TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
216 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰበር ዜና‼️

የሶማሌ ክልል መንግሥት ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ አንድ የካቢኔ አባልን ጨምሮ ስድስት ከፍተኛ አመራሮችን #ከኃላፊነታቸው አነሳ።

ካቢኔው ከኃላፊነት ካነሳቸው መካከል የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ፣የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ኃላፊና የምክትል ርዕሰ-መስተዳድር አማካሪ ይገኙበታል።

በክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጉሌድ ቦታም ቢሮውን በምክትል ቢሮ ኃላፊነት ደረጃ ሲመሩ በነበሩት በአቶ አብዱላሂ መሐመድ ተተክቷል።

የክልሉን ገዢ ፓርቲ የሶማሌ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(ሶሕዴፓ)ንና የክልሉን መንግሥት አስመልክቶ በማህበራዊ ድረ-ገጾች የሚናፈሰው ወሬ መሠረተ ቢስ መሆኑን አቶ #አብዱላሂ_መሐመድ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ገልጸዋል።

ምንጭ፦ ኢ..ዜ.አ.
@tsegabwolde @tikvahethiopia