TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከአምቦ ዩኒቨርሲቲው መምህር ስዩም ተሹመ የተገኘ መረጃ...

ዶ/ር አብይ አህመድ እና ፕ/ት #ኢሳያስ_አፈወርቂ #በአቡ_ዲያቢ ተገናኝተው ተወያይተዋል።
================================
ከአንድ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባልደረባ ባገኘሁት መረጃ መሰረት፣ የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ትላንት የአልጄርሱን ስምምነት ለመቀበል ያሳለፈው ውሳኔ የኢትዮጲያ መንግስት በተናጠል የወሰደው እርምጃ አለመሆኑን ለመረዳት ችያለሁ። ከዚያ ይልቅ፣ የኢትዮጲያ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከኤርትራው ፕረዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በአቡ ዲያቢ ተገናኝተው ተወያይተዋል።

ጠ/ሚ አብይ በሳውዲ አረቢያ ያደረጉትን ጉብኝት ካጠናቀቁ በኋላ ወደ አቡ-ዲያቢ ተጉዘው እንደነበር ይታወሳል። በተመሳሳይ ወቅት የኤርትራው ፕረዜዳንት “ለሕክምና” በሚል ሰበብ ወደ አቡ-ዲያቢ ማቅናታቸው ይታወሳል። ከላይ የጠቀስኩት የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባልደረባ እንደነገረኝ ከሆነ ሁለቱ መሪዎች በአቡ-ዲያቢ ተገናኝተው መክረዋል።

በመሆኑም የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የአልጄርሱን ስምምነት ለመቀበል የወሰነው በተናጠል ሳይሆን በቅድሚያ ከኤርትራ መንግስት ጋር በመነጋገር የተወሰደ እርምጃ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia