ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
69 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
1_5125580534726000876.pdf
369.4 KB
1_5125580534726000876.pdf

የቁርኣን ትንቢት

በፒዴፍ ደረጃ ለአንባቢያን ተበርክቷል። መልካም የንባብ ጊዜ።
ሦስቱ መላእክት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

29፥31 *መልእክተኞቻችንም ኢብራሂምን በብስራት በመጡት ጊዜ «እኛ የዚህችን ከተማ ሰዎች አጥፊዎች ነን፡፡ ሰዎቿ በዳዮች ነበሩና» አሉት*፡፡ وَلَمَّا جَاءَتْ رُسُلُنَا إِبْرَاهِيمَ بِالْبُشْرَىٰ قَالُوا إِنَّا مُهْلِكُو أَهْلِ هَـٰذِهِ الْقَرْيَةِ ۖ إِنَّ أَهْلَهَا كَانُوا ظَالِمِينَ

ኦሪት ዘፍጥረት ላይ አብርሃም ቤት ሦስት ሰዎች በእንግድነት እንደተስተናገዱ ይናገራል፤ ዐበይት ክርስቲያኖች፦ ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክ እና አንግሊካን እነዚህ ሦስት ሰዎች ሥላሴ ናቸው ይላሉ፤ እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 220 ድህረ-ልደት”AD” ቱርቱሊያም ይህንን አንቀጽ ይዞ የሥላሴን ቶኦሎጅይ ቴኦሌጃይዝ ያደረገው፤ በአገራችንም በየወሩ በሰባተኛው ቀን የአብርሃሙ ሦላሴ እየተባለ ይዘከራል፤ እውን ይህ አንቀጽ ለሥላሴ ተስተምህሮት መደላለል ይሆናልን? እስቲ ጥንልልና ጥንፍፍ አርገን እናስተንትነው፦
ዘፍጥረት 18፥1-2 በቀትርም ጊዜ እርሱ በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ *እግዚአብሔር በመምሬ የአድባር ዛፍ ተገለጠለት*። ዓይኑንም አነሣና እነሆ፥ *ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ*፤

እዚህ ጥቅስ ላይ ስለ ሥላሴ ምንም ሽታው እንኳን የለም። እነዚህ ሦስት ሰዎች አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ናቸው የሚል ዐውዱ ላይ ምንም አናገኝም። ይህንን አንቀጽ ለሥላሴ የተጠቀመ ነብይም ሆነ ሃዋርያ የለም፤ እነዚህ ሰዎች እነማን ናቸው ታዲያ? ለሚለው ጥያቄ መልስ ለዐውደ ንባቡ ቦታውን እንልቀቅ፦
ዘፍጥረት 18፥16 *ሰዎቹም ከዚያ ተነሥተው ወደ ሰዶም አቀኑ* አብርሃምም ሊሸኛቸው አብሮአቸው ሄደ።
ዘፍጥረት 18፥22 *ሰዎቹም ከዚያ ፊታቸውን አቀኑ፥ ወደ ሰዶምም ሄዱ* አብርሃም ግን በእግዚአብሔር ፊት ገና ቆሞ ነበር።

እነዚህ ሰዎች ከአብርሃም ቤት ወደ ሰዶም አቀኑ፣ ወደ ሰዶምም ሄዱ፤ ከዚያስ? በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ገቡ፦
ዘፍጥረት 19፥1 *ሁለቱም መላእክት በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ገቡ*፤

እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር ሲነጋገር የነበረው በሦስት ሰዎች ነው፤ ሁለቱ ሰዎች ሲሄዱ ግን “አብርሃም በእግዚአብሔር ፊት ገና ቆሞ ነበር” ይላል፤ እግዚአብሔር በአንዱ ሰው ሲነጋገር ሁለቱ ሰዎች ሎጥ ቤት ገብተዋል፦
ዘፍጥረት 19፥10 *ሁለቱም ሰዎች እጃቸውን ዘርግተው ሎጥን ወደ እነርሱ ዘንድ ወደ ቤት አገቡት መዝጊያውንም ዘጉት*።
ዘፍጥረት 19፥12 *ሁለቱም ሰዎች ሎጥን አሉት*።
ዘፍጥረት 19፥13 *እኛ ይህን ስፍራ እናጠፋለንና፥ ጩኸታቸው በእግዚአብሔር ፊት ትልቅ ሆኖአልና እናጠፋውም ዘንድ እግዚአብሔር ሰድዶናል*።

“ሁለቱ ሰዎች” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ ምን ትፈልጋለህ? ከአብርሃም ቤት ወጥተው ወደ ሎጥ ቤት የገቡት ሰዎች በቁጥር ሁለት መሆናቸውን እና ሁለት መላእክት መሆናቸውን ተገልጻል፤ እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ በአንድ ሰው ይናገራል፤ ይህም ሰው መልአክ ተብሏል፤ ለምሳሌ ያዕቆብ ሲታገለው የነበረው መልአክ ሰው ተብሏል፦
ዘፍጥረት 32፥28 አለውም፦ ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ እስራኤል ይባል እንጂ ያዕቆብ አይባል፤ *ከእግዚአብሔር እና ከሰውም ጋር ታግለህ አሸንፈሃልና*።
ሆሴዕ 12፥3-4 በማኅፀን ውስጥ ወንድሙን በተረከዙ ያዘው፥ በጕልማስነቱም ጊዜ *ከአምላክ ጋር ታገለ፤ ከመልአኩም ጋር ታግሎ አሸነፈ*፤ አልቅሶም ለመነው። በቤቴልም አገኘው፥ በዚያም *ከእኛ ጋር ተነጋገረ*።

“ከእኛ ጋር ተነጋገረ” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ እግዚአብሔር እዚህ አንቀጽ ላይ፦ “እኛ” የሚለው መልአኩን ጨምሮ እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል፤ ምነው ገብርኤል ሰው ተብሎ የለ እንዴ? መላእክት በሰው ቅርጽ ስለሚመጡ ሰው ይባላሉ፦
ዳንኤል 9፥21 ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው *የነበረው ሰው ገብርኤል* እነሆ እየበረረ መጣ፤ በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ።

እግዚአብሔር ግን ሰው አይደለም፤ አይበላም አይጠጣምም፦
ሆሴዕ 11፥9 *እኔ አምላክ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁምና*፥
መዝሙር 50፥12 *ብራብም ለአንተ አልነግርህም፥ ዓለምና ሞላው የእኔ ነውና። የፍሪዳውን ሥጋ እበላለሁን? የፍየሉንስ ደም እጠጣለሁን?*

ፈጣሪ፦ እበላለሁን? እጠጣለሁን? ሲል በምጸታዊ አነጋገር አልበላም አልጠጣም እያለ ነው፤ አንዳንድ ቂሎች፦ “አብርሃም ቤት የገቡት ሰዎች ምግብ በልተዋል፤ መላእክት እንዴት ይበላሉ? ብለው ይጠይቃሉ፤ የቱ ይቀላል መጋቢ ፈጣሪ መብላቱ ወይስ ፍጡር የሆኑት መላእክት መብላታቸው? አዎ መላእክቱ በልተዋል ይለናል፦
ዘፍጥረት 18፥8 እርጎና ወተትም ያዘጋጀውንም ጥጃ አመጣ፥ በፊታቸውም አቀረበው እርሱም ከዛፉ በታች በፊታቸው ቆሞ ነበር፥ *እነርሱም በሉ*።
ዘፍጥረት 19፥3 እጅግም ዘበዘባቸው ወደ እርሱም አቀኑ፥ ወደ ቤቱም ገቡ ማዕድ አቀረበላቸው፥ ቂጣንም ጋገረ *እነርሱም በሉ*።

ሎጥ ቤት የበሉት መላእክት ሥላሴ ናቸው ብላችሁ እንዳታርፉት፤ የዕብራውያን ጸሐፊ፦ “አንዳንዶች በእንግድነት መላእክትን ተቀብለዋል” በማለት አብርሃምን እና ሎጥን ያስታውሰናል፦
ዕብራውያን 13፥2 *እንግዶችን መቀበል አትርሱ*፤ በዚህ አንዳንዶች *ሳያውቁ መላእክትን እንግድነት ተቀብለዋልና*።
ሎጥ ቤት የበሉት መላእክት ሥላሴ ናቸው ብላችሁ እንዳታርፉት፤ የዕብራውያን ጸሐፊ፦ “አንዳንዶች በእንግድነት መላእክትን ተቀብለዋል” በማለት አብርሃምን እና ሎጥን   ያስታውሰናል፦
ዕብራውያን 13፥2 *እንግዶችን መቀበል አትርሱ*፤ በዚህ አንዳንዶች *ሳያውቁ መላእክትን እንግድነት ተቀብለዋልና*።

ከሎጥ ሌላ በእንግድነት እግር አጥቦና ጋብዞ እንግዳ የተቀበለ አብርሃም ነው። ደግሞም ድርሳነ ሚካኤል አብርሃም ቤት ገብተው አብርሃምን ያበሰሩት መላእክት እንደሆኑ ይናገራል፦
ድርሳነ ሚካኤል ዘሚያዝያ ቁጥር 11
ግዕዙ፦
*ወካዕበ መጽኡ መላእክት ወበጽሑ ኀበ አብርሃም ወነገርዎ ከመ ይትወለድ ይስሐቅ*።
አማርኛው፦
*ዳግመኛ መላእክት ወደ አብርሃም ዘንድ መጥተው ይስሐቅን እንደሚወልድ ነገሩት*።

አምላካችን አላህ ወደ ኢብራሂም ቤት በብስራት የመጡት መልእክተኞቹ እንደሆኑና እነዚህም መላእክትም ወደ ሉጥ ቤት እንደገቡ ይናገራል፦
29፥31 *መልክተኞቻችንም ኢብራሂምን በብስራት በመጡት ጊዜ «እኛ የዚህችን ከተማ ሰዎች አጥፊዎች ነን፡፡ ሰዎቿ በዳዮች ነበሩና» አሉት*፡፡ وَلَمَّا جَاءَتْ رُسُلُنَا إِبْرَاهِيمَ بِالْبُشْرَىٰ قَالُوا إِنَّا مُهْلِكُو أَهْلِ هَـٰذِهِ الْقَرْيَةِ ۖ إِنَّ أَهْلَهَا كَانُوا ظَالِمِينَ
11፥77 *መልእክተኞቻችንም ሉጥን በመጡት ጊዜ በእነርሱ ምክንያት አዘነ፡፡ ልቡም በነሱ ተጨነቀ፡፡ «ይህ ብርቱ ቀን ነውም» አለ*፡፡ وَلَمَّا جَاءَتْ رُسُلُنَا لُوطًا سِيءَ بِهِمْ وَضَاقَ بِهِمْ ذَرْعًا وَقَالَ هَـٰذَا يَوْمٌ عَصِيبٌ

እነዚህ መላእክት የቁጥራቸው መጠን ቁርኣን ላይ በእርግጥ አልተገለጸም፤ እንዲሁ ቁርኣን እነዚህ መላእክት በሉ አይልም፤ ኢብራሂም የተጠበሰን የወይፈን ስጋ ሲያመጣላቸው እጆቻቸውም ወደ ምግቡ የማይደርሱ መኾነቸውን ባየ ጊዜ ሸሻቸው፤ ምግብ የማይበሉ መሆናቸውን ሲረዳ ከእነርሱም ፍርሃት ተሰማው፦
11፥69 *መልእክተኞቻችንም ኢብራሂምን በልጅ ብስራት በእርግጥ መጡት፡፡ ሰላም አሉት፡፡ ሰላም አላቸው፡፡ ጥቂትም ሳይቆይ ወዲያውኑ የተጠበሰን የወይፈን ስጋ አመጣ*፡፡ وَلَقَدْ جَاءَتْ رُسُلُنَا إِبْرَاهِيمَ بِالْبُشْرَىٰ قَالُوا سَلَامًا ۖ قَالَ سَلَامٌ ۖ فَمَا لَبِثَ أَن جَاءَ بِعِجْلٍ حَنِيذٍ
11፥70 *እጆቻቸውም ወደ እርሱ የማይደርሱ መኾነቸውን ባየ ጊዜ ሸሻቸው፡፡ ከእነርሱም ፍርሃት ተሰማው፡፡ «አትፍራ እኛ ወደ ሉጥ ሕዝቦች ተልከናልና» አሉት*፡፡ فَلَمَّا رَأَىٰ أَيْدِيَهُمْ لَا تَصِلُ إِلَيْهِ نَكِرَهُمْ وَأَوْجَسَ مِنْهُمْ خِيفَةً ۚ قَالُوا لَا تَخَفْ إِنَّا أُرْسِلْنَا إِلَىٰ قَوْمِ لُوطٍ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ጥያቄ አለቀ!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

49፥7 *"በውስጣችሁም" የአላህ መልክተኛ መኖሩን ዕወቁ*፡፡ وَاعْلَمُوا أَنَّ فِيكُمْ رَسُولَ اللَّهِ

እሥልምና ዱር ሙሥሊሙ ሐሩር እንዲሆን ቀን ከሌሊት ደፋ ቀና፥ ጠብ እርግፍ የሚሉት አግድም አደግ ዕውቀት ያላቸው ሚሽነሪዎች የማይፈነቅሉት ድንጋይ፣ የማይቆፍሩት ጉድጓድ፣ የማይደረምሱት መሬት የለም። ኢየሱስ ሰው ነው፥ ሰው እያመለኩ እኛም ሰው በግድ ታመልካላችሁ ለማስባል የእከክልኝ ልከክልህ ጉዳይ ነውና፥ "ነቢያችሁ"ﷺ" በሁላችሁም ልባችሁ ውስጥ እንደ አምላክ ይኖራሉ" ይላሉ። እዚህ ድምዳሜ ላይ ያደራሳችሁ የትኛው አንቀጽ ነው? ስንላቸው፥ "ይህ አንቀጽ ነው" ይሉናል፦
49፥7 *"በውስጣችሁም" የአላህ መልክተኛ መኖሩን ዕወቁ*፡፡ وَاعْلَمُوا أَنَّ فِيكُمْ رَسُولَ اللَّهِ

ምን ይሻላችሁ ይሆን? ጥያቄ አለቀባችሁ? እዚህ አንቀጽ ላይ "በውስጣችሁም" የሚለው ቃል "ፊኩም" فِيكُمْ ሲሆን "በይነኩም" بَيْنَكُم ማለትም "በመካከላችሁ" ለማለት እንጂ "በልባችሁ" ለማለት በፍጹም አይደለም። "በልባችሁ" ለማለት ቢሆን ኖሮ "ቀሉቢኩም" قُلُوبِكُمْ ይል ነበር፥ ቅሉ ግን እንደዛ አላለም፦
2፥151 *በውስጣችሁ ከእናንተው የኾነን በእናንተ ላይ አንቀጾቻችንን የሚያነብላችሁና የሚያጠራችሁ፣ መጽሐፍንና ጥበብንም የሚያስተምራችሁ፣ ታውቁት ያልነበራችሁትንም ነገር የሚያሳውቃችሁ የኾነን መልእክተኛ እንደላክን ጸጋን ሞላንላችሁ*፡፡ كَمَا أَرْسَلْنَا فِيكُمْ رَسُولًا مِّنكُمْ يَتْلُو عَلَيْكُمْ آيَاتِنَا وَيُزَكِّيكُمْ وَيُعَلِّمُكُمُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَيُعَلِّمُكُم مَّا لَمْ تَكُونُوا تَعْلَمُونَ
3፥101 *የአላህም አንቀጾች በእናንተ ላይ የሚነበቡ ሲኾኑ መልእክተኛውም "በውስጣችሁ" ያለ ሲኾን እናንተ እንዴት ትክዳላችሁ?* በአላህም የሚጠበቅ ሰው ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ተመራ፡፡ وَكَيْفَ تَكْفُرُونَ وَأَنتُمْ تُتْلَىٰ عَلَيْكُمْ آيَاتُ اللَّهِ وَفِيكُمْ رَسُولُهُ ۗ وَمَن يَعْتَصِم بِاللَّهِ فَقَدْ هُدِيَ إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ

"በውስጣችሁ" መልእክተኛ ልከናል" ሲል "በልባችሁ" መልክእተኛ ልከናል ማለቱ ነው እንዴ" እረ በፍጹም። ባይሆን በመካከላቸው መልእክተኛ መላኩን የሚያሳይ ቢሆን እንጂ፦
40፥32 *"በውስጣቸውም" ከእነሱ የኾነን መልእክተኛ አላህን አምልኩ፥ ከእርሱ ሌላ አምላክ የላችሁም አትጠነቀቁምን? በማለት ላክን*፡፡ فَأَرْسَلْنَا فِيهِمْ رَسُولًا مِّنْهُمْ أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَـٰهٍ غَيْرُهُ ۖ أَفَلَا تَتَّقُونَ

"በውስጣቸው" ለሚለው የገባው ቃል ሦስተኛ መደብ "ፊሂም" فِيهِمْ ሲሆን "በይነሁም" بَيْنَهُمْ ማለትም "በመካከላቸው" የሚለውን ለማመልከት ነው። አላህ የትንሳኤ ቀን የሚቀጣውን ቅጣት ከተናገረ በኃላ፥ ከቅጣቱ በፊት ግን አስጠንቃቂ መልእክተኞችን በሕዝቦቻቸው መካከል እንደላከ ይናገራል፦
37፥72 *"በውስጣቸውም" አስጠንቃቂዎችን በእርግጥ ልከናል*፡፡ وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا فِيهِم مُّنذِرِينَ

ከነቢያችን"ﷺ" በፊት የተላኩት መልክተኞች "በውስጣቸው" ነው ማለት "በልባቸው" ነው ማለት ሳይሆን በመካከላቸው መሆኑን እሙን ነው፦
5፥20 ሙሳም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ፡- «ሕዝቦቼ ሆይ የአላህን ጸጋ *"በውስጣችሁ" ነቢያትን ባደረገና ነገሥታትንም ባደረጋችሁ ከዓለማትም ለአንድም ያልሰጠውን ችሮታ በሰጣችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ ያደረገውን ጸጋ አስታውሱ*፡፡» وَإِذْ قَالَ مُوسَىٰ لِقَوْمِهِ يَا قَوْمِ اذْكُرُوا نِعْمَةَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ إِذْ جَعَلَ فِيكُمْ أَنبِيَاءَ وَجَعَلَكُم مُّلُوكًا وَآتَاكُم مَّا لَمْ يُؤْتِ أَحَدًا مِّنَ الْعَالَمِينَ
አላህ ሙሳ ሕዝቦች በውስጣቸው ነቢያትን እና ነገሥታትን አደረገ ማለት በመካከላቸው ነቢያትን እና ነገሥታትን አደረገ ማለት እንጂ በልባቸው ነቢያትን እና ነገሥታትን አደረገ ማለት እንዳልሆነ ቅቡል ነው። ምነው አላህ ኑሕንም ወደ ሕዝቦቹ ልኮ "በውስጣቸውም" ሺህ ዓመትን አምሳ ዓመት ሲቀር ተቀመጠ ይል የለ እንዴ? በልባቸው ሺህ ዓመትን አምሳ ዓመት ሲቀር ተቀመጠ ማለት እንዳልሆነ ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ነው፦
29፥14 *ኑሕንም ወደ ሕዝቦቹ በእርግጥ ላክነው፡፡ "በውስጣቸውም" ሺህ ዓመትን አምሳ ዓመት ሲቀር ተቀመጠ*፡፡ እነርሱ በዳዮች ኾነውም የውሃው ማጥለቅለቅ ያዛቸው፡፡ وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوْمِهِ فَلَبِثَ فِيهِمْ أَلْفَ سَنَةٍ إِلَّا خَمْسِينَ عَامًا فَأَخَذَهُمُ الطُّوفَانُ وَهُمْ ظَالِمُونَ

ዒሣ ከማረጉ በፊት በሕዝቦቹ ውስጥ ነበር። ያ ማለት በልባቸው ውስጥ ነበረ ማለት ሳይሆን በመካከላቸው ነበር ማለት ነው፦
5፥117 «በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን ተገዙ ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ *”በውስጣቸውም" እስካለሁ ድረስ” በእነርሱ ላይ ”ምስክር” ነበርኩ*፡፡ *”በወሰድከኝም” ጊዜ አንተ በእነርሱ ላይ *”ተጠባባቂ”* ነበርክ፡፡ አንተም በነገሩ ሁሉ ላይ ዐዋቂ ነህ፡፡» مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ ۚ وَكُنتُ عَلَيْهِمْ شَهِيدًۭا مَّا دُمْتُ فِيهِمْ ۖ فَلَمَّا تَوَفَّيْتَنِى كُنتَ أَنتَ ٱلرَّقِيبَ عَلَيْهِمْ ۚ وَأَنتَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍۢ شَهِيدٌ

ምነው የእኔ እንጀራ እንደ ጋቢ ጥለቱ ቀጭን ነው አላችሁሳ? የኛ ዘንካታዎች እየተጎማለላችሁ ቁርኣን ውስጥ እንደገባችሁ ባይብል ላይ ገብተን እያነጻጸርን እናሳያችኃለን። ሙሴ፣ አሮን፣ ሳሙኤል፣ ነቢያት ከሞቱ ወዲህ በምእመናን መካከል እንደሚኖሩ ተነግሯል፦
መዝሙር 99፥6 *ሙሴና አሮን በካህናቱ ዘንድ፥ ሳሙኤልም ስሙን በሚጠሩት ዘንድ ናቸው*።
ሉቃስ 16፥29 አብርሃም ግን፦ *ሙሴና ነቢያት አሉአቸው፤ እነርሱን ይስሙ አለው*።

"ካህናቱ" እና "ሚጠሩት" በሚለው መነሻ ላይ ያለው "በ" የሚለው መስተዋድድ ልብ በል። "ፊ" فِي የግድ ውስጥ ብቻ ሳይሆን "በ" በሚል ይመጣል፥ ለምሳሌ፦ “ፊ ሰብሊልሏህ” فِي سَبِيلِ ٱللَّه ማለትም “በአላህ መንገድ” በሚል። ታዲያ ሙሴ፣ አሮን፣ ሳሙኤል፣ ነቢያት በሁሉም ስፍራ የሚኖሩ ናቸውን? ልክ እንደ አምላክ በአማንያን ልብ ውስጥ ይኖራሉ ማለት ነውን? አይ አርአያነታቸው እና ትምህርታቸው ነው ከተባለ፥ ከላይ ያለውንም የቁርኣን አንቀጽ አካላዊ መገኘት ሆኖ ሳለ ልባዊ ነው ካላችሁ እንግዲያውስ በቀላሉ በዚህ ልክና መልክ ተረዱት እንጂ ኢሥላም ጋር የሚመለክ ፍጡር የለም። "ነካክተው ነካክተው የተኛውን በሬ፥ እንደው አደረጉት አውሬ" ይላል ያገሬ ሰው። ሲያንቀለቅላችሁ ቆስቁሳችሁ፥ እሳት ላይ ተጣዳችሁ።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ተጎዳኝ የንጽጽር መጣጥፍ እና ኦድዮ ይፈልጋሉን? እንግዲያውስ ከታች ያሉትን ሊንክ ተጭነው ጎራ ይበሉ!
የኡስታዝ አቡ ሃይደር፦
@abuhyder

የኡስታዝ ኤልያህ፦
@religionandphylosophy

የኡስታዝ አቡ ዩሥራ፦
@Abuyusra3

የኡስታዝ የሕያህ፦
t.me/yahya5
ተርጂም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

12፥2 *እኛ ትገነዘቡ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን ሲሆን በእርግጥ አወረድነው*፡፡ إِنَّا أَنزَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ

አምላካችን አላህ ቁርኣንን ዐረቢኛ አድርጎ አወረደው፥ ቁርኣን በዐረብኛ የተነገረ ፍትሕ ነው፦
43፥3 *እኛ ትገነዘቡ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን አደረግነው*፡፡ إِنَّا جَعَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ
12፥2 *እኛ ትገነዘቡ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን ሲሆን በእርግጥ አወረድነው*፡፡ إِنَّا أَنزَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ
13፥37 *እንደዚሁ በዐረብኛ የተነገረ ፍትሕ ሲኾን አወረድነው*፡፡ وَكَذَٰلِكَ أَنزَلْنَاهُ حُكْمًا عَرَبِيًّا

“ዐረቢይ” عَرَبِيّ ማለት “ዐረብኛ” ማለት ሲሆን በሥነ-ሰዋስው ገላጭ ቅጽል ነው፥ ቁርኣን የወረደው ዐረቢኛ ሆኖ ነው። ከዐረቢኛው ቁርኣን ውጪ ያሉት የዐማርኛ፣ የእንግሊዝኛ፣ የፈረንሳይኛ፣ የስውዲንኛ መጽሐፎች ቁርኣን ሳይሆኑ የቁርኣን ትርጉም ናቸው፦
41፥3 አንቀጾቹ የተብራሩ የኾነ መጽሐፍ ነው፡፡ *ዐረብኛ ቁርኣን ሲኾን ለሚያውቁ ሕዝቦች የተብራራ ነው*፡፡ كِتَابٌ فُصِّلَتْ آيَاتُهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لِّقَوْمٍ يَعْلَمُونَ

"ተርጂም" تَرْجِم ማለት "ተርጀመ" تَرْجَمَ ‎ማለትም "ተረጎመ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ትርጉም"translation" ማለት ነው፥ "ሙተርጂም" مُتَرْجِم ወይም "ተርጁማን" تَرْجُمَان‎ ማለት ደግሞ "ተርጓሚ"translator" ማለት ነው። የሙተርጂም ወይም የተርጁማን ብዜት "ሙተርጂሙን" مُتَرْجِمُون ወይም "ተራጂም" تَرَاجِيم ማለትም "መተርጉማን" ነው። ለምሳሌ ቁርኣንን ወደ ሌላ ቋንቋ የመተርጎም ሥራ "ተርጂም" ይባላል። የቅዱስ ቁርኣን ትርጉም አሳቡን እንጂ ቃላቱን በትክክል አይተረጎምም። በዐረቢኛ አቻ ቃል ሳይገኝ ሲቀር ወይም ሌላ አንቀጽ ላይ የተብራራ አንቀጽ ሆኖ ሲገኝ የዐማርኛ ተርጓሚዎች በቅንፍ የማስቀመጥ ልምድ አላቸው፦
11፥112 *"እንደ ታዘዝከውም ቀጥ በል፡፡ ከአንተ ጋር ያመኑትም (ቀጥ ይበሉ)፡፡ ወሰንንም አትለፉ! እርሱ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና*፡፡ فَاسْتَقِمْ كَمَا أُمِرْتَ وَمَن تَابَ مَعَكَ وَلَا تَطْغَوْا ۚ إِنَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ

"ወ" وَ የሚለው አርፉል አጥፍ "እንዲሁ" የሚል ፍቺ ስላለው "ቀጥ ይበሉ" የሚለውን በውስጠ ታዋቂነት ስለመጣ በቅንፍ አስቀምጠውታል፥ ምክንያቱም ቀጣዩ ኃይለ-ቃል "ወሰንንም አትለፉ! እርሱ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና" የሚል የብዙ ቁጥር የግስ መደብ ሆኖ ስለመጣ ነው፦
3፥20 ቢከራከሩህም፡- *«ፊቴን ለአላህ ሰጠሁ፤ የተከተሉኝም ሰዎች (ለአላህ ሰጡ)*» በላቸው፡፡ فَإِنْ حَاجُّوكَ فَقُلْ أَسْلَمْتُ وَجْهِيَ لِلَّهِ وَمَنِ اتَّبَعَنِ

"ወ" وَ የሚለው አርፉል አጥፍ "እንዲሁ" የሚል ፍቺ ስላለው "ለአላህ ሰጡ" የሚለውን በውስጠ ታዋቂነት ስለመጣ በቅንፍ አስቀምጠውታል፦
2፥285 *መልክተኛው ከጌታው ወደ ርሱ በተወረደው አመነ፡፡ ምእምኖቹም (እንደዚሁ አመኑ)*፡፡ آمَنَ الرَّسُولُ بِمَا أُنزِلَ إِلَيْهِ مِن رَّبِّهِ وَالْمُؤْمِنُونَ

ዐረቢኛው ላይ ምንም የማያሻማ ሲሆን ወደ ዐማርኛው አቻ ቃል ሲጠፋ የዐማርኛ መተርጉማን በቅንፍ ያስቀምጣሉ እንጂ የኢንግሊሹን ብታዩት ግልጽ ነው፥ እስቲ በኢንግሊሹ ይህንኑ አንቀጽ እንይ፦
2፥285 The Messenger believeth in what hath been revealed to him from his Lord, as do the men of faith. Yusuf Ali (Saudi Rev. 1985)

"ወ" وَ የሚለውን አርፉል አጥፍ "እንዲሁ"as do" ብሎታል፥ ይህ የተለመደ ብዙ ቦታ ዐማርኛው ትርጉም ላይ አለ፦
22፥75 *አላህ ከመላእክት ውስጥ መልክተኞችን ይመርጣል፡፡ ከሰዎችም (እንደዚሁ)*፤ አላህ ሰሚ ተመልካች ነው፡፡ اللَّهُ يَصْطَفِي مِنَ الْمَلَائِكَةِ رُسُلًا وَمِنَ النَّاسِ ۚ إِنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ بَصِيرٌ
11፥3 *የመንቀልቀል ባለቤት የኾነችን እሳት በእርግጥ ይገባል*፡፡ سَيَصْلَىٰ نَارًا ذَاتَ لَهَبٍ
111፥4 *ሚስቱም (ትገባለች)*፤ እንጨት ተሸካሚ ስትኾን፡፡ وَامْرَأَتُهُ حَمَّالَةَ الْحَطَبِ

"ትገባለች" የሚለው የሚገልጸው ቃል "ወ" وَ የሚለው አርፉል አጥፍ ሲሆን "እንዲሁ"as do" ለማለት ተፈልጎ የገባ ቃል ነው፦
2፥45 *”በመታገስ እና በሶላትም ተረዱ፡፡ እርሷም(ሶላት) በፈሪዎች ላይ እንጅ በሌላው ላይ በእርግጥ ከባድ ናት*፡፡ وَاسْتَعِينُوا بِالصَّبْرِ وَالصَّلَاةِ ۚ وَإِنَّهَا لَكَبِيرَةٌ إِلَّا عَلَى الْخَاشِعِينَ

“ሃ” َّهَا ማለትም “እርሷ” የሚለው ተውላጠ-ስም ተክቶ የመጣው “መታገስ” የሚለው ቃል ሳይሆን የቅርብ ቃል የሆነውን “ሶላት” የሚለውን ስለሆነ፥ በዐማርኛ አሻሚ እንዳይሆን "ሶላት" የሚለውን በቅንፍ አስቀምጠውታል። ምክንያቱም "ሶብር" صَّبْر ሙዘከር ስለሆነ "ሶላህ" صَّلَاة ደግሞ ሙአነስ ስለሆነ ነው። “ሃ” َّهَا የሚለው ተሳቢ ሙአነስ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። እንቀጥል፦
17፥1 ያ ባሪያውን ከተከበረው መስጊድ ወደዚያ ዙሪያውን ወደ ባረክነው ወደ ሩቁ መስጊድ በሌሊት ውስጥ ያስኼደው (ጌታ) ጥራት ይገባው፡፡ ከተዓምራቶቻችን ልናሳየው (አስኼድነው)፡፡ *እነሆ እርሱ (አላህ) ሰሚው ተመልካቺው ነው*፡፡ سُبْحَانَ الَّذِي أَسْرَىٰ بِعَبْدِهِ لَيْلًا مِّنَ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ إِلَى الْمَسْجِدِ الْأَقْصَى الَّذِي بَارَكْنَا حَوْلَهُ لِنُرِيَهُ مِنْ آيَاتِنَا ۚ إِنَّهُ هُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ
"ሁወ" هُوَ ማለትም "እርሱ" የተባለው ባለቤት ተውላጠ-ስም መነሻ አንቀጽ ላይ "አልለዚ" الَّذِي ማለትም "ያ" የሚለውን አመልካች ተውላጠ-ስም ተክቶ ስለመጣ "እርሱ" የተባለው "አላህ" መሆኑን ለማሳየት በቅንፍ አስቀምጠዋል። ምክንያቱም አንደኛ "ልናሳየው" የሚለው ነቢያችንን"ﷺ" የሚያመለክት ስለሆነ፤ ሰው ሲያነብ "እርሱ" የተባለው ነቢያችንን"ﷺ" እንዳይመስለው። ሁለተኛ ብዙ ቦታ "ሰሚው ተመልካቺው ነው" የሚል ቃል ለነቢያችን"ﷺ" ሳይሆን ለአላህ የሚውል ነው፥ ሦስተኛ "ኢነ" إِنَّ የሚለው ሐርፉል ኑስብ "ሁ" هُ የሚለው ቃል ላይ መነሻ ሆኖ እንደመጣ ሁሉ "አላህ" ከሚለው ቃል በፊት መነሻ ሆኖ ሌሎች አናቅጽ ላይ መጥቷል፦
22፥75 *"አላህ ሰሚ ተመልካች ነውና*፡፡ إِنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ بَصِيرٌ
58፥1 *"አላህ ሰሚ ተመልካች ነውና*፡፡ إِنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ بَصِيرٌ
31፥28 *"አላህ ሰሚ ተመልካች ነውና*፡፡ إِنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ بَصِيرٌ

እንዲህ ዓይነት የትርጉም እጥረት ባይብል ላይ ይኖር ይሆን? እንዴታ! አለ እንጂ። ግሪኩ ላይ የሌለ ግን ትርጉም ስለማይሰጥ ዐማርኛ ላይ ወይም እንግሊዘኛ ላይ የጨመሩት ቃል አለ። ለምሳሌ፦
ማቴዎስ 10፥2 የአሥራ ሁለቱም ሐዋርያት ስም ይህ ነው፤ መጀመሪያው ጴጥሮስ የተባለው ስምዖን ወንድሙ እንድርያስም፥ የዘብዴዎስ *ልጅ* ያዕቆብም ወንድሙ ዮሐንስም፥
Τῶν δὲ δώδεκα ἀποστόλωντὰ ὀνόματά ἐστιν ταῦτα:πρῶτος Σίμων ὁ λεγόμενοςΠέτρος καὶ Ἀνδρέας ὁἀδελφὸς αὐτοῦ, καὶ Ἰάκωβοςὁ τοῦ Ζεβεδαίου καὶ Ἰωάννηςὁ ἀδελφὸς αὐτοῦ,

ግሪኩ ላይ "ሁዎስ" υἱός ወይም በአገናዛቢ ሙያ "ሁኦዩ" υἱοῦ ማለትም "ልጅ" የሚል የለም። ስለዚህ እዚህ አንቀጽ ላይ ያዕቆብ የዘብድዮስ ወንድም ይሁን፣ አጎት ይሁን፣ አባት ይሁን፣ ልጅ ይሁን የሚታወቀው ነገር የለም። ይህንን አንቀጽ የሚያብራራልን ሌላ መጽሐፍ ላይ፣ ሌላ ምዕራፍ ላይ፣ ሌላ አንቀጽ ላይ እናገኛለን፦
ማርቆስ 10፥35 የዘብዴዎስ *ልጆች* ያዕቆብ እና ዮሐንስም ወደ እርሱ ቀርበው፦ መምህር ሆይ፥ የምንለምንህን ሁሉ እንድታደርግልን እንወዳለን አሉት። Καὶ προσπορεύονται αὐτῷ Ἰάκωβος καὶ Ἰωάννης οἱ υἱοὶ Ζεβεδαίου λέγοντες αὐτῷ, Διδάσκαλε, θέλομεν ἵνα ὃ ἐὰν αἰτήσωμέν σε ποιήσῃς ἡμῖν.

እዚህ አንቀጽ ላይ "ሁኦኢ" υἱοὶ ማለትም "ልጆች" የሚል ቃል ስላለ፥ መተርጉማን "ልጅ" የሚለውን በማቴዎስ 10፥2 ላይ ግሪኩ ላይ የሌለውን አስገብተዋል። ሌላ ናሙና፦
ማርቆስ 9፥29 ይህ ወገን በጸሎት *"እና በጦም"* ካልሆነ በምንም ሊወጣ አይችልም" አላቸው። καὶ εἶπεν αὐτοῖς, Τοῦτο τὸ γένος ἐν οὐδενὶ δύναται ἐξελθεῖν εἰ μὴ ἐν προσευχῇ.

እዚህ አንቀጽ ላይ "ካይ ኔስቴአ" καὶ νηστείᾳ ማለትም "እና ጦም" የሚል ቃል ጭራሽኑ የለም። ይህንን አንቀጽ የሚያብራራልን ሌላ መጽሐፍ ላይ፣ ሌላ ምዕራፍ ላይ፣ ሌላ አንቀጽ ላይ አለ፦
ማቴዎስ 17፥21 ይህ ዓይነት ግን ከጸሎት *እና ከጦም* በቀር አይወጣም" አላቸው። Τοῦτο τὸ γένος ἐν οὐδενὶ δύναται ἐξελθεῖν εἰ μὴ ἐν προσευχῇ καὶ νηστείᾳ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ካይ ኔስቴአ" καὶ νηστείᾳ ማለትም "እና ጦም" የሚል ቃል ስላለ፥ መተርጉማን "እና በጦም" የሚለውን በማቴዎስ 17፥21 ላይ ግሪኩ ላይ የሌለውን አስገብተዋል። ሌላ ናሙና፦
1 ቆሮንቶስ 13፥3 *"ድሆችንም* ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም። κἂν ψωμίσω πάντα τὰ ὑπάρχοντά μου, καὶ ἐὰν παραδῶ τὸ σῶμά μου ἵνα καυχήσωμαι, ἀγάπην δὲ μὴ ἔχω, οὐδὲν ὠφελοῦμαι.

"ድሆች" በኮይኔ ግሪክ "ፕቶቾስ" πτωχοῖς ሲሆን ግሪኩ ላይ የለም። ስለዚህ እዚህ አንቀጽ ላይ ጳውሎስ "ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል" የሚለው ስለእነማን እንደሆነ የሚታወቀው ነገር የለም። ይህንን አንቀጽ የሚያብራራልን ሌላ መጽሐፍ ላይ፣ ሌላ ምዕራፍ ላይ፣ ሌላ አንቀጽ ላይ እናገኛለን፦
ማቴዎስ 19፥21 ኢየሱስም፦ ፍጹም ልትሆን ብትወድ፥ ሂድና ያለህን ሸጠህ *ለድሆች* ስጥ፥ መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ፥ መጥተህም ተከተለኝ፡ አለው። ἔφη αὐτῷ ὁ Ἰησοῦς, Εἰ θέλεις τέλειος εἶναι, ὕπαγε πώλησόν σου τὰ ὑπάρχοντα καὶ δὸς [τοῖς] πτωχοῖς, καὶ ἕξεις θησαυρὸν ἐν οὐρανοῖς, καὶ δεῦρο ἀκολούθει μοι.

እዚህ አንቀጽ ላይ "ፕቶቾስ" πτωχοῖς ማለትም "ድሆች" የሚል ቃል ስላለ፥ መተርጉማን "ድሆች" የሚለውን በ1 ቆሮንቶስ 13፥3 ላይ ግሪኩ ላይ የሌለውን አስገብተዋል። ብዙ ናሙናዎች በቁና ማቅረብ ይቻል ነበር፥ አንባቢያንን ላለማሰልቸት ነው።
"የባይብል መተርጉማን የሚተረጉሙት ቃላትን ሳይሆን አሳብን ነው" ከተባለ "እንግዲያውስ በዐማርኛው ላይ በቅንፍ የሚያስቀምጡት የቁርኣን መተርጉማን የሚተረጉሙት የቁርኣን ቃላት ሳይሆን አሳብን ነው" ብሎ በዚህ ስሌትና ቀመር መረዳት ነው። የተሰናኘ ስንኝ"syntax" ማኅበረሰቡ ሊረዳው በሚችል መልኩ መድረስ ይችላል፥ ይህንን ስንኝ ቃልን በቃል የመተርጎም ሥራ "የቃል ትርጉም"metaphrase translation" ሲባል፥ ቃልን በአሳብ የመተርጎም ሥራ ደግሞ "የአሳብ ትርጉም"paraphrase translation" ይባላል። ሙሥሊም የማያነብ ይመስላችኃል? አላህ ሂዳያህ ይስጣችሁ፥ ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የቅንፍ አጠቃቀም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

12፥2 *እኛ ትገነዘቡ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን ሲሆን በእርግጥ አወረድነው*፡፡ إِنَّا أَنزَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ

አምላካችን አላህ ቁርኣንን ዐረቢኛ አድርጎ አወረደው፥ ቁርኣን በዐረብኛ የተነገረ ፍትሕ ነው፦
43፥3 *እኛ ትገነዘቡ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን አደረግነው*፡፡ إِنَّا جَعَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ
12፥2 *እኛ ትገነዘቡ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን ሲሆን በእርግጥ አወረድነው*፡፡ إِنَّا أَنزَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ
13፥37 *እንደዚሁ በዐረብኛ የተነገረ ፍትሕ ሲኾን አወረድነው*፡፡ وَكَذَٰلِكَ أَنزَلْنَاهُ حُكْمًا عَرَبِيًّا

“ዐረቢይ” عَرَبِيّ ማለት “ዐረብኛ” ማለት ሲሆን በሥነ-ሰዋስው ገላጭ ቅጽል ነው፥ ቁርኣን የወረደው ዐረቢኛ ሆኖ ነው። ከዐረቢኛው ቁርኣን ውጪ ያሉት የዐማርኛ፣ የእንግሊዝኛ፣ የፈረንሳይኛ፣ የስውዲንኛ መጽሐፎች ቁርኣን ሳይሆኑ የቁርኣን ትርጉም ናቸው፦
41፥3 አንቀጾቹ የተብራሩ የኾነ መጽሐፍ ነው፡፡ *ዐረብኛ ቁርኣን ሲኾን ለሚያውቁ ሕዝቦች የተብራራ ነው*፡፡ كِتَابٌ فُصِّلَتْ آيَاتُهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لِّقَوْمٍ يَعْلَمُونَ

"ተርጂም" تَرْجِم ማለት "ተርጀመ" تَرْجَمَ ‎ማለትም "ተረጎመ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ትርጉም"translation" ማለት ነው፥ "ሙተርጂም" مُتَرْجِم ወይም "ተርጁማን" تَرْجُمَان‎ ማለት ደግሞ "ተርጓሚ"translator" ማለት ነው። የሙተርጂም ወይም የተርጁማን ብዜት "ሙተርጂሙን" مُتَرْجِمُون ወይም "ተራጂም" تَرَاجِيم ማለትም "መተርጉማን" ነው። ለምሳሌ ቁርኣንን ወደ ሌላ ቋንቋ የመተርጎም ሥራ "ተርጂም" تَرْجِم ይባላል። የቅዱስ ቁርኣን ትርጉም አሳቡ እንጂ ቃላቱ አይተረጎምም፥ ከባድ ነው። በዐረቢኛ አቻ ቃል ሳይገኝ ሲቀር ወይም ሌላ አንቀጽ ላይ የተብራራ አንቀጽ ሆኖ ሲገኝ የዐማርኛ ተርጓሚዎች በቅንፍ የማስቀመጥ ልምድ አላቸው። ስለዚህ የቅዱስ ቁርኣን ትርጉም "ተለዋዋጭ አቻ"dynamic equivalence" ትርጉም እንጂ "መደበኛ አቻ"formal equivalence" ትርጉም ስለሌለው የዐማርኛ መተርጉማን በቅንፍ ማስቀመጣቸው የአሳብ ትርጉምን ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው።
የተሰናኘ ስንኝ"syntax" ማኅበረሰቡ ሊረዳው በሚችል መልኩ መድረስ ይችላል፥ ይህንን ስንኝ ቃልን በቃል የመተርጎም ሥራ "የቃል ትርጉም"metaphrase or word-for-word translation" ሲባል፥ ቃልን በአሳብ የመተርጎም ሥራ ደግሞ "የአሳብ ትርጉም"paraphrase or Sense-for-sense translation" ይባላል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የከለር ልዩነት ውበት ነው!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

30፥22 ሰማያትንና ምድርንም መፍጠሩ፣ የቋንቋዎቻችሁ እና *”የመልኮቻችሁም መለያየት፣ ከአስደናቂ ተዓምራቶቹ ነው”*፡፡ በዚህ ውስጥ *”ለዐዋቂዎች ተዓምራቶች አሉበት”*፡፡ وَمِنْ ءَايَٰتِهِۦ خَلْقُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَٱخْتِلَٰفُ أَلْسِنَتِكُمْ وَأَلْوَٰنِكُمْ ۚ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَٰتٍۢ لِّلْعَٰلِمِينَ

“አደም” آدَم የሚለው ቃል 25 ጊዜ በቁርኣን የመጣ ሲሆን “አዳም” ማለትም “አፈር” “መሬት” “ቀይ” ወይም “ሰው” ከሚል ሴማዊ ቃል የመጣው ነው፤ አላህ አደምን የፈጠረው ከምድር አፈር ነው፦
15:28 ጌታህም ለመላእክት ባለጊዜ አስታውስ፡፡ *እኔ ሰውን ከሚቅጨለጨል ሸክላ ከሚገማ ጭቃ እፈጥራለሁ*፡፡ وَإِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي خَالِقٌ بَشَرًا مِّن صَلْصَالٍ مِّنْ حَمَإٍ مَّسْنُونٍ
38:71 ጌታህ «ለመላእክት እኔ ሰውን ከጭቃ ፈጣሪ ነኝ ባለ ጊዜ» አስታውስ፡፡ إِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي خَالِقٌ بَشَرًا مِّن طِينٍ
71:17 አላህም *ከምድር ማብቀልን አበቀላችሁ*። وَاللَّهُ أَنبَتَكُم مِّنَ الْأَرْضِ نَبَاتًا
71፥18 *ከዚያም በውስጧ ይመልሳችኋል። ማውጣትንም ያወጣችኋል*። ثُمَّ يُعِيدُكُمْ فِيهَا وَيُخْرِجُكُمْ إِخْرَاجًا
20፥55 *ከእርሷ ከምድር ፈጠርናችሁ፤ በእርሷም ውስጥ እንመልሳችኋለን፤ ከእርሷም በሌላ ጊዜ እናወጣችኋለን*። مِنْهَا خَلَقْنَاكُمْ وَفِيهَا نُعِيدُكُمْ وَمِنْهَا نُخْرِجُكُمْ تَارَةً أُخْرَىٰ

አላህ ምድር ላይ የተለያየ ከለር አብቅሏል፤ ከአፈር ብዙ ዓይነቶችም ቀለማት አድርጎ አበቀለን፦
50፥7 ምድርንም ዘረጋናት፡፡ በእርሷም ውስጥ ጋራዎችን ጣልንባት፡፡ በውስጧም ከሚያስደስት *”ዓይነት ሁሉ አበቀልን”*፡፡ وَٱلْأَرْضَ مَدَدْنَٰهَا وَأَلْقَيْنَا فِيهَا رَوَٰسِىَ وَأَنۢبَتْنَا فِيهَا مِن كُلِّ زَوْجٍۭ بَهِيجٍۢ
78፥7 *”ብዙ ዓይነቶችም”* አድርገን ፈጠርናችሁ፡፡ وَخَلَقْنَٰكُمْ أَزْوَٰجًۭا
71፥17 አላህም *”ከምድር ማብቀልን አበቀላችሁ”*፡፡ وَٱللَّهُ أَنۢبَتَكُم مِّنَ ٱلْأَرْضِ نَبَاتًۭا
30፥22 ሰማያትንና ምድርንም መፍጠሩ፣ የቋንቋዎቻችሁ እና *”የመልኮቻችሁም መለያየት፣ ከአስደናቂ ተዓምራቶቹ ነው”*፡፡ በዚህ ውስጥ *”ለዐዋቂዎች ተዓምራቶች አሉበት”*፡፡ وَمِنْ ءَايَٰتِهِۦ خَلْقُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَٱخْتِلَٰفُ أَلْسِنَتِكُمْ وَأَلْوَٰنِكُمْ ۚ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَٰتٍۢ لِّلْعَٰلِمِينَ

አላህ አደምን ከተለያየ የአፈር አይነት መፍጠሩ በዘሮቹ የቀለም ልዩነት ለማኖር ነው፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3213
አቡ ሙሳ እንደተረከው የአላህ መልክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ከፍ ያለው አላህ አደምን ከጭብጥ አፈር ፈጠረው፤ እርሱም ከሁሉም የምድር ክፍል ወስዶ ፈጠረው፤ ስለዚህ የአደም ልጆች አንዳንዶቹ ቀይ፣ ነጭ፣ ጥቁር፣ ጠይም ወዘተ…ሆኑ። عَنْ أَبِي مُوسَى الأَشْعَرِيِّ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ إِنَّ اللَّهَ تَعَالَى خَلَقَ آدَمَ مِنْ قَبْضَةٍ قَبَضَهَا مِنْ جَمِيعِ الأَرْضِ فَجَاءَ بَنُو آدَمَ عَلَى قَدْرِ الأَرْضِ فَجَاءَ مِنْهُمُ الأَحْمَرُ وَالأَبْيَضُ وَالأَسْوَدُ وَبَيْنَ ذَلِكَ وَالسَّهْلُ وَالْحَزْنُ وَالْخَبِيثُ وَالطَّيِّبُ ‏”‏

ሰውነታችን ውስጥ ካርበን፣ አይረን፣ ሃይድሮጅን፣ ናይትሮጅን፣ ካልሲየም፣ ማግኒዝየም፣ ፓታሺየም፣ ፎስፎረስ፣ ሰልፈር፣  ኮፐር፣ ዚንክ መኖራቸው በራሱ ከአፈር መሰራታችን ማስረጃዎች ናቸው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የእግዚአብሔር ልጅ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

18፥4 *እነዚያንም፦ “አላህ ልጅን ይዟል” ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት አወረደው*፡፡ وَيُنذِرَ الَّذِينَ قَالُوا اتَّخَذَ اللَّهُ وَلَدًا

ክርስቲያኖች ኢየሱስ “የእግዚአብሔር ልጅ” ነው ይላሉ፤ “ልጅ” ማለት ምን ማለት ነው? ስንላቸው፦ “አብን አህሎና መስሎ ከአብ “ባህርይ ዘእም-ባህርይ አካል ዘእም-አካል” ማለትም ከባህርይው ባህርይ ወስዶ ከአካሉ አካሉን ወስዶ ተወለደ” ይሉናል። እረ ከሰማናቸው፦ “አምላክ ዘእም-አምላክ ማለትም ከአምላክ የተገኘ አምላክ” ይሉናል። ይህ ኑባሬአዊ እሳቤ”ontological sense” ነው፤ ከእዚህ እሳቤ ቁርኣን በተቃራኒው፦ “አላህ ወለደ” ያሉ በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው፤ አላህ አልወለደም፤ አልተወለደምም፤ እንደውም አላህ ቁርኣን ካወረደበት ምክንያት አንዱ እነዚያንም፦ “አላህ ልጅን ይዟል” ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት ነው፦
37፥152 ፦ *“አላህ ወለደ” አሉ፤ እነርሱም በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው*፡፡ وَلَدَ اللَّهُ وَإِنَّهُمْ لَكَاذِبُونَ
112፥3 *አልወለደም፤ አልተወለደምም*፡፡ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ
18፥4 *እነዚያንም፦ “አላህ ልጅን ይዟል” ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት አወረደው*፡፡ وَيُنذِرَ الَّذِينَ قَالُوا اتَّخَذَ اللَّهُ وَلَدًا

ይህንን የቁርኣን እሳቤ ካየን ዘንዳ ባይብል ላይ እግዚአብሔር አባት መባሉ “አስገኚ” ወይም “ፈጣሪ” በሚል ፍካሬአዊ እሳቤ “ideological sense” መጥቷል፦
ሚልክያስ 2፥10 ለሁላችን *”አንድ አባት”* ያለን አይደለምን? *አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን*?
ዮሐንስ 8፥41 *አንድ አባት* አለን *እርሱም እግዚአብሔር ነው*፡ አሉት።
ኤፌሶን 4፥6 ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር *አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ*።

ለምሳሌ መላእክት መናፍስት ተብለዋል፤ እግዚአብሔር የመናፍስት አባት ነው። መናፍስቱ መላእክት የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው፦
ዕብራውያን 12፥9 እንዴትስ ይልቅ *ለመናፍስት አባት* አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር በተገባን?
ዕብራውያን 1፥14 *ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?*
ኢዮብ 38፥7 አጥቢያ ኮከቦች በአንድነት ሲዘምሩ፥ *የእግዚአብሔርም ልጆች* ሁሉ እልል ሲሉ፥

መላእክት የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉት ያለ እናት እና ያለ አባት ስለፈጠራቸው እንደሆነ ቅቡል ነው፤ አዳምም የእግዚአብሔር ልጅ ተብሏል፦
ሉቃስ 3፥38 የሴት ልጅ፥ የአዳም ልጅ፥ *የእግዚአብሔር ልጅ*።

አዳም የእግዚአብሔር ልጅ የተባለው ያለ እናት እና ያለ አባት ስለፈጠረው እንደሆነ እሙን ነው፤ ታዲያ ያለ አባት በእናት ብቻ የተፈጠረው ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ቢባል ምን ይደንቃል? ከማርያም ተጸንሶ የተወለደው ሰው መሆኑን አንርሳ፦
ሉቃስ 1፥35 ስለዚህ ደግሞ *ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል*።
ገላትያ 4 ፥4 ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ *እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ*፤

ማርያም የወለደችው መለኮትን ሳይሆን ሰው ብቻ ነው፤ ያም ሰው የእግዚአብሔር ልጅ መባሉ ፈጣሪ ያለ አባት ከእርሷ መፍጠሩን ያሳያል። አይ እግዚአብሔር ኢየሱስን ወለደው ይሉናል፦
መዝሙር 2፥7 ትእዛዙን እናገራለሁ፤ *እግዚአብሔር አለኝ። አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ “ወለድሁህ”*።
ዕብራውያን 1:5 ከመላእክትስ። *እግዚአብሔር አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ “ወልጄሃለሁ”*፥ (አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ጭራሽ ይህ ጥቅስ “ዛሬ” የምትለዋ ቃል መነሻ ጊዜን ታመለክታለች፣ ይህም የኢየሱስ መፈጠር በጊዜ ውስጥ መሆኑን ያሳያል፤ ሲቀጥል እዚህ ጥቅስ ላይ እግዚአብሔር ኢየሱስን፦ “አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ” ብሏል ተብሏል፤ ይህ የሚያሳየው ኢየሱስ “አንተ” ብሎ ካናገረው እግዚአብሔር የተለየ መሆኑን ያሳያል፣ እግዚአብሔር ለኢየሱስ “አባት እሆነዋለው” ኢየሱስ ለእግዚአብሔር “ልጅ ይሆነኛል” ብሏል ተብሏል” ሲሰልስ “ወልጄሃለሁ” የሚለው ቃል “ጌኔካ” γεγέννηκά ሲሆን “ጌኑስ” γένος ማለትም “ወለደ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን በፍካሬአዊ ትርጉም “ፈጠረ” ሲሆን አይሁዳውያን አምላክ ፆታ ስለሌለውን “መወለድ” ማለት “መፈጠር” ነው ብለው ያምናሉ፤ ምክንያቱን ተራራ እንደተወለደ ስለሚናገር፤ ያ ማለት ተራራ ተሰራ ማለት ነው፦
አሞፅ 4:13 እነሆ፥ *”ተራሮችን የሠራ”*፥
መዝሙር 90:2 *”ተራሮች ሳይወለዱ”*፥ בְּטֶרֶם, הָרִים יֻלָּדו
ግሪክ ሰፕቱአጀንት፦
πρὸ τοῦ ὄρη γενηθῆναι καὶ πλασθῆναι τὴν γῆν καὶ τὴν οἰκουμένην,

በዕብራይስጡ “ዩላዱ” יֻלָּדו ማለት “ሳይወለዱ” ማለት ነው። “ሳይወለዱ” የሚለው ፍካሬአዊ ቃል በእማሬያዊ ቃል “ሳይፈጠሩ” ማለት ነው። ግሪክ ሰፕቱአጀንት ላይ ደግሞ በተመሳሳይ “ጌኒቲና” γενηθηναι ማለትም “ሳይወለዱ” የሚለው በተመሳሳይ “ጌኑስ” γένος ማለትም “ወለደ” ከሚል ግስ የመጣ ነው፤ “ወለደ” ማለት “ፈጠረ” ማለት መሆኑን “የወለደህን አምላክ” የሚለው ቃል “የፈጠረውን አምላክ” በሚል ተለዋዋጭ ቃል መምጣቱ ነው፦
ዘዳግም 32፥18 *የወለደህን አምላክ ተውህ*፥ NIV
ዘዳግም 32፥15 ይሹሩን ወፈረ፥ ረገጠ፤ ወፈረ፥ ደነደነ፥ ሰባ፤ *የፈጠረውንም አምላክ ተወ*፤ NIV

“ይሽሩ” የእስራኤላውያን የቁልምጫ ስም ነው፤ አምላክ እስራኤላውን “ወለደ” ወይስ “ፈጠረ” ? አይ ፈጣሪ ጾታ ስለሌለው በእማሬአዊ ቃል ወለደ ማለት ሳይሆን በፍካሬአዊ ቃል ፈጠረ ለማለት ነው ከተባለ እንግዲያውስ ከላይ ያለውንም በዚህ ስሌትና ቀመር ተረዱት። መወለድ መፈጠር ባይሆን ኖሮ ሰማይንና ምድር ፍጥረት ሆኖ ሳለ “ልደት” ባልተባለ ነበር፤ ስለ ሰማይንና ምድር አፈጣጠር የሚናገረው መጽሐፍ “ዘፍጥረት” ይባላል፤ “ፍጥረት” በሚል ቃል ላይ ያለው መነሻ ቅጥያ “ዘ’ አያያዥ መስተዋድድ “የ” ማለት ነው፤ “የፍጥረት” ማለት ነው፤ በግዕዙ አርስት ላይ “ዘልደት” ይባላል፦
ዘፍጥረት 2፥4 እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድርን ባደረገ ቀን፥ በተፈጠሩ ጊዜ *”የሰማይና የምድር ልደት”* ይህ ነው።
ግዕዙ፦
ዝንቱ *”ፍጥረተ ሰማይ ወምድር”* ዘምአመ ኮነት ዕለት አንተ ባቲ ገብረ እግዚአብሔር ሰማየ ወምድረ።
ግሪክ ሰፕቱአጀንት፦
Αὕτη ἡ βίβλος γενέσεως οὐρανοῦ καὶ γῆς, ὅτε ἐγένετο· ᾗ ἡμέρᾳ ἐποίησε Κύριος ὁ Θεὸς τὸν οὐρανὸν καὶ τὴν γῆν

“ጀነሲዋስ” γενέσεως ማለት “ልደት” ማለት ነው፤ “Genesis” የሚለው የኢንግሊዝኛው ስያሜ “ጀነሲስ” γένεσις ከሚለው ከግሪኩ ቃል የመጣ ነው፤ መቼም ሰማይና ምድር ልደት አለው ሲባል ፈጣሪ ወለደው ማለት ሳይሆን መፍጠሩን የሚያሳይ ስለሆነ ግዕዙ፦ “ፍጥረተ ሰማይ ወምድር” ማለት “የሰማይና የምድር ፍጥረት” ማለት ነው፤ “ልደት” ማለት “ፍጥረት” ማለት ስለሆነ “አዲስ ፍጥረት” የሚለውን ተክቶ “አዲስ ልደት” ተብሏል፦
2ኛ ቆሮንቶስ 5፥17 ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን *”አዲስ ፍጥረት”* ነው።
ቲቶ 3፥5 እንደ ምሕረቱ መጠን *”ለአዲስ ልደት”* γένεσις በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥
ታዲያ ኢየሱስ ልደት አልነበረውምን? ልደቱ ግን ከመንፈስ ቅዱስ በመጸነስ ነው፤ ፈጣሪ ያለ ወንድ ዘር ስለፈጠረው ልደት አለው፤ ዓለም ሳይፈጠር በነበረው የቀድሞ ዕቅዱ ከድንግል ማርያም ማህጸን ፈጠረው፦
ማቴዎስ 1፥18 የኢየሱስ ክርስቶስም *”ልደት”* γένεσις እንዲህ ነበረ። እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች።
መዝሙር 110፥3 ከአንተ ጋር ቀድሞ በኃይልህ ቀን፥ በቅዱሳን ብርሃን፥ ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ ከማህጸን ወለድሁህ። μετὰ σοῦ ἡ ἀρχὴ ἐν ἡμέρᾳ τῆς δυνάμεώς σου ἐν ταῖς λαμπρότησι τῶν ἁγίων σου· ἐκ γαστρὸς πρὸ ἑωσφόρου ἐγέννησά σε.

የተወለደው በኃይሉ ቀን ነው፤ የቅዱሳን ብርሃን በሆነው በመንፈስ ቅዱስ ነው፤ ይህ የግሪክ ሰፕቱጀንት እንጂ የማሶሬቲኩ ላይ ቃላቱ የለም። ከማርያም ማህጸን “ወለድሁህ” ማለት “ፈጠርኩ” ማለት ካልሆነ ችግር ይፈጠራል። ሃይማኖተ-አበው ላይ የቂሳሪያው ባስልዮስ “ወለደኝ” ማለት “ፈጠረኝ” ማለት ነው ብሎ ፍርጥ አድርጎ ነግሮናል፦
ሃይማኖተ-አበው ዘባስልዮስ ምዕራፍ 32 ቁጥር 18
ግዕዙ፦
*”ወለደኒ ይተረጎም በወልደ እግዚአብሔር ወብሂለ ፈጠረኒ በእንተ ትስብእቱ”*
ትርጉም፦
*”ወለደኝ” ማለት የእግዚአብሔር ልጅ ስለመሆኑ “ፈጠረኝ” ማለትም ሰው ስለ መሆኑ ይተረጎማል”*

አንዳንድ ቂሎች “መወለድ” ከአብ “መውጣት” ነው ይላሉ፤ ምነው መንፈስ ቅዱስ ከአብ የሚወጣ ነው ትሉ የለ እንዴ? ለምን መንፈስ ቅዱስን የአብ ልጅ አትሉትም? አይ “መውጣት” ማለት “መስረጽ” ነው ካላችሁ ለምንስ ወልድን ከአብ የሰረጸ ነው አትሉትም? ምክንያቱም ወልድም ከአብ የወጣ ነው ስለሚል፤ አይ መውጣት መላክ ማለት ነው ካላችሁ ጥሩ። ካልሆነ ልጅ ማለት፦ “አብን አህሎና መስሎ ከአብ ባህርይ ዘእም-ባህርይ አካል ዘእም-አካል ማለትም ከባህርይው ባህርይ ወስዶ ከአካሉ አካሉን ወስዶ ተወለደ፤ አምላክ ዘእም-አምላክ ማለትም ከአምላክ የተገኘ አምላክ” ካላችሁ ይህንን እሳቤ አይደለም ቁርኣን ባይብላችሁም አይደግፋችሁ። በዚህ ስሌት ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል፦
19፥35 *ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል*፡፡ مَا كَانَ لِلَّهِ أَن يَتَّخِذَ مِن وَلَدٍ ۖ سُبْحَانَهُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ
2፥116 *አላህም ልጅ አለው አሉ፡፡ ከሚሉት ጥራት ተገባው፡፡ አይደለም በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ ሁሉም ለእርሱ ታዛዦች ናቸው*፡፡ وَقَالُوا۟ ٱتَّخَذَ ٱللَّهُ وَلَدًۭا ۗ سُبْحَٰنَهُۥ ۖ بَل لَّهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ ۖ كُلٌّۭ لَّهُۥ قَٰنِتُونَ
2፥117 ሰማያትንና ምድርን ያለብጤ ፈጣሪ ነው፤ *ነገርንም ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው፡- «ኹን» ነው፤ ወዲያውም ይኾናል*፡፡ بَدِيعُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ وَإِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ነጃሺይ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥83 *"ወደ መልክተኛውም የተወረደውን ቁርኣን በሰሙ ጊዜ እውነቱን ከማወቃቸው የተነሳ ዓይኖቻቸው እንባን ሲያፈሱ ታያለህ፡፡ «ጌታችን ሆይ! አመንን ከመስካሪዎቹም ጋር ጻፈን » ይላሉ"*፡፡ وَإِذَا سَمِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَى الرَّسُولِ تَرَىٰ أَعْيُنَهُمْ تَفِيضُ مِنَ الدَّمْعِ مِمَّا عَرَفُوا مِنَ الْحَقِّ ۖ يَقُولُونَ رَبَّنَا آمَنَّا فَاكْتُبْنَا مَعَ الشَّاهِدِينَ

"አል-ሐበሻህ" الْحَبَشَة ማለት "አሰባሳቢው" ማለት ሲሆን የመን ከሚኖሩ በመህራህ ሕዝቦች መካከል ሲኖሩ "የዕጣን አሰባሳቢዎች" ይባሉ የነበሩ ናቸው። "አል-ሐበሻህ" የመን ከሚኖሩ ከመህራህ ሕዝቦች ወደ ሰሜኑ ክፍል የተሰበሰቡ ሴማዊ ሕዝቦች መጠሪያ ነው። ስለ አል-ሐበሻህ በግርድፉና በሌጣው ካየን ዘንዳ ቁርኣን ሲወርድ በአል-ሐበሻህ ውስጥ ስለ ነገሠው ንጉሥ ደርዝና ፈርጅ ባለው መልኩ እንዳስሳለን።
"ነጃሺይ" نَّجَاشِيَّ ማለት "ንጉሥ" ማለት ሲሆን ወደ ጠቃሽ አመልካች መስተአምር "አል" ال ተደርጎ ሲነበብ "አን-ነጃሺይ" النَّجَاشِيَّ ሲሆን "ንጉሡ"the king" ማለት ነው። ይህ ንጉሥ እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠት ከ 614–631 ድኅረ-ልደት በአክሱም መንግሥት የነገሠ ንጉሥ ነው፥ ስሙም በዐረቢኛ አነባነብ "አስሐማህ" أَصْحَمَة ሲባል፥ በአገራችን "አርማህ" ይባላል። "ንጉሥ አርማህ" በነቢያችን"ﷺ" ሐዲስ በጥቅሉ "አስሐማህ አን-ነጃሺይ" أَصْحَمَةَ النَّجَاشِيِّ ይባላል። ይህ ንጉሥ የነቢያችን"ﷺ" ባልደረቦች ከ 615–616 ድኅረ-ልደት ተቀብሎ አስተናግዷል፥ እንዲሁ እርሱ እና ሹማምንቱ ወደ መልክተኛውም የተወረደውን ሱረቱል መርየምን በሰሙ ጊዜ እውነቱን ከማወቃቸው የተነሳ ዓይኖቻቸው እንባን አንብተዋል፦
5፥83 *"ወደ መልክተኛውም የተወረደውን ቁርኣን በሰሙ ጊዜ እውነቱን ከማወቃቸው የተነሳ ዓይኖቻቸው እንባን ሲያፈሱ ታያለህ፡፡ «ጌታችን ሆይ! አመንን ከመስካሪዎቹም ጋር ጻፈን » ይላሉ"*፡፡ وَإِذَا سَمِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَى الرَّسُولِ تَرَىٰ أَعْيُنَهُمْ تَفِيضُ مِنَ الدَّمْعِ مِمَّا عَرَفُوا مِنَ الْحَقِّ ۖ يَقُولُونَ رَبَّنَا آمَنَّا فَاكْتُبْنَا مَعَ الشَّاهِدِينَ

የንጉሡ መሥለም የኢሥላም ጠል"Islamophobia" አቀንቃኝ የሆነው ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እንደዋሸው የአክራሪዎች ፈጠራ ሳይሆን "ጌታችን ሆይ! አመንን ከመስካሪዎቹም ጋር ጻፈን" ብለው በቁርኣኑ ማመናቸውን አምላካችን አላህ በቅዱስ ቃሉ እንደነገረን ነው። ከመጽሐፉም ባለቤቶች ለአላህ ፈሪዎች በአላህ አንቀጾችም ጥቂትን ዋጋ የማይለወጡ እነ ነጃሺይ እና ሹማምንቱ በአላህ እና በዚያ ወደ እኛ በተወረደው ቁርኣን አምነዋል፦
3፥199 *"ከመጽሐፉም ባለቤቶች ለአላህ ፈሪዎች በአላህ አንቀጾችም ጥቂትን ዋጋ የማይለወጡ ሲኾኑ በአላህ እና በዚያ ወደ እናንተ በተወረደው፥ በዚያም ወደ እነርሱ በተወረደው የሚያምኑ ሰዎች አሉ፡፡ እነዚያ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው*፡፡ አላህ ምርመራው ፈጣን ነው፡፡ وَإِنَّ مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ لَمَن يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَمَا أُنزِلَ إِلَيْكُمْ وَمَا أُنزِلَ إِلَيْهِمْ خَاشِعِينَ لِلَّهِ لَا يَشْتَرُونَ بِآيَاتِ اللَّهِ ثَمَنًا قَلِيلًا ۗ أُولَـٰئِكَ لَهُمْ أَجْرُهُمْ عِندَ رَبِّهِمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ سَرِيعُ الْحِسَابِ

በአላህ እና በዚያ ወደ እኛ በተወረደው ቁርኣን ካመኑ ሠልመዋል ማለት ነው። በነቢያችንም"ﷺ" ሐዲስ ላይ ነቢያችን"ﷺ" ነጃሺይ ከመስለምም አልፎ ጻዲቅ ሰው እንደሆነ ነግረውናል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 63, ሐዲስ 103
ጃቢር እንደተረከው፦ "አን-ነጃሺይ በሞተ ጊዜ "ነቢዩም"ﷺ" አሉ፦ *"ዛሬ ጻዲቅ ሰው ሞቷል፥ ተነሱ! ለወንድማችሁ ለአስሐማህ የግንዘት ጸሎት አድርጉ!"*። عَنْ جَابِرٍ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم حِينَ مَاتَ النَّجَاشِيُّ ‏ "‏ مَاتَ الْيَوْمَ رَجُلٌ صَالِحٌ، فَقُومُوا فَصَلُّوا عَلَى أَخِيكُمْ أَصْحَمَةَ

"ሷሊሕ" صَالِح ማለት "መልካም" ወይም ጻዲቅ" ማለት ሲሆን የሷሊሕ ብዙ ቁጥር "ሷሊሒን" صَّالِحِين ማለትም "መልካሞች" ወይም "ጻድቃን" ማለት ነው፦
3፥114 በአላህና በመጨረሻው ቀን ያምናሉ፡፡ በጽድቅ ነገርም ያዛሉ፡፡ ከመጥፎ ነገርም ይከለክላሉ፡፡ በበጎ ሥራዎችም ይጣደፋሉ፡፡ እነዚያም ከመልካሞቹ ናቸው፡፡ يُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ وَيَأْمُرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَوْنَ عَنِ الْمُنكَرِ وَيُسَارِعُونَ فِي الْخَيْرَاتِ وَأُولَـٰئِكَ مِنَ الصَّالِحِينَ
2፥130 ከኢብራሂምም ሕግጋት እራሱን የበደለ ሰው ካልኾነ በስተቀር የሚያፈገፍግ ማነው? ማንም የለም። በቅርቢቱም ዓለም በእርግጥ መረጥነው፥ *በመጨረሻይቱም ዓለም እርሱ ከመልካሞቹ ነው*፡፡ وَمَن يَرْغَبُ عَن مِّلَّةِ إِبْرَاهِيمَ إِلَّا مَن سَفِهَ نَفْسَهُ ۚ وَلَقَدِ اصْطَفَيْنَاهُ فِي الدُّنْيَا ۖ وَإِنَّهُ فِي الْآخِرَةِ لَمِنَ الصَّالِحِينَ

አስሐማህ አን-ነጃሺይ "ሷሊሕ" መባሉን አስተውል። ከዚያ በመቀጠል እርሱ የነቢያችን"ﷺ" ባልደረቦች የሃይማኖት ወንድም ስለሆነ "አኺኩም" أَخِيكُمْ ማለትም "ወንድማችሁ" ተብሏል። ምእመናን ደግሞ ወንድማማቾች ናቸው፦
49፥10 *"ምእመናን ወንድማማቾች ናቸው"*፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ إِخْوَةٌ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 63, ሐዲስ 106
አቢ ሁረይራህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" ለባልደረቦቻቸው ስለ ስለዚያ ቀን ስለሞተበት ስለ ሐበሻው አን-ነጃሺይ ሞት እንደነገሯቸው፦ *"ለወንድማችሁ ኢሥቲግፋር አርጉ!"*። أَنَّ أَبَا هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ أَخْبَرَهُمَا أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم نَعَى لَهُمُ النَّجَاشِيَّ صَاحِبَ الْحَبَشَةِ فِي الْيَوْمِ الَّذِي مَاتَ فِيهِ، وَقَالَ ‏ "‏ اسْتَغْفِرُوا لأَخِيكُمْ ‏"‌‏
በኢሥላም "ሶላቱል ጀናዛህ" صَلَاة الجَنَازَة ማለትም "የግንዘት ጸሎት" የሚደረገው ለሙሥሊም ብቻ ነው። ለንጉሥ አርማህ ደግሞ የሶላቱል ጀናዛህ ክፍል የሆነው "ሶላቱል ጋኢብ" صَلَاة الغَائِبٌ ማለትም "የሩቅ ጀናዛህ" ተደርጓል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 63, ሐዲስ 105
ጃቢር አብኑ ዐብደሏህ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" አስሐማህ አን-ነጃሺይ ላይ የግንዘት ጸሎት አድርገዋል፥ አራት ተክቢራህ በእርሱ ላይ አድርገዋል"*። عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ ـ رضى الله عنهما أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم صَلَّى عَلَى أَصْحَمَةَ النَّجَاشِيِّ، فَكَبَّرَ عَلَيْهِ أَرْبَعًا‏

ከላይ የተዘረዘሩት ሐዲሳት ንጉሥ አርማህ የአላህ ጥሪ ተውሒድን እንደተቀበለ ፍንትውና ቁልጭ አድርጎ ያሳያሉ። ስለዚህ የኢሥላም ጠል አቀንቃኝ የሆነው ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በማኅበራዊ መገናኛ-ብዙኃን ላይ የነዛው ጨባጣና ለማጣ ወሬ እንዲህ ድባቅ ይገባል። አስሐማህ አን-ነጃሺይ መሥለሙ በዓለም የሚገኝ መላው ሙሥሊም ሁሉ የሚቀበለው እውነታ ነው። ይህን እውነታ አለመቀበል ትችላለክ፥ ግን ይህ ትርክት የአክራሪዎች እንጂ የሁሉም ሙሥሊም እንዳይደለ ለመቅጠፍ የሞከርከው ቅጥፈት ለዛሬ አልተሳካልህም። በአፈ-ጮሌነት ቤተ-መንግሥት እንደገባከው በአፈ-ጮሌነት ጀነት አትገባም። አላህ ሂዳያህ ይስጥህ፥ ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሙሲባህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

42፥30 *”ከመከራም ማንኛውም ያገኛችሁ ነገር እጆቻችሁ በሠሩት ምክንያት ነው”*፡፡ ከብዙውም ይቅር ይላል፡፡ وَمَا أَصَابَكُم مِّن مُّصِيبَةٍ فَبِمَا كَسَبَتْ أَيْدِيكُمْ وَيَعْفُو عَن كَثِيرٍ

አላህ “አል-ዐሊም” العَلِيم ማለትም “ሁሉን ዐዋቂ ነው፤ “ዒልም” عِلْم ማለትም “ዕውቀት” ደግሞ የእርሱ ባህርይ ነው፤ አላህ ሁሉን ነገር ያካበበው በዕውቀቱ ነው፦
65፥12 አላህ በነገር ሁሉ ቻይ መሆኑን አላህም *በነገሩ ሁሉ በእውቀት ያካበበ መሆኑን ታውቁ ዘንድ ይህንን አሳወቃችሁ*። أَنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ وَأَنَّ اللَّهَ قَدْ أَحَاطَ بِكُلِّ شَيْءٍ عِلْمًا

እዚህ አንቀፅ ላይ የምንመለከተው የአላህ “ዕውቀት” እና “ሸይእ” شَيْء ማለት “ነገር’thing” ሁለት ጉዳዮች መሆናቸውን ነው፥ “ዕውቀት” ምንም ነገር ሳይኖር የአላህ ባህርይ ሲሆን “ነገር” ደግሞ “ፍጡር” ነው፥ “ነገር” ደግሞ ጊዜና ቦታ ሁሉ ነው። አምላካችን አላህ ስለ አንድ ነገር ዕውቀት በመጽሐፍ ውስጥ ከሁሉ ነገር መከሰት፣ መደረግ እና መከናወን በፊት መዝግቦቷል፦
50፥4 ከእነርሱ ምድር የምታጎድለውን በእርግጥ *ዐውቀናል፡፡ እኛም ዘንድ ጠባቂ መጽሐፍ አለ*፡፡ قَدْ عَلِمْنَا مَا تَنقُصُ الْأَرْضُ مِنْهُمْ ۖ وَعِندَنَا كِتَابٌ حَفِيظٌ
22፥70 አላህ *በሰማይና በምድር ውስጥ ያለን ሁሉ በእርግጥ የሚያውቅ መኾኑን አታውቅምን? ይህ በመጽሐፍ ውስጥ የተመዘገበ ነው*፡፡ ይህ በአላህ ላይ ገር ነው፡፡ أَلَمْ تَعْلَمْ أَنَّ اللَّهَ يَعْلَمُ مَا فِي السَّمَاءِ وَالْأَرْضِ ۗ إِنَّ ذَٰلِكَ فِي كِتَابٍ ۚ إِنَّ ذَٰلِكَ عَلَى اللَّهِ يَسِيرٌ
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 54, ሐዲስ 414
የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ በመጀመሪያ ምንም ነገር ሳይኖር አላህ ነበረ፤ ከዚያ ዙፋኑን በውሃ ላይ ነበረ፤ *ከዚያ ሁሉን ነገር በመጽሐፍ ጻፈ*፤ ከዚያ ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ። كَانَ اللَّهُ وَلَمْ يَكُنْ شَىْءٌ غَيْرُهُ، وَكَانَ عَرْشُهُ عَلَى الْمَاءِ، وَكَتَبَ فِي الذِّكْرِ كُلَّ شَىْءٍ، وَخَلَقَ السَّمَوَاتِ وَالأَرْضَ ‏”‌‏.

“ለውሐል መሕፉዝ” لَوحَ المَّحْفُوظ ማለት “የተጠበቀው ሰሌዳ”preserved tablet” ማለት ሲሆን አላህ በለውሐል መሕፉዝ ላይ ድርጊቱን የከተበው ስለሚያውቀው እንጂ እንዲከናወን አይደለም።
ለምሳሌ ሀራም ነገር ማድረግ ከልክሏል፤ ያንን የከለከለው አንድ ሰው ከማድረጉ በፊት አላህ የከተበው ስለሚያውቀው እንጂ ያ ሰው እንዲያደርገው አይደለም፤ ያ ቢሆንማ አላህ እንዲያደርግ መከልከሉና በማድረጉ መቅጣቱ ትርጉም አይኖረውም ነበር። ስለዚህ አምላካችን አላህ አንድ ክስተት ከመከሰቱ ቢፊት፣ አንድ ድርጊት ከመደረጉ በፊት፣ አንድ ክንውን ከመከናወኑ በፊት ስለሚያውቀው ያንን ዕውቀት በተጠበቀው ሰሌዳ ከትቦታል፦
57፥22 በምድርም በነፍሶቻችሁም መከራ ማንንም አትነካም *ሳንፈጥራት በፊት በመጽሐፍ የተመዘገበች ብትኾን እንጅ*፡፡ ይህ በአላህ ላይ ገር ነው፡፡ مَا أَصَابَ مِن مُّصِيبَةٍ فِي الْأَرْضِ وَلَا فِي أَنفُسِكُمْ إِلَّا فِي كِتَابٍ مِّن قَبْلِ أَن نَّبْرَأَهَا ۚ إِنَّ ذَٰلِكَ عَلَى اللَّهِ يَسِيرٌ

“ሙሲባህ” مُّصِيبَة ማለት “መከራ” ማለት ሲሆን ይህ ሙሲባህ ክስተት ሆኖ ከመከሰቱ ቢፊት፣ ድርጊት ሆኖ ከመደረጉ በፊት፣ ክንውን ሆኖ ከመከናወኑ በፊት አላህ ስለዚያ ሙሲባህ ስለሚያውቀው ያንን ዕውቀት በተጠበቀው ሰሌዳ ከትቦታል። ያ ሙሲባህ የሚከሰተው አላህ ስለፈቀደ ነው፦
64፥11 *”መከራም ማንንም አይነካም በአላህ ፈቃድ ቢኾን እንጅ”*፤ በአላህም የሚያምን ሰው ልቡን ለትዕግስት ይመራዋል፤ አላህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ مَا أَصَابَ مِن مُّصِيبَةٍ إِلَّا بِإِذْنِ اللَّهِ ۗ وَمَن يُؤْمِن بِاللَّهِ يَهْدِ قَلْبَهُ ۚ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

የአላህ ፈቃድ በሁለት መልክ ለፍጡራን ተቀድሯል፤ አንዱ ያለፈቃዳቸው ሲሆን ሁለተኛው በተሰጣቸው ነጻ ፈቃድ ላይ ነው። የመጀመሪያው ፍጥረት ሲፈጠር ያለፈቃዱ በአላህ ፈቃድ የተፈጠረ ነው። ሰው በመወለድ፣ በሞት፣ በመተኛት፣ በማስነጠስ ምርጫ የለውም፦
28፥68 *ጌታህም የሚሻውን ይፈጥራል፤ ይመርጣልም፡፡ ለእነርሱ ለፍጡራን ምርጫ የላቸውም*፡፡ وَرَبُّكَ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ وَيَخْتَارُ ۗ مَا كَانَ لَهُمُ الْخِيَرَة

ለምሳሌ ሞት ሙሲባህ ነው፤ ግን መሞት አያስጠይቅም አያስቀጣም። ሁለተኛው ሙሲባህ ግን በተሰጠው ነጻ ፈቃድና ምርጫ የምናመጣው ስለሆነ ያስጠይቃል፦
21፥23 *ከሚሠራው ሁሉ አይጠየቅም፡፡ እነርሱ ፍጥረቶቹ ግን ይጠየቃሉ*፡፡ لَا يُسْأَلُ عَمَّا يَفْعَلُ وَهُمْ يُسْأَلُونَ
16፥93 *ትሠሩት ከነበራችሁትም ሁሉ በእርግጥ ትጠየቃላችሁ*፡፡ وَلَتُسْأَلُنَّ عَمَّا كُنتُمْ تَعْمَلُون
102፥8 ከዚያም *ከጸጋችሁ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃላችሁ*። ثُمَّ لَتُسْأَلُنَّ يَوْمَئِذٍ عَنِ النَّعِيمِ

“ነዒም” نَّعِيمِ ማለት “ጸጋ” ማለት ነው፤ በተሰጠን ነጻ ፈቃድና ምርጫ የምንሰራው መልካም ሥራ ሆነ ክፉ ሥራ ያስጠይቀናል ወይም ያስመነዳናል። ሁሉም ሙሲባህ ሳይሆን በተሰጠን ነጻ ምርጫ ከሙሲባህ የሚነካን እጆቻችን በሠሩት ፈሣድ ነው፦
42፥30 *”ከመከራም ማንኛውም ያገኛችሁ ነገር እጆቻችሁ በሠሩት ምክንያት ነው”*፡፡ ከብዙውም ይቅር ይላል፡፡ وَمَا أَصَابَكُم مِّن مُّصِيبَةٍ فَبِمَا كَسَبَتْ أَيْدِيكُمْ وَيَعْفُو عَن كَثِيرٍ
30፥41 *”የሰዎች እጆች በሠሩት ኃጢኣት ምክንያት የዚያን የሠሩትን ከፊሉን ያቀምሳቸው ዘንድ መከራው በየብስና በባሕር ተሰራጨ”*፡፡ እነርሱ ሊመለሱ ይከጀላልና፡፡ ظَهَرَ الْفَسَادُ فِي الْبَرِّ وَالْبَحْرِ بِمَا كَسَبَتْ أَيْدِي النَّاسِ لِيُذِيقَهُم بَعْضَ الَّذِي عَمِلُوا لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ
“ኃጢኣት” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ፈሣድ” ሲሆን “ፈሣድ” فَسَاد ማለት “ጥፋት” “ብክለት” “ብልሽት” ማለት ነው፥ ይህንን ድርጊት የሚተገብሩ ግለሰቦች ደግሞ “ሙፍሢድ” مُفْسِد ማለትም “አጥፊ” “አበላሺ” “በካይ” ይባላሉ። ሙሲባህ ሳይሆን “ከ”ሙሲባህ ሰዎችን የሚያገኘው የሰዎች እጆች በሠሩ ፈሣድ ነው። ለምሳሌ በምድሪቱ ላይ ረሃብ ያለው ምግብ ታጥቶ አሊያም ለእህል የሚሆን ተስማሚ የእርሻ ቦታ ታጥቶ ሳይሆን ክፋት፣ ጭካኔ፣ ስግብግብነት፣ ጥላቻ ስላለ ነው። በምድሪቱ ላይ ድህነት ያለው 80% የሚሆነውን የምድራችን ሃብት 20% የሚሆኑ የምድራችም ሃብታሞች በሞኖፓልና በስግብግብነት ስለያዙት ነው።
አላህም በሰጠህ ሀብት የመጨረሻይቱን አገር ፈልግ፤ ከቅርቢቱም ዓለም ፋንታህን አትርሳ፥ አላህም ወደ አንተ መልካምን እንዳደረገልህ ለሰዎች መልካምን አድርግ፤ በምድርም ውስጥ ፈሣድን አትፈልግ፡፡ አላህ ሙፍሠዲንን አይወድምና፦
28፥77 *”አላህም በሰጠህ ሀብት የመጨረሻይቱን አገር ፈልግ፤ ከቅርቢቱም ዓለም ፋንታህን አትርሳ፤ አላህም ወደ አንተ መልካምን እንዳደረገልህ ለሰዎች መልካምን አድርግ፤ በምድርም ውስጥ ማጥፋትን አትፈልግ፡፡ አላህ አጥፊዎችን አይወድምና”*። وَابْتَغِ فِيمَا آتَاكَ اللَّهُ الدَّارَ الْآخِرَةَ ۖ وَلَا تَنسَ نَصِيبَكَ مِنَ الدُّنْيَا ۖ وَأَحْسِن كَمَا أَحْسَنَ اللَّهُ إِلَيْكَ ۖ وَلَا تَبْغِ الْفَسَادَ فِي الْأَرْضِ ۖ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْمُفْسِدِينَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
እውነተኛ አምላክ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

28፥75 ከሕዝቦችም ሁሉ መስካሪን እናወጣለን፡፡ *"ያን ጊዜ እውነተኛውም አምላክነት ለአላህ ብቻ መኾኑን ያውቃሉ"*፡፡ ይቀጣጥፉት የነበሩትም ከእነርሱ ይጠፋቸዋል፡፡ وَنَزَعْنَا مِن كُلِّ أُمَّةٍ شَهِيدًا فَقُلْنَا هَاتُوا بُرْهَانَكُمْ فَعَلِمُوا أَنَّ الْحَقَّ لِلَّهِ وَضَلَّ عَنْهُم مَّا كَانُوا يَفْتَرُونَ

እውነተኛ አምላክ አንዱ አምላክ አላህ ብቻ ነው። ክርስቲያኖች፦ "ኢየሱስ እውነተኛ አምላክ ነው" ይላሉ። የትንሳኤ ቀን እውነተኛውም አምላክነት ለአላህ ብቻ መኾኑን ያውቃሉ፥ ይቀጣጥፉት የነበሩትም ከእነርሱ ይጠፋቸዋል፦
28፥75 ከሕዝቦችም ሁሉ መስካሪን እናወጣለን፡፡ *"ያን ጊዜ እውነተኛውም አምላክነት ለአላህ ብቻ መኾኑን ያውቃሉ"*፡፡ ይቀጣጥፉት የነበሩትም ከእነርሱ ይጠፋቸዋል፡፡ وَنَزَعْنَا مِن كُلِّ أُمَّةٍ شَهِيدًا فَقُلْنَا هَاتُوا بُرْهَانَكُمْ فَعَلِمُوا أَنَّ الْحَقَّ لِلَّهِ وَضَلَّ عَنْهُم مَّا كَانُوا يَفْتَرُونَ

ኢየሱስ በአንድ ወቅት ወደ አምላኩ ሲጸልይ እውነተኛ አምላክ ብቻውን የሆነው አምላኩ እንደሆነ ተናግሯል፦
ዮሐንስ 17፥3 *"እውነተኛ አምላክ ብቻህን የሆንህ አንተን እና የላክኸውን ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት*። αὕτη δέ ἐστιν ἡ αἰώνιος ζωή, ἵνα γινώσκωσιν σὲ τὸν μόνον ἀληθινὸν θεὸν καὶ ὃν ἀπέστειλας Ἰησοῦν Χριστόν.

የተጠቀምኩት 1980 አዲስ ትርጉም ነው፥ "አንተ ሰው ብቻ ነህ" ማለት እና "አንተ ብቻህን ሰው ነህ" ማለት ይለያያል። ግሪኩ ያስቀመጠው አብ ብቻውን እውነተኛ አምላክ እንደሆነ ነው። ኢየሱስ ደግሞ የእዚያ እውነተኛ አምላክ መልእክተኛ ስለሆነ "ካይ" καὶ ማለትም "እና" በሚል መስተጻምር "አንተ" ከተባለው ማንነት ከአብ ተነጥሏል። እንደ ባይብሉ ኢየሱስ እውነተኛ አምላክ ሳይሆን የእውነተኛ አምላክ ልጅ ነው፥ የመጣውና የተላከው ልጁ እንጂ አምላክ አልመጣም። አልተላከም፦
የሐዋርያት ሥራ 13፥23 *”ከዚህም ሰው ዘር “አምላክ” Θεὸς እንደ ተስፋው ቃል ለእስራኤል መድኃኒትን እርሱም ኢየሱስን አመጣ”*።
ገላትያ 4፥4 ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ *“አምላክ” Θεὸς ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ"*።

አምላክ ኢየሱስን ላከ ወይም አመጣ እንጂ እራሱ አልተላከም። አልመጣም። በስጋ የመጣው ልጁ ስለሆነ "የአምላክ ልጅ እንደ መጣ" ይለናል፦
1ኛ ዮሐንስ 5፥20 *የአምላክም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም የሆነው በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ አለን። ይህ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው*። οἴδαμεν δὲ ὅτι ὁ υἱὸς τοῦ θεοῦ ἥκει, καὶ δέδωκεν ἡμῖν διάνοιαν ἵνα γινώσκωμεν τὸν ἀληθινόν: καὶ ἐσμὲν ἐν τῷ ἀληθινῷ, ἐν τῷ υἱῷ αὐτοῦ Ἰησοῦ Χριστῷ. οὗτός ἐστιν ὁ ἀληθινὸς θεὸς καὶ ζωὴ αἰώνιος.

የግሪኩን በማመሳከር ለመጠቀም ሞክሬአለው። እዚህ አንቀጽ መነሻ ላይ "የአምላክም ልጅ እንደ መጣ" የሚለው ይሰመርበት። እውነተኛም አብ በእርሱ በልጁ አለን። ልጁ ስለ እውነተኛው አብ አስተምሯል፥ "በ" የሚለው መስተዋድድ መነሻ ያለው "እርሱ" ኢየሱስን ካመለከተ "እውነተኛ"the True One" የተባለው ደግሞ አብ ነው፥ ልጁ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ዕውቀትን በትምህርቱ ውስጥ እንደ ሰጠን እናውቃለን፦
ዮሐንስ 8፥26 ዳሩ ግን የላከኝ *እውነተኛ* ἀληθινῷ ነው እኔም ከእርሱ የሰማሁትን ይህን ለዓለም እናገራለሁ አላቸው።
ዮሐንስ 7፥28 እኔም በራሴ አልመጣሁም ነገር ግን እናንተ የማታውቁት የላከኝ *እውነተኛ* ἀληθινῷ ነው።

ይህንን ዕውቀት ያስተማረን የእዛ የእውነተኛው አብ ልጁ ነው። ግሪኩ "ሁኦ አውቶዩ" Υἱῷ αὐτοῦ ማለትም "የእርሱ ልጅ"his son" ይለናል። ልጅ የተባለው ኢየሱስ ከሆነ "የ" የሚለው አገናዛቢ መነሻ የሆነለት "አውቶስ" αὐτός ማለትም "እርሱ" ማን ነው? እርግጥ ነው። አብ ነው፥ ቀጥሎ "እርሱ" የሚለውን ተክቶ የመጣው አመልካች "ሆአውቶስ" οὗτός ማለትም "ይህ"this" አብን የሚያመለክት ነው። "ይህ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት" የተባለው አብ ነው፥ ኅዳጉም ዮሐንስ 17፥3 ይጠቁማል። በጣም ስመ-ጥርና ገናና ኮሜንታተር እውነተኛ አምላክ የተባለው ኢየሱስ ሳይሆን አብ ነው ብለው ሳያቅማሙ አስቀምጠዋል፦
1 John 5፥20 Christ has revealed the one true God, the source of eternal life ‘This is the true God’ does not refer to Jesus” "ክርስቶስ የዘላለም ሕይወት ምንጭ አንድ እውነተኛው አምላክ ገልጧል፥ ይህ እውነተኛ አምላክ ኢየሱስን አያመለክትም።

ዋቢ ኮሜንተሪይ ይመልከቱ፦
1.Grammatical Analysis of the Greek New Testament, Zerwick/Grosvenor, Rome Biblical Institue, 1981.
2.Peake’s Commentary on the Bible, Thomas Nelson and Sons, reprint of 1964.

አዲሱ መደበኛ የግርጌ ማስታወሻ ላይ 1ኛ ዮሐንስ 5፥20 "እውነተኛ አምላክ" የሚለው እግዚአብሔር አብን እንደሚያመለክት አስፍሯል። ደግሞ "ኢየሱስ ክርስቶስ" የሚለው ኃይለ-ቃል በደንገል 22፣ በደንገል 90፣ በደንገል 52፣ ኮዴክስ አሌክሳንድሪየስ ላይ፣ ኮዴክስ ኤፍሬማይ ላይ፣ ላቲን ቩልጌት ላይ የለም። ከሌለ በሌለ ነገር ላይ ተመስርተን እንዴት ቴኦሎጂን ቴኦሎጃይዝ ማድረግ ይቻላል? ዋቢ ማብራሪያ ይመልከቱ፦
Gill’s Exposition of the Whole Bible Commentary. 1 John 5፥20

የ 1ኛ ዮሐንስ 5፥20 ዐውድም ሲዘጋ፦ "ልጆች ሆይ፥ *ከጣዖታት* εἰδώλων ራሳችሁን ጠብቁ" በማለት ነው። ዐውዱ እውነተኛ አምላክን ከጣኦዖት መራቅ ጋር አያይዞ መናገሩ በራሱ እውነተኛ አምላክ የተባለው አብ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ምክንያቱም ከጣኦታት ዘወር የሚባልበት እውነተኛ አምላክን እና ልጁ ኢየሱስ ሁለት ኑባሬዎች እንደሆኑ በሌላ ጥቅስ ላይ መረጃ ስላለን ነው፦
1ተሰሎንቄ 1፥9-10 *እነርሱ ራሳቸው ወደ እናንተ መግባታችን እንዴት እንደነበረ ስለ እኛ ይናገራሉና፤ ለሕያው እና *ለእውነተኛ አምላክም* Θεῷ ζῶντι καὶ ἀληθινῷ ታገለግሉ ዘንድ፥ ከሙታንም ያስነሳውን *ልጁን* እርሱንም ኢየሱስን ከሚመጣው ቍጣ የሚያድነንን ከሰማይ ትጠብቁ ዘንድ፥ *ከጣዖቶች* εἰδώλων ወደ አምላክ Θεὸν እንዴት ዘወር እንዳላችሁ ይናገራሉ*።
"እውነተኛ አምላክ" ካለ በኃላ "የእርሱ ልጅ"his son" ይለናል። "ልጅ" የተባለው ኢየሱስ "እርሱ" የተባለው በግልጽ "እውነተኛ አምላክ" ነው። አይሁዶችም እውነተኛ አምላክ የሚሉት ጥንት ሲመለክ የነበረውን ያህዌን ብቻ ነው፦
ኤርሚያስ 10፥10 ያህዌህ וַֽיהוָ֤ה ግን *እውነተኛ አምላክ* אֱמֶת, הוּא-אֱלֹהִים ነው፤ እርሱም ሕያው አምላክና የዘላለም ንጉሥ ነው፤
2ኛ ዜና 15፥3 እስራኤልም ብዙ ዘመን ያለ *እውነተኛ አምላክ* אֱמֶת, הוּא-אֱלֹהִים ፥ ያለ አስተማሪም ካህን፥ ያለ ሕግም ይኖሩ ነበር።

ያ እውነተኛ አምላክ ያህዌህ ለእስራኤላውያን አምላካቸው ለኢየሱስ አባቱ እንደሆነ ተናግሯል፦
ዘዳግም 6፥4 *እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ አምላካችን ያህዌህ አንድ ያህዌህ ነው”*።
ዮሐንስ 8፥54 *”እናንተ አምላካችን የምትሉት አባቴ ነው”*።

ስለዚህ እውነተኛ አምላክ የተባለው ኢየሱስን የላከው እንጂ የተላከው ኢየሱስ በፍጹም አይደለም። "ሆአውቶስ" οὗτός ማለትም "ይህ"this" የሚለው አመልካች ተውላጠ-ስም "ኢየሱስ" ከሚለው በኃላ ስለመጣ ኢየሱስ ነው ማለት ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ አንካሳ የነበረው ሰው የማዕዘን ራስ የሆነው ይህ ድንጋይ ነው እንደ ማለት ነው፦
ሐዋ. ሥራ 4፥10-11 *እናንተ በሰቀላችሁት እግዚአብሔርም ከሙታን ባስነሣው በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይህ ደኅና ሆኖ በፊታችሁ እንደ ቆመ፥ ለእናንተ ለሁላችሁ ለእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ የታወቀ ይሁን። እናንተ ግንበኞች የናቃችሁት፥ የማዕዘን ራስ የሆነው "ይህ" οὗτός ድንጋይ ነው*።

ስለ ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ አንካሳ ስለነበረ ሰው አውርቶ "በአራት ነጥብ" (።) ከዘጋ በኃላ "ይህ" የሚለው ስለ ኢየሱስ እንደሆነ ሁሉ ስለ ኢየሱስ አውርቶ በአራት ነጥብ ከዘጋ በኃላ ይህ የሚለው ስለ ስለ አብ ነው። በኢሥላም እውነተኛ አምላክ አላህ ብቻ ነው፥ እነዚያ መሲሢሑን “አላህ ነው” ያሉ በእርግጥ ካዱ። ይህ በአላህ አምላክነትን ላይ ሰውን ማሻረክ ነው፥ እነሆ በአላህ ላይ የሚያጋራ ሰው አላህ በእርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም ስላደረገበት እና መኖሪያውም እሳት ስለሆነች መሲሢሑን “አላህ ነው” የምትሉ የተውበት በሩ ሳይዘጋ በተውበት ወደ አላህ ተመለሱ፦
5፥72 *” «አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ አልመሲህም አለ፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን ተገዙ፡፡» እነሆ! በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፡፡ መኖሪያውም እሳት ናት፡፡ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም”*፡፡ لَقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ ۖ وَقَالَ الْمَسِيحُ يَا بَنِي إِسْرَائِيلَ اعْبُدُوا اللَّهَ رَبِّي وَرَبَّكُمْ ۖ إِنَّهُ مَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدْ حَرَّمَ اللَّهُ عَلَيْهِ الْجَنَّةَ وَمَأْوَاهُ النَّارُ ۖ وَمَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ أَنصَارٍ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሁለት አምላክ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

16፥51 አላህም አለ፦ *"ሁለት አማልክትን አትያዙ"*፡፡ እርሱ *"አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ እኔንም ብቻ ፍሩ"*፡፡ وَقَالَ ٱللَّهُ لَا تَتَّخِذُوٓا۟ إِلَٰهَيْنِ ٱثْنَيْنِ ۖ إِنَّمَا هُوَ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَإِيَّٰىَ فَٱرْهَبُونِ

"ሸይእ" شَىْء ማለት "ነገር"thing" ማለት ሲሆን ማንኛውንም ነገር ሁሉ የፈጠረ አንድ አምላክ አላህ ብቻ ነው፦
39:62 አላህ *"የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው"*። እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው። ٱللَّهُ خَٰلِقُ كُلِّ شَىْءٍۢ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍۢ وَكِيلٌۭ
40:62 ይሃችሁ፣ ጌታችሁ አላህ ነው፤ *"የነገር ሁሉ ፈጣሪ ነው"*፤ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ ታዲያ ከእምነት ወዴት ትመለሳላችሁ?። ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمْ خَٰلِقُ كُلِّ شَىْءٍۢ لَّآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ فَأَنَّىٰ تُؤْفَكُونَ
6:102 ይህ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ *"ነገርን ሁሉ ፈጣሪ ነው"*፡፡ ስለዚህ አምልኩት፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነው፡፡ بَدِيعُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ ۖ أَنَّىٰ يَكُونُ لَهُۥ وَلَدٌۭ وَلَمْ تَكُن لَّهُۥ صَٰحِبَةٌۭ ۖ وَخَلَقَ كُلَّ شَىْءٍۢ ۖ وَهُوَ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمٌۭ
13፥16 *«አላህ ሁሉን ነገር ፈጣሪ ነው"*፡፡ እርሱም አንዱ አሸናፊው ነው» በል፡፡ قُلِ ٱللَّهُ خَٰلِقُ كُلِّ شَىْءٍۢ وَهُوَ ٱلْوَٰحِدُ ٱلْقَهَّٰرُ

ያ ማለት ከነገር ሁሉ ተቃራኒ ነገርን የፈጠረው አላህ ብቻ ነው፤ ለምሳሌ ሰማይንና ምድርን፣ ብርሃንንና ጨለማን፣ ሞትና ህይወትን፣ ወንድና ሴትን ሁሉ ማለት ነው፦
51፥49 ትገነዘቡም ዘንድ *"ከነገሩ ሁሉ ሁለት ተቃራኒ ዓይነትን ፈጠርን"*፡፡ وَمِن كُلِّ شَىْءٍ خَلَقْنَا زَوْجَيْنِ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ
6፥1 ምስጋና ለዚያ *"ሰማያትንና ምድርን ለፈጠረው፤ ጨለማዎችንና ብርሃንንም"* ላደረገው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ ٱلْحَمْدُ لِلَّهِ ٱلَّذِى خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ وَجَعَلَ ٱلظُّلُمَٰتِ وَٱلنُّورَ
67፥1 ያ የትኛችሁ ሥራው ይበልጥ ያማረ መኾኑን ሊሞክራችሁ *"ሞትንና ሕይወትን የፈጠረ ነው"*፡፡ እርሱም አሸናፊው መሓሪው ነው፡፡ ٱلَّذِى خَلَقَ ٱلْمَوْتَ وَٱلْحَيَوٰةَ لِيَبْلُوَكُمْ أَيُّكُمْ أَحْسَنُ عَمَلًۭا ۚ وَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْغَفُورُ
75፥39 ከእርሱም *"ሁለት ዓይነቶችን ወንድና ሴትን አደረገ"*፡፡ فَجَعَلَ مِنْهُ ٱلزَّوْجَيْنِ ٱلذَّكَرَ وَٱلْأُنثَىٰٓ

ይህ ሆኖ ሳለ ግን ዞራስተርያን ወይም ኖስቲዝም፦ "ሰማይን፣ ብርሃንን፣ ህይወትን፣ ወንድን የፈጠረው "አሁራ" የተባለው አምላክ ነው ሲሉ፤ በተቃራኒው ምድርን፣ ጨለማን፣ ሞት፣ ሴትን የፈጠረው "አንግራ" የተባለው አምላክ ነው ብለው ሁለት አምላክ ያመልካሉ፤ ይህ የሁለት አምላክ ጥምረት ትምህርት "ዱአ-ቴእይዝም"duotheism" ይባላል፤ "ዱአ-ቴእይዝም" δυοθεισμός ማለት የሁለት ቃላት ውቅር ነው፤ "ዱአ" δυο "ሁለት" እና "ቴኦስ" θεισμός "አምላክ" የሚል ትርጉም ነው፤ ትርጉሙም "ሁለት አምላክ"dual deity" ማለት ነው፤ ይህንን ትምህርት ቁርአን ክፉኛ ይቃወማል፦
16፥51 አላህም አለ፦ *"ሁለት አማልክትን አትያዙ"*፡፡ እርሱ *"አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ እኔንም ብቻ ፍሩ"*፡፡ وَقَالَ ٱللَّهُ لَا تَتَّخِذُوٓا۟ إِلَٰهَيْنِ ٱثْنَيْنِ ۖ إِنَّمَا هُوَ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَإِيَّٰىَ فَٱرْهَبُونِ

ይህ ትምህርት ከሥላሴ የሚለየው አምላክ በምንነት ሆነ በማንነት ሁለት ነው ሲሉ፤ ሥላሴያውያን ደግሞ በማንነት ሦስት በምንነት አንድ ናቸው ብለው ያምናሉ፤ ነገር ግን አንዱ አምላክ በማንነት ሆነ በምንነት አንድ ነው፤ በምንነቱ ሆነ በማንነቱ ተጋሪ የለውም፦
18፥110 ወደ እኔ የሚወረድልኝ "አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው፤ እኔም ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ" ማለት ነው፤ የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፤ መልካም ሥራን ይሥራ፡፡ በጌታውም አምልኮ *"አንድንም"* አያጋራ» በላቸው፡፡ قُلْ إِنَّمَآ أَنَا۠ بَشَرٌۭ مِّثْلُكُمْ يُوحَىٰٓ إِلَىَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَمَن كَانَ يَرْجُوا۟ لِقَآءَ رَبِّهِۦ فَلْيَعْمَلْ عَمَلًۭا صَٰلِحًۭا وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِۦٓ أَحَدًۢا