TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.61K videos
217 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሜሪካ የአየር ጥቃት ፈፀመች።

አሜሪካ #በአፍጋኒስታን ፣ ካቡል በፈፀመችው የድሮን ድብደባ አሸባሪዎችን ሳይሆን ንፁሃንን መግደሏን ካመነች ከቀናት በኃላ #በሶሪያ የአየር ጥቃት ፈፅማለች።

የአሜሪካ ጦር የአየር ጥቃቱ አንድ ከፍተኛ የአል-ቃይዳ የአሸባሪ በድን ኃላፊን ለመግደል ያለመ እንደሆነ አሳውቋል።

የአሜሪካ ማዕከላዊ ኮማንድ እንዳሳወቀው ከሆነ ጥቃቱ ኢድሊብ አቅራቢያ የተፈፀመ ሲሆን፤ ያነጣጠረው በሽብርተኛው የአል-ቃይዳ ቡድን ላይ ነው።

የአየር ጥቃቱን ተከትሎ ሲቪሎች ላይ ጉዳት መድረሱን የሚያሳይ ነገር እንደሌለ የአሜሪካ ጦር ገልጿል።

የፔንታጎን ባለስልጣናት ጥቃቱን አረጋግጠው ተጨማሪ መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

ትላንት በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የአሜሪካ የአየር ጥቃት የአል -ቃይዳ ተባባሪ የሆነውን "ሁራስ አል-ዲን" 2 ከፍተኛ ኃላፊዎችን መግደሉን የሚገልፁ መረጃዎች ሲሰራጩ ነበር።

@tikvahethiopia
👍1