ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ነጥብ አንድ
“ላም”
51፥56 *ጂኒን እና ሰውንም ሊያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም*፡፡ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

“የዕቡዱኒ” يَعْبُدُونِ በሚለው ግስ መነሻ ቅጥያ ላይ “ሊ” لِ የምትል መስተዋድድ አለች፤ ይህቺ “ላም” ل “ላሙል-ታዕሊል” ማለትም “የመንስኤ መስተዋድድ” prefixed particle of purpose” ትባላለች፤ ይህንን የሰዋስው ሙግት ለመረዳት ለናሙና ያክል አንድ ሌላ አንቀጽ እንመልከት፦
28፥9 *የፈርዖንም ሚስት፦ ለእኔም ለአንተም የዓይኔ መርጊያ ነው*፡፡ አትግደሉት፡፡ *”ሊ”ጠቅመን ወይም ልጅ አድርገን ልንይዘው ይከጀላልና» አለች፡፡ እነርሱም ፍጻሜውን የማያውቁ ሆነው አነሱት*፡፡ وَقَالَتِ امْرَأَتُ فِرْعَوْنَ قُرَّتُ عَيْنٍ لِّي وَلَكَ ۖ لَا تَقْتُلُوهُ عَسَىٰ أَن يَنفَعَنَا أَوْ نَتَّخِذَهُ وَلَدًا وَهُمْ لَا يَشْعُرُونَ

የፈርዖን ቤተሰቦች ሙሳን ከባህር ያነሱበት ዓላማ ሊጠቅማቸው ወይም ልጅ አድርገው ሊያሳድጉት ነው፤ እዚህ ጋር የገባችው “ላም” ل “ላሙል-ታዕሊል” እንደሆነች አንባቢ ልብ ይለዋል፤ ነገር ግን እነርሱ ማለትም የፈርዖን ቤተሰቦች ፍጻሜውን የማያውቁ ሆነው ከባህር አነሱት፤ አላህ ግን ፍጻሜውን ስለሚያውቅ፦ “ለእነርሱ ጠላት ሐዘንም ይሆን ዘንድ አነሱት” ብሎ ነገረን፦
28፥8 *የፈርዖን ቤተሰቦችም መጨረሻው “ለ”እነርሱ ጠላት ሐዘንም ይሆን ዘንድ አነሱት*፡፡ فَٱلْتَقَطَهُۥٓ ءَالُ فِرْعَوْنَ لِيَكُونَ لَهُمْ عَدُوًّۭا وَحَزَنًا

እዚህ ጋር ነው ነጥቡ፤ የፈርዖን ቤተሰቦች ሙሳን ከባህር ያነሱበት ዓላማ ሊጠቅማቸው ወይም ልጅ አድርገው ሊያሳድጉት ሆኖ ሳለ ነገር ግን ሙሳ ሲያድግ ለእነርሱ ጠላትና ሐዘን ሆነባቸው፤ አላህ ፍጻሜውን ስለሚያውቅ፦ “ለእነርሱ ጠላት ሐዘንም ይሆን ዘንድ አነሱት” አለን፤ እዚህ ጋር “የኩነ” يَكُونَ በሚለው ግስ መነሻ ቅጥያ ላይ “ሊ” لِ የምትል መስተዋድድ አለች፤ ይህቺ “ላም” ل “ላሙል-ዓቂባህ” ማለትም “የውጤት መስተዋድድ” prefixed particle of result” ትባላለች፤ ፍጻሜያቸውና መጨረሻቸው ምን እንደሆነ ቀድሞ በመታወቁ ምክንያት የምትመጣ መስተዋድድ ናት፤ ይህንን የሰዋሰው ሙግት ከተረዳን ጂን እና ሰው የተፈጠሩበት ዓላማ አላህን እንዲያመልክ ሆኖ ሳለ ነገር ግን ከጂን እና ከሰው በነጻ ፈቃዳቸው ልቦች እያላቸው የማያውቁ፣ አይኖች እያላቸው የማያዩ፣ ጆሮዎች እያላቸው የማይሰሙ ጀሃነም ይገባሉ፤ አላህ የእነዚህን ፍጻሜ ስለሚያውቅ፦ “ከጂኒዎችም ከሰዎችም ብዙዎችን ለገሀነም በእርግጥ ፈጠርን” አለ፦
7፥179 *ከጂኒዎችም ከሰዎችም ብዙዎችን ለገሀነም በእርግጥ ፈጠርን፡፡ ለእነርሱ በእርሳቸው የማያውቁባቸው ልቦች አሏቸው፡፡ ለእነርሱም በሳቸው የማያዩባቸው ዓይኖች አሉዋቸው፡፡ ለእነርሱም በሳቸው የማይሰሙባቸው ጆሮዎች አሉዋቸው፡፡ እነዚያ እንደ እንስሳዎች ናቸው፡፡ ይልቁንም እነርሱ በጣም የተሳሳቱ ናቸው፡፡ እነዚያ ዘንጊዎቹ እነርሱ ናቸው*። وَلَقَدْ ذَرَأْنَا لِجَهَنَّمَ كَثِيرًا مِّنَ الْجِنِّ وَالْإِنسِ ۖ لَهُمْ قُلُوبٌ لَّا يَفْقَهُونَ بِهَا وَلَهُمْ أَعْيُنٌ لَّا يُبْصِرُونَ بِهَا وَلَهُمْ آذَانٌ لَّا يَسْمَعُونَ بِهَا ۚ أُولَـٰئِكَ كَالْأَنْعَامِ بَلْ هُمْ أَضَلُّ ۚ أُولَـٰئِكَ هُمُ الْغَافِلُونَ

እዚሁ አንቀጽ ላይ “ጀሃነም” جَهَنَّمَ በሚለው ቃል መነሻ ቅጥያ ላይ “ሊ” لِ የምትል “ላም” ل “ላሙል-ዓቂባህ” የተባለችው የውጤት መስተዋድድ መግባቷ አንባቢ ልብ ይላታል፤ ስለዚህ እነዚያ ዘንጊዎቹ መጨረሻቸው ለገሃነም ናቸው፤ እነዚያን ዘንጊዎቹ የፈጠራቸው አላህ ነው።
ነጥብ ሁለት
“ሚን”
አላህ፦ ”ጂኒዎችም ሰዎችም ለገሀነም በእርግጥ ፈጠርን” አላለም፤ ጂኒዎችም ሰዎችም በሚሉት ቃላት መነሻ ቅጥያ ላይ “ሚን” مِن ማለትም “ከ” የሚል መስተዋድድ አለ፣ ይህም የሚያስረዳው ከጂንዎችና ከሰዎች መካከል ልቦች እያላቸው የማያውቁ፣ አይኖች እያላቸው የማያዩ፣ ጆሮዎች እያላቸው የማይሰሙ የገሃነም መሆናቸውን ነው፤ ይህንን ለመረዳት የሚቀጥለውን አንቀጽ እንመልከት፦
30፥8 *”ከ”ሰዎቹም ብዙዎቹ በጌታቸው መገናኘት ከሓዲዎች ናቸው*፡፡ وَإِنَّ كَثِيرًا مِّنَ النَّاسِ بِلِقَاءِ رَبِّهِمْ لَكَافِرُون

አንቀጹ ላይ የሚለው “ሰዎች በጌታቸው መገናኘት ከሐዲዎች ናቸው” ሳይሆን “ከሰዎቹም ብዙዎቹ በጌታቸው መገናኘት ከሐዲዎች ናቸው” ነው፤ “ሰዎች” በሚለው ቃል ላይ “ሚን” مِن የሚል መስተዋድድ አለ፣ ሌላ ናሙና እስቲ እንመልከት፦
4፥124 *”ከ”ወንድ ወይም “ከ”ሴት እርሱ አማኝ ኾኖ ከበጎ ሥራዎች አንዳችን የሚሠራም ሰው እነዚያ ገነትን ይገባሉ*፡፡ በተምር ፍሬ ላይ ያለችን ነጥብ ያክል እንኳ አይበደሉም፡፡ وَمَن يَعْمَلْ مِنَ الصَّالِحَاتِ مِن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَأُولَـٰئِكَ يَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ وَلَا يُظْلَمُونَ نَقِيرًا

አንቀጹ ላይ የሚለው “ወንድ ወይም ሴት እነዚያ ገነትን ይገባሉ” ሳይሆን “ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ ከበጎ ሥራዎች አንዳችን የሚሠራም ሰው እነዚያ ገነትን ይገባሉ” ነው፤ “ወንድ እና ሴት” በሚለው ቃል ላይ “ሚን” مِن የሚል መስተዋድድ አለ፣ ይህ የሚያሳየው ከወንድ ወይም ከሴት መካከል አማኝ ኾኖ ከበጎ ሥራዎች አንዳችን የሚሠራም ሰው ገነትን ይገባሉ ነው፤ እንዲሁ በተቃራኒው ከጂንዎችና ከሰዎች መካከል ልቦች እያላቸው የማያውቁ፣ አይኖች እያላቸው የማያዩ፣ ጆሮዎች እያላቸው የማይሰሙ ጀሃነም ይገባሉ ነው።

ነጥብ ሦስት
“አውላዒከ”
“አውላዒከ” أُولَـٰئِكَ ማለት “እነዚያ” ማለት ሲሆን አመልካች ተውላጠ-ስም ነው፤ የአንቀጹን ዓረፍተ-ነገር ከሃረጉ አፋቶ ማንበብ ክፉኛ መሃይምነት ነው፤ ከጂንዎችና ከሰዎች መካከል “እነዚያ” የተባሉት ልቦች እያላቸው የማያውቁ፣ አይኖች እያላቸው የማያዩ፣ ጆሮዎች እያላቸው የማይሰሙ ናቸው፤ ሆን ብለው የአላህን መልእክት ያስተባበሉ ናቸው፤ እነርሱ ልክ እንደ እንስሳ ውሳጣዊ ተፈጥሮአቸው ደንድኗል፣ ታውሯል፣ ደንቁሯል፦
25፥44 ይልቁንም *አብዛኛዎቻቸው የሚሰሙ ወይም የሚያውቁ መኾናቸውን ታስባለህን እነርሱ እንደ እንስሳዎች እንጂ ሌላ አይደሉም*፡፡ ከቶውንም እነሱ ይልቅ መንገድን የተሳሳቱ ናቸው፡፡ أَمْ تَحْسَبُ أَنَّ أَكْثَرَهُمْ يَسْمَعُونَ أَوْ يَعْقِلُونَ ۚ إِنْ هُمْ إِلَّا كَالْأَنْعَامِ ۖ بَلْ هُمْ أَضَلُّ سَبِيلًا
2:171 *የእነዚያም የካዱት እና ወደ ቅን መንገድ የሚጠራቸው ሰው ምሳሌ እንደዚያ ድምጽንና ጥሪን በስተቀር ሌላን በማይሰማ እንስሳ ላይ እንደሚጮህ ብጤ ነው፡፡ እነርሱ ደንቆሮዎች፣ ዲዳዎች፣ ዕውሮች ናቸው፤ ስለዚህ እነርሱ አያውቁም*፡፡ وَمَثَلُ الَّذِينَ كَفَرُوا كَمَثَلِ الَّذِي يَنْعِقُ بِمَا لَا يَسْمَعُ إِلَّا دُعَاءً وَنِدَاءً ۚ صُمٌّ بُكْمٌ عُمْيٌ فَهُمْ لَا يَعْقِلُونَ
7፥179 ከጂኒዎችም ከሰዎችም ብዙዎችን ለገሀነም በእርግጥ ፈጠርን፡፡ *ለእነርሱ በእርሳቸው የማያውቁባቸው ልቦች አሏቸው፡፡ ለእነርሱም በሳቸው የማያዩባቸው ዓይኖች አሉዋቸው፡፡ ለእነርሱም በሳቸው የማይሰሙባቸው ጆሮዎች አሉዋቸው፡፡ እነዚያ እንደ እንስሳዎች ናቸው፡፡ ይልቁንም እነርሱ በጣም የተሳሳቱ ናቸው፡፡ እነዚያ ዘንጊዎቹ እነርሱ ናቸው*። وَلَقَدْ ذَرَأْنَا لِجَهَنَّمَ كَثِيرًا مِّنَ الْجِنِّ وَالْإِنسِ ۖ لَهُمْ قُلُوبٌ لَّا يَفْقَهُونَ بِهَا وَلَهُمْ أَعْيُنٌ لَّا يُبْصِرُونَ بِهَا وَلَهُمْ آذَانٌ لَّا يَسْمَعُونَ بِهَا ۚ أُولَـٰئِكَ كَالْأَنْعَامِ بَلْ هُمْ أَضَلُّ ۚ أُولَـٰئِكَ هُمُ الْغَافِلُونَ
መደምደሚያ
ከላይ ያለውን ሙግት ከኡስታዙና አቡሃይደር አላህ ይጠብቀው የተማርኩት ሙግት ነው፤ ብዙ ጊዜ ካፊሮች የራሳቸው እያረረባቸው የእኛን ማማሰል ከጀመሩ ሰነበቱ፣ የተረዳነው ነገር ቢኖር መጽሐፋቸው ዞር ብለው እንደማያዩት ነው፣ እስቲ ይህንን ሂስ በነካ እጃችን እንሞግት፤ እግዚአብሔር ኀጥአንን ማለት ኀጢያተኞችን ለክፉ ቀን እንደፈጠራቸው ይናገራል፦
ምሳሌ 16:4 እግዚአብሔር ሁሉን ለእርሱ ለራሱ ፈጠረ፥ *ኀጥእን ደግሞ ”ለክፉ ቀን”*።

ክፉ ከሚለው ቃል በፊት “ለ” לְ ማለትም ”ለ” የሚለው ቃል መነሻ ቅጥያ ሆኖ የመጣ መስተዋድድ ነው፣ ጥያቄ እግዚአብሔር ኀጢያተኞችን የፈጠረ ለክፉ ቀን ነውን? ከዚህ የባሰ ክፋትን የፈጠረውስ? የሚያፈርሰውንም እንዲያጠፋ የፈጠረው እግዚአብሔር መሆኑን ይናገራል፦
ኢሳይያስ 45፥7 ብርሃንን ሠራሁ፥ ጨለማውንም ፈጠርሁ፤ ደኅንነትን እሠራለሁ፥ *”ክፋትንም እፈጥራለሁ”*፤ እነነዚህን ሁሉ ያደረግሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፤
ኢሳይያስ 54፥16 እነሆ፥ ፍሙን በወናፍ የሚያናፋ ለሥራውም መሣሪያ የሚያወጣ ብረት ሠሪን እኔ ፈጥሬአለሁ፤ *”የሚያፈርሰውንም እንዲያጠፋ ፈጥሬአለሁ”*።

ቢያንስም ቢበዛም ቁርኣን ላይ ላለው ጥያቄ መልስ ተሰጦበታል፣ ይህ ጥያቄ ሲመጣባቸው የሚሰጡት መልሱ፦
ሮሜ 9፥20-24 *አንተ ሰው ሆይ፥ ለእግዚአብሔር የምትመልስ ማን ነህ? ሥራ ሠሪውን፦ ስለ ምን እንዲህ አድርገህ ሠራኸኝ ይለዋልን? ወይም ሸክላ ሠሪ ከአንዱ ጭቃ ክፍል አንዱን ዕቃ ”ለ”ክብር አንዱንም ”ለ”ውርደት ሊሠራ በጭቃ ላይ ሥልጣን የለውምን?*

ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ ነገር ነው። ጥያቄ እግዚአብሔር ሁሉን የፈጠረው ለራሱ? ወይስ ለክፉ ቀን? ወይስ ለውርደት? ወይስ ለክብር? ሸክላ ሠሪ እግዚአብሔር አንዱን ለውርደት አንዱን ለክብር ለምን ይፈጥራል? ቁርአን ላይ ሲጠይቁ ልክ የራሳቸው ባይብል ሙሉ መልስ እንዳለው አድርገው ነው የሚጠይቁት፣ ነገር ግን ባይብል ላይ ሲጠየቁ እርርና ምርር ብለው ሲንጨረጨሩና ሲንተከተኩ ነው የሚገኙት፣ አላህ ሂዳያ ይስጣቸው ለእኛም ጽናቱን።

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር ሦስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 3
ሰዎችን የሚያጠመው ማን ነው? አላህ ወይንስ ሰይጣን?

አላህ፦
ሱራ 7፡186 “አላህ የሚያጠመውም ሰው ለእርሱ ምንም አቅኚ የለውም፡፡”

ሰይጣን፦
ሱራ 4፡119-120 “በእርግጥም አጠማቸዋለሁ ከንቱም አስመኛቸዋለሁ… የማይፈፀመውን ተስፋ ይሰጣቸዋል ያስመኛቸዋልም፡፡ ሰይጣንም ለማታለል እንጂ አይቀጥራቸውም”

“ሂዳያህ” هداية የሚለው ቃል “ምሪት” ማለት ሲሆን “ሁዳ” هُدً ማለትም “መሪ” ከሚለው ቃል የመጣ ነው፣ የሂዳያህ ተቃራኒ ደግሞ “ደላላህ” ضاله ሲሆን “ጥመት” ማለት ሲሆን “ደላል” ضلال ማለትም “ጠማማ” ከሚለው ቃል የመጣ ነው፣ አላህ በቁርአን ከገለጻቸው ስሞቹ መካከል “አል-ሃዲ” اللَهَادِ ሲሆን ትርጉሙ “አቅኚ” አሊያም “መሪ” ማለት ነው፦
22፥54 አላህም እነዚያን ያመኑትን ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ መሪ ነው፡፡ وَإِنَّ اللَّهَ لَهَادِ الَّذِينَ آمَنُوا إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ
25፥31 እንደዚሁም ለነቢዩ ሁሉ ከአመጸኞች የኾነ ጠላትን አድርገናል፡፡ *"መሪ እና ረዳትም በጌታህ በቃ"*፡፡ وَكَذَٰلِكَ جَعَلْنَا لِكُلِّ نَبِيٍّ عَدُوًّا مِّنَ الْمُجْرِمِينَ ۗ وَكَفَىٰ بِرَبِّكَ هَادِيًا وَنَصِيرًا

“ሃዲ” لَهَادِ ማለት “አቅኚ” ከሆነ የአቅኚ ተቃራኒ ቃል ደግሞ “ሙዲል” مُضِلٌّ ሲሆን ትርጉሙ “አሳሳች” አሊያም “አጥማሚ” ማለት ነው፣ በቁርአን አንድም ቦታ ላይ አላህ “ሙዲል” ተብሎ አይታወቅም፣ የሚሺነሪዎች ሙግት ዜሮ ገባ፣ ነገር ግን ሙዲል የተባለው ሸይጣን ነው፦
28፥15 ይህ ከሰይጣን ሥራ ነው፡፡ እርሱ ግልጽ *"አሳሳች"* ጠላት ነውና አለ፡፡ قَالَ هَـٰذَا مِنْ عَمَلِ الشَّيْطَانِ ۖ إِنَّهُ عَدُوٌّ مُّضِلٌّ مُّبِي

ሸይጣን አጥማሚነቱ የተገለጸው በስም መደብ “አጥማሚ” ተብሎ ነው፣ ይህም የሸይጣን መደበኛ ባህርይ መሆኑ ያስገነዝባል፣ ነገር ግን አላህ አቅኝነቱ የተገለጸው በስም መደብ “አቅኚ” ተብሎ ሲሆን ይህም የአላህን መደበኛ ባህርይ መሆኑ ያስገነዝባል፣ በቁርኣን አላህ እደሚያጠም በግስ መደብ “ያጠማል” የሚል ቃል ተቀምጧል። አላህ ያጠማል ማለት ሂዳያ አይሰጥም ማለት ነው። ለእነማን ነው ሂዳያ የማይሰጠው? ስንል የኢሥላም መልእክት ሰምተው ሆን ብለው ካስተባበልሉ አዎ አላህ ሂዳያ አይሰጥም። እውነትን ከመስማትህና ከማወቅህ በፊት በፍጹም ማንምም አያጠምም። ከእውነት በተዘነበልክ ጊዜ አላህ ልብህን አዘነበለብህ፤ አላህም እውነት ከመቀበል ይልቅ ያመጸን አመጸኛ አያቀናም፤ አላህ በሕዝቦች ዘንድ ያለውን ጸጋ በነፍሶቻቸው ያለውን ኹኔታ በራሳቸው እስከሚለውጡ ድረስ ሂዳያን በመንሳት አይለውጥም፦
61፥5 *”ከእውነት በተዘነበሉም ጊዜ አላህ ልቦቻቸውን አዘነበላቸው፡፡ አላህም አመጸኞችን ሕዝቦች አያቀናም”*፡፡ فَلَمَّا زَاغُوا أَزَاغَ اللَّهُ قُلُوبَهُمْ ۚ وَاللَّهُ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الْفَاسِقِينَ
13፥11 *አላህ በሕዝቦች ዘንድ ያለውን ጸጋ በነፍሶቻቸው ያለውን ኹኔታ እስከሚለውጡ ድረስ አይለውጥም*፡፡ አላህም በሰዎች ላይ ክፉን በሻ ጊዜ ለእርሱ መመለስ የለውም፡፡ ለእነርሱም ከእርሱ ሌላ ምንም ተከላካይ የላቸውም፡፡ إِنَّ اللَّهَ لَا يُغَيِّرُ مَا بِقَوْمٍ حَتَّىٰ يُغَيِّرُوا مَا بِأَنفُسِهِمْ ۗ وَإِذَا أَرَادَ اللَّهُ بِقَوْمٍ سُوءًا فَلَا مَرَدَّ لَهُ ۚ وَمَا لَهُم مِّن دُونِهِ مِن وَالٍ

“እመኑ” ተብሎ ጥሪ ቀርቦላቸው፣ ስለ እምነት ተነግሯቸው፣ መልክተኛውም እውነት መኾኑን ተመስክሮላቸው፣ የተብራሩ አንቀጾችም ከመጡላቸው በኋላ የካዱን ሕዝቦች አላህ እንዴት ያቀናል! አላህ በዳዮችንም ሕዝቦች አያቀናም፦
4፥170 እናንተ ሰዎች ሆይ! *መልክተኛው እውነትን ከጌታችሁ አመጣላችሁ፡፡ “እመኑም” ለእናንተ የተሻለ ይኾናል፡፡ ብትክዱም አትጐዱትም*”፡፡ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነውና፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ قَدْ جَاءَكُمُ الرَّسُولُ بِالْحَقِّ مِن رَّبِّكُمْ فَآمِنُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ وَإِن تَكْفُرُوا فَإِنَّ لِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ وَكَانَ اللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمًا
3፥86 *ከእምነታቸው እና መልክተኛውም እውነት መኾኑን ከመሰከሩ የተብራሩ አንቀጾችም ከመጡላቸው በኋላ የካዱን ሕዝቦች አላህ እንዴት ያቀናል! አላህ በዳዮችንም ሕዝቦች አያቀናም*፡፡ كَيْفَ يَهْدِي اللَّهُ قَوْمًا كَفَرُوا بَعْدَ إِيمَانِهِمْ وَشَهِدُوا أَنَّ الرَّسُولَ حَقٌّ وَجَاءَهُمُ الْبَيِّنَاتُ ۚ وَاللَّهُ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الظَّالِمِينَ
3፥125 *”አላህም ሊመራው የሚሻውን ሰው ልቡን ለኢሥላም ይከፍትለታል፡፡ ሊያጠመውም የሚሻውን ሰው ደረቱን ጠባብ ቸጋራ ወደ ሰማይ ለመውጣት አንደሚታገል ያደርገዋል”*፡፡ فَمَن يُرِدِ اللَّهُ أَن يَهْدِيَهُ يَشْرَحْ صَدْرَهُ لِلْإِسْلَامِ ۖ وَمَن يُرِدْ أَن يُضِلَّهُ يَجْعَلْ صَدْرَهُ ضَيِّقًا حَرَجًا كَأَنَّمَا يَصَّعَّدُ فِي السَّمَاءِ ۚ كَذَٰلِكَ يَجْعَلُ اللَّهُ الرِّجْسَ عَلَى الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ
አላህ ይፈትናል ማለት እና ሸይጧን ይፈትናል ማለት ለየቅል እንደሆነ ሁሉ አላህ ያጠማል ማለት እና ሸይጣንም ያጠማል ማለት ለየቅል ነው። እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው። ሰይጣን ፈታኝ ነው፦
ዘፍጥረት 22፥1 ከእነዚህም ነገሮች በኋላ *"እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው"*፥
ማቴዎስ 4፥3 *"ፈታኝም"* ቀርቦ፦ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል አለው።

እግዚአብሔር ፈታኝ ሰይጣን ነውን? ማነው ፈታኝ? እግዚአብሔር ወይስ ሰይጣን? እግዚአብሔር አጥፊ ተብሏል። ሰይጣንም አጥፊ ተብሏል፦
ዘጸአት 12፥12 እኔም በዚያች ሌሊት በግብፅ አገር አልፋለሁ፥ *"በግብፅም አገር ከሰው እስከ እንስሳ ድረስ በኵርን ሁሉ እገድላለሁ፤ በግብፅም አማልክት ሁሉ ላይ እፈርድባቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ"*።
ዕብራውያን 11፥28 *"አጥፊው"* የበኵሮችን ልጆች እንዳይነካ ፋሲካንና ደምን መርጨትን በእምነት አደረገ።
ራእይ 9፥11 *"በእነርሱም ላይ ንጉሥ አላቸው እርሱም የጥልቅ መልአክ ነው፥ ስሙም በዕብራይስጥ አብዶን በግሪክም አጶልዮን ይባላል"*።

በዕብራይስጥ "አብዶን" ማለት እና በግሪክ "አጶልዮን" ማለት ትርጉሙ "አጥፊ" ማለት ነው። እግዚአብሔር የጥልቁ መልአክ ሰይጣን ነውን? ማነው አጥፊ? እግዚአብሔር ወይስ ሰይጣን? እግዚአብሔር ሰዎችን የጠማምነትን መንፈስ በውስጣቸው በመደባለቅ ያጠማቸዋል፤ እርሱ ጠማማ ያደረገውን ማን ሊያቀናው ይችላል?
ኢሳይያስ 19፥14 *እግዚአብሔር የጠማምነትን መንፈስ በውስጥዋ ደባልቆአል*፤
መክብብ 7:13 የእግዚአብሔርን ሥራ ተመልከት እርሱ *ጠማማ ያደረገውን ማን ሊያቀናው* ይችላል?

ለነገሩ ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር የሆነውን ክፉን መንፈስ ይልካል፤ ይህም ክፉም መንፈስ ከእግዚአብሔር ጋር እተመካከረ ለእግዚአብሔር ያሳስትለታል፤ የሚሳሳተው ሰው እና የሚያሳስተው ክፉ መንፈስ ለእግዚአብሔር ናቸው፦
2ኛ ተሰሎንቄ 2፥12 ስለዚህም ምክንያት፥ በእውነት ያላመኑ ነገር ግን በዓመፅ ደስ ይላቸው የነበሩ ሁሉ ፍርድን እንዲቀበሉ፥ *ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል*።
መሣፍንት 9፥23 *እግዚአብሔር በአቤሜሌክና በሴኬም ሰዎች መካከል ክፉን መንፈስ ሰደደ*፤
1ኛ ነገሥት 22 20-23 እግዚአብሔርም፦ ወጥቶ በሬማት ዘገለዓድ ይወድቅ ዘንድ *አክዓብን የሚያሳስት ማን ነው?* አለ። አንዱም እንዲህ ያለ ነገር፥ ሌላውም እንዲያ የለ ነገር ተናገረ። *መንፈስም ወጣ በእግዚአብሔርም ፊት ቆሞ፦ እኔ አሳስተዋለሁ አለ*። እግዚአብሔርም፦ በምን? አለው እርሱም፦ *ወጥቼ በነቢያቶቹ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ እሆናለሁ አለ*። እግዚአብሔርም፦ *ማሳሳትስ ታሳስተዋለህ፥ ይሆንልሃልም ውጣ፥ እንዲሁም አድርግ አለ*። አሁንም፦ እነሆ፥ እግዚአብሔር በእነዚህ *በነቢያትህ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ አድርጎአል*፤ እግዚአብሔርም በላይህ ክፉ ተናግሮብሃል።
ኢዮብ 12፥16 ኃይልና ጥበብ በእርሱ ዘንድ ናቸው፤ *የሚስተውና የሚያስተው ለእርሱ ናቸው*።

እግዚአብሔር፦ “ነቢዩም ቢታለል ያንን ነቢይ ያታለልኩት እኔ እግዚአብሔር ነኝ” ይለናል፤ ሕዝቅኤልን፣ ኤርሚያስን እና ኢሳይያስን ያታለላቸው እርሱ እንደሆነ እራሳቸው ይናገራሉ፦
ሕዝቅኤል 14፥9 *ነቢዩም ቢታለል ቃልንም ቢናገር፥ ያንን ነቢይ ያታለልሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ*፥
ኤርሚያስ 20፥7 አቤቱ፥ *አታለልኸኝ እኔም ተታለልሁ*፥
ኢሳይያስ 63፥17 *አቤቱ፥ ከመንገድህ ለምን “አሳትኸን”?* እንዳንፈራህም ልባችንን ለምን አጸናህብን? ስለ ባሪያዎችህ ስለ ርስትህ ነገዶች ተመለስ።

እግዚአብሔር አታላይና አሳሳች ሰይጣን ነውን? ማነው አታላይና አሳሳች? እግዚአብሔር ወይስ ሰይጣን? አይ "እግዚአብሔር አታላይና አሳሳች የተባለው ሰይጣን አታላይና አሳሳች በተባለበት ስሌት አይደለም" ካላችሁ እንግዲያውስ ከላይ ያለውንም ጥያቄ በዚህ ሒሳብ ተረዱት። ይህንን ጉድ ይዞ ከላይ የቁርኣንን አናቅጽ መተቸት ማለት የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ እንደማለት ነው። አላህ ሂዳያ ይስጣችሁ፥ ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር አራት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 4
አማላጆች አሉ ወይስ የሉም?

አሉ፡-
ሱራ 42፡5 “… መላእክትም ጌታቸውን እያመሰገኑ ያወድሳሉ፤ በምድርም ላለው ፍጡር ምህረትን ይለምናሉ…”

የሉም፡-
“…ከርሱ ሌላ ረዳትም አማላጅም ምንም የላችሁም አትገሠፁምን?”

መልስ
“ሸፋዐህ” شَفَٰعَهማለት “ምልጃ” ማለት ሲሆን ምልጃ ሥስት ማንነቶችን ያቅፋል፤ እነርሱም፦ አንደኛው የሚማለደው ተማላጅ፣ ሁለተኛው የሚማለድለት ተመላጅ እና ሥስተኛው የሚማልደው አማላጅ ናቸው፤ አላህ የሁሉም ነገር ፈጣሪና አስተናባሪ በመሆኑ የሚማለድ ተማላጅ ነው፤ ከፍጡሮቹ መካከል ደግሞ እርሱ የፈቀደላቸው ፍጡሮቹ ደግሞ ተመላጆች እና አማላጆች ናቸው። ይህ ሦስቱ ሂደት “ምልጃ” ሲባል ይህ የምልጃ ፈቃድ የአላህ ብቻ ነው፦
39፥44 *”ምልጃ በሙሉ የአላህ ብቻ ነው፤ የሰማያትና የምድር ሥልጣን የእርሱ ብቻ ነው፡፡ ከዚያም ወደ እርሱ ትመለሳላችሁ”* በላቸው፡፡ قُل لِّلَّهِ الشَّفَاعَةُ جَمِيعًا ۖ لَّهُ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ ثُمَّ إِلَيْهِ تُرْجَعُونَ
34፥23 *ምልጃም እርሱ ለፈቀደለት ሰው ብቻ ቢሆን እንጂ እርሱ ዘንድ ምንም አትጠቅምም*፡፡ وَلَا تَنفَعُ الشَّفَاعَةُ عِندَهُ إِلَّا لِمَنْ أَذِنَ لَهُ
20፥109 *በዚያ ቀን ለእርሱ አልረሕማን የፈቀደለትን እና ለእርሱም ቃልን የወደደለትን ሰው ቢኾን እንጅ ምልጃ አንድንም አትጠቅምም*፡፡ يَوْمَئِذٍ لَّا تَنفَعُ الشَّفَاعَةُ إِلَّا مَنْ أَذِنَ لَهُ الرَّحْمَـٰنُ وَرَضِيَ لَهُ قَوْلًا

ነጥብ አንድ
“አማላጅ”
“ሸፊዕ” شَفِيع ማለት “አማላጅ” ማለት ሲሆን በአላህ ፈቃድ የሚያማልዱት መላእክት፣ ነቢያት፣ ሙዑሚን ናቸው፤ ለምሳሌ መላእክት፦
53፥26 *በሰማያት ውስጥ ካለ መልአክም ብዙዎች ሊማለዱለት ለሚሻው እና ለሚወደው ሰው ከፈቀደ በኋላ ቢኾን እንጅ ምልጃቸው ምንም አትጠቅምም*፡፡ وَكَم مِّن مَّلَكٍ فِي السَّمَاوَاتِ لَا تُغْنِي شَفَاعَتُهُمْ شَيْئًا إِلَّا مِن بَعْدِ أَن يَأْذَنَ اللَّهُ لِمَن يَشَاءُ وَيَرْضَىٰ
21፥28 በፊታቸው ያለውንና በኋላቸው ያለውንም ሁሉ ያውቃል፡፡ *ለወደደውም ሰው እንጅ ለሌላው አያማልዱም*፡፡ እነርሱም እርሱን ከመፍራታቸው የተነሳ ተጨናቂዎች ናቸው፡፡ يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَلَا يَشْفَعُونَ إِلَّا لِمَنِ ارْتَضَىٰ وَهُم مِّنْ خَشْيَتِهِ مُشْفِقُونَ

“ለወደደውም ሰው እንጅ ለሌላው አያማልዱም” የሚለው ሃይለ-ቃል መላእክት ለአማንያን እንደሚያማልዱ ያሳያል፤ ሌላው አማላጆች አላህ ቃል ኪዳን የገባላቸው ነብያት ናቸው፦
19፥87 *አልረሕማን ዘንድ ቃል ኪዳንን የያዘ ሰው ቢኾን እንጂ ማማለድን አይችሉም*፡፡ لَّا يَمْلِكُونَ الشَّفَاعَةَ إِلَّا مَنِ اتَّخَذَ عِندَ الرَّحْمَـٰنِ عَهْدًا
2፥255 *ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢኾን እንጅ የሚያማልድ ማነው?* مَن ذَا الَّذِي يَشْفَعُ عِندَهُ إِلَّا بِإِذْنِهِ
33፥7 *ከነቢያትም የጠበቀ ኪዳናቸውን ከአንተም፣ ከኑሕም፣ ከኢብራሒምም፣ ከሙሳም እና ከመርየም ልጅ ከዒሳም ጋር በያዝን ጊዜ አስታውስ፡፡ ከእነርሱም የከበደን ቃል ኪዳን ያዝን*፡፡ وَإِذْ أَخَذْنَا مِنَ النَّبِيِّينَ مِيثَاقَهُمْ وَمِنكَ وَمِن نُّوحٍ وَإِبْرَاهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ ۖ وَأَخَذْنَا مِنْهُم مِّيثَاقًا غَلِيظًا
ነጥብ ሁለት
“አማላጅ የለም”
ከላይ በግልፅና በማያሻማ መልኩ አላህ የፈቀደለት አማላጅ እና የሚማለድለት ተመላጅ ሰው እንዳለ ተቀምጧል፦
10፥3 *ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም፡፡ እነሆ! አላህ ጌታችሁ ነውና አምልኩት፤ አትገሰጹምን?* مَا مِن شَفِيعٍ إِلَّا مِن بَعْدِ إِذْنِهِ ۚ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ فَاعْبُدُوهُ ۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ

“ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት “አንድም አማላጅ የለም” ነገር ግን “ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ”።
ነገር ግን ጣዖታውያን ቁሬሾች ከአላህም ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ያመልካሉ፤ “እነዚህም አላህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው” ይላሉ፤ እነዚህም በትንሳኤ ቀን፦ “እነዚያንም እነርሱ በእናንተ ውስጥ ለአላህ ተጋሪዎች ናቸው የምትሉዋቸውን አማላጆቻችሁን ከእናንተ ጋር አናይም” ይባላሉ፦
10፥18 *ከአላህም ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ያመልካሉ፤ “እነዚህም አላህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው” ይላሉ*፡፡ وَيَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ مَا لَا يَضُرُّهُمْ وَلَا يَنفَعُهُمْ وَيَقُولُونَ هَـٰؤُلَاءِ شُفَعَاؤُنَا عِندَ اللَّهِ
6፥94 *እነዚያንም እነርሱ በእናንተ ውስጥ ለአላህ ተጋሪዎች ናቸው የምትሉዋቸውን አማላጆቻችሁን ከእናንተ ጋር አናይም፤ ግንኙነታችሁ በእርግጥ ተቋረጠ፡፡ ከእናንተም ያ ያማልደናል የምትሉት ጠፋ* ይባላሉ፡፡ وَمَا نَرَىٰ مَعَكُمْ شُفَعَاءَكُمُ الَّذِينَ زَعَمْتُمْ أَنَّهُمْ فِيكُمْ شُرَكَاءُ ۚ لَقَد تَّقَطَّعَ بَيْنَكُمْ وَضَلَّ عَنكُم مَّا كُنتُمْ تَزْعُمُونَ

እነዚያ ጣዖታውያን በአላህ ሌላ የሚያጋሩትን ጣዖታት፦ “አማላጆቻችን ናቸው” ይበሉ እንጂ ለእነርሱ ወደ አላህ የሚያማልድ አማላጅ የላቸው፦
6፥51 *እነዚያንም ከእርሱ ሌላ ረዳት እና አማላጅም የሌላቸው ሲኾኑ ወደ ጌታቸው መስሰብሰብን የሚፈሩትን ይጠነቀቁ ዘንድ በእርሱ በቁርኣን አስጠንቅቅ*፡፡ وَأَنذِرْ بِهِ الَّذِينَ يَخَافُونَ أَن يُحْشَرُوا إِلَىٰ رَبِّهِمْ ۙ لَيْسَ لَهُم مِّن دُونِهِ وَلِيٌّ وَلَا شَفِيعٌ لَّعَلَّهُمْ يَتَّقُونَ
40፥18 *ለበዳዮች ምንም ወዳጅ እና ተሰሚ አማላጅ የላቸውም*፡፡ مَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ حَمِيمٍ وَلَا شَفِيعٍ يُطَاع
32፥4 *ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት እናም አማላጅም ምንም የላችሁም፤ አትገሰጹምን?* مَا لَكُم مِّن دُونِهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا شَفِيعٍ ۚ أَفَلَا تَتَذَكَّرُون

“አትገሰጹምን” የሚለው ያልተገሰጹትን በዳዮች ነው፤ “ለበዳዮች ምንም ወዳጅ እና ተሰሚ አማላጅ የላቸውም” የሚለው ይሰመርበት፤ “ማ ለኩም ሚን ዱኒሂ ሚን ወሊይ” مَا لَكُمْ مِنْ دُونِهِ مِنْ وَلِيٍّ ማለትም “ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም” ማለት ሲሆን ከአላህ ውጪ በጀነት ለመጥቀምና በጀሃነም ለመቅጣት የሚችል ማንም እረዳት የላቸውም፤ “ሚን ዱኒሂ” مِنْ دُونِهِ ማለትም “ከእርሱ ሌላ” የሚለው ተሳቢ ተውላጠ-ስም ከሰዋስው አንፃር አላህ ብቻ በመጥቀምና በመጉዳት ረዳት መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፦
18፥26 *ለእነርሱ ከእርሱ በቀር ምንም ረዳት የላቸውም፤ በፍርዱም አንድንም አያጋራም*። أَبْصِرْ بِهِ وَأَسْمِعْ ۚ مَا لَهُم مِّن دُونِهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا يُشْرِكُ فِي حُكْمِهِ أَحَدًا

አንቀጹ ላይ፦ “ወላ ሸፊዒን” وَلَا شَفِيعٍ ማለት “እና አማላጅም የላችሁም” ማለት ሲሆን ከመጀመሪያው ሀረግ ለመለየት “ወ” وَ የሚል መስተዋድድ ይጠቀማል፤ ያ ማለት “በተጨማሪም አማላጅም የላችሁም” ማለት ነው፤ “ላ” لَا የሚለው “ሐርፉ ነፍይ” አፍራሽ ቃል ነው፤ ስለዚህ በመጀመሪያው ሀረግ ላይ “ማ” مَا የሚለው “መስደሪያ” አፍራሽ ቃል ሆኖ ገብቶ በተጨማሪ በሁለተኛው ሃረግ ላይ “ላ” لَا የሚለው አፍራሽ ቃል መደገሙ ጣኦታውያን ጣኦቶቻቸውን ወደ አላህ በማማለድ ያቀርቡናል ብለው የሚናገሩላቸውን ጣኦታት አማላጆች አለመሆናቸውን ለማሳየት “አማላጅ የላችሁም” በማለት ዘግቶታል፤ ለእነርሱም ከሚያጋሩዋቸው አማላጆች አይኖሯቸውም፦
30፥13 *ለእነርሱም ከሚያጋሩዋቸው አማላጆች አይኖሯቸውም*፤ وَلَمْ يَكُن لَّهُم مِّن شُرَكَائِهِمْ شُفَعَاءُ

ስለዚህ “አማላጅም ምንም የላችሁም” ማለት “ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ካልሆነ በቀር እናንተ ከምታጋሯቸው የሚያማልድ አንድም አማላጅ የለም” ማለት ነው እንጂ በአላህ ፈቃድ የሚያማልዱ አማላጆች የሉም ማለት አሊያም አላህ አማላጅ ነው ማለት አይደለም። ከአላህ ሌላ ከቅጣት ሊያድናቸው የሚችል ረዳት የላቸውም፤ እንዲሁ ቅጣት እንዳይቀጡ ወደ አላህ የሚያማልዱ አማላጅ የላቸውም ማለት ነው፦
36፥23 *”ከእርሱ ሌላ አማልክትን እይዛለሁን? አልረህማን በጉዳት ቢሻኝ ምልጃቸው ከእኔ ለመመለስ ምንም አትጠቅመኝም፤ አያድኑኝምም*፡፡ أَأَتَّخِذُ مِن دُونِهِ آلِهَةً إِن يُرِدْنِ الرَّحْمَـٰنُ بِضُرٍّ لَّا تُغْنِ عَنِّي شَفَاعَتُهُمْ شَيْئًا وَلَا يُنقِذُونِ

ሙፈሲሮችም በዚህ መልኩ ነው ተረድተው ያስቀመጡት:-
ተፍሲሩል ኢብኑ ከሲር 32፥4
*”ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም” ማለት “እርሱ ብቻ ሉአላዊ የሁሉንም ጉዳዮች ተቆጣጣሪ፣ የሁሉም ነገር ፈጣሪ፣ ሁሉን ነገር አድራጊ ነው፤ ከእርሱ ሌላ ፈጣሪ የለም” ማለት ነው። “እናም አማላጅም ምንም የላችሁም” ማለት “ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም” ማለት ነው*።
( ما لكم من دونه من ولي ولا شفيع )
أي : بل هو المالك لأزمة الأمور ، الخالق لكل شيء ، المدبر لكل شيء ، القادر على كل شيء ، فلا ولي لخلقه سواه ، ولا شفيع إلا من بعد إذنه .

መላእክት፣ ነቢያት፣ ሙዑሚን ያማልዳሉ ማለት እና እኛ ወደ ፍጡራን በሌሉበት መለማመን፣ መጠየቅ እና መጸለይ ይለያያል፤ ወደ ፍጡራን በሌሉበት መለማመን፣ መጠየቅ እና መጸለይ ምልጃ ሳይሆን ሺርክ ነው። የሁሉንም ፍጥረት ልመና፣ ጥያቄ እና ጸሎት ጊዜና ቦታ ሳይወስነው ሁሉን የሚሰማ፣ ሁሉን የሚያይ እና ሁሉን የሚያውቅ የዐለማቱ ጌታ አላህ ብቻ ነው።

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር አምስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 5
አላህ ያለሚስት ልጅ ሊኖረው ይችላል ወይስ አይችልም?

ይችላል፡-
ሱራ 39፡4 “አላህ ልጅን መያዝ በፈለገ ኖሮ ከሚፈጥረው ውስጥ የሚሻውን ይመርጥ ነበር ጥራት ተገባው፡፡”

አይችልም፡–
ሱራ 6፡101 “… ለርሱ ሚስት የሌለችው ሲሆን እንዴት ልጅ ይኖረዋል?”

መልስ
አበይት ክርስቲያኖች ኢየሱስ ዓለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቆጠር አብን አህሎና መስሎ ከአብ “ባህርይ ዘእም-ባህርይ አካል ዘእም-አካል” ማለትም ከባህርይው ባህርይ ወስዶ ከአካሉ አካሉን ወስዶ ተወለደ ይሉናል። ልጅ ከአባቱ አብራክ ሲገኝ ልጅ የአባት ቢጤ፣ ተጋሪ እና ወራሽ ነው፤ ሰው ሰውን ሲወልድ ሁለት ሰው እንጂ አንድ ሰው እንደማይባል ሁሉ “አምላክ ዘእም-አምላክ” ማለትም ከአምላክ አምላክ ከተገኘ ሁለት አምላክ ይሆናል። አምላካችን አላህ ቁርኣን ካወረደበት ምክንያት አንዱ እነዚያንም፦ “አላህ ልጅን ይዟል” ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት ነው፦
18፥4 *እነዚያንም፦ “አላህ ልጅን ይዟል” ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት አወረደው*፡፡ وَيُنذِرَ الَّذِينَ قَالُوا اتَّخَذَ اللَّهُ وَلَدًا

ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል፦
19፥35 *ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል*፡፡ مَا كَانَ لِلَّهِ أَن يَتَّخِذَ مِن وَلَدٍ ۖ سُبْحَانَهُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ
4፥171 *ለእርሱ ልጅ ያለው ከመኾን የጠራ ነው፡፡ በሰማያትና በምድር ያለ ሁሉ የእርሱ ነው*፡፡ መመኪያም በአላህ በቃ፡፡ سُبْحَانَهُ أَن يَكُونَ لَهُ وَلَدٌ ۘ لَّهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۗ وَكَفَىٰ بِاللَّهِ وَكِيلًا
10፥68 *«አላህ ልጅን ያዘ» አሉ፡፡ ከሚሉት ጥራት ተገባው፡፡ እርሱ ተብቃቂ ነው፡፡ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ እናንተ ዘንድ በዚህ በምትሉት ምንም አስረጅ የላችሁም፡፡ በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁን?* قَالُوا اتَّخَذَ اللَّهُ وَلَدًا ۗ سُبْحَانَهُ ۖ هُوَ الْغَنِيُّ ۖ لَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۚ إِنْ عِندَكُم مِّن سُلْطَانٍ بِهَـٰذَا ۚ أَتَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ
19፥92 *ለአልረሕማን ልጅን መያዝ አይገባውም*፡፡ وَمَا يَنبَغِي لِلرَّحْمَـٰنِ أَن يَتَّخِذَ وَلَدًا

ልጅ መጫወቻ መደሰቻ ነው፤ ይህም የቅርቢቱም ሕይወት ጨዋታ ነው፦
6፥32 *የቅርቢቱም ሕይወት ጨዋታ እና ላግጣ እንጅ ሌላ አይደለችም*፡፡ وَمَا الْحَيَاةُ الدُّنْيَا إِلَّا لَعِبٌ وَلَهْوٌ ۖ

አላህ ልጅን መያዝ ቢፈል ኖሮ ከእርሱ ዘንድ ይይዝ ነበር፤ ነገር ግን ጥራት ይገባው ያንን ሰሪ አይደለም፤ ልጅ አለው የሚሉት ብርቱ ቅጣት አላቸው፦
21፥17 *መጫወቻን ልንይዝ በሻን ኖሮ ከእኛ ዘንድ በያዝነው ነበር፡፡ ግን ሠሪዎች አይደለንም*፡፡ لَوْ أَرَدْنَا أَن نَّتَّخِذَ لَهْوًا لَّاتَّخَذْنَاهُ مِن لَّدُنَّا إِن كُنَّا فَاعِلِينَ
“ከእኛ ዘንድ” ማለት “ከሚፈጥረው” ማለት ነው፤ ለምሳሌ ልጅ ከእርሱ ዘንድ የሚሰጥ ነውና፦
39፥4 *አላህ ልጅን መያዝ በፈለገ ኖሮ “ከሚፈጥረው” ውስጥ የሚሻውን ይመርጥ ነበር፡፡ ጥራት ተገባው፡፡ እርሱ አሸናፊው አንዱ አላህ ነው*፡፡ لَّوْ أَرَادَ اللَّهُ أَن يَتَّخِذَ وَلَدًا لَّاصْطَفَىٰ مِمَّا يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ سُبْحَانَهُ ۖ هُوَ اللَّهُ الْوَاحِدُ الْقَهَّارُ
19፥5 «እኔም ከበኋላዬ ዘመዶቼን በእርግጥ ፈራሁ፡፡ ሚስቴም መካን ነበረች ስለዚህ *ከአንተ ዘንድ ለእኔ ልጅን ስጠኝ*፡፡ وَإِنِّي خِفْتُ الْمَوَالِيَ مِن وَرَائِي وَكَانَتِ امْرَأَتِي عَاقِرًا فَهَبْ لِي مِن لَّدُنكَ وَلِيًّا

“ከሚፈጥረው” እና “ከአንተ ዘንድ” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ “ከእኛ ዘንድ” ማለት እርሱ ዘንድ ያሉትም መላእክት ያመለክታል፤ ምክንያቱም ዐውዱ ላይ፦ “አልረሕማንም ከመላእክት ልጅን ያዘ” ብለዋልና፦
21፥19 በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉም የእርሱ ነው፡፡ *እርሱ ዘንድ ያሉትም መላእክት* እርሱን ከመገዛት አይኮሩም፡፡ አይሰለቹምም፡፡ وَلَهُ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ وَمَنْ عِندَهُ لَا يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِهِ وَلَا يَسْتَحْسِرُونَ
21፥26 *«አልረሕማንም ከመላእክት ልጅን ያዘ» አሉ፡፡ ጥራት ተገባው፡፡ አይደለም መላእክት የተከበሩ ባሮች ናቸው*፡፡ وَقَالُوا اتَّخَذَ الرَّحْمَـٰنُ وَلَدًا ۗ سُبْحَانَهُ ۚ بَلْ عِبَادٌ مُّكْرَمُونَ

የፈርዖንም ሚስት፦ “ለእኔ ለአንተም ልጅ አድርገን ልንይዘው” ማለቷ ይህ ልጅ አድርጎ መያዝ የፍጡር ባህርይ ነው፦
28፥9 የፈርዖንም ሚስት፦ “ለእኔ ለአንተም የዓይኔ መርጊያ ነው፤ አትግደሉት፡፡ ሊጠቅመን ወይም *ልጅ አድርገን ልንይዘው ይከጀላልና”* አለች፡፡ እነርሱም ፍጻሜውን የማያውቁ ሆነው አነሱት፡፡ وَقَالَتِ امْرَأَتُ فِرْعَوْنَ قُرَّتُ عَيْنٍ لِّي وَلَكَ ۖ لَا تَقْتُلُوهُ عَسَىٰ أَن يَنفَعَنَا أَوْ نَتَّخِذَهُ وَلَدًا وَهُمْ لَا يَشْعُرُونَ

ኸረ ልጅ ያዘ ከማለትም አልፈው ወለደ ብለዋል፤ እነርሱም በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው፤ አላህ አልወለደም፤ አልተወለደምም፦
37፥152 ፦ “አላህ ወለደ” አሉ፤ እነርሱም በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው፡፡ وَلَدَ اللَّهُ وَإِنَّهُمْ لَكَاذِبُونَ
112፥3 *አልወለደም፤ አልተወለደምም*፡፡ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ

አላህ የሚጋራው ባልደረባ ስለሌለው ልጅም አይኖረውም፤ ምክንያቱም ልጅ የአባት ምትክ፣ ተጋሪ፣ ሞክሼ ስለሚሆን ነው፦
6፥101 እርሱ ሰማያትንና ምድርን ያለ ብጤ ፈጣሪ ነው፡፡ *ለእርሱ ሚስት የሌለችው ሲኾን እንዴት ለእርሱ ልጅ ይኖረዋል? ነገርንም ሁሉ ፈጠረ*፡፡ እርሱም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ بَدِيعُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ أَنَّىٰ يَكُونُ لَهُ وَلَدٌ وَلَمْ تَكُن لَّهُ صَاحِبَةٌ ۖ وَخَلَقَ كُلَّ شَيْءٍ ۖ وَهُوَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

“የኩኑ” يَكُونُ ማለት “ይኖረዋል” ማለት ሲሆን ባሕርይን ያሳያል፤ አላህ ነገርንም ሁሉ ፈጠረ፤ ልጅ የሚመጣው በሴት ነው። ያለ ሴት እንዴት ልጅ ይኖራል? የሚለው የሥነ-አመክንዮ ጥያቄ ነው። ይህ ባሕርይ ታሳቢ ያደረገ እንጂ ችሎታን ታሳቢ ያደረገ አይደለም። እንዴት ይችላል? ተብሎ አልተጠየቀም። ሲቀጥል ከመነሻው “ሚስት” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሷሒበት” صَٰحِبَة ሲሆን “ባልደረባ” ማለት ነው፤ “አስሐብ” أَصْحَٰب ወይም “ሷሒብ صَاحِب ደግሞ “ባልደረባ” “አጋር” “ሞክሼ” “ባለንጀራ” ከሆነ ፈጣሪ ከመነሻው “ባልደረባ” “ተጋሪ” “አጋር” “ሞክሼ” “ባለንጀራ” የለውም፦
6፥163 *ለእርሱ ተጋሪ የለውም፡፡ በዚህም በማጥራት ታዘዝኩ*፡፡ እኔም የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ» በል፡፡ لَا شَرِيكَ لَهُ ۖ وَبِذَٰلِكَ أُمِرْتُ وَأَنَا أَوَّلُ الْمُسْلِمِينَ

ከእርሱም ጋር አንድም አምላክ የለም፤ ምንም ልጅን አልያዘም፤ ለአልረሕማን ልጅ የለውም እንጂ ቢኖረው እንገዛው ነበር ማለት አለመኖሩን የሚያጸና ነው፤ ለምሳሌ አንተ አምላክ ብትሆን አመልክህ ነበር ማለት አምላክ አይደለህም ማለት ነው፤ በተመሳሳይም ልጅ የለውም ማለት ነው፦
23፥91 *አላህ ምንም ልጅን አልያዘም፡፡ ከእርሱም ጋር አንድም አምላክ የለም፡፡ ያን ጊዜ ሌላ አምላክ በነበረ ኖሮ አምላክ ሁሉ በፈጠረው ነገር በተለየ ነበር፡፡ ከፊላቸውም በከፊሉ ለይ በላቀ ነበር፡፡ አላህ ከሚመጥኑት ሁሉ ጠራ*፡፡ مَا اتَّخَذَ اللَّهُ مِن وَلَدٍ وَمَا كَانَ مَعَهُ مِنْ إِلَـٰهٍ ۚ إِذًا لَّذَهَبَ كُلُّ إِلَـٰهٍ بِمَا خَلَقَ وَلَعَلَا بَعْضُهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ ۚ سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يَصِفُونَ

ስለዚህ እንዴት ይኖረዋል ማለት ባሕርይን ታሳቢ ያደረገ ሲሆን ቢፈልግል ከሚፈጥረው ይይዝ ነበር ማለት ደግሞ ችሎታን ዋቢ ያደረገ ነው።

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር ስድስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 6
አላህ ብቸኛ ረዳት ወይስ ሌሎች ረዳቶችም አሉ?

አላህ ብቸኛ ረዳት፡–
ሱራ 9፡116 “አላህ የሰማያትና የምድር ንግስና የርሱ ብቻ ነው፡፡ ህያው ያደርጋል ይገድላልም፤ ለናንተም ከርሱ በቀር ጠባቂም ረዳትም የላችሁም”

ሌሎች ረዳቶችም አሉ፡–
ሱራ 5፡55 “ረዳታችሁ አላህና መልክተኛው እነዚያም ያመኑት ብቻ ናቸው…”

መልስ
“እረዳት” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ወሊይ” وَلِىّ ወይም “ነሲር” نَصِير ሲሆን የአላህ እረዳትነት በመጥቀም ሆነ ከጉዳት በማዳን፣ በማሞት ሆነ ሕያው በማድረግ፤ ለሰናይ ሥራ በመሸለምና ለእኩይ ሥራ በመቅጣት ነው። በዚህ ስሌት አላህ ብቻውን እረዳት ነው። ከእርሱ ሌላ እረዳት የለም፦
4፥123 ነገሩ በምኞታችሁና በመጽሐፉ ሰዎች ምኞት አይደለም፡፡ *መጥፎን የሚሠራ ሰው በእርሱ ይቀጣል፡፡ ለእርሱም ከአላህ ሌላ ጠባቂንም ረዳትንም አያገኝም*፡፡ لَّيْسَ بِأَمَانِيِّكُمْ وَلَا أَمَانِيِّ أَهْلِ الْكِتَابِ ۗ مَن يَعْمَلْ سُوءًا يُجْزَ بِهِ وَلَا يَجِدْ لَهُ مِن دُونِ اللَّهِ وَلِيًّا وَلَا نَصِيرًا
4፥145 *መናፍቃን በእርግጥ ከእሳት በታችኛው አዘቅት ውስጥ ናቸው፡፡ ለእነርሱም ረዳትን አታገኝላቸውም*፡፡ إِنَّ الْمُنَافِقِينَ فِي الدَّرْكِ الْأَسْفَلِ مِنَ النَّارِ وَلَن تَجِدَ لَهُمْ نَصِيرًا
4፥173 *እነዚያማ ያመኑት መልካሞችንም የሠሩት ምንዳዎቻቸውን ይሞላላቸዋል፡፡ ከችሮታውም ይጨምርላቸዋል፡፡ እነዚያን የተጠየፉትንና የኮሩትንማ አሳማሚን ቅጣት ይቀጣቸዋል፡፡ ከአላህም ሌላ ለእነርሱ ዝምድንና ረዳትን አያገኙም*፡፡ فَأَمَّا الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ فَيُوَفِّيهِمْ أُجُورَهُمْ وَيَزِيدُهُم مِّن فَضْلِهِ ۖ وَأَمَّا الَّذِينَ اسْتَنكَفُوا وَاسْتَكْبَرُوا فَيُعَذِّبُهُمْ عَذَابًا أَلِيمًا وَلَا يَجِدُونَ لَهُم مِّن دُونِ اللَّهِ وَلِيًّا وَلَا نَصِيرًا
2፥107 አላህ የሰማያትና የምድር ንግሥና ለእርሱ ብቻ መኾኑን አታውቅምን? *ለእናንተም ከአላህ ሌላ ዘመድና ረዳት ምንም የላችሁም*። أَلَمْ تَعْلَمْ أَنَّ اللَّهَ لَهُ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۗ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ اللَّهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا نَصِيرٍ
9፥116 አላህ የሰማያትና የምድር ንግስና የእርሱ ብቻ ነው፡፡ *ሕያው ያደርጋል፤ ይገድላልም፡፡ ለእናንተም ከእርሱ በቀር ጠባቂም ረዳትም የላችሁም*፡፡ إِنَّ اللَّهَ لَهُ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ يُحْيِي وَيُمِيتُ ۚ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ اللَّهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا نَصِيرٍ

የወሊይ ብዙ ቁጥር “አውሊያ” أَوْلِيَاءَ ሲሆን ሰዎች እንደ አላህ ይረዱናል ብለው የሚይዟቸው እረዳቶች ብዙ ናቸው፤ ለምሳሌ የሚጠነቁሉና የሚያስጠነቁሉ ሰዎች ከአላህ ሌላ ይጠቅመኛል ይጎዳኛል ብሎ ሰይጣናትን ከአላህ ሌላ ረዳቶች አድርገው ይዘዋል፦
7፥30 ከፊሉን ወደ ቅን መንገድ መራ፡፡ ከፊሎቹም በእነርሱ ላይ ጥመት ተረጋግጦባቸዋል፡፡ *እነርሱ ሰይጣናትን ከአላህ ሌላ ረዳቶች አድርገው ይዘዋልና*፡፡ እነርሱም ቅኑን መንገድ የተመራን ነን ብለው ያስባሉ፡፡ فَرِيقًا هَدَىٰ وَفَرِيقًا حَقَّ عَلَيْهِمُ الضَّلَالَةُ ۗ إِنَّهُمُ اتَّخَذُوا الشَّيَاطِينَ أَوْلِيَاءَ مِن دُونِ اللَّهِ وَيَحْسَبُونَ أَنَّهُم مُّهْتَدُونَ

ሰዎች በተጨማሪም ወደ ነቢያትንና መላእክትን ዱዓ በማድረግ ሲለማመኑ ከአላህ ሌላ ረዳቶች አድርገው ይዘዋል፦
18፥102 እነዚያ የካዱት *ባሮቼን ከእኔ ሌላ አማልክት አድርገው መያዛቸውን የማያስቆጣኝ አድርገው አሰቡን?* እኛ ገሀነምን ለከሓዲዎች መስተንግዶ አዘጋጅተናል፡፡ أَفَحَسِبَ الَّذِينَ كَفَرُوا أَن يَتَّخِذُوا عِبَادِي مِن دُونِي أَوْلِيَاءَ ۚ إِنَّا أَعْتَدْنَا جَهَنَّمَ لِلْكَافِرِينَ نُزُلًا
17፥56 *«እነዚያን ከእርሱ ሌላ የምትሏቸውን ጥሩ፡፡ ከእናንተም ላይ ጉዳትን ማስወገድን ወደ ሌላ ማዞርንም አይችሉም»* በላቸው፡፤ قُلِ ادْعُوا الَّذِينَ زَعَمْتُم مِّن دُونِهِ فَلَا يَمْلِكُونَ كَشْفَ الضُّرِّ عَنكُمْ وَلَا تَحْوِيلًا

ሙሽሪኮች ጣዖቶቻቸውን ከአላህ ሌላ ይጠቅሙናል ይጎዱናል ብለው በማለት እረዳቶች አድርገው ይዘዋል፦
13፥16 «የሰማያትና የምድር ጌታ ማን ነው» በላቸው፡፡ «አላህ ነው» በል፡፡ *«ለነፍሶቻቸው ጥቅምንም ጉዳትንም የማይችሉን ረዳቶች ከእርሱ ሌላ ያዛችሁን»* በላቸው፡፡ قُلْ مَن رَّبُّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ قُلِ اللَّهُ ۚ قُلْ أَفَاتَّخَذْتُم مِّن دُونِهِ أَوْلِيَاءَ لَا يَمْلِكُونَ لِأَنفُسِهِمْ نَفْعًا وَلَا ضَرًّا ۚ
29፥41 *የእነዚያ ከአላህ ሌላ ረዳቶችን የያዙ ሰዎች ምሳሌ ቤትን እንደ ሠራች ሸረሪት ብጤ ነው፡፡ ከቤቶችም ሁሉ በጣም ደካማው የሸረሪት ቤት ነው፡፡ ቢያውቁ ኖሮ አማልክት አድርገው አይግገዟቸውም ነበር*፡፡ مَثَلُ الَّذِينَ اتَّخَذُوا مِن دُونِ اللَّهِ أَوْلِيَاءَ كَمَثَلِ الْعَنكَبُوتِ اتَّخَذَتْ بَيْتًا ۖ وَإِنَّ أَوْهَنَ الْبُيُوتِ لَبَيْتُ الْعَنكَبُوتِ ۖ لَوْ كَانُوا يَعْلَمُونَ

ይህንን ያደረጉበት መረዳትንም በመከጀል፣ መከበሪያ እንዲኾኑዋቸው፣ መቃረቢያ ይኾኑ ዘንድ ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ፦
36፥74 *መረዳትንም በመከጀል* ከአላህ ሌላ አማልክትን ያዙ፡፡ وَاتَّخَذُوا مِن دُونِ اللَّهِ آلِهَةً لَّعَلَّهُمْ يُنصَرُونَ
46፥28 *እነዚያም መቃረቢያ ይኾኑ ዘንድ ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው የያዙዋቸው አይረዷቸውም ኖሯልን?* በእርግጥ ከእነርሱ ራቁ፡፡ ይህም ውሸታቸውና በልማድ ይቀጥፉት የነበሩት ነው፡፡ فَلَوْلَا نَصَرَهُمُ الَّذِينَ اتَّخَذُوا مِن دُونِ اللَّهِ قُرْبَانًا آلِهَةً ۖ بَلْ ضَلُّوا عَنْهُمْ ۚ وَذَٰلِكَ إِفْكُهُمْ وَمَا كَانُوا يَفْتَرُونَ
19፥81 *ከአላህም ሌላ አማልክትን ለእነርሱ መከበሪያ እንዲኾኑዋቸው ያዙ*፡፡ وَاتَّخَذُوا مِن دُونِ اللَّهِ آلِهَةً لِّيَكُونُوا لَهُمْ عِزًّا
“አሊሀህ” آلِهَةٌ ማለትም “አማልክት” የሚለው ቃል “አውሊያ” أَوْلِيَاءَ በሚለው ተለዋዋጭ ቃል”interchange” ሆኖ መጥቷል፦
42፥6 *እነዚያም ከእርሱ ሌላ ረዳቶችን የያዙ*፤ አላህ በእነርሱ ላይ ተጠባባቂ ነው፡፡ አንተም በእነርሱ ላይ ኀላፊ አይደለህም፡፡ وَالَّذِينَ اتَّخَذُوا مِن دُونِهِ أَوْلِيَاءَ اللَّهُ حَفِيظٌ عَلَيْهِمْ وَمَا أَنتَ عَلَيْهِم بِوَكِيلٍ
25፥3 *ከሓዲዎች ከእርሱም ሌላ ምንንም የማይፈጥሩን፣ እነርሱም የሚፈጠሩን፣ ለነፍሶቻቸውም ጉዳትን ለመከላከል ጥቅምንም ለማምጣት የማይችሉን ሞትንና ሕይወትንም መቀስቀስንም የማይችሉን፣ አማልክት ያዙ*፡፡ وَاتَّخَذُوا مِن دُونِهِ آلِهَةً لَّا يَخْلُقُونَ شَيْئًا وَهُمْ يُخْلَقُونَ وَلَا يَمْلِكُونَ لِأَنفُسِهِمْ ضَرًّا وَلَا نَفْعًا وَلَا يَمْلِكُونَ مَوْتًا وَلَا حَيَاةً وَلَا نُشُورًا
21፥24 ይልቁንም *ከእርሱ ሌላ አማልክትን ያዙን?* «ማስረጃችሁን አምጡ፡፡ أَمِ اتَّخَذُوا مِن دُونِهِ آلِهَةً ۖ قُلْ هَاتُوا بُرْهَانَكُمْ ۖ
21፥21 *ይልቁንም ከምድር የኾኑን እነርሱ ሙታንን የሚያስነሱን አማልክት ያዙን?* የለም፡፡ أَمِ اتَّخَذُوا آلِهَةً مِّنَ الْأَرْضِ هُمْ يُنشِرُونَ

ስለዚህ “ወሊይ” وَلِىّ የሚለው “ኢላህ” إِلَٰه ማለትም “አምላክ” በሚለው ከመጣ ከአላህ በቀር መፍጠር፣ ማሞት፣ ሕያው ማድረግ የሚችል እረዳት የለም ማለት ነው፦
42፥9 *ከእርሱ ሌላ እረዳቶችን ያዙን? እረዳቶች አይደሉም፡፡ አላህም እረዳት እርሱ ብቻ ነው፡፡ እርሱም ሙታንን ሕያው ያደርጋል፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው*፡፡ أَمِ اتَّخَذُوا مِن دُونِهِ أَوْلِيَاءَ ۖ فَاللَّهُ هُوَ الْوَلِيُّ وَهُوَ يُحْيِي الْمَوْتَىٰ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
7፥3 ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ፡፡ *ከአላህም ሌላ ረዳቶችን አትከተሉ*፡፡ ጥቂትን ብቻ ትገሰጻላችሁ፡፡ اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ وَلَا تَتَّبِعُوا مِن دُونِهِ أَوْلِيَاءَ ۗ قَلِيلًا مَّا تَذَكَّرُونَ

“ምእምንና ምእምናትም ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው” የተባሉበት አላህ በተባለበት ስሌትና ቀመር ሳይሆን አላህ እና መልእክተኛው ባስቀመጡት ሑክም በመልካም በማዘዝና ከመጥፎ በመከልከል ነው፦
9፥71 *ምእምንና ምእምናትም ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡ በደግ ነገር ያዛሉ፤ ከክፉም ይከለክላሉ*፡፡ ሶላትንም ይሰግዳሉ፡፡ ዘካንም ይሰጣሉ፡፡ *አላህንና መልክተኛውንም ይታዘዛሉ*፡፡ እነዚያን አላህ በእርግጥ ያዝንላቸዋል፡፡ አላህ አሸናፊ ጥበበኛ ነውና፡፡ وَالْمُؤْمِنُونَ وَالْمُؤْمِنَاتُ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَاءُ بَعْضٍ ۚ يَأْمُرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَوْنَ عَنِ الْمُنكَرِ وَيُقِيمُونَ الصَّلَاةَ وَيُؤْتُونَ الزَّكَاةَ وَيُطِيعُونَ اللَّهَ وَرَسُولَهُ ۚ أُولَـٰئِكَ سَيَرْحَمُهُمُ اللَّهُ ۗ إِنَّ اللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٌ
3፥104 *ከእናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ በመልካም ሥራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ*፡፡ እነዚያም እነሱ የሚድኑ ናቸው፡፡ وَلْتَكُن مِّنكُمْ أُمَّةٌ يَدْعُونَ إِلَى الْخَيْرِ وَيَأْمُرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَوْنَ عَنِ الْمُنكَرِ ۚ وَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْمُفْلِحُونَ

እሩቅ ሳንሄድ በቤተሰብ ደረጃ ወንድም ለወንድሙ እረዳት ይሆናል እኮ፤ ለምሳሌ ሙሳ ወንድሙን ሃሩንን እረዳት እንዲሆንለት አላህ ለምሎ ነበር፤ አላህም ልመናውን ሰምቶ እረዳት አደረገለት፦
28፥34 «ወንድሜም ሃሩን እርሱ ምላሱ ከእኔ የተባ ነው፡፡ እውነተኛነቴንም የሚያረጋግጥልኝ *እረዳት* ኾኖ ከእኔ ጋር ላከው፡፡ እኔ ሊያስተባብሉኝ እፈራለሁና፡፡» وَأَخِي هَارُونُ هُوَ أَفْصَحُ مِنِّي لِسَانًا فَأَرْسِلْهُ مَعِيَ رِدْءًا يُصَدِّقُنِي ۖ إِنِّي أَخَافُ أَن يُكَذِّبُونِ
30፥29 «ከቤተሰቦቼም ለእኔ *እረዳትን* አድርግልኝ፡፡ وَاجْعَل لِّي وَزِيرًا مِّنْ أَهْلِي
25፥35 በእርግጥም ለሙሳ መጽሐፍን ሰጠነው፡፡ ከእርሱም ጋር ወንድሙን ሃሩንን *እረዳት* አደረግንለት፡፡ وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَى الْكِتَابَ وَجَعَلْنَا مَعَهُ أَخَاهُ هَارُونَ وَزِيرًا

ይህ አልገባ ካላችሁ ከራሳችሁ ባይብል አንድ ናሙና እናሳያችሁ፤ ፈጣሪ፦ “ከእኔ በቀር ሌላ አማላክ የለም” እያለ ይናገራል፦
ዘዳግም 32፥39 አሁንም እኔ ብቻዬን እኔ እንደ ሆንሁ፥ *ከእኔም በቀር አምላክ እንደሌለ እዩ*፤
ኢዩኤል 2፥27 እኔም አምላካችሁ ያህዌህ እንደ ሆንሁ፥ እኔም በእስራኤል መካከል እንዳለሁ፥ *ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ ታውቃላችሁ*፤ ሕዝቤም ለዘላለም አያፍርም።
ኢሳይያስ 44:6 የእስራኤል ንጉሥ ያህዌህ፥ የሚቤዥም የሠራዊት ጌታ ያህዌህ እንዲህ ይላል። እኔ ፊተኛ ነኝ እኔም ኋለኛ ነኝ፥ *ከእኔ ሌላም አምላክ የለም*።

ነገር ግን መላእክት፣ ነብያት፣ የእስራኤልን ፈራጆች አምላኮች ተብለዋል፦
መዝሙር 138:1 አቤቱ፥ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፥ የአፌን ነገር ሰምተኸኛልና፤ *“በአማልክትም”כֵּֽאלֹהִ֔ים ፊት እዘምርልሃለሁ*።
መዝሙር 82:1 እግዚአብሔር *በአማልክት ማኅበር ቆመ*፥
መዝሙር 82:6 እኔ ግን፦ *አማልክት ናችሁ*፥ ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁ፤
ዘጸአት 21:5 ባሪያውም። ጌታዬን ሚስቴን ልጅቼንም እወድዳለሁ፥ አርነት አልወጣም ብሎ ቢናገር፥ ጌታው *ወደ “አማልክትን”כֵּֽאלֹהִ֔ים ይውሰደው*፥
ዘጸአት 22:8 ሌባውም ባይገኝ ባለቤቱ *ወደ “አማልክትን”כֵּֽאלֹהִ֔ים ይቅረብ*፥ እጁንም በባልንጀራው ከብት ላይ እንዳልዘረጋ ይማል።

ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም፤ መላእክት፣ ነብያት፣ የእስራኤልን ፈራጆች አምላኮች መባላቸው የፈጣሪ አፈ-ቀላጤና ቃል አቀባይ ስለሆኑ የእነርሱም አምላክነት ስልጣንና ሹመትን እንጂ መመለክን አያመለክትም። ፈጣሪ አምላክ የተባለበት እነርሱ አምላኮች በተባሉበት ሒሳብ አይደለም ከተባለ እንግዲያውስ አላህም እረዳት የተባለው ምእመናን ለምእመናን እረዳቶች በተባሉበት ሒሳብ አይደለም ነው። በሰፈሩት ቁና መሰፈር”double standard” ይሉሃል እንደዚህ ነው።

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር ሰባት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 7
የመላእክት ስግደት ለማን ነው?

ለአላህ ብቻ፡–
ሱራ 7፡206 “እነዚያ እጌታህ ዘንድ ያሉት መላዕክት እርሱን ከመገዛት አይኮሩም ያወድሱታልም ለርሱ ብቻ ይሰግዳሉ፡፡”

ለአደም ሰግደዋል፡–
ሱራ 2፡34 “ለመላዕክት ለአደም ስገዱ ባልን ጊዜ አስታውስ ሁሉም ወዲያውኑ ሰገዱ ኢብሊስ ብቻ ሲቀር እምቢ አለ ኮራም ከከሐዲዎቹም ሆነ፡፡”

መልስ
የሰው ልጆች ሆነ ማንኛውም ነጻ ፈቃድ ያለው ፍጡር በውደታ ለአላህ የሚታዘዘው የውደታ ስግደት ይባላል፤ ይህም ስግደት “ሡጁዱል ዒባዳ” سُّجُود العبادة ማለትም “የአምልኮ ስግደት” ይባላል፦
53:62 ለአላህ “ስገዱ” وَاعْبُدُو “አምልኩትም” وَاعْبُدُو ።
22:77 እላንተ ያመናችሁ ስዎች ሆይ በስግደታችሁ አጎንብሱ፣ “በግንባራችሁም ተደፉ” وَاسْجُدُو፣ ጌታችሁንም “አምልኩ” وَاعْبُدُو ፤ በጎንም ነገር ሥሩ፤ ልትድኑ ይከጃልላችኃልና።
41፥37 ሌሊትና ቀንም ፀሐይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ ለፀሐይና ለጨረቃ “አትስገዱ”፡፡ ለእዚያም ለፈጠራቸው አላህ “ስገዱ” وَاسْجُدُو ፡፡ እርሱን ብቻ “የምታመልኩ” تَعْبُدُونَ እንደ ኾናችሁ ለሌላ አትስገዱ፡፡
7፥206 እነዚያ እጌታህ ዘንድ ያሉት መላእክት እርሱን “ከማምለክ” عِبَادَتِهِۦ አይኮሩም፡፡ ያወድሱታልም፡፡ “ለእርሱም ብቻ ይሰግዳሉ” وَيُسَبِّحُونَهُۥ ።
53፥62 ለአላህም ስገዱ አምልኩም فَٱسْجُدُوا۟ لِلَّهِ وَٱعْبُدُوا۟ ۩ ፡፡

ስግደት ከአምልኮ ጋር ከተያያዘ ያ ስግደት በኒያ “የአምልኮ ስግደት” ይሆናል፤ መላእክት “ለአላህ ብቻ ይሰግዳሉ” የተባለው ሡጁድ “ሡጁዱል ዒባዳ” سُّجُود العبادة ነው፤ ሌላው ሡጁድ ደግሞ “ሡጁዱ አተሒያ” سُّجُود التحيه ማለትም “የአክብሮት ስግደት” ነው፤ ይህ ስግደት በጥንት ባህል በሰላምታ እጅ መንሳት፣ ማጎንበስ እና መደፋትም ሲኖረው ማክበርን ያመለክታል፤ ለምሳሌ መላእክት ለአደም ሰግደው ነበር፦
7:11በእርግጥ ፈጠርናችሁ፤ ከዚያም ቀረጽናችሁ፤ ከዚያም ለመላእክቶች ለአደም “ስገዱ” اسْجُدُو አልን፤ ወዲያውም “ሰገዱ” فَسَجَدُو ፤ ኢብሊስ ሲቀር ከሰጋጆቹ አልሆነም። አላህ “ባዘዝኩህ” ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ? አለው፤ እኔ ከእርሱ የበለጥኩ ነኝ፤ ከእሳት ፈጠርከኝ፤ እርሱን ግን ከጭቃ ፈጠርከው አለ።
መቼም መላእክት ለአደም አክብሮትን እንጂ አምልኮትን እንዳልሰጡት እሙንና ቅቡል ነው፤ ምነው የዩሱፍ ወንድሞችና ወላጆች ለዩሱፍ ሰግደውለት የለ እንዴ አመለኩት ማለት ነውን? ወይስ አከበሩት?፦
12:4 ዩሱፍ ለአባቱ፦ አባቴ ሆይ! እኔ ዐሥራ አንድ ክዋክብትን ፀሐይንና ጨረቃን በሕልሜ አየሁ፤ ለእኔ “ሰጋጆች” سَاجِدِينَ ሆነው አየኋቸው ባለ ጊዜ አስታውስ ።
12:100 ወላጆቹንም በዙፋኑ ላይ አወጣቸው፤ ለእርሱም “ሰጋጆች” سُجَّد ሆነው ወረዱለት ፤ አባቴም ሆይ ይህ ፊት ያየኋት ሕልሜ ፍች ነው፤ ጌታዬ በእርግጥ እውነት አደረጋት፤

“ቂያም” قيام በሶላት ላይ “መቆም” ሲሆን የአምልኮ ክፍል ነው፤ ነገር ግን “መቆም” ሁሉ አምልኮ አይደለም፤ ምክንያቱም ሰው ለስራ ይቆማልና፣ “ሩኩዕ” رُكوع በሶላት ላይ “ማጎንበስ” ሲሆን የአምልኮ ክፍል ነው፤ ነገር ግን “ማጎንበስ” ሁሉ አምልኮ አይደለም፤ ምክንያቱም እቃ ለማንሳት ማጎንበስ አለና፣ “ሱጁድ” سُّجُود በሶላት ላይ “ስግደት” ሲሆን የአምልኮ ክፍል ነው፤ ነገር ግን “ስግደት” ሁሉ አምልኮ አይደለም፤ ምክንያቱም መላእክት ለአደም የዩሱፍ ወንድሞችና ወላጆች ለዩሱፍ ሰግደዋልና። መላእክት ለአላህ የሚሰግዱት እና ለአደም የሚሰግዱት ስግደት ይለያያል፤ ለምሳሌ መልክተኛውን እና የሥልጣን ባለቤቶችን በአላህ ፈቃድ እንታዘዛለን፤ አላህ ታዘዙ ሲባል አምልኩ ማለት ሲሆን መልክተኛውን እና የሥልጣን ባለቤቶችን ታዘዙ ማለት ደግሞ አክብሩት ማለት ነው፦
4:64 ማንንም መልክተኛ በአላህ ፈቃድ “ሊታዘዙት” لِيُطَاعَ እንጅ አልላክንም።
4፥59 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን አምልኩ፡፡ መልክተኛውን እና ከእናንተም የስልጣን ባለቤቶችን ታዘዙ፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ أَطِيعُوا۟ ٱللَّهَ وَأَطِيعُوا۟ ٱلرَّسُولَ وَأُو۟لِى ٱلْأَمْرِ مِنكُمْ
71:3 አላህን “አምልኩት” اعْبُدُو ፣ ፍሩትም፣ “ታዘዙኝም” وَأَطِيعُونِ በማለት አስጠንቅቂ ነኝ።
48:9 በአላህ እና በመልክተኛውም ልታምኑ እና ልትረዱትም “ልታከብሩትም” አላህን በጧትና ከቀትር በኋላ ልታወሱትም لِّتُؤْمِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَتُعَزِّرُوهُ وَتُوَقِّرُوهُ وَتُسَبِّحُوهُ بُكْرَةًۭ وَأَصِيلًا ።

ነገር ግን ይህ አክብሮት አቅጣጫውን ቀይሮ አምልኮ እየሆነ ስላለ ከሰላምታ ውጪ በሱጁድ ለፍጡራን ማጎብደድ፣ መተናነስ፣ ማሸርገድ ቁርአን ሲወርድ ቆሟል፤ የአክብሮት ስግደት ከአምልኮ ስግደት ጋር እንዳይደባለቅ የተከለከለው በነብያችን”ﷺ” ጊዜ ነው፦
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 9, ሐዲስ 1926:
አዝሃር ኢብኑ መርዋር እንዳለው፤ ሐማድ ኢብኑ ዘይድ እንዳለው፤ ከአዩብ፣ ከአል ቃሲሙል ሸይባኒይ፣ ዐብዲላህ ኢብኑ አቢ ዐውፋ እንዲህ አለ፡- ሙዓዝ ኢብኑ ጀበል ከሻም ምድር በተመለሰ ጊዜ *ለነቢዩ”ﷺ” ሰገደ፤ እሳቸውም፦ “ሙዓዝ ሆይ! ምንድነው ይህ?” አሉት፤ እርሱም፦ “ሻም ምድር ሄጄ ነበር፤ ለኤጲስ ቆጶሳቶቻቸው እና ለጳጳሳቶቻቸው ሲሰግዱ ተመለከትኩኝ፤ ይህንን ለእርሶ ልንሰራው ተመኘሁ” አለ፤ የአላህ መልክተኛም”ﷺ”፦ “ይህንን በፍጹም እንዳትሰሩ! እኔ ከአላህ ውጪ ስግደትን ለሰው የማዝ ብሆን ኖሮ ሴትን ለባሏ እንድትሰግድ አዛት ነበር፤ የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነው እምላለሁ፤ ሚስት የባሏን መብት እስክትወጣ ድረስ የጌታዋን የአላህ ሐቅ አትወጣምና”* አሉት حَدَّثَنَا أَزْهَرُ بْنُ مَرْوَانَ، حَدَّثَنَا حَمَّادُ بْنُ زَيْدٍ، عَنْ أَيُّوبَ، عَنِ الْقَاسِمِ الشَّيْبَانِيِّ، عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ أَبِي أَوْفَى، قَالَ لَمَّا قَدِمَ مُعَاذٌ مِنَ الشَّامِ سَجَدَ لِلنَّبِيِّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ قَالَ ‏”‏ مَا هَذَا يَا مُعَاذُ ‏”‏ ‏.‏ قَالَ أَتَيْتُ الشَّامَ فَوَافَقْتُهُمْ يَسْجُدُونَ لأَسَاقِفَتِهِمْ وَبَطَارِقَتِهِمْ فَوَدِدْتُ فِي نَفْسِي أَنْ نَفْعَلَ ذَلِكَ بِكَ ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏”‏ فَلاَ تَفْعَلُوا فَإِنِّي لَوْ كُنْتُ آمِرًا أَحَدًا أَنْ يَسْجُدَ لِغَيْرِ اللَّهِ لأَمَرْتُ الْمَرْأَةَ أَنْ تَسْجُدَ لِزَوْجِهَا وَالَّذِي نَفْسُ مُحَمَّدٍ بِيَدِهِ لاَ تُؤَدِّي الْمَرْأَةُ حَقَّ رَبِّهَا حَتَّى تُؤَدِّيَ حَقَّ زَوْجِهَا وَلَوْ سَأَلَهَا نَفْسَهَا وَهِيَ عَلَى قَتَبٍ لَمْ تَمْنَعْهُ ፡፡
ወደ ባይብል ስንገባ “ስግደት” የሚለው ቃል በዕብራይስጥ “ሻኻህ” שָׁחָה ሲሆን በግሪክ ደግሞ “ፕሩስኩኔኦ” προσκυνέω ይባላል፤ ይህም ለተለያየ ምንነት ሆነ ማንነት በኒያ”intention” የሚቀርብ አምልኮን”Adoration” ወይም አክብሮትን”prostration” ነው ለማመልከት በባይብል ተጠቅሞበታል፤ በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውም ተብሏል፦
ማቴዎስ 4፥10 ያን ጊዜ ኢየሱስ፦ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን *”ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ”* ተብሎ ተጽፎአልና አለው።
ዘዳግም 5፥8-9 በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፤ በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤ ለሚወድዱኝ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኛና *”አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውም*”።
ራዕይ 19፥10 *”ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ”*። እርሱም፦ እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ *”ለእግዚአብሔር ስገድ”*፤ …አለኝ።

ለማንም ለምን “አትስገድ” ከተባለ ለምንድን ነው ሰዎች ለሰዎች የሰገዱት?፦
ዘፍጥረት 23:7 አብርሃምም ተነሣ፥ ለምድሩ ሕዝብም፥ *”ለኬጢ ልጆች ሰገደ”* ።
ዘፍጥረት 27፥29 አሕዛብ ይገዙልህ ሕዝብም *”ይስገዱልህ”*፤ ለወንድሞችህ ጌታ ሁን፥ *”የእናትህም ልጆች ይስገዱልህ”*፤
ዘፍጥረት 37:9 ደግሞም ሌላ ሕልምን አለመ፥ ለወንድሞቹም ነገራቸው፥ እንዲህም አለ። እነሆ ደግሞ ሌላ ሕልምን አለምሁ፤ እነሆ ፀሐይና ጨረቃ አሥራ አንድ ከዋክብትም *”ሲሰግዱልኝ”* አየሁ።
ዘፍጥረት 42:6 ዮሴፍም በምድር ላይ ገዥ ነበረ፥ እርሱም ለምድር ሕዝብ ሁሉ ይሸጥ ነበር፤ የዮሴፍም ወንድሞች በመጡ ጊዜ በምድር ላይ *”በግምባራቸው ሰገዱለት”*።
ዘፍጥረት 43:26 ዮሴፍም ወደ ቤቱ በገባ ጊዜ በእጃቸው ያለውን እጅ መንሻ በቤት ውስጥ አቀረቡለት፥ *”ወደ ምድርም ወድቀው ሰገዱለት”*።
ዘፍጥረት 43:28 እነርሱም አሉት። ባሪያህ አባታችን ደኅና ነው፤ ገና በሕይወት አለ። *”አጐንብሰውም ሰገዱለት”*።
1ዜና.29:20፤ ዳዊትም ጉባኤውን ሁሉ። አምላካችሁን እግዚአብሔርን ባርኩ አላቸው። ጉባኤውም ሁሉ የአባታቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ባረኩ፥ ራሳቸውንም አዘንብለው ለእግዚአብሔር እና *”ለንጉሡ ሰገዱ”*።

አንዳንድ ቂል ሰዎች፦ “ሰዎች ናቸው የሰገዱት እንጂ ስገዱ አልተባሉም” ብለው ውሃ የማያነሳና የማይቋጥር ስሁት ሙግት ያቀርባሉ፤ ለመሆኑ ኢየሱስ ሲመጣ ኢአማንያንን መጥተው በአማንያን እግር ፊት ይሰግዱ ዘንድ ማድረጉ ስህተት ነውን?፦
ራእይ 3:9 እነሆ፥ አይሁድ ሳይሆኑ፦ አይሁድ ነን ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ እነሆ፥ መጥተው *”በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ”* προσκυνήσουσιν ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ።

ዮሐንስ ሊሰግድለት በእግሩ ፊት ሲደፋ “እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ባሪያ ነኝ ለእግዚአብሔር ስገድ” ብሎት እያለ ኢየሱስ ኢአማንያንን መጥተው በአማንያን እግር ፊት ይሰግዱ ዘንድ ማድረጉ አግባብ ነው ወይ? ስንል ፦አይ መልአኩ ለዮሐንስ ያለው “የአምልኮት ስግደት” ሲሆን ኢየሱስ ያለው ደግሞ “የአክብሮት ስግደት” ነው፤ የአምልኮት ስግደት በባህርይ የአንድ አምላክ ሃቅና ገንዘብ ሲሆን የአክብሮት ስግደት ደግሞ በፀጋ ለቅዱሳን ማክበን ያመለክታል” ይሉናል፤ እንግዲያውስ የቁርአኑንም በዚህ ስሌትና ቀመር ተረዱት፤ በሰፈሩት ቁና መሰፈር ይሉሃል እንደዚህ ነው፤ በተጨማሪም ፍጥረታት ሁሉ ለአዳም እንደሰገዱ በአሁን ጊዜ ጥንት ከሚባሉት እደ-ክታባት አንዱ በሆነው በአሌክሳድሪየስ ኮዴክስ በሚገኘው በሮሙ ክሌመንት ማለትም በቀለሚንጦስ ተገልጿል፦
ክሌመንት 1፥41 አራዊት፣ እንስሳት ወፎች “”እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ””ወደ አዳም ተሰበሰቡ ከፊቱ ቁመው ራሳቸውን አዘነበሉ፤ *ለአዳምም ሰገዱ"*።

በተጨማሪም በመቃብያን ላይ ዲያቢሎስ የወደቀበት ለአደም አልሰግድ በማለቱ እንደሆነ ተገልጿል፦
3ኛ መቃብያን 1፥6 የሚጠፉ በኔም የሚስቱ ሰዎች ፈጽመው ይበዙ ዘንድ የአዳምም ልጆች ይጠፉ ዘንድ ይህንን በተናገሩ ጊዜ እኔ ደስ ይለኛል። ለሚዋረድልኝ *"ለአዳም አልሰግድም በማለቴ እግዚአብሔር ስለአባታቸው ስለአዳም ከማዕረጌ አዋርዶኛልና"*።

"ሳያውቁ መናገር፥ ኃላ ለማፈር" ይላሉ አበው። መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር ስምንት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 8
የአላህ ቃል ይለወጣል ወይስ አይለወጥም?

ይለወጣል፡–
ሱራ 2፡106 “ከአንቀፅ ብንለውጥ ወይም እርሷን ብናስረሳህ ከርሷ የሚበልጥን ወይም ቢጤዋን እናመጣለን፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ከሃሊ (ቻይ) መሆኑን አታውቅምን?”

አይለወጥም፡-
ሱራ 18፡27 “ለቃላቱ ለዋጭ የላቸውም፡፡”

መልስ
የባይብል ሃያሲ በሃያሲያነ-ፅሑፍ”textual criticism” ላይ ባይብልን ሂስ ሲሰጡ ውጤቱ አይን ያስፈጠጠ ጥርስ ያስገጠጠ ግጭትና ፍጭት መሆኑ ብዙዎች ወደ ኢስላም እንዲመጡ ምክንያት ሆኗል፤ የሚሽነሪ ነውጠኞች ሰዎች ከክርስትና አካውንት ወደ ኢስላም አካውንት ሲጎፉ ሲያዩ በእልህ መሳ ለመሳ ቁርአን ላይ ግጭት ለማግኘት ያልቆፈረሩት ጉድጓድ ያልፈነቀለሉት ድንጋይ የለም፤ ይህ አልበቃ ሲላቸው የግለሰቦችን ስም ማንጓጠጥ ስራዬ ብለው ተያይዘውታል፤ በዚህ መሃል ግን ቁርአን ላይ የሚያነሱት ሂስ ተፋልሶ”Fallacy” ቢሆንም ለጊዜው እንደ እኔ አይነቱ ላይ ብዥታ መፍጠሩ አይቀሬ ነው፤ ይህንን ስሑት ሙግት ገለባ መሆኑን በስሙር ሙግት ማሳየት የሁላችንም ተቀዳሚ አላማ ሊሆን ይገባል፤ ለዚህም የተንሸዋረረ እይታ ምንጨታዊ ሥነ-አመክንዮ”deductive logic” በመጠቀም ሙግቴን እጀምራለው፤ አላህ ቃሉን ይለውጣል ወይስ አይለውጥም የሚለው ሂስ ከመነሻው በቋንቋ ሙግት ድባቅ ይገባል፤ ይህንን ለመረዳት ሁለት የሙግት ነጥቦች”premises” ተጠቅሜአለው፦

ነጥብ አንድ
“ተብዲል”
“ተብዲል” تَبْدِيل ማለት ደግሞ “ማስቀየር” ነው፤ ተብዲል የንግግርን ሃሳብ፣ የውሳኔ ቃል እና የተስፋ ቃል ማስቀየርን ያመለክታል፤ አላህ የተናገረውን የውሳኔ ቃል አሊያም የትንቢትና የተስፋ ቃል ማንም ማስቆም አሊያም ማስቀረት እንደማይችል አላህ በቃሉ ይናገራል፦
6:115 “”የጌታህም ቃላት እውነተኛና ትክክለኛ ስትኾን “ተፈጸመች”፡፡ ለቃላቱ #ለዋጭ የለም” لَا مُبَدِّلَ፡፡ እርሱም ሰሚው ዐዋቂው ነው፡፡
10:64 ለእነሱ በቅርቢቱ ሕይወትም በመጨረሻይቱም “ብስራት” አላቸው፤ “”የአላህ ቃላት “#መለወጥ የላትም*لَا تَبْدِيلَ ፤ ይህ እርሱ ታላቅ ዕድል ነው፡፡
6:34 ከበፊትህም መልክተኞች በእርግጥ ተስተባበሉ፡፡ በተስተባበሉበትም ነገርና በተሰቃዩት ላይ እርዳታችን እስከመጣላቸው ድረስ ታገሱ፡፡ “”የአላህንም ንግግሮች *#ለዋጭ የለም*وَلَا مُبَدَِّ፡፡
18:27 ከጌታህም መጽሐፍ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ፤ “ለቃላቶቹ #ለዋጭ የላቸውም” لَا مُبَدِّلَ፤

በተለይ “ተፈጸመች” እና “ብስራት” የሚሉት ቃላት የሚበሰርን እና የሚፈጸም ቃልን እንጂ በቀድሞ መጽሐፍት የተናገረውን መልእክት አያመለክትም፣ ኢማም ጦበራኒ ለሱረቱል አንአም 6፡115 የሰጡት ማብራሪያ እንዲህ ይላል፦
‹‹ለቃላቱ ለዋጭ የለም የሚለው ቃል አላህ በእርሱ መጽሀፍ ውስጥ ጉዳዩ ይከሰታል ብሎ ለመተግበሩ የሰጠው ቃል በጊዜው ከመተግበር ማንም አያግደውም እሱ እነደተናገረው ይፈጸማል ማለት ነው››
ኢማም ቁርጡቢም ተመሳሳይ ሀሳብ ያዘለ ማብራሪያቸውን እንዲህ ሲሉ ይገልጻል፦
‹‹ አልራሚኒ እንዳስተላለፉት አቡ ቀታዳ እንዲህ ይላሉ፡-ለኣላህ ፍርድ ምንም ለዋጭ የለውም የመጽሀፉ ሰዎች እንዳደረጉት ቃላቱን አንድ ሰው እንኳ ቢቀይረው የአላህ እውነተኛ ቃል ግን ከመፈጸም ወደ ኋላ አይልም የተለወጠው ቃል የሚፈጸመውን ቃል መለወጥ አይችልም፡፡››

ግራም ነፈሰ ቀኝ ሲጀመር “መለወጥ” የሚለው ቃል ተመሳሳይ ቃል ቢኖረው እንኳን ተመሳሳይ ሀሳብና ትርጉም አለው ማለት አይደለም፤ የአንድን ቃል አማራጭ ትርጒም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ ቅቡል ነው፤ ቃሉ ሳይሆን ቃሉ የወከለው ሐሳብ መታየት ያለበት።
ሲቀጥል “መለወጥ” የሚለው ንግግርን ማስቀየር “ተብዲል” መሆኑን እንጂ “ነሥኽ” እንዳልሆነ አይተናል።
ሲሰልስ ” መለወጥ” “ነሥኽ” ነው ተብሎ ቢባል እንኳን አላህ ሁሉን ቻይ ስለሆነ ቃሉን በሌላ ቃል መለወጥ ይችላል፤ ፍጡሮቹ ግን ወደ ነብያችን የወረደውን ቃል መለወጥ አይችሉም፤ ምክንያቱም “ሙበዲል” مُبَدِّل “ለዋጭ” የሚለው ቃል ከአላህ ውጪ የሆኑትን ማንነቶች እና ምንነቶች የሚያሳይ ስለሆነ፤ እንደዛ ከሆነ የሚቀጥለውን የሙግት ነጥብ እንመልከት፦
ነጥብ ሁለት
“ነሥኽ”
“ነሥኽ” نسخ ማለት “ሽረት”abrogation” ማለት ሲሆን ይህም ሽረት በሁለት እሳቤዎች አቅፏል፤ እነርሱም፦
1ኛ. “ናሢኽ” الناسخ ማለትም “ሻሪ”Abrogator” ሲሆን ይህ አንቀፅ ሻሪ አንቀፅ ይባላል።
2ኛ. “መንሡኽ” المنسوخ “ተሻሪ”Abrogated” ነው፤ ይህ አንቀጽ ተሻሪ አንቀፅ ይባላል።
“ሽረት” ህጉን ታሳቢና ዋቢ ያረደገ ሲሆን የማህበረሰቡትን ዕድገትና የአስተሳሰብ ደረጃ፣ የጊዜውን ቅድመ-ተከተል እና ዘመነ-መግቦት”dispensation” ያማከለ ነው፣ ይህም “ተከታታይ ግህደተ-መለኮት”progressive revelation” እሴትና ግብአት ነው፦
2:106 #ከአንቀጽ #ብንለውጥ نَنْسَخْ ወይም እርሷን ብናስረሳህ ከርሷ የሚበልጥን ወይም ብጤዋን #እናመጣለን#አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ #ቻይ #መኾኑን አታውቅምን?፡፡
16:101 #በአንቀጽም #ስፍራ #አንቀጽን #በለውጥን ጊዜ፣ አላህም #የሚያወርደውን ነገር አዋቂ ነው፤ አንተ ቀጣፊ እንጂ ሌላ አይደለህም ይላሉ፤ በእውነቱ አብዛኞቻቸው አያውቁም።

አላህ የሕጉን አንቀጽ በሌላ የህግ አንቀጽ የመሻሩ ሂደት በሁለት ይከፈላል፤ እርሱም፦
1ኛ. “ሁክሙ” ማለትም “ህጉ” ተነሥኾ ነገር ግን “መትኑ” ማለትም “የህጉ ጥሬ ቃል” የማይነሠኸው ሲሆን የተነሠኸው እና የነሠኸው አያህ ቁርአን ውስጥ ሰፍሮ ይገኛል።
2ኛ. ሁክሙ ተነሥኾ በተጨማሪም መትኑ ተነሥኾ፤ የነሠኸው አያህ ቁርአን ውስጥ ሰፍሮ፤ ነገር ግን የተነሠኸው አያህ ሁክሙና መትኑ የማይገኝ ሲሆን የተነሠኸው አያህ በማስረሳት በሌላ አያህ መተካት ነው፦
87:6-7 ቁርአንን በእርግጥ እናስነብብሃለን፤ #አትረሳምም፤ አላህ #ከሻዉ #በስተቀር
2:106 ከአንቀጽ ብንለውጥ ወይም እርሷን #ብናስረሳህ ከእርሷ የሚበልጥን ወይም ብጤዋን እናመጣለን፤

ስለዚህ ሁለት የተለያዩ ነጥቦችን አምጥቶ ይጋጫሉ ማለት የሥነ-አመክንዮ ተፋልሶ ነው። መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር ዘጠኝ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 9
በገሃነም ውስጥ የተጣሉ ሰዎች ምግባቸው አንድ ብቻ ነው ወይስ ብዙ?

ዶሪዕ የሚባል ዛፍ ብቻ፡–
ሱራ 86፡6 “ለነሱ ዶሪዕ ከሚባል (እሾሃም) ዛፍ እንጂ ሌላ ምግብ የላቸውም፡፡”

የዘቁም ዛፍ የሚባል፡–
ሱራ 37፡62-68 “በመስተንግዶ ይህ ይበልጣልን ወይስ የዘቁም ዛፍ?… እርሷ በገሃነም አዘቅት ውስጥ የምትወጣ ዛፍ ናት፡፡ እንቡጧ ልክ የሰይጣናት ራሶች ይመስላል፡፡ እነርሱም ከርሷ በይዎች ናቸው…”

የቁስል እጣቢ ብቻ፡–
ሱራ 69፡36 “ምግብም ከእሳት ሰዎች ቁስል እጣቢ (እዥ) በስተቀር የለውም”

መልስ
ወሒድ ሾርባ እንጂ ሌላ አይበላም ተብሎ ፈይሰል ደግሞ ስጋ እንጂ ሌላ አይበላም ቢባል ይህ ግጭት አይባልም። ምክንያቱም ፈይሰል የሚኖርበት ቤትና ወሒድ የሚኖርበት ቤት ይለያያልና፣ ከመነሻው የዐውዱ ፍሰት የሚናገረው ስለተለያዩ በቅጣት ላይ ስላሉ ሰዎች ነው። እስቲ መጀመሪያ ጀሃነም የተለያየ ደረጃና መኖርያ እንዳለው ከቁርአን እንረዳ፦
15፤44 *«ለእርሷ ሰባት ደጃፎች አሏት፡፡ ለየደጀፉም ሁሉ ከእነሱ የተከፈለ ፋንታ አለ"*፡፡ لَهَا سَبْعَةُ أَبْوَابٍ لِّكُلِّ بَابٍ مِّنْهُمْ جُزْءٌ مَّقْسُومٌ
16፥29 *«የገሀነምንም ደጃፎች በውስጧ ዘውታሪዎች ስትኾኑ ግቡ»* ይባላሉ፡፡ የኩሩዎችም መኖሪያ ገሀነም በእርግጥ ከፋች! فَادْخُلُوا أَبْوَابَ جَهَنَّمَ خَالِدِينَ فِيهَا ۖ فَلَبِئْسَ مَثْوَى الْمُتَكَبِّرِينَ

ጀሃነም ደጃፎች እንዳሏት ለየደጀፉም ሁሉ ከእነሱ የተከፈለ ፋንታ እና የተለያየ ደረጃዎች እንዳለ ከተመለከትን አንቀጹ ስለ እነማን እንደሚያወራ በአጽንኦት መመልከት ይቻላል። ፊቶች ተዋራጆች የሆኑ "ካፊሪን" كَافِرِين ማለትም "ከሃድያን" ዶሪዕ ከሚባል እሾሃም ዛፍ እንጅ ሌላ ምግብ የላቸውም፦
80፥40 *"ፊቶችም በዚያ ቀን በላያቸው ላይ ትቢያ አለባቸው"*፤ وَوُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ عَلَيْهَا غَبَرَةٌ
80፥42 *እነዚያ እነርሱ ከሓዲዎቹ አመጸኞቹ ናቸው"*፡፡ أُولَـٰئِكَ هُمُ الْكَفَرَةُ الْفَجَرَةُ
88፥2 *"ፊቶች በዚያ ቀን ተዋራጆች ናቸው"*፡፡ وُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ خَاشِعَةٌ
88፥6 *"ለእነርሱ ዶሪዕ ከሚባል እሾሃም ዛፍ እንጅ ሌላ ምግብ የላቸውም"*፡፡ لَّيْسَ لَهُمْ طَعَامٌ إِلَّا مِن ضَرِيعٍ

"እነርሱ ከሓዲዎቹ ናቸው" ናቸው የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት። ከካድያን በተቃራኒው አማንያን ሆነው መጥፎ ሥራ ሰርተው ተውበት ካላደረጉ ይቀጣሉ። እነዚህ
"ኻጢዑን" خَاطِئُون ማለትም "ኀጢኣተኞች" ይባላሉ፤ እነርሱ ከእሳት ሰዎች በተለየ መልኩ ምግባቸው እዥ በስተቀር የለውም፦
69፥36 *"ምግብም ከእሳት ሰዎች እዥ በስተቀር የለውም"*፡፡ وَلَا طَعَامٌ إِلَّا مِنْ غِسْلِينٍ
69፥37 *"ኀጢኣተኞች እንጅ ሌላ አይበላውም፤ ይባላል"*፡፡ لَّا يَأْكُلُهُ إِلَّا الْخَاطِئُونَ

አምልኮ የሚገባው የፈጠረን አላህ ብቻ ነው። በእርሱ ላይ ሌላ ማንነትና ምንነት ማጋራት ታላቅ በደል ነው። ለበደለኞች የዘቁም ዛፍ በይዎች ናቸው፦
37፥62 *"በመስተንግዶነት ይህ ይበልጣልን? ወይስ የዘቁም ዛፍ?"* أَذَٰلِكَ خَيْرٌ نُّزُلًا أَمْ شَجَرَةُ الزَّقُّومِ
37፥63 *"እኛ ለበዳዮች ፈተና አድርገናታል"*፡፡ إِنَّا جَعَلْنَاهَا فِتْنَةً لِّلظَّالِمِينَ
37፥66 እነርሱም ከእርሷ በይዎች ናቸው፤ ሆዶችንም ከእርሷ ሞይዎች ናቸው፡፡ فَإِنَّهُمْ لَآكِلُونَ مِنْهَا فَمَالِئُونَ مِنْهَا الْبُطُونَ

"ዛሊሚን" ظَّالِمِين ማለትም "ሙሽሪኮች" በገሃንም ውስጥ የቅጣት ምግብ ገደብ አልተደረገባቸውም። ስለዚህ ከመነሻው ዐረፍተ-ነገሩን ከዐውዱ አፋቶ መረዳት ሽርክት መረዳት ነው።
ሲቀጥል "ኢላ" إِلَّا የሚለው አፍራሽ ቃል “ኢስቲስናዕ” اِسْتِثْنَاء‏ ማለትም “ግድባዊት”Exceptional” ሆኖ የመጣ ነው፥ በአንጻራዊና በፍጹማዊ አገባብ ይመጣል። በፍጹማዊ ግድብነት“Absolute Exception” ሲመጣ “ሙጥለቅ” مطلق ይባላል፤ በአንጻራዊ ግድብነት“Relative Exception” ሲመጣ ቀሪብ” قريب ይባላል። ይህንን ለመረዳት አንድ ጥቅስ ማየት ይበቃል፦
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ “ከእኔ ሌላ አምላክ የለም” እና አምልኩኝ በማለት ወደ እርሱ *የምናወርድለት* ቢኾን እንጅ *ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም*፡፡ وَمَا أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدُونِ

"ኢላ" إِلَّا እዚህ ዐውድ ላይ አንጻራዊ ሆኖ መጥቷል። ወደ መልእክተኞቹ “ከእኔ ሌላ አምላክ የለም” ማለትን ብቻ ነው የሚያወርደው? አይ ወደ እነርሱ መልካም ሥራዎችን መሥራትን፣ ሶላትንም መስገድን፣ ዘካንም መስጠትን አውርዳል፦
21፥73 *”ወደ እነርሱም መልካም ሥራዎችን መሥራትን፣ ሶላትንም መስገድን፣ ዘካንም መስጠትን አወረድን”*፡፡ وَأَوْحَيْنَآ إِلَيْهِمْ فِعْلَ ٱلْخَيْرَٰتِ وَإِقَامَ ٱلصَّلَوٰةِ وَإِيتَآءَ ٱلزَّكَوٰة

ታዲያ ለምን "ከእኔ ሌላ አምላክ የለም” ማለት ብቻ ሆነ ስንል ከዐቂዳህ ጭብጥ አንጻር ነው እንጂ በጥቅሉ ሙጥለቅን አያመለክትም ከተባለ እንግዲያውስ የጀሃነም ምግብ "በስተቀር" የሚለው ከጀነት አስደሳች ምግቦች አንጻር እንጂ ሌላ አይደለም።

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር አስር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 10
ነቢዩ ቢሳሳት የሚጐዳው ማነው?
እስኪ የሚከተለውን የቁርኣን ጥቅስ በአንክሮ ያጢኑ፡-
ሱራ 34፡50 “ብሳሳት የምሳሳተው በራሴ ላይ ብቻ ነው ብመራም ጌታዬ ወደኔ በሚያወርደው ነው፡፡”

መልስ
34፥50 *«ብሳሳት የምሳሳተው በራሴ ላይ ብቻ ነው፡፡ ብመራም ጌታዬ ወደ እኔ በሚያወርደው ነው"*፡፡ እርሱ ሰሚ ቅርብ ነውና» በላቸው፡፡ قُلْ إِن ضَلَلْتُ فَإِنَّمَا أَضِلُّ عَلَىٰ نَفْسِي ۖ وَإِنِ اهْتَدَيْتُ فَبِمَا يُوحِي إِلَيَّ رَبِّي ۚ إِنَّهُ سَمِيعٌ قَرِيبٌ

ይህ ጥያቄ የግጭት ጥያቄ ሳይሆን የብዥታ ጥያቄ ነው። ነቢያችን”ﷺ” ቁርኣን ወደ እርሳቸው መወረዱን ተስፋ ሳያደርጉ ከቁርኣን በፊት ምንም ሳይሉ ማለትም፦ “ነብይ ወይም መልእክተኛ ነኝ” ሳይሉ ብዙ ዕድሜ ማለትም 40 ዓመት በእርግጥ ኖረዋል፦
28፥86 *መጽሐፉ ወደ አንተ መወረዱን ተስፋ የምታደርግ አልነበርክም፡፡ ግን ከጌታህ ችሮታ ተወረደልህ፡፡ ለከሓዲዎችም በፍጹም ረዳት አትኹን*፡፡ وَمَا كُنتَ تَرْجُو أَن يُلْقَىٰ إِلَيْكَ الْكِتَابُ إِلَّا رَحْمَةً مِّن رَّبِّكَ ۖ فَلَا تَكُونَنَّ ظَهِيرًا لِّلْكَافِرِينَ
10፥16 አላህ በሻ ኖሮ በእናንተ ላይ ባለነበብኩትም፤ አላህ እርሱን ባላሳወቃችሁም ነበር፡፡ *በእናንተም ውስጥ ከእርሱ በፊት ምንም ሳልል ብዙን ዕድሜ በእርግጥ ኖሬአለሁ፤ አታውቁምን?* በል። قُل لَّوْ شَاءَ اللَّهُ مَا تَلَوْتُهُ عَلَيْكُمْ وَلَا أَدْرَاكُم بِهِ ۖ فَقَدْ لَبِثْتُ فِيكُمْ عُمُرًا مِّن قَبْلِهِ ۚ أَفَلَا تَعْقِلُونَ

ከቁርኣን መውረድ በፊት በአርባ ዓመት ውስጥ በነበራቸው ቆይታ መጽሐፍን የሚያነቡ በቀኛቸውም የሚጽፉ አልነበሩም፤ አላህ ምንም የማያውቁ ሆነው ሳሉ ቁርኣንን በማውረድ መራቸው፦
29፥48 *ከእርሱ በፊትም መጽሐፍን የምታነብ በቀኝህም የምትጽፈው አልነበርክም*፡፡ ያን ጊዜ አጥፊዎቹ በእርግጥ በተጠራጠሩ ነበር፡፡ وَمَا كُنتَ تَتْلُو مِن قَبْلِهِ مِن كِتَابٍ وَلَا تَخُطُّهُ بِيَمِينِكَ ۖ إِذًا لَّارْتَابَ الْمُبْطِلُونَ
93፥7 *የሳትክም ኾነህ አገኘህ መራህም*፡፡ وَوَجَدَكَ ضَالًّا فَهَدَىٰ

“የሳትክ” የሚለው ቃል “አዷል” أَضَلّ ሲሆን “ምሪት አልባ” ማለት ነው፤ “ምሪት አልባ” ነበርክ ማለት “መጽሐፉም ምን እንደኾነ የምታውቅ አልነበርክም” ማለት ነው፤ “መራንህ” የሚለው “የምንሻውን ሰው በእርሱ የምንመራበት ብርሃን አደረግነው” በሚል መጥቷል፦
42፥52 እንደዚሁም ወደ አንተ ከትእዛዛችን ሲኾን መንፈስን አወረድን፡፡ *መጽሐፉም እምነቱም ምን እንደኾነ የምታውቅ አልነበርክም*፡፡ ግን ከባሮቻችን የምንሻውን ሰው በእርሱ *የምንመራበት ብርሃን አደረግነው*፡፡ አንተም ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ትመራለህ፡፡ وَكَذَٰلِكَ أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ رُوحًا مِّنْ أَمْرِنَا ۚ مَا كُنتَ تَدْرِي مَا الْكِتَابُ وَلَا الْإِيمَانُ وَلَـٰكِن جَعَلْنَاهُ نُورًا نَّهْدِي بِهِ مَن نَّشَاءُ مِنْ عِبَادِنَا ۚ وَإِنَّكَ لَتَهْدِي إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ
ስለዚህ የሳትክ ነበር ማለት መጽሐፉም ምን እንደኾነ የምታውቅ አልነበርክም ማለት ሲሆን ቁርኣንን የሚመራበት ብርሃን አድርጎ መራቸው ማለት ነው። ይህ ቁርኣን ወደ ቀጥተኛ መንገድ ይመራል፦
17፥9 *ይህ ቁርኣን ወደዚያች እርሷ ቀጥተኛ ወደ ኾነችው መንገድ ይመራል*፡፡ إِنَّ هَـٰذَا الْقُرْآنَ يَهْدِي لِلَّتِي هِيَ أَقْوَمُ

አንቀጹ ይቀጥልና፦ “ድኻም ኾነህ አገኘህ አከበረህም” ይላል፤ ሃብት ሙሉነት ሲሆን ድህነት ባዶነት ነው። እውነተኛ ሃብት ደግሞ የነፍስ ሃብት ቁርኣን ነው፤ ስለዚህ የሳትክ ነበርክ ማለት የቁርኣን ዕውቀቱ አልነበረክም ደሃ ነበርክ፤ መራንህ ማለት የነፍስ ሃብት በሆነው ቁርኣን አከበርንህ ማለት ነው፤ ታላቁ ሙፍሲር ኢብኑ ከሲር በዚህ መልኩ ነው ያስቀመጠው፦
93፥8 *ድኻም ኾነህ አገኘህ አከበረህም*፡፡ وَوَجَدَكَ عَائِلًا فَأَغْنَىٰ
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 81, ሐዲስ 35
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ *”ሃብት ማለት መጠነ ሰፊ ንብረት መያዝ አይደለም። ነገር ግን ሃብት ማለት የነፍስ ሃብት ነው*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ لَيْسَ الْغِنَى عَنْ كَثْرَةِ الْعَرَضِ، وَلَكِنَّ الْغِنَى غِنَى النَّفْسِ ‏”‌‏.‏

ስለዚህ "ደለልቱ" ضَلَلْتُ የሚለው ቃል “አዷል” أَضَلّ ማለትም “ምሪት አልባ” ከሚል የስም መደብ የመጣ ሲሆን "ባላውቅ" "ባልገነዘብ" "ምሪት አልባ ብሆን" ጉዳቱ በራሴ ላይ ነው፥ ብመራም ጌታዬ ወደ እኔ በሚያወርደው ቁርኣን ነው ማለት ነው። ቁርኣን ወደ ቀጥተኛ መንገድ ይመራል፦
17፥9 *ይህ ቁርኣን ወደዚያች እርሷ ቀጥተኛ ወደ ኾነችው መንገድ ይመራል*፡፡ إِنَّ هَـٰذَا الْقُرْآنَ يَهْدِي لِلَّتِي هِيَ أَقْوَمُ

ምሪት አልባ ባዶ ሰው እራሱን ይጎዳል እንጂ ሌላውን አይጎዳም። የሌለውን ከየት ይሰጣል? ሲቀጥል መሳት እና ማሳሳት ሁለት ለየቅል ዐረፍተ-ነገር ይሰራሉ። መሳሳት ጉዳቱ በራስ ላይ ነው፥ ቀጥሎ ሌላውን ማሳሳት ጉዳቱ በሌላውም ጭምር ነው፦
10፥108 «እናንተ ሰዎች ሆይ! እውነቱ ከጌታችሁ በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ *በእርሱ የተመራም ሰው የሚመራው ለራሱ ነው፡፡ የተሳሳተም ሰው የሚሳሳተው ጉዳቱ በራሱ ላይ ነው*፡፡ እኔም በእናንተ ላይ ተጠባበቂ አይደለሁም» በላቸው፡፡ قُلْ يَا أَيُّهَا النَّاسُ قَدْ جَاءَكُمُ الْحَقُّ مِن رَّبِّكُمْ ۖ فَمَنِ اهْتَدَىٰ فَإِنَّمَا يَهْتَدِي لِنَفْسِهِ ۖ وَمَن ضَلَّ فَإِنَّمَا يَضِلُّ عَلَيْهَا ۖ وَمَا أَنَا عَلَيْكُم بِوَكِيلٍ
17፥15 *የተመራ ሰው የሚመራው ለራሱ ብቻ ነው፡፡ የተሳሳተም ሰው የሚሳሳተው ጉዳቱ በእርሷ ላይ ነው፡፡ ተሸካሚም ነፍስ የሌላይቱን ኃጢኣት አትሸከምም"*፡፡ መልዕክተኛንም እስከምንልክ ድረስ የምንቀጣ አይደለንም፡፡ مَّنِ اهْتَدَىٰ فَإِنَّمَا يَهْتَدِي لِنَفْسِهِ ۖ وَمَن ضَلَّ فَإِنَّمَا يَضِلُّ عَلَيْهَا ۚ وَلَا تَزِرُ وَازِرَةٌ وِزْرَ أُخْرَىٰ ۗ وَمَا كُنَّا مُعَذِّبِينَ حَتَّىٰ نَبْعَثَ رَسُولًا

የተሳሳተ ሰው ጉዳቱ በራሱ ላይ ሲሆን ያሳሳተ ሰው ግን ሌላውን በማሳሳቱ ያሳሳተው ሰው የሚቀጣበትን ቅጣት ከሚቀጣው ሰው ላይ ሳይጨመር ሳይቀነስ በማሳሳቱ ይቀጣል፦
16፥25 ይህንንም የሚሉት በትንሣኤ ቀን ኀጢኣቶቻቸውን በሙሉ *”ከእነዚያም ያለ ዕውቀት ኾነው ከሚያጠሟቸው ሰዎች ኀጢአቶች ከፊሉን ሊሸከሙ ነው”*፡፡ ንቁ! የሚሸከሙት ኃጢኣት ምንኛ ከፋ! لِيَحْمِلُوا أَوْزَارَهُمْ كَامِلَةً يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۙ وَمِنْ أَوْزَارِ الَّذِينَ يُضِلُّونَهُم بِغَيْرِ عِلْمٍ ۗ أَلَا سَاءَ مَا يَزِرُونَ

አንድ ሰው ሌላውን ሰው ሲያሳስት አሳሳቹ በማሳሳቱ ምክንያት የተሳሳተው ሰው የሚያገኘውን ቅጣት ከሚሳሳተው ላይ ቅጣቱ ሳይቀነስ ሳይጨመር የተሳሳተውን ሰው ቅጣት አሳሳቹ ይቀበላል፤ አንድ ሰው ሌላውን ሰው ከመራ መሪው በመምራቱ ምክንያት የተመራው ሰው የሚያገኘውን አጅር ከሚመራው ላይ አጅሩ ሳይቀነስ ሳይጨመር የተመራውን ሰው አጅር መሪው ይቀበላል፤ ከላይ ያለው መልክእት ይህ ነው፤ ኢብኑ ከሲር ይህንን አንቀፅ በሐዲስ እንዲህ ይፈስረዋል፦
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 210
አነስ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“ማንም ጠሪ ሰዎችን ወደ ጥመት የሚጣራ የተከተሉት ሰዎች የሚሸከሙትን ኀጢአት ከእነርሱ ላይ ሳይጓደል ይሸከማል፤ ማንም ጠሪ ሰዎችን ወደ ምሪት የሚጣራ የተከተሉት ሰዎች የሚያገኙትን ምንዳ ከእነርሱ ላይ ሳይጓደል ያገኛል"*። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، عَنْ رَسُولِ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ أَنَّهُ قَالَ ‏ “‏ أَيُّمَا دَاعٍ دَعَا إِلَى ضَلاَلَةٍ فَاتُّبِعَ فَإِنَّ لَهُ مِثْلَ أَوْزَارِ مَنِ اتَّبَعَهُ وَلاَ يَنْقُصُ مِنْ أَوْزَارِهِمْ شَيْئًا وَأَيُّمَا دَاعٍ دَعَا إِلَى هُدًى فَاتُّبِعَ فَإِنَّ لَهُ مِثْلَ أُجُورِ مَنِ اتَّبَعَهُ وَلاَ يَنْقُصُ مِنْ أُجُورِهِمْ شَيْئًا ‏”

ነፍስ የሌላይቱን ኃጢአት አትሸከምም ማለት ለምሳሌ መቶ ኪሎ ጤፍ ተሸክሜ ከነበረ ሌላ ሰው ለእኔ ጤፉን ከተሸከመልኝ እኔ ላይ መቶ ኪሎ ጤፍ የለም ማለት ነው፤ ግን አጥማሚ የጠመመውን ሰው በእርሱ ምክንያት ነውና ከእርሱ ቅጣት ሳይጓደል ይቀጣል።

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር አስራ አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 11

ማርያም የተገለጡላት ስንት መላእክት ነበሩ?

ብዙ መላእክት፡–
3፥42 “መላእክትም ያሉትን አስታውስ፡- መርየም ሆይ! አላህ በእርግጥ መረጠሸ አነጻሽም በዓለማት ሴቶችም ላይ መረጠሸ”

አንድ መልአክ:-
19፥17 “ከእነሱም መጋረጃን አደረገች መንፈሳችንንም ወደ እርሷ ላክን ለርሷም ትክክለኛ ሰው ሆኖ ተመሰለላት፡፡

መልስ
ወደ መርየም የመጡት መላእክት ብዙ ሲሆን እነዚህን ሹማምንት ወክሎ ሲያናግር የነበረው የልኡካኑ አለቃ ግን ጂብሪል ነው፦
3፥42 *"መላእክትም ያሉትን አስታውስ"*፡፡ «መርየም ሆይ! አላህ በእርግጥ መረጠሸ፡፡ አነጻሽም፡፡ በዓለማት ሴቶችም ላይ መረጠሽ፡፡» وَإِذْ قَالَتِ الْمَلَائِكَةُ يَا مَرْيَمُ إِنَّ اللَّهَ اصْطَفَاكِ وَطَهَّرَكِ وَاصْطَفَاكِ عَلَىٰ نِسَاءِ الْعَالَمِين

እዚሁ ዐውድ ላይ ነጠላ መልአክ ያናግራት እንደነበረ ለመግለጽ በነጠላ "ቃለ" قَالَ ማለትም "አለ" የሚል ሃይለ-ቃል አለ፦
3፥47 *፡-ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለች፡፡ ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፤ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል አላት*፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

ስለዚህ ሱረቱል አለ-ዒምራን ላይ "ብዙ" መላእክት "ብቻ" እንጂ "አንድ" ብቻ አላናገራትም የሚል እና ሱረቱል መርየም ላይ አንድ መልአክ ብቻ እንጂ ብዙ መላእክት አላናገሯትም የሚል የለም። ይህ የመጨረሻ የወረደ ስሁት ሙግት ነው።
ይህ በቁርአን ውስጥ የተለመደ አገላለጽ ነው። ለምሳሌ ሩሕን በማውጣት የሚወስዱት መላእክት ብዙ መሆናቸው አንድ ቦታ ላይ ሲናገር ሌላ ቦታ ላይ ደግሞ አንድ መልአክ መለኩል መውት ተጠቅሷል፦
47:27 መላእክትም ፊቶቻቸውንና ጀርቦቻቸውን የሚመቱ ሲሆኑ በገደሉዋቸው ጊዜ ሁኔታቸው እንዴት ይሆናል?
32፥11 «በእናንተ የተወከለው መልአከ ሞት *”ይወስዳችኃል”*፡፡ ከዚያም ወደ ጌታችሁ ትመለሳላችሁ» በላቸው፡፡ قُلْ يَتَوَفَّىٰكُم مَّلَكُ ٱلْمَوْتِ ٱلَّذِى وُكِّلَ بِكُمْ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّكُمْ تُرْجَعُونَ
7፥37 የሞት መልክተኞቻችንም *”የሚወስዷቸው ኾነው በመጡባቸው ጊዜ”* «ከአላህ ሌላ የምትጠሯቸው የነበራችሁት የት አሉ» ይሏቸዋል፡፡ «ከእኛ ተሰወሩን» ይላሉ፡፡ እነርሱም ከሃዲያን እንደነበሩ በነፍሶቻቸው ላይ ይመሰክራሉ፡፡ حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءَتْهُمْ رُسُلُنَا يَتَوَفَّوْنَهُمْ قَالُوٓا۟ أَيْنَ مَا كُنتُمْ تَدْعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ ۖ قَالُوا۟ ضَلُّوا۟ عَنَّا وَشَهِدُوا۟ عَلَىٰٓ أَنفُسِهِمْ أَنَّهُمْ كَانُوا۟ كَٰفِرِين
8፥50 እነዚያንም የካዱትን *"መላእክት ፊቶቻቸውንና ጀርባዎቻቸውን እየመቱ «የቃጠሎንም ስቃይ ቅመሱ» እያሉ በሚወስዷቸው ጊዜ ብታይ ኖሮ አስደንጋጭን ነገር ታይ ነበር"*፡፡ وَلَوْ تَرَىٰ إِذْ يَتَوَفَّى الَّذِينَ كَفَرُوا ۙ الْمَلَائِكَةُ يَضْرِبُونَ وُجُوهَهُمْ وَأَدْبَارَهُمْ وَذُوقُوا عَذَابَ الْحَرِيق

ይህንን ለማስረዳት ከራሳችሁ ባይብል ናሙና ላቅርብ። በሳምንቱ የፊተኛው ቀን ወደ መቃብር የመጣው አንድ መልአክ ነው፦
ማርቆስ 16፥5 ወደ መቃብሩም ገብተው *ነጭ ልብስ የተጎናጸፈ ጎልማሳ በቀኝ በኩል ተቀምጦ አዩና ደነገጡ"*።
ማቴዎስ 28፥2 እነሆም፥ *የጌታ መልአክ ከሰማይ ስለ ወረደ"* ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ቀርቦም ድንጋዩን አንከባሎ በላዩ ተቀመጠ።

በሳምንቱ የፊተኛው ቀን ወደ መቃብር የመጡት ሁለት መላእክት ናቸው፦
ሉቃስ 24፥4 እነርሱም በዚህ ሲያመነቱ፥ እነሆ፥ *"ሁለት ሰዎች የሚያንጸባርቅ ልብስ ለብሰው ወደ እነርሱ ቀረቡ"*፤
ዮሐንስ 20፥12 *"ሁለት መላእክትም ነጭ ልብስ ለብሰው"* የኢየሱስ ሥጋ ተኝቶበት በነበረው አንዱ በራስጌ ሌላውም በእግርጌ ተቀምጠው አየች።

በሳምንቱ የፊተኛው ቀን ወደ መቃብር የመጡት መላእክት ብዛት ስንት ነው አንድ ወይስ ሁለት? መልሱ አንድ "ብቻ" ቢል ኖሮ እና ሌላ ቦታ ሁለት ቢል ኖሮ ግጭት ይሆን ነበር። ግን "ብቻ" የሚለው ገላጭ በዐረፍተ-ነገር ውስጥ እስከሌለ ድረስ አንዱ ያልተረከውን ሌላው አብራራው በሚል ስሌት ከተቀመጠ እንግዲያውስ ከላይ ያለው የቁርኣን አናቅጽ ላይ "ብቻ" የሚል ስለሌለ በዚህ ስሌትና ቀመር መረዳት ይቻላል።

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም