TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የእግር ኳስ ተጫዋች በነበረው አለልኝ አዘነ ግድያ የተከሰሱት ባለቤቱና የባለቤቱ እህት ባል የ16 እና 15 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈረደባቸው። በአለልኝ አዘነ ጉዳይ የመጨረሻ ፍርድ ለመስጠት ዛሬ የተሰየመዉ የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተከሳሽ የአለልኝ ባለቤት አደይ ጌታቸዉና በእህቷ ባል ላይ የ16 እና 15 ዓመት ፅኑ እስራት ፈርዶባቸዋል። ፍርድ ቤቱ ይህንን ዉሳኔ ያስተላለፈው መጋቢት…
#አለልኝ_አዘነ
ከአለልኝ አዘነ ግድያ ጋር በተያያዘ በባለቤቱ አደይ ጌታቸው እና በባለቤቱ እህት ባል ሉንጎ ሉቃስ ላይ የተላለፈው የፍርድ ውሳኔ " አንሷል " ሲሉ የተጫዋቹ ቤተሰቦች እና የቅርብ ጓደኞች ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአለልኝ አዘነ ጉዳይ የመጨረሻ ፍርድ ዛሬ የሰጠ ሲሆን በተከሳሽ የአለልኝ ባለቤት አደይ ጌታቸዉና በእህቷ ባል ሉንጎ ሉቃስ ላይ የ16 እና 15 ዓመት ፅኑ እስራት ፈርዶባቸዋል።
የፍርድ ጊዜዉም ከዛሬ ጀምሮ የሚቆጠር እንደሆነ የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ያመላክታል።
የተጫዋቹ ቤተሰቦችና የቅርብ ጓደኞች " የፍርድ ዉሳኔዉ አንሷል " በሚል ቅሬታቸዉን እያሰሙ እንደሚገኝ የፍርድ ሂደቱን የተከታተለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ገልጿል።
አለልኝ አዘነ ጋብቻውን በፈጸመ በጥቂት ቀናት ውስጥ ነው በባለቤቱና በባለቤቱ እህት ባል በተቀነባበረ ሁኔታ የተገደለው።
በወቅቱም " ራሱን አጠፋ " ነበር የተባለው።
ነገር ግን ባለቤቱ (አደይ ጌታቸው) እና የባለቤቱ እህት ባል (ሉንጎ ሉቃስ) በአለልኝ ግድያ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉና ክስም ከተመሰረተ በኃላ የጋሞ ዞን ከፍተኛው ፍ/ቤት ጉዳዩን ሲከታተለው ቆይቶ ዛሬ በተከሳሾቹ ላይ የ16 እና 15 ዓመት ፅኑ እስራት ፈርዶባቸዋል።
ቤተሰቦች እና የተጫዋቹ የቅርብ ጓደኞች ግን የፍርድ ውሳኔው አላስደሰታቸውም። ከተፈፀመው የግፍ ተግባር አንጻር የፍርድ ውሳኔው " አንሷል " የሚል ቅሬታ አላቸው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አርባ ምንጭ
#TikvahEthiopiaFamilyArbaminch
@tikvahethiopia

❤1.5K😢344😡118👏100😭91💔51🕊23😱19🤔18🥰8🙏8