TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ጨለማን ተገን በማድረግ የተፈፀመውን የማፍረስ ድርጊት በፅኑ እናወግዛለን " - ጠቅላይ ም/ቤቱ

በአዲስ አበባ ከተማ ፤ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ  10 የሚገኘው የተባረክ መስጅድ አጥር በለሊት እንዲፈርስ የተደረገበትን ድርጊት በፅኑ እንደሚያወግዝ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አሳቋል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ፥ " ከ1967 ዓ.ል ጅምሮ ለ50 ዓመታት መንፈሳዊ አገልግሎት እየሰጠ ባለው ተባረክ መስጂድ ላይ ከህጋዊ አሰራር ውጪ የተፈፀመውን የማፍረስ ድርጊት በፅኑ እናወግዛለን " ብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር በመነጋገር በህጋዊ መንገድ የመስጅዱ ቅጥር እንዲታጠር ቢያደርግም ትላንት ሌሊት ጨለማን ተገን በማድረግ ከመንግስት የስራ ሰዓት ውጪ እንዲፈርስ መደረጉ ጠቅላይ ምክር ቤቱን እንዳሳዘን ገልጿል።

ይህን ተግባር የፈፀሙ አካላት በህግ አግባብ እንዲጠየቁና መስጅዱ የደረሰበት ኪሳራ ተሸፍኖ ድጋሚ እንዲታጠር ለማድረግ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ አመልክቷል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ፥ " መስጅዶች የሙስሊሞች ቤተ አምልኮ ብቻ ሳይሆኑ እንደ ዐይን ብሌናቸው የሚጠብቋቸው መሰባሰቢያቸውና የልብ መርጊያቸው ጭምር በመሆናቸው ተመሳሳይ ድርጊቶች እንዳይፈፀሙም በዚሁ አጋጣሚ እናሳስባለን " ብሏል።

በሌላ በኩል የተባረክ መስጅድ ኢማም ሸይኽ ሙሳ አደም ለሃሩን ሚዲያ በሰጡት ቃል ፥
" ተባረክ (ጀርመን) መስጂድ ህጋዊ ካርታ ያለው ከ1967 ጀምሮ ሲሰገድበት የቆየ ነው " ብለዋል።

" ሙስሊሙ ማህበረሰብ ባላወቀበት ሁኔታ በህጋዊ መልኩ የተሰራን የመስጂድ አጥር እና ታፔላ በውድቅት ሌሊት መጥቶ ማፍረስ  ህገወጥ ተግባር ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" ለሰላማችን ትልቅ አስተዋፅኦ እያበረከተ ባለ አካል በዚህ መልኩ በውድቅት ለሊት የመስጂዱን አጥር እና ታፔላ ማፍረስ በእጅጉ አሳዝኖናል " ሲሉ አክለዋል።

" አሁንም የሚመለከተው የመንግስት አካል ህዝበ ሙስሊሙ ላይ የተፈፀመውን ትልቅ በደል በመልከት የመስጂዱን አጥር እና ታፔላ ወደነበረበት እንዲመለስ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲወጡ " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

#ተባረክመስጂድ #አዲስአበባ

@tikvahethiopia
😡1.73K👏350😭192189💔79🤔43🕊41🙏33😢19😱13🥰11