#Ethiopia
የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት ፣ ካሳ የሚከፈልበት እና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበት አዋጅ በ4 ተቃውሞ በ6 ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል።
አዋጁ ፤ ከዚህ በፊት በልማት ተነስተው የካሳ ክፍያ ያላገኙትን እና አሁንም ድረስ እየጠበቁ ያሉ የልማት ተነሺ ሰዎችን እንደማያካትት ተሰምቷል።
ከምክር ቤት አባላት ምን ተጠየቀ ? ምን ምላሽ ተሰጠ ?
Q. ከዚህ በፊት በርካታ የካሳ ክፍያዎች አዲሱ የካሳ ክፍያ እና ተነሺዎች መልሶ የሚቋቋሙበት አዋጅ እስከ ሚፀድቅ ድረስ እንዲቆዩ ተደርገዋል ይህ አዋጅ እንዴት ሊያስተናግዳቸው አስቧል ?
Q. ካሳ የመክፈሉ ኃላፊነት ለክልሎች በአዲሱ አዋጅ መስጠቱ ለሰራተኞቻቸው እንኳን ደሞዝ መክፈል ያልቻሉ ክልሎች ባሉበት ሰዓት እንዴት እንዲህ አይነት ክፍያ ሊከፍሉ ይችላል ?
Q. አንዳንድ የፍርድ ቤት ውሳኔዎች በተመለከተ ለፌደራል የመጀመሪያ ፍ/ቤት መስጠቱ አግባብነት የለውም። ይህ እንዴት ሊታይ ታስቦ ነው ለከፍተኛ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት ችግሮችን ለማየት ስልጣን የተሰጠው ?
ሌላው ፤ ከዚህ በፊት ከፍተኛ የሆነ ምዝበራ ይፈፀም የነበረው በክልሎችና በወረዳዎች በሚጣሉ የካሳ ተመኖች ነበር አዋጁ ይህ እንዲባባስ ሊያደር ይችላል የሚል ስጋት ተነስቷል።
በተ/ም/ቤት የህግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ፥ ከዚህ በፊት ከልማት ጋር በተያያዘ ያልተከፈሉ ክፍያዎች የሚዳኙት በቀድሞ አዋጅ መሰረት ነው ብለዋል።
አዲሱ አዋጅ የሚመለከተው ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ ያሉ የካሳ ክፍያዎች ብቻ እንደሆነ ገልጸዋል።
በክልሎች ያለው በጀት ጉድለት እንዳለ ሆኖ ለልማት ተነሺዎች የሚከፈለው የካሳ ክፍያ የሚፈፀመው የፌደራል መንግስት ለክልሎች በሚሰጠው የበጀት ድጎማ እንደሆነ ተመላክቷል።
በክልሎች አዳዲስ ፕሮጀክቶች ሲታቀዱ ለክልሎች የሚመደበው በጀት ላይ የካሳ ክፍያ ታሳቢ ይሆናል።
ከዳኙነቱ ጋር በተያያዘም ለተነሳው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ሌላኛው የቋሚ ኮሚቴ አባል ፤ " ውሳኔውን ለመስጠት የተፈለገው ልማቶች ሲካሄዱ ፈጣን ፍርድ ለማሰጠትና ሀብትን ከምዝበራ ለመታደግ በማሰብ ነው " ብለዋል።
#ShegerFM
#HoPR
@tikvahethiopia

😡313❤141🙏32🤔23🕊23😭16😱15🥰13👏13😢9
#HoPR
ዛሬ የህዝብ ተወካዮች ም/ ቤት 36ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ይገኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በምክር ቤቱ ተገኝተዋል።
በስብሰባው የ2016 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት እና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ እና ምላሽ ይሰጣሉ፡፡
በአሁን ሰዓት የምክር ቤት አባላት ጥያቄ እያቀረቡ ናቸው።

😡415❤109😭20👏19😱11🙏10🕊7
TIKVAH-ETHIOPIA
የምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ? " አጠቃላይ የሀገራችን የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታዎች በዋና ዋና አመላካቾች በምን ደረጃ ላይ ናቸው ? በተለይ የኑሮ ውድነት እየከፋ ነው። የዋጋ ንረትን ደግሞ ማረጋጋት አልተቻለም። በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያለው ማህበረሰብ እና የመንግሥት ሰራተኛው መኖር አቅቶታል። መኖር የቅድሚያ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ተግባር ነው። ስለሆነም እንደ መንግሥት በቀጣይ አመታት…
#HoPR
" ... ማንኛውም መንግስታዊ አገልግሎት የሚገኘው በገንዘብ እና በእጅ መንሻ ሆኗል " - የም/ቤት አባል
የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ?
አቶ አብርሃም በርታ (የተ/ም/ቤት አባል) ፦
" ብዙ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት እና አንዳንድ ዓለም አቀፍ ተቋማት ባወጡት ሪፖርት ሙስና በሀገራችን ከአመት አመት እየጨመረ መምጣቱን ያሳያሉ።
ይህን ስር የሰደደ መንግሥታዊ ሌብነት ወይም ሙስና ለመዋጋት ብሔራዊ የጸረሙስና ኮሚቴ መቋቋሙን ብንሰማም አርቂ ስራ ሲሰራም ሆነ በሙስና ምክንያት ያንዣበበውን ሀገራዊ አደጋ ለመቀልበስ እርባና ያለው ስራ ሲሰራ አልታየም።
በአጠቃላይ መንግሥት ሙስናን ለመዋጋት ይሄ ነው የሚባል መፍትሄ እየሰጠ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን ቁርጠኝነቱም ላይ ጥያቄ ይነሳል።
ምክንያቱም የህዝብ እና የመንግስት ሀብት በዘረፉ ሙሰኛ ባለስልጣናት ላይ መቀጣጫ የሚሆን እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ተጨማሪ ሹመት እና የቦታ ዝውውር በመስጠት መንግስት ሙሰኞችን አብሮ አቅፎ ይኖራል ማለት ይቻላል።
ከዚህ የተነሳ ፦
➡ የመንግስት መዋቅር በሌቦች ተጠልፏል።
➡ ማንኛውም መንግስታዊ አገልግሎት የሚገኘው በገንዘብ እና በእጅ መንሻ ሆኗል።
➡ ዜጎች የዕለት ኑሯቸውን ለመግፋት በአደባባይ ገንዘብ እየተጠየቁ ነው።
➡ ከፍተኛ የሀገር ሀብት ከሀገር ወጥቶ እየሸሸ ነው።
➡ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ከፍተኛ መጠን ያለው ሀብት እያባከኑ ነው።
➡ በኦዲት ሪፖርት መሰረት በየመ/ቤቱ ከፍተኛ የሆነ የጥሬ ገንዘብ ጉድለት ይታያል።
➡ መ/ቤቶች ገንዘብ ያለማስረጃ ወጪ በማድረግ ይጠቀማሉ ፣ ምንም ማስረጃ ሳያቀርቡ በወጪ ይመዘግባሉ፣ ከፋይናንስ መመሪያና ደንብ ውጭ የገንዘብ ክፍያ ይፈጸማል።
እንደሚታወቀው ብዙ ሀገራት ለችግሩ በሰጡት ትኩረት የማያወላውል እርምጃ ስለወሰዱ ችግሩን ማቃለል ችለዋል።
ለምሳሌ በቅርቡ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች ለልምድ ልውውጥ የጎበኟቸው የእስያ ሀገራት እነ ሲንጋፖር ፣ ቻይና፣ ደቡብ ኮሪያ ስንመለከት ለእድገታቸው ዋናው መሰረት በሙስና ላይ ያላቸው ቁርጠኝነት ነው።
በሀገራችን የሌብነት ችግር ለመቅረፍ አፋጣኝ እና አስተማሪ የሚሆን እርምጃ ካልተወሰደ በስተቀር የጸረ ሙስና ህጋችንን አሻሽለን ቢሆን በሀገራችን አሁን የምናያቸው ፈተናዎች ተደምረው ሙስና የሀገራችንን ህልውና መፈተኑ አይቀርም።
ክቡር ጠ/ሚኒስትር በህዝቡ የሚቀርበው ተደጋጋሚ ቅሬታና የጄነራል ኦዲተር መ/ቤት በማስረጃ አስደግፎ ያቀረበልን ስር የሰደደ የሙስናን ችግር ለመቅረፍ መንግስትዎ ምን ያህል ቁርጠኛ ነው ?
በተደጋጋሚ እንደታዘብነው ቃል ከመግባት ባለፈ ምን ተግባራዊ እርምጃ ለመውሰድ ታስቧል ?
ህዝቡስ ከመንግስትዎ ምን ይጠብቅ ? "

👏1K❤129🙏61😭26😢18🤔13😱10🥰8🕊8😡8
TIKVAH-ETHIOPIA
#HoPR " ... ማንኛውም መንግስታዊ አገልግሎት የሚገኘው በገንዘብ እና በእጅ መንሻ ሆኗል " - የም/ቤት አባል የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ? አቶ አብርሃም በርታ (የተ/ም/ቤት አባል) ፦ " ብዙ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት እና አንዳንድ ዓለም አቀፍ ተቋማት ባወጡት ሪፖርት ሙስና በሀገራችን ከአመት አመት እየጨመረ መምጣቱን ያሳያሉ። ይህን ስር የሰደደ መንግሥታዊ ሌብነት ወይም ሙስና…
የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ?
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ እና የተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ አበባው ደሳለው ፦
" የመንግስት ኃላፊዎች በተለያየ ጊዜያት በተደጋጋሚ ስለ ሀገራዊ ምክክር እና ስለ ሽግግር ፍትህ ሲያነሱ ይደመጣል።
ነገር ግን ከሀገራዊ ምክክር እና ከሽግግር ፍትህ በፊት መቅደም ያለባቸው ነገሮች አሉ። ከነዚህ ውስጥ አንደኛውና ዋነኛው የእምነት ግንባታ ነው።
መንግስት በህዝብ ዘንድ እምነት አልገነባም ብለን እናስባለን። ይሄም የሚገናኘው ከሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር ነው።
ባለፉት 10 ወራት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ሰበብ በማድረግ የመንግስት ኃይሎች ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጽመዋል።
ከነዚህ ጥሰቶች ውስጥ የጅምላ ግድያ፣ በሰብዓዊ / ባልታጠቁ ዜጎች ላይ የጅምላ ግድያ ተፈጽሟል። በበርካታ የአማራ ክልል ከተሞች።
ጥቂቱን ለመጥቀስ በመርዓዊ ፣ በጅጋ ፣ በደብረ ኤልያስ ፣ በፍትኖተ ሰላም፣ ደብረሲና አካባቢ ፣ ጎንደር እና ወሎም እንዲሁ ተፈጽሟል።
ይህንንም የተለያዩ የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብት ተቋማት የዘገቡት የአይን እማኞችም የሚመሰክሩት ጉዳይ ነው።
ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ጾታዊ ጥቃት፣ ድብደባ ፣ ዘረፋ ፣ ንብረት ማውደም ፣ የሲቪል ተቋማት በጤና ፣ በትምህርት ተቋማት ላይ ውድመት እንደደረሰ በርካታ ምስክሮች ገልጸዋል።
ሌላው የሰብዓዊ መብት ችግር በፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ምክንያት በርካታ ፖለቲከኞች የምክር ቤት አባላትን ጨምሮ ታስረዋል።
ከዚህ ባለፈ ጋዜጠኞች፣ አንቂዎች፣ አጠቃላይ ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት በተለይ በአማራ ክልል አማራዎች በጅምላ ለወራት በእስር እየማቀቁ ይገኛሉ።
የምክር ቤት አባላትን ስናነሳ የምክር ቤት አባላችን አቶ ክርስቲያን ታደለ የመንግስት ወጪ አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆኖ መንግስትን ከምዝበራ ያዳነ በሰላማዊ ትግልም በእጅጉ የሚያምን ሰው ነው አንድ አመት ለሚሞላ ጊዜ በእስር እየማቀቀ ያለው።
ሌሎችም በለውጡ ከእርሶ ጋር አብረው የሰሩ እንደ አቶ ዮሐንስ ቧያለው ፣ ዶ/ር ካሳው ተሻገርና አቶ ታዬ ደንደአ ያሉም ለውጡ ስህተት ፈጽሟል በትክክለኛው ጎዳና እየሄደ አይደለም ብለው ስለሞገቱ ብቻ ለወራት ታስረዋል።
ከዚህ የከፋው ግን የት እንኳን እንደታሰረ የማይታወቅ አንድ የአብን አባላችን ነው ሀብታሙ በላይነህ ይባላል።
ሀብታሙ በላይነህ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባል እና የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል ነው። እንዲሁም የሁለተኛ ደረጃ መምህር ነው። ላለፉት 4 ወራት የት እንደገባ አይታወቅም። ይህን ጉዳይ ቤተሰቡም እኔም ለተለያየ የመንግስት ኃላፊዎች አቤት ብለናል ምላሽ አላገኘንም። ዛሬ እርሶ ምላሽ ይሰጡናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን፤ እንማጸናለን።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ልክ እንዳበቃ ህጋዊ አሰራሩ ይቀጥላል ብለን እንገምት ነበር ነገር ግን አዋጁ አብቅቶ በኮማንድ ፖስቱ እየተዳደርን ያለበት ሁኔታ ነው ያለው።
የጅምላ እስር አሁንም አለ፣ ህገመንግስቱ በትክክል እየሰራ አይደለም። በደረቅ ወንጀል የተከሰሱ ሰዎች ብቻ መጠየቅ ሲገባቸው አሁንም በፖለቲካ አመለካከታቸው ዜጎች በእስር እየማቀቁ ይገኛሉ።
ስለዚህ ህብረተሰቡ ስለ ሽግግር ፍትህና ስለ ሀገራዊ ምክክር መንግስት ሲያወራ ይመነው ? እምነት አልገነባንም።
በጅምላ የታሰሩ፣ የህሊና እስረኞች ቢፈቱ፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን መርምረው አጥፊዎች ተጠያቂ እዲሆኑ ቢደረግ ያኔ እምነት መገንባት ይቻላል።
መንግስት ምን እቅድ አለው እምነት ለመገንባት ? የህሊና እስረኞችን ለመፍታት እና የጅምላ ግድያና ሌሎች ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማቆም ምን ወስኗል ? "
#TikvahEthiopia

👏1.51K❤205😡47🤔22🕊22🙏21😱19😢18😭17🥰12
ተጨማሪ በጀት ለፓርላማ ሊቀርብ ነው።
የኢትዮጵያ መንግስት ከዓለም አቀፍ አበዳሪ ድርጅቶች ያገኘውን ድጋፍ እና ብድር የያዘ ተጨማሪ በጀት በቅርቡ ለፓርላማ አቅርቦ እንደሚያስጸድቅ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ተናግረዋል።
ይህ የተናገሩት ዛሬ በነበረው የምክር ቤቱ አስቸኳይ ስብሰባ ወቅት ነው።
ተጨማሪ በጀቱ ፦
➡️ ለዝቅተኛ ተከፋይ የመንግስት ሰራተኞች ለሚደረግ የደመወዝ ጭማሪ፣
➡️ ለነዳጅ ድጎማ፣
➡️ ለዘይት ድጎማ፣
➡️ ለማዳበሪያ እና መድኃኒት ድጎማ የሚውል መሆኑን ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።
ፎቶ፦ ፋይል
#EthiopianInsider #HoPR #Ethiopia

😡878❤333😭135🙏131🥰44🤔39👏38😢27🕊19😱10
TIKVAH-ETHIOPIA
ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ሹመት ሰጥተዋል። በቅርቡ ፕሬዜዳንት ሆነው በተሰየሙት አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ምትክ የፍትሕ ሚኒስትሩን ጌዴዮን ጢሞቲዮስን (ዶ/ር) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አድርገው ሾመዋቸዋል። የኢትያጵ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩትን ሃና አርዓያስላሴን ደግሞ የፍትህ ሚኒስትር አድርገው ሹመዋል። በተጨማሪም ፥ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴዔታ…
#HoPR
የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ እያካሄደው በሚገኘው 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ የ5 ሚኒስትሮችን ሹመት በአብላጫ ድምጽ አጸድቋል።
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለከፍተኛ የመንግሥት ሃላፊነት ቦታዎች ሹመት እንፀድቅላቸው በደብዳቤ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ነው ሹመቱ በምክር ቤቱ እንዲጸድቅ የተደረገው።
ሹመታቸው የፀደቀው ፦
- የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጤሞቲዎስ(ዶ/ር)፣
- የፍትሕ ሚኒስትር ሃና አርዓያ ሥላሴ፣
- የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)፣
- የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ
- የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ናቸው፡፡
ምክር ቤቱ ሹመቱን በአንድ ተቃውሞ፣ በሁለት ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ አጽድቀዋል።

😡542❤92🙏31🤔30🕊23😭23😱14👏10🥰4😢3
#HopR
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ነው።
በስብሰባው ላይ የምክር ቤት አባላት ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም ለህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቅርበዋል።
አሁን ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጥያቄዎቹ ላይ ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።

😡484🥰64❤42🕊23😢18😱11🙏11🤔6😭1
" ለፕሮጀክቱ ግንባታ ከኩፖን እና ከቶንቦላ ትኬት አጠቃላይ 23.7 ሚሊዮን ብር ቢሸጥም ባንክ አልገባም " - የፌደራል ዋና ኦዲተር
የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የወሎ ተሪሸሪ ኬር የህክምናና ማስተማሪያ ሆስፒታል ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ከወሎ ዩኒቨርስቲ የሥራ ሀላፊዎች፣ ከፌደራል ኦዲተር መስሪያ ቤት እና ከተሪሸሪው የቦርድ አባላት ጋር በመሆን ከህብረተሰቡ የተሰበሰበውን ገንዘብ በማስመልከት በኦዲት ግኝት ዙሪያ ውይይት አድርጓል።
ቋሚ ኮሚቴው ምን አለ ?
⚫ ለወሎ ተርሸሪ ኬር የህክምናና የማስተማሪያ ሆስፒታል ፕሮጀክት ግንባታ የሚውል በየክልሎች ፣በውጭ ሀገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ኢምባሲዎች እና ቆንፅላ ጽ/ቤቶች በኩል ይሸጣል ተብሎ የተሰራጨው 9.3 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የኩፖን ትኬት ጠፍቷል። የሥራ አመራር ቦርዱ አጠቃላይ 17 ሚሊዮን የእዳ ሥረዛ ማድረጉ በኦዲት ሪፖርት ተረጋግጧል።
⚫ በህብረተሰቡ ተነሳሽነት የተሰበሰበው ገንዘብ ያለ አግባብ ሲባክንና ለፕሮጀክቱ ለታለመለት ዓላማ ሳይውል መቅረቱ ተገቢ አይደለም።
⚫ ሆስፒታሉ ሁሉም ኢትዮጵያዊና ለምስራቅ አፍሪካ ተስፋ ለነበረው ፕሮጀክት የሚሆን በኢምባሲዎች የተበታተነው የሎተሪ ዕጣዎችም የት እንደደረሱ አልታወቀም።
⚫ የኦዲት ግኝቱ መነሻ ህዝቡ ያነሳው ቅሬታ ስለሆነ ተጠያቂ መሆን ያለበት አካል መጠየቅ አለበት።
⚫ እስካሁን ባንክ ያልገባው ገንዘብ በማን እጅ እንዳለና ለምንስ ባንክ ገቢ እንዳልተደረገ እንዲሁም የተሸጡ ትኬቶችና ቦንዶች ባንክ ገቢ አልተደረጉም።
⚫ የሲቪል ማህበራት እንደገና ሲቋቋም ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ እንደገና መመዝገብ ቢኖርበትም አልተመዘገበም። ወሎ ዩኒቨርስቲ የተሰጠውን ስልጣንና ተግባራት በቦርዱ የተወሰነውን ውሳኔዎችን መቀበል አለበት።
⚫ ቦርዱ ውሳኔ ከወሰነ በኋላ የህዝብ ገንዘብ ወጪ እያደረገ ነበር። ቦርዱ ስልጣን ሳይኖረው 17 ሚሊዮን ብር የእዳ ስረዛ አድርጓል። የተወሳሰቡ ችግርች ናቸው ያሉት።
የፌደራል ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሰረት ዳምጤ ምን አሉ ?
🔴 ለፕሮጀክቱ ግንባታ ከኩፖን እና ከቶንቦላ ትኬት አጠቃላይ 23.7 ሚሊዮን ብር ቢሸጥም ባንክ አልገባም። ቦርዱ የመሰረዝ ስልጣን ሳይኖረው 11.1 ሚሊዮን የሚጠጉ የኩፖን ትኬቶችን የጠፉ በሚል ሰርዟል።
🔴 ባንክ ያልገባው ገንዘብ ለማን እንደተሰጠ ስለሚታወቅ ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ከሚፈልገው አካል ጋር በመሆን ገንዘቡን ለህዝቡ ይፋ ለማድረግ ወደ ባንክ መግባት አለበት።
🔴 ከ2010 ዓ.ም. እስከ 2016 ዓ.ም. የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከፕሮጀክቱ 9.1 ሚሊዮን ለተለያዩ የሥራ ማስኬጃዎች ተብሎ የወጣ ገንዘብ አለ ይህ መውጣት አልነበረበትም።
የፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ሚናስ ህሩይ ምን አሉ ?
🟠 ለፕሮጀክቱ የታቀደው ገንዘብ 3.5 ቢሊዮን ብር ነበር። የተሰበሰበው ግን 50 ሚሊዮን ብር ብቻ ነው።
🟠 በተለያዩ አካባቢዎች የተበተነው የተንቦላ ሎተሪ ገንዘብ በቸልተኝነት ተረስቷል። ቀጣይ አቅማችን በሚችለው መንገድ ለማስመለስ እንሰራለን። #HoPR

1🤔229❤124😡80😢32😱27😭23🕊15👏13🙏8🥰5
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሹመት : የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ መሐመድ እድሪስ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ አቶ መሐመድ እድሪስን የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አድርገው ሾመዋቸዋል። @tikvahethiopia
#ሹመት : ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሹመትን አስመልክቶ የቀረበለትን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ በአንድ ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።
በዚሁ መሠረት ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል።
ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) ማናቸው ?
➡️ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የስትራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን እና አለምአቀፋዊነት ጽህፈት ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ሲሰሩ ቆይተዋል።
➡️ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በጋዜጠኝነት እና ተግባቦት የትምህርት ዘርፍ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አግኝተዋል።
➡️ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተማሩበት የትምህርት ክፍል በአስተማሪነት አገልግለዋል።
➡️ በውጭ ቋንቋዎች የማስተርስ ዲግሪ ባገኙበት አምቦ ዩኒቨርስቲ እና በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ አስተምረዋል።
➡️ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ12 ዓመታት የማስተማር እና የአመራርነት ልምድ አለቸው።
➡️ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ከደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርስቲ (UNISA) በኮሚዩኒኬሽን አግኝተዋል።
➡️ በተለያዩ የምርምር ህትመቶች ላይ የወጡ ጽሁፎችን በግላቸው እና በጋራ አሳትመዋል።
➡️ በብሉምበርግ የአፍሪካ ሚዲያ ኢኒሼቴቭ ስር የሚሰጠውን የፋይናንስ ጋዜጠኝነት ስልጠናን በስራ አስኪያጅነት መርተዋል በሌሎች ተቋማትም በማማከር ስራዎች ተሳትፈዋል።
#HoPR #EthiopiaInsider

❤546🤔118😡78🙏69👏64😭29🕊27🥰16😱14😢11
" ተቋሙ የተገኘበትን የኦዲት ግኝት ማስተካከያ ለማድረግ ዝግጁነት የለውም " - የፌዴራል ዋና ኦዲተር
🚨 " ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ የበጀት ጉድለት ተገኝቶበታል !! "
" የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አላግባብ የህዝብና የመንግሥት ሀብት እንዲባክን አድርጓል " ሲል በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሰታወቀ።
ቋሚ ኮሚቴው ይህን ያለው የሚኒስቴሩን የፕሮጀክት ውልና የሰው ሀብት አስተዳደር አፈፃፀም የክዋኔ ሪፖርትን በገመገመበት ወቅት ነው።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የሺመቤት ደምሴ (ዶ/ር) ፤ " ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚያከናውናቸው ፕሮጀክቶች ወደ ትግበራ ከመግባታቸው በፊት የቅድመ አዋጭነት ጥናት ግምገማ ተደርጎላቸው እንዲከናወኑ አልተደረገም " ብለዋል።
" በመንግሥት በጀትና በዓለም አቀፍ ድጋፍና ብድር የሚከናወኑ ፕሮጀክቶች የትግበራ ቅደም ተከተል ተሰጥቷቸው ለምክረ ሀሳብ ለሚመለከታቸው አካለት አለማቅረቡ ተገቢነት የሌለው ነው " ሲሉ ገልፀዋል።
በተያዘላቸው ጊዜ ያላለቁ ፕሮጀክቶች ወቅታዊ ሁኔታ የማይታወቅ ሲሆን፣ የፋይናንስና የፊዚካል አፈፃፀማቸው የተስማሚነት ችግር እንዳለበት አሳውቀዋል።
በተጨማሪም ፕሮጀክቶች ሳይጠናቀቁ አቋርጦ በጀቱን ወደ ሌላ ፕሮጀክት የማዘዋወር ሂደት ረገድ የህግ፣ የመመሪያ፣ የአሰራር ጥሰት የታየበት በመሆኑ ሊታረም እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
" ለትራንስፖርት ኪራይ፣ ለዳታ ማዕከል ግንባታ፣ ለሳይንስ ካፌና ለሰራተኛ ደሞዝ ያለአግባብ የወጣውን ወጪ ኦዲት በማድረግ በ15 ቀናት ውስጥ ለቋሚ ኮሚቴው ሪፖርት እንዲያደርግ " ሲሉም አሳስበዋል።
ከሰው ሀብት ጋር ተያይዞም መስሪያ ቤቱ ሰራተኞችን #በሪኮመንዴሽን_የሚቀጥርበት ሁኔታ ህግና ስርዓት ያልተከተለ በመሆኑ ሰራተኞችን አወዳድሮ ሊቀጥርና አሰራሩ ሊታረም እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ከንብረት ማስመለስ ጋር በተያያዘም ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የለቀቁና ጡረታ የወጡ ሰራተኞች ያልመለሷቸውን በጥቅል ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውን የመንግስትና የህዝብ ሀብት በአግባቡ የማስመለስ ስራ መስራት አለበት ብለዋል፡፡
በተጨማሪም ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ የበጀት ጉድለት እንደተገኘበት በማመልከት የአሰራር ሂደቶችን በማረምና ለጉድለቱ መንስኤ የሆኑ ግለሰቦችን የህግ ተጠያቂ በማድረግ ለምክር ቤቱ እንዲያሳውቅ ቋሚ ኮሚቴው አሳስቧል።
የፌዴራል ዋና ኦዲተር ወይዘሮ መሰረት ደምጤ ፤ " ተቋሙ የተገኘበትን የኦዲት ግኝት ማስተካከያ ለማድረግ ዝግጁነት የለውም " ሲሉ ተናግረዋል።
" ተጀምሮ ላልተጠናቀቀ ፕሮጀክት ገንዘብ ወጪ ተደርጓል " ብለዋል።
" የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሰው ሀብትና የንብረት አስተዳደር ሂደቱ ደካማ ነው " ብለው " ከህግ አግባብ ውጪ የተከፈሉ ክፍያዎች ላይ በፍጥነት የእርምት እርምጃ መውሰድ ይጠበቅበታል " ሲሉ ተናግረዋል።
በኦዲት ክፍተቶች ላይ የፌዴራል ፀረ ሙስና ኮሚሽን ክትትል በማድረግ የህግ ተጠያቂነት ማስፈን እንደሚጠበቅበት ተመላክቷታ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ምን መለሱ ?
በለጠ (ዶ/ር) ፤ " ተቋሙ የሚሰራቸው ሥራዎች ዘርፈ ብዙ በመሆናቸው በአንዳንድ ዘርፎች የኦዲት ጉድለት ተከስቷል " ሲሉ ተደምጠዋል።
" ችግሮቹን ለመፍታት የድርጊት መርሐግብር በማዘጋጀት የተወሰዱ እርምጃዎችን ለቋሚ ኮሚቴው እናቀርባለን " ብለዋል።
" ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025ን ተግባራዊ ለማድረግ ከዓለም ባንክና ከአጋር አካለት ጋር የሚሰሩ ሥራዎች በአይነትና በቁጥር በርካታ ናቸው " ያሉት ሚኒስትሩ " የተስተዋሉ የኦዲት ክፍተቶችን ለማረም ዝግጁ ነን " ብለዋል። #EPA #HoPR

🙏278❤169😡101🤔74😭52😱39👏25💔21🕊12🥰8😢6
#HoPR : ዛሬ የፌዴራል መንግሥት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት የሚያሻሽለው አዋጅ ፀድቋል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 22ኛ መደበኛ ስብሰባ የፌዴራል መንግሥት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት ለመደንገግ የወጣ የማሻሻያ አዋጅን መርምሮ አጽድቋል።
አዋጁ እስከ አሁን በሥራ ላይ የነበረውን አዋጅ ቁጥር 359/ 1995 የሚያሻሽል ሲሆን፤ አዋጅ ቁጥር 1373/2017 ሆኖ በሁለት ድምጸ ተዐቅቦ በአብለጫ ድምፅ ጸድቋል፡፡
አዋጁ የክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን የቆይታ ጊዜ የማራዘም ስልጣን፤ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሚሰጥ ነው።
አዋጁ የፌደራል መንግስት በክልሎች የሚያቋቁመውን ጊዜያዊ አስተዳደር የስራ ዘመን ለሁለት ጊዜ የማራዘም ስልጣን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሚሰጥ ነው።
የአፈ ጉባኤው ውሳኔ በፌዴሬሽን ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ተቀባይነት ካላገኘ፤ ጊዜያዊ አስተዳደር በተቋቋመበት ክልል " በአራት ወራት ጊዜ ውስጥ ምርጫ እንዲደረግ " ያስገድዳል።
ይህ አዋጅ የፌዴራል መንግስት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን ስርአት ለመደንገግ በ1995 ዓ.ም የወጣውን አዋጅ ያሻሻለ ነው።

🤔338❤171😡91🕊34👏26😭25🙏15🥰13💔11
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ #ረቂቅአዋጅ የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ መሬትን በሊዝ በባለቤትነት መያዝ የሚያስችላቸው የአዋጅ ረቂቅ ነገ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይቀርባል። የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ የማይንቀሳቀስ ንብረት " ባለቤት ' ወይም " ባለይዞታ " የሚሆኑበትን አግባብ ለመደንገግ የወጣው ይህ " የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ የመኖሪያ ቤት ባለቤት የሚሆኑበት " ወይም " ለመኖሪያ ቤት ግንባታ የሚውል መሬት የሚያገኙበትን…
#Ethiopia
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ሀገር ዜጎች የማይንቀሳቀስ የመኖሪያ ቤት ባለቤት የመሆን መብት አዋጅን አጽድቋል።
በምክር ቤቱ የከተማ፣ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ " መሬት የመንግስት እና የህዝብ እንደመሆኑ ለኢንቨስትመንት የሚመጡ ዜጎች መሬቱን የመሸጥ እና የመለወጥ መብት የላቸውም " ብሏል።
የኢትዮጵያዊያንን መብት በማይነካ መልኩ የውጭ ሀገር ዜጎች የመኖርያ ቤት ባለቤት በመሆን ኢንቨስትመንት ላይ እንዲሰማሩ ሥራዎች ይሰራሉ ሲል ገልጷል።
የውጭ ሀገር ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በመኖሪያ ቤት ባለቤትነት ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የተቀመጠው የገንዘብ መጠን 150 ሺህ ዶላር ነው።
የተቀመጠው የገንዘብ መጠን 150 ሺህ ዶላር ሲሆን በጊዜ ሂደት እየተሻሻለ ይሄዳል ተብሏል። #HoPR #FMC

❤423😭197😡164🤔21😱14🕊13😢8💔8🙏3🥰2
#HoPR🇪🇹
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ነገ ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግስታቸውን የ2017 የዕቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡም ይጠበቃል።
በተጨማሪም የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የፌዴራል መንግሥት የ2018 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀትን እንደሚያፀድቅ ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ጉባኤው ከጥዋት 2:30 ጀምሮ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን በቀጥታ ይሰራጫል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😡888❤483😭41🙏25🤔23👏18🥰15💔15🕊13😱9😢3
TIKVAH-ETHIOPIA
#HoPR🇪🇹 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ነገ ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግስታቸውን የ2017 የዕቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡም ይጠበቃል። በተጨማሪም የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የፌዴራል መንግሥት የ2018 በጀት ዓመት ረቂቅ…
#HoPR🇪🇹
" የኑሮ ውድነት እና የዋጋ ግሽበት ከፍተኛ ጫና እያሳደረባቸው ካሉ የህብረተሰብ ክፍሎች የመንግሥት ሰራተኛው ግንባር ቀደም ነው ! " - የምክር ቤት አባል
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተዋል።
የምክር ቤቱ አባላትም ጥያቄያቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እያቀረቡ ይገኛሉ።
እስካሁን ከቀረቡ ጥያቄዎች መካከል ከኑሮ ውድነት፣ ከመንግሥት ሰራተኞች ፣ ጤና ባለሙያዎች እና መምህራን የደመወዝ ጭማሪ ጋር የተያያዘ ጥያቄ ይገኝበታል።
ጥያቄው የቀረበው በምክር ቤት አባሉ አቶ ግዛቸው አየለ ነው።
ምን አሉ ?
" የኑሮ ውድነት እና የዋጋ ግሽበት ከፍተኛ ጫና እያሳደረባቸው ካሉ የህብረተሰብ ክፍሎች የመንግሥት ሰራተኛው በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል።
በዚህ ምክንያት የጤና ባለሙያዎችን እና መምህራንን ጨምሮ የተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ የመንግሥት ሰራተኞች የደመወዝ ማሻሻያ እንዲደረግ ጥያቄ እያነሱ ይገኛሉ።
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር የመንግሥት ሰራተኛን የኑሮ ደረጃ ከማሻሻል አኳያ በመንግሥት ምላሽ ዙሪያ ማብራሪያ ቢሰጥበት።
በተጨማሪ መንግሥት የዜጎችን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ እንዳለ ይታወቃል ይሁን እንጂ ካለው የቤት ፈላጊ ቁጥር ጋር ተነጻጽሮ ሲታይ ገና ብዙ ስራ ይጠይቃል። መንግሥት በአጭር፣ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ በከተሞች የሚታየውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት ምን እየሰራ ይገኛል ? " ሲሉ ጠይቀዋል።
የምክር ቤቱ ስብሰባ በብሔራዊ ቴሌቪዥን ቀጥታ እየተላለፈ ይገኛል።
በተጨማሪ በምክር ቤቱ የዩትዩብ ገጽ መከታተል ይቻላል ፦ https://www.youtube.com/live/yLIns-2_vZM?feature=shared

❤797🙏78😡53😭28🤔20👏11😱6😢6🥰5
TIKVAH-ETHIOPIA
#HoPR🇪🇹 " የኑሮ ውድነት እና የዋጋ ግሽበት ከፍተኛ ጫና እያሳደረባቸው ካሉ የህብረተሰብ ክፍሎች የመንግሥት ሰራተኛው ግንባር ቀደም ነው ! " - የምክር ቤት አባል የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተዋል። የምክር ቤቱ አባላትም ጥያቄያቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እያቀረቡ ይገኛሉ። እስካሁን ከቀረቡ ጥያቄዎች መካከል ከኑሮ ውድነት፣ ከመንግሥት ሰራተኞች…
#HoPR🇪🇹
" በዝቋላ አቦና በተለያዩ ገዳማት ምንም መሳሪያ ያልታጠቁ መናኞች እና የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን ከሞት እና ከድብደባ ለመታደግ አግባብ ያለው የጸጥታ ሃይል የማይመድበው ለምንድነው ? " - የምክር ቤት አባሉ አበባው ደሳለው (ዶ/ር)
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉና አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አባሉ አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን ምን ጠየቁ ?
አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ፦
" የመንግሥት ሰራተኞች እና ዝቅተኛው የማህበረሰብ ክፍል በተደጋጋሚ በአሁን ሰዓት ያለውን የኑሮ ውድነት መቋቋም እንዳቃታቸው ይገልጻሉ።
እንደመገለጫም ፦
- እራሳቸውን እና ቤተሰባቸውን አብልቶ ማሳደር
- የቤት ኪራይ መክፈል
- የልብስ እና የትምህርት ወጪዎችን መሸፈን ዳገት እንደሆነባቸው ይዘረዝራሉ።
ከዚህ ጋር በተገናኘ የህክምና ባለሙያዎች የስራ ማቆም አድማ በማድረግ መሰረታዊ የዳቦ ጥያቄያቸው እንዲፈታ ጠይቀዋል። ሆኖም ግን መንግሥት ይህንን መሰረታዊ ጥያቄ የፖለቲካ ስም በመስጠት ጥያቄያቸው ሳይፈታ ተዳፍኖ ቀርቷል።
ለመሆኑ መንግሥት ' ድሃ ተኮር ኢኮኖሚ ሪፎርም አራማጅ ነኝ ' እያለ የመንግሥት ሰራተኛውን እና ዝቅተኛውን የማህበረሰብ ክፍሎችን ኑሮ ለማሻሻል ስራ የሚጀምረው መቼ ነው ?
ከዚህ ጋር በተገናኘ አጠቃላይ የኢኮኖሚው አካሄድ ላይ ጥያቄ ይነሳበታል። የኢኮኖሚክ ባላንሱ ችግር እንዳለበት ይነሳል። የተለያየ ጥረት እየተደረገ ነው inflation (የዋጋ ግሽበት) ለመቀነስ ግን IMF እኛን የሚደግፍ ኢኮኖሚክ ሪፎርሙን፣ ዓለም ባንክ ፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን ሳይቀር በጣም ፈተናዎች እንዳሉ ከኢኮኖሚክ ሪፎርሙ ጋር በተያያዘ ይገልጻሉ። ለምሳሌ ፦
° ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት እንዳለ፣
° ገበያ ተኮር ምንዛሬ በመጠቀማችን ምክንያት የብር ዶላር ልዩነት ከፍተኛ መሆኑ፣
° በህዝብ ስም የተበደርነው ዕዳ እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ፣
° ከፍተኛ ስራ አጥነት እንዳለ በአሁን ሰዓት በየአመቱ 2 ሚሊዮን ስራ አጦች እንደሚቀላቀሉ ይገለጻልና ይሄንን ችግር እንዴት ነው የምንፈታው በተለመደው አዙሪት ውስጥ ነው ወይ የምንቀጥለው ? ከኢኮኖሚ ችግሩ ለመውጣት ምን የታሰበ ነገር አለ ?
ሁለተኛ በዝቋላ አቦና በተለያዩ ገዳማት ምንም ጦር መሳሪያ ያልታጠቁ የሰማይ ቤትን ታሳቢ ያደረጉ መናኞች ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት እየተፈጸመ ለሞት፣ ለድብደባ እና እንግልት ሲዳረጉ ይታያል። ለመሆኑ መንግሥት እንደዚህ ያለ ተደጋጋሚ የንጹሃን የቤተክርስቲያን አገልጋዮችን ከሞት ፣ ከድብደባና እንግልት ለመታደግ አግባብ ያለው የጸጥታ ኃይል የማይመድበው ለምንድነው ?
ሶስተኛ መንግሥት ከፋኖ ፣ ከሸኔና ሌሎች የታጠቁ ኃይሎች ጋር ያለው የጸጥታ ችግር በድርድር እንዲፈታ ፣ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ (ከፖለቲካ እስረኞች ጋር ለተገናኘ በተደጋጋሚ ያቀረብነው ጥያቄ ነው) ጅምላ ጭፍጨፋ የመሩ የህወሓት ባለስልጣናት በቶሎ ነበር የተፈቱት ነገር ግን እንደዚህ አይነት ተሳትፎ (involvement) የሌላቸው የአማራ ፖለቲከኞች ፣ አንቂዎች፣ ጋዜጠኞች ከታሰሩ 2 ዓመት ሞልቷቸዋል።
የፍትህ ስርዓቱ በጣም ዘገምተኛ ነው፤ ቶሎ እየተፈታ አይደለም ፤ ምንም ምስክርም እየተሰማባቸው አይደለም በጄኖሳይድ ወይም በጦርነቱ ቀጥተኛ ተሳታፊ እንደሆኑ የሚያመለክት ነገር የለም ግን በእስር ቤት እየተሰቃዩ ይገኛሉ። አማራ ክልል ብቻ አይደለም ኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከተለያዩ የምክር ቤት አባላት ጋር ባደረግነው ንግግር እንደዚህ አይነት ተመሳሳይ ችግር አለ። ቶሎ ፍትህ የማግኘት ችግርን በኢትዮጵያ መቼ ነው የምንቀርፈው ? የረፈደ ፍትህ እንደተነፈገ ይቆጠራልነውና።
ሌላው ድሮንን ጨምሮ በሌሎች ከባድ መሳሪያዎች ጭምር ንጹሃን እንዳይጠፉ የምክር ቤት አባላት፣ የሰብዓዊ መብት ተቋማት ፣ኃያላን መንግሥታት አሜሪካን ጨምሮ ስንወተውት ቆይተናል። የተለያዩ መግለጫዎች ኃያላን መንግሥታት ጭምር ሲያወጡ ይታያል። ሆኖም ግን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተለይም በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ የመሳሰሉ ክልሎች ላይ የጸጥታ ችግሩ እስካሁን አልተቀረፈም።
ከዚህ ጋር በተገናኘ ' አግዙን ' ባሉን መሰረትም ሰላሙን ለማምጣት ወደ እርሶ ቢሮ መልዕክተኛ ብንልክም አልተሳካልንም። እንጂ እኛ ፖለቲከኞች፣ ተቃዋሚዎች ችግር መፍጠር ሳይሆን ችግሩ እንዲፈታ ቀረብ ብለን መነጋገር እንፈልጋለን ነገር ግን ያን መድረክ ልናገኝ አልቻልንም። ከዚህ ጋር በተገናኘ ምን የሚሉን ነገር አለ ሰላሙን ለማምጣት።
አራተኛ በተለያዩ አዲስ አበባ አካባቢዎች በሌሎች ትላልቅ የክልል ከተሞች ላይም ይሄ ችግር አለ ከ1998 ዓ/ም ጀምሮ መኖሪያ ቤት ሰርተው ፣ ውሃና መብራት አስገብተው፣ በርካታ የልማት ስራዎችን የሰሩ፣ መንግሥትዎን በድጋፍ ያገለገሉ ዜጎችን ያለምንም ምትክ ቤት ፣ መሬትና የገንዘብ ካሳ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው አቤቱታቸውን ይዘው የተለያዩ ቢሮዎች ቢሄዱም ጥያቄያቸው ውድቅ ሆኗል።
እነዚህ ሰዎች የሚያመለክተት ' ነገር ከ1998 ጀምሮ ነው ህገወጥ ከሆንን እናፍርስና በኮንዶሚኒየም እንደራጅ ' ስንል አይ ' እናተ ሰነድ አልባ ናችሁ እንጂ ህገወጥ አይደላችሁም በቅርቡ ህጋዊ እናደርጋችኃለን ' ተብለው እንደነበር ነው የሚያስታውሱት። በቅርቡ ያወጣነው አዋጅ አለ ከከተማ መሬት ጋር በተገናኘ ከ2004 ዓ/ም በፊት የተሰሩ ህገወጥ ቤቶች ህጋዊ እንደሚሆኑ የሚያመለክትና እነዚህን ሰዎች ለምድንነው በአግባቡ የማይስተናገዱት። የተለያዩ ቢሮዎች ሄደዋል አልተሳካላቸውም። በመጨረሻም እርሶን እንድጠይቅላቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ከሁለት ቀበሌ የተፈናቀሉ ከሰነድ ጋር ነው ያቀረቡልኝ። አመሰግናለሁ። "
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

2❤2.24K👏267🙏97😭35😡21🤔14🥰11🕊11😢8😱4
TIKVAH-ETHIOPIA
#EthiopianAirlines🇪🇹 የአፍሪካ ግዙፉ አየር መንገድ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዚህ ዓመት ተጨማሪ 13 አውሮፕላኖችን መግዛቱን ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ። አሁን ላይ አየር መንገዱ ያሉት አውሮፕላኖች ብዛት 180 መድረሱን ጠቁመዋል። በተመሳሳይ በዚህ ዓመት ብቻ 6 አዳዲስ መዳረሻዎችን በመጨመር አጠቃላይ መዳረሻውን ወደ 136 ከፍ ማድረጉን ገልጸዋል። አየር መንገዱ በዚህ…
#HoPR🇪🇹
" 3.5 ቢሊየን ዶላር ከዚህ ቀደም የነበሩ መንግስታት የተበደሩትን ገንዘብ ያለፉትን ሶስት እና አራት አመታት ተደራድረን የእዳ ሽግሽግ እንዲኖር አድርገናል የገንዘብ ሚንስቴር በትላንትናው እለት በፈረንሳይ ተፈራርሟል" - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከምክር ቤት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ።
የበጀት አመቱን አፈጻጸም በየዘርፉ አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግብርና ፣ በኢንዱስትሪ ፣በፋይናንስ እና በቱሪዝም ዘርፍ ተመዘገቡ ያሏቸውን ለውጦች ተናግረዋል።
በዚህም መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባነፈው አመት የ8.1 በመቶ እድገት ኢትዮጵያ ማስመዝገቧን በመግለጽ ዘንድሮ 8.4 በመቶ እድገት ለማስመዝገብ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል።
ጠቅላይ ሚንስትሩ በየዘርፉ አስመዘገብናቸው ስሏሏቸው ለውጦች ምን አሉ ?
ግብርና
- በግብርና ዘርፍ 6.1 በመቶ እድገት እንዲያመጣ ታቅዶ ነው እየተሰራ ያለው።
- ባለፈው አመት 26 ሚሊየን ሄክታር መሬት ማረስ ችለን ነበር ዘንድሮ 31.8 ሚሊየን ሄክታር መሬት ማረስ ተችሏል።
- ባለፈው አመት በሁሉም አይነት የእርሻ ምርቶች 1.2 ቢሊየን ኩንታል ምርት ነበር የሰበሰብነው ዘንድሮ 1.5 ቢሊየን ኩንታል ምርት መሰብሰብ ችለናል ይህም 24.7 በመቶ ጭማሪ አለው።
- ከ100 በላይ አነሰተኛ እና መካከለኛ ግድቦች ይሰራሉ።
- 50 ሺ ሄክታር አሲዳማ መሬት ታክሞ ወደ እርሻ ገብቷል።
ኢንዱስትሪ
° 12.8 በመቶ እድገት እንደሚያመጣ ታስቦ እየተሰራ ነው።
° የኢንዱስትሪው ሴክተር የኢነርጂ ፍላጎት 40 በመቶ ጨምሯል።
° የሲሚንቶ ምርት 6 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።
° የብረት ውጤቶች 18 በመቶ አድጓል።
° የመስታወት ፋብሪካ በቂ አልነበረም በአመት 600 ሺ ቶን የሚያመርት የመስታወት ፋብሪካ እየተሰራ ይገኛል ጥሬ እቃውንም ከሃገር ውስጥ ይጠቀማል ታህሳስ ወይም ጥር ላይ ያልቃል ተብሎ ይጠበቃል።
ማእድን
- ባለፈው አመት 4 ቶን ወርቅ ኤክስፖርት አድርገናል ዘንድሮ 37 ቶን ወርቅ ኤክስፖርት አድርገናል።
- አምና በወርቅ ኤክስፖርት 300 ሚሊየን ዶላር ዘንድሮ 3.5 ቢሊየን ዶላር አግኝተናል።
- ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚቀጥለው አመት የመጀመሪያውን የጋዝ ምርት ለገበያ ታቀርባለች።
- ምክር ቤቱ ከእረፍት ሳይመለስ ኢትዮጵያ የማዳበሪያ ፋብሪካ መስራት ትጀምራለች ከ 40 ወራት በኋላም ግንባታው ይጠናቀቃል።
- የማዕድን ዘርፍ በጋዝ ፣በወርቅ እና በማዳበሪያ የተለያዩ እድገቶችን እያመጣ ነው።
ቱሪዝም
° 1.3 ሚሊየን የውጭ ቱሪስት ኢትዮጵያን ጎብኝቷል።
° ዩኒቲ ፣ፍሬንድ ሺፕ ፣ ፓላሱን እና ሳይንስ ሙዚየምን ብቻ ከ 1.5 ሚሊየን ህዝብ በላይ ጎብኝቶታል ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ ገቢ አግኝተንበታል።
° አየር መንገድ በሃገር ውስጥ እና በውጭ 19 ሚሊየን ህዝብ አጓጉዟል።
ፋይናንስ
- ብድር ከአምና 75 በመቶ ጨምሯል የግሉ ሴክተር 80 በመቶ ድርሻ አላቸው።
- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 900 ቢሊየን ብር እዳ የነበረበት ተቋም ነበር እዳው ከባንኩ ወደ መንግሥት በመዘዋወሩ እና ለባንኩም 700 ሚሊየን ዶላር ድጎማ በመሰጠቱ ተቋሙንም ሆነ ሴክተሩም ማዳን ተችሏል።
- የሞባይል መኒ ተጠቃሚ 55 ሚሊየን ደንበኛ ደርሷል።
- ወደ 11 ሚሊየን ደንበኞች 24.5 ሚሊየን ብር ብድር በሞባይል መኒ አግኝተዋል።
ኤክስፖርት
° 5.1 ቢሊየን ዶላር ከኤክስፖርት ገቢ እናገኛለን ብለን አቅደን 8.2 ቢሊየን ዶላር አግኝተናል።

❤1.04K😡448🤔42🕊18😭17👏11🥰7🙏3💔2
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#HoPR🇪🇹
" ድንጋጌውን ' ትክክል ነው ' ብለው ሲከራከሩ የነበሩ የፓርላማ አባላት ነበሩ፤ ዛሬ ደግሞ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ መደገፋቸው በአንድ ራስ ሁለት ምላስ ያስብላል " - የፓርላማ አባል
በወንጀል የተገኘ ንብረትን ህጋዊ ማስመሰል እንዲሁም ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን " በሽፋን ስር " ሆኖ የመመርመር ኃላፊነት የተሰጠው ሰው፤ " ከግድያ በስተቀር " የሚፈጽማቸውን የወንጀል ድርጊቶች ከተጠያቂነት ነጻ የሚያደርገው ድንጋጌ ተሰረዘ።
ድንጋጌው የተሰረዘው አዋጁ " በሰፊው እንዲተረጎም ስለሚያደርግ " እና በአተገባበሩም ላይ " አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያስከትል ስለሆነ ነው " ተብሏል።
አወዛጋቢው ድንጋጌ ተካትቶ የነበረው፤ በወንጀል የተገኘ ንብረትን ህጋዊ ማስመሰል እንዲሁም ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣ አዋጅ ላይ ነበር።
አዲሱ አዋጅ በፓርላማ የጸደቀው ሰኔ 10፤ 2017 ዓ.ም. ነበር።
የተሰረዘድ ድንጋጌ " በሽፋን ስር የሚደረግ ምርመራ ወይም በቁጥጥር ስር የሚደረግ ማስተላለፍን እንዲያስፈጽም የተመደበ ሰው፤ በግዴታው ላይ እያለ ከአቅሙ በላይ በሆነ ምክንያት እና ከፈቃዱ ውጭ ሆኖ ከግድያ ወንጀል በስተቀር ለሚፈጽመው የወንጀል ድርጊት የወንጀል ክስ አይቀርብበትም " ይላል።
አዋጁ በጸደቀበት ዕለት የውሳኔ ሃሳብ ለፓርላማ አባላት ያቀረበው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚቴ፤ ድንጋጌው እንዲካተት የተደረገው " ልዩ የምርመራ ስራን " " ውጤታማ የሚያደርግ በመሆኑ "ምክንያት እንደሆነ ገልጾ ነበር።
ቋሚ ኮሚቴው " ልዩ የምርመራ ዘዴን " በመጠቀም ስራውን የሚያከናውን ሰው፤ " የህዝብን ጥቅም ለማስጠበቅ የሚሰራ መሆኑን " እንደ ደጋፊ ምክንያት አቅርቦ ነበር።
ይሁንና ቋሚ ኮሚቴው ዛሬ ሰኞ ሰኔ 30 በተደረገ የተወካዮች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባ ላይ፤ ድንጋጌው እንዲሰረዝ የሚያደርግ የውሳኔ ሃሳብ አቅርቧል።
ድንጋጌው " አዋጁ በሰፊው እንዲተረጎም የሚያደርግ እና አተገባበሩ ላይም አሉታዊ ተጽእኖ የሚያስከትል ስለሆነ፤ አዋጁ ለህትመት ያልበቃ እና በሂደት ላይ ያለ በመሆኑ፤ ቀሪ እንዲሆን ይህ የውሳኔ ሀሳብ ቀርቧል " ብሏል።
የውሳኔ ሀሳቡ በአንድ ድምጽ ተዐቅቦ ፀድቋል።
የፓርላማ አባላት ምን አሉ ?
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የፓርላማ ተወካይ አቶ ባርጠማ ፈቃዱ ፦
" አዋጁ ተመልሶ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መምጣቱ የምክር ቤቱን አቅም ጭምር የሚያሳይ ነው።
አዋጁ በሚጸድቅበት ወቅት ድንጋጌውን ' ትክክል ነው ' ብለው ሲከራከሩ የነበሩ የፓርላማ አባላት ነበሩ፤ ዛሬ ደግሞ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ መደገፋቸው በአንድ ራስ ሁለት ያስብላል " ብለዋል።
ሌላ የፓርላማ አባል ፦
" አዋጁ በሚጸድቅበት ጊዜ በድንጋጌው ላይ በመሰረታዊነት ክርክር ተደርጓል። በድንጋጌው ላይ የተለያየ መልክ ያለው ጫጫታ በብዛት ሲሰማ ነበር።
በምርመራ ወቅት የሚመረምረው አካል አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ባለበት ጊዜ፤ ከዚህ ውጪ ሊያደርግ የሚችለው ጉዳይ እንደሌለ፣ ዋስትና ሊያገኝ እንደሚገባ በደንብ ማብራሪያ የተሰጠበት ጉዳይ ነበር።
ድንጋጌው ከአዋጁ ውስጥ እንዲወጣ ሲደረግ፤ መርማሪዎች የተሰጣቸውን ዋስትና የሚያስቀር በመሆኑ ቀድሞ የጸደቀው ባለበት ቢቀጥል ይሻል ነበር።
የሚመረምሩ ሰዎች፣ አደገኛ ችግር ውስጥ ባሉበት ሁኔታ ውስጥ፤ የእዚህ አይነት ዋስትና ሊያገኙ የማይችሉ ካልሆነ ሊመረምሩ ፍቃደኛ ይሆናሉ ወይ? ሊገቡ ፍቃደኛ ይሆናሉ ወይ? የሚመረምሩ ሰዎች አደገኛ ችግር ውስጥ ባሉበት ሁኔታ ውስጥ ዋስትና የማንሰጣቸው ከሆነ፤ እንደዚህ አይነት risk ሊወስድ የሚችል አካል ላይኖር ይችላል። " ብለዋል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ምን አሉ ?
" ለእንደዚህ አይነት የምርመራ ስራዎች ዋስትና የሚሰጥ ህግ አለ። ዋስትና መስጠት እና ሌላ ነገር እንዲያደርግ ማድረግ የተለያየ ነገሮች ናቸው። ድንጋጌው መሰረዙ ተገቢ ነው። "
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገጽ ነው።

❤1.16K🤔118👏58😭31🕊24😡12🥰11💔5😱4😢4🙏2
TIKVAH-ETHIOPIA
" ተቀጣሪው ሰራተኛ በቀን አንድ ጊዜ በልቶ መዋል አልቻለም ምክንያቱም በርካታ ወጪዎች አሉበት ፤ ... ህክምና ሄዶ መታከም የማይችልበት ሁኔታ ላይ ደርሷል !! " - ኢሰማኮ ➡️ " ልማት ያለ ሰው ሰው ያለ ልማት ሊኖሩ አይችሉም !! " 🔴 " የኢትዮጵያ ሰራተኞች ኑሮን አልቻሉም፤ ቋሚ ኮሚቴው ፍቃደኛ ከሆነ ከስራ ሲውጡ ፌስታል ይዘው ሆቴል አካባቢ ቆመው የሚለምኑ ሰራተኞችን አብረን ማየት እንችላለን…
#HoPR🇪🇹
ነገ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ያካሂዳል።
በዚህም ስብሰባ ሰፊ ክርክር ሲካሄድበት ብዙ ሃሳቦች ሲሰነዘሩበት የነበረውን የፌዴራል ገቢ ግብር አዋጅ ያጸድቃል።
ረቂቅ አዋጁ በንግዱ ማህበረሰብና በተቀጣሪ ሠራተኞች ላይ ሊጣል የታሰበው የግብር ምጣኔ ከፍተኛ ነው የሚል ቅሬታ ሲነሳበት ቆይቷል።
አሁን ካለው የኑሮ ውድነትና የዋጋ ንረት አኳያ፣ እስከ 35 በመቶ የሚደርሰው የገቢ ግብር መጠን መቀነስ እንዳለበት ሲጠቆም ነበር።
የገቢ ግብር መነሻው 2,000 ብር ተብሎ የተቀመጠው ዝቅተኛ በመሆኑ መጠኑ ከፍ እንዲል ሲጠየቅ ነበር።
ለአካል ጉዳተኞች የግብር መጠኑ በተለየ መልኩ እንዲቀነስ እና ከተለያዩ የሙያና የንግድ ዘርፎች አንጻር የአዋጁ ድንጋጌዎች በደንብ ታይተው መስተካከል እንዳለባቸው ሲጠየቅ ነበር።
መንግስት ሲሰጥ የነበረዉ ማብራሪያ ደግሞ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ተደርጎ የታክስ ፍትሀዊነትን እና የኢኮኖሚ ልማት እንዲሁም እድገትን ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ የተዘጋጀ እንደሆነ ገልጿል።
ም/ቤቱ ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን እንዲሁም የስታርታፕ ረቂቅ አዋጅን ያፀድቃል።
መረጃው ከህ/ተ/ም/ቤት እና ካፒታል ጋዜጣ የተውጣጣ ነው።

❤594😡208🙏48😭42🤔18🥰4😱4🕊3
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia🇪🇹 በግለሰቦች፣ በብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች መካከል " ስጋት፣ ግጭትን፣ ጥርጣሬን እና አለመተማመንን የሚፈጥር ድርጊት ፈጽሟል " ያለውን የፖለቲካ ፓርቲ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከምዝገባ እንዲሰርዝ ስልጣን የሚሰጥ የአዋጅ ማሻሻያ ለፓርላማ ቀረበ። ቦርዱ የሌላ ፖለቲካ ፓርቲን " ህጋዊ እና ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ያደናቀፈ " የፖለቲካ ፓርቲ ላይ ተመሳሳይ እርምጃ የመውሰድ…
#HoPR🇪🇹
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ እያካሄደ ባለው አስቸኳይ ስብሰባ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነምግባር አዋጅ አጽዷል።
የተሻሻው አዋጅ በቀጣይ ዓመት ለሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ 26 አንቀፆች ላይ ማሻሻያ የተደረገበት ናው ተብሏል።
በተሻሻለው አዋጅ ሀገራዊ የፖለቲካ ፓርቲ ለመሆን የ6 ክልሎችን ድጋፍ ማግኘትን ያስገድዳል።
ምክር ቤቱ አዋጁን በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል።
ምክር ቤቱ በአስቸኳይ ስብሰባው ሰፊ ክርክር ሲነሳበት የነበረውን የፌደራል ገቢ ግብር ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ያጸድቃል ተብሎ እየተጠበቀ ነው።
የስታርት አፕ ረቂቅ አዋጅም ዛሬ ያጸድቃል።
@tikvahethiopia
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ እያካሄደ ባለው አስቸኳይ ስብሰባ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነምግባር አዋጅ አጽዷል።
የተሻሻው አዋጅ በቀጣይ ዓመት ለሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ 26 አንቀፆች ላይ ማሻሻያ የተደረገበት ናው ተብሏል።
በተሻሻለው አዋጅ ሀገራዊ የፖለቲካ ፓርቲ ለመሆን የ6 ክልሎችን ድጋፍ ማግኘትን ያስገድዳል።
ምክር ቤቱ አዋጁን በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል።
ምክር ቤቱ በአስቸኳይ ስብሰባው ሰፊ ክርክር ሲነሳበት የነበረውን የፌደራል ገቢ ግብር ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ያጸድቃል ተብሎ እየተጠበቀ ነው።
የስታርት አፕ ረቂቅ አዋጅም ዛሬ ያጸድቃል።
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😡386❤297🕊41🤔24🙏10😭9
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የፌደራል ገቢ ግብር አዋጅ ፀደቀ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌደራል ገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ አፀደቀ። ረቂቅ አዋጁ በአብላጫ ድምጽ ነው የፀደቀው። ረቂቅ አዋጁ ላይ ሰፊ ክርክር ሲነሳበት እንደነበር ይታወቃል። በተለይ የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማሕበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) ረቂቅ አዋጁ ላይ የደመወዝ ገቢ ግብር መነሻ ተብሎ የተቀመጠው 2,000 ብር ወደ 8…
#ግብር
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱም የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅን በ5 ተቃውሞ፣ በ12 ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ ነው ያፀደቀው።
በሕዝብ ተወካዮች ምር ቤት የፕላን፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ደሳለኝ ወዳጄ የገቢ ግብር አዋጅ ማሻሻያው ከግብር ነጻ የሆነው ከመቀጠር የሚገኘ ገቢ ከፍ እንዲል የተደረገ በመሆኑ ፦
- ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ተቀጣሪዎች ላይ የግብር ጫናው እንደሚቀንስ፤
- የግብር መሰረቱ እንዲሰፋ፤
- መንግስት ከገቢ ግብር የሚያገኘው ገቢ በአንጻራዊ ሁኔታ ከፍ እንዲል አጋዥ መሆኑን አመልክተዋል።
በማሻሻያው ላይ ከበርካታ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እንደተደረገበት እና እንደ ቋሚ ኮሚቴም ሰፊ ጊዜ ተወስዶበት የተዘጋጀ ማሻሻያ ነው ብለዋል።
የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ " ማሻሻያው ለረጅም ጊዜ ውይይት የተደረሀበት እና የሀገራት ልምድ የተወሰደበት ነው። ማሻሻያው ዘመኑን የዋጀ ነው " ሲሉ ተናገረዋል።
አዋጁን የተቃወሙ የምክር ቤት አባላት የገቢ ግብር ማሻሻያው የመንግስት ሠራተኛውን የኑሮ ሁኔታ ታሳቢ ያላደረገ ማሻሻያ በመሆኑ ምክር ቤቱ ማሻሻያውን በድጋሚ እንዲፈትሸው ጠይቀዋል፡፡
የገቢ ግብር አዋጁ ከዚህ ቀደም ሰፊ የክርክር ነጥቦች የተነሳባቸው ጉዳዮች ላይ ማስተካከያ ሳይደረግበት ነው በ5 ተቃውሞ ፣ በ12 ድምጸ ተዓቅዶ በአብላጫ ድምጽ የፀደቀው።
#HoPR🇪🇹
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱም የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅን በ5 ተቃውሞ፣ በ12 ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ ነው ያፀደቀው።
በሕዝብ ተወካዮች ምር ቤት የፕላን፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ደሳለኝ ወዳጄ የገቢ ግብር አዋጅ ማሻሻያው ከግብር ነጻ የሆነው ከመቀጠር የሚገኘ ገቢ ከፍ እንዲል የተደረገ በመሆኑ ፦
- ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ተቀጣሪዎች ላይ የግብር ጫናው እንደሚቀንስ፤
- የግብር መሰረቱ እንዲሰፋ፤
- መንግስት ከገቢ ግብር የሚያገኘው ገቢ በአንጻራዊ ሁኔታ ከፍ እንዲል አጋዥ መሆኑን አመልክተዋል።
በማሻሻያው ላይ ከበርካታ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እንደተደረገበት እና እንደ ቋሚ ኮሚቴም ሰፊ ጊዜ ተወስዶበት የተዘጋጀ ማሻሻያ ነው ብለዋል።
የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ " ማሻሻያው ለረጅም ጊዜ ውይይት የተደረሀበት እና የሀገራት ልምድ የተወሰደበት ነው። ማሻሻያው ዘመኑን የዋጀ ነው " ሲሉ ተናገረዋል።
አዋጁን የተቃወሙ የምክር ቤት አባላት የገቢ ግብር ማሻሻያው የመንግስት ሠራተኛውን የኑሮ ሁኔታ ታሳቢ ያላደረገ ማሻሻያ በመሆኑ ምክር ቤቱ ማሻሻያውን በድጋሚ እንዲፈትሸው ጠይቀዋል፡፡
የገቢ ግብር አዋጁ ከዚህ ቀደም ሰፊ የክርክር ነጥቦች የተነሳባቸው ጉዳዮች ላይ ማስተካከያ ሳይደረግበት ነው በ5 ተቃውሞ ፣ በ12 ድምጸ ተዓቅዶ በአብላጫ ድምጽ የፀደቀው።
#HoPR
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😡1.98K❤792😭282💔87🤔25🕊24👏14🥰13🙏9😱8