‹‹ሁሉም ኢትዮጵያዊ በኢሬቻ በዓል ላይ እንዲገኝ ጥሪ አስተላልፋለሁ››
/የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ም/ርዕሰ መስተዳድር፤ ሽመልስ አብዲሳ/
የኢትዮጵያ ሕዝብ ትልቅ #እድል አግኝቷል፤ ይሄን እድል በአግባቡ ካልተጠቀመ ትልቅ ኪሳራ ነው የሚሆነው። አገሪቱ ከፍተኛ ችግር ላይ ትወድቃለች።
ብዙ አገሮች እንደዚህ አይነት እድሎችን ባለመጠቀማቸው፣ የለውጥ እቅድ ተጨናግፎ፣ ብዙ ጥፋቶች ደርሰዋል፡፡ አገራቸው የማትወጣበት ማጥ ውስጥ ተዘፍቃ ኑሮ መከራ የሆነባቸው ብዙ አገሮችን መጥቀስ ይቻላል፡፡
በአገራችንም ብዙ ለውጦች ከሽፈዋል፡፡ አሁን ያገኘነው ለውጥ ግን ከፍተኛ ውጤት የተገኘበት ነው። ወደ ኋላ አንድ አመት ተኩል ተመልሰን ብናስታውስ፤ አስገራሚ የሆነ ለውጥ ተካሄዷል፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለውጡን ማስቀጠል ይገባዋል።
ሁላችንም፤ መንግስትም ሕዝብም ተባብረን በአንድ ላይ ይሄንን ለውጥ ማስቀጠል ከቻልን፣ የምንናፍቃትን ኢትዮጵያን እንፈጥራታለን፡፡ ሁሉንም እኩል የምታከብር፣ ብሔር ብሔረሰብ እኩል የሚከበርባት፣ ሁሉም የሚተሳሰብባት፣ ወንድማማችነት የሚጠነክርባት አገር መፍጠር እንችላለን፡፡
እኔን እንቅልፍ የሚነሳኝ ይሄንን እድል እየተጠቀምንበት ነው አይደለም? በየቀኑ ለውጡን የሚያስቀጥል ሥራ እያከናወንን ነው አይደለም? የሚለው ነው፡፡ ተግዳሮቶችን በትዕግስትና ከስሜት በፀዳ አስተሳሰብ እየተጋፈጥን ከሄድን፣ ነገሮች በፍጥነት ይቀየራሉ፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-14-5