TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🚨#Attention #ቦሌወረዳ11

🔴 “ ወንዙ በአፈር ተዘግቷል። ዶክሜንት፤ ዩኒፎርም፤ ጫማ አልቀረም። ከ100 በላይ አባወራ ሜዳ ላይ ወድቆ ነው ያለው ” - ነዋሪዎች

🔈 “ ምንም እቃ አልቀረልኝም ንብረቴ በስብሶ ነው ያለው። ከነልጆቼ ውጪ ነው ያደረኩት” - እያለቀሱ የተናገሩ አባት

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11፣ ቀጠና 2፣ “ወይናምባ ማርያም” ወደ ኢንዱስትሪ ፓርክ በሚወስደው ትልቁ ወንዝ አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች፣ ትላንት በጣለው ዝናብ ከፍተኛ የንብረት ጉዳት እንዳደረሰባቸው፣ ውሃው አሁንም ሙሉ ለሙሉ እንዳልተወገደ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬ ተናግረዋል።

አንድ እያለቀሱ ሁነቱን ያስረዱ ነዋሪ አባት፦

“ ምንም እቃ አልቀረልኝም። ንብረቴ በስብሶ ነው ያለው። ከነልጆቼ ውጪ ነው ያደረኩት። የተወሰኑ ሰዎች ናቸው የሚሰሩት ነገሩን።

ንብረቱስ ይቅር፤ አሁን ራሱ ቱቦው ተዘጋብን፣ ከነልጆቻችን ከቤት ውጪ ነን። ጭቃው፣ ሽታውና ብዙ ነገሩ በሽተኛ ሆነን ነው ያለነው።

መፍሄው የተዘጋውን ወንዝ መክፈት ነው።

ከ10 ዓመት በላይ የኖርንበት ሰፈር ነው። ከሦስት ዓመት ወዲህ ከበድ ያለ ዝናብ ሲዘንብ ብቻ የተወሰነ የቤት ግድግዳ ነክቶ ነበር የሚያልፈው፣ አሁን ግን ውጪ አሳደረን።

ከወንዙ አፈር የሚደፉ ግለሰቦች አቅምና ብር አላቸው፤ ከወረዳው ጋር ቅኝ እጅ ናቸው። ግለሰቦቹ እያንዳንዳቸው አንድ ክፍለ ከተማ ናቸው። ይታሰሩ አንልም፤ መንግስት አፈሩን ያስነሳልን። 

ግለሰቦቹ ወረዳውና ከክፍለ ከተማው አስተዳደር በላይ ናቸው፤ ክፍለ ከተማውም ያውቃል ጉዳዩን ማስፈጸም አልቻለም ላለፉት ሦስት ዓመታት ዘንድሮን ጨምሮ።

አምና ቴሌቪዥን፣ ፍሪጅ ተበላሸብን ገዝተን ተካን፣ ዘንድሮም እንደዚሁ። ሁል ጊዜ ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ከሚሆንብን ወንዙን የዘጋውን አፈር ያስነሱልን ” ብለዋል።

ሌላኛው ንብረት የተጎዳባቸው ነዋሪ፦

“ እያንዳንዱ ቤት ተማሪዎች አሉ፤ አንድ ዶክሜንት፤ ዩኒፎርም፤ ጫማ አልቀረም። 

አፈር በሲኖ እየመጣ ወንዙ ዘግቷል። እዛ ወንዙ ልክ ዝናብ በዘነበ ቁጥር እየሞላ፣ እየሞላ ከሰው ጎርፉ ቤት ገባ።

በአንድ ሰው ብቻ ከ200 ሺሕ በላይ የቤት ቁሳቁስ ነው የወደመው። በአንድ ሰፈር ያለው ከተከራዮች ውጭ ቢያንስ አንድ ግቢ ከ25 እስከ 30 የሚሆን ሰው ነው።

ንብረት አንድም የተረፈን ነገር የለም። አሁንም ሰዎች ወንዝ ዳር፣ ወንዝ ውስጥ ከጭቃ እቃ እየለቀሙ ነው ያሉት። 

ከተከራይ ከህፃናት እስከ አዋቂ ሁሉም ፀሐይ ላይ ነው። ከህዳር ወር ጀምሮ ነው አቤቱታ እያቀረብን የነበረነው። ይሄው ከባድ ዝናብ የዘነበው ትላንትና ከቀኑ 9 እስከ 10 ሰዓት አካባቢ ጀምሮ ነው። 

ወንዝ መሄጃ መንገዱን በግራና በቀኝ እየደፉ ገቡ የዛሬ አመት እንዲሁ ስንጨናነቅ ድልድዩ ወደቀ፤ ድልድዩን እያንዳንዱ ማህበረሰብ 500 ብር አዋጥቶ አስነሳ።

ዋናው ነገር አሁን ድረሱልን። ህዝብ ከሌለ መንግስት ብቻውን መቀመጥ አይችልም። የሄን ጉዳት እንዲደርስ ያደረጉት ደግሞ ሦስት ሰዎች ናቸው። ስለነዚህ ሰዎች ወረዳውን ስንጠይቀው ምንም የሚሰጠው ምላሽ የለም።

‘እናስተካክላለን፣ ለክፍለ ከተማ አመልክተናል’ ነው የሚሉት ሌላ የተሰጠ አማራጭ የለም። በምትችሉት ለነፍሳችን ድረሱልን” ነው ያሉት።

ሌላኛው የስፍራው ነዋሪ ፦

“ በጣም ችግር አለ። ተደጋጋሚ ነው። የዛሬ ሁለት፤ ሦስት ዓመታት ሆኖታል። ይሄ ሁሉ የሚሆነው በሦስት፤ አራት አባወራ ግለሰቦች ነው።

አፈር እየደፉ ወንዙን የዘጉት። ከሳይት የሚመጣ አፈር እያስደፉ፣ ብር ይቀበላሉ፤ ወንዙን ዘጉት ውሃው በየት ይሂድ። እስከ ወረዳና ክፍለ ከተማ ድረስ ይታወቃሉ፤ ግን ምንም መፍትሄ ነገር አልተሰጠም። 

የተከራዮቸ፣ የኔ ሙሉ የቤት እቃ፣ ደብተርና ዩኒፎርም ሙሉው የለም። አሁንም ቢዘንብ ተመልሶ ይገባል። 

#አሁንም ጎርፉ እንዳለ ነው። ለሚመለከተው ተናግረን ነው የመጣነው አሁን፤ ‘ክሰሱ’ ነው የተባልነው። እኛ ደግሞ አሁን አንገብጋቢ ቾግር ነው ያለብን። ዝናብ ቢጥል ተመልሶ ከቤት ነው የሚገባው።

ወረዳው፤ ክፍለ ከተማው ምንም መፍትሄ አልሰጡንም። ‘እናስጠርጋለን ነው’ የሚሉት። ከ100 በላይ አባወራ ሜዳ ላይ ወድቆ ነው ያለው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለእሳትና አደጋ ሥራ አመራር ከሸሚሽን ቅሬታውን አሁን አድርሷል።  ጉዳዩን ተከታትለን መረጃ እናቀርባለን።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😭871161😢114🙏50🕊23🤔16🥰10😱9👏6💔3😡3