TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
216 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከተሽከርካሪ ነፃ ቀን...!

#በጤና_ሚኒስቴር የሚዘጋጀው ከተሽከርካሪ ፍሰት ነፃ መንገዶች ቀን በመጪው እሁድ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ይካሄዳል ተብሏል፡፡

ከተሽከርካሪ ፍሰት ነፃ መንገዶች ቀን ተላላፊ ያልሆኑና ከኑሮ ዘይቤ መቀየር ጋር የሚከሰቱ ህመሞችን ለመከላከል በጤና ሚኒስቴር የተሰናዳ ፕሮግራም ነው፡፡

የፊታችን እሁድ በተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እና ነፃ የጤና ምርመራ በማድረግ በአዲስ አበባ እና በሁሉም የክልል ዋና ከተሞች ይካሄዳል ተብሏል፡፡

በአዲስ አበባ ዝግጅቱ በአራዳ፣ ልደታ፣ ኮልፌ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ እና ቦሌ ክፍለ ከተሞች ይደረጋል ሲል የጤና ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ተናግሯል፡፡

ለዝግጅቱ በክፍለ ከተሞቹ የሚገኙ እና ዝግ የሚሆኑ መንገዶች የተለዩ ሲሆን ከልደታ ፍ/ቤት ሜክሲኮ፣ ከሜክሲኮ ብሔራዊ ቲያትር፣ ከሚኒሊክ ሆስፒታል 6 ኪሎ፣ ከለቡ መብራት ሀይል ጆሞ ቁ1፣ ከቤቴል ኪዳነ-ምህረት እንዲሁም ከሳፋሪ ፊጋ በሚወስዱት ዋና መንገዶች ላይ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እና ነፃ የጤና ምርመራ የሚካሄድ ሲሆን በነዚህ መንገዶች የሚገለገሉ አሽከርካሪዎች ይህን አውቀው እሁድ የካቲት 24 ቀን 2011 ዓ/ም አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ሲል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አሳስቧል፡፡

Via shger fm 102.1

#የካቲት24
#CarFreeDay #ADDISABEBA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
😢2