ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.3K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ነጥብ ሥድስት
“ቴኦ-ክራሲ”
“ቴኦ-ክራሲ” ማለት “የአምላክ አገዛዝ” ማለት ነው፤ “ቴኦስ” θεός ማለት “አምላክ” ማለት ነው፤ ከአንድ እስከ ስድስት ያየናቸው የአገዛዝ ቅርጽ ምክር ቤት ውስጥ ያሉትን ሕገ-መንግሥት የሚያረቁት ከሰው አእምሮ ነው፤ ነገር ግን በቴኦክራሲ ቅርጽ መመሪያው መለኮታዊ ብቻ ነው። “መጅሊስ” مجلس‎ የሚለው የዐረቢኛ ቃል “ሲኖዶስ” σῠ́νοδος የሚለው የግሪክ ቃል ትርጉማቸው “ምክር ቤት”council” ማለት ነው፤ እዚህ ምክር ቤት ውስጥ ሕገ-መንግሥቱ ሸሪዓህ ነው፤ “ሸሪዓህ” شَرِيعَة የሚለው ቃል “ሺርዓህ” شِرْعَة ማለትም “ሕግ” ከሚለው የስም መደብ የመጣ ሲሆን “ትክክለኛ ሕግ” ማለት ነው፦
45፥18 *ከዚያም ከነገሩ ከሃይማኖት “በትክክለኛይቱ ሕግ” ላይ አደረግንህ*፡፡ ثُمَّ جَعَلْنَاكَ عَلَىٰ شَرِيعَةٍ مِّنَ الْأَمْرِ
5፥48 *ከእናንተ ለሁሉም ሕግን እና መንገድን አደረግን*፡፡ لِكُلٍّ جَعَلْنَا مِنكُمْ شِرْعَةً وَمِنْهَاجًا

አላህ ለሁሉም መልእክተኞች “ሕግ” እና “መንገድ” አድርጓል፤ “መንገድ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሚንሃጅ” مِنْهَاج ማለትም “ፋና” ማለት ሲሆን “መንሃጅ” منہاج የሚለው ቃል ጋር ተመሳሳይ ነው፤ ይህ ሕግ የሚዋቀረው ውቅር አራት ሲሆኑ፤ እነርሱም፦
1ኛ. “ቁርኣን” قرآن‌‎ ማለትም የአላህ ቃል፣
2ኛ. “ሡናህ” سنة የነብያችን”ﷺ” ሰሒህ ሐዲስ፣
3ኛ. “ቂያሥ” قياس‌‎ “ማመጣጠን”Analogy”
4ኛ. “ኢጅማዕ” إجماع‌‎ ማለትም የዐሊሞች ስብስብ ናቸው።
ስለዚህ ፍርድ ከአላህ በወረደው ሕግ ይፈረዳል፦
5፥48 *በመካከላቸውም አላህ ባወረደው ሕግ ፍረድ*፡፡ فَاحْكُم بَيْنَهُم بِمَا أَنزَلَ اللَّه

“ፍረድ” ለሚለው ቃል የተጠቀመበት “ፈሕኩም” فَاحْكُمْ ሲሆን “ሑክም” ለሚለው የግስ መደብ ነው፤ “ሑክም” حُكْم የሚለው ቃል”ሐከመ” حَكَمَ ማለትም “ፈረደ” የመጣ ሲሆን ፍርድ” ወይም “ሕግ” ማለት ነው፤ “አሕካም” أحكام ደግሞ የሑክም ብዙ ቁጥር ነው፤ በኢስላም “ሕጎች” በአምስት ይከፈላሉ፤ እነርሱም፦
1ኛ. “ፈርድ” فرض ማለትም “የታዘዘ”
2ኛ. “ሙሥተሐብ” مستحب” ማለትም “የተወደደ”
3ኛ. “ሙባሕ” مباح ማለትም “የተፈቀደ”
4ኛ. “መክሩህ” مكروه” ማለትም “የተጠላ”
5ኛ. “ሐራም” حرام” ማለትም “የተከለከለ” ናቸው።
“ፊቅህ” فقه ማለት “ጥልቅ መረዳት” ማለት ሲሆን የሥነ-ሕግ ጥናት”the study of law” ነው፤ ሕግ አዋቂ ደግሞ “ፈቂህ” فقيه ይባላል፤ “ፊቅህ” ማለት ቋንቋዊ ትርጉሙ “መረዳት” ማለት ነው፦
6፥98 *”ለሚያወቁ” ሕዝቦች አንቀጾችን በእርግጥ ዘረዘርን*፡፡ قَدْ فَصَّلْنَا الْآيَاتِ لِقَوْمٍ يَفْقَهُونَ

“ሚያወቁ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “የፍቀሁነ” يَفْقَهُونَ ሲሆን “ሚረዱ” ማለት ነው። ሙስሊሙ የስልጣን ባለቤቶች ለሆኑት ለአሚሮቻችን ይታዘዛል፤ የሚያወዘግብ ነገር ካለ ወደ አላህ ቁርኣን እና ወደ መልእክተኛው ሐዲስ መረጃ እና ማስረጃ ማግኘት ነው፦
4፥59 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገዙ፤ መልክተኛው እና *ከእናንተም የስልጣን ባለቤቶችን ታዘዙ*፡፡ በማንኛውም ነገር ብትከራከሩ በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ብትኾኑ *የተከራከራችሁበትን ነገር ወደ አላህ እና ወደ መልክተኛው መልሱት*፡፡ ይህ የተሻለ መጨረሻውም ያማረ ነው፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَطِيعُوا اللَّهَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ وَأُولِي الْأَمْرِ مِنكُمْ ۖ فَإِن تَنَازَعْتُمْ فِي شَيْءٍ فَرُدُّوهُ إِلَى اللَّهِ وَالرَّسُولِ إِن كُنتُمْ تُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ ۚ ذَٰلِكَ خَيْرٌ وَأَحْسَنُ تَأْوِيلًا

ነጥብ ስድስት ኢስላም የያዘውን ፓለቲካዊ ዘይቤ ቴኦ-ክራሲ ነው። እንደሚታወቀው የመጨረሻው ዘመን ጥናት”Eschatology” በኢስላም “አል-አኺሩል ዘማን” لَلْآخِر لَلْزَمَان ይባላል፤ የመጨረሻው ዘመን ምልክቶች በሁለት ይከፈላሉ፤ አንዱ ንዑሣን ምልክቶች ሲሆኑ ሁለተኛ ዐበይት ምልክቶች ናቸው፤ የኺላፋህ ሥርዓት ተመልሶ መምጣት ከንዑሳን ምልክቶች አንዱ ሲሆን በነብያችን”ﷺ” ትንቢት ውስጥ እንዲህ ተቀምጧል፦
ኢማም አሕመድ መጽሐፍ 14, ሐዲስ 163
ሑደይፋህ ኢብኑል-የማን እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ነብይነት አላህ እስከፈቀደው ጊዜ ይቆያል፤ ከዚያም በነብይነት ሚንሃጅ ኺላፋህ ይጀመርና አላህ እስከፈቀደው ጊዜ ይቆያል፤ ከዚያም ዘውዳዊ ንግሥና ቦታውን ይይዝና አላህ እስከፈቀደው ጊዜ ይቆያል፤ ከዚያም የአንባገነን ንግሥና ይነሳልና አላህ እስከፈቀደው ጊዜ ይቆያል፤ ከዚያም በስተመጨረሻም በነብይነት ሚንሃጅ ኺላፋህ ከእንደገና ይመጣል*። فَقَالَ حُذَيْفَةُ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ – صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ -: « تَكُونُ النُّبُوَّةُ فِيكُمْ مَا شَاءَ اللَّهُ أَنْ تَكُونَ ثُمَّ يَرْفَعُهَا إِذَا شَاءَ أَنْ يَرْفَعَهَا، ثُمَّ تَكُونُ خِلَافَةٌ عَلَى مِنْهَاجِ النُّبُوَّةِ فَتَكُونُ مَا شَاءَ اللَّهُ أَنْ تَكُونَ ثُمَّ يَرْفَعُهَا إِذَا شَاءَ اللَّهُ أَنْ يَرْفَعَهَا، ثُمَّ تَكُونُ مُلْكًا عَاضًّا فَيَكُونُ مَا شَاءَ اللَّهُ أَنْ يَكُونَ ثُمَّ يَرْفَعُهَا إِذَا شَاءَ أَنْ يَرْفَعَهَا، ثُمَّ تَكُونُ مُلْكًا جَبْرِيَّةً فَتَكُونُ مَا شَاءَ اللَّهُ أَنْ تَكُونَ ثُمَّ يَرْفَعُهَا إِذَا شَاءَ أَنْ يَرْفَعَهَا، ثُمَّ تَكُونُ خِلَافَةً عَلَى مِنْهَاجِ النُّبُوَّةِ

የነብያችን”ﷺ” ነብይነት ቆይታው እንደ ጎርጎሮሳውን አቆጣጠር ከ 610-632 ድህረ-ልደት ነበር፤ ከዚያም በነብያችን”ﷺ” ፋና አል-ኺላፈቱ አር-ረሺዳህ ከ 632-661 ድህረ-ልደት ነበር፤ ከዚያ የበኑ ኡመያድ ሥርወ-መንግሥት እና የበኑ ዐባሥ ሥርወ-መንግሥት ዘውዳዊ ንግሥና ሆኖ ከ 661-1258 ድህረ-ልደት ነበር፤ ከዚያም ከ 1258 ድህረ-ልደት እስከ ዘመናችን የአንባገነኖቹ ነገሥታት ጊዜ ውስጥ ነን፤ ከዚያም ኢንሻላህ በነብያችን”ﷺ” ፋና እንደገና የኺላፋህ ሥርዓት ይመለሳል፤ አላህ ቴኦክራሲን ያምጣልን! አሚን።

الإسلام هو الحل

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ነሲሓህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

9፥91 በደካሞች ላይ በበሽተኞችም ላይ በነዚያም የሚያወጡት ገንዘብ በማያገኙት ላይ *ለአላህ እና ለመልክተኛው ፍጹም ታዛዦች* ከኾኑ ባይወጡም ኃጢኣት የለባቸውም፡፡ በበጎ አድራጊዎች ላይ የወቀሳ መንገድ ምንም የለባቸውም፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ لَّيْسَ عَلَى ٱلضُّعَفَآءِ وَلَا عَلَى ٱلْمَرْضَىٰ وَلَا عَلَى ٱلَّذِينَ لَا يَجِدُونَ مَا يُنفِقُونَ حَرَجٌ إِذَا نَصَحُوا۟ لِلَّهِ وَرَسُولِهِۦ ۚ مَا عَلَى ٱلْمُحْسِنِينَ مِن سَبِيلٍۢ ۚ وَٱللَّهُ غَفُورٌۭ رَّحِيمٌۭ

“ነሲሓህ” نَّصِيحَة ማለት “ምክር” “ንጹሕ” “ቅንነት” “ፍጹምነት” “ታዛዥነት” የሚል ፍቺ አለው፥ “ናሲሕ” نَاصِح ማለት። ደግሞ “መካሪ” ማለት ነው፦
7፥68 «የጌታዬን መልክቶች አደርስላችኋለሁ፡፡ እኔም ለእናንተ ታማኝ *መካሪ* ነኝ፡፡» أُبَلِّغُكُمْ رِسَالَاتِ رَبِّي وَأَنَا لَكُمْ نَاصِحٌ أَمِينٌ

“ኑስሕ” نُصْح ማለት በራሱ “ምክር” ማለት ነው፦
11፥34 «ለእናንተም ልመክራችሁ ብሻ አላህ ሊያጠማችሁ ሽቶ እንደ ኾነ *ምክሬ* አይጠቅማችሁም፡፡ እርሱ ጌታችሁ ነው፡፡ ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ» አላቸው፡፡ وَلَا يَنفَعُكُمْ نُصْحِي إِنْ أَرَدتُّ أَنْ أَنصَحَ لَكُمْ إِن كَانَ اللَّهُ يُرِيدُ أَن يُغْوِيَكُمْ ۚ هُوَ رَبُّكُمْ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ
7፥62 «የጌታዬን መልክቶች አደርስላችኋለሁ፡፡ ለእናንተም *እመክራችኋለሁ*፡፡ ከአላህም በኩል የማታውቁትን ዐውቃለሁ፡፡» أُبَلِّغُكُمْ رِسَالَاتِ رَبِّي وَأَنصَحُ لَكُمْ وَأَعْلَمُ مِنَ اللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ

“እመክራችኋለሁ” የሚለው ቃል “አንሰሑ” أَنْصَحُ ሲሆን ምክር በሚል መጥቷል። ይህ ቃል እንደየ ዐውዱ ቃሉ የሚወክለው ትርጉም ይለያያል፥ ለምሳሌ “ነሡሕ” نَّصُوح የሚለው ቃል “ንጹሕ” የሚለው ትርጉም ይዞ መጥቷል፦
66፥8 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *ንጹሕ* የኾነችን ጸጸት በመጸጸት ወደ አላህ ተመለሱ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا تُوبُوا إِلَى اللَّهِ تَوْبَةً نَّصُوحًا

በሌላ ዓረፍተ-ነገር ላይ ደግሞ “ፍጹም ታዛዥነት” በሚል የግስ መደብ መጥቷል፦
9፥91 በደካሞች ላይ በበሽተኞችም ላይ በነዚያም የሚያወጡት ገንዘብ በማያገኙት ላይ *ለአላህ እና ለመልክተኛው ፍጹም ታዛዦች* ከኾኑ ባይወጡም ኃጢኣት የለባቸውም፡፡ በበጎ አድራጊዎች ላይ የወቀሳ መንገድ ምንም የለባቸውም፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ لَّيْسَ عَلَى ٱلضُّعَفَآءِ وَلَا عَلَى ٱلْمَرْضَىٰ وَلَا عَلَى ٱلَّذِينَ لَا يَجِدُونَ مَا يُنفِقُونَ حَرَجٌ إِذَا نَصَحُوا۟ لِلَّهِ وَرَسُولِهِۦ ۚ مَا عَلَى ٱلْمُحْسِنِينَ مِن سَبِيلٍۢ ۚ وَٱللَّهُ غَفُورٌۭ رَّحِيمٌۭ

“ፍጹም መታዘዝ” ለሚለው ቃል የመጣው “ነሰሑ” نَصَحُوا۟ ሲሆን ለአላህ እና ለመልእክተኛው “ቅንነትን”sincerity” ለማመልከት መጥቷል። በተመሳሳይም በነቢያችን”ﷺ” ንግግር ውስጥ “ነሲሓህ” نَّصِيحَة ማለት “ቅንነት” በሚል መጥቷል፦
ሡነን ነሣኢ መጽሐፍ 39 , ሐዲስ 49
ተሚም አድ-ዳሪይ እንደተረከው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ “ዲን ነሲሓህ ነው። ባልደረቦችም፦ "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ነሲሓህ ለማን ነው? ብለው አሉ። እርሳቸው፦ “ለአላህ፣ ለመጽሐፍቱ፣ ለመልእክተኞቹ፣ ለሙስሊሞች ኢማም እና ለጋራ ሕዝቦቻቸው” አሉ። عَنْ تَمِيمٍ الدَّارِيِّ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّمَا الدِّينُ النَّصِيحَةُ ‏”‏ ‏.‏ قَالُوا لِمَنْ يَا رَسُولَ اللَّهِ قَالَ ‏”‏ لِلَّهِ وَلِكِتَابِهِ وَلِرَسُولِهِ وَلأَئِمَّةِ الْمُسْلِمِينَ وَعَامَّتِهِمْ ‌‏.‏

እምላካችን አላህ በምክርና በመመካከር የምንመክርና የምንመካከር ሙእሚን ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
በሃይማኖት ማስገደድ የለም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

2፥256 በሃይማኖት ማስገደድ የለም፡፡ *ቅኑ መንገድ ከጠማማው በእርግጥ ተገለጠ*፡፡ لَا إِكْرَاهَ فِي الدِّينِ ۖ قَد تَّبَيَّنَ الرُّشْدُ مِنَ الْغَيِّ ۚ

እዚህ ቪድዮ የምትመከቱአቸው ስለ ኢሥላም ተነግሯቸው ሸሃዳ የያዙ ክርስቲያኖች ናቸው። ነገር ግን ሚድያ ላይ ተገደው እንደሰለሙ እንደ በቀቀን እይተደጋገመ እየተቀጠፈ ነው። እሥልምናን በምን እናጠልሸው ነው? አይሳካላችሁም። አንተ እራስክ ተገደህ ብትቀይር ልብህ ካልተቀየረ እስልምናውን አላህ ዘንድ ተቀባይነት የለውም። ወደ ኢሥላም በሦስት ምክንያት የሚገባ ሰው እሥልምናው ተቀባይነት የለውም። አንደኛ ለተቃራኒው ጾታ ብሎ፣ ሁለተኛ ለገንዘብ ብሎ፣ ሦስተኛ ተገዶ። ኢሥላም በግድ እመኑ ብሎ ምንሽርና ዝናር አይታጠቅም፥ በቀረርቶ፣ በሽለላ በፉከራ አያስገድድም፤ ምክንያቱም በሃይማኖት ማስገደድ የለም፤ የፈለገ ያምናል፥ ያልፈለገ ይክዳል፥ በኃላ የትንሳኤ ቀን የሚተሳሰበው አላህ ነው፦
2፥256 በሃይማኖት ማስገደድ የለም፡፡ *ቅኑ መንገድ ከጠማማው በእርግጥ ተገለጠ*፡፡ لَا إِكْرَاهَ فِي الدِّينِ ۖ قَد تَّبَيَّنَ الرُّشْدُ مِنَ الْغَيِّ ۚ
18፥29 *«እውነቱም ከጌታችሁ ነው፡፡ የሻም ሰው ይመን፤ የሻም ሰው ይካድ»* በላቸው፡፡ وَقُلِ الْحَقُّ مِن رَّبِّكُمْ ۖ فَمَن شَاءَ فَلْيُؤْمِن وَمَن شَاءَ فَلْيَكْفُر
10፥99 ጌታህም በሻ ኖሮ በምድር ያሉት ሰዎች ሁሉም የተሰበሰቡ ሆነው ባመኑ ነበር፡፡ *ታዲያ አንተ ሰዎችን አማኞች እንዲኾኑ ታስገድዳለህን?* وَلَوْ شَآءَ رَبُّكَ لَـَٔامَنَ مَن فِى ٱلْأَرْضِ كُلُّهُمْ جَمِيعًا ۚ أَفَأَنتَ تُكْرِهُ ٱلنَّاسَ حَتَّىٰ يَكُونُوا۟ مُؤْمِنِينَ
11፥28 «ሕዝቦቼ ሆይ! ንገሩኝ ከጌታዬ በግልጽ ማስረጃ ላይ ብሆን ከእርሱም ዘንድ የሆነን ችሮታ ነብይነት ቢሰጠኝ እና በእናንተ ላይ ብትደበቅባችሁ *እናንተ ለእርሷ ጠይዎች ስትሆኑ እርሷን በመቀበል እናስገድዳችኋለን?*» አላቸው፡፡ قَالَ يَٰقَوْمِ أَرَءَيْتُمْ إِن كُنتُ عَلَىٰ بَيِّنَةٍۢ مِّن رَّبِّى وَءَاتَىٰنِى رَحْمَةًۭ مِّنْ عِندِهِۦ فَعُمِّيَتْ عَلَيْكُمْ أَنُلْزِمُكُمُوهَا وَأَنتُمْ لَهَا كَٰرِهُونَ

ነቢያችንም”ﷺ” ከጌታቸው ወደ እርሳቸው የወረደውን መልእክት ግልጽ ማድረስ እንጅ ሌላ የለባቸውም፦
17፥15 *መልእክተኛንም እስከምንልክ ድረስ የምንቀጣ አይደለንም*፡፡ وَمَا كُنَّا مُعَذِّبِينَ حَتَّىٰ نَبْعَثَ رَسُولًا
5፥67 *አንተ መልክተኛ ሆይ! ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደውን አድርስ፡፡ ባትሠራም መልክቱን አላደረስክም*፡፡ َيَا أَيُّهَا الرَّسُولُ بَلِّغْ مَا أُنزِلَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ ۖ وَإِن لَّمْ تَفْعَلْ فَمَا بَلَّغْتَ رِسَالَتَهُ
5፥99 *በመልእክተኛው ላይ ማድረስ እንጅ ሌላ የለበትም፡፡ አላህም የምትገልጹትን ነገር የምትደብቁትንም ሁሉ ያውቃል*፡፡ مَّا عَلَى الرَّسُولِ إِلَّا الْبَلَاغُ ۗ وَاللَّهُ يَعْلَمُ مَا تُبْدُونَ وَمَا تَكْتُمُونَ
16፥82 *ከኢስላም ቢሸሹም በአንተ ላይ ያለብህ ግልጽ ማድረስ ብቻ ነው*፡፡ فَإِن تَوَلَّوْا فَإِنَّمَا عَلَيْكَ الْبَلَاغُ الْمُبِينُ

የባልቴት እና የወይዛዝርት የቡና ወሬ ከትልቅ እስከ ደቂቅ ያለ አንዳች ከልካይ ማዛመቱ ይገርማል። እኛም እውነትን መግለጥ ሐሰትን ማጋለጥ ተቀዳሚ ተግባራችን ይሁን! ሚድያ ለውሸት ምን ያህል አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳለው ካያችሁ ለእውነት አውንታዊ ተጽዕኖ ለማምጣት ሁላችንም ሼር እናርገው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሱረቱል ፋቲሓህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

15፥87 *ከሚደጋገሙ የኾኑን ሰባትን እና ታላቁንም ቁርኣን በእርግጥ ሰጠንህ*፡፡ وَلَقَدْ آتَيْنَاكَ سَبْعًا مِّنَ الْمَثَانِي وَالْقُرْآنَ الْعَظِيمَ

አምላካችን አላህ “ሙርሲል” مُرْسِل ማለትም “ላኪ” ነው፤ ነብያችን”ﷺ” ደግሞ “ረሱል” رِسَالَة ማለትም “መልክተኛው” ናቸው፤ እንዲሁ ቁርኣን የአላህ “ሪሳላ” رِسَالَ ማለትም “መልእክት” ነው። የመልእክቱ “ሙአለፍ” مؤلف ማለትም “አመንጪ”author” አምላካችን አላህ ሲሆን፤ ነብያችን”ﷺ” ደግሞ የመልእክቱ “ሙራሲል” مراسل ማለት “አስተላላፊ”reporter” ናቸው፤ አምላካችን አላህ ለነብያችን”ﷺ”፦ “ቁል” قُلْ ማለትም “በል” በሚል ትዕዛዛዊ ግስ ያዛቸዋል፦
112፥1 *በል «እርሱ አላህ አንድ ነው*፡፡ قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ
13፥30 እንደዚሁ ከበፊትዋ ብዙ ሕዝቦች በእርግጥ ያለፉ ወደኾነችው ሕዝብ እነርሱ በአልረሕማን የሚክዱ ሲኾኑ ያንን *ወደ አንተ ያወረድነውን ቁርኣን በእነርሱ ላይ ታነብላቸው ዘንድ ላክንህ፡፡ «እርሱ አልረሕማን ጌታዬ ነው፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ በእርሱ ላይ ተጠጋሁ፡፡ መመለሻዬም ወደ እርሱ ብቻ ነው» በላቸው*፡፡ كَذَٰلِكَ أَرْسَلْنَاكَ فِي أُمَّةٍ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهَا أُمَمٌ لِّتَتْلُوَ عَلَيْهِمُ الَّذِي أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ وَهُمْ يَكْفُرُونَ بِالرَّحْمَـٰنِ ۚ قُلْ هُوَ رَبِّي لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ عَلَيْهِ تَوَكَّلْتُ وَإِلَيْهِ مَتَابِ

“ወደ አንተ ያወረድነውን ቁርኣን በእነርሱ ላይ ታነብላቸው ዘንድ ላክንህ” የሚለው ሃይለ-ቃል ቁርኣንን አውራጅና ነብያችንን”ﷺ” ላኪው አላህ እራሱ “በል” ማለቱን እንረዳለን፤ በመቀጠል እዛው አንቀጽ ላይ “ቁል” قُلْ ብሎ መናገሩ በራሱ “በል” የሚለው ማንነት አላህ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፤ በተጨማሪም “በልን” ወደ ነብያችን”ﷺ” የሚጥለው እራሱ እንደሆነ ይናገራል፦
73፥5 *እኛ በአንተ ላይ ከባድ ቃልን እንጥላለንና*፡፡ إِنَّا سَنُلْقِي عَلَيْكَ قَوْلًا ثَقِيلًا

እዚህ አንቀጽ ላይ “ቃል” ለሚለው የተቀመው ቃላት “ቀውል” قَوْل ሲሆን “ቁል” قُلْ ከሚል ትዕዛዛዊ ግስ የመጣ ነው፤ ስለዚህ “በል” እያለ የሚያስነብባቸው እራሱ አላህ ነው፤ ሱረቱል ፋቲሓህ የሚደጋገሙ ሰባት አንቀጾች ናት፤ ምክንያቱም ሱረቱል ፋቲሓህ ሰባት አናቅጽ አላት፤ በተጨማሪም ነብያችን”ﷺ” ሱረቱል ፋቲሓህ የሚደጋገሙ ሰባት አንቀጾች ናት ብለው ነግረውናል፦
15፥87 *ከሚደጋገሙ የኾኑን ሰባትን እና ታላቁንም ቁርኣን በእርግጥ ሰጠንህ*፡፡ وَلَقَدْ آتَيْنَاكَ سَبْعًا مِّنَ الْمَثَانِي وَالْقُرْآنَ الْعَظِيمَ
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 66, ሐዲስ 28
አቢ ሠዒድ ኢብኑ ሙዐላ እንደተረከው *ሶላት ላይ ሆኜ ነብዩ”ﷺ” ጠሩኝ፤ ነገር ግን ጥሪያቸውን አልመለስኩላቸውም፤ በኃላ ላይ፦ “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ሶላት ላይ ነበርኩኝ” አልኩኝ፤ እሳቸውም፦ አላህ፦ “(መልእክተኛው) በጠራችሁ ጊዜ ለአላህ እና ለመልክተኛው ታዘዙ”8፥24 አላለምን? ከዚያም፦ “በቁርኣን ውስጥ ታላቂቱን ሱራህ ላስተምርህን? እርሷም፦ “ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው የምትለዋ የሚደጋገሙ የሆኑ ሰባት ሱረቱል ፋቲሐህን እና ታላቁ ቁርኣንን ተሰጠኝ”*። عَنْ أَبِي سَعِيدِ بْنِ الْمُعَلَّى، قَالَ كُنْتُ أُصَلِّي فَدَعَانِي النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم فَلَمْ أُجِبْهُ قُلْتُ يَا رَسُولَ اللَّهِ إِنِّي كُنْتُ أُصَلِّي‏.‏ قَالَ ‏”‏ أَلَمْ يَقُلِ اللَّهُ ‏{‏اسْتَجِيبُوا لِلَّهِ وَلِلرَّسُولِ إِذَا دَعَاكُمْ‏}‏ ثُمَّ قَالَ أَلاَ أُعَلِّمُكَ أَعْظَمَ سُورَةٍ فِي الْقُرْآنِ قَبْلَ أَنْ تَخْرُجَ مِنَ الْمَسْجِدِ ‏”‌‏.‏ فَأَخَذَ بِيَدِي فَلَمَّا أَرَدْنَا أَنْ نَخْرُجَ قُلْتُ يَا رَسُولَ اللَّهِ إِنَّكَ قُلْتَ لأُعَلِّمَنَّكَ أَعْظَمَ سُورَةٍ مِنَ الْقُرْآنِ‏.‏ قَالَ ‏”‌‏{‏الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ‏}‏ هِيَ السَّبْعُ الْمَثَانِي وَالْقُرْآنُ الْعَظِيمُ الَّذِي أُوتِيتُهُ ‏”‌‏.‏
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3415
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *አል-ሐምዱሊሏህ የቁርኣን እናት፣ የመጽሐፉ እናት እና ሰባት የተደጋገሙ ናት*። عَنِ ابْنِ أَبِي ذِئْبٍ، عَنِ الْمَقْبُرِيِّ، عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْحَمْدُ لِلَّهِ أُمُّ الْقُرْآنِ وَأُمُّ الْكِتَابِ وَالسَّبْعُ الْمَثَانِي ‏”

ሱረቱል ፋቲሓህ ላይ ከሚሽነሪዎች የሚነሳው ጥያቄ “ቀጥተኛውን መንገድ ምራን“ የሚለው የአላህ ንግግር ከሆነ አላህ ማንን ነው ምራን የሚለው? የሚል ነው፤ መልሱ “ቀጥተኛውን መንገድ ምራን” እኛ እንድንል ለእኛ ያለው ነው፤ ይህንም “ቁል” قُلْ የሚል ትዕዛዛዊ ግስ “ሙስተቲር” ْمُسْتَتِر ማለትም “ህቡዕ-ግስ”headen verb” ሆኖ የመጣ ነው፦
1፥6 *ቀጥተኛውን መንገድ ምራን*፡፡ اهْدِنَا الصِّرَاطَ الْمُسْتَقِيمَ
“ኢህዲና” اهْدِنَا ማለትም “ምራን” ብዙ ቁጥር ሲሆን ይህ ባለቤት ግስ አማኞችን ያመለክታል፤ ተሳቢው ግስ ደግሞ መሪውን አላህን ያመለክታል፤ ስለዚህ “ቁሉ” قُلُوا የሚለው ሙስተቲር ሆኖ የመጣ ነው፤ ለምሳሌ በሱረቱል በቀራህ 2፥187 ላይ “ከተበ” كَتَبَ ማለትም “ጻፈ” የሚለውን ወደ ኢንግሊሽ ሲቀየር “He wrote” ነው፣ “He” ደግሞ ወደ ዐረቢኛ “ሁወ” هُوَ ማለትም “እርሱ” ነው፤ “ሁወ” هُوَ የሚለው “ከተበ” كَتَبَ ላይ ሙስተቲር ሆኖ የመጣ ነው፤ “ቁል” ወይም “ቁሉ” ተደብቀው በሙስተቲር የሚመጡበት ብዙ ቦታ ነው፦
11፥2 *አላህን እንጂ ሌላን አታምልኩ፤ እኔ ለእናንተ ከእርሱ የተላክሁ አስጠንቃቂ እና አብሳሪ ነኝ*፡፡ أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا اللَّهَ ۚ إِنَّنِي لَكُم مِّنْهُ نَذِيرٌ وَبَشِيرٌ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ቁል” የሚለው የለም፤ ያ ማለት “አስጠንቃቂ እና አብሳሪ ነኝ” የሚለው አላህ ነው ማለት ቂልነት ነው፤ ምክንያቱም “ሚንሁ” مِّنْهُ የሚል ሃይለ-ቃል አለ፤ “ሚን” مِّن ማለት “ከ” ሲሆን መስተዋድድ ነው፤ በሚን ላይ “ሁ” هُ ማለት “እርሱ” የሚል ተሳቢ አለ፤ “እርሱ” የተባለው ላኪ አላህ ነው “አስጠንቃቂ እና አብሳሪ ነኝ” የሚሉት ደግሞ የተላኩት ነብያችን”ﷺ” ናቸው፦
35፥24 *እኛ አብሳሪ እና አስጠንቃቂ አድርገን በእውነቱ ላክንህ*፡፡ إِنَّا أَرْسَلْنَاكَ بِالْحَقِّ بَشِيرًا وَنَذِيرًا
7፥188 *እኔ ለሚያምኑ ሕዝቦች አስጠንቃቂ እና አብሳሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም» በላቸው*፡፡ قُل لَّا أَمْلِكُ لِنَفْسِي نَفْعًا وَلَا ضَرًّا إِلَّا مَا شَاءَ اللَّهُ ۚ وَلَوْ كُنتُ أَعْلَمُ الْغَيْبَ لَاسْتَكْثَرْتُ مِنَ الْخَيْرِ وَمَا مَسَّنِيَ السُّوءُ ۚ إِنْ أَنَا إِلَّا نَذِيرٌ وَبَشِيرٌ لِّقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ

“በል” ሳይል በአንድ አንቀጽ ላይ በውስጠ ታዋቂነት “እኔም በእናንተ ላይ ጠባቂ አይደለሁም” ይልና፤ ሌላ አንቀጽ ላይ “እኔም በእናንተ ላይ ጠባቂ አይደለሁም በል” የሚል ይጠቀማል፦
6፥104 *እኔም በእናንተ ላይ ጠባቂ አይደለሁም*፡፡ وَمَا أَنَا عَلَيْكُم بِحَفِيظٍ
6፥66 *በላቸው፡- «በእናንተ ላይ ጠባቂ አይደለሁም፡፡»* قُل لَّسْتُ عَلَيْكُم بِوَكِيلٍ

“በል” ሳይል በአንድ አንቀጽ ላይ በውስጠ ታዋቂነት “እኔም የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ” ይልና፤ ሌላ አንቀጽ ላይ “እኔም የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ በል” የሚል ይጠቀማል፦
6፥163 *«ለእርሱ ተጋሪ የለውም፡፡ በዚህም በማጥራት ታዘዝኩ፡፡ እኔም የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ»*፡፡ لَا شَرِيكَ لَهُ ۖ وَبِذَٰلِكَ أُمِرْتُ وَأَنَا أَوَّلُ الْمُسْلِمِينَ
39፥11 *በል* «እኔ አላህን ሃይማኖትን ለርሱ ያጠራሁ ኾኜ እንድግገዛው ታዘዝኩ፡፡ قُلْ إِنِّي أُمِرْتُ أَنْ أَعْبُدَ اللَّهَ مُخْلِصًا لَّهُ الدِّينَ
39፥12 *«የሙስሊሞችም መጀመሪያ እንድኾን ታዘዝኩ፡፡»* وَأُمِرْتُ لِأَنْ أَكُونَ أَوَّلَ الْمُسْلِمِينَ

ይህንን ከተረዳን ሱረቱል ፋቲሓህ ላይ “አንተን” ብለው በሚሉት ላይ “በል” ሳይል ሌላ አንቀጽ ላይ “አንተ በል” የሚል ይጠቀማል፦
3፥26 *በል*፡- «የንግስና ባለቤት የኾንክ አላህ ሆይ! ለምትሻው ሰው ንግሥናን ትሰጣለህ፡፡ ከምትሻውም ሰው ንግሥናን ትገፍፋለህ፡፡ የምትሻውንም ሰው ታልቃለህ፡፡ የምትሻውንም ሰው ታዋርዳለህ፡፡ መልካም ነገር ሁሉ በእጅህ በችሎታህ ነው፤ *”አንተ”* በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነህና፡፡ قُلِ اللَّهُمَّ مَالِكَ الْمُلْكِ تُؤْتِي الْمُلْكَ مَن تَشَاءُ وَتَنزِعُ الْمُلْكَ مِمَّن تَشَاءُ وَتُعِزُّ مَن تَشَاءُ وَتُذِلُّ مَن تَشَاءُ ۖ بِيَدِكَ الْخَيْرُ ۖ إِنَّكَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
በተጨማሪም ነብያችን”ﷺ” በሐዲስ ላይ ሱረቱል ፋቲሓን የሚለው የአላህ ባሪያ ወደ አላህ መሆኑን በግልጽ እና በማያሻማ መልኩ ነግረውናል፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 4 ሐዲስ 41
አቢ ሁረይራ”ረ.ዐ” እንደተረከው *ነብዩ”ﷺ” አሉ፦ “የቁርአን እናት ሳያነብ የሰገደ ሰው ሶላቱ ጎዶሎ ነው”* አንድ ሰው ለአቢ ሁረይራ፦ “ከአሰጋጁ በኋላ ብንሆንም እንኳን”? አለው፤ እርሱም አለ፦ “ለራስህ አንብብ ምክንያቱም ነብዩ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁና፦ *”ኃያሉና የተከበረው አላህ እንዲህ ብሏል፦ “ሶላትን በእኔ እና በባሪያዬ መካከል ለሁለት ከፍየዋለሁ እናም ባሪያዬ የጠየቀውን ያገኛል*፤ ባሪያው፦ *”ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው” ሲል አላህ፦ “ባሪያዬ አመሰገነኝ” ይላል*፤ ባሪያው፦ *”እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ” ሲል ደግሞ አላህ፦ “ባሪያዬ አሞገሰኝ’ ይላል*፤ ባሪያው፦ *”የፍርዱ ቀን ባለቤት ለኾነው” ሲል አላህ፦ ባሪያዬ አላቀኝ” ይላል*፤ ባሪያው፦ *”አንተን ብቻ እንግገዛለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን” በሚል ግዜ አላህ፦ “ይህ በእኔ እና በባሪያዬ መካከል ነው እናም ባሪያዬ የጠየቀውን ያገኛል” ይላል*፤ ባሪያው፦ *”ቀጥተኛውን መንገድ ምራን የእነዚያን በእነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን በእነርሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ ምራን” በሚል ግዜ ደግሞ አላህ፦ “ይህ ለባሪያዬ ነው፤ እናም ባሪያዬ የጠየቀውን ያገኛል” ይላል*፡፡ عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏”‏ مَنْ صَلَّى صَلاَةً لَمْ يَقْرَأْ فِيهَا بِأُمِّ الْقُرْآنِ فَهْىَ خِدَاجٌ – ثَلاَثًا – غَيْرُ تَمَامٍ ‏”‏ ‏.‏ فَقِيلَ لأَبِي هُرَيْرَةَ إِنَّا نَكُونُ وَرَاءَ الإِمَامِ ‏.‏ فَقَالَ اقْرَأْ بِهَا فِي نَفْسِكَ فَإِنِّي سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏”‏ قَالَ اللَّهُ تَعَالَى قَسَمْتُ الصَّلاَةَ بَيْنِي وَبَيْنَ عَبْدِي نِصْفَيْنِ وَلِعَبْدِي مَا سَأَلَ فَإِذَا قَالَ الْعَبْدُ ‏{‏ الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ‏}‏ ‏.‏ قَالَ اللَّهُ تَعَالَى حَمِدَنِي عَبْدِي وَإِذَا قَالَ ‏{‏ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ‏}‏ ‏.‏ قَالَ اللَّهُ تَعَالَى أَثْنَى عَلَىَّ عَبْدِي ‏.‏ وَإِذَا قَالَ ‏{‏ مَالِكِ يَوْمِ الدِّينِ‏}‏ ‏.‏ قَالَ مَجَّدَنِي عَبْدِي – وَقَالَ مَرَّةً فَوَّضَ إِلَىَّ عَبْدِي – فَإِذَا قَالَ ‏{‏ إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ‏}‏ ‏.‏ قَالَ هَذَا بَيْنِي وَبَيْنَ عَبْدِي وَلِعَبْدِي مَا سَأَلَ ‏.‏ فَإِذَا قَالَ ‏{‏ اهْدِنَا الصِّرَاطَ الْمُسْتَقِيمَ * صِرَاطَ الَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلاَ الضَّالِّينَ‏}‏ ‏.‏ قَالَ هَذَا لِعَبْدِي وَلِعَبْدِي مَا سَأَلَ ‏”‏ ‏.‏ قَالَ سُفْيَانُ حَدَّثَنِي بِهِ الْعَلاَءُ بْنُ عَبْدِ الرَّحْمَنِ بْنِ يَعْقُوبَ دَخَلْتُ عَلَيْهِ وَهُوَ مَرِيضٌ فِي بَيْتِهِ فَسَأَلْتُهُ أَنَا عَنْهُ ‏.‏

በዚህ መልኩ መረዳት ካልቻላችሁ የተለያየ ናሙና ከባይብል ላቅርብ፦
ዮሐንስ 20፥17 ኢየሱስም፦ ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ፦ እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ *ዓርጋለሁ ብለሽ ንገሪአቸው* አላት።

ወደ አምላኩ አራጊው ኢየሱስ ሆኖ ሳለ “ዓርጋለሁ ብለሽ ንገሪአቸው” ሲላት አራጊዋ መቅደላዊት ማርያም ሆና ነውን? አይ “ይላል” በይ ለማለት ተፈልጎ ነው ከተባለ “ይላል” የሚለውን የት አለ? በውስጠ-ታዋቂነት ይኖራል ከሆነ መልሱ እንግዲያውስ ሱረቱል ፋቲሐህንም በዚህ መልኩ መረዳት ይቻላል። ያለበለዚያ አራጊዋ መቅደላዊት ማርያም ትሆናለች። ከተባለ እንግዲያውስ ከላይ ያለውን በዚህ መልክና ልክ ተረዱት። ሕዝቅኤል፦ “እኔ ወደ አሕዛብ አርቄአቸዋለሁ” በል ተብሏል፦
ሕዝቅኤል 11፥16 ስለዚህ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ወደ አሕዛብ አርቄአቸዋለሁ፥ ወደ አገሮችም በትኛቸዋለሁ፤ ይሁን እንጂ፥ በመጡባቸው አገሮች በእነዚያ ትንሽ መቅደስ እሆናቸዋለሁ በል።

“እኔ ወደ አሕዛብ አርቄአቸዋለሁ” የሚለው ሕዝቅኤል ነውን? አይ አይ “ይላል” በል ለማለት ተፈልጎ ነው ከሆነ መልሱ፥ “ይላል” የሚለው የት አለ? ስንል በውስጠ ታዋቂነት አለ ከተባለ እንግዲያውስ ከላይ ያለውን በዚህ ስሌትና ቀመር ተረዱት። እግዚአብሔርም ሙሴን፦ “እኔም እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ” በላቸው” አለው፦
ዘጸአት 16 ፥11-12 *እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦* የእስራኤልን ልጆች ማንጐራጐር ሰማሁ፦ ወደ ማታ ሥጋን ትበላላችሁ፥ ማለዳም እንጀራን ትጠግባላችሁ፤ *እኔም እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ” በላቸው*።

“እኔም እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ” የሚለው ሙሴ ነውን? አይ “ይላል” በል ለማለት ተፈልጎ ነው ከሆነ መልሱ፥ “ይላል” የሚለው የት አለ? ስንል በውስጠ ታዋቂነት አለ ከተባለ እንግዲያውስ ከላይ ያለውን በዚህ ሒሳብ ተረዱት።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የቁርኣን ትንቢት

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

36፥36 ያ ምድር ከምታበቅለው፣ ከራሶቻቸውም፣ *ከማያውቁትም ነገር ጥንዶችን ሁሏንም የፈጠረ ጥራት ይገባው*፡፡ سُبْحَانَ الَّذِي خَلَقَ الْأَزْوَاجَ كُلَّهَا مِمَّا تُنبِتُ الْأَرْضُ وَمِنْ أَنفُسِهِمْ وَمِمَّا لَا يَعْلَمُونَ

“ዘውጅ” زَوْج የሚለው ቃል. "ዘወጀ" زَوَّجَ ማለትም "ተጠናዳ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ጥንድ” “ባል” “ሚስት” ተብሎ ተቀምጧል፦
58:1 አላህ የዚያችን *በባልዋ* ነገር የምትከራከርህንና ወደአላህ የምታስሙተውን ቃል በእርግጥ ሰማ። قَدْ سَمِعَ ٱللَّهُ قَوْلَ ٱلَّتِى تُجَٰدِلُكَ فِى زَوْجِهَا وَتَشْتَكِىٓ إِلَى ٱللَّهِ وَٱللَّهُ يَسْمَعُ تَحَاوُرَكُمَآ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ سَمِيعٌۢ بَصِيرٌ
7:19 አዳምም ሆይ! አንተም *ሚስትህም* ከገነት ተቀመጡ፤ وَيَٰٓـَٔادَمُ ٱسْكُنْ أَنتَ وَزَوْجُكَ ٱلْجَنَّةَ فَكُلَا مِنْ حَيْثُ شِئْتُمَا وَلَا تَقْرَبَا هَٰذِهِ ٱلشَّجَرَةَ فَتَكُونَا مِنَ ٱلظَّٰلِمِينَ
35:11 አላህም ከዐፈር፣ ከዚያም ከፍትወት ጠብታ ፈጠራችሁ፤ *ከዚያም ጥንዶች አደረጋችሁ*፤ وَٱللَّهُ خَلَقَكُم مِّن تُرَابٍۢ ثُمَّ مِن نُّطْفَةٍۢ ثُمَّ جَعَلَكُمْ أَزْوَٰجًۭا
53:45 እርሱም *ሁለቱን ዓይነቶችን ወንድ እና ሴትን ፈጠረ*። وَأَنَّهُۥ خَلَقَ ٱلزَّوْجَيْنِ ٱلذَّكَرَ وَٱلْأُنثَىٰ

“ዘውጀይኒ” زَّوْجَيْنِ ሙሰና ሲሆን ሁለት የወንድ እና የሴት ዓይነቶች በሚል መጥቷል፥ “ባልዋ” ለሚለው ቃል የገባው “ዘውጂሃ” زَوْجِهَا መሆኑ እና “ሚስትህ” ለሚለው ቃል የገባው ደግሞ “ዘውጅከ” َزَوْجُكَ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። "ተዝዊጅ" تَزْوِيج ማለት በራሱ "ጥንድነት" ማለት ሲሆን "ዘዋጅ" زَوَاج ማለት ደግሞ "ጋብቻ" "ሰርግ" ማለት ነው። እዚህ ድረስ ከተግባባን አምላካችን አላህ ለእኛ ከእጽዋት ልክ እንደ ሰው የተባእት እና የእንስት ህዋስ”gamete” ፈጥሯል። አላህ በዕፅዋት መካከል ጥንድ የሆኑ ተቃራኒ ጾታዎች እንዳሉ ለማመልከት “ዘውጀይኒ” زَوْجَيْنِ በማለት ይናገራል፦
13፥3 እርሱም ያ ምድርን የዘረጋ በእሷም ተራራዎችን እና ወንዞችን ያደረገ *በውስጧም "ከ"ፍሬዎች ሁሉ ሁለት ሁለት ጥንዶችን ያደረገ ነው*፡፡ ሌሊትን በቀን ይሸፍናል፡፡ *በዚህም ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች ታምራቶች አሉ*፡፡ وَهُوَ الَّذِي مَدَّ الْأَرْضَ وَجَعَلَ فِيهَا رَوَاسِيَ وَأَنْهَارًا ۖ وَمِن كُلِّ الثَّمَرَاتِ جَعَلَ فِيهَا زَوْجَيْنِ اثْنَيْنِ ۖ يُغْشِي اللَّيْلَ النَّهَارَ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ

“ኩል” كُلٌّ ማለትም “ሁሉ” የሚለው ቃል ፍጹማዊ “Absolute” ሆኖ ሲመጣ “ሙጥለቅ” مُطْلَق ሲባል፥ በአንጻራዊ “Relative” ሆኖ ሲመጣ ደግሞ “ቀሪብ” قَرِيب‎ ይባላል፥ እዚህ አንቀጽ ላይ "ኩል" ቀሪብ ሆኖ የምናውቀው "ሁሉ" በሚለው ገላጭ ቅጽል መነሻ ላይ "ሚን" مِن ማለትም "ከ" የሚል መስተዋድድ መኖሩ ነው። "ከ"ፍሬዎች ሁሉ" ማለት እና "ፍሬዎች ሁሉ" ማለት ሁለት ለየቅል ትርጉም አላቸው፥ ከፍራፍሬዎች መካከል ጥንድ ያልሆኑ በከፊል መኖራቸው ይህንኑ ያሳያል። ነቢያችን”ﷺ” በተላኩበት ጊዜ ላይ "ዕፅዋት ጾታ አላቸው" ብሎ ማንም ሰው ዐያውቅም ነበር፥ በዚህ ጊዜ አምላካችን አላህ ሁሉን ዐዋቂ በመሆኑ “ዘውጀይኒ” በማለት ዕፅዋት ጥንዶች እንደሆኑ ነግሮናል፦
36፥36 ያ ምድር ከምታበቅለው፣ ከራሶቻቸውም፣ *ከማያውቁትም ነገር ጥንዶችን ሁሏንም የፈጠረ ጥራት ይገባው*፡፡ سُبْحَانَ الَّذِي خَلَقَ الْأَزْوَاجَ كُلَّهَا مِمَّا تُنبِتُ الْأَرْضُ وَمِنْ أَنفُسِهِمْ وَمِمَّا لَا يَعْلَمُونَ

"ከማያውቁትም ነገር ጥንዶችን" ማለት በቁርኣን መውረድ ጊዜ የዕጽዋት ጥንድነት ዐለመታወቁን ያሳያል። አምላካችን አላህ ጊዜው ሲደርስ በ 19ኛው ክፍለ ዘመን ላይ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች ታምራት ይሆን ዘንድ ዕፅዋት ጾታ እንዳላቸው ዐሳውቆናል። “ጋይኒ” γυνή ማለት “ሴቴ” ማለት ሲሆን ይህቺ የዕፅዋት እንቁላል ህዋስ”gynoecious” በሥነ-ሕይወት ጥናት “ካርፔልስ”carpels” ትባላለች፥ “አንድሮ” ἀνήρ ማለት “ወንዴ” ማለት ሲሆን የዕፅዋት የዘር ህዋስ”Androecium” በሥነ-ሕይወት ጥናት “ስቴመንስ”stamens” ይባላል። ቁርኣን ከያዛቸው መካከል “አል-ገይቡል ሙሥተቅበል” ٱلْغَيْب ٱلْمُسْتَقْبَل ማለትም “መጻእያት የሩቅ ወሬ” ነው፥ ይህንን ትንቢት ከጊዜ በኋላ በእርግጥ ታውቁታላችሁ ባለን መሠረት ዛሬ በዘመናችን ዐውቀነዋል፦
38፥88 *«ትንቢቱንም ከጊዜ በኋላ በእርግጥ ታውቁታላችሁ፡፡* وَلَتَعْلَمُنَّ نَبَأَهُ بَعْدَ حِينٍ
6፥67 *ለትንቢት ሁሉ የሚደርስበት መርጊያ አለው፡፡ ወደፊትም ታውቁታላችሁ*፡፡ لِّكُلِّ نَبَإٍ مُّسْتَقَرٌّ ۚ وَسَوْفَ تَعْلَمُونَ

አምላካችን አላህ የነገረን "ከፍሬዎች ሁሉ ሁለት ሁለት ጥንዶችን" መሆናቸውን ብቻ ሳይሆን በዕጽዋት ውስጥ "ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች ታምራቶች አሉ" ይህንን ታምራት "ወደፊት ያሳያችኋል፥ ታውቁታላችሁ" ብሎ በነገረን መሠረት ዛሬ ይህንን ዐይተንማል፥ ዐውቀንማል። ምስጋናም ለአላህ ነው፦
13፥3 እርሱም ያ ምድርን የዘረጋ በእሷም ተራራዎችን እና ወንዞችን ያደረገ *በውስጧም "ከ"ፍሬዎች ሁሉ ሁለት ሁለት ጥንዶችን ያደረገ ነው*፡፡ ሌሊትን በቀን ይሸፍናል፡፡ *በዚህም ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች ታምራቶች አሉ*፡፡ وَهُوَ الَّذِي مَدَّ الْأَرْضَ وَجَعَلَ فِيهَا رَوَاسِيَ وَأَنْهَارًا ۖ وَمِن كُلِّ الثَّمَرَاتِ جَعَلَ فِيهَا زَوْجَيْنِ اثْنَيْنِ ۖ يُغْشِي اللَّيْلَ النَّهَارَ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ
6፥93 ምስጋናም ለአላህ ነው፡፡ *"ተዓምራቶቹን ወደፊት ያሳያችኋል፡፡ «ታውቁታላችሁ»* በላቸው፡፡ ጌታህም ከምትሠሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም፡፡ وَقُلِ الْحَمْدُ لِلَّهِ سَيُرِيكُمْ آيَاتِهِ فَتَعْرِفُونَهَا ۚ وَمَا رَبُّكَ بِغَافِلٍ عَمَّا تَعْمَلُونَ

ኢንሻሏህ ይቀጥላል.....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የቁርኣን ትንቢት

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

16፥8 *"ፈረሶችንም፣ በቅሎዎችንም፣ አህዮችንም ልትቀመጡዋቸውና ልታጌጡባቸው ፈጠረላችሁ፡፡ የማታውቁትንም ድንቅ ነገር ይፈጥራል"*፡፡ وَالْخَيْلَ وَالْبِغَالَ وَالْحَمِيرَ لِتَرْكَبُوهَا وَزِينَةً ۚ وَيَخْلُقُ مَا لَا تَعْلَمُونَ

ቁርአን በወረደበት ጊዜ ባሕላዊ መጓጓዣ ፈረሶች፣ በቅሎዎች፣ አህዮች ናቸው፦
16፥8 *"ፈረሶችንም፣ በቅሎዎችንም፣ አህዮችንም ልትቀመጡዋቸው እና ልታጌጡባቸው ፈጠረላችሁ፡፡ የማታውቁትንም ድንቅ ነገር ይፈጥራል"*፡፡ وَالْخَيْلَ وَالْبِغَالَ وَالْحَمِيرَ لِتَرْكَبُوهَا وَزِينَةً ۚ وَيَخْلُقُ مَا لَا تَعْلَمُونَ

”ልትቀመጡ” የሚለው ቃል “ሊተረከቡ” لِتَرْكَبُو ሲሆን “ረኪበ" رَكِبَ ማለትም “ጋለበ” “ተጓዘ” "ተሳፈረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ልትጋልቡ" "ልትጓዙ" "ልትሳፈሩ" የሚል ፍቺ አለው፦
40፥79 አላህ ያ ለእናንተ ግመልን ከብትንና ፍየልን ከእርሷ ከፊሏን *"ልትጋልቡ የፈጠረላችሁ ነው"*፡፡ ከእርሷም ትበላላችሁ፡፡ اللَّهُ الَّذِي جَعَلَ لَكُمُ الْأَنْعَامَ لِتَرْكَبُوا مِنْهَا وَمِنْهَا تَأْكُلُونَ
36፥42 ከመሰሉም በእርሱ *የሚሳፈሩበትን ለእነርሱ ፈጠርንላቸው"*፡፡ وَخَلَقْنَا لَهُم مِّن مِّثْلِهِ مَا يَرْكَبُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "የርከቡነ" يَرْكَبُونَ የሚለው ቃል "ረኪበ رَكِبَ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል። ቁርአን በወረደበት ጊዜ ፈረሶች፣ በቅሎዎች፣ አህዮች ለሰዎች መጋለቢያ፣ መጓጓዣ፣ መሳፈሪያ እንደ ነበሩ፥ በዚህ ዘመን አዲስ መጋለቢያ፣ መጓጓዣ፣ መሳፈሪያ ፈጥሯል። የዘመናችን መጓጓዣ“Trans-port” የሆኑትን የአየር መጓጓዣ”Air- port”፣ የየብስ መጓጓዣ”Geo-port” እና የባህር መጓጓዣ”Hydro-port” ተፈጥረዋል። የአየር መጓጓዣ እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 1799 ድኅረ-ልደት የንስር ወፍ ንድፍ ታይቶ አይሮፕላን የተሠራ ነው፣ የየብስ መጓጓዣ በ 1768 ድኅረ-ልደት አውቶ ሞቢል መኪና የፈረስ ንድፍ ታይቶ ሲሆን በተመሳሳይ ባቡርም በ 1550 ድኅረ-ልደት የአባጨጓሬ ንድፍ ታይቶ የተሠራ ነው፣ የባህር መጓጓዣ ባለ ሞተር “engine” መርከብ 1805 ድኅረ-ልደት የዶልፊን አሳ ንድፍ ታይቶ የተሠራ ነው። አምላካችን አላህ ይህ ክስተት ከመከሰቱ በፊት "የማታውቁትንም ድንቅ ነገር ይፈጥራል" ይለናል። "ይፈጥራል" ለሚለው የገባው ቃል "የኽሉቁ" يَخْلُقُ ሲሆን የወደፊት ግስ ሙሥተቅበል ነው። አላህ ኑሕ የሠራውን መርከብ "ፈጠርን" ብሏል፦
11፥37 አላህም፦ «በጥበቃችንና በትእዛዛችንም ሆነህ *መርከቢቱን ሥራ*፡፡ በእነዚያም በበደሉት ሰዎች ነገር አታናግረኝ እነሱ በእርግጥ ሰማጮች ናቸውና» አለው፡፡ وَاصْنَعِ الْفُلْكَ بِأَعْيُنِنَا وَوَحْيِنَا وَلَا تُخَاطِبْنِي فِي الَّذِينَ ظَلَمُوا ۚ إِنَّهُم مُّغْرَقُونَ
36፥41እኛም የቀድሞ ትውልዳቸውን *በተሞላች መርከብ* ውስጥ የጫን መኾናችን ለእነርሱ ምልክት ነው፡፡ وَآيَةٌ لَّهُمْ أَنَّا حَمَلْنَا ذُرِّيَّتَهُمْ فِي الْفُلْكِ الْمَشْحُونِ
36፥42 ከመሰሉም በእርሱ *የሚሳፈሩበትን ለእነርሱ ፈጠርንላቸው"*፡፡ وَخَلَقْنَا لَهُم مِّن مِّثْلِهِ مَا يَرْكَبُونَ

አላህ ኑሕ የሠራውን መርከብ "ፈጠርን" ካለ ዛሬ በዘመናችን ቁርኣን በወረደበት ጊዜ ያልነበሩትንና የማይታወቁትን ሰዎች የሠሩዋቸውን የአየር መጓጓዣ አይሮፕላን፣ የየብስ መጓጓዣ አውቶ ሞቢል መኪናና ባቡር፣ የባህር መጓጓዣ ባለ ሞተር “engine” መርከብ "ይፈጥራል" ብሎ ማስቀመጡ የሚያጅብ ነው። የሠው ሥራን እራሱ አላህ የፈጠረው ነው፥ “ፊዕል” فِعْل ማለት “ድርጊት”action” ማለት ሲሆን አራት ነገር ናቸው፥ እነርሱም፦ ጊዜ፣ ቦታ፣ ቁስ እና ነጻ ምርጫ ናቸው። እነዚህን ነገሮች የፈጠረው አላህ ነው፤ አላህ የነገር ሁሉ ፈጣሪ ነው፥ አላህ እኛንም እኛ የምንሠራውን ሁሉ የፈጠረ ነው፦
39፥62 *አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው*፡፡ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ
37፥96 *አላህ እናንተንም የምትሠሩትንም የፈጠረ ሲኾን*፡፡ وَاللَّهُ خَلَقَكُمْ وَمَا تَعْمَلُون

"የማታውቁትንም ድንቅ ነገር ይፈጥራል" መጻኢ የሩቅ ወሬ ስለሆነ ትንቢት ነው፦
38፥88 *«ትንቢቱንም ከጊዜ በኋላ በእርግጥ ታውቁታላችሁ፡፡* وَلَتَعْلَمُنَّ نَبَأَهُ بَعْدَ حِينٍ
6፥67 *ለትንቢት ሁሉ የሚደርስበት መርጊያ አለው፡፡ ወደፊትም ታውቁታላችሁ*፡፡ لِّكُلِّ نَبَإٍ مُّسْتَقَرٌّ ۚ وَسَوْفَ تَعْلَمُونَ

"ትንቢቱንም ከጊዜ በኋላ ወደፊት ታውቁታላችሁ" ብሎ በነገረን መሠረት የአየር መጓጓዣ አይሮፕላን፣ ጀት፣ ኢልኮፕተር፥ የየብስ መጓጓዣ አውቶ ሞቢል መኪና፣ ባቡር፣ ሜትሮ፣ ፔንደል፥ የባህር መጓጓዣ ባለ ሞተር መርከብ በዘመናችን ዐይተናል። አል-ሐምዱሊሏህ!
ኢንሻሏህ ይቀጥላል.....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የቁርኣን ትንቢት

ገቢር ሦስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

25፥6 *«ያ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለን ምስጢር የሚያውቀው አወረደው፡፡ እርሱ መሓሪ አዛኝ ነውና» በላቸው*፡፡ قُلْ أَنزَلَهُ الَّذِي يَعْلَمُ السِّرَّ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ إِنَّهُ كَانَ غَفُورًا رَّحِيمًا

"ዘራህ" ذَرَّة የሚለው ቃል "ደቂቅ" ንዑስ" "ኢምንት" "ብናኝ"Atom" ማለት ሲሆን ጥቃቅን ነገር ነው፦
99፥7 *የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሠራ ሰው ያገኘዋል*፡፡ فَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ خَيْرًا يَرَهُ
99፥8 *"የብናኝ ክብደት ያክልም ክፉን የሠራ ሰው ያገኘዋል"*፡፡ وَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ شَرًّا يَرَهُ

"ብናኝ" ለሚለው የገባው ቃል "ዘራህ" ذَرَّة መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። ዐረቦች ከጥቃቅን ፍጥረት አነስተኛ የሚሉት "ጉንዳን" ነበር። ነገር ግን ቁርኣኑ "ጉንዳን" ለሚለው ቃል የሚጠቀመው "ዘራህ" ذَرَّة ሳይሆን "ነምል" نَّمْل ነው፦
27፥18 *በጉንዳንም ሸለቆ በመጡ ጊዜ አንዲት ጉንዳን «እናንተ ጉንዳኖች ሆይ! ወደ መኖሪያዎቻችሁ ግቡ፡፡ ሱለይማንና ሰራዊቱ እነርሱ የማያውቁ ሲኾኑ አይሰባብሩዋችሁ» አለች*፡፡ حَتَّىٰ إِذَا أَتَوْا عَلَىٰ وَادِ النَّمْلِ قَالَتْ نَمْلَةٌ يَا أَيُّهَا النَّمْلُ ادْخُلُوا مَسَاكِنَكُمْ لَا يَحْطِمَنَّكُمْ سُلَيْمَانُ وَجُنُودُهُ وَهُمْ لَا يَشْعُرُونَ

ሲቀጥል "ጉንዳን" በሰማያትና በምድር ውስጥ አይገኝም። ብናኝ"Atom" ግን በሰማያትና በምድር ውስጥ አለ፦
34፥3 እነዚያ የካዱትም «ሰዓቲቱ አትመጣብንም» አሉ፡፡ በላቸው «አይደለም፤ ሩቁን ሁሉ ዐዋቂ በኾነው ጌታዬ እምላለሁ፡፡ በእርግጥ ትመጣባችኋለች፡፡ *"የብናኝ ክብደት ያክል እንኳ በሰማያትና በምድር ውስጥ ከእርሱ አይርቅም፡፡ ከይህ ያነሰም ኾነ የበለጠ የለም* በግልጹ መጽሐፍ ውስጥ የተመዘገበ ቢኾን እንጅ፡፡» وَقَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا لَا تَأْتِينَا السَّاعَةُ ۖ قُلْ بَلَىٰ وَرَبِّي لَتَأْتِيَنَّكُمْ عَالِمِ الْغَيْبِ ۖ لَا يَعْزُبُ عَنْهُ مِثْقَالُ ذَرَّةٍ فِي السَّمَاوَاتِ وَلَا فِي الْأَرْضِ وَلَا أَصْغَرُ مِن ذَٰلِكَ وَلَا أَكْبَرُ إِلَّا فِي كِتَابٍ مُّبِينٍ

እዚህ አንቀጽ ላይ በግልጹ መጽሐፍ በተጠበቀው ሰሌዳ ውስጥ ከብናኝ ያነሰም ኾነ የተለቀ ፍጥረት የተመዘገበ መሆኑን ፍትንትውና ቁልጭ አርጎ ያሳያል። "ዛሊከ" ذَٰلِكَ ማለትም "ይህ" የሚለው አመልካች ተውላጠ-ስም "ዘራህ" ذَرَّة የሚለውን ስም ተክቶ የመጣ ነው፥ ከአተም ያነሰ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለ ነገር ኤሌክትሮን፣ ፕሮቶን፣ ኒውትሮን ነው። ከአተም ያነሰ ነገር አለ ተብሎ ስለማይታመን "አቶም" ወይም "አተም" የሚለው ቃል እራሱ "አቶሞስ" ἄτομον ከሚል የግቲክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙ "የማይከፋፈል”indivisible” ማለት ነው። አቶም ሁሉም ቁስ የተገነባበት መሰረታዊ ንዑስ ነው፥ እስከ አስራ ዘጠነኛው ክፍለ-ዘመን ከአቶም ወደ ታች ፍጥረት አለ ተብሎ አይታመንም ነበር። የፊዚክስ ምሁር ጆን ዳልተን እንኳን አቶም በውስጡ ፍጥረት አለው ብሎ አያምንም ነበር፥ ነገር ግን እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 1897 ድኅረ-ልደት ላይ ጆን ቶምሶን፣ በ 1911 ድኅረ-ልደት ላይ ኤርነስት ራዘርፎርድ ወዘተ ከአተም ያነሱ የቁስ መጠን ክፍፍሎች“particle” አግኝተው ገለጡ። እነዚህም፦ ኤሌክትሮን፣ ፕሮቶን፣ ኒውትሮን፣ ፈርሚኦን፣ ሌፕቶን፣ ቦሶን፣ ፎቶን፣ ዲላቶን፣ ሳክሲኦን፣ አክሲኦን የመሳሰሉት ናቸው። በተለይ ኤሌክትሮን፣ ፕሮቶን እና ኒውትሮን በሁሉም ቁስ ላይ የሚገኙ ከአቶም በታች የሚገኙ ናቸው። እስከ 1897 ድኅረ-ልደት ድረስ ከአተም ወደ ታች ፍጥረት የለም ተብሎ ቢታመንም፣ አላህ ግን በቁርአን ከአቶም በታች ያሉት ፍጥረቶች በእውቀቱ መዝገብ ላይ ተጽፎ እንዳለ ነግሮናል። ከአተም በታች በሰማያትና በምድር ውስጥ ለምእመናን ሁሉ እርግጠኛ ታምራቶች አሉ፦
45፥3 *"በሰማያትና በምድር ውስጥ ለምእመናን ሁሉ እርግጠኛ ታምራቶች አሉ*። إِنَّ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ لَآيَاتٍ لِّلْمُؤْمِنِينَ
10፥6 ሌሊትና ቀን በመተካካታቸው አላህም *በሰማያትና በምድር ውስጥ በፈጠረው ሁሉ ለሚጠነቀቁ ሕዝቦች ታምራቶች አሉ*፡፡ إِنَّ فِي اخْتِلَافِ اللَّيْلِ وَالنَّهَارِ وَمَا خَلَقَ اللَّهُ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يَتَّقُونَ
ኤሌክትሮን፣ ፕሮቶን እና ኒውትሮን በአጽናፎቹ ውስጥ እና በራሳችን አካላት ውስጥ ያሉ ታምራቶች ናቸው፥ አላህ እነዚህ ታምራት ወደፊት እንደሚያሳየን እና እንደሚያሳውቀትን ቃል ገብቶልን ነበር፦
6፥93 ምስጋናም ለአላህ ነው፡፡ *"ተዓምራቶቹን ወደፊት ያሳያችኋል፡፡ «ታውቁታላችሁ»* በላቸው፡፡ ጌታህም ከምትሠሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም፡፡ وَقُلِ الْحَمْدُ لِلَّهِ سَيُرِيكُمْ آيَاتِهِ فَتَعْرِفُونَهَا ۚ وَمَا رَبُّكَ بِغَافِلٍ عَمَّا تَعْمَلُونَ
41፥53 እርሱም ቁርኣን እውነት መኾኑ ለእነርሱ እስከሚገለፅላቸው ድረስ *"በአጽናፎቹ ውስጥ እና በራሳቸውም ውስጥ ያሉትን ተዓምራቶቻችንን በእርግጥ እናሳያቸዋለን*"፡፡ ጌታህም እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ዐዋቂ መኾኑ አይበቃቸውምን? سَنُرِيهِمْ آيَاتِنَا فِي الْآفَاقِ وَفِي أَنفُسِهِمْ حَتَّىٰ يَتَبَيَّنَ لَهُمْ أَنَّهُ الْحَقُّ ۗ أَوَلَمْ يَكْفِ بِرَبِّكَ أَنَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ شَهِيدٌ

አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ዐዋቂ መኾኑ አይበቃንምን? ቁርኣን ሐቅ መሆኑ ለሁሉም የሚገለጸው የትንሳኤ ቀን ነው። ቁርኣን እውነት ሆኖ በመጣላቸው ጊዜ እነዚያ የካዱት፦ “ይህ ግልጽ ድግምት ነው” አሉ። ነገር ግን አላህ በትንሳኤ ቀን ስለ ቁርኣኑ፦ “ይህ እውነት አይደለምን? ብሎ ይጠይቃቸዋል፥ እነርሱም፦ “እውነት ነው፤ በጌታችን ይኹንብን” ይላሉ፦
46፥7 *”በእነርሱም ላይ አንቀጾቻችን ግልጾች ኾነው በተነበቡ ጊዜ እነዚያ እውነቱን በመጣላቸው ጊዜ የካዱት «ይህ ግልጽ ድግምት ነው» አሉ”*፡፡ وَإِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ آيَاتُنَا بَيِّنَاتٍ قَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا لِلْحَقِّ لَمَّا جَاءَهُمْ هَـٰذَا سِحْرٌ مُّبِينٌ
46፥34 *”እነዚያም የካዱት ሰዎች በእሳት ላይ በሚቀረቡ ቀን «ይህ እውነት አይደለምን?» ይባላሉ፡፡ «እውነት ነው፤ በጌታችን ይኹንብን» ይላሉ፡፡ አላህም «ትክዱ በነበራችሁት ምክንያት ቅጣቱን ቅመሱ» ይላቸዋል”*፡፡ وَيَوْمَ يُعْرَضُ الَّذِينَ كَفَرُوا عَلَى النَّارِ أَلَيْسَ هَـٰذَا بِالْحَقِّ ۖ قَالُوا بَلَىٰ وَرَبِّنَا ۚ قَالَ فَذُوقُوا الْعَذَابَ بِمَا كُنتُمْ تَكْفُرُونَ

ቁርኣን እውነት መኾኑ ለእነርሱ እስከሚገለፅላቸው እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ በአጽናፎቹ ውስጥ እና በራሳችን ውስጥ ያሉትን ተዓምራቶቹን በዘመናችን እያሳየን ነው፥ እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ማሳየቱ ይቀጥላል። ዛሬ የስሥ-ምርምር ጥናት ተመራማሪዎች በአጽናፎች ያሉትን ፈለኮች፣ ፕላኔቶች፣ ምህዳሮች፣ ፍኖተ-ሃሊብ፣ ክላስተሮች፣ አድማሳትን ወዘተ መርምረው አይተዋል። በራሶቻቸውም ያሉትን ሥነ-አካል"Physiology"፣ ሥነ-ልቦና"Psychology፣ ሥነ-ሕይወት"Biology፣ የወንድ ጾታ ጥናት"Andrology፣ የሴት ጾታ ጥናት"gynaecology" ወዘተ መርምረው አይተዋል። ይህን ቁርኣን በወረደበት ጊዜ የማይታሰብ ነው፥ ነገር ግን አላህ፦ "በአጽናፎቹ ውስጥ እና በራሳቸውም ውስጥ ያሉትን ተዓምራቶቻችንን በእርግጥ እናሳያቸዋለን" ብሎ ቃል በገባው መሠረት ተፈጽሟል። ቁርኣንስ ይህንን የሩቅ ወሬ ቀደም ብሎ እንዴት ሊይዝ ቻለ? መልሱ "ያ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለን ምስጢር የሚያውቀው አላህ ቁርኣንን ስላወረደው" ነው፦
25፥6 *«ያ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለን ምስጢር የሚያውቀው አወረደው፡፡ እርሱ መሓሪ አዛኝ ነውና» በላቸው*፡፡ قُلْ أَنزَلَهُ الَّذِي يَعْلَمُ السِّرَّ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ إِنَّهُ كَانَ غَفُورًا رَّحِيمًا

ኢንሻሏህ ይቀጥላል.....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ክርስቲያን

“ክርስቲያን” የሚለው ቃል “ክርስቲያኖስ” Χριστιανός ከሚል የግሪኩ ቃል የመጣ ነው። በግሪኩ አዲስ ኪዳን ሦስት ቦታ የሐዋርያት ሥራ 11፥26 የሐዋርያት ሥራ 26፥28 1ኛ ጴጥሮስ 4፥16 ይገኛል። በአማርኛ ባይብል ላይ አራት ቦታ የሐዋርያት ሥራ 11፥26 የሐዋርያት ሥራ 26፥28 1ኛ ጢሞቴዎስ 3፥6 1ኛ ጴጥሮስ 4፥16 ላይ ይገኛል።

“ክርስቲያኖስ” Χριστιανός ማለት ትርጉሙ “ክርስቶሶች” “ክርስቶሳውያን” “ቅቡዓን” ማለት ነው። ይህ ስም የወጣው በአንጾኪያ በፓጋኖቹ ለደቀመዛሙርቱ የወጣ የሽሙጥና የለበጣ ስም ነው እንጂ ክርስቲያን የሚለው መጠሪያ ነብያት ሆኑ ኢየሱስ ዐያውቁትም። ይህንን ጉዳይ የፕሮቴስታንት አስተማሪ ፓስተር ያሬድ ጥላሁን እና የኦርቶዶክስ መምህር ምሕረተ-አብ አሰፋ ፍርጥ አርገው እንቁጭን ይነግሩናል፥ እስቲ እናዳምጥ!

ተጨማሪ ትምህርት ለመከታተል እዚህ ጎራ ይበሉ፦
https://tttttt.me/Wahidcom
የቁርኣን ትንቢት

ገቢር አራት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

10፥92 *ዛሬማ፦ "ከኋላህ ላሉት ተዓምር ትሆን ዘንድ በድን ሆነህ ከባሕሩ እናወጣሃለን" ተባለ፡፡ ከሰዎችም ብዙዎቹ ከተዓምራታችን በእርግጥ ዘንጊዎች ናቸው*፡፡ فَالْيَوْمَ نُنَجِّيكَ بِبَدَنِكَ لِتَكُونَ لِمَنْ خَلْفَكَ آيَةً ۚ وَإِنَّ كَثِيرًا مِّنَ النَّاسِ عَنْ آيَاتِنَا لَغَافِلُونَ

"አል-የቂን" الْيَقِين ማለት "እርግጠኝነት" ማለት ነው፥ አል-የቂን ሦስት ደረጃዎች አሉት፥ እነርሱም፦ ዒልመል የቂን፣ ዐይነል የቂን፣ ሐቁል-የቂን ናቸው። "ዒልመል የቂን" عِلْمَ الْيَقِين ማለት የወደፊቱን ክንውን አምላካችን አላህ በነገረን ዕውቀት የምናረጋግጥበት ነው። "ዐይነል የቂን" عَيْنَ الْيَقِين ማለት አምላካችን አላህ ቀድሞ የነገረን ዕውቀት ጊዜ ደርሶ ሲከናወን በዓይናችን በማየት የምናረጋግጥበት ነው። "ሐቁል የቂን" حَقُّ الْيَقِين ማለት አምላካችን አላህ ቀድሞ የነገረን ዕውቀት ጊዜ ደርሶ ሲከናወን በሕዋሳችን አጣጥመን የምናረጋግጥበት ነው። እንደሚታወቀው አላህ በሙሣ ዘመን ለፈርዖን እና ለቤተሰቡ ማስጠንቀቂያ ተሰጧቸው ነበር፦
11፥97 *ወደ ፈርዖንና ወደ ሰዎቹ ላክነው፡፡ የፈርዖንንም ነገር ሕዝቦቹ ተከተሉ፡፡ የፈርዖን ነገርም ቀጥተኛ አልነበረም*፡፡ إِلَىٰ فِرْعَوْنَ وَمَلَئِهِ فَاتَّبَعُوا أَمْرَ فِرْعَوْنَ ۖ وَمَا أَمْرُ فِرْعَوْنَ بِرَشِيدٍ
54፥41 *"የፈርዖንንም ቤተሰቦች ማስጠንቀቂያዎች በእርግጥ መጡባቸው*፡፡ وَلَقَدْ جَاءَ آلَ فِرْعَوْنَ النُّذُرُ

ፈርዖን እና ቤተሰቡ ከአላህ የመጣውን መልእክት ሲያስተባብሉ እና የእስራኤልን ልጆች ሊያጠፉ ሲመጡ በባሕር ውስጥ ሰጠሙ፦
17፥103 ከምድርም ሊቀሰቅሳቸው አሰበ፡፡ *"እርሱን እና ከእርሱ ጋር የነበሩትንም ሰዎች ሁሉንም አሰጠምናቸው*፡፡ فَأَرَادَ أَن يَسْتَفِزَّهُم مِّنَ الْأَرْضِ فَأَغْرَقْنَاهُ وَمَن مَّعَهُ جَمِيعًا
2፥50 *በእናንተም ምክንያት ባሕሩን በከፈልን ጊዜ አስታውሱ፡፡ ወዲያውም አዳንናችሁ፡፡ የፈርዖንንም ቤተሰቦች እናንተ የምትመለከቱ ኾናችሁ አሰጠምናቸው*፡፡ وَإِذْ فَرَقْنَا بِكُمُ الْبَحْرَ فَأَنجَيْنَاكُمْ وَأَغْرَقْنَا آلَ فِرْعَوْنَ وَأَنتُمْ تَنظُرُونَ
10፥90 *የእስራኤልንም ልጆች ባሕሩን አሳለፍናቸው፡፡ ፈርዖንና ሰራዊቱም ወሰን ለማለፍና ለመበደል ተከተሏቸው፡፡ መስጠምም ባገኘው ጊዜ፡- «አመንኩ፡፡ እነሆ ከዚያ የእስራኤል ልጆች በርሱ ከአመኑበት በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ እኔም ከታዛዦቹ ነኝ» አለ*፡፡ وَجَاوَزْنَا بِبَنِي إِسْرَائِيلَ الْبَحْرَ فَأَتْبَعَهُمْ فِرْعَوْنُ وَجُنُودُهُ بَغْيًا وَعَدْوًا ۖ حَتَّىٰ إِذَا أَدْرَكَهُ الْغَرَقُ قَالَ آمَنتُ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا الَّذِي آمَنَتْ بِهِ بَنُو إِسْرَائِيلَ وَأَنَا مِنَ الْمُسْلِمِينَ

አምላካችን አላህ ለፈርዖን፦ "ከኋላህ ላሉት ተዓምር ትሆን ዘንድ በድን ሆነህ ከባሕሩ እናወጣሃለን" አለው፦
10፥92 *ዛሬማ፦ "ከኋላህ ላሉት ተዓምር ትሆን ዘንድ በድን ሆነህ ከባሕሩ እናወጣሃለን" ተባለ፡፡ ከሰዎችም ብዙዎቹ ከተዓምራታችን በእርግጥ ዘንጊዎች ናቸው*፡፡ فَالْيَوْمَ نُنَجِّيكَ بِبَدَنِكَ لِتَكُونَ لِمَنْ خَلْفَكَ آيَةً ۚ وَإِنَّ كَثِيرًا مِّنَ النَّاسِ عَنْ آيَاتِنَا لَغَافِلُونَ

"ዛሬ" የተባለው አላህ ለፈርዖን የተናገረበት ቀን ነው፥ ያኔ "ኑነጂከ" نُنَجِّيكَ ማለትም "እናወጣሃለን" ብሎት ትንቢት ተናግሮ ነበር፥ ይህ ዒልመል የቂን ነው። ለምን? በኃላ ላሉት ታምር ይሆን ዘንድ፥ ከሰዎችም ብዙዎቹ ከአላህ ታምራት በእርግጥ ዘንጊዎች ናቸው። አምላካችን አላህ "እናወጣሃለን" ብሎ በተናገረው መሠረት የፈርዖን በድን ከኤርትራ ባሕር እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 1975 ድኅረ-ልደት አውጥቶታል። ይህን የማውጣቱ መርሐ-ግብር የፈጸሙት ዶክተር ሞሪስ ሞካየ ናቸው፥ ይህ ዐይነል የቂን ነው። የፈርዖን በድንን ይቱብ ላይ ማየት ይቻላል፦
https://youtu.be/-dxDmbgEdcc

ይህ የአላህ ታምር ነው፥ በኃላ ላሉት ታምር ይሆን ዘንድ አላህ በዶክተር ሞሪስ ሞካየ አወጣው። አምላካችን አላህ ስለራሱ ፦ "ተዓምራቶቹን ወደፊት ያሳያችኋል፥ ታውቁታላችሁ" በል በማለት ቃል በገባልን መሠረት ለእኛ ታምር ይሆን ዘንድ የፈርዖን በድን ከኤርትራ ባሕር በማውጣት አሳይቶናል፥ ዐሳውቆናል። ምስጋናም ለአላህ ነው፦
6፥93 ምስጋናም ለአላህ ነው፡፡ *"ተዓምራቶቹን ወደፊት ያሳያችኋል፡፡ «ታውቁታላችሁ»* በላቸው፡፡ ጌታህም ከምትሠሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም፡፡ وَقُلِ الْحَمْدُ لِلَّهِ سَيُرِيكُمْ آيَاتِهِ فَتَعْرِفُونَهَا ۚ وَمَا رَبُّكَ بِغَافِلٍ عَمَّا تَعْمَلُونَ

ኢንሻሏህ ይቀጥላል.....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የቁርኣን ትንቢት

ገቢር አምስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

30፥3 *"በጣም ቅርብ በሆነችው ምድር፡፡ እነርሱም ከመሸነፋቸው በኋላ በእርግጥ ያሸንፋሉ"*፡፡ فِي أَدْنَى الْأَرْضِ وَهُم مِّن بَعْدِ غَلَبِهِمْ سَيَغْلِبُونَ

ሰዎች ነቢያችንን"ﷺ" ጥያቄ ለመጠየቅ ከመምጣታቸው በፊት አምላካችን አላህ፦ "የሥአሉነከ" يَسْأَلُونَكَ ማለትም "ይጠይቁሃል" በማለት ቀድሞ መልስ ይሰጣል። በጥያቄ ሲመጡ እውነተኛውን መልስ መስጠት የአላህ ድርሻ ነው፦
25፥33 *በጥያቄም አይመጡብህም እውነተኛውን መልስ መልካምን ፍችም የምናመጣልህ ብንኾን እንጅ*፡፡ وَلَا يَأْتُونَكَ بِمَثَلٍ إِلَّا جِئْنَاكَ بِالْحَقِّ وَأَحْسَنَ تَفْسِيرًا

የቁርኣን ደራሲ"author" የዓለማቱ ጌታ አላህ ለሚጠየቁት ጥያቄ መልስ በመስጠት የሬቅ ወሬ ወደ ነቢያችን"ﷺ" ያወርዳል፥ “አል-ገይብ” ٱلْغَيْب ማለት “የሩቅ ወሬ” “የሩቅ ሚስጥር” ማለት ሲሆን ከህዋስ ባሻገር ጥንት የተከሰተ፣ አሁን እየተከሰተ ያለ እና ወደ ፊት የሚከሰት ዕውቀት ነው፥ አላህ የሰማያትን እና የምድርን የሩቅ ሚስጥር ያውቃል። ይህንን የሩቅ ሚስጥር ለሚፈልገው መልእክተኛ ቢሆን እንጂ ለማንም ዐያሳውቅም፦
49፥18 *”አላህ የሰማያትንና የምድርን “ሩቅ ሚስጥር” ያውቃል”*። إِنَّ ٱللَّهَ يَعْلَمُ غَيْبَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ
72፥26 *«እርሱ ”የሩቅ ሚስጥር” ዐዋቂ ነው፡፡ በምስጢሩም ላይ አንድንም አያሳውቅም፡፡»* عَٰلِمُ ٱلْغَيْبِ فَلَا يُظْهِرُ عَلَىٰ غَيْبِهِۦٓ أَحَدًا
72፥27 *ከመልክተኛ ለወደደው ቢኾን እንጅ ለሌላ አይገልጽም*፡፡ إِلَّا مَنِ ٱرْتَضَىٰ مِن رَّسُولٍۢ

“አል-ገይብ” በሦስት ይከፈላል፥ እርሱም፦ አል-ገይቡል ማዲ፣ አል-ገይቡል ሙዷሪዕ እና አል-ገይቡል ሙሥተቅበል ነው። “አል-ገይቡል ማዲ” ٱلْغَيْب الْمَاضِي ማለት “ኀላፊያት የሩቅ ወሬ” ማለት ነው፥ ድርጊቱ ከዚህ በፊት አላፊ የሆነ ክስተት ነው። “አል-ገይቡል ሙዷሪዕ” ٱلْغَيْب ٱلْمُضَارِع ማለት “አሁናት የሩቅ ወሬ” ማለት ነው፥ ቁርኣን ሲወርድ ከህዋስ ባሻገት እየተፈጸመ ያለ ክስተት ነው። “አል-ገይቡል ሙሥተቅበል” ٱلْغَيْب ٱلْمُسْتَقْبَل ማለት “መጻእያት የሩቅ ወሬ” ማለት ነው፥ መጪው ክስተት ነው። ይህም ድርጊቱ ገና ያልተፈጸመ ወደፊት የሚከሰት ነው፥ በቁርኣን ተተንብዮ በነቢያችን"ﷺ" ዘመን ከተፈጸሙ ትንቢት አንዱ የሩም ጉዳይ ነው፦
30፥2 *"ሩም ተሸነፈች"*፡፡ غُلِبَتِ الرُّومُ
30፥3 *"በጣም ቅርብ በሆነችው ምድር፡፡ እነርሱም ከመሸነፋቸው በኋላ በእርግጥ ያሸንፋሉ"*፡፡ فِي أَدْنَى الْأَرْضِ وَهُم مِّن بَعْدِ غَلَبِهِمْ سَيَغْلِبُونَ
30፥4 *"በጥቂት ዓመታት ውስጥ ያሸንፋሉ፡፡ ትዕዛዙ በፊትም በኋላም የአላህ ነው፡፡ በዚያ ቀንም ምእመናን ይደሰታሉ"*፡፡ فِي بِضْعِ سِنِينَ ۗ لِلَّهِ الْأَمْرُ مِن قَبْلُ وَمِن بَعْدُ ۚ وَيَوْمَئِذٍ يَفْرَحُ الْمُؤْمِنُونَ

የአንጾኪያ ፍልሚያ የተጀመረው እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 613 ድኅረ-ልደት ነው፥ "አር-ሩም" الرُّوم የምትባለት የባዛንታይን ግዛት ስትሆን በጣም ቅርብ በሆነችው ምድር በፐርሺያን በ 614 ድኅረ-ልደት ተሸነፈች። ይህ አንቀጽ በዚሁ ጊዜ የወረደው በመካ ስለሆነ ሱራው እራሱ "መኪይ" ነው። አምላካችን አላህ፦ "እነርሱም ከመሸነፋቸው በኋላ በእርግጥ በጥቂት ዓመታት ውስጥ ያሸንፋሉ" ብሎ በተናገረው መሠረት ይህ ትንቢት በተነገረ በጥቂት 14 ዓመታት በ 628 ድኅረ-ልደት ሮማውያን ፐርሺያውያንን አሸንፈዋል። በወቅቱ ምእመናንም መለኮታዊ ቅሪት ያላቸው ክርስቶሳውያን የእሳት አምላኪዎች የሆኑትን ዞራስተሪያውያን በማሸነፋቸው ተደስተዋል።
እንግዲህ በቁርኣን ያለው ትንቢት ቢዘረዘር ብዙ ነው፥ ስለ ጀነት እና ጀሃነም ያለው የሩቅ ወሬ እራሱ ትንቢት ነው፦
3፥15 *«ከዚህ ሁሉ ነገር የሚበልጥን ልንገራችሁን» በላቸው”*፡፡ እርሱም «ለእነዚያ ለተጠነቀቁት ሰዎች በጌታቸው ዘንድ በሥራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች በውስጧ ሁልጊዜ ነዋሪዎች ሲኾኑ ንጹሕ የተደረጉ ሚስቶችም፣ ከአላህም የኾነ ውዴታ አላቸው፡፡ አላህም ባሮቹን ተመልካች ነው፡፡» قُلْ أَؤُنَبِّئُكُم بِخَيْرٍ مِّن ذَٰلِكُمْ ۚ لِلَّذِينَ اتَّقَوْا عِندَ رَبِّهِمْ جَنَّاتٌ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا وَأَزْوَاجٌ مُّطَهَّرَةٌ وَرِضْوَانٌ مِّنَ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ بَصِيرٌ بِالْعِبَادِ
22፥72 *«ከዚህ ይልቅ የከፋን ነገር ልንገራችሁን» በላቸው”*፡፡ «እርሱም እሳት ናት፡፡ አላህ ለእነዚያ ለካዱት ሰዎች ቀጥሯታል፡፡ ምን ትከፋም መመለሻ!» قُلْ أَفَأُنَبِّئُكُم بِشَرٍّ مِّن ذَٰلِكُمُ ۗ النَّارُ وَعَدَهَا اللَّهُ الَّذِينَ كَفَرُوا ۖ وَبِئْسَ الْمَصِيرُ

“ልንገራችሁ” ለሚለው ቃል የገባው “ነበኡኩም” نَبِّئُكُم ሲሆን “ነበአ” نَبَّأَ ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ነው። ይህንን እንዲናገሩ አላህ “ቁል” قُلْ የሚል ትእዛዝ ያወርዳል። ቁርኣን ላይ ብዙ ቦታ በትንሳኤ ቀን ምን እንደሚከሰት ለማሳወቅ “አስታውስ” እያለ ይናገራል፦
54፥6 *”ከእነርሱም ዙር፡፡ ጠሪው መልአክ ወደ አስደንጋጭ ነገር የሚጠራበትን ቀን አስታውስ”*፡፡ فَتَوَلَّ عَنْهُمْ ۘ يَوْمَ يَدْعُ الدَّاعِ إِلَىٰ شَيْءٍ نُّكُرٍ

ይህንን ትንቢት አምላካችን አላህ፦ “በእርግጥ ከጊዜ በኋላ ወደፊትም ታውቁታላችሁ” ይለናል፦
38፥88 *«ትንቢቱንም ከጊዜ በኋላ በእርግጥ ታውቁታላችሁ፡፡* وَلَتَعْلَمُنَّ نَبَأَهُ بَعْدَ حِينٍ
6፥67 *ለትንቢት ሁሉ የሚደርስበት መርጊያ አለው፡፡ ወደፊትም ታውቁታላችሁ*፡፡ لِّكُلِّ نَبَإٍ مُّسْتَقَرٌّ ۚ وَسَوْفَ تَعْلَمُونَ

“ኢዝ” إِذْ በሚለው የጊዜ ተውሳከ-ግስ ውስጥ “ፈዘከር” فَذَكِّرْ ማለትም “አስታውስ” የሚል ትእዛዝ አለ፥ አላህ ያለፈውን፣ ያሁኑን እና የሚመጣውን የሩቅ ወሬ እየነገራቸው “አስታውስ” ይላቸዋል። ነቢያችን”ﷺ” ደግሞ “ሙዘከር” مُذَكِّرٌ ማለትም “አስታዋሽ” ናቸው። ነቢያችን”ﷺ” የሚያሳታውሱት በተወረዳቸው “ዚክር” ብቻ ነው፥ ይህም “ዚክር” ذِكْر ማለትም “ማስታወሻ” ቁርኣን ነው፦
88፥21 *አስታውስም፤ አንተ አስታዋሽ ብቻ ነህና*፡፡ فَذَكِّرْ إِنَّمَا أَنتَ مُذَكِّرٌ
21፥50 *ይህም ያወረድነው የኾነ ብሩክ “ዚክር” *፡፡ ታዲያ እናንተ ለእርሱ ከሓዲዎች ናችሁን? وَهَـٰذَا ذِكْرٌ مُّبَارَكٌ أَنزَلْنَاهُ ۚ أَفَأَنتُمْ لَهُ مُنكِرُونَ
50፥45 ስለዚህ ዛቻዬን የሚፈራን ሰው *በቁርኣን አስታውስ*፡፡ فَذَكِّرْ بِالْقُرْآنِ مَن يَخَافُ وَعِيدِ

"""""""ተፈጸመ""""""""

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
መሢሕ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3:45 መላእክት ያሉትን አስታዉስ፡- መርየም ሆይ አላህ ከርሱ በሆነዉ ቃል፣ ስሙ “አል-መሲሕ” ዒሳ የመርየም ልጅ፣ በዚህ ዓለምና በመጨረሻዉም ዓለም የተከበረ፣ ከባለማሎችም በሆነ ያበስረሻል፤

“መሲሕ” مسيح የሚለው የአረቢኛ ቃል
“መሢሐ” מָשִׁ֫יחַ የሚለው የእብራይስጥ ቃል
“መሢሕ” ክמשיחא የሚለው የአረማይ ቃል
ሴማዊ መነሻ ሲኖረው ትርጉሙ “የተቀባ” ማለት ነው፣ በግሪክ ደግሞ “ክርስቶስ” Χριστός ነው፤ ይህ ማእረግ በብሉይ ኪዳን ለተለያየ ነገስታትና ነቢያት በግሪኩ ሰፕቱጀንት ላይ “ክርስቶስ” Χριστός በእብራይስጡ ደግሞ መሢሐ” מָשִׁ֫יחַ ተብሎ አገልግሎት ላይ ውሏል፤ መቀባት መሾምን ያመለክታል በአምላክ የተቀቡ የአምላክ መሢሖች ብዙ ናቸው፦
1ኛ ዜና 16፥22 “መሢሖቼን” בִּמְשִׁיחָ֔י አትዳስሱ፥ “በነቢያቴም” ክፉ አታድርጉ ብሎ፥ ሰው ግፍ ያደርግባቸው ዘንድ አልፈቀደም ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ።
መዝሙረ ዳዊት 105፥14-15 “መሢሖቼን” בִּמְשִׁיחָ֔י አትዳስሱ፥ “በነቢያቴም” ክፉ አታድርጉ ብሎ፥ ሰው ግፍ ያደርግባቸው ዘንድ አልፈቀደም ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ።

አንደኛ “ሳኦል”
1ሳኦል በትንቢት የተነገረለት መሢሐዊ ንጉስ ነው፦
1 ሳሙ 2:10 እግዚአብሔር እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል፤ “ለንጉሡም” ኃይል ይሰጣል፤ “የመሲሑንም” מְשִׁיחֽוֹ ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።

ይህንን ጥቅስ የአይሁድ ምሁራን እና ለዘብተኛ የብሉይ ተንታኞች ለሳኦል እንደሆነ ያትታሉ፤ በተጨማሪም በሳሙኤል ዘመን የተቀባ መሢሕ ሳኦል እንደሆነ በቁና መረጃ አለ፦
1ሳሙ 10:1፤ ሳሙኤልም የዘይቱን ብርሌ ወስዶ በራሱ ላይ አፈሰሰው፥ ሳመውም፥ እንዲህም አለው። በርስቱ ላይ አለቃ ትሆን ዘንድ እግዚአብሔር “ቀብቶሃል” מְשָׁחֲךָ ֧፤
1ሳሙ 12፥3 እነሆኝ በእግዚአብሔርና “በመሲሑ” מְשִׁיח֗וֹ ፊት መስክሩብኝ የማንን በሬ ወሰድሁ?
1ሳሙ 12፥5 እርሱም፦ በእጄ ምንም እንዳላገኛችሁ እግዚአብሔርና “መሲሑ” מְשִׁיח֗וֹ ዛሬ በእናንተ ላይ ምስክሮች ናቸው አላቸው፤

ሁለተኛ “ዳዊት”
2 ሳሙ 22፥51 የንጉሡን መድኃኒት ታላቅ ያደርጋል፤ ቸርነቱንም ለመሲሑ לִמְשִׁיח֛וֹ ለዳዊትና ለዘሩ፥ ለዘላለም ይሰጣል።
2 ሳሙ 23፥1 የዳዊትም የመጨረሻ ቃሉ ይህ ነው። ከፍ ከፍ የተደረገው፥ የያዕቆብም አምላክ መሢሕ מְשִׁ֙יחַ֙፥ በእስራኤል ዘንድ መልካም ባለ ቅኔ የሆነ፥ የእሴይ ልጅ የዳዊት ንግግር፤
መዝ 132:17 በዚያ ለዳዊት ቀንድን አበቅላለሁ፥ “ለመሢሔ” לִמְשִׁיחִֽי ሰው መብራትን አዘጋጃለሁ።

ሶስተኛ “ሰለሞን”
1ሳሙ 2:35 የታመነም ካህን ለእኔ አስነሣለሁ፥ በልቤም በነፍሴም እንዳለ እንዲሁ ያደርጋል፤ እኔም የታመነ ቤት እሠራለታለሁ፥ ዘመኑን ሁሉ በመሢሔ מְשִׁיחִ֖י ሰው ፊት ይሄዳል።

ይህ ጥቅስ ትንቢት ሲሆን ትንቢቱም ስለ ካህንና ካህኑ የሚሄድበት መሢሑ ናቸው፤ ምሁራን ካህኑ ሳዶቅ ሲሆን መሢሑ ደግሞ ቤት የሰራው ሰለሞን ነው፦
1 ኛ ነገሥት 1፥39 ካህኑም ሳዶቅ ከድንኳኑ የቅብዓቱን ቀንድ ወስዶ ሰሎሞንን ቀባ וַיִּמְשַׁ֖ח፤ ቀንደ መለከትም ነፉ፤ ሕዝቡም ሁሉ፦ ሰሎሞን ሺህ ዓመት ይንገሥ አሉ።

አራተኛ “ሴዴቂያስ”
ምሁራን በባቢሎን ምርኮ ጊዜ በጉድጓድ የተያዘው ሴዴቅያስ እንደሆነ ያትታሉ፤ ይህም ንጉስ መሲህ ተብሏል፦
ሰቆቃው ኤርምያስ 4፥20 ሬስ። ስለ እርሱ። በአሕዛብ መካከል በጥላው በሕይወት ያልነው “የእግዚአብሔር መሢሕ” מְשִׁ֣יחַ፥ የሕይወታችን እስትንፋስ፥ በጕድጓዳቸው ተያዘ።

አምስተኛ “ሙሴና ኤልያስ”
ዘካ 4:14 እርሱም። በምድር ሁሉ ጌታ አጠገብ የቆሙት “ሁለቱ የተቀቡት” הַיִּצְהָ֑ר እነዚህ ናቸው አለኝ።

በምድር ሁሉ ጌታ አጠገብ የቆሙት “ሁለቱ የተቀቡትየተባሉት ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን ካዘጋው ከኤልያስና ውኃዎችንም ወደ ደም ካስለወጠው ከሙሴ ሌላ እነማን ሊሆኑ ይችላሉ? ምሁራን በዚህ ሸክ የላቸውም፦
ራእይ 11፥3-10 “ለሁለቱም ምስክሮቼ” ማቅ ለብሰው ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን “ትንቢት” ሊናገሩ እሰጣለሁ። እነዚህ “በምድር ጌታ ፊት የሚቆሙ” ሁለቱ ወይራዎችና ሁለቱ መቅረዞች ናቸው።
ዘካርያስ 4፥11 እኔም መልሼ፦ በመቅረዙ በስተ ቀኝና በስተ ግራ ያሉ እነዚህ “ሁለት የወይራ ዛፎች” ምንድር ናቸው? አልሁት።
ዘካ 4:14 እርሱም። በምድር ሁሉ ጌታ አጠገብ የቆሙት “ሁለቱ የተቀቡት” הַיִּצְהָ֑ר እነዚህ ናቸው አለኝ።

ስድስተኛ “ኢየሱስ”
መዝሙረ ዳዊት 2፥2 የምድር ነገሥታት ተነሡ፥ አለቆችም በእግዚአብሔርና በመሢሑ מְשִׁיחֽוֹ ላይ እንዲህ ሲሉ ተማከሩ።

አይሁዳውያን በትንቢት የሚጠበቀው መሢሕ ኢየሱስ አይደለም ብለው ቢያስተባብሉም እኛ ሙስሊሞችና ሆነ የኢየሱስን ማንነት ያዛቡት ክርስቲያኖች ኢየሱስ ቃል የተገባለት መሢሕ ነው ብለን እናምናለን፤ ይህን ነጥብ ከሶስቱም ማእዘን እንመልከት፦
ነጥብ አንድ
“መሢሕ በአይሁድ”
አይሁዳውያን መሢሕ ቃል የተገባለት”the promised one” ንጉስና ነብይ ነው ብለው ይጠብቁት ነበር፤ መሢሕ አምላክ አሊያም ከአምላክ ጋር ኖሮ ኖሮ በኃላ በስጋ የሚመጣ ሳይሆን ከዳዊት ቤት የሚፈጠር ሰው ብቻ ነው ብለው ያምናሉ፤ መሢሕ አይሁዶች ይጠብቁት እንደነበረ የሚያመላክቱ ጥቅሶች አሉ፦
ሉቃ 3:15 ሕዝቡም “ሲጠብቁ” ሳሉ ሁሉም በልባቸው ስለ ዮሐንስ። “ይህ ክርስቶስ ይሆንን?” ብለው ሲያስቡ ነበር፥
ዮሐ 10:24 አይሁድም እርሱን ከበው። እስከ መቼ ድረስ በጥርጣሪ ታቆየናለህ? “አንተ ክርስቶስ” እንደ ሆንህ ገልጠህ ንገረን አሉት።
ሉቃ 22:67 “ክርስቶስ” አንተ ነህን? ንገረን አሉት። እርሱ ግን እንዲህ አላቸው። ብነግራችሁ አታምኑም፤
ዮሐ 4:25 ሴቲቱ። “ክርስቶስ የሚባል መሲሕ እንዲመጣ” አውቃለሁ፤ እርሱ ሲመጣ ሁሉን ይነግረናል አለችው።”
ዮሐ 4:29 ያደረግሁትን ሁሉ የነገረኝን ሰው ኑና እዩ፤ እንጃ እርሱ “ክርስቶስ” ይሆንን? አለች።
ዮሐ.7:41 ሌሎች። ይህ “ክርስቶስ ነው” አሉ፤ ሌሎች ግን። “ክርስቶስ በእውኑ ከገሊላ ይመጣልን”?
ነጥብ ሁለት
“መሲህ በክርስትና”
ኢየሱስ አይሁድ የሚጠብቁት መሢሕ መሆኑንና ግን ያንን ማንነቱን ለጊዜው ለማንም እንዳይናገሩ ተናግሯል፦
ዮሐ 4:25-26 ሴቲቱ። “ክርስቶስ የሚባል መሲሕ እንዲመጣ” አውቃለሁ፤ እርሱ ሲመጣ ሁሉን ይነግረናል አለችው። ኢየሱስ። የምናገርሽ “እኔ እርሱ ነኝ” አላት።
ማቴ 16:20 ያን ጊዜም እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ለማንም እንዳይነግሩ ደቀ መዛሙርቱን አዘዛቸው።

ሃዋርያትንም እኔ ማን ነኝ? ብሎ ሲጠይቃቸው አንተ ክርስቶስ ነህ ብሎ ጴጥሮስ መልሷል፤ ሃዋርያትም ኢየሱስ መሲህ መሆኑን መስክረዋል፤ በእርግጥም ክርስቶስ አይደለም ብሎ ኢየሱስን የሚያስተባብል ውሸተኛ ነው፦
ማር 8:29 እናንተስ “እኔ ማን እንደ ሆንሁ” ትላላችሁ? ብሎ ጠየቃቸው። ጴጥሮስም። “አንተ ክርስቶስ ነህ” ብሎ መለሰለት።
ሐዋ 5:42 ዕለት ዕለትም በመቅደስና በቤታቸው “ስለ ኢየሱስ እርሱ “ክርስቶስ” እንደ ሆነ ማስተማርንና መስበክን አይተዉም ነበር።
ሐዋ 17፥3 ይህ እኔ የምሰብክላችሁ “ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው” ይል ነበር።
ሐዋ 18፥5 ሲላስና ጢሞቴዎስም ከመቄዶንያ በወረዱ ጊዜ፥ ጳውሎስ “ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ” እንደ ሆነ ለአይሁድ እየመሰከረ ለቃሉ ይተጋ ነበር።
ሐዋ.18:28 “ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ” እንደ ሆነ ከመጻሕፍት እየገለጠ ለአይሁድ በሁሉ ፊት በጽኑ ያስረዳቸው ነበርና።
1ዮሐ.2:22 “ክርስቶስ አይደለም ብሎ ኢየሱስን” ከሚክድ በቀር ውሸተኛው ማን ነው?

ኢየሱስ በእርግጥ እግዚአብሔር አምላኩ በመንፈስ ቅዱስ ከባለንጀሮቹ ከነቢያትና ከነገስታት ይልቅ ኢንጅልን እንዲሰብክ
የቀባው ሰው ነው፦
ሐዋ 10:38 እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም “ቀባው”፥
ሉቃ4:17 ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ “ቀብቶኛልና” ።
ዕብ 1:9 ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት “ቀባህ”፤
ነጥብ ሶስት
“መሲሕ በኢስላም”
አምላካችን አላህ በተከበረው ቃሉ በዘጠኝ አንቀፆች 11 ጊዜ ኢየሱስ መሢሕ መሆኑን ነግሮናል፦ 3፥45 4፥157 4፥171 4፥172 5፥17 5፥17 5፥72 5፥72 5፥75 9፥30 9፥31
ለናሙና ያክል አንዳንድ ጥቅሶ ብንመለከት ኸይር ነው፦
3:45 መላእክት ያሉትን አስታዉስ፡- መርየም ሆይ አላህ ከርሱ በሆነዉ ቃል፣ ስሙ “አል-መሲሕ” ዒሳ የመርየም ልጅ፣ በዚህ ዓለምና በመጨረሻዉም ዓለም የተከበረ፣ ከባለማሎችም በሆነ ያበስረሻል፤

መርየም ከአላህ በሆነው ቃል
የተበሰረችው ልጇ፦
1. ስሙ አልመሲሕ ዒሳ መሆኑን
2. የመርየም ልጅ መሆኑን
3. በዚህ ዓለምና በመጨረሻዉም ዓለም የተከበረ መሆኑን
4. ከባለማሎችም አንዱ መሆኑን ነው።
ይህም የመርየም ልጅ ኢሳ የአላህ ባሪያ የሆነ መሲህ ነው፦
4:172 “አልመሲሕ” ለአላህ ባሪያ ከመሆን ፈጽሞ አይጠየፍም፤

ቁርአን ኢየሱስን መሢሕ ብሎታልና ለአምላክነቱ መስፈርት ነው ብሎ መሟገት ሌሎች መሲህ የተባሉትን ነቢያትና ነገስታት አምላክ ናቸው ብሎ መፈረጅም ነው፤ በተረፈ ይህንን የማርያምን ልጅ ኢየሱስን ከመሲህነት ወደ ፈጣሪነት ማሸጋገር ኩፍር ነው፦
5:17 እነዚያ አላህ اللَّهَ እርሱ የመርየም ልጅ “አልመሲሕ” الْمَسِيحُ ነው ያሉ፣ በእርግጥ ካዱ፤
5.72 እነዚያ አላህ اللَّهَ እርሱ የመርየም ልጅ “አልመሲሕ” الْمَسِيحُ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ፤

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም