‹‹እኔ ትክክለኛው ሞሀመዱ ቡሀሪ ነኝ፤ ይህንንም አረጋግጣለሁ፡፡››
የናይጄሪያው ፕሬዝደንት ሞሀመዱ ቡሀሪ ሞተዋል፤በምትካቸው ተመሳሳያቸው ነው ስልጣን ላይ ያሉት በሚል የሚነሱ ወሬዎች #ከእውነት_የራቁ መሆናቸውን ፕሬዝደንቱ አስተባበሉ፡፡
‹‹አንዳንድ ሰዎች ጁብሪል በሚባል ሱዳናዊ ተተክቷል ብለው ያምናሉ፤ እኔ ግን ትክክለኛው ቡሀሪ ነኝ፤ ይህንንም አረጋግጣለሁ›› ብለዋል ቡሀሪ፡፡ ከአንድ አመት በፊት በማህበራዊ መገናኛዎች ፕሬዝደንት ቡሀሪ ‹‹ጁብሪል›› በተሰኘ ሱዳናዊ ተመሳሳያቸው መተካታቸውን እና
እሳቸው በእንግሊዝ ሀገር ለህክምና በሄዱበት መሞታቸው ተሰራጭቶ ነበር፡፡
ቡሀሪ በፈረንጆቹ 2015 ስልጣን ከያዙበት ጊዜ ጀምሮ የጤና እክል ሲገጥማቸው ቆይቷል፡፡ የ76 ዓመቱ መሪ በ2017 እንግሊዝ ሀገር ታክመው ከመጡ ወዲህ ያን ያክል የጤና እክል እንዳልገጠማቸው ገልጸው ነበር፡፡ ፕሬዝደንቱ ማስተባበያውን የሰጡት በፖላንድ ሀገር የአየር ንብረት ለውጥን በተመለከተ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ባቀኑበት ወቅት ነው፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ (በቢንያም መስፍን-አብመድ)
@tsegabwilde @tikvahethiopia