ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.2K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዋቄፈና
አንዳንዴ አለመናገር መናገር ቢሆንና፥ ባለመናገር የምናገርውን መናገር ብንችል፥ መናገር ቆሞ አለመናገር መናገርን ባስረዳ ነበር። ሃይማኖትን ለፓለቲካ፣ ለጥቅም እና ለስልጣን ማትረፊያ ንግድ ባናደርግ ጥሩ ነው። ዋቄፈና ባዕድ አምልኮ ነው። ለፓለቲካ ስንል "ባህል ነው" "የተፈጥሮ ሥርዓት ነው" የምንል ሰዎች አላህን እንፍራ። ዱንያህ አጭር ናት፥ ለዱንያህ ብለን አኺራችንን የሚያሳጣ ቃላት አንጠቀም።
በማንበብ እራስዎን እና ማኅበረሰብዎን ከሺርክ፣ ከኩፍር፣ ከቢድዓ እና ከኒፋቅ ይጠብቁ! ዲናችንን ዕንወቅ! የበለጠ የሃይማኖት ንጽጽር ከፈለጉ እንግዲያውስ ጎራ ይበሉ፦
https://tttttt.me/Wahidcom
ዝንባሌ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

25፥43 *ዝንባሌውን አምላኩ አድርጎ የያዘውን ሰው አየህን? አንተ በእርሱ ላይ ጠባቂ ትኾናለህን?* أَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَـٰهَهُ هَوَاهُ أَفَأَنتَ تَكُونُ عَلَيْهِ وَكِيلًا

“ዒባዳህ” عِبَادَة ማለት “አምልኮ” ማለት ሲሆን፥ ዒባዳህ አላህ ዘንድ ተቀባይነት የሚያገኝባቸው ሥስት ሸርጦች አሉት፥ እነርሱም፦ ኢማን፣ ኢኽላስ እና ኢትባዕ ናቸው።
“ኢማን” إِيمَٰن የሚለው ቃል "አመነ" آمَنَ‎ ማለትም "አመነ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "እምነት" ማለት ነው።
“ኢኽላስ” إِخْلَاص የሚለው ቃል "አኽለሰ" أَخْلَصَ‎ ማለትም "አጠራ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን ከወቀሳና ሙገሳ ነጻ ሆኖ ለአላህ ውዴታ የሚደረግ "ማጥራት" ማለት ነው።
“ኢትባዕ” إِتْبَاع‎ የሚለው ቃል “አትበዐ” أَتْبَعَ ማለትም “ተከተለ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መከተል” ማለት ነው። ያለ ኢትባዕ ማንኛውም ዒባዳህ ተቀባይነት የለውም፥ ኢትባዕ ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ በተቀመጠው ብቻ ዒባዳህን መፈጸም ነው፦
6፥106 *ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደውን ተከተል*፡፡ اتَّبِعْ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ
7፥3 *ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ*። اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ

“ተከተሉ” የሚለው ቃል “ኢተቢዑ” اتَّبِعُوا ሲሆን “ኢትባዕ” ማለት ከአላህ ወደ ነቢያችን”ﷺ” የተወረደውን ብቻ መከተል ማለት ነው። “ቢድዓህ” بِدْعَة ደግሞ “በደዐ” بَدَّعَ ማለትም “ፈጠረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ፈጠራ” ማለት ነው። ቢድዓህ የኢትባዕ ተቃራኒ ነው። "ቢድዓህ" ማለት አላህ ሳያዘን እና ሳይፈቅድልን ዝንባሌአችንን ተከትለን የምናደርገው አዲስ አምልኮ ማለት ነው፦
57፥27 ከዚያም በዱካዎቻቸው ላይ መልክተኞቻችንን አስከታተልን፡፡ የመርየምን ልጅ ዒሳንም አስከተልን፡፡ ኢንጂልንም ሰጠነው፡፡ በእነዚያም በተከተሉት ሰዎች ልቦች ውሰጥ መለዘብንና እዝነትን አደረግን፡፡ *"አዲስ የፈጠሩዋትንም ምንኩስና በእነርሱ ላይ አልጻፍናትም፡፡ ግን የአላህን ውዴታ ለመፈለግ ሲሉ ፈጠሩዋት፡፡ ተገቢ አጠባበቋንም አልጠበቋትም*"፡፡ ከእነርሱም ለእነዚያ ላመኑት ምንዳቸውን ሰጠናቸው፡፡ ከእነርሱም ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው፡፡ ثُمَّ قَفَّيْنَا عَلَىٰ آثَارِهِم بِرُسُلِنَا وَقَفَّيْنَا بِعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ وَآتَيْنَاهُ الْإِنجِيلَ وَجَعَلْنَا فِي قُلُوبِ الَّذِينَ اتَّبَعُوهُ رَأْفَةً وَرَحْمَةً وَرَهْبَانِيَّةً ابْتَدَعُوهَا مَا كَتَبْنَاهَا عَلَيْهِمْ إِلَّا ابْتِغَاءَ رِضْوَانِ اللَّهِ فَمَا رَعَوْهَا حَقَّ رِعَايَتِهَا ۖ فَآتَيْنَا الَّذِينَ آمَنُوا مِنْهُمْ أَجْرَهُمْ ۖ وَكَثِيرٌ مِّنْهُمْ فَاسِقُونَ

"የፈጠሩዋትን" ለሚለው የገባው ቃል "ኢብተደዑሃ" ابْتَدَعُوهَا ሲሆን የግስ መደብ ነው፥ የስም መደቡ ደግሞ ቢድዓህ ነው። ያለ ኢትባዕ የአላህን ውዴታ ለመፈለግ ተብሎ የሚደረግ ማንኛውም አዲስ አምልኮ ቢድዓህ ነው፦
ሡነን ነሣኢ መጽሐፍ 19, ሐዲስ 23
ጃቢር ኢብኑ ዐብደላህ እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ኹጥባቸው ላይ እንደተናገሩት፦ *“አላህ የመራውን ማንም አያጠመውም፥ አላህ ያጠመመውን ማንም አያቀናውም። ከንግግር ሁሉ በላጩ የአላህ መጽሐፍ ነው፥ ከመመሪያ ሁሉ በላጩ የሙሐመድ መመሪያ ነው። ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓ ነው፥ ቢድዓህ ሁሉ ጥመት ነው። ጥመት ሁሉ የእሳት ነው*። عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ قَالَ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ فِي خُطْبَتِهِ يَحْمَدُ اللَّهَ وَيُثْنِي عَلَيْهِ بِمَا هُوَ أَهْلُهُ ثُمَّ يَقُولُ مَنْ يَهْدِهِ اللَّهُ فَلَا مُضِلَّ لَهُ وَمَنْ يُضْلِلْهُ فَلَا هَادِيَ لَهُ إِنَّ أَصْدَقَ الْحَدِيثِ كِتَابُ اللَّهِ وَأَحْسَنَ الْهَدْيِ هَدْيُ مُحَمَّدٍ وَشَرُّ الْأُمُورِ مُحْدَثَاتُهَا وَكُلُّ مُحْدَثَةٍ بِدْعَةٌ وَكُلُّ بِدْعَةٍ ضَلَالَةٌ وَكُلُّ ضَلَالَةٍ فِي النَّارِ
ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓህ ነው፥ ቢድዓህ ሁሉ ጥመት ነው፥ ጥመት ሁሉ የእሳት ከሆነ ካየን ዘንዳ ቢድዓህ የሚያራምድ ማንኛውም ሰው በዐሊሞች በያን ከተደረገበት “ሙብተዲዕ” مُبْتَدِئ ይባላል። የነቢያችንን"ﷺ" መንገድ ቀጥተኛ ሲኾን ተከተሉትም፡፡ የጥመት መንገዶችንም አትከተሉ፦
6፥153 *«ይህም ቀጥተኛ ሲኾን መንገዴ ነው፤ ተከተሉትም፡፡ የጥመት መንገዶችንም አትከተሉ፡፡ ከቀጥተኛው መንገድ እናንተን ይለያዩዋችኋልና፡፡እነሆ ትጠነቀቁ ዘንድ በእርሱ አዘዛችሁ፡፡»* በላቸው وَأَنَّ هَـٰذَا صِرَاطِي مُسْتَقِيمًا فَاتَّبِعُوهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعُوا السُّبُلَ فَتَفَرَّقَ بِكُمْ عَن سَبِيلِهِ ۚ ذَٰلِكُمْ وَصَّاكُم بِهِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُون

"ተከተሉ" የሚለውን ቁርኣን እና ሡናህ መሠረት ያደረገ የውዱ ነቢያችን"ﷺ" ቀጥተኛ መንገድ ሲሆን፥ "አትከተሉ" የተባልነው ደግሞ በተቃራኒው ቢድዓ የሆነውን የጥመት መንገዶች ሁሉ ነው። “አህዋእ” أَهْوَآء ማለት “ዝንባሌ”inclination” ማለት ነው፥ ቢድዓህ መሠረቱ “ዝንባሌ” ነው። በነፍሥ ውስጥ ያለው ዝንባሌ “ነፍሢያህ” نَفْسِيَّة‎ ይባላል፥ ዝንባሌ ደግሞ ቦታ ከተሰጠው ሊመለክ የሚችል ክፉ አዛዥ ነው፦
12፥53 «ነፍሴንም ከስሕተት አላጠራም፡፡ *ነፍስ ሁሉ ጌታዬ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር *”በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና*፡፡ ጌታዬ በጣም መሓሪ አዛኝ ነው» አለ፡፡ وَمَا أُبَرِّئُ نَفْسِي ۚ إِنَّ النَّفْسَ لَأَمَّارَةٌ بِالسُّوءِ إِلَّا مَا رَحِمَ رَبِّي ۚ إِنَّ رَبِّي غَفُورٌ رَّحِيمٌ
25፥43 *ዝንባሌውን አምላኩ አድርጎ የያዘውን ሰው አየህን? አንተ በእርሱ ላይ ጠባቂ ትኾናለህን?* أَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَـٰهَهُ هَوَاهُ أَفَأَنتَ تَكُونُ عَلَيْهِ وَكِيلًا

አምላካችን አላህ "ዝንባሌን አትከተሉ" ይለናል፥ ያለ ዕውቀት ዝንባሌን መከተል ያስጠይቃል፥ በዳይነትም ነው፦
4፥135 *"እንዳታደሉም ዝንባሌን አትከተሉ፡፡ ብታጠምሙም ወይም መመስከርን ብትተው አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው*፡፡ فَلَا تَتَّبِعُوا الْهَوَىٰ أَن تَعْدِلُوا ۚ وَإِن تَلْوُوا أَوْ تُعْرِضُوا فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرًا
17፥36 *ለአንተም በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር አትከተል፥ መስሚያ፣ ማያም እና ልብም እነዚህ ሁሉ ባለቤታቸው ከእነርሱ ተጠያቂ ነውና*። وَلَا تَقْفُ مَا لَيْسَ لَكَ بِهِ عِلْمٌ ۚ إِنَّ السَّمْعَ وَالْبَصَرَ وَالْفُؤَادَ كُلُّ أُولَـٰئِكَ كَانَ عَنْهُ مَسْئُولًا
2፥145 *"ከዕውቀትም ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌያቸውን ብትከተል አንተ ያን ጊዜ ከበዳዮች ነህ"*፡፡ وَلَئِنِ اتَّبَعْتَ أَهْوَاءَهُم مِّن بَعْدِ مَا جَاءَكَ مِنَ الْعِلْمِ ۙ إِنَّكَ إِذًا لَّمِنَ الظَّالِمِينَ

በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፦
79፥40 *በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ* وَأَمَّا مَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ وَنَهَى النَّفْسَ عَنِ الْهَوَى
79፥41 *ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት*፡፡ فَإِنَّ الْجَنَّةَ هِيَ الْمَأْوَىٰ

አላህ ከዝንባሌ ይጠብቀን፥ ከቢድዓህ እርቀን በኢትባዕ ብቻ እርሱ የምናመልክ ያርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዒሣ ቃል አይደለም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

19፥35 *ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል*፡፡ مَا كَانَ لِلَّهِ أَن يَتَّخِذَ مِن وَلَدٍ ۖ سُبْحَانَهُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

ለአላህ ልጅ መውለድ አያስፈልገው። ነገርን ማስገኘት ሲፈልግ በንግግሩ “ኹን” ይላል ይሆናል። መርየምም”፦ “ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል?” ስትል፥ መለኮታዊ ምላሽ፦ “አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፥ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል” የሚል ምላሽ ነው፦
3፥47 *፡-ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለች፡፡ ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፥ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል አላት*፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

ወደ መርየም የጣላት ቃላት፦ “ኩን” كُن የሚል ነው። አንድ ጊዜ ነጅራኖች ማለትም የየመን ክርስቲያኖች፦ “ዒሣ የአላህ ልጅ ካልሆነ እንግዲያውስ አባቱ ማን ነው? ብለው ጠየቁ፥ አምላካችን አላህም ይህንን አንቀጽ አወረደ፦
3፥59 አላህ ዘንድ *የዒሳ ምሳሌ እንደ አዳም ብጤ ነው፡፡ ከአፈር ፈጠረው፡፡ ከዚያም ለእርሱ «ኹን» አለው፤ ኾነም*፡፡ إِنَّ مَثَلَ عِيسَىٰ عِندَ اللَّهِ كَمَثَلِ آدَمَ ۖ خَلَقَهُ مِن تُرَابٍ ثُمَّ قَالَ لَهُ كُن فَيَكُونُ

አላህ አደምን ከአፈር ቅርጹን ካበጀ በኃላ በቃሉ “ኹን” አለው ሰው ሆነ፥ በተመሳሳይም ዒሣን ከመርየም “ኹን” አለው ሰው ሆነ። “ወከሊመቱል ቃሃ ኢላ መርየም* وَكَلِمَتُهُ أَلْقَاهَا إِلَىٰ مَرْيَمَ ማለትም “ወደ መርየም የጣላት የይኹን ቃላት” ነው፦
4:171 እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፤ በአላህም ላይ እውነትን እንጂ አትናገሩ፤ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ዒሳ፣ የአላህ መልክተኛ፣ *ወደ መርየም የጣላት የሁን ቃሉም ነው*፤ ከእርሱ የሆነ መንፈስም ብቻ ነው። يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا تَغْلُوا۟ فِى دِينِكُمْ وَلَا تَقُولُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ إِلَّا ٱلْحَقَّ ۚ إِنَّمَا ٱلْمَسِيحُ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ ٱللَّهِ وَكَلِمَتُهُۥٓ أَلْقَىٰهَآ إِلَىٰ مَرْيَمَ وَرُوحٌۭ مِّنْهُ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ከሊማት” كَلِمَت የከሊማህ ብዜት ሲሆን “ቃላት” ማለት ነው። ይቺ ቃላት ተባዕታይ መደብ ስለሆነች “አልቃሃ” أَلْقَاهَا ማለት “የጣላት” ተብላለች። ዒሣ ቃል ቢሆን ኖሮ በተባታይ መደብ “አልቃሁ” أَلْقَاهُ ማለትም “የጣለው” ይባል ነበር። ቅሉ ግን ይህቺ የይኹን ቃላት መንስኤ ስትሆን ዒሣ ደግሞ ውጤት ነው። ቀደምት ሠለፎች የተረዱት በዚህ መልክ እና ልክ ነው፦
ተፍሢፉል ኢብኑ ከሲር 4፥171
ኢብኑ አቢ ሐቲም እንደዘገበው፦ “አሕመድ ኢብኑ ሢናነል ዋሢጢይ እንደተናገረው፦ “ሻዝ ኢብኑ የሕያ”ረ.ዐ.” እንዲህ አለ፦ *”ወደ መርየም የጣላት የሁን ቃሉም ነው” የሚለው “ቃሊቷ እራሷ ዒሣ አልሆነችም፥ ነገር ግን በቃሊቱ ዒሣ ተገኘ እንጂ”*። وقال ابن أبي حاتم : حدثنا أحمد بن سنان الواسطي قال : سمعت شاذ بن يحيى يقول : في قول الله : ( وكلمته ألقاها إلى مريم وروح منه ) قال : ليس الكلمة صارت عيسى ، ولكن بالكلمة صار عيسى

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
መለኩት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

6፥75 እንደዚሁም ኢብራሂምን ከአረጋጋጮቹም ይኾን ዘንድ *የሰማያትን እና የምድርን መለኮት አሳየነው*፡፡ وَكَذَٰلِكَ نُرِي إِبْرَاهِيمَ مَلَكُوتَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَلِيَكُونَ مِنَ الْمُوقِنِينَ

"መለኩት" مَلَكُوت ማለት "ግዛት" ማለት ነው። ልክ "ማሊክ" እና "መሊክ" ተለዋዋጭ እንደሆኑ ሁሉ "መለኩት" እና "ሙልክ" ተለዋዋጭ ቃላት ናቸው፥ "ማሊክ" مَٰلِك ማለት "ባለቤት" ማለት ነው፣ "መሊክ" مَلِك ማለት "ንጉሥ" ማለት ነው፣ "ሙልክ" مُلْك ማለት "ንግሥና" ማለት ነው፦
67፥1 ያ *"ሙልክ"* በእጁ የኾነው አምላክ ችሮታው በዛ፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡ تَبَارَكَ الَّذِي بِيَدِهِ الْمُلْكُ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
23፥88 «የነገሩ ሁሉ *"መለኩት"* በእጁ የኾነ እርሱ የሚጠብቅ በእርሱ ላይ የማይጠበቅ ማን ነው የምታውቁ እንደኾናችሁ መልሱልኝ» በላቸው፡፡ قُلْ مَن بِيَدِهِ مَلَكُوتُ كُلِّ شَيْءٍ وَهُوَ يُجِيرُ وَلَا يُجَارُ عَلَيْهِ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "መለኩት" የተባለው "ግዛት" መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። ይህ ከገባን ዘንዳ አምላካችን አላህ ለኢብራሂም "የሰማያትን እና የምድርን መለኩት አሳየነው" ሲል ምን ማለት እንደሆነ በቀላሉ መረዳት ይቻላል፦
6፥75 እንደዚሁም ኢብራሂምን ከአረጋጋጮቹም ይኾን ዘንድ *የሰማያትን እና የምድርን መለኮት አሳየነው*፡፡ وَكَذَٰلِكَ نُرِي إِبْرَاهِيمَ مَلَكُوتَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَلِيَكُونَ مِنَ الْمُوقِنِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ ዐማርኛው ላይ "መለኮት" ለሚለው ቃል ዐረቢኛው የተጠቀመው "መለኩት" ነው። "መለኩት" مَلَكُوت ማለት "ግዛት" ማለት እንጂ "አምላክ" ማለት አይደለም። "መለኮት" የሚለው የግዕዝ ቃል እራሱ ሁለት ትርጉም አለው፥ አንዱ "አምላክ" ማለት ሲሆን ሁለተኛው "ግዛት" ማለት ነው። አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ገጽ 594-595 ላይ "መለኮት" ሁለት ትርጉም እንዳለው ገልጸዋል። አንዱ "ግዛት" "ንግሥና" "ሥልጣን" ማለት ሲሆን ሁለተኛ "አምላክነት" ማለት ነው። ባይብሉም ላይ "መለኮት" ማለት "ንግሥና" "ሥልጣን" "ግዛት" በሚል ይመጣል። ለምሳሌ "ግዛቱ" ለሚለው ቃል ግዕዙ "መለኮቱ" የሚል ቃል ተጠቅሟል፦
መዝሙር 103፥22 *ባርክዎ ለእግዚአብሔር ኵሉ ተግባሩ ውስተ ኵሉ በሐውርተ *"መለኮቱ"*። ትባርኮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር።

ትርጉም፦
"ፍጥረቶቹ ሁሉ *በግዛቱ* ስፍራ ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ባርኩ። ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኪ።"

"መለኮት" የሚለው "አምላክነት" በሚል መጥቷል፦
ሮሜ 1፥20 ወዘኢያስተርኢ እግዚአብሔር እምፍጥረተ ዓለን ይትዐወቅ በፍጥረቱ በሐልዮ ወበአእምሮ። ወከመዝ ይትአምር ኃይሉ *"ወመለኮቱ"* ዘለዓለም።

ትርጉም፦
"የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም ኃይሉ ደግሞም *አምላክነቱ* ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሠሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና።"

አላህ ለኢብራሂም "የሰማያትን እና የምድርን መለኮት አሳየነው" ሲባል "የሰማያትን እና የምድርን አምላክ አሳየነው" ማለት ሳይሆን "የሰማያትን እና የምድርን ግዛት አሳየነው" ማለት ነው። ቁርኣኑ አምላክ የሚለው መለኮት ለማመልከት “ኢላህ” إِلَـٰه የሚለው ቃል እንጂ "መለኩት" የሚለውን ቃል አይጠቀምም። “ኢላሂይ” إِلٰهِيّ‎ ማለት “መለኮታዊ” ወይም “አምላካዊ” ማለት ሲሆን “ኡሉሂያህ” أُلُوهِيَّة‎ ማለት ደግሞ “አምላክነት” ማለት ነው። “ኢላሂያት” إِلٰهِيَّات‎ ማለት በራሱ “ሥነ-መለኮት” ማለት ነው። አላህ ብቻውን አንድ መለኮት ነው፥ ከእርሱ በቀር ሌላ መለኮት የለም፦
4፥171 *አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው”*፡፡ ለእርሱ ልጅ ያለው ከመኾን የጠራ ነው፡፡ በሰማያትና በምድር ያለ ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ መመኪያም በአላህ በቃ፡፡ إِنَّمَا اللَّهُ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ ۖ سُبْحَانَهُ أَن يَكُونَ لَهُ وَلَدٌ ۘ لَّهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۗ وَكَفَىٰ بِاللَّهِ وَكِيلًا
6፥19 *«እርሱ አንድ አምላክ ብቻ ነው*፡፡ እኔም ከምታጋሩት ነገር ንጹሕ ነኝ» በላቸው፡፡ قُلْ إِنَّمَا هُوَ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ وَإِنَّنِي بَرِيءٌ مِّمَّا تُشْرِكُونَ
2፥163 *”አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፥ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም”*፡፡ እርሱ እጅግ በጣም ርኅሩህ አዛኝ ነው፡፡ وَإِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ ۖ لَّا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ الرَّحْمَـٰنُ الرَّحِيمُ

ግዕዝ ቋንቋ ላይ ተመሳሳይ ቃል ቢኖረው እንኳን ተመሳሳይ አሳብና ትርጉም አለው ማለት አይደለም። የአንድን ቃል አማራጭ ትርጉም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ ቅቡል ነው። መታየት ያለበት ቃሉ ሳይሆን ቃሉ የወከለው አሳብ ነው። ስለዚህ "ኢብራሂም አላህን አይቷል" የሚል የሚሽነሪዎች አርቲ ቡርቲ እና ቶራ ቦራ በሥነ-ቋንቋ ሙግት እንዲህ ድባቅ ይገባል።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኒያህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

64፥4 በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል፡፡ *"የምትደብቁትንም የምትገልጡትንም ያውቃል፡፡ አላህም በልቦች ውስጥ ያለውን ሁሉ ዐዋቂ ነው"*፡፡ يَعْلَمُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَيَعْلَمُ مَا تُسِرُّونَ وَمَا تُعْلِنُونَ ۚ وَاللَّهُ عَلِيمٌ بِذَاتِ الصُّدُورِ

“ኒያህ” نِيَّة የሚለው ቃል “ነዋ” نَوَى ማለትም “ወጠነ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ውጥን”intention” ማለት ነው። ኒያህ በልብ ውስጥ የሚቀመጥ እና አላህ ብቻ የሚያውቀው ጉዳይ ነው፦
64፥4 በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል፡፡ *"የምትደብቁትንም የምትገልጡትንም ያውቃል፡፡ አላህም በልቦች ውስጥ ያለውን ሁሉ ዐዋቂ ነው"*፡፡ يَعْلَمُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَيَعْلَمُ مَا تُسِرُّونَ وَمَا تُعْلِنُونَ ۚ وَاللَّهُ عَلِيمٌ بِذَاتِ الصُّدُورِ

የማንኛውም ሰው ሥራ የሚለካው በልብ ውስጥ በተቀመጠው ኒያህ ነው፥ ማንኛውምንም ሰው የነየተውን ያገኛል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 47
ዑመር እንደተረከው፦ "የአላህ መልክተኛ"ﷺ" እንዲህ ብለዋል፦ *"ሥራ የሚለካው በውጥን ነው፥ ማንኛውምንም ሰው የወጠነውን ያገኛል። ስደቱ ወደ አላህ እና መልክተኛው የሆነ ስደቱ ወደ አላህና መልክተኛው ነው፥ የስደቱ ግብ ለዲንያህ ጥቅም ወይም አንዲት ሴትን ሊያገባት ከሆነ ስደቱ ለተሰደደበት አላማ ነው"*። عَنْ عُمَرَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ الأَعْمَالُ بِالنِّيَّةِ، وَلِكُلِّ امْرِئٍ مَا نَوَى، فَمَنْ كَانَتْ هِجْرَتُهُ إِلَى اللَّهِ وَرَسُولِهِ، فَهِجْرَتُهُ إِلَى اللَّهِ وَرَسُولِهِ، وَمَنْ كَانَتْ هِجْرَتُهُ لِدُنْيَا يُصِيبُهَا، أَوِ امْرَأَةٍ يَتَزَوَّجُهَا، فَهِجْرَتُهُ إِلَى مَا هَاجَرَ إِلَيْهِ

"ኒያት" نِيَّات‎ የኒያህ ብዙ ቁጥር ሲሆን "ውጥኖች" ማለት ነው። አንድ ሰው ባለማወቅ ግን በልቡ "ስህተት አይደለም" ብሎ ወጥኖ እኩይ ሥራ ቢሠራ ስህተት ነው፥ ግን አይጠየቅበትም፤ አይቀጣም፦
33:5 *በእርሱ በተሳሳታችሁበትም ነገርም በእናንተ ላይ ሐጢያት የለባችሁም፤ ግን ልቦቻችሁ ዐዉቀው በሠሩት ሐጢያት አለባችሁ* አላህም መሃሪ አዛኝ ነው። وَلَيْسَ عَلَيْكُمْ جُنَاحٌۭ فِيمَآ أَخْطَأْتُم بِهِۦ وَلَٰكِن مَّا تَعَمَّدَتْ قُلُوبُكُمْ ۚ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورًۭا رَّحِيمًا
2፥286 አላህ ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም፡፡ ለእርስዋ የሠራችው አላት፡፡ በእርስዋም ላይ ያፈራችው ኀጢአት አለባት፡፡ በሉ፡- ጌታችን ሆይ! *"ብንረሳ ወይም ብንስት አትቅጣን"*፡፡ لَا يُكَلِّفُ اللَّهُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا ۚ لَهَا مَا كَسَبَتْ وَعَلَيْهَا مَا اكْتَسَبَتْ ۗ رَبَّنَا لَا تُؤَاخِذْنَا إِن نَّسِينَا أَوْ أَخْطَأْنَا

ሰው በእንቅልፍ ልብ፣ ለአቅመ-አደምና ለአቅመ-ሐዋ ባለመድረሱ ባለማወቅ እና በዐቅል መሳት ዕብደት በሚሠራው ሥራ አይጠየቅም። ዕያወቁ ሆን ተብሎ መሳሳት ዕጸጽ ሳይሆን ግድፈት ስለሆነ ያስጠይቃል። ዕጸጽ ማለት ግን ሆን ሳይባል እና በውስጡ ውጥን ሳይኖር እኩይ ነገር መሥራት ነው፥ ለምሳሌ በመኪና ሰው ገጭቶ መግደል ወዘተ.. ነው። ኒያህ ልብ ውስጥ የሚቀመጥ ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 36, ሐዲስ 22
አቡ ከብሻህ አል-አንማሪይ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ *"አንድ ባሪያ አላህ ሃብት እና ዕውቀት ያልወፈቀው፦ "ሀብት ቢኖረኝ እንዲህ እንዲያህ እሠራለው" ቢል ኒያህ አለው፥ ስለዚህ ሁለቱም(በልብ መነየት እና በድርጊት መሥራት) ኀጢአቶች ተመሳሳይ ናቸው"*። أَنَّهُ قَالَ حَدَّثَنِي أَبُو كَبْشَةَ الأَنْمَارِيُّ، أَنَّهُ سَمِعَ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ وَعَبْدٍ لَمْ يَرْزُقْهُ اللَّهُ مَالاً وَلاَ عِلْمًا فَهُوَ يَقُولُ لَوْ أَنَّ لِي مَالاً لَعَمِلْتُ فِيهِ بِعَمَلِ فُلاَنٍ فَهُوَ بِنِيَّتِهِ فَوِزْرُهُمَا سَوَاءٌ
ሡነን ነሣኢ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 153
አቢ ሙሣ እንደተረከው፦ ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ሁለት ሙስሊሞች ሾተል ከተማዘዙ፥ ገዳይም ተገዳይም እሳት ውስጥ ይሆናሉ"። እንዲህም ተባለ፦ "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ገዳይስ ይሁን፥ የሟች ጥፋት ለቅጣት የሚያበቃው ምን ሆኖ ነው? እርሳቸውም፦ *"ወዳጁን ለመግደል ቋምጦ ነበር" ሲሉ መለሱ"*። عَنْ أَبِي مُوسَى، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ إِذَا تَوَاجَهَ الْمُسْلِمَانِ بِسَيْفَيْهِمَا فَقَتَلَ أَحَدُهُمَا صَاحِبَهُ فَهُمَا فِي النَّارِ ‏"‏ ‏.‏ قِيلَ يَا رَسُولَ اللَّهِ هَذَا الْقَاتِلُ فَمَا بَالُ الْمَقْتُولِ قَالَ ‏"‏ أَرَادَ قَتْلَ صَاحِبِهِ

ተገዳይ ለመግደል ነይቶ ከነበረ እርሱም የትንሳኤ ቀን በነየተው እኩይ ኒያህ ይጠየቃል። በትንሳኤ ቀን ሰዎች የሚቀሰቀሱትና የሚበየንባቸው በነየቱት ኒያህ ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 4370
አቢ ሁራይራህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልክተኛ"ﷺ" እንዲህ ብለዋል፦ *"ሰዎች የሚቀሰቀሱትና የሚበየንባቸው በነየቱት ነው"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏:‏ ‏ "‏ إِنَّمَا يُبْعَثُ النَّاسُ عَلَى نِيَّاتِهِمْ
ለአላህ ብሎ ተነይቶ መልካም ሥራዎችን መሥራት ኢኽላስ ይባላል፥ “ኢኽላስ” إِخْلَاص የሚለው ቃል “አኽለሰ” أَخْلَصَ‎ ማለትም “አጠራ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን ከወቀሳና ሙገሳ ነጻ ሆኖ ለአላህ ውዴታ የሚደረግ “ማጥራት” ማለት ነው፦
13፥22 እነዚያም *የጌታቸውን ውዴታ ለመፈለግ የታገሱ፣ ሶላትንም አዘውትረው የሰገዱ፣ እኛ ከሰጠናቸው ሲሳይም በምስጢርም ኾነ በግልጽ የመጸወቱ፣ ክፉውንም ነገር በበጎ የሚገፈትሩ ናቸው*፡፡ እነዚያ ለእነርሱ መጨረሻይቱ ምስጉን አገር አለቻቸው*፡፡ وَالَّذِينَ صَبَرُوا ابْتِغَاءَ وَجْهِ رَبِّهِمْ وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ وَأَنفَقُوا مِمَّا رَزَقْنَاهُمْ سِرًّا وَعَلَانِيَةً وَيَدْرَءُونَ بِالْحَسَنَةِ السَّيِّئَةَ أُولَـٰئِكَ لَهُمْ عُقْبَى الدَّارِ
76፥9 *«የምናበላችሁ ለአላህ ውዴታ ብቻ ነው፡፡ ከእናንተ ዋጋንም ማመስገንንም አንፈልግም*፡፡ إِنَّمَا نُطْعِمُكُمْ لِوَجْهِ اللَّهِ لَا نُرِيدُ مِنكُمْ جَزَاءً وَلَا شُكُورًا
76፥10 *«እኛ ፊትን የሚያጨፈግግን ብርቱ ቀን ከጌታችን እንፈራለንና» ይላሉ*፡፡ إِنَّا نَخَافُ مِن رَّبِّنَا يَوْمًا عَبُوسًا قَمْطَرِيرًا

በተቃራኒው ለሰው እዩልኝና ስሙልኝ የሚደረግ መልካም ሥራ አር-ሪያእ ነው፥ “አር-ሪያእ” الرِّيَاء ማለት “እዩልኝ ስሙልኝ” ማለት ነው፦
2፥264 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *እንደዚያ ገንዘቡን ለሰዎች ማሳየት ሲል እንደሚሰጠው እና በአላህና በመጨረሻውም ቀን እንደማያምነው ሰው ምጽዋቶቻችሁን በመመጻደቅና በማስከፋት አታበላሹ"*። يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تُبْطِلُوا صَدَقَاتِكُم بِالْمَنِّ وَالْأَذَىٰ كَالَّذِي يُنفِقُ مَالَهُ رِئَاءَ النَّاسِ وَلَا يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ
107፥4 *ወዮላቸው ለሰጋጆች*፡፡ فَوَيْلٌۭ لِّلْمُصَلِّينَ
107፥6 *ለእነዚያ እነርሱ ይዩልኝ ባዮች ለኾኑት*፡፡ ٱلَّذِينَ هُمْ يُرَآءُونَ

አር-ሪያእ “ሺርኩል አስገር” شِّرْكُ الأَصْغَر ማለትም “ትንሹ ሺርክ” ነው፥ ነቢያችን”ﷺ” ስለ ትንሹ ሺርክ እንዲህ ያስጠነቅቁናል፦
ኢማም አሕመድ መጽሐፍ 5, ሐዲስ 428
መሕሙድ ኢብኑ ለቢድ እንደተረከው ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *”ትንሹን ሺርክ እፈራላችኃለው” ሰሓባዎችም፦ “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ትንሹን ሺርክ ምንድን ነው? ብለው ጠየቁ። እሳቸውም፦ “አር-ሪያእ ነው። በዋጋ በሚከፈልበት ቀን ሰዎች ዋጋቸውን በሚቀበሉበት ጊዜ አላህም፦ “ስታሳይዋቸው የነበሩት ከእነርሱ አጅር የምታገኙ ከሆነ ይክፈሏችሁ” ብሎ ይላቸዋል” ብለው መለሱ*። عَنْ مَحْمُودِ بْنِ لَبِيدٍ ، أَنّ النَّبِيَّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ : ” إِنَّ أَخْوَفَ مَا أَخَافُ عَلَيْكُمُ الشِّرْكَ الأَصْغَرَ ” ، قَالُوا : يَا رَسُولَ اللَّهِ ، وَمَا الشِّرْكُ الأَصْغَرُ ؟ قَالَ : ” الرِّيَاءُ ، يَقُولُ اللَّهُ لَهُمْ يَوْمَ يُجَازِي الْعِبَادَ بِأَعْمَالِهِمُ : اذْهَبُوا عَلَى الَّذِينَ كُنْتُم تُرَاءُونَ فِي الدُّنْيَا ، فَانْظُرُوا هَلْ تَجِدُونَ عِنْدَهُمْ جَزَاءً ” .

አር-ሪያእ “ሺርኩል ኸፊይ” شِّرْكُ الْخَفِي ማለትም “ድብቁ ሺርክ” እንደሆነ በሌላ ሐዲስ ነቢያችን”ﷺ” ተናግረዋል፦
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 4344
አቢ ሠዒድ እንደተናገረው፦ *”ስለ መሢሑ አድ-ደጃል በተወያየንበት ጊዜ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ወደ እኛ መጥተው፦ “ከመሢሑ አድ-ደጃል የባሰ የምፈራላችሁን ነገር ልንገራችሁን? አሉን፥ እኛም አዎ አልን። እርሳቸውም፦ “ድብቁ ሺርክ ነው፤ አንድ ሰው ሶላት ሲቆምና በሰው ፊት ጥሩ አድርጎ ለሰው እንዲያይለት ማድረግ ነው*። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ، قَالَ خَرَجَ عَلَيْنَا رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ وَنَحْنُ نَتَذَاكَرُ الْمَسِيحَ الدَّجَّالَ فَقَالَ ‏”‏ أَلاَ أُخْبِرُكُمْ بِمَا هُوَ أَخْوَفُ عَلَيْكُمْ عِنْدِي مِنَ الْمَسِيحِ الدَّجَّالِ ‏”‏ ‏.‏ قَالَ قُلْنَا بَلَى ‏.‏ فَقَالَ ‏”‏ الشِّرْكُ الْخَفِيُّ أَنْ يَقُومَ الرَّجُلُ يُصَلِّي فَيُزَيِّنُ صَلاَتَهُ لِمَا يَرَى مِنْ نَظَرِ رَجُلٍ ‏”‏ ‏

አንድ ሰናይ ሥራ ከመከናወኑ በፊት መልካም ተነሳሽነት ኒያህ አስፈላጊ እንደሆነ የመስኩ ምሁራን ተስማምተውበታል፥ ግን ማንኛውንም ተግባር ተቀባይነት ይኖረው ዘንድ የግድ ኒያህ ያስፈልገዋል ወይስ አያስፈልገውም? በሚለው ነጥብ ላይ አንድ አይነት አቋም የለም። የሻፊዒይ መዝሐብ፦ "እንደ ውዱእ ባሉ የዒባዳህ ቅድመ-ሁኔታ ላይ ኒያህ ቅድመ መስፈርት ነው" ሲሉ የሐነፊይ መዝሐብ፦ ደግሞ በዒባዳህ ላይ እንጂ ለዒባዳህ በሚደረጉ ቅድመ-ሁኔታ ላይ ኒያህ ቅድመ መስፈርት አይደለም" ብለዋል።
ከዒባዳህ ውጪ ከሰዎች ጋር በሚኖረን መስተጋብር እና ለምንሠራው ሥራ የምናልመው ዓላማ ቀስድ ይባላል፥ "ቀስድ" قَصْد የሚለው ቃል “ቀሰደ” قَصَدَ ማለትም “ዓለመ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ዓላማ” ማለት ነው።
አላህ በኢኽላስ ነይተው መልካም ሥራ ከሚሰሩ ሙኽሊሲን ባሮቹ ያድርገን! አሚን

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የሙሴ አምላክ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

10፥3 *ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው*፡፡ ከዚያም ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብር ሲኾን በዐርሹ ላይ ተደላደለ፡፡ ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም፡፡ እነሆ! *”አላህ ጌታችሁ ነውና አምልኩት*፤ አትገሰጹምን? إِنَّ رَبَّكُمُ ٱللَّهُ ٱلَّذِى خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ فِى سِتَّةِ أَيَّامٍۢ ثُمَّ ٱسْتَوَىٰ عَلَى ٱلْعَرْشِ ۖ يُدَبِّرُ ٱلْأَمْرَ ۖ مَا مِن شَفِيعٍ إِلَّا مِنۢ بَعْدِ إِذْنِهِۦ ۚ ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمْ فَٱعْبُدُوهُ ۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ

እኛ ሙስሊሞች ክርስቲያኖችን፦ “ኢየሱስ፦ እኔ አምላክ ነኝ፥ አምልኩኝ” ያለበት ጥቅስ ከባይብል አሳዩን ስላቸው፤ እንደዛ የሚልበት አንቀፅ እንደሌለ ሲያውቁት በእጅ አዙር ልከክልህ እከክልኝ በሚል ስሁት ሙግት አላህ፦ “እኔ እኔ አምላክ ነኝ፥ አምልኩኝ” ያለበት ጥቅስ ከቁርአን አሳዩን ብለው እህህና አሄሄ እያሉ ያለቃቅሳሉ፤ ቁርአን ላይ በቁና ጥቅስ አላህ፦ “እኔ አምላክ ነኝ፥ አምልኩኝ” ያለበት አናቅጽ ማቅረብ ይቻላል፤ ጥንትም ሙሳን ሲያናግር የነበረው የሙሳ አምላክ አላህ እራሱ ነው፤ አላህ ለሙሳ፦ “እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና አምልከኝ” ብሎታል፦
20፥14 *«እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና አምልከኝ*፡፡ ሶላትንም በእርሷ እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡ إِنَّنِىٓ أَنَا ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدْنِى وَأَقِمِ ٱلصَّلَوٰةَ لِذِكْرِىٓ

“ይህ እኮ ሙሳን ነው ያለው” የሚል ምላሽ ይሰጣል፤ ታዲያ እኮ ሙሳን ያናገረው አላህ እንደሆነ ቁርአን ይናገራል፤ የተፈለገው አላህ፦ “እኔ እኔ አምላክ ነኝ፥ አምልኩኝ” ያለበት ጥቅስ ነው፤ በተጨማሪም ሙሳን “እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና አምልከኝ” ብሎ የተናገረው ነብያችንን”ﷺ” የሚያናግር አላህ ለመሆኑ ሁለት ነጥቦችን ማየት እንችላለን፦

ነጥብ አንድ
“ተጠራ”
አላህ ለሙሳ፦ “እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና አምልከኝ” ብሎ ከማለቱ በፊት «ሙሳ ሆይ» በማለት ጠርቶታል፦
20፥11 በመጣም ጊዜ «ሙሳ ሆይ» በማለት *”ተጠራ*፡፡ فَلَمَّآ أَتَىٰهَا نُودِىَ يَٰمُوسَىٰٓ

ይህንን ጥሪ ጠርቶ ያነጋገረው እራሱ እንደሆነ በመጀመሪያ መደብ ለነብያችን”ﷺ”፦ “ጠራነው፤ ያነጋገርነውም ሲኾን አቀረብነው” በማለት ሙሴን የጠራው እርሱ እንደሆነ ይናገራል፦
19፥51 በመጽሐፉ ውስጥ *ሙሳንም አውሳ*፡፡ እርሱ ምርጥ ነበርና፡፡ መልክተኛ ነቢይም ነበር፡፡ وَٱذْكُرْ فِى ٱلْكِتَٰبِ مُوسَىٰٓ ۚ إِنَّهُۥ كَانَ مُخْلَصًۭا وَكَانَ رَسُولًۭا نَّبِيًّۭا
19፥52 ከጡር ቀኝ ጎን በኩልም *ጠራነው፤ ያነጋገርነውም* ሲኾን አቀረብነው፡፡ وَنَٰدَيْنَٰهُ مِن جَانِبِ ٱلطُّورِ ٱلْأَيْمَنِ وَقَرَّبْنَٰهُ نَجِيًّۭا

ነጥብ ሁለት
“የሚወረድልህንም”
አላህ ሙሳን፦ “እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና አምልከኝ” ብሎ ከማለቱ በፊት “የሚወረድልህንም ነገር አዳምጥ” ብሎታል፦
20፥13 «እኔም መረጥኩህ፤ *”የሚወረድልህንም”* ነገር አዳምጥ፡፡ وَأَنَا ٱخْتَرْتُكَ فَٱسْتَمِعْ لِمَا يُوحَىٰٓ

አላህ ከዚህ በፊት ለመልእክተኛ ምን ብሎ እንደሚያወርድ ሲናገር “ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ” በማለት እራሱ ወሕይ እንደሚያወርድ ለነብያችን”ﷺ” ይነግራቸዋል፦
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ *”ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ”* በማለት ወደ እርሱ *”የምናወርድለት”* ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ

ነጥብ ሶስት
“አምልኩኝ”
አላህ በመጀመሪያ መደብ “አዕቡዱኒ” َٱعْبُدُونِ “አምልኩኝ” ብሎ ይናገራል፤ በተጨማሪም በሶስተኛ መደብ ስለ እራሱ ሲናገር “አዕቡዱሁ” َٱعْبُدُوهُ “አምልኩት” ብሎ ይናገራል፦
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ *”እኔንም ብቻ አምልኩኝ”*፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ
21፥92 ይህች አንዲት መንገድ ስትሆን በእርግጥ ሃይማኖታችሁ ናት፤ *”እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ”*፡፡ إِنَّ هَٰذِهِۦٓ أُمَّتُكُمْ أُمَّةًۭ وَٰحِدَةًۭ وَأَنَا۠ رَبُّكُمْ فَٱعْبُدُونِ
6፥102 ይህ *”ጌታችሁ አላህ ነው፤ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፤ ነገርን ሁሉ ፈጣሪ ነው፤ ስለዚህ አምልኩት”*፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነው፡፡ ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمْ ۖ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ خَٰلِقُ كُلِّ شَىْءٍۢ فَٱعْبُدُوهُ ۚ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍۢ وَكِيلٌۭ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
አል-አወል ወል-አኺር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

57፥3 *"እርሱ ፊትም ያለ፣ ኋላም ቀሪ፣ ግልጽም፣ ስውርም ነው፡፡ እርሱም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው"*፡፡ هُوَ الْأَوَّلُ وَالْآخِرُ وَالظَّاهِرُ وَالْبَاطِنُ ۖ وَهُوَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

"አል-አወል" الْأَوَّل ማለት "መጀመሪያ የሌለው ፊተኛ" ማለት ሲሆን "አል-አኺር" الْآخِر ማለት ደግሞ "መጨረሻ የሌለው ኃለኛ" ማለት ነው። አምላካችን አላህ ከፍጥረት በፊት ቀዳማይ ፊተኛ፥ ከፍጥረት በኃላም ደኃራይ ኃለኛ ነው፦
57፥3 *"እርሱ ፊትም ያለ፣ ኋላም ቀሪ፣ ግልጽም፣ ስውርም ነው፡፡ እርሱም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው"*፡፡ هُوَ الْأَوَّلُ وَالْآخِرُ وَالظَّاهِرُ وَالْبَاطِنُ ۖ وَهُوَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 48, ሐዲስ 112
አቢ ሁራይራ እንደተረከው፦ "ፋጢማህ ወደ ነቢዩ"ﷺ" ስለ አገልጋይ ጠየቀች፥ እርሷቸውም ለእርሷ፦ *"አላህ ሆይ! የሰባቱ ሰማያት እና የታላቁ ዙፋን ጌታ ነህ፥ የነገር ሁሉ ጌታ ጌታችን ሆይ! ተውራትን፣ ኢንጂልን፣ ቁርኣንን አውራጅ ነህ፥ ቅንጣትን እና የፍሬ አጥንትን ፈልቃቂ ነህ። አንተ አናትን የምትይዝ ስትሆን ከእኩይ ነገር ሁሉ በአንተ እጠበቃለው። አንተ ፊተኛ ነህ፥ ከአንተ በፊት ምንም ነገር የለም። አንተ ኃለኛ ነህ፥ ከአንተ በኃላ ምንም ነገር የለም። አንተ ግልጽ ነህ፥ ከአንተ በላይ ምንም ነገር የለም። አንተ ስውር ነህ፥ ከአንተ ባሻገር ምንም ነገር የለም" በይ አሏት"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ جَاءَتْ فَاطِمَةُ إِلَى النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم تَسْأَلُهُ خَادِمًا فَقَالَ لَهَا ‏ "‏ قُولِي اللَّهُمَّ رَبَّ السَّمَوَاتِ السَّبْعِ وَرَبَّ الْعَرْشِ الْعَظِيمِ رَبَّنَا وَرَبَّ كُلِّ شَيْءٍ مُنْزِلَ التَّوْرَاةِ وَالإِنْجِيلِ وَالْقُرْآنِ فَالِقَ الْحَبِّ وَالنَّوَى أَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ كُلِّ شَيْءٍ أَنْتَ آخِذٌ بِنَاصِيَتِهِ أَنْتَ الأَوَّلُ فَلَيْسَ قَبْلَكَ شَيْءٌ وَأَنْتَ الآخِرُ فَلَيْسَ بَعْدَكَ شَيْءٌ وَأَنْتَ الظَّاهِرُ فَلَيْسَ فَوْقَكَ شَيْءٌ وَأَنْتَ الْبَاطِنُ فَلَيْسَ دُونَكَ شَيْءٌ

ከአላህ በፊት ምንም ነገር የለም፥ ከአላህ በኃላ ምንም ነገር የለም። "ሸይእ" شَيْء ማለት "ነገር" ማለት ሲሆን አጠቃላይ ፍጥረት ነው። ሁሉ ነገር ጠፊ ነው፥ ሁሉ ነገር ሲጠፋ ኃላ ቀሪ ኃለኛ አላህ ነው። ሁሉ ነገር ሳይኖር ፊትም ያለ ፊተኛ እርሱ ብቻ ነው፦
28፥88 ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አትግገዛ፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ *ነገሩ ሁሉ ከአላህ በቀር ጠፊ ነው*፡፡ ፍርዱ የእርሱ ብቻ ነው፡፡ ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ፡፡ وَلَا تَدْعُ مَعَ اللَّهِ إِلَـٰهًا آخَرَ ۘ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ كُلُّ شَيْءٍ هَالِكٌ إِلَّا وَجْهَهُ ۚ لَهُ الْحُكْمُ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 59, ሐዲስ 2
ዒምራም ኢብኑ ሑሰይን እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *”በመጀመሪያ ምንም ነገር ሳይኖር አላህ ነበረ"*፣ ከዚያ ዙፋኑን በውኃ ላይ ነበረ፣ ከዚያ ሁሉን ነገር ጻፈ፣ ከዚያ ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ። عَنْ عِمْرَانَ بْنِ حُصَيْنٍ، قَالَ إِنِّي عِنْدَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم كَانَ اللَّهُ وَلَمْ يَكُنْ شَىْءٌ غَيْرُهُ، وَكَانَ عَرْشُهُ عَلَى الْمَاءِ، وَكَتَبَ فِي الذِّكْرِ كُلَّ شَىْءٍ، وَخَلَقَ السَّمَوَاتِ وَالأَرْضَ ‏

አላህ መጀመሪያ ከሌለው ከጊዜ በኃላ መነሻ ያለው ምንም አይነት ሲፋህ የለውም። “ሲፋህ” صِفَة ማለት "ባሕርይ"attribute" ማለት ነው፥ የሲፋህ ብዙ ቁጥር “ሲፋት” صِفَات‎ ነው። የእርሱ ሲፋህ የእርሱ ምንነት መገለጫ ነው። እኔ መነሻ እስካለኝ ድረስ የእኔ ባሕርይ ጅማሬ አለው፥ አላህ ግን ጅማሬ ስለሌለው የእርሱ ባሕርይ ፍጥረታዊ ሳይሆን መለኮታዊ፤ ሰዋዊ ሳይሆን አምላካዊ ነው። እርሱ ከፍጥረት “ተብቃቂ” ነው፦
35፥15 እናንተ ሰዎች ሆይ! እናንተ ሁል ጊዜ ወደ አላህ ከጃዮች ናችሁ፡፡ *አላህም እርሱ “ተብቃቂው” ምስጉኑ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ أَنتُمُ الْفُقَرَاءُ إِلَى اللَّهِ ۖ وَاللَّهُ هُوَ الْغَنِيُّ الْحَمِيدُ

አላህ የማወቅ፣ የማፍቀር፣ የመስማት፣ የማየት ባሕርይ አለው፥ ይህ ባሕርይ መንስኤ የለውም። እኔ ለማወቅ የሚታወቅ ማንነትና ምንነት፣ ለማፍቀር የሚፈቀር ማንነትና ምንነት፣ ለመስማት የሚናገር ማንነትና ምንነት፣ ለማየት የሚታይ ማንነትና ምንነት ያስፈልገኛል። አላህ ግን ፍጥረት ሳይኖር ዐዋቂ፣ አፍቃሪ፣ ሰሚ፣ ተመልካች ነው። የእርሱ ባሕርይ ከማንም ከምንም ጋር አይመሳሰልም፦
42፥11 *”የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው”*፡፡ لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ ۖ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ

"ምንም ነገር" የሚለው ይሰመርበት። አላህ ለመስማት እና ለማየት ጊዜና ቦታ አይገድበውም። እኔ ለማየት ብርሃን ያስፈልገኛል፥ በጨለማ ውስጥ ያለውን ማየት አልችልም። አላህ ግን ለማየት ብርሃን አያስፈልገውም፥ በጨለማ ውስጥ ያለውን ያያል። እኔ ለመስማት ሞገድ ያስፈልገኛል። አላህ ግን ለመስማት ሞገድ አያስፈልገውም፥ በአንድ ጊዜ ሁሉንም ነገር መስማት ይችላል። ሰው "ሰሚዕ" سَّمِيع ማለትም "ሰሚ" እና "በሲር" بَصِير ማለትም "ተመልካች" ተብሏል፦
76፥2 እኛ ሰዉን በሕግ ግዳጅ የምንፈትነው ስንሆን ቅልቅሎች ከሆኑ የፍትወት ጠብታ ፈጠርነዉ፥ *"ሰሚ ተመልካችም አደረግነዉ"*። إِنَّا خَلَقْنَا الْإِنسَانَ مِن نُّطْفَةٍ أَمْشَاجٍ نَّبْتَلِيهِ فَجَعَلْنَاهُ سَمِيعًا بَصِيرًا

ሰው ሰሚ እና ተመልካች የተባለበት አላህ ሰሚ እና ተመልካች በተባለበት ስሌትና ቀመር እንዳልሆነ ከተረዳን ዘንዳ፥ ሰው ዐዋቂ እና አፍቃሪ የተባለው አላህ ዐዋቂ እና አፍቃሪ በተባለበት መልክና ልክ አይደለም። ሰው አፍቃሪ ለመባል ተፈቃሪ ነገር ያስፈልገዋል፥ ዐዋቂ ለመባል ታዋቂ ነገር ያስፈልገዋል። አላህ ግን ምንም ፍጥረት ሳይኖር በባሕርይ ያለ ታዋቂ ዐዋቂ፣ ያለ ተፈቃሪ አፍቃሪ፣ ያለ ተፈጣሪ ፈጣሪ ነው።
በእርሱ ባሕርይ "ነው" እንጂ "ሆነ" አይባልም። "ሆነ" ጅማሬ ላለው ነገር ነው፥ ፈጣሪ ሆነ፣ ዐዋቂ ሆነ፣ አፍቃሪ ሆነ አይባልም። እርሱ የሚያስሆን እንጂ የሚሆን አይደለም፥ የሚያደርግ እንጂ የሚደረግ አይደለም። የእርሱ ዐዋቂነት፣ አፍቃሪነት፣ ፈጣሪነት መነሻ መዳረሻ የሌለው ከፍጡራን ጋር የማይመሳሰል ባሕርይ ነው። እርሱ እስካለ ድረስ የእርሱ ዐዋቂነት፣ አፍቃሪነት፣ ፈጣሪነት ከፍጥረት በፊት ነበረ። ያለ ፍጥረት ፈጣሪ የለም ካልን ከፍጥረት በፊት እግዚአብሔር አማንያንን መርጧል፥ ያውቃቸው ነበር" ማለት ትርጉም አይኖረውም፦
ኤፌሶን 1፥4 *"ዓለም ሳይፈጠር በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን"*።
1 ጴጥሮስ 1፥20 *"ዓለም ሳይፈጠር እንኳ አስቀድሞ ታወቀ"*፥

ያለ ተመራጭ መራጭ፥ ያለ ዐዋቂ ታዋቂ እንዴት ይኖራል? እኔ የሚመረጥ ነገር ሳይኖር መምረጥ ስለማልችልና የሚታወቅ ነገር ሳኖር ማወቅ ስለማልችል እግዚአብሔር የሚመረጥ ነገር ሳይኖር እንዴት ከፍጥረት በፊት መረጠ? የሚታወቅ ነገር ሳኖር እንዴት ዐወቀ? ምን ነካህ ወሒድ "የፈጣሪ ባሕርይ ከፍጡራን ጋር አይመሳሰልም" ከሆነ መልሱ እንግዲያውስ አላህ ከፍጥረት በፊት አፍቃሪ ለመባል ተፈቃሪ ነገር መኖር መስፈርት አይደለም። አይ "ሦስቱ አካላት እግዚአብሔር አብ፣ እግዚአብሔር ወልድ፣ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እርሱ በእርሳቸው ይፋቀሩ ስለነበር ነው" ካላችሁ ፈጣሪ ከጊዜ በኃላ የተገኘ ባሕርይ ከሌለው ይቅርባይቱ እና ፈጣሪነቱ አብሮት ከነበረ የሥላሴ አባላት እርስ በርሳቸው ይቅር ሲባባሉ እና ሲፈጣጠሩ ነው የኖሩት? እግዚአብሔር ዓለም ሳይፈጠር ንጉሥ ነበር፦
መዝሙር 74፥12 *"እግዚአብሔር ግን ከዓለም አስቀድሞ ንጉሥ ነው"*።

በማን ላይ ንጉሥ ነበር? አንደኛው እግዚአብሔር አብ በሌሎች እግዚአብሔር ላይ ነግሦባቸው ነበረን? ተነጋሽ ሳይኖር ነጋሽ አይታሰብም ከተባል ማለት ነው። ይህ አለሌ ጥያቄ መጽሐፍትን ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ስላልሆነ ስሁት ሙግት ነው። ፍልስፍና የተቆላ ገብስ ነው፤ ሲበሉት ይጣፍጣል፥ ግን ሲዘሩት አይበቅልም። ይህ ፍልስፍና ተገልብጦ እራሳቸውን እስር ቤት የሚከታቸው ጥያቄ ነው። አላህ ሂዳያህ ይስጣቸው፥ ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ስድብ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

49፥11 *"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ወንዶች ከወንዶች አይቀልዱ፡፡ ከእነርሱ የበለጡ ሊኾኑ ይከጀላልና፡፡ ሴቶችም ከሴቶች አይሳለቁ፡፡ ከእነርሱ የበለጡ ሊኾኑ ይከጀላልና፡፡ እራሳችሁንም አታነውሩ፡፡ በመጥፎ ስሞችም አትጠራሩ፡፡ ከእምነት በኋላ የማመጽ ስም ከፋ፡፡ ያልተጸጸተም ሰው እነዚያ እነርሱ በዳዮቹ ናቸው"*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا يَسْخَرْ قَوْمٌ مِّن قَوْمٍ عَسَىٰ أَن يَكُونُوا خَيْرًا مِّنْهُمْ وَلَا نِسَاءٌ مِّن نِّسَاءٍ عَسَىٰ أَن يَكُنَّ خَيْرًا مِّنْهُنَّ ۖ وَلَا تَلْمِزُوا أَنفُسَكُمْ وَلَا تَنَابَزُوا بِالْأَلْقَابِ ۖ بِئْسَ الِاسْمُ الْفُسُوقُ بَعْدَ الْإِيمَانِ ۚ وَمَن لَّمْ يَتُبْ فَأُولَـٰئِكَ هُمُ الظَّالِمُونَ

“በደል” ሦስት አይነት ነው፥ እርሱም፦ አላህን መበደል፣ ሰውን መበደል እና እራስን መበደል ነው። ሰውን መበደል ማንኛውም ሰው ሌላው ላይ የሚያደርሰው በደል ነው። ሰውን መበደል ማለት የሰው ሐቅ መንካት ነው፥ የሰው ሐቅ ተነክቶ የሚመለሰው በካሳ ወይም በይቅርታ ብቻ ነው። “ከፋራህ” كَفّارَة ማለት “ካሳ” መክፈል ማለት ሲሆን “ዐፉው” عَفُوّ ማለት ደግሞ “ይቅርታ” ማለት ነው። የበደልነውን ሰው በካሳ ወይም በይቅርታ ሐቁን ካልመለስን የትንሳኤ ቀን በአላህ ዘንድ ያስጠይቀናል። ሰውን መዝረፍ፣ ማማት፣ መስደብ፣ መማታት፣ መግደል ሰውን መበደል ነው። ዛሬ የምናየው ነጥብ ስለ ስድብ ነው፥ አምላካችን አላህ፦ "እራሳችሁንም አታነውሩ፡፡ በመጥፎ ስሞችም አትጠራሩ፡፡ ከእምነት በኋላ የማመጽ ስም ከፋ፡፡ ያልተጸጸተም ሰው እነዚያ እነርሱ በዳዮቹ ናቸው" ይለናል፦
49፥11 *"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ወንዶች ከወንዶች አይቀልዱ፡፡ ከእነርሱ የበለጡ ሊኾኑ ይከጀላልና፡፡ ሴቶችም ከሴቶች አይሳለቁ፡፡ ከእነርሱ የበለጡ ሊኾኑ ይከጀላልና፡፡ እራሳችሁንም አታነውሩ፡፡ በመጥፎ ስሞችም አትጠራሩ፡፡ ከእምነት በኋላ የማመጽ ስም ከፋ፡፡ ያልተጸጸተም ሰው እነዚያ እነርሱ በዳዮቹ ናቸው"*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا يَسْخَرْ قَوْمٌ مِّن قَوْمٍ عَسَىٰ أَن يَكُونُوا خَيْرًا مِّنْهُمْ وَلَا نِسَاءٌ مِّن نِّسَاءٍ عَسَىٰ أَن يَكُنَّ خَيْرًا مِّنْهُنَّ ۖ وَلَا تَلْمِزُوا أَنفُسَكُمْ وَلَا تَنَابَزُوا بِالْأَلْقَابِ ۖ بِئْسَ الِاسْمُ الْفُسُوقُ بَعْدَ الْإِيمَانِ ۚ وَمَن لَّمْ يَتُبْ فَأُولَـٰئِكَ هُمُ الظَّالِمُونَ

"ቀውም" قَوْم ማለት "ሕዝብ" ማለት ነው፥ አንደኛው ሕዝብ በሌላ ሕዝብ ላይ መቀለድ ሐራም ነው። ለምሳሌ የኦሮሞ ሕዝብ በአማራ ሕዝብ፥ የአማራ ሕዝብ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ማለት ነው። አንደኛዋ ሴት በሌላ ሴት ላይ መሳለቅ ሐራም ነው። ቀልድና ስላቅ የስድብ አይነቶች ናቸው። "እራሳችሁን አታነውሩ" ማለት "እርስ በእርሳችሁ አትዘላለፉ" ማለት ነው፥ ትልቁ ነውር ስድብ ነው። በስድብ ሰው ማነወር ሐራም ነው፥ ማበሻቀጥ ሆነ ማብጠልጠል አሊያም መዝለፍ የስድብ አይነት ነው። "አታነውሩ" ለሚለው ቃል የገባው "ላ ተልሚዙ" لَا تَلْمِزُو ሲሆን "አትዝለፉ" ማለት ነው፥ "ሉመዛህ" لُّمَزَة ማለት በራሱ "ዘላፊ" "ተሳዳቢ" "አነዋሪ" ማለት ነው፦
104፥1 *"ለሃሜተኛ ለዘላፊ ሁሉ ወዮለት"*፡፡ وَيْلٌ لِّكُلِّ هُمَزَةٍ لُّمَزَةٍ
68፥11*"ሰውን አነዋሪን እና በማሳበቅ ኼያጅን አትታዘዝ"*፡፡ هَمَّازٍ مَّشَّاءٍ بِنَمِيمٍ

"አልቃብ" أَلْقَٰب ማለት "እኩይ ስም" ማለት ነው፥ በዚህ የመበሻሸቂያ ስም መጠራራት ከእምነት በኋላ የማመጽ ስም ነው፡፡ "በመጥፎ ስሞችም አትጠራሩ" የሚለው አንቀጽ የወረደበት ምክንያት ይህ ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3578
አቢ ጀቢራህ ኢብኑ አድ-ደሓክ እንደተረከው፦ *"አንድ ሰው ከመካከላችን በሁለት ወይም በሦስት ስም ይታወቃል፥ እርሱም ከሚጠላው በአንዱ ስም ተጠራ። ከዚያም፦ "በመጥፎ ስሞችም አትጠራሩ" የሚለው አንቀጽ ወረደ"*። يُحَدِّثُ عَنْ أَبِي جَبِيرَةَ بْنِ الضَّحَّاكِ، قَالَ كَانَ الرَّجُلُ مِنَّا يَكُونُ لَهُ الاِسْمَيْنِ وَالثَّلاَثَةَ فَيُدْعَى بِبَعْضِهَا فَعَسَى أَنْ يَكْرَهَ قَالَ فَنَزَلَتْ هَذِهِ الآيَةُ ‏(‏ وَلاَ تَنَابَزُوا بِالأَلْقَابِ ‏)‏ ‏.‏

"መጥፎ ስም" ማለት ሰውዬው ቢጠራበት ደስ የማይለው እና ስሜቱ የሚጎዳበት ስም ነው። በእኩይ ስም ሰውን የሚጠራ እና በዚህ ድርጊቱ ያልተጸጸተም ሰው በደለኛ ነው። ይህ ሥራው ዓመፅ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 41
ዐብደሏህ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ሙሥሊምን መሳደብ ፉሡቅ ነው፥ መግደል ደግሞ ኩፍር ነው"*። فَقَالَ حَدَّثَنِي عَبْدُ اللَّهِ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ سِبَابُ الْمُسْلِمِ فُسُوقٌ، وَقِتَالُهُ كُفْرٌ
"ፉሡቅ" فُسُوق ወይም ፊሥቅ" فِسْق የሚለው ቃል "ፈሠቀ" فَسَقَ ማለትም "ዓመፀ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ዓመፅ" ማለት ነው። አምላካችን አላህ በቁርኣኑ "እራሳችሁን አታነውሩ" ሲለን፥ ነቢያችን"ﷺ" ደግሞ "ሙሥሊምን መሳደብ ፉሡቅ ነው" ብለውናል። እርስ በእርስ መዘላለፍ ከተጀመረ ቀጣዩ ደረጃ እርስ በእርስ መገዳደል ነው፦
4፥29 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ገንዘቦቻችሁን በመካከላችሁ ያለ አግባብ አትብሉ፡፡ ግን ከእናንተ በመዋደድ የኾነችውን ንግድ ብሉ፡፡ *”እራሳችሁንም አትግደሉ”*፡፡ አላህ ለእናንተ አዛኝ ነውና፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَأْكُلُوا أَمْوَالَكُم بَيْنَكُم بِالْبَاطِلِ إِلَّا أَن تَكُونَ تِجَارَةً عَن تَرَاضٍ مِّنكُمْ ۚ وَلَا تَقْتُلُوا أَنفُسَكُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ كَانَ بِكُمْ رَحِيمًا

"እራሳችሁንም አትግደሉ" ማለት "እርስ በእርሳችሁ አትገዳደሉ" ማለት ነው። ይህ ደግሞ ከዓመፅ ወደ ክህደት ያመራል፥ ለዛ ነው ነቢያችን"ﷺ" "ሙሥሊምን መግደል ደግሞ ኩፍር ነው" ያሉት። በግል ደረጃ እንኳን እራስን ለመግደል መንስኤው እራስን ማነወር ነው። ሰው ራሱ ስለ ራሱ ጥሩ ካልተሰማው እራሱን ዝቅ አድርጎ ማነወር ይጀምራል፥ ይህ ሂደት ስር ሲሰድ እራስን ወደ መግደል እርምጃና ደረጃ ይደርሳል። ወደተነሳንበት ነጥብ ስንመለስ ስድብ ፈሳዱ ይህን ያክል አደገኛ ነው ማለት ነው፥ የራሳችን እምነት እንዳይሰደብ ከፈለግን የሌላውን እምነት መሳደብ የለብንም፦
6፥108 *"እነዚያንም ከአላህ ሌላ የሚገዙዋቸውን አትሳደቡ፡፡ ድንበርን በማለፍ ያለዕውቀት አላህን ይሳደባሉና"*፡፡ وَلَا تَسُبُّوا الَّذِينَ يَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ فَيَسُبُّوا اللَّهَ عَدْوًا بِغَيْرِ عِلْمٍ

ጣዖታውያን ከአላህ ሌላ የሚጠሯቸውን ማንነት ሆነ ምንነት ከዘለፍን እነርሱም ድንበርን በማለፍ ያለዕውቀት አላህን ይሳደባሉና። የሌላውን እምነት መዝለፍ እራሱ የሌላ ሰው ሐቅ መንካት ስለሆነ በደል ነው። ስድብ አሳብን በተሻለ አሳብ ማሸነፍ ሲያቅተን የምንጠቀምበት ዱላ ነው። ይህ ጽርፈት ሥር ከሰደደ የመግደል ስሜት ይፈጥራል። አላህ ከጽርፈት ይጠብቀን፥ ለሁላችንም ሂዳያህ ይስጠን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
መልካም ንግግር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

2፥263 *መልካም ንግግር እና ምሕረት ማድረግ ማስከፋት ከሚከተላት ምጽዋት በላጭ ነው*፡፡ አላህም ተብቃቂ ታጋሽ ነው፡፡ قَوْلٌ مَّعْرُوفٌ وَمَغْفِرَةٌ خَيْرٌ مِّن صَدَقَةٍ يَتْبَعُهَا أَذًى ۗ وَاللَّهُ غَنِيٌّ حَلِيمٌ

ከሥነ-ምግባር እሴት አንዱ መልካም ቃልን መናገር ነው፤ ሰይጣን መልካም ቃል በማይናገሩት በመካከላቸው ያበላሻል፤ አላህ መልካምን ቃልን ፍሬ በምትሰጥ መልካም ዛፍ ሲመስላት ክፉ ቃልን ደግሞ ፍሬ በማይሰጥ ክፉ ዛፍ ይመስለዋል፦
17፥53 ለባሮቼም በላቸው፦ ያችን እርሷ *“መልካም የሆነችውን ቃል ይናገሩ”፤ ሰይጣን በመካከላቸው ያበላሻልና*፤ ሰይጣን ለሰው ግልጽ ጠላት ነውና። وَقُل لِّعِبَادِى يَقُولُوا۟ ٱلَّتِى هِىَ أَحْسَنُ ۚ إِنَّ ٱلشَّيْطَٰنَ يَنزَغُ بَيْنَهُمْ ۚ إِنَّ ٱلشَّيْطَٰنَ كَانَ لِلْإِنسَٰنِ عَدُوًّۭا مُّبِينًۭا
14፥24 *አላህ መልካምን ቃል ሥርዋ በምድር ውስጥ የተደላደለች ቅርንጫፍዋም ወደ ሰማይ የረዘመች እንደሆነች መልካም ዛፍ አድርጎ ምሳሌን እንዴት እንደገለጸ አላየኽምን?* أَلَمْ تَرَ كَيْفَ ضَرَبَ اللَّهُ مَثَلًا كَلِمَةً طَيِّبَةً كَشَجَرَةٍ طَيِّبَةٍ أَصْلُهَا ثَابِتٌ وَفَرْعُهَا فِي السَّمَاءِ
14፥25 *ፍሬዋን በጌታዋ ፈቃድ በየጊዜው ትሰጣለች፡፡ አላህም ለሰዎች ይገሰጹ ዘንድ ምሳሌዎችን ይገልጻል*፡፡ تُؤْتِي أُكُلَهَا كُلَّ حِينٍ بِإِذْنِ رَبِّهَا ۗ وَيَضْرِبُ اللَّهُ الْأَمْثَالَ لِلنَّاسِ لَعَلَّهُمْ يَتَذَكَّرُونَ
14፥26 *የመጥፎም ቃል ምሳሌ ከምድር በላይ የተጎለሰሰች ለእርሷ ምንም መደላደል የሌላት እንደኾነች መጥፎ ዛፍ ነው*፡፡ وَمَثَلُ كَلِمَةٍ خَبِيثَةٍ كَشَجَرَةٍ خَبِيثَةٍ اجْتُثَّتْ مِن فَوْقِ الْأَرْضِ مَا لَهَا مِن قَرَارٍ
22፥24 *ከንግግርም ወደ መልካሙ ተመሩ*፡፡ ወደ ምስጉንም መንገድ ተመሩ፡፡ وَهُدُوا إِلَى الطَّيِّبِ مِنَ الْقَوْلِ وَهُدُوا إِلَىٰ صِرَاطِ الْحَمِيدِ

ምእመናን ከውድቅ ንግግር ራቂዎች ናቸው፤ መልካም ንግግር ማስከፋት ከሚከተላት ምጽዋት በላጭ ነው፦
23፥3 *እነዚያም እነርሱ ከውድቅ ንግግር ራቂዎች*፡፡ وَالَّذِينَ هُمْ عَنِ اللَّغْوِ مُعْرِضُونَ
2፥263 *መልካም ንግግር እና ምሕረት ማድረግ ማስከፋት ከሚከተላት ምጽዋት በላጭ ነው*፡፡ አላህም ተብቃቂ ታጋሽ ነው፡፡ قَوْلٌ مَّعْرُوفٌ وَمَغْفِرَةٌ خَيْرٌ مِّن صَدَقَةٍ يَتْبَعُهَا أَذًى ۗ وَاللَّهُ غَنِيٌّ حَلِيمٌ
35፥10 ማሸነፍን የሚፈልግ የኾነ ሰው አሸናፊነት ለአላህ ብቻ ነው፤ ማሸነፍን በመግገዛት ይፈልገው፡፡ *መልካም ንግግር ወደ እርሱ ይወጣል*፤ በጎ ሥራም ከፍ ያደርገዋል፡፡ مَن كَانَ يُرِيدُ الْعِزَّةَ فَلِلَّهِ الْعِزَّةُ جَمِيعًا ۚ إِلَيْهِ يَصْعَدُ الْكَلِمُ الطَّيِّبُ وَالْعَمَلُ الصَّالِحُ يَرْفَعُه

ነቢያችንም”ﷺ” በቅዱስ ንግግራቸው፦ “በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የሚያምን መልካም ይናገር አሊያም ዝም ይበል” ብለዋል፤ በተጨማሪም “መልካም ንግግር ሰደቃ ነው” ብለዋል፦
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 36, ሐዲስ 46
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ *”የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ “በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የሚያምን መልካም ይናገር አሊያም ዝም ይበል*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ “‏ مَنْ كَانَ يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الآخِرِ فَلْيَقُلْ خَيْرًا أَوْ لِيَسْكُتْ ‏”
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 12, ሐዲስ 72
አቢ ሀረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ ሰደቃህ በእያንዳንዱ የጸሐይ መውጫ ቀን በእያንዳንዱ የሰው መገጣጠሚያ ግዴታ ነው፤ በሁለት ወገን ፍትሕ ማድረግ ሰደቃ ነው፤ በእንስሳ ላይ የሚጋልብን ማማከር ወይም ሊጭን ሲል መርዳት ሰደቃ ነው፤ *”መልካም ንግግር ሰደቃ ነው”*፤ ወደ ሶላት ማንኛውም እርምጃ ማድረግ ሰደቃ ነው፤ ከመንገድ ላይ እኩይ ነገር ማስወገድ ሰደቃ ነው። وَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ كُلُّ سُلاَمَى مِنَ النَّاسِ عَلَيْهِ صَدَقَةٌ كُلَّ يَوْمٍ تَطْلُعُ فِيهِ الشَّمْسُ – قَالَ – تَعْدِلُ بَيْنَ الاِثْنَيْنِ صَدَقَةٌ وَتُعِينُ الرَّجُلَ فِي دَابَّتِهِ فَتَحْمِلُهُ عَلَيْهَا أَوْ تَرْفَعُ لَهُ عَلَيْهَا مَتَاعَهُ صَدَقَةٌ – قَالَ – وَالْكَلِمَةُ الطَّيِّبَةُ صَدَقَةٌ وَكُلُّ خَطْوَةٍ تَمْشِيهَا إِلَى الصَّلاَةِ صَدَقَةٌ وَتُمِيطُ الأَذَى عَنِ الطَّرِيقِ صَدَقَةٌ ‏

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ቅዱስ ቁርኣን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

56፥77 እርሱ *የከበረ* ቁርኣን ነው። إِنَّهُۥ لَقُرْءَانٌۭ كَرِيمٌۭ

ቅዱስ ቁርኣን የምንልበት ምክንያት ቁርኣን "ከሪም" ስለተባለ ነው፤ "ከሪም" كَرِيم የሚለው ቃል "ቅዱስ" "ክቡር" "ብፁዕ" "ንኡድ" "ውዱስ" "ስቡህ" "እኩት" "እጹብ" የሚል ፍቺ አለው፦
56፥77 እርሱ *የከበረ* ቁርኣን ነው። إِنَّهُۥ لَقُرْءَانٌۭ كَرِيمٌۭ

"መጽሐፍ ቅዱስ" ማለት "ቅዱስ መጽሐፍ" ማለት ነው፤ የፈጣሪ ንግግር ብቻ ነው ቅዱስ እንጂ የሰው ንግግር ቅዱስ አይደለም። ባይብል የሰው ንግግር ስላለበት ቅዱስ መጽሐፍ አይባልም። ስለዚህ ባይብልን "መጽሐፍ ቅዱስ" በማለት ፋንታ "ባይብል" በሉት፤ "ባይብል" የሚለው የኢንግሊሹ ቃል "ቢብሊያ" βιβλία ከሚል የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙ "ጥቅሎች"scrolls" ማለት ነው፣ በነጠላ ደግሞ "ቢብሊኦን" βιβλίον ሲሆን "ጥቅል"scroll" ማለት ነው። ይህ ቃል ለማንኛውም መጽሐፍ ቃሉ ያገለግላል። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ቁርኣን ብቻ ነው፤ ምክንያቱም የቁርኣን ተናጋሪ ፈጣሪ ብቻ ስለሆነ ማለት ነው፤ በእግጥም ቁርኣን "ቅዱስ" "ክቡር" "ብፁዕ" "ንኡድ" "ውዱስ" "ስቡህ" "እኩት" "እጹብ" ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ነቢያችን"ﷺ" አይመለኩም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

48፥9 *"በአላህ እና በመልክተኛውም ልታምኑ፣ ልትረዱትም፣ ልታከብሩትም። አላህን በጧትና ከቀትር በኋላ ልታወድሱትም ላክነው"*፡፡ لِّتُؤْمِنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ وَتُعَزِّرُوهُ وَتُوَقِّرُوهُ وَتُسَبِّحُوهُ بُكْرَةً وَأَصِيلًا

በክርስትና የቀጥታ አምልኮ የሚያመልኩት ሦስት አካላትን እና የኢየሱስን ሰውነት ሲሆን፥ የተዛዋዋሪ አምልኮ የሚያመልኩት ደግሞ ቅዱሳን ሰዎችን እና ቅዱሳን መላእክትን ነው። ይህንን ግሳንግስ የአምልኮ እሳቤ ለመሸፈን፦ "እናንተ ሙሥሊሞች ነቢያችሁን ታመልካላችሁ" ብለው አረፉት። እዚህ ድምዳሜ ላይ አደረሰን ያሉትን አንቀጽ ጥልልና ጥንፍፍ አርገን እስቲ እንመልከት። ነቢያችን"ﷺ" የተላኩበት ዓላማ በአላህ አምላክነት እና በእርሳቸው ነቢይነት እንድናምን፣ እርሳቸውን ልንረዳና ልናከብር፣ አላህን በጧትና ከቀትር በኋላ እንድናወድሰው ነው፦
48፥9 *"በአላህ እና በመልክተኛውም ልታምኑ፣ ልትረዱትም፣ ልታከብሩትም። አላህን በጧትና ከቀትር በኋላ ልታወድሱትም ላክነው"*፡፡ لِّتُؤْمِنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ وَتُعَزِّرُوهُ وَتُوَقِّرُوهُ وَتُسَبِّحُوهُ بُكْرَةً وَأَصِيلًا

አላህ አንድ አምላክ እንደሆነ፥ ከእርሱም በቀር አምላክ እንደሌለ ማመን እና ነቢያችን"ﷺ" ከእርሱ የተላኩ መልእክተኛ መሆናቸውን ማመን ፈርድ ነው፦
48፥13 *"በአላህ እና በመልክተኛው ያላመነም ሰው እኛ ለከሓዲዎች እሳትን አዘጋጅተናል"*፡፡ وَمَن لَّمْ يُؤْمِن بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ فَإِنَّا أَعْتَدْنَا لِلْكَافِرِينَ سَعِيرًا

"ቱዐዘሩ" تُعَزِّرُو ማለት "ልትረዱ" ማለት ሲሆን "ቱዐዘሩ" تُعَزِّرُو በሚል ግስ ላይ "ሁ" هُ ማለትም "እርሱ" የሚል ተሳቢ ተውላጠ-ስም ነቢያችንን"ﷺ" ለማመልከት የገባ ነው፥ በተመሳሳይም "ቱወቀሩ" تُوَقِّرُو ማለት "ልታከብሩ" ማለት ሲሆን "ቱወቀሩ" تُوَقِّرُو በሚል ግስ ላይ "ሁ" هُ ማለትም "እርሱ" የሚል ተሳቢ ተውላጠ-ስም ነቢያችንን"ﷺ" ለማመልከት የገባ ነው። መርዳትና ማክበር በሌላ አንቀጽም ለነቢያችን"ﷺ" አገልግሎት ላይ ውሏል፦
7፥157 እነዚያም በእርሱ ያመኑ *"ያከበሩትም የረዱትም"* ያንንም ከእርሱ ጋር የተወረደውን ብርሃን የተከተሉ እነዚያ እነሱ የሚያድኑ ናቸው፡፡ فَالَّذِينَ آمَنُوا بِهِ وَعَزَّرُوهُ وَنَصَرُوهُ وَاتَّبَعُوا النُّورَ الَّذِي أُنزِلَ مَعَهُ ۙ أُولَـٰئِكَ هُمُ الْمُفْلِحُونَ

ቀጥሎ "ቱሠበሑሁ" تُسَبِّحُوهُ ማለት ግን "ልታጠሩት" ማለት ነው። “ሡብሓን” سُبْحَٰن የሚለው ቃል “ሠበሐ” سَبَّحَ ማለትም “አመሰገነ” ወይም “አጠራ” “አወደሰ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማህሌት” “ውዳሴ” “ስብሐት” ማለት ነው፥ “ተሥቢሕ” تَسْبِيح ማለት ደግሞ “ተስብሖት” ማለት ነው። በጧት በምናነጋ ጊዜ እና ከቀትር በኋላ በምናመሽ ጊዜ ተሥቢሕ የምናቀርበው ለአላህ ብቻ ነው፦
33፥42 *በቀኑ መጀመሪያና መጨረሻም አጥሩት*፡፡ وَسَبِّحُوهُ بُكْرَةً وَأَصِيلًا
30፥17 አላህንም በምታመሹ ጊዜ በምታነጉም ጊዜ አጥሩት”*፡፡ فَسُبْحَانَ اللَّهِ حِينَ تُمْسُونَ وَحِينَ تُصْبِحُونَ

"ሁ" هُ ማለትም "እርሱ" የሚለው ተውላጠ-ስም 48፥9 የአንቀጹ መነሻ ላይ "አላህ" اللَّه የሚለውን ስም ተክቶ የመጣ ነው፥ በተጨማሪም 30፥17 ላይ የምናጠራው አላህን እንደሆነ ተናግሯል። “አጥሩ” ለሚለው ቃል የገባው “ሡብሓነ” سُبْحَانَ ሲሆን ለአላህ የምናቀርበው ስብሐት ከላይ አንቀጹ ላይ እንደተቀመጠው “ሡብሓነ አሏህ” سُبْحَانَ اللَّه ነው። ስለዚህ "በጧትና ከቀትር በኋላ ልታወድሱትም" የተባለው ነቢያችን"ﷺ" ሳይሆኑ አላህ ነው። ምክንያቱም ተሥቢሕ እራሱ አምልኮ ነው፥ ነቢያችን"ﷺ" ደግሞ ይከበራሉ እንጂ አይመለኩም። "ቱሠበሑሁ" تُسَبِّحُوهُ የተባለው አላህ እንደሆነ የነቢያችን"ﷺ" ዘመድ እና ባልደረባ ኢብኑ ዐባሥ"ረ.ዐ." ተናግሯል፦
ተፍሢሩል ኢብኑ ዐባሥ ሱረቱል ፈትሕ 48፥9
*"ልታጠሩትም" ማለት "አላህ ልታጠሩት" ማለት ነው፥ "በጧትና ከቀትር በኋላ" ማለት "ጠዋትና ማታ" ማለት ነው"*።
{ وتسبحوه} أي تسبحون اللّه، { بكرة وأصيلاً} أي أول النهار وآخره،

አላህ እራሱ ነቢያችንን"ﷺ" "ሠበሕ" سَبِّح ማለትም "አሞግስ" ይላቸዋል፥ የሚሞገሰው ደግሞ ከሁሉ በላይ የኾነውን ጌታ ብቻ ነው። ሙሥሊሞች አላህ ስሙ እንዲወሳ ባዘዘው ቤቶች ውስጥ በጧት እና በማታ ለእርሱ ያጠራሉ፥ በአላህ ቤቶች በመስጊዶችም ውስጥ ከአላህ ጋር አንድንም ማንነትና ምንነት አይገዙም፦
87፥1 *"ከሁሉ በላይ የኾነውን ጌታህን ስም አሞግሥ"*፡፡ سَبِّحِ اسْمَ رَبِّكَ الْأَعْلَى
24፥36 *"አላህ እንድትከበር እና ስሙ በውስጧ እንዲወሳ ባዘዘው ቤቶች ውስጥ አወድሱት፡፡ በውስጧ በጧት እና በማታ ለእርሱ ያጠራሉ"*፡፡ فِي بُيُوتٍ أَذِنَ اللَّهُ أَن تُرْفَعَ وَيُذْكَرَ فِيهَا اسْمُهُ يُسَبِّحُ لَهُ فِيهَا بِالْغُدُوِّ وَالْآصَالِ
72፥18 *"እነሆ መስጊዶችም የአላህ ብቻ ናቸው፡፡ በውስጣቸው ከአላህ ጋር አንድንም አትገዙ" ማለትን ተወረደለኝ"*፡፡ وَأَنَّ الْمَسَاجِدَ لِلَّهِ فَلَا تَدْعُوا مَعَ اللَّهِ أَحَدًا

ስለዚህ "ሙሥሊሞች ነቢያችሁን ታመልካላችሁ" የሚለው ግንዛቤ ቁርኣኑን በትክክል ካለመረዳት እና ዳተኛና ቸልተኛ ከመሆን የሚመጣ የተውረገረገ፣ የተንሸዋረረ፣ የደፈረሰ፣ የተሳከረ ስሑት ግንባቤ ነው። ከጸለምተኛ ግንዛቤ ወጥታችሁ አብርኆተኛ እንድትሆኑ አላህ ይርዳችሁ! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዘረኝነት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

30፥22 ሰማያትንና ምድርንም መፍጠሩ፣ *የቋንቋዎቻችሁ እና የመልኮቻችሁም መለያየት ከአስደናቂ ታምራቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለዐዋቂዎች ተዓምራቶች አሉበት*፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ خَلْقُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَاخْتِلَافُ أَلْسِنَتِكُمْ وَأَلْوَانِكُمْ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّلْعَالِمِينَ

“ዘረኝነት”racism” ማለት የራስን ቋንቋና ዘውግ አተልቆ የሌላውን ማሳነስ፣ ማግለል፣ መቃረን እና ማራከስ ነው። ዘረኝነት ትዳርን፣ ቤተሰብን፣ ጉርብትናን፣ ማህበረሰብን፣ ሃይማኖት፣ መንግሥትን፣ አገርን የሚበትን ክፉ በሽታ ነው። ዘረኝነት፣ ጎጠኝነት፣ ጠርዘኝነት፣ ቡድንተኝነት ምንጫቸው “ዝንባሌ”inclination” ነው። እኛ ሁላችንም የአንድ አባት የአደም፥ የአንድ እናት የሐዋ ልጆች ነን። ታዲያ የአንድ እናት እና አባት ልጆች ከሆንን አንዱን ዘር ማብለጥ ሌላውን ማሳነስ ጠባብነት አይደለምን? አማራ፣ ኦሮሞ፣ ጉራጌ፣ ትግሬ ወዘተ ቋንቋ ነው፤ የቋንቋዎቻችን መለያየት ከአስደናቂ ታምራቶቹ ነው፤ በዚህ ውስጥ ለዐዋቂዎች ተዓምራቶች አሉበት፦
30፥22 ሰማያትንና ምድርንም መፍጠሩ፣ *የቋንቋዎቻችሁ እና የመልኮቻችሁም መለያየት ከአስደናቂ ታምራቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለዐዋቂዎች ተዓምራቶች አሉበት*፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ خَلْقُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَاخْتِلَافُ أَلْسِنَتِكُمْ وَأَلْوَانِكُمْ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّلْعَالِمِينَ

ቋንቋዎች ይዘውት የመጡት ታሪክ፣ ባህል፣ ልማድ፣ ትውፊት፣ ወግ፣ ክህሎት እና ሙዳየ-ቃላት “ዘውግ” ethnic” ሆኗል፤ ይህ እራሱ የቻለ ውበት ነው። ዘረኝነት ግን ከቋንቋ አሊያም ከቀለም የሚመጣ ሳይሆን የልብና የአስተሳሰብ በሽታ ነው። የቋንቋዎቻችሁ እና የመልኮቻችሁም መለያየት ከአስደናቂ ታምራቶቹ እንጂ መኩሪያ ወይም ማብጠልጠሊያ አይደለም፤ ዘረኝነት በዲንያ በአላህ ዘንድ ዋጋ የሚያሳጣ ሲሆን በአኺራም ደግሞ ለጀሃነም ይዳርጋል፦
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 344
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ *”አላህ ዐዘ ወጀል ከእናንተ የዘመነ-ጃሂሊያን ኩራት አስወግዷል፤ ይህም በዘር መኩራት ነው። ይህ ለጥንቁቁ አማኝም ወይም ለአደገኛው ካሃዲ አንድ ብቻ ነው። እናንተ የአደም ልጆች ናችሁ፤ አደም ከአፈር ነው የመጣው፤ ሰዎች በዘራቸው የሚኮሩ ከሆነ ጀሃነምን ይሞሏታል፤ ወይም አላህ ዘንድ ዋጋቸው ጥንዚዛ በአፍንጫው ከሚሽከረከር ጉድፍ ያነሰ ከሆኑት ይሆናል*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ إِنَّ اللَّهَ عَزَّ وَجَلَّ قَدْ أَذْهَبَ عَنْكُمْ عُبِّيَّةَ الْجَاهِلِيَّةِ وَفَخْرَهَا بِالآبَاءِ مُؤْمِنٌ تَقِيٌّ وَفَاجِرٌ شَقِيٌّ أَنْتُمْ بَنُو آدَمَ وَآدَمُ مِنْ تُرَابٍ لَيَدَعَنَّ رِجَالٌ فَخْرَهُمْ بِأَقْوَامٍ إِنَّمَا هُمْ فَحْمٌ مِنْ فَحْمِ جَهَنَّمَ أَوْ لَيَكُونُنَّ أَهْوَنَ عَلَى اللَّهِ مِنَ الْجِعْلاَنِ الَّتِي تَدْفَعُ بِأَنْفِهَا النَّتْنَ ‏”‏

የአደም ልጆች የአንድ አባት እና እናት ልጆች ነን ብሎ ማስተንተን መጠበብ ሲሆን በዘረኝነት አራንቋ መለከፍ መጥበብ ነው፦
ሱነን ነሳኢ መጽሐፍ 37 , ሐዲስ 150
ጁንደብ ኢብኑ ዐብደላህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ *”ማንም ሰው ግልጽ ባልሆነ ነገር፣ በዘረኝነት ጥብቅና፣ በዘረኝነት መንገድ የተጋደለ ግድያው የጃህሊያ ነው*። عَنْ جُنْدُبِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَنْ قَاتَلَ تَحْتَ رَايَةٍ عُمِّيَّةٍ يُقَاتِلُ عَصَبِيَّةً وَيَغْضَبُ لِعَصَبِيَّةٍ فَقِتْلَتُهُ جَاهِلِيَّةٌ ‏”‏

“ጃህሊያህ” جَاهِلِيَّةٌ ማለት “መሃይምነት” ማለት ነው፤ ቅድመ-ቁርኣን ያለው ጊዜ ዘመነ-ጃህሊያህ ይባላል፤ በእርግጥም በዘመነ-ጃህሊያህ ጊዜ የነበረችው ዘረኝነት ጥንብ ናት፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 45, ሐዲስ 81
ጃቢር ኢብኑ ዐብደላህ እንዳስተላለፈው፦ “በጉዞ ከነቢዩ”ﷺ” ጋር ነበርን፤ አንድ ሰው ከሙሃጅር ከአንሷር የሆነውን አንድ ሰው ጀርባውን መታው፤ አንሷሩም፦ “አንሷሪ ሆይ! አለ፤ ሙሃጅሩም፦ “ሙሃጅር ሆይ! አለ። ከዚያም የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” *”ይህ የጃህሊያህ አጠራር አይደለምን? አሉ፤ እነርሱም፦ “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አንድ ሰው ከሙሃጅር ከአንሷር የሆነውን አንድ ሰው ጀርባውን መታው” አሉ፤ እርሳቸው፦ “እርሷን(ዘረኝነትን) ተዋት ጥንብ ናት” አሉ*። جَابِرَ بْنَ عَبْدِ اللَّهِ يَقُولُ كُنَّا مَعَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم فِي غَزَاةٍ فَكَسَعَ رَجُلٌ مِنَ الْمُهَاجِرِينَ رَجُلاً مِنَ الأَنْصَارِ فَقَالَ الأَنْصَارِيُّ يَا لَلأَنْصَارِ وَقَالَ الْمُهَاجِرِيُّ يَا لَلْمُهَاجِرِينَ ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ مَا بَالُ دَعْوَى الْجَاهِلِيَّةِ ‏”‏ ‏.‏ قَالُوا يَا رَسُولَ اللَّهِ كَسَعَ رَجُلٌ مِنَ الْمُهَاجِرِينَ رَجُلاً مِنَ الأَنْصَارِ ‏.‏ فَقَالَ ‏”‏ دَعُوهَا فَإِنَّهَا مُنْتِنَةٌ ‏
‏ ‏
“ሙሃጅር” مُهَاجِر ማለት “ስደተኛ” ማለት ሲሆን ከመካ የተሰደዱትን ሶሓብይን ያመለክታል፤ “አንሷር” أَنْصَارٍ ማለት “ረዳት” ማለት ሲሆን ከመካ የተሰደዱት የተቀበሉ የመዲና ሶሓብይን ያመለክታል። አንዱ ዘር ተነስቶ ሌላውን ዘር ሲበድል የተበደለው ያልበደለውን በዘሩ ብቻ በቁርሾ ለመበቀል መነሳት ጠባብነት ነው፤ በኢስላም የቀደሙት ትውልድ በሰሩት ወንጀል የአሁኑን ትውልድ መጠየቅ ወይም መቅጣት እራሱ ሕግ መተላለፍ ነው፦
ሱነን ነሳኢ መጽሐፍ 37 , ሐዲስ 162
ዐብደላህ እንደተረከው ነብዩም”ﷺ” አሉ፦.. *ሰው በአባቱ ወይም በወንድሙ ወንጀል አይቀጣም*። وَلاَ يُؤْخَذُ الرَّجُلُ بِجَرِيرَةِ أَبِيهِ وَلاَ بِجَرِيرَةِ أَخِيهِ ‏”
በተጨማሪም አንድ ሰው ባጠፋው ብዙኃኑን ዘር ማንቋሸሽ ወይም ማዋረድ ሐራም ነው፦
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 33, ሐዲስ 106
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ከሰዎች መካከል ትልቁ ውሸታም ሌላው ሰው ማንቋሸሽ እና መላውን ዘር ማዋረድ ነው*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ “‏ إِنَّ أَعْظَمَ النَّاسِ فِرْيَةً لَرَجُلٌ هَاجَى رَجُلاً فَهَجَا الْقَبِيلَةَ بِأَسْرِهَا

እረ እሩቅ ሳንሄድ ወደ ዘረኝነት የሚጣራ፣ በዘረኝነት መንገድ የሚታገል፣ በዘረኝነት መንገድ ሲከተል የሞተ ሰው ከነብያችን”ﷺ” ሱናህ ውጪ ነው፦
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 349
ጁበይር እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ወደ ዘረኝነት የሚጣራ ከእኛ አይደለም። በዘረኝነት መንገድ የሚታገኝ ከእኛ አይደለም። በዘረኝነት መንገድ ሲከተል የሞተ ከእኛ አይደለም*። عَنْ جُبَيْرِ بْنِ مُطْعِمٍ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ لَيْسَ مِنَّا مَنْ دَعَا إِلَى عَصَبِيَّةٍ وَلَيْسَ مِنَّا مَنْ قَاتَلَ عَلَى عَصَبِيَّةٍ وَلَيْسَ مِنَّا مَنْ مَاتَ عَلَى عَصَبِيَّةٍ ‏”‏

በድንበር፣ በክልል፣ በወሰን የከፋፈሉን ሰዎች ናቸው። ምድር እኮ የአላህ ናት። እንግዲህ ዲኑል ኢሥላምን የመሰለ ሰውን የሚያስተሳስር የአላህ ገመድ እያለ በዘረኝነት፣ በጎጠኝነት፣ በጠርዘኝነት፣ በቡድንተኝነት መለያየት “አትለያዩ” ያለን አላህ አለመታዘዝ ነው። ዛሬ በመሃይምነት አራንቋ ተጠቅተን በማህበራዊ ሚድያ ዘረኝነትን ስናራግብ እንውላለን፤ ኢስላም ዓለም-ዐቀፍ ሆኖ ሳለ ምነው ጠበብንሳ? ምነው ይህ ያህል ኢማናችን ወረደሳ? የኢሥላም ልዕልና ከዘር፣ ከብሔር፣ ከቋንቋ፣ ከቀለም፣ ከፓለቲካ በላይ ነው። አላህ ሁላችንም ያስተካክለን፥ ሂዳያ ይስጠን፣ ከጥንቧ ዘረኝነት ይጠብቀን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
አል-ሑሩፉል ሙቀጧዓት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

10፥1 *"አሊፍ ላም ሯ"* ይህቺ ጥበብ ከተመላው መጽሐፍ አንቀጾች ናት፡፡ الر ۚ تِلْكَ آيَاتُ الْكِتَابِ الْحَكِيمِ

ነቢያችን"ﷺ" በቁርኣን ከተሰጣቸው አንዱ አንድ ቃላት ሰፊ ትርጉም ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 21, ሐዲስ 7
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"በነቢያት ላይ በስድስት ነገር ከብሬአለው፥ እርሱም፦ "ጀዋሚዓል ከሊም ተሰቶኛል፣ በጠላት ልብ ውስጥም ፍርሀት እንዲጣል በመደረግ ተረዳኹኝ፣ የምርኮ ገንዘብ ሐላል ሆነውልኛል፣ ምድር በጠቅላላ ጡሀራና የመስገጃ ክልል ተደረገልኝ፣ ለፍጡራን ሁሉ ተላኩኝ፣ የነቢያት መደምደሚያ ሆንኩኝ"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ فُضِّلْتُ عَلَى الأَنْبِيَاءِ بِسِتٍّ أُعْطِيتُ جَوَامِعَ الْكَلِمِ وَنُصِرْتُ بِالرُّعْبِ وَأُحِلَّتْ لِيَ الْغَنَائِمُ وَجُعِلَتْ لِيَ الأَرْضُ مَسْجِدًا وَطَهُورًا وَأُرْسِلْتُ إِلَى الْخَلْقِ كَافَّةً وَخُتِمَ بِيَ النَّبِيُّون

"ጀዋሚዓል ከሊም" جَوَامِعَ الْكَلِم የሁለት ቃላት ውቅር ነው፥ የጀዋሚዕ እና የከሊም ነው። "ጀዋሚዕ" جَوَامِع ማለት "ብዛት" ማለት ሲሆን በነጠላ "ጃሚዕ" جَامِع ሲሆን ደግሞ "ብዙ" ማለት ነው። "ከሊም" كَلِم ወይም "ከሊማት" كَلِمَات ማለት "ቃላት" ማለት ሲሆን በነጠላ "ከሊማህ" كَلِمَة ሲሆን ደግሞ "ቃል" ማለት ነው። "ጀዋሚዓል ከሊም" ማለት "አንድ ቃል ሆኖ ብዛት ቃላት ያለው ትርጉም" ማለት ነው። ይህንን ከተረዳን ዘንዳ ሰለ አል-ሑሩፉል ሙቀጧዓት ሙሉ ትርጉም የሚያውቀው አላህ ብቻ ነው፥ ነገር ግን መጠነኛ ዕውቀት ከቀደምት ሠለፍ ተገኝቷል።
"አል-ሑሩፉል ሙቀጧዓት" الْحُرُوف الْمُقَطَّعَات ማለት "አጽርዖተ-ፊደላት" ወይም "አጫጭር ፊደላት" ማለት ነው። በቁርኣን ከ 114 ምዕራፎች ውስጥ በ 29 ምዕራፎች መግቢያ ላይ ስላሉ "ፈዋቲሕ" فَوَاتِح ማለትም "ከፋች" ይባላሉ። እነዚህም ሐርፎች 14 ናቸው፥ እነርሱም "አሊፍ" أ "ላም" ل "ሚም" م "ሯ" ر "ኑን" ن ወዘተ ናቸው። እነዚህ ሐርፎች ለምሳሌ "አሊፍ" أ የሚለው ሐርፍ "አና" أَنَا ለሚለው ቃል ምጻረ-ቃል ነው፣ "ላም" ل የሚለው ሐርፍ "አሏህ" الله ለሚለው ቃል ምጻረ-ቃል ነው፣ "ሚም" م የሚለው ሐርፍ "ዐሊም" عَلِيم ለሚለው ቃል ምጻረ-ቃል ነው፣ "ሯ" ر የሚለው ሐርፍ "በሲር" بَصِير ለሚለው ቃል ምጻረ-ቃል ነው፣ "ኑን" ن የሚለው ሐርፍ "ሑት" حُوت ለሚለው ቃል ተለዋዋጭ ነው። ይህ በወፍ በረር ለቅምሻ ያክል ነው፥ እስቲ አንዳንድ ናሙናዎችን በመጠኑ እንይ፦
29፥1 *"አሊፍ ላም ሚም"* الم

ከላይ በተቀመጠው መሠረት "አሊፍ ላም ሚም" الم ማለት "አና አሏሁ ዐሊም" أَنَا اللَّهُ عَلِيم ማለት ነው፥ ትርጉሙም "እኔ አላህ ዐዋቂ ነኝ" ማለት ነው። ይህንን ኢብኑ ዐባሥ ሲያስቀምጠው እንዲህ ይላል፦
ተፍሢሩል ኢብኑ ዐባሥ 29፥1 "ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *"የላቀው አላህ ንግግር ስለ አሊፍ ላም ሚም ማለት "እኔ አላህ ነኝ፥ ዐውቃለው" ማለት ነው"*። عن ابن عباس في قوله تعالى : " الۤـمۤ " ، أي : أنا الله أعلم

ሌላ ናሙና፦
10፥1 *"አሊፍ ላም ሯ"* ይህቺ ጥበብ ከተመላው መጽሐፍ አንቀጾች ናት፡፡ الر ۚ تِلْكَ آيَاتُ الْكِتَابِ الْحَكِيمِ

ከላይ በተቀመጠው መሠረት "አሊፍ ላም ሯ" الر ማለት "አና አሏሁ በሲር" أَنَا اللَّهُ بَصِير ማለት ነው፥ ትርጉሙም "እኔ አላህ ተመልካች ነኝ" ማለት ነው። ይህንን ኢብኑ ዐባሥ ሲያስቀምጠው እንዲህ ይላል፦
ተፍሢሩል ኢብኑ ዐባሥ 10፥1 "ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *"የላቀው አላህ ንግግር ስለ አሊፍ ላም ሯ ማለት "እኔ አላህ ነኝ፥ ዐያለው" ማለት ነው"*። عن ابن عباس في قوله تعالى : " الر " ، أي : أنا الله أرى
ሌላ ናሙና፦
68፥1 *"ኑን"* በብርእ እምላለሁ በዚያም መልአኮች በሚጽፉት፡፡ ن ۚ وَالْقَلَمِ وَمَا يَسْطُرُونَ

እዚህ ሱራህ ላይ ስለ የዓሣው ባለቤት ስለ ዩኑስ ስለሚናገር ይህ መግቢያ "ኑን" ይላል፦
68፥48 ለጌታህም ፍርድ ታገሥ! በመበሳጨትና ባለ መታገሥ *"እንደ ዓሣው ባለቤትም"* አትኹን፡፡ እርሱ በጭንቀት የተመላ ኾኖ ጌታውን በተጣራ ጊዜ፡፡ فَاصْبِرْ لِحُكْمِ رَبِّكَ وَلَا تَكُن كَصَاحِبِ الْحُوتِ إِذْ نَادَىٰ وَهُوَ مَكْظُومٌ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ዓሣ" ለሚለው ቃል የገባው "ሑት" حُوت ሲሆን በሌላ ሱራህ ላይ "ዓሣ" ለማለት የገባው "ኑን" نُّون ነው፦
21፥87 *"የዓሳውንም ባለቤት ተቆጥቶ በኼደ ጊዜ አስታውስ"*፡፡ وَذَا النُّونِ إِذ ذَّهَبَ مُغَاضِبًا

ስለ አስራ አራቱም ሐርፎች ለመናገር ሰፊ ጊዜና ቦታ ይፈልጋል፥ ግን ለማሟሻ ያክል ይህ በቂ ነው። ይህ ትርጓሜ ከኢብኑ ዐባሥ የተገኘ ሪዋያህ ነው፥ ይህንን ትርጓሜ አምላካችን አላህ ያስተማረው ትርጓሜ ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 171
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ያዙኛና እንዲህ አሉ፦ *"አላህ ሆይ! ጥበብን እና የመጽሐፉ ትርጉም አስተምረው"*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ ضَمَّنِي رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ إِلَيْهِ وَقَالَ ‏ "‏ اللَّهُمَّ عَلِّمْهُ الْحِكْمَةَ وَتَأْوِيلَ الْكِتَابِ

"ትርጉም" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ተእዊል" تَأْوِيل ነው። "ሙሕከማት" مُّحْكَمَات ማለት "ግልጽ"clear" ማለት ነው፥ የመጽሐፉ መሠረት የሆኑት የኢሥላም እና የኢማን መሠረት ግልጾች አናቅጽ ናቸው። "ሙተሻቢያት" مُتَشَابِهَات ማለት "ምሳሌአዊ"allegorical" ማለት ነው፥ ምሳሌአዊ አናቅጽን ትርጉም አላህ እና በዕውቀትም የጠለቁት እንጂ ሌላ ማንም ዐያውቀውም፦
3፥7 *"እርሱ ያ በአንተ ላይ መጽሐፉን ያወረደ ነው፡፡ ከእርሱ ከመጽሐፉ ግልጽ የኾኑ አንቀጾች አሉ፡፡ እነርሱ የመጽሐፉ መሠረቶች ናቸው፡፡ ሌሎችም ምሳሌአዊ አንቀጾች አሉ፡፡ እነዚያማ በልቦቻቸው ውስጥ ጥመት ያለባቸው ሰዎች ማሳሳትን ለመፈለግ እና ትርጉሙን ለመፈለግ ከእርሱ ሙተሻቢውን ይከታተላሉ፡፡ ፍቺውን አላህ እና በዕውቀትም የጠለቁት ብቻ እንጅ ሌላ አያውቀውም፡፡ እነርሱም፦ «በእርሱ አምነናል፤ ሁሉም ከጌታችን ዘንድ ነው» ይላሉ፡፡ የአእምሮ ባለቤቶችም እንጅ ሌላው አይገሰጽም"*፡፡ هُوَ الَّذِي أَنزَلَ عَلَيْكَ الْكِتَابَ مِنْهُ آيَاتٌ مُّحْكَمَاتٌ هُنَّ أُمُّ الْكِتَابِ وَأُخَرُ مُتَشَابِهَاتٌ ۖ فَأَمَّا الَّذِينَ فِي قُلُوبِهِمْ زَيْغٌ فَيَتَّبِعُونَ مَا تَشَابَهَ مِنْهُ ابْتِغَاءَ الْفِتْنَةِ وَابْتِغَاءَ تَأْوِيلِهِ ۗ وَمَا يَعْلَمُ تَأْوِيلَهُ إِلَّا اللَّهُ ۗ وَالرَّاسِخُونَ فِي الْعِلْمِ يَقُولُونَ آمَنَّا بِهِ كُلٌّ مِّنْ عِندِ رَبِّنَا ۗ وَمَا يَذَّكَّرُ إِلَّا أُولُو الْأَلْبَابِ

ከላይ ያቀረብኩት ከዐረቢኛው ጋር ተቀራራቢ ትርጉም ያለውን የሻኪር ትርጉም"translation" ነው። ይህ አተረጓጎም የቁርኣንን መሠረትና ውቅር፣ ዋልታና ማገር፣ ጥልቀትና ስፋት፣ ድርና ማግ በቅጡ በማወቅ የጠለቁት ያውቁታል። ስለ አል-ሑሩፉል ሙቀጧዓት እሳቤ በግርድፉና በሌጣው ለመጨበጥ እንጂ ደርዝና ፈርጅ ባለው መልኩ ለማሳወቅ እንዳልሆነ አንባቢ ግምት ውስጥ ያስገባልኝ።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የፍጥረት በኵር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥47 *፡-ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለች፡፡ ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፤ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል አላት*፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

በ 325 ድህረ-ልደት በኒቂያ ጉባኤ በአትናቴዎስ እና በአርዮስ መካከል ውይይት ከተደረገ በኃላ የአርዮስ ተከታዮች ከዐበይት የሥላሴያውያን መሪዎች ግዝት እና ግዞት ደርሶባቸዋል፤ የአርዮስ እሳቤ ባዕዳና እንግዳ ኢያም ያረጀና ያፈጀ እሳቤ ሳይሆን ጳውሎሳዊ እሳቤ ነው፤ በግሪክ ኮይኔ “ፕሮቶኮስ” πρωτότοκος ማለት “በኵር” “ቀዳማይ” “መጀመሪያ” ማለት ነው፦
ቆላስይስ 1፥15 እርሱም የማይታይ አምላክ መልክ እና *”የፍጥረት ሁሉ በኵር ነው”*። who is the image of the invisible God, the firstborn of all creation; (English Revised Version)
ግሪክ፦ πρωτότοκος πάσης κτίσεως

“ፓሰስ” πάσης ማለት “ሁሉ” ማለት ነው፤ “የፍጥረት ሁሉ በኵር” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርት፤ “ክቲሶስ” κτίσεως ማለት “ፍጥረት” ማለት ነው። “ፍጡር” በነጠላ “ፍጥረት” በብዜት ነው፤ የፍጥረት ሁሉ በኵር ማለት መጀመሪያ የተፈጠረ ማለት ነው። ይህንን ናሙና ለመረዳት አንድ ተመሳሳይ ሰዋስው እንይ፦
ራእይ 1፥5 ከታመነውም ምስክር *”የሙታንም በኵር”* and from Jesus Christ, who is the faithful witness, the firstborn of the dead, (English Revised Version)
ግሪክ፦ πρωτότοκος τῶν νεκρῶν

“ኔክሮን” νεκρῶν ማለት “ሙታን” ማለት ነው። “ሙት” በነጠላ “ሙታን” በብዜት ነው፤ የሙታን በኵር ማለት መጀመሪያ የተነሳ ማለት ከሆነ የፍጥረት በኩር ማለት መጀመሪያ የተፈጠረ ማለት ካልሆነ ምን ማለት ነው? እንቀጥል፦
1 ቆሮንቶስ 15፥20 አሁን ግን *”ክርስቶስ ላንቀላፉት በኵር ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል”*።
ግሪክ፦ Νυνὶ δὲ Χριστὸς ἐγήγερται ἐκ νεκρῶν, ἀπαρχὴ τῶν κεκοιμημένων.

“በኵር” የሚለው የግሪኩ ቃል “አፕ-አርኬ” ἀπαρχὴ ሲሆን የሁለት ቃላት ውቅር ነው፤ “አፓ” ἀπό ማለትም “ከ” እና “አርኬ” ἀρχή ማለትም “መጀመሪያ” ነው፤ ላንቀላፉት ሙታን “መጀመሪያ” ነው ማለት መጀመሪያ የተነሳ ማለት ከሆነ የእግዚአብሔር ፍጥረት መጀመሪያ ማለት መጀመሪያ የተፈጠረ ማለት ነው፦
ራእይ 3፥14 አሜን የሆነው፥ የታመነውና እውነተኛው ምስክር፥ *”የእግዚአብሔር ፍጥረት መጀመሪያ”* የነበረው እንዲህ ይላል፦ the beginning of the creation of God. (English Revised Version)
ግሪኩ፦ ἡ ἀρχὴ τῆς κτίσεως τοῦ θεοῦ: