TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ታላቁ ሩጫ‼️

ህዳር 9 ቀን 2011 ዓመተ ምህረት የሚካሄደው የዘንደሮው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መነሻና መድረሻ ቦታ #ለውጥ  እንደተደረገበት ተገለፀ።

ለ18ኛ ጊዜ የሚዘጋጀው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ  ከዚህ በፊት  መነሻና መድረሻ ከነበረው  መስቀል አደባባይ  የቦታ ቅያሪ ማድረጉ ተጠቁሟል።

የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ #ኤርሚያስ_አየለ ፥ ውድድሩ ይካሄዳል ተብሎ በተያዘበት እለት ከአፍሪካ ህብረት ልዩ የመሪዎች ጉባኤ ጋር በመገጣጠሙ ቦታው እንዲቀየር መደረጉን አስታውቀዋል።

ስራ አስኪያጁ ከሩጫው ቀን ይልቅ ሩጫው የሚካሄድበትን ቦታ መቀየር ቀላልና የተሻለው አማራጭ ሆኖ መገኘቱንም ጠቅሰዋል።

በመሆኑም ከመላው ዓለም የሚመጡትን ጨምሮ በጠቅላላው 44 ሺህ ህዝብ ይሳተፍበታል ተብሎ የሚጠበቀው የዘንድሮው ሩጫ መነሻና መድረሻ ቦታ ስድስት ኪሎ የሚገኘው የሰማእታት ሀውልት እንዲሆን ተወስኗል።

በዚህም መሰረት ሩጫው ከአደባባዩ በመነሳት በሚኒሊክ ሆስፒታል፣ እንግሊዝ ኤምባሲ በኩል ሾላ ገበያን በመዞር በአድዋ ደልድይ አደርጎ አራት ኪሎ ፓርላማን በማቋረጥ ስደስት ኪሎ ሰማእታት ሀውል ሲደረስ ያበቃል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia