TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
217 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
በትግራይ ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል ? (ከቲክቫህ የመቐለ ቤተሰብ አባል) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በሦስት ከፍተኛ የሰራዊት አመራሮችና በክልሉ የሰላምና የፀጥታ ቢሮ ሃላፊ ላይ ያሳለፉትን ጊዚያዊና ዘላቂ እግድ ተከትሎ በትግራይ ብዙ ልክ ያልሆኑ ነገሮች በመታየት ላይ ይገኛሉ። የቲክቫህ አባል ከመጋቢት 1/2017 ዓ/ም በኃላ በትግራይ ያለውን ፓለቲካዊ ትኩሳትና…
" እስካሁን ማህተሙ በእጄ ነው ፤ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት እኔው ነኝ " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ጊዜያዊ አስታዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እስካሁን ድረስ በጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ላይ የተደረገ ለውጥ እንደሌለ ገለጹ።

ይህን የገለጹት ከአዲስ አበባ ሆነው ' ርዕዮት ' ከተሰኘ የማህበራዊ ሚዲያ ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ነው።

" ማህተምም አላስረከብኩም " ያሉት አቶ ጌታቸው " ምናልባት የሚደረግ ለውጥ ወይም የሚደረግ ሽግግር ካለ በይፋ እስካውቀው ድረስ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት እንደሆንኩ ነው የማውቀው " ብለዋል።

" ጉዳዩ ይሄን ያህል ሊያጨቃጭቅ የሚገባው አልነበረም ፤ ግን እስካሁን ማህተሙ በእጄ ላይ ነው ያለው " ሲሉ ተናግረዋል።

ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ " የፌዴራል መንግሥት አቶ ጌታቸው ረዳን አንስቶ ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ፕሬዝዳንት ለማድረግ ስምምነት ላይ ደርሷል " የሚል መረጃ ሲሰራጭ ነበር።

በዚህ ጉዳይ ላይ ቃላቸውን የሰጡት አቶ ጌታቸው " እኔ የማውቀው ምንም የተደረሰበት ስምምነት የለም " ብለዋል።

" ጊዜያዊ አስተዳደሩ 2 ዓመት ሞልቶታል ፤ እንዳለመታደል ሆኖ የተቋቋመበትን አላማ ፈጽሞ በምርጫ ለሚመረጥ መንግሥት የሚያስረክብበት ጊዜ ነበር " ያሉቱ ፕሬዝዳንቱ " በተቋቋመበት ደንብ መሰረት ሌላ ተጨማሪ 6 ወር በፌዴራል መንግሥት ካቢኔ መራዘም ይኖርበታል " ብለል።

ባለፈው ሳምንት ወደ አዲስ አበባ የመጡት አቶ ጌታቸው በቀጥታ ከዚህ ጉዳይ ጋር ባይሆንም አጠቃላይ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ስራዎች ጋር በተያያዘ ስለማራዘምም ጭምር ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ም ጥያቄዎች ስለነበራቸው ተገናኝተው አጭር ውይይት ማድረጋቸውን ጠቁመዋል።

" ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ውይይት ያደረኩት ብቻዬን ነው ፤ ባደረግነው ውይይት የሁለት ዓመት ፣ 6 ወርም እስከ ምርጫ ሊሆንም ይችላል አላውቅም የፌዴራል መንግሥት አዋጅ ላይ የሚመሰረት ነው የሚሆነው መራዘም እንደሚኖርበት ጊዜያዊ አስተዳደሩ ቀጣይነት እንዲኖረው ፍቃደኝነት እንዳለ ፣ የሁለት ዓመት ጉዞውን በዝርዝር አይቶ ቀጣይ አቅጣጫዎችን በሚመለከት ለውጥ ያስፈልግ እንደሆነ ለውጥ የሚደረግበት ፤ በአንድ ወይም በሌላ መንገድ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ያልሰራቸውን ስራዎች ማጠናቀቅ የሚችልበት ተጨማሪ እድሜ በሚያገኝበት ጉዳይ ላይ እኔ ባለሁበት እንደሚመከር ነው የማውቀው " ሲሉ ተደምጠዋል።

" ከዛ በኃላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የTPLF ' ጉባኤ አድርጊያለሁ ' የሚለውን ወኪል / ወገን እንዳገኙ አውቃለሁ ባገኙበት ወቅትም ተመሳሳይ መልዕክት እንዳስተላለፉ ነው የሚገባኝ " ብለዋል።

" ከዚህ ውጭ እገሌ ይሁን እገሌ አይሁን በሚል ጉዳይ ላይ እስካሁን በበኩሌ የሰማሁት ነገር የለም። ይሄ ሂደት በድብቅ የሚደረግ ስላልሆነ እንደሚወራው እገሌ እግሌ የሚባል ነገር ካለ ያው በይፋ እስከምሰማው እጠብቃለሁ " ሲሉ ገልጸዋል።

" እንዲህ ያለው ነገር ርዕስ ሊሆንም የማይገባው ነበር እገሌ ሆኗ እገሌ ተሹሟል ከተባ ይሾማል ማለት ነው እኔ እስካሁን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ያደረኩት አጭር ውይይት ከዚህ ጋር የተያያዘ ነው የማራዘም ጉዳይ የህግ ስርዓት ያስፈልገዋል እስከዛው የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝደንት እኔው ነኝ " ብለዋል።

#Tigray #AtoGetachewReda #TigrayInterimAdministration #Mekelle

@tikvahethiopia
🕊361214🤔95👏44😡41😭29🙏24😢10💔9😱6🥰5