TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጌዴኦ‼️

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት አቶ ነጉሱ ጥላሁን #በጌዴኦ ላሉ ተፈናቃዮች የዕለት ምግብ ተደራሽ ለማድረግ መንግሥት #ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። መንግሥት የዕለት ደራሽ ምግብ ለሚያስፈልጋቸው #ድጋፍ ለማድረግ ከፌደራል እና ከክልል ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ከዚህ ቀደምም ሲሰራ ቆይቷል፤ በዚህም እንዲቋቋሙ የተደረጉ እንዳሉም ገልጸዋል።

ነገር ግን አሁንም #የዕለት_ደራሽ_ምግብ ያልደረሳቸው ዜጎች እንዳሉ እና ችግር ላይ እንደወደቁ መንግሥት ተረድቶ የዕለት ምግብ ተደራሽ እንዲሆን ትኩረት ተሰጥቶት ተጎጂዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል። ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት ዜጎችን በማቋቋም፣ #የህግ_የበላይነትን በማረጋገጥ የሚደርሱ ማፈናቀሎችን ማስቆም መቻል ላይ መንግሥት ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia