#ETEX2025 : ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ ልታዘጋጅ ነው።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በጋራ በመሆን የሚያዘጋጁት ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ (Ethiopian Tech Expo - ETEX 2025) ከግንቦት 8 እስከ 10/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ፣ አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ይካሄዳል፡፡
ዛሬ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በጋራ በመሆን ሁነቱን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ (Ethiopian Tech Expo - ETEX 2025) በ5 ዋና ዋና መስኮች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚካሄድ ይሆናል ተብሏል።
እነዚህም፦
- በሳይበር ደህንነት፣
- በሰው ሰራሽ አስተውሎት(AI)፣
- ፋይናንስ ቴክኖሎጂ (FinTech)፣
- ስማርት ከተማ (Smart City)፣
- በቴክኖሎጂ ትምህርት (Tech Education) ናቸው።
ይህም ከዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ እና ከአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 ጋር ተጣጣሚነት ያለው ተብሏል።
ለሦስት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው በዚህ ኤክስፖ የመጀመሪያው የመክፈቻ ቀን ከሳይበር ደህንነት ጋር የተያያዙ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መርሃ ግብሮች እንደሚከናወኑ ተገልጿጻ።
በሁለተኛው ቀን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዙሪያ ላይ ያተኮሩ መርሃ ግብሮች የሚከናወኑ ይሆናል ተብሏል።
በሦስተኛው ቀን አጠቃላይ ለሕብረተሰቡ ለጉብኝት ክፍት የሚሆን ሲሆን ሌሎች የመዝጊያ መርሃ ግብሮች የሚከናወኑ ይሆናል፡፡
ያንብቡ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-03-26
#INSA #EthiopianArtificialIntelligenceInstitute
@tikvahethiopia

❤158😭52👏27😡24🤔19🕊9🙏4🥰3