TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
217 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ፌደራል ፖሊስ⬇️

ለኦነግ አባላትና አመራር በአዲስ አበባ የተዘጋጀው የአቀባበል ስነስርዓት #ያለአንዳች ችግር መጠናቀቁን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል አስታወቁ።

ኮሚሸነሩ ከfbc ጋር ባደረጉት ቆይታ በአቀባበል ስነስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ የሀገር መከላከያ፣ የኦሮሚያ ፖሊስ፣ የፌደራል ፖሊስ እና ደህንነት የተጠናከረ ጥበቃ ሲያደርጉ መቆየታቸውንም አንስተዋል።

በአቀባበል ስነስርቱ ላይ ከአራት ሚሊየን (4,000,000) #በላይ ህዝብ የተገኘ ሲሆን፥ የህዝቡን ሰላም በጠበቀ መልኩ #በሰላም መጠናቀቁን ገልጸዋል።

በአቀባበል ስነስርዓቱ ላይ የተገኙ #ወጣቶችም ከፖሊስ ጋር #ትብብር ሲያደርጉ መቆየታቸውን ያነሱት ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ #ጸጥታውን ለማስከበርም በጋር ሲፈትሹ እንደነበረም ጠቅሰዋል።

በዚህም #ቄሮዎችን ያመሰገኑ ሲሆን፥ ለሌሎችም አርአያ የሚሆን ተግባር መፈጸማቸውን ጠቅሰዋል።

የአዲስ አበባ ወጣትም የአቀባበል ስነስርዓቱ መጠናቀቅን ተከትሎ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች የሚመለሱ ወጣቶችን #ምግብና ውሃ በማዘጋጀት ግብዣ ሲያካሂድ እንደነበረ ገልጸዋል።

ኮሚሽነሩ ይህ #አንድነትን ይበልጥ የሚያጠናክርና ለሀገሪቱም ትልቅ #ተስፋ መሆኑን አንስተዋል።

አንዳንድ ቦታዎች ላይ "ወጣት ነን" የሚሉ ግለሰቦች #ድንጋይ የመወርወር አዝማሚያ ማሳየታቸውን የጠቀሱ ሲሆን፥ ፖሊስም #በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸው ተናግረዋል።

በተመሳሳይ በአዲስ አበባ #ዙሪያ በቄሮ ስም #የሚነግዱ ቄሮ ያልሆኑ ከአቀባበል ስነ ስርዓቱ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ግለሰቦች ዝርፊያና #ግድያ መፈጸማቸውን አንስተዋል።

በዚህም ፌደራል ፖሊስ፣ የኦሮሚያ ፖሊስ እና የሀገር መከላከያ ወደ አካባቢው በመሄድ ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር እያዋለ ይገኛል ብለዋል።

በጥቅሉ አቀባበሉ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የታየበት ጥሩ መንፈስ የነፈሰበት ህዝቡ እንግዶቹን ተቀብሎ በሰላም እንዲጠናቀቅ ያደረገበት ነው ብለዋል።

የአቀባበል ስነስርዓቱ በሰላም መጠናቀቅ ህዝቡ ላደረገው ትብብር፣ ለቄሮ እና ለአዲስ አበባ ህዝብ ምስጋና አቅርበዋል።

በአቀባበል ስነስርዓቱ ላይ የነበሩ ቄሮዎች ባሳዩት ትብብር ፖሊስ መኩራቱን ገልጸው በቀጣይም ፖሊስ ጋር በመሆን እጅና ጓንት ሆነው እንደሚሰሩ እምነታቸውን ገልፀዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በቡራዩ ነዋሪዎች ላይ የደረሰውን አሰቃቂ ግድያ በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በወጡ ሰዎች ላይ የፀጥታ ሐይል የፈጸመው #ግድያ እንዲመረመር ዓለማቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምንስቲ ኢንተርናሽናል አሳስቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ክፍል 1-ኃላፊነት የጎደለው የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም የሚያስከፍለው ዋጋ!

ሐሳብን በነፃነት መግለጽ የዴሞክራሲ ማዕከላዊ መርህ ነው፡፡ ይህ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ #መብት ደግሞ በይበልጥ እንዲተገበርና እንዲከበር ካደረጉ የታሪክ ክስተቶች፣ የቅርብ ጊዜውና ትልቁ ተጠቃሽ የማኅበራዊ ሚዲያ ነው፡፡ ማኅበራዊ ሚዲያ በባህርይው በማዕከላዊነት የሚደረግ የይዘት ቁጥጥር ባለመኖሩ፣ ተጠቃሚዎች የሚፈልጉትን ጉዳይ ያለማንም ገምጋሚነትና አርታኢነት በመቶ ሺሕዎች ለሚቆጠሩ ተጠቃሚ ተከታዮቻቸው በአነስተኛ ወጪ ያስተላልፋሉ፡፡ ይህም ሳንሱር እንዲጠፋ የሚደረገው ትግልና ክርክር እርባን አልባ እንዲሆን በማድረግ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ እሳቤ፣ ይህን ያህል ይሄዳል ተብሎ ያልተጠበቀበት ደረጃ አድርሶታል፡፡

በዚህም ምክንያት የማኅበራዊ ሚዲያው ለዴሞክራሲ ልምምድ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ሚና እንደሚጫወት ዕሙን ነው፡፡ ዛሬ አንድ ግለሰብ በስልኩ የሚያደርገው ግንኙነት እ.ኤ.አ. በ1980ዎቹ ሮናልድ ሬገን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሳሉ ያደርጉት ከነበረው እንደሚልቅ፣ ከ20 ዓመታት በፊት የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩት ቢል ክሊንተን ያገኙት ከነበረው መረጃ የበለጠ አንድ የ13 ዓመት ታዳጊ በስልኩ እንደሚያገኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ መረጃ ኃይል ነውና በዚህ ዘመን በቀላሉ የሚገኝ መረጃ ለዴሞክራሲ ልምምድ ብሎም በመረጃ ላይ የተመረኮዘ ውሳኔ ለመስጠት ትልቁን ሚና ይጫወታል፡፡ ከመሪዎቹ የሚገዳደር መረጃ እጁ ጫፍ ላይ የያዘ ዜጋ የመንግሥትት ተጠያቂነት እንዲኖር ለማድረግ ይችላልና፡፡ ከአንድ የዓለም ጫፍ የተከሰተን ጉዳይ  ማግኘትና መተንተን፣ ከዚያም ለውሳኔ መዘጋጀት ከኢንተርኔት ዘመን አስቀድሞ የደኅንነት ተቋማት ተግባር ነበር፡፡ አሁን ግን ከደኅንነት ተቋማት በማይተናነስ ደረጃ ማንኛውም ዜጋ መረጃ አለው፡፡ ይህም መንግሥት የሚወስዳቸውን ዕርምጃዎች እየተከታተሉ ለምን? እንዴት? ለማን ተወሰኑ? በሚሉ ጥያቄዎች ማረምና ተጠያቂነትን ማምጣት ይቻላል፡፡

ይሁንና በ1980ዎቹ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩት ሬገንና ከ20 ዓመታት በፊት በተመሳሳይ ሥልጣን ላይ የነበሩት ክሊንተን ያገኟቸው የነበሩ መረጃዎች፣ አሁን ላይ ማንም ከሚያገኛቸው መረጃዎች የሚለዩበት አንድ ነጥብ አለ፣ ተዓማኒነት፡፡ ፕሬዚዳንቶቹ ለሚያስተላልፏዋቸው ውሳኔዎች እንዲረዷቸው መረጃዎቹን ከታማኝ ምንጮች ያገኛሉ፡፡ ለመተንተን ይረዳቸውም ዘንድ ከባለሙያዎች ጋር ይነጋገራሉ፡፡ ነገር ግን አሁን ላይ ከስልኮቻችን፣ በተለይም ከማኅበራዊ ሚዲያ የምናገኛቸው መረጃዎች ተዓማኒነታቸው አናሳ በመሆኑ የሚተላለፉ ውሳኔዎች አደገኛ እንዲሆኑ ያደርጋሉ፡፡

ለዚህ የቅርብ ጊዜ ማሳያ የሚሆነው በማይናማር (በርማ) በሮሂንጂያ የእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ የተፈጸመው #ግድያ ነው፡፡ በዚህች የደቡብ ምሥራቅ እስያ አገር የሚኖሩና እንደ አገሪቱ ዜጎች የማይቆጠሩት የሮሂንጊያ ማኅበረሰብ እ.ኤ.አ. በ2016 በአገሪቱ ወታደሮች በተፈጸመባቸው ጥቃት ከአሥር ሺሕ በላይ ሰዎች ሲሞቱባቸው፣ ከ700 ሺሕ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቤት ንብረታቸውን ጥለው ለመሰደድ በቅተዋል፡፡ በዚህች አብዛኛው ማኅበረሰብ #ዜናም ሆነ ተያያዥ መረጃዎችን ከማኅበራዊ ገጾች በተለይም #ከፌስቡክ እንደሚያገኝ በሚገለጽባት አገር፣ በሮሂንጂያ ማኅበረሰብ ላይ የተፈጸመው በደል ‹በዓለማችን እጅግ በጣም የተጨፈጨፉ ሰዎች› በመባል እንዲታወቅ ያደረገ ጥፋት እንዲፈጸም ያደረገው #በፊስቡክ የሚለቀቅ መረጃ ነበር፡፡

በማይናማር የቡድሂስት መነኩሴ የሆኑት #አሺን_ዊራቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የፌስቡክ ተከታይ ያላቸው ሲሆኑ፣ ይኼንን የተከታዮቻቸውን መብዛት ለበጎ ሳይሆን የውሸት መረጃዎችን በማሠራጨት ለበርካቶች #ሞት መንስዔ ሆነዋል፡፡ እኚህ የማይናማር ቢን ላዲን በመባል የተሰየሙት መነኩሴ ለተከታዮቻቸው ሙስሊም የሆነ አንድ ባለድርጅት አሠሪ፣ የቡድሂስት እምነት ተከታይ የሆነችን ሴት ደፍሯል የሚሉ የሐሰት ማስረጃ ቢያስራጩም ተጠያቂ አልሆኑም ነበር፡፡ ፌስቡክም በተደጋጋሚ ሪፖርት ቢደረግለትም እ.ኤ.አ. እስከ 2018 ድረስ ዕርምጃ ባለመውሰዱ ከፍተኛ ጥፋት እንዲፈጸም ምክንያት ሆኗል፡፡

በዚህ የማኅበራዊ ሚዲያዎች በተንሰራፉበት ዓለም እንደ ኢትዮጵያ ያሉ በማደግ ላይ ያሉና አብዛኛው ኅብረተሰብ ያልተማረ በሆነባቸው አገሮች፣ የማይናማር ዕጣ ፈንታ ሊደገምባቸው እንደማይችል ማረጋገጫ እንደሌለ ባለሙያዎች ያስጠነቅቃሉ፡፡ ይህ በተለይ የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ፈር ካልተበጀለት #አጥፊነቱ ሊከፋ ይችላልም ይላሉ፡፡
.
.
ክፍል ሁለት 6:00 ላይ🔄

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጀማል አስክሬን እንዲሟሟ ተደርጓል‼️

ጋዜጠኛ #ጀማል_ካሾጊ ከተገደለ በኋላ አስከሬኑ ተቆራርጦ #እንዲሟሟ ተደርጓል አሉ የፕሬዚዳንት #ኤርዶሃን ኣማካሪ።

የአሁኑ የአማካሪው መግለጫ “የጋዜጠኛው አስከሬን በአሲድ እንዲጠፋ ተደርጓል መባሉን ለማጣራት ምርመራ እየተካሄደ ነው” በማለት
አንድ ከፍተኛ የቱርክ ባለስልጣን ለዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ የሰጡትን መረጃ እውነትነት #ያረጋግጣል ተብሏል።

አማካሪው ያሲን አክታይ ቱርክ ውስጥ ለሚታተመው ሁርየት የተባለ ጋዜጣ እንደተናገሩት የካሾጊ አስከሬን ተቆራርጦ ብቻ ሳይሆን ሟሙቶ እንዲወገድ መደረጉን ነው ማወቅ የቻልነው ብለዋል።

እጃችን ላይ እንደደረሰው መረጃ ከሆነ ገዳዮቹ አስከሬኑን የቆራረጡት በቀላሉ ለማሟሟት እንዲመቻቸው ነው ብለዋል አማካሪው።

የቱርክ ዋና ዐቃቢ ህግ ባለፈው ረቡዕ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰጡት መግለጫ ካሾጊ ኢስታንቡል ወደሚገኘው የሳዑዲ ቆንስላ እንደገባ በተደራጀ ሁኔታ #ግድያ ተፈጽሞበት አስከሬኑም ተቆራርጦ እንዲወገድ መደረጉን አረጋግጠዋል።

“አንድም የሰውነቱ አካል እንዳይገኝ አልመው ያደረጉት ነገር ነው። ንጹህ ሰው መግደል አንድ ወንጀል ሆኖ ሳለ አስከሬኑ እንዲጠፋ የተደረገበት መንገድ ደግሞ ሌላ አስከፊ ወንጀል ነው ብለዋል ያሲን አክታይ።

ምንጭ፦ ARTS TV WORLD
@tsegabwolde @tikvahethiopia
1
የሼክ አላሙዲን ነገር⁉️

"ቢቢሲ ዛሬ በለቀቀው ዘጋቢ ፊልም እነ ሼክ አላሙዲንን ከሳዑዲ ልዑላውያን ጋር ደምሮ ያሳረዉ የሳዑዲ መንግስት በታሳሪዎቹ ላይ የከፋ #ድብደባ እና #ማሰቃየት እንዲሁም #ግድያ እየፈፀመ ነዉ ሲል ዘጋቢ ፊልም ሰርቷል። ከሟቾች ዉስጥ ጄኔራል አሊ አልካታኒ አንዱ ናቸዉ። ሞሐመድ ቢን ሰልማን የሚባለዉ እና ፖለቲካዊ አመለካከቱ ሊበራል ነዉ ተብሎ ሲወደስ የነበረዉ በቅጽል ስሙ ኤም ቢ ኤስ የተባለዉ የሳዑዲ አልጋወራሽ በእርሱ ትዕዛዝ የታሰሩ ባለሀብቶችና ንጉሣውያን ቤተሰቦች በድብደባ ምክንያት የደረሰባቸውን ጉዳት በሌላ ሆስፒታል እንዳይታከሙ በሪትዝ ሆቴል ተንቀሳቃሽ ሆስፒታል ከፍቷል። ይህ ዘገባ የተሰራዉ በቅርቡ ቱርክ በሚገኘዉ በሳዑዲ አረቢያ ቆንስላ
በጋዜጠኛ #ጀማል_ካሾጊ ላይ የተፈፀመዉን ግድያ ጋር ተንተርሶ ነዉ። አላሙዲን ምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ? የኢትዮጵያ መንግስት ያለዉ መረጃ
ምንድነዉ? ከአላሙዲን ጋር ሲበሉ ሲጠጡ ሲያተርፉ ሲነግዱ ያዙን ልቀቁን ሲሉ የነበሩ የት አሉ ? አላሙዲ ታሰረ አልታሰረ ጉዳያቸዉ አይደለም። ነገር ግን በእርሳቸዉ እርዳታ ህክምና ላገኙ እርዳታ ለተደረገላቸው ጥቂት ኢትዮጵያውያን ቤት ተሰርቶ ለተሰጣቸዉ ድሆች ስንል የመሐመድ ቢን ሰልማን ሰለባ እንዲሆኑ አንሻም። በሙስና የሚጠየቁ ከሆነም በፍርድ ቤት በአግባቡ መሆን አለበት ከጥላሁን ገሠሠ እስከ ካሚላት ላደረጉት በጎ ምግባር እናመሰግናለን።"

©Hailemelekot Agizew
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“ኦነግ በሬ እያረደ በተቀበለው ህዝብ ላይ ዘረፋና #ግድያ ፈጽሟል” ጄኔራል #ብርሃኑ_ጁላ

• ሠራዊቱ ከትግራይ እንዳይወጣ የሞከሩት ህዝቡና የክልሉ መንግሥት አይደሉም

• መከላከያን ከኃላፊነቱ ውጪ የክልሎችና የፖለቲካ ሥራን የማሠራት ፍላጎት አለ

• በሠራዊቱ ላይ ጥላቻ በመንዛት አገርን ለማፍረስ የሚሠሩ አሉ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
1
#ሰበር_ዜና የኢትዮጵያ መንግሥት #በሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት ላይ ተከታታይ #ግድያ የመፈጸም #ዕቅድ እንደነበር አስታውቋል።

🗞ሰኔ 20/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert ለባለስልጣናቱ #ግድያ አዴፓ ራሱን ተጠያቂ እንዲያደርግ ህወሐት ጠየቀ። ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የህወሐት ማዕከላዊ ኮሚቴ አስቸኳይ ስብሰባ ዛሬ ተጠናቋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/TPLF-07-10

@tsegabwolde @tikvahethiopia
👏1
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba የ32 ዓመቷ ወጣት በፖሊስ ጥይት ከጀርባዋ ተመታ ህይወቷ ያለፈ ሲሆን ፖሊስ የድርጊቱ ፈፃሚ በቁጥጥር ስር ይገኛል ብሏል። በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ነዋሪ የሆነች የ32 አመት ወጣት ከፖሊስ አባል በተተኮሰ ጥይት ተመታ ህይወቷ አልፏል። በፖሊስ አባል ጥቃት የደረሰባት ኢየሩሳሌም አስራት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ነዋሪ ስትሆን ጥቃቱ ካጋጠማት በኋላ በጥቁር አንበሳ…
#AddisAbaba

#ሕዳር

* ባለፈው ሕዳር 13/2016 በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ነዋሪ የሆነች የ32 አመት ወጣት እየሩሳሌም አስራት ከፖሊስ አባል በተተኮሰ ጥይት ከጀርባዋ ተመታ ህይወቷ ማለፉ መነገሩ አይዘነጋም። ይህች ወጣት በፖሊስ አባል ጥቃት ካጋጠማት በኋላ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የቀዶ ጥገና እና ሕክምና ክትትል ሲደረግላት የነበረ ቢሆንም ህይወቷ ሊተርፍ ግን አልቻለም።

* አሁን ደግሞ ዶ/ር እስራኤል ጥላሁን የተባለ የጤና ባለሞያ የፖሊስ አባል ነው በተባለ ግለሰብ ሕዳር 28 ቀን 2016 በተተኮሰ ጥይት ህይወቱን እንዳጣ ተሰምቷል። ይህ ወጣት የጤና ባለሞያ " ስፖኪዮ ገጭቶ አመለጠ " በሚል አንድ የፖሊስ አባል " ጎማውን መትቼ ለማስቆም " ነው ብሎ በታጠቀው መሳሪያ ዶክተሩ ላይ በመተኮስ #ግድያ እንደፈፀመ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን ተናግሯል።

@tikvahethiopia
😭1.48K😡46087😢67🕊28😱7🙏7
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba ታህሳስ 7 ቀን 2016 ዓ/ም ምሽት አዲስ አበባ ቦሌ ኤድና ሞል አካባቢ አንድ ሰው በጥይት ተመቶ ተገድሏል። ድርጊቱ የተፈፀመው ቦሌ ከኤድናሞል ወረድ ብሎ በሚገኝ አንድ የመዝናኛ ስፍራ አካባቢ ነው። ምሽት አራት ሰዓት ገደማ ሟች #አባተ_አበበ በአንድ #መሳሪያ_በታጠቀ ግለሰብ በጥይት ተመቶ መገደሉ ታውቋል። አባተ አበበ ተወልዶ ባደገበት ፣ በሚኖርበት  አካባቢ እንዲሁም ደግሞ በስራ…
#ግድያ #የፖሊስ_ምላሽ

" ፖሊስ ሥራውን እየሰራ ነው። ግልጽ ማድረግ በሚገባን ሰዓት ላይ ግልጽ እናደርጋለን " - ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ

አቶ አባተ አበበ የተባሉ ግለሰብ ታህሳስ 7 ቀን 2016 ዓ/ም አዲስ አበባ ቦሌ ኤድናሞል አካባቢ ዝቅ ብሎ በሚገኝ መዝናኛ 'በጥይት ተመትቶ ተገደለ' መባሉን በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ጠይቋል።

የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ " ፖሊስ ሥራ እየሰራ ነው። ግልጽ ማድረግ በሚገባን ሰዓት ላይ ግልጽ እናደርጋለን " ብለዋል።

ኮማንደሩ በሰጡት ማብራሪያ፣ " ሰው ወዲያው እንደሞተ ወደ ሚዲያ መውጣት አለበት ? " ሲሉ ጠይቀው፣ " በጣም አሁን እኮ አንዳንድ ፀሐፊዎች እንዳውም ፎቶ ግራፉን ሁሉ ' ተጠርጣሪ ይሄ ነው ' እያሉ እየለጠፉ ነው። ይሄ ኢቲካል እኮ አይደለም " ብለዋል።

አክለውም፣ " ይሄን ሰውየ እኮ ፍርድ ቤት ነው 'ጥፋተኛ ነህ' ብሎ ጥፋተኛ መሆኑን የሚገልጽለት እንጂ ግለሰብ እየተነሳ 'ጥፋተኛ ነው' ብሎ ፎቶ እየለጠፉ ትክክል እኮ አይደለም " ብለዋል።

ምክትል ኮማንደር ማርቆስ የጉዳዩን አሳሳቢነት ሲያስረዱም ፦

- " ፍርድ ቤት እኮ ጥፋተኛ እስከሚለው እኮ ነፃ ሆኖ የመቆጠር መብት አለው። "

- " ከሕግ አንጻር እኮ ማዬት መቻል አለብን። ይሄ ነገር #የሚያስከትለውን ነገር ማየት መቻል አለበት። "

- " ቤተሰቦቹን ማሰብ መቻል አለበት። አሁን እነዚህ ሰዎች #ጎረቤታሞች ቢሆኑ እኮ የዛ ቤተሰብ መጥቶ እዚህ ልጅ ላይ እርምጃ ሊወስድ ነው። እንዴት እንደዚህ አይታሰብም ? ብቻ በአጠቃላይ በጣም ቀውሷል ሚዲያው ፤ ከባድ ቀውስ ላይ ነው ያለነው " ሲሉ አስረድተዋል።

የሟቹን ጉዳይ በተመለከተ ፖሊስ ያገኘው መረጃ እና የጀመረው ምርመራ እንዳለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው ኮማንደር ማርቆስ፣ " ፖሊስ ሥራ እየሰራ ነው። ግልጽ ማድረግ በሚገባን ሰዓት ላይ ግልጽ እናደርጋለን። አሁን ሥራ እየተሰራ ነው " ሲሉ አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

የአባተ አበበን ጉዳይ በተመለከተ እየተከታተልን የምናቀርብ ይሆናል።

ይህን መረጃ አዘጋጅቶ የላከው የአ/አ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
😡1.22K280😭131👏78😢76🙏53🕊50🥰25😱22
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
🇪🇹 የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹

" ... አሁንም ቢሆን ለያዥ እና ገናዥ አስቸጋሪ የሆነው የመንግስት አቋም ነው " - መረራ ጉዲና (ፕሮፌሰር)

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ( #ኦፌኮ ) ሊቀመንበር መረራ ጉዲና (ፕ/ር) በሀገራችን ጉዳይ ላይ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

Q. በተለያዩ ቦታዎች ያለውን የጸጥታው ችግር እንዴት ትገመግሙታላቹ ? መፍትሄውስ ምንድን ነው ?

ፕ/ር መረራ ጉዲና ፦

" ብሔራዊ እርቅ እና ብሔራዊ መግባባት የሚባለውን እኮ ከኢህአዴግ መጀመሪያ ዓመት ጀምሮ እስከ 30 ዓመታት ስንጠይቅ ቆይተናል።

አሁንም ቢሆን መልክ አልይዝ እያለ ያስቸገረው / ለያዥና ለገናዥ አስቸጋሪ የሆነው የመንግስት አቋም ነው።

ስልጣንን በMonopoly መያዝ ከንጉሱ ዘመን ጀምሮ እንደ ባህል ተይዟል። አሁንም ቀጥሏል። የኢትዮጵያ መሪዎች ከዛ አልወጣ አሉ። ውጤቱ ደግሞ የታወቀ ነው። 

ደርግ ወጣቶችን ጨፍልቆ ነው የሄደው ፤ ኢህአዴግ ለ27 ዓመታት አገሪቱን ቀላል ያልሆነ ቀውስ ውስጥ ከቷት ነው ጡረታ የወጣው ፤ ብልጽግናም በባሰ መንገድ ይህንኑ ሁኔታ እየተከተለ ነው።

የኢትዮጵያ ጸጥታ ሁኔታ ' ከድጡ ወደ ማጡ ' ተብሎ የሚገለጽበት ደረጃ ላይ ነው።  መፍትሄው ቁጭ ብሎ መወያዬት ነው።

ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን #ከመገዳደል ፓለቲካ ወደ #መደራደር ፓለቲካ ማምጣት እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። "

Q. በየጊዜው የንጹሐን ሕይወት በግፍ እየተቀጠፈ ነው። ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ መስራትም የሞት ጊዜን እንደማፋጠን ሆኖ ይስተዋላል።  መፍትሄ እንዲመጣ ምን እየሰራችሁ ነው ?

ፕ/ር መረራ ጉዲና፦

" ለ30 ይሁን ለ6ቱ ዓመታት በዴሞክራሲ የሚደረገው ለውጥ በተለይ ዴሞክራሲያዊ ምህዳርን እንዲያሰፉ ደጋግመን ስንጠይቅ ነበር።

አሁንም ያን መጠየቅ ቀጥለናል። ሜዳው / ምህዳሩ ግን በተቃራኒው እየጠበበ፣ አስቸጋሪ ሁኔታዎች በአገሪቷ ላይ እየተንሰራፉ የመጡበት ሁኔታ ነው ያለው።

ምህዳሩ ካልሰፋ፣ ለዴሞክራሲ የሚደረገው ትግል መልክ ካልያዘ፣ ወጣቱንም ወደ ጫካ እየተገፋ የትም አያደርሰንም። "

Q. ከመንግስት የሚደርስባችሁ ጫና ምንድን ነው ?

ፕ/ር መረራ ጉዲና ፦

" ከኦነግ ቀጥሎ ከፍተኛ ጫና ያለበት የእኛ ፓርቲ ነው።

ለምሳሌ የዛሬ 4 ዓመት ከ200 በላይ ቢሮዎች ነበሩን፤ አሁን ያሉን 3 ብቻ ናቸው። አባሎቻችን #ግድያ እና #እስራት ይፈጸምባቸዋል። 

ለምሳሌ ፦ የምሥራቅ ወለጋ የቢሮ ኃላፊ ከተወሰደ የት እንደገባ አላወቅንም 2 ዓመታት ሊሆነው ነው።

የምሥራቅ ሸዋ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላችን ለዚያውም የዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር ታስሯል።

አምቦ 4 ወጣቶች ታስረው 2 ሳምንታት ሆኗቸዋል። "

Q. #ብልሹ_አሰራርና #ሙስናን በተመለከተ ኢትዮጵያ በምን ደረጃ ትገኛለች ? መፍትሄውስ ?

ፕ/ር መረራ ጉዲና ፦

" በኢትዮጵያ ታሪክ የተለዬ/የከፋ የሙስና ደረጃ ነው ያለው።

መንግስትና ተቋማቱ የአንድ ቡድን ጉዳይ አስፈጻሚ ሆነው ሲዋቀሩ እንዲህ አይነት ሁኔታዎች ይፈጠራሉ።

አሁንም መንግስት ተጠያቂነት ባለው መንገድ እንደገና ካልተዋቀረ በስተቀር፣ ከዚህ በሽታ የምንወጣበት መንገድ ያለ አይመስለኝም።

Q. የኑሮ ውድነቱ ሕዝቡን በእጅጉ አማሮታል። ፓርቲያችሁ ለመንግስት ያላችሁ ግምገማን ቢያጋሩ ?

ፕ/ር መረራ ጉዲና ፦

" ዜጎች እጅግ አስቸጋሪ ፣ ፈታኝ ሁኔታ ላይ ደርሰዋል።

መንግስት አስፈላጊ እርምጃ እንዲወስድ በተደጋጋሚ ተይቀናል።

መንግስት ግን ጆሮ ያለው አይመስልም። ችግሩ ግን እጅግ በጣም ፈታኝ ነው። "

Q. በቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ተመራጭ ሆኖ ለመቅረብ ዝግጅት እያደረጋችሁ ነው ?

ፕ/ር መረራ ጉዲና ፦

" የፓለቲካ ምህዳር ለማግኘት የመገዳደል ፓለቲካው እንዲቆም እየጠየቅን ነው። ምርጫ ከዚያ በኋላ የሚመጣ ነው።

ለነፃና ፍትሃዊ ምርጫ አስቻይ የሆነ ሁኔታ ኢትዮጵያ ውስጥ የለም።

ትልልቆቹ አማራና ኦሮሚያ ክልሎች ጦርነት ውስጥ ናቸው። በዚህ ሁኔታ ምን አይነት ምርጫ እንደሚካሄ የምናየው ነው። መደራጀቱን ቀጥለናል። "

#TikvahEthiopiaFamilyAA

#ቲክቫህኢትዮጵያ
#የፖለቲካ_ፓርቲዎች_ምን_ይላሉ?

@tikvahethiopia
588👏154😡55🕊41🤔30😭24😱20🙏19😢18🥰10
TIKVAH-ETHIOPIA
#ይነበብ🚨 " በወንጀል የተገኘን ንብረት #ህጋዊ_ማስመሰልና #ሽብርተኝነትን_በገንዘብ_የመርዳት ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር " የወጣ ረቂቅ አዋጅ ለሕ/ተ/ም/ቤት ቀርቧል። በዚሁ ረቂቅ ላይ በክፍል 5 ' ስለ ምርመራ '  ሰፍሯል። ረቂቁ ስለ #ምርመራ ምን ይላል ? - በወንጀል የተገኘ ንብረት ህጋዊ ማስመሰል ወይም ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ወይም የወንጀል ፍሬን ተከታትሎ ለመለየት…
#ኢትዮጵያ

በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን የሚመረምር ሰው፤ በምርመራ ወቅት ከአቅሙ በላይ በሆነ ምክንያት ከ #ግድያ ውጪ የትኛውንም ዓይነት ወንጀል ቢፈጽም ተጠያቂ የማያደርግ አዋጅ ጸደቀ፡፡

በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቋል፡፡

አዋጁ በሽፋን ስር የሚደረግ ምርመራ (Under cover investigation) እንዲያስፈጽም የተመደበ ሰው፤ በግዴታ ላይ እያለ ከአቅሙ በላይ በሆነ ምክንያትና ከፈቃዱ ውጪ በሆነ ከግድያ ወንጀል በስተቀር ለሚፈጽመው የወንጀል ድርጊት የወንጀል ክስ አይቀርብበትም ይላል።

የምክር ቤት አባሉ አለሙ ጎንፋ (ዶ/ር) በአዋጁ 5/15 ላይ የቀረበው ዐረፍተ ነገር ትንሽ ከባድ መስሎ እንደታያቸው ተናግረው አዋጁ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

" እንደዚህ ዓይነት አዋጅ በተለይ ሽብርን ለመከላከል ለሀገራችን ያስፈልጋታል " ሲሉ የምክር ቤት አባሉ ተናግረዋል፡፡

‘’ የሆነው ሆኖ ግን ' አንድ ሰው በግዳጅ ላይ እያለ ከግድያ በስተቀር ለሚፈጽመው ወንጀል አይጠየቅም ' ይላል፡፡ አንደኛ ወንጀል ፈጽሟል ይላል፣ ወንጀል ፈጽሞ አለመጠየቅ ትክክለኛ አይመስለኝም፡፡ ወይም ድርጊቶቹ ተዘርዝረው ህጋዊ መብት የተሰጠው ሰው ሚወስዳቸው እርምጃዎች ወንጀል አይደሉም ብለን ማለፍ እንጂ አንድ ሰው በግዳጅ ላይ እያለ ለሚፈጽመው ወንጀል ከግድያ በስተቀር የሚለውን ሰው እንደፈለገ እንዲሆን የሚያደርግ ነው’ " ሲሉ አለሙ (ዶ/ር) ሃሳበቸውን አስረድተዋል፡፡

ሌላ ሙሉቀን አሰፋ የተባሉ የምክር ቤት አባል በበኩላቸው " እኔ በግሌ እንደተፎካካሪ የፖለቲካ ሰው አዋጁ ባለሀብቶችን፣ ጋዜጠኞችን፣ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን እና የታዋቂ ሰዎችን መብት የሚገድብ ነው " ብለዋል፡፡

" እንዲያውም የመናገር መብትን ይከለክላል የሚል እምነት ነው እኔ ያለኝ " ያሉት የምክር ቤት አባሉ ‘" ምክንያቱም አዋጁን ስናየው በ10 ዓመት ገድቦ ነው የወጣው’ " ሲሉ ተናግረዋል፡፡

" ህግ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ነው ተግባራዊ መደረግ ያለበት’ " ያሉት አቶ ሙሉቀን " ስለዚህ ከ10 ዓመት ወዲህ ብሎ ማውጣቱ የተወሰኑ ግለሰቦችን ወይም ቡድኖችን ለማጥቃት ያሰበ ስለሆነ ለሀገራችንም ጥሩ አይደለም የሚል እምነት አለኝ " ብለዋል፡፡

" በአለም አቀፍ ስምምነቶች ላይ እንደተገለጸው ሀይልን በመጠቀም፣ ንጹሃንን በማስገደድ አላማቸውን ለማስፈጽም የሚሳተፉ ተዋናዮችን ተጠያቂ ለማድረግ ሳይሆን አዋጁ እየዋለ ያለው በዋነኝነት የመንግስት ተቃዋሚዎችን፣ መንግስት ውስጥ ሆነው መንግስትን የሚተቹትን እና ጋዜጠኞችን ነው " ያሉት ደግሞ ሌላው የምክር ቤት አባል የሆኑት ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

" የአዋጁን ዝርዝር ካየንው በጣም አስገራሚ የሆኑ ድንጋጌዎችን ይዟል " ያሉት የምክር ቤት አባሉ " ለምሳሌ የፋይናንስ ድህንነት አገልግሎት አጠራጣሪ ግብይትን ለ7 ቀን አግዶ ማቆየት ይችላል ይላል ያውም ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ " ብለዋል፡፡

" አዋጁ በሽፋን ስር ምርመራ የሚያካሄድ መርማሪ ከግድያ ወንጀል ውጭ በሌላ ወንጀል አይጠየቅም ይላል " ያሉት  ደሳለኝ ጫኔ(ዶ/ር)  " ለምሳሌ መርማሪው በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ተደራድሮ ከሆነ ከወንጀለኛው ጋር መቀበሉን ብናውቅ አይጠየቅም ማለት ነው?  ማሰቃየት ቢፈጽም፣ የመብት ጥሰት ቢፈጽም አይጠየቅም ማለት ነው? መሆን ያለበት ግን ኢትዮጵያ በፈረመቻቸው አለም አቀፍ ድንጋጌዎች የተካተቱ ወንጀሎችን አለመፈጸሙ ነው " ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሌላው አቶ ዘካሪያስ የተባሉ የምክር ቤት አባል በበኩላቸው  " አዋጁ አንዳንድ የምክር ቤት አባላት እንደሚሉት ተቃዋሚን እና የሚዲያ ሰዎችን ለማፈን አይደለም " ብለዋል፡፡

አቶ ሳዲቅ አደም የተባሉ የምክር ቤት አባል በበኩላቸው " አዋጁ ጠንከር ያለ መሆኑን ተናግረው ጠንከር ያለበት ምክንያትም ግልጽ ነው " ሲሉ ተናግረዋል፡፡

" ያለንበት ቀጠና አስቸጋሪ ነው፤ ሽብርተኝነት የሚበዛበት በመሆኑ የአዋጁ ከበድ ማለት ተገቢ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ከመብት አንፃር ሊታዩ የሚችሉ ነገሮች አሉ ያሉት አቶ ሳዲቅ ከህገ መንግስታችንም ስንነሳ ፍጹም የሚባል መብት የለም " ብለዋል፡፡

" ከመብቶች ሁሉ የላቀ ዋና መብት የሚባለው በህይወት የመኖር መብት ነው ይህ መብትም ፍጹም አይደለም " ሲሉ የተናገሩት የምክር ቤት አባሉ " ስለዚህ መብት የሚባለው ነገር ለህዝብ፣ ለማህበረሰብ እና ለሀገር ድህንነት ሲባል በየትኛውም ሀገር መብቶችን ፍጹማዊ አድርጎ የሚያስቀምጥ የለም " ሲሉ ተናግረዋል፡፡

" ስጋት አድርጎ የሚወስድ ወገን ሊኖር ይችላል ግን ለምን ይሰጋል? " ሲሉ የጠየቁት የምክር ቤት አባሉ " ይህ አዋጅ ሲወጣ ለመጠርጠርም መሟላት ያለበት ነገር አለ ማንኛውም ወገን እነዚህ በአዋጁ የተቀመጡ ነገሮችን ካሟላ አይነካም ዋናው መስፈርቱን ማሟላት ነው " ብለዋል፡፡

" አዋጁ የወጣው በንድፍ ሃሳብ የምንፈራቸውን ለመከላከል ሳይሆን በተግባር እያየን እየኖርንበት ያለውን ነው "  የሚሉት አቶ ሳደቅ " ሽብርተኝነት በሀገራችን በስፋት አለ ኤ ቤ ሲ ብለን ልንጠራቸው የምንችላቸው ግለሰቦች እና ወገኖች አሉ ስለዚህ ይህን ለመከላከል ለምን እንሰጋለን " ብለዋል፡፡

የህግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ኢሳ ቦሮ በበኩላቸው በሰጡት ምላሽ የሚደረገው ምርመራ ልዩ መሆኑን ተናግረው አዋጁ አንድን ቡድን ለማጥቃት ታስቦ የወጣ አይደለም ብለዋል፡፡

በመጨረሻም ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው በማሻሽያ ረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ በሶስት ተቃዉሞ በአንድ ድምጽ ተአቅቦ  እና በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል፡፡

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

#ShegerFM

@tikvahethiopia
1.04K😭959😡363🤔66😱28💔28😢20🕊16🙏14🥰5👏5