TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
218 files
4.4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጀርመን ፍራንክፈርት‼️

ከክቡር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር ጥቅምት 21 ቀን 2011 ዓ.ም በሚደረገው የውይይት መድረክ የሚሳተፉ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን የዳያስፖራ አባላት ወደ ጀርመን ፍራንክፈርት #መግባት ጀምረዋል፡፡

ኢትዮጵያውያኑና በአውሮፓ ከሚገኙ 12 ኤምባሲዎች የተወከሉ ዲፕሎማቶች ፍራንክፈርት እየደረሱ ሲሆን መድረኩ “በአንድነት እንነሳ፣ ነገንም እንገንባ” በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄድ ነው፡፡

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር #ብርቱካን_አያኖ የሚመራው ብሄራዊ ኮሚቴ ከበርሊን የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና የፍራንክፈርት የቆንስላ ጽ/ቤት እንዲሁም የዳያስፖራ አባላት ጋር በመሆን ለስነስርዓቱ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

ኮሚቴው የእስከአሁኑን ዝግጅትና አጠቃላይ ሂደት አስመልክቶ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የፍራንክፈርቱ ዝግጅት የተሳካ እንዲሆን 200 የበጎ ፍቃድ ሠራተኛ ኢትዮጵያውያን ተሳታፊ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡

በሰሜን አሜሪካ ክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ከጥቂት ወራት በፊት ያደረጉት ጉብኝት ቀጣይ ምዕራፍ የሆነው ይኸው መድረክ የአንድነትና የፍቅር ድልድይ በመገንባቱ የተፈጠረው የህብረት መንፈስ ለአገር ግንባታ ማዋል እንዲቻል ጥሪ ይቀርብበታል ተብሎ
ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia