ደኢህዴን‼️
በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ባሉ አንዳንድ የዞን ም/ቤቶች የሚነሱ #የክልልነት_ጥያቄዎች ከደኢህዴን ጉባኤ አቅጣጫ ውጭ መሆናቸውን የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡
ማዕከላዊ ኮሚቴው ይህን ያስታወቀው በክልሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ መሆኑን የማዕከላዊ ኮሚቴው ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡
ኃላፊው እንዳሉት ማዕከላዊ ኮሚቴው የህብረተሰቡን ጥያቄዎች ለመመለስ በ10ኛው የደኢህዴን ድርጅታዊ ጉባኤ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን አፈፃፀም ሂደት ገምግሟል፡፡
አስተዳደራዊ አደረጃጀትን በተመለከተ ዝርዝር ጥናት እየተደረገ መሆኑን የጠቀሰው ማዕከላዊ ኮሚቴው ጥናቱ ሲጠናቀቅ በጉባኤው የፀደቁ አዳዲስ የመዋቅር አደረጃጀቶች በክልሉ ም/ቤት ህጋዊ ማዕቀፍ ኖሯቸው እንደሚቋቋሙ ገልጿል፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በክልሉ እየተበራከቱ የመጡትን የክልላዊ አደረጃጀት ጥያቄዎች በተመለከተም ጥልቅ ጥናት የሚያደርግ ከባለሙያዎች፣ ምሁራንና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጣ ቡድን መቋቋሙ ተገልጿል፡፡
ጥናቱን ተከትሎም ተገቢው ምላሽ እንደሚሰጥና ከዚህ ውጭ በዞን ም/ቤቶችና በተለያየ መልኩ የሚነሱ ጥያቄዎች ከድርጅቱ ጉባኤ አቅጣጫ ውጭ መሆናቸውን ማዕከላዊ ኮሚቴው አስታውቋል፡፡
ተቋማትን በመዝጋትና የዜጎችን ነፃ እንቅስቃሴ በመገደብ ሃሳብን በኃይል ለመጫን የሚደረጉ ተግባራት ተቀባይነት የላቸውም ያለው ኮሚቴው የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ግልፅ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
ማዕከላዊ ኮሚቴው የኅብረተሰቡን ጥያቄዎች ተከትሎ በተከሰቱ ግጭቶች በደረሰው የህይወት መጥፋትና የአካል ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘንም መግለፁን የማዕከላዊ ኮሚቴው ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ተናግረዋል፡፡
ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia