ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.2K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ከእነዚህ ሁለት በዓል ውጪ ሌሎች በዓላት ተቀባይነት የላቸውም፤ ማንም ሰው አላህ እና መልእክተኛው ያልደነገጉትን ቢድዓን ያስተዋወቀ ያንን ፈለግ የተከተሉትን ሰዎች የሚያገኙትን ኀጢአት ከእነርሱ ላይ ሳይቀነስና ሳይጨመር ይሸከማል፤ ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓ ነው፤ ቢድዓ ሁሉ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ የእሳት ነው፦
ኢማም ቡኻርይ : መጽሐፍ 53, ሐዲስ 7
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ማንኛውም ሰው ከትእዛዛችን ያልሆነ አንድ ነገር ቢፈጥር ተቀባይነት የለውም”* عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَنْ أَحْدَثَ فِي أَمْرِنَا هَذَا مَا لَيْسَ فِيهِ فَهُوَ رَدٌّ ‏”‌‏.‏
ሡነን ኢብኑ ማጃህ : መጽሐፍ 1, ሐዲስ 210
ከሲር ኢብኑብ ዐብደላህ እንደተረከው አባቱ ከአያቱ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰማው ያለው፦ “ማንኛውም ሰው የእኔን ሡናህ ሱናህ ያደረገ ከእኔ በኃላ የእኔን ፈለግ የሚከተሉትን ሰዎች የሚያገኙትን አጅር ከእነርሱ ላይ ሳይቀነስና ሳይጨመር ያገኛል፤
*ማንም ሰው አላህ እና መልእክተኛው ያልደነገጉትን ቢድዓን ያስተዋወቀ ያንን ፈለግ የተከተሉትን ሰዎች የሚያገኙትን ኀጢአት ከእነርሱ ላይ ሳይቀነስና ሳይጨመር ይሸከማል*። حَدَّثَنِي كَثِيرُ بْنُ عَبْدِ اللَّهِ، عَنْ أَبِيهِ، عَنْ جَدِّهِ، قَالَ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ يَقُولُ ‏ “‏ مَنْ أَحْيَا سُنَّةً مِنْ سُنَّتِي قَدْ أُمِيتَتْ بَعْدِي فَإِنَّ لَهُ مِنَ الأَجْرِ مِثْلَ أَجْرِ مَنْ عَمِلَ بِهَا مِنَ النَّاسِ لاَ يَنْقُصُ مِنْ أُجُورِ النَّاسِ شَيْئًا وَمَنِ ابْتَدَعَ بِدْعَةً لاَ يَرْضَاهَا اللَّهُ وَرَسُولُهُ فَإِنَّ عَلَيْهِ مِثْلَ إِثْمِ مَنْ عَمِلَ بِهَا مِنَ النَّاسِ لاَ يَنْقُصُ مِنْ آثَامِ النَّاسِ شَيْئًا ‏”‏ ‏.‏
ሡነን ነሣኢ : መጽሐፍ 19, ሐዲስ 23
ጃቢር ኢብኑ ዐብደላህ እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሑጥባቸው ላይ እንደተናገሩት፦ “አላህ የመራውን ማንም አያጠመውም፤ አላህ ያጠመመውን ማንም አያቀናውም። ከንግግር ሁሉ በላጩ የአላህ መጽሐፍ ነው፤ ከመመሪያ ሁሉ በላጩ የሙሐመድ መመሪያ ነው። *ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓ ነው፤ ቢድዓ ሁሉ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ የእሳት ነው*። عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ قَالَ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ فِي خُطْبَتِهِ يَحْمَدُ اللَّهَ وَيُثْنِي عَلَيْهِ بِمَا هُوَ أَهْلُهُ ثُمَّ يَقُولُ مَنْ يَهْدِهِ اللَّهُ فَلَا مُضِلَّ لَهُ وَمَنْ يُضْلِلْهُ فَلَا هَادِيَ لَهُ إِنَّ أَصْدَقَ الْحَدِيثِ كِتَابُ اللَّهِ وَأَحْسَنَ الْهَدْيِ هَدْيُ مُحَمَّدٍ وَشَرُّ الْأُمُورِ مُحْدَثَاتُهَا وَكُلُّ مُحْدَثَةٍ بِدْعَةٌ وَكُلُّ بِدْعَةٍ ضَلَالَةٌ وَكُلُّ ضَلَالَةٍ فِي النَّارِ

ስለዚህ እዚህ እምነት ውስጥ ያላችሁ ዋቄፈታዎች የነቢያት አምላክ የሆነውን አንዱን አምላክ አላህን በብቸኝነት እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው፤ ሙስሊሞች ሆናችሁ ይህንን በዓል ባለማወቅ የምታከብሩምና የምታመልኩ ካላችሁ በንስሃ ወደ አላህ ተመለሱ። አላህ ወደ እርሱ በመጸጸት ለሚመለሱት ይቅር ባይና አዛኝ ነው፦
2፥160 እነዚያ ከመደበቅ የተጸጸቱና ሥራቸውን ያሳመሩም የደበቁትን የገለጹም ብቻ ሲቀሩ፡፡ *እነዚህም በእነርሱ ላይ ጸጸታቸውን እቀበላለሁ፤ እኔም ጸጸትን በጣም ተቀባይ አዛኙ ነኝ*፡፡ إِلَّا الَّذِينَ تَابُوا وَأَصْلَحُوا وَبَيَّنُوا فَأُولَـٰئِكَ أَتُوبُ عَلَيْهِمْ ۚ وَأَنَا التَّوَّابُ الرَّحِيمُ

ስለ ዋቄፈና ዋቢ መጽሐፍት፦
1. Mulugeta Jaleta Gobenooromo; Indiginious Religion: Anthroplogical Understanding of Waaqeffanna-Nature Link, With Highlight on Livelihood in Guji Zone, Adola Redde and Girja Districts, A thesis submitted to the department of Social Anthropology, College of Social Science Addis Ababa University, June 2017,
2. Census (PDF), Ethiopia, 2007,
3. Workinesh Kelbessa, Traditional Oromo Attitudes towards the Environment, Social Science Research Report Series.

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የመስቀል ቦታ ጽዳት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

5፥2 *"በበጎ ነገርና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ፡፡ ግን በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና"*፡፡ وَتَعَاوَنُوا عَلَى الْبِرِّ وَالتَّقْوَىٰ ۖ وَلَا تَعَاوَنُوا عَلَى الْإِثْمِ وَالْعُدْوَانِ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

አምላካችን አላህ ከሰው ጋር በሚኖረን ማሕበራዊ ዘይቤ እንዴት መኗኗር እንዳለብን እንዲህ ይነግረናል፦
4፥36 *አላህንም አምልኩ፤ በእርሱም ምንንም አታጋሩ፡፡ በወላጆች፣ በቅርብ ዝምድና ባለቤትም፣ በየቲሞችም፣ በምስኪኖችም፣ በቅርብ ጎረቤትም፣ በሩቅ ጎረቤትም፣ በጎን ባልደረባም፣ በመንገደኛም፣ እጆቻችሁም ንብረት ባደረጓቸው መልካምን ሥሩ*፤ አላህ ኩራተኛ ጉረኛ የኾነን ሰው አይወድም፡፡ وَاعْبُدُوا اللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا ۖ وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا وَبِذِي الْقُرْبَىٰ وَالْيَتَامَىٰ وَالْمَسَاكِينِ وَالْجَارِ ذِي الْقُرْبَىٰ وَالْجَارِ الْجُنُبِ وَالصَّاحِبِ بِالْجَنبِ وَابْنِ السَّبِيلِ وَمَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ مَن كَانَ مُخْتَالًا فَخُورًا
4፥135 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *በትክክል ፍትሕ ቀዋሚዎች በራሳችሁ ወይም በወላጆች እና በቅርብ ዘመዶች ላይ ቢኾንም እንኳ ለአላህ መስካሪዎች ኹኑ፡፡ ሀብታም ወይም ድኻ ቢኾን አላህ በእነርሱ ከእናንተ ይበልጥ ተገቢ ነው፡፡ እንዳታደሉም ዝንባሌን አትከተሉ፡፡ ብታጠምሙም ወይም መመስከርን ብትተው አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ بِالْقِسْطِ شُهَدَاءَ لِلَّهِ وَلَوْ عَلَىٰ أَنفُسِكُمْ أَوِ الْوَالِدَيْنِ وَالْأَقْرَبِينَ ۚ إِن يَكُنْ غَنِيًّا أَوْ فَقِيرًا فَاللَّهُ أَوْلَىٰ بِهِمَا ۖ فَلَا تَتَّبِعُوا الْهَوَىٰ أَن تَعْدِلُوا ۚ وَإِن تَلْوُوا أَوْ تُعْرِضُوا فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرًا

እዚህ አንቀጽ ላይ “ተዕዲሉ” تَعْدِلُوا የሚለው ቃል ይሰመርበት፤ ይህ ቃል የስም መደቡ “ዐድል” عَدْل ሲሆን “ፍትሕ” ማለት ነው፤ ፍትሕ ለአላህ ፍራቻ ተብሎ እና አላህ በምንሠራው ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው ተብሎ የሚደረግ ነው። ይህ ለአላህ ተብሎ የሚደረግ ፍትሕ ለአማንያን ብቻ ሳይሆን ለከሃድያንም ጭምር ነው፦
60፥8 *ከእነዚያ በሃይማኖት ካልተጋደሏችሁ፣ ከአገሮቻችሁም ካላወጡዋችሁ ከሓዲዎች መልካም ብትውሉላቸው እና ወደ እነርሱ ብታስተካክሉ አላህ አይከለክላችሁም፡፡ አላህ ትክክለኞችን ይወዳልና*፡፡ لَّا يَنْهَاكُمُ اللَّهُ عَنِ الَّذِينَ لَمْ يُقَاتِلُوكُمْ فِي الدِّينِ وَلَمْ يُخْرِجُوكُم مِّن دِيَارِكُمْ أَن تَبَرُّوهُمْ وَتُقْسِطُوا إِلَيْهِمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُقْسِطِينَ

ዲናችንን አክብረው ካልተጋደሉንና ካላሳደዱን ከሃድያን ጋር በዝምድና፣ በባልደረባ፣ በጉርብትና መልካም መዋዋል እና ማስተካከል ይቻላል። “ብታስተካክሉ” ለሚለው ቃል አሁንም የገባው “ቱቅሢጡ” َتُقْسِطُوا ሲሆን የስም መደቡ “ቂሥጥ” قِسْط ማለትም “ፍትሕ” ነው፤ ለአላህ ብለን ስናስተካክል “ሙቅሢጢን” مُقْسِطِين ማለትም “ፍትኸኞችን” “ትክክለኞች” “አስተካካዮች” እንሰኛለን፤ አላህ ሙቅሢጢንን ይወዳልና። በበጎ ነገርና አላህን በመፍራትም መረዳዳት ተፈቅዷል፦
49፥9 *በነገሩ ሁሉ አስተካክሉም፡፡ አላህ አስተካካዮችን ይወዳልና*፡፡ وَأَقْسِطُوا ۖ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُقْسِطِينَ
5፥2 *"በበጎ ነገር እና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ፡፡ ግን በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና"*፡፡ وَتَعَاوَنُوا عَلَى الْبِرِّ وَالتَّقْوَىٰ ۖ وَلَا تَعَاوَنُوا عَلَى الْإِثْمِ وَالْعُدْوَانِ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

"በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ" የሚለው ይሰመርበት። ወደ ኩፍርና ሺርክ ሊያስገባ የሚችለውን ሥራ ከሌላ እምነት ጋር መሥራት ከኢሥላም ያስወጣል፥ ይህ ወሰን ማለፍ ነው፦
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 15, ሐዲስ 311
ሰሙራህ ኢብኑ ጁንዱብ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እዲህ አሉ፦ *”ከሙሽሪክ ጋር ያበረ እና የተኗኗረ እርሱን(ሙሽሪኩን) ይመስላል”*። أَمَّا بَعْدُ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَنْ جَامَعَ الْمُشْرِكَ وَسَكَنَ مَعَهُ فَإِنَّهُ مِثْلُهُ ‏
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 12, ሐዲስ 34
ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም አሉ፦ *”ከማንኛውም ሕዝብ ጋር የሚመሳሰል ከእነርሱ ነው”*። عَنِ ابْنِ عُمَرَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَنْ تَشَبَّهَ بِقَوْمٍ فَهُوَ مِنْهُمْ
ስለዚህ የማይመለከተን ነገር ውስጥ ለመመሳሰል ለምሳሌ ቤተ ክርስቲያን ማጽዳት፣ የመስቀል ደመራ ቦታ ማጽዳት፣ የጥምቀት ቦታ ማጽዳት፥ ታቦት መሸኘት፣ በዓላቸውን ማክበር፣ መዝሙራቸውን መዘመር ከኢሥላም አጥር ያስወጣል። አንዳንድ ቂሎች፦ “ለመረዳዳት ነው” ይሉናል። በጋራ እሴት ማለትም በልማት፣ በጉርብትና፣ በአስኳላ ትምህርት፣ በሰብአዊነት ወዘተ… ልንረዳዳ እንችላለን፥ ነገር ግን በእምነት ጉዳይ እረዳቶች አድርገን ከያዝናቸው ከእነርሱ እንደ አንዱ ነን፦
4፥144 *”እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከምእምናን ሌላ ከሓዲዎችን ረዳቶች አድርጋችሁ አትያዙ*፤ ለአላህ በእናንተ ላይ ግልጽ ማስረጃዎችን ልታደርጉ ትፈልጋላችሁን? يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا الْكَافِرِينَ أَوْلِيَاءَ مِن دُونِ الْمُؤْمِنِينَ ۚ أَتُرِيدُونَ أَن تَجْعَلُوا لِلَّهِ عَلَيْكُمْ سُلْطَانًا مُّبِينًا
5፥51 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አይሁዶችንና ክርስቲያኖችን ረዳቶች አድርጋችሁ አትያዙ፡፡ ከፊላቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡ ከእናንተም ውስጥ ረዳቶች የሚያደርጋቸው ሰው እርሱ ከእነርሱ ነው*፡፡ አላህ አመጸኞችን ሕዝቦች አያቀናም፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا الْيَهُودَ وَالنَّصَارَىٰ أَوْلِيَاءَ ۘ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَاءُ بَعْضٍ ۚ وَمَن يَتَوَلَّهُم مِّنكُمْ فَإِنَّهُ مِنْهُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الظَّالِمِينَ
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 24, ሐዲስ 2939
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”የሙሽሪክ እርዳታ አያስፈልገንም”* عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ إِنَّا لاَ نَسْتَعِينُ بِمُشْرِكٍ ‏

ምን ይሁን ብለን ነው ለመስቀል በዓል የምናጸዳው? መስቀል እኮ ስግደት እና ምስጋና ይቀበላል። መስቀል በሃውልት ድንጋይ፣ እንጨት፣ ወርቅ፣ ብር፣ ብረት፣ ነሐስ ወዘተ ነው። ይህ ግዑዝ ነገር ይሰገድለታል፥ ምስጋና ይቀርበለታል፤ ይህ በተግባር ሲሆን በጽሑፍ ደግሞ የዘወትር ፀሎት ላይ እንዲህ ይነበባል፦
ግዕዙ፦
“እሰግድ “ለ”መስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘተቀደሰ በደሙ ክቡር”
ትርጉም፦
“ዓለምን ለማዳን ሲል ኢየሱስ ክርስቶስ “ለ”ተሰቀለበት መስቀል እሰግዳለው”
ግዕዙ፦
“ስብሐት “ለ”መስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ በምህረቱ ይዘከረነ”
ትርጉም፦
” “ለ”ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ምስጋና ይገባዋል”

እንግዲህ ሄደክ ስታጸዳ እንዲያሻርኩ እያመቻቸክላቸው እንደሆነ አትርሳ። ይህንን ድርጊት መተባበር ሺርክ እይደለምን? መከባበር በዚህ ነው እንዴ? ሰዎቹን በሰውነታቸው እናከብራቸዋል እንጂ ለአምልኮታቸው ዕውቅና ሰጥቶ እሹሩሩ ማለት ምን የሚሉት ማሽቃበጥ ነው? መንግሥት ይሉንታ በማስያዝ በሃይማኖት ጣልቃ አይግባብን። ሙሥሊሙ የራሱ ለማጽዳት የሌላ እገዛ አይሻም። መሣጂዶችን እንዲያጸዱልን አንፈልግም። እኛም የእነርሱን ማጽዳት የለብንም፥ የራሳቸውን እራሳቸው ያጽዱ። ኡስታዞች፣ ዐሊሞች፣ መሻይኮች ምነው ዝምታውን መረጡዛ? በዝምታው ምእመኑን በእምነቱ እንዲሸማቀቅ እና እዲሳቀቅ እያረጋችሁት ነው። አብሮነት፣ መከባበር፣ የአገር ልማትና ግንባታ በዚህ አይለካም። አብሮነት፣ መከባበር፣ የአገር ልማትና ግንባታ እናመጣለን በሚል ሽፋን ኡማውን የዝቅተኝነት ስሜት በማከናነብ ከድጡ ወደ ማጡ አትክተቱት። ኢትዮጵያዊነት በመሆን እንጂ በመምሰል አይለካም። ምንም ሳይገባውና ሳያውቀው የሚሳተፈውን ሙሥሊም በትህትና የማስጠንቀቅ የሁላችንም ሃላፍትና ነው። ይህንን መልእክት ለሁሉም በማስተላለፍ ዲናዊ ግዴታዎን ይወጡ! አላህ ለሁላችንም ሂዳያ ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ተውባህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

2፥160 እነዚያ ከመደበቅ የተጸጸቱና ሥራቸውን ያሳመሩም የደበቁትን የገለጹም ብቻ ሲቀሩ፡፡ *”እነዚህም በእነርሱ ላይ ጸጸታቸውን እቀበላለሁ፤ እኔም ጸጸትን በጣም ተቀባይ አዛኙ ነኝ”*፡፡ إِلَّا الَّذِينَ تَابُوا وَأَصْلَحُوا وَبَيَّنُوا فَأُولَـٰئِكَ أَتُوبُ عَلَيْهِمْ ۚ وَأَنَا التَّوَّابُ الرَّحِيمُ

"ንስሐ" የሚለው የግዕዝ ቃል "ነስሐ" ማለትም "ተመለሰ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "በጸጸት መመለስ" ማለት ነው። “ተውባህ” تَوْبَة የሚለው ቃል "ታበ" تَابَ ማለትም "ተመለሰ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ከነበሩበት ስህተት በንስሐ ወደ አላህ መመለስ” ማለት ነው፥ አላህ ወደ እርሱ የሚመለሱት ንስሐን የሚቀበል ስለሆነ “አት-ተዋብ” التَّوَّاب ማለትም "ጸጸትን ተቀባይ" ነው። እርሱም፦ “እኔም ጸጸትን በጣም ተቀባይ አዛኙ ነኝ” ይላል፦
2፥160 እነዚያ ከመደበቅ የተጸጸቱና ሥራቸውን ያሳመሩም የደበቁትን የገለጹም ብቻ ሲቀሩ፡፡ *”እነዚህም በእነርሱ ላይ ጸጸታቸውን እቀበላለሁ፤ እኔም ጸጸትን በጣም ተቀባይ አዛኙ ነኝ”*፡፡ إِلَّا الَّذِينَ تَابُوا وَأَصْلَحُوا وَبَيَّنُوا فَأُولَـٰئِكَ أَتُوبُ عَلَيْهِمْ ۚ وَأَنَا التَّوَّابُ الرَّحِيمُ

ወደ አላህ በንስሐ የሚመለሱት ሰዎች ደግሞ “አት-ተዋቡን” التَّوَّابُون ይባላሉ። አላህ ከኃጢኣት ተመላሾችን ይወዳል፥ በመሳሳት አጥፍተን ወደ እርሱ ለምንመለስ መሓሪ ነው፦
2፥222 *"አላህ ከኃጢኣት ተመላሾችን ይወዳል፤ ተጥራሪዎችንም ይወዳል በላቸው"*፡፡ اللَّهَ يُحِبُّ التَّوَّابِينَ وَيُحِبُّ الْمُتَطَهِّرِينَ
4፥25 *"ጌታችሁ በነፍሶቻችሁ ውስጥ ያለውን ሁሉ አዋቂ ነው፡፡ ታዛዦችም ብትኾኑ በመሳሳትም ብታጠፉ እርሱ ለተመላሾች መሓሪ ነው"*፡፡ رَّبُّكُمْ أَعْلَمُ بِمَا فِي نُفُوسِكُمْ ۚ إِن تَكُونُوا صَالِحِينَ فَإِنَّهُ كَانَ لِلْأَوَّابِينَ غَفُورًا

ነቢያችን"ﷺ" በሐዲስ ላይ፦ "የአደም ልጆች ሁሉ ተሳሳች ናቸው፡፡ ከተሳሳቾቹ ሁሉ በላጩ ግን ከስህተታቸው በተውበት ተመላሾቹ ናቸው" ብለውናል፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 4392
አነሥ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”የአደም ልጆች ሁሉ ተሳሳች ናቸው፡፡ ከተሳሳቾቹ ሁሉ በላጩ ግን ከስህተታቸው በተውበት ተመላሾቹ ናቸው”*። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏:‏ ‏ “‏ كُلُّ بَنِي آدَمَ خَطَّاءٌ وَخَيْرُ الْخَطَّائِينَ التَّوَّابُونَ
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 50, ሐዲስ 13
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"በዚያ ነፍሴ በእጁ በኾነው በአላህ እምላለው! እናንተ ኃጢአትን ባታደርጉ ኖሮ፥ አላህ እናንተን ያስወግዳችሁ እና ኃጢአትን አድርገው ከዛም ይቅርታ ጠይቀው፣ አላህ ይቅር የሚላቸውን ሕዝብ ያመጣ ነበር"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ وَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ لَوْ لَمْ تُذْنِبُوا لَذَهَبَ اللَّهُ بِكُمْ وَلَجَاءَ بِقَوْمٍ يُذْنِبُونَ فَيَسْتَغْفِرُونَ اللَّهَ فَيَغْفِرُ لَهُمْ ‏"‏ ‏

እዚህ ሐዲስ ላይ "ለው" لَوْ ተለዋዋጭ ቃሉ "ኢን" إِن ነው፥ "ለው" ወይም "ኢን" በሰዋሰው አቀማመጥ "አርፉ አሽ-ሸርጥ" حَرْف الشَرْط ማለትም ሁኔታዊ መስተዋድድ"conditional particle" ነው። "ኖሮ" የሚለው አርፉ አሽ-ሸርጥ ከገባን "እናንተ ኃጢአትን ባታደርጉ ኖሮ" ማለት ኃጢአትን ታደርጋላችሁ፥ የአደም ልጆች ሁሉ ተሳሳች ናቸው። ከተሳሳቾቹ ሁሉ በላጩ ግን ከስህተታቸው በተውበት ተመላሾቹ ናቸው ማለት ነው። ይህንን ተመሳሳይ ሰዋስው ከቁርኣን እንመልከት፦
7፥143 ሙሳም ለቀጠሯችን በመጣና ጌታውም ባነጋገረው ጊዜ፡- *«ጌታዬ ሆይ! አሳየኝ ወደ አንተ እመለከታለሁና» አለ፡፡ አላህም፡- «በፍጹም አታየኝም ግን ወደ ተራራው ተመልከት፡፡ "በስፍራውም ቢረጋ በእርግጥ ታየኛለህ"» አለው፡፡ ጌታው ለተራራው በተገለጸ ጊዜ እንኩትኩት አደረገው፡፡ ሙሳም ጮሆ ወደቀ*፡፡ በአንሰራራም ጊዜ «ጥራት ይገባህ፡፡ ወደ አንተ ተመለስኩ፡፡ እኔም የምእምናን መጀመሪያ ነኝ» አለ፡፡ وَلَمَّا جَاءَ مُوسَىٰ لِمِيقَاتِنَا وَكَلَّمَهُ رَبُّهُ قَالَ رَبِّ أَرِنِي أَنظُرْ إِلَيْكَ ۚ قَالَ لَن تَرَانِي وَلَـٰكِنِ انظُرْ إِلَى الْجَبَلِ فَإِنِ اسْتَقَرَّ مَكَانَهُ فَسَوْفَ تَرَانِي ۚ فَلَمَّا تَجَلَّىٰ رَبُّهُ لِلْجَبَلِ جَعَلَهُ دَكًّا وَخَرَّ مُوسَىٰ صَعِقًا ۚ فَلَمَّا أَفَاقَ قَالَ سُبْحَانَكَ تُبْتُ إِلَيْكَ وَأَنَا أَوَّلُ الْمُؤْمِنِينَ

"በስፍራውም ቢረጋ" ማለት "አይረጋም" ማለት ከሆነ "እናንተ ኃጢአትን ባታደርጉ ኖሮ" ማለት "እናንተ ኃጢአትን አለማድረግ አትችሉም" ማለት ነው። "በስፍራውም ቢረጋ በእርግጥ ታየኛለህ" ማለት "አይረጋም እንጂ ቢረጋ ታየኛለህ" ማለት እንደሆነ ሁሉ "እናንተ ኃጢአትን ባታደርጉ ኖሮ አላህ እናንተን ያስወግዳችሁ እና ኃጢአትን አድርገው ከዛም ይቅርታ ጠይቀው፣ አላህ ይቅር የሚላቸውን ሕዝብ ያመጣ ነበር" ማለት "እናንተ ኃጢአትን አለማድረግ አትችሉም እንጂ ብትችሉ ኃጢአትን አድርገው ከዛም ጌታቸውን ምሕረትን ጠይቀው፣ እሱም ይቅር የሚላቸውን ሕዝብ ያመጣ ነበር" ማለት ነው። " በእርግጥ ታየኛለህ" የሚለው ተራራው መርጋት እንደማይችል ግነት ሆኖ እንደመጣ ሁሉ "አላህ እናንተን ያስወግዳችሁ እና ኃጢአትን አድርገው ከዛም ይቅርታ ጠይቀው፣ አላህ ይቅር የሚላቸውን ሕዝብ ያመጣ ነበር" የሚለውም "እናንተ ኃጢአትን አለማድረግ አትችሉም" የሚለውን ለማሳየት የመጣ ግነታዊ ቃል ነው። ሌላ ናሙና፦
21፥22 *በሁለቱ በሰማያትና በምድር ውስጥ ከአላህ ሌላ አማልክት በነበሩ "ኖሮ" በተበላሹ ነበር"*፡፡ የዐርሹ ጌታ አላህም ከሚሉት ሁሉ ጠራ፡፡ لَوْ كَانَ فِيهِمَا آلِهَةٌ إِلَّا اللَّهُ لَفَسَدَتَا ۚ فَسُبْحَانَ اللَّهِ رَبِّ الْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ
እዚህ አንቀጽ ላይ "ለው" لَوْ የሚለው አርፉ አሽ-ሸርጥ "ኖሮ" የሚለው ለማመልከት የገባ ነው። "አማልክት በነበሩ ኖሮ" ማለት "አማልክት የሉም" ማለት እንደሆነ ሁሉ "እናንተ ኃጢአትን ባታደርጉ ኖሮ" ማለት "እናንተ ኃጢአትን አለማድረግ አትችሉም" ማለት ነው። ከፊሉ በከፊሉ ላይ በመላቅ ሊበላሹ የሚችሉት ከመነሻው አማልክት ቢኖሩ ኖሮ ነበር እንጂ ይበላሻሉ ማለት እንዳልሆነ ሁሉ ኃጢአትን አድርገው ከዛም ጌታቸውን ምሕረትን ጠይቀው፣ እሱም ይቅር የሚላቸውን ሕዝብ የሚያመጣው እናንተ ኃጢአትን የማታደርጉ ቢሆን ነበር ማለት ነው። የመጨረሻ ናሙና፦
43፥81 *«ለአልረሕማን ልጅ ቢኖረው እኔ ለልጁ የተገዢዎቹ መጀመሪያ ነኝ» በላቸው*፡፡ قُلْ إِن كَانَ لِلرَّحْمَـٰنِ وَلَدٌ فَأَنَا أَوَّلُ الْعَابِدِينَ

"ለአልረሕማን ልጅ ቢኖረው" ማለት "ለአልረሕማን ልጅ የለውም" ማለት እንደሆነ ሁሉ "እናንተ ኃጢአትን ባታደርጉ ኖሮ" ማለት "እናንተ ኃጢአትን አለማድረግ አትችሉም" ማለት ነው። እኔ ለልጁ ተገዢ መሆን የምችለው ከመነሻው ልጅ ቢኖረው ኖሮ ነበር እንጂ ለልጁ ተገዢ ነኝ ማለት እንዳልሆነ ሁሉ ኃጢአትን አድርገው ከዛም ጌታቸውን ምሕረትን ጠይቀው፣ እሱም ይቅር የሚላቸውን ሕዝብ የሚያመጣው እናንተ ኃጢአትን የማታደርጉ ቢሆን ነበር ማለት ነው። ስለዚህ የሐዲሱ መልእክት ያዘለው "እናንተ ኃጢአትን አለማድረግ ስለማትችሉ" ያላችሁ ምርጫ ተውበት አድርጉ! የአደም ልጆች ሁሉ ተሳሳች ናቸው፡፡ ከተሳሳቾቹ ሁሉ በላጩ ግን ከስህተታቸው በተውበት ተመላሾቹ ናቸው” የሚል ነው እንጂ "አላህ ሰዎች ኃጢአትን ካላደረጉ ይቅርባይነቱ ይቀርበታል" የሚል የሚሽነሪዎችን የቡና ወሬ አያሲዝም። ባይሆን እግዚአብሔር ሲያጠፋችሁ ሲያፈርሳችሁም ደስ ይለዋል፦
ዘዳግም28፥63 እግዚአብሔርም በጎ ያደርግላችሁ ዘንድ ያበዛችሁም ዘንድ ደስ ይለው እንደ ነበረ፥ እንዲሁ *እግዚአብሔር ሲያጠፋችሁ ሲያፈርሳችሁም ደስ ይለዋል"*።

ለነገሩ ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር የሆነውን ክፉን መንፈስ ይልካል፥ ይህም ክፉም መንፈስ ከእግዚአብሔር ጋር እተመካከረ ለእግዚአብሔር ያሳስትለታል። የሚሳሳተው ሰው እና የሚያሳስተው ክፉ መንፈስ ለእግዚአብሔር ናቸው፦
2ኛ ተሰሎንቄ 2፥12 ስለዚህም ምክንያት፥ በእውነት ያላመኑ ነገር ግን በዓመፅ ደስ ይላቸው የነበሩ ሁሉ ፍርድን እንዲቀበሉ፥ *ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል*።
መሣፍንት 9፥23 *እግዚአብሔር በአቤሜሌክና በሴኬም ሰዎች መካከል ክፉን መንፈስ ሰደደ*፤
1ኛ ነገሥት 22 20-23 እግዚአብሔርም፦ ወጥቶ በሬማት ዘገለዓድ ይወድቅ ዘንድ *አክዓብን የሚያሳስት ማን ነው?* አለ። አንዱም እንዲህ ያለ ነገር፥ ሌላውም እንዲያ የለ ነገር ተናገረ። *መንፈስም ወጣ በእግዚአብሔርም ፊት ቆሞ፦ እኔ አሳስተዋለሁ አለ*። እግዚአብሔርም፦ በምን? አለው እርሱም፦ *ወጥቼ በነቢያቶቹ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ እሆናለሁ አለ*። እግዚአብሔርም፦ *ማሳሳትስ ታሳስተዋለህ፥ ይሆንልሃልም ውጣ፥ እንዲሁም አድርግ አለ*። አሁንም፦ እነሆ፥ እግዚአብሔር በእነዚህ *በነቢያትህ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ አድርጎአል*፤ እግዚአብሔርም በላይህ ክፉ ተናግሮብሃል።
ኢዮብ 12፥16 ኃይልና ጥበብ በእርሱ ዘንድ ናቸው፤ *የሚስተው እና የሚያስተው ለእርሱ ናቸው*።

ይህ ሁላ ባተሎና ዘባተሎ እሳቤ ባይብል ላይ እያለ ከላይ ያለው ሐዲስ ለመተቸት የሚያስችል የሞራል ብቃት፣ አቅም፣ ወኔም የላችሁም። አላህ ሂዳያ ይስጣችሁ፥ ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ክርስቲያን፦ "ፍጡሮቹ ፈጣሪን ገደሉት"
ሙሥሊም፦ "ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?
ክርስቲያን፦ "ፈጣሪ ሁሉን ቻይ ነው"
ሙሥሊም፦ ፈጣሪ ሁሉን ቻይ አመሆን ይችላልን?
ክርስቲያን፦ "ይህማ የፈጣሪ ባሕርይ አይደለም"
ሙሥሊም፦ ባይሆን በፍጡሮቹ ፈጣሪ መገደሉ ነው የእርሱ ባሕርይ የማይሆነው። እሺ ፈጣሪ ሲሞት እርሱ ያሞተው ማን ነው?
ክርስቲያን፦ "ሌላ አካል አለ፥ እርሱን ያሞተው እና ከሞት ያስነሳው"
ሙሥሊም፦ እርሱ ደግሞ ማን ነው?
ክርስቲያን፦ "አብ ይባላል"
ሙሥሊም፦ አብ ከወልድ ጋር በባሕርይ አንድ ነው ብላችሁ ታምናላችሁ፥ ወልድ ሲሞት ከአብ ባሕርይ ጋር አንድ የሆነው ባሕርይ ሞቷል ወይስ አልሞተም?
ክርስቲያን፦ "ሥላሴን እመራመራለው ብትል አይምሮህን ታጣዋለህ፥ እክዳለው ብትል ነፍስህን ታጣለህ"
ሙሥሊም፦ ይህ ነው መልሱ?
ክርስቲያን፦ "አዎ! እምነት ሞኝነት ነው"
ሙሥሊም፦ እሺ ይኹንልህ ግን አእምሮህ እረፍት የለውም። ፈጣሪ በፍጡሮቹ መገደሉ ሲገርመኝ፥ እርሱን ያሞተው ሌላ ፈጣሪ መኖሩ አስደመመኝ"።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሰኞ እና ሐሙስ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና። وَمَآ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمْ عَنْهُ فَٱنتَهُوا۟ ۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ

ሙሥሊም በሳምንት ውስጥ ሁለት ቀናት የሡናህ አፅዋማት ይፆማል፥ እነርሱም ሰኞ እና ሐሙስ ናቸው። ሰኞ የሚፆምበት አራት ምክንያት አሉ፥ እነርሱም፦
1ኛ ወደ ነቢያችን"ﷺ" ወሕይ የመጣበት ቀን ነው።
2ኛ. ነቢያችን"ﷺ" የተወለዱበት ቀን ነው።
3ኛ. ሥራዎች ወደ አላህ የሚቀርቡበት ቀን ነው።
4ኛ. አላህ ይቅር የሚልበት ቀን ነው፦
ኢማም ሙስሊም: መጽሐፍ 13, ሐዲስ 256
አቢ ቀታደህ አንሷሪይ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ *”የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሰኞ ቀን ስለሚጾምበት ተጠየቁ፥ እርሳቸውም፦ “የተወለድኩበት እና ወሕይ የወረደልኝ ቀን ነው” አሉ*። عَنْ أَبِي قَتَادَةَ الأَنْصَارِيِّ، رضى الله عنه أَنَّرَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم سُئِلَ عَنْ صَوْمِ الاِثْنَيْنِ فَقَالَ ‏ “‏ فِيهِ وُلِدْتُ وَفِيهِ أُنْزِلَ عَلَىَّ ‏”‏ ‏.‏
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 66
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ሥራዎች ሰኞ እና ሐሙስ ወደ አላህ ይቀርባሉ፥ ሥራዬ ፆመኛ ሆኜ እንዲቀርብልኝ እወዳለሁኝ"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ تُعْرَضُ الأَعْمَالُ يَوْمَ الاِثْنَيْنِ وَالْخَمِيسِ فَأُحِبُّ أَنْ يُعْرَضَ عَمَلِي وَأَنَا صَائِم
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 7, ሐዲስ 1812
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" ሰኞ እና ሐሙስ ይፆሙ ነበር። እንዲህም ተባለ፦ *"የአላህ መልክተኛ"ﷺ" ሆይ! ለምን ሰኞ እና ሐሙስ ይፆማሉ? እርሳቸውም፦ "ሰኞ እና ሐሙስ አላህ ሁሉንም ሙሥሊም ይቅር ይላል ከተቷቷዉት ሁለት በስተቀር። እርሳቸውም፦ "እነዚህ ሁለቱን እስኪስማሙ ድረስ ተዋቸው"*። عَنْ سُهَيْلِ بْنِ أَبِي صَالِحٍ، عَنْ أَبِيهِ، عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ النَّبِيَّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ كَانَ يَصُومُ الاِثْنَيْنِ وَالْخَمِيسَ ‏.‏ فَقِيلَ يَا رَسُولَ اللَّهِ إِنَّكَ تَصُومُ يَوْمَ الاِثْنَيْنِ وَالْخَمِيسِ فَقَالَ ‏ "‏ إِنَّ يَوْمَ الاِثْنَيْنِ وَالْخَمِيسِ يَغْفِرُ اللَّهُ فِيهِمَا لِكُلِّ مُسْلِمٍ إِلاَّ مُهْتَجِرَيْنِ يَقُولُ دَعْهُمَا حَتَّى يَصْطَلِحَا ‏"‏ ‏

ሐሙስ የሚፆምበት ምክንያት ሁለት ሲሆን እርሱ ከላይ ሐዲሱ ላይ እንደተገለጸው ሥራዎች ወደ አላህ የሚቀርቡበት እና አላህ ይቅር የሚልበት ቀን ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 45, ሐዲስ 43
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም እንዲህ አሉ፦ *"የጀነት ደጃፎች በአላህ ላይ ምንም ነገር ላላሻረከ ሁሉ ሰኞ ቀን እና ሐሙስ ቀን ይከፈታል፥ አንድ ሰው በውስጡ መራራነት በወንድሙ ላይ ካለበት በስተቀር"። እንዲህም ይባላል፦ "በሁለቱ መካከል ዕርቅ እስኪሆን ድረስ አጢኑ፣ በሁለቱ መካከል ዕርቅ እስኪሆን ድረስ አጢኑ፣ በሁለቱ መካከል ዕርቅ እስኪሆን ድረስ አጢኑ"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ تُفْتَحُ أَبْوَابُ الْجَنَّةِ يَوْمَ الاِثْنَيْنِ وَيَوْمَ الْخَمِيسِ فَيُغْفَرُ لِكُلِّ عَبْدٍ لاَ يُشْرِكُ بِاللَّهِ شَيْئًا إِلاَّ رَجُلاً كَانَتْ بَيْنَهُ وَبَيْنَ أَخِيهِ شَحْنَاءُ فَيُقَالُ أَنْظِرُوا هَذَيْنِ حَتَّى يَصْطَلِحَا أَنْظِرُوا هَذَيْنِ حَتَّى يَصْطَلِحَا أَنْظِرُوا هَذَيْنِ حَتَّى يَصْطَلِحَا

የጀነት ደጃፎች ሰኞ ቀን እና ሐሙስ ቀን ክፍት የሆነው ቂም ወይም ጥላቻ በሙሥሊም ወንድሙ ላይ በልቡ ላልቋጠረ ሙሥሊም ነው። ሰኞ እና ሐሙስ ሳምንታዊ መጠነ-ሰፊ የአምልኮ ጊዜ ለማመልከት እንጂ ሌላውን የአዘቦት ቀናት ሥራዎች አይቀርቡም ወይም አላህ ይቅር አይልም ማለትን አያሲዝም። እንግዲህ እነዚህን የሡናህ አፅዋማት እንድንፆም የተሰጠን ከመልእክተኛው ነው፦
59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና። وَمَآ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمْ عَنْهُ فَٱنتَهُوا۟ ۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 64
ዓኢሻህ እንደተረከችው፥ እንዲህ አለች፦ *"ነቢዩ"ﷺ" ሰኞ እና ሐሙስ ይፆሙ ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم يَتَحَرَّى صَوْمَ الاِثْنَيْنِ وَالْخَمِيسِ

ኢሥላም ሰው ሠራሽ ሕግና ሥርዓት ሳይሆን ዐቂደቱ አር-ረባንያህ ነው። ይህንን ስንል አርቲ ቡርቲና ቶራ ቦራ የሆነ ስሁትና መሪር የቡና ወሬ ይዘን ሳይሆን ቁርኣንና ሐዲስን ያማከለ ስሙርና ጥዑም ማስረጃ ይዘን ነው።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኢሕሣን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥195 በአላህም መንገድ ለግሱ፡፡ በእጆቻችሁም ነፍሶቻችሁን ወደ ጥፋት አትጣሉ፡፡ *"በጎ ሥራንም ሥሩ! አላህ በጎ ሠሪዎችን ይወዳልና"*፡፡ وَأَنفِقُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَلَا تُلْقُوا بِأَيْدِيكُمْ إِلَى التَّهْلُكَةِ ۛ وَأَحْسِنُوا ۛ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُحْسِنِينَ

“ኢሕሣን” إِحْسَٰن የሚለው ቃል "አሕሠነ" أَحْسَنَ ማለትም "አስዋበ" "አሳመረ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማስዋብ” “ማሳመር” ማለት ነው። ለምሳሌ “ሐሠን” حَسَن ማለት “ውብ” "ያማረ" "መልካም" "ጥሩ" "በጎ" ማለት ሲሆን “ሑሥን” حُسْن ማለት ደግሞ “ውበት” “መልካምነት” "ጥሩነት" "በጎነት" ማለት ነው። ኢሕሣን የዲን ማሳመሪያና ማስዋቢያ ነው።
“ዲን” دِين ማለት “ሃይማኖት” “ፍትህ” “ፍርድ” “ሕግ” “መርሕ” ማለት ነው። "ዲን" መርሕ እና ሥነ-ምግባር ያቀፈ ሥርወ-እምነት ነው። “ዲን” ደግሞ ሦስት ደረጃ አሉት፥ እነርሱም፦
1ኛ. “ኢሥላም” إِسْلَٰم
2ኛ. “ኢማን” إِيمَٰن
3ኛ. “ኢሕሣን” إِحْسَٰن ናቸው።
“ኢሥላም” ማለት “አንዱን አምላክ ብቻ ማምለክ” ነው፥ አምስት መሠረቶች አሉት።
“ኢማን” ማለት “እምነት” ማለት ነው፥ ስድስት መሠረቶች አሉት።
“ኢሕሣን” ማለት ደግሞ “አላህን እንደምታየው አርገህ ማምለክ፥ አሊያም አላህ እንደሚያይህ አርገህ ማምለክ" ማለት ነው፦
ሡነን ነሣኢይ መጽሐፍ 47 , ሐዲስ 6
ዑመር ኢብኑ ኸጣብ እንዳስተላለፈው፦ “አንድ በጣም ነጭ ልብስ የለበሰና በጣም ጥቁር ጸጉር ያለው ሰው በመጣ ጊዜ ከአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ጋር ነበርን፣ ወደ እርሳቸው ሲጓዝ አይታይም ነበር፥ ወደ ነቢዩ”ﷺ” እስከሚደርስ ድረስ ከእኛ መካከል ማንም ዐላወቀውም፤ ጉልበቱን በእራሳቸው ጉልበት ተቃራኒ አድርጎ ከዚያም እንዲህ አለ፦ *”ሙሐመድ ሆይ! ስለ ኢሥላም ንገረኝ አለ፥ እርሳቸውም፦ "ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፥ ሙሐመድም የአላህ መልእክተኛ ነው” የሚል ምስክርነት፣ ሶላትን መቆም፣ ዘካህን መስጠት፣ ረመዷንን መፆም እና ለመጓዝ አቅም ካለህ የአላህን ቤት መጎብኘት ነው" አሉ። እርሱም፦ "እውነት ተናገርክ" አለ፥ እኛም በሚጠይቃቸው ነገር ተገረምን። ከዚያም ስለ ኢማን ንገረኝ አለ፥ እርሳቸውም፦ “በአላህ ማመን፣ በመላእክቱ ማመን፣ በመጽሐፍቱ ማመን፣ በነቢያቱ ማመን፣ በመጨረሻው ቀን ማመን እና በሰናይ እና እኩይ ቀደር ማመን ነው” አሉ። እርሱም፦ "እውነት ተናገርክ" አለ፥ ከዚያም ስለ ኢሕሣን ንገረኝ አለ፥ እርሳቸውም፦ "አላህን እንደምታየው አርገህ ማምለክ፥ አሊያም አላህ እንደሚያይህ አርገህ ማምለክ ነው" አሉ"*። قَالَ حَدَّثَنِي عُمَرُ بْنُ الْخَطَّابِ، قَالَ بَيْنَمَا نَحْنُ عِنْدَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ذَاتَ يَوْمٍ إِذْ طَلَعَ عَلَيْنَا رَجُلٌ شَدِيدُ بَيَاضِ الثِّيَابِ شَدِيدُ سَوَادِ الشَّعَرِ لاَ يُرَى عَلَيْهِ أَثَرُ السَّفَرِ وَلاَ يَعْرِفُهُ مِنَّا أَحَدٌ حَتَّى جَلَسَ إِلَى رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَأَسْنَدَ رُكْبَتَيْهِ إِلَى رُكْبَتَيْهِ وَوَضَعَ كَفَّيْهِ عَلَى فَخِذَيْهِ ثُمَّ قَالَ يَا مُحَمَّدُ أَخْبِرْنِي عَنِ الإِسْلاَمِ قَالَ ‏"‏ أَنْ تَشْهَدَ أَنْ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللَّهِ وَتُقِيمَ الصَّلاَةَ وَتُؤْتِيَ الزَّكَاةَ وَتَصُومَ رَمَضَانَ وَتَحُجَّ الْبَيْتَ إِنِ اسْتَطَعْتَ إِلَيْهِ سَبِيلاً ‏"‏ ‏.‏ قَالَ صَدَقْتَ ‏.‏ فَعَجِبْنَا إِلَيْهِ يَسْأَلُهُ وَيُصَدِّقُهُ ثُمَّ قَالَ أَخْبِرْنِي عَنِ الإِيمَانِ قَالَ ‏"‏ أَنْ تُؤْمِنَ بِاللَّهِ وَمَلاَئِكَتِهِ وَكُتُبِهِ وَرُسُلِهِ وَالْيَوْمِ الآخِرِ وَالْقَدَرِ كُلِّهِ خَيْرِهِ وَشَرِّهِ ‏"‏ ‏.‏ قَالَ صَدَقْتَ ‏.‏ قَالَ فَأَخْبِرْنِي عَنِ الإِحْسَانِ قَالَ ‏"‏ أَنْ تَعْبُدَ اللَّهَ كَأَنَّكَ تَرَاهُ فَإِنْ لَمْ تَكُنْ تَرَاهُ فَإِنَّهُ يَرَاكَ

አላህን እንደምታየው አርገህ ማምለክ፥ አሊያም አላህ እንደሚያይህ አርገህ ማምለክ የዲን ማሳመሪያና ማስዋቢያ ነው። አንድ ሰው በኢስላም “ሙሥሊም” مُسْلِم ሲባል፣ በኢማን “ሙእሚን” مُؤْمِن ሲባል፣ በኢሕሣን ደግሞ “ሙሕሢን” مُحْسِن ይባላል። “ሙሕሢን” مُحْسِن ማለት “ጥሩ ሠሪዎች” “መልካም ሠሪዎች” “በጎ ሠሪዎች” ማለት ነው፥ የዲን መዋቢያውና ማሳመሪያው “መልካም ሥራ” ነው። አላህ ሙሕሢን ከሚባሉትን ባሮቹ ጋር ነው፥ እርሱ ሙሕሢን የሚባሉትን ባሮች ይወዳል፦
29፥69 እነዚያም በእኛ መንገድ የታገሉ መንገዳችንን በእርግጥ እንመራቸዋለን፡፡ *"አላህም በእርግጥ ከበጎ ሠሪዎች ጋር ነው"*፡፡ وَالَّذِينَ جَاهَدُوا فِينَا لَنَهْدِيَنَّهُمْ سُبُلَنَا ۚ وَإِنَّ اللَّهَ لَمَعَ الْمُحْسِنِينَ
2፥195 በአላህም መንገድ ለግሱ፡፡ በእጆቻችሁም ነፍሶቻችሁን ወደ ጥፋት አትጣሉ፡፡ *"በጎ ሥራንም ሥሩ! አላህ በጎ ሠሪዎችን ይወዳልና"*፡፡ وَأَنفِقُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَلَا تُلْقُوا بِأَيْدِيكُمْ إِلَى التَّهْلُكَةِ ۛ وَأَحْسِنُوا ۛ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُحْسِنِينَ

"በጎ ሥራንም ሥሩ" ለሚለው ቃል የገባው "አሕሢኑ" َأَحْسِنُوا ሲሆን "አሕሠነ" أَحْسَنَ ማለትም "አስዋበ" ወይም "አሳመረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ነው። አላህ ሙሕሢን ከሚላቸው ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኢቅራ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

96፥1 *”አንብብ በዚያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም”*፡፡ اقْرَأْ بِاسْمِ رَبِّكَ الَّذِي خَلَقَ

አምላካችን አላህ በጂብሪል ለነቢያችን”ﷺ” “ኢቅራ” اقْرَأْ ማለትም “አንብብ” ወይም “አነብንብ” ብሎ አዟቸዋል፦
96፥1 *”አንብብ በዚያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም”*፡፡ اقْرَأْ بِاسْمِ رَبِّكَ الَّذِي خَلَقَ

“ቁርኣን” قُرْءَان የሚለው ቃል “ቀረአ” قَرَأَ ማለትም “አነበበ” ወይም “አነበነበ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “መነባነብ”recitation” ማለት ነው። “ኢቅራ” اقْرَأْ ትእዛዛዊ ግስ ነው። አስቀሪ ቁርኣንን ይቀራልህና ከዚያ ያስቀርሃል። የግድ በወረቀት የተጻፈ ክታብ መኖር መስፈት አይደለም። “ቁርኣን” قُرْءَان ማለት “በልብ ታፍዞ በምላስ የሚነበነብ መነባነብ” ማለት ሲሆን ይህም ቁርኣን አምላካችን አላህ በጂብሪል ለነብያችን”ﷺ” የሚያስቀራቸው ቂራኣት ነው፦
2፥252 *እነዚህ በእውነት በአንተ ላይ የምናነባቸው ሲኾኑ የአላህ አንቀጾች ናቸው*፤ تِلْكَ آيَاتُ اللَّهِ نَتْلُوهَا عَلَيْكَ بِالْحَ
87፥6 *ቁርኣንን በእርግጥ እናስነብብሃለን፤ አትረሳምም*፡፡ سَنُقْرِئُكَ فَلَا تَنسَىٰ
75:18 *ባነበብነውም ጊዜ ንባቡን ተከተል*። فَإِذَا قَرَأْنَاهُ فَاتَّبِعْ قُرْآنَه
75፥17 *በልብህ ውስጥ መሰብሰቡ እና ማንበቡ በእኛ ላይ ነውና*፡፡ إِنَّ عَلَيْنَا جَمْعَهُ وَقُرْآنَهُ

“ማንበቡ” ለሚለው ቃል የገባው “ቁርኣነሁ” َقُرْآنَهُ ሲሆን የግስ መደብ ነው፤ የስም መደቡ ደግሞ “ቁርኣን” قُرْءَان ነው፤ ይህ የሚነበበው አንቀጽ የአላህ የራሱ ንግግር ስለሆነ አላህ በመጀመሪያ መደብ “አያቱና” آيَاتُنَا ማለትም “አንቀጾቻችን” በማለት ይናገራል፦
46፥7 *በእነርሱም ላይ አንቀጾቻችን ግልጾች ኾነው በተነበቡ ጊዜ* እነዚያ እውነቱን በመጣላቸው ጊዜ የካዱትን «ይህ ግልጽ ድግምት ነው» አሉ፡፡ وَإِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ آيَاتُنَا بَيِّنَاتٍ قَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا لِلْحَقِّ لَمَّا جَاءَهُمْ هَـٰذَا سِحْرٌ مُّبِينٌ

“ቃሪእ” قَارِئ‎ ማለት “በልብ አፍዞ በምላስ አነብናቢ”reciter” ማለት ነው፤ የቃሪእ ብዙ ቁጥር “ቁርራ” قُرَّاء ነው፤ አንድ ቃሪ የሆነ ሰው ቁርኣንን ሲቀራ አዳማጩ የሚያደምጠው የአላህን ንግግር ነው፦
ኢማም ሙስሊም: መጽሐፍ 4, ሐዲስ 166
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *”በአላህ አዘ ወጀል ንግግር፦ “በቁርኣን ንባብ ልትቸኩል ምላስህን በእርሱ አታላውስ” ነብዩ”ﷺ” ጂብሪል ወደ እሳቸው ሲያወርድ ምላሳቸውና ከንፈራቸውን ለማንበብ በማንበብ ያላውሱ ስለነበር ነው፤ ይህ ችግር አልፎ አልፎ ይታይ ነበርና፤ አላህ ተዓላ፦ “በቁርኣን ንባብ ልትቸኩል ምላስህን በእርሱ አታላውስ” የሚለውን አወረደ፤ “በልብህ ውስጥ መሰብሰቡና ማንበቡ በእኛ ላይ ነውና” ብሎ ሰበሰበው፤ በእርግጥም በልብህ ውስጥ እንድትቀራው እንጠብቀዋለን አንተም ትቀራዋለህ” ማለት ነው፤ “ባነበብነውም ጊዜ ካለቀ በኋላ ንባቡን ተከተል፣ ከዚያም ማብራራቱ በእኛ ላይ ነው” ማለት “በምላስህ ላይ ማስቀመጡ በእኛ ላይ ነው” ማለት ነው፤ ጂብሪል ወደ እርሳቸው በሚመጣ ጊዜ ዝም ይላሉ፤ ከእርሳቸው በተለየ ጊዜ አላህ ቃል እንደገባላቸው ይቀራሉ*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، فِي قَوْلِهِ عَزَّ وَجَلَّ ‏{‏ لاَ تُحَرِّكْ بِهِ لِسَانَكَ‏}‏ قَالَ كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم إِذَا نَزَلَ عَلَيْهِ جِبْرِيلُ بِالْوَحْىِ كَانَ مِمَّا يُحَرِّكُ بِهِ لِسَانَهُ وَشَفَتَيْهِ فَيَشْتَدُّ عَلَيْهِ فَكَانَ ذَلِكَ يُعْرَفُ مِنْهُ فَأَنْزَلَ اللَّهُ تَعَالَى ‏{‏ لاَ تُحَرِّكْ بِهِ لِسَانَكَ لِتَعْجَلَ بِهِ‏}‏ أَخْذَهُ ‏{‏ إِنَّ عَلَيْنَا جَمْعَهُ وَقُرْآنَهُ‏}‏ إِنَّ عَلَيْنَا أَنْ نَجْمَعَهُ فِي صَدْرِكَ ‏.‏ وَقُرْآنَهُ فَتَقْرَأُهُ ‏{‏ فَإِذَا قَرَأْنَاهُ فَاتَّبِعْ قُرْآنَهُ‏}‏ قَالَ أَنْزَلْنَاهُ فَاسْتَمِعْ لَهُ ‏{‏ إِنَّ عَلَيْنَا بَيَانَهُ‏}‏ أَنْ نُبَيِّنَهُ بِلِسَانِكَ فَكَانَ إِذَا أَتَاهُ جِبْرِيلُ أَطْرَقَ فَإِذَا ذَهَبَ قَرَأَهُ كَمَا وَعَدَهُ اللَّهُ ‏

“ጀመዐ” جَمَعَ ማለት “ሰበሰበ” ማለት ሲሆን “ጀመዕ” جَمَع ማለት ደግሞ “ስብስብስ”Collection” ማለት ነው። በልብ ላይ ለመሰብሰብ ደግሞ በቃል ነው የሚታፈዘው እንጂ በወረቀት አይደለም። አምላካችም አላህ ቁርኣንን በነብያችን”ﷺ” ልብ ላይ ያወረደው መነባነብ እንጂ በወረቀት የተጻፈን መጽሐፍ አላወረደም፦
26፥194 ከአስስጠንቃቂዎቹ ትኾን ዘንድ *በልብህ ላይ አወረደው*፡፡ عَلَىٰ قَلْبِكَ لِتَكُونَ مِنَ الْمُنذِرِينَ
2፥97 *በአላህ ፈቃድ በልብህ ላይ አውርዶታልና*፡፡ فَإِنَّهُ نَزَّلَهُ عَلَىٰ قَلْبِكَ بِإِذْنِ اللَّهِ
6፥7 *በአንተም ላይ በወረቀት የተጻፈን መጽሐፍ ባወረድን እና በእጆቻቸው በነኩት ኖሮ እነዚያ የካዱት ሰዎች «ይህ ግልጽ ድግምት እንጅ ሌላ አይደለም» ባሉ ነበር*፡፡ وَلَوْ نَزَّلْنَا عَلَيْكَ كِتَابًا فِي قِرْطَاسٍ فَلَمَسُوهُ بِأَيْدِيهِمْ لَقَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا إِنْ هَـٰذَا إِلَّا سِحْرٌ مُّبِينٌ

“ቂርጧስ” قِرْطَاس ማለት በብራና የተጻፈ “ወረቀት” ነው፤ ቁርኣን በዚህ ቁስ ተጽፎ አልወረደም፤ ወደ ነብያችን”ﷺ” ልብ የተወረደው ተንዚል ወሕይ ነው።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ፍትሐዊነት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥8 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለአላህ ቀጥተኞች በትክክል መስካሪዎች ኹኑ፡፡ ሕዝቦችንም መጥላት ባለማስተካከል ላይ አይገፋፋችሁ፡፡ አስተካክሉ፡፡ እርሱ ማስተካከል ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ لِلَّهِ شُهَدَاءَ بِالْقِسْطِ ۖ وَلَا يَجْرِمَنَّكُمْ شَنَآنُ قَوْمٍ عَلَىٰ أَلَّا تَعْدِلُوا ۚ اعْدِلُوا هُوَ أَقْرَبُ لِلتَّقْوَىٰ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ

"ዐድል" عَدْل የሚለው ቃል "ዐደለ" عَدَلَ ማለትም "አስተካከለ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ማስተካከል" "ፍርድ" "ፍትሕ" ማለት ነው፥ "ዐዲል" عَادِل‎ ማለት "ፍትሓዊ" ማለት ሲሆን "ተዕዲል" تَعْدِيل‎ ማለት ደግሞ "ፍትሐዊነት" ማለት ነው። አምላካችን አላህ በፍትሕ ያዛል፥ ከአስከፊም፣ ከሚጠላም ነገር ሁሉ እና ከመበደልም ይከለክላል፦
16፥90 *አላህ በማስተካከል፣ በማሳመርም፣ ለዝምድና ባለቤት በመስጠትም ያዛል፡፡ ከአስከፊም፣ ከሚጠላም ነገር ሁሉ እና ከመበደልም ይከለክላል፡፡ ትገነዘቡ ዘንድ ይገስጻችኋል*፡፡ إِنَّ اللَّهَ يَأْمُرُ بِالْعَدْلِ وَالْإِحْسَانِ وَإِيتَاءِ ذِي الْقُرْبَىٰ وَيَنْهَىٰ عَنِ الْفَحْشَاءِ وَالْمُنكَرِ وَالْبَغْيِ ۚ يَعِظُكُمْ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ማስተካከል” ለሚለው ቃል የገባው “ዐድል” عَدْل መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል። የፍትሕ ተቃራኒ ዙልም ነው፥ “ዙልም” ظُلْم የሚለው ቃል “ዞለመ” ظَلَمَ ማለትም “በደለ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “በደል” ማለት ነው። "ከሚጠላ ነገር ሁሉ" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። አላህ ዘንድ የሚጠላ ነገር ሺርክ፣ ኩፍር፣ ዘረኝነት፣ ጎጠኝነት፣ ብሔርተኝነት፣ ዘውገኝነት ነው። የአንድን ሰው ዘውግ፣ ብሔር፣ ዘር መጥላት በራሱ የተጠላ ነገር ነው። ሰውን በቋንቋው፣ በዘሩ፣ በዘውጉ፣ በብሔሩ መጥላት የፍትሕ ተቃራኒ ነው፦
5፥8 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለአላህ ቀጥተኞች በትክክል መስካሪዎች ኹኑ፡፡ ሕዝቦችንም መጥላት ባለማስተካከል ላይ አይገፋፋችሁ፡፡ አስተካክሉ፡፡ እርሱ ማስተካከል ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ لِلَّهِ شُهَدَاءَ بِالْقِسْطِ ۖ وَلَا يَجْرِمَنَّكُمْ شَنَآنُ قَوْمٍ عَلَىٰ أَلَّا تَعْدِلُوا ۚ اعْدِلُوا هُوَ أَقْرَبُ لِلتَّقْوَىٰ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ

አሁንም "አስተካክሉ" ለሚለው የገባው ቃል “ተዕዲሉ” تَعْدِلُوا መሆኑ ልብ በል። "ሕዝቦችን መጥላት" ወደ ፍትሕ አልባ ይገፋፋል፥ ፍትሕ ግን ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው። በፍትሕ የሚጠላ ነገር ሁሉ ለአላህ ብሎ ጠልቶ መከልከል ከመበደል ይታደጋል። ፍትሕ ከራስ፣ ከወላጅ እና ከቅርብ ዘመድ በላይ ለአላህ ተብሎ የሚደረግ፣ ከዝንባሌ የጸዳ፣ ሀብታም ወይም ድኻ ሳይል፣ አላህ ውስጠ ዐዋቂ ነው ብሎ በትክክል መቆም ነው፦
4፥135 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *በትክክል ፍትሕ ቀዋሚዎች በራሳችሁ ወይም በወላጆች እና በቅርብ ዘመዶች ላይ ቢኾንም እንኳ ለአላህ መስካሪዎች ኹኑ፡፡ ሀብታም ወይም ድኻ ቢኾን አላህ በእነርሱ ከእናንተ ይበልጥ ተገቢ ነው፡፡ እንዳታደሉም ዝንባሌን አትከተሉ፡፡ ብታጠምሙም ወይም መመስከርን ብትተው አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ بِالْقِسْطِ شُهَدَاءَ لِلَّهِ وَلَوْ عَلَىٰ أَنفُسِكُمْ أَوِ الْوَالِدَيْنِ وَالْأَقْرَبِينَ ۚ إِن يَكُنْ غَنِيًّا أَوْ فَقِيرًا فَاللَّهُ أَوْلَىٰ بِهِمَا ۖ فَلَا تَتَّبِعُوا الْهَوَىٰ أَن تَعْدِلُوا ۚ وَإِن تَلْوُوا أَوْ تُعْرِضُوا فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرًا

አሁንም እዚህ አንቀጽ ላይ “ተዕዲሉ” تَعْدِلُوا የሚለው ቃል ይሰመርበት። ማዳላት የሚመጣው ዝንባሌን ከመከተል ስለሆነ "እንዳታደሉም ዝንባሌን አትከተሉ" ብሎ ነግሯናል። “አህዋ” أَهْوَآء ማለትም “ዝንባሌ”inclination” ነው፤ አንድ ሙስሊም ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት። ዝንባሌ ደግሞ ከተከተሉት ሊመለክ የሚችል አደገኛ ጣዖት ነው፦
79፥40-41 በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ *ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት*፡፡ وَأَمَّا مَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ وَنَهَى النَّفْسَ عَنِ الْهَوَىٰ فَإِنَّ الْجَنَّةَ هِيَ الْمَأْوَىٰ
25:43 *ዝንባሌውን አምላኩ አድርጎ የያዘውን ሰው አየህን? አንተ በእርሱ ላይ ጠባቂ ትሆናለህን?* أَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَـٰهَهُ هَوَاهُ أَفَأَنتَ تَكُونُ عَلَيْهِ وَكِيلًا

ማደላት ከዝንባሌ የሚመጣ ሲሆን ፍትሐዊነት ግን ለአላህ ተብሎ የሚደረግ የሥነ-ምግባር እሴት ነው። ይህ ፍትሓዊነት ለመላው የሰው ዘር ሁሉ በሰውነትን የምናደርገው ነው፦
60፥8 *ከእነዚያ በሃይማኖት ካልተጋደሏችሁ፣ ከአገሮቻችሁም ካላወጡዋችሁ ከሓዲዎች መልካም ብትውሉላቸው እና ወደ እነርሱ ብታስተካክሉ አላህ አይከለክላችሁም፡፡ አላህ ትክክለኞችን ይወዳልና*፡፡ لَّا يَنْهَاكُمُ اللَّهُ عَنِ الَّذِينَ لَمْ يُقَاتِلُوكُمْ فِي الدِّينِ وَلَمْ يُخْرِجُوكُم مِّن دِيَارِكُمْ أَن تَبَرُّوهُمْ وَتُقْسِطُوا إِلَيْهِمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُقْسِطِينَ

ዲናችንን አክብረው ካልተጋደሉንና ካላሳደዱን ማናቸውም ሕዝቦች ጋር በዝምድና፣ በባልደረባ፣ በጉርብትና መልካም መዋዋል እና ማስተካከል ይቻላል። “ብታስተካክሉ” ለሚለው ቃል የገባው “ቱቅሢጡ” َتُقْسِطُوا ሲሆን የስም መደቡ “ቂሥጥ” قِسْط ማለትም “ፍትሕ” ነው። ለአላህ ብለን ስናስተካክል “ሙቅሢጢን” مُقْسِطِين ማለትም “ፍትኸኞችን” “ትክክለኞች” “አስተካካዮች” እንባላለን። አላህ ሙቅሢጢንን ይወዳል፦
49፥9 *በነገሩ ሁሉ አስተካክሉም፡፡ አላህ አስተካካዮችን ይወዳልና*፡፡ وَأَقْسِطُوا ۖ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُقْسِطِينَ
ለዘሩ፣ ለብሔሩ፣ ለፓለቲካው፣ ለዝንባሌው፣ ለስሜቱ ብሎ መውደድ እና መጥላት ኪሳራ አለው፥ በዱንያም በአኺራም ይጎዳል። ነገር ግን ለአላህ ብሎ መውደድ እና መጥላት ትርፍ አለው፥ በዱንያም በአኺራም ይጠቅማል፦
አቢ ዳውድ መጽሐፍ 42, ሐዲስ 86
አቢ ኡማማህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ማንኛውም ሰው ለአላህ ብሎ የወደደ እና የጠላ፣ ለአላህ ብሎ የሰጠ እና የነፈገ የተሟላ ኢማን አለው”*። عَنْ أَبِي أُمَامَةَ، عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم أَنَّهُ قَالَ ‏ “‏ مَنْ أَحَبَّ لِلَّهِ وَأَبْغَضَ لِلَّهِ وَأَعْطَى لِلَّهِ وَمَنَعَ لِلَّهِ فَقَدِ اسْتَكْمَلَ الإِيمَان

ለእዩልኝና ስሙልኝ ሳይሆን ለአላህ ብሎ መስጠት የተሟላ ኢማን ነው። የምንሰጠው ልግስና ለጥፋት ለምሳሌ ለሲጋራ፣ ለጫት፣ ለመጠጥ እንደሚውል ተረድተን ለአላህ ብሎ መንፈግ የተሟላ ኢማን ነው። ለአላህ ብሎ መውደድ እና መጥላት የተሟላ ኢማን ነው። ይህ አል-ወላእ ወል በራእ ነው። “ወላእ” وَلَاء ማለት “መውደድ” “መቅረብ” “መርዳት” ማለት ሲሆን አላህን፣ መልእክተኛው፣ እንዲሁም ዲነል ኢሥላምን እና ሙሥሊሞችን መወደድ፣ መቅረብ እና መርዳት ነው። “በራእ” بَراء‎ ማለት “መጥላት” “መራቅ” “መተው” ማለት ሲሆን ከአላህ ውጭ የሚመለኩ ጣዖታትን እና የአላህ ጠላቶችን ለአላህ ብሎ መጥላት፣ መራቅ እና መተው ነው። ከዚህ በተረፈ ዝንባሌን ተከትለው ለሰዎች የማያዝኑ አላህ ለእነርሱ አያዝንላቸውም፥ ሰዎችን በዱንያ ያለ ፍትሕ የሚቀጡ አላህ ይቀጣቸዋል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97 ሐዲስ 6
ጀሪር ኢብኑ ዐብደሏህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" አሉ፦ *"ለሰዎች የማያዝኑ አላህ ለእነርሱ አያዝንላቸውም"*። ظَبْيَانَ عَنْ جَرِيرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ لاَ يَرْحَمُ اللَّهُ مَنْ لاَ يَرْحَمُ النَّاسَ
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 45 ሐዲስ 157
ዑርዋህ ኢብኑ ዙበይር እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው፦ *"እነዚያ ሰዎችን በዱንያ ያለ ፍትሕ የሚቀጡ አላህ ይቀጣቸዋል"*። عَنْ عُرْوَةَ، بْنِ الزُّبَيْرِ فَقَالَ مَا هَذَا إِنِّي سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ "‏ إِنَّ اللَّهَ يُعَذِّبُ الَّذِينَ يُعَذِّبُونَ النَّاسَ فِي الدُّنْيَا

ለሰዎች ማዘን ማለት በትክክል መመዘን፣ ተመዛኙንም አለማጉደል፣ አደራዎችን ወደ ባለቤቶቻቸው ማድረስ በሰዎችም መካከል በፍትሕ መበየን ነው፦
55፥9 *"መመዘንንም በትክክል መዝኑ፡፡ ተመዛኙንም አታጉድሉ"*፡፡ وَأَقِيمُوا الْوَزْنَ بِالْقِسْطِ وَلَا تُخْسِرُوا الْمِيزَانَ
4፥58 *"አላህ አደራዎችን ወደ ባለቤቶቻቸው እንድታደርሱ ያዛችኋል፡፡ በሰዎችም መካከል በፈረዳችሁ ጊዜ በትክክል እንድትፈርዱ ያዛችኋል"*፡፡ አላህ በርሱ የሚገሥጻችሁ ነገር ምን ያምር! አላህ ሰሚ ተመልካች ነው፡፡ إِنَّ اللَّهَ يَأْمُرُكُمْ أَن تُؤَدُّوا الْأَمَانَاتِ إِلَىٰ أَهْلِهَا وَإِذَا حَكَمْتُم بَيْنَ النَّاسِ أَن تَحْكُمُوا بِالْعَدْلِ ۚ إِنَّ اللَّهَ نِعِمَّا يَعِظُكُم بِهِ ۗ إِنَّ اللَّهَ كَانَ سَمِيعًا بَصِيرًا
11፥85 «ሕዝቦቼም ሆይ! *"ስፍርንና ሚዛንን በትክክል ሙሉ፡፡ ሰዎችንም ምንም ነገራቸውን አታጉድሉባቸው፡፡ በምድርም ውስጥ አጥፊዎች ሆናችሁ አታበላሹ"*፡፡ وَيَا قَوْمِ أَوْفُوا الْمِكْيَالَ وَالْمِيزَانَ بِالْقِسْطِ ۖ وَلَا تَبْخَسُوا النَّاسَ أَشْيَاءَهُمْ وَلَا تَعْثَوْا فِي الْأَرْضِ مُفْسِدِين

አላህ ፍትሓዊ ከሚላቸው ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ፊታቸው ይቀየራልን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

6፥79 *«እኔ ለዚያ ሰማያትንና ምድርን ለፈጠረው ቀጥተኛ ስኾን "ፊቴን" አዞርኩ፡፡ እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም»* አለ፡፡ إِنِّي وَجَّهْتُ وَجْهِيَ لِلَّذِي فَطَرَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ حَنِيفًا ۖ وَمَا أَنَا مِنَ الْمُشْرِكِينَ

የኢሥላምን መሠረትና ውቅር፣ ዋልታና ማገር፣ ጥልቀትና ስፋት፣ ድርና ማግ በቅጡ ያልተረዱ ሚሽነሪዎች፦ በሐዲስ ላይ ለሶላት ሶፍን ያልጠበቁትን አላህ ፊታቸውን ይቀይረዋል ይላል፥ ያልጠበቁ ፊታቸው የተቀየሩ አሁን የት አሉ? ብለው ይጠይቃሉ። በኢሥላም ያሉ የመስኩ ሊሒቃን፦ “ውኃን ከጡሩ፥ ነገርን ከሥሩ” ይላሉና እኛም የኢሥላም ዐቃቢያነ-እምነት እንደመሆናችን መጠን ከሥሩ ስለ "ፊት" በትክክለኛ የአስተላለፍና የአስነዛዘር ሙግት መልስ እንሰጣለን።
"ወጀህ" وَجْه ማለት "ፊት" ማለት ሲሆን በተለያየ ትርጉም ሊመጣ ይችላል። ወጀህ "ቀልብ" قَلْب ማለትም "ልብ" በሚል መጥቷል፦
37፥84 *ወደ ጌታው "በቅን ልብ" በመጣ ጊዜ የኾነውን አስታውስ*፡፡፡ إِذْ جَاءَ رَبَّهُ بِقَلْبٍ سَلِيمٍ

እነዚህ አናቅጽ ላይ "ቅን" ለሚለው ቃል የገባው "ሠሊም" سَلِيم ሲሆን ይህም ቃል "አሥለመ" أَسْلَمَ ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ተገዢ" "ታዛዥ" የሚለውንም ያስይዛል። ኢብራሂም ወደ አላህ በሠሊም ልብ የመጣው ልቡን ለአላህ በመስጠት ነው፦
6፥79 *«እኔ ለዚያ ሰማያትንና ምድርን ለፈጠረው ቀጥተኛ ስኾን "ፊቴን" አዞርኩ፡፡ እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም»* አለ፡፡ إِنِّي وَجَّهْتُ وَجْهِيَ لِلَّذِي فَطَرَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ حَنِيفًا ۖ وَمَا أَنَا مِنَ الْمُشْرِكِينَ

ኢብራሂም "ፊቴን" አዞርኩኝ ሲል ከአንገት በላይ ያለውን ቅል ማለት ሳይሆን ልቤን ማለቱ ነው፦
26፥89 *ወደ አላህ "በንጹህ ልብ" የመጣ ሰው ቢኾን እንጅ*፡፡» إِلَّا مَنْ أَتَى اللَّهَ بِقَلْبٍ سَلِيم
31፥22 እርሱ መልካም ሠሪ ሆኖ *ፊቱን ወደ አላህ የሚሰጥም* ሰው ጠንካራን ገመድ በእርግጥ ጨበጠ፡፡ የነገሩም ሁሉ ፍጻሜ ወደ አላህ ነው፡፡ وَمَن يُسْلِمْ وَجْهَهُ إِلَى اللَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَىٰ ۗ وَإِلَى اللَّهِ عَاقِبَةُ الْأُمُورِ

"ወደ አላህ በንጹህ ልብ የመጣ ሰው" ማለት እና "ፊቱን ወደ አላህ የሚሰጥም ሰው" የሚለው ቃል ተለዋዋጭ ቃል ሆኖ መጥቷል። "የሰጠ" ለሚለው ቃል "ዩሥሊም" يُسْلِمْ መሆኑ በራሱ "ሠሊም" سَلِيم ከሚለው ጋር ምን ያህል ዝምድና እንዳለው አንባቢ ያጤነዋልም። እዚህ ድረስ ከተግባባን ሐዲሱ ላይ ያለው ጥያቄ ኢንሻአላህ ይመለሳል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 10, ሐዲስ 112
አን'ኑዕማን ኢብኑ በሺር እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ረድፎቻችሁን ቀጥ ታደርጋላችሁ ወይም አላህ በፊቶቻችሁ መሃል ይቀይራል"*። قَالَ سَمِعْتُ النُّعْمَانَ بْنَ بَشِيرٍ، يَقُولُ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ لَتُسَوُّنَّ صُفُوفَكُمْ أَوْ لَيُخَالِفَنَّ اللَّهُ بَيْنَ وُجُوهِكُمْ ‏ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 272
አን'ኑዕማን ኢብኑ በሺር እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ከሰዎች በላይ በፊታቸው እንዲህ ሦስት ጊዜ፦ *"ረድፎቻችሁን ቀጥ አድርጉ! አሉ። "ወላሂ ረድፎቻችሁን ቀጥ ታደርጋላችሁ ወይም አላህ በልቦቻችሁ መሃል ይቀይራል" አሉ*። قَالَ سَمِعْتُ النُّعْمَانَ بْنَ بَشِيرٍ، يَقُولُ أَقْبَلَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم عَلَى النَّاسِ بِوَجْهِهِ فَقَالَ ‏"‏ أَقِيمُوا صُفُوفَكُمْ ‏"‏ ‏.‏ ثَلاَثًا ‏"‏ وَاللَّهِ لَتُقِيمُنَّ صُفُوفَكُمْ أَوْ لَيُخَالِفَنَّ اللَّهُ بَيْنَ قُلُوبِكُمْ ‏ ‏

"ሶፍ" صَفّ የሚለው ቃል "ሶፈ" صَفَّ ማለትም "ተሰለፈ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ሰልፍ" ወይም "ረድፍ" ማለት ነው፥ የሶፍ ብዙ ቁጥር እነዚህ ሐዲሳት ላይ የተቀመጠው "ሱፉፍ" صُفُوف‎ ነው። እዚህ ላይ ዋናው ነጥቡ የሚያሳየው ሶፍን እኩል አድርጎ ሶላት ዉስጥ መቆም ግዴታ መሆኑን ነው። ያለው ምርጫ ሁለት ነው፥ አንዱ ረድፎቻችሁን ቀጥ ታደርጋላችሁ ወይም ሌላው አላህ በልቦቻችሁ መሃል ይቀይራል። እንግዲህ ፊት የሚለው ልብ በሚለው እንደተፈሠረ ከላይ ዘንዳ ለሶላት ሶፍን ያልጠበቀውን ልቡን ይቀይረዋል ማለት እንጂ ከአንገት በላይ ያለው ቅል ይቀይረዋል ማለት አይደለም።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የይኹን ቃላት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

16፥40 *ለማንኛውም ነገር መኾኑን በሻነው ጊዜ ቃላችን ለእርሱ “ኹን” ማለት ብቻ ነው፥ ወዲውም ይኾናል*፡፡ إِنَّمَا قَوْلُنَا لِشَيْءٍ إِذَا أَرَدْنَاهُ

“ከላም” كَلَٰم የሚለው ተባታይ ቃል “ከለመ” كَلَّمَ ማለትም “ተናገረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ንግግር” ማለት ነው። “ከሊማህ” كَلِمَة ደግሞ የከላም አንስታይ ነው፥ የከሊማህ ብዙ ቁጥር "ከሊመት" كَلِمَت ነው። አላህ “ሲፋቱል ከላም” صفات الكلام ማለትም “የመናገር ባሕርይ” አለው። አምላካችን አላህ “ሙተከለም” مُتَكَلِّم ማለትም “ተናጋሪ”speaker” ነው፤ የራሱ “ከላም” كَلَٰم ማለትም “ንግግር”speech” የራሱ ባሕርይ ነው፤ “ከላም” እራሱ “ሐርፍ” حَرْف ማለትም “ሆሄ” ነው። አላህ “አል-ኻሊቅ” الخَٰلِق ማለትም “ፈጣሪ” ሲሆን ነገር ሁሉ “መኽሉቅ” مَخْلُق ነው፤ አላህ ነገርን የሚፈጥርበት ንግግሩ ደግሞ ፈጣሪም ፍጡርም ሳይሆን የራሱ ባሕርይ ነው፤ አምላካችን አላህ ደግሞ የሁሉ ነገር ፈጣሪ ነው። ነገር ማስገኘት በሻ ጊዜ “ኹን” ይለዋል፥ ወዲያው ይኾናልም፦
39፥62 *አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው*፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው፡፡ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ
36፥82 *ነገሩም አንዳችን በሻ ጊዜ “ኹን” ማለት ነው፡፡ ወዲያው ይኾናልም*፡፡ إِنَّمَا أَمْرُهُ إِذَا أَرَادَ شَيْئًا أَن يَقُولَ لَهُ كُن فَيَكُونُ
16፥40 *ለማንኛውም ነገር መኾኑን በሻነው ጊዜ ቃላችን ለእርሱ “ኹን” ማለት ብቻ ነው፤ ወዲውም ይኾናል*፡፡ إِنَّمَا قَوْلُنَا لِشَيْءٍ إِذَا أَرَدْنَاهُ أَن نَّقُولَ لَهُ كُن فَيَكُونُ

“ቃላችን” የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ “ሸይእ” شَىْء ማለት “ነገር’thing” ማለት ሲሆን “ነገር” በሚለው ቃል ውስጥ ፍጥረት ይካተታል። የሚፈጥበት የይኹን ቃል ግን ከነገር ውጪ የፈጣሪ ባሕርይ ነው። ክርስቲያኖች፦ "ፈጣሪ ልጅ አለው" ሲሉ አምላካችን አላህ፦ “ነገርንም ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው “ኹን” ነው፥ ወዲያውም ይኾናል” የሚል ምላሽ ሰጠ፦
19፥35 *ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል*፡፡ مَا كَانَ لِلَّهِ أَن يَتَّخِذَ مِن وَلَدٍ ۖ سُبْحَانَهُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

ለአላህ ልጅ መውለድ አያስፈልገው፤ ነገርን ማስገኘት ሲፈልግ በንግግሩ “ኹን” ይላል ይሆናል። መርየምም”፦ “ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል?” ስትል፥ መለኮታዊ ምላሽ፦ “አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፤ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል” የሚል ምላሽ ነው፦
3፥47 *፡-ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለች፡፡ ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፤ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል አላት*፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

ወደ መርየም የጣላት ቃላት፦ "ኩን" كُن የሚል ነው። አንድ ጊዜ ነጅራኖች ማለትም የየመን ክርስቲያኖች፦ “ዒሣ የአላህ ልጅ ካልሆነ እንግዲያውስ አባቱ ማን ነው? ብለው ጠየቁ፥ አምላካችን አላህም ይህንን አንቀጽ አወረደ፦
3፥59 አላህ ዘንድ *የዒሳ ምሳሌ እንደ አዳም ብጤ ነው፡፡ ከዐፈር ፈጠረው፡፡ ከዚያም ለእርሱ «ኹን» አለው፤ ኾነም*፡፡ إِنَّ مَثَلَ عِيسَىٰ عِندَ اللَّهِ كَمَثَلِ آدَمَ ۖ خَلَقَهُ مِن تُرَابٍ ثُمَّ قَالَ لَهُ كُن فَيَكُونُ

አላህ አደምን ከዐፈር ቅርጹን ካበጀ በኃላ በቃሉ “ኹን” አለው ሰው ሆነ፤ በተመሳሳይም ዒሣን ከመርየም “ኹን” አለው ሰው ሆነ፤ “ወከሊመቱሁ አልቃሃ ኢላ መርየም" وَكَلِمَتُهُ أَلْقَاهَا إِلَىٰ مَرْيَمَ ማለትም “ወደ መርየም የጣላት የይኹን ቃል ነው” የሚለው ለዛ ነው፦
4:171 እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፤ በአላህም ላይ እውነትን እንጂ አትናገሩ፤ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ዒሳ፣ የአላህ መልክተኛ፣ *ወደ መርየም የጣላት የሁን ቃሉም ነው*፤ ከእርሱ የሆነ መንፈስም ብቻ ነው። يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا تَغْلُوا۟ فِى دِينِكُمْ وَلَا تَقُولُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ إِلَّا ٱلْحَقَّ ۚ إِنَّمَا ٱلْمَسِيحُ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ ٱللَّهِ وَكَلِمَتُهُۥٓ أَلْقَىٰهَآ إِلَىٰ مَرْيَمَ وَرُوحٌۭ مِّنْهُ

“ወ-ከሊመቱ አልቃሃ ኢላ መርየም* وَكَلِمَتُهُ أَلْقَاهَا إِلَىٰ مَرْيَم ማለትም “ወደ መርየም የጣላት የይኹን ቃሊት ናት” ማለት ነው፥ “ከሊማህ” كَلِمَة አንስታይ መደብ ናት። ይቺ ቃሊት አንስታይ መደብ ስለሆነች “አልቃሃ” أَلْقَاهَا ማለት “የጣላት” ተብላለች፥ ዒሣ ቃል ቢሆን ኖሮ በተባታይ መደብ “አልቃሁ” أَلْقَاهُ ማለትም “የጣለው” ይባል ነበር። ቅሉ ግን ይህቺ የይኹን ቃላት መንስኤ ስትሆን ዒሣ ደግሞ ውጤት ነው። ቀደምት ሠለፎች የተረዱት በዚህ መልክ እና ልክ ነው፦
ተፍሢፉል ኢብኑ ከሲር 4፥171
ኢብኑ አቢ ሐቲም እንደዘገበው፦ *“አሕመድ ኢብኑ ሢናነል ዋሢጢይ እንደተናገረው፦ “ሻዝ ኢብኑ የሕያ”ረ.ዐ.” እንዲህ አለ፦ ”ወደ መርየም የጣላት የሁን ቃሉም ነው” የሚለው “ቃሊቷ እራሷ ዒሣ አልሆነችም፥ ነገር ግን በቃሊቱ ዒሣ ተገኘ እንጂ”*። وقال ابن أبي حاتم : حدثنا أحمد بن سنان الواسطي قال : سمعت شاذ بن يحيى يقول : في قول الله : ( وكلمته ألقاها إلى مريم وروح منه ) قال : ليس الكلمة صارت عيسى ، ولكن بالكلمة صار عيسى

አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የአላህ ንግግር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

9፥6 *"ከሙሽሪኮችም አንዱ ጥገኝነትን ቢጠይቅህ የአላህን ንግግር እስኪሰማ ድረስ አስጠጋው"*፡፡ ከዚያም ወደ መጠበቂያው ስፍራ አድርሰው፡፡ ይህ እነርሱ የማያውቁ ሕዝቦች በመኾናቸው ነው፡፡ وَإِنْ أَحَدٌ مِّنَ الْمُشْرِكِينَ اسْتَجَارَكَ فَأَجِرْهُ حَتَّىٰ يَسْمَعَ كَلَامَ اللَّهِ ثُمَّ أَبْلِغْهُ مَأْمَنَهُ ۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ قَوْمٌ لَّا يَعْلَمُونَ

“ከላም” كَلَٰم የሚለው ተባታይ መደብ “ከለመ” كَلَّمَ ማለትም “ተናገረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ንግግር” ማለት ነው። “ከሊማህ” كَلِمَة ደግሞ የከላም አንስታይ መደብ ነው፥ የከሊማህ ብዙ ቁጥር "ከሊማት" كَلِمَت ነው። አምላካችን አላህ “ሲፈቱል ከላም” صِفَة الكَلَٰم ማለትም “የመናገር ባሕርይ” አለው። እርሱ “ሙተከለም” مُتَكَلِّم ማለትም “ተናጋሪ”speaker” ሲሆን፥ የራሱ “ከላም” كَلَٰم ማለትም “ንግግር”speech” ደግሞ የራሱ ባሕርይ ነው። ይህ የአላህ ንግግር በሁለት ይከፈላል፥ እርሱም፦ አንዱ “ከላሙ አት-ተክውኒይ” كَلَٰم التَكْو۟نِي ሲባል፥ ሁለተኛው ደግሞ "ከላሙ አት-ተሽሪዒይ” كَلَٰم التَشْرِعِي ይባላል። ይህንን ነጥብ በነጥብ ማየት ይቻላል፦

ነጥብ አንድ
“ከላሙ አት-ተክውኒይ”
“ተክውኒይ” تَكْو۟نِي የሚለው ቃል "ከወነ" كَوَّنَ‎ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ኹነት” ማለት ነው። አላህ “አል-ኻሊቅ” الخَٰلِق ማለትም “ፈጣሪ” ሲሆን፥ ነገር ሁሉ ደግሞ “መኽሉቅ” مَخْلُق ማለትም "ፍጡር" ነው፥ አላህ ነገርን መፍጠር ሲፈልግ በቃሉ "ኩን" كُن ማለትም "ኹን" ይለዋል፥ ይኾናል፦
39፥62 *አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው*፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው፡፡ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ
16፥40 *ለማንኛውም ነገር መኾኑን በሻነው ጊዜ ቃላችን ለእርሱ “ኹን” ማለት ብቻ ነው፥ ወዲውም ይኾናል*፡፡ إِنَّمَا قَوْلُنَا لِشَيْءٍ إِذَا أَرَدْنَاهُ أَن نَّقُولَ لَهُ كُن فَيَكُونُ

“ቃላችን” የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። “ሸይእ” شَىْء ማለት “ነገር’thing” ማለት ሲሆን “ነገር” በሚለው ቃል ውስጥ ፍጥረት ይካተታል። የሚፈጥበት የይኹን ቃል ግን ከነገር ውጪ የፈጣሪ ባሕርይ ነው። ክርስቲያኖች፦ "ፈጣሪ ልጅ አለው" ሲሉ አምላካችን አላህ፦ “ነገርንም ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው “ኹን” ነው፥ ወዲያውም ይኾናል” የሚል ምላሽ ሰጠ፦
19፥35 *ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል*፡፡ مَا كَانَ لِلَّهِ أَن يَتَّخِذَ مِن وَلَدٍ ۖ سُبْحَانَهُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

ለአላህ ልጅ መውለድ አያስፈልገው። ነገርን ማስገኘት ሲፈልግ በንግግሩ “ኹን” ይላል ይሆናል። መርየምም”፦ “ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል?” ስትል፥ መለኮታዊ ምላሽ፦ “አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፥ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል” የሚል ምላሽ ነው፦
3፥47 *፡-ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለች፡፡ ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፥ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል አላት*፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

ወደ መርየም የጣላት ቃላት፦ "ኩን" كُن የሚል ነው። አንድ ጊዜ ነጅራኖች ማለትም የየመን ክርስቲያኖች፦ “ዒሣ የአላህ ልጅ ካልሆነ እንግዲያውስ አባቱ ማን ነው? ብለው ጠየቁ፥ አምላካችን አላህም ይህንን አንቀጽ አወረደ፦
3፥59 አላህ ዘንድ *የዒሳ ምሳሌ እንደ አዳም ብጤ ነው፡፡ ከአፈር ፈጠረው፡፡ ከዚያም ለእርሱ «ኹን» አለው፤ ኾነም*፡፡ إِنَّ مَثَلَ عِيسَىٰ عِندَ اللَّهِ كَمَثَلِ آدَمَ ۖ خَلَقَهُ مِن تُرَابٍ ثُمَّ قَالَ لَهُ كُن فَيَكُونُ

አላህ አደምን ከአፈር ቅርጹን ካበጀ በኃላ በቃሉ “ኹን” አለው ሰው ሆነ፥ በተመሳሳይም ዒሣን ከመርየም “ኹን” አለው ሰው ሆነ። “ወከሊመቱል ቃሃ ኢላ መርየም* وَكَلِمَتُهُ أَلْقَاهَا إِلَىٰ مَرْيَمَ ማለትም “ወደ መርየም የጣላት የይኹን ቃላት" ነው፦
4:171 እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፤ በአላህም ላይ እውነትን እንጂ አትናገሩ፤ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ዒሳ፣ የአላህ መልክተኛ፣ *ወደ መርየም የጣላት የሁን ቃሉም ነው*፤ ከእርሱ የሆነ መንፈስም ብቻ ነው። يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا تَغْلُوا۟ فِى دِينِكُمْ وَلَا تَقُولُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ إِلَّا ٱلْحَقَّ ۚ إِنَّمَا ٱلْمَسِيحُ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ ٱللَّهِ وَكَلِمَتُهُۥٓ أَلْقَىٰهَآ إِلَىٰ مَرْيَمَ وَرُوحٌۭ مِّنْهُ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ከሊማት" كَلِمَت የከሊማህ ብዜት ሲሆን "ቃላት" ማለት ነው። ይቺ ቃላት ተባዕታይ መደብ ስለሆነች "አልቃሃ" أَلْقَاهَا ማለት "የጣላት" ተብላለች። ዒሣ ቃል ቢሆን ኖሮ በተባታይ መደብ "አልቃሁ" أَلْقَاهُ ማለትም "የጣለው" ይባል ነበር። ቅሉ ግን ይህቺ የይኹን ቃላት መንስኤ ስትሆን ዒሣ ደግሞ ውጤት ነው።
ነጥብ ሁለት
"ከላሙ አት-ተሽሪዒይ"
“ተሽሪዒይ” تَشْرِعِي የሚለው ቃል "ሸረዐ" شَرَّعَ‎ ማለትም "ደነገገ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ድንጋጌ" ወይም "ሕግጋት" ማለት ነው። ይህ ሸሪዓህ ከአላህ ወደ ነቢያቱ የሚወርድ መመሪያ፣ መርሕ፣ ሥርዓት ነው። “ሸሪዓህ” شَرِيعَة ማለት “ትክክለኛ ሕግ” ማለት ነው፦
45፥18 ከዚያም ከትእዛዝ *በትክክለኛይቱ ሕግ* ላይ አደረግንህ፡፡ ስለዚህ ተከተላት፡፡ የእነዚያንም የማያውቁትን ሕዝቦች ዝንባሌዎች አትከተል፡፡ ثُمَّ جَعَلْنَاكَ عَلَىٰ شَرِيعَةٍ مِّنَ الْأَمْرِ فَاتَّبِعْهَا وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَاءَ الَّذِينَ لَا يَعْلَمُون

“ትክክለኛይቱ ሕግ” ለሚለው ቃል የገባው “ሸሪዓህ” شَرِيعَة የሚል ነው፥ ይህም ቃል “ሺርዓህ” شِرْعَة ማለትም “ሕግ” ከሚል ቃል የመጣ ነው፦
5፥48 ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭ እና በእርሱ ላይ ተጠባባቂ ሲኾን በእውነት አወረድን፡፡ በመካከላቸውም *”አላህ ባወረደው ሕግ ፍረድ”*፡፡ እውነቱም ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌዎቻቸውን አትከተል፡፡ *”ከእናንተ ለሁሉም ሕግን እና መንገድን አደረግን”*፡፡ وَأَنزَلْنَآ إِلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ مُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَمُهَيْمِنًا عَلَيْهِ ۖ فَٱحْكُم بَيْنَهُم بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَآءَهُمْ عَمَّا جَآءَكَ مِنَ ٱلْحَقِّ ۚ لِكُلٍّۢ جَعَلْنَا مِنكُمْ شِرْعَةًۭ وَمِنْهَاجًۭا

እዚህ አንቀጽ ላይ “ሕግ” ለሚለው ቃል የገባው “ሺርዓህ” شِرْعَة መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። "እናንተም" የሚለው ነቢያትን ነው፥ ከነቢያት ለሁሉም መልእክተኞች "ሕግ" እና "መንገድ" አድርጓል፥ “መንገድ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሚንሃጅ” مِنْهَاج ሲሆን “መንሃጅ” مَنْهَج ማለት ነው። ይህ ሕግ እና መንገድ ወሕይ ሆኖ ወደ መልእክተኞቹ ይወርዳል፦
57፥25 *"መልክተኞቻችንን በግልጽ ማስረጃዎች በእርግጥ ላክን፡፡ ሰዎችም በትክክል ቀጥ እንዲሉ መጽሐፎችን እና ሚዛንን ወደ እነርሱ አወረድን"*። ብረትንም በውስጡ ብርቱ ኀይልና ለሰዎችም መጠቃቀሚያዎች ያሉበት ሲኾን አወረድን፡፡لَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلَنَا بِالْبَيِّنَاتِ وَأَنزَلْنَا مَعَهُمُ الْكِتَابَ وَالْمِيزَانَ لِيَقُومَ النَّاسُ بِالْقِسْطِ ۖ وَأَنزَلْنَا الْحَدِيدَ فِيهِ بَأْسٌ شَدِيدٌ وَمَنَافِعُ لِلنَّاسِ

“አወረድን” ለሚለው ቃል የገባው “አውሐይና” أَوْحَيْنَا ሲሆን “አውሓ” أَوْحَىٰٓ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ገለጥን” ማለት ነው። “ወሕይ” وَحْي የሚለው ቃል “አውሓ” أَوْحَىٰٓ ማለትም “ገለጠ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ግልጠተ-መለኮት” ወይም “ግህደተ-መለኮት” አሊያም “መለኮታዊ ራእይ”Revelation” ማለት ነው። ወሕይ ከላሙ አት-ተሽሪዒይ ነው። የመጽሐፉ ሰዎች አይሁዳውያን እና ክርስቲያኖች ከነቢያችን"ﷺ" በፊት የነበሩት የአላህ ንግግር በሰው ንግግር በመቀላቀል እና የአላህን ንግግር በመቀነስ በርዘዋል፦
3፥71 *የመጸሐፉ ሰዎች ሆይ! “እዉነቱን በዉሸት” ለምን *ትቀላቅላላችሁ*? “እዉነቱንም” እናንተ የምታወቁ ስትሆኑ ለምን *ትደብቃላችሁ?* يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لِمَ تَلْبِسُونَ ٱلْحَقَّ بِٱلْبَٰطِلِ وَتَكْتُمُونَ ٱلْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ
2፥79 *ለነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያም በርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው*፡፡ ለነርሱም ከዚያ እጆቻቸው ከጻፉት ወዮላቸው፡፡ ለነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት ኃጢኣት ወዮላቸው፡፡ فَوَيْلٌۭ لِّلَّذِينَ يَكْتُبُونَ ٱلْكِتَٰبَ بِأَيْدِيهِمْ ثُمَّ يَقُولُونَ هَٰذَا مِنْ عِندِ ٱللَّهِ لِيَشْتَرُوا۟ بِهِۦ ثَمَنًۭا قَلِيلًۭا ۖ فَوَيْلٌۭ لَّهُم مِّمَّا كَتَبَتْ أَيْدِيهِمْ وَوَيْلٌۭ لَّهُم مِّمَّا يَكْسِبُونَ

እዚው ዐውድ ላይ ስንመለከት ከመጽሐፉ ሰዎች የአላህን ንግግር የሚሰሙ እና ከዚያም ከተረዱት በኋላ እነርሱ እያወቁ የሰው ንግግር በእጆቻቸው ፅፈው «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ብለው በርዘውታል፦
2፥75 *ከእነርሱ የኾኑ ጭፍሮች የአላህን ንግግር የሚሰሙ እና ከዚያም ከተረዱት በኋላ እነርሱ እያወቁ “የሚለውጡት” ሲኾኑ ለእናንተ ማመናቸውን ትከጅላላችሁን?”* أَفَتَطْمَعُونَ أَن يُؤْمِنُوا لَكُمْ وَقَدْ كَانَ فَرِيقٌ مِّنْهُمْ يَسْمَعُونَ كَلَامَ اللَّهِ ثُمَّ يُحَرِّفُونَهُ مِن بَعْدِ مَا عَقَلُوهُ وَهُمْ يَعْلَمُون
“የሚለውጡት” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ዩሐረፉነሁ” يُحَرِّفُونَهُ ሲሆን “የሚበርዙት” ማለት ነው፥ “ዩሐረፉ” يُحَرِّفُ የሚለው አላፊ ግስ “ሐረፈ” حَرَّفَ ማለትም “በረዘ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል። የሚበርዙት ፊደል እና ንግግር “ሐርፍ” حَرْف ሲባል፥ የመበረዙ ድርጊቱ ደግሞ “ተሕሪፍ” تَحْرِيف ይባላል። አላህ ከቁርኣን በፊት የነበሩትን መጽሐፍት እንዲጠብቁ አላፍትና የሰጠው ለሰዎች ነበር፦
5፥44 እኛ ተውራትን በውስጥዋ መምሪያና ብርሃን ያለባት ስትኾን አወረድን፡፡ እነዚያ ትዕዛዝን የተቀበሉት ነቢያት በእነዚያ አይሁዳውያን በኾኑት ላይ በርሷ ይፈርዳሉ፡፡ ሊቃውንቱና ዐዋቂዎቹም *ከአላህ መጽሐፍ እንዲጠብቁ በተደረጉት* እና በእርሱም ላይ መስካሪዎች በኾኑት ይፈርዳሉ፡፡ إِنَّا أَنزَلْنَا التَّوْرَاةَ فِيهَا هُدًى وَنُورٌ ۚ يَحْكُمُ بِهَا النَّبِيُّونَ الَّذِينَ أَسْلَمُوا لِلَّذِينَ هَادُوا وَالرَّبَّانِيُّونَ وَالْأَحْبَارُ بِمَا اسْتُحْفِظُوا مِن كِتَابِ اللَّهِ وَكَانُوا عَلَيْهِ شُهَدَاءَ ۚ

"እንዲጠብቁ" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። አንድ መጽሐፍ ወርዶ ቢበረዝ ሌላ ነቢይ ስለሚመጣ እና በሌላ መጽሐፍ ስለሚተካ እውነትን በውሸት ቀላቅለው ለመበረዝ ችለዋል። ነገር ግን ከነቢያችም”ﷺ” በኃላ የሚመጣ ነብይ፣ የሚላክ መልእክተኛ እና የሚወርድ ተንዚል ስለሌለ አላህ ቁርኣን እራሱ አውርዶ ከኋላውም ከፊቱም ውሸት እንዳይመጣበት እራሱ ይጠብቀዋል፦
33፥40 ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንድም ሰው አባት አይደለም፡፡ ግን *የአላህ መልክተኛ እና የነቢያት መደምደሚያ ነው*፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ مَّا كَانَ مُحَمَّدٌ أَبَا أَحَدٍ مِّن رِّجَالِكُمْ وَلَـٰكِن رَّسُولَ اللَّهِ وَخَاتَمَ النَّبِيِّينَ ۗ وَكَانَ اللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمًا
15፥9 *እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን*፡፡ إِنَّا نَحْنُ نَزَّلْنَا ٱلذِّكْرَ وَإِنَّا لَهُۥ لَحَٰفِظُونَ
41፥42 *ከኋላውም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም*፡፡ ጥበበኛ ምስጉን ከኾነው ጌታ የተወረደ ነው፡፡ لَّا يَأْتِيهِ ٱلْبَٰطِلُ مِنۢ بَيْنِ يَدَيْهِ وَلَا مِنْ خَلْفِهِۦ ۖ تَنزِيلٌۭ مِّنْ حَكِيمٍ حَمِيدٍۢ

ስለዚህ ቁርኣን የመጨረሻው ከላሙ አት-ተሽሪዒይ ነው፦
9፥6 *"ከሙሽሪኮችም አንዱ ጥገኝነትን ቢጠይቅህ የአላህን ንግግር እስኪሰማ ድረስ አስጠጋው"*፡፡ ከዚያም ወደ መጠበቂያው ስፍራ አድርሰው፡፡ ይህ እነርሱ የማያውቁ ሕዝቦች በመኾናቸው ነው፡፡ وَإِنْ أَحَدٌ مِّنَ الْمُشْرِكِينَ اسْتَجَارَكَ فَأَجِرْهُ حَتَّىٰ يَسْمَعَ كَلَامَ اللَّهِ ثُمَّ أَبْلِغْهُ مَأْمَنَهُ ۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ قَوْمٌ لَّا يَعْلَمُونَ

ይህንን የመጨረሻው ከላሙ አት-ተሽሪዒይ ሰምተው፣ ቀርተው፣ ተምረው፣ ተረድተው ከሚተገብሩት ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አውሬው 666

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

3፥78 *ከእነርሱም እርሱ ከመጽሐፉ ያይደለ ሲኾን ከመጽሐፉ መኾኑን እንድታስቡ በመጽሐፉ ምላሶቻቸውን የሚያጣምሙ ክፍሎች አሉ፡፡ እርሱ ከአላህ ዘንድ ያልኾነ ሲኾን «እርሱ ከአላህ ዘንድ ነውም» ይላሉ፡፡ እነርሱ የሚያውቁ ሲኾኑም በአላህ ላይ ውሸትን ይናገራሉ*፡፡ وَإِنَّ مِنْهُمْ لَفَرِيقًا يَلْوُونَ أَلْسِنَتَهُم بِالْكِتَابِ لِتَحْسَبُوهُ مِنَ الْكِتَابِ وَمَا هُوَ مِنَ الْكِتَابِ وَيَقُولُونَ هُوَ مِنْ عِندِ اللَّهِ وَمَا هُوَ مِنْ عِندِ اللَّهِ وَيَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ الْكَذِبَ وَهُمْ يَعْلَمُونَ

ጽዮናዊነትን የሚያራምደው ወሊድ ሹዒባት፦ "ራእይ ላይ ከባሕር የሚወጣው አውሬ መህዲ ሲሆን ከምድር የሚወጣው አውሬ ደግሞ ዒሣ ነው" የሚል የራሱን ዝንባሌ በመከተል የሚተረጉምበት አተረጓጎም አለው። ይህ ትርጓሜ ለቤተክርስቲያንም ሆነ ለታሪክ እንግዳ ትርጓሜ ነው። የክርስትና ዐቃቢያነ-እምነት ሳም ሻሙስ እና ጀምስ ኃይት ይህንን አተረጓጎ ክፉኛ የተሳሳተ እንደሆነ ይሞግታሉ። ራእይ ላይ ስለ አውሬው የሚናገረው ነገር ትንቢት ነው፥ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም፦
2 ጴጥሮስ 1፥20 ይህን በመጀመሪያ እወቁ፤ *"በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም"*።

ይህንን ከተረዳን በጥንቃቄ ስለ አውሬው ለማየት እንሞክር። "አውሬ" ማለት "ጨካኝ" "ተናካሽ" "አረመኔ" "ስግብግብ" ማለት ነው። ባይብል ክፉዎችን የምድር መንግሥታትን "አውሬ" ይላቸዋል። ዳንኤል አንበሳ፣ ድብ፣ ነብር እና የምታስፈራ አራት ታላላቅ አራዊት ከባሕር ሲወጡ አይቷል፥ እነዚህ አራዊት በምድር ላይ ኃያላን መንግሥታት የነበሩ ባቢሎን፣ ፋርስ፣ ግሪክ እና ሮም ናቸው፦
ዳንኤል 7፥3 *"አራትም ታላላቅ አራዊት ከባሕር ወጡ፥ እያንዳንዲቱም ልዩ ልዩ ነበረች"*።
ዳንኤል 7፥17 *"እነዚህ አራቱ ታላላቅ አራዊት ከምድር የሚነሡ አራት ነገሥታት ናቸው"*።

ይህ ስለ አውሬ እሳቤው እንዲኖራችሁ ማሟሻ ነው። ይህንን እሳቤ ይዘን ራእይ ላይ ያሉትን አራዊት መረዳት እንችላለን፦
ራእይ 13፥1 *"አንድም አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ አሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፥ በቀንዶቹም ላይ አሥር ዘውዶች በራሶቹም ላይ የስድብ ስም ነበረ"*።

ይህ አውሬ በኦርቶዶክስ የትርጓሜ መጽሐፍ ላይ ሐሳዌ መሢሕ ነው፦
ራእይ 13፥1 አንድምታ፦ *"አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ" አለ። ሐሳዌ መሢሕ ነው፥ መንግሥቱም ገና አልተደላደለችምና "እም ባሕር" አለ። ታሪክ የሐሳዌ መሢሕን ትውልድ ከዚህ ይናገሩለታል፦ እናቱ ከዳን ነገድ፥ አባቱ ከኤሳው ነገድ ናቸው"*።
*"አሐቲ ዐይኑ ዘፍስሐት" ይላል፤ -አንድ ዐይኑ የሞተች ናት፥ "ወአሐዱ ዐይኑ ዘስሩር በደም" ይላል። አንድ ዐይኑ ደም የሰረበው ፈጣጣ ነው"*።

አንድ ሰው ኦርቶዶስ ሆኖ "ይህ አውሬ መህዲ ነው" ማለት የጤና ነውን? መህዲ ከነቢያችን"ﷺ" ሥርወ-ግንድ ከዐሊይ እና ከፋጢማ የሚመጣ እንጂ ከአይሁድ ሥርወ-ግንድ የሚመጣ በፍጹም አይደለም። ይህ አንድ ዐይኑ የሞተች ባለ አንድ ዐይን ሐሳዌ መሢሕ ስም አለው፥ ስሙ ቁጥር አለው፦
ራእይ 13፥17-18 *"የአውሬውም ስም ወይም የስሙ ቍጥር ያለው ምልክት የሌለበት ማንም ሊገዛ ወይም ሊሸጥ እንዳይችል ያደርጋል"*። ጥበብ በዚህ አለ። አእምሮ ያለው የአውሬውን ቍጥር ይቍጠረው፤ ቍጥሩ የሰው ቍጥር ነውና፥ *"ቍጥሩም ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ነው"*።
ራእይ 15፥2 *"በአውሬው እና በምስሉም በስሙም ቍጥር"* ላይ ድል ነሥተው የነበሩት የእግዚአብሔርን በገና ይዘው በብርጭቆ ባሕር ላይ ሲቆሙ አየሁ።

ስሙ መርምያዋዖስ ሲሆን የስሙ ቁጥር 666 ነው፦
ራእይ 13፥17-18 አንድምታ፦ "ስሙም በዕብራይስጥ "መርምያዋዖስ" በግዕዝ ደግሞ "ፀራዊ" ማለትም "ተቃዋሚ" ወይም "ሐሳዊ" ማለትም "ሐሰተኛ" የሚል ነው። "መርምያዋዖስ" የሚለው ቁጥሩ፦
1. ሜም 40
2. ሬስ 200
3. ሜም 40
4. ዮድ 10
5. ዋው 6
6. ዔ 70
7. ሳን 300
ድምር 666 ይሆናል።

ማሳሰቢያ፦ በፓፒረስ 115 እና ኮዴክድ ኤፍሬማይ 616 ἑξακόσιοι δέκα ἕξ እንጂ 666 ἑξακόσιοι ἑξήκοντα ἕξ አይልም። ኦርጅናሉም 616 ነው የሚል ሙግት አለ፥ ይህ ሌላ ርእስ ነው።

በኦርቶዶክስ ዘንድ አንድም ቀን ይህ አውሬ "በኢሥላም የሚጠበቀው መህዲ ነው" ብሎ ያስተማረ አንድም ሊቅ የለም።
ከባሕር ከወጣው አውሬ ቀጥሎ ደግሞ ከምድር የወጣው ሌላውን አውሬ ሐሰተኛው ነቢይ ይለዋል፦
ራእይ 13፥11 *"ሌላም አውሬ ከምድር ሲወጣ አየሁ፥ የበግ ቀንዶችን የሚመስሉ ሁለት ቀንዶችም ነበሩት እንደ ዘንዶም ይናገር ነበር"*።
ራእይ 13፥14 *"በአውሬውም ፊት ያደርግ ዘንድ ከተሰጡት ምልክቶች የተነሣ በምድር የሚኖሩትን ያስታል"*።
ራእይ 19፥20 አውሬውም ተያዘ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛው ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ"*።

ይህ ሐሰተኛው ነቢይ በኦርቶዶክስ አንድምታ "ኤልያስ ነኝ" ብሎ የሚመጣ "ሐሰተኛው ኤልያስ" ነው። እንደ አንድምታው ከሆነ ኤልያስ እንዴት አርጎ ነው ዒሣ የሚሆነው? በኢሥላም ተስተምህሮት ውስጥ ኤልያስ ይመጣል የሚል ትምህርት የለም። በኦርቶዶክስ ዘንድ አንድም ቀን ይህ ሐሰተኛው ኤልያስ "በኢሥላም የሚጠበቀው ዒሣ ነው" ብሎ ያስተማረ አንድም ሊቅ የለም። ይህ ከላይ ያየነው የኦርቶዶክስ አተረጓጎም ነው።
የፕሮቴስታት ትርጓሜ ደግሞ ላይ አውሬው "አሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት" በሚል ይነሱና ዳንኤል ላይ ያለውን "አራተኛው አውሬ ነው" ይላሉ፦
ዳንኤል 7፥7 *"ታላላቅም የብረት ጥርሶች የነበሩአት አራተኛ አውሬ ነበረች"*፥ ትበላና ታደቅቅ ነበር፥ የቀረውንም በእግርዋ ትረግጥ ነበር፤ ከእርስዋም በፊት ከነበሩት አራዊት ሁሉ የተለየች ነበረች *"አሥር ቀንዶችም ነበሩአት"*።
ዳንኤል 7፥23-24 እንዲህም አለ፦ *"አራተኛይቱ አውሬ በምድር ላይ አራተኛ መንግሥት ትሆናለች"*፥ እርሱም ከመንግሥታት ሁሉ የተለየ ይሆናል፥ ምድሪቱንም ሁሉ ይበላል፥ ይረግጣታል ያደቅቃትማል። *"አሥሩም ቀንዶች ከዚያ መንግሥት የሚነሡ አሥር ነገሥታት ናቸው"*።

አራተኛይቱ መንግሥት ከባቢሎን፣ ከፋርስ፣ ከግሪክ በኃላ የተነሳችው የሮም መንግሥት ናት። የሮም መንግሥት አስቀድሞ ነበረ፥ በራእይ ወደ ፊት ሲመለከት የለም። ከዚያ ከጥልቁ ባሕር ከሕዝብ ተመልሶ ይነሳል፦
ራእይ 17፥8 *ያየኸው አውሬ አስቀድሞ ነበረ፥ አሁንም የለም፥ ከጥልቁም ይወጣ ዘንድ አለው፥ ወደ ጥፋትም ይሄዳል፤ ስሞቻቸውም ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ በሕይወት መጽሐፍ ያልተጻፉ በምድር የሚኖሩ አውሬው አስቀድሞ እንደነበረ አሁንም እንደሌለ፥ ነገር ግን እንዳለ ሲያዩ ያደንቃሉ*"።

ይህ የሮም መንግሥት 666 "ኖሮ ቄሳር" ነው" ተብሎ ይታመናል። "ኔሮውን ቅስር" נרון קסר‎ በዕብራይስ ቁጥር፦
1. ኖን 50
2. ሬስ 200
3. ዋው 6
4. ኖን 50
5. ቆፍ 100
6. ሳምኬት 60
7. ሬስ 200
ድምር 666 ይሆናል።
ይህ አውሬ አሁን የለም። ተመልሶ የኔሮ ቄሳር የሮሙ መንግሥት ሆኖ ከባሕር ማለትም ከሕዝብ ይነሳል። ይህ የፕሮቴስታንት ትርጓሜ ነው። ስመ ጥርና ዝነኛ ከሆኑትን የፕሮቴስታንት ምሁራን አንዳቸውም ይህ አውሬ "በኢሥላም የሚጠበቀው መህዲ ነው" ብለው አላስተማሩም።
ከባሕር ከወጣው አውሬን ቀጥሎ ደግሞ ከምድር የወጣው ሌላውን አውሬ ሐሰተኛው ነቢይን ደግሞ ዳንኤል ላይ ካለው ጋር ያዛምዱታል፦
ዳንኤል 7፥8 *"ቀንዶችንም ተመለከትሁ፤ እነሆም፥ በመካከላቸው ሌላ ትንሽ ቀንድ ወጣ፥ በፊቱም ከቀደሙት ቀንዶች ሦስት ተነቃቀሉ፤ እነሆም፥ በዚያ ቀንድ እንደ ሰው ዓይኖች የነበሩ ዓይኖች በትዕቢትም የሚናገር አፍ ነበሩበት"*።
ዳንኤል 7፥24-25 *"ከእነርሱም በኋላ ሌላ ይነሣል፥ እርሱም ከፊተኞች የተለየ ይሆናል፥ ሦስቱንም ነገሥታት ያዋርዳል። በልዑሉም ላይ ቃልን ይናገራል፥ የልዑልንም ቅዱሳን ይሰባብራል፥ ዘመናትንና ሕግን ይለውጥ ዘንድ ያስባል፤ እስከ ዘመንና እስከ ዘመናት እስከ እኵሌታ ዘመንም በእጁ ይሰጣሉ"*።

ሐሰተኛ ነቢይ ከእውነተኛው ነቢይ ከኢየሱስ በተቃራኒው የሚያሳስት ሐሳዌ መሢሕ ነው ብለው ያብራራሉ። ይህ ሐሳዌ መሢሕ "በኢሥላም የሚጠበቀው ዒሣ ነው" ብለው አላስተማሩም።
እንግዲህ ሁለቱም ማለት የኦርቶዶክስ እና የፕሮቴስታንት አተረጓጎም ቢለያይም፥ ቅሉ ግን ጽዮናዊነትን የሚያራምደው የወሊድ ሹዒባት ቅጥፈት ድባቅ ያስገባዋል። እርሱ ይህንን አተረጓጎም ያመጣው ለኢሥላም ካለው ጥላቻ የመነጨ እንጂ የሥነ-አፈታትን ጥናት ያማከለ አይደለም። መጽሐፉን በምላስ አጣሞ ትርጉሙ ከፈጣሪ ዘንድ ነው ማለት ዋሾዎች ጋር የተለመደ ነው፡፡ እነደነዚህ ያሉ ቀልማዳዎች ዕያወቁ በፈጣሪ ላይ ውሸትን ይናገራሉ፦
3፥78 *ከእነርሱም እርሱ ከመጽሐፉ ያይደለ ሲኾን ከመጽሐፉ መኾኑን እንድታስቡ በመጽሐፉ ምላሶቻቸውን የሚያጣምሙ ክፍሎች አሉ፡፡ እርሱ ከአላህ ዘንድ ያልኾነ ሲኾን «እርሱ ከአላህ ዘንድ ነውም» ይላሉ፡፡ እነርሱ የሚያውቁ ሲኾኑም በአላህ ላይ ውሸትን ይናገራሉ*፡፡ وَإِنَّ مِنْهُمْ لَفَرِيقًا يَلْوُونَ أَلْسِنَتَهُم بِالْكِتَابِ لِتَحْسَبُوهُ مِنَ الْكِتَابِ وَمَا هُوَ مِنَ الْكِتَابِ وَيَقُولُونَ هُوَ مِنْ عِندِ اللَّهِ وَمَا هُوَ مِنْ عِندِ اللَّهِ وَيَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ الْكَذِبَ وَهُمْ يَعْلَمُونَ
በራእይ ላይ የተተነበየው ሐሳዌ መሢሕ በኢሥላም መሢሑ አድ-ደጃል ነው። “አል-መሢሑ አድ-ደጃል” الْمَسِيحَ الدَّجَّال የሁለት ስም ውቅር ነው፥ የመሢሕ እና የደጃል የሚሉ ሁለት ስም ውቅር ነው። “አል-መሢሕ” الْمَسِيح የሚለው የዐረቢኛው ቃል “መሠሐ” مَسَحَ ማለትም “አበሰ” አሸ” “ቀባ” ከሚል ሥርወ-ቃል የተገኘ ሲሆን “የቀባ” አሊያም “የተቀባ” ወይንም “የሚያብስ” አሊያም “የታበሰ” ወይንም “የሚያሽ” አሊያም “የሚታሽ” የሚል ፍቺ አለው። ዒሣ ኢብኑ መርየም በሽተኞችን፣ ህሙማንን እና ሙታንን በማበስ፣ በማሸት እና በመቀባት ከበሽታቸው በአላህ ፈቃድ ያሽራቸው ስለነበረ እና በአላህ የተሾመ(የተቀባ) ነቢይ ስለሆነ “አል-መሢሕ” ተብሏል። አምላካችን አላህ በተከበረው ቃሉ በዘጠኝ አንቀፆች 11 ጊዜ ኢየሱስ መሢሕ መሆኑን ነግሮናል፤ ለናሙና ያክል አንዱን አንቀጽ ብንመለከት በቂ ነው፦
3፥45 መላእክት ያሉትን አስታዉስ፡- መርየም ሆይ አላህ ከእርሱ በሆነዉ ቃል ስሙ *አል-መሢሕ* ዒሣ የመርየም ልጅ፣ በዚህ ዓለምና በመጨረሻዉም ዓለም የተከበረ፣ ከባለማሎችም በሆነ ያበስረሻል። إِذْ قَالَتِ ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ يَٰمَرْيَمُ إِنَّ ٱللَّهَ يُبَشِّرُكِ بِكَلِمَةٍۢ مِّنْهُ ٱسْمُهُ ٱلْمَسِيحُ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ وَجِيهًۭا فِى ٱلدُّنْيَا وَٱلْـَٔاخِرَةِ وَمِنَ ٱلْمُقَرَّبِينَ

መርየም ከአላህ በሆነው ቃል የተበሰረችው ልጇ፦ ስሙ አልመሲሕ ዒሣ መሆኑን፣ የመርየም ልጅ መሆኑን፣ በዚህ ዓለምና በመጨረሻዉም ዓለም የተከበረ መሆኑን እና ከባለማሎችም አንዱ መሆኑን ነው።
ይህንን ካየን ዘንዳ ወደ መሢሑል ደጃል መሄድ እንችላለን፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 54, ሐዲስ 129
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ደጃል ዓይኑ የታበሰ ነው፤ በዓይኖቹ መካከል “ካፊር” የሚል ጽሑፍ አለ፤ ከዚያም “ከፈረ” የሚል አነባነብ ሁሉም ሙሥሊም ያነበዋል”*። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ الدَّجَّالُ مَمْسُوحُ الْعَيْنِ مَكْتُوبٌ بَيْنَ عَيْنَيْهِ كَافِرٌ ‏”‏ ‏.‏ ثُمَّ تَهَجَّاهَا ك ف ر ‏”‏ يَقْرَؤُهُ كُلُّ مُسْلِمٍ ‏”‏

“የታበሰ” ለሚለው ቃል የገባው “መምሡሑ” مَمْسُوحُ ሲሆን ቁርኣን ላይ “ማበስ” ለሚለው የስም መደብ “መሥሕ” مَسْح በሚል መጥቷል፦
38፥33 «በእኔ ላይ መልሷት» አለ አጋዶችዋንና አንገቶችዋንም *ማበስ* ያዘ፡፡ رُدُّوهَا عَلَىَّ ۖ فَطَفِقَ مَسْحًۢا بِٱلسُّوقِ وَٱلْأَعْنَاقِ

በዓይኖቹ መካከል “ካፊር” የሚል ጽሑፍ አለ፤ “ካፊር” كَافِر ማለት “ከሃዲ” ማለት ሲሆን “ከፈረ” የሚል አነባነብ ሁሉም ሙሥሊም ያነበዋል፤ “ከፈረ” كَفَرَ ማለት “ካደ” ማለት ነው፤ “ፋ” ف በሸዳ ተሽዲድ ስናረጋት ደግሞ “ከፍፈረ” كَفَّرَ ሲሆን “ሸፈነ” ማለት ነው፤ “ካፉር” كَافُور ማለት “የተሸፈነ” ማለት ነው፤ ለምሳሌ በጀነት ለበጎ አድራጊዎች መበረዣዋ “ካፉር” ተብላለች፦
76፥5 በጎ አድራጊዎች መበረዣዋ *ካፉር* ከኾነች ጠጅ ይጠጣሉ፡፡ إِنَّ ٱلْأَبْرَارَ يَشْرَبُونَ مِن كَأْسٍۢ كَانَ مِزَاجُهَا كَافُورًا

“አድ-ደጃል” الدَّجَّال የሚለው ቃል “ደጀለ” دَجَلَ ማለትም “አጭበረበረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “አጭበርባሪ” ወይም "ሐሳዌ" ማለት ነው። ዋናው ደጃል “መሢሑ አድ-ደጃል” ማለትም “ሐሳዌ መሢሕ” ሲሆን እርሱ ከመምጣቱ በፊት የሚመጡ ሠላሳ ደጃሎች አሉ።
“ደጃሉን” دَجَّالُونَ የሚለው ቃል “ደጃል” دَجَّال‎ ለሚለው ነጠላ ቃል ብዜት ነው። እነዚህ ወደ ሠላሳ የሚቃረቡ ደጃሎች “እኔ የአላህ መልእክተኛ ነኝ” ወይም “እኔ የአላህ ነብይ ነኝ” ብለው ይነሳሉ፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 54, ሐዲስ 108
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“የመጨረሻይቱ ሰአት አትቆምም ሠላሳ የሚቃረቡ ደጃሎች ቀጣፊዎች ተነስተውስ፦ “እኔ የአላህ መልእክተኛ ነኝ” ብለው ቢናገሩ ቢሆን እንጂ”*። عَنْ أَبِي، هُرَيْرَةَ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ” لاَ تَقُومُ السَّاعَةُ حَتَّى يُبْعَثَ دَجَّالُونَ كَذَّابُونَ قَرِيبٌ مِنْ ثَلاَثِينَ كُلُّهُمْ يَزْعُمُ أَنَّهُ رَسُولُ اللَّهِ
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 13
የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ከእኔ ዑማ ውስጥ ሠላሳ የሚያህሉ ቀጣፊዎች፦ “ነብይ ነኝ” ብለው ይነሳሉ፤ ነገር ግን እኔ የነብያት መደምደሚያ ነኝ፤ ከእኔ በኃላ ነብይ የለም”*። وَحَتَّى تَعْبُدَ قَبَائِلُ مِنْ أُمَّتِي الأَوْثَانَ وَإِنَّهُ سَيَكُونُ فِي أُمَّتِي كَذَّابُونَ ثَلاَثُونَ كُلُّهُمْ يَزْعُمُ أَنَّهُ نَبِيٌّ وَأَنَا خَاتَمُ النَّبِيِّينَ لاَ نَبِيَّ بَعْدِي

ስለዚህ ይህ ሰው መሢሕ ነኝ ብሎ ሲነሳ እውነተኛ መሢሕ ሳይሆን ሐሰተኛ መሢሕ ነው። ስንጠቀልለው “መሢሑ አድ-ደጃል” ማለት “-ዓይኑ የታበሰ” ወይም “ሐሳዌ መሢሕ” ማለት ነው። ነገር ግን ወሊድ ሹዒባት እና ቡችሎቹ የሚያጣምሙት ለኢሥላም ካለው ጥላቻ የመነጨ ነው። አላህ ሂዳያህ ይስጣቸው፥ ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም