TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ከተፈታኝ መምህራኑ 49 በመቶ የሚሆኑት ከ50% በታች ዉጤት በማስመዝገባቸው ወደ ማስተማር እንዳይገቡ ተደርጓል " - የቤንች ሸኮ ዞን ትምህርት መምሪያ

የቤንች ሸኮ ዞን ትምህርት መምሪያ በዞኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመምህራን የመግቢያ ፈተና መስጠቱ ተሰምቷል።

ለመጀመርያ ጊዜ በዞኑ ትምርት መምሪያ ተዘጋጅቶ በተሰጠዉ የመግቢያ ፈተና ከአጠቃላይ ተፈታኞች 51 በመቶ ተፈታኞች ብቻ ናቸው 50% እና በላይ በማምጣት ያለፉት።

ከተፈታኝ መምህራኑ 49 በመቶ የሚሆኑት ከ50% በታች ዉጤት በማስመዝገባቸው ወደ ማስተማር ስራ እንዳይገቡ መደረጉንም መምሪያው አስታውቋል፡፡

ወደ ማስተማር አይገቡም የተባሉት ተፈትነው ከ50% በታች ያመጡ መምራን በቀጣይ ዕጣ ፋንታቸው ምንእንደሆነ በግልፅ አልተነገረም።

ፈተናውን ማለፍ ባልቻሉ መምህራን ክፍተት እንዳይፈጠር #አዳዲስ_መምህራን እየተመዘኑ እንዲቀጠሩ ይደረጋል ተብሏል፡፡

የዞኑ ትምህርት መምርያ በመምህርነት የተመረቁትን ለመጀመርያ ጊዜ የመግቢያ ፈተናን በመፈተን ወደ መማር ማስተማሩ ስራ እንዲገቡ መደረጉንና ይህ አሰራር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል።

የተማሪ ዉጤትና ስነ ምግባርን ለማሻሻል ከሚሰሩ ዘርፈ ብዙ ተግባራት መካከል የሰው ሀይል ልማትና ብቃት ወሳኝ በመሆኑ በቀጣይነት አዲስ የሚቀጠሩ መምህራን ለሚያስተምሩት የትምህርት እርከን የሚመጥንና ከመማር ማስተማሩ ጋር ተያያዠነት ያለዉ የመግቢያ ፈተና እየተሰጠ ብቁ የሰዉ ሀይል የትምህርት ዘርፉን እንዲቀላቀል በትኩረት ይሰራል ብሏል።

ምንም እንኳ ስራዉ ዘንድሮ የተጀመረ ቢሆንም በቀጣይነት የተቋሙ አሰራር ሁኖ እንዲፈፀም በትምህርት መምርያዉ ማኔጅመት ተወስኖ ወደ ስራ መገባቱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሚዛና ፋና ኤፍ ኤም / ከቤንች ሸኮ ዞን ኮሚኒኬሽን ያገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
👏1.39K😱171154😭147😡47🙏41🕊34🥰22😢16