" የ9 ዓመት ታዳጊን ጨምሮ የ7 ሴቶች ሕይወት ጠፍቷል " - ሸካ ዞን
ሸካ ዞን ገበያ ውስጥ የነበረ ትልቅ ዛፍ ሰዎች ላይ ወድቆ 7 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። በ8 ሰዎች ላይ ከባድ እና መካከለኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የሸካ ዞን ኮሚኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙልጌታ አደሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት ሸካ ዞን ፊዴ ታዳጊ ከተማ በሚገኘዉና በተለምዶ ሐሙስ ገበያ ተብሎ በሚጠራው ገበያ ዉስጥ ዛሬ ከቀኑ 7:20 አከባቢ ሰዎች በደራ ገበያ ላይ እያሉ ትልቅ የዋርካ ዛፍ በድንገት ወድቆ የ7 ሰዎችን ህይወት መቅጠፉን ተናግረዋል፡፡
የ9 ዓመት ታዳጊን ጨምሮ ሞቾቹ ሙሉ በሙሉ ሴቶች ናቸዉ ያሉት አቶ ሙሉጌታ በአንፃሩ በአደጋዉ 4 ከባድና 4 መካከለኛ ጉዳት የደረሰባቸዉ 8ቱ ወንዶች መሆናቸዉን ገልፀዋል።
ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸዉ 4 ተጎጂዎች ወደ ጅማ እና ሚዛን ቴፒ ሪፌራል ሆስፒታል መላካቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
#TikvahErhiopiaFamilyHW
@tikvahethiopia

😭1.59K😢117❤103🕊64🙏37😁12😱12🥰11🤔11👏5😡2
TIKVAH-ETHIOPIA
" በተከሰተዉ ወረርሽኝ በሁለት ቀናት ብቻ 380 በላይ የቀንድ ከብቶች ሞተዉብናል " - የጋርዳ ማርታ ወረዳ አስተዳደር ➡️ " የኑሮ ዋስትናችን የሆኑ ከብቶቻችንን በወረርሽኙ እየተነጠቅን ነዉ " - አርሶና አርብቶ አደሮች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ዳርጋ ማርታ ወረዳ የአየር ንብረት ለዉጥን ተከትሎ ተከሰተ በተባለዉ ቦቪን ፓስፖርተስሎስ (Bovine pasteurollosis) በተሰኘ ዳልጋ ከብት…
🚨 #Attention
" በሽታዉ ከጋሞ ዞን በተጨማሪ ወደ ጎፋ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች ተሰራጭቷል " - ዶክተር አዲሱ ኢዮብ
➡️ " በጋርዳ ማርታ ወረዳ የሞቱት ከብቶች ቁጥር 650 በልጧል !!! "
ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች ከሰሞኑ የአየር ንብረት ለዉጥን ተከትሎ ተከሰተ የተባለዉ የቀንድ ከብቶች በሽታ በጋሞ ዞን ጋርዳ ማርታ ወረዳ ብቻ በሁለት ቀናት 380 በላይ የቀንድ ከብቶችን መሞታቸውን መረጃ ተለዋውጠን ነበር።
የክትባት ተደራሽነትና አስቸኳይ ዘመቻም ካልተደረገ በሽታዉ ወደ ሌሎች ከከባቢዎችም ሊዛመት እንደሚችል ተጠቁሞም ነበር።
ዛሬ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የእንስሳት ጤናና ግብአት አቅርቦት ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር አዲሱ ኢዮብ አነጋግረናቸው ነበር።
እንደ ዶክተር ኢዮብ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ በሽታዉ እንደተባለውም በአየር ንብረት ለዉጥን ምክንያት የሚከሰት እንደሆነ ገልጸዋል።
አስቀድሞ በጋሞ ዞን አንድ ወረዳ ብቻ ተከስቶ የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ዞኑ ከጎፋና ደቡብ ኦሞ ዞኖች በሚዋሰንባቸዉ አከባቢዎች መከሰቱን አረጋግጠዋል።
" ከብቶቹ የሚጠጧቸዉ የጋራ የዉሃ ቦታዎች ለበሽታዉ ስርጭት ዋነኛ መንስኤ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል " ያሉት የክልሉ ምክትል ቢሮ ኃላፊ የፌደራልና የክልሉ ተጠሪ ተቋማት ለጉዳዩ ትልቅ ትኩረት በመስጠት በመድሐኒት አቅርቦትና ተያያዥ የጥንቃቄ ስራዎች ከሶስቱም ዞኖችና ወረዳ መዋቅሮች ጋር በቅንጅት እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል።
የደቡብ ኦሞ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ምንላርገው አዲሱ ፤ ይህ ድንገተኛ በሽታ በደቡብ ኦሞ ዞን ማሌ እና ፃሜይ ወረዳዎች መከሰቱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል
የሞቱ እንስሳት ቁጥር ልየታ እየተሰራ መሆኑንና በዞኑ በርካታ ቁጥር ያላቸዉ አርብቶ አደሮች እንደመኖራቸው መጠን የወረዳ፣ የዞን፣ የክልሉና የፌደራል መዋቅር በቅንጅት ርብርብ እያደረገ ነዉ ብለዋል።
አስቀድሞ በሽታዉ በተከሰተበት የጋርዳ ማርታ ወረዳ የሞቱ ከብቶች ቁጥር 655 ደርሷል።
የወረዳዉ እንስሳትና አሳ ሃብት ጽ/ቤት ፥ ከመጋቢት 8/2017 ዓ/ም ምሽት 12 ሰዓት አንስቶ ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት መጋቢት 9/2017 3 ሰዓት ድረስ ምንም ከብት አለመሞቱንና በአብዛኛዉ ሽታዉን ወደ መቆጣጠር ደረጃ እየተደረሰ ነዉ ብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ካነጋገራቸው አርሶአደሮች አንደኛው የነበራቸዉ አምስት ከብት ሙሉ በሙሉ በአንድ ቀን ልዩነት ማለቁንና በቀጣይ ጊዜያት ለከፍተኛ ችግር እንደሚጋለጡ ያላቸዉን ስጋት ገልጸዋል።
ከዚህ ቀደም የበሽታዉን ምንነት በተመለከተ በዘርፉ ባለሙያዎች ቦቪን ፓስትሮሎስስ (bovin pastirolosis) ተብሎ ተገልፆ የነበረ ቢሆንም ዶክተር አዲሱ ኢዮብ በጂንካና ሶዶ የምርምር ማዕከል ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገ ነዉ ብለዋል።
ባለሙያዎች ምን ይመክራሉ ?
🐂 ለተወሰኑ ቀናት ከብቶች እርጥብ ሳር እንዳይበሉ መከላከል !!
🐂 የእንስሳት ልቅ ግጦሽን ማስቆም !!
🐂 እንስሳትን በህፃናት አለማሰማራት /እንስሳትን ህፃናት እንዲጠብቁ አለማድረግ !!
🐂 ደረቅ ሳር ብቻ እንዲመገቡ ማድረግ !!
🐂 የታመሙ እንስሳት ተለይተዉ በፍጥነት እንዲታከሙ ማድረግና በበሽታዉ ያልተያዙትን መከተብ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ያግዛል ሲሉ ባለሙያዎች ይመክራሉ።

😢364😭127❤67🙏37😱9🕊8😡5🤔3🥰1💔1