማቂውን፣ አስጨማቂውን፣ ተሸካሚውን እና የሚሸከሙለትንም ሁሉ ተጠያቂዎች ናቸው፦
ሡነንን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 27, ሐዲስ 6:
ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር”ረ.ዐ.” እንዳስተላለፈው የአላህ መልክተኛም”ﷺ” አሉ፦ ”አላህ ኸምርን ጠጪውን፣ ቀጂውን፣ ሻጩንም፣ ገዢውንም፣ ጨማቂውን፣ አስጨማቂውን፣ ተሸካሚውን እና የሚሸከሙለትንም ሁሉ ረግሟቸዋል"። أَنَّهُمَا سَمِعَا ابْنَ عُمَرَ، يَقُولُ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ لَعَنَ اللَّهُ الْخَمْرَ وَشَارِبَهَا وَسَاقِيَهَا وَبَائِعَهَا وَمُبْتَاعَهَا وَعَاصِرَهَا وَمُعْتَصِرَهَا وَحَامِلَهَا وَالْمَحْمُولَةَ إِلَيْهِ ‏”‏
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 74, ሐዲስ 1:
ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር”ረ.ዐ.” እንደተረከው የአላህ መልክተኛም”ﷺ” አሉ፦ "የሚያሰክር ነገር ሁሉ ኸምር ነው፤ የሚያሰክር ነገር ሁሉ ሐራም ነው፡፡ በዱኒያህ ኸምርን የጠጣ እና በእሷም ላይ ዘውትሮ ሳይቶብት የሞተ ሰው በአኺራ የጀነቷን አይጠጣትም"። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عُمَرَ ـ رضى الله عنهما ـ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ مَنْ شَرِبَ الْخَمْرَ فِي الدُّنْيَا، ثُمَّ لَمْ يَتُبْ مِنْهَا، حُرِمَهَا فِي الآخِرَةِ ‏”‌‏.‏

አሏህ ከአስካሪ መጠጥ እና በአስካሪ መጠጥ ከሚመጣ ጥፋት ይጠብቀን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሪያእ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

107፥6 ለእነዚያ እነርሱ ይዩልኝ ባዮች ለኾኑት ወዮላቸው፡፡ ٱلَّذِينَ هُمْ يُرَآءُونَ

"ሪያእ" رِيَاء የሚለው ቃል "ራኣ" رَاءَى ማለትም "አሳየ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "እዩልኝ" ማለት ሲሆን መልካም ሥራን የሰዎችን ፊት ተከጅሎ ከተሠራ "ሪያእ" رِيَاء ይባላል፦
2፥264 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እንደዚያ ገንዘቡን ለሰዎች ማሳየት ሲል እንደሚሰጠውና በአላህና በመጨረሻውም ቀን እንደማያምነው ሰው ምጽዋቶቻችሁን በመመጻደቅ እና በማስከፋት አታበላሹ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تُبْطِلُوا صَدَقَاتِكُم بِالْمَنِّ وَالْأَذَىٰ كَالَّذِي يُنفِقُ مَالَهُ رِئَاءَ النَّاسِ وَلَا يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ማሳየት" ለሚለው ግሣዊ ስም የገባው ቃል "ሪያእ" رِيَاء መሆኑን ልብ አድርግ! መልካም ሥራን ለሰዎች ለማሳየት መሥራት "መን" ነው፥ "መን" مَنّ ማለት "መመጻደቅ" ማለት ነው። ያለመመጻደቅ የአሏህን ፊት ከጅለው መልካም ሥራ የሚሠሩ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው፥ በእነርሱም ላይ ፍርሃት የለባቸውም። እነርሱም አያዝኑም፦
2፥262 እነዚያ ገንዘቦቻቸውን በአላህ መንገድ የሚለግሱ ከዚያም የሰጡትን ነገር መመጻደቅን እና ማስከፋትን የማያስከትሉ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው፡፡ በእነርሱም ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነርሱም አያዝኑም፡፡ الَّذِينَ يُنفِقُونَ أَمْوَالَهُمْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ ثُمَّ لَا يُتْبِعُونَ مَا أَنفَقُوا مَنًّا وَلَا أَذًى ۙ لَّهُمْ أَجْرُهُمْ عِندَ رَبِّهِمْ وَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ
49፥17 በመሥለማቸው በአንተ ላይ ይመጻደቃሉ። «በእሥምናችሁ በእኔ ላይ አትመጻደቁ! ይልቁንም አላህ ወደ እምነት ስለ መራችሁ ይመጸደቅባችኋል። እውነተኞች ብትኾኑ መመጻደቅ ለአላህ ነው» በላቸው፡፡ يَمُنُّونَ عَلَيْكَ أَنْ أَسْلَمُوا ۖ قُل لَّا تَمُنُّوا عَلَيَّ إِسْلَامَكُم ۖ بَلِ اللَّهُ يَمُنُّ عَلَيْكُمْ أَنْ هَدَاكُمْ لِلْإِيمَانِ إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ

መመጻደቅ የአሏህ ሐቅ ብቻ ነው፥ "ሥራዬን ዓይታችሁ ተፈኩር እና ተደቡር አርጉ" ማለት የእርሱ መብት ብቻ ነው። ሪያእ የኢኽላስ ተቃራኒ ነው፥ "ኢኽላስ" إِخْلَاص‎ የሚለው ቃል "አኽለሶ" أَخْلَصَ‎ ማለትም "አጠራ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን እውነት ለማንገሥ ሐሠትን ለማርከሥ የሚደረግ “መተናነስ” ወይም ከሙገሳ እና ከወቀሳ ነጻ ሆኖ ለአሏህ ውዴታ የሚደረግ “ማጥራት” ማለት ነው። እዩልኝ ባዮች ወዮላቸው የተባለባቸው ሥራቸው ሺርክ ለሆነ ነው፦
107፥4 ወዮላቸው ለሰጋጆች፡፡ فَوَيْلٌۭ لِّلْمُصَلِّينَ
107፥6 ለእነዚያ እነርሱ ይዩልኝ ባዮች ለኾኑት ወዮላቸው፡፡ ٱلَّذِينَ هُمْ يُرَآءُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ይዩልኝ ባዮች" ለሚለው የገባው ቃል "ዩራኡን" يُرَآءُون ሲሆን በሪያእ ድርጊት የተሰማሩ ሰዎች አመላካች ነው፥ "ሺርኩል ኸፊይ" شِّرْكُ الْخَفِي ማለት "ድብቁ ሺርክ" ማለት ሲሆን ሪያእ በሰው ልብ ውስጥ ተደብቆ ያለ ድብቁ ሺርክ ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 4344
አቢ ሠዒድ እንደተናገረው፦ "ስለ መሢሑል ደጃል በተወያየንበት ጊዜ የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” ወደ እኛ መጥተው፦ "ከመሢሑል ደጃል የባሰ የምፈራላችሁን ነገር ልንገራችሁን? አሉን፥ እኛም አዎ አልን። እርሳቸውም፦ "አንድ ሰው ሶላት ሲቆምና በሰው ፊት ጥሩ አድርጎ ለሰው እንዲያይለት ማድረግ ድብቁ ሺርክ ነው። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ، قَالَ خَرَجَ عَلَيْنَا رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ وَنَحْنُ نَتَذَاكَرُ الْمَسِيحَ الدَّجَّالَ فَقَالَ ‏”‏ أَلاَ أُخْبِرُكُمْ بِمَا هُوَ أَخْوَفُ عَلَيْكُمْ عِنْدِي مِنَ الْمَسِيحِ الدَّجَّالِ ‏”‏ ‏.‏ قَالَ قُلْنَا بَلَى ‏.‏ فَقَالَ ‏”‏ الشِّرْكُ الْخَفِيُّ أَنْ يَقُومَ الرَّجُلُ يُصَلِّي فَيُزَيِّنُ صَلاَتَهُ لِمَا يَرَى مِنْ نَظَرِ رَجُلٍ ‏”‏ ‏.‏

