ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
69 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
አንድ አምላክ" በሚለው ቃል ላይ "አንድ" የሚለውን የተጠቀመበት "ዋሒድ" وَٰحِد ሲሆን አላህ በምንነቱ ላይ ምንም ምንነት ተጋሪ እንደሌለው ያሳያል፤ "አንድንም አያጋራ" በሚለው ቃል የተጠቀመበት ቃል "አሐድ" أَحَد ሲሆን በአላህ ምንነት ላይ ማንም ማንነት ተጋሪ እንደሌለ ያሳያል፦
72፥20 «እኔ የምግገዛው ጌታየን ብቻ ነው፡፡ በእርሱም *"አንድንም"* አላጋራም» በል፡፡ قُلْ إِنَّمَآ أَدْعُوا۟ رَبِّى وَلَآ أُشْرِكُ بِهِۦٓ أَحَدًۭا
112፥1 በል «እርሱ አላህ *"አንድ"* ነው፡፡ قُلْ هُوَ ٱللَّهُ أَحَدٌ

"አላህ አንድ ነው" በሚለው ቃል ላይ "አንድ" የሚለው "አሐድ" أَحَد መሆኑ በራሱ አላህ አንድ ማንነት ብቻ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፤ ከእርሱ ማንነት ጋር መለኮትን የሚጋራ አንድም ማንነት የለም፦
112፥4 ለእርሱም *"አንድም"* ብጤ የለውም፡፡ وَلَمْ يَكُن لَّهُۥ كُفُوًا أَحَدٌۢ

"ለም" لَمْ ማለት "አፍራሽ ቃል"negative particle" ሲሆን ለማንነት የሚመጣ አፍራሽ ቃል ነው፤ ለእርሱ ማንም ብጤ የሌለው መሆኑን ያሳያል፤ "ለይሠ" لَيْسَ ማለት "አፍራሽ ቃል"negative particle" ሲሆን ለምንነት የሚመጣ አፍራሽ ቃል ነው፤ አላህ የሚመስለው ምንም ምንነት የለም፦
42፥11 *የሚመስለው ምንም ነገር የለም*፡፡ እርሱም *ሰሚው ተመልካቹ* ነው፡፡ لَيْسَ كَمِثْلِهِۦ شَىْءٌۭ ۖ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْبَصِيرُ

ይህንን ጥልልና ጥንፍፍ ያለ የተውሒድ ትምህርት ከተረዳን በክርስትናው አንጃ ውስጥ የይሆዋ ምስክሮች ደግሞ፦ "ዓለማት ከመፈጠራቸው በፊት ያህዌህ ኢየሱስ ፈጠረውና በኢየሱስ ሁሉን ነገር ፈጠረ" ብለው ያምናሉ፤ ይህ እንጥል ከመቧጠጥ ምንም አይተናነስም፤ ኢየሱስን አናመልክም ሲሉ ተውሒደል ኡሉሂያን ሲያሟሉ፤ ግን ዓለማትን ሲፈጥር ግን አጋዥ ነበረው ብሎ ማለት ተውሒደ አር-ሩቡቢያን ላይ ማሻረክ ነው፤ ከአላህ ጋር በምንነት ተለይቶ ግን ፍጥረትን ሲፈጥር ሆነ ዓለማትን ሲያስተናብር የሚያግዘው አጋዥ የለውም፤ ወደ አላህ በንስሃ ተመለሱ እንላለን፦
34፥22 እነዚያን ከአላህ ሌላ የምታስቧቸውን ጥሩ፡፡ በሰማያትም በምድርም ውስጥ *"የብናኝ ክብደት ያክል ምንንም አይችሉም"*፡፡ ለእነርሱም በሁለቱም ውስጥ *"ምንም ሽርክና የላቸውም"*፡፡ ከእነርሱም ለእርሱ *"ምንም አጋዥ የለውም"*» በላቸው፡፡ قُلِ ٱدْعُوا۟ ٱلَّذِينَ زَعَمْتُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ ۖ لَا يَمْلِكُونَ مِثْقَالَ ذَرَّةٍۢ فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَلَا فِى ٱلْأَرْضِ وَمَا لَهُمْ فِيهِمَا مِن شِرْكٍۢ وَمَا لَهُۥ مِنْهُم مِّن ظَهِيرٍۢ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አል-መሢሕ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥45 መላእክት ያሉትን አስታውስ፡- «መርየም ሆይ! *አላህ ከእርሱ በኾነው ቃል ስሙ፦ አል-መሲሕ ዒሣ የመርየም ልጅ በዚህ ዓለምና በመጨረሻውም ዓለም የተከበረ ከባለሟሎችም በኾነ ያበስርሻል*፡፡» إِذْ قَالَتِ الْمَلَائِكَةُ يَا مَرْيَمُ إِنَّ اللَّهَ يُبَشِّرُكِ بِكَلِمَةٍ مِّنْهُ اسْمُهُ الْمَسِيحُ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ وَجِيهًا فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ وَمِنَ الْمُقَرَّبِينَ

አምላካችን አላህ በመልአኩ ለመርየም ያበሰራት ቃል ልጇ፦ "ስሙ፦ አልመሲሕ ዒሳ የመርየም ልጅ እንደሆነ፥ በዚህ ዓለምና በመጨረሻውም ዓለም የተከበረ ከባለሟሎችም እንደሆነ ነው፦
3፥45 መላእክት ያሉትን አስታውስ፡- «መርየም ሆይ! *አላህ ከእርሱ በኾነው ቃል ስሙ፦ አል-መሲሕ ዒሣ የመርየም ልጅ በዚህ ዓለምና በመጨረሻውም ዓለም የተከበረ ከባለሟሎችም በኾነ ያበስርሻል*፡፡» إِذْ قَالَتِ الْمَلَائِكَةُ يَا مَرْيَمُ إِنَّ اللَّهَ يُبَشِّرُكِ بِكَلِمَةٍ مِّنْهُ اسْمُهُ الْمَسِيحُ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ وَجِيهًا فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ وَمِنَ الْمُقَرَّبِينَ

"ዩበሺሩኪ ቢከሊማህ" يُبَشِّرُكِ بِكَلِمَةٍ ማለት "በቃል ያበስርሻል" ማለት ነው፥ ይህም የምስራች ቃል ስሙ፦ "አል-መሲሕ ዒሣ" መባሉ ነው። እዚህ አንቀጽ ላይ ሚሽነሪዎች፦ "አል-መሲሕ" الْمَسِيح የዒሣ "ስሙ" መባሉ "ስህተት ነው" ይላሉ። ምክንያታችሁ ምንድን ነው? ስንላቸው፥ "አል" الْ የሚለው "መዕሪፍ" مَعْرِف ማለትም "ጠቃሽ አመልካች መስተአምር"definite article" ካለበት ስም አይደለም" ብለው አረፉት፥ ይህ የሚያሳየው ስለ ስም ያላቸው ግንዛቤ ዜሮ እንደሆነ ነው። “ኢሥም” اِسْم የሚለው ቃል “ሠማ” سَمَّى ማለትም “ጠራ” “ሰየመ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መጠሪያ” ወይም “ስም” ማለት ነው፥ የኢሥም ብዙ ቁጥር “አሥማእ” أَسْمَاء‎ ነው። “ስም” የአንድ ማንነት ወይም ምንነት “መጠሪያ” ነው። ለምሳሌ “አሏህ” ٱللَّه የሚለው ስም “ኢሥሙል ዐለም” اِسْم العَلَم ማለትም “የተጸውዖ ስም”proper name” ቢሆንም በቁርኣን የተገለጹ “አል-ኻሊቅ” الْخَالِق “አል-ባሪእ” الْبَارِئُ “አል-ገኒይ” الْغَنِيّ “አል-ሙሰዊር” الْمُصَوِّرُ ወዘተ የሚባሉ “ኢሥሙል መዕሪፍ” اِسْم اللمَعْرِف አሉት፦
29፥24 *”እርሱ አላህ ፈጣሪው ከኢምንት አስገኚው ቅርጽን አሳማሪው ነው፤ ለእርሱ መልካሞች ስሞች አሉት”*። هُوَ اللَّهُ الْخَالِقُ الْبَارِئُ الْمُصَوِّرُ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَى

እዚህ አንቀጽ ላይ የተጠቀሱት ስሞች “አል-ኻሊቅ” الْخَالِق “አል-ባሪእ” الْبَارِئُ “አል-ሙሰዊር” الْمُصَوِّرُ ላይ "አል" الْ የሚል መዕሩፍ እንዳላቸው ልብ አድርግ። ልክ እንደዚሁ “ዒሣ” عِيسَى የሚለው ስም “ኢሥሙል ዐለም” اِسْم العَلَم ማለትም “የተጸውዖ ስም”proper name” ሲሆን "አል-መሲሕ" الْمَسِيح ደግሞ “ኢሥሙል መዕሪፍ” اِسْم اللمَعْرِف ነው።
ይህንን ለመረዳት ከባይብል አንዳንድ ናሙናዎችን እያየን እናነጻጽራለን፦
ማቴዎስ 24፥5 ብዙዎች፦ *እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና*፤ ብዙዎችንም ያስታሉ።

"ክርስቶስ" የማዕረግ ስም ነው፥ ግን ለኢየሱስ ስሙ ስለሆነ "በስሜ" በማለት "ክርስቶስ" ስሙ መሆኑን አስረግጦ ነግሮናል። በተጨማሪም የማዕረግ ስም ስለሚተረጎም "ክርስቶስ" Χριστός የሚለው የግሪኩ ቃል ከዕብራይስጥ "ሀ-መሢአሕ" המשיח የተተረጎመ ነው። "መሢአሕ" ስም ሆኖ ሳለ "ሀ" ה የሚል ጠቃሽ አመልካች መስተአምር ይጠቀማል፦
ማርቆስ 8፥29 እናንተስ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? ብሎ ጠየቃቸው። ጴጥሮስም፦ *አንተ ክርስቶስ ὁ Χριστός ነህ* ብሎ መለሰለት።

"ክርስቶስ" Χριστός የሚለው ቃል ላይ "ሆ" ὁ የሚል ጠቃሽ አመልካች መስተአምር ስለተጠቀመ "ክርስቶስ" ስም አለመሆኑ ማስረጃ ሊሆን አይችልም። ሌላ ናሙና በኢሳይያስ ዘመን የተወለድ ሕጻን ስሙ "ምርኮ ፈጠነ፥ ብዝበዛ ቸኰለ" ተብሏል፦
ኢሳይያስ 8፥4 *ስሙን፦ ምርኮ ፈጠነ፥ ብዝበዛ ቸኰለ" ብለህ ጥራው" አለኝ*።

ለሕጻኑ ማዕረጉ "ስሙ" እንደተባለ ልብ አድርግ። ሌላ ናሙና "ዔሳው" የይስሐቅ ልጅ የተጸውዖ ስም ሲሆን ቅጽል ስሙ "ኤዶም" ነው፦
ዘፍጥረት 25፥30 ዔሳውም ያዕቆብን፦ ከዚህ ከቀዩ ወጥ አብላኝ፥ እኔ እጅግ ደክሜአለሁና አለው፤ ስለዚህ *"ስሙ ኤዶም ተባለ"*።

"ኤዶም" ማዕረግ ሆኖ ሳለ "ስሙ" መባሉን አንባቢ ልብ ይለዋል። ሌላ ናሙና አዳም ለእንስሳት ሁሉ፥ ለሰማይ ወፎችም ሁሉ፥ ለምድር አራዊትም ሁሉ ስም አወጣላቸው። ከእንስሳት መካከል አንበሳ እና አህያ ናቸው፦
ዘፍጥረት 2፥20 *አዳምም ለእንስሳት ሁሉ፥ ለሰማይ ወፎችም ሁሉ፥ ለምድር አራዊትም ሁሉ ስም አወጣላቸው"*።
1ኛ ነገሥት 13፥28 ሄደም፥ ሬሳውም በመንገድ ወድቆ፥ በሬሳውም አጠገብ *አህያው וַֽחֲמוֹר֙ እና አንበሳው* וְהָ֣אַרְיֵ֔ה ቆመው፥ አንበሳው ሬሳውን ሳይበላው፥ አህያውንም ሳይሰብረው አገኘ።

እዚህ አንቀጽ ላይ "ሙውር" מוֹר֙ ማለትም "አህያ" በሚል ቃል እና "አርየህ" אַרְיֵ֔ה ማለትም "አንበሳ" በሚል ቃል መነሻ ላይ "ሀ" ה የሚል ውስን መስተአምር ይጠቀማል። ውስን መስተአምር መኖሩ "አንበሳ" እና "አህያ" ስም አለመሆናቸውን እንደማያሳይ ሁሉ "መሲሕ مَسِيح በሚለው ቃል መነሻ ላይ "አል" الْ የሚል ውስን መስተአምር መኖሩ "አል-መሢሕ" ስም አለመሆኑ አያሳይም። የተገባባን ይመስለኛል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የምስራቹ ቃል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥45 መላእክት ያሉትን አስታውስ፡- «መርየም ሆይ! *አላህ ከእርሱ በኾነው ቃል ስሙ፦ አል-መሲሕ ዒሣ የመርየም ልጅ በዚህ ዓለምና በመጨረሻውም ዓለም የተከበረ ከባለሟሎችም በኾነ ያበስርሻል*፡፡» إِذْ قَالَتِ الْمَلَائِكَةُ يَا مَرْيَمُ إِنَّ اللَّهَ يُبَشِّرُكِ بِكَلِمَةٍ مِّنْهُ اسْمُهُ الْمَسِيحُ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ وَجِيهًا فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ وَمِنَ الْمُقَرَّبِينَ

“ቡሽራ” بُشْرَىٰ የሚለው ቃል “በሸረ” بَشَّرَ ማለትም “አበሰረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “የምስራች” ማለት ነው። አምላካችን አላህ በመልአኩ ለመርየም አብስሯታል፦
3፥45 መላእክት ያሉትን አስታውስ፡- «መርየም ሆይ! *አላህ ከእርሱ በኾነው ቃል ስሙ፦ አል-መሲሕ ዒሣ የመርየም ልጅ በዚህ ዓለምና በመጨረሻውም ዓለም የተከበረ ከባለሟሎችም በኾነ ያበስርሻል*፡፡» إِذْ قَالَتِ الْمَلَائِكَةُ يَا مَرْيَمُ إِنَّ اللَّهَ يُبَشِّرُكِ بِكَلِمَةٍ مِّنْهُ اسْمُهُ الْمَسِيحُ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ وَجِيهًا فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ وَمِنَ الْمُقَرَّبِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ያበስርሻል" ለሚለው ቃል የገባው "ዩበሺሩኪ" يُبَشِّرُكِ መሆኑን አስተው። "ዩበሺሩኪ ቢከሊማህ" يُبَشِّرُكِ بِكَلِمَةٍ ማለት "በቃል ያበስርሻል" ማለት ነው፥ ይህም ከአላህ የሆነው የምስራች ቃል፦ "ስሙ አል-መሲሕ ዒሣ የመርየም ልጅ በዚህ ዓለምና በመጨረሻውም ዓለም የተከበረ ከባለሟሎችም በኾነ ያበስርሻል" የሚል ነው። መርየምም በዚህ በጌታዋን ቃላት እና በመጽሐፍቱ አምናለች፥ ከታዛዦቹም ነበረች፦
66፥12 የዒምራንን ልጅ መርየምንም ያችን ብልቷን የጠበቀችውን ምሳሌ አደረገ፡፡ በእርሱም ውስጥ ከመንፈሳችን ነፋን፡፡ *በጌታዋ ቃላት እና በመጻሕፍቱም አረጋገጠች፡፡ ከታዛዦቹም ነበረች*፡፡ وَمَرْيَمَ ابْنَتَ عِمْرَانَ الَّتِي أَحْصَنَتْ فَرْجَهَا فَنَفَخْنَا فِيهِ مِن رُّوحِنَا وَصَدَّقَتْ بِكَلِمَاتِ رَبِّهَا وَكُتُبِهِ وَكَانَتْ مِنَ الْقَانِتِينَ

"ሶደቀት" صَدَّقَتْ የሚለው "አመነት" آمَنَتْ በሚል እንደመጣ አንባቢ ልብ ይለዋል። ከጌታዋ የሆነው የምስራች ቃል በሰማች ጊዜ አምናለች፥ መርየም በጌታዋ ቃላት እንደተበሰረችው ሁሉ ዘከርያም ከእርሷ በፊት ከአላህ በኾነው የምስራች ቃል ተበስሯል፦
3፥39 እርሱም በጸሎት ማድረሻው ክፍል ቆሞ ሲጸልይ *መላእክትም፦ «አላህ በየሕያ ከአላህ በኾነ ቃል የሚያረጋግጥ ጌታም ድንግልም ከደጋጎቹ ነቢይም ሲኾን ያበስርሃል» በማለት ጠሩት*፡፡ فَنَادَتْهُ الْمَلَائِكَةُ وَهُوَ قَائِمٌ يُصَلِّي فِي الْمِحْرَابِ أَنَّ اللَّهَ يُبَشِّرُكَ بِيَحْيَىٰ مُصَدِّقًا بِكَلِمَةٍ مِّنَ اللَّهِ وَسَيِّدًا وَحَصُورًا وَنَبِيًّا مِّنَ الصَّالِحِينَ

መልአኩ ለመርየም "ዩበሺሩኪ" يُبَشِّرُكِ ማለትም "ያበስርሻል" እንዳላት ሁሉ ለዘከርያም "ዩበሺሩከ" يُبَشِّرُكَ ማለትም "ያበስርሃል" ብሎታል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አጅነቢይ መጨበጥ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

17፥32 *ዝሙትንም አትቅረቡ፡፡ እርሱ በእርግጥ መጥፎ ሥራ ነውና፡፡ መንገድነቱም ከፋ*! وَلَا تَقْرَبُوا الزِّنَىٰ ۖ إِنَّهُ كَانَ فَاحِشَةً وَسَاءَ سَبِيلًا

"አጅነቢይ" أَجْنَبِيّ ማለት "ባዕድ" ማለት ሲሆን አንድ ሙሥሊም ወይም አንዲት ሙሥሊም በተቃራኒ ፆታ ያሉትን ለመጨበጥ ወይም ጸጉሯን ለማየት ሐላል ያልሆነ ሰው ማለት ነው።
አንድ ሙሥሊም ወንድ ጸጉሯ ለማየት ሆነ እጇን ለመጨበጥ ሐላል የሆኑለት እንስት እናቱ፣ አክስቱ፣ እህቱ፣ የወንድሙን ሴት ልጅ፣ የእህቱን ሴት ልጅ፣ ሚስቱ፣ ሴት ልጁ፣ የሚስቱ እናት ናቸው።
አንዲት ሙሥሊም ሴት ጸጉሯ ለማሳየት ሆነ ለመጨበጥ ሐላል የሆኑላት ተባዕት አባቷ፣ አጎቷ፣ ወንድሟ፣ የወንድሟ ወንድ ልጅ፣ የእህቷ ወንድ ልጅ፣ ባሏ፣ ወንድ ልጇ፣ የባሏ አባት ናቸው።
አንድ ሙሥሊም ወንድ ጸጉሯ ለማየት ሆነ እጇን ለመጨበጥ ሐራም የሆኑበት እንስት የአጎት ልጅ፣ የአክስት ልጅ፣ የወንድም ሚስት፣ የሚስት እህት፣ የጎረቤት ሴት፣ የአብነት ሴት፣ የአስኳላ ሴት፣ የሥራ ባልደረባ ሴት ወዘተ ናቸው።
አንዲት ሙሥሊም ሴት ጸጉሯ ለማሳየት ሆነ ለመጨበጥ ሐራም የሆኑባትት ተባዕት የአጎት ልጅ፣ የአክስት ልጅ፣ የእህት ባል፣ የባል ወንድም፣ የጎረቤት ወንድ፣ የአብነት ወንድ፣ የአስኳላ ወንድ፣ የሥራ ባልደረባ ወንድ ወዘተ ናቸው።

አጅነቢይ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ቋንቋዊ እና ሃይማኖታዊ ፍቺውን ከተመለከትን ዘንዳ የሁላችንም አርአያ የሆኑት ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" አጅነቢይ ሴቶችን በእጃቸው አይጨብጡም ነበር፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 33, ሐዲስ 131
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" አጅነቢይ ሴቶችን በእጃቸው አይጨብጡም ነበር"*። أَنَّ عَائِشَةَ، أَخْبَرَتْهُ عَنْ بَيْعَةِ النِّسَاءِ، قَالَتْ مَا مَسَّ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم بِيَدِهِ امْرَأَةً

"ቢ-የድ-ሂ" بِيَدِهِ ማለትም "በ-እጁ" የሚለው ይሰመርበት። በመላው ዓለም የሚገኙ ሙሥሊሞች ይህንን የነቢያችንን"ﷺ" ፈለግ በመከተል አጅነቢይ የሆነን ወንድ ወይም ሴት አይጨብጡም፦
33፥21 ለእናንተ አላህንና የመጨረሻውን ቀን የሚከጅል ለሆነ ሰው፣ አላህንም በብዙ ለሚያወሳ *በአላህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አላችሁ*፡፡ لَّقَدْ كَانَ لَكُمْ فِي رَسُولِ اللَّهِ أُسْوَةٌ حَسَنَةٌ لِّمَن كَانَ يَرْجُو اللَّهَ وَالْيَوْمَ الْآخِرَ وَذَكَرَ اللَّهَ كَثِيرًا

"በአላህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አላችሁ" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። በኢሥላም ሐራም የሚባለው ዝሙት ብቻ ሳይሆን ወደዚያ ሊያመሩ የሚችሉ ቅድመ-ሁኔታዎች ሁሉ ክልክል ናቸው፦
17፥32 *ዝሙትንም አትቅረቡ፡፡ እርሱ በእርግጥ መጥፎ ሥራ ነውና፡፡ መንገድነቱም ከፋ*! وَلَا تَقْرَبُوا الزِّنَىٰ ۖ إِنَّهُ كَانَ فَاحِشَةً وَسَاءَ سَبِيلًا

"ሰቢል" سَبِيل ማለት "መንገድ" ማለት ሲሆን ወደ ዝሙት ሊገፋፉ፣ ሊነሽጡ፣ ሊወሰውሱ የሚችሉ ነገሮች ሁሉ ያጠቃልላል።
በተረፈ በባይብል ሾላ በድፍኑ ዝሙት ኃጢአት ነው ይላል እንጂ "የዝሙት መቃረቢያዎች ኃጢአት ናቸው" የሚልበት አንዳችም ቁብ የለውም። ስለዚህ እዛ ሰፈር፦ "አጅነቢይን መጨበጥ ለምን ክልክል ሆነ" ብሎ አቧራ ማስነሳት መናኛ ምክንያት ነው፥ ሳይቀመጡ እግር መዘርጋት ለመፈንገል ነው። ባይብል ላይ የተሻለ እሳቤ ሳይኖር ኢሥላም ላይ መንፈቅፈቅና መነፋረቅ ቋ ያለ ጉፋያ እና እንጉልፋቶ ትችት ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
እውነተኛ ቃል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

19፥34 *ይህ የመርየም ልጅ ዒሣ ነው፡፡ ያ “በ”እርሱ የሚከራከሩበት እውነተኛ ቃል ነው*፡፡ ذَٰلِكَ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ ۚ قَوْلَ ٱلْحَقِّ ٱلَّذِى فِيهِ يَمْتَرُونَ

አምላካችን አላህ የዒሣን አፈጣጠር ከኣደም አፈጣጠር ጋር እንደሚመሳሰል በተከበረው ንግግሩ እንዲህ ይናገራል፦
3፥59 *”አላህ ዘንድ የዒሣ ምሳሌ እንደ ኣደም ብጤ ነው፡፡ ከአፈር ፈጠረው፡፡ ከዚያም ለ”እርሱ” «ኹን» አለው፤ ኾነም”*፡፡ إِنَّ مَثَلَ عِيسَىٰ عِندَ ٱللَّهِ كَمَثَلِ ءَادَمَ ۖ خَلَقَهُۥ مِن تُرَابٍۢ ثُمَّ قَالَ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ

“ኸለቀ” خَلَقَ ማለትም “ፈጠረ” በሚለው ግስ መዳረሻ ቅጥያ ላይ “ሁ” هُۥ ማለት “እርሱ” የሚል ተሳቢ ተውላጠ-ስም አለ፥ ይህም የስም ምትክ “ኣደም” ءَادَم የሚለውን የተጸውዖ ስም ተክቶ የመጣ ነው። አላህ ኣደምን ያለ አባት እና እናት ከአፈር "ኹን" በሚለው ቃል እንደፈጠረው ሁሉ ዒሣን ያለ አባት ከመርየም "ኹን" በሚለው ቃል ፈጥሮታል፦
3፥47 *፡-ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለች፡፡ ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፤ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል አላት*፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

አምላካችን አላህ ስለ ዒሣ አፈጣጠር እና ተልእኮ ከ 45-61 ከተረከልን በኃላ ይህ ትርክት "እውነተኛ ታሪክ ነው" ይለናል፦
3፥62 *”ይህ እርሱ በእርግጥ እውነተኛ ታሪክ ነው”*፡፡ አምላክም ከአላህ በስተቀር ምንም የለም፡፡ አላህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡ إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ ٱلْقَصَصُ ٱلْحَقُّ ۚ وَمَا مِنْ إِلَٰهٍ إِلَّا ٱللَّهُ ۚ وَإِنَّ ٱللَّهَ لَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ

"እውነተኛ ታሪክ ነው" የተባለው ዒሣ ሳይሆን አምላካችን አላህ ስለ ዒሣ የነገረን ትርክት ነው። አላህ በሱረቱል ዐለ-ዒምራን ላይ ያለውን የተንጠለጠለ ትርክት በሱረቱል መርየም ላይ ስለ አፈጣጠሩ እና ስለ ተልእኮው አፈጣጠር ደጋሚ ይነግረናል፦
19፥20 *«ሰው ያልነካኝ ሆኜ አመንዝራም ሳልሆን ለእኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል!» አለች*፡፡ قَالَتْ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي غُلَامٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ وَلَمْ أَكُ بَغِيًّا
19፥21 *አላት «ነገሩ እንደዚህሽ ነው፡፡» ጌታሽ «እርሱ በእኔ ላይ ገር ነው፡፡ ለሰዎችም ታምር ከእኛም ችሮታ ልናደርገው ይህንን ሠራን የተፈረደም ነገር ነው» አለ*፡፡ قَالَ كَذَٰلِكِ قَالَ رَبُّكِ هُوَ عَلَيَّ هَيِّنٌ ۖ وَلِنَجْعَلَهُ آيَةً لِّلنَّاسِ وَرَحْمَةً مِّنَّا ۚ وَكَانَ أَمْرًا مَّقْضِيًّا

አምላካችን አላህ ስለ ዒሣ አፈጣጠር እና ተልእኮ ከ 20-33 ከተረከልን በኃላ ይህ ትርክት "እውነተኛ ቃል ነው" ይለናል፦
19፥34 *ይህ የመርየም ልጅ ዒሣ ነው፡፡ ያ “በ”እርሱ የሚከራከሩበት እውነተኛ ቃል ነው*፡፡ ذَٰلِكَ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ ۚ قَوْلَ ٱلْحَقِّ ٱلَّذِى فِيهِ يَمْتَرُونَ

“የምተሩነ” يَمْتَرُونَ ማለት “የሚከራከሩበት” ማለት ነው። ብዙ ሰዎች በዒሣ ምንነት ቢከራከሩበትም አላህ ስለ ዒሣ የነገረን ግን እውነተኛ ንግግር ነው። "ሂ" هِ ማለትም "እርሱ" የተባለው ዒሣ ሲሆን “እርሱ” በሚለው መነሻ ቅጥያ ላይ “ፊ” فِي የሚል መስተዋድድ ሲኖር “ስለ”about” ማለት ነው፦ That is Jesus, son of Mary. ˹And this is˺ a word of truth, *“about”* which they dispute.

ስለዚህ ስለ ዒሣ የሚከራከሩበት ግን አላህ የነገረን ቃል እውነት ነው፥ "እውነተኛ ታሪክ" ማለት ስለ ዒሣ የተነገረን እውነተኛ ታሪክ ነው ማለት እንደሆነ ሁሉ "እውነተኛ ቃል" ማለት ስለ ዒሣ የተነገረን እውነተኛ ቃል ነው ማለት ነው። ዒሣ ታሪክ እንዳልሆነም ሁሉ ቃልም አይደለም። የመጣጥፉ ጭብጥ "ዒሣ እውነተኛ ቃል ነው" አልተባለም" የሚል ነው፥ ባይሆን አላህ ስለ ዒሣ የነገረን ቃል እውነተኛ ቃል ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዕውቀት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

96፥5 *ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን*፡፡ عَلَّمَ ٱلْإِنسَٰنَ مَا لَمْ يَعْلَمْ

“ዒልም” عِلْم‎ ማለት “ዕውቀት” ማለት ሲሆን “ጀህል” جَهْل ማለት ደግሞ “መሃይምነት” ማለት ነው። ዕውቀት የእምነት መሠረት ነው፥ ያለ ዕውቀት በጭፍንነት የምንከተለው ነገር ጥፋት ነው፦
17፥36 *"ለአንተም በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር አትከተል፡፡ መስሚያ፣ ማያም፣ ልብም እነዚህ ሁሉ ባለቤታቸው ከእነርሱ ተጠያቂ ነውና"*፡፡ وَلَا تَقْفُ مَا لَيْسَ لَكَ بِهِ عِلْمٌ ۚ إِنَّ السَّمْعَ وَالْبَصَرَ وَالْفُؤَادَ كُلُّ أُولَـٰئِكَ كَانَ عَنْهُ مَسْئُولًا

ዕውቀት ለማግኘት ደግሞ ማንበብ ጉልህ ሚና አለው። አምላካችን አላህ በጂብሪል ለነቢያችን”ﷺ” “ኢቅራ” اقْرَأْ ማለትም “አንብብ” ብሎ አዟቸዋል፦
96፥1 *”አንብብ በዚያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም”*፡፡ اقْرَأْ بِاسْمِ رَبِّكَ الَّذِي خَلَقَ

“ኢቅራ” ትእዛዛዊ ግስ ሲሆን ቁርኣን ሲጀምር የሚነበበው “ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም” ነው፥ ከአንድ ሱራህ በስተቀር እያንዳንዱ ሱራህ ከሌላው ሱራህ የሚለየው እና የሚጀምረው “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በጣም አዛኝ በኾነው” በሚል ነው፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 398
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *”ነቢዩ”ﷺ” ሁለት ሱራዎች አይለያዩ በመካከላቸው “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው” የሚለው ቃል ወደ እርሳቸው ቢወርድላቸው እንጂ”*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم لاَ يَعْرِفُ فَصْلَ السُّورَةِ حَتَّى تُنَزَّلَ عَلَيْهِ ‏{‏ بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ ‏}

“ቱነዘለ ዐለይሂ” تُنَزَّلَ عَلَيْهِ ማለትም “ወደ እርሳቸው ቢወርድላቸው” የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው” ከአላህ ወደ ነቢያችን”ﷺ” እኛ እንድናነበው የወረደ ነው፦
29፥45 ከመጽሐፍ *ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ*፡፡ اتْلُ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِنَ الْكِتَابِ
18፥27 ከጌታህም መጽሐፍ *ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ*፡፡ وَاتْلُ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِن كِتَابِ رَبِّك

ቁርኣንን በማንበብ የሚገኘው ዕውቀት "ነቅል" ይባላል፥ "ነቅል" نَقْل የሚለው ቃል "ነቀለ"نَقَلَ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን ከአላህ በነቢይ የሚተላለፍ ዕውቀት ነው። አምላካችን አላህ ቁርኣንን በነቢዩ ዐሳወቀ፥ "ዐለመ" عَلَّمَ ማለት "ዐሳወቀ" ማለት ነው። አላህ የማናውቀውን ሁሉ በቁርኣን ስላሳወቀን፥ እርሱ ዘንድ በላጩ ነገር ቁርኣንን ዐውቆ ማሳወቅ ነው፦
55፥2 *"ቁርኣንን አስተማረ"*፡፡ عَلَّمَ الْقُرْآنَ
4፥113 *አላህም በአንተ ላይ መጽሐፍንና ጥበብን አወረደ፡፡ የማታውቀውንም ሁሉ አስተማረህ*፡፡ የአላህም ችሮታ በአንተ ላይ ታላቅ ነው፡፡ وَأَنزَلَ اللَّهُ عَلَيْكَ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَعَلَّمَكَ مَا لَمْ تَكُن تَعْلَمُ ۚ وَكَانَ فَضْلُ اللَّهِ عَلَيْكَ عَظِيمًا
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 66, ሐዲስ 49
ዑስማን"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ከእናንተ በላጩ ቁርኣንን ዐውቆ ያሳወቀ ነው"*። نْ عُثْمَانَ ـ رضى الله عنه ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ خَيْرُكُمْ مَنْ تَعَلَّمَ الْقُرْآنَ وَعَلَّمَهُ

በመቀጠል አሁንም አምላካችን አላህ "አንብብ" የሚል ለሁለተኛ ጊዜ ያዛል፥ አላህ ሰውን ያላወቀውን ሁሉ በቀለም ያሳወቀው ቸር ጌታ ነው፦
96፥3 *"አንብብ! ጌታህ በጣም ቸር ሲኾን"*። اقْرَأْ وَرَبُّكَ الْأَكْرَمُ
96፥4 *"ያ በብርዕ ያስተማረ"*፡፡ ٱلَّذِى عَلَّمَ بِٱلْقَلَمِ
96፥5 *ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን*፡፡ عَلَّمَ ٱلْإِنسَٰنَ مَا لَمْ يَعْلَمْ

"ቀለም" قَلَم የሚለው ቃል "ቀለመ" قَلَمَ‎ ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ብዕር" ማለት ነው። በቀለም ዕውቀት በማንበብ የምናገኘው ዕውቀት "ዐቅል" ይባላል፥ "ዐቅል" عَقْل የሚለው ቃል "ዐቀለ"عَقَلَ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን በቀለም የሚተላለፍ ዕውቀት ነው። አምላካችን አላህ ሰውን ሲፈጥረው ቋንቋ መናገርን ዐሳወቀው፥ "ዐለመ" عَلَّمَ ማለት አሁንም "ዐሳወቀ" ማለት ነው፦
55፥3 *"ሰውን ፈጠረ"*፡፡ خَلَقَ ٱلْإِنسَٰنَ
55፥4 *መናገርን አስተማረው*፡፡ عَلَّمَهُ الْبَيَانَ
2፥31 *አደምንም ስሞችን ሁሏንም አስተማረው*፡፡ وَعَلَّمَ ءَادَمَ ٱلْأَسْمَآءَ كُلَّهَا

አምላካችን አላህ ለኣደም የነገርን ስም ዐሳወቀው፥ ይህንን ዕውቀት በማንበብ መፈለግ የሁሉም ሙሥሊም ግዴታ ነው፥ "አንብብ" የሚለው ትእዛዝ ቀዳማይ ተደራሲነቱ ለነቢያችን"ﷺ" ቢሆንም ደኃራይ ተደራሲነቱ ለመላው የሰው ዘር በሙሉ ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 229
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"*" አሉ፦ *"ዕውቀት መፈለግ በሁሉም ሙሥሊም ላይ ግዴታ ነው"*። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ طَلَبُ الْعِلْمِ فَرِيضَةٌ عَلَى كُلِّ مُسْلِمٍ

እውነት ነው፤ ዕውቀትን በማንበብ ማግኘት ይቻላል፥ ቀጣዩ ይህንን ዕውቀት በጥበብ መጠቀም ነው። ጥበብን የተሰጠው ሰው ብዙን መልካም ነገር በእርግጥ ተሰጦታል፦
2፥269 *ለሚሻው ሰው ጥበብን ይሰጣል፤ ጥበብንም የሚሰጠው ሰው ብዙን መልካም ነገር በእርግጥ ተሰጠ*፡፡ የአእምሮዎች ባለቤቶች እንጂ ሌላው አይገሰጽም፡፡ يُؤْتِى ٱلْحِكْمَةَ مَن يَشَآءُ ۚ وَمَن يُؤْتَ ٱلْحِكْمَةَ فَقَدْ أُوتِىَ خَيْرًۭا كَثِيرًۭا ۗ وَمَا يَذَّكَّرُ إِلَّآ أُو۟لُوا۟ ٱلْأَلْبَٰبِ

ይህ ሁሉ የሚሆነው አላህ የሻ እንደሆነ ነው፥ አላህ ለሚሻው ሰው ጥበብን ይሰጣል። ይህ ዲን የነቅል ዕውቀት እሳቤ ሆነ የዐቅል ዕውቀት እሳቤ አቅፏል፥ አላህ መልካም የሻለት ሰው ዱኑን ያስገነዝበዋል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 57, ሐዲስ 25
ሙዓዊያህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"አላህ መልካም የሻለት ሰው ዱኑን ያስገነዝበዋል"*። أَنَّهُ سَمِعَ مُعَاوِيَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ مَنْ يُرِدِ اللَّهُ بِهِ خَيْرًا يُفَقِّهْهُ فِي الدِّينِ،

አምላካችን አላህ እርሱ በቁርኣኑ የገለጠውን ዲኑል ኢሥላምን ያስገንዝበን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የተረሳው ጂሃድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥190 *እነዚያንም የሚጋደሉዋችሁን በአላህ መንገድ ተጋደሉ፡፡ ወሰንንም አትለፉ፤ አላህ ወሰን አላፊዎን አይወድምና*፡፡ وَقَاتِلُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ الَّذِينَ يُقَاتِلُونَكُمْ وَلَا تَعْتَدُوا ۚ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْمُعْتَدِينَ

“ጂሃድ” جِهَاد የሚለው ቃል “ጃሀደ” جَٰهَدَ ማለትም “ታገለ” ወይም “ጣረ” አሊያም “ተጋደለ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ትግል” ወይም “ጥረት” አሊያም “ገድል” ማለት ነው። እውነትን ለማንገስ ሐሰትን ለማርከስ፥ ከሙገሳ እና ከወቀሳ ነጻ ሆኖ በአላህ መንገድ በልቡ፣ በምላሱ እና በእጁ የሚታገል ሙጃሂድ” ْمُجَاهِد ይባላል፥ በብዜት ደግሞ “ሙጃሂዲን” مُجَٰهِدِين ይባላሉ። የመጀመሪያው ጂሃድ ከራስ ጋር የሚደረግ ትግል ነው። ተዝኪያህ ከራሳችን ዝንባሌ ጋር የሚደረግ ጂሃድ ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 22, ሐዲስ 3
ፈዷላህ ኢብኑ ዑበይድ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው፦ *”ከራሱ ነፍስ ጋር የታገለ ሙጃሂድ ነው”*። فَضَالَةَ بْنَ عُبَيْدٍ، وَسَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏”‏ الْمُجَاهِدُ مَنْ جَاهَدَ نَفْسَهُ

እዚህ ሐዲስ ላይ “የታገለ” ለሚለው የገባው ቃል “ጃሀደ” جَاهَدَ መሆኑን ልብ አድርግ። ነፍስን ለማጥራት ተዝኪያህ ማድረግም “ጁሁድ” جُهْد ነው፥ ሸይኩል ኢሥላም ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁሏህ ስለ ጂሃዱ አን-ነፍሥ ሲናገሩ እንዲህ ብለዋል፦
ረውደቱል ሙሒቢን 1/478
*”ከነፍስ እና ከስሜት ጋር የሚደረግ ጂሃድ ከኩፋር እና ከሙናፊቂ ጋር ለሚደረግ ጂሃድ መሠረት ነው። እርሱ(ሙሥሊም) እነርሱን ከመታገሉ በፊት ቅድሚያ ነፍሱና ስሜቱን መታገል ይቀድማልና”*። جِهَادُ النَّفْسِ وَالْهَوَى أَصْلُ جِهَادِ الْكُفَّارِ وَالْمُنَافِقِينَ فَإِنَّهُ لَا يَقْدِرُ عَلَى جِهَادِهِمْ حَتَّى يُجَاهِدَ نَفْسَهُ وَهَوَاهُ أَوَّلًا حَتَّى يَخْرُجَ إلَيْهِمْ

ቅድሚያ ውስጣቸን ካለው ዘረኝነት፣ ጎጠኝነት፣ ጠርዘኝነት፣ ቡድንተኝነት ጋር መፋለም አለብን። ይህ ጂሃዱ አን-ነፍሥ ሲሆን ሁለተኛ ጂሃድ ከኩፋር እና ከሙናፊቂ ጋር የሚደረግ ጂሃድ ነው። ይህ ጂሃድ ከኢማን ቀጥሎ ያለው የተሻለ ሥራ ነው፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 25 , ሐዲስ 7:
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው፦ *“ነቢዩ”ﷺ” የትኛው ነው የተሻለ ድርጊት? ተብለው ተጠይቀው ነበር፥ እርሳቸውም፦ “በአላህ እና በመልእክተኛው ማመን” አሉ። በመቀጠልስ? ተብለው ተጠየቁ፥ እርሳቸውም፦ “በአላህ መንገድ ጂሃድ ላይ መሳተፍ” አሉ። በመቀጠልስ? ተብለው ተጠየቁ፥ እርሳቸውም፦ “ሐጅ መብሩር” አለ*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ سُئِلَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم أَىُّ الأَعْمَالِ أَفْضَلُ قَالَ ‏”‏ إِيمَانٌ بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ ‏”‌‏.‏ قِيلَ ثُمَّ مَاذَا قَالَ ‏”‏ جِهَادٌ فِي سَبِيلِ اللَّهِ ‏”‌‏.‏ قِيلَ ثُمَّ مَاذَا قَالَ ‏”‏ حَجٌّ مَبْرُورٌ ‏”‌‏.‏
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 15, ሐዲስ 28
አነሥ እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *”በንብረታችሁ፣ በነፍሶቻችሁ እና በአንደበታችሁ ሙሽሪኮችን ታገሉ”*። عَنْ أَنَسٍ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏:‏ ‏ “‏ جَاهِدُوا الْمُشْرِكِينَ بِأَمْوَالِكُمْ وَأَنْفُسِكُمْ وَأَلْسِنَتِكُمْ ‏

"ጃሂዱ" جَاهِدُوا የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። ይህም ጂሃድ ወሰን አልፈው ለሚመጡ ሁሉ በአላህ መንገድ መጋደል ነው፦
2፥190 *እነዚያንም የሚጋደሉዋችሁን በአላህ መንገድ ተጋደሉ፡፡ ወሰንንም አትለፉ፤ አላህ ወሰን አላፊዎን አይወድምና*፡፡ وَقَاتِلُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ الَّذِينَ يُقَاتِلُونَكُمْ وَلَا تَعْتَدُوا ۚ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْمُعْتَدِينَ
2፥218 *እነዚያ ያመኑትና እነዚያም ከአገራቸው የተሰደዱት በአላህም መንገድ ላይ የተጋደሉት እነዚያ የአላህን እዝነት ይከጅላሉ*፡፡ አላህም እጅግ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَالَّذِينَ هَاجَرُوا وَجَاهَدُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ أُولَـٰئِكَ يَرْجُونَ رَحْمَتَ اللَّهِ ۚ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
2፥193 *ሁከት እስከማይገኝ እና ሃይማኖት ለአላህ ብቻ እስከሚኾን ድረስ ተጋደሉዋቸው፡፡ ቢከለክሉም ወሰንን ማለፍ በበዳዮች ላይ እንጂ የለም ወሰን አትለፉባቸው*፡፡ وَقَاتِلُوهُمْ حَتَّىٰ لَا تَكُونَ فِتْنَةٌ وَيَكُونَ الدِّينُ لِلَّهِ ۖ فَإِنِ انتَهَوْا فَلَا عُدْوَانَ إِلَّا عَلَى الظَّالِمِينَ
ይህ የሚሆነው ሰላም ሆኖ ሁከት እስከሚጠፋ ድረስ እና ሃይማኖት ለአላህ እስከሚሆን ድረስ ነው። “እነዚያንም የሚጋደሉዋችሁን በአላህ መንገድ ተጋደሉ” እስከ መቼ? “ሃይማኖት ለአላህ ብቻ እስከሚኾን ድረስ” እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ወሰን አልፎ በሚመጣው ላይ ለእነዚያ ለሚገደሉት ምእመናን እነርሱ የተበደሉ በመኾናቸው መጋደል ተፈቀደላቸው፦
22፥39 *ለእነዚያ ለሚገደሉት ምእመናን እነርሱ የተበደሉ በመኾናቸው መጋደል ተፈቀደላቸው*፡፡ أُذِنَ لِلَّذِينَ يُقَاتَلُونَ بِأَنَّهُمْ ظُلِمُوا ۚ وَإِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ نَصْرِهِمْ لَقَدِيرٌ

መጋደል ከሌለ ገዳማት፣ ቤተክርስቲያኖችም፣ ምኩራቦችም በውስጣቸው የአላህ ስም በብዛት የሚወሳባቸው መስጊዶችም ይፈርሳሉ፦
22፥40 *ለእነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ከማለታቸው በስተቀር ያለ አግባብ ከአገራቸው የተባረሩ ለሆኑት ተፈቀደ፡፡ አላህ ሰዎችን ከፊላቸውን በከፊሉ መገፍተሩ ባልነበረ ኖሮ ገዳማት፣ ቤተክርስቲያኖችም፣ ምኩራቦችም በውስጣቸው የአላህ ስም በብዛት የሚወሳባቸው መስጊዶችም፤ በተፈረሱ ነበር*፡፡ አላህም ሃይማኖቱን የሚረዳውን ሰው በእርግጥ ይረዳዋል፡፡ አላህ ብርቱ አሸናፊ ነውና፡፡ الَّذِينَ أُخْرِجُوا مِن دِيَارِهِم بِغَيْرِ حَقٍّ إِلَّا أَن يَقُولُوا رَبُّنَا اللَّهُ ۗ وَلَوْلَا دَفْعُ اللَّهِ النَّاسَ بَعْضَهُم بِبَعْضٍ لَّهُدِّمَتْ صَوَامِعُ وَبِيَعٌ وَصَلَوَاتٌ وَمَسَاجِدُ يُذْكَرُ فِيهَا اسْمُ اللَّهِ كَثِيرًا ۗ وَلَيَنصُرَنَّ اللَّهُ مَن يَنصُرُهُ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَقَوِيٌّ عَزِيزٌ

በአላህ መንገድ ከጠላት ጋር የሚደረግ ጂሃድ ሦስት አይነት ነው፥ እርሱም በእጅ የሚደረግ፣ በምላስ የሚደረግ እና በልብ የሚደረግ ነው፦
ሪያዱ አስ-ሷሊሒን መጽሐፍ 1, ሐዲስ 184
አቢ ሠዒድ አል-ኹድሪይ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “የአላህ መልክተኛ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦ *“ከእናንተ ውስጥ እኩይ ነገር ያየ በእጁ ይቀይረው፣ ካልቻለ በምላሱ ያውግዝ፣ ይህንንም ካልቻለ በልቡ ይጥላው። በልብ መጥላት ደካማው ኢማን ነው”*። عن أبي سعيد الخدري رضي الله عنه قال‏:‏ سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول‏:‏ ‏ “‏من رأى الخد منكرًا فليغيره بيده ، فإن لم يستطع فبلسانه، فإن لم يستطع فبقلبه وذلك أضعف الإيمان

ሡናውን የሚይዙ እና በትእዛዙ የሚመሩ ቀደምት ሠለፎች ጂሃድን መንሃጃቸው አርገው አልፈዋል፥ የሚያሳዝነው ዛሬ ያለነው "ከእነርሱ በኃላ የማያደርጉትን የሚናገሩ እና ያልታዘዙትን የሚያደርጉ ተተኪዎች ይመጣሉ" የተባልነው ትውልድ ነን፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 86
ዐብደላህ ኢብኑ መሥዑድ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"አላህ ከእኔ ሕዝብ በፊት ከነቢይ አንድንም አላከም፥ ሡናውን የሚይዙ እና በትእዛዙ የሚመሩ ሐዋርያት እና ባልደረቦች ከሕዝቡ ቢያደርግለት እንጂ። ከዚያም ከእነርሱ በኃላ የማያደርጉትን የሚናገሩ እና ያልታዘዙትን የሚያደርጉ ተተኪዎች ይመጣሉ። እነርሱን በእጁ የታገላቸው እርሱ አማኝ ነው፣ በምላሱ የታገላቸው እርሱ አማኝ ነው፣ በልቡ የታገላቸው እርሱ አማኝ ነው። ከዚህ ውጪ የጎመንዘር ያህል ኢማን የለም"*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ مَسْعُودٍ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ‏ "‏ مَا مِنْ نَبِيٍّ بَعَثَهُ اللَّهُ فِي أُمَّةٍ قَبْلِي إِلاَّ كَانَ لَهُ مِنْ أُمَّتِهِ حَوَارِيُّونَ وَأَصْحَابٌ يَأْخُذُونَ بِسُنَّتِهِ وَيَقْتَدُونَ بِأَمْرِهِ ثُمَّ إِنَّهَا تَخْلُفُ مِنْ بَعْدِهِمْ خُلُوفٌ يَقُولُونَ مَا لاَ يَفْعَلُونَ وَيَفْعَلُونَ مَا لاَ يُؤْمَرُونَ فَمَنْ جَاهَدَهُمْ بِيَدِهِ فَهُوَ مُؤْمِنٌ وَمَنْ جَاهَدَهُمْ بِلِسَانِهِ فَهُوَ مُؤْمِنٌ وَمَنْ جَاهَدَهُمْ بِقَلْبِهِ فَهُوَ مُؤْمِنٌ وَلَيْسَ وَرَاءَ ذَلِكَ مِنَ الإِيمَانِ حَبَّةُ خَرْدَلٍ ‏

በእጅ፣ በምላስ እና በልቡ ያልታገለ የጎመንዘር ያህል ኢማን የለውም። ምእምናን ማለት በገንዘቦቻቸው እና በነፍሶቻቸውም በአላህ መንገድ የታገሉት ብቻ ናቸው፥ እነዚያ እነርሱ እውነተኞቹ ናቸው። አላህ እኛን ውርደት ያከናነበን ከጂሃድ በመራቃችን ነው፦
49፥15 *ምእምናን እነዚያ በአላህ እና በመልእከተኛው ያመኑት ከዚያም ያልተጠራጠሩት “በገንዘቦቻቸው እና በነፍሶቻቸውም በአላህ መንገድ የታገሉት ብቻ ናቸው”፡፡ እነዚያ እነርሱ እውነተኞቹ ናቸው*፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ الَّذِينَ آمَنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ ثُمَّ لَمْ يَرْتَابُوا وَجَاهَدُوا بِأَمْوَالِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ ۚ أُولَـٰئِكَ هُمُ الصَّادِقُونَ
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 24, ሐዲስ 47
ኢብኑ ዑመር"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"በሪባ በተገበያያቹህ ጊዜ፣ ከብቶችን በተከትላችሁ ጊዜ፣ እርሻኝ በወዳዳቹህ ጊዜ እና ጂሃድን በተዋቹህ ጊዜ አላህ ውርደት ያከናንባችኃል፥ ይህንንም ውርደት ወደ ዲናቹህ እስካልተመለሳቹህ ድረስ ከእናንተ አያነሳም"*። عَنِ ابْنِ عُمَرَ، قَالَ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ "‏ إِذَا تَبَايَعْتُمْ بِالْعِينَةِ وَأَخَذْتُمْ أَذْنَابَ الْبَقَرِ وَرَضِيتُمْ بِالزَّرْعِ وَتَرَكْتُمُ الْجِهَادَ سَلَّطَ اللَّهُ عَلَيْكُمْ ذُلاًّ لاَ يَنْزِعُهُ حَتَّى تَرْجِعُوا إِلَى دِينِكُمْ

መሣጂዶች ሲፈርሱና ሲቃጠሉ በእጃችን ካተከላከልን ወይም በምላሳችን ካልተቃወምን አሊያም በልባችን ጉዳዩን ካልጠላን የእኛ ዲነኛ መሆን ፋይዳው ምኑ ላይ ነው? አላህ በእርሱን መንገድ የሚታገሉ ሙጃሂድ ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ቅድስት ሥላሴ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

4፥171 *”እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፡፡ በአላህም ላይ እውነትን እንጅ አትናገሩ”*፡፡ .. *”«ሦስት ናቸው» አትበሉም”*፡፡ ተከልከሉ፤ ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ *”አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው”*፡፡ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا تَغْلُوا۟ فِى دِينِكُمْ وَلَا تَقُولُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ إِلَّا ٱلْحَقَّ ۚ إِنَّمَا ٱلْمَسِيحُ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ ٱللَّهِ وَكَلِمَتُهُۥٓ أَلْقَىٰهَآ إِلَىٰ مَرْيَمَ وَرُوحٌۭ مِّنْهُ ۖ فَـَٔامِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦ ۖ وَلَا تَقُولُوا۟ ثَلَٰثَةٌ ۚ ٱنتَهُوا۟ خَيْرًۭا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا ٱللَّهُ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ سُبْحَٰنَهُۥٓ أَن يَكُونَ لَهُۥ وَلَدٌۭ ۘ لَّهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ ۗ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَكِيلًۭا

አምላካችን አላህ በቁርኣን ከተገለጹት ስሞቹ አንዱ "አል-ቁዱሥ" الْقُدُّوس ሲሆን ትርጉሙ "ቅዱሱ" ወይም "ከጉድለት ሁሉ የጠራው" ማለት ነው፦
59፥23 እርሱ አላህ ነው፡፡ ያ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ፣ ንጉሡ፣ *ቅዱሱ*፣ የሰላም ባለቤቱ፣ ጸጥታን ሰጪው፣ ባሮቹን ጠባቂው፣ አሸናፊው፣ ኀያሉ፣ ኩሩው ነው፡፡ አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፡፡ هُوَ اللَّهُ الَّذِي لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ الْمَلِكُ الْقُدُّوسُ السَّلَامُ الْمُؤْمِنُ الْمُهَيْمِنُ الْعَزِيزُ الْجَبَّارُ الْمُتَكَبِّرُ ۚ سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يُشْرِكُونَ
62፥1 በሰማያት ያለው በምድርም ያለው ሁሉ ለአላህ ንጉሥ፣ *ቅዱስ*፣ አሸናፊ፣ ጥበበኛ ለኾነው ያሞግሳል፡፡ يُسَبِّحُ لِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ الْمَلِكِ الْقُدُّوسِ الْعَزِيزِ الْحَكِيمِ

በባይብልም ከሄድን አንዱ አምላክ "ቅዱስ" ተብሏል፥ እንደ እርሱ ያለ ቅዱስ የለም፦
1ኛ ሳሙኤል 2፥2 *“እንደ ያህዌህ ቅዱስ የለምና”፥ እንደ አምላካችንም ጻድቅ የለምና፤ “ከአንተ በቀር ቅዱስ” የለም*።
ራእይ 15፥4 *“አንተ ብቻ ቅዱስ” ነህና*፥

“አንተ” የሚለው ነጠላ ተውላጠ-ስም አንድ ነጠላ ማንነት ብቻ ቅዱስ እንደተባለ ፍትውና ቁልጭ አድርጎ ያስረዳል፥ ሶስት ማንነትቶች ቢሆኑ ኖሮ “እናንተ” ተብሎ ይቀመጥ ነበር። “ከእናንተ” በቀር ቅዱስ የለም” ቢል ኖሮ ለሶስት አካላት ያዋጣ ነበር፥ ቅሉ ግን "አንተ ብቻ ቅዱስ ነህ" ተብሏል። እርሱ ቅዱስ የተባለው ፍጡራን በተባሉበት ስሌትና ቀመር አይደለም፥ ለምሳሌ ሰው እና መላእክት ቅዱሳን ተብለዋል፦
ዘሌዋውያን 11፥45 *እንግዲህ “እኔ ቅዱስ ነኝ እና እናንተ ቅዱሳን”* ሁኑ።
ኢዮብ 15፥15 እነሆ፥ *በቅዱሳኑ ስንኳ አይታመንም*፤ ሰማያትም በፊቱ ንጹሐን አይደሉም።

"ቅዱስ" ነጠላ ተባዕታይ መደብ ሲሆን የቅዱስ ብዙ ቁጥር "ቅዱሳን" ነው። የሥላሴ አማንያን"Trinitarian"፦ "መላእክት አንዱን አምላክ ሦስት ጊዜ “ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ” ማለታቸው ሦስት አካላት እንዳሉ ማሳያ ነው" የሚል ስሁት ሙግት አላቸው፦
ኢሳይያስ 6፥3 አንዱም ለአንዱ፦ *“ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥” የሠራዊት ጌታ ያህዌህ፤ ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮኽ ነበር*።
ራእይ 4፥8 *“ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ” የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እያሉ ቀንና ሌሊት አያርፉም*።

ይህ ሙግት ውኃ የማያነሳ እና የማይቋጥር ሙግት ነው። ምክንያቱም አንድ ነገር ሦስት ጊዜ መጠቀሱ ያንን ነገር ሦስት ካደረገው ኤርሚያስ ምድርን ሦስት ጊዜ “ምድር ሆይ፥ ምድር ሆይ፥ ምድር ሆይ” ብሎ ጠርቷል፦
ኤርምያስ 22፥29 *“ምድር ሆይ፥ ምድር ሆይ፥ ምድር ሆይ”*፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሚ።

ምድር ሦስት ጊዜ መጠራቷ ምድር ሦስት አካላት ናት ያሰኛልን? በተጨማሪ ኤርሚያስ የእግዚአብሔርን መቅደስ ሦስት ጊዜ “የእግዚአብሔር መቅደስ፥ የእግዚአብሔር መቅደስ፥ የእግዚአብሔር መቅደስ” ብሎ ጠርቷል፦
ኤርሚያስ 7፥4 *የእግዚአብሔር መቅደስ፥ የእግዚአብሔር መቅደስ፥ የእግዚአብሔር መቅደስ ይህ ነው እያላችሁ በሐሰት ቃል አትታመኑ*።

የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሦስት ጊዜ መጠራቱ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሦስት አካላት ነው ያሰኛልን? ሌላ ናሙና የይሁዳ ምድር ባድማ እንደሚያደርጋት ሦስት ጊዜ ተናግሯል፦
ሕዝቅኤል 21፥27 *ባድማ፥ ባድማ፥ ባድማ አደርጋታለሁ*።

ባድማ እንደሚያደርግ ሦስት ጊዜ መናገሩ ሦስት ጊዜ ማድረጉን ያሰኛልን? መጽሐፈ ኩፋሌ የሚባለው የኦርቶዶክስ የቀኖና መጽሐፍ ላይ ደግሞ አብርሃምን ሦስት ጊዜ አብርሃም፥ አብርሃም፥ አብርሃም” ይለዋል፦
ኩፋሌ 14፥5 “እግዚአብሔርም *አብርሃምን፥ “አብርሃም፥ አብርሃም፥ አብርሃም” ብሎ ጠራው፥ አብርሃምም “አቤት አለሁ”አለ*።

አብርሃም ሦስት ጊዜ መጠራቱ አብርሃም ሦስት አካላት ነው ያሰኛልን? መልክአ ኢየሱስ የሚባለው የኦርቶዶክስ መጽሐፍ ላይ ኢየሱስን ሦስት ጊዜ “ኢየሱስ፥ ኢየሱስ፥ ኢየሱስ" ይለዋል፦
*“ኢየሱስ ኢየሱስ፥ ኢየሱስ”* ክርስቶስ ዘሰረጽከ እመቤተ ሌዊ ኮሬባዊ መለኮታዊ ቃል ሰማያዊ እም ድንግል ተወለደ።

ኢየሱስ የሚለው ቃል ሦስት ጊዜ መደገሙ ከድንግል የተወለደው ኢየሱስ ሦስት አካላት ነውን? ዘፍጥረት ላይ ደግሞ አብርሃም ሁለቴ ስሙ ተደግሟል፦
ዘፍጥረት 22፥11የእግዚአብሔር መልአክም ከሰማይ ጠራና። *“አብርሃም፥ አብርሃም”* አለው።
አብርሃም ሁለት አካል ነውን? ኢየሱስን ሁለት ጊዜ “ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ” ይሉታል፦
ማቴዎስ 7፥21 *“ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ”* የሚለኝ ሁሉ መንግስተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።

ኢየሱስ ሁለት አካል ነውን? ሙሴ ሁለት ጊዜ “ሙሴ ሙሴ፥ ሙሴ ሙሴ” ተብሏል፦
ዘጽአት 3፥4 “እግዚአብሔር ከቁጥቋጦው ውስጥ እርሱን ጠርቶ፦ *ሙሴ፥ ሙሴ ሆይ አለ*።

ሙሴ ሁለት አካል ነውን? እንዳትሰክሩ ብለን እንጂ ማስረጃ በቁና ሰፍረን መስጠት እንችላለን። አይሁዶች በሥላሴ አያምኑም፥ ታዲያ ለምን አንድ ጉዳይ ሶስት ጊዜ ተደጋገመ? ለሚለው መልሳቸው "አንድ ስም ከአንድ በላይ ጊዜ መጠራት ጉዳዩን አጽንዖትና አንክሮት ለመስጠት እንጂ ያንን ስም ብዙ አካል አያደርገውም" ይላሉ።
ሲቀጥል “ቅዱስ” ተባታይ ሲሆን “ቅድስት” አንስታይ ነው፥ ሥላሴ ልክ እንደ “አጋእዝት” ማለትም “ጌቶች” ተብለው እንደሚጠቀሙበት “ቅዱሳን” ተብሎ መጠራት ነበረባቸው እንጂ እንደ ሴት “ቅድስት” እንዴት ይባላሉ? ሥላሴ ሴት ናት እንዴ “ቅድስት” የተባለችው? "አይ አዛኝ “ስለሆኑ” ነው" ብሎ አንድ ክርስቲያን ወገን የቋንቋ፣ የሰዋስው ወይም የባይብል መረጃ የሌለው የጨበጣ መልስ ሰቶኛል። “ስለሆነ” ተብሎ የሚመለክ እንጂ “ስለሆኑ” ተብለው የሚመለኩ ሦስት ቅዱሳን የሉም።

ሢሰልስ "ቅድስት" ለብዙ ቁጥር ወይም ለማኅበር ይውላል፥ ለዛ ነው "ሥሉስ ቅዱስ" ማለትም "ሦስት ቅዱስ" የሚሉት። "ሦስት ቅዱስ አለ" ብሎ ማመን የጤንነት ነውን? በሦስነቱ ሲቀደስ እና ሢሰለስ የሚኖር አምላክ በባይብል ሽታው የለም። ከዚህ በተቃራኒ ውዳሴ ማርያም ይወድስዋ ላይ መልአኩ ማርያምን ሦስት ቅዱስ እንዳለና ወልድ "ከሦስቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ ነው" ይለናል፦
"መልአኩም እንዲህ አላት፦ "መንፈስ ቅዱስ ይጠብቅሻል የልዑል ኃይልም ያድርብሻል፥ *ይህ የሚወለደው ከሦስቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ ነው*።

"ይህ የሚወለደው ከሦስቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ ነው" የሚለው ኃይለ-ቃል ሉቃስ ላይ አለመኖሩ በራሱ የተጭበረበረ ሐረግ ነው። እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በአላህም ላይ እውነትን እንጅ አትናገሩ፡፡ ፈጣሪን «ሦስት ናቸው» አትበሉም፥ ተከልከሉ። ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አላህ በአንድነቱ ላይ ሦስትነት የሌለበት አንድ አምላክ ብቻ ነው፦
4፥171 *”እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፡፡ በአላህም ላይ እውነትን እንጅ አትናገሩ”*፡፡ .. *”«ሦስት ናቸው» አትበሉም”*፡፡ ተከልከሉ፤ ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ *”አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው”*፡፡ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا تَغْلُوا۟ فِى دِينِكُمْ وَلَا تَقُولُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ إِلَّا ٱلْحَقَّ ۚ إِنَّمَا ٱلْمَسِيحُ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ ٱللَّهِ وَكَلِمَتُهُۥٓ أَلْقَىٰهَآ إِلَىٰ مَرْيَمَ وَرُوحٌۭ مِّنْهُ ۖ فَـَٔامِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦ ۖ وَلَا تَقُولُوا۟ ثَلَٰثَةٌ ۚ ٱنتَهُوا۟ خَيْرًۭا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا ٱللَّهُ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ سُبْحَٰنَهُۥٓ أَن يَكُونَ لَهُۥ وَلَدٌۭ ۘ لَّهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ ۗ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَكِيلًۭا

አላህ ሂዳያ ይስጣችሁ፥ እኛንም በተውሒድ ያጽናን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ታላቁ ታምር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

6:124 "ታምርም" በመጣላቸው ጊዜ፡- «የአላህ መልክተኞች የተሰጡትን ብጤ እስክንሰጥ ድረስ በፍጹም አናምንም» አሉ وَإِذَا جَآءَتْهُمْ ءَايَةٌۭ قَالُوا۟ لَن نُّؤْمِنَ حَتَّىٰ نُؤْتَىٰ مِثْلَ مَآ أُوتِىَ رُسُلُ ٱللَّهِ ۘ ٱللَّهُ أَعْلَمُ حَيْثُ يَجْعَلُ رِسَالَتَهُۥ ۗ سَيُصِيبُ ٱلَّذِينَ أَجْرَمُوا۟ صَغَارٌ عِندَ ٱللَّهِ وَعَذَابٌۭ شَدِيدٌۢ بِمَا كَانُوا۟ يَمْكُرُونَ ፡፡

ቁርኣን ለነቢያችን ነቢይነት ማረጋገጫ ይሆን ዘንድ ከተሰጣቸው ተአምራት ውስጥ ታላቁ እና ዋነኛው ነው፣ የቁርኣን ተአምራዊነት ከቀደምት ነቢያት ተአምራት በሁለት መልኩ ይለያል፦
አንደኛ የቀደምት ነቢያት ተአምራት በአይን የሚታይ፣ በእጅ የሚዳሰስ ነው፣ ይህም ታምር ”ሒስሲይ” ይባላል፣ የቀደምት ነቢያት ተአምር ከነቢይነት ዘመናቸው ጋር ብቻ የተቆራኘ ነው፣ ከእነርሱ ሞት በኋላ ያበቃል፣ ይህም ታምር ”ወቅቲይ” ማለትም ጊዜአዊ ይሰኛል፡፡
ሁለተኛ ለነቢያችን ነቢይነት እንደ ማስረጃ የተሰጣቸው ቁርኣን ግን ህሊናን የሚያናግር፡ አእምሮን የሚቆጣጠርና ልብን የሚገዛ፣ በሚያስተላልፋቸው መልእክቱ ሰዎችን ለለውጥ የሚዳርግ ነው፣ ይህም ታምር ”መዕነዊይ” ይባላል፣ ቁርኣን ከነቢያችን ሞት በኋላ እንኳ ተአምራዊነቱ አላከተመም፣ እስከ ቂያማ ድረስ በነበረው ተአምራዊነቱ ይቀጥላል፤ በዚህም ”አበዲይ” ይሰኛል፡፡ እስቲ ይህንን ታላቅ ታምር በወረደበት ወቅት ሰዎች እንዴት እንዳስተባበሉት እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
"የአላህ ታምራት"
ቁርአን በወረደ ጊዜ ሰዎች፦ "ከጌታውም በእርሱ ላይ ለምን ተዓምር አልተወረደም" አሉ፤ አምላካችን አላህም፦ "አላህ ተአምርን በማውረድ ላይ ቻይ ነው" በላቸው ብሎ መለሰ ሰጠ፦
6:37 *«ከጌታውም በእርሱ ላይ ለምን ተዓምር አልተወረደም»* አሉ፡፡ *«አላህ ተአምርን በማውረድ ላይ ቻይ ነው» በላቸው*፡፡ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡

አላህ ቁርኣንን ታምር አድርጎ ለነቢያችን ነቢይነት ማረጋገጫ ይሆን ዘንድ እንዳወረደው ይናገራል፦
3:108 ይህች በአንተ ላይ በእዉነት የምናነባት ስትሆን የአላህ *ታምራት* آيَاتُ ናት፤
45:6 እነዚህ፣ በአንተ ላይ በእውነት የምናነባቸው ሲኾኑ *የአላህ ታምራት* آيَاتُ ናቸው፤ ከአላህና *ከታምራቶቹም* وَآيَاتِهِ ወዲያ በየትኛው ንግግር ያምናሉ?
2:252 እነዚህ በእውነት በአንተ ላይ የምናነባቸው ሲኾኑ *የአላህ ታምራት* آيَاتُ ናቸው፤
3:58 ይህ *ከታምራቶች"* الْآيَاتِ እና ጥበብን ከያዘዉ ተግሣጥ ሲሆን በአንተ ላይ እናነበዋለን።

አላህ የሚነበብ ሆኖ ቁርአን መወረዱ ታምር እንደሆነ እንደነገረን ሁሉ ነብያችንም ቁርአን ለእሳቸው ነብይነት ታምር እንደሆነ በአጽንኦትና በአንክሮት ነግረውናል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 66 , ሐዲስ 3:
አቢ ሁረይራህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ ነብዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ ማንኛውም ነብይ ህዝቦቹ ያምኑበት ዘንድ ታምር ተሰጠውታል፣ ነገር ግን ለእኔ የተሰጠኝ ታምር አላህ ወደ እኔ ያወረደው ወህይ ነው عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ مَا مِنَ الأَنْبِيَاءِ نَبِيٌّ إِلاَّ أُعْطِيَ مَا مِثْلُهُ آمَنَ عَلَيْهِ الْبَشَرُ، وَإِنَّمَا كَانَ الَّذِي أُوتِيتُ وَحْيًا أَوْحَاهُ اللَّهُ إِلَىَّ فَأَرْجُو أَنْ أَكُونَ أَكْثَرَهُمْ تَابِعًا يَوْمَ الْقِيَامَةِ ‏" ።

ነጥብ ሁለት
"ማስተባበያ"
ሰዎች ቁርአን ታምር ሆኖ በመጣላቸው ጊዜ፡- "የአላህ መልክተኞች የተሰጡትን ብጤ እስክንሰጥ ድረስ በፍጹም አናምንም" ወይም "ለሙሳ የተሰጠው ቢጤ አይሰጠውም ኖሯልን ” ብለው ይህንን ታምር አስተባበሉ፦
6:124 *"ታምርም በመጣላቸው ጊዜ"*፡- «የአላህ መልክተኞች የተሰጡትን ብጤ እስክንሰጥ ድረስ በፍጹም አናምንም» አሉ፡፡
28:48 እውነቱም ከእኛ ዘንድ በመጣላቸው ጊዜ “ለሙሳ የተሰጠው ቢጤ አይሰጠውም ኖሯልን ” አሉ ። ከዚህ በፊት ሙሳ በተሰጠው አልካዱምን? አሉም “የተረዳዱ ሁለት ድግምተኞች ናቸው” ፤ አሉም “እኛ በሁለቱም ከሀዲዎች ነን”።

ለሙሳ የተሰጠው ግልጽ የሆኑን "ዘጠኝ ታምራቶች" ናቸው፦
17:101 ለሙሳም ግልጽ የሆኑን "ዘጠኝ ታምራቶች" በእርግጥ ሰጠነው፤

አላህ ታምር ብሎ "ዘጠኝ ታምራቶች" ቢያሳይም በወቅቱ ሙሳና ሃሩንን "የተረዳዱ ሁለት ድግምተኞች ናቸው” አሉ፤ ከዚህ ታምር ይልቅ "ሙሳ ሆይ አላህን በግልጽ እስከምናይልህ ድረስ ለአንተ በፍጹም አናምንልህም" አሉ፦
2:55 ሙሳ ሆይ አላህን በግልጽ እስከምናይልህ ድረስ በአንተ በፍጹም አናምንልህም ”

በወቅቱ የነበሩ ሰዎች ስለ ነብያችን፦ "ለሙሳ የተሰጠው ቢጤ አይሰጠውም ኖሯልን ” አሉ፤ አላህም፦ "ከዚህ በፊት ሙሳ በተሰጠው አልካዱምን?" በማለት ያ የተባለው ታምር ተመልሶ ቢመጣ አሁን ማስተባበላቸውን እንደማይቀር ተናግሯል።
ነጥብ ሶስት
"አስጠንቃቂ"
እነዚያም የካዱት፦ "በእርሱ ላይ ከጌታው ታምር ለምን አልተወረደለትም?" ብለው የጠየቁት ታምር የአላህ መልክተኞች የተሰጡትን ብጤ አይነት ታምር ነው፤ ይህንን ታምር ነብያችን በራሳቸው ማምጣት አይችሉም፤ እርሳቸው አስጠንቃቂ እንጂ በፍላጎታቸው ታምር እውራጅ አይደሉም፤ ታምር አውራጅ አላህ ነው፤ ስለሆነም ቁርአን በእርሳቸው ላይ ታምር አድርጎ አውርዷል፦
13:7 እነዚያም የካዱት፦ "በእርሱ ላይ ከጌታው ታምር ለምን አልተወረደለትም?" ይላሉ፤ አንተ "አስጠንቃቂ" ብቻ ነህ ለሕዝብም ሁሉ መሪ አላቸው።
10:20 በእርሱ ላይም ከጌታው የሆነች ታምር ለምን አትወረድለትም ይላሉ፡፡ «ሩቅ ነገርም ሁሉ የአላህ ብቻ ነው፡፡ ተጠባበቁም፤ እኔ ከናንተ ጋር ከሚጠባበቁት ነኝና» በላቸው፡፡
6:37 «ከጌታውም በእርሱ ላይ ለምን ተዓምር አልተወረደም» አሉ፡፡ «አላህ ተአምርን በማውረድ ላይ ቻይ ነው» በላቸው፡፡

በእርግጥም አንድ መልእክተኛ ሲመጣ አላህ በፈቃዱ ከሚሰጠው ታምር በራሱ ሊያመጣ አይችል፦
13:38 ለማንኛውም *መልክተኛ በአላህ ፈቃድ እንጂ፥ ታምር ሊያመጣ አይገባውም*፤
40:78 ለማንኛውም *መልክተኛ በአላህ ፈቃድ ካልሆነ ታምርን ሊያመጣ አይገባውም*።

መደምደሚያ
በኢየሱስ ዘመንም ኢየሱስ ብዙ ታምር እያደረገ በዘመኑ የነበሩ ሰዎች የሚጠይቁት ታምር ግን ከሰማይ ነው፤ ኢየሱስም እነርሱን የጠየቁትን ታምር ከመፈፀም ይልቅ "ለዚህ ትውልድ *"ምልክት አይሰጠውም"* ብሎ መለሰ፦
ማርቆስ 8፥11-12 ፈሪሳውያንም ወጡና ሊፈትኑት *"ከሰማይ ምልክት"* ከእርሱ ፈልገው ከእርሱ ጋር ይከራከሩ ጀመር። በመንፈሱም እጅግ ቃተተና፦ ይህ ትውልድ ስለ ምን *"ምልክት"* ይፈልጋል? እውነት እላችኋለሁ፥ ለዚህ ትውልድ *"ምልክት አይሰጠውም"* አለ።
ማቴዎስ 16:4 ክፉና አመንዝራ ትውልድ *"ምልክት"* ይሻል፥ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር *"ምልክት አይሰጠውም"*። *ትቶአቸውም ሄደ*።

ኢየሱስ፦ "ለዚህ ትውልድ ምልክት አይሰጠውም" ማለቱ ሰዎች የፈለጉት ከሰማይ ምልክት አላደርግም ማለት እንጂ ምልክት አለማድረግን አያሳይም፣ እነርሱ የፈለጉት ምልክት ከሰማይ ምልክት ነው፣ ነገር ግን ኢየሱስ እነርሱ ከጠየቁት ታምር በተቃራኒው ያደረገውን ታምር በፊታቸው ምንም ቢያደርግ በእርሱ አላመኑም፦
ዮሐንስ 12፥37-38 ነገር ግን ይህን ያህል *"ምልክት በፊታቸው ምንም ቢያደርግ"* ነቢዩ ኢሳይያስ፦ ጌታ ሆይ፥ ማን ምስክርነታችንን አመነ? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገለጠ? ብሎ የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ *"በእርሱ አላመኑም"*።

በተመሳሳይም በነቢያችን ዘመን የነበሩት ሰዎች ታምር ብለው የሚሉትና አላህ ታምር የሚለው ሁለት ለየቅል ነው፣ የቁርአንን ታላቅ ታምርነት በወቅቱ የነበሩት ሰዎች እነርሱ በሚፈልጉት መልኩ ባይመጣም ለሰው የሚበጅ ታምር ማምጣት የሚችለው አላህ ብቻ ነው፤ ከላይ የቀረበውን ነጥብ በኢየሱስ ታምር ማሳያነት በቀላሉ መረዳት ይቻላል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያ ረሱሉሏህ!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

94፥4 *መወሳትህንም ለአንተ ከፍ አድርገንልሃል*፡፡ وَرَفَعْنَا لَكَ ذِكْرَكَ

አምላካች አላህ እኛ አማንያን ነቢያችንን"ﷺ" በሸሃደተይን፣ በዒቃም፣ በአዛን፣ በተሸሁድ ጊዜ እና ስማቸው ሲጠራ ሶለዋት በማውረድ እንደናወሳቸው አድርጓል፦
94፥4 *መወሳትህንም ለአንተ ከፍ አድርገንልሃል*፡፡ وَرَفَعْنَا لَكَ ذِكْرَكَ

በተጨማሪም መወሳትን ከፍ ለማድረግ "ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያ ረሱሉሏህ" فِدَاكَ أَبِي وَأُمِّي يَا رَسُولَ اللَّه ማለትም "አባቴ እና እናቴ ለእርሶ ቤዛ ይሁንልዎ" እንላለን። እዚህ መወሳት ላይ ሚሽነሪዎች ረብጣ በሆነ ዕውቀት እጦት ሁለት ዐበይት ጥያቄ ያነሳሉ። አንዱ "መስዋዕት ለዛውም ሰው የሆኑ አባት እና እናት መስዋዕት እንዴት ለፍጡር ይቀርባል? ሲሆን ሁለተኛው "አንድ ማንነት በሌለበት በሁለተኛ መደብ "ሆይ" በማለት ማናገር ዱዓእ አይደለምን? በማለት ይጠይቃሉ። እነዚህ ጥያቄዎች በሰላና በሰከነ አእምሮ ለመመለስ ሁለት የሙግት ነጥቦችን እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
"ቤዛ"
"ፊዳእ" فِدَاء የሚለው ቃል "ፈዳ" فَدَى ማለትም "ቤዘወ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ቤዛ" "ዋቢ" "ዋስ" "ተያዥ" ማለት ነው። እኛ ነቢያችንን"ﷺ" "ፊዳከ አቢ ወኡሚ" የምንልበት እሳቸውን ዋቢ ለማድረግ እንጂ ለእርሳቸው መስዋዕት ማቅረባችንን በፍጹም አያሳይም። ምክንያቱም እራሳቸውን ነቢያችን"ﷺ" ባልደረባቸውን "ፊዳከ አቢ ወኡሚ" ብለውታል፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 1
ዐሊይ እንደተረከው፡- "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ወላጆቹን በመሰብሰብ ለሰዕድ ኢብኑ ማሊክ እንዳሉት ለማንም ሲሉ አልሰማኋቸውም፥ እኔ የኡሑድ ዘመቻ ቀን እንዲህ ሲሉ ሰማኋቸው፡፦ "ሰዕድ ሆይ! በጠላት ላይ በትርህን ወርውር! *"አባቴ እና እናቴ ቤዛ ይሁኑልክ"*። عَنْ عَلِيٍّ، قَالَ مَا رَأَيْتُ رَسُولَ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ جَمَعَ أَبَوَيْهِ لأَحَدٍ غَيْرِ سَعْدِ بْنِ مَالِكٍ فَإِنَّهُ قَالَ لَهُ يَوْمَ أُحُدٍ ‏ "‏ ارْمِ سَعْدُ فِدَاكَ أَبِي وَأُمِّي ‏

እዚህ ሐዲስ ላይ "ቤዛ" የሚለውን "መስዋዕት" በሚል ብቻ ብንረዳው ነቢያችን"ﷺ" ለሰዕድ ኢብኑ ማሊክ መስዋዕት ያቀርቡ ነበር ይባል ነበር፥ ቅሉ ግን እንደዛ አይደለም። ምክንያቱም የሰው መስዋዕት አይደለም ለሰው ለአምላክ አይቀርብም። ሲቀጥል የነቢያችን"ﷺ" አባት እና እናት በሕይወት የሉም ፥ የሌሉትን "ቤዛ ይሁኑልክ" ማለት "ዋቢ ይሁኑልክ" "ዋስ ይሁኑልክ" ማለት እንጂ "የእርድ መስዋዕት ይሁኑልክ" ማለት በፍጹም አይደለም። ይህ ፍቅርን የሚገልጹበት ዘይቤአዊ አንጋገር ነው። ሢሰልስ “መስዋዕት” የሚለው ቃል “ኑሡክ” نُسُك ሲሆን ለአላህ ብቻ የሚቀርብ "እርድ" ነው፦
22፥34 *ለሕዝብም ሁሉ ወደ አላህ መስዋዕት ማቅረብን ደነገግን*፡፡ ከቤት እንስሳት በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ብቻ ያወሱ ዘንድ አዘዝናቸው፡፡ وَلِكُلِّ أُمَّةٍ جَعَلْنَا مَنسَكًا لِّيَذْكُرُوا اسْمَ اللَّهِ عَلَىٰ مَا رَزَقَهُم مِّن بَهِيمَةِ الْأَنْعَامِ
6፥162 *«ስግደቴ፣ መስዋዕቴም፣ ሕይወቴም፣ ሞቴም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ነው»* በል፡፡ قُلْ إِنَّ صَلَاتِي وَنُسُكِي وَمَحْيَايَ وَمَمَاتِي لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ

“ሀድይ” هَدْي ማለት “የእርድ እንስሳ” ሲሆን ጊደር፣ በግ፣ ፍየል፣ ጥጃ፣ ግመል ነው፥ ይህ ለአላህ የሚቀርበው መስዋዕት “ቁርባን” ይባላል። “ቁርባን” قُرْبَان የሚለው ቃል “ቀረበ” قَرَّبَ ማለትም “ቀረበ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መቃረቢያ” “አምኃ” “እጅ መንሻ” ማለት ነው።
"ቤዛ" ማለት የግድ "መስዋዕት" ማለት ብቻ ነው ብሎ መተርጎም ክፉኛ ስህተት ነው፥ "ቤዛ" በሚለው ቃል ዙሪያ የቋንቋ ምሁራን "ዋቢ" "ዋስ" "ተያዥ" ማለት ነው ብለው አስቀምጠዋል። የተለያዩ ሙዳየ-ቃላት ይመልከቱ፦
1. አለቃ ኪዳነ ወልደ ክፍሌ 1948 ድኅረ-ልደት ገጽ 266.
2. ከሣቴ ብርሃን ተሰማ 1951 ድኅረ-ልደት ገጽ 532.

ይህንን ሙግት ወደ ባይብል በማነጻጸር ስንመለከት "ቤዛ" ማለት የግድ "መስዋዕት" ማለት ከሆነ ሀብት ለሰው ነፍስ መስዋዕት ነው ማለት ነው፦
ምሳሌ13፥8 *ለሰው ነፍስ ቤዛው ሀብቱ ነው*፤ ድሀ ግን ተግሣጽን አይሰማም።

ሀብት ለሰው ነፍስ ዋስትና ነው ማለት እንጂ ልክ እንደ በግ፣ በሬ፣ ፍየል ለፈጣሪ የሚቀርብ እርድ ነው ማለት እንዳልሆነ እሙን ነው፦
ምሳሌ 21፥18 *ኀጥእ የጻድቅ ቤዛ ነው፥ በደለኛም የቅን ሰው ቤዛ ነው*።
ኢሳይያስ 43፥3 *ግብጽን ለአንተ ቤዛ አድርጌ፥ ኢትዮጵያንና ሳባንም ለአንተ ፋንታ ሰጥቻለሁ*።

"ኀጥእ የጻድቅ ቤዛ ነው፣ በደለኛ የቅን ሰው ቤዛ ነው፣ ግብጽን ለእስራኤል ቤዛ ነው" ማለት "ኀጥእ የጻድቅ መስዋዕት ነው፣ በደለኛ የቅን ሰው መስዋዕት ነው፣ ግብጽ ለእስራኤል መስዋዕት ነው" ማለት እንደልሆነ ቅቡል ነው፦
የሐዋርያት ሥራ7፥35 በመልአኩ እጅ እግዚአብሔር ሹምና *ቤዛ አድርጎ ላከው*።

"ሙሴ ለእስራኤል ቤዛ ነው" ማለት "ሙሴ ለእስራኤል መስዋዕት ነው" ማለት አይደለም። እኛ ነቢያችንን"ﷺ" "ፊዳከ አቢ ወኡሚ" ማለታችን በዚህ ስሌትና ቀመር ተረዱት። ይህንን የሙግት ዚቅ በስሜት ሳይሆን በስሌት፥ በሙቀት ሳይሆን በዕውቀት ለመረዳት ሞክሩ።
ነጥብ ሁለት
"ሆይ"
በሁለተኛ መደብ "ያ" يَا ማለት "ሆይ" ማለት ሲሆን "ሐርፉ አን-ኒዳእ" حَرْف النِدَاء ማለትም "ሙያዊ መስተዋድድ"vocative particle" ነው። "አንድ ማንነት ሌላውን ማንነት "ሆይ" ብሎ መጠቀሙ ዱዓእ ነው" ብሎ ማለት ስህተት ነው። ምክንያቱም አምላካችን አላህ ነቢያትን አደም ሆይ! ኢብራሂም ሆይ! ሙሳ ሆይ! ዳውድ ሆይ! እያለ ይናገራል፦
2፥33 *«አደም ሆይ!* ስሞቻቸውን ንገራቸው» አለው፡፡ قَالَ يَا آدَمُ أَنبِئْهُم بِأَسْمَائِهِمْ
37፥104 ጠራነውም፤ አልነው *«ኢብራሂም ሆይ!* وَنَادَيْنَاهُ أَن يَا إِبْرَاهِيمُ
27፥9 *«ሙሳ ሆይ!* እነሆ እኔ አሸናፊው ጥበበኛው አላህ ነኝ፡፡ يَا مُوسَىٰ إِنَّهُ أَنَا اللَّهُ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ
38፥26 *ዳውድ ሆይ!* እኛ በምድር ላይ ምትክ አድርገንሃልና በሰዎች መካከል በእውነት ፍረድ፡፡ يَا دَاوُودُ إِنَّا جَعَلْنَاكَ خَلِيفَةً فِي الْأَرْضِ فَاحْكُم بَيْنَ النَّاسِ بِالْحَقِّ

በተጨማሪ ሙያዊ መስተዋድድ ተጠቅሞ "ሆይ" ማለት ወደዚያ ማንነት መጸለይን አለማሳየቱ አምላካችን አላህ ነቢያችንን"ﷺ" በሁለተኛ መደብ "አንተ ተከናናቢው ሆይ! አንተ ደራቢው ሆይ! አንተ መልክተኛ ሆይ! አንተ ነቢዩ ሆይ! በማለት መናገሩ ነው፦
73፥1 *አንተ ተከናናቢው ሆይ!* يَا أَيُّهَا الْمُزَّمِّلُ
74፥1 *አንተ ደራቢው ሆይ!* يَا أَيُّهَا الْمُدَّثِّرُ
5፥67 *አንተ መልክተኛ ሆይ!* يَا أَيُّهَا الرَّسُولُ
33፥45 *አንተ ነቢዩ ሆይ!* يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ

እንግዲህ "ሆይ" ማለት አላህ እየጸለየ ነው የሚለውን እንደማያሲዝ ሁሉ እኛም ቁርኣን ባነበነብን ቁጥር አንተ ተከናናቢው ሆይ! አንተ ደራቢው ሆይ! አንተ መልክተኛ ሆይ! አንተ ነቢዩ ሆይ! በማለት እናስታውሳቸዋለን። ልክ እንደዚሁ "ያ ረሱሉሏህ" يَا رَسُولَ اللَّه እንላቸዋለን።
ይህ በፍጹም ጸሎት ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም በባይብል እራሱ የሌሉ አካላትን በሌሉበት ያዕቆብ ሆይ! ዛብሎን ሆይ! ይሳኮር ሆይ! እያለ ይናገራል፦
ዘኍልቍ 24፥5 *ያዕቆብ ሆይ*፥
ዘዳግም 33፥18 *ዛብሎን ሆይ* በመውጣትህ፥
*ይሳኮር ሆይ*፥ በድንኳንህ ውስጥ ደስ ይበላችሁ።

እሩቅ ሳንሄድ የማይሰሙ አካላትን ምንጭ ሆይ! ተራሮች ሆይ! ምድር ሆይ! በገና ሆይ! ፍርስራሾች ሆይ! ሰይፍ ሆይ! ሞት ሆይ! ሲኦል ሆይ! አጥንቶች ሆይ! እንስሶች ሆይ! ፈረሶች ሆይ! የጥድ ዛፍ ሆይ! እያለ ይናገራል፦
ዘኍልቍ 21፥17 አንተ *ምንጭ ሆይ*፥
2ኛ ሳሙኤል 1፥21 *እናንተ የጊልቦዓ ተራሮች ሆይ*፥
ኢዮብ 16፥18 *ምድር ሆይ*፥
መዝሙር 108፥2 *በገና ሆይ*፥
ኢሳይያስ 52፥9 እናንተ የኢየሩሳሌም *ፍርስራሾች ሆይ*፥
ኤርምያስ 47፥6 አንተ የእግዚአብሔር *ሰይፍ ሆይ*፥
ሆሴዕ 13፥14 *ሞት ሆይ*፥ ቸነፈርህ ወዴት አለ? *ሲኦል ሆይ*፥ ማጥፋትህ ወዴት አለ?
ሕዝቅኤል 37፥4 እናንተ የደረቃችሁ *አጥንቶች ሆይ*፥
ኢዮኤል 2፥22 እናንተ የምድር *እንስሶች ሆይ*፥
ኤርሚያስ 46፥9 *ፈረሶች ሆይ*፥
ዘካሪያስ 11፥2 *የጥድ ዛፍ ሆይ*፥

መቼም እነዚህን በድን እና ዐቅል የሌላቸው አካላት ሙያዊ መስተዋድድ ተጠቅሞ "ሆይ" ማለት ወደ እነዚያ አካላት መጸለይን ሳይሆን ዘይቤአዊ አነጋገር ነው ካላችሁ እንግዲያውስ ከላይ ያለውን ጥያቄ በዚህ ልክና መልክ ተረዱት። የእናንተን ጥያቄ እንደ ውኃ ፈሳሽ እንደ እንግዳ ደራሽ ለመመለስ መቸኮል ሳይሆን እረጋ ብለን ልጡ የተራሰ ጉድጓዱ የተማሰ መልስ መስጠት ግድ ይላል።
ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያ ረሱሉሏህ!

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
አማኑኤል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥47 *፡-ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለች፡፡ ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፤ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል አላት*፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

አምላካችን አላህ የሩቅ ነገር ሁሉ ዐዋቂ ነው፥ ከነቢያችን"ﷺ" በፊት የተከሰተው ክስተት ለነቢያችን"ﷺ" ይተርክላቸዋል። ከተረከላቸው የሩቅ ወሬ መካከል የዒሣ ከመርየም በድንግልና መወለድ ነው፦
3፥47 *፡-ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለች፡፡ ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፤ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል አላት*፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

በባይብል ስንሄድ ኢየሱስ በድንግልና እንደተወለደ በተመሳሳይ ይናገራል፥ ነገር ግን ዐበይት ክርስትና፦ "የተወለደው አምላክ ነው" የሚል እምነት አላቸው። እዚህ ድምዳሜ ላይ ያደረሳቸው "ኢየሱስ በትንቢት አማኑኤል መባሉ ነው" የሚል ሙግት ያቀርባሉ፦
ኢሳይያስ 7፥14 *ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች*።לָכֵן יִתֵּן אֲדֹנָי הוּא, לָכֶם--אוֹת: הִנֵּה הָעַלְמָה, הָרָה וְיֹלֶדֶת בֵּן, וְקָרָאת שְׁמוֹ, עִמָּנוּ אֵל.

"ኢማኑ-ኤል" עִמָּנוּ אֵל የሁለት ቃላት ውቅር ነው፥ "ኢማኑ" עִמָּ֥נוּ ማለት "ከእኛ ጋር" ማለት ሲሆን "ኤል" אֵֽל ማለት ደግሞ "አምላክ" ማለት ነው። በጥቅሉ "አምላክ ከእኛ ጋር" ማለት ነው፥ ልክ እንደ "እስማ-ኤል" "ሳሙ-ኤል" "መላል-ኤል" "ባቱ-ኤል" "እስራ-ኤል" ወዘተ..ነው። "አምላክ" የሚለው አጫፋሪ ስም መድረሻ ቅጥያsuffix" ሆኖ የመጣ ነው፥ "አምላክ" አጫፋሪ ስም ሆኖ በመድረሻ ቅጥያ ላይ መግባት አምላክነትን ካሳየማ "እስማ-ኤል" "ሳሙ-ኤል" "መላል-ኤል" "ባቱ-ኤል" "እስራ-ኤል" ወዘተ.. አምላክ ይሆኑ ነበር። ቅሉ ግን "ኤል" አምላካዊ ማዕረግን"theo-phoric" እንጂ አምላክነትን በፍጹም አያሳይም። ሲቀጥል ይህ ስም የወጣው በወቅቱ ለተወለደ ሕጻን ነው፦
ኢሳይያስ 8፥3 *"ወደ ነቢይቱም ቀረብሁ፤ እርስዋም ፀነሰች ወንድ ልጅንም ወለደች"*።
ኢሳይያስ 8፥8 *አማኑኤል ሆይ፥ የክንፉ መዘርጋት የአገርህን ስፋት ትሞላለች*።
ኢሳይያስ 8፥10 *አምላክ ከእኛ ጋር ነውና*።

"ነቢይቱ" የተባለችው ሴት ማርያም እንዳልሆነች ቅቡል ነው፥ ያ የተወለውን ሕጻን በሁለተኛ መደብ "አማኑኤል ሆይ" በማለት ያናግረዋል። በወቅቱ የተወለደውን የአማኑኤልን አገር የአሦር መንግስት ሞልቶቷም። በዚህ ጊዜ ምልክቱ አምላክ ከእነርሱ ጋር ነው፥ "አምላክ ከእኛ ጋር ነውና" ተብሎ የተቀመጠው የዕብራይስጥ ቃል "ኢማኑ-ኤል" עִמָּנוּ אֵל መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። ይህ ሕጻን አምላክ ከእስራኤላውያን ጋር ለመሆኑ ምልክት ስለሆነ ስሙ "አማኑኤል" ነው። በአካዝ ዘመን የሶርያ ንጉሥ ረአሶን የእስራኤልም ንጉሥ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ ኢየሩሳሌምን ሊወጉ ሲመጡ፥ አምላክ ከሶርያ ጋር የተባበሩትን የኤፍሬምን ነገድ በ 65 ዓመት ውስጥ እንደሚሰባብር ምልክት ይሆን ዘንድ አምላክ አካዝን እንዲጠይቅ ተጠይቆ ለዛ ምልክት ምላሽ "ሕፃኑ ክፉን ለመጥላት መልካሙን ለመምረጥ ሳያውቅ የፈራሃቸው የሁለቱ ነገሥታት አገር ባድማ ትሆናለች" የሚል ነው፦
ኢሳይያስ 7፥16 *ሕፃኑ ክፉን ለመጥላት መልካሙን ለመምረጥ ሳያውቅ የፈራሃቸው የሁለቱ ነገሥታት አገር ባድማ ትሆናለች*።
ኢሳይያስ 8፥4 *ሕፃኑ አባቱንና እናቱን መጥራት ሳያውቅ የደማስቆን ሀብትና የሰማርያን ምርኮ በአሦር ንጉሥ ፊት ይወስዳልና"*።

ይህ ሕጻን አባት ስላለው “አባቱንና እናቱን” የሚል ኃይለ-ቃል እናነባለን። “ድንግል” ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጡ ቃል “አልማ” הָעַלְמָ֗ה ሲሆን “ልጃገረድ” “ወጣት ሴት” “ኮረዳ” “ቆንጂት” “ድንግል” “ብላቴናይት” ማለት ነው፦
ዘፍጥረት 24፥43 እነሆ፥ እኔ በውኃው ምንጭ ላይ ቆሜአለሁ፤ ውኃ ልትቀዳ ለምትመጣውም *ቆንጆ* הָֽעַלְמָה֙ ጥቂት ውኃ ከእንስራሽ አጠጪኝ፡ ስላት፥
ዘጸአት 2:8 የፈርዖንም ልጅ፦ ሂጂ አለቻት፤ *ብላቴናይቱም* הָֽעַלְמָ֔ה ሄዳ የሕፃኑን እናት ጠራች።

ስለዚህ ወጣት ሴት ወይም ድንግል ሴት አሊያም ብላቴናይት ልጅ የምትወልደው አግብታ ነው። ነቢይቱም አማኑኤልን በወቅቱ ወልዳዋለች፥ ልጇ "አማኑኤል" መባሉ አምላክ መሆኑን ወይም አምላክ መወለዱን በፍጹም አያሳያም። ስለዚህ ከመነሻው የኢሳይያስን 7፥14 ዐውደ-ንባብ በወቅቱ ለተወለደ ሕጻን ነው፥ የማቴዎስ ጸሐፊ ይህንን ትንቢት ለኢየሱስ ነው ይለናል፦
ማቴዎስ 1፥22-23 *በነቢይ ከጌታ ዘንድ፦ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው*።

የማቴዎስ ጸሐፊ እራሱ ማቴዎስ አይደለም። ይህ ሌላ አርስት ነው፥ ነገር ግን የማቴዎስ ጸሐፊ ከኢሳይያስ 7፥14 “የቀጥታ ጥቅስ”metaphrase quotation” ሲያስቀምጥ በትክክል አላስቀመጠም። ኢሳይያስ "ብላ ትጠራዋለች" የሚለውን አዛብቶ "ይሉታል" ብሎ አስቀምጦታል፥ "ትለዋለች" የሚለውን ለውጦ "ይሉታል" የሚለውን ከየት አምጥቶ ነው? ምን አለ ኮፒ ሲደረግ በትክክል ኮፒ ቢደረግ? ማን ነው የተሳሳተው መንፈስ ቅዱስ ወይስ ጸሐፊው? መንፈስ ቅዱስ ስለማይሳሳት ጸሐፊው ወይም ከጊዜ በኃላ እደ-ክታባትን ያዘጋጁት ተሳስተዋል። ሲቀጥል ኢሳይያስ የጠቀሳት ሴት ልጇን ስሙንም አማኑኤል ብላ እንደምትጠራው ይናገራል፥ ማርያም ግን ልጇን የምትጠራው "አማኑኤል" ብላ ሳይሆን "ኢየሱስ" ብላ ነው፦
ሉቃስ 1፥31 *"እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ*።
ሉቃስ 2፥21 *ሊገርዙት ስምንት ቀን በሞላ ጊዜ፥ በማኅፀን ሳይረገዝ በመልአኩ እንደ ተባለ፥ ስሙ ኢየሱስ ተብሎ ተጠራ*።

ስለዚህ አማኑኤል ብላ ካልጠራችው ኢሳይያስ የጠቀሳት ሴት ማርያም ሳትሆን በወቅቱ የነበረችው ነብይቱ ናት። ዋናው የመጣጥፉ ነጥብ ኢሳይያስ 7፥14 "አምላክ ይወለዳል" የሚለው የተንሸዋረረ መረዳት በፍጹም አያሳይም ነው። ፈጣሪ መውለድ እና መወለድ የሚባሉ የፍጡራን ባሕርይ የለውም፦
112፥3 *"አልወለደም አልተወለደምም"*። لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኃያል አምላክ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

22፥74 አላህን ተገቢ ክብሩን አላከበሩትም፡፡ *"አላህ በጣም ኃያል አሸናፊ ነው"*፡፡ مَا قَدَرُوا اللَّهَ حَقَّ قَدْرِهِ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَقَوِيٌّ عَزِيزٌ

ብዙ ዐበይት ክርስትና፦ "አምላክ ተወልዷል" ብለው ከሚጠቅሷቸው አናቅጽ መካከል ይህ ጥቅስ ነው፦
ኢሳይያስ 9፥6 *ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል*። לם רבה (לְמַרְבֵּה) הַמִּשְׂרָה וּלְשָׁלוֹם אֵין-קֵץ, עַל-כִּסֵּא דָוִד וְעַל-מַמְלַכְתּוֹ, לְהָכִין אֹתָהּ וּלְסַעֲדָהּ, בְּמִשְׁפָּט וּבִצְדָקָה; מֵעַתָּה, וְעַד-עוֹלָם, קִנְאַת יְהוָה צְבָאוֹת, תַּעֲשֶׂה-זֹּאת

"ሕጻን" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። የዚህን ጥቅስ ዐውደ-ንባብ ስመለከት ይህ ሕጻን በወቅቱ የተወለደ ሕጻን ነው፦
ኢሳይያስ 7፥16 *ሕፃኑ ክፉን ለመጥላት መልካሙን ለመምረጥ ሳያውቅ የፈራሃቸው የሁለቱ ነገሥታት አገር ባድማ ትሆናለች*።
ኢሳይያስ 8፥4 *ሕፃኑ አባቱንና እናቱን መጥራት ሳያውቅ የደማስቆን ሀብትና የሰማርያን ምርኮ በአሦር ንጉሥ ፊት ይወስዳልና"*።
ኢሳይያስ 8፥3 *"ወደ ነቢይቱም ቀረብሁ፤ እርስዋም ፀነሰች ወንድ ልጅንም ወለደች"*።

"ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና" የተባለው ሕጻን ነቢይቱ የወለደችው ወንድ ልጅ እንደሆነ ፍትውና ቁልጭ አርጎ ያሳያል። ይህ ሕጻን የማዕረግ ስሙ፦ "ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ" የሚል ነው፥ እነዚህ አራት ስም የሁለት ውሕደት ስም"compound Noun" ናቸው። አጉራ ዘለል መረዳት ያላቸው ሰዎች "ኃያል አምላክ" የሚለውን ለአምላክነቱ ከተጠቀሙ "የዘላለም አባት" የሚለውን ለአብነቱ መጠቀም ነበረባቸው፥ ምክንያቱም "ኤል" אֵ֣ל ማለትም "አምላክ" የሚለው እና "አብ" אֲבִ ማለትም "አባት" የሚለው በዕብራይስጡ በመነሻ ቅጥያ"prefix" አጫፋሪ ስም ሆነው የመጡ ናቸው። ልክ "ኤል-ጊቦር" אֵ֣ל גִּבּ֔וֹר ለሕጻኑ ስም እንደሆነ ሁሉ "ኤል-አብ" "ኤል-አታህ" "ኤል-ናታህ" "ኤል-ሹአ" "ኤል-ያህ" ለሰዎች ስም ሆኖ መጥቷል፥ ልክ "አብ-አድ" אֲבִיעַ֖ד ለሕጻኑ ስም እንደሆነ ሁሉ "አብ-ራሃም" "አብ-ጋኤል" "አብ-አሳፍ" "አብ-አልቦን" "አብ-ያህ" ለሰዎች ስም ሆኖ መጥቷል። እነዚህ ሰዎች "አምላክ" እና "አብ" እንዳልሆኑ ሁሉ ሕጻኑም "አምላክ" እና "አብ" አይደለም።
ቅሉ ግን "ኤል" אֵ֣ל አምላካዊ ማዕረግን"theo-phoric" እንጂ አምላክ መሆንን እንደማያሳይ ሁሉ "አብ" אֲבִ አባታዊ ማዕረግን"Patro-phoric" እንጂ አብ መሆን በፍጹም አያሳይም።
ሙግቱን አጥብበን ሕጻኑ ኢየሱስ ነው ብለን ብንቀበል እንኳን ኢየሱስ አምላክ እና አባት ነው ማለት አይደለም፥ ምክንያቱም ኢየሱስ የራሱ አምላክ እና አባት አለው፦
2ቆሮንቶስ 1፥3 *"የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እና አባት ይባረክ*።

"ኢየሱስ አባትነቱ ለእኛ እንጂ የራሱ አባት አለው" ካላችሁ እንግዲያውስ አምላክነቱ ለእናንተ እንጂ የራሱ አምላክ አለው። ይህም አባት እና አምላክ የሁሉም አንድ አባት እና አንድ አምላክ ነው፦
ሚልኪያስ 2፥10 *ለሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን? አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን?*
ኤፌሶን 4፥6 *ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ*።

ኢየሱስ "የእኔ አምላክ" "የእኔ አባት" የሚለው ይህንን አንድ አምላክ እና አንድ አባት ነው፦
ዮሐንስ 20፥17 *"እኔ" ወደ አባቴ እና ወደ አባታችሁ፥ ወደ አምላኬ እና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ"* ብለሽ ንገሪአቸው፤ አላት።

"ወደ" የሚለው መስተዋድድ "እኔ" የሚለውን ማንነት ከአንዱ አምላክ እና ከአንዱ አባት ነጥቶ ቁጭ አርጎታል። "አምላክ" በሚለው መድረሻ ቃል ላይ "ክ" የነበረውን ሳድስ ወደ "ኬ" ኃምስ ስናመጣው "ኬ" በሚለው ቃል ውስጥ "የእኔ" የሚል በውስጠ-ታዋቂ አገናዛቢ ዘርፍ አለ፥ "አባት" በሚለው መድረሻ ቃል ላይ "ት" የነበረውን ሳድስ ወደ "ቴ" ኃምስ ስናመጣው "ቴ" በሚለው ቃል ውስጥ "የእኔ" የሚል በውስጠ-ታዋቂ አገናዛቢ ዘርፍ አለ። ስዚህ አንዱ አምላክ እና አባት አምላክነቱ እና አባትነቱ ለኢየሱስ ሙሉ "እኔነት" እንጂ ለስጋው፣ ለሰውነቱ፣ ለቁርበቱ የሚል ድራማና ቁማር አይሠራም።
ሲቀጥል ወንድ ልጅም "ተሰጥቶናል" በሚለው ኃይለ-ቃል ሕጻኑን የሰጠ ማንነት እንዳለ ያሳያል፥ ሕጻኑ ኢየሱስ ነው ከተባለ ባይብሉ አምላክ ኢየሱስን እንደሰጠ ይናገራል፦
ዮሐንስ 3፥16 *"አምላክ" Θεὸς አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና"*።
አምላክ አምላክን ከሰጠ ሁለት አምላክ ይሆናል፥ ቅሉ ግን አምላክ የሰጠው እራሱ ወይም ሌላ አምላክን ሳይሆን ልጁን ነው።
ሢሠልስ አምላክ አሊያም አብ ተጠቅልሎ ይተኛልን? ሕጻኑ ግን ተኝቷል፦
ሉቃስ 2፥12 ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ *ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም "ተኝቶ" ታገኛላችሁ*።
ሉቃስ 2፥16 ፈጥነውም መጡ ማርያምን እና ዮሴፍን *ሕፃኑንም በግርግም "ተኝቶ" አገኙ*።

አንድ አምላክ አይተኛም፥ አያንቀላፋም። አምላክ አሊያም አብ ያድጋልን? ሕጻኑ ግን አድጓል፦ የአምላክም ጸጋ በላዩ ላይ ነበረ፦
ሉቃ2:40 *"ሕፃኑም አደገ"፥ ጥበብም ሞልቶበት በመንፈስ ጠነከረ፤ የአምላክም ጸጋ በእርሱ ላይ ነበረ*።
ሉቃስ 2፥52 *ኢየሱስም ደግሞ በጥበብና በቁመት በሞገስም በአምላክ እና በሰው ፊት "ያድግ" ነበር*።

"የአምላክም ጸጋ በአምላክ ላይ ነበረ፥ አምላክ በአምላክ ፊት ያድግ ነበር" ትርጉም አይሰጥም። አምላክ አሊያም አብ እናት አለውን? ሕጻኑ ግን እናት አለው፦
ማቴዎስ 2፥13 *ሕፃኑን እና እናቱንም* ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ።
ማቴዎስ 2፥20 *ሕፃኑን እናቱንም* ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሂድ አለ።

ሲያረብብ ሕጻኑ "ኤል-ጊቦር" אֵ֣ל גִּבּ֔וֹר ማለትም "ኃያል አምላክ" ቢባል እንኳን "ኤል-ሻዳይ" אֵ֣ל שַׁדַּ֔י ማለትም "ሁሉን የሚችል አምላክ" ነው ማለት አይደለም። ምክንያቱም ነገሥታት ""ኤል-ጊቦር" ተብለዋልና፦
ሕዝቅኤል 32፥21፤ *"ኃያላን አምላክ" በሲኦል ውስጥ ሆነው ከረዳቶቹ ጋር ይናገሩታል፤ በሰይፍም የተገደሉት ያልተገረዙ ወርደው ተኝተዋል*። יְדַבְּרוּ-לוֹ אֵלֵי גִבּוֹרִים, מִתּוֹךְ שְׁאוֹל--אֶת-עֹזְרָיו; יָרְדוּ שָׁכְבוּ הָעֲרֵלִים, חַלְלֵי-חָרֶב

በእንግሊዝኛው Young's Literal Translation የሚባለው ትርጉም ይመልከቱ። ዐማርኛው ላይ እና አንዳንድ እንግሊዝኛ ላይ በትክክል ለማስቀመጥ ቢዳዳቸውም ዕብራይስጡ ግን "ኤል-ጊቦሪም" אֵלֵ֧י גִבּוֹרִ֛ים በማለት ሳቅማማ አስቀምጦታል፥ "ጊቦሪም" גִבּוֹרִ֛ים የጊቦር ብዙ ቁጥር ሲሆን "ኃያላን" ማለት ነው። ይህ የተለመደ አገላለጽ ነው፥ "ኤል" אֵ֣ל የሚለው አጫፋሪ ስም ለቦታ ስም ሆኖ መጥቷል፦
ዘፍጥረት 35፥7 *"የዚያንም ቦታ ስም "ኤል-ቤቴል" ብሎ ጠራው"*።

"ኤል-ቤቴል" אֵ֖ל בֵּֽית אֵ֖ל ማለት "የቤቴል አምላክ" ማለት ነው። ያ ቦታ አምላክ ነውን? "አይ የቦታው ስም እንጂ ምንነቱ አምላክ አይደለም" ካላችሁ እንግዲያውስ የሕጻኑ ስም እንጂ ምንነቱ አምላክ አይደለም። ኢሳይያስ 9፥6 "ስሙም" ስለሚል "ኃያል አምላክ" ልክ እንደ "ኤል-ቤቴል" የሕጻኑ ስም እንጂ እንደ ያህዌህ በቀጥታ "ኃያል አምላክ" አልተባለም፦
ኢሳይያስ 10፥21 *"የያዕቆብም ቅሬታ ወደ ኃያል አምላክ ይመለሳሉ*"።

መቼም በኢሳይያስ ዘመን የተወለደው የነቢይቱ ልጅ ሕጻኑን ስሙ እንጂ "ኃያል አምላክ" ነው እንደማትሉ ሁሉ ኢሳይያስ 9፥6 ላይ ለኢየሱስ ድርብ ትንቢት ነው ካላችሁ እንግዲያውስ ሕጻኑ ኢየሱስ ስሙ እንጂ ምንነቱ "ኃያል አምላክ" አይደለም። ስለዚህ ብዙ ዐበይት ክርስትና፦ "አምላክ ተወልዷል" የሚለው ድምዳሜአችሁ ሥረ-መሠረት የሌለው የእምቧይ ካብ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሰንበት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

16፥124 *"ሰንበት የተደረገው በእነዚያ በእርሱ በተለያዩበት ሰዎች ላይ ብቻ ነው"*፡፡ ጌታህም በትንሣኤ ቀን ይለያዩበት በነበሩት ነገር በመካከላቸው በእርግጥ ይፈርዳል፡፡ إِنَّمَا جُعِلَ السَّبْتُ عَلَى الَّذِينَ اخْتَلَفُوا فِيهِ ۚ وَإِنَّ رَبَّكَ لَيَحْكُمُ بَيْنَهُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ فِيمَا كَانُوا فِيهِ يَخْتَلِفُونَ

"ሠብት" سَّبْت የሚለው ቃል "ሡባት" سُبَات ማለትም "ዕረፍት" ከሚለው የስም መደብ የረባ ሲሆን "ሰንበት" ማለት ነው፦
78፥9 *እንቅልፋችሁንም "ዕረፍት" አደረግን*፡፡ وَجَعَلْنَا نَوْمَكُمْ سُبَاتًا

እዚህ አንቀጽ ላይ "ዕረፍት" ለሚለው ቃል የገባው "ሡባት" سُبَات መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። ይህንን ሰንበት ለማወቅ ሳምንታዊ ቀናትን እንዳስስ፦
1. "አሐድ" أحَد ማለት "አንድ" ማለት ነው፥ "እሑድ" የሚለው የግዕዙ ቃል በራሱ “አሐደ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "አንድ" ማለት ነው።
2. "ኢስነይን" اِثْنَيْن‎ ማለት "ሁለት" ማለት ነው፥ "ሰኞ" ማለት "ሰነየ" ማለትም "ደገመ" ከሚል የመጣ ሲሆን "ሁለተኛ" ማለት ነው።
3. "ሱላሳእ" ثُّلَاثَاء ማለት "ሦስት" ማለት ነው፥ "ማክሰኞ" ማለት "ማግስት" ማለት ነው፤ የእሁድ ማግስት "ሦስተኛ" ቀን ነው።
4. "አርቢዓእ" أَرْبِعَاء ማለት "አራት" ማለት ነው፥ "ረቡዕ" ማለት "ረበዓ" ከሚል የመጣ ሲሆን "አራተኛ" ማለት ነው።
5. "ኸሚሥ" خَمِيس ማለት "አምስት" ማለት ነው፥ "ሐሙስ" ማለት "አምሽት" "አምስት" ከሚል የመጣ ሲሆን "አምስተኛ" ማለት ነው።
6. "ጁሙዓህ" جُمُعَة ማለት "ስብስብ" ማለት ነው፥ "ዓርብ" የሚለው "ረበዐ" ማለትም "ሰበሰበ" ማለት ሲሆን "መሰብሰቢያ" ስድስተኛ ነው።
7. "ሠብት" سَّبْت ማለት "ዕረፍት" ማለት ነው፥ "ቅዳሜ" ማለት "ቀዳሚት" ማለት ሲሆን የጥንቷና የቀደመችው ሰንበት ናት። "ሰንበት" የሚለው የግዕዙ ቃል በራሱ "እረፍት" ማለት ነው።
ስለዚህ ይህቺ ሰንበት ሰባተኛዋ ቀን ናት፥ "ሠብዓህ" سَبْعَة ማለት እራሱ "ሰባት" ማለት ነው። በዚህ በሰባተኛው ቀን እረፍት የተደረገው በእስራኤል ልጆች ብቻ ነው፦
16፥124 *"ሰንበት የተደረገው በእነዚያ በእርሱ በተለያዩበት ሰዎች ላይ ብቻ ነው"*፡፡ ጌታህም በትንሣኤ ቀን ይለያዩበት በነበሩት ነገር በመካከላቸው በእርግጥ ይፈርዳል፡፡ إِنَّمَا جُعِلَ السَّبْتُ عَلَى الَّذِينَ اخْتَلَفُوا فِيهِ ۚ وَإِنَّ رَبَّكَ لَيَحْكُمُ بَيْنَهُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ فِيمَا كَانُوا فِيهِ يَخْتَلِفُونَ

በዚህ ቀን ሥራ መሥራት የተከለከለ ነው፥ አምላካችን አላህም፦ "በሰንበት ቀን ትዕዛዝን አትተላልፉ" ብሏቸው ነበር፦
4፥154 በቃል ኪዳናቸውም ምክንያት የጡርን ተራራ ከበላያቸው አነሳን፡፡ ለእነሱም «ደጃፉን አጎንባሾች ኾናችሁ ግቡ» አልን፡፡ *ለእነርሱም «በሰንበት ቀን ትዕዛዝን አትተላልፉ» አልን*፡፡ ከእነሱም ከባድን ቃል ኪዳን ያዝን፡፡ وَرَفَعْنَا فَوْقَهُمُ الطُّورَ بِمِيثَاقِهِمْ وَقُلْنَا لَهُمُ ادْخُلُوا الْبَابَ سُجَّدًا وَقُلْنَا لَهُمْ لَا تَعْدُوا فِي السَّبْتِ وَأَخَذْنَا مِنْهُم مِّيثَاقًا غَلِيظًا

"ቁልና" قُلْنَا የሚለው "ወሶይና" وَصَّيْنَا ለሚለው ቃል ተለዋዋጭ ሲሆን "አዘዝን" ማለት ነው። በሰንበት ቀን እንዲያርፉ እና ይህንን ትእዛዝ እንዳይተላለፉ አዟቸው ነበር። ቅሉ ግን በቀይ ባሕር ዳርቻ በምድያም እና በሲና መካከል ባለችው ከተማ በእረፍታቸው ቀን ለፈተና ዓሦቻቸው የተከማቹ ኾነው ይመጡላቸው ነበር፥ በአዘቦት ቀናት ግን አይመጡም ነበር፦
7፥163 *ከዚያችም በባሕሩ ዳርቻ ከነበረችው ከተማ በሰንበት ቀን ወሰን ባለፉ ጊዜ፥ በሰንበታቸው ቀን ዓሦቻቸው የተከማቹ ኾነው በሚመጡላቸው ጊዜ የኾነውን ጠይቃቸው፡፡ ሰንበትንም በማያከብሩበት ቀን አይመጡላቸውም፡፡ እንደዚሁ ያምጹበት በነበሩት ምክንያት እንፈትናቸዋለን*፡፡ وَاسْأَلْهُمْ عَنِ الْقَرْيَةِ الَّتِي كَانَتْ حَاضِرَةَ الْبَحْرِ إِذْ يَعْدُونَ فِي السَّبْتِ إِذْ تَأْتِيهِمْ حِيتَانُهُمْ يَوْمَ سَبْتِهِمْ شُرَّعًا وَيَوْمَ لَا يَسْبِتُونَ ۙ لَا تَأْتِيهِمْ ۚ كَذَٰلِكَ نَبْلُوهُم بِمَا كَانُوا يَفْسُقُونَ

"ሰንበታቸው" ለሚለው ቃል የገባው "ሰብቲሂም" سَبْتِهِمْ ሲሆን "እረፍታቸው" ማለት ነው። "ሰንበትንም በማያከብሩበት" ለሚለው ቃል የገባው የግስ መደብ "ላ ተሥቢቱነ" لَا يَسْبِتُونَ ሲሆን "በማያርፉበት" ማለት ነው። በእረፍት ቀን ዓሣ በማጥመድ በአላህ ትእዛዝ ላይ ሲያምጹ "ወራዶች ዝንጀሮዎች ኹኑ" አላቸው ሆኑም፦
7፥166 *ከእርሱም ከተከለከሉት ነገር በኮሩ ጊዜ ለእነርሱ «ወራዶች ዝንጀሮች ኹኑ አልን» ኾኑም*፡፡ فَلَمَّا عَتَوْا عَن مَّا نُهُوا عَنْهُ قُلْنَا لَهُمْ كُونُوا قِرَدَةً خَاسِئِينَ
2፥65 *እነዚያንም ከእናንተ ውስጥ *"በሰንበት ቀን ዓሣን በማጥመድ ወሰን ያለፉትን እና ለእነርሱ «ወራዶች ዝንጀሮዎች ኹኑ» ያልናቸውን በእርግጥ ዐወቃችሁ*፡፡ وَلَقَدْ عَلِمْتُمُ الَّذِينَ اعْتَدَوْا مِنكُمْ فِي السَّبْتِ فَقُلْنَا لَهُمْ كُونُوا قِرَدَةً خَاسِئِينَ

ይህ ክስተት የተከሰተው አላህ ወደ ሙሳ ተውራትን ባወረደበት ዘመን ነው፥ አላህ ወደ ሙሳ ተውራትን ሲያወርድ ነቢያችን”ﷺ” አልነበሩም። ይህንን የሙሳ ወሬ “ነቁሱ ዐለይከ” نَقُصُّ عَلَيْكَ ማለትም “እንተርክልሃለን” በማለት ለነቢያችን”ﷺ” የሚተርከው እራሱ ወደ ሙሳም ትዕዛዝን ያወረደው አምላክ ነው፦
28፥44 *ወደ ሙሳም ትዕዛዝን ባወረድንለት ጊዜ ከተራራው በምዕራባዊው ጎን አልነበርክም* ከተጣዱትም አልነበርክም፡፡ وَمَا كُنتَ بِجَانِبِ الْغَرْبِيِّ إِذْ قَضَيْنَا إِلَىٰ مُوسَى الْأَمْرَ وَمَا كُنتَ مِنَ الشَّاهِدِينَ
20፥9 *የሙሳም ወሬ በእርግጥ መጥቶልሃል*፡፡ وَهَلْ أَتَاكَ حَدِيثُ مُوسَىٰ

አምላካችን አላህ ከመልክተኞቹም ወሬዎች ለነብያችን”ﷺ” መተረኩ ለምእምናን ግሳጼ እና ማስታወሻ ነው፦
11:120 *ከመልክተኞቹም ወሬዎች* ተፈላጊውን ሁሉንም ልብህን በእርሱ የምናረካበትን “እንተርክልሃለን"፤ በዚህችም እውነቱ ነገር "ለምእምናን ግሳጼ እና ማስታወሻ" መጥቶልሃል*፡፡ وَكُلًّۭا نَّقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنۢبَآءِ ٱلرُّسُلِ مَا نُثَبِّتُ بِهِۦ فُؤَادَكَ ۚ وَجَآءَكَ فِى هَٰذِهِ ٱلْحَقُّ وَمَوْعِظَةٌۭ وَذِكْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ
ወደ ባይብል ስንመጣ እስራኤላውያን ስድስት ቀን ሠርተው በሰባተኛው ቀን ዕረፍት ነበሩ፣ ስድስት ወር ሠርተው በሰባተኛው ወር በ 1ኛው ቀን በ 10ኛው ቀን ዕረፍት ነበሩ፣ ስድስት ዓመት ሠርተው በሰባተኛው ዓመት ዕረፍት ነበሩ፦
ዘሌዋውያን 23፥3 *ስድስት ቀን ሥራ ይሠራል፤ በሰባተኛው ቀን ግን የዕረፍት ሰንበት ነው*።
ዘሌዋውያን 23፥24 ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ *በሰባተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ዕረፍት፥ በመለከት ድምፅ መታሰቢያ፥ የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ*።
ዘሌዋውያን 25፥4 *"ስድስት ዓመት እርሻህን ዝራ፥ ስድስት ዓመትም ወይንህን ቍረጥ ፍሬዋንም በሰባተኛው ዓመት ግን ለምድሪቱ የዕረፍት ሰንበት፥ ለእግዚአብሔር ሰንበት፥ ትሁን"*

ነዶ ካመጡበት ቀን በኋላ ከሰንበት ማግስት 7×7= 49 ኛው ቀን ሲያልፍ 50 ኛው ቀን እረፍት ያርፋሉ፥ ከኒሳን ወር 7×7= 49 ኛው ዓመት ሲያልፍ 50 ኛው ዓመት ኢዮቤልዩ እረፍት ያርፋሉ፦
ዘሌዋውያን 23፥15 *የወዘወዛችሁትን ነዶ ከምታመጡበት ቀን በኋላ ከሰንበት ማግስት ፍጹም ሰባት ጊዜ ሰባት ቀን ቍጠሩ፤ እስከ ሰባተኛ ሰንበት ማግስት ድረስ አምሳ ቀን ቍጠሩ"*።
ዘሌዋውያን 25፥8 *"ሰባት ጊዜ ሰባት አድርገህ የዓመታትን ሰንበት ሰባት ቍጠር፤ የሰባት ዓመታትም ሰንበት ዘመን አርባ ዘጠኝ ዓመት ትቈጥራለህ*።
ዘሌዋውያን 25፥10 *አምሳኛውንም ዓመት ትቀድሳላችሁ፥ በምድሪቱም ለሚኖሩባት ሁሉ ነጻነትን ታውጃላችሁ፤ እርሱ ለእናንተ ኢዮቤልዩ ነው"*።

እስራኤላውያን አንድ ሰንበት ብቻ አልነበራቸው፥ ከላይ እንደተጠቀሰው ብዙ ሰንበታት ነበሩ። እርሱም፦ "ሰንበታቴን" ይላል፦
ሕዝቅኤል 20፥12 በእኔ እና በእነርሱ መካከል ምልክት ይሆኑ ዘንድ *ሰንበታቴን* ሰጠኋቸው።

እነዚህ ቀንን፣ ወርን፣ ዓመትን እየተጠበቁ የሚታረፉ ሰንበታት ጳውሎስ ደካማ እና የተናቀ ስለሆነ ተሽሯል እያለን ነው፦
ገላትያ 4፥9 *ወደ ደካማ ወደሚናቅም ወደ መጀመሪያ ትምህርት እንዴት ትመለሳላችሁ? እንደ ገና ባሪያዎች ሆናችሁ ዳግመኛ ለዚያ ልትገዙ ትወዳላችሁን? ቀንንና ወርን ዘመንንም ዓመትንም በጥንቃቄ ትጠብቃላችሁ*።
ዕብራውያን 7፥18 *ሕጉ ምንም ፍጹም አላደረገምና፥ ስለዚህም የምትደክም የማትጠቅምም ስለሆነች የቀደመች ትእዛዝ ተሽራለች"*።
ኤፌሶን 2፥14 *በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ"*
ቆላስይስ 2፥16 *እንግዲህ በመብል ወይም በመጠጥ ወይም ስለ በዓል ወይም ስለ ወር መባቻ ወይም ስለ "ሰንበት" ማንም አይፍረድባችሁ። እነዚህ ሊመጡ ያሉት ነገሮች ጥላ ናቸውና፥ አካሉ ግን የክርስቶስ ነው*።

ዘሌዋውያን ላይ በአዋጅ የተነገሩትን የትእዛዛትን ሕግ ሰንበታት ናቸው፥ እነዚህ ሰንበታት አካሉን የሚያመላክቱ ጥላ"Typology" ስለሆኑ ተሽረዋል እያለን ነው። ስለዚህ ሰንበታት አዲስ ኪዳን ላይ የሉም።ለእኛ ለሙሥሊሞች የሚኖረው አንድምታ አላህ ለእስራኤላውያን ያዘዘው ሰንበት ለሁሉም ሕዝቦች አለመሆኑ ማሳያ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አዲስ ዓመት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

7፥3 *ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ*። اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ

የፈረንጆች አዲስ ዓመት ጃኑአርይ ነው። “ጃኑአርይ” ማለት “ጃኑስ” የተባለው ጣዖት የሚመለክበት ወር ነው። ይህ በዓል ጁለስ ቄሳር በ 46 ቅድመ-ልደት ስለጀመረው በዚህ ወር ዓመቱ ስለሚቀየር ጁሊያን የዘመን አቆጣጠር ይባላል። ቁጥሩ ደግሞ ኢየሱስ ከተወለደበት ጀምሮ የሚቆጠር የክርስትና በዓል ያደረገው በ 1582 ድኅረ-ልደት ግሪጎሪ ወይም ጎርጎርዮስ የተባለው ጳጳስ ነው፥ በዚህም የጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር ይባላል። ይህ ዓመታዊ በዓል ዓረማዊ እና ክርስትናን ቀላቅሎ የያዘ በዓል ነው፥ በዚህ ጊዜ "እንኳን አደረስን" ወይም "እንኳን አደረሳችሁ" ስንል ይህንን በዓል ታሳቢ እና ዋቢ ያደረገ ነው። ሙሥሊም ያሉት ዓመታዊ በዓል ሁለት ብቻ ናቸው፥ እነርሱም ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ናቸው፦
ሡነን አቢ ዳዉድ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 745
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” መዲና ሲገቡ የመዲና ሠዎች የሚደሰቱባቸው ሁለት በዓላት እንዳሏቸው አወቁ። እርሳቸውም እነዚህ ሁለቱ ቀናት ምንድን ናቸው? በማለት ጠየቁ፤ ሰዎችም በጃሂሊያ ጊዜ እንጫወትባቸው የነበሩ በዓላት ናቸው አሏቸው። የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ *”አላህ ከእነርሱ የተሻሉ ሁለት ዒዶችን ሠጥቷችኋል፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓን። አሏቸው”*። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ قَدِمَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْمَدِينَةَ وَلَهُمْ يَوْمَانِ يَلْعَبُونَ فِيهِمَا فَقَالَ ‏”‏ مَا هَذَانِ الْيَوْمَانِ ‏”‏ ‏.‏ قَالُوا كُنَّا نَلْعَبُ فِيهِمَا فِي الْجَاهِلِيَّةِ ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّ اللَّهَ قَدْ أَبْدَلَكُمْ بِهِمَا خَيْرًا مِنْهُمَا يَوْمَ الأَضْحَى وَيَوْمَ الْفِطْرِ ‏”‏ ‏.‏
ጃሚዒ አት-ቲርሚዚህ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፤ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው”*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ‏”‏
ጃሚዒ አት-ቲርሚዚህ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 91
አቡ ሰዒደል ኹድሪይ እንደተረከው፥ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” *”በሁለቱ በዓል በዒደል አደሐ እና ዒደል ፈጥር መጾም ከልክለዋል”*። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ، قَالَ نَهَى رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم عَنْ صِيَامَيْنِ يَوْمِ الأَضْحَى وَيَوْمِ الْفِطْرِ ‏.

“ዒድ” عِيد የሚለው ቃል “ዓደ” عَادَ ማለትም “ተመላለሰ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ምልሰት” ማለት ነው፥ ይህ “መደሰቻ” ወይም “በዓል” በየዓመቱ ስለሚመላለስ ይህንን ስያሜ አግኝቷል። ስለዚህ ከአላህ የወረዱትን ቁርኣን እና ሐዲስ ብቻ መከተል አለብን፦
7፥3 *ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ*። اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ

“ተከተሉ” የሚለው ቃል “ኢተቢዑ” اتَّبِعُوا ሲሆን “ኢትባዕ” إِتْبَاع‎ ማለት ከአላህ ወደ ነቢያችን”ﷺ” የተወረደውን ብቻ መከተል ማለት ነው። ሙሥሊም የተወረደውን ብቻ ሲከተል ሁለት ብቻ ዒድ ያከብራል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም