ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.3K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የማይቃጠለው ቁርኣን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

75፥17 *በልብህ ውስጥ መሰብሰቡ እና ማንበቡ በእኛ ላይ ነውና*፡፡ إِنَّ عَلَيْنَا جَمْعَهُ وَقُرْآنَهُ

ኖርዌህ የኢሥላም ጠል"Islamophobia" ያለባቸው ቡድን መሪ የቁርኣንን ሙስሐፍ ሲያቃጥል ነበር። ነገር ግን ቁርኣን የተጻፈበትን ቁስ ሰዎች ያቃጥሉ ይሆናል እንጂ የአላህን ንግግር በፍጹም ማቃጠል አይችሉም፥ ምክንያቱም ቁርኣን በአማንያን ልብ ውስጥ አላህ የሰበሰበው ታምር ነው። “ቁርኣን” قُرْءَان ማለት “በልብ ታፍዞ በምላስ የሚነበነብ መነባነብ” ማለት ማለት ነው፦
75:18 *ባነበብነውም ጊዜ ንባቡን ተከተል*። فَإِذَا قَرَأْنَاهُ فَاتَّبِعْ قُرْآنَه
75፥17 *በልብህ ውስጥ መሰብሰቡ እና ማንበቡ በእኛ ላይ ነውና*፡፡ إِنَّ عَلَيْنَا جَمْعَهُ وَقُرْآنَهُ
“ማንበቡ” ለሚለው ቃል የገባው “ቁርኣነሁ” َقُرْآنَهُ ሲሆን የግስ መደብ ነው፤ የስም መደቡ ደግሞ “ቁርኣን” قُرْءَان ነው። “ቃሪእ” قَارِئ‎ ማለት “በልብ አፍዞ በምላስ አነብናቢ”reciter” ማለት ነው፤ የቃሪእ ብዙ ቁጥር “ቁርራ” قُرَّاء ነው፤ አንድ ቃሪ የሆነ ሰው ቁርኣንን ሲቀራ አዳማጩ የሚያደምጠው የአላህን ንግግር ነው፦
7፥204 *ቁርኣንም በተነበበ ጊዜ እርሱን አዳምጡ፤ ጸጥም በሉ፤ ይታዘንላችኋልና*፡፡ وَإِذَا قُرِئَ الْقُرْآنُ فَاسْتَمِعُوا لَهُ وَأَنصِتُوا لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ
9፥6 ከአጋሪዎችም አንዱ ጥገኝነትን ቢጠይቅ *የአላህን ንግግር ይሰማ ዘንድ አስጠጋው*፡፡ وَإِنْ أَحَدٌ مِّنَ الْمُشْرِكِينَ اسْتَجَارَكَ فَأَجِرْهُ حَتَّىٰ يَسْمَعَ كَلَامَ اللَّهِ

“ዚክር” ذِكْر የሚለው ቃል “ዘከረ” ذَكَرَ ማለትም “አስታወሰ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማስታወስ”memorization” ማለት ነው፤ አምላካችን አላህ ቁርኣን በልብ እንዲታፈዝ አግርቶታል፦
54፥17 *ቁርኣንንም ለማስታወስ በእርግጥ አገራነው፡፡ አስታዋሽም አለን?* وَلَقَدْ يَسَّرْنَا ٱلْقُرْءَانَ لِلذِّكْرِ فَهَلْ مِن مُّدَّكِرٍۢ

አላህ፦ እኔ ቁርኣንን በቃላችሁ እንድትዙት ገር አርጌዋለው፤ ሙደኪር የት አለ? ብሎ ይጠይቃል፤ “ሙደኪር” مُّدَّكِرٍۢ ማለት “አስታዋሽ”Memorizer” ማለት ነው፤ አላህ ቁርአንን በቀልባችን እንድናፍዘው ብቻ ሳይሆን ስንቀራው በምላስ እንዲቀል እና በዐረቢኛው ቋንቋ እንድንገነዘበው አግርቶታል፦
12፥2 *እኛ ትገነዘቡ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን ሲሆን በእርግጥ አወረድነው*፡፡ إِنَّآ أَنزَلْنَٰهُ قُرْءَٰنًا عَرَبِيًّۭا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ
44፥58 *ቁርአኑን በምላስህ ያገራነው ይገነዘቡ ዘንድ ነው*። فَإِنَّمَا يَسَّرْنَاهُ بِلِسَانِكَ لَعَلَّهُمْ يَتَذَكَّرُونَ
And indeed, We have eased the Qur’an in your tongue that they might be reminded.

“ዩሥራ” يُسْرَىٰ ማለት “ገር” ወይም “ቀላል” ማለት ሲሆን በልብ ለማስታወስ፣ በምላስ ላይ ለመቅራት፣ በቋንቋው ለመረዳት አግርቶታል። “ሊሣን” لِسَان የሚለው ቃል “ምላስ” ወይም “ቋንቋ” ማለት ነው፤ አላህ ቁርአንን በልባችን እንደሚሰበስበው ቃል ገብቶልናል፦
75፥17 *በልብህ ውስጥ መሰብሰቡ እና ማንበቡ በእኛ ላይ ነውና*፡፡ إِنَّ عَلَيْنَا جَمْعَهُ وَقُرْآنَهُ
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 4, ሐዲስ 166
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *”በአላህ አዘ ወጀል ንግግር፦ “በቁርኣን ንባብ ልትቸኩል ምላስህን በእርሱ አታላውስ” ነብዩ”ﷺ” ጂብሪል ወደ እሳቸው ሲያወርድ ምላሳቸውና ከንፈራቸውን ለማንበብ በማንበብ ያላውሱ ስለነበር ነው፤ ይህ ችግር አልፎ አልፎ ይታይ ነበርና፤ አላህ ተዓላ፦ “በቁርኣን ንባብ ልትቸኩል ምላስህን በእርሱ አታላውስ” የሚለውን አወረደ፤ “በልብህ ውስጥ መሰብሰቡና ማንበቡ በእኛ ላይ ነውና” ብሎ ሰበሰበው፤ በእርግጥም በልብህ ውስጥ እንድትቀራው እንጠብቀዋለን አንተም ትቀራዋለህ” ማለት ነው፤ “ባነበብነውም ጊዜ ካለቀ በኋላ ንባቡን ተከተል፣ ከዚያም ማብራራቱ በእኛ ላይ ነው” ማለት “በምላስህ ላይ ማስቀመጡ በእኛ ላይ ነው” ማለት ነው፤ ጂብሪል ወደ እርሳቸው በሚመጣ ጊዜ ዝም ይላሉ፤ ከእርሳቸው በተለየ ጊዜ አላህ ቃል እንደገባላቸው ይቀራሉ*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، فِي قَوْلِهِ عَزَّ وَجَلَّ ‏{‏ لاَ تُحَرِّكْ بِهِ لِسَانَكَ‏}‏ قَالَ كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم إِذَا نَزَلَ عَلَيْهِ جِبْرِيلُ بِالْوَحْىِ كَانَ مِمَّا يُحَرِّكُ بِهِ لِسَانَهُ وَشَفَتَيْهِ فَيَشْتَدُّ عَلَيْهِ فَكَانَ ذَلِكَ يُعْرَفُ مِنْهُ فَأَنْزَلَ اللَّهُ تَعَالَى ‏{‏ لاَ تُحَرِّكْ بِهِ لِسَانَكَ لِتَعْجَلَ بِهِ‏}‏ أَخْذَهُ ‏{‏ إِنَّ عَلَيْنَا جَمْعَهُ وَقُرْآنَهُ‏}‏ إِنَّ عَلَيْنَا أَنْ نَجْمَعَهُ فِي صَدْرِكَ ‏.‏ وَقُرْآنَهُ فَتَقْرَأُهُ ‏{‏ فَإِذَا قَرَأْنَاهُ فَاتَّبِعْ قُرْآنَهُ‏}‏ قَالَ أَنْزَلْنَاهُ فَاسْتَمِعْ لَهُ ‏{‏ إِنَّ عَلَيْنَا بَيَانَهُ‏}‏ أَنْ نُبَيِّنَهُ بِلِسَانِكَ فَكَانَ إِذَا أَتَاهُ جِبْرِيلُ أَطْرَقَ فَإِذَا ذَهَبَ قَرَأَهُ كَمَا وَعَدَهُ اللَّهُ ‏

“ጀመዐ” جَمَعَ ማለት “ሰበሰበ” ማለት ሲሆን “ጀመዕ” جَمَع ማለት ደግሞ “ስብስብስ”Collection” ማለት ነው። ይህ በቃል ደረጃ”oral form” የተሰበሰበው ቁርኣን በሙተዋቲር ከነብያችን”ﷺ” ወደ ሶሐባዎች፣ ከሶሐባዎች ወደ ታቢኢይዎች፣ ከታቢኢይዎች ወደ አትባኡ ታቢኢይዎች እያለ በሙተዋቲር አስራ አራት ትውልድ አሳልፎ መጥቷል፥ “ሙተዋቲር” مُتَواتِر ማለት ቁርኣን ከአንድ ኢስናድ በላይ በጀመዓ የሚደረግ ዘገባ ነው። አላህ ቁርኣንን እራሱ አውርዶ ከኋላውም ከፊቱም ውሸት እንዳይመጣበት እራሱ በአማኞች ልብ እንዲሰበሰብ ገር በማድረግ እና በምላስ እንዲቀራ ገር በማድረግ ይጠብቀዋል፦
15፥9 *እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን*፡፡ إِنَّا نَحْنُ نَزَّلْنَا ٱلذِّكْرَ وَإِنَّا لَهُۥ لَحَٰفِظُونَ
41፥42 *ከኋላውም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም*፡፡ ጥበበኛ ምስጉን ከኾነው ጌታ የተወረደ ነው፡፡ لَّا يَأْتِيهِ ٱلْبَٰطِلُ مِنۢ بَيْنِ يَدَيْهِ وَلَا مِنْ خَلْفِهِۦ ۖ تَنزِيلٌۭ مِّنْ حَكِيمٍ حَمِيدٍۢ

በጽሑፍ ደረጃ የተሰበሰቡት ጥራዞች ሁሉ ጠፉ ቢባል እንኳን ቁርኣን በቃሪእዎች ልብ ውስጥ አለ፦
ኢማም ቡኻርይ : መጽሐፍ 65, ሐዲስ 4937
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ *”ነብዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ያ ልክ ቁርኣንን በልቡ ሓፍዞ የሚቀራ በሰማይ ከተከበሩ ጸሐፊዎች(መላእክት) ጋር ይሆናል፤ ያ ልክ ቁርኣንን በልቡ እያወቀው በጣም እየከበደው የሚቀራ እጥፍ ምንዳ አለው*። عَنْ عَائِشَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ مَثَلُ الَّذِي يَقْرَأُ الْقُرْآنَ وَهْوَ حَافِظٌ لَهُ مَعَ السَّفَرَةِ الْكِرَامِ الْبَرَرَةِ، وَمَثَلُ الَّذِي يَقْرَأُ الْقُرْآنَ وَهْوَ يَتَعَاهَدُهُ وَهْوَ عَلَيْهِ شَدِيدٌ، فَلَهُ أَجْرَانِ ‏”‌‏.‏
ነብያችን”ﷺ” በሕይወታቸው ዘመን ማብቂያ ላይ ስለ ሙሉ ቁርኣን በልብ ውስጥ እንዴት እንደሚቀራ እንዲህ ተናግረዋል፦
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 66, ሐዲስ 78
ዐብደላህ ኢብኑ ዐምር እንደተረከው፦ *”ነብዩም”ﷺ” እኔን፦ “ሙሉ ቁርኣንን ቀርቶ ለመጨረስ ስንት ጊዜ ይወስድብሃል? ብለው ጠየቁኝ*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، قَالَ لِي النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ فِي كَمْ تَقْرَأُ الْقُرْآنَ ‏”‌‏.‏
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 66, ሐዲስ 79
ዐብደላህ ኢብኑ ዐምር እንደተረከው፦ *”የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ “ሙሉ ቁርኣንን በአንድ ወር ጊዜ ቅራ”። እኔም፦ “ከዛ በታች ለመቅራት ችሎታው አለኝ” አልኩኝ፤ እርሳቸው፦ “በሰባት ቀናት ቅራው፤ ከዚያ በታች ሙሉውን ለመቅራት አይቻልም*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ اقْرَإِ الْقُرْآنَ فِي شَهْرٍ ‏”‌‏.‏ قُلْتُ إِنِّي أَجِدُ قُوَّةً حَتَّى قَالَ ‏”‏ فَاقْرَأْهُ فِي سَبْعٍ وَلاَ تَزِدْ عَلَى ذَلِكَ ‏”‌‏.‏

በሰባት ቀናት ከፋፍሎ መቅራት “መንዚል” منزل ይባላል፤ ሌላው ቁርኣን ሠላሳ ጁዝዕ” አለው፤ “ጁዝዕ” جُزْءْ‎ ማለት “ክፍል”part” ማለት ሲሆን በሠላሳ ቀናት ከፋፍሎ መቀራትን ያሳያል፤ በተለይ በተራዊህ ሶላት ላይ ሙሉ ሠላሳ ጁዝዕ ይቀራል፤ “ተራዊህ” تراويح‌‎ ማለትም “በረመዳን የሌሊት ሶላት” ማለት ነው። ስለዚህ ቁርኣን ከትውልድ ወደ ትውልድ በቃሪእዎች ልብ ውስጥ በሙተዋቲር የሚተላለፍ ታምር ነው። በምድር ላይ ያሉትን የቁርኣን ሙስሐፍ ሰብስባችሁ ብታቃጥሉት ቁርኣን በቃሪእዎች ልብ ውስጥ ስለታፈዘ ሊጠፋ አይችልም። ቁርኣንን ለማጥፋት ሙስሊሞችን ቅድሚያ ማጥፋት ያስፈልጋል፤ ሙሥሊሞች ከሌሉ ደግሞ ትንሳኤ ይቆማል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ተፍሲል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

10፥37 ይህም ቁርኣን ከአላህ ሌላ ከሆነ ፍጡር የተቀጠፈ ሊሆን አይገባውም፡፡ ግን ያንን *”ከእርሱ በፊት ያለውን”* የሚያረጋግጥ እና *”በመጽሐፉ ውስጥ ያለውን የሚዘረዝር”* በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲሆን ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው፡፡ وَمَا كَانَ هَٰذَا ٱلْقُرْءَانُ أَن يُفْتَرَىٰ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَلَٰكِن تَصْدِيقَ ٱلَّذِى بَيْنَ يَدَيْهِ وَتَفْصِيلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا رَيْبَ فِيهِ مِن رَّبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ

አላህ ከነብያችንም”ﷺ” በፊት መልክተኞቹን በግልጽ ማስረጃዎች ልኳል፤ ሰዎችም በትክክል ቀጥ እንዲሉ መጽሐፎችን ወደ እነርሱ አውርዷል፤ ነብያችንም”ﷺ” ወደ መልክተኞቹ የተወረደውን ለሰዎች ሊገልጹ ቁርአን ወርዶላቸዋል፦
57፥25 መልክተኞቻችንን በግልጽ ማስረጃዎች በእርግጥ ላክን፡፡ ሰዎችም በትክክል ቀጥ እንዲሉ *”መጽሐፎችንና ሚዛንን ወደ እነርሱ አወረድን”*፤ لَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلَنَا بِٱلْبَيِّنَٰتِ وَأَنزَلْنَا مَعَهُمُ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْمِيزَانَ لِيَقُومَ ٱلنَّاسُ بِٱلْقِسْطِ
16፥44 በግልጽ ማስረጃዎች እና በመጻሕፍት ላክናቸው፡፡ ወደ አንተም ለሰዎች *”ወደ እነርሱ የተወረደውን ልትገልጽላቸው”* እና ያስተነትኑም ዘንድ ቁርኣንን አወረድን፡፡ بِٱلْبَيِّنَٰتِ وَٱلزُّبُرِ ۗ وَأَنزَلْنَآ إِلَيْكَ ٱلذِّكْرَ لِتُبَيِّنَ لِلنَّاسِ مَا نُزِّلَ إِلَيْهِمْ وَلَعَلَّهُمْ يَتَفَكَّرُون

ቁርአን ከእርሱ በፊት ወደ ነብያት የተወረደውን መጽሐፍ የሚያረጋግጥ እና በውስጡ ያለውን የሚዘረዝር ሲሆን ከዓለማቱ ጌታ የተወረደ ነው፦
4፥136 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህ እና በመልክተኛው በዚያም *በመልክተኛው ላይ ባወረደው መጽሐፍ በዚያም ከበፊቱ ባወረደው መጽሐፍ እመኑ*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا آمِنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ وَالْكِتَابِ الَّذِي نَزَّلَ عَلَىٰ رَسُولِهِ وَالْكِتَابِ الَّذِي أَنزَلَ مِن قَبْلُ ۚ
10፥37 ይህም ቁርኣን ከአላህ ሌላ ከሆነ ፍጡር የተቀጠፈ ሊሆን አይገባውም፡፡ ግን ያንን *”ከእርሱ በፊት ያለውን የሚያረጋግጥ እና በመጽሐፉ ውስጥ ያለውን የሚዘረዝር”* በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲሆን ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው፡፡ وَمَا كَانَ هَٰذَا ٱلْقُرْءَانُ أَن يُفْتَرَىٰ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَلَٰكِن تَصْدِيقَ ٱلَّذِى بَيْنَ يَدَيْهِ وَتَفْصِيلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا رَيْبَ فِيهِ مِن رَّبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ

"ተፍሲል" تَفْصِيل ማለት "ፈስሰለ" فَصَّلَ ማለትም "አብራራ" "ተነተነ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ማብራሪያ" ወይም "መተንተኛ"explanation" ማለት ነው፤ አምላካችን አላህ በበፊቱ በወረደው መጽሐፍ ላይ ምን ብሎ ተናግሮ እንደነበረ ለመናገር፦ "ከተብና" َكَتَبْنَا ማለትም "አልን" በማለት ይናገራል፤ ለናሙና ያክል በተውራት ምን ተናግሮ እንደነበር ያብራራዋል፦
5፥32 በዚህ ምክንያት በእስራኤል ልጆች ላይ፦ “እነሆ ያለ ነፍስ መግደል ወይም በምድር ላይ ያለማጥፋት ካልሆነ በስተቀር ነፍስን የገደለ ሰው ሰዎቹን ሁሉ እንደገደለ ነው፤ ሕያው ያደረጋትም ሰው ሰዎቹን ሁሉ ሕያው እንዳደረገ ነው” ማለትን *ጻፍን*፡፡ مِنْ أَجْلِ ذَٰلِكَ كَتَبْنَا عَلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ أَنَّهُ مَن قَتَلَ نَفْسًا بِغَيْرِ نَفْسٍ أَوْ فَسَادٍ فِي الْأَرْضِ فَكَأَنَّمَا قَتَلَ النَّاسَ جَمِيعًا وَمَنْ أَحْيَاهَا فَكَأَنَّمَا أَحْيَا النَّاسَ جَمِيعًا
5፥45 በእነርሱም ላይ በውስጧ፦ “ነፍስ በነፍስ ዓይንም በዓይን አፍንጫም በአፍንጫ ጆሮም በጆሮ ጥርስም በጥርስ ይያዛል፤ ቁስሎችንም ማመሳሰል አለባቸው” ማለትን *ጻፍን*፡፡ وَكَتَبْنَا عَلَيْهِمْ فِيهَا أَنَّ النَّفْسَ بِالنَّفْسِ وَالْعَيْنَ بِالْعَيْنِ وَالْأَنفَ بِالْأَنفِ وَالْأُذُنَ بِالْأُذُنِ وَالسِّنَّ بِالسِّنِّ وَالْجُرُوحَ قِصَاصٌ

“ከተበ” كَتَبَ ደግሞ “ቃለ” قَالَ ማለትም “አለ” ወይም “ከለመ” كَلَّمَ ማለትም “ተናገረ” በሚል ይመጣል፤ "ከተብና" َكَتَبْنَا የሚለው ቃል "ቁልና" قُلْنَا ወይም "አውሐይና" َأَوْحَيْنَا በሚል ተለዋዋጭ ቃል መጥቷል፦
2፥60 ሙሳም ለሕዝቦቹ መጠጥን በፈለገ ጊዜ የኾነውን አስታውሱ፡፡ «ድንጋዩንም በበትርህ ምታ» *አልነው*፡፡ وَإِذِ اسْتَسْقَىٰ مُوسَىٰ لِقَوْمِهِ فَقُلْنَا اضْرِب بِّعَصَاكَ الْحَجَر
26፥63 ወደ ሙሳም «ባሕሩን በበትርህ ምታው» *ስንል ላክንበት*፡፡ መታውና ተከፈለም፡፡ ክፍሉም ሁሉ እንደ ታላቅ ጋራ ኾነ፡፡ فَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ مُوسَىٰ أَنِ اضْرِب بِّعَصَاكَ الْبَحْرَ ۖ فَانفَلَقَ فَكَانَ كُلُّ فِرْقٍ كَالطَّوْدِ الْعَظِيمِ

ከላይ የዘረዘርናቸው አንቀጾች በአይሁዳውያን ቀኖና ውስጥ መልእክቱ በቅሪት ደረጃ ተቀምጠዋል፦
ዘጸአት 14፥16 *አንተም በትርህን አንሣ፥ እጅህንም በባሕሩ ላይ ዘርጋ*፥ ክፈለውም፤ የእስራኤልም ልጆች በባሕሩ ውስጥ በየብስ ያልፋሉ።
ዘጸአት 20፥7-8 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ *በትርህን ውሰድ፤ አንተና ወንድምህ አሮን ማኅበሩን ሰብስቡ፥ ድንጋዩም ውኃን እንዲሰጥ እነርሱ ሲያዩ ተናገሩት፤ ከድንጋዩም ውኃ ታወጣላቸዋለህ*፤ እንዲሁም ማኅበሩን ከብቶቻቸውንም ታጠጣላቸዋለህ።
ዘጸአት 21፥24-25 *ዓይን በዓይን፥ ጥርስ በጥርስ፥ እጅ በእጅ፥ እግር በእግር፥ መቃጠል በመቃጠል፥ ቍስል በቍስል፥ ግርፋት በግርፋት ይከፈል*።
ሚሽናህ ሳንድሬህ 4፥4 *በምድር ላይ ያለማጥፋት ነፍስን የገደለ ሰው፣ ሰዎቹን ሁሉ እንደገደለ ነው፤ ሕያው ያደረጋትም ሰው፣ ሰዎቹን ሁሉ ሕያው እንዳደረገ ነው*።
በተለይ ሚሽናህ ሳንድሬህ በኢየሩሳሌም ታልሙድ ላይ የተገኘው ከቁኣን መውረድ በኃላ ቢሆንም አላህ ግን ነብያችን”ﷺ” የመጽሐፉ ባለቤቶች ከመጽሐፉ ይሸሽጉት ከነበሩት ነገር ብዙውን ለእነርሱ የሚገልጹ ሆነው ከእርሱ ተልከዋል፦
5፥15 የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! *”ከመጽሐፉ ትሸሽጉት ከነበራችሁት ነገር ብዙውን ለእናንተ የሚገልጽ ከብዙውም የሚተው ሲኾን መልክተኛችን በእርግጥ መጣላችሁ*፡፡ ከአላህ ዘንድ ብርሃንና ገላጭ መጽሐፍ በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ قَدْ جَآءَكُمْ رَسُولُنَا يُبَيِّنُ لَكُمْ كَثِيرًۭا مِّمَّا كُنتُمْ تُخْفُونَ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَيَعْفُوا۟ عَن كَثِيرٍۢ ۚ قَدْ جَآءَكُم مِّنَ ٱللَّهِ نُورٌۭ وَكِتَٰبٌۭ مُّبِينٌۭ

“ከብዙውም የሚተው ሲኾን” ማለት የመጽሐፉ ባለቤቶች ከደበቋቸው ሁሉንም አልተናገሩም ማለት ነው፤ በቀኖና ያላካተቷቸው ግን የሸሸጓቸውን አላህ ተናግሮት እንደነበረ ለማሳየት "አልን" እያለ ይዘረዝርልናል፦
7፥166 ከእርሱም ከተከለከሉት ነገር በኮሩ ጊዜ ለእነሱ «ወራዶች ዝንጀሮች ኹኑ» *አልን* ኾኑም፡፡ فَلَمَّا عَتَوْا عَن مَّا نُهُوا عَنْهُ قُلْنَا لَهُمْ كُونُوا قِرَدَةً خَاسِئِينَ
17፥2 ሙሳንም መጽሐፉን ሰጠነው፡፡ ለእስራኤልም ልጆች መሪ አደረግነው፡፡ "ከእኔ ሌላ መጠጊያን አትያዙ"፤ *አልናቸውም*፡፡ وَآتَيْنَا مُوسَى الْكِتَابَ وَجَعَلْنَاهُ هُدًى لِّبَنِي إِسْرَائِيلَ أَلَّا تَتَّخِذُوا مِن دُونِي وَكِيلًا

እስቲ በፔንታተች አሊያም በታልሙድ ላይ ፈጣሪ፦ "ወራዶች ዝንጀሮች ኹኑ" ወይም "ከእኔ ሌላ መጠጊያን አትያዙ" ያለበትን ንግግር ወይም ሃሳብ ፈልጉ! ፈጽማችሁ አታገኙም። አላህ ወደ ሙሳ ተውራትን ሲያወርድ ነብያችን"ﷺ" አልነበሩም፤ ይህንን የሙሳ ወሬ “ነቁስሱ አለይከ” نَقُصُّ عَلَيْكَ ማለትም “እንተርክልሃለን” በማለት ለነብያችን”ﷺ” የሚተርከው እራሱ ወደ ሙሳም ትዕዛዝን ያወረደው አምላክ ነው፦
28፥44 *ወደ ሙሳም ትዕዛዝን ባወረድንለት ጊዜ ከተራራው በምዕራባዊው ጎን አልነበርክም* ከተጣዱትም አልነበርክም፡፡ وَمَا كُنتَ بِجَانِبِ الْغَرْبِيِّ إِذْ قَضَيْنَا إِلَىٰ مُوسَى الْأَمْرَ وَمَا كُنتَ مِنَ الشَّاهِدِينَ
20፥9 *የሙሳም ወሬ በእርግጥ መጥቶሃል*፡፡ وَهَلْ أَتَاكَ حَدِيثُ مُوسَىٰ
20፥99 እንደዚሁ በእርግጥ *ካለፉት ወሬዎች በአንተ ላይ እንተርካለን*፡፡ ከእኛም ዘንድ ቁረኣንን በእርግጥ ሰጠንህ፡፡ كَذَٰلِكَ نَقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنبَاءِ مَا قَدْ سَبَقَ ۚ وَقَدْ آتَيْنَاكَ مِن لَّدُنَّا ذِكْرًا

“ወሬ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ነበእ” نَبَإِ ሲሆን “ነቢይ” نبي የሚለው ቃል የመጣበት ሥርወ-ቃል ነው፤ ይህን የመልእክተኞች ወሬ አላህ ምን ተናግሮ እንደነበር ለነብያችን”ﷺ” መተረኩ ለምእምናን ግሳጼ እና ማስታወሻ ነው፦
11:120 *ከመልክተኞቹም ወሬዎች* ተፈላጊውን ሁሉንም ልብህን በእርሱ የምናረካበትን “*እንተርክልሃለን*፤ በዚህችም እውነቱ ነገር *ለምእምናን ግሳጼ እና ማስታወሻ* መጥቶልሃል፡፡ وَكُلًّۭا نَّقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنۢبَآءِ ٱلرُّسُلِ مَا نُثَبِّتُ بِهِۦ فُؤَادَكَ ۚ وَجَآءَكَ فِى هَٰذِهِ ٱلْحَقُّ وَمَوْعِظَةٌۭ وَذِكْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አር-ሩቂያህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

26፥80 *"በታመምኩም ጊዜ እርሱ ያሽረኛል"*፡፡ وَإِذَا مَرِضْتُ فَهُوَ يَشْفِينِ

ብዙ ጊዜ ሐኪም ቤት ሄደን መፍትሔ ስናጣ ወደ አላህ ከመጠየቅ ይልቅ ወደ ኩፍር መንደር ጎራ እንላለን፥ ይህ በራሱ ሺርክ ነው። የኩፍር መንደር ከጥንስሱ እስከ ድፍርሱ በሸያጢን አሠራር የሚካሄድ ነው። ሳሩን እንጂ ገደሉን ሳያዩ ብዙዎች መጨረሻቸው አላማረም፥ "የጨነቀው እርጉዝ ያገባል፥ ስትወልድ ገደል ይገባል" ይላሉ አበው። በኢሥላም ያለው ፈውስ በቁርኣን "ሺፋእ" ይባላል። "ሺፋእ" شِفَآء የሚለው ቃል "ሸፈ" شَفَى‎ ማለትም "ፈወሰ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ፈውስ" ማለት ነው። በሽታን የሚፈውስ አምላካችን አላህ ነው፦
26፥80 *"በታመምኩም ጊዜ እርሱ ያሽረኛል"*፡፡ وَإِذَا مَرِضْتُ فَهُوَ يَشْفِينِ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ያሽረኛል" ለሚለው ቃል የገባው "የሽፊኒ" يَشْفِينِ ሲሆን ሥርወ-ቃሉ "ሸፈ" شَفَى‎ መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል። እዚህ አንቀጽ ላይ ኢብራሂም "ይፈውሰኛል" የሚለው የዓለማቱን ጌታ አላህን ነው። አምላካችን አላህ ፈዋሽ ነው፥ ቁርኣንን መፈወሻ ፈውስ አርጎ አውርዶታል፦
10፥57 *እናንተ ሰዎች ሆይ! ከጌታችሁ ግሳጼ በደረቶች ውስጥም ላለው በሽታ "መድኃኒት" ለምእምናንም ብርሃንና እዝነት በእርግጥ መጣላችሁ*፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ قَدْ جَاءَتْكُم مَّوْعِظَةٌ مِّن رَّبِّكُمْ وَشِفَاءٌ لِّمَا فِي الصُّدُورِ وَهُدًى وَرَحْمَةٌ لِّلْمُؤْمِنِينَ
41፥44 በአጀምኛ የኾነ ቁርኣን ባደረግነው ኖሮ አንቀጾቹ በምናውቀው ቋንቋ አይብራሩም ኖሯልን? ቁርኣኑ አጀምኛ እና መልክተኛው ዐረባዊ ይኾናልን?» ባሉ ነበር። *በል እርሱ ለእነዚያ ለአመኑት መምሪያ እና "መፈወሻ" ነው*፡፡ وَلَوْ جَعَلْنَاهُ قُرْآنًا أَعْجَمِيًّا لَّقَالُوا لَوْلَا فُصِّلَتْ آيَاتُهُ ۖ أَأَعْجَمِيٌّ وَعَرَبِيٌّ ۗ قُلْ هُوَ لِلَّذِينَ آمَنُوا هُدًى وَشِفَاءٌ

ይህ ፈውስ በነቢያችን"ﷺ" ሐዲስ "አር-ሩቂያህ" الرُّقِيْة ይባላል። በልብ ላለው በሽታ ማለት ለዐይኑ አን-ናሥ፣ ለሲሕር እና ለሸያጢን መጸናወት መድኃኒቱ ሩቂያህ ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 31, ሐዲስ 3641
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"ነቢዩም"ﷺ" ከመጥፎ ዓይን ሩቂያህ እንድትቀራ አዘዟት"*። عَنْ عَائِشَةَ، أَنَّ النَّبِيَّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ أَمَرَهَا أَنْ تَسْتَرْقِيَ مِنَ الْعَيْنِ ‏
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 31, ሐዲስ 3618
ዐቃድ ኢብኑል ሙጊራህ ከአባቱ ሰምቶ እንደተተከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ማንም የታመመ በህክምና ወይም በሩቂያ ያደረገ፥ ራሱን በአላህ ይመካል"*። عَنْ عَقَّارِ بْنِ الْمُغِيرَةِ، عَنْ أَبِيهِ، عَنِ النَّبِيِّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ قَالَ ‏ "‏ مَنِ اكْتَوَى أَوِ اسْتَرْقَى فَقَدْ بَرِئَ مِنَ التَّوَكُّلِ

በአላህ ላይ መመካት “ተወኩል” تَوَكُّل‎ ይባላል። ሰይጧን በእነዚያ ባመኑት እና በአላህ ላይ በሚመኩት ላይ ስልጣን የለውም፦
16፥99 *”እርሱ በእነዚያ ባመኑት እና በጌታቸው ላይ በሚጠጉት ላይ ለእርሱ ስልጣን የለውምና”*፡፡ إِنَّهُ لَيْسَ لَهُ سُلْطَانٌ عَلَى الَّذِينَ آمَنُوا وَعَلَىٰ رَبِّهِمْ يَتَوَكَّلُونَ

“በሚጠጉት” ለሚለው ቃል የገባው “የተወከሉን” يَتَوَكَّلُون ሲሆን ቁርጥ ሐሳብም ባደረጉ ጊዜ አላህ በቂዬ ነው ብለው በአላህ ላይ ሙሉ ለሙሉ የተወከሉ ባሮቹ ደግሞ “ሙተወከሉን” مُتَوَكِّلُون ይባላል። “ኢሥቲዓዛህ” إِسْتِعَاذَة የሚለው ቃል “ኢሥተዓዘ” اِسْتَعَاذَ ማለትም “ተጠበቀ” ለሚለው ቃል መስደር ሲሆን “መጠበቅ” ማለት ነው። ይህም ኢሥቲዓዛህ “አዑዙ ቢሏሂ ሚነሽ ሸይጧኒር ረጂም” أَعُوذُ بِاللَّهِ مِنَ الشَّيْطَانِ الرَّجِيمِ ነው። “አዑዙ ቢሏሂ ሚነሽ ሸይጧኒር ረጂም” ማለት “እርጉም ከኾነው ሰይጣን በአላህ እጠበቃለው” ማለት ነው፦
16፥98 *”ቁርኣንንም ባነበብህ ጊዜ እርጉም ከኾነው ሰይጣን በአላህ ተጠበቅ”*፡፡ فَإِذَا قَرَأْتَ الْقُرْآنَ فَاسْتَعِذْ بِاللَّهِ مِنَ الشَّيْطَانِ الرَّجِيمِ

“አል-ሙዐወዘተይን” الْمُعَوِّذَتَيْن የሚባሉት ሁለቱ ሱራዎች ሱረቱል ፈለቅ እና ሱረቱ አን-ናሥ ለፈውስ የወረዱ ሱራህ ናቸው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 6 , ሐዲስ 319:
የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ *ዛሬ ምን አስደናቂ አንቀጾች ዛሬ ወርደዋል፤ ይህም ብጤአቸው ታይቶ አያውቅም! እነርሱም፦ “በል «በተፈልቃቂው ጎህ ጌታ እጠበቃለሁ” እና በል «በሰዎች ፈጣሪ እጠበቃለሁ» ናቸው*። قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ أَلَمْ تَرَ آيَاتٍ أُنْزِلَتِ اللَّيْلَةَ لَمْ يُرَ مِثْلُهُنَّ قَطُّ ‏{‏ قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ الْفَلَقِ‏}‏ وَ ‏{‏ قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ النَّاسِ‏}‏ ‏”‏
ታላቁ ሙፈሢር ኢብኑ ከሲር እነዚህ ሱራዎች በሐዲሱ መሠረት ፈሥሯቸዋል፦
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 113፥1 *“አል-ሙዐወዘተይን” ሲናገር፦ “በሌላ ሐዲስ እንደተዘገበው፦ “ጂብሪል ወደ ነብዩ”ﷺ” መጥቶ እንዲህ አላቸው፦ “ሙሐመድ”ﷺ” ሆይ በማንኛውም ህመም እየተሰቃየህ ነውን? ነቢዩም”ﷺ” "ነዐም" ብለው መለሱ። ጂብሪልም በአላህ ስም ሩቂያ እቀራብሃለው፤ ከማንኛውም በሽታ አንተን የጎዳህን፤ ከእያንዳንዱ ሸረኛ እና ክፉ ዓይን፤ አላህ ይፈውስሃል”*።
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 10 , ሐዲስ 8:
“ጂብሪል ወደ ነቢዩ”ﷺ” መጥቶ እንዲህ አላቸው፦ *“ሙሐመድ”ﷺ” ሆይ በማንኛውም ህመም እየተሰቃየህ ነውን? ነብዩም”ﷺ” "ነዐም" ብለው መለሱ። ጂብሪልም በአላህ ስም ሩቂያ እቀራብሃለው፤ ከማንኛውም በሽታ አንተን የጎዳህን፤ ከእያንዳንዱ ሸረኛ እና ክፉ ዓይን፤ አላህ ይፈውስሃል”*። أَنَّ جِبْرِيلَ، أَتَى النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم فَقَالَ يَا مُحَمَّدُ اشْتَكَيْتَ قَالَ ‏ “‏ نَعَمْ ‏”‏ ‏.‏ قَالَ بِاسْمِ اللَّهِ أَرْقِيكَ مِنْ كُلِّ شَيْءٍ يُؤْذِيكَ مِنْ شَرِّ كُلِّ نَفْسٍ وَعَيْنِ حَاسِدٍ بِاسْمِ اللَّهِ أَرْقِيكَ وَاللَّهُ يَشْفِيكَ ‏.‏
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 31, ሐዲስ 3652
አቢ ሠዒድ እንደተረከው፦ "ጂብሪል ወደ ነቢዩ"ﷺ" መጥቶ እንዲ አለ፦ *"ሙሐመድ ሆይ! ታመሃል፥ እርሳቸውም "ነዐም" አሉ። ጂብሪልም፦ "መጥፎ ከሆነ ነገር ሁሉ በአላህ ስም ሩቂያ አረግልሃለው፥ ከሁሉ መጥፎ ነፍስ ወይም መጥፎ ዓይን አሊያም ከምቀኝነት። አላህ ይፈውስህ! በአላህ ስም ሩቂያ አረግልሃለው"*። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ، أَنَّ جِبْرَائِيلَ، أَتَى النَّبِيَّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ فَقَالَ يَا مُحَمَّدُ اشْتَكَيْتَ قَالَ ‏ "‏ نَعَمْ ‏"‏ ‏.‏ قَالَ بِسْمِ اللَّهِ أَرْقِيكَ مِنْ كُلِّ شَىْءٍ يُؤْذِيكَ مِنْ شَرِّ كُلِّ نَفْسٍ أَوْ عَيْنٍ أَوْ حَاسِدٍ اللَّهُ يَشْفِيكَ بِسْمِ اللَّهِ أَرْقِيكَ

"አያቱ አር-ሩቂያህ"‎ آيَات الرُّقِيْة ማለት "የሩቂያህ
አናቅጽ" ማለት ነው፥ እነዚህም ዐበይት የሩቂያህ
አናቅጽ የሚቀሩት ሱቱል ፋቲሓህ 1 ጊዜ፣ ሱረቱል በቀራህ 2፥255 7 ጊዜ ወይም 11 ወይም 21 አሊያም 41 ጊዜ፣ ሱረቱል ኢኽላስ 3 ጊዜ፣ ሱረቱል ፈለቅ 3 ጊዜ፣ ሱረቱ አን-ናሥ 3 ጊዜ ናቸዉ። ከቁርኣንም ለምእመናን መድኀኒት የወረዱት ዐበይት አናቅጽ እነዚህ ናቸው፦
17፥82 *ከቁርኣንም ለምእመናን "መድኀኒት" እና እዝነት የኾነን እናወርዳለን*፡፡ በዳዮችንም ከሳራን እንጂ ሌላ አይጨምርላቸውም፡፡ وَنُنَزِّلُ مِنَ الْقُرْآنِ مَا هُوَ شِفَاءٌ وَرَحْمَةٌ لِّلْمُؤْمِنِينَ ۙ وَلَا يَزِيدُ الظَّالِمِينَ إِلَّا خَسَارًا

አምላካችን አላህ ቁርኣንን ቀርተው ከሚጠቀሙ ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
1_5125580534726000876.pdf
369.4 KB
1_5125580534726000876.pdf

የቁርኣን ትንቢት

በፒዴፍ ደረጃ ለአንባቢያን ተበርክቷል። መልካም የንባብ ጊዜ።
ሦስቱ መላእክት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

29፥31 *መልእክተኞቻችንም ኢብራሂምን በብስራት በመጡት ጊዜ «እኛ የዚህችን ከተማ ሰዎች አጥፊዎች ነን፡፡ ሰዎቿ በዳዮች ነበሩና» አሉት*፡፡ وَلَمَّا جَاءَتْ رُسُلُنَا إِبْرَاهِيمَ بِالْبُشْرَىٰ قَالُوا إِنَّا مُهْلِكُو أَهْلِ هَـٰذِهِ الْقَرْيَةِ ۖ إِنَّ أَهْلَهَا كَانُوا ظَالِمِينَ

ኦሪት ዘፍጥረት ላይ አብርሃም ቤት ሦስት ሰዎች በእንግድነት እንደተስተናገዱ ይናገራል፤ ዐበይት ክርስቲያኖች፦ ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክ እና አንግሊካን እነዚህ ሦስት ሰዎች ሥላሴ ናቸው ይላሉ፤ እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 220 ድህረ-ልደት”AD” ቱርቱሊያም ይህንን አንቀጽ ይዞ የሥላሴን ቶኦሎጅይ ቴኦሌጃይዝ ያደረገው፤ በአገራችንም በየወሩ በሰባተኛው ቀን የአብርሃሙ ሦላሴ እየተባለ ይዘከራል፤ እውን ይህ አንቀጽ ለሥላሴ ተስተምህሮት መደላለል ይሆናልን? እስቲ ጥንልልና ጥንፍፍ አርገን እናስተንትነው፦
ዘፍጥረት 18፥1-2 በቀትርም ጊዜ እርሱ በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ *እግዚአብሔር በመምሬ የአድባር ዛፍ ተገለጠለት*። ዓይኑንም አነሣና እነሆ፥ *ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ*፤

እዚህ ጥቅስ ላይ ስለ ሥላሴ ምንም ሽታው እንኳን የለም። እነዚህ ሦስት ሰዎች አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ናቸው የሚል ዐውዱ ላይ ምንም አናገኝም። ይህንን አንቀጽ ለሥላሴ የተጠቀመ ነብይም ሆነ ሃዋርያ የለም፤ እነዚህ ሰዎች እነማን ናቸው ታዲያ? ለሚለው ጥያቄ መልስ ለዐውደ ንባቡ ቦታውን እንልቀቅ፦
ዘፍጥረት 18፥16 *ሰዎቹም ከዚያ ተነሥተው ወደ ሰዶም አቀኑ* አብርሃምም ሊሸኛቸው አብሮአቸው ሄደ።
ዘፍጥረት 18፥22 *ሰዎቹም ከዚያ ፊታቸውን አቀኑ፥ ወደ ሰዶምም ሄዱ* አብርሃም ግን በእግዚአብሔር ፊት ገና ቆሞ ነበር።

እነዚህ ሰዎች ከአብርሃም ቤት ወደ ሰዶም አቀኑ፣ ወደ ሰዶምም ሄዱ፤ ከዚያስ? በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ገቡ፦
ዘፍጥረት 19፥1 *ሁለቱም መላእክት በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ገቡ*፤

እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር ሲነጋገር የነበረው በሦስት ሰዎች ነው፤ ሁለቱ ሰዎች ሲሄዱ ግን “አብርሃም በእግዚአብሔር ፊት ገና ቆሞ ነበር” ይላል፤ እግዚአብሔር በአንዱ ሰው ሲነጋገር ሁለቱ ሰዎች ሎጥ ቤት ገብተዋል፦
ዘፍጥረት 19፥10 *ሁለቱም ሰዎች እጃቸውን ዘርግተው ሎጥን ወደ እነርሱ ዘንድ ወደ ቤት አገቡት መዝጊያውንም ዘጉት*።
ዘፍጥረት 19፥12 *ሁለቱም ሰዎች ሎጥን አሉት*።
ዘፍጥረት 19፥13 *እኛ ይህን ስፍራ እናጠፋለንና፥ ጩኸታቸው በእግዚአብሔር ፊት ትልቅ ሆኖአልና እናጠፋውም ዘንድ እግዚአብሔር ሰድዶናል*።

“ሁለቱ ሰዎች” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ ምን ትፈልጋለህ? ከአብርሃም ቤት ወጥተው ወደ ሎጥ ቤት የገቡት ሰዎች በቁጥር ሁለት መሆናቸውን እና ሁለት መላእክት መሆናቸውን ተገልጻል፤ እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ በአንድ ሰው ይናገራል፤ ይህም ሰው መልአክ ተብሏል፤ ለምሳሌ ያዕቆብ ሲታገለው የነበረው መልአክ ሰው ተብሏል፦
ዘፍጥረት 32፥28 አለውም፦ ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ እስራኤል ይባል እንጂ ያዕቆብ አይባል፤ *ከእግዚአብሔር እና ከሰውም ጋር ታግለህ አሸንፈሃልና*።
ሆሴዕ 12፥3-4 በማኅፀን ውስጥ ወንድሙን በተረከዙ ያዘው፥ በጕልማስነቱም ጊዜ *ከአምላክ ጋር ታገለ፤ ከመልአኩም ጋር ታግሎ አሸነፈ*፤ አልቅሶም ለመነው። በቤቴልም አገኘው፥ በዚያም *ከእኛ ጋር ተነጋገረ*።

“ከእኛ ጋር ተነጋገረ” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ እግዚአብሔር እዚህ አንቀጽ ላይ፦ “እኛ” የሚለው መልአኩን ጨምሮ እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል፤ ምነው ገብርኤል ሰው ተብሎ የለ እንዴ? መላእክት በሰው ቅርጽ ስለሚመጡ ሰው ይባላሉ፦
ዳንኤል 9፥21 ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው *የነበረው ሰው ገብርኤል* እነሆ እየበረረ መጣ፤ በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ።

እግዚአብሔር ግን ሰው አይደለም፤ አይበላም አይጠጣምም፦
ሆሴዕ 11፥9 *እኔ አምላክ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁምና*፥
መዝሙር 50፥12 *ብራብም ለአንተ አልነግርህም፥ ዓለምና ሞላው የእኔ ነውና። የፍሪዳውን ሥጋ እበላለሁን? የፍየሉንስ ደም እጠጣለሁን?*

ፈጣሪ፦ እበላለሁን? እጠጣለሁን? ሲል በምጸታዊ አነጋገር አልበላም አልጠጣም እያለ ነው፤ አንዳንድ ቂሎች፦ “አብርሃም ቤት የገቡት ሰዎች ምግብ በልተዋል፤ መላእክት እንዴት ይበላሉ? ብለው ይጠይቃሉ፤ የቱ ይቀላል መጋቢ ፈጣሪ መብላቱ ወይስ ፍጡር የሆኑት መላእክት መብላታቸው? አዎ መላእክቱ በልተዋል ይለናል፦
ዘፍጥረት 18፥8 እርጎና ወተትም ያዘጋጀውንም ጥጃ አመጣ፥ በፊታቸውም አቀረበው እርሱም ከዛፉ በታች በፊታቸው ቆሞ ነበር፥ *እነርሱም በሉ*።
ዘፍጥረት 19፥3 እጅግም ዘበዘባቸው ወደ እርሱም አቀኑ፥ ወደ ቤቱም ገቡ ማዕድ አቀረበላቸው፥ ቂጣንም ጋገረ *እነርሱም በሉ*።

ሎጥ ቤት የበሉት መላእክት ሥላሴ ናቸው ብላችሁ እንዳታርፉት፤ የዕብራውያን ጸሐፊ፦ “አንዳንዶች በእንግድነት መላእክትን ተቀብለዋል” በማለት አብርሃምን እና ሎጥን ያስታውሰናል፦
ዕብራውያን 13፥2 *እንግዶችን መቀበል አትርሱ*፤ በዚህ አንዳንዶች *ሳያውቁ መላእክትን እንግድነት ተቀብለዋልና*።
ሎጥ ቤት የበሉት መላእክት ሥላሴ ናቸው ብላችሁ እንዳታርፉት፤ የዕብራውያን ጸሐፊ፦ “አንዳንዶች በእንግድነት መላእክትን ተቀብለዋል” በማለት አብርሃምን እና ሎጥን   ያስታውሰናል፦
ዕብራውያን 13፥2 *እንግዶችን መቀበል አትርሱ*፤ በዚህ አንዳንዶች *ሳያውቁ መላእክትን እንግድነት ተቀብለዋልና*።

ከሎጥ ሌላ በእንግድነት እግር አጥቦና ጋብዞ እንግዳ የተቀበለ አብርሃም ነው። ደግሞም ድርሳነ ሚካኤል አብርሃም ቤት ገብተው አብርሃምን ያበሰሩት መላእክት እንደሆኑ ይናገራል፦
ድርሳነ ሚካኤል ዘሚያዝያ ቁጥር 11
ግዕዙ፦
*ወካዕበ መጽኡ መላእክት ወበጽሑ ኀበ አብርሃም ወነገርዎ ከመ ይትወለድ ይስሐቅ*።
አማርኛው፦
*ዳግመኛ መላእክት ወደ አብርሃም ዘንድ መጥተው ይስሐቅን እንደሚወልድ ነገሩት*።

አምላካችን አላህ ወደ ኢብራሂም ቤት በብስራት የመጡት መልእክተኞቹ እንደሆኑና እነዚህም መላእክትም ወደ ሉጥ ቤት እንደገቡ ይናገራል፦
29፥31 *መልክተኞቻችንም ኢብራሂምን በብስራት በመጡት ጊዜ «እኛ የዚህችን ከተማ ሰዎች አጥፊዎች ነን፡፡ ሰዎቿ በዳዮች ነበሩና» አሉት*፡፡ وَلَمَّا جَاءَتْ رُسُلُنَا إِبْرَاهِيمَ بِالْبُشْرَىٰ قَالُوا إِنَّا مُهْلِكُو أَهْلِ هَـٰذِهِ الْقَرْيَةِ ۖ إِنَّ أَهْلَهَا كَانُوا ظَالِمِينَ
11፥77 *መልእክተኞቻችንም ሉጥን በመጡት ጊዜ በእነርሱ ምክንያት አዘነ፡፡ ልቡም በነሱ ተጨነቀ፡፡ «ይህ ብርቱ ቀን ነውም» አለ*፡፡ وَلَمَّا جَاءَتْ رُسُلُنَا لُوطًا سِيءَ بِهِمْ وَضَاقَ بِهِمْ ذَرْعًا وَقَالَ هَـٰذَا يَوْمٌ عَصِيبٌ

እነዚህ መላእክት የቁጥራቸው መጠን ቁርኣን ላይ በእርግጥ አልተገለጸም፤ እንዲሁ ቁርኣን እነዚህ መላእክት በሉ አይልም፤ ኢብራሂም የተጠበሰን የወይፈን ስጋ ሲያመጣላቸው እጆቻቸውም ወደ ምግቡ የማይደርሱ መኾነቸውን ባየ ጊዜ ሸሻቸው፤ ምግብ የማይበሉ መሆናቸውን ሲረዳ ከእነርሱም ፍርሃት ተሰማው፦
11፥69 *መልእክተኞቻችንም ኢብራሂምን በልጅ ብስራት በእርግጥ መጡት፡፡ ሰላም አሉት፡፡ ሰላም አላቸው፡፡ ጥቂትም ሳይቆይ ወዲያውኑ የተጠበሰን የወይፈን ስጋ አመጣ*፡፡ وَلَقَدْ جَاءَتْ رُسُلُنَا إِبْرَاهِيمَ بِالْبُشْرَىٰ قَالُوا سَلَامًا ۖ قَالَ سَلَامٌ ۖ فَمَا لَبِثَ أَن جَاءَ بِعِجْلٍ حَنِيذٍ
11፥70 *እጆቻቸውም ወደ እርሱ የማይደርሱ መኾነቸውን ባየ ጊዜ ሸሻቸው፡፡ ከእነርሱም ፍርሃት ተሰማው፡፡ «አትፍራ እኛ ወደ ሉጥ ሕዝቦች ተልከናልና» አሉት*፡፡ فَلَمَّا رَأَىٰ أَيْدِيَهُمْ لَا تَصِلُ إِلَيْهِ نَكِرَهُمْ وَأَوْجَسَ مِنْهُمْ خِيفَةً ۚ قَالُوا لَا تَخَفْ إِنَّا أُرْسِلْنَا إِلَىٰ قَوْمِ لُوطٍ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ጥያቄ አለቀ!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

49፥7 *"በውስጣችሁም" የአላህ መልክተኛ መኖሩን ዕወቁ*፡፡ وَاعْلَمُوا أَنَّ فِيكُمْ رَسُولَ اللَّهِ

እሥልምና ዱር ሙሥሊሙ ሐሩር እንዲሆን ቀን ከሌሊት ደፋ ቀና፥ ጠብ እርግፍ የሚሉት አግድም አደግ ዕውቀት ያላቸው ሚሽነሪዎች የማይፈነቅሉት ድንጋይ፣ የማይቆፍሩት ጉድጓድ፣ የማይደረምሱት መሬት የለም። ኢየሱስ ሰው ነው፥ ሰው እያመለኩ እኛም ሰው በግድ ታመልካላችሁ ለማስባል የእከክልኝ ልከክልህ ጉዳይ ነውና፥ "ነቢያችሁ"ﷺ" በሁላችሁም ልባችሁ ውስጥ እንደ አምላክ ይኖራሉ" ይላሉ። እዚህ ድምዳሜ ላይ ያደራሳችሁ የትኛው አንቀጽ ነው? ስንላቸው፥ "ይህ አንቀጽ ነው" ይሉናል፦
49፥7 *"በውስጣችሁም" የአላህ መልክተኛ መኖሩን ዕወቁ*፡፡ وَاعْلَمُوا أَنَّ فِيكُمْ رَسُولَ اللَّهِ

ምን ይሻላችሁ ይሆን? ጥያቄ አለቀባችሁ? እዚህ አንቀጽ ላይ "በውስጣችሁም" የሚለው ቃል "ፊኩም" فِيكُمْ ሲሆን "በይነኩም" بَيْنَكُم ማለትም "በመካከላችሁ" ለማለት እንጂ "በልባችሁ" ለማለት በፍጹም አይደለም። "በልባችሁ" ለማለት ቢሆን ኖሮ "ቀሉቢኩም" قُلُوبِكُمْ ይል ነበር፥ ቅሉ ግን እንደዛ አላለም፦
2፥151 *በውስጣችሁ ከእናንተው የኾነን በእናንተ ላይ አንቀጾቻችንን የሚያነብላችሁና የሚያጠራችሁ፣ መጽሐፍንና ጥበብንም የሚያስተምራችሁ፣ ታውቁት ያልነበራችሁትንም ነገር የሚያሳውቃችሁ የኾነን መልእክተኛ እንደላክን ጸጋን ሞላንላችሁ*፡፡ كَمَا أَرْسَلْنَا فِيكُمْ رَسُولًا مِّنكُمْ يَتْلُو عَلَيْكُمْ آيَاتِنَا وَيُزَكِّيكُمْ وَيُعَلِّمُكُمُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَيُعَلِّمُكُم مَّا لَمْ تَكُونُوا تَعْلَمُونَ
3፥101 *የአላህም አንቀጾች በእናንተ ላይ የሚነበቡ ሲኾኑ መልእክተኛውም "በውስጣችሁ" ያለ ሲኾን እናንተ እንዴት ትክዳላችሁ?* በአላህም የሚጠበቅ ሰው ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ተመራ፡፡ وَكَيْفَ تَكْفُرُونَ وَأَنتُمْ تُتْلَىٰ عَلَيْكُمْ آيَاتُ اللَّهِ وَفِيكُمْ رَسُولُهُ ۗ وَمَن يَعْتَصِم بِاللَّهِ فَقَدْ هُدِيَ إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ

"በውስጣችሁ" መልእክተኛ ልከናል" ሲል "በልባችሁ" መልክእተኛ ልከናል ማለቱ ነው እንዴ" እረ በፍጹም። ባይሆን በመካከላቸው መልእክተኛ መላኩን የሚያሳይ ቢሆን እንጂ፦
40፥32 *"በውስጣቸውም" ከእነሱ የኾነን መልእክተኛ አላህን አምልኩ፥ ከእርሱ ሌላ አምላክ የላችሁም አትጠነቀቁምን? በማለት ላክን*፡፡ فَأَرْسَلْنَا فِيهِمْ رَسُولًا مِّنْهُمْ أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَـٰهٍ غَيْرُهُ ۖ أَفَلَا تَتَّقُونَ

"በውስጣቸው" ለሚለው የገባው ቃል ሦስተኛ መደብ "ፊሂም" فِيهِمْ ሲሆን "በይነሁም" بَيْنَهُمْ ማለትም "በመካከላቸው" የሚለውን ለማመልከት ነው። አላህ የትንሳኤ ቀን የሚቀጣውን ቅጣት ከተናገረ በኃላ፥ ከቅጣቱ በፊት ግን አስጠንቃቂ መልእክተኞችን በሕዝቦቻቸው መካከል እንደላከ ይናገራል፦
37፥72 *"በውስጣቸውም" አስጠንቃቂዎችን በእርግጥ ልከናል*፡፡ وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا فِيهِم مُّنذِرِينَ

ከነቢያችን"ﷺ" በፊት የተላኩት መልክተኞች "በውስጣቸው" ነው ማለት "በልባቸው" ነው ማለት ሳይሆን በመካከላቸው መሆኑን እሙን ነው፦
5፥20 ሙሳም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ፡- «ሕዝቦቼ ሆይ የአላህን ጸጋ *"በውስጣችሁ" ነቢያትን ባደረገና ነገሥታትንም ባደረጋችሁ ከዓለማትም ለአንድም ያልሰጠውን ችሮታ በሰጣችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ ያደረገውን ጸጋ አስታውሱ*፡፡» وَإِذْ قَالَ مُوسَىٰ لِقَوْمِهِ يَا قَوْمِ اذْكُرُوا نِعْمَةَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ إِذْ جَعَلَ فِيكُمْ أَنبِيَاءَ وَجَعَلَكُم مُّلُوكًا وَآتَاكُم مَّا لَمْ يُؤْتِ أَحَدًا مِّنَ الْعَالَمِينَ
አላህ ሙሳ ሕዝቦች በውስጣቸው ነቢያትን እና ነገሥታትን አደረገ ማለት በመካከላቸው ነቢያትን እና ነገሥታትን አደረገ ማለት እንጂ በልባቸው ነቢያትን እና ነገሥታትን አደረገ ማለት እንዳልሆነ ቅቡል ነው። ምነው አላህ ኑሕንም ወደ ሕዝቦቹ ልኮ "በውስጣቸውም" ሺህ ዓመትን አምሳ ዓመት ሲቀር ተቀመጠ ይል የለ እንዴ? በልባቸው ሺህ ዓመትን አምሳ ዓመት ሲቀር ተቀመጠ ማለት እንዳልሆነ ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ነው፦
29፥14 *ኑሕንም ወደ ሕዝቦቹ በእርግጥ ላክነው፡፡ "በውስጣቸውም" ሺህ ዓመትን አምሳ ዓመት ሲቀር ተቀመጠ*፡፡ እነርሱ በዳዮች ኾነውም የውሃው ማጥለቅለቅ ያዛቸው፡፡ وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوْمِهِ فَلَبِثَ فِيهِمْ أَلْفَ سَنَةٍ إِلَّا خَمْسِينَ عَامًا فَأَخَذَهُمُ الطُّوفَانُ وَهُمْ ظَالِمُونَ

ዒሣ ከማረጉ በፊት በሕዝቦቹ ውስጥ ነበር። ያ ማለት በልባቸው ውስጥ ነበረ ማለት ሳይሆን በመካከላቸው ነበር ማለት ነው፦
5፥117 «በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን ተገዙ ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ *”በውስጣቸውም" እስካለሁ ድረስ” በእነርሱ ላይ ”ምስክር” ነበርኩ*፡፡ *”በወሰድከኝም” ጊዜ አንተ በእነርሱ ላይ *”ተጠባባቂ”* ነበርክ፡፡ አንተም በነገሩ ሁሉ ላይ ዐዋቂ ነህ፡፡» مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ ۚ وَكُنتُ عَلَيْهِمْ شَهِيدًۭا مَّا دُمْتُ فِيهِمْ ۖ فَلَمَّا تَوَفَّيْتَنِى كُنتَ أَنتَ ٱلرَّقِيبَ عَلَيْهِمْ ۚ وَأَنتَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍۢ شَهِيدٌ

ምነው የእኔ እንጀራ እንደ ጋቢ ጥለቱ ቀጭን ነው አላችሁሳ? የኛ ዘንካታዎች እየተጎማለላችሁ ቁርኣን ውስጥ እንደገባችሁ ባይብል ላይ ገብተን እያነጻጸርን እናሳያችኃለን። ሙሴ፣ አሮን፣ ሳሙኤል፣ ነቢያት ከሞቱ ወዲህ በምእመናን መካከል እንደሚኖሩ ተነግሯል፦
መዝሙር 99፥6 *ሙሴና አሮን በካህናቱ ዘንድ፥ ሳሙኤልም ስሙን በሚጠሩት ዘንድ ናቸው*።
ሉቃስ 16፥29 አብርሃም ግን፦ *ሙሴና ነቢያት አሉአቸው፤ እነርሱን ይስሙ አለው*።

"ካህናቱ" እና "ሚጠሩት" በሚለው መነሻ ላይ ያለው "በ" የሚለው መስተዋድድ ልብ በል። "ፊ" فِي የግድ ውስጥ ብቻ ሳይሆን "በ" በሚል ይመጣል፥ ለምሳሌ፦ “ፊ ሰብሊልሏህ” فِي سَبِيلِ ٱللَّه ማለትም “በአላህ መንገድ” በሚል። ታዲያ ሙሴ፣ አሮን፣ ሳሙኤል፣ ነቢያት በሁሉም ስፍራ የሚኖሩ ናቸውን? ልክ እንደ አምላክ በአማንያን ልብ ውስጥ ይኖራሉ ማለት ነውን? አይ አርአያነታቸው እና ትምህርታቸው ነው ከተባለ፥ ከላይ ያለውንም የቁርኣን አንቀጽ አካላዊ መገኘት ሆኖ ሳለ ልባዊ ነው ካላችሁ እንግዲያውስ በቀላሉ በዚህ ልክና መልክ ተረዱት እንጂ ኢሥላም ጋር የሚመለክ ፍጡር የለም። "ነካክተው ነካክተው የተኛውን በሬ፥ እንደው አደረጉት አውሬ" ይላል ያገሬ ሰው። ሲያንቀለቅላችሁ ቆስቁሳችሁ፥ እሳት ላይ ተጣዳችሁ።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ተጎዳኝ የንጽጽር መጣጥፍ እና ኦድዮ ይፈልጋሉን? እንግዲያውስ ከታች ያሉትን ሊንክ ተጭነው ጎራ ይበሉ!
የኡስታዝ አቡ ሃይደር፦
@abuhyder

የኡስታዝ ኤልያህ፦
@religionandphylosophy

የኡስታዝ አቡ ዩሥራ፦
@Abuyusra3

የኡስታዝ የሕያህ፦
t.me/yahya5
ተርጂም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

12፥2 *እኛ ትገነዘቡ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን ሲሆን በእርግጥ አወረድነው*፡፡ إِنَّا أَنزَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ

አምላካችን አላህ ቁርኣንን ዐረቢኛ አድርጎ አወረደው፥ ቁርኣን በዐረብኛ የተነገረ ፍትሕ ነው፦
43፥3 *እኛ ትገነዘቡ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን አደረግነው*፡፡ إِنَّا جَعَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ
12፥2 *እኛ ትገነዘቡ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን ሲሆን በእርግጥ አወረድነው*፡፡ إِنَّا أَنزَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ
13፥37 *እንደዚሁ በዐረብኛ የተነገረ ፍትሕ ሲኾን አወረድነው*፡፡ وَكَذَٰلِكَ أَنزَلْنَاهُ حُكْمًا عَرَبِيًّا

“ዐረቢይ” عَرَبِيّ ማለት “ዐረብኛ” ማለት ሲሆን በሥነ-ሰዋስው ገላጭ ቅጽል ነው፥ ቁርኣን የወረደው ዐረቢኛ ሆኖ ነው። ከዐረቢኛው ቁርኣን ውጪ ያሉት የዐማርኛ፣ የእንግሊዝኛ፣ የፈረንሳይኛ፣ የስውዲንኛ መጽሐፎች ቁርኣን ሳይሆኑ የቁርኣን ትርጉም ናቸው፦
41፥3 አንቀጾቹ የተብራሩ የኾነ መጽሐፍ ነው፡፡ *ዐረብኛ ቁርኣን ሲኾን ለሚያውቁ ሕዝቦች የተብራራ ነው*፡፡ كِتَابٌ فُصِّلَتْ آيَاتُهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لِّقَوْمٍ يَعْلَمُونَ

"ተርጂም" تَرْجِم ማለት "ተርጀመ" تَرْجَمَ ‎ማለትም "ተረጎመ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ትርጉም"translation" ማለት ነው፥ "ሙተርጂም" مُتَرْجِم ወይም "ተርጁማን" تَرْجُمَان‎ ማለት ደግሞ "ተርጓሚ"translator" ማለት ነው። የሙተርጂም ወይም የተርጁማን ብዜት "ሙተርጂሙን" مُتَرْجِمُون ወይም "ተራጂም" تَرَاجِيم ማለትም "መተርጉማን" ነው። ለምሳሌ ቁርኣንን ወደ ሌላ ቋንቋ የመተርጎም ሥራ "ተርጂም" ይባላል። የቅዱስ ቁርኣን ትርጉም አሳቡን እንጂ ቃላቱን በትክክል አይተረጎምም። በዐረቢኛ አቻ ቃል ሳይገኝ ሲቀር ወይም ሌላ አንቀጽ ላይ የተብራራ አንቀጽ ሆኖ ሲገኝ የዐማርኛ ተርጓሚዎች በቅንፍ የማስቀመጥ ልምድ አላቸው፦
11፥112 *"እንደ ታዘዝከውም ቀጥ በል፡፡ ከአንተ ጋር ያመኑትም (ቀጥ ይበሉ)፡፡ ወሰንንም አትለፉ! እርሱ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና*፡፡ فَاسْتَقِمْ كَمَا أُمِرْتَ وَمَن تَابَ مَعَكَ وَلَا تَطْغَوْا ۚ إِنَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ

"ወ" وَ የሚለው አርፉል አጥፍ "እንዲሁ" የሚል ፍቺ ስላለው "ቀጥ ይበሉ" የሚለውን በውስጠ ታዋቂነት ስለመጣ በቅንፍ አስቀምጠውታል፥ ምክንያቱም ቀጣዩ ኃይለ-ቃል "ወሰንንም አትለፉ! እርሱ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና" የሚል የብዙ ቁጥር የግስ መደብ ሆኖ ስለመጣ ነው፦
3፥20 ቢከራከሩህም፡- *«ፊቴን ለአላህ ሰጠሁ፤ የተከተሉኝም ሰዎች (ለአላህ ሰጡ)*» በላቸው፡፡ فَإِنْ حَاجُّوكَ فَقُلْ أَسْلَمْتُ وَجْهِيَ لِلَّهِ وَمَنِ اتَّبَعَنِ

"ወ" وَ የሚለው አርፉል አጥፍ "እንዲሁ" የሚል ፍቺ ስላለው "ለአላህ ሰጡ" የሚለውን በውስጠ ታዋቂነት ስለመጣ በቅንፍ አስቀምጠውታል፦
2፥285 *መልክተኛው ከጌታው ወደ ርሱ በተወረደው አመነ፡፡ ምእምኖቹም (እንደዚሁ አመኑ)*፡፡ آمَنَ الرَّسُولُ بِمَا أُنزِلَ إِلَيْهِ مِن رَّبِّهِ وَالْمُؤْمِنُونَ

ዐረቢኛው ላይ ምንም የማያሻማ ሲሆን ወደ ዐማርኛው አቻ ቃል ሲጠፋ የዐማርኛ መተርጉማን በቅንፍ ያስቀምጣሉ እንጂ የኢንግሊሹን ብታዩት ግልጽ ነው፥ እስቲ በኢንግሊሹ ይህንኑ አንቀጽ እንይ፦
2፥285 The Messenger believeth in what hath been revealed to him from his Lord, as do the men of faith. Yusuf Ali (Saudi Rev. 1985)

"ወ" وَ የሚለውን አርፉል አጥፍ "እንዲሁ"as do" ብሎታል፥ ይህ የተለመደ ብዙ ቦታ ዐማርኛው ትርጉም ላይ አለ፦
22፥75 *አላህ ከመላእክት ውስጥ መልክተኞችን ይመርጣል፡፡ ከሰዎችም (እንደዚሁ)*፤ አላህ ሰሚ ተመልካች ነው፡፡ اللَّهُ يَصْطَفِي مِنَ الْمَلَائِكَةِ رُسُلًا وَمِنَ النَّاسِ ۚ إِنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ بَصِيرٌ
11፥3 *የመንቀልቀል ባለቤት የኾነችን እሳት በእርግጥ ይገባል*፡፡ سَيَصْلَىٰ نَارًا ذَاتَ لَهَبٍ
111፥4 *ሚስቱም (ትገባለች)*፤ እንጨት ተሸካሚ ስትኾን፡፡ وَامْرَأَتُهُ حَمَّالَةَ الْحَطَبِ

"ትገባለች" የሚለው የሚገልጸው ቃል "ወ" وَ የሚለው አርፉል አጥፍ ሲሆን "እንዲሁ"as do" ለማለት ተፈልጎ የገባ ቃል ነው፦
2፥45 *”በመታገስ እና በሶላትም ተረዱ፡፡ እርሷም(ሶላት) በፈሪዎች ላይ እንጅ በሌላው ላይ በእርግጥ ከባድ ናት*፡፡ وَاسْتَعِينُوا بِالصَّبْرِ وَالصَّلَاةِ ۚ وَإِنَّهَا لَكَبِيرَةٌ إِلَّا عَلَى الْخَاشِعِينَ

“ሃ” َّهَا ማለትም “እርሷ” የሚለው ተውላጠ-ስም ተክቶ የመጣው “መታገስ” የሚለው ቃል ሳይሆን የቅርብ ቃል የሆነውን “ሶላት” የሚለውን ስለሆነ፥ በዐማርኛ አሻሚ እንዳይሆን "ሶላት" የሚለውን በቅንፍ አስቀምጠውታል። ምክንያቱም "ሶብር" صَّبْر ሙዘከር ስለሆነ "ሶላህ" صَّلَاة ደግሞ ሙአነስ ስለሆነ ነው። “ሃ” َّهَا የሚለው ተሳቢ ሙአነስ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። እንቀጥል፦
17፥1 ያ ባሪያውን ከተከበረው መስጊድ ወደዚያ ዙሪያውን ወደ ባረክነው ወደ ሩቁ መስጊድ በሌሊት ውስጥ ያስኼደው (ጌታ) ጥራት ይገባው፡፡ ከተዓምራቶቻችን ልናሳየው (አስኼድነው)፡፡ *እነሆ እርሱ (አላህ) ሰሚው ተመልካቺው ነው*፡፡ سُبْحَانَ الَّذِي أَسْرَىٰ بِعَبْدِهِ لَيْلًا مِّنَ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ إِلَى الْمَسْجِدِ الْأَقْصَى الَّذِي بَارَكْنَا حَوْلَهُ لِنُرِيَهُ مِنْ آيَاتِنَا ۚ إِنَّهُ هُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ
"ሁወ" هُوَ ማለትም "እርሱ" የተባለው ባለቤት ተውላጠ-ስም መነሻ አንቀጽ ላይ "አልለዚ" الَّذِي ማለትም "ያ" የሚለውን አመልካች ተውላጠ-ስም ተክቶ ስለመጣ "እርሱ" የተባለው "አላህ" መሆኑን ለማሳየት በቅንፍ አስቀምጠዋል። ምክንያቱም አንደኛ "ልናሳየው" የሚለው ነቢያችንን"ﷺ" የሚያመለክት ስለሆነ፤ ሰው ሲያነብ "እርሱ" የተባለው ነቢያችንን"ﷺ" እንዳይመስለው። ሁለተኛ ብዙ ቦታ "ሰሚው ተመልካቺው ነው" የሚል ቃል ለነቢያችን"ﷺ" ሳይሆን ለአላህ የሚውል ነው፥ ሦስተኛ "ኢነ" إِنَّ የሚለው ሐርፉል ኑስብ "ሁ" هُ የሚለው ቃል ላይ መነሻ ሆኖ እንደመጣ ሁሉ "አላህ" ከሚለው ቃል በፊት መነሻ ሆኖ ሌሎች አናቅጽ ላይ መጥቷል፦
22፥75 *"አላህ ሰሚ ተመልካች ነውና*፡፡ إِنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ بَصِيرٌ
58፥1 *"አላህ ሰሚ ተመልካች ነውና*፡፡ إِنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ بَصِيرٌ
31፥28 *"አላህ ሰሚ ተመልካች ነውና*፡፡ إِنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ بَصِيرٌ

እንዲህ ዓይነት የትርጉም እጥረት ባይብል ላይ ይኖር ይሆን? እንዴታ! አለ እንጂ። ግሪኩ ላይ የሌለ ግን ትርጉም ስለማይሰጥ ዐማርኛ ላይ ወይም እንግሊዘኛ ላይ የጨመሩት ቃል አለ። ለምሳሌ፦
ማቴዎስ 10፥2 የአሥራ ሁለቱም ሐዋርያት ስም ይህ ነው፤ መጀመሪያው ጴጥሮስ የተባለው ስምዖን ወንድሙ እንድርያስም፥ የዘብዴዎስ *ልጅ* ያዕቆብም ወንድሙ ዮሐንስም፥
Τῶν δὲ δώδεκα ἀποστόλωντὰ ὀνόματά ἐστιν ταῦτα:πρῶτος Σίμων ὁ λεγόμενοςΠέτρος καὶ Ἀνδρέας ὁἀδελφὸς αὐτοῦ, καὶ Ἰάκωβοςὁ τοῦ Ζεβεδαίου καὶ Ἰωάννηςὁ ἀδελφὸς αὐτοῦ,

ግሪኩ ላይ "ሁዎስ" υἱός ወይም በአገናዛቢ ሙያ "ሁኦዩ" υἱοῦ ማለትም "ልጅ" የሚል የለም። ስለዚህ እዚህ አንቀጽ ላይ ያዕቆብ የዘብድዮስ ወንድም ይሁን፣ አጎት ይሁን፣ አባት ይሁን፣ ልጅ ይሁን የሚታወቀው ነገር የለም። ይህንን አንቀጽ የሚያብራራልን ሌላ መጽሐፍ ላይ፣ ሌላ ምዕራፍ ላይ፣ ሌላ አንቀጽ ላይ እናገኛለን፦
ማርቆስ 10፥35 የዘብዴዎስ *ልጆች* ያዕቆብ እና ዮሐንስም ወደ እርሱ ቀርበው፦ መምህር ሆይ፥ የምንለምንህን ሁሉ እንድታደርግልን እንወዳለን አሉት። Καὶ προσπορεύονται αὐτῷ Ἰάκωβος καὶ Ἰωάννης οἱ υἱοὶ Ζεβεδαίου λέγοντες αὐτῷ, Διδάσκαλε, θέλομεν ἵνα ὃ ἐὰν αἰτήσωμέν σε ποιήσῃς ἡμῖν.

እዚህ አንቀጽ ላይ "ሁኦኢ" υἱοὶ ማለትም "ልጆች" የሚል ቃል ስላለ፥ መተርጉማን "ልጅ" የሚለውን በማቴዎስ 10፥2 ላይ ግሪኩ ላይ የሌለውን አስገብተዋል። ሌላ ናሙና፦
ማርቆስ 9፥29 ይህ ወገን በጸሎት *"እና በጦም"* ካልሆነ በምንም ሊወጣ አይችልም" አላቸው። καὶ εἶπεν αὐτοῖς, Τοῦτο τὸ γένος ἐν οὐδενὶ δύναται ἐξελθεῖν εἰ μὴ ἐν προσευχῇ.

እዚህ አንቀጽ ላይ "ካይ ኔስቴአ" καὶ νηστείᾳ ማለትም "እና ጦም" የሚል ቃል ጭራሽኑ የለም። ይህንን አንቀጽ የሚያብራራልን ሌላ መጽሐፍ ላይ፣ ሌላ ምዕራፍ ላይ፣ ሌላ አንቀጽ ላይ አለ፦
ማቴዎስ 17፥21 ይህ ዓይነት ግን ከጸሎት *እና ከጦም* በቀር አይወጣም" አላቸው። Τοῦτο τὸ γένος ἐν οὐδενὶ δύναται ἐξελθεῖν εἰ μὴ ἐν προσευχῇ καὶ νηστείᾳ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ካይ ኔስቴአ" καὶ νηστείᾳ ማለትም "እና ጦም" የሚል ቃል ስላለ፥ መተርጉማን "እና በጦም" የሚለውን በማቴዎስ 17፥21 ላይ ግሪኩ ላይ የሌለውን አስገብተዋል። ሌላ ናሙና፦
1 ቆሮንቶስ 13፥3 *"ድሆችንም* ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም። κἂν ψωμίσω πάντα τὰ ὑπάρχοντά μου, καὶ ἐὰν παραδῶ τὸ σῶμά μου ἵνα καυχήσωμαι, ἀγάπην δὲ μὴ ἔχω, οὐδὲν ὠφελοῦμαι.

"ድሆች" በኮይኔ ግሪክ "ፕቶቾስ" πτωχοῖς ሲሆን ግሪኩ ላይ የለም። ስለዚህ እዚህ አንቀጽ ላይ ጳውሎስ "ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል" የሚለው ስለእነማን እንደሆነ የሚታወቀው ነገር የለም። ይህንን አንቀጽ የሚያብራራልን ሌላ መጽሐፍ ላይ፣ ሌላ ምዕራፍ ላይ፣ ሌላ አንቀጽ ላይ እናገኛለን፦
ማቴዎስ 19፥21 ኢየሱስም፦ ፍጹም ልትሆን ብትወድ፥ ሂድና ያለህን ሸጠህ *ለድሆች* ስጥ፥ መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ፥ መጥተህም ተከተለኝ፡ አለው። ἔφη αὐτῷ ὁ Ἰησοῦς, Εἰ θέλεις τέλειος εἶναι, ὕπαγε πώλησόν σου τὰ ὑπάρχοντα καὶ δὸς [τοῖς] πτωχοῖς, καὶ ἕξεις θησαυρὸν ἐν οὐρανοῖς, καὶ δεῦρο ἀκολούθει μοι.

እዚህ አንቀጽ ላይ "ፕቶቾስ" πτωχοῖς ማለትም "ድሆች" የሚል ቃል ስላለ፥ መተርጉማን "ድሆች" የሚለውን በ1 ቆሮንቶስ 13፥3 ላይ ግሪኩ ላይ የሌለውን አስገብተዋል። ብዙ ናሙናዎች በቁና ማቅረብ ይቻል ነበር፥ አንባቢያንን ላለማሰልቸት ነው።
"የባይብል መተርጉማን የሚተረጉሙት ቃላትን ሳይሆን አሳብን ነው" ከተባለ "እንግዲያውስ በዐማርኛው ላይ በቅንፍ የሚያስቀምጡት የቁርኣን መተርጉማን የሚተረጉሙት የቁርኣን ቃላት ሳይሆን አሳብን ነው" ብሎ በዚህ ስሌትና ቀመር መረዳት ነው። የተሰናኘ ስንኝ"syntax" ማኅበረሰቡ ሊረዳው በሚችል መልኩ መድረስ ይችላል፥ ይህንን ስንኝ ቃልን በቃል የመተርጎም ሥራ "የቃል ትርጉም"metaphrase translation" ሲባል፥ ቃልን በአሳብ የመተርጎም ሥራ ደግሞ "የአሳብ ትርጉም"paraphrase translation" ይባላል። ሙሥሊም የማያነብ ይመስላችኃል? አላህ ሂዳያህ ይስጣችሁ፥ ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የቅንፍ አጠቃቀም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

12፥2 *እኛ ትገነዘቡ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን ሲሆን በእርግጥ አወረድነው*፡፡ إِنَّا أَنزَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ

አምላካችን አላህ ቁርኣንን ዐረቢኛ አድርጎ አወረደው፥ ቁርኣን በዐረብኛ የተነገረ ፍትሕ ነው፦
43፥3 *እኛ ትገነዘቡ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን አደረግነው*፡፡ إِنَّا جَعَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ
12፥2 *እኛ ትገነዘቡ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን ሲሆን በእርግጥ አወረድነው*፡፡ إِنَّا أَنزَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ
13፥37 *እንደዚሁ በዐረብኛ የተነገረ ፍትሕ ሲኾን አወረድነው*፡፡ وَكَذَٰلِكَ أَنزَلْنَاهُ حُكْمًا عَرَبِيًّا

“ዐረቢይ” عَرَبِيّ ማለት “ዐረብኛ” ማለት ሲሆን በሥነ-ሰዋስው ገላጭ ቅጽል ነው፥ ቁርኣን የወረደው ዐረቢኛ ሆኖ ነው። ከዐረቢኛው ቁርኣን ውጪ ያሉት የዐማርኛ፣ የእንግሊዝኛ፣ የፈረንሳይኛ፣ የስውዲንኛ መጽሐፎች ቁርኣን ሳይሆኑ የቁርኣን ትርጉም ናቸው፦
41፥3 አንቀጾቹ የተብራሩ የኾነ መጽሐፍ ነው፡፡ *ዐረብኛ ቁርኣን ሲኾን ለሚያውቁ ሕዝቦች የተብራራ ነው*፡፡ كِتَابٌ فُصِّلَتْ آيَاتُهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لِّقَوْمٍ يَعْلَمُونَ

"ተርጂም" تَرْجِم ማለት "ተርጀመ" تَرْجَمَ ‎ማለትም "ተረጎመ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ትርጉም"translation" ማለት ነው፥ "ሙተርጂም" مُتَرْجِم ወይም "ተርጁማን" تَرْجُمَان‎ ማለት ደግሞ "ተርጓሚ"translator" ማለት ነው። የሙተርጂም ወይም የተርጁማን ብዜት "ሙተርጂሙን" مُتَرْجِمُون ወይም "ተራጂም" تَرَاجِيم ማለትም "መተርጉማን" ነው። ለምሳሌ ቁርኣንን ወደ ሌላ ቋንቋ የመተርጎም ሥራ "ተርጂም" تَرْجِم ይባላል። የቅዱስ ቁርኣን ትርጉም አሳቡ እንጂ ቃላቱ አይተረጎምም፥ ከባድ ነው። በዐረቢኛ አቻ ቃል ሳይገኝ ሲቀር ወይም ሌላ አንቀጽ ላይ የተብራራ አንቀጽ ሆኖ ሲገኝ የዐማርኛ ተርጓሚዎች በቅንፍ የማስቀመጥ ልምድ አላቸው። ስለዚህ የቅዱስ ቁርኣን ትርጉም "ተለዋዋጭ አቻ"dynamic equivalence" ትርጉም እንጂ "መደበኛ አቻ"formal equivalence" ትርጉም ስለሌለው የዐማርኛ መተርጉማን በቅንፍ ማስቀመጣቸው የአሳብ ትርጉምን ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው።
የተሰናኘ ስንኝ"syntax" ማኅበረሰቡ ሊረዳው በሚችል መልኩ መድረስ ይችላል፥ ይህንን ስንኝ ቃልን በቃል የመተርጎም ሥራ "የቃል ትርጉም"metaphrase or word-for-word translation" ሲባል፥ ቃልን በአሳብ የመተርጎም ሥራ ደግሞ "የአሳብ ትርጉም"paraphrase or Sense-for-sense translation" ይባላል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የከለር ልዩነት ውበት ነው!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

30፥22 ሰማያትንና ምድርንም መፍጠሩ፣ የቋንቋዎቻችሁ እና *”የመልኮቻችሁም መለያየት፣ ከአስደናቂ ተዓምራቶቹ ነው”*፡፡ በዚህ ውስጥ *”ለዐዋቂዎች ተዓምራቶች አሉበት”*፡፡ وَمِنْ ءَايَٰتِهِۦ خَلْقُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَٱخْتِلَٰفُ أَلْسِنَتِكُمْ وَأَلْوَٰنِكُمْ ۚ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَٰتٍۢ لِّلْعَٰلِمِينَ

“አደም” آدَم የሚለው ቃል 25 ጊዜ በቁርኣን የመጣ ሲሆን “አዳም” ማለትም “አፈር” “መሬት” “ቀይ” ወይም “ሰው” ከሚል ሴማዊ ቃል የመጣው ነው፤ አላህ አደምን የፈጠረው ከምድር አፈር ነው፦
15:28 ጌታህም ለመላእክት ባለጊዜ አስታውስ፡፡ *እኔ ሰውን ከሚቅጨለጨል ሸክላ ከሚገማ ጭቃ እፈጥራለሁ*፡፡ وَإِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي خَالِقٌ بَشَرًا مِّن صَلْصَالٍ مِّنْ حَمَإٍ مَّسْنُونٍ
38:71 ጌታህ «ለመላእክት እኔ ሰውን ከጭቃ ፈጣሪ ነኝ ባለ ጊዜ» አስታውስ፡፡ إِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي خَالِقٌ بَشَرًا مِّن طِينٍ
71:17 አላህም *ከምድር ማብቀልን አበቀላችሁ*። وَاللَّهُ أَنبَتَكُم مِّنَ الْأَرْضِ نَبَاتًا
71፥18 *ከዚያም በውስጧ ይመልሳችኋል። ማውጣትንም ያወጣችኋል*። ثُمَّ يُعِيدُكُمْ فِيهَا وَيُخْرِجُكُمْ إِخْرَاجًا
20፥55 *ከእርሷ ከምድር ፈጠርናችሁ፤ በእርሷም ውስጥ እንመልሳችኋለን፤ ከእርሷም በሌላ ጊዜ እናወጣችኋለን*። مِنْهَا خَلَقْنَاكُمْ وَفِيهَا نُعِيدُكُمْ وَمِنْهَا نُخْرِجُكُمْ تَارَةً أُخْرَىٰ

አላህ ምድር ላይ የተለያየ ከለር አብቅሏል፤ ከአፈር ብዙ ዓይነቶችም ቀለማት አድርጎ አበቀለን፦
50፥7 ምድርንም ዘረጋናት፡፡ በእርሷም ውስጥ ጋራዎችን ጣልንባት፡፡ በውስጧም ከሚያስደስት *”ዓይነት ሁሉ አበቀልን”*፡፡ وَٱلْأَرْضَ مَدَدْنَٰهَا وَأَلْقَيْنَا فِيهَا رَوَٰسِىَ وَأَنۢبَتْنَا فِيهَا مِن كُلِّ زَوْجٍۭ بَهِيجٍۢ
78፥7 *”ብዙ ዓይነቶችም”* አድርገን ፈጠርናችሁ፡፡ وَخَلَقْنَٰكُمْ أَزْوَٰجًۭا
71፥17 አላህም *”ከምድር ማብቀልን አበቀላችሁ”*፡፡ وَٱللَّهُ أَنۢبَتَكُم مِّنَ ٱلْأَرْضِ نَبَاتًۭا
30፥22 ሰማያትንና ምድርንም መፍጠሩ፣ የቋንቋዎቻችሁ እና *”የመልኮቻችሁም መለያየት፣ ከአስደናቂ ተዓምራቶቹ ነው”*፡፡ በዚህ ውስጥ *”ለዐዋቂዎች ተዓምራቶች አሉበት”*፡፡ وَمِنْ ءَايَٰتِهِۦ خَلْقُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَٱخْتِلَٰفُ أَلْسِنَتِكُمْ وَأَلْوَٰنِكُمْ ۚ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَٰتٍۢ لِّلْعَٰلِمِينَ

አላህ አደምን ከተለያየ የአፈር አይነት መፍጠሩ በዘሮቹ የቀለም ልዩነት ለማኖር ነው፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3213
አቡ ሙሳ እንደተረከው የአላህ መልክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ከፍ ያለው አላህ አደምን ከጭብጥ አፈር ፈጠረው፤ እርሱም ከሁሉም የምድር ክፍል ወስዶ ፈጠረው፤ ስለዚህ የአደም ልጆች አንዳንዶቹ ቀይ፣ ነጭ፣ ጥቁር፣ ጠይም ወዘተ…ሆኑ። عَنْ أَبِي مُوسَى الأَشْعَرِيِّ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ إِنَّ اللَّهَ تَعَالَى خَلَقَ آدَمَ مِنْ قَبْضَةٍ قَبَضَهَا مِنْ جَمِيعِ الأَرْضِ فَجَاءَ بَنُو آدَمَ عَلَى قَدْرِ الأَرْضِ فَجَاءَ مِنْهُمُ الأَحْمَرُ وَالأَبْيَضُ وَالأَسْوَدُ وَبَيْنَ ذَلِكَ وَالسَّهْلُ وَالْحَزْنُ وَالْخَبِيثُ وَالطَّيِّبُ ‏”‏

ሰውነታችን ውስጥ ካርበን፣ አይረን፣ ሃይድሮጅን፣ ናይትሮጅን፣ ካልሲየም፣ ማግኒዝየም፣ ፓታሺየም፣ ፎስፎረስ፣ ሰልፈር፣  ኮፐር፣ ዚንክ መኖራቸው በራሱ ከአፈር መሰራታችን ማስረጃዎች ናቸው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የእግዚአብሔር ልጅ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

18፥4 *እነዚያንም፦ “አላህ ልጅን ይዟል” ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት አወረደው*፡፡ وَيُنذِرَ الَّذِينَ قَالُوا اتَّخَذَ اللَّهُ وَلَدًا

ክርስቲያኖች ኢየሱስ “የእግዚአብሔር ልጅ” ነው ይላሉ፤ “ልጅ” ማለት ምን ማለት ነው? ስንላቸው፦ “አብን አህሎና መስሎ ከአብ “ባህርይ ዘእም-ባህርይ አካል ዘእም-አካል” ማለትም ከባህርይው ባህርይ ወስዶ ከአካሉ አካሉን ወስዶ ተወለደ” ይሉናል። እረ ከሰማናቸው፦ “አምላክ ዘእም-አምላክ ማለትም ከአምላክ የተገኘ አምላክ” ይሉናል። ይህ ኑባሬአዊ እሳቤ”ontological sense” ነው፤ ከእዚህ እሳቤ ቁርኣን በተቃራኒው፦ “አላህ ወለደ” ያሉ በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው፤ አላህ አልወለደም፤ አልተወለደምም፤ እንደውም አላህ ቁርኣን ካወረደበት ምክንያት አንዱ እነዚያንም፦ “አላህ ልጅን ይዟል” ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት ነው፦
37፥152 ፦ *“አላህ ወለደ” አሉ፤ እነርሱም በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው*፡፡ وَلَدَ اللَّهُ وَإِنَّهُمْ لَكَاذِبُونَ
112፥3 *አልወለደም፤ አልተወለደምም*፡፡ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ
18፥4 *እነዚያንም፦ “አላህ ልጅን ይዟል” ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት አወረደው*፡፡ وَيُنذِرَ الَّذِينَ قَالُوا اتَّخَذَ اللَّهُ وَلَدًا

ይህንን የቁርኣን እሳቤ ካየን ዘንዳ ባይብል ላይ እግዚአብሔር አባት መባሉ “አስገኚ” ወይም “ፈጣሪ” በሚል ፍካሬአዊ እሳቤ “ideological sense” መጥቷል፦
ሚልክያስ 2፥10 ለሁላችን *”አንድ አባት”* ያለን አይደለምን? *አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን*?
ዮሐንስ 8፥41 *አንድ አባት* አለን *እርሱም እግዚአብሔር ነው*፡ አሉት።
ኤፌሶን 4፥6 ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር *አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ*።

ለምሳሌ መላእክት መናፍስት ተብለዋል፤ እግዚአብሔር የመናፍስት አባት ነው። መናፍስቱ መላእክት የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው፦
ዕብራውያን 12፥9 እንዴትስ ይልቅ *ለመናፍስት አባት* አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር በተገባን?
ዕብራውያን 1፥14 *ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?*
ኢዮብ 38፥7 አጥቢያ ኮከቦች በአንድነት ሲዘምሩ፥ *የእግዚአብሔርም ልጆች* ሁሉ እልል ሲሉ፥

መላእክት የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉት ያለ እናት እና ያለ አባት ስለፈጠራቸው እንደሆነ ቅቡል ነው፤ አዳምም የእግዚአብሔር ልጅ ተብሏል፦
ሉቃስ 3፥38 የሴት ልጅ፥ የአዳም ልጅ፥ *የእግዚአብሔር ልጅ*።

አዳም የእግዚአብሔር ልጅ የተባለው ያለ እናት እና ያለ አባት ስለፈጠረው እንደሆነ እሙን ነው፤ ታዲያ ያለ አባት በእናት ብቻ የተፈጠረው ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ቢባል ምን ይደንቃል? ከማርያም ተጸንሶ የተወለደው ሰው መሆኑን አንርሳ፦
ሉቃስ 1፥35 ስለዚህ ደግሞ *ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል*።
ገላትያ 4 ፥4 ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ *እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ*፤

ማርያም የወለደችው መለኮትን ሳይሆን ሰው ብቻ ነው፤ ያም ሰው የእግዚአብሔር ልጅ መባሉ ፈጣሪ ያለ አባት ከእርሷ መፍጠሩን ያሳያል። አይ እግዚአብሔር ኢየሱስን ወለደው ይሉናል፦
መዝሙር 2፥7 ትእዛዙን እናገራለሁ፤ *እግዚአብሔር አለኝ። አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ “ወለድሁህ”*።
ዕብራውያን 1:5 ከመላእክትስ። *እግዚአብሔር አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ “ወልጄሃለሁ”*፥ (አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ጭራሽ ይህ ጥቅስ “ዛሬ” የምትለዋ ቃል መነሻ ጊዜን ታመለክታለች፣ ይህም የኢየሱስ መፈጠር በጊዜ ውስጥ መሆኑን ያሳያል፤ ሲቀጥል እዚህ ጥቅስ ላይ እግዚአብሔር ኢየሱስን፦ “አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ” ብሏል ተብሏል፤ ይህ የሚያሳየው ኢየሱስ “አንተ” ብሎ ካናገረው እግዚአብሔር የተለየ መሆኑን ያሳያል፣ እግዚአብሔር ለኢየሱስ “አባት እሆነዋለው” ኢየሱስ ለእግዚአብሔር “ልጅ ይሆነኛል” ብሏል ተብሏል” ሲሰልስ “ወልጄሃለሁ” የሚለው ቃል “ጌኔካ” γεγέννηκά ሲሆን “ጌኑስ” γένος ማለትም “ወለደ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን በፍካሬአዊ ትርጉም “ፈጠረ” ሲሆን አይሁዳውያን አምላክ ፆታ ስለሌለውን “መወለድ” ማለት “መፈጠር” ነው ብለው ያምናሉ፤ ምክንያቱን ተራራ እንደተወለደ ስለሚናገር፤ ያ ማለት ተራራ ተሰራ ማለት ነው፦
አሞፅ 4:13 እነሆ፥ *”ተራሮችን የሠራ”*፥
መዝሙር 90:2 *”ተራሮች ሳይወለዱ”*፥ בְּטֶרֶם, הָרִים יֻלָּדו
ግሪክ ሰፕቱአጀንት፦
πρὸ τοῦ ὄρη γενηθῆναι καὶ πλασθῆναι τὴν γῆν καὶ τὴν οἰκουμένην,

በዕብራይስጡ “ዩላዱ” יֻלָּדו ማለት “ሳይወለዱ” ማለት ነው። “ሳይወለዱ” የሚለው ፍካሬአዊ ቃል በእማሬያዊ ቃል “ሳይፈጠሩ” ማለት ነው። ግሪክ ሰፕቱአጀንት ላይ ደግሞ በተመሳሳይ “ጌኒቲና” γενηθηναι ማለትም “ሳይወለዱ” የሚለው በተመሳሳይ “ጌኑስ” γένος ማለትም “ወለደ” ከሚል ግስ የመጣ ነው፤ “ወለደ” ማለት “ፈጠረ” ማለት መሆኑን “የወለደህን አምላክ” የሚለው ቃል “የፈጠረውን አምላክ” በሚል ተለዋዋጭ ቃል መምጣቱ ነው፦
ዘዳግም 32፥18 *የወለደህን አምላክ ተውህ*፥ NIV
ዘዳግም 32፥15 ይሹሩን ወፈረ፥ ረገጠ፤ ወፈረ፥ ደነደነ፥ ሰባ፤ *የፈጠረውንም አምላክ ተወ*፤ NIV

“ይሽሩ” የእስራኤላውያን የቁልምጫ ስም ነው፤ አምላክ እስራኤላውን “ወለደ” ወይስ “ፈጠረ” ? አይ ፈጣሪ ጾታ ስለሌለው በእማሬአዊ ቃል ወለደ ማለት ሳይሆን በፍካሬአዊ ቃል ፈጠረ ለማለት ነው ከተባለ እንግዲያውስ ከላይ ያለውንም በዚህ ስሌትና ቀመር ተረዱት። መወለድ መፈጠር ባይሆን ኖሮ ሰማይንና ምድር ፍጥረት ሆኖ ሳለ “ልደት” ባልተባለ ነበር፤ ስለ ሰማይንና ምድር አፈጣጠር የሚናገረው መጽሐፍ “ዘፍጥረት” ይባላል፤ “ፍጥረት” በሚል ቃል ላይ ያለው መነሻ ቅጥያ “ዘ’ አያያዥ መስተዋድድ “የ” ማለት ነው፤ “የፍጥረት” ማለት ነው፤ በግዕዙ አርስት ላይ “ዘልደት” ይባላል፦
ዘፍጥረት 2፥4 እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድርን ባደረገ ቀን፥ በተፈጠሩ ጊዜ *”የሰማይና የምድር ልደት”* ይህ ነው።
ግዕዙ፦
ዝንቱ *”ፍጥረተ ሰማይ ወምድር”* ዘምአመ ኮነት ዕለት አንተ ባቲ ገብረ እግዚአብሔር ሰማየ ወምድረ።
ግሪክ ሰፕቱአጀንት፦
Αὕτη ἡ βίβλος γενέσεως οὐρανοῦ καὶ γῆς, ὅτε ἐγένετο· ᾗ ἡμέρᾳ ἐποίησε Κύριος ὁ Θεὸς τὸν οὐρανὸν καὶ τὴν γῆν

“ጀነሲዋስ” γενέσεως ማለት “ልደት” ማለት ነው፤ “Genesis” የሚለው የኢንግሊዝኛው ስያሜ “ጀነሲስ” γένεσις ከሚለው ከግሪኩ ቃል የመጣ ነው፤ መቼም ሰማይና ምድር ልደት አለው ሲባል ፈጣሪ ወለደው ማለት ሳይሆን መፍጠሩን የሚያሳይ ስለሆነ ግዕዙ፦ “ፍጥረተ ሰማይ ወምድር” ማለት “የሰማይና የምድር ፍጥረት” ማለት ነው፤ “ልደት” ማለት “ፍጥረት” ማለት ስለሆነ “አዲስ ፍጥረት” የሚለውን ተክቶ “አዲስ ልደት” ተብሏል፦
2ኛ ቆሮንቶስ 5፥17 ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን *”አዲስ ፍጥረት”* ነው።
ቲቶ 3፥5 እንደ ምሕረቱ መጠን *”ለአዲስ ልደት”* γένεσις በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥
ታዲያ ኢየሱስ ልደት አልነበረውምን? ልደቱ ግን ከመንፈስ ቅዱስ በመጸነስ ነው፤ ፈጣሪ ያለ ወንድ ዘር ስለፈጠረው ልደት አለው፤ ዓለም ሳይፈጠር በነበረው የቀድሞ ዕቅዱ ከድንግል ማርያም ማህጸን ፈጠረው፦
ማቴዎስ 1፥18 የኢየሱስ ክርስቶስም *”ልደት”* γένεσις እንዲህ ነበረ። እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች።
መዝሙር 110፥3 ከአንተ ጋር ቀድሞ በኃይልህ ቀን፥ በቅዱሳን ብርሃን፥ ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ ከማህጸን ወለድሁህ። μετὰ σοῦ ἡ ἀρχὴ ἐν ἡμέρᾳ τῆς δυνάμεώς σου ἐν ταῖς λαμπρότησι τῶν ἁγίων σου· ἐκ γαστρὸς πρὸ ἑωσφόρου ἐγέννησά σε.

የተወለደው በኃይሉ ቀን ነው፤ የቅዱሳን ብርሃን በሆነው በመንፈስ ቅዱስ ነው፤ ይህ የግሪክ ሰፕቱጀንት እንጂ የማሶሬቲኩ ላይ ቃላቱ የለም። ከማርያም ማህጸን “ወለድሁህ” ማለት “ፈጠርኩ” ማለት ካልሆነ ችግር ይፈጠራል። ሃይማኖተ-አበው ላይ የቂሳሪያው ባስልዮስ “ወለደኝ” ማለት “ፈጠረኝ” ማለት ነው ብሎ ፍርጥ አድርጎ ነግሮናል፦
ሃይማኖተ-አበው ዘባስልዮስ ምዕራፍ 32 ቁጥር 18
ግዕዙ፦
*”ወለደኒ ይተረጎም በወልደ እግዚአብሔር ወብሂለ ፈጠረኒ በእንተ ትስብእቱ”*
ትርጉም፦
*”ወለደኝ” ማለት የእግዚአብሔር ልጅ ስለመሆኑ “ፈጠረኝ” ማለትም ሰው ስለ መሆኑ ይተረጎማል”*

አንዳንድ ቂሎች “መወለድ” ከአብ “መውጣት” ነው ይላሉ፤ ምነው መንፈስ ቅዱስ ከአብ የሚወጣ ነው ትሉ የለ እንዴ? ለምን መንፈስ ቅዱስን የአብ ልጅ አትሉትም? አይ “መውጣት” ማለት “መስረጽ” ነው ካላችሁ ለምንስ ወልድን ከአብ የሰረጸ ነው አትሉትም? ምክንያቱም ወልድም ከአብ የወጣ ነው ስለሚል፤ አይ መውጣት መላክ ማለት ነው ካላችሁ ጥሩ። ካልሆነ ልጅ ማለት፦ “አብን አህሎና መስሎ ከአብ ባህርይ ዘእም-ባህርይ አካል ዘእም-አካል ማለትም ከባህርይው ባህርይ ወስዶ ከአካሉ አካሉን ወስዶ ተወለደ፤ አምላክ ዘእም-አምላክ ማለትም ከአምላክ የተገኘ አምላክ” ካላችሁ ይህንን እሳቤ አይደለም ቁርኣን ባይብላችሁም አይደግፋችሁ። በዚህ ስሌት ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል፦
19፥35 *ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል*፡፡ مَا كَانَ لِلَّهِ أَن يَتَّخِذَ مِن وَلَدٍ ۖ سُبْحَانَهُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ
2፥116 *አላህም ልጅ አለው አሉ፡፡ ከሚሉት ጥራት ተገባው፡፡ አይደለም በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ ሁሉም ለእርሱ ታዛዦች ናቸው*፡፡ وَقَالُوا۟ ٱتَّخَذَ ٱللَّهُ وَلَدًۭا ۗ سُبْحَٰنَهُۥ ۖ بَل لَّهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ ۖ كُلٌّۭ لَّهُۥ قَٰنِتُونَ
2፥117 ሰማያትንና ምድርን ያለብጤ ፈጣሪ ነው፤ *ነገርንም ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው፡- «ኹን» ነው፤ ወዲያውም ይኾናል*፡፡ بَدِيعُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ وَإِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም