ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
የዘረኝነት አራንቋ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

3፥103 *የአላህንም የማመን ገመድ ሁላችሁም ያዙ፡፡ አትለያዩም፡፡ ጠበኞችም በነበራችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ የዋለውን የአላህን ጸጋ አስታውሱ፡፡ በልቦቻችሁም መካከል አስማማ፡፡ በጸጋውም ወንድማማቾች ኾናችሁ፡፡ በእሳት ጉድጓድ አፋፍም ላይ ነበራችሁ፡፡ ከእርስዋም አዳናችሁ*፡፡ እንደዚሁ ትመሩ ዘንድ አላህ ለእናንተ አንቀጾቹን ያብራራል፡፡ وَاعْتَصِمُوا بِحَبْلِ اللَّهِ جَمِيعًا وَلَا تَفَرَّقُوا ۚ وَاذْكُرُوا نِعْمَتَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ إِذْ كُنتُمْ أَعْدَاءً فَأَلَّفَ بَيْنَ قُلُوبِكُمْ فَأَصْبَحْتُم بِنِعْمَتِهِ إِخْوَانًا وَكُنتُمْ عَلَىٰ شَفَا حُفْرَةٍ مِّنَ النَّارِ فَأَنقَذَكُم مِّنْهَا ۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمْ آيَاتِهِ لَعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ

አማራ፣ ኦሮሞ፣ ጉራጌ፣ ትግሬ ወዘተ ቋንቋ ነው፤ የቋንቋዎቻችን መለያየት ከአስደናቂ ታምራቶቹ ነው፤ በዚህ ውስጥ ለዐዋቂዎች ተዓምራቶች አሉበት፦
30፥22 ሰማያትንና ምድርንም መፍጠሩ፣ *የቋንቋዎቻችሁ እና የመልኮቻችሁም መለያየት ከአስደናቂ ታምራቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለዐዋቂዎች ተዓምራቶች አሉበት*፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ خَلْقُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَاخْتِلَافُ أَلْسِنَتِكُمْ وَأَلْوَانِكُمْ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّلْعَالِمِينَ

ቋንቋዎች ይዘውት የመጡት ታሪክ፣ ባህል፣ ልማድ፣ ትውፊት፣ ወግ፣ ክህሎት እና ሙዳየ-ቃላት “ዘውግ” ethnic” ሆኗል፤ ይህ እራሱ የቻለ ውበት ነው። ዘረኝነት ግን ከቋንቋ አሊያም ከቀለም የሚመጣ ሳይሆን የልብና የአስተሳሰብ በሽታ ነው።
“ዘረኝነት”racism” ማለት የራስን ቋንቋና ዘውግ አተልቆ የሌላውን ማሳነስ፣ ማግለል፣ መቃረን እና ማራከስ ነው። ዘረኝነት ትዳርን፣ ቤተሰብን፣ ጉርብትናን፣ ማህበረሰብን፣ ሃይማኖት፣ መንግሥትን፣ አገርን የሚበትን ክፉ በሽታ ነው። ዘረኝነት ምንጩ “አህዋ” أَهْوَآء ማለትም “ዝንባሌ”inclination” ነው። ዘረኝነት በዲንያ በአላህ ዘንድ ዋጋ የሚያሳጣ ሲሆን በአኺራም ደግሞ ለጀሃነም ይዳርጋል፦
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 344
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ *”አላህ ዐዘ ወጀል ከእናንተ የዘመነ-ጃሂሊያን ኩራት አስወግዷል፤ ይህም በዘር መኩራት ነው። ይህ ለጥንቁቁ አማኝም ወይም ለአደገኛው ካሃዲ አንድ ብቻ ነው። እናንተ የአደም ልጆች ናችሁ፤ አደም ከአፈር ነው የመጣው፤ ሰዎች በዘራቸው የሚኮሩ ከሆነ ጀሃነምን ይሞሏታል፤ ወይም አላህ ዘንድ ዋጋቸው ጥንዚዛ በአፍንጫው ከሚሽከረከር ጉድፍ ያነሰ ከሆኑት ይሆናል*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ إِنَّ اللَّهَ عَزَّ وَجَلَّ قَدْ أَذْهَبَ عَنْكُمْ عُبِّيَّةَ الْجَاهِلِيَّةِ وَفَخْرَهَا بِالآبَاءِ مُؤْمِنٌ تَقِيٌّ وَفَاجِرٌ شَقِيٌّ أَنْتُمْ بَنُو آدَمَ وَآدَمُ مِنْ تُرَابٍ لَيَدَعَنَّ رِجَالٌ فَخْرَهُمْ بِأَقْوَامٍ إِنَّمَا هُمْ فَحْمٌ مِنْ فَحْمِ جَهَنَّمَ أَوْ لَيَكُونُنَّ أَهْوَنَ عَلَى اللَّهِ مِنَ الْجِعْلاَنِ الَّتِي تَدْفَعُ بِأَنْفِهَا النَّتْنَ ‏”‏

የአደም ልጆች የአንድ አባት እና እናት ልጆች ነን ብሎ ማስተንተን መጠበብ ሲሆን በዘረኝነት አራንቋ መለከፍ መጥበብ ነው፦
ሱነን ነሳኢ መጽሐፍ 37 , ሐዲስ 150
ጁንደብ ኢብኑ ዐብደላህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ *”ማንም ሰው ግልጽ ባልሆነ ነገር፣ በዘረኝነት ጥብቅና፣ በዘረኝነት መንገድ የተጋደለ ግድያው የጃህሊያ ነው*። عَنْ جُنْدُبِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَنْ قَاتَلَ تَحْتَ رَايَةٍ عُمِّيَّةٍ يُقَاتِلُ عَصَبِيَّةً وَيَغْضَبُ لِعَصَبِيَّةٍ فَقِتْلَتُهُ جَاهِلِيَّةٌ ‏”‏

“ጃህሊያህ” جَاهِلِيَّةٌ ማለት “መሃይምነት” ማለት ነው፤ ቅድመ-ቁርኣን ያለው ጊዜ ዘመነ-ጃህሊያህ ይባላል፤ በእርግጥም በዘመነ-ጃህሊያህ ጊዜ የነበረችው ዘረኝነት ጥንብ ናት፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 45, ሐዲስ 81
ጃቢር ኢብኑ ዐብደላህ እንዳስተላለፈው፦ “በጉዞ ከነቢዩ”ﷺ” ጋር ነበርን፤ አንድ ሰው ከሙሃጅር ከአንሷር የሆነውን አንድ ሰው ጀርባውን መታው፤ አንሷሩም፦ “አንሷሪ ሆይ! አለ፤ ሙሃጅሩም፦ “ሙሃጅር ሆይ! አለ። ከዚያም የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” *”ይህ የጃህሊያህ አጠራር አይደለምን? አሉ፤ እነርሱም፦ “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አንድ ሰው ከሙሃጅር ከአንሷር የሆነውን አንድ ሰው ጀርባውን መታው” አሉ፤ እርሳቸው፦ “እርሷን(ዘረኝነትን) ተዋት ጥንብ ናት” አሉ*። جَابِرَ بْنَ عَبْدِ اللَّهِ يَقُولُ كُنَّا مَعَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم فِي غَزَاةٍ فَكَسَعَ رَجُلٌ مِنَ الْمُهَاجِرِينَ رَجُلاً مِنَ الأَنْصَارِ فَقَالَ الأَنْصَارِيُّ يَا لَلأَنْصَارِ وَقَالَ الْمُهَاجِرِيُّ يَا لَلْمُهَاجِرِينَ ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ مَا بَالُ دَعْوَى الْجَاهِلِيَّةِ ‏”‏ ‏.‏ قَالُوا يَا رَسُولَ اللَّهِ كَسَعَ رَجُلٌ مِنَ الْمُهَاجِرِينَ رَجُلاً مِنَ الأَنْصَارِ ‏.‏ فَقَالَ ‏”‏ دَعُوهَا فَإِنَّهَا مُنْتِنَةٌ ‏
‏ ‏
“ሙሃጅር” مُهَاجِر ማለት “ስደተኛ” ማለት ሲሆን ከመካ የተሰደዱትን ሶሓብይን ያመለክታል፤ “አንሷር” أَنْصَارٍ ማለት “ረዳት” ማለት ሲሆን ከመካ የተሰደዱት የተቀበሉ የመዲና ሶሓብይን ያመለክታል።
አንዱ ዘር ተነስቶ ሌላውን ዘር ሲበድል የተበደለው ያልበደለውን በዘሩ ብቻ በቁርሾ ለመበቀል መነሳት ጠባብነት ነው፤ በኢሥላም የቀደሙት ትውልድ በሰሩት ወንጀል የአሁኑን ትውልድ መጠየቅ ወይም መቅጣት እራሱ ሕግ መተላለፍ ነው፦
ሱነን ነሳኢ መጽሐፍ 37 , ሐዲስ 162
ዐብደላህ እንደተረከው ነብዩም”ﷺ” አሉ፦.. *ሰው በአባቱ ወይም በወንድሙ ወንጀል አይቀጣም*። وَلاَ يُؤْخَذُ الرَّجُلُ بِجَرِيرَةِ أَبِيهِ وَلاَ بِجَرِيرَةِ أَخِيهِ ‏”
በተጨማሪም አንድ ሰው ባጠፋው ብዙኃኑን ዘር ማንቋሸሽ ወይም ማዋረድ ሐራም ነው፦
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 33, ሐዲስ 106
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ከሰዎች መካከል ትልቁ ውሸታም ሌላው ሰው ማንቋሸሽ እና መላውን ዘር ማዋረድ ነው*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ “‏ إِنَّ أَعْظَمَ النَّاسِ فِرْيَةً لَرَجُلٌ هَاجَى رَجُلاً فَهَجَا الْقَبِيلَةَ بِأَسْرِهَا

እረ እሩቅ ሳንሄድ ወደ ዘረኝነት የሚጣራ፣ በዘረኝነት መንገድ የሚታገል፣ በዘረኝነት መንገድ ሲከተል የሞተ ሰው ከነብያችን”ﷺ” ሱናህ ውጪ ነው፦
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 349
ጁበይር እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ወደ ዘረኝነት የሚጣራ ከእኛ አይደለም። በዘረኝነት መንገድ የሚታገኝ ከእኛ አይደለም። በዘረኝነት መንገድ ሲከተል የሞተ ከእኛ አይደለም*። عَنْ جُبَيْرِ بْنِ مُطْعِمٍ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ لَيْسَ مِنَّا مَنْ دَعَا إِلَى عَصَبِيَّةٍ وَلَيْسَ مِنَّا مَنْ قَاتَلَ عَلَى عَصَبِيَّةٍ وَلَيْسَ مِنَّا مَنْ مَاتَ عَلَى عَصَبِيَّةٍ ‏”‏

እሥልምና ሁሉን ብሔር፣ ቋንቋ፣ ዘውግ ዐቃፊ እንጂ አንዱን ብሔር፣ ቋንቋ፣ ዘውግ ከሌላ ነቃፊ በፍጹም አይደለም። የእኔ ብሔር፣ ቋንቋ፣ ዘውግ ተነካ ብሎ ዘራፍ ማለት እና የሌላውን ብሔር፣ ቋንቋ፣ ዘውግ ማንቋሸሽ፣ ማብጠልጠል እና ማበሻቀጥ በዘረኝነት በሽታ የተጠቃ ሰው አይነተኛ መለያ ጠባይ ነው። በዘረኝነት አራንቋ የተጠቃ ሰው የእሥልምና ልዕልና ከመጤፍና ከመቁብ አለመቁጠር ይታይበታል። እርሱ የሚያስጨንቀው እሥልምናው ሳይሆን የመጣበት የብሔር፣ የቋንቋ፣ የዘውግ ዳራ ነው። በአሳብ መሞገት አብርኆት ሲሆን የሰውን ብሔር፣ ቋንቋ፣ ዘውግ መጥረግና ማጥረግረግ ጽልመት ነው። ሰው በአሳብ መሞገት ሲያቅተው የምላስ ፍልጥ የሆነውን ጽርፈተ-ቃላት ይጠቀማል። ዘረኞች በብዕራቸው ጭረውና በጉልበታቸው ተፍጨርጭረው በስሌት ሳይሆን በስሜት፥ በፈሊጥ ሳይሆን በፍልጥ ለኡማው ጦስና ጥንቡሳስ ሲሆኑ ይታያል።
እሥልምና ከሙገሳና ከወቀሳ ነጻ ሆነን ዕውቀታችንን፣ ጊዜአችንን፣ ጉልበታችንን እና ንዋያችን የምናፈስለት ዲን እንጂ ሙገሳውን ሽቶና ወቀሳውን ሸሽቶ የምጓዝበት ፋናና ፍኖት አይደለም።
ከዚው ሁሉ የሚያጅበት በአንድ ወቅት ለእሥልምና ተቆርቋሪ ነን የሚሉ ልጆችም አሸሼ ገዳዬ፣ ያዙኝ ልቀቁኝ፣ እንቧ ከረዮ፣ እሪ ከረዮ ሲሉ ይታያሉ። በበሽታው መጠቃታቸው የሚያሳየው ተዉ! ሲባሉ ከመስማት ይልቅ ተገልጥብጠው፦ "አንድ እንትን ነህ እንዴ? በማለት እርርና ምርር ብለው ሲንጨረጨሩና ሲንተከተኩ "በሞቀበት ጣዱኝ" ሲሉ ይስተዋላል። ዲኑል ኢሥላምን ሰውን የሚያስተሳስር የአላህ ገመድ እያለ በዘረኝነት መለያየት “አትለያዩ” ያለን አላህ አለመታዘዝ ነው። በዘመነ-ጃህሊያህ ጊዜ ጠበኞችም በነበርን ጊዜ በእኛ ላይ የዋለውን የአላህን ጸጋ እናስታውስ፤ በልቦቻችሁም መካከል አስማማን፤ በጸጋውም ወንድማማቾች ሆንን፥ በእሳት ጉድጓድ አፋፍም ላይ በነበር ጊዜ አዳነን፦
3፥103 *የአላህንም የማመን ገመድ ሁላችሁም ያዙ፡፡ አትለያዩም፡፡ ጠበኞችም በነበራችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ የዋለውን የአላህን ጸጋ አስታውሱ፡፡ በልቦቻችሁም መካከል አስማማ፡፡ በጸጋውም ወንድማማቾች ኾናችሁ፡፡ በእሳት ጉድጓድ አፋፍም ላይ ነበራችሁ፡፡ ከእርስዋም አዳናችሁ*፡፡ እንደዚሁ ትመሩ ዘንድ አላህ ለእናንተ አንቀጾቹን ያብራራል፡፡ وَاعْتَصِمُوا بِحَبْلِ اللَّهِ جَمِيعًا وَلَا تَفَرَّقُوا ۚ وَاذْكُرُوا نِعْمَتَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ إِذْ كُنتُمْ أَعْدَاءً فَأَلَّفَ بَيْنَ قُلُوبِكُمْ فَأَصْبَحْتُم بِنِعْمَتِهِ إِخْوَانًا وَكُنتُمْ عَلَىٰ شَفَا حُفْرَةٍ مِّنَ النَّارِ فَأَنقَذَكُم مِّنْهَا ۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمْ آيَاتِهِ لَعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ

በእሥልምና ዐቅብተ እምነት ውስጥ ያላችሁ ልጆች በዚህ ረገድ ጉልህ ሚና ልትጫወቱ ይገባችኃል። አበው፦ "እፍ ብለህ ታነዳነህ እፍ ብለህ ታጠፋለህ አጠቃቀምህ ነው" ይላሉ። ስለዚህ መገናኛ ብዙኃንን መርፌ ወስፌ ሆነን ሌላው ከምንጎዳ ለአውንታዊ ነገር እንጠቀምበት። የኢሥላም ልዕልና ከዘር፣ ከብሔር፣ ከቋንቋ፣ ከቀለም፣ ከፓለቲካ በላይ ነው። አላህ ሁላችንም ያስተካክለን፥ ሂዳያ ይስጠን፣ ከጥንቧ ዘረኝነት ይጠብቀን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ወርቃማው ሕግ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥36 አላህንም አምልኩ፡፡ በእርሱም ምንንም አታጋሩ፡፡ *"በወላጆችና በቅርብ ዝምድና ባለቤትም፣ በየቲሞችም፣ በምስኪኖችም፣ በቅርብ ጎረቤትም፣ በሩቅ ጎረቤትም፣ በጎን ባልደረባም፣ በመንገደኛም፣ እጆቻችሁም ንብረት ባደረጓቸው፣ መልካምን ሥሩ"*። አላህ ኩራተኛ ጉረኛ የኾነን ሰው አይወድም፡፡ وَاعْبُدُوا اللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا ۖ وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا وَبِذِي الْقُرْبَىٰ وَالْيَتَامَىٰ وَالْمَسَاكِينِ وَالْجَارِ ذِي الْقُرْبَىٰ وَالْجَارِ الْجُنُبِ وَالصَّاحِبِ بِالْجَنبِ وَابْنِ السَّبِيلِ وَمَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ مَن كَانَ مُخْتَالًا فَخُورًا

ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ያለ አብላጫውን ሾላ በድፍኑ ሆኖ፦ "እኔ ከሞትኩኝ ሰርዶ በእኔ ላይ አይብቀል" እንዳለችው አህያ ሆኗል ብዬ ብናገር እብለት ወይም ቅጥፈት አሊያም ግነት አይሆንብኝም። አበው፦ "እፍ ብለህ ታነዳነህ እፍ ብለህ ታጠፋለህ አጠቃቀምህ ነው" ይላሉ። መገናኛ ብዙኃንን ለአውንታዊ ማሕበረሰብ ግንባታ አሊያም ለአውንታዊ ማኅበረሰብ ውድቀት ሊውል ይችላል፥ አጠቃቀማችን ነው። ለአሉታዊ ከተጠቀምንበት በለስ የቀናው ያጠፋበታል እድል የጎደለው ይጠፋበታል። ማኅበራዊ ሚድያ ላይ ያለው አብዛኛውን ማለት ይቻላል የሌላን ሰው ስሜት፣ ፍላጎት፣ አስተሳሰብ፣ አመለካከት ማንቋሸሽ ሥራዬ ብሎ ተያይዞታል። ይህ የሆነው ወርቃማውን ሕግ ስለረሳን ነው። ይህ ወርቃማው ሕግ ምንድን ነው?
አምላካችን አላህ ስለ ሥነ-ምግባር መርኆ ሲናገር፦ "በወላጆችና በቅርብ ዝምድና ባለቤትም፣ በየቲሞችም፣ በምስኪኖችም፣ በቅርብ ጎረቤትም፣ በሩቅ ጎረቤትም፣ በጎን ባልደረባም፣ በመንገደኛም፣ እጆቻችሁም ንብረት ባደረጓቸው፣ መልካምን ሥሩ" ነው፦
4፥36 አላህንም አምልኩ፡፡ በእርሱም ምንንም አታጋሩ፡፡ *"በወላጆችና በቅርብ ዝምድና ባለቤትም፣ በየቲሞችም፣ በምስኪኖችም፣ በቅርብ ጎረቤትም፣ በሩቅ ጎረቤትም፣ በጎን ባልደረባም፣ በመንገደኛም፣ እጆቻችሁም ንብረት ባደረጓቸው፣ መልካምን ሥሩ"*። አላህ ኩራተኛ ጉረኛ የኾነን ሰው አይወድም፡፡ وَاعْبُدُوا اللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا ۖ وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا وَبِذِي الْقُرْبَىٰ وَالْيَتَامَىٰ وَالْمَسَاكِينِ وَالْجَارِ ذِي الْقُرْبَىٰ وَالْجَارِ الْجُنُبِ وَالصَّاحِبِ بِالْجَنبِ وَابْنِ السَّبِيلِ وَمَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ مَن كَانَ مُخْتَالًا فَخُورًا

ለሰዎች በጎ ማድረግ ካልተቻለ ሰዎች እኛ ላይ ሊያደርጉብህ የማንፈልገውን ነገር በሌላው ላይ አለማድረግ ነው። ይህ ወርቃማ ሕግ ይባላል። ነቢያችን"ﷺ" ስለዚህ ወርቃማ ሕግ ሲናገሩ፦ "ከእናንተ አንድም አላመነም ለራሱ የሚወደውን ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ ወይም ለራሱ የሚወደውን ለጎረቤቱ እስካልወደደ ድረስ" ብለዋል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 77
አነሥ ኢብኑ ማሊክ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ ነቢዩም"ﷺ" አሉ፦ *"ከእናንተ አንድም አላመነም ለራሱ የሚወደውን ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ ወይም ለራሱ የሚወደውን ለጎረቤቱ እስካልወደደ ድረስ"*፡፡ يُحَدِّثُ عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ لاَ يُؤْمِنُ أَحَدُكُمْ حَتَّى يُحِبَّ لأَخِيهِ - أَوْ قَالَ لِجَارِهِ - مَا يُحِبُّ لِنَفْسِه
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 6
አነሥ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ ነቢዩም"ﷺ" አሉ፦ *"ከእናንተ አንድም አላመነም ለራሱ የሚወደውን ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ"*፡፡ عَنْ أَنَسٍ ـ رضى الله عنه ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم‏.‏
وَعَنْ حُسَيْنٍ الْمُعَلِّمِ، قَالَ حَدَّثَنَا قَتَادَةُ، عَنْ أَنَسٍ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ لا يُؤْمِنُ أَحَدُكُمْ حَتَّى يُحِبَّ لأَخِيهِ مَا يُحِبُّ لِنَفْسِهِ

ኢማም ነወዊይ ይህንን ሐዲስ ሲያብራሩ፦
ሸርሑል አርበዒን 13
*"እዚህ ንግግር ላይ "ወንድሙ" የተባለው በጥቅሉ ሙሥሊሙንም ካፊሩንም ነው"*። الأولى أن يحمل ذلك على عموم الأخوة حتى يشمل الكافر والمسلم فيحب لأخيه الكافر ما يحب لنفسه من دخوله في الإسلام كما يحب لأخيه المسلم دوامه على الإسلام ولهذا كان الدعاء بالهداية للكافر مستحبا والمراد بالمحبة إرادة الخير والمنفعة ثم المراد المحبة الدينية لا المحبة البشرية

የራሱ ስሜት፣ ፍላጎት፣ አስተሳሰብ፣ አመለካከት እንዲነካበት የማይፈልግ የሌላው ሰው ስሜት፣ ፍላጎት፣ አስተሳሰብ፣ አመለካከት አይነካም። ይህ ወርቃማ የሥነ-ምግባር ሕግ የነቢያት ሁሉ አስተምህሮት ነው፦
ማቴዎስ 7፥12 እንግዲህ *"ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ ሕግም ነቢያትም ይህ ነውና"*።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ታላቁ ታምር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

6:124 “ታምርም” በመጣላቸው ጊዜ፡- «የአላህ መልክተኞች የተሰጡትን ብጤ እስክንሰጥ ድረስ በፍጹም አናምንም» አሉ وَإِذَا جَآءَتْهُمْ ءَايَةٌۭ قَالُوا۟ لَن نُّؤْمِنَ حَتَّىٰ نُؤْتَىٰ مِثْلَ مَآ أُوتِىَ رُسُلُ ٱللَّهِ ۘ ٱللَّهُ أَعْلَمُ حَيْثُ يَجْعَلُ رِسَالَتَهُۥ ۗ سَيُصِيبُ ٱلَّذِينَ أَجْرَمُوا۟ صَغَارٌ عِندَ ٱللَّهِ وَعَذَابٌۭ شَدِيدٌۢ بِمَا كَانُوا۟ يَمْكُرُونَ ፡፡

መግቢያ
ቁርኣን ለነቢያችን ነቢይነት ማረጋገጫ ይሆን ዘንድ ከተሰጣቸው ተአምራት ውስጥ ታላቁ እና ዋነኛው ነው፣ የቁርኣን ተአምራዊነት ከቀደምት ነቢያት ተአምራት በሁለት መልኩ ይለያል፦
አንደኛ የቀደምት ነቢያት ተአምራት በአይን የሚታይ፣ በእጅ የሚዳሰስ ነው፣ ይህም ታምር ”ሒስሲይ” ይባላል፣ የቀደምት ነቢያት ተአምር ከነቢይነት ዘመናቸው ጋር ብቻ የተቆራኘ ነው፣ ከእነርሱ ሞት በኋላ ያበቃል፣ ይህም ታምር ”ወቅቲይ” ማለትም ጊዜአዊ ይሰኛል፡፡
ሁለተኛ ለነቢያችን ነቢይነት እንደ ማስረጃ የተሰጣቸው ቁርኣን ግን ህሊናን የሚያናግር፡ አእምሮን የሚቆጣጠርና ልብን የሚገዛ፣ በሚያስተላልፋቸው መልእክቱ ሰዎችን ለለውጥ የሚዳርግ ነው፣ ይህም ታምር ”መዕነዊይ” ይባላል፣ ቁርኣን ከነቢያችን ሞት በኋላ እንኳ ተአምራዊነቱ አላከተመም፣ እስከ ቂያማ ድረስ በነበረው ተአምራዊነቱ ይቀጥላል፤ በዚህም ”አበዲይ” ይሰኛል፡፡ እስቲ ይህንን ታላቅ ታምር በወረደበት ወቅት ሰዎች እንዴት እንዳስተባበሉት እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
“የአላህ ታምራት”
ቁርአን በወረደ ጊዜ ሰዎች፦ “ከጌታውም በእርሱ ላይ ለምን ተዓምር አልተወረደም” አሉ፤ አምላካችን አላህም፦ “አላህ ተአምርን በማውረድ ላይ ቻይ ነው” በላቸው ብሎ መለሰ ሰጠ፦
6:37 *«ከጌታውም በእርሱ ላይ ለምን ተዓምር አልተወረደም»* አሉ፡፡ *«አላህ ተአምርን በማውረድ ላይ ቻይ ነው» በላቸው*፡፡ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡

አላህ ቁርኣንን ታምር አድርጎ ለነቢያችን ነቢይነት ማረጋገጫ ይሆን ዘንድ እንዳወረደው ይናገራል፦
3:108 ይህች በአንተ ላይ በእዉነት የምናነባት ስትሆን የአላህ *ታምራት* آيَاتُ ናት፤
45:6 እነዚህ፣ በአንተ ላይ በእውነት የምናነባቸው ሲኾኑ *የአላህ ታምራት* آيَاتُ ናቸው፤ ከአላህና *ከታምራቶቹም* وَآيَاتِهِ ወዲያ በየትኛው ንግግር ያምናሉ?
2:252 እነዚህ በእውነት በአንተ ላይ የምናነባቸው ሲኾኑ *የአላህ ታምራት* آيَاتُ ናቸው፤
3:58 ይህ *ከታምራቶች”* الْآيَاتِ እና ጥበብን ከያዘዉ ተግሣጥ ሲሆን በአንተ ላይ እናነበዋለን።

አላህ የሚነበብ ሆኖ ቁርአን መወረዱ ታምር እንደሆነ እንደነገረን ሁሉ ነብያችንም ቁርአን ለእሳቸው ነብይነት ታምር እንደሆነ በአጽንኦትና በአንክሮት ነግረውናል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 66 , ሐዲስ 3:
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ ነብዩ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ማንኛውም ነብይ ህዝቦቹ ያምኑበት ዘንድ ታምር ተሰጠውታል፣ ነገር ግን ለእኔ የተሰጠኝ ታምር አላህ ወደ እኔ ያወረደው ወህይ ነው عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَا مِنَ الأَنْبِيَاءِ نَبِيٌّ إِلاَّ أُعْطِيَ مَا مِثْلُهُ آمَنَ عَلَيْهِ الْبَشَرُ، وَإِنَّمَا كَانَ الَّذِي أُوتِيتُ وَحْيًا أَوْحَاهُ اللَّهُ إِلَىَّ فَأَرْجُو أَنْ أَكُونَ أَكْثَرَهُمْ تَابِعًا يَوْمَ الْقِيَامَةِ ‏” ።
ነጥብ ሁለት
“ማስተባበያ”
ሰዎች ቁርአን ታምር ሆኖ በመጣላቸው ጊዜ፡- “የአላህ መልክተኞች የተሰጡትን ብጤ እስክንሰጥ ድረስ በፍጹም አናምንም” ወይም “ለሙሳ የተሰጠው ቢጤ አይሰጠውም ኖሯልን ” ብለው ይህንን ታምር አስተባበሉ፦
6:124 *”ታምርም በመጣላቸው ጊዜ”*፡- «የአላህ መልክተኞች የተሰጡትን ብጤ እስክንሰጥ ድረስ በፍጹም አናምንም» አሉ፡፡
28:48 እውነቱም ከእኛ ዘንድ በመጣላቸው ጊዜ “ለሙሳ የተሰጠው ቢጤ አይሰጠውም ኖሯልን ” አሉ ። ከዚህ በፊት ሙሳ በተሰጠው አልካዱምን? አሉም “የተረዳዱ ሁለት ድግምተኞች ናቸው” ፤ አሉም “እኛ በሁለቱም ከሀዲዎች ነን”።

ለሙሳ የተሰጠው ግልጽ የሆኑን “ዘጠኝ ታምራቶች” ናቸው፦
17:101 ለሙሳም ግልጽ የሆኑን “ዘጠኝ ታምራቶች” በእርግጥ ሰጠነው፤

አላህ ታምር ብሎ “ዘጠኝ ታምራቶች” ቢያሳይም በወቅቱ ሙሳና ሃሩንን “የተረዳዱ ሁለት ድግምተኞች ናቸው” አሉ፤ ከዚህ ታምር ይልቅ “ሙሳ ሆይ አላህን በግልጽ እስከምናይልህ ድረስ ለአንተ በፍጹም አናምንልህም” አሉ፦
2:55 ሙሳ ሆይ አላህን በግልጽ እስከምናይልህ ድረስ በአንተ በፍጹም አናምንልህም ”

በወቅቱ የነበሩ ሰዎች ስለ ነብያችን፦ “ለሙሳ የተሰጠው ቢጤ አይሰጠውም ኖሯልን ” አሉ፤ አላህም፦ “ከዚህ በፊት ሙሳ በተሰጠው አልካዱምን?” በማለት ያ የተባለው ታምር ተመልሶ ቢመጣ አሁን ማስተባበላቸውን እንደማይቀር ተናግሯል።

ነጥብ ሶስት
“አስጠንቃቂ”
እነዚያም የካዱት፦ “በእርሱ ላይ ከጌታው ታምር ለምን አልተወረደለትም?” ብለው የጠየቁት ታምር የአላህ መልክተኞች የተሰጡትን ብጤ አይነት ታምር ነው፤ ይህንን ታምር ነብያችን በራሳቸው ማምጣት አይችሉም፤ እርሳቸው አስጠንቃቂ እንጂ በፍላጎታቸው ታምር እውራጅ አይደሉም፤ ታምር አውራጅ አላህ ነው፤ ስለሆነም ቁርአን በእርሳቸው ላይ ታምር አድርጎ አውርዷል፦
13:7 እነዚያም የካዱት፦ “በእርሱ ላይ ከጌታው ታምር ለምን አልተወረደለትም?” ይላሉ፤ አንተ “አስጠንቃቂ” ብቻ ነህ ለሕዝብም ሁሉ መሪ አላቸው።
10:20 በእርሱ ላይም ከጌታው የሆነች ታምር ለምን አትወረድለትም ይላሉ፡፡ «ሩቅ ነገርም ሁሉ የአላህ ብቻ ነው፡፡ ተጠባበቁም፤ እኔ ከናንተ ጋር ከሚጠባበቁት ነኝና» በላቸው፡፡
6:37 «ከጌታውም በእርሱ ላይ ለምን ተዓምር አልተወረደም» አሉ፡፡ «አላህ ተአምርን በማውረድ ላይ ቻይ ነው» በላቸው፡፡

በእርግጥም አንድ መልእክተኛ ሲመጣ አላህ በፈቃዱ ከሚሰጠው ታምር በራሱ ሊያመጣ አይችል፦
13:38 ለማንኛውም *መልክተኛ በአላህ ፈቃድ እንጂ፥ ታምር ሊያመጣ አይገባውም*፤
40:78 ለማንኛውም *መልክተኛ በአላህ ፈቃድ ካልሆነ ታምርን ሊያመጣ አይገባውም*።
መደምደሚያ
በኢየሱስ ዘመንም ኢየሱስ ብዙ ታምር እያደረገ በዘመኑ የነበሩ ሰዎች የሚጠይቁት ታምር ግን ከሰማይ ነው፤ ኢየሱስም እነርሱን የጠየቁትን ታምር ከመፈፀም ይልቅ “ለዚህ ትውልድ *”ምልክት አይሰጠውም”* ብሎ መለሰ፦
ማርቆስ 8፥11-12 ፈሪሳውያንም ወጡና ሊፈትኑት *”ከሰማይ ምልክት”* ከእርሱ ፈልገው ከእርሱ ጋር ይከራከሩ ጀመር። በመንፈሱም እጅግ ቃተተና፦ ይህ ትውልድ ስለ ምን *”ምልክት”* ይፈልጋል? እውነት እላችኋለሁ፥ ለዚህ ትውልድ *”ምልክት አይሰጠውም”* አለ።
ማቴዎስ 16:4 ክፉና አመንዝራ ትውልድ *”ምልክት”* ይሻል፥ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር *”ምልክት አይሰጠውም”*። *ትቶአቸውም ሄደ*።

ኢየሱስ፦ “ለዚህ ትውልድ ምልክት አይሰጠውም” ማለቱ ሰዎች የፈለጉት ከሰማይ ምልክት አላደርግም ማለት እንጂ ምልክት አለማድረግን አያሳይም፣ እነርሱ የፈለጉት ምልክት ከሰማይ ምልክት ነው፣ ነገር ግን ኢየሱስ እነርሱ ከጠየቁት ታምር በተቃራኒው ያደረገውን ታምር በፊታቸው ምንም ቢያደርግ በእርሱ አላመኑም፦
ዮሐንስ 12፥37-38 ነገር ግን ይህን ያህል *”ምልክት በፊታቸው ምንም ቢያደርግ”* ነቢዩ ኢሳይያስ፦ ጌታ ሆይ፥ ማን ምስክርነታችንን አመነ? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገለጠ? ብሎ የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ *”በእርሱ አላመኑም”*።

በተመሳሳይም በነቢያችን ዘመን የነበሩት ሰዎች ታምር ብለው የሚሉትና አላህ ታምር የሚለው ሁለት ለየቅል ነው፣ የቁርአንን ታላቅ ታምርነት በወቅቱ የነበሩት ሰዎች እነርሱ በሚፈልጉት መልኩ ባይመጣም ለሰው የሚበጅ ታምር ማምጣት የሚችለው አላህ ብቻ ነው፤ ከላይ የቀረበውን ነጥብ በኢየሱስ ታምር ማሳያነት በቀላሉ መረዳት ይቻላል። አላህ ታምር ሲመጣላቸው እነርሱ የሚፈልጉት ያንን ታምር ስላልሆነ ይሸሻሉ፦

36:46 ከጌታቸውም ታምራት ማንኛይቱም ታምር አትመጣላቸውም፤ ከእርሷ የሚሸሹ ቢሆኑ እንጂ። وَمَا تَأْتِيهِم مِّنْ ءَايَةٍۢ مِّنْ ءَايَٰتِ رَبِّهِمْ إِلَّا كَانُوا۟ عَنْهَا مُعْرِضِينَ

እነዚያን በአላህ ታምራት ያስተባበሉ እሳት ይገባሉ፦
4፥56 እነዚያን *በተአምራታችን ያስተባበሉትን በእርግጥ እሳትን እናገባቸዋለን*፡፡ إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَا سَوْفَ نُصْلِيهِمْ نَارًۭا

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም።
ልብ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

51፥21 *”በራሳችሁም ውስጥ” ምልክቶች አሉ፤ ታዲያ አትመለከቱምን?* وَفِي أَنفُسِكُمْ ۚ أَفَلَا تُبْصِرُونَ

የሥነ-ልቦና ጥናት”Psychology” ጥናቱን ያደረገው በልብ ላይ ነው፤ “ሳይኮ” ψυχή ማለት “መንፈስ” “ነፍስ” “ልብ” “ህሊና” “አእምሮ” ማለት ነው፤ “ሎጂአ” λογία ደግሞ “ጥናት” ማለት ነው፤ የሰው መንፈስ ማዕከሉ “ልብ” ነው።
“ልብ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ቀልብ” قَلْب “ፉዓድ” فُؤَاد እና “ሰድር” صَدْر ሲሆን የውስጥን ማንነት ለማሳወቅ የመጣ ቃል ነው፤ ሰዎች ውሳጣዊ ተፈጥሮን “ቆሌ” “ቆሽት” “አንጀት” “ናላ” ብለው በእማራዊ ቃላት ፍካሬአዊ ልብን ይገልጡታል፤ “ሕሊና” የሚለው ቃል “ሐለየ” ማለትም “አሰበ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማሰቢያ” ማለት ነው፤ “ልብ” የሚለው ቃል “ለበወ” ማለትም “አመዛዘነ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማመዛዘኛ” ማለት ነው፤ “አእምሮ” የሚለው ቃል “አእመረ” ማለትም “ዐወቀ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማወቂያ” ማለት ነው፤ ልብ የኢማን መቀመጫ፣ በዚክር የሚረጥብ፣ በአላህ ንግግር የሚረጋጋ እና በአምልኮ የሚሰፋ ውስጣዊ ማንነት ነው፤ እነዚህ ከቃሉ መረዳት ይቻላል፦
“ቀልብ”
2፥97 ለጂብሪል ጠላት የኾነ ሰው በቁጭት ይሙት በላቸው፡፡ እርሱ ከበፊቱ ለነበሩት አረጋጋጭ ለምእመናን መሪና ብስራት ሲኾን በአላህ ፈቃድ *”በልብህ” ላይ አውርዶታልና፡፡ قُلْ مَن كَانَ عَدُوًّۭا لِّجِبْرِيلَ فَإِنَّهُۥ نَزَّلَهُۥ عَلَىٰ قَلْبِكَ بِإِذْنِ ٱللَّهِ مُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ وَهُدًۭى وَبُشْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ
26፥194 ከአስጠንቃቂዎቹ ትኾን ዘንድ *”በልብህ”* ላይ አወረደው፡፡ عَلَىٰ قَلْبِكَ لِتَكُونَ مِنَ ٱلْمُنذِرِينَ
13፥28 እነርሱም እነዚያ ያመኑ *”ልቦቻቸውም”* አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው፡፡ ንቁ! አላህን በማውሳት *”ልቦች”* ይረካሉ፡፡ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ ٱللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ ٱللَّهِ تَطْمَئِنُّ ٱلْقُلُوبُ

“ፉዓድ”
11፥120 ከመልክተኞቹም ዜናዎች ተፈላጊውን ሁሉንም *”ልብህን”* በእርሱ የምናረካበትን እንተርክልሃለን፡፡ በዚህችም ሱራ እውነቱ ነገር ለምእምናን ግሳጼና ማስታወሻ መጥቶልሃል፡፡ وَكُلًّۭا نَّقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنۢبَآءِ ٱلرُّسُلِ مَا نُثَبِّتُ بِهِۦ فُؤَادَكَ ۚ وَجَآءَكَ فِى هَٰذِهِ ٱلْحَقُّ وَمَوْعِظَةٌۭ وَذِكْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ
25፥32 እነዚያ የካዱትም «ቁርኣን በእርሱ ላይ ለምን በጠቅላላ አንድ ጊዜ አልተወረደም» አሉ፡፡ እንደዚሁ በእርሱ *”ልብህን”* ልናረጋ ከፋፍለን አወረድነው፡፡ ቀስ በቀስ መለያየትንም ለየነው፡፡ وَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لَوْلَا نُزِّلَ عَلَيْهِ ٱلْقُرْءَانُ جُمْلَةًۭ وَٰحِدَةًۭ ۚ كَذَٰلِكَ لِنُثَبِّتَ بِهِۦ فُؤَادَكَ ۖ وَرَتَّلْنَٰهُ تَرْتِيلًۭا

“ሰድር”
94፥1*”ልብህን”* ለአንተ አላሰፋንልህምን? أَلَمْ نَشْرَحْ لَكَ صَدْرَكَ
20፥25 (ሙሳም) አለ «ጌታዬ ሆይ! “ልቤን” አስፋልኝ፡፡ قَالَ رَبِّ ٱشْرَحْ لِى صَدْرِى
39፥22 አላህ *”ደረቱን”* ለእስልምና ያስፋለትና እርሱም ከጌታው ዘንድ በብርሃን ላይ የኾነ ሰው ልቡ እንደ ደረቀ ሰው ነውን? *”ልቦቻቸውም”* ከአላህ መወሳት ለደረቁ ሰዎች ወዮላቸው፡፡ እነዚያ በግልጽ መሳሳት ውስጥ ናቸው፡፡ أَفَمَن شَرَحَ ٱللَّهُ صَدْرَهُۥ لِلْإِسْلَٰمِ فَهُوَ عَلَىٰ نُورٍۢ مِّن رَّبِّهِۦ ۚ فَوَيْلٌۭ لِّلْقَٰسِيَةِ قُلُوبُهُم مِّن ذِكْرِ ٱللَّهِ ۚ أُو۟لَٰٓئِكَ فِى ضَلَٰلٍۢ مُّبِينٍ

ይህ ቀልብ ከተስተካከለ ሙሉ አካላችን ይስተካከላል። ቀልብ በአካል ላይ አውንታዊና አሉታዊ ተጽእኖ ማድረግ ይችላል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 22, ሐዲስ 133
ኑዕማን ኢብኑ በሽር እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"በአካል ውስጥ አንዲት ቁራጭ ስጋ አለች፥ እርሷ ከተስተካከለች ሁሉም አካል ተስተካከለ፤ እርሷ ከተበላሸች ሁሉም አካል ተበላሸ። ይህቺም ልብ ናት"*። وَإِنَّ فِي الْجَسَدِ مُضْغَةً إِذَا صَلَحَتْ صَلَحَ الْجَسَدُ كُلُّهُ وَإِذَا فَسَدَتْ فَسَدَ الْجَسَدُ كُلُّهُ أَلاَ وَهِيَ الْقَلْبُ ‏

የውስጥ ተፈጥሮ የሆነውን ቀልብ በማጥራት የምናስተነትንበት ትምህርት “አት-ተሰዉፍ” الْتَّصَوُّف‎ ይባላል፤ በማጥራት የሚያስተነትነው ሰው “ሙተሰዉፍ” مُتَصَوُّف‎ ይባላል። በራሳችን ውስጥ ያለው ውሳጣዊ ምልክትቶች ብዙ ናቸው፤ ይህንን ውሳጣዊ ነገር ሁሉ አላህ ብቻ ነው የሚያውቀው፦
51፥21 *”በራሳችሁም ውስጥ” ምልክቶች አሉ፤ ታዲያ አትመለከቱምን?* وَفِي أَنفُسِكُمْ ۚ أَفَلَا تُبْصِرُونَ
17፥25 *ጌታችሁ በራሳችሁ ውስጥ ያለውን ሁሉ አዋቂ ነው*፡፡ ታዛዦችም ብትኾኑ በመሳሳትም ብታጠፉ እርሱ ለተመላሾች መሓሪ ነው፡፡ رَّبُّكُمْ أَعْلَمُ بِمَا فِي نُفُوسِكُمْ ۚ إِن تَكُونُوا صَالِحِينَ فَإِنَّهُ كَانَ لِلْأَوَّابِينَ غَفُورًا

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
መተት

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

17፥47 እኛ ወደ አንተ በሚያዳምጡ ጊዜ እነርሱም በሚንሾካሾኩ ጊዜ በዳዮች እርስ በርሳቸው *”የተደገመበትን ሰው እንጂ አትከተሉም በሚሉጊዜ”* በእርሱ የሚያዳምጡበትን ምክንያት ዐዋቂ ነን፡፡ نَّحْنُ أَعْلَمُ بِمَا يَسْتَمِعُونَ بِهِۦٓ إِذْ يَسْتَمِعُونَ إِلَيْكَ وَإِذْ هُمْ نَجْوَىٰٓ إِذْ يَقُولُ ٱلظَّٰلِمُونَ إِن تَتَّبِعُونَ إِلَّا رَجُلًۭا مَّسْحُورًا

“ዒስማ” عِصْمَة‌‎ ማለት ከኃጢያት “ጥበቃ”protection” ማለት ሲሆን “ማዕሱም” معصوم‌‎ ደግሞ ከኃጢያት የሚጠበቀው ነብይ ነው፤ ኃጢያት በሁለት ይከፈላል፦
“ከባኢር” كبائر ማለት “አበይት ኃጢያት”ሲሆን እነርሱም፦ ሺርክ፣ ዝሙት፣ አራጣ፣ ቁማር፣ ቅጥፈት፣ ሌብነት ወዘተ..ናቸው።
“ሰጋኢር” صغائر ማለት “ንዑሳን ኃጢያት” ሲሆኑ በአለማወቅ አሊያም በአለፍፅምና የሚመጡ ስህተት ናቸው፤ ለምሳሌ መናደድ፣ መቆጣት፣ ማዘን፣ መበሳጨት ወዘተ፦
53፥32 እነዚያ የኃጢያትን “ታላላቆችና” አስጠያፊዎቹን የሚርቁ ናቸው፤ ግን “ትናንሾቹ” የሚማሩ ናቸው። ጌታህ ምሕረተ ሰፊ ነውና፤ ٱلَّذِينَ يَجْتَنِبُونَ كَبَٰٓئِرَ ٱلْإِثْمِ وَٱلْفَوَٰحِشَ إِلَّا ٱللَّمَمَ ۚ إِنَّ رَبَّكَ وَٰسِعُ ٱلْمَغْفِرَةِ
4፥31 ከእርሱ ከተከለከላችሁት “ታላላቆቹን” ብትርቁ “ትናንሾቹን ኃጢአቶቻችሁን” ከእናንተ እናብሳለን፤ የተከበረንም ስፍራ እናገባችኋለን፡፡ إِن تَجْتَنِبُوا۟ كَبَآئِرَ مَا تُنْهَوْنَ عَنْهُ نُكَفِّرْ عَنكُمْ سَيِّـَٔاتِكُمْ وَنُدْخِلْكُم مُّدْخَلًۭا كَرِيمًۭا
42፥37 ለእነዚያም “የኀጢያትን ታላላቆችና” ጠያፎችን የሚርቁ በተቆጡም ጊዜ እነርሱ የሚምሩ ለሆኑት። وَٱلَّذِينَ يَجْتَنِبُونَ كَبَٰٓئِرَ ٱلْإِثْمِ وَٱلْفَوَٰحِشَ وَإِذَا مَا غَضِبُوا۟ هُمْ يَغْفِرُونَ

እንግዲያውስ በኢስላም ነብያት የሚጠበቁት ከአበይት ኃጢያት ነው፤ ከንዑሳን ኃጢያት እንደማንኛውም ሰው አለፍፅምና ስላለባቸው በራሳቸው ሆነ በሰይጣን ሊሳሳቱ ይችላሉ፤ ለምሳሌ አደም ነብይ ነው፤ ግን ሰይጣን ወደ እርሱ ጎትጉቶት የጌታውን ትእዛዝ ጣሰ፤ ተሳሳተም፦
20፥120 ሰይጣንም ወደ እርሱ ጎተጎተ «አደም ሆይ! በመዘውተሪያ ዛፍ በማይጠፋ ንግሥናም ላይ ላመላክትህን አለው፡፡ فَوَسْوَسَ إِلَيْهِ ٱلشَّيْطَٰنُ قَالَ يَٰٓـَٔادَمُ هَلْ أَدُلُّكَ عَلَىٰ شَجَرَةِ ٱلْخُلْدِ وَمُلْكٍۢ لَّا يَبْلَىٰ
20፥121 ከእርሷም በሉ፡፡ ለእነርሱም ኀፍረተ ገላቸው ተገለጸች፡፡ ከገነትም ቅጠል በላያቸው ላይ ይለጥፉ ጀመር፡፡ *”አደምም የጌታውን ትእዛዝ ጣሰ፤ ተሳሳተም”*፡፡ فَأَكَلَا مِنْهَا فَبَدَتْ لَهُمَا سَوْءَٰتُهُمَا وَطَفِقَا يَخْصِفَانِ عَلَيْهِمَا مِن وَرَقِ ٱلْجَنَّةِ ۚ وَعَصَىٰٓ ءَادَمُ رَبَّهُۥ فَغَوَىٰ

በተመሳሳይ ሰይጣን ኢዮብን በጉዳትና በስቃይ ጎድቶታል፤ እንደ ባይብሉም ከእግሩ ጫማ ጀምሮ እስከ አናቱ ድረስ በክፉ ቍስል መቶታል፤ ይህ ሲደረግ ሰይጣንን እግዚአብሔርም ሕይወቱን ተወው እንጂ እርሱ በእጅህ ነው አለው፦
38፥41 ባሪያችንን አዩብንም አውሳላቸው፡፡ *«እኔ ሰይጣን በጉዳትና በስቃይ ነካኝ»* ሲል ጌታውን በተጣራ ጊዜ፡፡ وَٱذْكُرْ عَبْدَنَآ أَيُّوبَ إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُۥٓ أَنِّى مَسَّنِىَ ٱلشَّيْطَٰنُ بِنُصْبٍۢ وَعَذَابٍ
ኢዮብ 2፥6-7 እግዚአብሔርም ሰይጣንን ሕይወቱን ተወው እንጂ እነሆ፥ እርሱ በእጅህ ነው አለው። ሰይጣንም ከእግዚአብሔር ፊት ወጣ፥ ኢዮብንም ከእግሩ ጫማ ጀምሮ እስከ አናቱ ድረስ በክፉ ቍስል መታው።

እንዲሁ ሰይጣን ዳዊትን፦ “ሂድ፥ እስራኤልንና ይሁዳን ቍጠር” ብሎ አዞት ቆጥሯል፦
2ኛ ሳሙኤል 24.1 ደግሞም የእግዚአብሔር ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፥ ዳዊትንም፦ *ሂድ፥ እስራኤልንና ይሁዳን ቍጠር* ብሎ በላያቸው አስነሣው።
1ኛ ዜና መዋዕል 21፥1 ሰይጣንም በእስራኤል ላይ ተነሣ፥ እስራኤልንም ይቈጥር ዘንድ ዳዊትን “አንቀሳቀሰው”።

በተመሳሳይ ሰይጣን ኢየሱስን ወደ ከተማና ወደ ተራራ እየወሰደ የዓለምንም መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም ያሳየው ነበር፦
ማቴዎስ 4፥5 ከዚህ በኋላ *”ዲያቢሎስ ወደ ቅድስት ከተማ ወሰደው”* እና እርሱን በመቅደስ ጫፍ ላይ አቁሞ።
ማቴዎስ 4፥8 ደግሞ *”ዲያቢሎስ እጅግ ረጅም ወደ ሆነ ተራራ ወሰደው”*፥ የዓለምንም መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም አሳይቶ።
ሉቃስ 4:13 ዲያቢሎስም ፈተናውን ሁሉ ከጨረሰ በኋላ *”እስከ ጊዜው ከእርሱ ተለየ”*።

“እስከ ጊዜው ከእርሱ ተለየ” የሚለው ይሰመርበት፤ ሰይጣን ከኢየሱስ ከመለየቱ በፊት ከኢየሱስ ጋር ነበር ማለት ነው፤ የተለየውም ለጊዜው እንደሆነ ተጽፏል፤ ሰይጣን ይህ ሁሉ ነገር በነብያቱ ላይ ሲፈፀም አምላክ እንዴት ዝም አለ? አይ ፈጣሪ ዝም የሚልበት የራሱ ጥበብ አለው ከሆነ መልሱ እንግዲያውስ ነብያችን”ﷺ” በድግምት ተፅእኖ ቢደርስባቸው ምኑ ያስደንቃል? እስቲ ስለ መተት ተፅዕኖ በሁለቱም መጽሐፍት እንመልከት፦
ነጥብ አንድ
“መተት በቁርአን”
ስለ መተት በቁርአን ያለው እሳቤ እንመልከት፤ “ሲሕር” سِحْر የሚለው ቃል “ሰሐረ” سحر ማለትም “ደገመ” ከሚል ስርወ-ግንድ የረባ ሲሆን “ድግምት” “መተት” “አስማት” ማለት ነው፤ ድግምቱን የሚሰራው ሰው ደግሞ “ሳሒር” سَٰحِر ይባላል፤ “ሱሑር” سحور ማለትም በረመዳን ፆም ለመያዝ ከሌሊቱ መጨረሻ የሚመገቡት ምግብ እና “ሰሐር” سَحَر ማለትም “የሌሊት መጨረሻ”before down” የሚሉት ሁለቱ ቃላት ልክ እንደ ሲሕር “ሰሐረ” سحر ከሚለው ስርወ-ግንድ የመጡ ናቸው።
በባቢሎት በሚገኙት በሀሩትና በማሩት ላይ የተወረደው የሲሕር ትምህርት ሰዎችን እንዴት እንደሚጎዳ ማስጠንቀቂያ ሆኖ ነው፤ ነገር ግን ሰይጣናትም በሱለይማን ዘመነ መንግስት ሰዎችን የሚያስተምሩት ለአሉታዊ ነገር ነበር፦
2፥102 ሰይጣናትም በሱለይማን ዘመነ መንግስት የሚያነቡትን ተከተሉ፡፡ ሱለይማንም አልካደም፤ ግን ሰይጣናት ሰዎችን ድግምትን የሚያስተምሩ ሲኾኑ ካዱ፡፡ ያንንም በባቢል በሁለቱ መላእክት በሃሩትና ማሩት ላይ የተወረደውን ነገር ያስተምሩዋቸዋል፡፡ «እኛ መፈተኛ ነንና አትካድ» እስከሚሉም ድረስ አንድንም አያስተምሩም፡፡ ከእነሱም በሰውየውና በሚስቱ መካከል በርሱ የሚለዩበትን ነገር ይማራሉ፡፡ وَٱتَّبَعُوا۟ مَا تَتْلُوا۟ ٱلشَّيَٰطِينُ عَلَىٰ مُلْكِ سُلَيْمَٰنَ ۖ وَمَا كَفَرَ سُلَيْمَٰنُ وَلَٰكِنَّ ٱلشَّيَٰطِينَ كَفَرُوا۟ يُعَلِّمُونَ ٱلنَّاسَ ٱلسِّحْرَ وَمَآ أُنزِلَ عَلَى ٱلْمَلَكَيْنِ بِبَابِلَ هَٰرُوتَ وَمَٰرُوتَ ۚ وَمَا يُعَلِّمَانِ مِنْ أَحَدٍ حَتَّىٰ يَقُولَآ إِنَّمَا نَحْنُ فِتْنَةٌۭ فَلَا تَكْفُرْ ۖ فَيَتَعَلَّمُونَ مِنْهُمَا مَا يُفَرِّقُونَ بِهِۦ بَيْنَ ٱلْمَرْءِ وَزَوْجِهِۦ

ሲሕር በግብጻውያን ዘንድ በጣም የታወቀ ስራ ነው፤ የግብጻውያን ሳሒሪን ዘንጎቻቸውን ወደ እባብ በመቀየት የሰዎች ዓይኖች ላይ ደግመውባቸው ነበር፦
20፥66 «አይደለም ጣሉ» አላቸው፡፡ ወዲያውም ገመዶቻቸውና ዘንጎቻቸው *”ከድግምታቸው የተነሳ እነርሱ የሚሮጡ እባቦች ኾነው ወደ እርሱ ተመለሱ”*፡፡ قَالَ بَلْ أَلْقُوا۟ ۖ فَإِذَا حِبَالُهُمْ وَعِصِيُّهُمْ يُخَيَّلُ إِلَيْهِ مِن سِحْرِهِمْ أَنَّهَا تَسْعَىٰ
7፥116 «ጣሉ» አላቸው፡፡ በጣሉም ጊዜ *”የሰዎቹን ዓይኖች ደገሙባቸው”*፡፡ አስፈራሩዋቸውም፡፡ *ትልቅ ድግምትንም”* አመጡ፡፡ قَالَ أَلْقُوا۟ ۖ فَلَمَّآ أَلْقَوْا۟ سَحَرُوٓا۟ أَعْيُنَ ٱلنَّاسِ وَٱسْتَرْهَبُوهُمْ وَجَآءُو بِسِحْرٍ عَظِيمٍۢ

ትእይንቱን ከሚከታተሉት እና አይኖቻቸው የሚቀጣጥፉትን የድግምተኛ ተንኮል ካዩት መካከል ሙሳ በነፍሱ ውስጥ ፍርሃትን አሳደረ፦
20፥67 ሙሳም *”በነፍሱ ውስጥ ፍርሃትን አሳደረ”*፡፡ فَأَوْجَسَ فِى نَفْسِهِۦ خِيفَةًۭ مُّوسَىٰ

ነገር ግን አላህ ሲሕር ሲሰራ ዝም ማለቱ ለሲሕሩ ማክሸፈያ ሊያመጣ መሆኑን ያሳያል፤ የሙሳ በትር የሚቀጣጥፉትን ዘንግ ውጣዋለች፦
20፤69 «በቀኝ እጅህ ያለቸውንም በትር ጣል፡፡ ያንን የሠሩትን ትውጣለችና፡፡ *”ያ የሠሩት ሁሉ የድግምተኛ ተንኮል ነውና”*፡፡ ድግምተኛም በመጣበት ስፍራ ሁሉ አይቀናውም» አልን፡፡ وَأَلْقِ مَا فِى يَمِينِكَ تَلْقَفْ مَا صَنَعُوٓا۟ ۖ إِنَّمَا صَنَعُوا۟ كَيْدُ سَٰحِرٍۢ ۖ وَلَا يُفْلِحُ ٱلسَّاحِرُ حَيْثُ أَتَىٰ
7፥117 ወደ ሙሳም፡- «በትርህን ጣል» ስንል ላክን፡፡ ጣላትም ወዲያውኑም *”የሚቀጣጥፉትን ትውጣለች”*፡፡ وَأَوْحَيْنَآ إِلَىٰ مُوسَىٰٓ أَنْ أَلْقِ عَصَاكَ ۖ فَإِذَا هِىَ تَلْقَفُ مَا يَأْفِكُونَ
በተመሳሳይ ነብያችን”ﷺ” ላይ ሲሕር ተደርጎባቸው ነበር፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 80 , ሐዲስ 86:
ዓኢሻ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” በድግምት ተፅእኖ ደርሶባቸው ነበር፤ ያላደረጉትን እንዳደረጉ ያስቡ ነበር፤ عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم طُبَّ حَتَّى إِنَّهُ لَيُخَيَّلُ إِلَيْهِ قَدْ صَنَعَ الشَّىْءَ وَمَا صَنَعَهُ،

አላህም ለሲሕሩ ማክሸፈያ “አል-ሙዐወዘተይን” الْمُعَوِّذَتَيْن የሚባሉት ሁለቱ ሱራዎች ሱረቱል ፈለቅ እና ሱረቱ አን-ናስ አውርዷል፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 6 , ሐዲስ 319:
የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ ዛሬ ምን አስደናቂ አንቀጾች ዛሬ ወርደዋል፤ ይህም ብጤአቸው ታይቶ አያውቅም! እነርሱም፦ “በል «በተፈልቃቂው ጎህ ጌታ እጠበቃለሁ” እና በል «በሰዎች ፈጣሪ እጠበቃለሁ» ናቸው። قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ أَلَمْ تَرَ آيَاتٍ أُنْزِلَتِ اللَّيْلَةَ لَمْ يُرَ مِثْلُهُنَّ قَطُّ ‏{‏ قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ الْفَلَقِ‏}‏ وَ ‏{‏ قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ النَّاسِ‏}‏ ‏”‏

ታላቁ ሙፈሲር ኢብኑ ከሲር ስለ “አል-ሙዐወዘተይን” ሲናገር፦ “በሌላ ሐዲስ እንደተዘገበው፦ “ጂብሪል ወደ ነብዩ”ﷺ” መጥቶ እንዲህ አላቸው፦ “ሙሐመድ”ﷺ” ሆይ በማንኛውም ህመም እየተሰቃየህ ነውን? ነብዩም”ﷺ” ነዐም ብለው መለሱ፤ ጂብሪልም በአላህ ስም ሩቂያ እቀራብሃለው፤ ከማንኛውም በሽታ አንተን የጎዳህን፤ ከእያንዳንዱ ሸረኛ እና ክፉ ዓይን፤ አላህ ይፈውስሃል”።
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 10 , ሐዲስ 8:
“ጂብሪል ወደ ነብዩ”ﷺ” መጥቶ እንዲህ አላቸው፦ “ሙሐመድ”ﷺ” ሆይ በማንኛውም ህመም እየተሰቃየህ ነውን? ነብዩም”ﷺ” ነዐም ብለው መለሱ፤ ጂብሪልም በአላህ ስም ሩቂያ እቀራብሃለው፤ ከማንኛውም በሽታ አንተን የጎዳህን፤ ከእያንዳንዱ ሸረኛ እና ክፉ ዓይን፤ አላህ ይፈውስሃል”። أَنَّ جِبْرِيلَ، أَتَى النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم فَقَالَ يَا مُحَمَّدُ اشْتَكَيْتَ قَالَ ‏ “‏ نَعَمْ ‏”‏ ‏.‏ قَالَ بِاسْمِ اللَّهِ أَرْقِيكَ مِنْ كُلِّ شَيْءٍ يُؤْذِيكَ مِنْ شَرِّ كُلِّ نَفْسٍ وَعَيْنِ حَاسِدٍ بِاسْمِ اللَّهِ أَرْقِيكَ وَاللَّهُ يَشْفِيكَ ‏.‏
.
“አል-ሙዐወዘተይን” እራሱ ለሲሕር “ሩቂያ” رقيّة ነው፤ ሩቂያ ማለት “ፈውስ” ማለት ሲሆን የቁርአን አናቅፅ መድሃኒት ነው፦
17:82 “ከቁርአንም” ለምእመናን ”መድኀኒት” እና እዝነት የሆነን ”እናወርዳለን”፤በዳዮችንም ከሳራን እንጂ ሌላን አይጨምርላቸውም። وَنُنَزِّلُ مِنَ ٱلْقُرْءَانِ مَا هُوَ شِفَآءٌۭ وَرَحْمَةٌۭ لِّلْمُؤْمِنِينَ ۙ وَلَا يَزِيدُ ٱلظَّٰلِمِينَ إِلَّا خَسَارًۭا
10:57 እናንተ ሰዎች ሆይ! ከጌታችሁ ግሳጼ ”በደረቶች” ውስጥም ላለው በሽታ “”መድኃኒት”” ለምእምናንም ብርሃንና እዝነት በእርግጥ “መጣችላችሁ”፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ قَدْ جَآءَتْكُم مَّوْعِظَةٌۭ مِّن رَّبِّكُمْ وَشِفَآءٌۭ لِّمَا فِى ٱلصُّدُورِ وَهُدًۭى وَرَحْمَةٌۭ لِّلْمُؤْمِنِينَ

የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” የሲሕር በሽታ ፈውስ ካገኙ በኃላ ይህ በቅጠላ-ቅጠል እና የዕፅ ስር በመበጠስ ሰው ላይ ለሚተበተብ በሽታ ጠዋት ጠዋት ሰባት የዘንባባ ተምር መብላት መድሃኒት እንደሆነ ነግረውናል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 70 , ሐዲስ 74:
የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ ማንኛውም ሰው ጠዋት ጠዋት ሰባት የዘንባባ ተምር የሚበላ በበላበት ቀን በመርዝ እና በመተት አይጠቃም። حَدَّثَنَا جُمْعَةُ بْنُ عَبْدِ اللَّهِ، حَدَّثَنَا مَرْوَانُ، أَخْبَرَنَا هَاشِمُ بْنُ هَاشِمٍ، أَخْبَرَنَا عَامِرُ بْنُ سَعْدٍ، عَنْ أَبِيهِ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَنْ تَصَبَّحَ كُلَّ يَوْمٍ سَبْعَ تَمَرَاتٍ عَجْوَةً لَمْ يَضُرُّهُ فِي ذَلِكَ الْيَوْمِ سُمٌّ وَلاَ سِحْرٌ ‏”‌‏.‏

በኢስላም ወንጀለኛ ሲሕር የተደረገበት ሰው ሳይሆን ድግምተኛ ሰው ነው፤ በነብያችን”ﷺ” ወቅት የነበሩ በዳዮች ነብያችንን”ﷺ” የተደገመበትን ሰው ይሉ ነበር፤ ይህ የከንቱዎች መሳለቂያ ነበር፦
17፥47 እኛ ወደ አንተ በሚያዳምጡ ጊዜ እነርሱም በሚንሾካሾኩ ጊዜ በዳዮች እርስ በርሳቸው *”የተደገመበትን ሰው እንጂ አትከተሉም በሚሉ ጊዜ”* በእርሱ የሚያዳምጡበትን ምክንያት ዐዋቂ ነን፡፡ نَّحْنُ أَعْلَمُ بِمَا يَسْتَمِعُونَ بِهِۦٓ إِذْ يَسْتَمِعُونَ إِلَيْكَ وَإِذْ هُمْ نَجْوَىٰٓ إِذْ يَقُولُ ٱلظَّٰلِمُونَ إِن تَتَّبِعُونَ إِلَّا رَجُلًۭا مَّسْحُورًا
25፥8 «ወይም ወደ እርሱ ድልብ አይጣልለትምን ወይም ከእርሷ የሚበላላት አትክልት ለእርሱ አትኖረውምን» አሉ፡፡ *በዳዮቹም ለአመኑት «የተደገመበትን ሰው እንጂ ሌላ አትከተሉም» አሉ*፡፡ أَوْ يُلْقَىٰٓ إِلَيْهِ كَنزٌ أَوْ تَكُونُ لَهُۥ جَنَّةٌۭ يَأْكُلُ مِنْهَا ۚ وَقَالَ ٱلظَّٰلِمُونَ إِن تَتَّبِعُونَ إِلَّا رَجُلًۭا مَّسْحُورًا

ለተሳላቂዎች ደግሞ አላህ በቂ ምላሽ ሰጥቷል፦
25፥41 ባዩህም ጊዜ ያ አላህ መልእክተኛ አድርጎ የላከው ይህ ነውን እያሉ *” መሳለቂያ እንጂ ሌላ አያደርጉህም”*፡፡ وَإِذَا رَأَوْكَ إِن يَتَّخِذُونَكَ إِلَّا هُزُوًا أَهَٰذَا ٱلَّذِى بَعَثَ ٱللَّهُ رَسُولًا
15፥95 *”ተሳላቂዎችን ሁሉ እኛ በቅተንሃል”*፡፡ إِنَّا كَفَيْنَٰكَ ٱلْمُسْتَهْزِءِينَ

ኢንሻላህ ስለ መተት በባይብል በክፍል ሁለት ይቀጥላል….

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
መተት

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

ነጥብ ሁለት
“መተት በባይብል”
ስለ መተት በባይብል ያለው እሳቤ ደግሞ እስቲ በመጠኑን ቢሆን እንመልከት፤ “ፋርማሲይ”pharmacy” የሚለውም ቃል “ፋርማኮን” φάρμακον ከሚለው የግሪኩ ቃል የመጣ ሲሆን “ዕፅ”drug” ማለት ነው፤ ጥንት ግብፃውያን መተት፣ አስማት እና ድግምት የሚሰሩት በዕፅዋት ቅመማ ነው፤ በአገራችን “ዕፀ-መሰውር” ይሉታል፤ ይህ የዕፅ ሥራ በግሪክ ኮይኔ “ፋርማኮስ” φαρμάκων ሲባል ቃሉ አዲስ ኪዳን እንዲህ ሰፍሯል፦
ራእይ 18:23 የመብራትም ብርሃን ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስየምድር አይበራም፥ የሙሽራና የሙሽራይቱም ድምጽ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፤ ነጋዴዎችሽ የምድር መኳንንት ነበሩና፥ *በአስማትሽም* φαρμακείᾳ አሕዛብ ሁሉ ስተዋልና።”
ራእይ 9:21 ስለ መግደላቸውም ቢሆን ወይም ስለ *”አስማታቸው”* φαρμάκων ወይም ስለ ዝሙታቸው ወይም ስለ ስርቆታቸው ንስሐ አልገቡም።
ራእይ 21:8 ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም *”የአስማተኛዎችም”* φαρμακοῖς ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው።”
ራእይ 22:15 ውሻዎችና *”አስማተኞች”* φαρμακοὶ ሴሰኛዎችም ነፍሰ ገዳዮችም ጣዖትንም የሚያመልኩት ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ አሉ።”

“ምዋርት” ወይም “አስማት” ለሚለው ቃል የተጠቀመበት “ፋርማኮስ” φαρμάκων መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል፤ በብሉይ ኪዳን ግሪክ ሰፕቱጀንት”LXX” ላይም ይህ ቃል ነው የሰፈረው፤ በዕብራይስጡ ደግሞ “ከሻፍ” כָּשַׁף ሲሆን ግብጻውያን በሙሴ ዘመን የሰሩትት መተት ለማመልከት ተጠቅሞበታል፦
ዘጸአት 7:11 ፈርዖንም ጠቢባንን እና *”መተተኞችን” לָטִים ጠራ፤ የግብፅም ጠንቋዮች በአስማታቸው”* እንዲሁ ደግሞ አደረጉ።

ይህ ካየን ስለ በለዓም እንይ፤ በለዓም እግዚአብሔር የሚያናግረው የእግዚአብሔር ነብይ ነው፦
2ኛ የጴጥሮስ 2፥16 ነገር ግን ስለ መተላለፉ ተዘለፈ፤ ቃል የሌለው አህያ በሰው ቃል ተናግሮ *”የነቢዩን እብድነት”* አገደ።
ዘኍልቍ 23፥16 *እግዚአብሔርም በለዓምን ተገናኘ፥ ቃልንም በአፉ አድርጎ፦ ወደ ባላቅ ተመለስ፥ እንዲህም በል አለው*።

ይህ ነብይ አስማተኛ እና ምዋርተኛ ነበር፦
ዘኍልቍ 24፥1 በለዓምም እግዚአብሔር እስራኤልን ይባርክ ዘንድ እንዲወድድ ባየ ጊዜ፥ *”አስቀድሞ ያደርግ የነበረውን አስማት ይሻ ዘንድ አልሄደም”*፤ ነገር ግን ወደ ምድረ በዳ ፊቱን አቀና።
ኢያሱ 13፥22 ከገደሉአቸውም ሰዎች ጋር የእስራኤል ልጆች *”ምዋርተኛውን የቢዖርን ልጅ በለዓምን በሰይፍ ገደሉት”*።

የእስራኤል ልጆች ብዔልፌጎርን የተባለውን ጣዖት እንዲያመልኩ እና ከሞዓብ ልጆች ጋር ያመነዝሩ ያደረገው ይህ ነብይ ነው፦
ራእይ 2፥14 ዳሩ ግን *”ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉ እና እንዲሴስኑ በእስራኤል ልጆች ፊት ማሰናከያን ሊያኖርባቸው ባላቅን ያስተማረ የበልዓምን ትምህርት”* የሚጠብቁ በዚያ ከአንተ ጋር ስላሉ ፥ የምነቅፍህ ጥቂት ነገር አለኝ ።
ዘኍልቍ 31:16 እነሆ፥ እነዚህ በፌጎር ምክንያት *”በበለዓም ምክር”* እግዚአብሔርን *”ይበድሉ ዘንድ ለእስራኤል ልጆች ዕንቅፋት ሆኑ”*፤ ስለዚህም በእግዚአብሔር ማኅበር ላይ መቅሠፍት ሆነ።
ዘኍልቍ 25፥1-3 እስራኤልም በሰጢም ተቀመጡ፤ *ሕዝቡም ከሞዓብ ልጆች ጋር ያመነዝሩ ጀመር። ሕዝቡንም ወደ አምላኮቻቸው መሥዋዕት ጠሩ፤ ሕዝቡም በሉ፥ ወደ አምላኮቻቸውም ሰገዱ። እስራኤልም ብዔልፌጎርን ተከተለ*፤ የእግዚአብሔርም ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ።
ይሁዳ 1፥11 ወዮላቸው፥ በቃየል መንገድ ሄደዋልና ስለ ደመወዝም *”ለበለዓም ስሕተት”* ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል በቆሬም መቃወም ጠፍተዋል።

ምዋርተኛውና አስማተኛው የአምላክ ነብይ በለዓም “በያዕቆብ ላይ አስማት የለም፥ በእስራኤልም ላይ ምዋርት የለም” ይበል እንጂ ድብን አድርጎ በእስራኤል ላይ “አስማት” ነበረ፦
ዘኍልቍ 23፥23 በያዕቆብ ላይ “አስማት” כְּשָׁפַ֔יִךְ የለም፥ በእስራኤልም ላይ “ምዋርት” የለም፤
2ኛ ነገሥት 21፥6 ልጁንም በእሳት አሳለፈ፥ ሞራ ገላጭም ሆነ፥ *”አስማትም” כְּשָׁפַ֔יִךְ አደረገ”*፥ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችንም ሰበሰበ፤ ያስቈጣውም ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ክፉ ነገር አደረገ።
ኢሳይያስ 47፥9 አሁን ግን በአንድ ቀን እነዚህ ሁለት ነገሮች፥ የወላድ መካንነትና መበለትነት፥ በድንገት ይመጡብሻል፤ *ስለ “መተቶችሽ” כְּשָׁפַ֔יִךְ ብዛትና ስለ “አስማቶችሽ” ጽናት ፈጽመው ይመጡብሻል*።
ኢሳይያስ 47:12 ምናልባትም መጠቀም ትችዪ ወይም ታስደነግጪ እንደ ሆነ፥ *”ከአስማቶችሽ” כְּשָׁפַ֔יִךְ እና ከሕፃንነትሽ ጀምረሽ ከደከምሽበት ከመተቶችሽ ብዛት ጋር ቁሚ*።

ታዲያ የቱ ይከብዳል መተት የተደረገበት ነብይ ወይስ መተት አድራጊ ነብይ? ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉና እንዲሴስኑ በእስራኤል ልጆች ፊት ማሰናከያን ያደረገ ነብይ ወይስ ተውሒድን ያስተማሪ ነብይ? ሰው ላይ አስማት ማድረግስ ወንጀል አይደለምን?፦
ዘዳግም 18፥11 *”አስማተኛም፥ መተተኛም”፥ በድግምት የሚጠነቍልም፥ መናፍስትንም የሚጠራ፥ ጠንቋይም፥ ሙታን ሳቢም በአንተ ዘንድ አይገኝ*።
ዘሌዋውያን 19፥26 ከደሙ ጋር ምንም አትብሉ፤ *”አስማትም አታድርጉ”*፥ ሞራ ገላጭም አትሁኑ።
መደምደሚያ
ሲጀመር ሲሕር በነብያችን”ﷺ” ላይ ተፅዕኖ ያሳደረባቸው በድርጊታቸው ላይ እንጂ በወሕይ ላይ አይደለም፤ ሲቀጥል ሲሕሩ በቅጠላ-ቅጠል ብጠሳ የሚደረግ በሽታ ነው፤ ሲሰልስ አላህ ነብያችን”ﷺ” ላይ ሲሕር ተፅዕኖ ሲያሳድር ዝም ያለበት ጥበብ ሰዎች ሲሕር ሲደርግባቸው እንዴት ማክሸፍ እንዳለባቸው ለማስተማር ነው እንጂ የተሳሳተ ሰው የተመራን ሰው አይጎዳም፦
5፥105 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እራሳችሁን ከእሳት ጠብቁ፤ *”በተመራችሁ ጊዜ የተሳሳተ ሰው አይጎዳችሁም”*፡፡ የሁላችሁም መመለሻ ወደ አላህ ብቻ ነው፡፡ ትሠሩትም የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ عَلَيْكُمْ أَنفُسَكُمْ ۖ لَا يَضُرُّكُم مَّن ضَلَّ إِذَا ٱهْتَدَيْتُمْ ۚ إِلَى ٱللَّهِ مَرْجِعُكُمْ جَمِيعًۭا فَيُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ

ሲያረብብ ከምንም በላይ ሰይጣን ሙኽሊሲን በሚባሉት የአላህ ባሮች ላይ ስልጣን የለውም፤ “ሙኽሊስ” مُخْلِص ማለት “አጥሪ” ማለት ሲሆን አምልኮቱ “ኢኽላስ” ያለው ማለት ነው፤ “ኢኽላስ” إخلاص ማለት እዩልኝና ስሙልኝ ያልታከለበት፣ ከሙገሳና ከወቀሳ ነጻ የሆነ፣ ለአላህ ውዴታ ተብሎ የሚደረግ ማጥራት፣ ፍጽምና፣ መተናነስ፣ መጎባደድ ማለት ነው፤ ሰይጣን ቃል የገባው ሙኽሊስ የተባሉትን የአላህ ባሮች እንደማይነካ ነው፦
38፥83 «ከእነርሱ *”ምርጥ የኾኑት ባሮችህ”* ብቻ ሲቀሩ፡፡» إِلَّا عِبَادَكَ مِنْهُمُ ٱلْمُخْلَصِينَ
15:40 «ከእነርሱ *”ፍጹሞቹ ባሮችህ”* ብቻ ሲቀሩ፡፡» إِلَّا عِبَادَكَ مِنْهُمُ ٱلْمُخْلَصِينَ
15፥42 «እነሆ *ባሮቼ በእነርሱ ላይ ለአንተ ስልጣን የለህም*፡፡ ከጠማሞቹ የተከተለህ ሰው ብቻ ሲቀር፡፡» إِنَّ عِبَادِى لَيْسَ لَكَ عَلَيْهِمْ سُلْطَٰنٌ إِلَّا مَنِ ٱتَّبَعَكَ مِنَ ٱلْغَاوِينَ
16፥109 እርሱ በእነዚያ ባመኑት እና በጌታቸው ላይ *”በሚጠጉት ላይ ለእርሱ ስልጣን የለውምና”*፡፡ إِنَّهُۥ لَيْسَ لَهُۥ سُلْطَٰنٌ عَلَى ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَلَىٰ رَبِّهِمْ يَتَوَكَّلُونَ
16፥100 *”ስልጣኑ በእነዚያ በሚታዘዙት ላይ እና በእነዚያም እነርሱ በእርሱ ምክንያት አጋሪዎች በኾኑት ላይ ብቻ ነው”*፡፡ إِنَّمَا سُلْطَٰنُهُۥ عَلَى ٱلَّذِينَ يَتَوَلَّوْنَهُۥ وَٱلَّذِينَ هُم بِهِۦ مُشْرِكُونَ

አላህ ሙኽሊሲን ከሚላቸው ባሮቹ ያርገን አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ሸኸ ዑመር ሙኽታር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

61፥4 *አላህ እነዚያን እነርሱ ልክ እንደ ተናሰ ግንብ የተሰለፉ ኾነው በመንገዱ የሚጋደሉትን ይወዳል"*፡፡ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الَّذِينَ يُقَاتِلُونَ فِي سَبِيلِهِ صَفًّا كَأَنَّهُم بُنْيَانٌ مَّرْصُوصٌ

የበረሃው አንበሳ የሆኑትን ሸኸ ዑመር ሙኽታርን የኢጣሊያው መሪ ለማነጋጋርና እንዲድ ሲል ጠየቃቸው፦
ከኢጣሊያኖች ጋር ተዋግተሃልን?
ዑመር፦ አዎ
መሪው፦ ሰዎች እንዲዋጉን ቅስቀሳ አድርግርሃልን?
ዑመር ፦ አዎ
መሪው፦ የሰራሃው ስራ ቅጣቱ ምን እንደሆነ ታውቃለህን?
ዑመር ፦ አዎ
መሪው፦ በምትናገረውን ንግግር ለማረጋጋጥ ዝግጁ ነህን ?
ዑመር ፦ አዎ
መሪው፦ ለስንት አመታት ከኢጣልያ ጋር ተዋጋህ?
ዑመር ፦ ለ20 አመታት ያክል
መሪው፦ በሠራኸው ሥራ ተፀፅተሃልን ?
ዑመር ፦ አልተፀፀትኩም ?
መሪው፦ በግድያ እንደምትቀጣ አውቀሃልን ?
ዑመር ፦ አዎ

ዳኛውም፦ አክሎ እንዲህ አለው፦ "መጨረሻህ ይህ በመሆኑም አዝናለው!
ዑመርም፦ ይልቁንስ የዚች ዓለም ሕይወቴ በዚህ መልኩ መጠናቀቁ በጣም የተመረጠ ነው"።
በዚህ ጊዜ ዳኛው በጥቅም ሊሽነግላቸው ሞከረ፥ እኛን እየተዋጉን ያሉትን ታጋዩች መዋጋታቸውን እንዲያቆሙ ትእዛዝ ጽፈህ አስተላልፍላቸው አንተን ይቅር እንልሃለን! አላቸው።
የዑመር ምላሽም እንዲህ የሚል ነበር፦ "ሁሌም ላ ኢላሃ ኢለሏህ ሙሐመድ ረሱሉሏህ" በማለት የምትጠቁመው አመልካች ጣቴ 'በባጢል' ነገር ላይ መጻፍ አትችልም"

እነርሱም በስቅላት እንዲቀጣ ወሰኑበት ተስቀለም። አላህ ይዘንለት ሸይኽ ዑመር ሙኽታር።
ሸሂድ ዑመር ሙኽታር የኖረው ከ1858 -1931 ድህረ-ልደት ሲሆን የሙጃሂዲን ሸኽና የበረሃው አንበሳ የሚል ቅጥያ የተሰጣቸው ጀግና ነበሩ። እውነተኛዎቹ ምእምናን እነዚያ በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸውም በአላህ መንገድ የታገሉት ብቻ ናቸው፡፡ እነዚያ እነርሱ እውነተኞቹ ናቸው፦
49፥15 *"እውነተኛዎቹ ምእምናን"* እነዚያ በአላህና በመልእከተኛው ያመኑት ከዚያም ያልተጠራጠሩት *በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸውም በአላህ መንገድ የታገሉት ብቻ ናቸው፡፡ እነዚያ እነርሱ እውነተኞቹ ናቸው"*፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ الَّذِينَ آمَنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ ثُمَّ لَمْ يَرْتَابُوا وَجَاهَدُوا بِأَمْوَالِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ ۚ أُولَـٰئِكَ هُمُ الصَّادِقُونَ
61፥4 *አላህ እነዚያን እነርሱ ልክ እንደ ተናሰ ግንብ የተሰለፉ ኾነው በመንገዱ የሚጋደሉትን ይወዳል"*፡፡ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الَّذِينَ يُقَاتِلُونَ فِي سَبِيلِهِ صَفًّا كَأَنَّهُم بُنْيَانٌ مَّرْصُوصٌ
3፥195 ጌታቸውም «እኔ ከእናንተ ከወንድ ወይም ከሴት የሠሪን ሥራ አላጠፋም፡፡ ከፊላችሁ ከከፊሉ ነው፤ በማለት ለነርሱ ልመናቸውን ተቀበለ፡፡ እነዚያም የተሰደዱ ከአገሮቻቸውም የተባረሩ በመንገዴም የተጠቁ የተጋደሉም የተገደሉም ክፉ ሥራዎቻቸውን ከእነርሱ በእርግጥ አብሳለሁ፡፡ በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በእርግጥ አገባቸዋለሁ፡፡ ከአላህ ዘንድ የኾነን ምንዳ ይመነዳሉ፡፡ አላህም እርሱ ዘንድ መልካም ምንዳ አልለ፡፡ » فَاسْتَجَابَ لَهُمْ رَبُّهُمْ أَنِّي لَا أُضِيعُ عَمَلَ عَامِلٍ مِّنكُم مِّن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ ۖ بَعْضُكُم مِّن بَعْضٍ ۖ فَالَّذِينَ هَاجَرُوا وَأُخْرِجُوا مِن دِيَارِهِمْ وَأُوذُوا فِي سَبِيلِي وَقَاتَلُوا وَقُتِلُوا لَأُكَفِّرَنَّ عَنْهُمْ سَيِّئَاتِهِمْ وَلَأُدْخِلَنَّهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ ثَوَابًا مِّنْ عِندِ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ عِندَهُ حُسْنُ الثَّوَابِ

"እነዚያም የተሰደዱ ከአገሮቻቸውም የተባረሩ በመንገዴም የተጠቁ የተጋደሉም የተገደሉም ክፉ ሥራዎቻቸውን ከእነርሱ በእርግጥ አብሳለሁ" የሚለው ይሰመርበት። አላህ የሙጅሂዲንን ጅሃድ እና የሹሃዳን ሸሂድ በኢኽላስ ይቀበላቸው! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ሥነ-ምግባር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

57፥25 *"መልክተኞቻችንን በግልጽ ማስረጃዎች በእርግጥ ላክን"*፡፡ ሰዎችም በትክክል ቀጥ እንዲሉ *"መጽሐፎችንና ሚዛንን ወደ እነርሱ አወረድን"*፤ لَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلَنَا بِٱلْبَيِّنَٰتِ وَأَنزَلْنَا مَعَهُمُ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْمِيزَانَ لِيَقُومَ ٱلنَّاسُ بِٱلْقِسْطِ

“አኽላቅ” أخلاق ማለት ሥነ-ምግባር”ethics” ማለት ሲሆን “አደብ” أدب ማለት ደግሞ ግብረ-ገብ”manners” ማለት ነው፤ አንድ ነገር ትክክል ነው ወይም ስህተት ነው፣ እውነት ነው ወይም ሐሰት ነው፣ አሊያም ክፉ ነው ወይም ጥሩ ነው የምንልበት ተስተምህሮት ሥነ-ምግባር ይሰኛል። ነገር ግን ይህ ግብረ-ገብ ከባህል ወደ ባህል፣ ከልማድ ወደ ልማድ፣ ከእምነት ወደ እምነት ይለያያል፤ አንድ ነገር ትክክል ነው ወይም ስህተት ነው፣ አሊያም እውነት ነው ወይም ሐሰት ነው የምንልበት ለሰው ልጆች የሚሆን መመዘኛ አላህ ወደ ነብያት አውርዷል፦
57፥25 *"መልክተኞቻችንን በግልጽ ማስረጃዎች በእርግጥ ላክን"*፡፡ ሰዎችም በትክክል ቀጥ እንዲሉ *"መጽሐፎችንና ሚዛንን ወደ እነርሱ አወረድን"*፤ لَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلَنَا بِٱلْبَيِّنَٰتِ وَأَنزَلْنَا مَعَهُمُ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْمِيزَانَ لِيَقُومَ ٱلنَّاسُ بِٱلْقِسْطِ
42፥17 አላህ ያ *"መጽሐፉን በእውነት ያወረደ ነው፡፡ ሚዛንንም እንደዚሁ*"፡፡ ሰዓቲቱ ምንአልባት ቅርብ መኾንዋን ምን ያሳውቅሃል? ٱللَّهُ ٱلَّذِىٓ أَنزَلَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ وَٱلْمِيزَانَ ۗ وَمَا يُدْرِيكَ لَعَلَّ ٱلسَّاعَةَ قَرِيبٌۭ

"ሚዛን" مِيزَان እውነትን ከሐሰት፣ ትክክለኛውን ከስህተት፣ ሰናዩን ከእኩይ የምንለይበት መመዘኛ ነው፤ ይህ ሚዛን "ፉርቃን" فُرْقَان ይባላል፤ ቁርኣን እውነትን ከሐሰት፣ ትክክለኛውን ከስህተት፣ ሰናዩን ከእኩይ የምንለይበት ፉርቃን ነው፦
25፥1 ያ *"ፉርቃንን"* በባሪያው ላይ ለዓለማት አስጠንቃቂ ይኾን ዘንድ ያወረደው አምላክ ክብርና ጥራት ተገባው፡፡ تَبَارَكَ ٱلَّذِى نَزَّلَ ٱلْفُرْقَانَ عَلَىٰ عَبْدِهِۦ لِيَكُونَ لِلْعَٰلَمِينَ نَذِيرًا
3፥4 ከእርሱ በፊት ለሰዎች መሪ አድርጎ አወረዳቸው፡፡ *"ፉርቃንንም አወረደ"*፡፡ مِن قَبْلُ هُدًۭى لِّلنَّاسِ وَأَنزَلَ ٱلْفُرْقَانَ

ለሙሳ የወረደለት ተውራትም ፉርቃን ተብሏል፦
2፥53 ሙሳንም *"መጽሐፍንና ፉርቃንንም"* ትመሩ ዘንድ በሰጠነው ጊዜ አስታውሱ፡፡ وَإِذْ ءَاتَيْنَا مُوسَى ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْفُرْقَانَ لَعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ
21፥48 ለሙሳና ለሃሩንም *"ፉርቃንን ለጥንቁቆችም መገሰጫን በእርግጥ ሰጠናቸው"*፡፡ وَلَقَدْ ءَاتَيْنَا مُوسَىٰ وَهَٰرُونَ ٱلْفُرْقَانَ وَضِيَآءًۭ وَذِكْرًۭا لِّلْمُتَّقِينَ

አላህ ለሁሉም መልእክተኞች ሕግን እና መንገድን አድርጓል፦
5፥48 ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭና በእርሱ ላይ ተጠባባቂ ሲኾን በእውነት አወረድን፡፡ በመካከላቸውም *"አላህ ባወረደው ሕግ ፍረድ"*፡፡ እውነቱም ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌዎቻቸውን አትከተል፡፡ *"ከእናንተ ለሁሉም ሕግን እና መንገድን አደረግን"*፡፡ وَأَنزَلْنَآ إِلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ مُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَمُهَيْمِنًا عَلَيْهِ ۖ فَٱحْكُم بَيْنَهُم بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَآءَهُمْ عَمَّا جَآءَكَ مِنَ ٱلْحَقِّ ۚ لِكُلٍّۢ جَعَلْنَا مِنكُمْ شِرْعَةًۭ وَمِنْهَاجًۭا

እዚህ አንቀጽ ላይ ስናስተውለው “ሕግ” የሚለው ቃል “ሺርዓ” شِرْعَة ሲሆን “ሸሪዓ” شَرِيعَة ደግሞ “ትክክለኛ ሕግ” ማለት ነው።
ቀጥሎ “መንገድ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሚንሃጅ” مِنْهَاج ሲሆን “መንሃጅ” منہاج ማለት ነው፤ "አላህ ባወረደው ሕግ ፍረድ" ስለሚል፥ አንድ ነገር ትክክል ነው ወይም ስህተት ነው፣ እውነት ነው ወይም ሐሰት ነው፣ አሊያም እኩይ ነው ወይም ሰናይ ነው የምንለው አላህ ባወረደው ሕግ ስንመዝን ብቻ ነው።
በዓለማችን ላይ ባሉት አበይት የሃይማኖት መጽሐፍት ላይ የመለኮት ቃል ቅሪት ስላለ የሥነ-ምግባር ጤናማ ማህበረሰብ በመጠኑም ቢሆን ገንብቷል፤ ነገር ግን ስለ ሥነ-ምግባር ያለው የምዕራባውያን እሳቦት እና እርዮት ከሰው ዝንባሌ እና ፍልስፍና የበቀሉ ሲሆኑ፣ ከበስተኃላ የካባላ፣ የፍሪ ሜሶን እና የኢሉሚኔቲቭ ንድፈ ሃሳብ ይዟል። ዋናው አጀንዳው የመለኮት ሥነ-ምግባርን እሳቤ አጥፍቶ ለዘብተኛ ፍልስፍናን ማከናነብ ነው። አላህ ከእነርሱ ሴራና ደባ ይጠብቀን፤ በፉርቃን ያጽናን አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

አንድን ሰው፦ "ያምሃልን? ስትሉት እርሱም፦ "አንተም ያምሃል" ካለ መታመሙን አረጋግጧል ማለት ነው። አንድን ሚሽነሪይ፦ "ባይብል ይጋጫል" ስትሉት እርሱም፦ "ቁርኣንም ይጋጫል" ካለ ባይብል መጋጨቱን አረጋግጧል ማለት ነው። ይህ እከክልኝ ልከክልህ ነገር ነው። አንድ ሚሽነሪይ፦ "ቁርኣን ይጋጫል" ቢለን እኛ፦ "እረ በፍጹም" እስቲ ጥቀሰው እንጂ ባይብልም ይጋጫል አንለውም። ምክንያቱም ባይብል የሰው ንግግር ስለገባበት እና ሥረ-መሠረቱ ሳይኖር ቀርቶ ቅጂ ስለሆነ፥ ገልባጮቹ ስህተት እንደሰሩ የባይብል ለዘብተኛም ጽንፈኛም ምሁራን ይስማማሉ። የቁርኣን ግጭት ተብሎ የቀረበው የዛሬ ስድስት ዓመት አንሰሪንግ ኢሥላም ላይ የቀረቡ እንጂ አዲስ ነገር የለውም። መልሱን በተከታታይ ኢንሻላህ በጽሑፍ እና በድምጽ እንሰጣለን፦

ጥያቄ 1
አጋሪ ሴቶችን ማግባት ተፈቅዷል ወይስ አልተፈቀደም?

አልተፈቀደም:-
ሱራ 2፡221 “በአላህ አጋሪ የሆኑ ሴቶችን እስኪያምኑ ድረስ አታግቧቸው፡፡

ተፈቅዷል:-
ሱራ 5፡5 “ከነዚያ ከናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡት ሴቶች ጥብቆቹም ዘማዊዎችና የሚስጢር ወዳጅ ያዢዎች ሳትሆኑ ጥብቆች ሆናችሁ መህሮቻቸውን በሰጣችኋቸው ጊዜ ልታገቧቸው የተፈቀዱ ናቸው።
መልስ
5፥5 ዛሬ መልካሞች ሁሉ ለእናንተ ተፈቀዱ፡፡ *የእነዚያም መጽሐፍን የተሰጡት ሰዎች ምግብ ያረዱት ለእናንተ የተፈቀደ ነው፡፡ ምግባችሁም ለእነሱ የተፈቀደ ነው*፡፡ ከምእመናት ጥብቆቹም *ከእነዚያ ከእናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡት ሴቶች ጥብቆቹም፤ ዘማዊዎችና የምስጢር ወዳጅ ያዢዎች ሳትኾኑ ጥብቆች ኾናችሁ መህሮቻቸውን በሰጣችኋቸው ጊዜ ልታገቡዋቸው የተፈቀዱ ናቸው*፡፡ ከእምነትም የሚመለስ ሰው በእርግጥ ሥራው ተበላሸ፡፡ በመጨረሻም ቀን እርሱ ከከሳሪዎቹ ነው፡፡ ٱلْيَوْمَ أُحِلَّ لَكُمُ ٱلطَّيِّبَٰتُ ۖ وَطَعَامُ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ حِلٌّۭ لَّكُمْ وَطَعَامُكُمْ حِلٌّۭ لَّهُمْ ۖ وَٱلْمُحْصَنَٰتُ مِنَ ٱلْمُؤْمِنَٰتِ وَٱلْمُحْصَنَٰتُ مِنَ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ مِن قَبْلِكُمْ إِذَآ ءَاتَيْتُمُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ مُحْصِنِينَ غَيْرَ مُسَٰفِحِينَ وَلَا مُتَّخِذِىٓ أَخْدَانٍۢ ۗ وَمَن يَكْفُرْ بِٱلْإِيمَٰنِ فَقَدْ حَبِطَ عَمَلُهُۥ وَهُوَ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ مِنَ ٱلْخَٰسِرِينَ

አምላካችን አላህ በእርሱ ላይ ሌሎች ማንነትንና ምንነትን የሚያጋሩ ሙሽሪኮችን እንዳናገባ እና ከእርሱ ስም ውጪ በሌላ ፍጡር ስም ተባርኮ የታረደን እርድ እንዳንበላ ከልክሏል፦
2፥221 *አጋሪ የሆኑ ሴቶች እስከሚያምኑ ድረስ አታግቡዋቸው*፡፡ ከአጋሪይቱ ምንም ብትደንቃችሁም እንኳ ያመነችው ባሪያ በእርግጥ በላጭ ናት፡፡ *ለአጋሪዎቹም እስከሚያምኑ ድረስ አትዳሩላቸው*፡፡ ከአጋሪው ጌታ ምንም ቢደንቃችሁ ምእምኑ ባሪያ በላጭ ነው፡፡ *እነዚያ አጋሪዎች ወደ እሳት ይጣራሉ፡፡ አላህም በፈቃዱ ወደ ገነትና ወደ ምሕረት ይጠራል*፡፡ ሕግጋቱንም ለሰዎች ይገልጻል እነርሱ ሊገሰጹ ይከጀላልና፡፡ وَلَا تَنكِحُوا الْمُشْرِكَاتِ حَتَّىٰ يُؤْمِنَّ ۚ وَلَأَمَةٌ مُّؤْمِنَةٌ خَيْرٌ مِّن مُّشْرِكَةٍ وَلَوْ أَعْجَبَتْكُمْ ۗ وَلَا تُنكِحُوا الْمُشْرِكِينَ حَتَّىٰ يُؤْمِنُوا ۚ وَلَعَبْدٌ مُّؤْمِنٌ خَيْرٌ مِّن مُّشْرِكٍ وَلَوْ أَعْجَبَكُمْ ۗ أُولَـٰئِكَ يَدْعُونَ إِلَى النَّارِ ۖ وَاللَّهُ يَدْعُو إِلَى الْجَنَّةِ وَالْمَغْفِرَةِ بِإِذْنِهِ ۖ وَيُبَيِّنُ آيَاتِهِ لِلنَّاسِ لَعَلَّهُمْ يَتَذَكَّرُونَ
6፥121 *በእርሱም ላይ የአላህ ስም ካልተጠራበት ነገር አትብሉ*፡፡ እርሱም በእርግጥ አመጽ ነው፡፡ ሰይጣናትም ወደ ወዳጆቻቸው በክትን በመብላት ይከራከሯችሁ ዘንድ ያሾከሹካሉ፡፡ *ብትታዘዙዋቸውም እናንተ በእርግጥ አጋሪዎች ናችሁ*፡፡ وَلَا تَأْكُلُوا مِمَّا لَمْ يُذْكَرِ اسْمُ اللَّهِ عَلَيْهِ وَإِنَّهُ لَفِسْقٌ ۗ وَإِنَّ الشَّيَاطِينَ لَيُوحُونَ إِلَىٰ أَوْلِيَائِهِمْ لِيُجَادِلُوكُمْ ۖ وَإِنْ أَطَعْتُمُوهُمْ إِنَّكُمْ لَمُشْرِكُونَ

“ሺርክ” شِرْك የሚለው ቃል “አሽረከ” أَشْرَكَ ማለትም “አጋራ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “ማጋራት” ማለት ነው፤ የሚያጋራው ሰው ደግሞ “ሙሽሪክ” مُشْرِك ማለትም “አጋሪ” ይባላል፤ እንዲሁ በአላህ ላይ የሚያጋሩት ማንነትና ምንነት “ሸሪክ” شَرِيك ማለትም “ተጋሪ” ይባላሉ፤ ከአህለል ኪታብ ሙሉ ለሙሉ ባይሆንም ከነሳራዎች አበይት የሚባሉት ሙሽሪኪን ናቸው፦
5፤72 *እነዚያ «አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ*፡፡ አልመሲህም አለ፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን ተገዙ፡፡» *እነሆ! በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በእርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ*፡፡ መኖሪያውም እሳት ናት፡፡ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም፡፡ لَقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ ۖ وَقَالَ الْمَسِيحُ يَا بَنِي إِسْرَائِيلَ اعْبُدُوا اللَّهَ رَبِّي وَرَبَّكُمْ ۖ إِنَّهُ مَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدْ حَرَّمَ اللَّهُ عَلَيْهِ الْجَنَّةَ وَمَأْوَاهُ النَّارُ ۖ وَمَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ أَنصَارٍ

እነዚያ «አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ፤ እነሆ ይህ ንግግራቸው ማጋራት ነውና አላህ በእርሱ ላይ የሚያጋራ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፤ መኖሪያውም እሳት ናት፡፡ ይህ ጥቅላዊ መልእክት “ሙጅመል” مجمل ወይም “ዓም” عام ይባላል፤ ነገር ግን አላህ ከሙሽሪኪን አህለል ኪታቦችን በተናጥል “ሙፈሰል” مُفَصَّل ወይም “ኻስ” خاص በማድረግ ለያቸው፤ ይህም ሙሽሪኪን እና አህለል ኪታብ በሚሉ ቃላት መካከል “ወ” وَ ማለትም “እና” የሚል መስተጻምር አስቀምጧል፦
98፥1 *እነዚያ ከመጽሐፉ ባለቤቶች እና ከአጋሪዎቹም የካዱት ግልጹ አስረጅ እስከ መጣላቸው ድረስ ተወጋጆች አልነበሩም፡፡ لَمْ يَكُنِ الَّذِينَ كَفَرُوا مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ وَالْمُشْرِكِينَ مُنفَكِّينَ حَتَّىٰ تَأْتِيَهُمُ الْبَيِّنَةُ
“በእርሱም ላይ የአላህ ስም ካልተጠራበት ነገር አትብሉ” የሚለው “ዓም” عام ሆኖ ከመጣ በኃላ “የእነዚያም መጽሐፍን የተሰጡት ሰዎች ምግብ ያረዱት ለእናንተ የተፈቀደ ነው” “ኻስ” خاص ሆኖ እንደመጣ ኢብኑ ዐባሥ”ረ.ዐ” ተናግሯል፦
ሱነን አቢ ዳውድ :መጽሐፍ 16, ሐዲስ 30
ኢብኑ ዐባሥ”ረ.ዐ” እንደተናገረው፦ 6፥118 “የአላህ ስም በእርሱ ላይ ከተወሳበት እንስሳ ብሉ” የሚለው አንቀጽ እና 6፥116 “በእርሱም ላይ የአላህ ስም ካልተጠራበት ነገር አትብሉ” የሚለው አንቀጽ ኢስቲስናዕ በመሆን “የእነዚያም መጽሐፍን የተሰጡት ሰዎች ምግብ ያረዱት ለእናንተ የተፈቀደ ነው” በሚለው ተነሥኻል” عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ ‏{‏ فَكُلُوا مِمَّا ذُكِرَ اسْمُ اللَّهِ عَلَيْهِ ‏}‏ ‏{‏ وَلاَ تَأْكُلُوا مِمَّا لَمْ يُذْكَرِ اسْمُ اللَّهِ عَلَيْهِ ‏}‏ فَنُسِخَ وَاسْتَثْنَى مِنْ ذَلِكَ فَقَالَ ‏{‏ وَطَعَامُ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ حِلٌّ لَكُمْ وَطَعَامُكُمْ حِلٌّ لَهُمْ ‏}‏ ‏.‏

ይህንን ሪዋያህ ሼኹል አልባኒ ሐሠን ነው ብለውቷል፤ “ወኢሥተስና” وَاسْتَثْنَى የሚለው ይሰመርበት፤ “ኢሥቲስናዕ” اِسْتِثْنَاء‏ ማለት “ግድባዊ ቃል”Exceptional word” ነው፤ ከዚህ ሐዲስ የምረዳው አምላካችን አላህ ከጥቅላዊ መልእክት ተናጥሏዊ መልእክት ይህንን አንቀጽ ማውረዱ ነው፦
5፥5 ዛሬ መልካሞች ሁሉ ለእናንተ ተፈቀዱ፡፡ *የእነዚያም መጽሐፍን የተሰጡት ሰዎች ምግብ ያረዱት ለእናንተ የተፈቀደ ነው፡፡ ምግባችሁም ለእነሱ የተፈቀደ ነው*፡፡ ከምእመናት ጥብቆቹም *ከእነዚያ ከእናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡት ሴቶች ጥብቆቹም፤ ዘማዊዎችና የምስጢር ወዳጅ ያዢዎች ሳትኾኑ ጥብቆች ኾናችሁ መህሮቻቸውን በሰጣችኋቸው ጊዜ ልታገቡዋቸው የተፈቀዱ ናቸው*፡፡ ከእምነትም የሚመለስ ሰው በእርግጥ ሥራው ተበላሸ፡፡ በመጨረሻም ቀን እርሱ ከከሳሪዎቹ ነው፡፡ ٱلْيَوْمَ أُحِلَّ لَكُمُ ٱلطَّيِّبَٰتُ ۖ وَطَعَامُ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ حِلٌّۭ لَّكُمْ وَطَعَامُكُمْ حِلٌّۭ لَّهُمْ ۖ وَٱلْمُحْصَنَٰتُ مِنَ ٱلْمُؤْمِنَٰتِ وَٱلْمُحْصَنَٰتُ مِنَ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ مِن قَبْلِكُمْ إِذَآ ءَاتَيْتُمُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ مُحْصِنِينَ غَيْرَ مُسَٰفِحِينَ وَلَا مُتَّخِذِىٓ أَخْدَانٍۢ ۗ وَمَن يَكْفُرْ بِٱلْإِيمَٰنِ فَقَدْ حَبِطَ عَمَلُهُۥ وَهُوَ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ مِنَ ٱلْخَٰسِرِينَ

አላህ ለሙስሊም ወንድ ከአህለል ኪታብ ሴትን የፈቀደበት ሂክማ ሴት በቀጥታ ሙስሊም ቤት ስለምትገባ ነው፤ በተቃራኒው ሴት ሙስሊም ወንድ ካፊርን ማግባት ያልፈቀደበት ሴቷ ሙስሊም ሙሽሪክ ቤት ስለምትገባ ነው። በማን ስም እንደታረደ ካልታወቀ ደግሞ ቢሥሚላህ ተብሎ መብላት እንደሚቻይ ይህ ሐዲስ ያሳያል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 34, ሐዲስ 11
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ *”ሕዝቦች፦ “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ስጋ በሕዝቦች ለእኛ ቀርቦልናል፤ የአላህ ስም ይወሳበት አይወሳበት እርግጠኛ አይደለንም” አሉ፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ “የአላህን ስም አውሱበት ከዚያ ብሉት”*። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ أَنَّ قَوْمًا، قَالُوا يَا رَسُولَ اللَّهِ، إِنَّ قَوْمًا يَأْتُونَنَا بِاللَّحْمِ لاَ نَدْرِي أَذَكَرُوا اسْمَ اللَّهِ عَلَيْهِ أَمْ لاَ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ سَمُّوا اللَّهَ عَلَيْهِ وَكُلُوهُ

የሙሥሊም ስጋ ቤት ካለ አንድ ሙሥሊም ምርጫው መሆን ያለበት የሙሥሊም ስጋ ቤት ነው፤ የሙሥሊም ስጋ ቤት ከሌለ ግን የእነርሱን ስጋ ቤት መጠቀም ሙባህ ነው፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 21, ሐዲስ 17
አቡ ሰለባህ ሲናገር እንደሰማሁት፦ “ወደ አላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሄጄ፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሆይ! በአህለል ኪታብ አገር ውስጥ ነው የምንኖረው፤ የእነርሱን ምግብ እንበላለን” አልኩኝ፤ እርሳቸውም፦ “ከእነርሱ ሌላ(የሙሥሊም) ካገኘህ ከእነርሱ አትብላ፤ ከእነርሱ ሌላ ካላገኘህ አጥበህ ከእነርሱ ብላ”*። አቡ ዒሣ እንዳለው ይህ ሐዲስ ሐሠን ሰሒሕም ነው። يَقُولُ أَخْبَرَنِي أَبُو إِدْرِيسَ الْخَوْلاَنِيُّ، عَائِذُ اللَّهِ بْنُ عُبَيْدِ اللَّهِ قَالَ سَمِعْتُ أَبَا ثَعْلَبَةَ الْخُشَنِيَّ، يَقُولُ أَتَيْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَقُلْتُ يَا رَسُولَ اللَّهِ إِنَّا بِأَرْضِ قَوْمٍ أَهْلِ كِتَابٍ نَأْكُلُ فِي آنِيَتِهِمْ قَالَ ‏ “‏ إِنْ وَجَدْتُمْ غَيْرَ آنِيَتِهِمْ فَلاَ تَأْكُلُوا فِيهَا فَإِنْ لَمْ تَجِدُوا فَاغْسِلُوهَا وَكُلُوا فِيهَا ‏”‏ ‏.‏ قَالَ أَبُو عِيسَى هَذَا حَدِيثٌ حَسَنٌ صَحِيحٌ
ከላይ የተዘረዘረው ግንዛቤ የዐሊሞቻችን አንዱ ረእይ ማለትም እይታ”dimension” ነው።  በሙሽሪክ እና በአህለል ኪታብ “ኢሥቲስናዕ” اِسْتِثْنَاء‏ ማለት “ግድባዊ ቃል”Exceptional word” በመሆን ስለ “ዓም” عام ማለትም “ጥቅላዊ መልእክት” እና ስለ “ኻስ” خاص ማለትም “ተናጥሏዊ መልእክት” አይተን ነበር፤ ይህ አንደኛው የዐሊሞቻችን እይታ”dimension” ነው፤ ስለ አህለል ኪታብ ሁለተኛው የዐሊሞቻችን እይታ” ደግሞ “ሢያቅ” سیاق ማለትም “አውዳዊ መልእክት”context” ነው። ይህም ከሙሳ እና ዒሳ ተከታዮች ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው፤ ነገር ግን አላህ ከእነርሱም ለእነዚያ ላመኑት ምንዳቸውን ሰጣቸው፤ በእነርሱ ላይ ቁርአን በሚነበብላቸውም ጊዜ «በእርሱ አምነናል፡፡ እርሱ ከጌታችን የኾነ እውነት ነው፤ እኛ ከእርሱ በፊት ሙስሊሞች ነበርን» ይላሉ፦
28፥52 እነዚያ ከእርሱ በፊት መጽሐፍን የሰጠናቸው እነርሱ *በእርሱ ያምናሉ*፡፡ الَّذِينَ آتَيْنَاهُمُ الْكِتَابَ مِن قَبْلِهِ هُم بِهِ يُؤْمِنُونَ
28፥53 በእነርሱ ላይ በሚነበብላቸውም ጊዜ «በእርሱ አምነናል፡፡ እርሱ ከጌታችን የኾነ እውነት ነው፡፡ *እኛ ከእርሱ በፊት ሙስሊሞች ነበርን*» ይላሉ፡፡ وَإِذَا يُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ قَالُوا آمَنَّا بِهِ إِنَّهُ الْحَقُّ مِن رَّبِّنَا إِنَّا كُنَّا مِن قَبْلِهِ مُسْلِمِينَ

እዚህ ጥቅስ ላይ ልብ አድርግ “እኛ ከእርሱ ማለትም ከቁርአን መውረድ በፊት ሙስሊም ነበርን” ማለታቸው ምክንያታዊ ነው። ሙስሊም” مُسْلِم ትርጉሙ “አቢድ” عَابِدُ ማለትም “አምላኪ” አሊያም “ቃኒት” قَانِتِ ማለትም “ታዛዥ” ማለት ነው። እንደሚታወቀው ከመጽሐፉ ሰዎች ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው፤ አይሁዳውያን አላህ የተቆጣባቸው ሲሆኑ ክርስቲያኖች ደግሞ የተሳቱተት ናቸው፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3212
ዐዲይ ኢብኑ ሓቲም እንደተረከው ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ አይሁዳውያን የተቆጣባቸው ናቸው፤ ክርስቲያኖች የተሳቱተት ናቸው። عَنْ عَدِيِّ بْنِ حَاتِمٍ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ الْيَهُودُ مَغْضُوبٌ عَلَيْهِمْ وَالنَّصَارَى ضُلاَّلٌ ‏”‏ ‏.‏

ነገር ግን ከአይሁዳውያን ጥቂት ያልተቆጣቸው፤ እንዲሁ ከክርስቲያኖች ጥቂት ያልተሳሳቱ ነበሩ፤ እኛም ከመንገዱ እንዳንስት የእነዚያን በእነርሱ ላይ በጎ የዋለላቸውን መንገድ ምራን ብለን እንቀራለን፦
1፥7 የእነዚያን በእነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን፣ በእነርሱ ላይ *”ያልተቆጣህባቸውን እና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ ምራን”*፤ በሉ። صِرَٰطَ ٱلَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ غَيْرِ ٱلْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلَا ٱلضَّآلِّينَ
ኢማም ቡኻርይ : መጽሐፍ 65, ሐዲስ 4475
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ “ኢማሙ፦ “ያልተቆጣህባቸውን እና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ ምራን” ባለ ጊዜ አሚን በሉ፤ عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏”‏ إِذَا قَالَ الإِمَامُ ‏{‏غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلاَ الضَّالِّينَ‏}‏ فَقُولُوا آمِينَ‏.

ስለዚህ ከመጽሐፉ ሰዎች በተውሒድ ያሉትን የኢስራኢል ልጆች እና ነሳራዎች ያረዱትን መብላትን እና በሃላል ሴቶቻቸውን ማግባት ተፈቅዷል፦
5፥5 ዛሬ መልካሞች ሁሉ ለእናንተ ተፈቀዱ፡፡ *የእነዚያም መጽሐፍን የተሰጡት ሰዎች ምግብ ያረዱት ለእናንተ የተፈቀደ ነው፡፡ ምግባችሁም ለእነሱ የተፈቀደ ነው*፡፡ ከምእመናት ጥብቆቹም *ከእነዚያ ከእናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡት ሴቶች ጥብቆቹም፤ ዘማዊዎችና የምስጢር ወዳጅ ያዢዎች ሳትኾኑ ጥብቆች ኾናችሁ መህሮቻቸውን በሰጣችኋቸው ጊዜ ልታገቡዋቸው የተፈቀዱ ናቸው*፡፡ ٱلْيَوْمَ أُحِلَّ لَكُمُ ٱلطَّيِّبَٰتُ ۖ وَطَعَامُ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ حِلٌّۭ لَّكُمْ وَطَعَامُكُمْ حِلٌّۭ لَّهُمْ ۖ وَٱلْمُحْصَنَٰتُ مِنَ ٱلْمُؤْمِنَٰتِ وَٱلْمُحْصَنَٰتُ مِنَ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ مِن قَبْلِكُمْ إِذَآ ءَاتَيْتُمُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ مُحْصِنِينَ غَيْرَ مُسَٰفِحِينَ وَلَا مُتَّخِذِىٓ أَخْدَانٍۢ ۗ وَمَن يَكْفُرْ بِٱلْإِيمَٰنِ فَقَدْ حَبِطَ عَمَلُهُۥ وَهُوَ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ مِنَ ٱلْخَٰسِرِينَ

“መጽሐፍን የተሰጡት” በሚለው ቃል መነሻ ቅጥያ ላይ “ሚን” مِنَ ማለትም “ከ” የሚል መስተዋድድ አለ፤ ያ የሚያሳየው ከአህለል ኪታብ መካከል ያሉትን ያላሻረኩ፣ የፍጡር ስም ሳይሆን የአላህን ስም ብቻ የሚጠሩ እና ከዝሙት ብልቶቻቸውን ጥብቆች የሆኑ ሴቶች ማግባት ሙባህ ነው። ይህ ሁለተኛው እይታ ነው። ሁለቱም እይታዎች ቁርኣናዊ ናቸው፤ መርጦ መቀበል የግል ምርጫ ነው።

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 2
ጂን እና ሰው የተፈጠሩት ለምንድ ነው?

አላህን ለማመለክ:-
ሱራ 52፡56 “ጂን እና ሰው ሊያመልኩኝ እንጂ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም”

ለገሃነም:-
ሱራ 7፡179 “ከጂን እና ከሰው ብዙዎችን ለገሃነም በእርግጥ ፈጠርን፡፡”

መልስ
አምላካችን አላህ ብዙ አንቀጾች ላይ “አምልኩኝ” እያለ በመጀመሪያ መደብ ይናገራል፦
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ *”እኔንም ብቻ አምልኩኝ”*፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ
21፥92 ይህች አንዲት መንገድ ስትሆን በእርግጥ ሃይማኖታችሁ ናት፤ *”እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ”*፡፡ إِنَّ هَٰذِهِۦٓ أُمَّتُكُمْ أُمَّةًۭ وَٰحِدَةًۭ وَأَنَا۠ رَبُّكُمْ فَٱعْبُدُونِ
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ *”ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ”* በማለት ወደ እርሱ *”የምናወርድለት”* ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ

ጂን እና ሰው የተፈጠረበት ዓላማ ሁሉንም የፈጠረውን አንዱን አምላክ አላህ በብቸኝነት እንዲያመልኩት ነው፦
51፥56 *ጂኒን እና ሰውንም ሊያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም*፡፡ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