ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
69 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ሡጁድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

13፥15 በሰማያት እና በምድርም ያሉት በውድ እና በግድ ለአላህ ይሰግዳሉ። وَلِلَّهِ يَسْجُدُ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ طَوْعًا وَكَرْهًا

"ሡጁድ" سُّجُود የሚለው ቃል "ሠጀደ" سَجَدَ ማለትም "ሰገደ" "ታዘዘ" "ተገዛ" ከሚለው ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ስግደት" "መታዘዝ" "መገዛት" ማለት ነው፥ ፍጥረት በሁለት መልኩ ለአሏህ ይሰግዳል። አንዱ በግድ ሲሆን ይህ የግዴታ ስግደት "ሡጁዱ አት-ተክውኒይ" سُّجُود التَكْو۟نِي ይባላል፥ ሁለተኛው ደግሞ በውድ ሲሆን ይህ የውዴታ ስግደት "ሡጁዱ አት-ተሽሪዒይ" سُّجُود التَشْرِعِي ይባላል፦
13፥15 በሰማያት እና በምድርም ያሉት በውድ እና በግድ ለአላህ ይሰግዳሉ። وَلِلَّهِ يَسْجُدُ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ طَوْعًا وَكَرْهًا
3፥83 በሰማያት እና በምድር ያሉ በውድ እና በግድ ለእርሱ የታዘዙ ወደ እርሱም የሚመለሱ ሲኾኑ ከሓዲዎች ከአላህ ሃይማኖት ሌላን ይፈልጋሉን? أَفَغَيْرَ دِينِ اللَّهِ يَبْغُونَ وَلَهُ أَسْلَمَ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ طَوْعًا وَكَرْهًا وَإِلَيْهِ يُرْجَعُونَ

"ይሰግዳሉ" የሚለው "የታዘዙ" በሚል ተለዋዋጭ ቃል መምጣቱን ልብ አድርግ! "ከርህ" كَرْه ማለት ደግሞ "ግዳጅ" ማለት ሲሆን "ጠውዕ" طَوْع ማለት "ፈቃደኝነት" ማለት ነው። ይህንን ነጥብ በነጥብ ማየት ይቻላል፦

ነጥብ አንድ
"ሡጁዱ አት-ተክውኒይ"
"ተክውኒይ" تَكْو۟نِي ማለት "ኹነት" ማለት ሲሆን የሚሆን ማንኛውም ፍጥረት ያለ ምርጫው እና ያለ ፈቃዱ ለአሏህ ይታዘዛል፥ ለምሳሌ ፀሐይ እና ጨረቃ፣ ከዋክብት በትእዛዙ የተገሩ ናቸው፦
7፥54 ፀሐይን እና ጨረቃን፣ ከዋክብትን "በትእዛዙ የተገሩ ሲኾኑ" ፈጠራቸው፡፡ وَالشَّمْسَ وَالْقَمَرَ وَالنُّجُومَ مُسَخَّرَاتٍ بِأَمْرِهِ

ፀሐይ እና ጨረቃ፣ ከዋክብት አሏህ ላወጣው ለተፈጥሮ ሕግ ይታዘዛሉ፥ ይህ የግዴታ መታዘዝን ሲያመለክት በግዴታ ለአሏህ ይሰግዳሉ፦
22፥18 አላህ በሰማያት ያለው እና በምድርም ያለው፣ ፀሐይ እና ጨረቃ፣ ከዋክብት፣ ተራራዎች፣ ዛፎች፣ ተንቀሳቃሾች፣ ከሰዎች ብዙዎችም ለእርሱ የሚሰግዱለት መሆኑን አታውቁምን? أَلَمْ تَرَ أَنَّ اللَّهَ يَسْجُدُ لَهُ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَمَن فِي الْأَرْضِ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ وَالنُّجُومُ وَالْجِبَالُ وَالشَّجَرُ وَالدَّوَابُّ وَكَثِيرٌ مِّنَ النَّاسِ

የብዙዎቻችን መረዳት ሡጁድ ሲባል ቂያም፣ ሩኩዕ እና ኸር ያለበት ብቻ ስለሚመስለን ፀሐይ እና ጨረቃ፣ ከዋክብት ጎንበስ ቀና እያሉ ይሰግዳሉ እንዴ? ብለን እንጠይቃለን፥ ቅሉ ግን ሡጁድ መታዘዝን እና መገዛትን የሚያመለክት ቃል ሆኖ ይገባል። ስለዚህ መላው ፍጥረት ነጻ ፈቃድ እና ምርጫ በሌለበት ጉዳት ላይ ተገዶ ለአሏህ ታዛዥ ነው፥ ለምሳሌ ሰው ለመወለድ፣ ለመሞት፣ ለመተኛት፣ ለመራብ፣ ለመጠማት፣ ለመብላት፣ ለመጠጣት፣ ለመሽናት፣ ለመጸዳዳት ሕግ በግድ ይታዘዛል።

ነጥብ ሁለት
"ሡጁዱ አት-ተሽሪዒይ"
"ተሽሪዒይ" تَشْرِعِي ማለት "ሕግጋት" ማለት ሲሆን ከአሏህ ወደ ነቢያቱ የሚወርድ መመሪያ፣ መርሕ፣ ሕግ፣ ሥርዓት ነው፦
21፥73 ወደ እነርሱም መልካም ሥራዎችን መሥራትን፣ ሶላትንም መስገድን፣ ዘካንም መስጠትን አወረድን፡፡ وَأَوْحَيْنَا إِلَيْهِمْ فِعْلَ الْخَيْرَاتِ وَإِقَامَ الصَّلَاةِ وَإِيتَاءَ الزَّكَاةِ ۖ

ይህ በነቢያቱ የሚወርደው የውዴታ ስግደት፦
"ቂያም" قِيَام ማለትም "መቆም"
"ሩኩዕ" رُكوع ማለትም "ማጎንበስ"
"ኸር" خَرّ ማለትም "መደፋት" ያካትታል፦
22፥77 እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ! በስግደታችሁ አጎንብሱ፣ በግንባራችሁም ተደፉ፣ ጌታችሁንም አምልኩ፣ በጎንም ነገር ሥሩ፣ ልትድኑ ይከጀልላችኋልና፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا ارْكَعُوا وَاسْجُدُوا وَاعْبُدُوا رَبَّكُمْ وَافْعَلُوا الْخَيْرَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ ۩

ይህንን ስግደት በነጻ ፈቃድ እና ምርጫ መስገድ አለመስገድ የሚቻል ሲሆን የውዴታ እና የፈቃደኝነት ስግደት ነው።
ይህንን ነጥብ ይዘን ወደ ባይብል እንደ ውኃ ፈሳሽ፥ እንደ እንግዳ ደራሽ ዘው ብለን ብንገባ ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት፣ ብርሃን ሁሉ፣ ሰማየ ሰማያት፣ ውኃ ተሥቢሕ ያደርጋሉ፦
መዝሙር 148፥3 ፀሐይ እና ጨረቃ አመስግኑት! ከዋክብት እና ብርሃን ሁሉ አመስግኑት!። سَبِّحِيهِ يا شَمسُ، وَأنتَ يا قَمَرُ سَبِّحْهُ يا كُلَّ النُّجُومِ المُتَلألِئَةِ، سَبِّحِيهِ
መዝሙር 148፥4 ሰማየ ሰማያት አመስግኑት! የሰማያት በላይም ውኃ። أيَّتُها السَّماواتُ وَالمِياهُ مِنْ فَوقُ، سَبِّحِيهِ

"ተሥቢሕ" تَسْبِيح ማለት ደግሞ "ተስብሖት" ማለት ነው፥ "አመስግኑት" የሚለው የግዕዙ ትእዛዋዊ ግስ እራሱ “ይሴብሕዎ” ሲሆን “ሠበሐ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ነው። የሚያቀርቡት "ስብሐት" ደግሞ "ተስብሖት" ይባላል፦
መዝሙር 148፥3 ይሴብሕዎ ፀሓይ ወወርኅ! ይሴብሕዎ ኵሉ ከዋክብት ወብርሃን።
መዝሙር 148፥4 ይሴብሕዎ ሰማያተ ሰማያት ወማይኒ ዘመልዕልተ ሰማያት።

ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት፣ ብርሃን ሁሉ፣ ሰማየ ሰማያት፣ ውኃ መታዘዛቸው ከገረማችሁ ስብሐት ማቅረባቸው ያስደምማኃል? ምሁራን፦ “ስህተት ለማረም ብሎ ስህተት መሥራት ትልቅ ስህተት ነው” ይላሉ። የእኛን ጥያቄ ለማስረሳት የሚመጡ አዳዲስ ጥያቄዎች እራሳቸው በማንጸሪያ ሲፈተሹ ጥያቄዎቹ ተከረባብተው እራሳቸው ላይ እንደሚዘፈዘፉ አያጤኗቸውም፥ በአንድ ራስ ሁለት ምላስ፤ በአንድ ቢላ ሁለት የሚከላ ለያዙት ለእነርሱ ሐቁ እንዲህ ፈጦና ገጦ ሲመጣ ብስል እና ጥሬ ይለያሉ ብለን እናምናለን። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዓይናቸውን ቁልጭ ቁልጭ እያረጉ ሚድያ ላይ በአደባባይ ለሚታዩ እኅቶች እንዲህ ብላችሁ ንገሯቸው፦
24፥31 ለምእምናትም ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ፡፡ وَقُل لِّلْمُؤْمِنَاتِ يَغْضُضْنَ مِنْ أَبْصَارِهِنَّ
33፥33 በቤቶቻችሁም ውስጥ እርጉ፡፡ እንደ ፊተኛይቱ መሃይምነት ጊዜ መገለጥም በማጌጥ አትገለጡ፡፡ وَقَرْنَ فِي بُيُوتِكُنَّ وَلَا تَبَرَّجْنَ تَبَرُّجَ الْجَاهِلِيَّةِ الْأُولَىٰ

በተለይ የሰውነት ቅርፅ የሚያሳይ ልብስ እየለበሱ መታየት አደገኛ ፈሣድ ነው።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom
ጎግ ማጎግ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

21፥96 የእጁጅ እና መእጁጅም እነርሱ ከየተረተሩ ሁሉ የሚንደረደሩ ሲኾኑ ግድባቸው በተከፈተች ጊዜ። حَتَّىٰ إِذَا فُتِحَتْ يَأْجُوجُ وَمَأْجُوجُ وَهُم مِّن كُلِّ حَدَبٍ يَنسِلُونَ

"ጎግ" አንድ ግለሰብ ሳይሆን ልክ እንደ "አጼ" "ቄሳር" "ፈርዖን" ወደፊት ከሰሜን ለሚመጣው የሰሜን ንጉሥ፣ አለቃ እና መሪ የማዕረግ ስም ሲሆን "ማጎግ" ደግሞ የጎግ መንግሥት፣ ግዛት፣ ሕዝብ ነው፥ ጋሜር፣ ማጎግ፣ ቶቤል፣ ሞሳሕ የያፌት ልጅ ናቸው፦
ዘፍጥረት 10፥2 "የያፌት ልጆች ጋሜር፥ ማጎግ፥ ማዴ፥ ያዋን፥ ይልሳ፥ ቶቤል፥ ሞሳሕ፥ ቴራስ ናቸው"።
1 ዜና 1፥5 "የያፌት ልጆች፤ ጋሜር፥ ማጎግ፥ ማዴ፥ ያዋን፥ ቶቤል፥ ሞሳሕ፥ ቴራስ"።

የጎግ ሕዝብ "ማጎግ" የት እንደጠፉ እና እንደተሰወሩ ታሪክ በዝምታ ያለፋቸው የሲታያን ሕዝብ ናቸው፥ የማጎግ ንጉሥ ጎግ የሞሳሕ እና የቶቤል ዋነኛ አለቃ ነው፦
ሕዝቅኤል 38፥2 የሰው ልጅ ሆይ! ፊትህን በጎግ ላይ እና በማጎግ ምድር ላይ፥ በሞሳሕ እና በቶቤል ዋነኛ አለቃ ላይ አቅናበት፥ ትንቢትም ተናገርበት።

"ሞሳሕ" የያፌት ልጅ ሲሆን የአሁኗ "ሞስኮ(ሩሲያ) ናት፥ "ቶቤል" ደግሞ የያፌት ልጅ ሲሆን የአሁኗ "ጂዮርጂያ" ናት። ጎግ የሁለቱ አገራት ዋነኛ አለቃ ሆኖ ከማጎግ ሕዝብ ይወጣል፥ ከጎግ ጋር ፋርስ፣ ኩሽ፣ ፉጥን ለማገዝ ይነሳሉ፦
ሕዝቅኤል 38፥5 ፋርስ፣ ኩሽ፣ ፉጥን ከእነርሱ ጋር ጋሻ እና የራስ ቍርን የለበሱትን ሁሉ አወጣለው።

"ፋርስ(ኤላም) የሴም ልጅ ሲሆን የአሁኗ "ኢራን" ናት፣ "ኩሽ" የካም ልጅ ሲሆን የአሁኗ "ኢትዮጵያ እና ሱዳን" ናቸው፣ "ፉጥ" የካም ልጅ ሲሆን የአሁኗ "ሊቢያ" ናት፥ በተጨማሪም ከጎግ ጋር ጋሜር እና ቴርጋማን ለማገዝ ይነሳሉ፦
ሕዝቅኤል 38፥6 ጋሜርንና ጭፍሮቹን ሁሉ፥ በሰሜን ዳርቻም ያለውን የቴርጋማን ቤት እና ጭፍሮቹን ሁሉ፥ ብዙዎችንም ሕዝቦች ከአንተ ጋር አወጣለሁ።

"ጋሜር" የያፌት ልጅ ሲሆን የአሁኗ "ኢራቅ" ወይም "ኩዌት" ናቸው፥ "ቴርጋሜን" ደግሞ የጋሜር ልጅ ሲሆን የአሁኗ "አርሜንያ" ናት፥ ጎግ የእነዚህ ሁሉ አለቃ ይሆናል፦
ሕዝቅኤል 38፥7 አንተ እና ወደ አንተ የተሰበሰቡ ወገኖችህ ሁሉ ተዘጋጁ፥ አንተም ራስህን አዘጋጅተህ አለቃ ሁናቸው።

በመጨረሻው ዘመን ጎግ ከተለያየ አገራት ወደ ፍልስጤም ምድር ወደ ተሰበሰቡት ይገባል፦
ሕዝቅኤል 38፥8 ከብዙ ዘመንም በኋላ ትፈለጋለህ፤ በኋለኛውም ዘመን፥ የዘላለም ባድማ በነበሩ በእስራኤል ተራሮች ላይ ከብዙ ሕዝብ ውስጥ ወደ ተሰበሰበች፥ ከሰይፍ ወደ ተመለሰች ምድር ትገባለህ፤ እርስዋም ከሕዝብ ውስጥ ወጥታለች ሁሉም ሳይፈሩ ይቀመጡባታል።

የኦርቶዶክስ አዋልድ መጽሐፍት መጽሐፈ ዜና እስክንድር እና መጽሐፈ ንህብ ላይ አንድ ታላቅ ንጉሥ የማጎግ ሕዝቦችን ነሐስ አቅልጦ ዘጋባቸው እና እግዚአብሔር እንደ ሰወራቸው ይናገራል። ስለ ዘጋባቸው ንጉሥ ስለ ዙል ቀርነይን ይመልከቱ፦ https://tttttt.me/Wahidcom/2608

የማጎግ ሕዝቦችን በአንድ ወቅት ይኖሩ የነበረ እና አሁን ላይ የት እንዳሉ የማይታወቅ ሲሆን ቅሉ ግን በመጨረሻው ዘመን ከተሰወሩበት ይወጣሉ፦
ሕዝቅኤል 38፥9 አንተም ትወጣለህ፥ እንደ ዐወሎ ነፋስም ትመጣለህ፤ አንተና ጭፍሮችህ ሁሉ ከአንተም ጋር ብዙ ሕዝብ ምድርን እንደ ደመና ትሸፍናላችሁ።

"ትወጣለህ" የሚለው ይሰመርበት! ሲመጡ ምድርን እንደ ደመና ይሸፍናሉ። የማጎግ ሕዝብ ሙሉ ለሙሉ ቢጠፉ ኖሮ "ከሰሜን ዳርቻ ከስፍራችሁ ትመጣላችሁ" ባልተባለ ነበር፦
ሕዝቅኤል 38፥15 አንተም፥ ከአንተም ጋር ብዙ ሕዝብ ሁላቸው በፈረሶች ላይ የተቀመጡ፥ ታላቅ ወገንና ብርቱ ሠራዊት፥ ከሰሜን ዳርቻ ከስፍራችሁ ትመጣላችሁ።

ጎግ ማጎግ ስፍራቸው ሰሜን ሲሆን ግን የት እንዳሉ አሁን ላይ ማንም አያውቅም። የሰሜን ንጉሥ ሴልድሲያስ፣ አንጥያኮስ፣ ካሊኒክስ እያለ የማጎግ ሕዝብ ንጉሥ ጎግ የሰሜኑ ንጉሥ ሲሆን የደቡብ ንጉሥ ደግሞ በጥሊሞስ ሶተር፣ በጥሊሞስ ፊላዴልፈስ፣ በጥሊሞስ ኤጵፋኒዎስ እያለ በፍጻሜ ዘመን ከግብጽ የሚነሳ ንጉሥ አለ፥ በፍጻሜ ዘመንም የደቡብ ንጉሥ ከሰሜኑ ንጉሥ ከጎግ ጋር ይዋጋል፦
ዳንኤል 11፥40 በፍጻሜ ዘመንም የደቡብ ንጉሥ ከእርሱ ጋር ይዋጋል፤ የሰሜንም ንጉሥ ከሰረገሎችና ከፈረሰኞች ከብዙም መርከቦች ጋር እንደ ዐውሎ ነፋስ ይመጣበታል፤ ወደ አገሮችም ይገባል፥ ይጐርፍማል፥ ያልፍማል።
የሰሜንም ንጉሥ ጎግ ከከባድ የትራንስፓት ጋር በፍጥነት በደቡብ ንጉሥ ላይ ይመጣበታል፥ ጎግ ወደ አገሮችም ይገባል፣ ይጐርፍማል፣ ያልፍማል፣ ወደ መልካሚቱም ምድር ወደ በይቱል መቅዲሥ ይገባል፦
ዳንኤል 11፥41-42 ወደ መልካሚቱም ምድር ይገባል፥ ብዙ አገሮችም ይወድቃሉ፤ ነገር ግን ኤዶምያስና ሞዓብ ከአሞንም ልጆች የበለጡት ከእጁ ይድናሉ። እጁን በአገሮች ላይ ይዘረጋል፥ የግብፅም ምድር አታመልጥም።

ጎግ ሲመጣ ብዙ አገሮችም ይወድቃሉ፥ ነገር ግን ኤዶምያስ፣ ሞዓብ፣ አሞን የሚባሉት ዐረብ አገራት ከእጁ ይድናሉ። እጁን በአገሮች ላይ ይዘረጋል፥ የግብፅም ምድር አታመልጥም። በወርቅ፣ በብርም መዝገብ ላይ፣ በከበረችም በግብፅ ዕቃ ሁሉ ላይ ይሠለጥናል፥ የልብያ እና የኩሽ ሰዎችም ይከተሉታል፦
ዳንኤል 11፥43 በወርቅና በብርም መዝገብ ላይ፥ በከበረችም በግብፅ ዕቃ ሁሉ ላይ ይሠለጥናል፤ የልብያና የኩሽ ሰዎችም ይከተሉታል።

ልብያ ፉጥ ስትሆን ኩሽ ሱዳን እና ኢትዮጵያ ናቸው፥ ጎግ ብዙ ሰዎችንም ይገድል ዘንድና ፈጽሞ ያጠፋ ዘንድ በታላቅ ቍጣ ከተሰወረበት ይወጣል፦
ዳንኤል 11፥44 ከምሥራቅና ከሰሜን ግን ወሬ ያውከዋል፤ ብዙ ሰዎችንም ይገድል ዘንድና ፈጽሞ ያጠፋ ዘንድ በታላቅ ቍጣ ይወጣል።

ጎግ ንጉሣዊ ድንኳኑንም በሜድትራኒያ ባሕር እና በከበረው በቅዱስ ተራራ በበይቱል መቅዲሥ መካከል ይተክላል፥ ወደ ፍጻሜው ግን ይመጣል። ማንም አይረዳውም፥ ጎግ በያዕቁብ ምድር ላይ በመጣ ጊዜ የፈጣሪ መቅሰፍት በመዓት ይመጣና ይጠፋል፦
ዳንኤል 11፥45 ንጉሣዊ ድንኳኑንም በባሕር እና በከበረው በቅዱስ ተራራ መካከል ይተክላል፥ ወደ ፍጻሜው ግን ይመጣል፥ ማንም አይረዳውም።
ሕዝቅኤል 38፥18 በዚያም ቀን ጎግ በእስራኤል ምድር ላይ በመጣ ጊዜ መቅሠፍቴ በመዓቴ ይመጣል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ሕዝቅኤል 38፥22 በቸነፈርና በደም እፈርድበታለሁ፤ ዶፍም የበረዶም ድንጋይ እሳትና ድኝም በእርሱና በጭፍሮቹ ከእርሱም ጋር ባሉ በብዙ ሕዝብ ላይ አዘንባለሁ።

በጎግ እና ከእርሱም ጋር ባሉ በብዙ ሕዝብ ማለትም በተከተሉት በሩሲያ፣ በኢራን፣ በኢራቅ፣ በኩዌት፤ በሱዳን፣ በኢትዮጵያ፣ በሊብያ ወዘተ... ዶፍ፣ የበረዶም ድንጋይ፣ እሳት እና ድኝ ይወርድባቸውና ይጠፋሉ። ስለ የእጁጅ እና መእጁጅ በኢሥላም ያለውን ትምህርት ይህንን ሊንክ በማስፈንጠር ይመልከቱ፦ https://tttttt.me/Wahidcom/2612

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የአጎት እና የአክስት ልጅ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

16፥116 በአላህም ላይ ውሸትን ልትቀጣጥፉ ምላሶቻችሁ በሚመጥኑት ውሸት «ይህ የተፈቀደ ነው፥ ይህም እርም ነው» አትበሉ፡፡ وَلَا تَقُولُوا لِمَا تَصِفُ أَلْسِنَتُكُمُ الْكَذِبَ هَـٰذَا حَلَالٌ وَهَـٰذَا حَرَامٌ لِّتَفْتَرُوا عَلَى اللَّهِ الْكَذِبَ

የአባት ወንድም የሆነ አጎት "ዐም" عَمّ ሲባል የአባት እኅት የሆነች አክስት "ዐማህ" عَمَّة ትባላለች፥ የእናት ወንድም የሆነ አጎት(ሹማ) ደግሞ "ኻል" خَال ሲባል የእናት እኅት የሆነች አክስት(ሹሜ) "ኻላህ" خَالَة ትባላለች። በኢሥላም የአጎት ልጅ ሆነ የአክስት ልጅ ማግባት ሐላል ነው፦
33፥50 እነዚያንም ከአንተ ጋር የተሰደዱትን የአጎትህን ሴቶች ልጆች፣ የአክስቶችህንም ሴቶች ልጆች፣ የየሹማህንም ሴቶች ልጆች፣ የየሹሜዎችህንም ሴቶች ልጆች ማግባትን ለአንተ ፈቅደንልሃል፡፡ يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ إِنَّا أَحْلَلْنَا لَكَ أَزْوَاجَكَ اللَّاتِي آتَيْتَ أُجُورَهُنَّ وَمَا مَلَكَتْ يَمِينُكَ مِمَّا أَفَاءَ اللَّهُ عَلَيْكَ وَبَنَاتِ عَمِّكَ وَبَنَاتِ عَمَّاتِكَ وَبَنَاتِ خَالِكَ وَبَنَاتِ خَالَاتِكَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ፈቅደናል" ለሚለው የገባው የግሥ መደብ "አሕለይና" أَحْلَلْنَا ነው፥ የስም መደቡ "ሐላል" حَلَال ሲሆን "የተፈቀደ" ማለት ነው። ሚሽነሪዎች፦ "የአጎት ልጅ ወይም የአክስት ልጅ ማግባት ለምን ተፈቀደ? ብለው እርርና ምርር በማለት ሲንጨረጨሩ እና ሲንተከተኩ ይታያል፥ ለመሆኑ የአጎት ልጅ ወይም የአክስት ልጅ ማግባት ከመነሻው መቼ ክልክል ሆኖ ያውቃል? ባይብል ላይ "ዘመድ" በሚለው ፈርጅ ውስጥ የአጎት ልጅ ወይም የአክስት ልጅ ማግባት አልተካተተም፦
ዘሌዋውያን 18፥6 ከእናንተም ማንም ሰው ኃፍረተ ሥጋውን ይገልጥ ዘንድ ወደ "ዘመዱ" ሁሉ አይቅረብ! እኔ ያህዌህ ነኝ።

ዘሌዋውያን 18፥7-18 ላይ እናት፣ የእንጀራ አባት እናት፣ እኅት፣ ልጅና የልጅ ልጅ፣ አክስት፣ የአጎት ሚስት፣ ምራት(የልጅ ሚስት)፣ የወንድም ሚስት፣ የሚስት እኅት ማግባት ተከልክሏል፥ ቅሉ ግን የአጎት ልጅ ወይም የአክስት ልጅ ማግባት የተከለከለበት ጥቅስ ከዘፍጥረት እስከ ራእይ በባትሪ ብትፈልጉ አታገኙም። ከዚያ ይልቅ የአጎት ልጅ ማግባት የተፈቀደ ነው፥ እንበረም የአጎቱን ልጅ ዮካብድን አግብቶ አሮን እና ሙሴን ወልደዋል፦
ዘጸአት 6፥20 እንበረምም የአጎቱን ልጅ ዮካብድን አገባ፥ አሮን እና ሙሴንም ወለደችለት።

ለሙሴ ኦሪት ከተሰጠ በኃላም ቢሆን በኦሪት ውስጥ የአጎት ልጅ ወይም የአክስት ልጅ ማግባት ከመፈቀዱም አልፎ የተወደደ ሆኗል፥ የሰለጰዓድ ልጆች ማህለህ፣ ቲርጻ፣ ዔግላ፣ ሚልካ፣ ኑዓ ፈጣሪ አዟቸው ከአጎቶቻቸው ልጆች ጋር ተጋብተዋል፦
ዘኍልቍ 36፥10-11 ያህዌህም ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ የሰለጰዓድ ሴቶች ልጆች አደረጉ። የሰለጰዓድ ልጆች ማህለህ፣ ቲርጻ፣ ዔግላ፣ ሚልካ፣ ኑዓ "ከአባታቸው ወንድሞች ልጆች ጋር ተጋቡ"።

"ከአባታቸው ወንድሞች ልጆች ጋር ተጋቡ" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! ይህንን ጥቅስ አፍጦና አፋጦ፤ አግጦና አንጋጦ ስታነቡ ቆሌ ተገፎ እና ቆሽት አሮ፦ "ሰማይ ተንዶ ሊናጫነኝ ነው፥ ምድር ተከፍቶ ሊውጠኝ ነው" እንደምትሉ እሙን ነው። አሏህ ያላለውን በምትመጥኑት ውሸት «ይህ የተፈቀደ ነው፥ ይህም እርም ነው» አትበሉ፦
16፥116 በአላህም ላይ ውሸትን ልትቀጣጥፉ ምላሶቻችሁ በሚመጥኑት ውሸት «ይህ የተፈቀደ ነው፥ ይህም እርም ነው» አትበሉ፡፡ وَلَا تَقُولُوا لِمَا تَصِفُ أَلْسِنَتُكُمُ الْكَذِبَ هَـٰذَا حَلَالٌ وَهَـٰذَا حَرَامٌ لِّتَفْتَرُوا عَلَى اللَّهِ الْكَذِبَ

ስለዚህ "ሰባት ቤት ድረስ ማግባት ክልክል ነው" የሚለው መርሕ ሰው ሠራሽ ሕግ ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ጁሙዓህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

62፥9 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በጁሙዓህ ቀን ለሶላት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ፡፡ መሸጥንም ተዉ፡፡ ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነወ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا نُودِيَ لِلصَّلَاةِ مِن يَوْمِ الْجُمُعَةِ فَاسْعَوْا إِلَىٰ ذِكْرِ اللَّهِ وَذَرُوا الْبَيْعَ ۚ ذَٰلِكُمْ خَيْرٌ لَّكُمْ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ

"ጁሙዓህ" جُمُعَة የሚለው ቃል "ጀመዐ" جَمَعَ ማለትም "ሰበሰበ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ስብስብ" ማለት ነው፥ ይህ ቀን አደም የተፈጠረበት፣ ወደ ጀናህ የገባበት፣ ከጀናህ የወጣበት፣ የሞተበት እና በተጨማሪም ትንሣኤ የሚቆምበት ቀን ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 7, ሐዲስ 26
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "መልካም ቀን ፀሐይ ከወጣችበት የጁሙዓህ ቀን ነው፥ በዚያ ቀን አደም ተፈጠረ። በዚያ ቀን ወደ ጀናህ ገብቷል፥ ከእርሷም በዚያ ቀን ወጥቷል"። أَنَّهُ سَمِعَ أَبَا هُرَيْرَةَ، يَقُولُ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ خَيْرُ يَوْمٍ طَلَعَتْ عَلَيْهِ الشَّمْسُ يَوْمُ الْجُمُعَةِ فِيهِ خُلِقَ آدَمُ وَفِيهِ أُدْخِلَ الْجَنَّةَ وَفِيهِ أُخْرِجَ مِنْهَا
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 4, ሐዲስ 1
አቡ ሁራይራህ እንደተረከው፦ “ነቢዩ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ”መልካም ቀን ፀሐይ ከወጣችበት የጁሙዓህ ቀን ነው፥ በዚያ ቀን አደም ተፈጠረ፣ በዚያ ቀን ወደ ጀነት ገብቷል፥ ከጀነት በዚያ ቀን ወጥቷል፣ ሰዓቲቱ በጁሙዓህ ቀን እንጂ አትቆምም”*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ خَيْرُ يَوْمٍ طَلَعَتْ فِيهِ الشَّمْسُ يَوْمُ الْجُمُعَةِ فِيهِ خُلِقَ آدَمُ وَفِيهِ أُدْخِلَ الْجَنَّةَ وَفِيهِ أُخْرِجَ مِنْهَا وَلاَ تَقُومُ السَّاعَةُ إِلاَّ فِي يَوْمِ الْجُمُعَةِ ‏”‏
ሡነን አቢ ዳዉድ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 658
አውሥ ኢብኑ አውሥ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "ከቀናችሁ በላጩ ቀን የጁሙዓህ ቀን ነው፥ በዚያ ቀን አደም ተፈጠረ፥ በዚያ ቀን ሞተ። በዚያ ቀንም መለከት ይነፋል፥ ሁሉ በድንጋጤ ይሞታል"። عَنْ أَوْسِ بْنِ أَوْسٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّ مِنْ أَفْضَلِ أَيَّامِكُمْ يَوْمَ الْجُمُعَةِ فِيهِ خُلِقَ آدَمُ وَفِيهِ قُبِضَ وَفِيهِ النَّفْخَةُ وَفِيهِ الصَّعْقَةُ

"አዛን" أَذَان የሚለው ቃል "አዚነ" أَذِنَ‎ ማለትም “ጠራ” ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ጥሪ" ማለት ነው፥ ለሶላት ወደ አሏህ የሚጣራው ተጣሪ “ሙአዚን” مُؤَذِّن ይባላል። አምላካችን አላህ፦ “በጁሙዓህ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ” ብሎናል፦
62፥9 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በጁሙዓህ ቀን ለሶላት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ፡፡ መሸጥንም ተዉ፡፡ ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነወ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا نُودِيَ لِلصَّلَاةِ مِن يَوْمِ الْجُمُعَةِ فَاسْعَوْا إِلَىٰ ذِكْرِ اللَّهِ وَذَرُوا الْبَيْعَ ۚ ذَٰلِكُمْ خَيْرٌ لَّكُمْ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ

"ኹጥባህ" خُطْبَة የሚለው ቃል "ኸጦበ" خَطَبَ ማለትም "ሰበከ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ስብከት"sermon" ማለት ነው፥ በጁሙዓህ ኹጥባህ የሚያረገው ሰው "ኻጢብ" خَاطِب ይባላል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 7, ሐዲስ 44
አቡ ዑመር እንደተረከው፦ የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" በቆሙበት ኹጥባህ በጁሙዓህ ቀን ያረጉ ነበር፣ ከዚያ ይቀመጣሉ፣ ከዚያ ይቆሙና ያረጋሉ። ልክ በአሁኑ ጊዜ ሙሥሊሞች እንደሚያደርጉት ማለት ነው"። عَنِ ابْنِ عُمَرَ، قَالَ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَخْطُبُ يَوْمَ الْجُمُعَةِ قَائِمًا ثُمَّ يَجْلِسُ ثُمَّ يَقُومُ ‏.‏ قَالَ كَمَا يَفْعَلُونَ الْيَوْمَ ‏.‏

"ዙሁር" ظُهْر‎ ማለት "ቀትር" ማለት ሲሆን ሶላቱ አዝ-ዝሁር ባለ አራት ረክዓት ሲሆን የጁሙዓህ ቀን ግን ሁለት ረከዓህ ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 5, ሐዲስ 261
ዑመር እንደተረከው፥ እንዲህ አለ፦ "ሶላቱ አሥ-ሠፈር ሁለት ረክዓህ ነው፣ የጁሙዓህ ሶላት ሁለት ረክዓህ ነው፣ የዒድ ሶላት ሁለት ረከዓህ ነው"። عَنْ عُمَرَ، قَالَ صَلاَةُ السَّفَرِ رَكْعَتَانِ وَالْجُمُعَةُ رَكْعَتَانِ وَالْعِيدُ رَكْعَتَانِ .‏

የጁሙዓህ ቀን የእረፍት ቀን አይደለም። "ዓርብ" የሚለው ቃል እራሱ "ረበዐ" ማለትም "ሰበሰበ" "አጠናቀቀ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መሰብሰቢያ" "ማጠናቀቂያ" ማለት ነው፥ ይህም ቀን ስድስተኛ ቀን ነው። "ቅዳሜ" ማለት "ቀዳሚት" ማለት ሲሆን የጥንቷና የቀደመችው ሰንበት ናት፥ "ሠብት" سَّبْت ማለት "ዕረፍት" ማለት ነው። "ሰንበት" የሚለው የግዕዙ ቃል በራሱ "እረፍት" ማለት ነው፥ ስለዚህ ይህቺ ሰንበት ሰባተኛዋ ቀን ናት። "ሠብዓህ" سَبْعَة ማለት እራሱ "ሰባት" ማለት ነው፥ በዚህ በሰባተኛው ቀን ሰንበት የተደረገው በእስራኤል ልጆች ብቻ ነው፦
16፥124 ሰንበት የተደረገው በእነዚያ በእርሱ በተለያዩበት ሰዎች ላይ ብቻ ነው፡፡ ጌታህም በትንሣኤ ቀን ይለያዩበት በነበሩት ነገር በመካከላቸው በእርግጥ ይፈርዳል፡፡ إِنَّمَا جُعِلَ السَّبْتُ عَلَى الَّذِينَ اخْتَلَفُوا فِيهِ ۚ وَإِنَّ رَبَّكَ لَيَحْكُمُ بَيْنَهُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ فِيمَا كَانُوا فِيهِ يَخْتَلِفُونَ

ሰንበት የተደረገው በእስራኤል ልጆች ብቻ ከሆነ "ጁሙዓህ የሙሥሊም ሰንበት ነው" የሚል ዲስኩር ቅጥፈት ነው፥ ምክንያቱም የጁሙዓህ ሶላት ተሰግዶ ሲያልቅ ሁሉም ሰው ወደ ሥራ ይበተናል እንጂ እንደ ሰንበት አያርፍም፦
62፥10 ሶላቲቱም በተፈጸመች ጊዜ በምድር ላይ ተበተኑ፡፡ ከአላህም ችሮታ ፈልጉ፡፡ አላህንም በብዙ አውሱ፡፡ ልትድኑ ይከጀላልና፡፡ فَإِذَا قُضِيَتِ الصَّلَاةُ فَانتَشِرُوا فِي الْأَرْضِ وَابْتَغُوا مِن فَضْلِ اللَّهِ وَاذْكُرُوا اللَّهَ كَثِيرًا لَّعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ

አምላካችን አሏህ ለሶላት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ እርሱ ማውሳት የምንሄድ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ተውሒድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

21፥108 «ያ ወደ እኔ የሚወረደው፦ "አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው" ማለትን ነው፥ ታዲያ እናንተ ፍጹም ታዛዦች ናችሁን?» በላቸው"፡፡ قُلْ إِنَّمَا يُوحَىٰ إِلَيَّ أَنَّمَا إِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّسْلِمُونَ

ኢሥላም የትምህርቱ ጭብጥ እና የመልእክት አንኳር ተውሒድ ነው፥ አህሉል ኪታብን ስናገኛቸው ቅድሚያ ወደ ተውሒድ እሳቤ እንጠራቸዋለን። ይህ የተውሒድ እሳቤ "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ” لَا إِلٰهَ إِلَّا اللّٰه ነው፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 24 ሐዲስ 1
“ኢብኑ ዐባሥ"ረ.ዐ." እንዳስተላለፈው ነቢዩ”ﷺ” ሙዓዝን"ረ.ዐ." ወደ የመን በላኩ ጊዜ እንዲህ አሉ፦ "ከአሏህ በቀር አምላክ እንደሌለ እና እኔም የአሏህ መልእክተኛ መሆኔን እንዲመሰክሩ ጥራቸው"። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما ـ أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم بَعَثَ مُعَاذًا ـ رضى الله عنه ـ إِلَى الْيَمَنِ فَقَالَ ‏ "‏ ادْعُهُمْ إِلَى شَهَادَةِ أَنْ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ، وَأَنِّي رَسُولُ اللّٰه
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 97 ሐዲስ 2
“ኢብኑ ዐባሥ እንዳስተላለፈው ነቢዩ”ﷺ” ሙዓዝን ወደ የመን በላኩ ጊዜ እንዲህ አሉ፦ ”ከመጽሐፍ ሰዎች የሆኑ ሕዝቦች ታገኛለህ፡፡ በቅድሚያ የላቀውን አሏህን "አንድ ነው" እንዲሉ ትጠራቸዋለህ” ። يَقُولُ سَمِعْتُ ابْنَ عَبَّاسٍ، يَقُولُ لَمَّا بَعَثَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم مُعَاذًا نَحْوَ الْيَمَنِ قَالَ لَهُ ‏ "‏ إِنَّكَ تَقْدَمُ عَلَى قَوْمٍ مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ فَلْيَكُنْ أَوَّلَ مَا تَدْعُوهُمْ إِلَى أَنْ يُوَحِّدُوا اللَّهَ تَعَالَى

እዚህ ሐዲስ ላይ “ዩወሐዱ” يُوَحِّدُوا የሚለው የግስ መደብ ይሰመርበት! “ዋሒድ” وَٰحِد የሚለው ቃል "ዋሐደ" وَٰحَدَ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "አንድ"one" ማለት ነው፥ "ተውሒድ" تَوْحِيد ማለት ደግሞ "አንድ-ነት"one-ness" ወይም "አሐዳዊነት"Monotheism" ማለት ነው፦
21፥108 «ያ ወደ እኔ የሚወረደው፦ "አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው" ማለትን ነው፥ ታዲያ እናንተ ፍጹም ታዛዦች ናችሁን?» በላቸው"፡፡ قُلْ إِنَّمَا يُوحَىٰ إِلَيَّ أَنَّمَا إِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّسْلِمُونَ

"አንድ" ለሚለው ቃል የገባው ቃል “ዋሒድ” وَٰحِد መሆኑ አንባቢ ልብ አድርግ! ስለዚህ "ተውሒድ" የሚለው ቃል "ዋሒድ" በሚለው ቃል "ኢሥቲንባጥ" اِسْتِنْبَاطْ ሲደረግ ቁርኣን ላይም አለ ማለት ነው። "አሏህ አንድ ነው" ብሎ የሚያምን “ሙዋሒድ” مُوَٰحِد ማለትም "አሐዳዊ"Monotheist" ይባላል፥ "ተውሒድ" تَوْحِيد የሚለውን ቃል ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ተጠቅመውታል፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 39, ሐዲስ 25
ጃቢር እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "አንዳንድ "የተውሒድ ባለቤቶች" የሆኑ ሰዎች ፍም እስኪሆኑ ድረስ በእሳት ይቀጣሉ፥ ከዚያም የአሏህ ምሕረት ይደርሳቸውና ከእሳቱ ይወጣሉ"። عَنْ جَابِرٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ يُعَذَّبُ نَاسٌ مِنْ أَهْلِ التَّوْحِيدِ فِي النَّارِ حَتَّى يَكُونُوا فِيهَا حُمَمًا ثُمَّ تُدْرِكُهُمُ الرَّحْمَةُ فَيُخْرَجُونَ

የተውሒድ ባለቤቶች እስካላሻረኩ ድረስ አህሉል ጀናህ ናቸው፥ ቅሉ ግን ከሺርክ ውጪ ያሉትን ወንጀሎች ንስሓ እስካልገቡ ድረስ ለሥራቸው ተመጣጣኝ ቅጣት ተቀብለው ወደ ጀነት ይገባሉ፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 113
አቡ ዘር እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ጂብሪል ወደ እኔ መጥቶ እንዲህ ሲል አበሰረኝ፦ "ማንም ምንም ነገር በአሏህ ላይ ያላሻረከ ወደ ጀነናህ ይገባል። እኔም፦ "ቢሰርቅም እና ቢያመነዝርም? ብዬ ጠየኩት። እርሱም፦ "ቢሰርቅም እና ቢያመነዝርም" አለኝ"*። عَنِ الْمَعْرُورِ، قَالَ سَمِعْتُ أَبَا ذَرٍّ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ أَتَانِي جِبْرِيلُ فَبَشَّرَنِي أَنَّهُ مَنْ مَاتَ لاَ يُشْرِكُ بِاللَّهِ شَيْئًا دَخَلَ الْجَنَّةَ ‏"‌‏.‏ قُلْتُ وَإِنْ سَرَقَ وَإِنْ زَنَى قَالَ ‏"‏ وَإِنْ سَرَقَ وَإِنْ زَنَى
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 40, ሐዲስ 33
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "አንዳንድ የተውሒድ ባለቤቶች የሆኑ ሰዎች ከእሳት ይወጣሉ፥ ወደ ጀነት ይገባሉ"። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم أَنَّهُ قَالَ ‏"‏ سَيَخْرُجُ قَوْمٌ مِنَ النَّارِ مِنْ أَهْلِ التَّوْحِيدِ وَيَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ ‏"‏ ‏

"ተውሒድ" የሚለው ቃል ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ የለም" የሚሉ ሚሽነሪዎች ምንተ ሐፍረታቸው ሲገለጥ ተመልከቱ! "ሥላሴ" የሚለው ቃል ግን ባይብል ላይ እንደሌለ የክርስትና ምሁራን ይስማማሉ። እኛም ጥያቄአችን "ሥላሴ" የሚለው ቃል ባይብል ላይ አለ ወይ? ሳይሆን "ሥላሴ" የሚለው ቃል የወከለው አሳብ አለ ወይ? የሚል ነው፥ አሳቡ፦ "አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ናቸው" እና "አንዱ አምላክ ሦስት አካላት አሉት" የሚል ሲሆን ይህ እሳቤ ባይብል ላይ የለም። "ሥላሴ" የሚለው ቃል "ሠለሠ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ሦስት-ነት" ማለት ነው፥ የስም መደቡ "ሥሉስ" ማለትም "ሦስት" ነው። "አምላክ በአካል ሦስት ነው" የሚለው ይቅርና "ሦስት" የሚለው ቃል አምላክ አካባቢ ዝር ብሎ አያውቅም፥ ሥላሴ ሰው በማመኑ የሚድነበት በመካዱ የሚጠፋበት ትምህርት ቢሆን ኖሮ ከነቢያት ወይም ከሐዋርያት መካከል፦ "አምላክ አንድ ነው" ባሉበት አፋቸው ሳት ብሏቸው እንኳን "አምላክ ሦስት ነው" ብለው ያስተምሩ ነበር።
እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! «ሦስት ነው» አትበሉም! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አሏህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፦
4፥171 «ሦስት ነው» አትበሉም! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ وَلَا تَقُولُوا ثَلَاثَةٌ ۚ انتَهُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا اللَّهُ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ

አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የዓላማ አንድነት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥80 መልክተኛውን የሚታዘዝ ሰው በእርግጥ አላህን ታዘዘ፡፡ مَّن يُطِعِ الرَّسُولَ فَقَدْ أَطَاعَ اللَّهَ

አንድ ጊዜ እኔ አንዱን ሰው፦ "ኢየሱስ እኔ አምላክ ነኝ አምልኩኝ" ያለበትን ጥቅስ አሳየን ብዬ ስጠይቀው፥ እርሱም፦ "አንተም፦ "ኢየሱስ "እኔ አምላክ አይደለሁም አታምልኩኝ" ያለበትን ጥቅስ አሳየን ብሎ አረፈው። እኔም በመቀጠል፦ "ኢየሱስ "እኔ አምላክ አይደለሁም አታምልኩኝ" ያለበትን ጥቅስ ባይገኝ ኢየሱስ አምላክ መሆኑን እና መመለኩን ያሳያልን? ብዬ ጠየኩት፥ እርሱም አዳልጦት "አዎ" አለኝ። እኔም በመቀጠል፦ "ስለዚህ የእምነት አባት አብርሃም "እኔ አምላክ አይደለሁም አታምልኩኝ" አላለም፤ አለማለቱ ግን አብርሃም አምላክ ለመሆን እና ለመመለክ መስፈርት ነውን? ስለው ተለጉሞ ይህንን ጥቅስ ጠቀሰልኝ፦
ዮሐንስ 10፥30 እኔ እና አብ አንድ ነን። ἐγὼ καὶ ὁ Πατὴρ ἕν ἐσμεν.

ብዙ ጊዜ ክርስቲያኖች "ለኢየሱስ አምላክነት ድምዳሜ ያደርሰናል" ብለው የሚጠቅሳቸው ጥቅሶች ለእኔ ኢየሱስ አምላክ አለመሆን የሚያሳዩ ናቸው። "ኤጎ" ἐγὼ ማለት "እኔ" ማለት ሲሆን ኢየሱስ የራሱ እኔነት ያለው ማንነት መሆኑን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፥ "ፓቴር" Πατὴρ ማለት "አብ" "አባት" "አስገኝ" ማለት ሲሆን አብ "እኔ" ከሚለው ማንነት የተለየ ለመሆኑ "ካይ" καὶ ማለትም "እና" የሚል አያያዥ መስተጻምር ይጠቀማል። "እኔ" የሚለው ኢየሱስ እና አብ ሁለት የተለያዩ ማንነቶች መሆናቸው ለማሳየት "ኤስሜን" ἐσμεν ማለትም "ነን" የሚል የብዜት አያያዥ ግሥ ይጠቀማል፥ "እኔ አብ ነኝ"("ኤጎ ኤይሚ ሆ ፓቴር" ἐγὼ εἰμί ὁ Πατὴρ) ማለት እና "እኔ እና አብ አንድ ነን"("ኤጎ ካይ ሆ ፓቴር ሄን ኤስሜን" ἐγὼ καὶ ὁ Πατὴρ ἕν ἐσμεν) ማለት ሁለት የተለያየ ትርጉም አለው። ስለዚህ "ኢየሱስ አብ ወይም አምላክ ነው" ለሚል ሙግት "ነን" ማስረጃ አይሆንም፥ "ሄን" ἕν ማለት "አንድ" ማለት ሲሆን የአብን እና የኢየሱስን የዓላማ አንድነት ለማሳየት የገባ እንጂ የመለኮት አንድነት ለማሳየት የገባ በፍጹም አይደለም፦
ዮሐንስ 17፥11 ቅዱስ አባት ሆይ እነዚህን የሰጠኸኝን እንደ እኛ አንድ እንዲሆኑ በስምህ ጠብቃቸው። Πάτερ ἅγιε, τήρησον αὐτοὺς ἐν τῷ ὀνόματί σου ᾧ δέδωκάς μοι, ἵνα ὦσιν ἓν καθὼς ἡμεῖς.

እዚህ አንቀጽ ላይ "እነዚህ" የሚለው አሥራ ሁለቱን ሐዋርያት ሲሆን አሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ከሌሎች ሰዎች አንድ የሆኑት በማንነት አሊያም በምንነት ሳይሆን የዓላማ አንድነት ነው፥ ምክንያቱም በማንነት አሥራ ሁለት ሰዎች ሲሆኑ በምንነት ደግሞ ከሌሎች ሰዎች ጋር "ሰው" ስለሆኑ አንድ ናቸው። ቅሉ ግን ከዓለም ተመርጠው አንድ ያረጋቸው ይህ አንድነት ልክ እንደ አብ እና ወልድ አንድነት ስለሆነ ኢየሱስ "እንደ እኛ አንድ እንዲሆኑ" በማለቱ የሐዋርያት አንድነት የመለኮት ሳይሆን የዓላማ እንደሆነ ሁሉ የአብ እና የወልድ አንድነት የዓላማ አንድነት ነው፥ "ካቶስ" καθώς የሚለው ተውሳከ ግሥ "እንደ" ማለት ሲሆን የሐዋርያት አንድነት "እንደ" አብ እና ወልድ አንድነት ወይም የአብ እና የወልድ አንድነት "እንደ" ሐዋርያት አንድነት እንደሆነ ቁልጭ እና ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው። የሚገርመው ሐዋርያት "አንድ" የተባሉበት ገላጭ ቅጽል በተመሳሳይ "ሄን" ἓν ነው፥ መቼም ሐዋርያት አሥራ ሁለት ሰዎች ሆነው ሳሉ ጨፍልቀን "አንድ መለኮት" ናቸው አንልም። "የሰጠኸኝን በስምህ ጠብቃቸው" ሲል በጎቹን አብ ጠባቂ መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን ወልድ "በስምህ እኔ እጠብቃቸው ነበር" ሲል ወልድ በአብ ትእዛዝ ይጠብቅ ስለነበር ነው፦
ዮሐንስ 17፥12 ከእነርሱ ጋር በዓለም ሳለሁ የሰጠኸኝን በስምህ እኔ እጠብቃቸው ነበር።
ዮሐንስ 10፥28-29 ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም። የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፥ ከአባቴም እጅ ሊነጥቃቸው ማንም አይችልም።

"ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም" የወልድን እረኛ መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን "ከአባቴም እጅ ሊነጥቃቸው ማንም አይችልም" የአብን ጥበቃ የሚያሳይ ነው፥ ይህን ካለ በኃላ "እኔ እና አብ አንድ ነን" በማለት ዓላማቸው አንድ እንደሆነ ያስረዳል። "የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል" ሲል ከሁሉም የሚበልጠው አብ ለወልድ በጎቹን የሰጠው እንጂ ከራሱ የራሱ አልነበሩም፦
ዮሐንስ 17፥6 ከዓለም ለሰጠኸኝ ሰዎች ስምህን ገለጥሁላቸው። የአንተ ነበሩ ለእኔም ሰጠሃቸው።
ከዓለም መርጦ ለኢየሱስ የሰጠው አሥራ ሁለቱ ሐዋርያት የአብ ነበሩ ለወልድ እንዲንከባከባቸው ሰጣቸው፥ ወልድ በአምላኩ ኃይል እና ስም መንጋውን ስለሚጠብቅ አምላኩ እረኛ አርጎ አቁሞታል፦
ሚክያስ 5፥4 እርሱም ይቆማል፥ በያህዌህም ኃይል በአምላኩ በያህዌህ ስም ግርማ መንጋውን ይጠብቃል።
ሕዝቅኤል 34፥23 በላያቸውም አንድ እረኛ አቆማለሁ እርሱም ያሰማራቸዋል፥ እርሱም ባሪያዬ ዳዊት ነው፤ ያሰማራቸዋል እረኛም ይሆናቸዋል።

አብ የሚጠብቀው በራሱ ስም ሲሆን ወልድ ግን መልእክተኛ ስለሆነ የሚጠብቀው በራሱ ስም ሳይሆን በአምላኩ ስም ነው፥ እዚህ አንቀጽ ላይ "ዳዊት" የተባለው የሰሎሞን አባት ሳይሆን የሚመጣው መሢሕ ነው።

ሌላው ተመሳሳይ የሰዋስው አወቃቀር ጳውሎስ እና አጵሎስ ሁለት የተለያዩ ሰዎች ሲሆኑ በወንጌል የዓላማ አንድነት ነበራቸው፥ የሚተክል ጳውሎስ እና የሚያጠጣ አጵሎስ በመለኮት ሳይሆን በዓላማ አንድ ናቸው፦
1 ቆሮንቶስ 3፥6 እኔ ተከልሁ አጵሎስም አጠጣ ነገር ግን እግዚአብሔር ያሳድግ ነበር።
1 ቆሮንቶስ 3፥8 የሚተክል እና የሚያጠጣ አንድ ናቸው። ὁ φυτεύων δὲ καὶ ὁ ποτίζων ἕν εἰσιν,

እዚህ አንቀጽ ላይ "ናቸው" ለሚለው የገባው የሦስተኛ መደብ አያያዥ ግሥ "ኤይሲን" εἰσιν ጳውሎስ እና አጵሎስ ሁለት ማንነቶች መሆናቸው እንደሚያሳይ ሁሉ "ነን" ለሚለው የገባው የመጀመሪያ መደብ አያያዥ ግሥ "ኤስሜን" ἐσμεν ደግሞ ወልድ እና አብ ሁለት ማንነቶች መሆናቸውን ያሳያል፥ ስለዚህ የሚተክል ጳውሎስ እና የሚያጠጣ አጵሎስ በመለኮት ሳይሆን በዓላማ አንድ እንደሆኑ ሁሉ ወልድን የፈጠረ አብ እና በአብ የተፈጠረ ወልድ በዓላማ አንድ ናቸው። እግዚአብሔር እና ለሄኖክ የተገለጠለት መልአክ አንድ ናቸው፦
መጽሐፈ ሄኖክ 16፥39 ከእኔ ጋር የሚኖር ከእግዚአብሔር ጋር አንድነት ያለው መልአኩም፦ "እነዚህ ሁለቱ አውሬዎች በእግዚአብሔር ገናነነት ተጠብቀው የእግዚአብሔር መቅሠፍቱ በክ እንዳታደርጋቸው ይመገቡ ዘንድ የተዘጋጁ ናቸው" አለኝ ።

"ከእግዚአብሔር ጋር አንድነት ያለው መልአኩ" ስለተባለ እግዚአብሔር እና መልአኩ በመለኮት አንድ አይደሉም፥ ባይሆን መልአኩ ከእግዚአብሔር እየሰማ የሚናገር ፍጡር ነው። በተመሳሳይ ወልድ ከአብ እየሰማ እንጂ ከራሱ ምንም ስለማይናገር ከአብ ጋር በዓላማ አንድ ናቸው፦
ዮሐንስ 14፥10 እኔ የምነግራችሁን ቃል ከራሴ አልናገረውም።
ዮሐንስ 14፥24 የምትሰሙትም ቃል የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም።
ዮሐንስ 12፥49 እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና፤ ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ።
ዮሐንስ 7፥16 ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ፥ እንዲህም አላቸው፦ ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከእኔ አይደለም።

የተላከው ኢየሱስ የላከውን መልእክት እንጂ ከራሱ ምንም ካላስተማረ በእርግጥም ኢየሱስ እና የላከው በዓላማ አንድ ስለሆኑ መልእክተኛው ኢየሱስን የሚታዘዝ የላከውን አንድ አምላክ ታዘዘ፦
4፥80 መልክተኛውን የሚታዘዝ ሰው በእርግጥ አላህን ታዘዘ፡፡ مَّن يُطِعِ الرَّسُولَ فَقَدْ أَطَاعَ اللَّهَ

ኢየሱስን መልእክተኛ አድርጎ መልእክት የሰጠውን እና የላከውን አንዱን አምላክ አሏህን በብቸኝነት እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። አሏህን ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሹሩጡል ዒባዳህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

28፥50 እሺ ባይሉህም የሚከተሉት ዝንባሌዎቻቸውን ብቻ መኾኑን ዕወቅ፡፡ فَإِن لَّمْ يَسْتَجِيبُوا لَكَ فَاعْلَمْ أَنَّمَا يَتَّبِعُونَ أَهْوَاءَهُمْ

“ዒባዳህ” عِبَادَة የሚለው ቃል “ዓበደ” عَبَدَ ማለትም “አመለከ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “አምልኮ” ማለት ነው። "ሸርጥ" شَرْط የሚለው ቃል "ሸረጠ" شَرَطَ ማለትም "ሰፈረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መስፈርት" ማለት ነው፥ የሸርጥ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ሹሩጥ" شُرُوط ነው። በጥቅሉ "ሹሩጡል ዒባዳህ" شُرُوط الْعِبَادَة ማለት "የአምልኮ መስፈርቶች" ማለት ነው፥ ሹሩጡል ዒባዳህ የሚባሉት ኢማን፣ ኢኽላስ እና ኢትባዕ ናቸው። እነዚህን ነጥብ በነጥብ እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
"ኢማን"
"ኢማን" إِيمَٰن የሚለው ቃል "አሚነ" أَمِنَ ማለትም "አመነ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "እምነት" ማለት ነው፥ ያለ እምነት የተሠራ ማንኛውም መልካም ሥራ በአኺራ ተቀባይነት የለውም፦
24፥39 እነዚያም የካዱት ሰዎች መልካም ሥራዎቻቸው በበረሃ ሜዳ እንዳለ ሲሪብዱ የጠማው ሰው "ውኃ ነው" ብሎ እንደሚያስበው በመጣውም ጊዜ ምንም ነገር ኾኖ እንደማያገኘው ነው፡፡ وَالَّذِينَ كَفَرُوا أَعْمَالُهُمْ كَسَرَابٍ بِقِيعَةٍ يَحْسَبُهُ الظَّمْآنُ مَاءً حَتَّىٰ إِذَا جَاءَهُ لَمْ يَجِدْهُ شَيْئًا وَوَجَدَ اللَّهَ عِندَهُ فَوَفَّاهُ حِسَابَهُ ۗ وَاللَّهُ سَرِيعُ الْحِسَابِ
14፥18 የእነዚያ በጌታቸው የካዱት ሰዎች ምሳሌ መልካም ሥራዎቻቸው በነፋሻ ቀን ነፋስ በእርሱ እንደ በረታችበት አመድ ነው፡፡ በሠሩት ሥራ በምንም ላይ ሊጠቀሙ አይችሉም፡፡ ይህ እርሱ ሩቅ ጥፋት ነው፡፡ مَّثَلُ الَّذِينَ كَفَرُوا بِرَبِّهِمْ ۖ أَعْمَالُهُمْ كَرَمَادٍ اشْتَدَّتْ بِهِ الرِّيحُ فِي يَوْمٍ عَاصِفٍ ۖ لَّا يَقْدِرُونَ مِمَّا كَسَبُوا عَلَىٰ شَيْءٍ ۚ ذَٰلِكَ هُوَ الضَّلَالُ الْبَعِيدُ

በኢማን የሚሠራ መልካም ሥራ በአኺራ ከአሏህ ዘንድ ትርሲት እና ምንዳ ያስገኛል፦
22፥56 "እነዚያም ያመኑት መልካም ሥራዎችንም የሠሩት በመደሰቻ ገነቶች ውስጥ ናቸው"፡፡ ۚ فَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ فِي جَنَّاتِ النَّعِيمِ

ነጥብ ሁለት
"ኢኽላስ"
“ኢኽላስ” إِخْلَاص‎ የሚለው ቃል "አኽለሶ" أَخْلَصَ‎ ማለትም "አጠራ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን እውነት ለማንገሥ ሐሠትን ለማርከሥ የሚደረግ "መተናነስ" ወይም ከሙገሳ እና ከወቀሳ ነጻ ሆኖ ለአሏህ ውዴታ የሚደረግ "ማጥራት" ማለት ነው፥ ሊሏህ ሳይሆን ለእዩልኝ እና ለስሙልኝ ተብሎ የሚሠራ ማንኛው መልካም ሥራ አሏህ ዘንድ መቅቡል ሳይሆን መርዱድ ነው፦
2፥264 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እንደዚያ ገንዘቡን ለሰዎች ማሳየት ሲል እንደሚሰጠው እና በአላህና በመጨረሻውም ቀን እንደማያምነው ሰው ምጽዋቶቻችሁን በመመጻደቅና በማስከፋት አታበላሹ”። يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تُبْطِلُوا صَدَقَاتِكُم بِالْمَنِّ وَالْأَذَىٰ كَالَّذِي يُنفِقُ مَالَهُ رِئَاءَ النَّاسِ وَلَا يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ
107፥4 ወዮላቸው ለሰጋጆች፡፡ فَوَيْلٌۭ لِّلْمُصَلِّينَ
107፥6 ለእነዚያ እነርሱ ይዩልኝ ባዮች ለኾኑት፡፡ ٱلَّذِينَ هُمْ يُرَآءُونَ

በኢኽላስ የሚሠራ መልካም ሥራ በአኺራ ከአሏህ ዘንድ ስርጉት እና ትሩፋት ያስገኛል፦
13፥22 እነዚያም "የጌታቸውን ውዴታ ለመፈለግ" የታገሱ፣ ሶላትንም አዘውትረው የሰገዱ፣ እኛ ከሰጠናቸው ሲሳይም በምስጢርም ኾነ በግልጽ የመጸወቱ ክፉውንም ነገር በበጎ የሚገፈትሩ ናቸው፡፡ እነዚያ ለእነርሱ መጨረሻይቱ ምስጉን አገር አለቻቸው*፡፡ وَالَّذِينَ صَبَرُوا ابْتِغَاءَ وَجْهِ رَبِّهِمْ وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ وَأَنفَقُوا مِمَّا رَزَقْنَاهُمْ سِرًّا وَعَلَانِيَةً وَيَدْرَءُونَ بِالْحَسَنَةِ السَّيِّئَةَ أُولَـٰئِكَ لَهُمْ عُقْبَى الدَّارِ
76፥9 «የምናበላችሁ "ለአላህ ውዴታ ብቻ ነው"፡፡ ከእናንተ ዋጋንም ማመስገንንም አንፈልግም፡፡ إِنَّمَا نُطْعِمُكُمْ لِوَجْهِ اللَّهِ لَا نُرِيدُ مِنكُمْ جَزَاءً وَلَا شُكُورًا
76፥10 «እኛ ፊትን የሚያጨፈግግን ብርቱ ቀን ከጌታችን እንፈራለንና» ይላሉ፡፡ إِنَّا نَخَافُ مِن رَّبِّنَا يَوْمًا عَبُوسًا قَمْطَرِيرًا
ነጥብ ሦስት
"ኢትባዕ"
"ኢትባዕ" إِتْبَاع‎ የሚለው ቃል "አትበዐ" أَتْبَعَ ማለትም "ተከተለ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መከተል" ማለት ነው፥ ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ በተቀመጠው ብቻ ዒባዳህን መፈጸም "ኢትባዕ" ይባላል፦
6፥106 ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደውን ተከተል፡፡ اتَّبِعْ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ
7፥3 ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ። اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ

"ተከተሉ" የሚለው ቃል “ኢተቢዑ” اتَّبِعُوا ሲሆን ስለዚህ "ኢትባዕ" ማለት ከአሏህ ዘንድ ወደ ነቢያችን"ﷺ" የተወረደውን ብቻ እና ብቻ ተከትለን አምልኮ ስንፈጽም ማለት ነው፥ አንድ ሥራን መልካም ወይም ክፉ ተብሎ መስፈቱ ያለው ከአሏህ ዘንድ በተወረደው ግልጠተ መለኮት ነው። የኢትባዕ ተቃራኒ ደግሞ "ቢድዓህ" ነው፥ የራሳችን ዝንባሌ ተከትለን የምፈጽመው አምልኮ "ቢድዓህ" ነው፦
28፥50 እሺ ባይሉህም የሚከተሉት ዝንባሌዎቻቸውን ብቻ መኾኑን ዕወቅ፡፡ ከአላህም የኾነ መመሪያ ሳይኖረው ዝንባሌውን ከተከተለ ሰው ይበልጥ የጠመመ አንድም የለም፡፡ فَإِن لَّمْ يَسْتَجِيبُوا لَكَ فَاعْلَمْ أَنَّمَا يَتَّبِعُونَ أَهْوَاءَهُمْ ۚ وَمَنْ أَضَلُّ مِمَّنِ اتَّبَعَ هَوَاهُ بِغَيْرِ هُدًى مِّنَ اللَّهِ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 81, ሐዲስ 76
አቢ ሁራይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "እሳት በዝንባሌዎች ዙሪያ ነው፥ ጀናህ ደግሞ በመላቀቅ ዙሪያ ናት"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ حُجِبَتِ النَّارُ بِالشَّهَوَاتِ، وَحُجِبَتِ الْجَنَّةُ بِالْمَكَارِهِ ‏”‌‏.‏

"አህዋእ" أَهْوَآء ማለት "ዝንባሌ"inclination" ማለት ነው፥ "ቢድዓህ" بِدْعَة ደግሞ "በደዐ" بَدَّعَ ማለትም "ፈጠረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ፈጠራ" ማለት ነው። ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓህ ነው፥ ቢድዓህ ሁሉ ጥመት ነው። ጥመት ሁሉ በእሳት ውስጥ ያረጋል፦
ሡነን ነሣኢይ መጽሐፍ 19, ሐዲስ 23
ጃቢር ኢብኑ ዐብደላህ እንደተረከው፦ የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ ኹጥባቸው ላይ እንደተናገሩት፦ "አሏህ የመራውን ማንም አያጠመውም፥ አሏህ ያጠመመውን ማንም አያቀናውም። ከንግግር ሁሉ በላጩ የአሏህ መጽሐፍ ነው፥ ከመመሪያ ሁሉ በላጩ የሙሐመድ መመሪያ ነው። ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓህ ነው፥ ቢድዓህ ሁሉ ጥመት ነው። ጥመት ሁሉ በእሳት ውስጥ ያረጋል"። عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ قَالَ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ فِي خُطْبَتِهِ يَحْمَدُ اللَّهَ وَيُثْنِي عَلَيْهِ بِمَا هُوَ أَهْلُهُ ثُمَّ يَقُولُ مَنْ يَهْدِهِ اللَّهُ فَلَا مُضِلَّ لَهُ وَمَنْ يُضْلِلْهُ فَلَا هَادِيَ لَهُ إِنَّ أَصْدَقَ الْحَدِيثِ كِتَابُ اللَّهِ وَأَحْسَنَ الْهَدْيِ هَدْيُ مُحَمَّدٍ وَشَرُّ الْأُمُورِ مُحْدَثَاتُهَا وَكُلُّ مُحْدَثَةٍ بِدْعَةٌ وَكُلُّ بِدْعَةٍ ضَلَالَةٌ وَكُلُّ ضَلَالَةٍ فِي النَّارِ

አምላካችን አሏህ እርሱ ባስቀመጠልን መስፈርት በኢማን፣ በኢኽላስ፣ በኢትባዕ የምናመልከው ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ጽርፈት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

43፥59 እርሱ በእርሱ ላይ የለገስንለት እና ለእስራኤልም ልጆች ተአምር ያደረግነው የኾነ ባሪያ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ إِنْ هُوَ إِلَّا عَبْدٌ أَنْعَمْنَا عَلَيْهِ وَجَعَلْنَاهُ مَثَلًا لِّبَنِي إِسْرَائِيلَ

"ጽርፈት" ማለት "ስድብ”blasphemy" ማለት ሲሆን አይሁዳውያን በእነርሱ እሳቤ ያልተገባ ደረጃ "ይገባኛል" የሚል ማንነት ሲናገር የሚቃወሙበት ቃል ነው፥ በአይሁዳውያን እሳቤ የሚያምኑት የሚመጣው መሢሕ "አምላክ" ወይም ፈጣሪ ነው" ብለው ሳይሆን "ንጉሥ እና ነቢይ ነው" ብለው ነው፦
ማርቆስ 14፥61-62 እርሱ ግን ዝም አለ አንዳችም አልመለሰም። ደግሞ ሊቀ ካህናቱ ጠየቀውና፦ የቡሩክ ልጅ ክርስቶስ አንተ ነህን? አለው። ኢየሱስም አለ፦ "እኔ ነኝ"፤ የሰው ልጅም በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ።

አይሁዳውያን የሚመጣው መሢሕ "የቡሩክ ልጅ ነው" የሚል እምነት ስለነበራቸው ኢየሱስ ያ የቡሩክ ልጅ "እኔ ነኝ" በማለቱ "ስድብ ነው" ብለዋል፦
ማርቆስ 14፥63-64 ሊቀ ካህናቱም ልብሱን ቀደደና፦ ከእንግዲህ ወዲህ ምስክሮችን ምን ያስፈልገናል? ስድቡን ሰማችሁ፤ ምን ይመስላችኋል? አለ። እነርሱም ሁሉ፦ "ሞት ይገባዋል" ብለው ፈረዱበት።

ኢየሱስን "ሞት ይገባዋል" ብለው የፈረዱበት የሚመጣው መሢሕ "እኔ ነኝ" ወይም "የአምላክ ልጅ ነኝ" በማለቱ ነው፦
ዮሐንስ 19፥7 አይሁድም መልሰው፦ እኛ ሕግ አለን፥ እንደ ሕጋችንም ሊሞት ይገባዋል፥ "ራሱን የእግዚአብሔር ልጅ አድርጎአልና" አሉት።

ኢየሱስ እራሱን "የእግዚአብሔር ልጅ" በሚል የመሢሑን ደረጃ በማስቀመጡ ድንጋይ ሊወግሩ አነሱበት፦
ዮሐንስ 10፥29 የሰጠኝ "አባቴ" ከሁሉ ይበልጣል፥ "ከአባቴም" እጅ ሊነጥቃቸው ማንም አይችልም።
ዮሐንስ 10፥31 አይሁድ ሊወግሩት ደግመው ድንጋይ አነሡ።
ዮሐንስ 10፥33 አይሁድም፦ ስለ መልካም ሥራ አንወግርህም፤ ስለ "ስድብ"፤ አንተም ሰው ስትሆን ራስህን አምላክ ስለ ማድረግህ ነው እንጂ፡ ብለው መለሱለት።

ኢየሱስ "አባቴ" "አባቴ" በማለት እራሱ "የእግዚአብሔር ልጅ" ስላለ "ስድብ ነው" አሉ፥ እርሱም ያለው፦ "አምላክ ነኝ" ሳይሆን "የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ስላልሁ" ስድብ አይደለም በማለት መለሰ፦
ዮሐንስ 10፥36 "የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ" ስላልሁ እናንተ አብ የቀደሰውን ወደ ዓለምም የላከውን፦ "ትሳደባለህ" ትሉታላችሁን?

"አንተም ሰው ስትሆን ራስህን አምላክ ስለ ማድረግህ ነው" ለሚለው የሐሰት ክሳቸው ደግሞ ፈጣሪ ነቢያትን ሁሉ "አማልክት" ብሏቸዋል የሚል ምላሽ ሰቷቸዋል፦
ዮሐንስ 10፥34 ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፦ እኔ፦ "አማልክት ናችሁ" አልሁ" ተብሎ በሕጋችሁ የተጻፈ አይደለምን?
መዝሙር 82፥6 እኔ ግን፦ "አማልክት ናችሁ፥ ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁ።

"አምላክ" በነጠላ ሲሆን በጸያፍ ርቢ ብዜት "አምላኮች" ለሚለው ምትክ "አማልክት" ነው፥ የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸው ነቢያት ሁሉ "አማልክት" እና "የእግዚአብሔር ልጆች" ናቸው፦
ዮሐንስ 10፥35 መጽሐፉ ሊሻር አይቻልምና እነዚያን የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸውን አማልክት ካላቸው።
መጽሐፈ ምሥጢር ምዕራፍ 4 ቁጥር 25
"ወበእንተ ነቢያት ይቤ አንሰ እቤ አማልክት አንትሙ ወደቂቀ ልዑል ኲልክሙ"

ትርጉም፦ "ስለ ነቢያትም እኔ፦ "እናንተ አማልክት ናችሁ፥ ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁ" አልሁ"።

ስለዚህ ኢየሱስ "አምላክ ነኝ" አላለም፥ ቢል እንኳን የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸውን ነቢያት "አማልክት እና የእግዚአብሔር ልጆች" ካላቸው እርሱ "የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ" በማለቱ እንዴት ጽርፈት ይሆናል? ኢየሱስ "ልጅ" የተባለበት ነቢያት በተባሉበት ሒሣብ እና ስሌት ነው፥ ምክንያቱም የኢየሱስ አምላክ አንዱ አምላክ የአማልክት አምላክ ተብሏል፦
ዮሐንስ 10፥36 "የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ" ስላልሁ እናንተ አብ የቀደሰውን ወደ ዓለምም የላከውን፦ "ትሳደባለህ" ትሉታላችሁን?
መዝሙር 82፥1 አምላክ በአማልክት ማኅበር ቆመ፥ በአማልክትም መካከል ይፈርዳል።
መዝሙር 136፥2 የአማልክትን አምላክ አመስግኑ! ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።

እኛ ሙሥሊሞች አይሁዳውያን የሚጠብቁት መሢሕ ኢየሱስ ነው ብለን እናምናለን፥ ኢየሱስ አሏህ መጽሐፍ እና ነቢይነት የለገሰው ባሪያ እና ያለ አባት በመወለድ ለእስራኤልም ልጆች ተአምር የተደረገ ባሪያ ነው፦
43፥59 እርሱ በእርሱ ላይ የለገስንለት እና ለእስራኤል ልጆች ተአምር ያደረግነው የኾነ ባሪያ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ إِنْ هُوَ إِلَّا عَبْدٌ أَنْعَمْنَا عَلَيْهِ وَجَعَلْنَاهُ مَثَلًا لِّبَنِي إِسْرَائِيلَ

ለኢየሱስ ነቢይነትን እና መጽሐፍን የሰጠውን አንዱን አምላክ አሏህን እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ተጠየቅ ዘኦርቶዶክስ

ሰማያት 14 ናቸውን? "ሰባቱ ሰማያትን ፈጥረን ከጨረስን በኋላ በቅፅበት ሌሎች ሰባት ሰማዮችን ፈጠርን" በማለት ከሰባት ሰማያት መፈጠር በኃላ ሌሎች ሰባት ሰማያት እንደተፈጠሩ ቀሌምንጦስ ይናገራል፦
ቀሌምንጦስ 6፥25 ብርሃኑ በሰማዮች ያለ ነው። ይህም ብርሃን አያልቅም አይለወጥምም፥ የሁሉም መድረሻና መነሻ እኛ ነን። ሁሉም የሚኖረው በመዳፋችን ነው። ሰባቱ ሰማያትን ፈጥረን ከጨረስን በኋላ በቅፅበት ሌሎች ሰባት ሰማዮችን ፈጠርን፥ የፈጠርነውም በቃላችን ነው።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom
ግጥም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥269 አላህ ለሚሻው ሰው ጥበብን ይሰጣል፥ ጥበብንም የተሰጠው ሰው ብዙን መልካም ነገር በእርግጥ ተሰጠው፡፡ يُؤْتِي الْحِكْمَةَ مَن يَشَاءُ ۚ وَمَن يُؤْتَ الْحِكْمَةَ فَقَدْ أُوتِيَ خَيْرًا كَثِيرًا

"ሐኪም" حَكِيم የሚለው ቃል "ሐከመ" حَكَمَ ማለትም "ተጠበበ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ጥበበኛ" ማለት ነው፥ አምላካችን አሏህ የጥበብ ምንጭ ስለሆነ "አል-ሐኪም" ٱلْحَكِيم ነው፦
28፥9 «ሙሳ ሆይ! እነሆ እኔ አሸናፊው "ጥበበኛው" አላህ ነኝ፡፡ يَٰمُوسَىٰٓ إِنَّهُۥٓ أَنَا ٱللَّهُ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ
3፥6 እርሱ ያ በማሕጸኖች ውስጥ እንደሚሻ አድርጎ የሚቀርጻችሁ ነው፡፡ ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ አሸናፊው "ጥበበኛው" ነው፡፡ هُوَ ٱلَّذِى يُصَوِّرُكُمْ فِى ٱلْأَرْحَامِ كَيْفَ يَشَآءُ ۚ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ

"ሒክማህ" حِكْمَة ማለት "ጥበብ" ማለት ሲሆን አሏህ ለሚሻው ሰው ሒክማህ ይሰጣል፥ ሒክማህ የተሰጠው ሰው ብዙን መልካም ነገር በእርግጥ ተሰጠው፦
2፥269 አላህ ለሚሻው ሰው ጥበብን ይሰጣል፥ ጥበብንም የተሰጠው ሰው ብዙን መልካም ነገር በእርግጥ ተሰጠው፡፡ የአእምሮዎች ባለቤቶች እንጂ ሌላው አይገሰጽም፡፡ يُؤْتِي الْحِكْمَةَ مَن يَشَاءُ ۚ وَمَن يُؤْتَ الْحِكْمَةَ فَقَدْ أُوتِيَ خَيْرًا كَثِيرًا ۗ وَمَا يَذَّكَّرُ إِلَّا أُولُو الْأَلْبَابِ

ጥበብ ከተሰጠው ሰው ብዙ መልካም ነገር አንዱ ግጥም ነው። "ሸዕር" شِّعْر የሚለው ቃል "ሸዐረ" شِعَرَ ማለትም "ገጠመ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ግጥም"poetry" ማለት ነው፥ በእርግጥ አንዳንድ ግጥም ጥበብ ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 118
ዐብደሏህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "በእርግጥ አንዳንድ ግጥም ጥበብ ነው"። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ إِنَّ مِنَ الشِّعْرِ حِكْمَةً ‏"‏

"አሽ-ሸዕር" الشِّعْر በሚለው ቃል ላይ "ሚን" مِن የሚለው ሐርፉል ጀር መምጣቱ በራሱ "አንዳንድ ግጥም" ጥበብ ሆነው መልካም እንደሆኑ ሰዎች ለአሉታዊ የሚጠቀሙባቸው መጥፎ ግጥም ሊኖሩ ይችላሉ፦
አል-አደቡል ሙፍረድ መጽሐፍ 36, ሐዲስ 10
ዐብደሏህ ኢብኑ ዐምሪው እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ግጥም ልክ እንደ ንግግር ነው። መልካሙ ልክ እንደ መልካሙ ንግግር ነው፥ መጥፎው ልክ እንደ መጥፎ ንግግር ነው"። عَنْ عَبْدِ اللهِ بْنِ عَمْرٍو قَالَ‏:‏ قَالَ رَسُولُ اللهِ صلى الله عليه وسلم‏:‏ الشِّعْرُ بِمَنْزِلَةِ الْكَلاَمِ، حَسَنُهُ كَحَسَنِ الْكَلامِ، وَقَبِيحُهُ كَقَبِيحِ الْكَلامِ‏.‏

ስለዚህ "በእሥልምና ግጥም ሐራም ነው" የሚለው የሚሽነሪዎች አላዋቂነት ውኃ በላው። ለአሉታዊ መልእክት የሚጠቀሙበት መጥፎ ግጥም እንዳለ ሁሉ ለአውንታዊ መልእክት የሚጠቀሙበት መልካም ግጥም አለ፥ አመዛዝኖ ጥሩውን መቀበል እና መጥፎውን መተው የእኛ ድርሻ ነው፦
አል-አደቡል ሙፍረድ መጽሐፍ 36, ሐዲስ 11
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተናገረች፦ "ከመልካም የሆነ ግጥም አለ፥ ከመጥፎ የሆነ ግጥም አለ። መልካሙን ወስደህ ክፉውን ተወው!"። عَنْ عَائِشَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهَا، أَنَّهَا كَانَتْ تَقُولُ‏:‏ الشِّعْرُ مِنْهُ حَسَنٌ وَمِنْهُ قَبِيحٌ، خُذْ بِالْحَسَنِ وَدَعِ الْقَبِيحَ

በአንድ ወቅት ከሸይጧን የሆነውን መጥፎ ግጥም በተገጠመ ጊዜ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ"፦ "የሰው ሆድ መግል መሙላት ከዚህ ግጥም ከመሙላት ይሻላል" ብለዋል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 41, ሐዲስ 10
አቢ ሠዒድ አል-ኹድሪይ እንደተረከው፦ "ከአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" ጋር እየሄደን ልክ በዐርጅ እንደረስን የሚገጥም ገጣሚ በተገናኘን ጊዜ የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ሸይጧኑን ያዙት ወይም ሸይጧኑን አስወጡት! የሰው ሆድ መግል መሙላት ከዚህ ግጥም ከመሙላት ይሻላል"። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ، قَالَ بَيْنَا نَحْنُ نَسِيرُ مَعَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم بِالْعَرْجِ إِذْ عَرَضَ شَاعِرٌ يُنْشِدُ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ خُذُوا الشَّيْطَانَ أَوْ أَمْسِكُوا الشَّيْطَانَ لأَنْ يَمْتَلِئَ جَوْفُ رَجُلٍ قَيْحًا خَيْرٌ لَهُ مِنْ أَنْ يَمْتَلِئَ شِعْرًا ‏"‏ ‏.‏

"መግል" የቱን ያህል መጥፎ ነገር ቢሆንም መጥፎ ግጥም ከመግጠም ይልቅ የተሻለ መሆኑ መገለጹ በራሱ መጥፎ ግጥም ምን ያህል ጎጂ መሆኑን አመላካች ነው፥ መጥፎ ግጥም ለዘፈን፣ ለኩፍር ፓለቲካ፣ ለዘረኝነት፣ ለጎጠኝነት፣ ለነገር፣ ለአሽሙር ሊውል ይችላል። ሌላው በመሣጂድ ውስጥ ግጥም መግጠም ክልክል መሆኑን ሚሽነሪዎች "ግጥም በእሥልምና የተጠላ ነው" የሚል የሐሰት ፕሮፓጋንዳ አላቸው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 4, ሐዲስ 15
ዐምሪው ኢብኑ ሹዐይብ ከአባቱ እና ከአያቱ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" መግዛት፣ መሸጥ እና ግጥም መግጠም በመሣጂድ ውስጥ ከልክለዋል"። عَنْ عَمْرِو بْنِ شُعَيْبٍ، عَنْ أَبِيهِ، عَنْ جَدِّهِ، قَالَ نَهَى رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ عَنِ الْبَيْعِ وَالاِبْتِيَاعِ وَعَنْ تَنَاشُدِ الأَشْعَارِ فِي الْمَسَاجِدِ ‏.‏

መግዛት እና መሸጥ በንግድ ቦታ ክልክል እንዳልሆነ ሁሉ ግጥም መግጠም በቦታው ክልክል አይደለም፥ "በመሣጂድ ውስጥ" የምትለዋን ኃይለ ቃል ነጥሎ "ክልክል" የምትለዋል ቃል "ግጥም መግጠም" ከሚለው ጋር አጣፍቶ ማምታታት እጅግ ሲበዛ ክፉኛ ጠማማነት ነው። ደግሞ፦ "የግጥም ክህሎት ያላችሁ ሙሥሊሞች አሳዘናችሁን" ይላሉ፥ ምስኪን! መቅኖ እንዳጣ ገልቱ የምታሳዝኑት በውሸት ጊዜያችሁን፣ ጉለበታችሁን፣ ዐቅማችሁን የምታቃጥሉት ናችሁ። አሏህን ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኑን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

68፥1 "ኑን" በብርዕ እምላለሁ በዚያም በሚጽፉት። نٓ ۚ وَٱلْقَلَمِ وَمَا يَسْطُرُونَ

"ሑሩፉል ሙቀጧዓት" حُرُوف الْمُقَطَّعَات ማለት "አጽርዖተ-ፊደላት" ወይም "አጫጭር ፊደላት" ማለት ነው፥ ሑሩፉል ሙቀጧዓት በቁርኣን ከ 114 ምዕራፎች ውስጥ በ 29 ምዕራፎች መግቢያ ላይ ስላሉ "ፈዋቲሕ" فَوَاتِح ማለትም “ከፋች” ይባላሉ። እነዚህም ሐርፎች 14 ናቸው፥ ከአሥራ አራቱ አንዱ ፊደል "ኑን" ነው፦
68፥1 "ኑን" በብርዕ እምላለሁ በዚያም በሚጽፉት። نٓ ۚ وَٱلْقَلَمِ وَمَا يَسْطُرُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ኑን" نٓ ሙቀጧዓህ ሐርፍ ሆኖ በመክፈቻነት እንደ ሌሎቹ መጥቷል፥ "ኑን" نُّون ማለት "ዓሣ" ማለት ነው፦
21፥87 የዓሣውንም ባለቤት ተቆጥቶ በኼደ ጊዜ አስታውስ፡፡ وَذَا النُّونِ إِذ ذَّهَبَ مُغَاضِبًا فَظَنَّ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ዓሣ" ለሚለው ቃል የገባው "ኑን" نُّون ሲሆን ነቢዩ ዩኑሥ "ዙ አን-ኑን" ተብሏል፥ "ዙ አን-ኑን" ذَا النُّون ማለት "የዓሣው ባለቤት" ማለት ነው። የሚያጅበው ሡረቱል ቀለም ላይ ነቢዩ ዩኑሥ "የዓሣው ባለቤት" ተብሏል፦
68፥48 ለጌታህም ፍርድ ታገሥ! እንደ ዓሣው ባለቤትም" አትኹን፡፡ እርሱ በጭንቀት የተመላ ኾኖ ጌታውን በተጣራ ጊዜ፡፡ فَاصْبِرْ لِحُكْمِ رَبِّكَ وَلَا تَكُن كَصَاحِبِ الْحُوتِ إِذْ نَادَىٰ وَهُوَ مَكْظُومٌ

እዚህ አንቀጽ ላይ "የዓሣው ባለቤት" ለሚለው የገባው ቃል "ሷሒቡል ሑት" صَاحِبِ الْحُوت ሲሆን "ዙ አን-ኑን" ذَا النُّون ማለት ነው፥ ስለዚህ "ኑን" نُّون ማለት በትርጉም ደረጃ "ሑት" حُوت ማለት ነው።

"ኑን ሐርፉል ሙቀጧህ ነው" በሚል ጁሙሑር ዑለማእ ይስማማሉ፥ ቅሉ ግን ከኢብኑ ዐባሥ በተገኘው ሪዋያ ኢብኑ ከሲር፣ ቁርጡቢይ፣ ጦበሪይ ወዘተ.. "ከምድር በታች ባለው ውኃ ውስጥ ያለ ትልቅ ዓሣ ነው" ብለው ፈሥረዋል። ኢብኑ ዐባሥ ይህንን ያመጣው ከተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ሳይሆን ከዕበል አሕባር ከሚባል የመን ይኖር የነበረ አይሁዳዊ ሠለምቴ ነው፥ ስለዚህ "ከምድር በታች ባለው ውኃ ውስጥ ትልቅ ዓሣ አለ" የሚለው ኢሥራዒልያህ ነው።

በተጨማሪም "ምድር በውኃ ላይ ናት፣ ውኃው ደግሞ በዓለት ላይ ነው፣ ዓለቱም በዓሣ ነባሪ ጀርባ ላይ ነው" የሚለው ትርክት ደረጃው መውዱዕ" مَوْضُوْع ማለትም "የተፈበረከ"Fabrication" ነው፦
፨ሸይኽ አልባኒይ ሲልሲላት አል-አሒዲስ ዳዒፍ ወልመውዱዕ ገጽ 462 ሐዲስ ቁጥር 294 "ምድር በውኃ ላይ ናት፣ ውኃው ደግሞ በዓለት ላይ ነው፣ ዓለቱም በዓሣ ነባሪ ጀርባ ላይ ነው፣ ዓሣ ነባሪውም በመልአክ ትከሻ ላይ ነው። الأرض على الماء والماء على صخرة والصخرة على ظهر حوت يلتقي حرفاه بالعرش والحوت على كاهل ملك قدماه في الهواء
፨መናር አል-መኒፍ በኢብኑል-ቀይም "ረሒመሁሏህ" ቁጥር 67 “ምድር በዓለት ላይ ናት፣ ዓለቱ ደግሞ የበሬ ቀንድ ላይ ነው፣ በሬው ቀንዱን ሲያንቀሳቅስ ዓለቱ ይንቀሳቀሳል፣ ምድርም እንዲሁ የምትንቀጠቀጥ ስትሆን ትንቀሳቀሳለች። إنَّ الأرضَ على صخرةٍ والصَّخرةُ على قرنِ ثورٍ فإذا حرَّكَ الثَّورُ قرنَهُ تحرَّكتِ الصَّخرةُ فتحرَّكتِ الأرضُ وَهيَ الزَّلزلةُ.

በተመሳሳይ፦
፨ኢማሙ ዘሀቢይ ሚዛን አል-ኢዕቲዳል በተሰኘው መጽሐፉ ገጽ 144 ቁጥር 2 ላይ ዘገባውን "ደዒፍ" ضَعِيْف ማለትም "ደካማ"weak" ብሎታል።
፨ኢብኑ ቀይሰራኒም በመጽሐፋቸው ደኺራ አል-ሃፊዝ ገፅ 254 ላይ ኢስናዱን "ደዒፉል ጂዳን" ضَعِيْف الجِدًّا ማለትም "እጅግ ደካማ"very weak" ብለውታል።
፨ኢማም ኢብኑ ሐጀር አል-አስቀላኒም ቱህፈቱል ነበላዕ በተሰኘው መጽሐፋቸው ገጽ 60 ላይ ኑን አሰነባሪ ነው የሚለውን የመራል ሀምዳኒይ ሪዋያ ዶዒፍ መሆኑን ተናግረዋል።
፨ኢብኑ ከሢርም አል-ቢዳያ ወኒሃያ በተባለው መጽሐፉ ገጽ 32 ላይ ዘገባው ኢሥራዒልያት መሆኑን ከተናገረ ቡኋለ መትሩክ እንደሆነ ገልጿል።
፨የሐዲስ ሊቅ የሆነው ኢብኑ ሒባን አል-መጅሩሂን በተሰኘው መጽሐፉ ገፅ 404 ላይ ኢስናዱ ዶዒፍ መሆኑን ተናግሯል።
ከዕበል አሕባር ማለት በሁለተኛው ኸሊፋ በዑመር"ረ.ዐ" ጊዜ እሥልምናን የተቀበለ የየመን ረብቢ ማለትም የአይሁድ መምህር ነበር፥ ይህ ሰው ከልጅነቱ ጀምሮ ከኦሪትን ጀምሮ ያሉትን የአይሁዳውያን መጽሐፍት እያነበበ ያደገ ሰው ነው። ወደ እሥልምና ከመጣ በኃላም ብዙ የአይሁዳውያንን ወጎች ከእሥልምና ጋር በመቀላቀሉ ምክንያት በበርካታ ጥንታውያን ሊቃውንት ትርክቱ ውድቅ ሆኗል፥ "ምድርን የተሸከመው ዓሣ ነው" የሚለውንም ትርክቱ በባይብል ሆነ በአዋልድ አሊያም በትውፊት ላይ ያለ ነው። ባይብል ምድር የተዘረጋችው በውኃ ወይም በባሕር ላይ እንደሆነ ይናገራል፦
መዝሙር 136፥6 "ምድርን በውኃ ላይ ያጸና"።
መዝሙር 24፥1 እርሱ በባሕሮች ላይ መሥርቶአታልና። כִּי־ ה֖וּא עַל־ יַמִּ֣ים
1ኛ መቃብያን 27፥1 "ምድርንም በውኃ ላይ አጸናት"።
ቀለሜንጦስ 6፥50 "ምድርንም በውኃ ላይ እኛ ፈጠርናት"።

በገድላት ላይ ምድርን በውኃ ላይ ወይም በባሕር ጀርባ ላይ እንደ ዘረጋት ይናገራሉ፦
ገድለ ተክለ ሃይማኖት 60፥2 ሰማይን እንደ ዋልታ በሰቀለ፣ "ምድርን ያለመሠረት በውኃ ላይ እንደ አረንጓዴ የዘረጋት"።
ገድለ ቅዱስ ቂርቆስ 12ኛ ተአምር ቁጥር 4 ጌታዬ ሆይ! መሬትን በባሕር ላይ ያጸናህ አንተ ነህ"።

በድርሳናት ላይ ምድርን በውኃ ላይ ወይም በባሕር ጀርባ ላይ እንደ ዘረጋት ይናገራሉ፦
ድርሳነ ሚካኤል ዘወርኃ ኅዳር 3፥118 ምድርን በባሕር ላይ በዘረጋው"።
ድርሳነ መድኃኒ ዓለም ዘሰኑይ 7፥17 "አቤቱ አንተ ምድርን በባሕር ላይ ያጸናኃት"።
ድርሳነ መስቀል ዘወርኃ መጋቢት 19፥19 "ምድርን በባሕር ጀርባ ላይ የዘረጋት" እግዚአብሔርን እናመሰግናለን።

በተጨማሪም በዕብራይስጥም "ኑን" נ‎ ማለት "አንበሪ" "ታላቁ ዓሣ" ማለት ሲሆን ይህ ታላቁ ዓሣ ከምድር በታች ባለው ውኃ ውስጥ እንዳለ ይናገራል፦
ዘጸአት 20፥4 "ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር" የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ።
ዘዳግም 4፥18 "ከምድርም በታች በውኃ ውስጥ የሚኖረውን "የዓሣን" ሁሉ ምሳሌ እንዳታደርጉ።

"ከምድር በታች በውኃ ውስጥ የሚኖረው ዓሣ" የሚለው ይሰመርበት! "ከምድር በታች ውኃ አለ" የሚለው ትምህርት ከአፈ ታሪክ የተቀዳ ነው፥ በከነዓናውያን ደግሞ "ነህስ" ނ ማለት "ታላቁ እባብ" ማለት ሲሆን "ሌዋታን" ይባላል። ሌዋታን እባብ የሚኖረው በጥልቁ ባሕር ውስጥ ነው፦
ኢሳይያስ 27፥1በዚያም ቀን እግዚአብሔር ፈጣኑን እባብ ሌዋታንን ጠማማውንም እባብ ሌዋታንን በጠንካራ በታላቅም በብርቱም ሰይፍ ይቀጣል።
አሞጽ 9፥3 በጥልቅ ባሕርም ውስጥ ከዓይኔ ቢደበቁ ከዚያ እባቡን አዝዛለሁ፥ እርሱም ይነድፋቸዋል።
1ኛ መቃብያን 25፥5 ከምድር በታች ያለውን እባብ አዘዋለሁ፥ በባሕርም ውስጥ ያለውን ዓሣ አዘዋለሁ።

"ከምድር በታች ባለው ባሕር ውስጥ ሌዋታን የሚባል ዘንድ ወይም ታላቁ እባብ አለ" የሚለው ትምህርት ከፓጋን የተቀዳ ነው። ድርሳናት እና ሃይማኖተ አበው ከምድር በታች በውኃ ውስጥ የተሰወሩ ፍጥረት እንዳሉ ይናገራሉ፦
ድርሳነ መስቀል ዘወርኃ ታህሣሥ 11፥26 "ከምድር በታች የተሰወሩትን የሰው እና የእንስሳት ድምፅ ይሰማሉ"።
ድርሳነ ሚካኤል ዘወርኃ ኅዳር 3፥118 "ከምድር በታች በውኃ ውስጥ ካለው ፍጥረት ሁሉ አንተ አምላክ አታብጅ"።
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 129፥ ቁጥር 3 "ከምድር በታች በሚገኙ በውኃዎች ውስጥ ባሉ ፍጥረታት አምሳል ጣዖት አታብጅ"።

ስለዚህ "ከምድር በታች ውኃ አለ እና በውኃ ውስጥ ትልቅ ዓሣ አለ" የሚለው ትርክት ኢሥራዒልያህ እንጂ አሥ-ሠለፉል ኢጅማዕ አይደለም። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም