TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Pagume

የአዲስ ዓመት አቀባበልን አስመልክቶ “ጳጉሜን ፌስቲቫል” በሚል ስያሜ የተዘጋጀው ፕሮግራም ካለፈው ዓርብ ጀምሮ በጉለሌ እፅዋት ማእከል በመካሄድ ላይ ነው። ዝግጅቱ በስድስቱም የጳጉሜን ቀናት በልዩ ልዩ ዝግጅቶች የሚከበር ሲሆን የተለያዩ የብሄር ብሄረሰቦች ባህላዊ ጨዋታዎች፣ ባህላዊ ምግቦች አሰራርና አመጋገብ፣ አልባሳት ኤግዚቢሽንና ሽያጭ፣ የፎቶ ግራፍ አውደ ርእይና ሌሎች በየክልሉ የሚገኙ ባህላዊ እሴቶች በዝግጅቱ ላይ ለእይታ እየቀረቡ ይገኛሉ። የ“ጳጉሜን ፌስቲቫል” ድርጅት ሀሳብ አፍላቂ፣ መስራችና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ሀይለአብ መረሳ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፣ የዚህ ድርጅት ሀሳብ የመነጨው የዛሬ አሥር ዓመት ገደማ ሲሆን ሁሉንም ነገር አጠናቅቆ ወደ ሥራ የገባው የዛሬ ሁለት ዓመት ነው። ይህ አሁን እየተከበረ ያለው ሁለተኛው “ጳጉሜን ፌስቲቫል” ዝግጅት ሲሆን ከአምናው ዘንድሮ በተሻለ ሁኔታና በድምቀት በመከበር ላይ ነው ብለዋል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia