" ኦነግ የሚቆም ትግል አልጀመረም ፤ የተቋቋመበትን አላማ ከግብ ሳያደርስ አያቆመም " - አቶ ዳውድ ኢብሳ
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ ) ከ5 ዓመታት ቆይታ በኃላ በአዲስ አበባ የሚገኘውን ጽ/ቤት ዳግም መክፈቱን ተከትሎ ይፋዊ ፕሮግራም በጽ/ቤቱ አካሂዷል።
በወቅቱ መስሪያ ቤቱ ሊዘጋ የቻለው በኦነግ አመራሮች መካከል አለመግባባት በመፈጠሩ ነበር።
ዛሬ በተካሄደው በዚህ የመክፈቻ መርኃግብር ላይ የፖርቲው ሊቀ-መንበር የሆኑት አቶ ዳውድ ኢብሳ ባደረጉት ንግግር " ኦነግ የሚቆም ትግል አልጀመረም፥ የተቋቋመበትን አላማ ከግብ ሳያደርስ አያቆመም " ሲሉ ተናግረዋል።
አቶ ዳውድ በንግግራቸው ኦሮሞ ያካሄደውን ትግል ወደኋላ በመመለስ ያስታወሱ ሲሆን፥ ከሜጫ እና ቱለማ ማኅበር ምስረታ ጀምሮ እስከ ዛሬ ያለው እንቅስቃሴ በሰላም ለሚደረገው ትግል እድል ካለመስጠት የመነጨ መሆኑን ገልጸዋል።
አክለውም ከጓደኞቻቸው ጋር ያለፉበትን ውጣ ውረዶች በመስታወስ " የሚቆም ትግል አልጀመርንም " ያሉ ሲሆን በሰላም መንገድ የመታገል ዕድሉ መስፋት አለበት ሲሉ ጥያቄ አቅርበዋል።
ሊቀመንበሩ ፥ ላለፈው ምርጫ በሚደረግ እንቅስቃሴ አሁን የተመለሰላቸውን ጨምሮ በሌሎች አከባቢዎች ያሉ ቢሮዎቻቸውም እንደተዘጋባቸው አባላቶቻቸው ለእስርና ለእንግልት እንደተጋለጡ በማስታወስ በኋላ ላይም በፓርቲው መሪዎች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ከምርጫው እንዳሶጣቸው ነው የገለጹት።
በነበሩት ጊዜያት ፓርቲያቸው ከኃላፊዎች እስከ አባላት ድረስ ብዙ ስቃይ እንደደረሰባቸው ገልጸዋል ፤ በዚሁ መንገድ ህወታቸውን ያጡ የመኖራቸውንም አመልክተዋል።
እዚህ ላይ አቶ በቴ ኡርጌሳን በማንሳት ተናግረዋል።
አቶ ዳውድ " እስካሁን ድረስ ባልታወቀ አካል ተገድሏል (አቶ በቴ ኡርጌሳ) ፤ በህይወት ባለ ጊዜ ባደረገው ትግል ብዙ ነገር አድርጎልናል " በማለት አመስግነዋል።
አቶ ዳውድ፥ መንግስት በሰላም መንገድ ለሚደረገው ትግል እድል እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።
በተጨማሪም ፥ ዋና መስሪያ ቤታቸውን ለማስመለስ ትልቅ ትግል እንደነበር በማንሳት፣ በዚህ ትግል ውስጥ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ትልቁን ድርሻ እንደተወጡ ተናግረዋል።
ሌሎች ሳይመለስላቸው የቀሩትን የተቋሙ መስሪያ ቤቶች እንዲመለስላቸው በመጠየቅ ሂደት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።
አቶ ዳውድ ኢብሳ ፥ የብሔራዊ ምክክሩን በተመለከት ሁሉን አቀፍ ሀገራዊ ምክክር አስፈላጊ መሆኑን በመጠቆም አሳታፊ ውይይትና ፍትህ የተሞላበት እንዲሆን እየጠየቁ እንደነበርና ያ ሳይሆን ሲቀር መሳተፍ እንደተዉ ተናግረዋል።
#OLF #BBCAfaanOromoo
@tikvahethiopia

❤1.01K😡653🕊54🤔39😢13😭11👏10💔7🥰6😱3