"ሽርኩል አስገር" شِّرْكُ اَلْأَصْغَر ማለት "ትንሹ ሺርክ" ማለት ሲሆን በሰው ልብ ተደብቆ ያለ ድብቁ ሺርክ ሪያእ "ሽርኩል አስገር" شِّرْكُ اَلْأَصْغَر ነው፦
ቡሉጉል መራም መጽሐፍ 8 ሐዲስ 1035
መሕሙድ ለቢድ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ትንሹ ሺርክ የሆነውን ሪያእን እፈራላችኃለው"። وَعَنْ مَحْمُودِ بْنِ لَبِيدٍ ‏- رضى الله عنه ‏- قَالَ: قَالَ رَسُولُ اَللَّهِ ‏- صلى الله عليه وسلم ‏-{ إِنَّ أَخْوَفَ مَا أَخَافُ عَلَيْكُمْ اَلشِّرْكُ اَلْأَصْغَرُ: اَلرِّيَاءُ }

አሏህ ከሪያእ ይጠብቀን! መልካም ሥራዎቻችንን በኢኽላስ ይቀበለን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የጀናህ ኸምር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

32፥17 ይሠሩትም በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለእነርሱ የተደበቀላቸውን ጸጋ ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም፡፡ فَلَا تَعْلَمُ نَفْسٌ مَّا أُخْفِيَ لَهُم مِّن قُرَّةِ أَعْيُنٍ جَزَاءً بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ

“ጀናህ” جَنَّة የሚለው ቃል “ጀነ” جَنَّ ማለትም “ተሰወረ” ወይም “ተደበቀ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “ድብቅ” ወይም “ስውር” ማለት ነው፥ በጀነት ውስጥ ያለው ለሙሥሊሞች የተደበቀላቸውን ፀጋ ደግሞ ማንኛይቱም ነፍስ ስለማያውቅ ድብቅ እና ስውር ነው። በሐዲሰል ቁድሢይ ላይ የተዘጋጀው የጀነት ጸጋ ዓይን ዓይቶት፣ ጆሮ ሰምቶት፣ ልብ አስቦት የማያውቅ መሆኑ ተገልጿል፦
32፥17 ይሠሩትም በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለእነርሱ የተደበቀላቸውን ጸጋ ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም፡፡ فَلَا تَعْلَمُ نَفْسٌ مَّا أُخْفِيَ لَهُم مِّن قُرَّةِ أَعْيُنٍ جَزَاءً بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 123:
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ ነብዩ”ﷺ” እንዲህ ብለው አሉ፦ "አላህም እንዲህ አለ፦ እኔ ለደጋግ ባሮቼ ዓይን ዓይቶት የማያውቅ፣ ጆሮ ሰምቶት የማያውቅ እና በሰው ልቦና ውል ብሎ የማያውቅ ጸጋን አዘጋጅቻለው”። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ قَالَ اللَّهُ أَعْدَدْتُ لِعِبَادِي الصَّالِحِينَ مَا لاَ عَيْنٌ رَأَتْ، وَلاَ أُذُنٌ سَمِعَتْ، وَلاَ خَطَرَ عَلَى قَلْبِ بَشَرٍ ‏”

ስለዚህ በጀነት ውስጥ ያሉትን አሏህ ለባሮቹ ያዘጋጃቸው ፀጋዎች ዓይን ዓይቶት፣ ጆሮ ሰምቶት፣ ልብ አስቦት የማያውቅ ከሆነ ሙዝ፣ ዘንባባ፣ ወይን፣ ተምር የመሳሰሉት የስም መመሳሰል እንጂ ቅርጽና ይዘቱ አሊያም ጥፍጥናውና ጣዕሙ ከዚህ ዓለም ጋር አንድ አይደለም፥ ይህንን አምላካችን አሏህ እንዲህ ይለናል፦
47፥15 የዚያች ጥንቁቆች ተስፋ የተሰጧት ገነት “ምሳሌ” በውስጧ ሺታው ከማይለወጥ ውሃ ወንዞች ጣዕሙ ከማይለውጥ ወተትም ወንዞች ለጠጪዎች ሁሉ ጣፋጭ ከኾነች የወይን ጠጅም ወንዞች፤ ከተነጠረ ማርም ወንዞች አሉባት፤ ለእነሱም በውስጧ ከፍሬዎች ሁሉ በያይነቱ ከጌታቸው ምሕረትም አላቸው። مَّثَلُ الْجَنَّةِ الَّتِي وُعِدَ الْمُتَّقُونَ ۖ فِيهَا أَنْهَارٌ مِّن مَّاءٍ غَيْرِ آسِنٍ وَأَنْهَارٌ مِّن لَّبَنٍ لَّمْ يَتَغَيَّرْ طَعْمُهُ وَأَنْهَارٌ مِّنْ خَمْرٍ لَّذَّةٍ لِّلشَّارِبِينَ وَأَنْهَارٌ مِّنْ عَسَلٍ مُّصَفًّى ۖ وَلَهُمْ فِيهَا مِن كُلِّ الثَّمَرَاتِ وَمَغْفِرَةٌ مِّن رَّبِّهِمْ ۖ كَمَنْ هُوَ خَالِدٌ فِي النَّارِ وَسُقُوا مَاءً حَمِيمًا فَقَطَّعَ أَمْعَاءَهُمْ
2፥25 ከእርሷ ከፍሬ ዓይነት ሲሳይን በተመገቡ ቁጥር ፍሬዎችዋ ስለሚመሳሰሉ «ይህ ያ ከአሁን በፊት የተገመብነው ነው» ይላሉ፡፡ እርሱንም ተመሳሳይ ኾኖ ተሰጣቸው*፡፡ ۖ كُلَّمَا رُزِقُوا مِنْهَا مِن ثَمَرَةٍ رِّزْقًا ۙ قَالُوا هَـٰذَا الَّذِي رُزِقْنَا مِن قَبْلُ ۖ وَأُتُوا بِهِ مُتَشَابِهًا ۖ وَلَهُمْ فِيهَا أَزْوَاجٌ مُّطَهَّرَةٌ ۖ وَهُمْ فِيهَا خَالِدُونَ

“መሰል” مَثَل ማለት “ምሳሌ” ማለት ሲሆን እዚህ ላይ የተዘረዘሩት ውኃ፣ ወተት፣ የወይን ጠጅም፣ ማር፣ ፍሬዎች “ምሳሌ” ናቸው፥ ምክንያቱም የዚህ ዓለም ውኃ ሲቆይ ይሸታል፣ ወተት ሲቆይ ረግቶ ይቀየራል፣ ማርና ወይንም ጥፍጥናው ይሰለቻል። ነገር ግን የጀነት ውኃ፣ ወተት፣ የወይን ጠጅም፣ ማር፣ ፍሬዎች ግን የተለየ ነው፥ የዚህ ዓለም ወይን ከቆየ ይቆመጥጥና ያሰክራል። ነገር ግን የጀነት ወይን ጠጅ አያሰክርም፦
56፥19 ከእርሷ የራስ ምታት አያገኛቸውም፤ አይሰክሩምም። لَّا يُصَدَّعُونَ عَنْهَا وَلَا يُنزِفُونَ
37፥47 በእርሷ ዉስጥም ራስ ምታት የለባትም። እነርሱም ከእርሷ የሚሰክሩ አይደሉም። لَا فِيهَا غَوْلٌ وَلَا هُمْ عَنْهَا يُنزَفُونَ

"ከእርሷ የሚሰክሩ አይደሉም" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! ስካር ራስምታ ያመጣል ወይም ውድቅ ንግግር ያናግራል አሊያም ወንጀል ያሠራል፥ ጀነት ውስጥ ያለው ወይን ግን ራስምታት የለውም፣ ውድቅ ንግግር አያናግርም እና ወንጀልም አያሠራም። ምክንያቱም ምንም አልኮል የሌለበት “ንጹህ” የሆነ ነው፦
52፥23 በውስጧ መጠጥን ይሰጣጣሉ፤ በውስጧ ውድቅ ንግግር እና ወንጀልም የለም። يَتَنَازَعُونَ فِيهَا كَأْسًا لَّا لَغْوٌ فِيهَا وَلَا تَأْثِيمٌ
76፥21 ጌታቸውም ንጹህ የሆኑን መጠጥ ያጠጣቸዋል። رَبُّهُمْ شَرَابًا طَهُورًا
የመጨረሻው አንቀጽ ላይ "ንጹህ" ለሚለው ቃል የገባው "ጦሁር" طَهُور ሲሆን ይህም ከአልኮልነት ነጻ የሆነ የተጣራ ወይን መሆኑን ቁልጭ አርጎ ያሳያል፥ ይህ ምንም አልኮል የሌለበት ወይን "ረሒቅ" رَّحِيق ይባላል፦
83፥25 ተጣርቶ ከታተመ ጠጅ ይጠጣሉ። يُسْقَوْنَ مِن رَّحِيقٍ مَّخْتُومٍ

"ተጣርቶ" ለሚለው ቃል የገባው "ጦሁር" طَهُور ሲሆን ይህም ንጹህ ወይን መበረጃው "ካፉር" ነው፥ "ካፉር" كَافُور የሚለው ቃል "ከፈረ" كَفَّرَ ማለትም "ሸፈነ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ሽፍን" ማለት ነው፦
76፥5 በጎ አድራጊዎች መበረዣዋ ካፉርው ከሆነች ጠጅ ይጠጣሉ። إِنَّ الْأَبْرَارَ يَشْرَبُونَ مِن كَأْسٍ كَانَ مِزَاجُهَا كَافُورًا

ጀነት ውስጥ ያለው ወይን ዓይን ዓይቶት፣ ጆሮ ሰምቶት፣ ልብ አስቦት የማያውቅ ስለሆነ ካፉር ተብሏል፥ በተጨማሪም "ኸምር" خَمْرየሚለው ቃል "ኸመረ" خَمَرَ ማለትም "ሸፈነ" "ደበቀ" "ሰወረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ "ሽፍን" "ድብቅ" "ስውር" መሆኑ በራሱ የጀናህ ወይን ዓይን ዓይቶት፣ ጆሮ ሰምቶት፣ ልብ አስቦት የማያውቅ መሆኑን አመላካች ነው። እኅቶቻችን ከሚሰተሩበት ሒጃብ መካከል "ጉፍታ" እራሱ በቁርኣን "ኺማር" خِمَار ይባላል፦
24፥31 ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ ያጣፉ። وَلْيَضْرِبْنَ بِخُمُرِهِنَّ عَلَىٰ جُيُوبِهِنَّ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ጉፍታዎች" ለሚለው በብዜት የገባው ቃል "ኹሙር" خُمُر ሲሆን በነጠላ ደግሞ "ኺማር" خِمَار ነው፥ “ኺማር” خِمَار የሚለው ቃል ልክ እንደ “ኸምር” خَمْر ሥርወ-ቃሉ “ኸመረ” خَمَرَ ነው። ጉፍታ ራስን ስለሚሸፍን “ኺማር” خِمَار እንሚባል ሁሉ ጀነት ውስጥ ያለው ወይን ከሰው ዕውቀት የተደበቀ ስለሆነ "ኸምር" خَمْر ይባላል። በተመሳሳይ ይህ ወይን መበረጃው "ዘንጀቢል" زَنجَبِيل “እና "ተሥኒም" تَسْنِيم ነው፦
76፥17 በእርሷም መበረዣዋ ዘንጀቢል የሆነችን ጠጅ ይጠጣሉ። وَيُسْقَوْنَ فِيهَا كَأْسًا كَانَ مِزَاجُهَا زَنجَبِيلًا
83፥27 መበረዣውም ከተሥኒም ነው። وَمِزَاجُهُ مِن تَسْنِيمٍ

ሚሽነሪዎች፦ "እሺ የጀነት ወይን የማያሳክር ከሆነ እንዴት ጀነት ውስጥ ይኖራል?" ብለው ይጠይቃሉ፥ ምነው በእናንተ መንግሥተ ሰማይ ውስጥ የሚበላ ዛፍ እና የሚጠጣ ወይን የለም እንዴ? አንብቡት፦
ማቴዎስ 26፥29 ነገር ግን እላችኋለሁ በአባቴ መንግሥት ከእናንተ ጋር አዲሱን ወይን ፍሬ እስከምጠጣበት እስከዚያ ቀን ድረስ ከዛሬ ጀምሬ ከዚህ ከወይን ፍሬ አልጠጣም። But I say unto you, I will not drink henceforth of this fruit of the vine, until that day when I drink it new vine with you in my Father’s kingdom.
ራእይ 2፥7 ድል ለነሣው በእግዚአብሔር ገነት ካለው ከሕይወት ዛፍ እንዲበላ እሰጠዋለሁ።

በመንግሥተ ሰማይ ወይም በገነት መብላት እና መጠጣት ብቻ ሳይሆን መብል እና መጠጥ መኖሩ በራሱ ቁርኣንን ለመተቸት ሞራል እና ዐቅም ያሳጣችኃል። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የጣዖታውያን ዲን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

109፥6 ለእናንተ ሃይማኖታችሁ አላችሁ፡፡ ለእኔም ሃይማኖቴ አለኝ፡፡ لَكُمْ دِينُكُمْ وَلِيَ دِينِ

አምላካችን አሏህ ለነቢያች"ﷺ" "ለእናንተ ሃይማኖታችሁ አላችሁ፡፡ ለእኔም ሃይማኖቴ አለኝ" በል በማለት ለከሓዲዎች እንዲናገሩ አዟቸዋል፦
109፥1 በላቸው፦ "እናንተ ከሓዲዎች ሆይ! قُلْ يَا أَيُّهَا الْكَافِرُونَ
109፥6 ለእናንተ ሃይማኖታችሁ አላችሁ፡፡ ለእኔም ሃይማኖቴ አለኝ፡፡ لَكُمْ دِينُكُمْ وَلِيَ دِينِ

"ለእኔም ሃይማኖቴ አለኝ" ሲሉ ይህ ሃይማኖት ዲኑል ኢሥላም ነው፥ "ለእናንተ ሃይማኖታችሁ አላችሁ" ሲሉ ጣዖታውያኑ የነበራቸው ሃይማኖት ምንድን ነው? "ዲን" دِين የሚለው ቃል "ዳነ" دَانَ ማለትም "ፈረደ" "ደነገገ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ፍርድ" "ሕግ" ማለት ነው፦
1፥4 የፍርዱ ቀን ባለቤት ለኾነው፡፡ مَالِكِ يَوْمِ الدِّينِ
12፥76 አላህ ባልሻ ኖሮ በንጉሡ "ሕግ" ወንድሙን ሊይዝ አይገባውም ነበር፡፡ كَانَ لِيَأْخُذَ أَخَاهُ فِي دِينِ الْمَلِكِ إِلَّا أَن يَشَاءَ اللَّهُ

እነዚህ አናቅጽ ላይ "ፍርድ" "ሕግ" ለሚለው የገባው ቃል "ዲን" دِين መሆኑ ልብ አድርግ! ጣዖታውያን የነበራቸው ፍርድ እና ሕግ የሚያገኙት ከሸያጢን ነበር፦
6፥121 በእርሱም ላይ የአላህ ስም ካልተጠራበት ነገር አትብሉ፡፡ እርሱም በእርግጥ አመጽ ነው፡፡ ሰይጣናትም ወደ ወዳጆቻቸው በክትን በመብላት ይከራከሯችሁ ዘንድ ያሾከሹካሉ፡፡ ብትታዘዙዋቸውም እናንተ በእርግጥ አጋሪዎች ናችሁ፡፡ وَلَا تَأْكُلُوا مِمَّا لَمْ يُذْكَرِ اسْمُ اللَّهِ عَلَيْهِ وَإِنَّهُ لَفِسْقٌ ۗ وَإِنَّ الشَّيَاطِينَ لَيُوحُونَ إِلَىٰ أَوْلِيَائِهِمْ لِيُجَادِلُوكُمْ ۖ وَإِنْ أَطَعْتُمُوهُمْ إِنَّكُمْ لَمُشْرِكُونَ

ሸያጢን ለወዳጆቻቸው መገለጥ በመስጠት በክትን እንዲበሉ ይነግሯቸው ነበር፥ እነዚህም ወዳጆቻቸው ጣዖታውያን ናቸው። "ያሾከሹካሉ" ለሚለው የገባው ቃል "ለዩሑነ" لَيُوحُونَ ሲሆን ሥርወ-ቃሉ "አውሓ" أَوْحَىٰٓ ማለትም "ገለጠ" ነው፥ የጣዖታውያኑ ዲን ከሸያጢን የተገለጠ ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 121
ዐብደሏህ ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ "ጥቂት ሰዎች ወደ ነቢዩ"ﷺ" በመምጣት፦ "የአሏህ መልእክተኛ ሆይ! የገደልነውን መብላት እንችላለን፥ ነገር ግን አሏህ የገደለውን የማንበላው ለምንድን ነው? አሉ፥ አሏህም፦ "በእርሱም ላይ የአላህ ስም ካልተጠራበት ነገር አትብሉ" የሚለውን አንቀጽ "ብትታዘዙዋቸውም እናንተ በእርግጥ አጋሪዎች ናችሁ" እስከሚለው አወረደ"። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ أَتَى أُنَاسٌ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم فَقَالُوا يَا رَسُولَ اللَّهِ أَنَأْكُلُ مَا نَقْتُلُ وَلاَ نَأْكُلُ مَا يَقْتُلُ اللَّهُ فَأَنْزَلَ اللَّهُ ‏(‏ وَلَا تَأْكُلُوا مِمَّا لَمْ يُذْكَرِ اسْمُ اللَّهِ عَلَيْهِ)‏ إِلَى قَوْلِهِ ‏:‏ ‏(‏وَإِنْ أَطَعْتُمُوهُمْ إِنَّكُمْ لَمُشْرِكُونَ ‏)‏ ‏.‏

ጣዖታውያኑ "በክትን ብሉ" የሚል ሑክም የሚቀበሉት ከሸያጢን ስለሆነ የጣዖታውያኑ ዲን ይህ ነው፥ ጣዖታውያኑ ከሸያጢን የሚቀበሉትን ሑክም የሚታዘዝ ሰው በአሏህ ሐቅ ማሻረክ ስለሆነ ጣዖታውያኑን የሚታዘዝ በእርግጥ "ሙሽሪክ" مُشْرِك ነው። ታዲያ ዛሬ ያሉትን ምዕራባውያን "ወንድ እና ወንድ፣ ሴት እና ሴት፣ ወላጅ እና ልጅ መጋባት ሐላል ነው" ሲሉ እሺ ማለት አያስከፍርምን? ይህስ መገለጥ ከሸያጢን አይደለምን? "ሰው እና እንስሳ መጋባት ሐላል ይሁንልን" የሚል ወረቀት በፓርላማ ገብቷል፥ ከጸደቀ ደግሞ ምን ዓይነት ፍጥረት ሊፈጠር እንደሚችል አስቡት! ይህ ጣጉት ቤተሰብ ለማፈራረስ የተነሳ ነው፦
42፥21 ከሃይማኖት አላህ በእርሱ ያልፈቀደውን ለእነርሱ የደነገጉ ተጋሪዎች ለእነርሱ አሏቸውን? أَمْ لَهُمْ شُرَكَاءُ شَرَعُوا لَهُم مِّنَ الدِّينِ مَا لَمْ يَأْذَن بِهِ اللَّهُ

"ሸሪክ" شَرِيك ማለት "ተጋሪ" ማለት ነው፥ የሸሪክ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ሹረካእ" شُرَكَاء ሲሆን "ተጋሪዎች" ማለት ነው፥ አሏህ በእርሱ ያልፈቀደውን ነገር ሐላል ማድረግ ለእነርሱ የደነገጉ በአላህ ሐቅ ላይ ተጋሪዎች አሏቸው። "የደነገጉ" ለሚለው የገባው ቃል "ሸረዑ" شَرَعُوا ሲሆን ሸሪዓህ መደንገጋቸው የሚያሳይ ቃል ነው፥ ለዚህ ነው "ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው" ነው ያለው። አሏህ ከዲሞክራሲያህ ጣጉት ይጠብቀን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም