TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ⬇️

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በያዝነው የትምህርት ዘመን ወደ ዩኒቨርሲቲው የሚመጡ ተማሪዎችን #ለመቀበል ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከፊታችን ጥቅምት 10 እስከ 12 ወደ ዩኒቨርሲቲው የሚገቡ ተማሪዎችን ይቀበላል፡፡ ለዚህም ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አረጋግጧል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶር. #ፍሬው_ተገኘ እንደተናገሩት ተማሪዎችን ለመቀበል ሙሉ ዝግጅት ተደርጓል፡፡ ‹‹ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲውን ልክ እንደ ወላጆቻቸው ቤት እንዲቆጥሩት እና በቆይታቸውም እንዲደሰቱ ለማድረግ የበኩላችንን እንወጣለን፤ ወላጆችም ልጆቻቸውን ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲልኩ በአስተማማኝ ሰላም ላይ እንዳሉ ሊሰማቸው ይገባል›› ነው ያሉት፡፡ ‹‹ቃላችን ጠብቀን ተማሪዎችን አስተምረን ወደ ወላጆቻቸው እንመልሳለን›› ብለዋል ዶክተር ፍሬው፡፡

የሀገር ሽማግሌዎች ፣የሀይማኖት አባቶች እና ከማህበረሰቡ የተውጣጡ ግለሰቦች ተማሪዎችን እንደሚቀበሉም በመግለጫው ተመላክቷል፡፡

የባሕር ዳር ከተማ ከንቲባ ሙሉቀን አየሁ ህብረተሰቡ ተማሪዎችን ለመቀበል መዘጋጀቱንና የከተማ አስተዳደሩ ጸጥታውን አስተማማኝ አድርጎ እንደሚያስቀጥል ነው የተናገሩት፡፡

የከተማው ማህበረሰብም ተማሪዎቹን በእንግዳ ተቀባይነት እንዲያስተናግዳቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ምንጭ፦ አ.ብ.መ.ድ.
@tsegabwolde @tikvahethiopia