TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
217 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Mekelle

በመቐለ የሚገኘው " ፍሬምናጦስ የአረጋውያን የአእምሮ ህሙማን የህፃናት እንክብካቤ ማእከል " በእሳት ቃጠሎ አደጋ ምክንያት ከፍተኛ ወድመት አጋጥሞታል። 

አደጋው ያጋጠመው ሚያዝያ 7/ 2016 ዓ.ም ሲሆን ለበጎ አድራጊዎች ሁሉ የእርዳታ ጥሪ ተማጽኖ አቅርቧል።

የምግባረ ሰናይ ድርጅቱን የተለያዩ በጎ አድራጊዎች ሲረዱት ቆይተዋል።

የሚያዘያ 7ቱ የእሳት አደጋ ከአጋዦቹ አንዱ የሆነው መስፍን ኢንዳስትሪያል ኢንጅነሪንግ ሚሊዮን ብሮች በመስጠት ባሰራው አዳራሽ ነው የደረሰው።

በተነሳው ቃጠሎም አዳራሹ ሙሉ በሙሉ ሲወድም በተረጂዎች ማደሪያ ፣ መመገብያና ፣ መስሪያ ክፍሎች ወድመት ደርሷል።

በከፍተኛ ውጪ የተሰራው አዳራሽ ሚያዝያ 6/2016 ዓ.ም. የተመረቀ ሲሆን በነጋታው  ሚያዝያ 7/2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት ነው በእሳት ሙሉ በሙሉ የወደመው።

የአደጋው መንስኤ በኤሌክትሪክ ማስተላለፍያ በተነሳ ቃጠሎ ነው ተብሏል።

ያጋጠመው ቃጠሎ ከፍተኛ የነበረ ቢሆንም በህዝብና በመቐለ የእሳት አደጋ መከላከያ ብርጌድ የተቀናጀ ርብርብ በማእከሉ በሚገኙ አቅመ ደካሞች የህይወት ማጣት አደጋ  አልደረሰም።

ምግባረ ሰናይ ድርጅቱ በእሳት አደጋ ቃጠሎ ምክንያት የመኝታ፣ መመግብያ ክፍሎቻቸው የተቃጠለባቸው የሚንከባከባችው አቅሞ ደካሞች ሜዳ ላይ ተጥለው እንደሚገኙ በመጠቆም በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ሰብአውያን ሁሉ እንዲረዱት ጥሪ አቅርበዋል።    

መርዳት የሚፈልጉ ወገኖች ፍሬምናጦስ  የአረጋውያን የእአምሮ ህሙማንና የህፃናት እንክብካቤ ማእከል በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000622132404 ሂሳብ ቁጥር መጠቀም ይችላሉ።

#TikvahFamilyMekelle

@tikvahethiopia
😢578😭17479🙏23😱15🤔11🕊8👏5🥰3😡1
#Mekelle

በመቐለ ከተማ መምህራን ለመኖሪያ መስሪያ በእጣ መሬት ተሰጣቸው።

ለመኖሪያ በእጣ በተሰጠው መሬት በ19 ማህበራት የታቀፉ ከ400 በላይ የመቐለ መምህራን ተጠቃሚ እንደሆኑ ተነግሯል።  

ዛሬ የተካሄደው የመምህራን የመኖሪያ መሬት በእጣ የማስተላለፍ ስነ-ሰርዓት ሂደት ከጦርነት በፊት የተጀመረውን ያሰቀጠለ ነው።

ከጦርነቱ በፊት የትግራይ ክልል መምህራን ለመኖሪያ መስሪያ የሚሆን በዕጣ የተሰጣቸው መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በተለይ በመቐለ የዕድሉ ተጠቃሚ ሳይሆኑ የቆዩት በ19 ማህበራት የታቀፉ ከ400 በላይ መምህራን ዛሬ ተጠቃሚ ሆነዋል።

መምህራን ደመወዝ ጨምሮ ሌሎች የሚጠይቁዋቸው ጥያቄዎች በየደረጃው መመለስ እንዳለበት ይህም ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

የትግራይ መምህራን ፦

° በጦርነቱ ምክንያት ያልተሰጣቸው ውዙፍ 17 ወራት ደመወዝ እንዲከፈላቸው ፣

° የመኪና የሰርቪስ አገልግሎትም ጨምሮ ሌሎችም ጥያቄዎች ለጊዚያዊ አስተዳደሩ ደጋግመው ጠይቀው አጥጋቢ መልስ ማግኘት እንዳልቻሉ የሚመለከቱ ተከታታይ ዘገባዎች ስናቀርብ መቆያታችን ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
                                  
@tikvahethiopia            
👏52589🙏23🕊23😭19😢14🥰10😱8🤔6😡6
#Mekelle

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የመቐለ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተገልጿል።

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ አገልግሎት መስጠት የጀመረው ዛሬ ነው።

በዚህም በጊዜያዊነት የጀመራቸው አገልግሎቶች ፦
☑️ ፓስፖርት ማደስ፣
☑️ የጠፋ ፓስፖርት መተካት፣
የተበላሸ ወይ እርማት የመስጠት አገልግሎቶች እንደሆነም ተገልጿል።

የመቐለ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ፅህፈት ቤት ተወካይ ክንፈሚካኤል ረዳሀኝ ዛሬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ከጦርነቱ በፊት በፅህፈት ቤቱ በርካታ አገልግሎት ሲሰጥ እንደነበር አመልክተዋል።

በጦርነቱ ሁሉም አገልግሎት ተቋርጦ እንደነበር አስታውሰዋል።

ከፕሪቶሪያ ሰላም ስምምነት በኃላ ቢዘገይም የፓስፓርት እድሳት አገልግሎት አሁም መሰጠት እንደተጀመረ ገልጸው ፤ " በመላ ትግራይ የሚገኙ የፓስፓርት እድሳት ፈላጊዎች በአካል መምጣት ሳይስፈልጋቸው ባሉበት ሆኖው በኦንላይን መገለግል ይችላሉ " ብለዋል።

ተገልጋዮች ወደ (መቐለ) ፅ/ቤቱ መምጣት ያለባቸው ሁሉም ነገር ጨርሰው ማህተም ለማስመታት ብቻ እንደሆነ ጠቁመዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
            
161👏47🙏13😡12😢7😱5🕊1
#Mekelle

" የሴቶች ጥቃትና እገታ ይቁም ! " በሚል ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ።

ሰላማዊ ሰልፉ በራስ ተነሳሽነት በተነሳሱ ወጣት ሴቶች የተደራጀ ሲሆን ዛሬ ከጠዋቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ በመቐለ ዋና ዋና መንዶች ተካሂዷል።

የሰላማዊ ሰልፉ ተሳታፊዎች ፦

➡️ የሴቶች ጥቃት በቃል ሳይሆን በተግባር ይቁም !!

➡️ ፍትህ የማይሰጥ ፍትህ ቢሮ ይዘጋ !! 

➡️ የሴቶች ጥቃትና እገታ ይቁም !!

➡️ መንግስት አጥፊዎች የሚቀጣ ጥርስ ይኑርህ !!

➡️ የእምነት ተቋማት የሴቶች ጥቃትና እገታ አውግዙ !!

➡️ ፆታ ተኮር ጥቃት ይቁም !!

➡️ የዘውዲና የማህሌት ገዳዮች ወደ ፍርድ ይቅረቡ !!

➡️ የሴቶች መብት ይከበር !! 

የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል።

የሴቶች ጥቃትና እገታ እንዲቆም በራስ ተነሳሽነት በመሰባሰብ ሰላማዊ ሰልፍ ያካሄዱት ወጣት ሴቶች፣ ልጃገረዶች ፣ እናቶች አርቲስቶችና ታዋቂ ሴቶች ሲሆኑ በቂ የፀጥታ አካላት ጥበቃና እጀባ እንደተደረገላቸው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ከቦታው ዘግቧል።

በትግራይ ከጦርነቱ ወዲህ ሴቶች ላይ የሚፈጸም ጥቃትና እገታ መባባሱ በተደጋጋሚ የሚገለጽ ሲሆን በቅርቡ ከ91 ቀናት እገታ በኃላ ተገድላና ተቀብራ የተገኘችው የተማሪ ማህሌት ተኽላይ ጉዳይ ብዙዎችን ያስቆጣ እንደሆነ ይታወሳል።

Photo Credit - DW TV

@tikvahethiopia            
1.08K👏363😭94😢43🕊32😱18😡18🥰16🤔16🙏14
#Tigray #Mekelle

ባለፉት 11 ወራት ብቻ በመቐለ 12 ሴቶች ሲገደሉ 80 ሴቶች የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተፈጽሞባቸዋል።

የመቐለ ፓሊስ ከሀምሌ 2015 ዓ/ም እስከ ሰኔ 2016 ዓ/ም ባሉት 11 ወራት ግድያ ጨምሮ 4,340 ከባድና ቀላል የወንጀል ተግባራት በከተማዋ እንደተፈጸሙ አሳውቋል።

የተፈፀሙት ከባድና ቀላል ወንጀሎች በቁጥር ፦
 
➡️ የሴቶች ግድያ 12 

➡️ አስገድዶ መድፈር 80

➡️ ስርቆት 1,953

➡️ ድብደባ  583

➡️ ዝርፍያ 349

➡️ የመገደል ሙከራ 178

➡️ እገታ 10 

ፖሊድ ወንጀል ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያግዙ 170 የፓሊስ ኮሚኒቲዎች መቋቋማቸውን ገልጿል።

እየተፈፀሙ ያሉ የወንጀል ተግባራት ያልተለመዱ ናቸው ያለው ፖሊስ የሚፈጸሙትን ወንጀሎች ለመቆጣጠር ከወትሮው በተለየ የህብረተሰብ ተሳትፎ እጅግ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ አስገንዝቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
😢703😭28287😡66👏33🕊32😱30🤔19🙏13🥰12
#Tigray

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ተጠርጣሪዎችን የመያዝ ኦፕሬሽን መጀመሩ ተሰማ።
 
በተለያዩ ህጋዊ ያልሆኑ ተግባራት የተሳተፉ አካላት እና ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋል መጀመሩን ጊዚያዊ አስተዳደሩ አሳውቋል።

በትግራይ ከጊዜ ወደ ጊዜ ለመንግስት እና ለህዝብም ድህንነት አስጊ የሆኑ ኢ-ህጋዊ ተግባራት እየተበራከቱ መምጣታቸውን አስተዳደሩ አመልክቷል።

ይህን ለመቆጣጠር ኮሚቴዎችን አቋቁሞ በማጣራት ላይ መቆየቱን አሁን ላይ አብዛኞቹ የማጥራት ስራዎች እየተጠናቀቁ መሆናቸውን አመልክቷል።

በዚህም መሰረት ፥ በተለያዩ ህገወጥ ተግባራት ላይ " እጃቸው አለበት " የተባሉ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል እርምጃ ወደመውሰድ መግባቱን ገልጿል።

በተለይ ዛሬ የብረታ ብረት ስርቆት በመሳሰሉ ወንጀሎች የተሳተፉ አካላትን መያዝ መጀመሩን አስታውቋል።

ለጊዜው ምን ያህል ተጠርጣሪ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እንዳዋሉ በዝርዝር አልታወቀም።

#Tigray
#Mekelle

@tikvahethiopia            
👏54697🕊30😡24😭22🤔15😱15😢11🙏5
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ተጠርጣሪዎችን የመያዝ ኦፕሬሽን መጀመሩ ተሰማ።   በተለያዩ ህጋዊ ያልሆኑ ተግባራት የተሳተፉ አካላት እና ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋል መጀመሩን ጊዚያዊ አስተዳደሩ አሳውቋል። በትግራይ ከጊዜ ወደ ጊዜ ለመንግስት እና ለህዝብም ድህንነት አስጊ የሆኑ ኢ-ህጋዊ ተግባራት እየተበራከቱ መምጣታቸውን አስተዳደሩ አመልክቷል። ይህን ለመቆጣጠር ኮሚቴዎችን አቋቁሞ በማጣራት…
#Mekelle

መቐለ ከተማ ውስጥ በሚገኙ 14 የመኪና የማደሪያ ቦታዎች (ፓርክ የሚደረግበት) 140 ባለቤትነታቸው ያልታወቁ ተሽከርካሪዎች ማግኘቱ የመቐለ ከተማ ፓሊስ ፅሕፈት ቤት አስታውቋል።

ፖሊስ በመቐለ ከተማ የመኪና ማደሪዎች ድንገተኛ ፍተሻ አድርጎ ነበር።

በዚህም140 ባለቤታቸው ያልታወቁ ተሽከርካሪዎች ሊገኙ እንደቻሉ ገልጿል።

የተገኙት ተሽከርካሪዎች ባለቤትነታቸው ለማወቅ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የማጣራት ስራ እየተሰራ እንደሆነ አመልክቷል።

" ባለንብረት ነኝ " የሚል አካል ማረጋገጫ ማስረጃ ይዞ መቅረብ ይችላል ተብሏል።

የመቐለ ፓሊስ ከተሽከርካሪ ፣ ብረታብረትና ሌሎች ንብረቶች ጋር ተያይዞ የማጣራት ስራ በመስራት ላይ እንደሆነ ገልጿል።

የሚካሄደው ምርመራ ግኝቶች በየጊዜው ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አረጋግጧል።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ሐምሌ 4 ባወጣው መግለጫ በክልሉ በቀላል እና ከባባድ ወንጀሎች ተሳትፈዋል ያላቸው ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የማዋል ኦፕሬሽን መጀመሩ መግለፁ መዘገባችን ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
 
🤔379👏192119😱33🕊29😢17😭16😡15🥰10🙏9
#Mekelle

° " መንግስት ቃሉና መመሪያው ማክበር አለበት " - የ70 ካሬ የቤት ግንባታ ማህበር አመራሮች

° " ወደ ላይ እንጂ ወደ ጎን የሚሰጥ የቤት መስሪያ ቦታ የለም " - የትግራይ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ


በመላ ትግራይ በተለይ በመቐለ የሚገኙ የ70 ካሬ የቤት ግንባታ ማህበር አመራሮች ከቤት መስሪያ ቦታ ጋር በተያያዘ ከአንድ ሳምንት በላይ ወደ ክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ፅ/ቤት ምላሽ ለማግኘት ቢመላለሱም ሰሚ እንዳላገኙ ገልጸዋል።

ትላንት በጊዚያዊ አስተዳደሩ ፅ/ቤት የተሰባሰቡት የ 3043 የ70 ካሬ የቤት ግንባታ ማህበር አመራሮች ለጥያቄያቸው ምላሽ ለማግኘት ያደረጉት ሙከራ ሳይሳካ ቀርተዋል።

በቦታው የተገኘው የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል የ70 ካሬ የቤት ግንባታ ማህበር አመራሮችና ጥያቄና የክልሉ መንግስት ምላሽ ተመልክቷል።

60,860 አባላት ያቀፉት 3,043 የ70 ካሬ የቤት ግንባታ ማህበራት ከጦርነቱ በፊት ተደራጅተው ህጋዊ እውቅና በማግኘት ለቤት መስሪያ የሚሆን ገንዘብ በባንክ ሲቆጥቡ መቆየታቸው ይናገራሉ።

ማህበራቱ ቢያንስ በአንድ ቤተሰብ 5 አባላት ቢኖሩ መንግሰት ቃሉ እንዲጠብቅ እየቀረበለት ያለው ጥያቄ የ300 ሺህ ሰዎች መሆኑን ጠቁመዋል።

ተወካዮቹ ፤ " እኛ በሦስተኛ ዙር የ70 ካሬ የቤት ግንባታ ማህበር ስንደራጅ በክልሉ መመሪያ 4/2011 መሰረት ከኛ በፊት በሁለት ዙር እንደተስተናገዱት 70 ካሬ ለቤት መስሪያ ቦታ እንዲሰጠን ተሰማምተን ነው " ብለዋል።

የክልሉ አስተዳደር ግን ከጦርነቱ በኋላ ጥያቄያቸውን ላለመለስ ጀሮ ዳባ ልበስ ማለቱ እንዳሰዘናቸው በአደባባይ ወጥተው ገልፀዋል።

" የክልሉ አስተዳደር በመመሪያ 4/2011 የገባው ቃል ይተግብር " ተወካዮቹ ፥ በሚሰጣቸው 70 ካሬ ቦታ ቤት ለመስራት እንጂ ኮንደሚንየም ማለትም የጋራ መኖሪያ ቤት ለመስራት ቃል እንዳልፈፀሙ አስረድተዋል።

የማህበራቱ አመራሮች ከቀናት በፊት ለጥያቄያቸው ተገቢ ምላሽ ለማግኘት ለክልሉ ምክትል ጊዚያዊ አስተዳደር ሌተናል ጀነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ጥያቄ አቅርበው ከክልሉ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ በመነጋገር መልስ እንደሚሰጣቸው የተነገራቸው ቢሆንም አስከ አሁን የተሰጣቸው ምላሽ እንደሌለ ተናግረዋል።

ከአንድ ሳምንት በፊት የክልሉ የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ አልማዝ ገ/ፃድቕ ለድምፂ ወያነ ትግራይ ጉዳዩ በማስመልከት በሰጡት ማብራርያ ፤ ማህበራቱ ከጦርነቱ በፊት ለእንያንዳንዱ አባል 70 ካሬ መሬት ለቤት መገንብያ እንዲሰጥ በሚፈቅደው መመሪያ መደራጀታቸው አምነዋል።

"ይሁን እንጂ ከአሁን በኋላ ወደ ላይ እንጂ ወደ ጎን የሚሰጥ የቤት መስሪያ ቦታ የለም ፤ ስለሆነም ማህበራቱ የሚሰጣቸው ቦታ G+4 ወደ ላይ የሚገነባ የጋራ መኖሪያ አፓርታማ ነው " ብለዋል።

የማህበራቱ ተወካዮች በቢሮ ሃላፊዋ መልስ እንደማይስማሙ ገልጸዋል።

ለፍትሃዊ ጥያቄያቸው ፍትሃዊ ምላሽ ለማግኘት በማለምም ትላንት ቅዳሜ ቀኑን ሙሉ በጊዚያዊ አስተዳደሩ ፅ/ቤት ጠብቀው የሚያናግራቸው የመንግስት የስራ ሃላፊ ባለመገኘቱ ነገ ሰኞ ጥያቄቸውን በሰላማዊ ሁኔታ ማቅረብ እንደሚቀጥሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
215😭47🕊21🙏20😢19🥰8🤔8😱7👏6
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Mekelle

የኮሚሽነር ግርማይ ከበደ (ግርማይ ማንጁስ) ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ።
 
የቀድሞ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ እና የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ኮሚሽነር ግርማይ ከበደ (ግርማይ ማንጁስ) ስርዓተ ቀብር ዛሬ በመቐለ ተፈጽሟል።

የቀብር ስነስርዓቱ በመቐለ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን የአርበኞች የመቃብር ቦታ ነው የተፈጸመው።

በቀብር ስነስርዓቱ የሟች ቤተሰቦች፣ የመቐለ ነዋሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር አመራሮች ፣ የህወሓትን ጨምሮ የተለያዩ የፓለቲካ ፓርቲ አመራሮች እንዲሁም የትግል ጓዶቻቸው ተገኝተው ነበር።

የ3 ሴት ልጆች አባት የሆኑት ኮሚሽነር ግርማይ ከበደ (ግርማይ ማንጁስ) ባደረባቸዉ ህመም ምክንያት ህክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው መስከረም 24 / 2017 ዓ.ም በተወለዱ በ60 ዓመታቸው ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት።

Photo Credit - Tigrai Communication & Demtsi Woyane

@tikvahethiopia
😭531200🕊81😢69🙏47😡30🤔28😱27👏25🥰12
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ትግራይ

" ቡድኑ ለስልጣን ሲል ማንኛውም ዓይነት ጥፋት ከመፈፀም ወደ ኋላ እንደማይል በተደጋጋሚ እየታየ ነው " - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር

የትግራይ ጊዚያዊ አስተደደር ዛሬ ህዳር 1/2017 ዓ.ም የፅሁፍ መግለጫ አውጥቷል።

በዚህም " በአንደኛው ገፅ ልዩነቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተካረሩ ሄደዋል በሌላኛው ገፅ ደግሞ የጊዚያዊ አስተዳደሩ እቅዶች የማደናቀፍ እና የማዳከም የተቀናጀ ዘመቻ ሲደረግ ቆይቷል አሁንም ቀጥሏል " ሲል ገልጿል።

በተለይም ከነሀሴ 2016 ዓ/ም ጀምሮ በህወሓት ከፍተኛ አመራሮች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት እና በግልፅ የታየው ልዪነት መሰረታዊ የህዝብ ጥያቄያዎች በተቀናጀ መልኩ እንዳይፈቱ ከባድ እንቅፋት ፈጥረዋል ብሏል።

የጊዚያዊ አስተዳደሩን እቅዶች በተቀናጀ መልኩ የሚያደናቅፈው ህጋዊ ያልሆነ ጉባኤ ያካሄደው ቡድን ከፍተኛ አመራር ነው ያለው ጊዜያዊ አስተዳደሩ " ደርጊቱ ህዝቡ ተስፋ እንዲቆርጥ ሆነ ተብሎ የሚደረግ ሃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው " ሲል አውግዞታል። 

" የቡድኑ ተግባር የጊዚያዊ አስተዳደሩ እቅዶች ከማደናቀፍ በዘለለ ይፋዊ ወደ ሆነ የመንግስት ግልበጣ እና ስርዓት አልበኝነት ማስስፋፋት ከፍ ብሏል " ሲል ከሷል።

ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ በመቐለ ከተማ  ፣ በሰሜናዊ እና ማእከላዊ ዞኖች የታዩት የመንግስት ግልበጣና ስርዓት አልበኝነት ምልክቶች የቡድኑ ህግ አልበኝነት ማሳያ ናቸው ሲል አስረድቷል።

" ቡድኑ በአሁኑ ሰዓት ደግሞ የመንግስት የአመራር እርከን ከላይ እስከ ታች ለመቆጣጠር ጨርሰናል " የሚል የማደናገሪያ እቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ገልጿል።

" የቡድኑ ማደናገሪያ በአጉል ተስፋ ራስን ከማታለል የዘለለ ቅንጣት ሀቅ እንደሌለው መታወቅ አለበት " ያለው አስተዳደሩ " ቡድኑ ለስልጣን ሲል ማንኛውም ዓይነት ጥፋት ከመፈፀም ወደ ኋላ እንደማይል በተደጋጋሚ እየታየ መጥቷል " ሲል ገልጿል።

" ' ከሰራዊት አመራሮች ተግባብተናል ' በሚል እየነዛው ያለው ማደናገሪያ ለጠባብ የስልጣን ፍላጎቱ ማሟያ ነው " ብሏል።

" በትግራይ ህልውና የቆመው ሃይል ከመጠቀም እንደማይመለስም ማሳያ ነው " ሲል አክሏል።

" ቡድን " ሲል የገለፀው አካል በሃይማኖት አባቶች የተጀመረው ነገሮች በውይይት የመፍታት ሂደት እንደማይቀበል በአደባባይ ገልፀዋልም ሲል ጊዜያዊ አስተዳደሩ ገልጿል።

የጊዚያዊ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮቼ አሁንም ነገሮች በሰከነ አኳሃን በሰላም እና በውይይት ለመፍታት ዝግጁ ናቸው ብሏል።

የጊዜያዊ አስተዳደሩ አመራሮች የጀመሩት የሰላምና የውይይት ጥረት እንዲሳካ ሁሉም ከጎኑ እንዲሰለፍ ጥሪ አቅርቧል።

በቅርቡ የትግራይ ሃይማኖት አባቶች የህወሓት አመራሮች በመካከላቸው ያለውን ልዩነት በንግግር እንዲፈቱ ለማድረግ ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል እና አቶ ጌታቸው ረዳ እና አመራሮቻቸውን በአካል አገናኝተው ነበር።

ከዚህ መድረክ በኃላ በወጡ የተለያዩ ፎቶዎች በርካቶች " ችግሩ በንግግር ሊፈታ ነው " በሚል ብዙ ተስፋ አድርገው ነበር።

በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ትናንት በትግራይ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት አባቶች አማካኝነት ሁለቱ የህወሓት ቡድኖች ያደረጉት የፊት ለፊት ግንኙነት ከብፁአን የሃይማኖት አባቶች ተግሳፅና ምክር የዘለለ ውጤት እንደሌለው ተናገረ።

የደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ህወሓት ዛሬ ምሽት አጭር መግለጫ አውጥቷል።

አንዳንድ ሚዲያዎች ደግሞ " ለእርቅና ሽምግልና ተስማምተዋል " የሚል መረጃ እስከማሰራጨትም ደርሰው ነበር።

በኃላ በዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት ፥ " በብፁአን አበው የተዘጋጀው ፊት ለፊት የማገናኘት መርሃ ግብር ልዩነቶች በህግ ፣ ተቋማዊ ስርዓት ማእከል በማድረግ ህዝብን ከአደጋ መታደግ በሚችል የሰለጠነ ሰላማዊ መንገድ ችግሮቻችን እንድንፈታ ያለመ የምክርና የተግሳፅ መድረክ ነበር " ሲል አሳውዋል።

" ብፁአን አበው ላቀረቡልን ምክርና ተግሳፅ ያለንን ክብርና ድጋፍ ገልፀናል ፤ ከዚህ በዘለለ የተለያዩ አካላትና ሚዲያዎች ' ለእርቅ እና ሽምግልና ተስማምተዋል ' በማለት የሚያሰራጩት መረጃ ከእውነት የራቀ ነው " ሲል ነበር የገለጸው።

በቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ።

#TikvahEthiopiaFamilyAA #Tigray #Mekelle

@tikvahethiopia
🤔378224🕊97😡71👏41😢28😱21😭20🥰11🙏3
#Mekelle

ዛሬ በመቐለ ከተማ በሚገኝ በአንድ የመንግስት ትምህርት ቤት በራፍ በጠራራ ፀሐይ ነዋሪዎችን ያስደነገጠ ድርጊት ተፈጽሟል።

አንድ መምህር በተማሪው በስለት ብዙ ቦታ ተውግቶ በህክምና እርዳታ ህይወቱ ተርፏል።

ተማሪው በምሳ ሰአት መውጪያ ላይ የደበቀውን ስል ቢላዋ በማውጣት መምህሩን 2 ጊዜ ደረቱ ላይ፣ 1 ጊዜ በሆዱ ላይ ፣ 1 ጊዜ በጀርባው ላይ ፣ 1 ጊዜ ጉኑ ላይ በአጠቃላይ 5 ቦታ ላይ ወግቶታል።

መምህሩን ወድያውኑ ወደ ዓይደር ሆስፒታል ማድረስ በመቻሉ በከባድ የቆዶ ህክምና ህይወቱ መታደግ ተችሏል። 

ይህንን መረጃ ያጋሩት የዓይደር ኮምፕረሄንሲቭ ሆስፒታል ሃኪም የሆኑት ዶ/ር ፋሲካ ዓምደስላሴ " ብዙ ተማሪዎች ስለት ይዘው እንደሚንቀሳቀሱ እየሰማን ነው እንደ ማህበረሰብ አንድ ነገር ማድረግ አለብን " ብለዋል።

ድርጊቱን በተመለከተ ከፖሊስ በኩል የተባለ ነገር የለም።

ሆኖም ወላጆች እባካችሁ የልጆቻችሁን ውሎ ተከታተሉ። ካልተገባ ተግባርም እንዲርቁ ምከሩ ፤ ቸል አትበሏቸዋል እንላለን።

በሌላ በኩል ፤ በዛው መቐለ 6 ቀናት ያስቆጠረ ህፃን እናቱ ከቤት ትታው ወደ መፀዳጃ ቤት ታመራለች ፤ ዳናዋን ተከትሎ ህፃኑ ወደ ተኛበት ክፍል የገባ የቤታቸው ውሻ የህፃኑ መራብያ አካል ላይ ጉዳት አድርሷል።

እናቲቱ ወድያውኑ ደርሳ ልጇን ወደ ዓይደር ኮምፕረሄንሲቭ ሆስፒታል ይዛው እንደመጣች ዶ/ር ፋሲካ ዓምደስላሴ አጋርተዋል።

በእነዲህም አለና ወላጆች ልጨቅላ ልጆቻቹ የምታደረጉት ጥንቃቄ አይለያችሁ።

የተከሰቱት ድርጊቶች ምንም እንኳን ለመስማት የሚከብዱ ቢሆኑም ለወላጆች ጥንቃቄ ሲባል ያጋራናቸው ናቸው።

#Mekelle #AyderHospital

@tikvahethiopia
😢1.08K😭366144🙏67👏43😱39😡38🤔35🕊25🥰13
TIKVAH-ETHIOPIA
ዓዲግራት ከተማ ሁለት ከንቲባ ተሾመባት። አንደኛውን ከንቲባ የአቶ ጌታቸው ረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር ሲሾም አንዱን በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን ነው የሾመው። ከትላንት በስቲያ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ምስራቃዊ ዞን ፅ/ቤት በፃፈው የሹመት ደብዳቤ የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ መምህሩን ዓለም አረጋዊን የከተማይቱ ከንቲባ አድርጎ ሾሟል። አቶ ዓለም የሹመት ደብዳቤ እንደደረሳቸው አረጋግጠዋል። …
#Mekelle

በመቐለም ሁለት ከንቲባ መሾሙ ተሰማ።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ለመቐለ ከተማ አዲስ ከንቲባ ሾመ።

ከተማዋ በቅርቡ በም/ቤት ከንቲባ ተሹሞላት እንደነበር አይዘነጋም።

በጊዚያዊ አስተዳደሩ አዲስ የተሾሙት ከንቲባ ብርሃነ ገ/የሱስ ህወሓት ለሁለት ሳይሰነጠቅ የፓለቲካ ፓርቲው የማእከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩ ናቸው።

በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ይፋዊ ደብዳቤ የተሾሙት ብርሃነ ገ/የሱስ ከጦርነቱ በፊት የከተማዋ ምክትል ከንቲባ በመሆን ያገለገሉ ናቸው።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ባገኘው መረጃ አዲሱ ከንቲባ ከዛሬ ጀምሮ የከንቲባ ስልጣናቸው የሚፀና ይሆናል።

ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ እሁድ 22/2017 ዓ.ም ከትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ወጣቶች ባደረጉት ውይይት ፤ " ሁለት ከንቲባ የሚባል አይሰራም ፤ አንድ ከንቲባ ነው ያለው ያውም መንግስት የመደበው ብቻ ነው። በምክር ቤት ስም የሚካሄድ ከንቲባ የመቀየር ሂደት ተቀባይነት የለውም ፤ ህገ-ወጥ አካሄዱ መልክ እንዲይዝ ይሰራል " ብለዋል።

ባለፈው ጥቅምት 2017 ዓ.ም በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ረዳኢ በርሀ (ዶ/ር) የከተማዋ ከንቲባ በማድረግ የሾመ ሲሆን የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ሹመቱ ውድቅ ማድረጉ መረጃ መለዋወጣችን ይታወሳል።

ከቀናት በፊት ዒግራይ ላይ የአቶ ጌታቸው ረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር ዐለም አረጋዊን ከንቲባ አድርጎ ሲሾም በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን ደግሞ ረዳኢ ገ/እግዚአብሔርን ከንቲባ አድርጎ መሾሙ ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia            
🤔33380🕊42😭25🥰21👏18😡14😱12😢8
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Mekelle

" ህዝቡ ከገባበት የጦርነት ጦስ እንዲያንሰራራ ከመምራት ይልቅ ለስልጣናቸው ብቻ ሲሯሯጡ የህዝቡን ስቃይ እጅግ መራራ አድርገውታል " - ተገልጋይ

በትግራይ ክልል ፣ መቐለ ከተማ በሁለቱ የህወሓት ቡድኖች የተመደቡ ከንቲባዎች በስራ ገበታ የሉም ፤ የከንቲባ ፅህፈት ቤት ታሽጎ በፀጥታ ሃይሎች ጥበቃ ስር ይገኛል።

ተገልጋዮች ከከንቲባ ማግኘት ያለባቸው አገልግሎት ለማግኘት ቢመላለሱም የሚያስተናግዳቸው የለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ዛሬ ማክሰኞ ታህሳስ 8/2017 ዓ.ም ጠዋት መቐለ አስተዳደር ፅህፈት ቅጥር ግቢ ድረስ ተጉዞ አጭር ምልከታ አደርጓል።

በአስተዳደሩ ዋና በር በቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑ ተገለግጋሎች ሲገቡ ሲወጡ ይታዩሉ ፤ ፍትሻ በሚካሄድበት ቦታ ከተለመደው በተለየ ብዛት ያላቸው የፀጥታ አካላት ይስተዋላሉ።

5ኛ ፎቅ ላይ የሚገኘው የዋና ከንቲባ ፅህፈት ቢሮ  (ከህዳር 22/2017 ዓ.ም ) እንደታሸገ ሆኖ ግራና ቀኝ የፓሊስ ደንብ ልብስ በለበሱ የፀጥታ አካላት ይጠበቃል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከከንቲባ የሚሰጥ አገልግሎት ለማግኘት ከአንድ ወር በላይ የተመላለሰ ተገልጋይ አግኝቶ አስተያየቱ ተቀብሏል።

ተልጋዩ ፀጋዛኣብ ርእሰደብሪ ይባላል የመቐለ ቀዳማይ ወያነ ክፍለ ከተማ ነዋሪ ነው።

ያለውን የመሬት ጉዳይ አስመልክቶ ከንቲባ አግኝቶ ለማነጋገር ቢመላለስም እስካሁን እንዳልተሳከለት ገልጿል።

" በሁለቱም በኩል ያሉ የህወሓት አመራሮች ማሰብ ተሰኗቸዋል ? ፤ ህዝቡ ከገባበት የጦርነት ጦስ እንዲያንሰራራ ከመምራት ይልቅ ለስልጣናቸው ብቻ ሲሯሯጡ የህዝቡን ስቃይ እጅግ መራራ አድርገውታል " ሲል በምሬት ተናግሯል።

ካለፈው ወርሀ ነሃሴ 2017 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ ወደ ሁለት ቡድን መሰንጠቃቸው ያወጁት የደረብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) እና የአቶ ጌታቸው ረዳ ቡድን በየፊናቸው በየቦታው አመራር በመመደብና በመገለጫዎች መወራረፍ ቀጥለውበታል።

ባለፈው ወርሃ ጥቅምት 2017 ዓ.ም የቀድሞ ከንቲባ ይትባረክ ኣምሃ ተክቶ በደረብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ህወሓት እጩ አቅራቢነት በከተማው ምክር ቤት ከንቲባ ሆነው የተሾሙት ረዳአ በርሀ (ዶ/ር) በጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ወድያውኑ ተቀባይነት ማጣታቸው ተከትሎ ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም ብርሃነ ገ/የሱስ በጊዚያዊ አስተዳደሩ ተሹመዋል።

በጊዚያዊ አስተዳደሩ ከንቲባ ሆነው የተሸሙት ብርሃነ ገ/የሱስ ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም በፅህፈት ቤቱና በክፍለ ከተሞች አመራሮች በቅጥር ግቢው በሚገኘው የመሰብሰብያ አዳራሽ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጨምሮ ሚድያዎች በተገኙበት አቀባበል ቢደረግላቸውም ከነጋታው ጀምሮ ይህ ዜና አስከተጠናቀረበት ሰዓት ተመልሰው ቢሮ አልገቡም።

በወርሃ ጥቅምት 2017 ዓ.ም የተሾሙት ረዳኢ በርሀ (ዶ/ር) እንዲሁም ቢሮ ላይ የሉም።

በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ምክር ቤቶች በመጠቀም ፤ በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ህወሓት ደግሞ በጊዚያዊ አስተዳደሩ " በተሰጠኝ ስልጣን መሰረት " በማለት መቐለ ጨምሮ በትግራይ ስድስት ዞኖች የየራሳቸው አስተዳዳሪዎች በመሾም ህዝቡን ግራ አጋብተውታል።

ይህንን መሰል ግራ የገባው የሁለቱ የህወሓት ቡድኖች አካሄድ ማብቅያው መቼ ይሆን ? የብዙዎች ጥያቄ ነው።

#TikvahEthiopiaMekelleFamily

@tikvahethiopia
🕊473😭331216🙏89🤔71😡47🥰42😢42👏8😱7
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Mekelle

መቐለ ያለ ከንቲባ አንድ ወር ሆናዋታል።

በጊዚያዊ አስተዳደሩ ከተማዋ እንዲስተዳድሩ  ህዳር 22/2017 ዓ.ም የተሾሙት ብርሃነ ገ/የሱስ ህዳር 23/2017 ዓ.ም በአስተዳደሩ ቅጥር ግቢ አቀባበል ከተደረገላቸው በኋላ ወደ ፅህፈት ቤታቸው አልገቡም።

የከንቲባ ፅህፈት ቤት ታሽጎ በፓሊስ ጥበቃ ስር እንደሚገኝ የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ አባል መግለጹ ይታወሳል።

ከህዳር 23 አስከ ዛሬ እሮብ ታህሳስ 23/ 2017 ዓ.ም አንድ ወር ሙሉ የትግራይ ክልል ዋና ከተማ የሆነቸው መቐለ የሚያስተዳድራት ከንቲባ የለም ፤ ተገልጋዮች ከፍተኛ መጉላላት እየደረሰባቸው እንደሆን በምሬት ይገልፃሉ።

ዛሬ ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም ከመቐለ እና አከባቢዋ የተወጣጡ ወጣቶች በጊዚያዊ አስተዳደሩ የተሾሙ ከንቲባ ስራ እንዲጀምሩ ያለመ ሰልፍ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።

ወጣት ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ህጋዊው ከንቲባ ወደ ፅህፈት ቤታቸው ሳይገቡ ከቦታው ንቅንቅ እንደማይሉ ፤ ከተማዋ የግርግር እና ረብሻ ምንጭ እንድትሆን እንደማይፈቅዱ ድምፃቸው በማሰማት ላይ ይገኛሉ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ጉዳዩ ተከታትሎ ያቀርባል።

@tikvahethiopia
266🕊76🤔53😡36👏31😢27😭10🥰7😱4
#Mekelle

ለመቐለ የውሃ አቅርቦት በሚውል ትራንስፎርመር ላይ በተፈፀመ ስርቆት አገልግሎቱ መቋረጡን የከተማዋ የውሃና ፈሳሽ አገልግሎት ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

የተዘረፈው ትራንስፎርመር ለከተማዋ በቀን 1.9 ሚሊየን ሊትር ውሃ ከጉድጓድ እንዲመነጭ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረ ነው።

ፓሊስ አደገኛ የስርቆት ተግባሩን " እያጣራሁት ነው " ብለዋል።

የትራንስፎርመር ስርቆቱ የካቲት 24/2017 ዓ.ም ሌሊት ፤ ሐድነት ክፍለ ከተማ አይናአለም ቀበሌ ልዩ ቦታ ' ሻፋት ' ነው የተፈፀመው።

ፅ/ቤቱ በትራንፎርመሩ ስርቆት ምክንያት በቀን 1.9 ሚሊየን ሊትር ውሃ የሚያመነጨው ጉድጓድ ሙሉ በሙሉ ከአገልግሎት ወጪ መሆኑ ገልጾ " ህዝቡ የውሃ አቅርቦት አገልግሎቱ እስኪመለስ እንዲታገስ " ሲል ጠይቋል።

ትራንስፎርመሩ ጨምሮ ጠቅላላ የደረሰው ወድመት ከ5 ሚሊዮን ብር ላይ ይገመታል ሲልም አክሏል።

ፖሊስ ከባድ የስርቆት ተግባሩ የቦታውን ሁለት ጥበቃዎች ላይ የአካል ጉዳት በማድረስ መፈፀሙ ጠቅሶ ፈፃሚዎቹ በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል የቀናጀ ስራ እየተሰራ ነው ብሏል።

ዘራፊዎቹ በጥበቃዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ማድረሳቸው የተነገረ ሲሆን ተጣርጣሪዎቹ ለመያዝ በሚድረገው እንቅስቃሴ የህዝቡ ተሳትፎ እና ጥቆማ እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ፓሊስ አመልክቷል።

@tikvahethiopia
😁216😢14876😡43😭24😱10👏7🕊5🙏4🥰3🤔1
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray " ህወሓት ለበርካታ ጊዚያት በተጠራቀሙ ችግሮች ተተብትቦ ወደ ፊት መራመድ ተስኖታል " አሉ ጊዜያዊ አስተዳደሩ የሾማቸው የመቐለ ከንቲባ ብርሃነ ገ/ኢየሱስ። ከንቲባው ይህን ያሉት ከከተማዋ ወጣቶች ጋር በመከሩበት ወቅት ነው። " ህወሓት ለበርካታ ጊዚያት በተጠራቀሙ ችግሮች ተተብትቦ ወደ ፊት መራመድ ተስኖታል " ያሉት ከንቲባው " ፓርቲው ጠልፈው የጣሉት ችግሮቹ ከመፍታት ይልቅ ማሰብ አቁሞ…
#Mekelle

🔴 " ህወሓት መዳን ከፈለገች መልሳ ጉባኤ ማድረግ አለባት የሚል እምነት አለኝ "- ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ 

⚫️ " ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ እርምጃ ውሰድ ፤ ካልሆነ በራሳችን መንገድ እንሄዳለን " - የመቐለ ከተማ ወጣቶች


ዛሬ ለመቐለ ከተማ ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር የመከሩ ወጣቶች የደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት "  ኋላቀር ለውጥ አደናቃፊ " ሲሉ  ወረፉ።

ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ዛሬ ከመቐለ 7 ከፍለ ከተሞች ከተወጣጡ ወጣቶች በፅህፈት ቤታቸው የተወያዩ ሲሆን ለተነሱላቸው ጥያቄዎች መልስና ማብራርያ ሰጥተዋል። 

ወጣቶቹ በመድረኩ ባቀረቡት አስተያየትና አካሄድ የደብረፅዮኑ (ዶ/ር) ህወሓት " ' እኔ ባልቀደስኩት መአድ ለመብላት እጅ መሰድድ አይታሰብም ' በሚል አካሄድ ተጠምደዋል " ሲሉ  ተችተዋል።

" ' እኔ ብቻ ነኝ ፈላጭ ቆራጭ ' የሚል ፈሊጥ ያለንበት ወቅት የማይዋጅ ኋላቀር " ሲሉ በስሜት የተናገሩት ወጣቶቹ የደብረፅዮኑ (ዶ/ር) ህወሓት የጠቅላይነት መንገድና አካሄድ አይሰራም ብለዋል።

የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት " ፀረ ለውጥ " ሲሉ በፈረጁት የደብረፅዮኑ ህወሓት ላይ እርምጃ ባለመወሰዱ አምርረው የነቀፉት ወጣቶቹ  " ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ እርምጃ ውሰድ ፤ ካልሆነ በራሳችን መንገድ እንሄዳለን " በማለት ቁጣቸው አሰምተዋል።  

" መንግስት መንግስትን በመሆን የለውጥ ጥያቄያችን ይመልስ እኛ ወጣቶች ትዕግስታችን ተሟጠዋል " ሲሉም ገልጸዋል።

ህዝቡ የአስተማማኝ ሰላም ባለቤት እንዲሆን በምርጫ የሰየመው መንግስት ሊኖረው ይገባል ሲሉ ምላሽ የሰጡት ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ይህንን እውን እንዲሆን ከስሜት የፀዳ ትግልና አካሄድ ከወጣቱ ይጠበቃል ብለዋል። 

" ህወሓት ጠላት ነው " የሚል ነገር ስህተት እንደሆነ የገለፁት ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው  " ፓርቲው እንዲድን ከተፈለገ እንደ አዲስ አሳታፊ ጉባኤ ማካሄድ ይጠበቅበታል " የሚል ምክረ ሃሳብ አቅርበዋል። 

በትግራይ ያለው ችግር በህወሓት ብቻ ይፈታል ማለት ስህተት ነው ፤/ስለሆነም ላሉት ዘርፈ በዙ ችግሮች አሳታፊ ሁሉን አቀፍ ፓለቲካ ዋነኛ ተመራጭ መንገድ ነው ሲሉ አክለዋል።

ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የመቐለ ከተማ ያለ ከንቲባ ከሦስት ወራት በላይ መቆየት፣ የDDR መቋረጥ ፣ በክልሉ የሚታዩ በርካታ የፀጥታ ችግሮች በማስመልከት ከወጣቶች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች መልስና ማብራርያ መስጠታቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

Photo Credit - Tigrai TV

@tikvahethiopia
😁515311🕊137👏99🙏48😭30😡27🤔21🥰20😢12
TIKVAH-ETHIOPIA
በትግራይ ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል ? (ከቲክቫህ የመቐለ ቤተሰብ አባል) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በሦስት ከፍተኛ የሰራዊት አመራሮችና በክልሉ የሰላምና የፀጥታ ቢሮ ሃላፊ ላይ ያሳለፉትን ጊዚያዊና ዘላቂ እግድ ተከትሎ በትግራይ ብዙ ልክ ያልሆኑ ነገሮች በመታየት ላይ ይገኛሉ። የቲክቫህ አባል ከመጋቢት 1/2017 ዓ/ም በኃላ በትግራይ ያለውን ፓለቲካዊ ትኩሳትና…
" እስካሁን ማህተሙ በእጄ ነው ፤ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት እኔው ነኝ " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ጊዜያዊ አስታዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እስካሁን ድረስ በጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ላይ የተደረገ ለውጥ እንደሌለ ገለጹ።

ይህን የገለጹት ከአዲስ አበባ ሆነው ' ርዕዮት ' ከተሰኘ የማህበራዊ ሚዲያ ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ነው።

" ማህተምም አላስረከብኩም " ያሉት አቶ ጌታቸው " ምናልባት የሚደረግ ለውጥ ወይም የሚደረግ ሽግግር ካለ በይፋ እስካውቀው ድረስ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት እንደሆንኩ ነው የማውቀው " ብለዋል።

" ጉዳዩ ይሄን ያህል ሊያጨቃጭቅ የሚገባው አልነበረም ፤ ግን እስካሁን ማህተሙ በእጄ ላይ ነው ያለው " ሲሉ ተናግረዋል።

ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ " የፌዴራል መንግሥት አቶ ጌታቸው ረዳን አንስቶ ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ፕሬዝዳንት ለማድረግ ስምምነት ላይ ደርሷል " የሚል መረጃ ሲሰራጭ ነበር።

በዚህ ጉዳይ ላይ ቃላቸውን የሰጡት አቶ ጌታቸው " እኔ የማውቀው ምንም የተደረሰበት ስምምነት የለም " ብለዋል።

" ጊዜያዊ አስተዳደሩ 2 ዓመት ሞልቶታል ፤ እንዳለመታደል ሆኖ የተቋቋመበትን አላማ ፈጽሞ በምርጫ ለሚመረጥ መንግሥት የሚያስረክብበት ጊዜ ነበር " ያሉቱ ፕሬዝዳንቱ " በተቋቋመበት ደንብ መሰረት ሌላ ተጨማሪ 6 ወር በፌዴራል መንግሥት ካቢኔ መራዘም ይኖርበታል " ብለል።

ባለፈው ሳምንት ወደ አዲስ አበባ የመጡት አቶ ጌታቸው በቀጥታ ከዚህ ጉዳይ ጋር ባይሆንም አጠቃላይ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ስራዎች ጋር በተያያዘ ስለማራዘምም ጭምር ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ም ጥያቄዎች ስለነበራቸው ተገናኝተው አጭር ውይይት ማድረጋቸውን ጠቁመዋል።

" ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ውይይት ያደረኩት ብቻዬን ነው ፤ ባደረግነው ውይይት የሁለት ዓመት ፣ 6 ወርም እስከ ምርጫ ሊሆንም ይችላል አላውቅም የፌዴራል መንግሥት አዋጅ ላይ የሚመሰረት ነው የሚሆነው መራዘም እንደሚኖርበት ጊዜያዊ አስተዳደሩ ቀጣይነት እንዲኖረው ፍቃደኝነት እንዳለ ፣ የሁለት ዓመት ጉዞውን በዝርዝር አይቶ ቀጣይ አቅጣጫዎችን በሚመለከት ለውጥ ያስፈልግ እንደሆነ ለውጥ የሚደረግበት ፤ በአንድ ወይም በሌላ መንገድ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ያልሰራቸውን ስራዎች ማጠናቀቅ የሚችልበት ተጨማሪ እድሜ በሚያገኝበት ጉዳይ ላይ እኔ ባለሁበት እንደሚመከር ነው የማውቀው " ሲሉ ተደምጠዋል።

" ከዛ በኃላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የTPLF ' ጉባኤ አድርጊያለሁ ' የሚለውን ወኪል / ወገን እንዳገኙ አውቃለሁ ባገኙበት ወቅትም ተመሳሳይ መልዕክት እንዳስተላለፉ ነው የሚገባኝ " ብለዋል።

" ከዚህ ውጭ እገሌ ይሁን እገሌ አይሁን በሚል ጉዳይ ላይ እስካሁን በበኩሌ የሰማሁት ነገር የለም። ይሄ ሂደት በድብቅ የሚደረግ ስላልሆነ እንደሚወራው እገሌ እግሌ የሚባል ነገር ካለ ያው በይፋ እስከምሰማው እጠብቃለሁ " ሲሉ ገልጸዋል።

" እንዲህ ያለው ነገር ርዕስ ሊሆንም የማይገባው ነበር እገሌ ሆኗ እገሌ ተሹሟል ከተባ ይሾማል ማለት ነው እኔ እስካሁን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ያደረኩት አጭር ውይይት ከዚህ ጋር የተያያዘ ነው የማራዘም ጉዳይ የህግ ስርዓት ያስፈልገዋል እስከዛው የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝደንት እኔው ነኝ " ብለዋል።

#Tigray #AtoGetachewReda #TigrayInterimAdministration #Mekelle

@tikvahethiopia
🕊361214🤔95👏44😡41😭29🙏24😢10💔9😱6🥰5
#Mekelle : በመቐለ ከተማ ሰሜን ክፍለ ከተማ ላጪ ተብሎ በሚጠራ ቀበሌ መጋቢት 16/2017 ዓ.ም ሌሊት ባጋጠመ የእሳት አደጋ ወላጅ እናት ከሁለት ልጆችዋ ጋር ህይወታቸው አልፏል።

በቤት ውስጥ የተቀመጠ ቤንዚን ተቀጣጥሎ ነው አሰቃቂ የሞት አደጋ ያስከተለው ተብሏል።

ቤንዚኑ በጀሪካን በቤት የተቀመጠ ነበር ያለው የከተማው ፖሊስ ቃጥሎውን ተከትሎ እናት እና ልጆቿ ህይወታቸው እንደጠፋ አመልክቷል።

በአደጋው ምክንያት ወላጅ እናት ዕድሚያቸው 5 ወር እና 4 ዓመት ትኩል ከሆኑ ልጆቻ ጋር ነው ህይወቷ ያለፈው።

ቤተሰቡ ለማዳን ጥረት ያደረገው አባት ሳይሳካለት ቀርቶ ከባድ ጉዳት ደርሶት ሆስፒታል ገብቶ ክትትል እዘየተደረገለት ይገኛል።

የአሰቃቂ የቃጠሎ አደጋውን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ፓሊስ ማጥራቱን መቀጠሉ አስታውቋል።

ህብረተሰቡ ቃጠሎ የሚያባብሰሱ ነገሮች በመኖሪያ ቤት ከማስቀመጥ እንዲቆጠብ መልእክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
😭1.4K💔17562😢48🕊33🙏18🥰5🤔5👏2
TIKVAH-ETHIOPIA
" ለፍትሃዊ ጥያቄያችን ፍትሃዊ ምላሽ እንሻለን !! " የመቐለ 70 ካሬ የቤት ግንባታ ማህበራት አመራርና አባላት " ጥያቄያችን ላለፉት 6 ዓመታት ሰሚ ጀሮ አጥቷል " በማለት በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የፕሬዜዳንት ፅ/ቤት በሰላማዊ ሰልፍ ምሬታቸውን ገልፀዋል። ከ6 ዓመታት በፊት ለአንድ አባወራ 70 ካሬ ሜትር የመኖሪያ የቤት ግንባታ መሬት ለመሰጠት በሚፈቅድ መመሪያ መደራጀታቸው ገልጸው ከጦርነት…
#Mekelle

የ70 ካሬ ቤት ግንባታ አባላትና አመራርሮች በድጋሚ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ።

አባላቱ ሀሙስ በጠሩት ሰላማዊ ሰልፍ ለ6 ዓመታት የዘለቀው የመብት ጥያቄያቸው ቁርጥ ያለ ምላሽ  እንዲሰጠው በምሬት ጠይቀዋል። 

በሰልፉ ላይ ፦
- " ትግራይ የመሬት ጥበት የላትም ! "
- " የመኖሪያ ቤት ጥየቄ መሰረታዊ እንጂ የምቾት ጥያቄ አይደለም ! "
- " ለ70 ካሬ የቤት ግንባታ እንጂ ለአፓርታማ አልተደራጀንም ! "
- " ፍትህ ለ70 ካሬ የቤት ግንባታ አባላት ! "

 የሚሉና ሌሎች መፈክሮች ተስተጋብተዋል።

በትግራይ ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት ደጃፍ ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) ወደ ስልጣን ከመጡ ለሁለተኛ ጊዜ በተካሄደውና በመቶዎች የሚቆጠሩ የቤት ፈላጊዎች የተሳተፉበት ድምፅ ሰምቶ ምላሽ የሚሰጥ የመንግስት የስራ ሃላፊ አልተገኘም።

የ70 ካሬ የቤት ግንባታ ማህበር አባላት ባለፈው ሳምንት በመቐለ አስተዳደር የሰብሰባ አዳራሽ ተገኝተው በአጭር ጊዜ ቁርጥ ያለ ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠይቀው ምላሽ ባለማግኘታቸው ሰልፍ ሊጠሩ መገደዳቸውን አስረድተዋል።

ሰላማዊ ሰልፈኞቹ በተደራጁበት መመሪያ 4/2011 ዓ.ም መሰረት ለ70 ካሬ የቤት ግንባታ እንዲሰጣቸው ያቀረቡት ጥያቄ እስኪመለስ የመብት ትግላቸው በሰላማዊ መንገድ እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።

ከጦርነቱ በፊት በመላ ትግራይ ለ70 ካሬ የቤት ግንባታ በማህበራት የተደራጁ ከ60 ሺህ አባላት መኖራቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ በተደጋጋሚ መረጃ ማጋራቱ ይታወሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
 
@tikvahethiopia
377😭70👏49🕊35🤔21🥰18🙏17😢16😡16
#Mekelle

የመቐለ ከተማ የፀጥታ ፅህፈት ቤት የከተማው ፓሊስና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ሰኔ 19/2017 ዓ.ም ውይይት አካሂዷል።

በተካሄደው ውይይት ፦
- ወንጀል ፈፃሚዎች ላይ የሚወሰደው ህጋዊ እርምጃ ተገቢና አስተማሪ ባለመሆኑ ምክንያት በፀጥታ ስራ ስጋት እንደፈጠረ

- የተወሰኑ የፀጥታ አካላት የፀጥታ ስራን ከፓለቲካ ጋር የማገናኘት ፣ የመንደርተኝነት አስተሳሳብ ማንፀባረቅ ፣ ራሳቸው የፀጥታ ስጋት መሆን ፤

- ህብረተሰቡን የፀጥታው ባለቤት አለማደረግ አለማሳተፍ እንደሚታይ

- በከተማው በተደጋጋሚ በሚታዩት የግድያ ፣ ስርቆትና የማጭበርበር ወንጀሎች በመቆጣጠር ላይ መሰረታዊ ለውጥ አለማምጣት የሚሉት ተነስተዋል።

በተለይ ከጦርነቱ በኋላ በህዝብና መንግስት መሰረተ ልማቶች የሚፈፀም ስርቆትና ውድመት ባልተለመደ ሁኔታ መበራከቱ ፓሊስ ገልጿል።

ባለፉት 10 ወራት በ99 የህዝብና የመንግስት መሰረተ ልማቶች ውድመትና ስርቆት መፈፀሙ በማስረጃ አስደግፎ አቅርቧል።

ሰኔ 16/2017 ዓ.ም ለመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ውሃ በሚያቀርበው የገረብ ሰገን ግድብ 2.1 ኪ.ሜ መስመር ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶ ከ1 ሚሊዮን ህዝብ በላይ ለውሃ ጥም መዳረጉንና አሁን ተጠግኖ አገልግሎት መሰጠት መጀመሩ ተጠቅሷል።

በውይይቱ ማጠቃለያ የፀጥታ ስራ ከፓለቲካና ከመንደርተኝነት አስተሳሰብ በፀዳ መንገድ መከናወን እንደሚገባ አፅንኦት ተስጥቶታል።

በክልሉ ያለው የፖለቲካ ቀውስ የፀጥታ ስጋቱን እያባባሰው መሆኑም በመድረኩ ተነስቷል።

መረጃው ከትግራይ ቴሌቪዥን የተገኘ ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia        
377😭24🕊23🙏10🤔7🥰6💔5😢4😱2