TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
218 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#SPAIN

በስፔን ላ ፓዝ ሆስፒታል ውስጥ ነርሶችና የጤና ባለሞያዎች በኮቪድ-19 ህይወቱ ያለፈውን ከፍተኛ የቀዶ ጥገና ሐኪም ጃክዊን ዲያዝን በህሊና ፀሎት አስበውት ውለዋል።

በስፔን ከ200ሺህ በላይ በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] የተያዙ ሰዎች ቢኖሩባትም ቫይረዳሱ የመዛመቱ ፍጥነትና መጠን እየወረደ መሆኑን ባልሥልጣናቱ አስታውቀዋል።

#VOA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SPAIN

(በቢቢሲ እና ሲጂቲኤን)

በስፔን ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የ164 ሰዎች ሞት ሪፖርት ተደርጓል ፤ ይህ የሟቾች ቁጥር ከመጋቢት 9/2012 ዓ/ም በኃላ የተመዘገበ #ዝቅተኛው ቁጥር ነው።

በአሁን ሰዓት በአጠቃላይ 217,446 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ 25,264 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል።

በሌላ በኩል በስፔን ከነገ ጀምሮ በሕዝብ ትራንስፖርት ውስጥ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ (ማስክ) ማድረግ ግድ መሆኑን አስታውቃለች። አገሪቷ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ የጣለቻቸውን ጥብቅ ገደቦች ቀስ በቀስ እያላላች ነው፡፡

በስፔን የሚገኙ አዋቂዎች ከሰባት ሳምንታት በኋላ እሁድ ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከቤት በመውጣት አካላዊ እንቅስቃሴ አድርገዋል፡፡ ከ14 ዓመት በታች ላሉ ህጻናት በቤት ውስጥ የመቀመጥ ገደቡ የላላው ከሳምንት በፊት ነበር፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia