TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🔈 #የአሽከርካሪዎች_ድምጽ

“ አንድ ቀን አሽከርካሪዎች ችግር መንገድ ላይ ገጥሟቸው በሚቆሙበት ሰዓት ፤ የሆነ ነገር ብሷቸው ከሥራ ቢገለሉ የመጀመሪያው ተጎጂ ህብረተሰቡ ነው ” - የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር

➡️ “ አሽከርካሪዎችን ሁሉም ይንከባከብ !! ”

“ ሹፌሮች ብሷቸው ከስራ ቢገለሉ ” ተጎጂው ማህበረሰቡ በመሆኑ፣ ሁሉም አካል አሽከርካሪዎችን ሊንከባከብ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አሳሰበ።

“ አንድ ቀን አሽከርካሪዎች ችግር መንገድ ላይ ገጥሟቸው በሚቆሙበት ሰዓት የሆነ ነገር ብሷቸው ከሥራ ቢገለሉ የመጀመሪያው ተጎጂ ህብረተሰቡ ነው ” ሲል አስጠንቅቋል።

አሽከርካሪዎች ከሥራ ቢገለሉ የነዳጅ፣ መድኃኒት፣ ምግብ፣ ዘይት፣ ሸቀጣሸቀጥ ግብዓት ማግኘት እንደማይቻል፣ ግብይቱ እንደሚዛባ ገልጾ፣ ማህበረሰቡ ከአሽከርካሪዎች ጎን እንዲቆም አስገንዝቧል።

ማኀበሩ፣ “ይህንን ያልተረዱ የመንግስት አካላት ግንዛቤ ኖሯቸው ህግን ያስከብሩ፣ ህገ ወጥ አሽከርካሪዎች ካሉም በህግ ይጠየቁ። ከዚያ ውጭ ያሉ እንቅስቃሴን የሚገድቡ ነገሮችን ባያደርጉብን ” ሲልም አክሏል።

“ በተለይ የገቢ ወጭ ንግድን ማቋረጥ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ትልቁ እንቅፋት ስለሚሆን ሎጂስቲኩንም ስለሚያናጋው አሽከርካሪዎችን ሁሉም አካል ይንከባከብ ” ነው ያለው።

“ አሽከርካሪዎች ለኢትዮጵያ የሎጂስቲክስ እንቅስቃሴ ወሳኝ አምድ ናቸው። እነሱ ከሌሉ ምንም ነገር ይቆማል ” ሲል አስጠንቅቋል።

ማኀበሩ፣ “ ስለዚህ ከህብረተሰቡ ጀምሮ እስከላይ ያለው አካል ጥቅማቸውንና አገልግሎታቸውን ተረድቶ በሚሄዱበት ሁሉ ይጠብቃቸው የሚጓጉዙት የህብረተሰቡ መሰረታዊ ፍላጎቶችን ነው ” ብሏል።

“ ሹፌር ተገደለ፣ መኪና ተቃጠለ ብቻ ሳይሆን ሁልጊዜ በየቀኑ እንደዜና ሁሉም ሚዲያዎች ” ፕሮግራም ይዘው የሹፌሮደችን ጉዳይ እንዲዘግቡ ተጠይቋል።

“ ለምሳሌ ግንቦት 9/2017 ዓ/ም የሹፌሮችን ቀን አክብረን ውለናል” ያለው ማኀበሩ፣ “ አንድም ሚዲያ አልመጣልንም። አንድ አርቲስት አልበም ሲያስመርቅ ማይክራፎኑ ይበዛል። ማይክሮፎን አርቲስቶቹ የሚዘፍኑበትንም ሁሉ ያመጣው ግን አሽከርካሪ ነው ” ሲል ማኀበሩ ወቅሷል።

“ የኢትዮጵያ ከባድ መኪናዎች አሽከርካሪ በኢትዮጵያ ሚዲያዎች በጠቅላላ አዝኗል። አንድ ሚድያ መጥቶ አልዘገበልንም። ይሄን ሚዲያዎች ትኩረት እንዲሰጡ ይደረግ ” ሲልም በአጽንኦት ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
1.66K🙏159👏62😭57🕊46🤔25😢19🥰10😱7