TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ማሳሰቢያ ሰጠ!

በኦሮሚያ #የተጠየቀም ሆነ #የተፈቀደ ሰልፍ አለመኖሩን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል። የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ከፍያለው ተፈራ ዛሬ በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በአፋን ኦሮሞ ለሚታተመው በሪሳ ጋዜጣ በክልሉ በየትኛውም አካባቢ የቀረበ የሰልፍ ጥያቄም ሆነ የተፈቀደ ሰልፍ አለመኖሩን ተናግረዋል።

በማንኛውም ጉዳዮች ዙሪያ መንግስት ከሚመለከታቸው አካሎች ጋር እየተወያየ መፈትሄ እንዲያገኙ ያደርጋል እንጂ ሰልፍ የሚያስወጣ ምንም ዓይነት ጉዳይ አይኖርም ብለዋል ኮሚሽነሩ። በመሆኑም ህብረተሰቡ በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚናፈሱ አሉባልታዎችን ተከትሎ እንዳይሳሳት ኮሚሽነሩ አበክረው አሳስበዋል። ለሁሉም የክልሉ ዞኖችና ከተሞች አቅጣጫ የተሰጠ መሆኑን የገለጹት ኮሚሽነሩ ከፖሊስ እውቅና ውጪ የሚካሄድ ሰልፍ ካለ የክልሉ ፖሊስ የህግ የበላይነትን ለማስከበር ተገቢውን እርምጃ እንደሚወስድ ኮሚሽነሩ አሳስበዋል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia