TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኢቫንካ ትራምፕ ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው🔝

የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ልጅ እንዲሁም የዋይት ሀውስ አማካሪ የሆኑት #ኢቫንካ_ትራምፕ በአፍሪካ የ4 ቀናት ጉብኝት ሊደርጉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኢቫንካ ትራምፕ ጉብኝት ከሚመሩት ዓለም አቀፍ የሴቶች ፕሮጀክት ጋር የተያያዘ መሆኑም ተነግሯል፡፡

ኢቫንካ ትራምፕ ወደ አፍሪካ የሚመጡት በያዝነው #የኤፕሪል ወር፤ መዳረሻዎቻቸውም #ኢትዮጵያና #አይቮሪኮስት መሆናቸው ታውቋል፡፡

ኢቫንካ ትራምፕ በአይቮሪኮስት ቆይታቸው ትኩረቱን በሴቶች ኢኮኖሚያዊ አቅም ግንባታ ላይ አድርጎ በአገሪቱ በሚካሄደው ጉባኤ ላይ የሚሳተፉ ይሆናል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በሁለቱም አገራት የመስክ ጉብኝቶችን እንደሚያደርጉና ከፖለቲካ መሪዎች ጋር ተገናኝተው እንደሚመክሩ ተገልጿል፡፡

ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች መሪዎችና በስራ ፈጠራ ላይ ከተሰማሩ ሴቶች ጋር እንደሚወያዩም ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፦ኤቢሲ ኒውስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮጵያን እየጎበኝ የሚገኙት #ኢቫንካ ትራምፕ #በቦይንግ አውሮፕላን አደጋ #ህይዎታቸውን ላጡ ዜጎች #የአበባ_ጉንጉን አስቀምጠዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia