TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ጥቆማ
(ለሚመለከተው አካል - አዲስ አበባ)

" በሰውና መኪና ላይ ወድቆ ጉዳት እንዳይደርስ መፍትሄ ይፈለግለት ! "

" ይህ በቪድዮው ላይ የምትመለከቱት የመብራት ኮንክሪት ፖል ታቹ ተበልቶ አልቆ ለመውደቅ ጫፍ ላይ ደርሷል። ከጎኑ ትራንስፎርመርንም አለ።

ቦታው ከጋርመንት ወደ ጀሞ አንድ ሲኬድ መብራት ተሻግሮ (ቫርኔሮ የመኖሪያ መንደር አካባቢ) ዘመን ማደያ ጋር ነው ሲሆን ብዙ ሰው የሚመላለስበት መኪናም የሚንቀሳቀስበት ነው።

ፖሉ ወድቆ በሰው እና በመኪና ጉዳት ሳያደርስ በፊት መፍትሄ ይፈለግለት። ወቅቱም ክረምት በመሆኑ ዝናቡና ንፋሱ ኃይለኛነውና ፈጣን መፍትሄ ይፈለግለት። " - ዮሴፍ (ከአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
761🙏239👏46😭41🕊21😱16🤔4😡1
#ለጥንቃቄ
#ጥቆማ_ለሚመለከተው_አካል!

አዲስ አበባ ጎተራ አካባቢ በሚገኘው የኢሚግሬሽ እና ዜግነት አገልግሎት አካባቢ ከሰሞኑን የሜትር ታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ በማስመሰል የዘረፋ ተግባር ላይ በተሰማሩ ሰዎች የተሞከረባትን የዘረፋ ሙከራ አንድ የቤተሰባችን አባል ለጥንቃቄ አጋርታለች።

የጎተራው አገልግሎት መ/ቤት የውጭ ዜጎች አገልግሎት ፣ የቪዛም አገልግሎት የሚገኝበት በመሆኑ ብዙ ከውጭ ሀገር የሚመጡ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውን ለአገልግሎት ይሄዳሉ።

በባለፈው ሳምንት ለዚሁ የውጭ አገልግሎት የሄደች አንዲት ከአሜሪካ የመጣች የቤተሰባችን አባል የዘረፉ ሙከራ ተፈጽሞባታል።

ነገሩ እንዲህ ነው ...

ቦታው እንደልብ ትራንስፖርት የማይገኝበት እና ጭር ያለ ነው።

ልክ ከአገልግሎቱ መ/ቤቱ ስትወጣ በቦታው ቀድሞውንም የነበሩ የሜትር ታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ የሚመስሉ ሰዎች " ይኸው ነይ የሜትር ታክሲ አገልግሎት " ይሏት።

እሷም ወደ መኪናው ትገባለች።

ብዙ ሳይጓዙ መኪናውን የሚያሽከረክረው ሰው መኪናውን ያቆመውና አንድ ሰው ገቢና ይጨምራል።

" ለምን ሰው ትጨምራለህ ? " ብትለውም " ምን አገባሽ ዝም ብለሽ ቁጭበይ " የሚል መልስ ይሰጣታል።

ነገሩ ያላማራት ይህች እህታችን ሁኔታውን በንቃት መከታተል ትጀምራለች።

አሁንም ትንሽ ከተጓዙ በኃላ መኪናውን አንድ ግብረአበራቸው ጋር ያቆሙና እሷ በተቀመጠችበት በር በኩል እንዲገባ ይነግሩታል።

በዚህ ወቅት እሷ " እኔ አልከፍትም በዛኛው ተቃራኒ በኩል ከፍቶ ይግባ " የሚል ምላሽ ትሰጣለች። ልክ ሰውየው በዛኛው በር ለመግባት ሲሄድ የነበረችበትን በር በመክፈት ወርዳ ወደ ኃሏ ሩጣ ማምለጥ ችላለች።

ሰዎቹ መንገዱ ወደፊት እንጂ ወደኃላ መመለስ የማያስችል በመሆኑ ሊከተሏት አልቻሉም።

በኃላም አካባቢው ግር ስላለባት በጎተራ ድልድይ አድርጋ ወደ ሳሪስ አቅጣጫ በእግር እየሮጠች ራሷን አትርፋለች።

በሩጫ በምታመልጥበት ወቅት ሰዎቹ " ነቃሽብን አይደል " እንዳሏት ታስታውሳለች።

ታርጋውን ለማየት ባትችልም የመኪናው ቀለም ' ብሉብላክ ' ቶዮታ ቪትዝ እንደነበር አስተውላለች።

አካባቢው ጭር ያለም ስለሆነ ብዙ ከውጭ የሚመጡ ሰዎች የሚስተናገዱበት በመሆኑ እያንዳንዱ እንቅስቃሴ መከታተል ይገባል።

የሜትር ታክሲ አገልግሎት የምትጠቀሙም " ኑ ታክሲ ይኸው " ብትባሉ እንዳትገቡ። ይልቁም ወደ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶቹ ስልክ በመወደል እና የተመዘገበ ህጋዊ መኪና ወደእናተ እንዲመጣ ማስደረግ አለባችሁ።

በማንኛውም ሁኔታ ስልካችሁ ባልተመዘገበበት እና ባለመኪናውም በድርጅት በህጋዊነት የተመዘገበ መሆኑን ሳታረጋግጡ ትራንስፖርት ለመጠቀም አትሞክሩ።

መንገድ ላይ የምትገቡም ከሆነ ስልካችሁን የግድ አስመስግባችሁ መልዕክት ሲመጣላችሁ ብቻ ተንቀሳቀሱ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamliyAA

@tikvahethiopia
1.74K🙏405👏120🤔21😢17🥰15😭8😡8😱6🕊5