TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የመውጫፈተና #ምረቃ

➡️ " ትምህርታችን በአግባቡ ብንጨርስም ለ8 ወራት ትዘገያላችሁ ተብለናል " - ተማሪዎች

➡️ " ይህ ውሳኔ የመጣዉ #ከትምህርት_ሚኒስቴር በመሆኑ ምንም ማድረግ አልቻልንም " -  የኮሌጅ አመራሮች

➡️ " የመጀመሪያ ዲግሪ የሚማሩ ተማሪዎች የተቋም ቆይታቸው ቢያንስ 4 ዓመት ነው " - ትምህርት ሚኒስቴር

ከሰሞኑን በርካታ #የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ከምረቃ እና ከመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የቅሬታ መልዕክቶችን ልከዋል።

ቅሬታቸውን ከላኩት መካከል በአዲስ አበባ፣ በሀዋሳ ደሴ እና ሌሎች ከተማ የሚገኙ የኮሌጅ  ተማሪዎች ይገኙበታል።

ተማሪዎቹ " በ4 አመታት ውስጥ ማጠናቀቅ ያለብንን ትምህርታችን በአግባቡ ጨርሰን ፤ ክሊራንስም ሆነ የመውጫ ፈተና ለመውሰድ ክፍያ ብንፈጽምም ድንገት ለ8 ወራት መቆየት አለባችሁ ተባልን " ሲሉ  ገልጸዋል ።

ቅሬታ አቅራቢ ተማሪዎቹ ፦

° ከሌሎች ተመራቂ ተማሪዎች እኩል በሚባል ደረጃ ትምህርት እንደጀመሩ፤

° መወሰድ የሚጠበቅባቸው አስፈላጊውን ኮርስ ወስደው ማጠናቀቃቸውን፤

° የመዉጫ ፈተና የማዘጋጃ ቲቶሪያል መውሰዳቸውን ገልጸዋል።

ይሁንና " የመዉጫ ፈተናዉን ልንወስድ ጥቂት ቀናት ሲቀሩን የመመረቂያ ቀናችሁ ጊዜ በሚቀጥለዉ ዓመት ጥር ላይ ነው " በማለት የመውጫ ፈተናውን መውሰድ እንደማይጠቅመን እና የሀምሌ ወር ምረቃችን መሰረዙ ተነገረን ሲሉ ቅሬታቸዉን ገልጸዋል።

ተማሪዎቹ " ተመሳሳይ ባች ከሆኑ የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች እኛ በምን ተለይተን ነው ይሄ የተደረገው ? ለምን ሌላው ሊፈተን ሲዘጋጅ እኛ ግን ' ብትፈተኑም ጥቅም የለውም ቀጣይ ዓመት ጠብቁ ' ተባልን ? ይህ በፍጹም አግባብነት የለውም ፤ መፍትሄ እንሻለን " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ከደረሱት ብዛት ያላቸው ቅሬታዎች በመነሳት ኮሌጆችን ለማነጋገር ጥረት አድርጓል።

ከነዚህም ውስጥ አንዱ ተማሪዎቹ የሚጠበቅባቸዉን ኮርስና ሌሎች አስፈላጊ ጉዳዮችን ማጠናቀቃቸዉን ልክ እንደሆነ ገልጿል።

ይሁንና የመመረቂያ ጊዜያቸዉ የተወሰነዉ ከትምህርት ሚኒስቴር በመጣ አቅጣጫ መሆኑን አስረድቷል።

ኮሌጁ ፤ ተማሪዎቹ #የተፈተኑበት_ጊዜ ምንም እንኳን 2012 ዓ/ም መሆኑን በወቅቱ ከትምህርት ሚኒስቴር በኩል ያገኙት 'የኦንላይን ዶክሜንት' ቢያሳይም በኋላ የመጣላቸዉ ኦሪጅናል ደግሞ 2013 ዓ/ም እንደሚል ገልጿል።

ይህም ደግሞ ተማሪዎቹን ወደኋላ እንደሚያቆያቸዉና ለሚቀጥሉት ወራት የተለያዩ ትሬኒጎችና የመዉጫ ፈተና መለማመጃዎች እየሰጡ ለማቆየት መታሰቡን አስረድቷል።

በሌላ በኩል ፤ ከትምህርት ሚኒስቴር ለተለያዩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላከ አንድ ደብዳቤ ተመልክተዋል።

ደብዳቤው ፦

በ2013 ዓ/ም ሁለተኛ ሴሚስተር ትምህርት የጀመሩ ተማሪዎች ለሰኔ ወር 2016 ዓ/ም የመውጫ ፈተና እንዲወስዱ እንዲደረግላቸው የጠየቁ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዳሉ ያስረዳል።

ነገር ግን የትምህርት ሥልጠና ፓሊሲው የመጀመሪያ ዲግሪ የሚማሩ ተማሪዎች የተቋም ቆይታቸው ቢያንስ 4 ዓመት እንደሆነ እንደሚደነግግ ይገልጻል።

አንዳንድ ተቋማት ህጋዊ ባልሆነ አግባብ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና እንዲወስዱ መጠየቃቸውን በማንሳት ይህ የሚያስጠይቅ ነገር ስለሆነ ተቋማት ተማሪዎችን በአግባቡ በማብቃት የትምህርት ጥራት እንዲረጋገጥ እንዲሰሩ አስጠንቅቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተጨማሪ መረጃዎችን ከትምህርት ሚኒስቴር በኩል ጠይቆ ለማቅረብ ጥረት ያደርጋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
😡706222😭128🙏72😢51🤔30👏29🥰28😱28🕊24
TIKVAH-ETHIOPIA
#ExitExam " ፈተናው የሚሰጠው ከሰኔ 2-10/2017 ዓ.ም መሆኑን እንገልጻለን " - ትምህርት ሚኒስቴር በ2017 ዓ.ም በሰኔ ወር የሚሰጠው የመውጫ ፈተና መመዝገቢያ ጊዜ እስከ ግንቦት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ብቻ የተራዘመ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። እስከ አሁን ያልተመዘገቡ የድጋሚ ተፈታኞች (resitters) ከዚህ በፊት ለምዝገባ በተከፈተውና በተገለጸው መመዝገቢያ…
#የመውጫፈተና

የከፍተኛ ትምህርት ቅድመ ምረቃ መርሃ ግብር ተማሪዎች መውጫ ፈተና ከሰኔ 2 እስከ 10/ 2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

ተፈታኞች ለፈተና ሲመጡ ብሄራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) መያዝ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) " የ2017 የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና ከሰኔ 2 እስከ ሰኔ 10 /2017 ዓ.ም. በ51 ዩኒቨርስቲዎች በተዘጋጁ 87 የፈተና ማዕከላት ይሰጣል " ብለዋል።

ፈተናውን በ238 የትምህርት መርሃ ግብሮች ለ190 ሺ 787 ቅድመ መደበኛ እጩ ተመራቂ ተማሪዎች በበይነ መረብ ለመስጠት  አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡

ለፈተናው 102 ሺ 360 ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ፤ 88 ሺ 422 ተማሪዎች ደግሞ ዳግም የሚፈተኑ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ተማሪዎች ወደ ፈተና ማዕከላት ሲመጡ አገር አቀፍ ፋይዳ /ብሄራዊ መታወቂያ መያዝ እንደሚጠበቅባቸውም ኃላፊው አስገንዝበዋል፡፡

በፈተና ወቅት ፦
- ተንቀሳቃሽ ስልክ ፣
- ሜሞሪ ያለው የእጅ ሰዓት ፣
- የራስ ያልሆነ መታወቂያ፣
- ያልተፈቀዱ ሂሳብ ማሽኖች፣
- አጫጭር ማስታወሻዎች፣
- የተጭበረበሩ ሰነዶች
- ማንኛውንም ዓይነት የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት ክልክል መሆኑን አስገንዝበዋል።

ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ ፦
° አደንዛዥ ዕጽ ተጠቅሞ መምጣት፣
° ከፈተና አስፈጻሚዎች ጋር አሉታዊ ተጽእኖ ያላቸው ውዝግቦችን መፍጠር ፣
° ያለመታወቂያ ካርድ ወደ ፈተና ማእከል መሄድ ፣
° ያለፈቃድ ፈተና ማዕከል መገኘት
° ለሌላ ሰው መፈተን ፍጹም የተከለከሉ ዲሲፒሊን ጥሰቶች መሆናቸውን አሳስበዋል።

ከሰኔ 2 እስከ 10/ 20017 በሚሰጠው አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና 4 ሺ 17 ፈተና አስፈጻሚዎች እንደሚሳተፉ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ተናግረዋል።

መረጃው የትምህርት ሚኒስቴር ነው።

@tikvahethiopia
1.14K😭136🙏64🤔40💔31😢23🥰21😱21😡20🕊16👏13