ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
69 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
የቁርኣን ትንቢት

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

36፥36 ያ ምድር ከምታበቅለው፣ ከራሶቻቸውም፣ *ከማያውቁትም ነገር ጥንዶችን ሁሏንም የፈጠረ ጥራት ይገባው*፡፡ سُبْحَانَ الَّذِي خَلَقَ الْأَزْوَاجَ كُلَّهَا مِمَّا تُنبِتُ الْأَرْضُ وَمِنْ أَنفُسِهِمْ وَمِمَّا لَا يَعْلَمُونَ

“ዘውጅ” زَوْج የሚለው ቃል. "ዘወጀ" زَوَّجَ ማለትም "ተጠናዳ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ጥንድ” “ባል” “ሚስት” ተብሎ ተቀምጧል፦
58:1 አላህ የዚያችን *በባልዋ* ነገር የምትከራከርህንና ወደአላህ የምታስሙተውን ቃል በእርግጥ ሰማ። قَدْ سَمِعَ ٱللَّهُ قَوْلَ ٱلَّتِى تُجَٰدِلُكَ فِى زَوْجِهَا وَتَشْتَكِىٓ إِلَى ٱللَّهِ وَٱللَّهُ يَسْمَعُ تَحَاوُرَكُمَآ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ سَمِيعٌۢ بَصِيرٌ
7:19 አዳምም ሆይ! አንተም *ሚስትህም* ከገነት ተቀመጡ፤ وَيَٰٓـَٔادَمُ ٱسْكُنْ أَنتَ وَزَوْجُكَ ٱلْجَنَّةَ فَكُلَا مِنْ حَيْثُ شِئْتُمَا وَلَا تَقْرَبَا هَٰذِهِ ٱلشَّجَرَةَ فَتَكُونَا مِنَ ٱلظَّٰلِمِينَ
35:11 አላህም ከዐፈር፣ ከዚያም ከፍትወት ጠብታ ፈጠራችሁ፤ *ከዚያም ጥንዶች አደረጋችሁ*፤ وَٱللَّهُ خَلَقَكُم مِّن تُرَابٍۢ ثُمَّ مِن نُّطْفَةٍۢ ثُمَّ جَعَلَكُمْ أَزْوَٰجًۭا
53:45 እርሱም *ሁለቱን ዓይነቶችን ወንድ እና ሴትን ፈጠረ*። وَأَنَّهُۥ خَلَقَ ٱلزَّوْجَيْنِ ٱلذَّكَرَ وَٱلْأُنثَىٰ

“ዘውጀይኒ” زَّوْجَيْنِ ሙሰና ሲሆን ሁለት የወንድ እና የሴት ዓይነቶች በሚል መጥቷል፥ “ባልዋ” ለሚለው ቃል የገባው “ዘውጂሃ” زَوْجِهَا መሆኑ እና “ሚስትህ” ለሚለው ቃል የገባው ደግሞ “ዘውጅከ” َزَوْجُكَ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። "ተዝዊጅ" تَزْوِيج ማለት በራሱ "ጥንድነት" ማለት ሲሆን "ዘዋጅ" زَوَاج ማለት ደግሞ "ጋብቻ" "ሰርግ" ማለት ነው። እዚህ ድረስ ከተግባባን አምላካችን አላህ ለእኛ ከእጽዋት ልክ እንደ ሰው የተባእት እና የእንስት ህዋስ”gamete” ፈጥሯል። አላህ በዕፅዋት መካከል ጥንድ የሆኑ ተቃራኒ ጾታዎች እንዳሉ ለማመልከት “ዘውጀይኒ” زَوْجَيْنِ በማለት ይናገራል፦
13፥3 እርሱም ያ ምድርን የዘረጋ በእሷም ተራራዎችን እና ወንዞችን ያደረገ *በውስጧም "ከ"ፍሬዎች ሁሉ ሁለት ሁለት ጥንዶችን ያደረገ ነው*፡፡ ሌሊትን በቀን ይሸፍናል፡፡ *በዚህም ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች ታምራቶች አሉ*፡፡ وَهُوَ الَّذِي مَدَّ الْأَرْضَ وَجَعَلَ فِيهَا رَوَاسِيَ وَأَنْهَارًا ۖ وَمِن كُلِّ الثَّمَرَاتِ جَعَلَ فِيهَا زَوْجَيْنِ اثْنَيْنِ ۖ يُغْشِي اللَّيْلَ النَّهَارَ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ

“ኩል” كُلٌّ ማለትም “ሁሉ” የሚለው ቃል ፍጹማዊ “Absolute” ሆኖ ሲመጣ “ሙጥለቅ” مُطْلَق ሲባል፥ በአንጻራዊ “Relative” ሆኖ ሲመጣ ደግሞ “ቀሪብ” قَرِيب‎ ይባላል፥ እዚህ አንቀጽ ላይ "ኩል" ቀሪብ ሆኖ የምናውቀው "ሁሉ" በሚለው ገላጭ ቅጽል መነሻ ላይ "ሚን" مِن ማለትም "ከ" የሚል መስተዋድድ መኖሩ ነው። "ከ"ፍሬዎች ሁሉ" ማለት እና "ፍሬዎች ሁሉ" ማለት ሁለት ለየቅል ትርጉም አላቸው፥ ከፍራፍሬዎች መካከል ጥንድ ያልሆኑ በከፊል መኖራቸው ይህንኑ ያሳያል። ነቢያችን”ﷺ” በተላኩበት ጊዜ ላይ "ዕፅዋት ጾታ አላቸው" ብሎ ማንም ሰው ዐያውቅም ነበር፥ በዚህ ጊዜ አምላካችን አላህ ሁሉን ዐዋቂ በመሆኑ “ዘውጀይኒ” በማለት ዕፅዋት ጥንዶች እንደሆኑ ነግሮናል፦
36፥36 ያ ምድር ከምታበቅለው፣ ከራሶቻቸውም፣ *ከማያውቁትም ነገር ጥንዶችን ሁሏንም የፈጠረ ጥራት ይገባው*፡፡ سُبْحَانَ الَّذِي خَلَقَ الْأَزْوَاجَ كُلَّهَا مِمَّا تُنبِتُ الْأَرْضُ وَمِنْ أَنفُسِهِمْ وَمِمَّا لَا يَعْلَمُونَ

"ከማያውቁትም ነገር ጥንዶችን" ማለት በቁርኣን መውረድ ጊዜ የዕጽዋት ጥንድነት ዐለመታወቁን ያሳያል። አምላካችን አላህ ጊዜው ሲደርስ በ 19ኛው ክፍለ ዘመን ላይ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች ታምራት ይሆን ዘንድ ዕፅዋት ጾታ እንዳላቸው ዐሳውቆናል። “ጋይኒ” γυνή ማለት “ሴቴ” ማለት ሲሆን ይህቺ የዕፅዋት እንቁላል ህዋስ”gynoecious” በሥነ-ሕይወት ጥናት “ካርፔልስ”carpels” ትባላለች፥ “አንድሮ” ἀνήρ ማለት “ወንዴ” ማለት ሲሆን የዕፅዋት የዘር ህዋስ”Androecium” በሥነ-ሕይወት ጥናት “ስቴመንስ”stamens” ይባላል። ቁርኣን ከያዛቸው መካከል “አል-ገይቡል ሙሥተቅበል” ٱلْغَيْب ٱلْمُسْتَقْبَل ማለትም “መጻእያት የሩቅ ወሬ” ነው፥ ይህንን ትንቢት ከጊዜ በኋላ በእርግጥ ታውቁታላችሁ ባለን መሠረት ዛሬ በዘመናችን ዐውቀነዋል፦
38፥88 *«ትንቢቱንም ከጊዜ በኋላ በእርግጥ ታውቁታላችሁ፡፡* وَلَتَعْلَمُنَّ نَبَأَهُ بَعْدَ حِينٍ
6፥67 *ለትንቢት ሁሉ የሚደርስበት መርጊያ አለው፡፡ ወደፊትም ታውቁታላችሁ*፡፡ لِّكُلِّ نَبَإٍ مُّسْتَقَرٌّ ۚ وَسَوْفَ تَعْلَمُونَ

አምላካችን አላህ የነገረን "ከፍሬዎች ሁሉ ሁለት ሁለት ጥንዶችን" መሆናቸውን ብቻ ሳይሆን በዕጽዋት ውስጥ "ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች ታምራቶች አሉ" ይህንን ታምራት "ወደፊት ያሳያችኋል፥ ታውቁታላችሁ" ብሎ በነገረን መሠረት ዛሬ ይህንን ዐይተንማል፥ ዐውቀንማል። ምስጋናም ለአላህ ነው፦
13፥3 እርሱም ያ ምድርን የዘረጋ በእሷም ተራራዎችን እና ወንዞችን ያደረገ *በውስጧም "ከ"ፍሬዎች ሁሉ ሁለት ሁለት ጥንዶችን ያደረገ ነው*፡፡ ሌሊትን በቀን ይሸፍናል፡፡ *በዚህም ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች ታምራቶች አሉ*፡፡ وَهُوَ الَّذِي مَدَّ الْأَرْضَ وَجَعَلَ فِيهَا رَوَاسِيَ وَأَنْهَارًا ۖ وَمِن كُلِّ الثَّمَرَاتِ جَعَلَ فِيهَا زَوْجَيْنِ اثْنَيْنِ ۖ يُغْشِي اللَّيْلَ النَّهَارَ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ
6፥93 ምስጋናም ለአላህ ነው፡፡ *"ተዓምራቶቹን ወደፊት ያሳያችኋል፡፡ «ታውቁታላችሁ»* በላቸው፡፡ ጌታህም ከምትሠሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም፡፡ وَقُلِ الْحَمْدُ لِلَّهِ سَيُرِيكُمْ آيَاتِهِ فَتَعْرِفُونَهَا ۚ وَمَا رَبُّكَ بِغَافِلٍ عَمَّا تَعْمَلُونَ

ኢንሻሏህ ይቀጥላል.....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የቁርኣን ትንቢት

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

16፥8 *"ፈረሶችንም፣ በቅሎዎችንም፣ አህዮችንም ልትቀመጡዋቸውና ልታጌጡባቸው ፈጠረላችሁ፡፡ የማታውቁትንም ድንቅ ነገር ይፈጥራል"*፡፡ وَالْخَيْلَ وَالْبِغَالَ وَالْحَمِيرَ لِتَرْكَبُوهَا وَزِينَةً ۚ وَيَخْلُقُ مَا لَا تَعْلَمُونَ

ቁርአን በወረደበት ጊዜ ባሕላዊ መጓጓዣ ፈረሶች፣ በቅሎዎች፣ አህዮች ናቸው፦
16፥8 *"ፈረሶችንም፣ በቅሎዎችንም፣ አህዮችንም ልትቀመጡዋቸው እና ልታጌጡባቸው ፈጠረላችሁ፡፡ የማታውቁትንም ድንቅ ነገር ይፈጥራል"*፡፡ وَالْخَيْلَ وَالْبِغَالَ وَالْحَمِيرَ لِتَرْكَبُوهَا وَزِينَةً ۚ وَيَخْلُقُ مَا لَا تَعْلَمُونَ

”ልትቀመጡ” የሚለው ቃል “ሊተረከቡ” لِتَرْكَبُو ሲሆን “ረኪበ" رَكِبَ ማለትም “ጋለበ” “ተጓዘ” "ተሳፈረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ልትጋልቡ" "ልትጓዙ" "ልትሳፈሩ" የሚል ፍቺ አለው፦
40፥79 አላህ ያ ለእናንተ ግመልን ከብትንና ፍየልን ከእርሷ ከፊሏን *"ልትጋልቡ የፈጠረላችሁ ነው"*፡፡ ከእርሷም ትበላላችሁ፡፡ اللَّهُ الَّذِي جَعَلَ لَكُمُ الْأَنْعَامَ لِتَرْكَبُوا مِنْهَا وَمِنْهَا تَأْكُلُونَ
36፥42 ከመሰሉም በእርሱ *የሚሳፈሩበትን ለእነርሱ ፈጠርንላቸው"*፡፡ وَخَلَقْنَا لَهُم مِّن مِّثْلِهِ مَا يَرْكَبُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "የርከቡነ" يَرْكَبُونَ የሚለው ቃል "ረኪበ رَكِبَ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል። ቁርአን በወረደበት ጊዜ ፈረሶች፣ በቅሎዎች፣ አህዮች ለሰዎች መጋለቢያ፣ መጓጓዣ፣ መሳፈሪያ እንደ ነበሩ፥ በዚህ ዘመን አዲስ መጋለቢያ፣ መጓጓዣ፣ መሳፈሪያ ፈጥሯል። የዘመናችን መጓጓዣ“Trans-port” የሆኑትን የአየር መጓጓዣ”Air- port”፣ የየብስ መጓጓዣ”Geo-port” እና የባህር መጓጓዣ”Hydro-port” ተፈጥረዋል። የአየር መጓጓዣ እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 1799 ድኅረ-ልደት የንስር ወፍ ንድፍ ታይቶ አይሮፕላን የተሠራ ነው፣ የየብስ መጓጓዣ በ 1768 ድኅረ-ልደት አውቶ ሞቢል መኪና የፈረስ ንድፍ ታይቶ ሲሆን በተመሳሳይ ባቡርም በ 1550 ድኅረ-ልደት የአባጨጓሬ ንድፍ ታይቶ የተሠራ ነው፣ የባህር መጓጓዣ ባለ ሞተር “engine” መርከብ 1805 ድኅረ-ልደት የዶልፊን አሳ ንድፍ ታይቶ የተሠራ ነው። አምላካችን አላህ ይህ ክስተት ከመከሰቱ በፊት "የማታውቁትንም ድንቅ ነገር ይፈጥራል" ይለናል። "ይፈጥራል" ለሚለው የገባው ቃል "የኽሉቁ" يَخْلُقُ ሲሆን የወደፊት ግስ ሙሥተቅበል ነው። አላህ ኑሕ የሠራውን መርከብ "ፈጠርን" ብሏል፦
11፥37 አላህም፦ «በጥበቃችንና በትእዛዛችንም ሆነህ *መርከቢቱን ሥራ*፡፡ በእነዚያም በበደሉት ሰዎች ነገር አታናግረኝ እነሱ በእርግጥ ሰማጮች ናቸውና» አለው፡፡ وَاصْنَعِ الْفُلْكَ بِأَعْيُنِنَا وَوَحْيِنَا وَلَا تُخَاطِبْنِي فِي الَّذِينَ ظَلَمُوا ۚ إِنَّهُم مُّغْرَقُونَ
36፥41እኛም የቀድሞ ትውልዳቸውን *በተሞላች መርከብ* ውስጥ የጫን መኾናችን ለእነርሱ ምልክት ነው፡፡ وَآيَةٌ لَّهُمْ أَنَّا حَمَلْنَا ذُرِّيَّتَهُمْ فِي الْفُلْكِ الْمَشْحُونِ
36፥42 ከመሰሉም በእርሱ *የሚሳፈሩበትን ለእነርሱ ፈጠርንላቸው"*፡፡ وَخَلَقْنَا لَهُم مِّن مِّثْلِهِ مَا يَرْكَبُونَ

አላህ ኑሕ የሠራውን መርከብ "ፈጠርን" ካለ ዛሬ በዘመናችን ቁርኣን በወረደበት ጊዜ ያልነበሩትንና የማይታወቁትን ሰዎች የሠሩዋቸውን የአየር መጓጓዣ አይሮፕላን፣ የየብስ መጓጓዣ አውቶ ሞቢል መኪናና ባቡር፣ የባህር መጓጓዣ ባለ ሞተር “engine” መርከብ "ይፈጥራል" ብሎ ማስቀመጡ የሚያጅብ ነው። የሠው ሥራን እራሱ አላህ የፈጠረው ነው፥ “ፊዕል” فِعْل ማለት “ድርጊት”action” ማለት ሲሆን አራት ነገር ናቸው፥ እነርሱም፦ ጊዜ፣ ቦታ፣ ቁስ እና ነጻ ምርጫ ናቸው። እነዚህን ነገሮች የፈጠረው አላህ ነው፤ አላህ የነገር ሁሉ ፈጣሪ ነው፥ አላህ እኛንም እኛ የምንሠራውን ሁሉ የፈጠረ ነው፦
39፥62 *አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው*፡፡ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ
37፥96 *አላህ እናንተንም የምትሠሩትንም የፈጠረ ሲኾን*፡፡ وَاللَّهُ خَلَقَكُمْ وَمَا تَعْمَلُون

"የማታውቁትንም ድንቅ ነገር ይፈጥራል" መጻኢ የሩቅ ወሬ ስለሆነ ትንቢት ነው፦
38፥88 *«ትንቢቱንም ከጊዜ በኋላ በእርግጥ ታውቁታላችሁ፡፡* وَلَتَعْلَمُنَّ نَبَأَهُ بَعْدَ حِينٍ
6፥67 *ለትንቢት ሁሉ የሚደርስበት መርጊያ አለው፡፡ ወደፊትም ታውቁታላችሁ*፡፡ لِّكُلِّ نَبَإٍ مُّسْتَقَرٌّ ۚ وَسَوْفَ تَعْلَمُونَ

"ትንቢቱንም ከጊዜ በኋላ ወደፊት ታውቁታላችሁ" ብሎ በነገረን መሠረት የአየር መጓጓዣ አይሮፕላን፣ ጀት፣ ኢልኮፕተር፥ የየብስ መጓጓዣ አውቶ ሞቢል መኪና፣ ባቡር፣ ሜትሮ፣ ፔንደል፥ የባህር መጓጓዣ ባለ ሞተር መርከብ በዘመናችን ዐይተናል። አል-ሐምዱሊሏህ!
ኢንሻሏህ ይቀጥላል.....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የቁርኣን ትንቢት

ገቢር ሦስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

25፥6 *«ያ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለን ምስጢር የሚያውቀው አወረደው፡፡ እርሱ መሓሪ አዛኝ ነውና» በላቸው*፡፡ قُلْ أَنزَلَهُ الَّذِي يَعْلَمُ السِّرَّ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ إِنَّهُ كَانَ غَفُورًا رَّحِيمًا

"ዘራህ" ذَرَّة የሚለው ቃል "ደቂቅ" ንዑስ" "ኢምንት" "ብናኝ"Atom" ማለት ሲሆን ጥቃቅን ነገር ነው፦
99፥7 *የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሠራ ሰው ያገኘዋል*፡፡ فَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ خَيْرًا يَرَهُ
99፥8 *"የብናኝ ክብደት ያክልም ክፉን የሠራ ሰው ያገኘዋል"*፡፡ وَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ شَرًّا يَرَهُ

"ብናኝ" ለሚለው የገባው ቃል "ዘራህ" ذَرَّة መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። ዐረቦች ከጥቃቅን ፍጥረት አነስተኛ የሚሉት "ጉንዳን" ነበር። ነገር ግን ቁርኣኑ "ጉንዳን" ለሚለው ቃል የሚጠቀመው "ዘራህ" ذَرَّة ሳይሆን "ነምል" نَّمْل ነው፦
27፥18 *በጉንዳንም ሸለቆ በመጡ ጊዜ አንዲት ጉንዳን «እናንተ ጉንዳኖች ሆይ! ወደ መኖሪያዎቻችሁ ግቡ፡፡ ሱለይማንና ሰራዊቱ እነርሱ የማያውቁ ሲኾኑ አይሰባብሩዋችሁ» አለች*፡፡ حَتَّىٰ إِذَا أَتَوْا عَلَىٰ وَادِ النَّمْلِ قَالَتْ نَمْلَةٌ يَا أَيُّهَا النَّمْلُ ادْخُلُوا مَسَاكِنَكُمْ لَا يَحْطِمَنَّكُمْ سُلَيْمَانُ وَجُنُودُهُ وَهُمْ لَا يَشْعُرُونَ

ሲቀጥል "ጉንዳን" በሰማያትና በምድር ውስጥ አይገኝም። ብናኝ"Atom" ግን በሰማያትና በምድር ውስጥ አለ፦
34፥3 እነዚያ የካዱትም «ሰዓቲቱ አትመጣብንም» አሉ፡፡ በላቸው «አይደለም፤ ሩቁን ሁሉ ዐዋቂ በኾነው ጌታዬ እምላለሁ፡፡ በእርግጥ ትመጣባችኋለች፡፡ *"የብናኝ ክብደት ያክል እንኳ በሰማያትና በምድር ውስጥ ከእርሱ አይርቅም፡፡ ከይህ ያነሰም ኾነ የበለጠ የለም* በግልጹ መጽሐፍ ውስጥ የተመዘገበ ቢኾን እንጅ፡፡» وَقَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا لَا تَأْتِينَا السَّاعَةُ ۖ قُلْ بَلَىٰ وَرَبِّي لَتَأْتِيَنَّكُمْ عَالِمِ الْغَيْبِ ۖ لَا يَعْزُبُ عَنْهُ مِثْقَالُ ذَرَّةٍ فِي السَّمَاوَاتِ وَلَا فِي الْأَرْضِ وَلَا أَصْغَرُ مِن ذَٰلِكَ وَلَا أَكْبَرُ إِلَّا فِي كِتَابٍ مُّبِينٍ

እዚህ አንቀጽ ላይ በግልጹ መጽሐፍ በተጠበቀው ሰሌዳ ውስጥ ከብናኝ ያነሰም ኾነ የተለቀ ፍጥረት የተመዘገበ መሆኑን ፍትንትውና ቁልጭ አርጎ ያሳያል። "ዛሊከ" ذَٰلِكَ ማለትም "ይህ" የሚለው አመልካች ተውላጠ-ስም "ዘራህ" ذَرَّة የሚለውን ስም ተክቶ የመጣ ነው፥ ከአተም ያነሰ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለ ነገር ኤሌክትሮን፣ ፕሮቶን፣ ኒውትሮን ነው። ከአተም ያነሰ ነገር አለ ተብሎ ስለማይታመን "አቶም" ወይም "አተም" የሚለው ቃል እራሱ "አቶሞስ" ἄτομον ከሚል የግቲክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙ "የማይከፋፈል”indivisible” ማለት ነው። አቶም ሁሉም ቁስ የተገነባበት መሰረታዊ ንዑስ ነው፥ እስከ አስራ ዘጠነኛው ክፍለ-ዘመን ከአቶም ወደ ታች ፍጥረት አለ ተብሎ አይታመንም ነበር። የፊዚክስ ምሁር ጆን ዳልተን እንኳን አቶም በውስጡ ፍጥረት አለው ብሎ አያምንም ነበር፥ ነገር ግን እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 1897 ድኅረ-ልደት ላይ ጆን ቶምሶን፣ በ 1911 ድኅረ-ልደት ላይ ኤርነስት ራዘርፎርድ ወዘተ ከአተም ያነሱ የቁስ መጠን ክፍፍሎች“particle” አግኝተው ገለጡ። እነዚህም፦ ኤሌክትሮን፣ ፕሮቶን፣ ኒውትሮን፣ ፈርሚኦን፣ ሌፕቶን፣ ቦሶን፣ ፎቶን፣ ዲላቶን፣ ሳክሲኦን፣ አክሲኦን የመሳሰሉት ናቸው። በተለይ ኤሌክትሮን፣ ፕሮቶን እና ኒውትሮን በሁሉም ቁስ ላይ የሚገኙ ከአቶም በታች የሚገኙ ናቸው። እስከ 1897 ድኅረ-ልደት ድረስ ከአተም ወደ ታች ፍጥረት የለም ተብሎ ቢታመንም፣ አላህ ግን በቁርአን ከአቶም በታች ያሉት ፍጥረቶች በእውቀቱ መዝገብ ላይ ተጽፎ እንዳለ ነግሮናል። ከአተም በታች በሰማያትና በምድር ውስጥ ለምእመናን ሁሉ እርግጠኛ ታምራቶች አሉ፦
45፥3 *"በሰማያትና በምድር ውስጥ ለምእመናን ሁሉ እርግጠኛ ታምራቶች አሉ*። إِنَّ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ لَآيَاتٍ لِّلْمُؤْمِنِينَ
10፥6 ሌሊትና ቀን በመተካካታቸው አላህም *በሰማያትና በምድር ውስጥ በፈጠረው ሁሉ ለሚጠነቀቁ ሕዝቦች ታምራቶች አሉ*፡፡ إِنَّ فِي اخْتِلَافِ اللَّيْلِ وَالنَّهَارِ وَمَا خَلَقَ اللَّهُ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يَتَّقُونَ
ኤሌክትሮን፣ ፕሮቶን እና ኒውትሮን በአጽናፎቹ ውስጥ እና በራሳችን አካላት ውስጥ ያሉ ታምራቶች ናቸው፥ አላህ እነዚህ ታምራት ወደፊት እንደሚያሳየን እና እንደሚያሳውቀትን ቃል ገብቶልን ነበር፦
6፥93 ምስጋናም ለአላህ ነው፡፡ *"ተዓምራቶቹን ወደፊት ያሳያችኋል፡፡ «ታውቁታላችሁ»* በላቸው፡፡ ጌታህም ከምትሠሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም፡፡ وَقُلِ الْحَمْدُ لِلَّهِ سَيُرِيكُمْ آيَاتِهِ فَتَعْرِفُونَهَا ۚ وَمَا رَبُّكَ بِغَافِلٍ عَمَّا تَعْمَلُونَ
41፥53 እርሱም ቁርኣን እውነት መኾኑ ለእነርሱ እስከሚገለፅላቸው ድረስ *"በአጽናፎቹ ውስጥ እና በራሳቸውም ውስጥ ያሉትን ተዓምራቶቻችንን በእርግጥ እናሳያቸዋለን*"፡፡ ጌታህም እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ዐዋቂ መኾኑ አይበቃቸውምን? سَنُرِيهِمْ آيَاتِنَا فِي الْآفَاقِ وَفِي أَنفُسِهِمْ حَتَّىٰ يَتَبَيَّنَ لَهُمْ أَنَّهُ الْحَقُّ ۗ أَوَلَمْ يَكْفِ بِرَبِّكَ أَنَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ شَهِيدٌ

አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ዐዋቂ መኾኑ አይበቃንምን? ቁርኣን ሐቅ መሆኑ ለሁሉም የሚገለጸው የትንሳኤ ቀን ነው። ቁርኣን እውነት ሆኖ በመጣላቸው ጊዜ እነዚያ የካዱት፦ “ይህ ግልጽ ድግምት ነው” አሉ። ነገር ግን አላህ በትንሳኤ ቀን ስለ ቁርኣኑ፦ “ይህ እውነት አይደለምን? ብሎ ይጠይቃቸዋል፥ እነርሱም፦ “እውነት ነው፤ በጌታችን ይኹንብን” ይላሉ፦
46፥7 *”በእነርሱም ላይ አንቀጾቻችን ግልጾች ኾነው በተነበቡ ጊዜ እነዚያ እውነቱን በመጣላቸው ጊዜ የካዱት «ይህ ግልጽ ድግምት ነው» አሉ”*፡፡ وَإِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ آيَاتُنَا بَيِّنَاتٍ قَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا لِلْحَقِّ لَمَّا جَاءَهُمْ هَـٰذَا سِحْرٌ مُّبِينٌ
46፥34 *”እነዚያም የካዱት ሰዎች በእሳት ላይ በሚቀረቡ ቀን «ይህ እውነት አይደለምን?» ይባላሉ፡፡ «እውነት ነው፤ በጌታችን ይኹንብን» ይላሉ፡፡ አላህም «ትክዱ በነበራችሁት ምክንያት ቅጣቱን ቅመሱ» ይላቸዋል”*፡፡ وَيَوْمَ يُعْرَضُ الَّذِينَ كَفَرُوا عَلَى النَّارِ أَلَيْسَ هَـٰذَا بِالْحَقِّ ۖ قَالُوا بَلَىٰ وَرَبِّنَا ۚ قَالَ فَذُوقُوا الْعَذَابَ بِمَا كُنتُمْ تَكْفُرُونَ

ቁርኣን እውነት መኾኑ ለእነርሱ እስከሚገለፅላቸው እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ በአጽናፎቹ ውስጥ እና በራሳችን ውስጥ ያሉትን ተዓምራቶቹን በዘመናችን እያሳየን ነው፥ እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ማሳየቱ ይቀጥላል። ዛሬ የስሥ-ምርምር ጥናት ተመራማሪዎች በአጽናፎች ያሉትን ፈለኮች፣ ፕላኔቶች፣ ምህዳሮች፣ ፍኖተ-ሃሊብ፣ ክላስተሮች፣ አድማሳትን ወዘተ መርምረው አይተዋል። በራሶቻቸውም ያሉትን ሥነ-አካል"Physiology"፣ ሥነ-ልቦና"Psychology፣ ሥነ-ሕይወት"Biology፣ የወንድ ጾታ ጥናት"Andrology፣ የሴት ጾታ ጥናት"gynaecology" ወዘተ መርምረው አይተዋል። ይህን ቁርኣን በወረደበት ጊዜ የማይታሰብ ነው፥ ነገር ግን አላህ፦ "በአጽናፎቹ ውስጥ እና በራሳቸውም ውስጥ ያሉትን ተዓምራቶቻችንን በእርግጥ እናሳያቸዋለን" ብሎ ቃል በገባው መሠረት ተፈጽሟል። ቁርኣንስ ይህንን የሩቅ ወሬ ቀደም ብሎ እንዴት ሊይዝ ቻለ? መልሱ "ያ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለን ምስጢር የሚያውቀው አላህ ቁርኣንን ስላወረደው" ነው፦
25፥6 *«ያ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለን ምስጢር የሚያውቀው አወረደው፡፡ እርሱ መሓሪ አዛኝ ነውና» በላቸው*፡፡ قُلْ أَنزَلَهُ الَّذِي يَعْلَمُ السِّرَّ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ إِنَّهُ كَانَ غَفُورًا رَّحِيمًا

ኢንሻሏህ ይቀጥላል.....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ክርስቲያን

“ክርስቲያን” የሚለው ቃል “ክርስቲያኖስ” Χριστιανός ከሚል የግሪኩ ቃል የመጣ ነው። በግሪኩ አዲስ ኪዳን ሦስት ቦታ የሐዋርያት ሥራ 11፥26 የሐዋርያት ሥራ 26፥28 1ኛ ጴጥሮስ 4፥16 ይገኛል። በአማርኛ ባይብል ላይ አራት ቦታ የሐዋርያት ሥራ 11፥26 የሐዋርያት ሥራ 26፥28 1ኛ ጢሞቴዎስ 3፥6 1ኛ ጴጥሮስ 4፥16 ላይ ይገኛል።

“ክርስቲያኖስ” Χριστιανός ማለት ትርጉሙ “ክርስቶሶች” “ክርስቶሳውያን” “ቅቡዓን” ማለት ነው። ይህ ስም የወጣው በአንጾኪያ በፓጋኖቹ ለደቀመዛሙርቱ የወጣ የሽሙጥና የለበጣ ስም ነው እንጂ ክርስቲያን የሚለው መጠሪያ ነብያት ሆኑ ኢየሱስ ዐያውቁትም። ይህንን ጉዳይ የፕሮቴስታንት አስተማሪ ፓስተር ያሬድ ጥላሁን እና የኦርቶዶክስ መምህር ምሕረተ-አብ አሰፋ ፍርጥ አርገው እንቁጭን ይነግሩናል፥ እስቲ እናዳምጥ!

ተጨማሪ ትምህርት ለመከታተል እዚህ ጎራ ይበሉ፦
https://tttttt.me/Wahidcom
የቁርኣን ትንቢት

ገቢር አራት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

10፥92 *ዛሬማ፦ "ከኋላህ ላሉት ተዓምር ትሆን ዘንድ በድን ሆነህ ከባሕሩ እናወጣሃለን" ተባለ፡፡ ከሰዎችም ብዙዎቹ ከተዓምራታችን በእርግጥ ዘንጊዎች ናቸው*፡፡ فَالْيَوْمَ نُنَجِّيكَ بِبَدَنِكَ لِتَكُونَ لِمَنْ خَلْفَكَ آيَةً ۚ وَإِنَّ كَثِيرًا مِّنَ النَّاسِ عَنْ آيَاتِنَا لَغَافِلُونَ

"አል-የቂን" الْيَقِين ማለት "እርግጠኝነት" ማለት ነው፥ አል-የቂን ሦስት ደረጃዎች አሉት፥ እነርሱም፦ ዒልመል የቂን፣ ዐይነል የቂን፣ ሐቁል-የቂን ናቸው። "ዒልመል የቂን" عِلْمَ الْيَقِين ማለት የወደፊቱን ክንውን አምላካችን አላህ በነገረን ዕውቀት የምናረጋግጥበት ነው። "ዐይነል የቂን" عَيْنَ الْيَقِين ማለት አምላካችን አላህ ቀድሞ የነገረን ዕውቀት ጊዜ ደርሶ ሲከናወን በዓይናችን በማየት የምናረጋግጥበት ነው። "ሐቁል የቂን" حَقُّ الْيَقِين ማለት አምላካችን አላህ ቀድሞ የነገረን ዕውቀት ጊዜ ደርሶ ሲከናወን በሕዋሳችን አጣጥመን የምናረጋግጥበት ነው። እንደሚታወቀው አላህ በሙሣ ዘመን ለፈርዖን እና ለቤተሰቡ ማስጠንቀቂያ ተሰጧቸው ነበር፦
11፥97 *ወደ ፈርዖንና ወደ ሰዎቹ ላክነው፡፡ የፈርዖንንም ነገር ሕዝቦቹ ተከተሉ፡፡ የፈርዖን ነገርም ቀጥተኛ አልነበረም*፡፡ إِلَىٰ فِرْعَوْنَ وَمَلَئِهِ فَاتَّبَعُوا أَمْرَ فِرْعَوْنَ ۖ وَمَا أَمْرُ فِرْعَوْنَ بِرَشِيدٍ
54፥41 *"የፈርዖንንም ቤተሰቦች ማስጠንቀቂያዎች በእርግጥ መጡባቸው*፡፡ وَلَقَدْ جَاءَ آلَ فِرْعَوْنَ النُّذُرُ

ፈርዖን እና ቤተሰቡ ከአላህ የመጣውን መልእክት ሲያስተባብሉ እና የእስራኤልን ልጆች ሊያጠፉ ሲመጡ በባሕር ውስጥ ሰጠሙ፦
17፥103 ከምድርም ሊቀሰቅሳቸው አሰበ፡፡ *"እርሱን እና ከእርሱ ጋር የነበሩትንም ሰዎች ሁሉንም አሰጠምናቸው*፡፡ فَأَرَادَ أَن يَسْتَفِزَّهُم مِّنَ الْأَرْضِ فَأَغْرَقْنَاهُ وَمَن مَّعَهُ جَمِيعًا
2፥50 *በእናንተም ምክንያት ባሕሩን በከፈልን ጊዜ አስታውሱ፡፡ ወዲያውም አዳንናችሁ፡፡ የፈርዖንንም ቤተሰቦች እናንተ የምትመለከቱ ኾናችሁ አሰጠምናቸው*፡፡ وَإِذْ فَرَقْنَا بِكُمُ الْبَحْرَ فَأَنجَيْنَاكُمْ وَأَغْرَقْنَا آلَ فِرْعَوْنَ وَأَنتُمْ تَنظُرُونَ
10፥90 *የእስራኤልንም ልጆች ባሕሩን አሳለፍናቸው፡፡ ፈርዖንና ሰራዊቱም ወሰን ለማለፍና ለመበደል ተከተሏቸው፡፡ መስጠምም ባገኘው ጊዜ፡- «አመንኩ፡፡ እነሆ ከዚያ የእስራኤል ልጆች በርሱ ከአመኑበት በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ እኔም ከታዛዦቹ ነኝ» አለ*፡፡ وَجَاوَزْنَا بِبَنِي إِسْرَائِيلَ الْبَحْرَ فَأَتْبَعَهُمْ فِرْعَوْنُ وَجُنُودُهُ بَغْيًا وَعَدْوًا ۖ حَتَّىٰ إِذَا أَدْرَكَهُ الْغَرَقُ قَالَ آمَنتُ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا الَّذِي آمَنَتْ بِهِ بَنُو إِسْرَائِيلَ وَأَنَا مِنَ الْمُسْلِمِينَ

አምላካችን አላህ ለፈርዖን፦ "ከኋላህ ላሉት ተዓምር ትሆን ዘንድ በድን ሆነህ ከባሕሩ እናወጣሃለን" አለው፦
10፥92 *ዛሬማ፦ "ከኋላህ ላሉት ተዓምር ትሆን ዘንድ በድን ሆነህ ከባሕሩ እናወጣሃለን" ተባለ፡፡ ከሰዎችም ብዙዎቹ ከተዓምራታችን በእርግጥ ዘንጊዎች ናቸው*፡፡ فَالْيَوْمَ نُنَجِّيكَ بِبَدَنِكَ لِتَكُونَ لِمَنْ خَلْفَكَ آيَةً ۚ وَإِنَّ كَثِيرًا مِّنَ النَّاسِ عَنْ آيَاتِنَا لَغَافِلُونَ

"ዛሬ" የተባለው አላህ ለፈርዖን የተናገረበት ቀን ነው፥ ያኔ "ኑነጂከ" نُنَجِّيكَ ማለትም "እናወጣሃለን" ብሎት ትንቢት ተናግሮ ነበር፥ ይህ ዒልመል የቂን ነው። ለምን? በኃላ ላሉት ታምር ይሆን ዘንድ፥ ከሰዎችም ብዙዎቹ ከአላህ ታምራት በእርግጥ ዘንጊዎች ናቸው። አምላካችን አላህ "እናወጣሃለን" ብሎ በተናገረው መሠረት የፈርዖን በድን ከኤርትራ ባሕር እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 1975 ድኅረ-ልደት አውጥቶታል። ይህን የማውጣቱ መርሐ-ግብር የፈጸሙት ዶክተር ሞሪስ ሞካየ ናቸው፥ ይህ ዐይነል የቂን ነው። የፈርዖን በድንን ይቱብ ላይ ማየት ይቻላል፦
https://youtu.be/-dxDmbgEdcc

ይህ የአላህ ታምር ነው፥ በኃላ ላሉት ታምር ይሆን ዘንድ አላህ በዶክተር ሞሪስ ሞካየ አወጣው። አምላካችን አላህ ስለራሱ ፦ "ተዓምራቶቹን ወደፊት ያሳያችኋል፥ ታውቁታላችሁ" በል በማለት ቃል በገባልን መሠረት ለእኛ ታምር ይሆን ዘንድ የፈርዖን በድን ከኤርትራ ባሕር በማውጣት አሳይቶናል፥ ዐሳውቆናል። ምስጋናም ለአላህ ነው፦
6፥93 ምስጋናም ለአላህ ነው፡፡ *"ተዓምራቶቹን ወደፊት ያሳያችኋል፡፡ «ታውቁታላችሁ»* በላቸው፡፡ ጌታህም ከምትሠሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም፡፡ وَقُلِ الْحَمْدُ لِلَّهِ سَيُرِيكُمْ آيَاتِهِ فَتَعْرِفُونَهَا ۚ وَمَا رَبُّكَ بِغَافِلٍ عَمَّا تَعْمَلُونَ

ኢንሻሏህ ይቀጥላል.....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የቁርኣን ትንቢት

ገቢር አምስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

30፥3 *"በጣም ቅርብ በሆነችው ምድር፡፡ እነርሱም ከመሸነፋቸው በኋላ በእርግጥ ያሸንፋሉ"*፡፡ فِي أَدْنَى الْأَرْضِ وَهُم مِّن بَعْدِ غَلَبِهِمْ سَيَغْلِبُونَ

ሰዎች ነቢያችንን"ﷺ" ጥያቄ ለመጠየቅ ከመምጣታቸው በፊት አምላካችን አላህ፦ "የሥአሉነከ" يَسْأَلُونَكَ ማለትም "ይጠይቁሃል" በማለት ቀድሞ መልስ ይሰጣል። በጥያቄ ሲመጡ እውነተኛውን መልስ መስጠት የአላህ ድርሻ ነው፦
25፥33 *በጥያቄም አይመጡብህም እውነተኛውን መልስ መልካምን ፍችም የምናመጣልህ ብንኾን እንጅ*፡፡ وَلَا يَأْتُونَكَ بِمَثَلٍ إِلَّا جِئْنَاكَ بِالْحَقِّ وَأَحْسَنَ تَفْسِيرًا

የቁርኣን ደራሲ"author" የዓለማቱ ጌታ አላህ ለሚጠየቁት ጥያቄ መልስ በመስጠት የሬቅ ወሬ ወደ ነቢያችን"ﷺ" ያወርዳል፥ “አል-ገይብ” ٱلْغَيْب ማለት “የሩቅ ወሬ” “የሩቅ ሚስጥር” ማለት ሲሆን ከህዋስ ባሻገር ጥንት የተከሰተ፣ አሁን እየተከሰተ ያለ እና ወደ ፊት የሚከሰት ዕውቀት ነው፥ አላህ የሰማያትን እና የምድርን የሩቅ ሚስጥር ያውቃል። ይህንን የሩቅ ሚስጥር ለሚፈልገው መልእክተኛ ቢሆን እንጂ ለማንም ዐያሳውቅም፦
49፥18 *”አላህ የሰማያትንና የምድርን “ሩቅ ሚስጥር” ያውቃል”*። إِنَّ ٱللَّهَ يَعْلَمُ غَيْبَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ
72፥26 *«እርሱ ”የሩቅ ሚስጥር” ዐዋቂ ነው፡፡ በምስጢሩም ላይ አንድንም አያሳውቅም፡፡»* عَٰلِمُ ٱلْغَيْبِ فَلَا يُظْهِرُ عَلَىٰ غَيْبِهِۦٓ أَحَدًا
72፥27 *ከመልክተኛ ለወደደው ቢኾን እንጅ ለሌላ አይገልጽም*፡፡ إِلَّا مَنِ ٱرْتَضَىٰ مِن رَّسُولٍۢ

“አል-ገይብ” በሦስት ይከፈላል፥ እርሱም፦ አል-ገይቡል ማዲ፣ አል-ገይቡል ሙዷሪዕ እና አል-ገይቡል ሙሥተቅበል ነው። “አል-ገይቡል ማዲ” ٱلْغَيْب الْمَاضِي ማለት “ኀላፊያት የሩቅ ወሬ” ማለት ነው፥ ድርጊቱ ከዚህ በፊት አላፊ የሆነ ክስተት ነው። “አል-ገይቡል ሙዷሪዕ” ٱلْغَيْب ٱلْمُضَارِع ማለት “አሁናት የሩቅ ወሬ” ማለት ነው፥ ቁርኣን ሲወርድ ከህዋስ ባሻገት እየተፈጸመ ያለ ክስተት ነው። “አል-ገይቡል ሙሥተቅበል” ٱلْغَيْب ٱلْمُسْتَقْبَل ማለት “መጻእያት የሩቅ ወሬ” ማለት ነው፥ መጪው ክስተት ነው። ይህም ድርጊቱ ገና ያልተፈጸመ ወደፊት የሚከሰት ነው፥ በቁርኣን ተተንብዮ በነቢያችን"ﷺ" ዘመን ከተፈጸሙ ትንቢት አንዱ የሩም ጉዳይ ነው፦
30፥2 *"ሩም ተሸነፈች"*፡፡ غُلِبَتِ الرُّومُ
30፥3 *"በጣም ቅርብ በሆነችው ምድር፡፡ እነርሱም ከመሸነፋቸው በኋላ በእርግጥ ያሸንፋሉ"*፡፡ فِي أَدْنَى الْأَرْضِ وَهُم مِّن بَعْدِ غَلَبِهِمْ سَيَغْلِبُونَ
30፥4 *"በጥቂት ዓመታት ውስጥ ያሸንፋሉ፡፡ ትዕዛዙ በፊትም በኋላም የአላህ ነው፡፡ በዚያ ቀንም ምእመናን ይደሰታሉ"*፡፡ فِي بِضْعِ سِنِينَ ۗ لِلَّهِ الْأَمْرُ مِن قَبْلُ وَمِن بَعْدُ ۚ وَيَوْمَئِذٍ يَفْرَحُ الْمُؤْمِنُونَ

የአንጾኪያ ፍልሚያ የተጀመረው እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 613 ድኅረ-ልደት ነው፥ "አር-ሩም" الرُّوم የምትባለት የባዛንታይን ግዛት ስትሆን በጣም ቅርብ በሆነችው ምድር በፐርሺያን በ 614 ድኅረ-ልደት ተሸነፈች። ይህ አንቀጽ በዚሁ ጊዜ የወረደው በመካ ስለሆነ ሱራው እራሱ "መኪይ" ነው። አምላካችን አላህ፦ "እነርሱም ከመሸነፋቸው በኋላ በእርግጥ በጥቂት ዓመታት ውስጥ ያሸንፋሉ" ብሎ በተናገረው መሠረት ይህ ትንቢት በተነገረ በጥቂት 14 ዓመታት በ 628 ድኅረ-ልደት ሮማውያን ፐርሺያውያንን አሸንፈዋል። በወቅቱ ምእመናንም መለኮታዊ ቅሪት ያላቸው ክርስቶሳውያን የእሳት አምላኪዎች የሆኑትን ዞራስተሪያውያን በማሸነፋቸው ተደስተዋል።
እንግዲህ በቁርኣን ያለው ትንቢት ቢዘረዘር ብዙ ነው፥ ስለ ጀነት እና ጀሃነም ያለው የሩቅ ወሬ እራሱ ትንቢት ነው፦
3፥15 *«ከዚህ ሁሉ ነገር የሚበልጥን ልንገራችሁን» በላቸው”*፡፡ እርሱም «ለእነዚያ ለተጠነቀቁት ሰዎች በጌታቸው ዘንድ በሥራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች በውስጧ ሁልጊዜ ነዋሪዎች ሲኾኑ ንጹሕ የተደረጉ ሚስቶችም፣ ከአላህም የኾነ ውዴታ አላቸው፡፡ አላህም ባሮቹን ተመልካች ነው፡፡» قُلْ أَؤُنَبِّئُكُم بِخَيْرٍ مِّن ذَٰلِكُمْ ۚ لِلَّذِينَ اتَّقَوْا عِندَ رَبِّهِمْ جَنَّاتٌ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا وَأَزْوَاجٌ مُّطَهَّرَةٌ وَرِضْوَانٌ مِّنَ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ بَصِيرٌ بِالْعِبَادِ
22፥72 *«ከዚህ ይልቅ የከፋን ነገር ልንገራችሁን» በላቸው”*፡፡ «እርሱም እሳት ናት፡፡ አላህ ለእነዚያ ለካዱት ሰዎች ቀጥሯታል፡፡ ምን ትከፋም መመለሻ!» قُلْ أَفَأُنَبِّئُكُم بِشَرٍّ مِّن ذَٰلِكُمُ ۗ النَّارُ وَعَدَهَا اللَّهُ الَّذِينَ كَفَرُوا ۖ وَبِئْسَ الْمَصِيرُ

“ልንገራችሁ” ለሚለው ቃል የገባው “ነበኡኩም” نَبِّئُكُم ሲሆን “ነበአ” نَبَّأَ ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ነው። ይህንን እንዲናገሩ አላህ “ቁል” قُلْ የሚል ትእዛዝ ያወርዳል። ቁርኣን ላይ ብዙ ቦታ በትንሳኤ ቀን ምን እንደሚከሰት ለማሳወቅ “አስታውስ” እያለ ይናገራል፦
54፥6 *”ከእነርሱም ዙር፡፡ ጠሪው መልአክ ወደ አስደንጋጭ ነገር የሚጠራበትን ቀን አስታውስ”*፡፡ فَتَوَلَّ عَنْهُمْ ۘ يَوْمَ يَدْعُ الدَّاعِ إِلَىٰ شَيْءٍ نُّكُرٍ

ይህንን ትንቢት አምላካችን አላህ፦ “በእርግጥ ከጊዜ በኋላ ወደፊትም ታውቁታላችሁ” ይለናል፦
38፥88 *«ትንቢቱንም ከጊዜ በኋላ በእርግጥ ታውቁታላችሁ፡፡* وَلَتَعْلَمُنَّ نَبَأَهُ بَعْدَ حِينٍ
6፥67 *ለትንቢት ሁሉ የሚደርስበት መርጊያ አለው፡፡ ወደፊትም ታውቁታላችሁ*፡፡ لِّكُلِّ نَبَإٍ مُّسْتَقَرٌّ ۚ وَسَوْفَ تَعْلَمُونَ

“ኢዝ” إِذْ በሚለው የጊዜ ተውሳከ-ግስ ውስጥ “ፈዘከር” فَذَكِّرْ ማለትም “አስታውስ” የሚል ትእዛዝ አለ፥ አላህ ያለፈውን፣ ያሁኑን እና የሚመጣውን የሩቅ ወሬ እየነገራቸው “አስታውስ” ይላቸዋል። ነቢያችን”ﷺ” ደግሞ “ሙዘከር” مُذَكِّرٌ ማለትም “አስታዋሽ” ናቸው። ነቢያችን”ﷺ” የሚያሳታውሱት በተወረዳቸው “ዚክር” ብቻ ነው፥ ይህም “ዚክር” ذِكْر ማለትም “ማስታወሻ” ቁርኣን ነው፦
88፥21 *አስታውስም፤ አንተ አስታዋሽ ብቻ ነህና*፡፡ فَذَكِّرْ إِنَّمَا أَنتَ مُذَكِّرٌ
21፥50 *ይህም ያወረድነው የኾነ ብሩክ “ዚክር” *፡፡ ታዲያ እናንተ ለእርሱ ከሓዲዎች ናችሁን? وَهَـٰذَا ذِكْرٌ مُّبَارَكٌ أَنزَلْنَاهُ ۚ أَفَأَنتُمْ لَهُ مُنكِرُونَ
50፥45 ስለዚህ ዛቻዬን የሚፈራን ሰው *በቁርኣን አስታውስ*፡፡ فَذَكِّرْ بِالْقُرْآنِ مَن يَخَافُ وَعِيدِ

"""""""ተፈጸመ""""""""

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
መሢሕ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3:45 መላእክት ያሉትን አስታዉስ፡- መርየም ሆይ አላህ ከርሱ በሆነዉ ቃል፣ ስሙ “አል-መሲሕ” ዒሳ የመርየም ልጅ፣ በዚህ ዓለምና በመጨረሻዉም ዓለም የተከበረ፣ ከባለማሎችም በሆነ ያበስረሻል፤

“መሲሕ” مسيح የሚለው የአረቢኛ ቃል
“መሢሐ” מָשִׁ֫יחַ የሚለው የእብራይስጥ ቃል
“መሢሕ” ክמשיחא የሚለው የአረማይ ቃል
ሴማዊ መነሻ ሲኖረው ትርጉሙ “የተቀባ” ማለት ነው፣ በግሪክ ደግሞ “ክርስቶስ” Χριστός ነው፤ ይህ ማእረግ በብሉይ ኪዳን ለተለያየ ነገስታትና ነቢያት በግሪኩ ሰፕቱጀንት ላይ “ክርስቶስ” Χριστός በእብራይስጡ ደግሞ መሢሐ” מָשִׁ֫יחַ ተብሎ አገልግሎት ላይ ውሏል፤ መቀባት መሾምን ያመለክታል በአምላክ የተቀቡ የአምላክ መሢሖች ብዙ ናቸው፦
1ኛ ዜና 16፥22 “መሢሖቼን” בִּמְשִׁיחָ֔י አትዳስሱ፥ “በነቢያቴም” ክፉ አታድርጉ ብሎ፥ ሰው ግፍ ያደርግባቸው ዘንድ አልፈቀደም ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ።
መዝሙረ ዳዊት 105፥14-15 “መሢሖቼን” בִּמְשִׁיחָ֔י አትዳስሱ፥ “በነቢያቴም” ክፉ አታድርጉ ብሎ፥ ሰው ግፍ ያደርግባቸው ዘንድ አልፈቀደም ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ።

አንደኛ “ሳኦል”
1ሳኦል በትንቢት የተነገረለት መሢሐዊ ንጉስ ነው፦
1 ሳሙ 2:10 እግዚአብሔር እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል፤ “ለንጉሡም” ኃይል ይሰጣል፤ “የመሲሑንም” מְשִׁיחֽוֹ ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።

ይህንን ጥቅስ የአይሁድ ምሁራን እና ለዘብተኛ የብሉይ ተንታኞች ለሳኦል እንደሆነ ያትታሉ፤ በተጨማሪም በሳሙኤል ዘመን የተቀባ መሢሕ ሳኦል እንደሆነ በቁና መረጃ አለ፦
1ሳሙ 10:1፤ ሳሙኤልም የዘይቱን ብርሌ ወስዶ በራሱ ላይ አፈሰሰው፥ ሳመውም፥ እንዲህም አለው። በርስቱ ላይ አለቃ ትሆን ዘንድ እግዚአብሔር “ቀብቶሃል” מְשָׁחֲךָ ֧፤
1ሳሙ 12፥3 እነሆኝ በእግዚአብሔርና “በመሲሑ” מְשִׁיח֗וֹ ፊት መስክሩብኝ የማንን በሬ ወሰድሁ?
1ሳሙ 12፥5 እርሱም፦ በእጄ ምንም እንዳላገኛችሁ እግዚአብሔርና “መሲሑ” מְשִׁיח֗וֹ ዛሬ በእናንተ ላይ ምስክሮች ናቸው አላቸው፤

ሁለተኛ “ዳዊት”
2 ሳሙ 22፥51 የንጉሡን መድኃኒት ታላቅ ያደርጋል፤ ቸርነቱንም ለመሲሑ לִמְשִׁיח֛וֹ ለዳዊትና ለዘሩ፥ ለዘላለም ይሰጣል።
2 ሳሙ 23፥1 የዳዊትም የመጨረሻ ቃሉ ይህ ነው። ከፍ ከፍ የተደረገው፥ የያዕቆብም አምላክ መሢሕ מְשִׁ֙יחַ֙፥ በእስራኤል ዘንድ መልካም ባለ ቅኔ የሆነ፥ የእሴይ ልጅ የዳዊት ንግግር፤
መዝ 132:17 በዚያ ለዳዊት ቀንድን አበቅላለሁ፥ “ለመሢሔ” לִמְשִׁיחִֽי ሰው መብራትን አዘጋጃለሁ።

ሶስተኛ “ሰለሞን”
1ሳሙ 2:35 የታመነም ካህን ለእኔ አስነሣለሁ፥ በልቤም በነፍሴም እንዳለ እንዲሁ ያደርጋል፤ እኔም የታመነ ቤት እሠራለታለሁ፥ ዘመኑን ሁሉ በመሢሔ מְשִׁיחִ֖י ሰው ፊት ይሄዳል።

ይህ ጥቅስ ትንቢት ሲሆን ትንቢቱም ስለ ካህንና ካህኑ የሚሄድበት መሢሑ ናቸው፤ ምሁራን ካህኑ ሳዶቅ ሲሆን መሢሑ ደግሞ ቤት የሰራው ሰለሞን ነው፦
1 ኛ ነገሥት 1፥39 ካህኑም ሳዶቅ ከድንኳኑ የቅብዓቱን ቀንድ ወስዶ ሰሎሞንን ቀባ וַיִּמְשַׁ֖ח፤ ቀንደ መለከትም ነፉ፤ ሕዝቡም ሁሉ፦ ሰሎሞን ሺህ ዓመት ይንገሥ አሉ።

አራተኛ “ሴዴቂያስ”
ምሁራን በባቢሎን ምርኮ ጊዜ በጉድጓድ የተያዘው ሴዴቅያስ እንደሆነ ያትታሉ፤ ይህም ንጉስ መሲህ ተብሏል፦
ሰቆቃው ኤርምያስ 4፥20 ሬስ። ስለ እርሱ። በአሕዛብ መካከል በጥላው በሕይወት ያልነው “የእግዚአብሔር መሢሕ” מְשִׁ֣יחַ፥ የሕይወታችን እስትንፋስ፥ በጕድጓዳቸው ተያዘ።

አምስተኛ “ሙሴና ኤልያስ”
ዘካ 4:14 እርሱም። በምድር ሁሉ ጌታ አጠገብ የቆሙት “ሁለቱ የተቀቡት” הַיִּצְהָ֑ר እነዚህ ናቸው አለኝ።

በምድር ሁሉ ጌታ አጠገብ የቆሙት “ሁለቱ የተቀቡትየተባሉት ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን ካዘጋው ከኤልያስና ውኃዎችንም ወደ ደም ካስለወጠው ከሙሴ ሌላ እነማን ሊሆኑ ይችላሉ? ምሁራን በዚህ ሸክ የላቸውም፦
ራእይ 11፥3-10 “ለሁለቱም ምስክሮቼ” ማቅ ለብሰው ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን “ትንቢት” ሊናገሩ እሰጣለሁ። እነዚህ “በምድር ጌታ ፊት የሚቆሙ” ሁለቱ ወይራዎችና ሁለቱ መቅረዞች ናቸው።
ዘካርያስ 4፥11 እኔም መልሼ፦ በመቅረዙ በስተ ቀኝና በስተ ግራ ያሉ እነዚህ “ሁለት የወይራ ዛፎች” ምንድር ናቸው? አልሁት።
ዘካ 4:14 እርሱም። በምድር ሁሉ ጌታ አጠገብ የቆሙት “ሁለቱ የተቀቡት” הַיִּצְהָ֑ר እነዚህ ናቸው አለኝ።

ስድስተኛ “ኢየሱስ”
መዝሙረ ዳዊት 2፥2 የምድር ነገሥታት ተነሡ፥ አለቆችም በእግዚአብሔርና በመሢሑ מְשִׁיחֽוֹ ላይ እንዲህ ሲሉ ተማከሩ።

አይሁዳውያን በትንቢት የሚጠበቀው መሢሕ ኢየሱስ አይደለም ብለው ቢያስተባብሉም እኛ ሙስሊሞችና ሆነ የኢየሱስን ማንነት ያዛቡት ክርስቲያኖች ኢየሱስ ቃል የተገባለት መሢሕ ነው ብለን እናምናለን፤ ይህን ነጥብ ከሶስቱም ማእዘን እንመልከት፦
ነጥብ አንድ
“መሢሕ በአይሁድ”
አይሁዳውያን መሢሕ ቃል የተገባለት”the promised one” ንጉስና ነብይ ነው ብለው ይጠብቁት ነበር፤ መሢሕ አምላክ አሊያም ከአምላክ ጋር ኖሮ ኖሮ በኃላ በስጋ የሚመጣ ሳይሆን ከዳዊት ቤት የሚፈጠር ሰው ብቻ ነው ብለው ያምናሉ፤ መሢሕ አይሁዶች ይጠብቁት እንደነበረ የሚያመላክቱ ጥቅሶች አሉ፦
ሉቃ 3:15 ሕዝቡም “ሲጠብቁ” ሳሉ ሁሉም በልባቸው ስለ ዮሐንስ። “ይህ ክርስቶስ ይሆንን?” ብለው ሲያስቡ ነበር፥
ዮሐ 10:24 አይሁድም እርሱን ከበው። እስከ መቼ ድረስ በጥርጣሪ ታቆየናለህ? “አንተ ክርስቶስ” እንደ ሆንህ ገልጠህ ንገረን አሉት።
ሉቃ 22:67 “ክርስቶስ” አንተ ነህን? ንገረን አሉት። እርሱ ግን እንዲህ አላቸው። ብነግራችሁ አታምኑም፤
ዮሐ 4:25 ሴቲቱ። “ክርስቶስ የሚባል መሲሕ እንዲመጣ” አውቃለሁ፤ እርሱ ሲመጣ ሁሉን ይነግረናል አለችው።”
ዮሐ 4:29 ያደረግሁትን ሁሉ የነገረኝን ሰው ኑና እዩ፤ እንጃ እርሱ “ክርስቶስ” ይሆንን? አለች።
ዮሐ.7:41 ሌሎች። ይህ “ክርስቶስ ነው” አሉ፤ ሌሎች ግን። “ክርስቶስ በእውኑ ከገሊላ ይመጣልን”?
ነጥብ ሁለት
“መሲህ በክርስትና”
ኢየሱስ አይሁድ የሚጠብቁት መሢሕ መሆኑንና ግን ያንን ማንነቱን ለጊዜው ለማንም እንዳይናገሩ ተናግሯል፦
ዮሐ 4:25-26 ሴቲቱ። “ክርስቶስ የሚባል መሲሕ እንዲመጣ” አውቃለሁ፤ እርሱ ሲመጣ ሁሉን ይነግረናል አለችው። ኢየሱስ። የምናገርሽ “እኔ እርሱ ነኝ” አላት።
ማቴ 16:20 ያን ጊዜም እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ለማንም እንዳይነግሩ ደቀ መዛሙርቱን አዘዛቸው።

ሃዋርያትንም እኔ ማን ነኝ? ብሎ ሲጠይቃቸው አንተ ክርስቶስ ነህ ብሎ ጴጥሮስ መልሷል፤ ሃዋርያትም ኢየሱስ መሲህ መሆኑን መስክረዋል፤ በእርግጥም ክርስቶስ አይደለም ብሎ ኢየሱስን የሚያስተባብል ውሸተኛ ነው፦
ማር 8:29 እናንተስ “እኔ ማን እንደ ሆንሁ” ትላላችሁ? ብሎ ጠየቃቸው። ጴጥሮስም። “አንተ ክርስቶስ ነህ” ብሎ መለሰለት።
ሐዋ 5:42 ዕለት ዕለትም በመቅደስና በቤታቸው “ስለ ኢየሱስ እርሱ “ክርስቶስ” እንደ ሆነ ማስተማርንና መስበክን አይተዉም ነበር።
ሐዋ 17፥3 ይህ እኔ የምሰብክላችሁ “ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው” ይል ነበር።
ሐዋ 18፥5 ሲላስና ጢሞቴዎስም ከመቄዶንያ በወረዱ ጊዜ፥ ጳውሎስ “ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ” እንደ ሆነ ለአይሁድ እየመሰከረ ለቃሉ ይተጋ ነበር።
ሐዋ.18:28 “ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ” እንደ ሆነ ከመጻሕፍት እየገለጠ ለአይሁድ በሁሉ ፊት በጽኑ ያስረዳቸው ነበርና።
1ዮሐ.2:22 “ክርስቶስ አይደለም ብሎ ኢየሱስን” ከሚክድ በቀር ውሸተኛው ማን ነው?

ኢየሱስ በእርግጥ እግዚአብሔር አምላኩ በመንፈስ ቅዱስ ከባለንጀሮቹ ከነቢያትና ከነገስታት ይልቅ ኢንጅልን እንዲሰብክ
የቀባው ሰው ነው፦
ሐዋ 10:38 እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም “ቀባው”፥
ሉቃ4:17 ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ “ቀብቶኛልና” ።
ዕብ 1:9 ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት “ቀባህ”፤
ነጥብ ሶስት
“መሲሕ በኢስላም”
አምላካችን አላህ በተከበረው ቃሉ በዘጠኝ አንቀፆች 11 ጊዜ ኢየሱስ መሢሕ መሆኑን ነግሮናል፦ 3፥45 4፥157 4፥171 4፥172 5፥17 5፥17 5፥72 5፥72 5፥75 9፥30 9፥31
ለናሙና ያክል አንዳንድ ጥቅሶ ብንመለከት ኸይር ነው፦
3:45 መላእክት ያሉትን አስታዉስ፡- መርየም ሆይ አላህ ከርሱ በሆነዉ ቃል፣ ስሙ “አል-መሲሕ” ዒሳ የመርየም ልጅ፣ በዚህ ዓለምና በመጨረሻዉም ዓለም የተከበረ፣ ከባለማሎችም በሆነ ያበስረሻል፤

መርየም ከአላህ በሆነው ቃል
የተበሰረችው ልጇ፦
1. ስሙ አልመሲሕ ዒሳ መሆኑን
2. የመርየም ልጅ መሆኑን
3. በዚህ ዓለምና በመጨረሻዉም ዓለም የተከበረ መሆኑን
4. ከባለማሎችም አንዱ መሆኑን ነው።
ይህም የመርየም ልጅ ኢሳ የአላህ ባሪያ የሆነ መሲህ ነው፦
4:172 “አልመሲሕ” ለአላህ ባሪያ ከመሆን ፈጽሞ አይጠየፍም፤

ቁርአን ኢየሱስን መሢሕ ብሎታልና ለአምላክነቱ መስፈርት ነው ብሎ መሟገት ሌሎች መሲህ የተባሉትን ነቢያትና ነገስታት አምላክ ናቸው ብሎ መፈረጅም ነው፤ በተረፈ ይህንን የማርያምን ልጅ ኢየሱስን ከመሲህነት ወደ ፈጣሪነት ማሸጋገር ኩፍር ነው፦
5:17 እነዚያ አላህ اللَّهَ እርሱ የመርየም ልጅ “አልመሲሕ” الْمَسِيحُ ነው ያሉ፣ በእርግጥ ካዱ፤
5.72 እነዚያ አላህ اللَّهَ እርሱ የመርየም ልጅ “አልመሲሕ” الْمَسِيحُ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ፤

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የማይቃጠለው ቁርኣን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

75፥17 *በልብህ ውስጥ መሰብሰቡ እና ማንበቡ በእኛ ላይ ነውና*፡፡ إِنَّ عَلَيْنَا جَمْعَهُ وَقُرْآنَهُ

ኖርዌህ የኢሥላም ጠል"Islamophobia" ያለባቸው ቡድን መሪ የቁርኣንን ሙስሐፍ ሲያቃጥል ነበር። ነገር ግን ቁርኣን የተጻፈበትን ቁስ ሰዎች ያቃጥሉ ይሆናል እንጂ የአላህን ንግግር በፍጹም ማቃጠል አይችሉም፥ ምክንያቱም ቁርኣን በአማንያን ልብ ውስጥ አላህ የሰበሰበው ታምር ነው። “ቁርኣን” قُرْءَان ማለት “በልብ ታፍዞ በምላስ የሚነበነብ መነባነብ” ማለት ማለት ነው፦
75:18 *ባነበብነውም ጊዜ ንባቡን ተከተል*። فَإِذَا قَرَأْنَاهُ فَاتَّبِعْ قُرْآنَه
75፥17 *በልብህ ውስጥ መሰብሰቡ እና ማንበቡ በእኛ ላይ ነውና*፡፡ إِنَّ عَلَيْنَا جَمْعَهُ وَقُرْآنَهُ
“ማንበቡ” ለሚለው ቃል የገባው “ቁርኣነሁ” َقُرْآنَهُ ሲሆን የግስ መደብ ነው፤ የስም መደቡ ደግሞ “ቁርኣን” قُرْءَان ነው። “ቃሪእ” قَارِئ‎ ማለት “በልብ አፍዞ በምላስ አነብናቢ”reciter” ማለት ነው፤ የቃሪእ ብዙ ቁጥር “ቁርራ” قُرَّاء ነው፤ አንድ ቃሪ የሆነ ሰው ቁርኣንን ሲቀራ አዳማጩ የሚያደምጠው የአላህን ንግግር ነው፦
7፥204 *ቁርኣንም በተነበበ ጊዜ እርሱን አዳምጡ፤ ጸጥም በሉ፤ ይታዘንላችኋልና*፡፡ وَإِذَا قُرِئَ الْقُرْآنُ فَاسْتَمِعُوا لَهُ وَأَنصِتُوا لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ
9፥6 ከአጋሪዎችም አንዱ ጥገኝነትን ቢጠይቅ *የአላህን ንግግር ይሰማ ዘንድ አስጠጋው*፡፡ وَإِنْ أَحَدٌ مِّنَ الْمُشْرِكِينَ اسْتَجَارَكَ فَأَجِرْهُ حَتَّىٰ يَسْمَعَ كَلَامَ اللَّهِ

“ዚክር” ذِكْر የሚለው ቃል “ዘከረ” ذَكَرَ ማለትም “አስታወሰ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማስታወስ”memorization” ማለት ነው፤ አምላካችን አላህ ቁርኣን በልብ እንዲታፈዝ አግርቶታል፦
54፥17 *ቁርኣንንም ለማስታወስ በእርግጥ አገራነው፡፡ አስታዋሽም አለን?* وَلَقَدْ يَسَّرْنَا ٱلْقُرْءَانَ لِلذِّكْرِ فَهَلْ مِن مُّدَّكِرٍۢ

አላህ፦ እኔ ቁርኣንን በቃላችሁ እንድትዙት ገር አርጌዋለው፤ ሙደኪር የት አለ? ብሎ ይጠይቃል፤ “ሙደኪር” مُّدَّكِرٍۢ ማለት “አስታዋሽ”Memorizer” ማለት ነው፤ አላህ ቁርአንን በቀልባችን እንድናፍዘው ብቻ ሳይሆን ስንቀራው በምላስ እንዲቀል እና በዐረቢኛው ቋንቋ እንድንገነዘበው አግርቶታል፦
12፥2 *እኛ ትገነዘቡ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን ሲሆን በእርግጥ አወረድነው*፡፡ إِنَّآ أَنزَلْنَٰهُ قُرْءَٰنًا عَرَبِيًّۭا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ
44፥58 *ቁርአኑን በምላስህ ያገራነው ይገነዘቡ ዘንድ ነው*። فَإِنَّمَا يَسَّرْنَاهُ بِلِسَانِكَ لَعَلَّهُمْ يَتَذَكَّرُونَ
And indeed, We have eased the Qur’an in your tongue that they might be reminded.

“ዩሥራ” يُسْرَىٰ ማለት “ገር” ወይም “ቀላል” ማለት ሲሆን በልብ ለማስታወስ፣ በምላስ ላይ ለመቅራት፣ በቋንቋው ለመረዳት አግርቶታል። “ሊሣን” لِسَان የሚለው ቃል “ምላስ” ወይም “ቋንቋ” ማለት ነው፤ አላህ ቁርአንን በልባችን እንደሚሰበስበው ቃል ገብቶልናል፦
75፥17 *በልብህ ውስጥ መሰብሰቡ እና ማንበቡ በእኛ ላይ ነውና*፡፡ إِنَّ عَلَيْنَا جَمْعَهُ وَقُرْآنَهُ
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 4, ሐዲስ 166
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *”በአላህ አዘ ወጀል ንግግር፦ “በቁርኣን ንባብ ልትቸኩል ምላስህን በእርሱ አታላውስ” ነብዩ”ﷺ” ጂብሪል ወደ እሳቸው ሲያወርድ ምላሳቸውና ከንፈራቸውን ለማንበብ በማንበብ ያላውሱ ስለነበር ነው፤ ይህ ችግር አልፎ አልፎ ይታይ ነበርና፤ አላህ ተዓላ፦ “በቁርኣን ንባብ ልትቸኩል ምላስህን በእርሱ አታላውስ” የሚለውን አወረደ፤ “በልብህ ውስጥ መሰብሰቡና ማንበቡ በእኛ ላይ ነውና” ብሎ ሰበሰበው፤ በእርግጥም በልብህ ውስጥ እንድትቀራው እንጠብቀዋለን አንተም ትቀራዋለህ” ማለት ነው፤ “ባነበብነውም ጊዜ ካለቀ በኋላ ንባቡን ተከተል፣ ከዚያም ማብራራቱ በእኛ ላይ ነው” ማለት “በምላስህ ላይ ማስቀመጡ በእኛ ላይ ነው” ማለት ነው፤ ጂብሪል ወደ እርሳቸው በሚመጣ ጊዜ ዝም ይላሉ፤ ከእርሳቸው በተለየ ጊዜ አላህ ቃል እንደገባላቸው ይቀራሉ*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، فِي قَوْلِهِ عَزَّ وَجَلَّ ‏{‏ لاَ تُحَرِّكْ بِهِ لِسَانَكَ‏}‏ قَالَ كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم إِذَا نَزَلَ عَلَيْهِ جِبْرِيلُ بِالْوَحْىِ كَانَ مِمَّا يُحَرِّكُ بِهِ لِسَانَهُ وَشَفَتَيْهِ فَيَشْتَدُّ عَلَيْهِ فَكَانَ ذَلِكَ يُعْرَفُ مِنْهُ فَأَنْزَلَ اللَّهُ تَعَالَى ‏{‏ لاَ تُحَرِّكْ بِهِ لِسَانَكَ لِتَعْجَلَ بِهِ‏}‏ أَخْذَهُ ‏{‏ إِنَّ عَلَيْنَا جَمْعَهُ وَقُرْآنَهُ‏}‏ إِنَّ عَلَيْنَا أَنْ نَجْمَعَهُ فِي صَدْرِكَ ‏.‏ وَقُرْآنَهُ فَتَقْرَأُهُ ‏{‏ فَإِذَا قَرَأْنَاهُ فَاتَّبِعْ قُرْآنَهُ‏}‏ قَالَ أَنْزَلْنَاهُ فَاسْتَمِعْ لَهُ ‏{‏ إِنَّ عَلَيْنَا بَيَانَهُ‏}‏ أَنْ نُبَيِّنَهُ بِلِسَانِكَ فَكَانَ إِذَا أَتَاهُ جِبْرِيلُ أَطْرَقَ فَإِذَا ذَهَبَ قَرَأَهُ كَمَا وَعَدَهُ اللَّهُ ‏

“ጀመዐ” جَمَعَ ማለት “ሰበሰበ” ማለት ሲሆን “ጀመዕ” جَمَع ማለት ደግሞ “ስብስብስ”Collection” ማለት ነው። ይህ በቃል ደረጃ”oral form” የተሰበሰበው ቁርኣን በሙተዋቲር ከነብያችን”ﷺ” ወደ ሶሐባዎች፣ ከሶሐባዎች ወደ ታቢኢይዎች፣ ከታቢኢይዎች ወደ አትባኡ ታቢኢይዎች እያለ በሙተዋቲር አስራ አራት ትውልድ አሳልፎ መጥቷል፥ “ሙተዋቲር” مُتَواتِر ማለት ቁርኣን ከአንድ ኢስናድ በላይ በጀመዓ የሚደረግ ዘገባ ነው። አላህ ቁርኣንን እራሱ አውርዶ ከኋላውም ከፊቱም ውሸት እንዳይመጣበት እራሱ በአማኞች ልብ እንዲሰበሰብ ገር በማድረግ እና በምላስ እንዲቀራ ገር በማድረግ ይጠብቀዋል፦
15፥9 *እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን*፡፡ إِنَّا نَحْنُ نَزَّلْنَا ٱلذِّكْرَ وَإِنَّا لَهُۥ لَحَٰفِظُونَ
41፥42 *ከኋላውም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም*፡፡ ጥበበኛ ምስጉን ከኾነው ጌታ የተወረደ ነው፡፡ لَّا يَأْتِيهِ ٱلْبَٰطِلُ مِنۢ بَيْنِ يَدَيْهِ وَلَا مِنْ خَلْفِهِۦ ۖ تَنزِيلٌۭ مِّنْ حَكِيمٍ حَمِيدٍۢ

በጽሑፍ ደረጃ የተሰበሰቡት ጥራዞች ሁሉ ጠፉ ቢባል እንኳን ቁርኣን በቃሪእዎች ልብ ውስጥ አለ፦
ኢማም ቡኻርይ : መጽሐፍ 65, ሐዲስ 4937
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ *”ነብዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ያ ልክ ቁርኣንን በልቡ ሓፍዞ የሚቀራ በሰማይ ከተከበሩ ጸሐፊዎች(መላእክት) ጋር ይሆናል፤ ያ ልክ ቁርኣንን በልቡ እያወቀው በጣም እየከበደው የሚቀራ እጥፍ ምንዳ አለው*። عَنْ عَائِشَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ مَثَلُ الَّذِي يَقْرَأُ الْقُرْآنَ وَهْوَ حَافِظٌ لَهُ مَعَ السَّفَرَةِ الْكِرَامِ الْبَرَرَةِ، وَمَثَلُ الَّذِي يَقْرَأُ الْقُرْآنَ وَهْوَ يَتَعَاهَدُهُ وَهْوَ عَلَيْهِ شَدِيدٌ، فَلَهُ أَجْرَانِ ‏”‌‏.‏
ነብያችን”ﷺ” በሕይወታቸው ዘመን ማብቂያ ላይ ስለ ሙሉ ቁርኣን በልብ ውስጥ እንዴት እንደሚቀራ እንዲህ ተናግረዋል፦
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 66, ሐዲስ 78
ዐብደላህ ኢብኑ ዐምር እንደተረከው፦ *”ነብዩም”ﷺ” እኔን፦ “ሙሉ ቁርኣንን ቀርቶ ለመጨረስ ስንት ጊዜ ይወስድብሃል? ብለው ጠየቁኝ*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، قَالَ لِي النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ فِي كَمْ تَقْرَأُ الْقُرْآنَ ‏”‌‏.‏
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 66, ሐዲስ 79
ዐብደላህ ኢብኑ ዐምር እንደተረከው፦ *”የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ “ሙሉ ቁርኣንን በአንድ ወር ጊዜ ቅራ”። እኔም፦ “ከዛ በታች ለመቅራት ችሎታው አለኝ” አልኩኝ፤ እርሳቸው፦ “በሰባት ቀናት ቅራው፤ ከዚያ በታች ሙሉውን ለመቅራት አይቻልም*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ اقْرَإِ الْقُرْآنَ فِي شَهْرٍ ‏”‌‏.‏ قُلْتُ إِنِّي أَجِدُ قُوَّةً حَتَّى قَالَ ‏”‏ فَاقْرَأْهُ فِي سَبْعٍ وَلاَ تَزِدْ عَلَى ذَلِكَ ‏”‌‏.‏

በሰባት ቀናት ከፋፍሎ መቅራት “መንዚል” منزل ይባላል፤ ሌላው ቁርኣን ሠላሳ ጁዝዕ” አለው፤ “ጁዝዕ” جُزْءْ‎ ማለት “ክፍል”part” ማለት ሲሆን በሠላሳ ቀናት ከፋፍሎ መቀራትን ያሳያል፤ በተለይ በተራዊህ ሶላት ላይ ሙሉ ሠላሳ ጁዝዕ ይቀራል፤ “ተራዊህ” تراويح‌‎ ማለትም “በረመዳን የሌሊት ሶላት” ማለት ነው። ስለዚህ ቁርኣን ከትውልድ ወደ ትውልድ በቃሪእዎች ልብ ውስጥ በሙተዋቲር የሚተላለፍ ታምር ነው። በምድር ላይ ያሉትን የቁርኣን ሙስሐፍ ሰብስባችሁ ብታቃጥሉት ቁርኣን በቃሪእዎች ልብ ውስጥ ስለታፈዘ ሊጠፋ አይችልም። ቁርኣንን ለማጥፋት ሙስሊሞችን ቅድሚያ ማጥፋት ያስፈልጋል፤ ሙሥሊሞች ከሌሉ ደግሞ ትንሳኤ ይቆማል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ተፍሲል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

10፥37 ይህም ቁርኣን ከአላህ ሌላ ከሆነ ፍጡር የተቀጠፈ ሊሆን አይገባውም፡፡ ግን ያንን *”ከእርሱ በፊት ያለውን”* የሚያረጋግጥ እና *”በመጽሐፉ ውስጥ ያለውን የሚዘረዝር”* በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲሆን ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው፡፡ وَمَا كَانَ هَٰذَا ٱلْقُرْءَانُ أَن يُفْتَرَىٰ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَلَٰكِن تَصْدِيقَ ٱلَّذِى بَيْنَ يَدَيْهِ وَتَفْصِيلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا رَيْبَ فِيهِ مِن رَّبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ

አላህ ከነብያችንም”ﷺ” በፊት መልክተኞቹን በግልጽ ማስረጃዎች ልኳል፤ ሰዎችም በትክክል ቀጥ እንዲሉ መጽሐፎችን ወደ እነርሱ አውርዷል፤ ነብያችንም”ﷺ” ወደ መልክተኞቹ የተወረደውን ለሰዎች ሊገልጹ ቁርአን ወርዶላቸዋል፦
57፥25 መልክተኞቻችንን በግልጽ ማስረጃዎች በእርግጥ ላክን፡፡ ሰዎችም በትክክል ቀጥ እንዲሉ *”መጽሐፎችንና ሚዛንን ወደ እነርሱ አወረድን”*፤ لَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلَنَا بِٱلْبَيِّنَٰتِ وَأَنزَلْنَا مَعَهُمُ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْمِيزَانَ لِيَقُومَ ٱلنَّاسُ بِٱلْقِسْطِ
16፥44 በግልጽ ማስረጃዎች እና በመጻሕፍት ላክናቸው፡፡ ወደ አንተም ለሰዎች *”ወደ እነርሱ የተወረደውን ልትገልጽላቸው”* እና ያስተነትኑም ዘንድ ቁርኣንን አወረድን፡፡ بِٱلْبَيِّنَٰتِ وَٱلزُّبُرِ ۗ وَأَنزَلْنَآ إِلَيْكَ ٱلذِّكْرَ لِتُبَيِّنَ لِلنَّاسِ مَا نُزِّلَ إِلَيْهِمْ وَلَعَلَّهُمْ يَتَفَكَّرُون

ቁርአን ከእርሱ በፊት ወደ ነብያት የተወረደውን መጽሐፍ የሚያረጋግጥ እና በውስጡ ያለውን የሚዘረዝር ሲሆን ከዓለማቱ ጌታ የተወረደ ነው፦
4፥136 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህ እና በመልክተኛው በዚያም *በመልክተኛው ላይ ባወረደው መጽሐፍ በዚያም ከበፊቱ ባወረደው መጽሐፍ እመኑ*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا آمِنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ وَالْكِتَابِ الَّذِي نَزَّلَ عَلَىٰ رَسُولِهِ وَالْكِتَابِ الَّذِي أَنزَلَ مِن قَبْلُ ۚ
10፥37 ይህም ቁርኣን ከአላህ ሌላ ከሆነ ፍጡር የተቀጠፈ ሊሆን አይገባውም፡፡ ግን ያንን *”ከእርሱ በፊት ያለውን የሚያረጋግጥ እና በመጽሐፉ ውስጥ ያለውን የሚዘረዝር”* በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲሆን ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው፡፡ وَمَا كَانَ هَٰذَا ٱلْقُرْءَانُ أَن يُفْتَرَىٰ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَلَٰكِن تَصْدِيقَ ٱلَّذِى بَيْنَ يَدَيْهِ وَتَفْصِيلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا رَيْبَ فِيهِ مِن رَّبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ

"ተፍሲል" تَفْصِيل ማለት "ፈስሰለ" فَصَّلَ ማለትም "አብራራ" "ተነተነ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ማብራሪያ" ወይም "መተንተኛ"explanation" ማለት ነው፤ አምላካችን አላህ በበፊቱ በወረደው መጽሐፍ ላይ ምን ብሎ ተናግሮ እንደነበረ ለመናገር፦ "ከተብና" َكَتَبْنَا ማለትም "አልን" በማለት ይናገራል፤ ለናሙና ያክል በተውራት ምን ተናግሮ እንደነበር ያብራራዋል፦
5፥32 በዚህ ምክንያት በእስራኤል ልጆች ላይ፦ “እነሆ ያለ ነፍስ መግደል ወይም በምድር ላይ ያለማጥፋት ካልሆነ በስተቀር ነፍስን የገደለ ሰው ሰዎቹን ሁሉ እንደገደለ ነው፤ ሕያው ያደረጋትም ሰው ሰዎቹን ሁሉ ሕያው እንዳደረገ ነው” ማለትን *ጻፍን*፡፡ مِنْ أَجْلِ ذَٰلِكَ كَتَبْنَا عَلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ أَنَّهُ مَن قَتَلَ نَفْسًا بِغَيْرِ نَفْسٍ أَوْ فَسَادٍ فِي الْأَرْضِ فَكَأَنَّمَا قَتَلَ النَّاسَ جَمِيعًا وَمَنْ أَحْيَاهَا فَكَأَنَّمَا أَحْيَا النَّاسَ جَمِيعًا
5፥45 በእነርሱም ላይ በውስጧ፦ “ነፍስ በነፍስ ዓይንም በዓይን አፍንጫም በአፍንጫ ጆሮም በጆሮ ጥርስም በጥርስ ይያዛል፤ ቁስሎችንም ማመሳሰል አለባቸው” ማለትን *ጻፍን*፡፡ وَكَتَبْنَا عَلَيْهِمْ فِيهَا أَنَّ النَّفْسَ بِالنَّفْسِ وَالْعَيْنَ بِالْعَيْنِ وَالْأَنفَ بِالْأَنفِ وَالْأُذُنَ بِالْأُذُنِ وَالسِّنَّ بِالسِّنِّ وَالْجُرُوحَ قِصَاصٌ

“ከተበ” كَتَبَ ደግሞ “ቃለ” قَالَ ማለትም “አለ” ወይም “ከለመ” كَلَّمَ ማለትም “ተናገረ” በሚል ይመጣል፤ "ከተብና" َكَتَبْنَا የሚለው ቃል "ቁልና" قُلْنَا ወይም "አውሐይና" َأَوْحَيْنَا በሚል ተለዋዋጭ ቃል መጥቷል፦
2፥60 ሙሳም ለሕዝቦቹ መጠጥን በፈለገ ጊዜ የኾነውን አስታውሱ፡፡ «ድንጋዩንም በበትርህ ምታ» *አልነው*፡፡ وَإِذِ اسْتَسْقَىٰ مُوسَىٰ لِقَوْمِهِ فَقُلْنَا اضْرِب بِّعَصَاكَ الْحَجَر
26፥63 ወደ ሙሳም «ባሕሩን በበትርህ ምታው» *ስንል ላክንበት*፡፡ መታውና ተከፈለም፡፡ ክፍሉም ሁሉ እንደ ታላቅ ጋራ ኾነ፡፡ فَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ مُوسَىٰ أَنِ اضْرِب بِّعَصَاكَ الْبَحْرَ ۖ فَانفَلَقَ فَكَانَ كُلُّ فِرْقٍ كَالطَّوْدِ الْعَظِيمِ

ከላይ የዘረዘርናቸው አንቀጾች በአይሁዳውያን ቀኖና ውስጥ መልእክቱ በቅሪት ደረጃ ተቀምጠዋል፦
ዘጸአት 14፥16 *አንተም በትርህን አንሣ፥ እጅህንም በባሕሩ ላይ ዘርጋ*፥ ክፈለውም፤ የእስራኤልም ልጆች በባሕሩ ውስጥ በየብስ ያልፋሉ።
ዘጸአት 20፥7-8 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ *በትርህን ውሰድ፤ አንተና ወንድምህ አሮን ማኅበሩን ሰብስቡ፥ ድንጋዩም ውኃን እንዲሰጥ እነርሱ ሲያዩ ተናገሩት፤ ከድንጋዩም ውኃ ታወጣላቸዋለህ*፤ እንዲሁም ማኅበሩን ከብቶቻቸውንም ታጠጣላቸዋለህ።
ዘጸአት 21፥24-25 *ዓይን በዓይን፥ ጥርስ በጥርስ፥ እጅ በእጅ፥ እግር በእግር፥ መቃጠል በመቃጠል፥ ቍስል በቍስል፥ ግርፋት በግርፋት ይከፈል*።
ሚሽናህ ሳንድሬህ 4፥4 *በምድር ላይ ያለማጥፋት ነፍስን የገደለ ሰው፣ ሰዎቹን ሁሉ እንደገደለ ነው፤ ሕያው ያደረጋትም ሰው፣ ሰዎቹን ሁሉ ሕያው እንዳደረገ ነው*።
በተለይ ሚሽናህ ሳንድሬህ በኢየሩሳሌም ታልሙድ ላይ የተገኘው ከቁኣን መውረድ በኃላ ቢሆንም አላህ ግን ነብያችን”ﷺ” የመጽሐፉ ባለቤቶች ከመጽሐፉ ይሸሽጉት ከነበሩት ነገር ብዙውን ለእነርሱ የሚገልጹ ሆነው ከእርሱ ተልከዋል፦
5፥15 የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! *”ከመጽሐፉ ትሸሽጉት ከነበራችሁት ነገር ብዙውን ለእናንተ የሚገልጽ ከብዙውም የሚተው ሲኾን መልክተኛችን በእርግጥ መጣላችሁ*፡፡ ከአላህ ዘንድ ብርሃንና ገላጭ መጽሐፍ በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ قَدْ جَآءَكُمْ رَسُولُنَا يُبَيِّنُ لَكُمْ كَثِيرًۭا مِّمَّا كُنتُمْ تُخْفُونَ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَيَعْفُوا۟ عَن كَثِيرٍۢ ۚ قَدْ جَآءَكُم مِّنَ ٱللَّهِ نُورٌۭ وَكِتَٰبٌۭ مُّبِينٌۭ

“ከብዙውም የሚተው ሲኾን” ማለት የመጽሐፉ ባለቤቶች ከደበቋቸው ሁሉንም አልተናገሩም ማለት ነው፤ በቀኖና ያላካተቷቸው ግን የሸሸጓቸውን አላህ ተናግሮት እንደነበረ ለማሳየት "አልን" እያለ ይዘረዝርልናል፦
7፥166 ከእርሱም ከተከለከሉት ነገር በኮሩ ጊዜ ለእነሱ «ወራዶች ዝንጀሮች ኹኑ» *አልን* ኾኑም፡፡ فَلَمَّا عَتَوْا عَن مَّا نُهُوا عَنْهُ قُلْنَا لَهُمْ كُونُوا قِرَدَةً خَاسِئِينَ
17፥2 ሙሳንም መጽሐፉን ሰጠነው፡፡ ለእስራኤልም ልጆች መሪ አደረግነው፡፡ "ከእኔ ሌላ መጠጊያን አትያዙ"፤ *አልናቸውም*፡፡ وَآتَيْنَا مُوسَى الْكِتَابَ وَجَعَلْنَاهُ هُدًى لِّبَنِي إِسْرَائِيلَ أَلَّا تَتَّخِذُوا مِن دُونِي وَكِيلًا

እስቲ በፔንታተች አሊያም በታልሙድ ላይ ፈጣሪ፦ "ወራዶች ዝንጀሮች ኹኑ" ወይም "ከእኔ ሌላ መጠጊያን አትያዙ" ያለበትን ንግግር ወይም ሃሳብ ፈልጉ! ፈጽማችሁ አታገኙም። አላህ ወደ ሙሳ ተውራትን ሲያወርድ ነብያችን"ﷺ" አልነበሩም፤ ይህንን የሙሳ ወሬ “ነቁስሱ አለይከ” نَقُصُّ عَلَيْكَ ማለትም “እንተርክልሃለን” በማለት ለነብያችን”ﷺ” የሚተርከው እራሱ ወደ ሙሳም ትዕዛዝን ያወረደው አምላክ ነው፦
28፥44 *ወደ ሙሳም ትዕዛዝን ባወረድንለት ጊዜ ከተራራው በምዕራባዊው ጎን አልነበርክም* ከተጣዱትም አልነበርክም፡፡ وَمَا كُنتَ بِجَانِبِ الْغَرْبِيِّ إِذْ قَضَيْنَا إِلَىٰ مُوسَى الْأَمْرَ وَمَا كُنتَ مِنَ الشَّاهِدِينَ
20፥9 *የሙሳም ወሬ በእርግጥ መጥቶሃል*፡፡ وَهَلْ أَتَاكَ حَدِيثُ مُوسَىٰ
20፥99 እንደዚሁ በእርግጥ *ካለፉት ወሬዎች በአንተ ላይ እንተርካለን*፡፡ ከእኛም ዘንድ ቁረኣንን በእርግጥ ሰጠንህ፡፡ كَذَٰلِكَ نَقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنبَاءِ مَا قَدْ سَبَقَ ۚ وَقَدْ آتَيْنَاكَ مِن لَّدُنَّا ذِكْرًا

“ወሬ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ነበእ” نَبَإِ ሲሆን “ነቢይ” نبي የሚለው ቃል የመጣበት ሥርወ-ቃል ነው፤ ይህን የመልእክተኞች ወሬ አላህ ምን ተናግሮ እንደነበር ለነብያችን”ﷺ” መተረኩ ለምእምናን ግሳጼ እና ማስታወሻ ነው፦
11:120 *ከመልክተኞቹም ወሬዎች* ተፈላጊውን ሁሉንም ልብህን በእርሱ የምናረካበትን “*እንተርክልሃለን*፤ በዚህችም እውነቱ ነገር *ለምእምናን ግሳጼ እና ማስታወሻ* መጥቶልሃል፡፡ وَكُلًّۭا نَّقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنۢبَآءِ ٱلرُّسُلِ مَا نُثَبِّتُ بِهِۦ فُؤَادَكَ ۚ وَجَآءَكَ فِى هَٰذِهِ ٱلْحَقُّ وَمَوْعِظَةٌۭ وَذِكْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አር-ሩቂያህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

26፥80 *"በታመምኩም ጊዜ እርሱ ያሽረኛል"*፡፡ وَإِذَا مَرِضْتُ فَهُوَ يَشْفِينِ

ብዙ ጊዜ ሐኪም ቤት ሄደን መፍትሔ ስናጣ ወደ አላህ ከመጠየቅ ይልቅ ወደ ኩፍር መንደር ጎራ እንላለን፥ ይህ በራሱ ሺርክ ነው። የኩፍር መንደር ከጥንስሱ እስከ ድፍርሱ በሸያጢን አሠራር የሚካሄድ ነው። ሳሩን እንጂ ገደሉን ሳያዩ ብዙዎች መጨረሻቸው አላማረም፥ "የጨነቀው እርጉዝ ያገባል፥ ስትወልድ ገደል ይገባል" ይላሉ አበው። በኢሥላም ያለው ፈውስ በቁርኣን "ሺፋእ" ይባላል። "ሺፋእ" شِفَآء የሚለው ቃል "ሸፈ" شَفَى‎ ማለትም "ፈወሰ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ፈውስ" ማለት ነው። በሽታን የሚፈውስ አምላካችን አላህ ነው፦
26፥80 *"በታመምኩም ጊዜ እርሱ ያሽረኛል"*፡፡ وَإِذَا مَرِضْتُ فَهُوَ يَشْفِينِ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ያሽረኛል" ለሚለው ቃል የገባው "የሽፊኒ" يَشْفِينِ ሲሆን ሥርወ-ቃሉ "ሸፈ" شَفَى‎ መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል። እዚህ አንቀጽ ላይ ኢብራሂም "ይፈውሰኛል" የሚለው የዓለማቱን ጌታ አላህን ነው። አምላካችን አላህ ፈዋሽ ነው፥ ቁርኣንን መፈወሻ ፈውስ አርጎ አውርዶታል፦
10፥57 *እናንተ ሰዎች ሆይ! ከጌታችሁ ግሳጼ በደረቶች ውስጥም ላለው በሽታ "መድኃኒት" ለምእምናንም ብርሃንና እዝነት በእርግጥ መጣላችሁ*፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ قَدْ جَاءَتْكُم مَّوْعِظَةٌ مِّن رَّبِّكُمْ وَشِفَاءٌ لِّمَا فِي الصُّدُورِ وَهُدًى وَرَحْمَةٌ لِّلْمُؤْمِنِينَ
41፥44 በአጀምኛ የኾነ ቁርኣን ባደረግነው ኖሮ አንቀጾቹ በምናውቀው ቋንቋ አይብራሩም ኖሯልን? ቁርኣኑ አጀምኛ እና መልክተኛው ዐረባዊ ይኾናልን?» ባሉ ነበር። *በል እርሱ ለእነዚያ ለአመኑት መምሪያ እና "መፈወሻ" ነው*፡፡ وَلَوْ جَعَلْنَاهُ قُرْآنًا أَعْجَمِيًّا لَّقَالُوا لَوْلَا فُصِّلَتْ آيَاتُهُ ۖ أَأَعْجَمِيٌّ وَعَرَبِيٌّ ۗ قُلْ هُوَ لِلَّذِينَ آمَنُوا هُدًى وَشِفَاءٌ

ይህ ፈውስ በነቢያችን"ﷺ" ሐዲስ "አር-ሩቂያህ" الرُّقِيْة ይባላል። በልብ ላለው በሽታ ማለት ለዐይኑ አን-ናሥ፣ ለሲሕር እና ለሸያጢን መጸናወት መድኃኒቱ ሩቂያህ ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 31, ሐዲስ 3641
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"ነቢዩም"ﷺ" ከመጥፎ ዓይን ሩቂያህ እንድትቀራ አዘዟት"*። عَنْ عَائِشَةَ، أَنَّ النَّبِيَّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ أَمَرَهَا أَنْ تَسْتَرْقِيَ مِنَ الْعَيْنِ ‏
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 31, ሐዲስ 3618
ዐቃድ ኢብኑል ሙጊራህ ከአባቱ ሰምቶ እንደተተከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ማንም የታመመ በህክምና ወይም በሩቂያ ያደረገ፥ ራሱን በአላህ ይመካል"*። عَنْ عَقَّارِ بْنِ الْمُغِيرَةِ، عَنْ أَبِيهِ، عَنِ النَّبِيِّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ قَالَ ‏ "‏ مَنِ اكْتَوَى أَوِ اسْتَرْقَى فَقَدْ بَرِئَ مِنَ التَّوَكُّلِ

በአላህ ላይ መመካት “ተወኩል” تَوَكُّل‎ ይባላል። ሰይጧን በእነዚያ ባመኑት እና በአላህ ላይ በሚመኩት ላይ ስልጣን የለውም፦
16፥99 *”እርሱ በእነዚያ ባመኑት እና በጌታቸው ላይ በሚጠጉት ላይ ለእርሱ ስልጣን የለውምና”*፡፡ إِنَّهُ لَيْسَ لَهُ سُلْطَانٌ عَلَى الَّذِينَ آمَنُوا وَعَلَىٰ رَبِّهِمْ يَتَوَكَّلُونَ

“በሚጠጉት” ለሚለው ቃል የገባው “የተወከሉን” يَتَوَكَّلُون ሲሆን ቁርጥ ሐሳብም ባደረጉ ጊዜ አላህ በቂዬ ነው ብለው በአላህ ላይ ሙሉ ለሙሉ የተወከሉ ባሮቹ ደግሞ “ሙተወከሉን” مُتَوَكِّلُون ይባላል። “ኢሥቲዓዛህ” إِسْتِعَاذَة የሚለው ቃል “ኢሥተዓዘ” اِسْتَعَاذَ ማለትም “ተጠበቀ” ለሚለው ቃል መስደር ሲሆን “መጠበቅ” ማለት ነው። ይህም ኢሥቲዓዛህ “አዑዙ ቢሏሂ ሚነሽ ሸይጧኒር ረጂም” أَعُوذُ بِاللَّهِ مِنَ الشَّيْطَانِ الرَّجِيمِ ነው። “አዑዙ ቢሏሂ ሚነሽ ሸይጧኒር ረጂም” ማለት “እርጉም ከኾነው ሰይጣን በአላህ እጠበቃለው” ማለት ነው፦
16፥98 *”ቁርኣንንም ባነበብህ ጊዜ እርጉም ከኾነው ሰይጣን በአላህ ተጠበቅ”*፡፡ فَإِذَا قَرَأْتَ الْقُرْآنَ فَاسْتَعِذْ بِاللَّهِ مِنَ الشَّيْطَانِ الرَّجِيمِ

“አል-ሙዐወዘተይን” الْمُعَوِّذَتَيْن የሚባሉት ሁለቱ ሱራዎች ሱረቱል ፈለቅ እና ሱረቱ አን-ናሥ ለፈውስ የወረዱ ሱራህ ናቸው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 6 , ሐዲስ 319:
የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ *ዛሬ ምን አስደናቂ አንቀጾች ዛሬ ወርደዋል፤ ይህም ብጤአቸው ታይቶ አያውቅም! እነርሱም፦ “በል «በተፈልቃቂው ጎህ ጌታ እጠበቃለሁ” እና በል «በሰዎች ፈጣሪ እጠበቃለሁ» ናቸው*። قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ أَلَمْ تَرَ آيَاتٍ أُنْزِلَتِ اللَّيْلَةَ لَمْ يُرَ مِثْلُهُنَّ قَطُّ ‏{‏ قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ الْفَلَقِ‏}‏ وَ ‏{‏ قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ النَّاسِ‏}‏ ‏”‏
ታላቁ ሙፈሢር ኢብኑ ከሲር እነዚህ ሱራዎች በሐዲሱ መሠረት ፈሥሯቸዋል፦
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 113፥1 *“አል-ሙዐወዘተይን” ሲናገር፦ “በሌላ ሐዲስ እንደተዘገበው፦ “ጂብሪል ወደ ነብዩ”ﷺ” መጥቶ እንዲህ አላቸው፦ “ሙሐመድ”ﷺ” ሆይ በማንኛውም ህመም እየተሰቃየህ ነውን? ነቢዩም”ﷺ” "ነዐም" ብለው መለሱ። ጂብሪልም በአላህ ስም ሩቂያ እቀራብሃለው፤ ከማንኛውም በሽታ አንተን የጎዳህን፤ ከእያንዳንዱ ሸረኛ እና ክፉ ዓይን፤ አላህ ይፈውስሃል”*።
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 10 , ሐዲስ 8:
“ጂብሪል ወደ ነቢዩ”ﷺ” መጥቶ እንዲህ አላቸው፦ *“ሙሐመድ”ﷺ” ሆይ በማንኛውም ህመም እየተሰቃየህ ነውን? ነብዩም”ﷺ” "ነዐም" ብለው መለሱ። ጂብሪልም በአላህ ስም ሩቂያ እቀራብሃለው፤ ከማንኛውም በሽታ አንተን የጎዳህን፤ ከእያንዳንዱ ሸረኛ እና ክፉ ዓይን፤ አላህ ይፈውስሃል”*። أَنَّ جِبْرِيلَ، أَتَى النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم فَقَالَ يَا مُحَمَّدُ اشْتَكَيْتَ قَالَ ‏ “‏ نَعَمْ ‏”‏ ‏.‏ قَالَ بِاسْمِ اللَّهِ أَرْقِيكَ مِنْ كُلِّ شَيْءٍ يُؤْذِيكَ مِنْ شَرِّ كُلِّ نَفْسٍ وَعَيْنِ حَاسِدٍ بِاسْمِ اللَّهِ أَرْقِيكَ وَاللَّهُ يَشْفِيكَ ‏.‏
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 31, ሐዲስ 3652
አቢ ሠዒድ እንደተረከው፦ "ጂብሪል ወደ ነቢዩ"ﷺ" መጥቶ እንዲ አለ፦ *"ሙሐመድ ሆይ! ታመሃል፥ እርሳቸውም "ነዐም" አሉ። ጂብሪልም፦ "መጥፎ ከሆነ ነገር ሁሉ በአላህ ስም ሩቂያ አረግልሃለው፥ ከሁሉ መጥፎ ነፍስ ወይም መጥፎ ዓይን አሊያም ከምቀኝነት። አላህ ይፈውስህ! በአላህ ስም ሩቂያ አረግልሃለው"*። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ، أَنَّ جِبْرَائِيلَ، أَتَى النَّبِيَّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ فَقَالَ يَا مُحَمَّدُ اشْتَكَيْتَ قَالَ ‏ "‏ نَعَمْ ‏"‏ ‏.‏ قَالَ بِسْمِ اللَّهِ أَرْقِيكَ مِنْ كُلِّ شَىْءٍ يُؤْذِيكَ مِنْ شَرِّ كُلِّ نَفْسٍ أَوْ عَيْنٍ أَوْ حَاسِدٍ اللَّهُ يَشْفِيكَ بِسْمِ اللَّهِ أَرْقِيكَ

"አያቱ አር-ሩቂያህ"‎ آيَات الرُّقِيْة ማለት "የሩቂያህ
አናቅጽ" ማለት ነው፥ እነዚህም ዐበይት የሩቂያህ
አናቅጽ የሚቀሩት ሱቱል ፋቲሓህ 1 ጊዜ፣ ሱረቱል በቀራህ 2፥255 7 ጊዜ ወይም 11 ወይም 21 አሊያም 41 ጊዜ፣ ሱረቱል ኢኽላስ 3 ጊዜ፣ ሱረቱል ፈለቅ 3 ጊዜ፣ ሱረቱ አን-ናሥ 3 ጊዜ ናቸዉ። ከቁርኣንም ለምእመናን መድኀኒት የወረዱት ዐበይት አናቅጽ እነዚህ ናቸው፦
17፥82 *ከቁርኣንም ለምእመናን "መድኀኒት" እና እዝነት የኾነን እናወርዳለን*፡፡ በዳዮችንም ከሳራን እንጂ ሌላ አይጨምርላቸውም፡፡ وَنُنَزِّلُ مِنَ الْقُرْآنِ مَا هُوَ شِفَاءٌ وَرَحْمَةٌ لِّلْمُؤْمِنِينَ ۙ وَلَا يَزِيدُ الظَّالِمِينَ إِلَّا خَسَارًا

አምላካችን አላህ ቁርኣንን ቀርተው ከሚጠቀሙ ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም