TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Peace #Unity
" የትግራይ ህዝብ ከአስከፊው ጦርነት ገና አላገገመም።
በአመራሮች ክፍፍል እና ስልጣን ምክንያት ዳግም ውጥረት ውስጥ መገባቱ እጅግ በጣም የሚያሳዝን ነው።
ላለፈው በደል እና ለደረሰው ጥፋት መቼ ፍትህ ተሰጠ ? መቼ ተጠያቂነት ተረጋገጠ ? መቼ የተጎዳ ተካሰ ? ለመሆኑ እነዚያ አስከፊ የጨለማ ወራት እንዴት ተረሱ ?
እነዚያ በሰላም መጥፋትና ጦርነት ምክንያት ሴቶች በግፍ በጭካኔ የተደፈሩበት ፣ ወጣቶች የተረሸኑበት ፣ የብዙዎች ደም የፈሰሰበት ፣ በርካቶች ሀገራቸውን ጥለው የሸሹበት ፣ ህጻናት ያለቁበት ፣ እናቶች ልጆቻቸውን ተሸክመው መግቢያ ያጡበት ፣ አዛውንቶች በመጦሪያ እድሜያቸው የጦርነት ሰለባ የሆኑባቸው ወቅቶች ከመቼው ተረሱ ?
ሰላም ሰፈነ ተብሎ ፍትህ እና ማገገም ሲጠበቅ ዳግም እንዲህ ያለ ውጥረት ውስጥ መገባቱ እጅግ የሚያሳዝን ነው።
የሃይማኖት አባቶች ፣ የሃገር ሽማግሌዎች ሁሉ እባካችሁ አሁንም ልዩነት በተፈጠረባቸው ወገኖችና አመራሮች መካከል ሰላም ይወርድ ዘንድ ፤ የከፋ እልቂት እንዳይመጣ ጥረታችሁን ቀጥሉ።
የእርስ በእርስ ልዩነቱና ያለው አጠቃላይ ሁኔታ ለአንዳንዱ ሰርግና ምላሽ ሆኖለት ዳግም የከፋ የደም መፋሰስ እስኪመጣ በጉጉት እየጠበቀ ነው። ለግላቸው የፖለቲካ ትርፍ የህዝብን ደም መፋሰስ የሚጠብቁ ብዙዎች አሰፍስፈው እየጠበቁ ነው።
ይህ የሰላም መደፍረስ እና ህዝብን ጭንቀት ላይ የሚጥል ሁኔታ ሊቆም ይገባል። እልህ መገባባት ውጤቱ ደም መፋሰስ ብቻ ነው። በእርስ በእርስ መለያየት አንድም ቀን ማደር አይገባም። የትግራይ ህዝብም ዳግም ሊሰቃይ አይገባም።
ለህዝብ ስትሉ ችግሮቻችሁን በጠረጴዛ ዙሪያ ፍቱ !!!
በእግዚአብሔር ስም፤በአላህ ስም እንማፀናለን !! "
From : Tikvah Ethiopia Family Tigray Region
@tikvahethiopia

❤725🕊296🙏75😁53😢43😭28👏10